ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
197K subscribers
281 photos
1 video
16 files
209 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
💀የጠፋው ሬሳ💀
#ክፍል ሀያ-ሁለት


...ብልጭ ድርግም በሚለው የሆስፒታሉ መብራት የሆነ ሰው ይታየኛል አሁን ፊቴን አኮሳትሬ ግንባሬን ጨምድጄ እልሄን ሰብስቤ ወደፊት መጠጋቴን ጀመርኩ የጓደኞቼን ደም ለመበቀል ከመፈለጌ የተነሳ ወደኔ እንኳን እስኪመጣ አልጠበኩትም ራሴ ተጠጋሁት የያዝኩትን ቢላ ዘቅዝቄ እጀታውን በማርያም ጣቴ ጋር አድርጌ ስለቱን ወደ ክርኔ አስደግፌ በለዘበ አረማመድ መጠጋቴ ቀጠልኩ ነገር ከኔ ተቃራኒ ጥግ ላይ ያለው ሰው አይንቀሳቀስም ለምን እንደሆነ ባላውቅም እኔ ግን በድፍረት እና በንዴት እየተጠጋሁት ነው...የሆስፒታሉ መብራት ብልጭ ድርግሙን ትቶ ቀጥ ብሎ በራ ጥግ የተመለከትኩት ነገር አይደለም ሊገለኝ ይልቁና በፍርሃት ተሸማቆ ራሱን አሳንሶ ተኮራምቶ ፊቱን ሸሽጎ ተቀምጧል..."እንደ ወንድ ተነስተህ ና እንደ ፈሪ አትሸፋፈን እንደ ገዳይ ፊት ለፊት ውጣ አትርመጥመጥ" አልኩት ንግግሬን በእርጋት ጀምሬ ንዴቴ ሲብስ እየጮውኩኝ ነገር ግን አሁንም ዝምታ ነበር መልሱ...ወደሗላ አድርጌ የነበረውን ስለት ወደ ፊት መልሼ ደረቱ ላይ ለመሰንቀር ወደ ተቀመጠበት ስፍራ ኮቴ ቢስ በሆነ እርምጃ ተጠጋሁት ነገር ግን ከሗላይ በሰከንድ ሽርፍራፊ እጅግ ፈጣን ሰው አለፈ...ከመቅፅበትም ፊቴን መልሼ የያዝኩን ስለታማ ቢላ ሰነዘርኩኝ ነገር ግን አንዳች ያጠቃሁት ፍጡር የለም ከአጠገቤ ያለው የሆስፒታሉ ክፍል አሁን እንደተከፈተ ያስታውቃል እንቅስቃሴውን እንኳን አላቆመም...በጥሞና ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁኝ ግን ማንም አልነበረም ከቆምኩበት ሁለት ከፍል አለፍ ብሎ የሚገኘው ሶስተኛው ክፍል ሲከፈት ተሰማኝ ሆስፒታሉ ፀጥ ብሎ ስለነበር ሲከፈት ያለው የበር ድምፅ ይሰማል "ሲጢጥ" ሲል....አሁን መሃል ላይ ገብቻለሁ ከፊትለፊት የሆነ ሰው አለ ከሗላ ደግሞ ተኮራምቶ የተቀመጠው ፡...ዞር ብዬ ጀርባዬን ቃኘው ማንም ያ ሰው አሁንም ኩርምት እንዳለ ነው የመግደልም አቅም ያለው አልመሰለኝም ልክ እንደኔና ጓደኞቼ ጥቃት የደረሰበት ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ ይሄን ሁላ ማሰላስለው ሲከፈት ድምፁ ወደተሰማኝ በር እያመራሁ በአይኖቼም መለስ ብዬ ጀርባዬን እየተመለከትኩ ነው አሁን ክፍሉጋ ልደርስ አንድ እርምጃ ያህል ቀርቶኛል የቀረኝንም እርምጃ እግሬን አንስቼ ልራመድ ስል መብራቱ ድርግም ብሎ ጠፋ ከመቅፅበትም አጠገቤ ያለው ግድግዳ ላይ ተደግፌ ቁልቁል ወርጄ ድምፄን አጥፍቼ ፀጥ አልኩኝ በጨለማው መሀል የትልቅ ከስክስ ጫማ ድምፅ ተሰማኝ ሰፋ ያለ የእግር አጣጣል እንዳለው ከምሰማው የእግር ኮቴ ተረዳሁ ውስስጤ ፍርሃት የሚባል የለም በቀል እንጂ ነገር ግን ጨለማወው ነገሮችን በብዙ እያከበደብኝ ነው "ቢሆንም ግን ገድዬው ወይ ገሎኝ ከዚ አረመኔ ነፍሰ በላ ጋር እለያያለሁ" አልኩኝ ለራሴ እርምጃው እየቀረበኝ ነው የያዝኩትን ስለት በተጠንቀቅ አዘጋጅቼ እየጠበኩ ነው...