ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
215K subscribers
284 photos
1 video
16 files
219 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ስምንት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ደስ ደስ ብሏታል፡ ከእውነተኛ ሌባ ጋር መወዳጀቷን ማመን
እያቃታት ነው፡ አንድ ሰው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት አታምነውም፡ ነገር ግን
ሄሪ አንድ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ተከሶ ስላየችው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት እውነቱን መሆኑን አወቀች።

ከስርዓት ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ማለትም ወንጀለኞች ለህግና ለመንግስት የማይገዙ ሰዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎችና በረንዳ አዳሪዎች ሁልጊዜ
ያስደንቋታል፡ እነሱ ነጻ ሰዎች ናቸው፡፡ በእርግጥ በህብረተሰቡ የተተፋ ሰው
ጥሩ ነው የሚል አመለካከት የላትም፡፡ ነገር ግን እንደ ሄሪ ያሉ ሰዎች አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለማድረግ አይፈቅዱም፡ይህ ነጻነታቸው ነው ማርጋሬትን የሚያስቀናት፡፡ አንዳንዴ የወታደር ልብስ ለብሶ ጠመንጃውን ታጥቆ በየመንደሩ እየዞረ ህዝብ የሚዘርፍ ሽፍታ መሆን ያምራታል እንደዚህ አይነት ሰዎች ገጥመዋት አያውቁም: አንድ ጊዜ በለንደን ጎዳናዎች
ላይ ሴተኛ አዳሪ መስላቸው ሊደፍሯት የመጡትን ሰዎች ባታይ የምታውቅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡

ሄሪ እሷ የምትመኘውን ነገር ሁሉ ያሟላ ሆኖ ነው ያገኘችው የፈለገውን ማድረግ የሚችል ሰው! ዛሬ ጧት አሜሪካ ለመሄድ ወሰነና ዛሬ ከሰዓት በኋላ አይሮፕላኑ ላይ ተገኘ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ መደነስና ቀኑን በሙሉ መጋደም ከፈለገ ያደርገዋል፡ ከልካይ የለበትም፡፡ መብላት የፈለገውን ይበላል፧ መጠጣት የፈለገውን ይጠጣል፡ ገንዘብ ከፈለገ ገንዘባቸውን መጣያ
ካጡ ባለጸጎች ይሰርቃል፡ እሱ ነጻ የሆነ ሰው ነው፡
ስለሄሪ በይበልጥ ማወቅ ፈለገች፡ ከእሱ ጋር ራት ሳትበላ ያሳለፈቻቸው
ቀናት ቁጭት ውስጥ ጣሏት፡፡

ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ቀጥሎ ተቀምጠዋል እነዚህ ሰዎች ይሁዲ ስለሆኑ ነው ገና ወደ መብል ክፍሉ እንደገቡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ክፉኛ የገላመጧቸው፡አብረዋቸው
የተቀመጡት ኦሊስ ፊልድና ፍራንክ ጎርደን ናቸው፡፡ ፍራንክ ጎርደን በዕድሜ
hሄሪ ብዙም የማይበልጥ መልከ መልካም ወጣት ነው፡፡ ኦሊስ ፊልድ ደግሞ
ኑሮ የጠመመበት የመሰለ በዕድሜ ገፋ ያለ ራሰ በራ ሰው ነው፡፡

ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሁሉም ሰው ከአይሮፕላኑ ወጥቶ
በየፊናው ሲበታተን እነዚህ ሁለት ሰዎች አይሮፕላኑ ውስጥ በመቅረታቸው
የለው ሁሉ መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡

ሶስተኛው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ሉሉ ቤልና ሾርባው ጨው የበዛበት ነው እያሉ ሲያማርሩ የዋሉት ልዕልት ላቪኒያ ተቀምጠዋል ከነሱ ጋር ፎየንስ ላይ የተሳፈሩት ሚስተር ላቭሴይና ሚስስ ሌኔሃን ተቀምጠዋል። ወሬ መለቃቀም የሚወደው ፔርሲ እነዚህ ሰዎች ባልና ሚስት ባይሆኑም የሙሽሮቹን ክፍል እንደሚጋሩ ወሬ ለጠማቸው አውርቷል
ባልና ሚስት ያልሆኑ ሰዎች ይህን ክፍል እንዲይዙ ፓን አሜሪካን አየር
መንገድ እንዴት እንደፈቀደላቸው ማርጋሬት ገርሟታል። አየር መንገዱ ብዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ መሄድ ስለፈለጉ ህጉን መጋፋት የግድ ሆኖበታል፡

