አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
772 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
ለአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት 25 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

ከነዚ ዉስጥ ኢትዮጵያ ቡና 4 ተጫዋቾች አስመርጦል

በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚከናወነው መጪው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው #የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ቡድን በመጋቢት ወር ከማዳጋስካር እና ኮትዲቯር ጋር እንደሚጫወት ይጠበቃል

#ተክለማርያም_ሻንቆ
#አሥራት_ቱንጆ
#አማኑኤል_ዮሐንስ
#አቡበከር_ናስር

ብሔራዊ ቡድኑ ለመጨረሻ ጊዜ ለዝግጅት ከተጠራቸው ተጫዋቾች ውስጥ ፋሲል ገብረሚካኤል ፣ #ወንድሜነህ_ደረጄ ፣ ኤልያስ አታሮ ፣ አምሳሉ ጥላሁን ፣ #ታፈሰ_ሰለሞን ፣ መስፍን ታፈሰ እና አቤል ያለው በዚህኛው ምርጫ አልተካተቱም

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
"ለብሔራዊ ብድናችን የመጀመሪያ ጎል በማስቆጠሬ በጣም ደስ ብሎኛል መታሰቢያነቱ በህይወት ላጣነዉ ለወንድማችን ቴዲ እንዲሆን እፈልጋለሁ"
#አቡበከር_ናስር

😭ነፍስ ይማር ቴዲዬ🙏

🤝የወዳጀነት ጨዋታ

🇪🇹ኢትዮጵያ 4-0 ማላዊ 🇲🇼
⚽️ መሱድ 16'
⚽️ ጌታነህ 45'
⚽️ ሱራፌል 55'
⚽️ አቡበከር 71'

🏟ባህርዳር 🌴

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ | 16ኛ ሳምንት ምርጥ 11

በባህር ዳር የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ በመመስረት ሶከር ኢትዮጵያ ተከታዩን ስብስብ በሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ አካታለች።

አሰላለፍ (4-1-4-1)

አሰልጣኝ – ካሣዬ_አራጌ

የኢትዮጵያ ቡናው አለቃ ለሦስተኛ ጊዜ የድረገፃችን የሳምንቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል።

ከሽንፈት የተመለሰውን እና በመጀመሪያ ተሰላፊዎቹ ላይ ጉዳቶች ያስተናገደውን ቡድን አዋቅረው ጥሩ መነቃቃት ላይ በመሆኑ ሊፈትናቸው ይችላል ተብሎ የነበረው ድሬዳዋ ከተማን ያለብዙ ችግር ማሸነፍ ችለዋል።

ከዚ ዉስጥ ኢትዮጵያ ቡና
ሁለት ተጫዎቾች በቆሚ አስመርጦል

#አስራት_ቱንጆ በተከላካይ

የብሔራዊ ቡድን ተመራጩ የግራ መስመር ተከላካይ እንደወትሮው ሁሉ በድሬዳዋው ጨዋታም የማጥቃት ድፍረቱን ደጋግሞ አሳይቷል።

በዚህ ጥረቱም የቡድኑ ቀዳሚ ጎል እንዲቆጠር ምክንያት የሆነውን ጥቃት ሲያስጀምር ወደ ተጋጣሚው ሳጥን ዘልቆ መግባት በቻለበት አጋጣሚም የቡድኑን ሁለተኛ ግብ የአጥቂ በሚመስል አጨራረስ ማስቆጠር ችሏል።

#ዊሊያም_ሰለሞን በአማካይ

ወጣቱ አማካይ ልዩ ብቃቱን ካሳየባቸው ጨዋታዎች የዚህ ሳምንቱ የድሬዳዋው ጨዋታ ቀዳሚው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

የቴክኒክ ብቃቱ እና እይታው ለተጋጣሚዎቹ ፈተና ሆኖ በታየበት በዚህ ሳምንት ለአቡበከር ናስር ሁለት ያለቀላቸው ዕድሎች መፍጠር ችሎ አንዱ ወደ ግብ ሲቀየር ለሦስተኛው ግብ መገኘት መነሻ የነበረውን ተንጠልጣይ ኳስ ወደ ሳጥን በማድረስም የበኩሉን አድርጓል።