በድንገት መብራቱ ፏ ብሎ በራ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነስቼ የእግር ዱካው ይሰማኝ ወደነበረው ስፍራ የያዝኩትን ስለታም ቢላ ሰነዘርኩኝ ነገር ግን ማንም አልነበረም ወዲያውኑ ጎላና ጎርነን ባለ ድምፅ ልብን የሚያርድ ሳቅ ተሰማ ባለሁበት ተንበረከኩ እንደሚዲህ ህፃን ቀዳዴ እየሄድኩ ግራና ቀኜን ተመለከትኩ ነገር ግን ምንም የለም ነበር ሳቁ ሳቅ ብቻ አይደለም አንዳች ሃይል አለው ቁጣዬን ነጠቀኝ እልሄን በፍርሃት ለወጠው በቀሌን የሽሽት አደረገው በጣም ተደነኩኝ አብዝቶም ገረመኝ ካልመጣ ስል የነበርኩት ቤት ልውጣ ብዬ ተጨነኩኝ ጣቶቼ ቢላውን መጨበጥ እስኪያቅታቸው ተብረከረኩ በዛ የውድቅት ምሽት ከየት መጡ የማይባሉ ቁራዎች ሆስፒታሉ ውስጥ ተመሙ ራሳቸውን ከግድግዳ ጋር እያጋጩ ኮሪደሩን በደም አጨቀዩት አብዝተውም ይጮሁ ነበር መሃል ላይ ሆኜ በግንባሬ ከወለሉ ተዋድጄ ሞቴን መጠበቅ ጀመርኩኝ አቀርቅሬ ባለሁበት ጊዜ አንገቴ ላይ ያለው የብር ሃብል ወለሉ ላይ ተመለከትኩት ግንባሬንም ቀና አድርጌ የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆነው አንድ አምላክ የተሰቀለበት መስቀል ነበር መስቀሉ ላይም የኔ እና የዓለሙ አዳኝ እንዳላቀረቅር አቀርቅሮ አየሁት ህመሜን ታሞልኝ ተቸንክሮ አየሁት....እሱን ባየው ጊዜ ንዴቴ እና እልሄ መታደስ ጀመረ ስልቱን ጨብጬ በሁለት እግሬ ቆምኩኝ ነገር ግን ሆስፒታሉ በደም ጨቅይቶ የነበረው በቁራ ድምፅ የታወከው ስነሳ ግን ሰላም ነበር...መጀመሪያ ጥግ ላይ ካየሁት ሰው በቀር በድጋሜ ማንም አልነበረም ወደዛም ሰው ቀጥ ብዬ ተጠጋሁ ስደርስም "እባክህ አትግደለኝ እባክህ" እያለች ሳግ እየተናነቃት የምትማፀን ሴት ነበረች "አይዞሽ አልጎዳሽም ተነሺ" ስላት "ሜርሲዬ" ብላ አቀፈችኝ የመየውን ማመን አልቻልኩም ሞቱ ካልኳቸው ጓደኞቼ መሃል ቄድስቴ ነች "ቅድስቴ አንቺ ነሽ እንዴ ተጎዳሽ የሆንሽው ነገር አለ?" ብዬ ጠየኳት ሰውነቷን እየደባበስኩ "ምንም አልሆንኩም ባባን ወስዶታል ባርሳ ደሞ የት እንዳለች አላውቅም" አለችኝ "አታልቅሺ እናገኛቸዋለን" ብዬ አባበልኳትና እጇን ይዤ ወደ መውጫው ሳመራ "ሜርሲዬ ይሄ ለመገለን የሚፈልገው ሰው ትዝ ካለሽ ከወር በፊት ጠፋ የተባለ ሬሳ ነበር ሰዎችም እንደሚሉትም ሞቶ የተነሳ የመናፍስት እጅ ያለበት...እያለች እየነገረችኝ ሳለ ዞር ብዬ የምትለው ገርሞኝ እንግዳ ሆኖብኝም ልሰማ ስቆም ሰውዬው ከየት መጣ ሳይባል የእግሩ ዱካ ሳይሰማ አንዳችም ነገር ሳይታወቀን በንፋስ ፍጥነት ከቅድስታ ጀርባ ቆሟል..............

