አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
183K subscribers
4.94K photos
156 videos
14 files
749 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
እስካሁን በዚህ ክረምት የዝውውር መስኮት ክለባችንን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ❗️

1⃣ #ሀብታሙ_ታደሰ#ወልቂጤ_ከነማ ( አጥቂ forward )

2⃣ #ሰይፈ_ዛኪር#ፌደራል_ፓሊስ ( አጥቂ forward )

3⃣ #ፈቱዲን_ጀማል#ሲዳማ_ቡና ( ተከላካይ defence )

4⃣ #አለምአንተ_ካሳ#ባህርዳር_ከነማ( ተከላካይ denfence)

5⃣ #ተክለማርያም_ሻንቆ#ሀዋሳ_ከነማ ( ግብ ጠባቂ Goal keeper )

6⃣ #ብስራት_ገበየሁ#ወልቂጤ_ከነማ ( የተከላካይ አማካይ defencive midfielder )

7⃣#ታፈሰ_ሰለሞን (ታፌ) ከ #ሀዋሳ_ከነማ ( የመሀል አማካይ central midfilder )

👉 #በዝውውሩ_ደስተኛ_ናችሁ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#ኢትዮጵያ_ቡና_የክረምቱ_የመጨረሻ_ፈራሚውን_ዝውውር_አጠናቀቀ ❗️

👉 በክረምቱ በርካታ ዝውውርን ያከናወኑት ኢትዮጵያ ቡናዎች ፍቅረየሱስ ተክለብርሃንን የግላቸው አድርገዋል።


የቀድሞው የኢትዮጵያ #ንግድ ባንክ እና #የሀዋሳ #የመሃል ሜዳ ተጨዋች #ፍቅረየሱስ በክረምቱ መከላከያን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም መከላከያ በፕሪምየር ሊጉ ማይሳተፍ መሆኑን ካረጋገጠ በኃላ ለክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየት የካሳዬ አራጌ ቡድንን ተቀላቅሏል።

👉 ኳስ ቁጥጥር ላይ መሰረት ያደረገው የካሳዬ አጨዋወትን ለመተግበር ዋነኛ የሆነውን የመሀል ሜዳቸውን እያጠናከሩ ሚገኙት ቡናዎች ከዚህ ቀደም #አለም አንተካሳ(ማርዮ)፣ #ታፈሰ ሰለሞን#አዲስ ፍስሀ፣ ማስፈረማቸው ሚታወስ ነው።


➡️ በዝዋይ በመከተም የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማከናወን ላይ ሚገኙት ኢትዮጵያ ቡና በሚቀጥሉት ቀናት ወደ# አዲስ አበባ ተመልሰው በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናሉ።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#ታፈሰ_ሰለሞን

በሁለተኛው ሳምንት ከጅማ አባጅፋር ጋር በነበረን ጨዋታ ላይ ጉዳት አጋጥሞት የሊጉ ጨዋታዎች ያመለጡት ታፈሰ ሰለሞን ያለፉትን ሳምንታት የልምምድ ሜዳ ላይ #ሙሉ_ልምምድ ማከናወን #የጀመረ ሲሆን በህክምና ክፍሉ እና በአሰልጣኞች ውሳኔ መሰረት ሜዳ ላይ የምንመለከተው ይሆናል ።