ፔርሲ ጥቁር የይሁዲዎች ኮፊያ አናቱ ላይ ደፍቷል፡ ማርጋሬት ይህን ስታይ በሳቅ ተንፈቀፈቀች፡፡ ከየት ነው ያመጣው! አባቱ ግን ‹‹ጅል!›› ብለው ተሳድበው ኮፍያውን መንጭቀው ወረወሩት፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ኤልሳቤት ተለይታቸው ከሄደች ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ ፊታቸው በመጠኑ ፈካ ብሏል፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ‹‹የራት ሰዓታችን ገና ነው›› አሉ፡፡
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ‹‹አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል እኮ›› አሉ፡፡
‹‹ለምንድነው ታዲያ ያልጨለመው?››
‹‹እንግሊዝ አገር አሁን ጨለማ ነው፡ አሁን ግን ከአየርላንድ ባህር
ጠረፍ ሶስት መቶ ማይል ርቀት ላይ ነው የምንገኘው ጸሃይዋን እያሳደድን
ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

‹‹መቼም መጨለሙ አይቀርም››
‹‹ምናልባት ሶስት ሰዓት ላይ የሚጨልም ይመስለኛል›› አለ ፔርሲ
‹‹ጥሩ›› አሉ እናት፡፡
እንደማይጨልም
‹‹ጸሃይዋን ተከትለን በፍጥነት ብንጓዝ
እንደማይጨልም ታውቃላችሁ? አለ ፔርሲ፡፡

‹‹እንደዚህ አይነት ፍጥነት ያለው አይሮፕላን የሰው ልጅ ይሰራል ብዬ አልገምትም›› አሉ አባት ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ግብዝነት፡
ቦትውድ ካናዳ ለመድረስ አስራ ስድስት ሰዓት ተኩል ይፈጃል›› አለ ፔርሲ ‹‹እዚያ በግሪንዊች ሰዓት አቆጣጠር ከጧቱ ሶስት ሰአት እንደርሳለን››
‹‹ካናዳ ስንት ሰዓት ይሆናል ማለት ነው?,,
‹‹የኒውፋንድላንድ ካናዳ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች የሰዓት አቆጣጠር ሶስት ሰዓት ወደ ኋላ ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

እናት የፔርሲን ችሎታ አጤኑና ‹‹ወንዶች የቴክኒክ እውቀት ላይ ጎበዞች ናቸው›› አሉ፡፡

ማርጋሬት በእናቷ አነጋገር ተናደደች፡፡ እናት የቴክኒክ ነገሮች ሴቶች አይገባቸውም ብለው ያምናሉ፡፡ ‹‹ወንዶች ሴቶች ጎበዝ ሲሆኑ አይወዱም››
ብለዋታል ብዙ ጊዜ፡ በዚህ ጉዳይ ማርጋሬት ከእናቷ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት ባትፈልግም እሷ ግን አታምንበትም፡ ይህን የሚቀበሉ ወንዶች ደደቦች ናቸው ብላ ነው የምትገምተው ጎበዝ ወንድ ጎበዝ ሴት ይወዳል፡

አጠገባቸው ካለው ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጡት ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ክርክር ገጥመዋል አጠገባቸው ያሉት የጠረጴዛ ተጋሪዎች
ባይገባቸውም በጸጥታ ያዳምጣሉ: ሁለቱ ሰዎች አይሮፕላኑ ላይ ከወጡ
ጀምሮ ጥልቅ ውይይት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ በዓለም ከታወቀ ሳይንቲስት
ጋር እንደዚህ ያለውን ውይይት የምታደርጉ ከሆነ ውይይቱ ጥብቅ መሆኑ
አያስደንቅም፡፡ በክርክራቸው ውስጥ ፍልስጤምንና እስራኤልን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡ ማርጋሬት የውይይት ርዕሳቸውን ስትሰማ
‹‹አባባ ምን ይል
ይሆን?›› እያለች አስሬ ታያቸዋለች፡፡ እሳቸውም የሁለቱ ሰዎች ውይይት
አልጥም ብሏቸው አኩርፈዋል፡፡ አባቷ ነገር እንዳይጭሩ ርዕስ ለማስለወጥ
‹‹አይሮፕላኑ የሚጓዘው ኃይለኛ ነፋስ በቀላቀለ ዝናብ ውስጥ ነው›› አለች
‹‹እንዴት አወቅሽ?›› አለ ፔርሲ አነጋገሩ ቅናት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በበረራ መረጃ ከማርጋሬት ይልቅ እሱ ነው ኤክስፐርቱ።
‹‹ሄሪ ነገረኝ››
‹‹እሱ እንዴት ያውቃል?››
‹‹እሱ ዛሬ ራት የበላው ከበረራ መሃንዲሱና ከናቪጌተሩ ጋር ነው፡››
ማርጋሬት ዝናቡ ችግር ይፈጥራል ብላ አልገመተችም፡፡ በእርግጥ
በዝናብ ውስጥ መጓዝ ምቾት ቢነሳም ለክፉ አይሰጥም፡፡