..........ይቀጥላል...........

ቀጣዩን#ክፍል ሀያ ሶስት እንዲቀጥል👍
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን

📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖
💀የጠፋው ሬሳ💀
#ክፍል ሀያ-ሶስት

...የማየውን ማመን አቃተኝ ኮቴውን ወይም ድምፁን አልሰማሁኝም ግን አጠገባችን ተገኝቷል ቅድስቴ እንዳለችውም ይህ ሰው በአንድ መናፍስታዊ አገዛዝ ስር እንዳለ ውስጤ አረጋገጠልኝ...ሰውዬውን ከጀርባዋ እንደተመለከትኩት የቅድስቴ ስም ጠርቼ ወደራሴ ጎተትኳት ተያይዘንም እሷ ከላይ እኔ ከታች ሆኜ ወለሉ ላይ ወደቅን አንገቴን ከፍ አድርጌ ስመለከት ሰውዬው የለም ትቶን እንደሄደ አስቤ ደስ አለኝ "አይዞሽ ቅድስቴ ተርፈናል ሌሎቹን ፈልገን ከዚ እንሄዳሀን" አልኳት ነገር ግን መልስ አልሰጠችኝም...አይርገበገብም እንጂ አይኖ ተከፍቷል በጣም ግራ ተጋባሁ ሰውዬው ምንም ሲያረግ አልተመለከትኩትም ነበር እና ምን ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል...ደግሜ ደጋግሜ ስሟን ጠራሁት ግን ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠችኝም ነበር ፊቷ ላይ የመጎዳት ነገር አይነበብበትም ቀስ አድርጌ ከላዬ ላይ አንስቼ ወገቧን ደገፍ አድርጌ በጀርባዋ ሳስተኛት የዛገ የሚመስል ስለታማ ብረት በጉሮሮዋ ወጣ ከድንጋጤዬ የተነሳ እጅግ በብዙ ድምፅ ጮውኩኝ ደጋገምኩት አይኔንም ከሷ ላይ መልሼ በዳዴ ከአጠገቧ ሸሸሁ አንዱ ጥግ ላይ ሆኜ ተኮራምቼም አነባሁኝ ያ አረመኔ ሰውዬ እኔን ለምን እንደማይገድለኝ ትንግርት ሆኖብኛል... ቅድስቴ ወለሉ ላይ እንደተንጋለለች ነው እኔ ደግሞ እሷን ማየት ፈርቼ ከአንዱ ጥግ ላይ ነኝ...አሁን መቋቋም የማልችለው ገደብ ያጣ ቁጣ ውስጤ መንፎልፎል ጀመረ ግን ደግሞ የቅድስቴን ሞት ሳይ ጓደኛዬን ያላተረፈ እልህ ብዬም ራሴን አኮማሽሻለሁ...የተቀመጥኩበት ሆኜ ራሴን ከግድግዳው እያጋጨሁ ምንም ሳላወራ መራር እንባዬን አፈሰስኩ አለቀስኩ የእንባ ከረጢቴም እስኪደርቅ ድረስ...ክፉኛ ራስ ምታትም ስቃዬን አበዛው...ሳላስበው እዛው ከተቀመጥኩበት ስፍራ እንቅልፍ አሸለበኝ በስቃይ የዛለ ሰውነቴ ከዚ በላይ የመቆየት አቅም አልነበረውም ነበር...ይመስለኛል ለሰዓታት ያህል ቁጭ ባልኩበት ስፍራ ተኝቻለሁ...እንደነቃሁም እንደምንም ብዬ ወደ ቅድስቴ በድን ዞር አልኩኝ ነገር ግን ቅድስቴ አልነበረችም ነበር ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ አይኔንም ጠራርጌ በድጋሜ ተመለከትኩ ቅድስቴ ፈፅሞ የለችም...እንደ ፈጣሪ ቃል የጓደኞቼ በድን ከአፈር ሳይዋሃድ በሰው አውሬ ተበልቶ አለቀ ይሄ ምነኛ የሚያም እና የማይሽር ቁስል እንደሆነ እኔና እኔ ነኝ የምናውቀው...ቀስ ብዬ በድኗ ወደነበረበት ወለል ተጠጋሁ መሬት ላይ እየጎተተ እንደወሰዳት የደም ምልክቱ ያሳያል የጣልኩትን ቢላ አንስቼ ደሙን እየተከተልኩ ቀስ ባለ እርምጃ መሄድ ጀመርኩኝ እነሱ ወዳሉበት ክፍል በሚወስደው በር በኩል ይጠቁማል የደም ምልክቱ እኔም ያለ አንዳች ፍራቻ በተረጋጋ እና ማስተዋል በሞላበት እርምጃ መጠጋቴን ቀጠልኩ..."ከሞት በላይ ምንም ሊመጣ አይችልም ቀኔ ከሆነ ትንታም ይገለኛል አይደለም ይሄ ክፉ አረመኔ ሰው" እያልኩኝ ውስጤን ለጭካኔ እያነሳሳሁ እና እያጀገንኩ ገዳይን ለመግደል በተጠንቀቅ ራሴን አዘጋጀሁ...የደሙ ምልክት ብዙ ጋውኖች ወደተሰቀሉበት ክፍል ይጠቁማል የሮቤል በድን ወደነበረበት...አሁን በጣም ድንጋጤዬ መጣ እነዛ ንፋስ የሚቆርጡ የሚመስሉ ስለቶች የቅድስቴ ገላ ላይ ሊያርፉ እንደሆነ ገብቶኛል ይሄኔ እርምጃዬን ጨመር አድርጌ ግን ደግሞ ጥንቃቄ ሳይለየኝ ወደ በሩ ተቀረብኩኝ አልተዘጋም ነበር ገርበብ እንዳለ ነው አንገቴን ወደ ውስጥ ቀስ ብዬ ላኩት ሰውዬው ለሮቤል ሲያረግ የነበረውን ሁሉ አድርጓል ከጋወን እስከ ጓንት ድረስ ትጥቁን አማልቷል የቀረው ቢኖር ያ የዋይታ እና የሰቆቃ ነገር ግን እሱን የሚያስደስተው እና ሰላም የሚሰጠው ድምፅ ብቻ ቀርቷል እንደጠበኩትም ያንን የሚሰቀጥጥ የስቃይ ዋይታ ከፈተው አሁን በይበልጥ ከፊል ሰውነቴን ወደ ውስጥ አስገብቼ ሁኔታውን መከታተል ጀመርኩ ለሮቤል እንዳረገው ሁሉ ለቅድስቴም ዘይት ጥዷል እያፏጨ እና እየተንቀሳቀሰ ስለቶቹን መመራረጥ ጀመረ በድንገት ዋይታው ፀጥ አለ ሰውዬውም ከእንቅስቃሴው ተገታ ባለበትም ቦላ በአርምሞ ቆመ እኔም አመሉን ስለማውቀው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረኩም ነበር ትንሽ እንደቆየ ጩኸቱ ጀመረ በዚ ጊዜ የሰውነቴ ክብደት በበሩ ቀድሞ በገባው እግሬ ላይ ስለበር ድካም ተሰማኝና ራሴን ለማሳረፍ ወደነበርኩበት ቦታ ልመለስ ስል አነስ የምትለዋ ሴትዮ ከፊት ለፊቴ ነጭ ጋወን ለብሳ የብረት መዶሻ ይዛ ቆማለች በጣም ደነገጥኩኝ ደነዘዝኩኝም ሴትየዋ ጊዜ አልፈጀችም ነበር ወዲያውኑ በመዶሻው ግንባሬን ስትለኝ በሩን በርግጄ ወለሉ ላይ ተዘረጋሁ እይየተስለመለመ ወደላይ ስመለከት አረመኔው ሰውዬ መጥረቢያውን ከፍ አረጎ መሀል ጭንቅላቴ.............

