አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
772 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
ለአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት 25 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

ከነዚ ዉስጥ ኢትዮጵያ ቡና 4 ተጫዋቾች አስመርጦል

በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚከናወነው መጪው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው #የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ቡድን በመጋቢት ወር ከማዳጋስካር እና ኮትዲቯር ጋር እንደሚጫወት ይጠበቃል

#ተክለማርያም_ሻንቆ
#አሥራት_ቱንጆ
#አማኑኤል_ዮሐንስ
#አቡበከር_ናስር

ብሔራዊ ቡድኑ ለመጨረሻ ጊዜ ለዝግጅት ከተጠራቸው ተጫዋቾች ውስጥ ፋሲል ገብረሚካኤል ፣ #ወንድሜነህ_ደረጄ ፣ ኤልያስ አታሮ ፣ አምሳሉ ጥላሁን ፣ #ታፈሰ_ሰለሞን ፣ መስፍን ታፈሰ እና አቤል ያለው በዚህኛው ምርጫ አልተካተቱም

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ወንድሜነህ_ደረጄ
ያለፉትን አመታት #በተከላካይ ስፍራ ተጫዋችነት #ኢትዮጵያ_ቡና ያገለገለው ወንድሜነህ ደረጄ #ጉዳት አጋጥሞት #ቀዶ_ጥገናን አድርጓል አሁን ላይ #በማገገም ላይ ይገኛል #የመጀመሪያው ዙር አጋማሽ ላይ ወደ #ሜዳ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
#በቶሎ አግመህ ወደ ሜዳ እንድትመለስ እንመኝልሃለን #በርታልን

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ዜና_የኢትዮጵያ_ቡና

👉 የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የቅድመ-ውድድር ዝግጅቱን ለማድረግ የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 4/2015 ዓ.ም አዳማ ከተማ ላይ የሚከትም ሲሆን ቡድኑ ከአርብ ነሐሴ 05/2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ልምምዱን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

👉 ዘጠኝ የአሰልጣኝ ቡድን እና 29 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ አዳማ ከተማ የሚያቀናው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከወዲሁ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችንም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

👉 በ2015 ዓ.ም የውድድር ዓመት ጉዳት የገጠማቸው #ሮቤል ተ/ሚካኤል፣ #አስራት ቶንጆ እና #መሐመድኑር ናስር ከቅድመ-ውድድር ዝግጅቱ ውጪ መሆናቸው ሲታወቅ የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር መጀመሪያ ላይ ቡድኑን የሚቀላቀሉ ይሆናል። ባንፃሩ ለረጅም ጊዜ በጉዳት ላይ የነበረው ተከላካዩ #ወንድሜነህ ደረጄ ሙሉ ለሙሉ ከጉዳት በማገገሙ ቡድኑን ይቀላቀላል።

👉 ሁለት የውጭ ተጫዋቾች በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ቡድኑን የሚቀላቀሉ ሲሆን የመጫወቻ ቦታቸውም የፊት አጥቂ እና ተከላካይ ቦታ ላይ ነው ።

👉 ለ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት አዲስ ሁለት የውጭ አሰልጣኞችን ወደ ቡድናችን ሲቀላቀሉ ዋናው አሰልጣኝ #Kavazovic_Nikola እና የአካል ብቃት አሰልጣኙ #Vasiljevic_Marko ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ሲጠበቅ፤ ነገ ወደ አዳማ ከተማ የሚያቀኑ ይሆናል።

በሁለቱ አሰልጣኞች የውል ዘመን፣ እና በውል ውስጥ የተካተቱ ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣይ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።
አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና-አደገኛ
💛🤎@coffeefc💛🤎
💛🤎@coffeefc💛🤎