ሎርድ ኦክሰንፎርድ ብርጭቋቸው ውስጥ የቀረውን ቪኖ አጋቡና ሌላ
እንዲጨመርላቸው ቆጣ ብለው ጠየቁ፡፡ ዝናቡ ችግር ያመጣል ብለው ፈሩ
እንዴ? ከተለመደው በላይ እየጠጡ መሆናቸውን ማርጋሬት ተገንዝባለች።
ፊታቸው ከመጠጥ ብዛት ፍም መስሏል: ዓይናቸው ፈጧል፡ ምናልባትም
ነርቭ ሆነዋል፡፡በኤልሳቤት መኮብለል ክፉኛ ተበሳጭተዋል
እናትም ማርጋሬትን ‹‹ሚስተር መምበሪን አጫውቺው›› አሏት፡
ማርጋሬት የእናቷ አባባል ገርሟት ‹‹ለምን?›› ስትል ጠየቀች፡ ሲያዩት
ሰው እንዲያናግረው የሚፈልግ አይመስልም፡

‹‹ምናልባትም አይናፋር ሳይሆን አይቀርም›› አሉ እናት፡፡

እማማ ከመቼ ወዲህ ነው ለአይናፋሮች መቆርቆር የጀመረችው?የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ‹‹ግን ምን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀች ማርጋሬት።
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ስምንት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ››

‹‹በባሏ ጠርጥራሽ ነው አይደል …?››ያው እኔ ሳላስበው ነው ቀደም ቀድም የምለው ….ምክንያቱም እሷ ታሪኳን በቃላት አቀናብራ ለሶፊ ከመናገሯ በፊት እሷ ቀድሞ ይታያታል…ንስሯ የበራፍ  በረንዳ ላይ ሶፊ ከለቀቀችበት ወንበር ላይ ተፈናጦ ክፍት በሆነው በራፍ ወደውስጥ አጨንቁሮል ….እርግጥ ልጅቷ ጀርባውና ስለሰጠችው እስከአሁን አላየችውም… እሷ ግን ፊት ለፊት ይታያታል ሁለቱም የልጅቷን ታሪክ ላይ አተኩረዋል …ለዛ ነው ቀደም ቀደም የምትለው….ያ ደግሞ ልጅቷን ግራ እያጋባት ስለሆነ መረጋጋት እንዳለባት ለራሷ እየነገረች ነው፡፡

‹‹አዎ ትክክል ነሽ…ብታይ ጭራቅ ሴት ነች፡፡ቅናቷ አያድረስ ነው፡፡በቃ ሰይጣናዊ የቅናት ዛር ነው የሰፈረባት፡፡ኑሮዬን ሁሉ ሲኦል ነው ያደረገችው፡፡››

‹‹ሙሉውን ሶስት አመት እዛው ነው የኖርሺው…?››

‹‹አዎ ሶስት አመት ሙሉ አንድ ቤት ነበርኩ…እርግጥ መጀመሪያውን  አንድ አመት አካባቢ ጥሩ ሴት ነበረች…ሁሉ ነገር መልካም ነበር… ደሞዜን በስርአቱ ትከፍለኛለች..እርግጥ እስከመጨረሻውም ደሞዜን ከልክላኝ ወይም አቋርጣብኝ አታውቅም…ለቤተሰቦቼ የምልከው ተጨማሪ ብር ሁሉ ትሰጠኝ ነበር፡፡ከዛ ድንገት ፀባይዋ ተቀያየረ….ለዓይኖቾ ተጠየፈችኝ….