......ይቀጥላል...........

ቀጣዩን#ክፍል ሀያ አራት እንዲቀጥል👍
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን

📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ሶስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


በተቃራኒው ጦርነት
ወደ ተዘፈቀች አገር መመለሱ ራሱ አንድ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡.... እዚህ ነገር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ለምን ገባሁ? አለች ልቧ
እየተሰበረ ሁን ለመጸጸት ጊዜ የለም፡ አንዴ ስለወሰንኩ ወደ ኋላ
የምልበት ነገር የለም፡፡ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥም አለች መልሳ
በሆዷ ሀሳቧ አንድ ቦታ አልረጋ ብሏት፡

ማርክ እጇን ለቀም አድርጎ ሲይዝ እንዳይለቃት ፈራች፡፡ ‹አንድ ጊዜ ሃሳብሽን ለውጠሻል። አሁንም ደግመሽ መለወጥ ትችያለሽ›› አለ ለማሳመን፡፡
ከኔ ጋር አሜሪካ እንሂድና ላግባሽ፡፡ ልጆቻችንን ይዘን ባህር ዳር እንጫወታለን የምንወልዳቸው ልጆች ቴኒስ እየተጫወቱ፣ እየዋኙ ብስክሌት እየነዱ ያድጋሉ፡ ስንት ልጅ ነው መውለድ የምትፈልጊው?››

አሁን መወላወሉን አቁማለች፡፡ ‹‹ማርክ እያደረኩት ያለሁት ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ ተመልሼ ወዳገሬ እሄዳለሁ›› አለች፡፡
ያለችውን የተቀበለ መሆኑን ተረዳች፡፡ ሁለቱም ሀዘን ገብቷቸውና የሚሰሩትን አጥተው ዓይን ላይን ይተያያሉ፡፡ የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም
ዝም ብለዋል፡

ከዚያም መርቪን ቡና ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፡፡

ዳያና ባሏ ፊቷ መጥቶ ድቅን ሲልባት ዓይኗን ማመን አቃታት፡ ልክ
አንድ የሆነ መንፈስ ፊት የቆመ ይመስል አፈጠጠችበት፡ እንዴት እዚህ ሊመጣ ቻለ? ሊሆን አይችልም

‹‹እዚህ ተገኘሽ አይደል!›› አለ መርቪን በተለመደው አስገምጋሚ ድምጹ
ዳያና ግራ ተጋባች፡፡ መርቪን እዚህ መገኘቱ አስደንቋታል፣ አስፈርቷታል፣ እፎይታ ሆኗታል፣ ቅሌት ውስጥም ከቷታል፡፡ ከሌላ ወንድ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ ባሏ ሲደርስባት በደመነፍስ እጇን ከማርክ እጅ መንጭቃ አላቀቀች