©eyobed_belayneh_coffee

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#5 👌
#ታፈሰ_ሰለሞን

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ብዙዎች ጨዋታ አዋቂ ነው ይሉታል። አንዳንድ ጊዜ ለቀልድ የሚያደርጋቸው ድርጊቶቹ እራሱ ላይ ትልቅ መዘዝ ይዘውበት ሲመጡ ይታያል..... የእግር ኳስ ችሎታውን ማንም ከጥያቄ የሚከተው የለም።
ኮልፌ ቀራኒዮ ተወልዶ ያደገው እና እስካሁንም እዛው የሚኖረው የዊንጌቱ ልጅ..... ከአቶ ሰለሞን ሸዋመነ እና ከወ/ሮ ንጋቱ ማሙዬ የተገኘው የዛሬው የምን እንጠይቅልዎ ተጋባዥ 5 ቁጥር ለባሹ #ታፈሰ_ሰለሞን ነው።
የእግር ኳስ ህይወቱ የሚጀመረው በአካባቢው በሚገኝ ትምህርት ቤት ግርማ ደቻሳ ፕሮጀክት ውስጥ ነው። ድንቅ ብቃቱን የተመለከቱት የኒያላ ስፖርት ክለብ በታዳጊ ቡድኑ ውስጥ ተይዞ 6 ወር ያክል ለታዳጊ ቡድኑ እንደተጫወተ ወደ ዋናው ቡድን በ2002 ዓ.ም ተካትቶ መጫወት ጀመረ። ለሁለት የውድድር ዓመት ኒያላ ከተጫወተ በኋላ ኢትዮ ኤሌትሪክን በመቀላቀልለሁለት ዓመት ቆይታ አድርጓል። ለ2006-2011 ዓ. ም ለስድስት ዓመታት ለሃዋሳ ከተማ መጫወትን ችሏል።
 ይህ ድንቅ ጥበበኛ ተጫዋች በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚመራውን የኢትዮጵያ ቡናን ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በማገልገል ላይ ይገኛል። በዛሬው ምን እንጠይቅዎ ዝግጅታችን ታፈሰ ሰለሞን ከእናንተ ለቀረበለት 10 ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል።

በሀዋሳ ቆይታህ በርካታ ጎሎች ታስቆጥር ነበር። በአለፈው ዓመት ይህንን ማድረግ አልቻልክም ለምን? 2013 ምን እንጠብቅ?

👉 ሀዋሳ አገባቸው እንደነበሩት ጎሎች በባለፈው ዓመት ለክለቤ ማስቆጠር አልቻልኩም። ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በተደጋጋሚ የደረሰብኝ ጉዳት ነው። ያ ደሞ ብዙ ጎል እንዳላስቆጥር ተጽዕኖ አድርጎብኛል። በዚህኛው የውድድር ዘመን የተሰጠኝ ሚና የበለጠ ወደጎል ስለሚደርስ የተሻለ ብዛት ያለው ጎሎች ይኖረኛል ብዬ እጠብቃለሁ።

በተጫዋች ዘመንህ ትልቅ ቦታ የምትሰጠው አሰልጣኝ ማነው?

👉 በፊት ላይ ለኔ ከማንም የማላወዳድረው ውበቱ አባተን ነበረ። አሁን ላይ ግን ካህሳዬን ማንም ላይደርስበት የተቀመጠ ነው። ለእርሱ ትልቅ ቦታ አለኝ!!

ከካሳዬ አጨዋወት ስልት ያመጣኸው ለውጥ ምንድን ነው ?

👉 ብዙ ማለት ይቻላል ግን አንድ ነገር ልበል ...... ከዚህ ቀደም በተጫወትኩባቸው ክለቦች ውስጥ ዘጠና ደቂቃ መጨረስ ይከብደኝ ነበር። በካሳዬ አጨዋወት ግን ምንም ሳይመስለኝ 90ደቂቃ ጨርሼ እወጣለሁ።

አሁን ባለን የተጨዋቾች ስብስብ ሻምፒዮን መሆን እንችላለን?

👉 ስብስብ በሚባል ነገር ብዙ ዕምነት የለኝም። አሁን በቡድኑ ውስጥ ባለነው ተጫዋቾች ሻምፒዮን ለመሆን የሚያግደን ነገር የለም። ስብስብህ አቅምና ፍላጎት ያሟላ ከሆነ ስም ያን ይህል ትርጉም የለዉም። ዋናው ለፍልስፍናው የሚሆኑ ልጆች አሉ ወይ ነው? ለዚህ ጥያቄ መልስ በቂ የሆነ የስም ስብስብ ባይኖረንም አቅምና ፍላጎላት ያላቸው ተጫዋቾችን የያዘው የኛ ቡድን ሻምፒዮን ከመሆን የሚያግደው የሚችል ነገር የለም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጥ በረኛ ተከላካይና የመሀል ተጫዋች እና አጥቂ .......