‹‹ለምን ታዲያ አትለቂም ነበር..?ማለት ሌላ ማዳም ጋር ቀይረሽ መስራት ትቺይ ነበር…››

‹‹ያው እንደነገርኩሽ በህገወጥ መንገድ ነው የሄድኩት.. እንደልቤ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሼ ስራ ማማረጥ አልችልም..ሌላው …››ብላ ዝም አለች ..ላውራ ወይስ ይቅርብኝ እያለች ከራሷ ጋ ሙግት የገጠመች መሆኑን አውቃባታለች…

‹‹ሌላው ምን…?››

‹‹ሰውዬው በጣም መልካም ሰው ነው…ልጆቹንም በጣም ነው የምወዳቸው….ለእነሱ ስል ነው ታግሼያት የኖርኩት››

ፈገግ አለች‹‹መጨረሻ ታዲያ እንዴት ሆነ?››

‹‹ቅናቷ ከቁጥጥር በላይ ሆነብኛ››
‹‹ያው  ምታደርጉትን እኮ ስለምታይ ነው››

‹‹ማለት…? እንዴት ታውቃለች……?›.
‹‹እርግጥ የእሷን አለመኖር  እየጠበቃችሁ ነው ፍቅራችሁን የምትወጡት… ግን እሷ በደንብ ታውቃለች ..እንደውም ጥሩ ሰው ነች››አለቻት
ልጅቷ ግራ ገባት ..ከድንጋጤዋ የተነሳም ከተቀመጠችበት ተነስታ ቤቱን ሁሉ ለቃ  መውጣት ፈልጋለች..…

‹‹አይዞሽ አትደንግጪ …እሷን ለማስቀየም ወይም ለመበደል ብለሽ ሳይሆን ፍቅር ላይ ስለወደቅሽ ነው እንደዛ ያደረግሽው…ያ ደግሞ ከሰውዬው ቀረቤታ እና መልካምነት የተነሳ ነው..በዛ ላይ በጣም ቆንጆ እና ዘናጭ ነው…እንደምትወጂው አውቃለሁ  ፡፡እሱም በደንብ ነው የሚያፈቅርሽ፡፡በጣም የከፋው ነገር ግን ቅናተኛ ላልሻት ሴት ደግሞ ሰውዬው ሁለመናዋ ነው…እናንተ እርስ በርስ ከምትዋደዱት በላይ እሷ እሱን ትወደዋለች፡፡እና ሴትዬዋ በተፈጥሮዋ መጥፎ ሆና አንቺን በማሰቃየት የምትረካ ስለሆነች ሳይሆን ባሏን ላለማጣት የምታደረግው መፋለም እና ጥረት  ነበር፡፡እንደውም አንቺን ባሰቃየች ቁጥር እሱንም የምታስከፋው እና የምታጣው  መስሎ ስለሚሰማት በጣም ትጨናነቅ እና ትጠነቀቅ  ነበር…አንቺን ጎድታኛለች ብለሽ ከምታወሪው በላይ እሷ እራሷን አሰቃይታለች ….የጨጋራ በሽተኛ ሆናለች….››

‹‹ቆይ አንቺ ይሄን ሁሉ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ…?››

እሱን ልታስረዳት አልቻለችም ‹‹..ትኩረት ከሰጠው  አንዳንድ ነገሮችን ማየት እችላለሁ፡፡

በውስጥሽ ይህቺ ልጅ ጠንቆይ ነች እንዴ…? እያልሽ እያሰብሽ እንደሆነ አውቃለሁ..እንደዛ በይው ችግር  የለውም››

‹‹አይ ማለቴ ….ልዋሽሽ አልችልም እንዳልሽው ነበር እያሰብኩ ያለሁት…ይገርማል ያልሻቸውን  ብዙውን ነገሮች ትክክል ነሽ››

‹‹ምንድነው ትክክል ያልሆንኩት…?››

‹‹እሷ ስለእኛ ግንኙነት በእርግጠኝነት ማወቋን እና..ከእኔ በላይ እሱን ማፍቀሯን››

‹‹ሁለታችሁ ፍቅር የምትሰሩት አንቺ ክፍል አይደል…?››

‹‹አዎ ግን እሷ ስራ በምትሆንበት እና ከቤት እርቃ በሄደችበት ጌዜ ጠብቀንና ተጠንቅቀን ነው››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ …በሁለታችሁ ያልተለመደ መቀራረብ ጥርጣሬ ካደረባት በኃላ ግን ክፍልሽ ውስጥ በስውር ካሜራ ስላስቀመጠች የተቀዳውን በፈለገችው ጌዜ ከፍታ ታየው ነበር፡፡››