ማርክም ‹‹ምንድነው እሱ?›› ሲል ጠየቃት ነገሩ ስላልገባው፡

መርቪን ሁለት እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ ፊታቸው ተገትሯል፡

‹‹ማነው ይሄ ፊታችን የተገተረው?›› ሲል ጠየቀ ማርክ፡፡

‹‹ባሌ መርቪን ነው›› አለች በደከመ ድምጽ፡

‹‹ወይ አምላኬ!›› አለ ማርክ፡

‹‹እንዴት እዚህ ልትመጣ ቻልክ መርቪን?›› ስትል ጠየቀች ዳያና የምንተ እፍረቷን፡፡

‹‹ብራሴ አይሮፕላን በርሬ መጣሁ›› አለ ቁርጥ ባለ የአነጋገር ባህሪው:
ቆዳ ጃኬት የለበሰ ሲሆን በእጁ የሞተር ሳይክል ነጂ ቆብ አንጠልጥሏል፡፡
‹‹ኧረ ለመሆኑ እዚህ መሆናችንን እንዴት አወቅህ?›› ስትል ጥያቄዋን
ደገመች፡፡

‹በጻፍሽልኝ ደብዳቤ አሜሪካ እንደምትሄጂ ገልጸሻል፡ ወደ አሜሪካ
የሚኬደው ደግሞ በሰማይ በራሪ ጀልባ ብቻ መሆኑ ይታወቃል›› አለ በድል
አድራጊነት፡፡

የሷን ዱካ ተከታትሎ የምትሄድበትን መንገድ ገምቶ እሷ ጋ በመድረሱ ደስ እንዳለው ከገጽታው ይነበባል፡ በራሱ አይሮፕላን በርሮ ሊደርስባቸው
እንደሚችል ፈጽሞ አልጠረጠረችም፡፡ በዚህ መንገድ ተከታትሎ ስለደረሰባት ደካማ ነኝ ስትል አሰበች፡፡

ከእነሱ ትይዩ ባለው
ወንበር ላይ ተቀመጠና
‹‹እስቲ ዊስኪ አምጪልኝ›› ሲል አዘዘ አስተናጋጇን፡፡

ማርክ ብርጭቆውን አንስቶ ባንዴ ሲጨልጥ ዳያና ታየዋለች::በመጀመሪያ መርቪንን ሲያየው ተርበትብቶ ነበር፡፡ በኋላ ግን መርቪን አምባጓሮ እንደማያነሳ ሲገነዘብ ተረጋጋ ሆኖም ወምበሩን ገፋ አደረገና ከዳያና ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ፡፡ የሰው ሚስት እጅ እንደያዝ ባሏ ከተፍ ሲልበት ሳያፍር አልቀረም፡

ዳያና ድፍረት እንዲሰጣት ብላ ከአልኮሉ ተጎነጨች፡ መርቪን በጭንቀት ያያታል። ግራ መጋባቱንና መጎዳቱን ከፊቱ ስታይ ደረቱ ውስጥ
ተወሸቂ! ተወሸቂ! አላት፡፡ ከፊቱ ምን እንደሚጠብቀው ሳያውቅ እሷን ፍለጋ
አገር አቋርጦ መጥቷል፡፡ እጇን ሰዳ በማጽናናት ሁኔታ ክንዱን ያዝ አደረገችው፡፡

ሚስቱ በውሽማዋ ፊት ያዝ ስታደርገው መርቪን ማርክን በእፍረት አየት አደረገው፡፡ ዊስኪው ሲመጣለት አንስቶ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠው::
ማርክ በበኩሉ ዳያናን የሚያጣ መስሎት ወምበሩን ወደ እሷ አስጠጋ
ዳያና በሁኔታው ግራ ተጋባች፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ከዚህ በፊት
ገጥሟት አያውቅም:: ሁለቱም ሰዎች ይወዱዋታል ከሁለቱም ጋር ተኝታለች፡ ሁለቱም ይህን ያውቃሉ፡፡ በጣም አሳፋሪ፡፡ ሁለቱንም ማጽናናት ፈለገች፧ ሆኖም ፈራች፡፡ አሁን ወደ መከላከሉ አዘምብላለች። ከሁለቱም ራቅ ብላ ተቀመጠችና ‹‹መርቪን አንተን ልጎዳ ብዬ አይደለም እዚህ መዘዝ ውስጥ የገባሁት›› አለች

መርቪን ፊቱን ቅጭም አድርጎ ‹‹አምንሻለሁ›› አለ
‹‹ታምነኛለህ? የሆነውን ሁሉ ትቀበለዋለህ?›› አለች ዳያና፡፡

መርቪን ማርክ ላይ አፍጥጦ ነገር ለመፈለግ በሚመስል ሁኔታ
ተጠጋውና ውሽማሽ አሜሪካዊ ይመስላል፤ከአፍ የወደቀ ጥሬ!
የተመኘሺውን አግኘተሻል›› አለ፡፡