ሁለት በተጠባባቂነት ተካተዋል
#አቡበከር_ናስር
#ሬድዋን_ናስር
©️ ሶከር 

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ እስከ #16ተኛ ሳምንት
የኢትዮጵያ ቡና #34 ጊዜ ኳስና መረብን ያገናኝ ሲሆን #19 ጎል ደም ተቆጥሮበታል በቡና በኩል የጎል አስቆጣሪዎቹን ዝርዝር በደረጃ እንደሚከተለዉ አስቀምጠነዋል


#አቡበከር_ናስር ~ 20
#ሀብታሙ_ታደሰ ~ 5
#አስራት_ቱንጆ ~ 3
#ታፈሰ_ሰለሞን ~ 2
#ሚኪያስ_መኮንን ~ 1
#አማኑኤል_ዮሃንስን ~ 1
#ዊሊያም_ሰለሞን ~ 1
#እንዳለ_ደባልቄ ~ 1

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#‍ኢትዮጵያ_ቡና እስከ 16ተኛ ሳምንት ያረጋቸዉ ጨዋታዎች እና ዉጤቶች

🇪🇹1ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 2-2 ወልቂጤ ከነማ
⚽️ 51' #አቡበከር_ናስር
⚽️ 68' #አቡበከር_ናስር
🏟አ.አ

🇪🇹2ተኛሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ፋሲል ከነማ 1-3 ኢትዮጵያ ቡና
በዛብህ 38' ታፈሰ 35'
⚽️#አቡበከር_ናስር 58' (ፍ)
ሀብታሙ 65'
🏟አ.አ

🇪🇹3ተኛሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 3-2 ድሬዳዋ
8'85' ሐብታሙ
55' አማኑኤል
🏟አ.አ

🇪🇹4ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና 0-1ሀዋሳ
🏟አ.አ

🇪🇹5ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና 3-2 ሰበታ ከተማ
#አቡበከር_ናስር 27' 65'⚽️⚽️
ሀብታሙ_ታደሰ 52'
🏟አ.አ

🇪🇹6ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-3 ኢትዮጵያ ቡና
⚽️⚽️⚽️#አቡበከር_ናስር 16'25'90'

🏟አ.አ

🇪🇹7ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

አራፊ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና

🇪🇹8ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 3-1ጅማ አባ ጅፋር
⚽️ #አቡበከር_ናስር 22'
አስራት 81'
ዊሊያም 87'
🏟ጅማ

🇪🇹9ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 1 - 2 ወላይታ ዲቻ
#አቡበከር_ናስር 24'⚽️
🏟ጅማ

🇪🇹10ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 2 - 2 ባህር ዳር ከነማ
ሚኪያስ 6'
⚽️ #አቡበከር_ናስር 53' (ፍ)
🏟ጅማ

🇪🇹11ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ሲዳማ ቡና 0-5 ኢትዮጵያ ቡና
#አቡበከር_ናስር 59' 64' 82'⚽️⚽️⚽️
ሀብታሙ 67'
አስራት_ቱንጆ 90'
🏟ጅማ

🇪🇹12ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 0 - 0 ሀዲያ
🏟ባህርዳር 🌴

🇪🇹13ተኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

አዳማ ከተማ 1-4 ኢትዮጵያ ቡና
#አቡበከር_ናስር⚽️⚽️⚽️ 57'78'(p)88
ታፈሰ 90'
🏟ባህርዳር 🌴

🇪🇹14ተኛ ሳምንትቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ
ወልቂጤ ከነማ 1-2 ኢትዮጵያ ቡና
#አቡበከር_ናስር 4' 58'⚽️⚽️
🏟ባህርዳር 🌴

🇪🇹15ተኛ ሳምንትቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 0 - 1 ፋሲል
🏟ባህርዳር 🌴

🇪🇹16ተኛ ሳምንትቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 3 - 1 ድሬዳዋ

#አቡበከር_ናስር 2'⚽️
አስራት 57'
እንዳለ 83'

🏟ባህርዳር 🌴

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#አቡበከር_ናስር እስከ 16 ሳምንት 20 ጎሎች ያስቆጠረባቸዉ ጨዋታዎች