👉 በረኛ ጎሜዝ (ተክለማርያም)፣ ተከላካይ አስቻለው ታመነ ፣ መሀል ሚኪ (ሚኪያስ) አጥቂ አቡኪ (አቡበከር) የእኔ ቅድሚ ምርጫዎቼ ናቸው።

የቡናን ማሊያ መልበስ ምን አይነት ስሜት አለው?

👉የኢትዮጵያ ቡና ታላቅ ክለብ ነው። ማሊያውን ሜዳ ላይ በምትመለከትበት ጊዜ በተጋጣሚ ቡድኖች ላይ ትልቅ ተጽዕኖን ያሳድራል። እኔ ኢትዮጵያ ቡናን ልቀላቀል ስል የተሻለ ጥቅም ሊሰጡኝ የተዘጋጁ ክለቦች ነበሩ። እኔ ኢትዮጵያ ቡናን የመረጥኩበት ምክንያት ነበረኝ ።ይህንን ማልያ ለኔ መልበስ ትልቅ ቁም ነገር ነበረው። ማሊያውን ስትለብስ የማታውቀው ስሜት አብሮ ይጋባብሀል። እኔ በዚህ ማሊያ አንድ የሚፃፍ ታሪክ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ።

ስለ ፎቶው.....?

👉 በዕለቱ በብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ላይ እያለን እንደቀልድ የተነሳ ፎቶ እጅ ያላሰብኩትና አሁንም የሚቆጨኝ እና የሚያናድደኝ ድርጊት እንዲሆን አድርጎታል። ፎቶውን አስቻለው ታመነ ለምን እንደለቀቀው ባልገባኝ ልክ  ተለቆ ሳየው በጣም ነው የደነገጥኩት። በወቅቱ ማድረግ የሚችለው ደጋፊዎቻችንና በዚህ ድርጊት ያስከፋኋቸውን ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ነበር ። እጅግ በጣም ተረብሼ ነበር። አሁንም በዚህ ድርጊቴ ያስከፋኋቸውን ሰዎች፣ በተለይ የክለቤን ደጋፊዎች በድጋሚ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ።

ደጋፊው......

👉 ሰፈር (ዊንጌት)እጅግ ብዙ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች አሉ። ገና እንደፈረምኩ ተሰብስበው እቤት ነበር የመጡት። በወቅቱ በጣም ነበር ደስ ያለኝ ብዙ ብርታህ ሆነውኝም ነበር። በባለፈው የውድድር ዓመት በጉዳት ምክንያት ብዙ ከእኔ የሚጠበቀውን አልሰጠዋቸውም። ለዚህ 'ምንም ለክለብህ አድርግ' ቢባል ወደኋላ ለማይለው ደጋፊ በዚህኛው ዓመት ዋንጫ አንስተን አብረነው ብንደሰት ስሜቴ ነው። ደግሞም እናሳካዋለን።

በልጅነትህ ለየትኛው ክለብ መጫወት ትመኝ ነበር?

👉በልጅነቴ ያን ያክል ገብቼ ልጫወትበት የሚለው ቡድን አልነበረም። ኳስን ዝም ብዬ መጫወት ብቻ ነው የማስበው። በ2002 ዓ.ም ኒያላን ስቀላቀል እና ስታዲየም እየመጣሁ ኳስ መመልከት ስጀምር ግን ከኳስ ጋር ባላቸው እንቅስቃሴ በመነሳት ለቡና እና ለኤልፓ መጫወት እፈልግ ነበር።

በሜዳ ላይ በጣም አስቸጋሪ የምትለው ተጫዋች ማን ነው?

👉 ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሁለቴ አላስብም እንኳን አንድ ለመጥራት ይቅርና ከ1-10 ጥራ ብትለኝ አቡኪ፣አቡኩ ፣አቡኪ፣ አቡኪ ....... እልሀለው!!

 በመጨረሻም......