ማርክ አፈገፈገ፤ ምንም ቃል ሳይተነፍስ መርቪንን አፍጥጦ ያየዋል ማርክ ጠብ ፈላጊ አይነት ሰው አይደለም፡፡ ሁኔታው ግራ አጋብቶታል፡ ከዚህ በፊት ተገናኝተው ባያውቁም መርቪን ዋና ባላንጣው ነው፡፡ ማታ ማታ ዳያና አቅፋው የምትተኛው ሰው ማን ይሆን?› ሲል ራሱን ሲጠይቅ ከርሟል፡፡ አሁን ማን እንደሆነ አውቆታል። ከማርክ ጋር ሲተያይ መርቪን ስለማርክ ምንም የተጨነቀ አይመስልም፡፡
ዳያና ሁለቱን ባላንጣዎች ተመለከተቻቸው፡ ምንም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም መርቪን ዘንካታ፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚል፣ ኮስታራና ነርቨስ ነው ማርክ
ደግሞ አጭር፣ ሽክ ያለ፣ ነቃ ያለና ስው ሲናገር ጆሮ የሚሰጥ ሰው ነው ማርክ
አንድ ቀን ይህን ታሪክ በኮመዲ ስራው ውስጥ አካቶ ሳያቀርበው አይቀርም ስትል ዳያና አሰበች፡

አይኖቿ እምባ አንቆርዝዘዋል፡ መሃረብ አውጥታ ንፍጧን ተናፈጠች
«ልክስክስ መሆኔን አውቄዋለሁ›› አለች፡

‹‹ልክስክስ!›› ሲል አሾፈ መርቪን ቃሉ አንሶበት፡፡ ‹‹በጣም የጅል ስራ
ዳያና ባሏ በተናገረው ተሸማቀቀች፡ ብዙ ጊዜ ስድቡ አፏን እንዳዘጋት
ነው፡፡ ዛሬ ግን ከስድብም በላይ ይገባታል፡፡

አስተናጋጇና ጥግ ተቀምጠው መጠጣቸውን የሚኮመኩሙት ሁለት
ሰዎች ሁሉን ነገር ጣጥለው ትእይንቱን በጉጉት ይመለከታሉ፤ ‹‹ምን ይከተል ይሆን?› እያሉ።

መርቪን አስተናጋጇን ጠራና ‹የኔ ቆንጆ ሳንድዊች ብታመጪልኝ›› ሲል አዘዛት እሷም ‹‹እሺ የኔ ጌታ›› አለችው በፍጹም ትህትና፡፡
አስተናጋጆች መርቪንን ይወዱታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮ እያስጠላኝ መጥቷል ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው አሜሪካ ለመሄድ የወሰንኩት›› አለች ዳያና፡፡

"ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው ያልሽው! አሜሪካ ጓደኛ የለሽ፣ ዘመድ የለሽ፣ ቤት የለሽ. . .አዕምሮሽ ማሰብ አቆመ እንዴ!›› አለ መርቪን፡፡

ዳያና መርቪን ስለደረሰላት አምላኳን ብታመሰግንም እንዳይጨክንባት
ፈርታለች ማርክ በእጁ ትከሻዋን ነካ አደረገና ‹‹ለምንድነው አሜሪካ ደስታ
የማታገኚው፧ እዚያ ለመሄድ ማሰብሽ ስህተት አይደለም›› አላት ድምጹን
ዝቅ አድርጎ፡፡

መርቪንን ከዚህ በላይ ማናደዱ አስፈርቷታል፡፡ ምናልባትም ትቷት
ተመልሶ ይሄድ ይሆናል፡ በማርክና በሉሉ ቤል ፊት ‹‹አልፈልግሽም›› ብሎ
ቢላት እንዴት እንደሚያበሳጫት መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ አያደርግም
አይባልም፡፡ መርቪን ተከትሏት ባይመጣ ጥሩ ነበር፡፡ ይህ ማለት ደግሞ
እዚሁ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ ይኖርበታል፡፡ ከዚያም ብርጭቆዋን አነሳችና ከንፈሯን አስነክታ ‹‹ይህን መጠጥ አልፈልግም›› ብላ መልሳ አስቀመጠችው

በዚህ ጊዜ ማርክ ‹‹ሻይ ላምጣልሽ?›› አላት፡፡
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ሶስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