‹‹ያማ አይሆንም..…?እንዴት ተደርጎ…?››

‹‹እንደዛ ነበር የሆነው…ከእኔ በላይ አታፈቅረውም ያልሺው ደግሞ ያው በራስሽ ሚዛን ስለምትመዝኚው ነው እንደዛ የምታስቢው እንጂ እንቺ በእሷ ቦታ ብትሆኚ እርግጠኛ ነኝ ወይ ጥለሺው ትሄጂያለሽ ..ወይ ሌላ እርምጃ ትወስጂያለሽ ….እሷ  ግን ካንቺ ጋር ብትጨቃጨቅም ….አንቺን ላይ ችግር ለመፍጠር ብትሞክርም አንድ ቀን እንኳን እሱ ላይ ተነጫንጫበት ወይንም  ጉዳዩን አንስታበትና ወቅሳው አታውቅም..ለእሷ እሱ ብቸኛው ፍቅሯ ነው..ለአንቺ ግን የመጀመሪያ ምርጫሽ አይደለም..ስለምታፈቅሪው ብቻ ሳይሆን ማዳሞ ከምታውቀው ሌላ ተጨማሪ ብር ስለሚሰጥሽ ነው  ..ፍቅርሽ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ምንጭሽም ስለሆነ ነው…ለእሷ ግን እንደዛ አልነበረም…››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው….የእውነት ካሜራው ኖሮ የምናደርገውን ሁሉ እያየች በትዕግስት አልፋን ከሆነ የሚገርም ነው…እኔ ብሆን ልገድለው ሁሉ እችላለሁ…አረ ሁለቱንም ነው በተቃቀፉበት የማጠፋቸው››

‹‹አየሽ..ሴትየዋ የምታስቢያትን ያህል ክፉ አልነበረችም….ከዚህም በላይ ልታሰቃይሽ ምክንያቱን ሰጥተሻት ነበር…ግን እሷ በተቻላት መጠን እራሷን ለመቆጣጠር ሞክራለች፡፡››

‹‹አዎ አንቺ ይገርማል… አሁን ሳስበው በህይወት ስላለውም እድለኛ ነኝ….››

‹‹እና እዚህ ስትመጪ ደግሞ ሌላ ታሪክ አጋጠመሽ››

‹‹አዎ በጣም የሚያንገበግበው እና ስብርብር ያደረገኝ ደግሞ ይሄኛው ነው›› አለች …..አሁን በፍራቻ እና በአድናቆት ነበር የምትመልስልኝ
የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች‹‹መቼስ ታውቂዋለሽ…አንድ ቀን ወደ ሀገሬ ስመለስ ቤት ይኖረኛል….አገባዋለሁ..ልጅ ወልድለታለሁ ብዬ ደሞዜንም .ሰውዬው ይሰጠኝ የነበረውንም ብር እልክለት ነበር…ቤት እየሰራው ነው ይለኛል….የቤት ዕቃ እያሞለው ነው ይለኛል..ምን አለፋሽ ከሶስት መቶ ሺ ብር በላይ  ነው የላኩለት …..ግን ስደርስ ሌላ ሴት አግብቶ አንድ ልጅ ወልዶ ጠበቀኝ…..ከዛ ምን ልንገርሽ ሁሉ ነገር አስጠላኝ …ክፍለሀገር ወደ ቤተሰቦቼም መሄድ አልፈለግኩም እንዴት ብዬ ምን ይዤ ሄዳለሁ…?……..  
‹‹አዎ ለእሱ ያልሽውን ሶስት መቶ ሺብር ስትልኪለት ለቤተሰቦችሽ የላክሺው ብር ሲደመር 50 ሺ ብርም አይሞላም..››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ..የሚያንገበግበኝ እና ሞራሌን እንክትክት ያደረገው እና ዛሬ እዚህ ያስገኘኝ ይሄው  ነው….

አይዞሽ እናስተካክለዋለን ..በእኔ ተማመኚ..አልኳትና የደረሰውን ቁርስ አቅርቤ መብላት ጀመርን›…

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 29,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18