🎯ከዚህ በፊት በተፈጠረው ነገር በእኔ ላዘኑት በድጋሚ ታላቅ ይቅርታን እየጠየኩ ፤ በወቅቱ ለተረዱኝ እና ብርታት ለሆኑኝ በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
 
  
👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ለአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት 25 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

ከነዚ ዉስጥ ኢትዮጵያ ቡና 4 ተጫዋቾች አስመርጦል

በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚከናወነው መጪው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው #የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ቡድን በመጋቢት ወር ከማዳጋስካር እና ኮትዲቯር ጋር እንደሚጫወት ይጠበቃል

#ተክለማርያም_ሻንቆ
#አሥራት_ቱንጆ
#አማኑኤል_ዮሐንስ
#አቡበከር_ናስር

ብሔራዊ ቡድኑ ለመጨረሻ ጊዜ ለዝግጅት ከተጠራቸው ተጫዋቾች ውስጥ ፋሲል ገብረሚካኤል ፣ #ወንድሜነህ_ደረጄ ፣ ኤልያስ አታሮ ፣ አምሳሉ ጥላሁን ፣ #ታፈሰ_ሰለሞን ፣ መስፍን ታፈሰ እና አቤል ያለው በዚህኛው ምርጫ አልተካተቱም

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና- አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

#የባህር ዳር_ስታድየም የመጨረሻ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናል።
ጉዳት ያጋጠመውን ሱራፌል ጌታቸውን በሄኖክ ገምቴሳ ብቻ ለውጠው ወደ ሜዳ የገቡት የድሬዳዋው አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በጊዮርጊሱ ጨዋታ የነበረባቸውን የአጨራረስ ችግር ለመቅረፍ ልምምዶችን እንደሰሩ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ተናግረዋል።

በባህር ዳር የነበራቸውን ቆይታ በውጤት ለማገባደድ እንዳለሙ የተናገሩት አሠልጣኝ #ካሳዬ በበኩላቸው የፋሲልን ውጤት ሳያስቡ የራሳቸውን ሥራ ብቻ እየሰሩ ለመቀጠል ሀሳብ እንዳላቸው ተናግረዋለወ።

ከፋሲሉ ጨዋታም #ታፈሰ_ሰለሞን እና #አማኑኤል_ዮሃንስን በፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን እና እያሱ ታምሩ ለውጠው ለዛሬው ጨዋታ ቀርበዋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ እስከ #16ተኛ ሳምንት
የኢትዮጵያ ቡና #34 ጊዜ ኳስና መረብን ያገናኝ ሲሆን #19 ጎል ደም ተቆጥሮበታል በቡና በኩል የጎል አስቆጣሪዎቹን ዝርዝር በደረጃ እንደሚከተለዉ አስቀምጠነዋል


#አቡበከር_ናስር ~ 20
#ሀብታሙ_ታደሰ ~ 5
#አስራት_ቱንጆ ~ 3
#ታፈሰ_ሰለሞን ~ 2
#ሚኪያስ_መኮንን ~ 1
#አማኑኤል_ዮሃንስን ~ 1
#ዊሊያም_ሰለሞን ~ 1
#እንዳለ_ደባልቄ ~ 1

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች – ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ

ምሽት ላይ ከሚጀምረው ጨዋታ በፊት ተከታዮቹን መረጃዎች እንድትጋሩ ጋብዘናል።

ባህር ዳር ላይ ድሬዳዋ ከተማን ካሸነፉበት ስብስብ ውስጥ የአንድ ተጫዋች ለውጥ ያደረጉት አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ #ፍቅረየሱስ_ተወልደብርሀንን#ታፈሰ_ሰለሞን ተክተዋል።
በሀዋሳ ከተማ በኩል ከሰበታ ከተማው ሽንፈት ሦስት የአሰላለፍ ለውጦች ተደርገዋል።

በለውጦቹ አሰልጣኝ መሉጌታ ምህረት ብርሀኑ በቀለ ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ እና ተባረክ ሄፋሞን በአለልኝ አዘነ ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና መስፍን ታፈሰ ቦታ ተጠቅመዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ ነመሀል ዳኝነት ይመራዋል።

የቡድኖቹ የዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ኢትዮጵያ ቡና
99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
14 እያሱ ታምሩ
15 ሬድዋን ናስር
13 ዊሊያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