እዚህ አብሬያቸው ከምኖረው የሰው ልጆች የበለጠ እውቀትና የረቀቀ ጥበብ የሰጣችሁ እሱ መሆኑን ታማናለችሁ ወይ? .በመካከላችሁ ያለው ግንኙነትስ እንዴት ነው ?ማለቴ በእናንተ እና በእግዚያብሄር መካከል…አንድ ጊዜ ስለአንተ ከእማዬ የሰማሁትን ለአንድ ቄስ ብነግራቸው….እነሱ ከእግዚያብሄር ተጣልተው ወደምድር ተወርውረው የነበሩ የመላእክት ዘሮች ናቸው ብለው አስረዱኝ...ወደምድር መጥተው ከሰው ልጆች ጋር ተስማምተው እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸውም.እነሱ ግን መላውን የሰው ልጅ በከሉት ..ሰላማዊውን ፍጡር ጦር መሳሪያ አሰራርና ጎራዴ አሞረረድ ከዛም አልፎ የጦርነት ጥበብ እና የዘረፋና ግድያ ስልቶችን በማስተማር እርስ  በርስ አጫረሱት ..በስርዓትና ይኖር የነበረውን ግብረሰዶምና ሊዚቢያ አደረጉት..እግዚያብሄር በጥበብና በፍቅር በመፍጠር በምድር የበተናቸውን እንስሳትን አንዱን ከሌላው እያዳቀሉ አስፈሪና አጥፊ ፍጥረታትና መፍጠር ጀመሩ..የጥንቆላና የሞርት ጥበብን ለሰው ልጅ በማስተማር አእምሮውን በከሉት ከዛ አምላክ ተቆጣና የጥፋት ውሀ ላከ ..ምድርንም በውስጦ ያሉትን ከእነሱ ጋር የተባበሩትን ትምህርታቸውንና በጥባቸው የተደሙትን ሁሉ አጠፋ…የሰው  ለጅና እንስሳቱ ለዘር እንዲሆን ጥንድ እየሆነ በኖህ መርከብ ተጠልሎ እንደተረፈ ሁሉ.አነሱም የተወሰኑት የረቀቀ ጥበባቸው በመጠቀም ምድርን ለቀው በመሰደድ በጥፋት ውሀው ሙሉ በሙሉ ከመጥፋት እራሳቸውን ያተረፉ ይመስለኛል ….

እንደምገምተው ከሆነ አሁን አባቴ የምትይውና በሌላ አለም እንደሚኖር ለእናትሽ የነገራት ፍጥረት ከእነሱ አንዱ ነው አሉኝ…..፡፡ከእግዚያብሄር ጋረ የሚያቀያይምሽና ሀይማኖትሽ የሚያስክድሽ ከይሲ ፍጥረት ስለሆነ ቢመጣ እንኳን እንዳትቀርቢው.በስመአብ፤ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በማለት ደጋግመሽ በማማተብ ከስርሽ አባሪው ብለው መከሩኝ ..አልተከራከርኮቸውም ምን አልባት ያሉት እውነት ሊሆን ይችላል ብዬ አሰብኩ፡፡እንኳን ሙለ በመሉ የእናንተ ዘር መሆነን ተችሎ ይቅርና እኔ እራሱ ያንተ ደም በውስጤ ስላለ በውስጤ የሚንቀለቀለው የክፋት ኃይልና የወሲብ ጥማት እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ከቄሱ ጋር ያልተስማማሁበት አንድ ነገር ቢኖር ቢመጣ እንዳትቀርቢው ብለው ያሉኝን ነው..ወይ ብትመጣ እንዴት እንደምጠመጠምብህ ሳስበው እራሱ ውስጤ በደስታ ይነዝራል፡፡

ይቀልዳሉ እንዴ? ሴይጣንም ሆንክ እግዚያሄር አባቴ ነህ…መርጬ አይደለም ካንተ የተፈጠርኩት..
እና ለማለት የፈለኩት እውነትም ቄሱ ያሉኝ ነገር የእውነት ከሆነ በመጀመሪያ በእናንተና በእግዚያሄር መካከል  የነበረውንም አለመጋባባት ምክንያትም የሚያስረዳኝ አካል አላገኘሁም…ስለዚህ ማን ጥፋተኛ ማን ትክክል  እንደሆነ መወሰን አልችልም…ደግሞ እግዚያብሄር ይሳሳታል እንዴ?አቦ እኔ እንጃ …ለማኛውም እስከአሁን የዘበዘብኩትን ሁሉ እርሳውና ለእናቴ እባክህ ምትችለውን አድርግ…›ሀሳቧን ሳትቋጭ ዝናቡ ዣ ብሎ መርገፈ ጀመረ….በትላልቅ ዕድሜ ጠገብ ዛፎችና በርካታ ቁጥቆጦችና ሰርጎ  የሚረግፍ በመሆኑ ዝናቡ ከላይ በሚረግፈው ልክ ሳይሆን በየቅርንጫፎቹ እየተሹለኮለከ በቅጠሎች ላይ  የተንኳለለ ነበር እሷ  ጋር ሚደርሰው፡፡ እሷ  ግን ግድም አልነበራትም…..ቦታም ቀይራ ለመጠለል አልሞከረችም…. ልክ እዛ ደን ውስጥ ዛፎቹ  ስር ተተክላ እንደበቀለች ታዳጊ ችግኝ.. በደስታ ቅርንጫፎቾንና መላ አካሏን ወዲህ ወዲያ እያዋወዘች የሚዘንበውን ዝናብ በፍቅር እንደምትመጥ አይነት እሷም ተመሳሳዩን ነበር ያደረገችው..