🇪🇹1ኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 2-2 ወልቂጤ ከነማ
⚽️ 51' #አቡበከር_ናስር
⚽️ 68' #አቡበከር_ናስር

🇪🇹2ኛሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ፋሲል ከነማ 1-3 ኢትዮጵያ ቡና
በዛብህ 38' ታፈሰ 35'
⚽️#አቡበከር_ናስር 58' (ፍ)
ሀብታሙ 65'

🇪🇹4ኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና 3-2 ሰበታ ከተማ
#አቡበከር_ናስር 27' 65'⚽️⚽️
ሀብታሙ_ታደሰ 52'

🇪🇹5ኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-3 ኢትዮጵያ ቡና
⚽️⚽️⚽️#አቡበከር_ናስር 16'25'90'

🇪🇹8ኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 3-1ጅማ አባ ጅፋር
⚽️ #አቡበከር_ናስር 22'
አስራት 81'
ዊሊያም 87'

🇪🇹9ኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 1 - 2 ወላይታ ዲቻ
#አቡበከር_ናስር 24'⚽️

🇪🇹10ኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 2⃣ - 2⃣ ባህር ዳር ከነማ
ሚኪያስ 6'
⚽️ #አቡበከር_ናስር 53' (ፍ)

🇪🇹11ኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ሲዳማ ቡና 0-5 ኢትዮጵያ ቡና
#አቡበከር_ናስር 59' 64' 82'⚽️⚽️⚽️
ሀብታሙ 67'
አስራት_ቱንጆ 90'

🇪🇹13ኛ ሳምንት ቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

አዳማ ከተማ 1-4 ኢትዮጵያ ቡና
#አቡበከር_ናስር⚽️⚽️⚽️ 57'78'(p)88
ታፈሰ 90'

🇪🇹14ኛ ሳምንትቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ
ወልቂጤ ከነማ 1-2 ኢትዮጵያ ቡና
#አቡበከር_ናስር 4' 58'⚽️⚽️

🇪🇹16ተኛ ሳምንትቤትኪንግየኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ

ኢትዮጵያ ቡና 3 - 1 ድሬዳዋ

#አቡበከር_ናስር 2'⚽️
አስራት 57'
እንዳለ 83'



👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ቅድመ ዳሰሳ | ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ዛሬ ምሽት የሚደረገውን ተጠባቂው የሸገር ደርቢን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

የውድድር ዓመቱን አራተኛ ሽንፈት በሀዋሳ ከተማ ካስተናገዱ በኋላ ሰበታን በመርታት ዳግም ወደ አሸናፊነት የተመለሱት ኢትዮጵያ ቡናዎች የድል ጉዞዋቸውን ለማስቀጠል፣ ከመሪው ፋሲል ከነማ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ እንዲሁም ተጋጣሚያቸው ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ ከሚከተሏቸው ብድኖች ለመራቅ በነገው ጨዋታ ሦስት ነጥብ ያስፈልጋቸዋል።

ድል ካደረጉ አራት የጨዋታ ሳምንታት ያለፋቸው ቅዱስ ጊዮርጊሶች በበኩላቸው ከአስከፊው ውጤት አልባ ጉዞ ለመላቀቅ፣ ከመሪው ፋሲል ከነማ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ፣ ደረጃቸውን ለማሻሻል እና ከድል ጋር ለመታረቅ ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ቡድን (36) የሆነው የአሠልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ ኢትዮጰያ ቡና የፊት መስመሩ ስልነት ለተጋጣሚዎች የራስ ምታት ሆኗል።

ምንም እንኳን ቡድኑ ኳስን በትዕግሰት ተቆጣጥረው ከሚጫወቱ ቡድኖች መካከል ቀዳሚው ቢሆንም ፊት መስመሩ ትዕግስት እና ርህራሄ የሚባል ነገር አያውቅም።

በተለይም የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ #አቡበከር_ናስር ብቃት ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያገኝ እያስቻለው ይገኛል።
ነገም በተመሳሳይ ቀልጣፋው አቡበከር ፍጥነቱን እና ቴክኒካዊ ብቃቱን ተጠቅሞ የሚያደርጋቸው የጎል ፊት እንቅስቃሴዎች የጨዋታውን ውጤት እንደሚወስኑ ይገመታል።