ከ20 ደቂቃ በኃላ ዝናቡ  ቢያባራም እየተንኳለለ ከቅርንጫፎቹ ቅጠሎች  የሚንጠባጠበው ውሀ ግን አልተቋረጠም ነበር….ንስሯ እንደአካሄዷ አካባቢውን እየደረማመሰ መጥቶ ከፊት ለፊቷ   አረፈ፤በቅርንጫፎቹ  ውስጥ እየሾለከ ሲመጣ አካሉ ላይ ካረፉበት የውሀ እንክበብሎች በስተቀር ሲሄድ እንደነበረው ፍፅም ደረቅ አካል ነው ያለው፡፡ያው ይሄ የእሱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ንስሮች ፀጋ ነው፡ዝናብ ሲዘንብ ደመናውን ሰንጥቀው አልፈው ከበላዩ ይሆኑን ወደታች አዘቅዝቀው በትዝብት ያዩታል..ምድርና በውስጧ ያሉት ሌሎች ፍጥረቶች ሁሉ ግን በሰማይ የሚበሩትን ሌሎች እዋፍቶችም ሳይቀሩ ወደዱም አልወዱም ወይ መሸሸጊያ ዋሻ  ይፈልጋሉ ወይ ደግሞ በዝናቡ ይቀጠቀጣሉ፡፡

‹‹እሺ የት ሄደህ መጣህ?››

እምሮውን ከፈተላት.የሄደበትን ቦታ ሳይሆን እናቷ የምትድንበትን ዘዴ ነው የነገራት፡፡መጀመሪያው መድሀኒት ጨካኝ ነፍስ ያላቸው…ከ7 ሰዎች በላይ የገደሉ የሶስት ሰዎችን አንገት ቆርጦ እናትትሽ ቤት ውስጥ መቅበር ነው›የሚል መልዕክት በእምሮዋ ፃፈላት፡

‹‹ምን  እያልከኝ ነው….እኔ ሰው ልገድል ነው…?ለዛውም አስፈሪና ጭራቅ የሆኑ ሰዎችን?››
‹‹ለዚህ እኮ ነው….የእናትሽን ሞት በፀጋ ተቀበይ የምልሽ››ሲል በእምሮ መለሰላት፡፡

‹‹አንተ ከእናቴ ነጥለህ ብቻዬን ምን ልታደርገኝ  አስበሀል….?ሀዘኔ ያስደስትሀል ማለት ነው..?››

እዕምሮውን በነጭ  ቀለም ሞላው …እንዲህ የሚያደርገው ሲያዝንና በንግግሯ ወይም በድርጊቷ ሲበሳጭ እንደሆነ ታውቃለች፡››

‹‹ይቅርታ ላስከፋህ ፈልጌ አይደለም….በቃ አደርገዋለሁ…ሶስት ሰው ጭንቅላት አይደል፡፡ለዛውም የሶስት ጨካኝና ገዳይ የሆኑ ሰዎች ጭንቅላት… .አረ አደርገዋለሁ ደግሞ ለእናቴ››ስትል ፎከረች፡፡

‹‹እንደዛ ከሆነ በ15 ቀን ውስጥ ጭንቅላቱ ተገኝቶ መቀበር አለበት….ይሄ ጉዳይ በትክክል ከተፈፀመ እናትሽን ለአንድ አመት  በህይወት ያቆያታል፡፡

‹‹ፈክቶና በተስፋ  ተሞልቶ የነበረው ፊቷ በአንዴ ጨለመ››

‹‹ምን ማለት ነው…?እኔ ለእናቴ እኮ መቶ አመት ነው የምመኝላት….ከተቻለም ዘላለም እንድትኖር፡››

‹‹መጀመሪያ ይሄንን ማድረግ ነው የምትችይው ..ከዛ ደግሞ ሌላውን ዕድሜ እናትሽ እንድታገኝ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እናወራለን›››

‹‹ለምን ያኔ ?አሁን አትነግረኝም…ምን ያሰደብቅሀል ?››

‹‹የመጀመሪያው ካልተሳካ ሁለተኛውን ማወቅሽ ምንም እርባን የለውም …..››ብሎ ፍቃዷን ሳይጠብቅ ከአካባቢው ለቆ በረረ…ሆዱ ባዶ ስለሆነ የሚበላ ነገር ለማደን ነው ወደ ደኑ በጥልቀት የገባው….እሷም እንዴት አድርጋ  ጨካኝና ወንጀለኛ   ሰዎችን ጭንቅላት በ3 ቀን ውስጥ ማግኘት እደምተችል እያሰላሰለች ወደቤቷ  ጉዞዋን ቀጠለች፡፡  

ንስሯ ግን ተከትሏት አልሄደም..በተቃራኒው ሰማዩን ሰንጥቆ በረረ…

ይቀጥላል

#ክፍል 24,,እንዲለቀቀ(10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