ከእርሱ በተጨማሪ ከመስመር የሚነሱት የቡድኑ ተጫዋቾች ተጨማሪ የጎል ምንጭ እንደሚሆኑ ይታሰባል።

የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች ከኳስ ጋር ጥሩ ቢሆኑም ከኳስ ውጪ የሚያሳልፉት ጊዜ ብዙም የተዋጣለት አይደለም።
በተለይ ቡድኑ ከማጥቃት ወደ መከላከል በሚያደርገው ሽግግር ተጋጣሚዎች በጎ ነገሮችን ለራሳቸው እያገኙበት ይገኛል።

ከዚህም መነሻነት ነገ በዚህ ክፍተት ፈጣሪ የመከላከል አደረጃጀቱ ፈተና ላይ እንዳይወድቅ ያሰጋል።
በተጨማሪም ቡድኑ ኳስ ከኋላ ሲጀምር መጠነኛ የቅብብል ስህተቶችን ሲሰራ ይስተዋላል።

በተለይ ተጭኖት የሚጫወት ቡድን ሲገጥም ይህ ችግሩ በጉልህ ይታያል። ስለዚህም ቡና በዚህ ረገድ ነገ ችግር እንዳይገጥመው ያሳስባል።

በቡናማዎቹ በኩል የኮቪድ ውጤታቸው ዘገባውን እስካጠናከርንበት ወቅት ባይደርስም አቤል ከበደ እና ኃይሌ ገብረትንሳኤ በጉዳት ምክንያት ከነገው ጨዋታው ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ከአዲሱ አሠልጣኛቸው #ፍራንክ_ነታል ጋር ለመሻሻል የሚያልሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የ17ኛ ሳምንት አራፊ ቡድን በመሆናቸው ከሰበታ ጋር ጨዋታቸውን ካደረጉ በኋላ ወደ ቢሾፍቱ ተጉዘው ነበር።
ቡድኑ በቢሾፍቱም ልምምዱን ለሳምንት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ትናንት ከሰዓት ድሬዳዋ ደርሷል።
ነታል ሰበታን ሲገጥሙ ቡድኑ ላይ የታየው የእንቅስቃሴ መሻሻል ነገ የቡድኑ ደጋፊዎች ተስፋን እንዲሰንቁ አድርጓል።
በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ ተጫዋቾቹ ላይ የታየው የማሸነፍ ፍላጎት ከወትሮ ለየት ያለ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም ለበርካታ ጊዜያት ቡድኑ አቶት የነበረውም ፍጥነት በተወሰነ መልኩ አግኝቶት ተመልክተናል።
ከዚህም መነሻነት ነገም ቡድኑ ኳስ ሲይዝ በፍጥነት ነገሮችን ለመከወን ከሞከረ በጎ ነገሮችን ሊያገኝ እንደሚችል ይታሰባል።

ባለፉት አራት ጨዋታዎች በድምሩ ከሁለት ያልበለጡ ግቦችን ብቻ ተጋጣሚ ላይ ያስቆጠረው ቡድኑ ከነገው ጨዋታ ሦስት ነጥብ ከፈለገ ከመቼውም ጊዜ በላይ ስል ሆኖ መቅረብ አለበት።
እርግጥ ቡድኑ ግቦችን ማስቆጠር ብቻ ሳይሆን የግብ ዕድሎችንም በተደጋጋሚ የመፍጠር ችግር አለበት።
ከላይ እንደገለፅነው በሰበታው ጨዋታ የታየው ነገር በተወሰነ መልኩ ችግሩ ሊቀረፍ እንደሚችል ፍንጭ የሰጠ ቢሆንም ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ፊት ላይ አስፈሪ መሆን ይሻዋል።
ከዚህ ውጪ መጠነኛ ድክመት የሚታይበት የኋላ መስመሩ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ መሆን የግድ ይለዋል።

እንደ ኢትዮጵያ ቡና ሁሉ ይህንን ዘገባ በምንሰራበት ሰዓት የፈረሰኖቹም የኮቪድ-19 የምርመራ ውጤት ባይደርስም አዲስ ግዳይ እና ሮቢን ንጋላንዴ ባጋጠማቸው ጉዳት የነገው ጨዋታ እንደሚያመልጣቸው ታውቋል።

እርስ በእርስ ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ 41 ጊዜ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 ጨዋታ ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያ ቡና 7 ድል አሳክቷል።
በ16 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

በሸገር ደርቢ ባለፉት 41 ግንኙነቶች 78 ጎሎች ተቆጥረዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ 51፤ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 27 ጎሎች ማስቆጠር ችለዋል።

* ወቅታዊው የኮቪድ ወረርሺኝ በቡድኖቹ የስብስብ ምርጫ ላይ እያሳደረ ካለው ተለዋዋጭነት አንፃር ግምታዊ አሰላለፍ ለማውጣት አዳጋች በመሆኑ የወትሮው የአሰላለፍ ትንበያችን በዳሰሳው ያልተካተተ መሆኑን እንገልፃለን።

© ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#አቡበከር_ናስር ቡናን በአንበልነት እየመራ ነዉ
ዕለተ-እሁድ ግንቦት 8/2013 ዓ.ም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 🇪🇹🍵ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና ከረፋዱ 4፡00 ላይ ወሳኝ ጨዋታቸውን ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ የጨዋታው ውጤት ቀደም ሲል እንደነበሩት ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ነበር የተጠናቀቀው፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በነበረው ነጥብ ላይ አንድ ነጥብ ጨምሮ ሁለተኛ ደረጃውን አስጠብቆ ወጥቷል፡፡

ጨዋታው 3 አቻ በሆነው ውጤት ተጠናቀቀበት.... የሶስቱም ግቦች ባለቤት ፊት-አውራሪው #አቡበከር_ናስር በሆነበት በዛ ጨዋታ..... ትንሹ ልዑል ፍፁም ቁጭትና እልህ ይነበብበት ነበር.... ደስታ በፊቱ ላይ የለም....የክለቡ አሸንፎ ያለመውጣት አንገብግቦታል፡፡

ገና በለጋነቱ ከኑሮ ጋር ትግል ገጥሞ ማሸነፍ የቻለው፣ ድንቅ ብቃቱን በሰፈሩም በታዳጊዎች ውድድር በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ማስመስከር የቻለው፣ የወደፊት ራዕዩና ግቡ እሩቅ የሆነው፣ ሙሉ ትኩረቱ ህይወቴ ብሎ በያዘው እግር ኳስ ላይ ያደረገው፣ ፈረሃ-ፈጣሪ የተላበሰ፣ሁሉን አክባሪ፣ትሁትና ሲናገር ቁጥብ ነው፣  ከሜዳ ውጭ ቀጭን- ሜዳ ውስጥ የሚገዝፍ ፣ ኳስ በሱ እግር ስር ስትሆን የማይርበተበት ተከላካይ፣በፍርሃት የማይርድ ግብ ጠባቂ የለም። በዘንድሮ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ያሉ በረኞች ሁሉ ከእርሱ እግር ስር ከሚነሳ ኳስ መረታት አላመለጡም፡፡

ጥበብ፣በራስ መተማመን፣ፍጥነት፣ብስለትና አርቆ ማየትና ማሰብ የግሉ ናቸው፡፡ ከዕድሜው ቀድሞ ስኬቱን ማስመስከር ችሏል-የቡናው ልጅ አቡበከር ናስር (አቡኪ)

ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ መጠናቀቁን የሚያበስር ፊሽካ ሲነፋ የዕለቱ ዳኞች  ወደ መሃል ሜዳ መጡ፡፡ 10 ቁጥር ለባሹ የቡናም የኢትዮጵያ ፈርጥ ወደነሱ አመራ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መላው ዓለም እየተከታተለው ለአራተኛ ጊዜ ሶስታይ/ሀትሪክ/ሰርቶ ኳስዋን ተቀበለ፡፡

አቡበከር በዕለቱ የተረከበው ኳስን ብቻ ሳይሆን በርካታ ክብሮችን ጭምር ነው፡፡በቡና ደረጀ በታፈሰ ተስፋዬ የተያዘውን የኮከብ ግብ አግብነት፣ በዮርዳኖስ የተያዘውን 24 ጎል እና በ2009 በጌታነህ ከበደ የተያዘው የ25 ጎል ኮከብ ግብ አግብነት ሪከርድን ጠቅልሎ ወሰደው፡፡የእግር ኳስን ክብር የግሉ አደረገ፡፡የኢትዮጵያ ቡና ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም አለኝታና ክብር መሆኑን በተግባር አስመሰከረ፡፡ገና ሁለት ጨዋታ እየቀረው ያገባቸውን ጎሎችን ቁጥር 27 በማድረስ በቀጣይ ይህንን ሪከርድ የሚሰብር ይኖር ይሁን የሚል ጥያቄን በበርካቶች ውስጥ አጫረ፡፡እውነት ሌላ ሰው ይሞክረው ይሆን??? ወይስ በቀጣይ ጨዋታዎች ተጨማሪ ጎሎችን በማስቆጠር ከማይደረስበት ቦታ ከፍታውንና ስሙን ይሰቅል ይሆን?? ከቀናት በኋላ ምላሹ እውን ይሆናል፡፡

በኢትዮጵያ ቡና ቤት አዳዲስ ነገሮችን መጀመር፣ሪከርዶችን ማስመዝገብ፣ተምሳሌትና አርኣያ መሆን የሠርክ ተግባር ነው፡፡የተሟላ አደረጃጀት፣ ዘመኑን የተከተለ አሠራር፣ ጠንካራ አመራር፣ ፅኑ ደጋፊ፣ ብቸኛው እውቅና ያለው አንጋፋ የደጋፊዎች ማህበር፣ በየአመቱ ቁጥሩ የሚጨምር ብርቱ ደጋፊ፣ ለመስጠት የማይሳሳ ቤተሰብ፣ በአፍሪካ መድረክ የግብፅ ክለቦችን ያንበረከከ፣ የግሉን ሚዲያ በመመስረት ቀዳሚ፣ ለውጤት ብቻ ሳይሆን ለውበት የሚተጋ፣ለእግር ኳሱ ዕድገት ፋና ወጊው የኢትዮጵያ ቡና......

በኢትዮጵያ ቡና ቤት ሪከርድም አዲስ ነገርም የተለመዱ ናቸው፡፡
አቡበከር
👉የኢትዮጵያ ቡና ሁነኛ ተምሳሌት
👉 የአጠቃላይ የቡድኑ ጥንካሬም ህብረትም ወካይ
👉ለሚመለከተው ሰው ሙሉ ሀላፊነትን ሠጥቶ ፍሬውን የማየት ማሳያ
👉 የጠንካራ አመራረርና ክትትል ነፃ-ብራቅ
👉 ለስፖርት የሚከፈል መስዋዕትነት፣ከልብ ለሚወዱት የሚሰጥ የስጦታ/ዋጋ ማሳያ ነው፡፡

በእርሱ ስኬት ውስጥ የቡድኑ ከፍታ አለ፡፡ በርሱ ደስታ ውስጥ የሚሊየኖች ደስታና ሳግ አለ፡፡በርሱ ስኬት ውስጥ የእግር ኳሳችን ትንሳኤ ቁልጭ ብሎ ይታያል፡፡

በርሱ ኮከብነት ውሥጥ ጠንካራ አሰልጣኞች፣ #ትጉህ_ተጨዋቾች#የሚሳሱ_ወጌሻዎች#የማይተኙ_አመራሮች#የማይደክሙ_ደጋፊዎች አብረውት አሉ፡፡ ምክንያቱም ቡና እርስ በራሳቸው የተጋመዱ እልፎች እንደ ካስማ ያቆሙት የሀገር ዋልታ ነው!!

በቀጣይ በአፍሪካ መድረክ ሌላ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ እና ኢትዮጵያ ለመወከል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። ያኔም በአፍሪካ መድረክ እንደምቃለን

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
🇪🇹 25ተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ

48'

ሀዲያ ሆሳዕና 1-1 ኢትዮጵያ ቡና
#ደስታ_ዋሚሾ 43' #አቡበከር_ናስር 1'

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