አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
772 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
#15 👍
#ሬድዋን_ናስር

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#15 👍
#ሬድዋን_ናስር

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ቅድመ ዳሰሳ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና

የስድስተኛ ሳምንት መክፈቻ የሆነውን የሸገር ደርቢ የተመለከተው ዳሰሳችንን እነሆ።

የመዲናይቱ ሁለት ክለቦች ከድል መልስ የሚገናኙበት ተጠባቂ ጨዋታ ነገ ረፋድ ላይ ይከናወናል።

በእርግጥ ባለፉት ዓመታት የሸገር ደርቢ በሜዳ ላይ የታሰበውን ያህል ፉክክር ሳያሳየን የጎል ድርቅም እየመታው ሲጠናቀቅ ቆይቷል።

ይህ መሆኑ ተጠባቂነቱን ባይቀንሰውም ጓጉቶ ለሚጠብቀው የስፖርት ቤተሰብ የሚጠበቀውን ያህል አዝናኝ አለመሆኑ ቅሬታን የሚፈጥር ነው።

ለዚህ እንደአንድ ምክንያትነት የሚነሳው የሜዳ ላይ ጡዘቱ ወደ ደጋፊዎች ግጭት እንዳያመራ የመሰጋቱ ነገር ዘንድሮ በኮቪድ 19 ምክንያት ጨዋታዎች በዝግ በመካሄዳቸው የማይኖር በመሆኑ ጨዋታው ከፍ ያለ ፉክክር እንዲኖረው በር ሊከፍት እንደሚችል ይገመታል።

የቡድኖቹ ተጨዋቾችም ቀለል ባለ ጫና ውስጥ ሆነው ሲገናኙ የተሻለ ብቃታቸውን አውጥተው ለመጨወት ዕድል እንደሚያገኙም ይታሰባል።

ከሰባት ቀናት በኋላ ወደ ጨዋታ የሚመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስት ተከታታይ ድሎችን በማሳካት መልካም አቋም ላይ ይገኛል።

ከማሸነፍ በዘለለ በየጨዋታዎቹ ያስቆጠራቸው ግቦች ቁጥር ከፍ ማለትም ከእንደነገው ዓይነት ጨዋታ በፊት የቡድኑን በራስ መተማመን ከፍ ለማድረግ የሚረዳ ሌላው በጎ ነጥብ ነው።

ወደ ቀደመ የቀጥተኛነት አጨዋወቱ የማዘንበል ባህሪ እየታየበት ያለው ጊዮርጊስ ከተከላካይ ጀርባ የሚገኙ ክፍተቶችን በአግባቡ በመጠቀም ጥንካሬውን ማሳየት ችሏል።

ነባሮቹም ሆኑ አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ግብ በማስቆጠር እና ጨዋታ ለዋጭ ተፅዕኖዎችን በመፍጠር እያሳዩ ያሉት ብቃት ቡድኑ አማራጮች እንዲሰፉለት ጨዋታው ቢከብደው እንኳን በተጫዋቾች የግል ብቃት የሚገኙ ግቦችን ለማስቆጠር የሚረዳው ጉዳይ ነው።

በተለይ ኢትዮጵያ ቡና ከኃላ መስመር ላይ ከሚሰራው ተደጋጋሚ ስህተት አንፃር የፈረሰኞቹ ቀጥተኝነት እና ፊት ላይ ያሉ ተሰላፊዎቻቸው ፍጥነት ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይገመታል።

ቡድኑ መሀል ሜዳ ላይ ኳስን የማቆየት ሀሳብ ካለው ግን የተሻለ ውህደት ባለው ተጋጣሚው መፈተኑ የሚቀር አይመስልም።
ኢትዮጵያ ቡና እንደተጋጣሚው ረዘም ያለ የማገገሚያ ጊዜ ባይኖረውም ከኋላ ተነስቶ ያሸነፈበት የሰበታው ጨዋታ ትዝታ ትኩስ መሆኑ የቡድኑ ጉልበት ላይ የሚጨምርለት አዕምሯዊ ጥንካሬ ይኖራል።

የኳስ ቁጥጥር የበላይነትን አብዝተው የሚፈልጉት ቡናማዎቹ እንደ ሰበታው ጨዋታ ታታሪነት የታከለበት እና የፊት መስመር ተሰላፊዎች እገዛ ያልተለየው እንቅስቃሴ የመሀል ሜዳውን ጦርነት ለማሸነፍ ትልቅ እገዛ ያደርግላቸዋል።

እንደ #ዊሊያም_ሰለሞን እና #ሬድዋን_ናስር ዓይነት ወጣት ተጫዋቾቻቸው ጭምር ቡድኑ ለሚፈልገው አካሄድ በጨዋታ ጭምር ተፈትነው ለደርቢው መድረሳቸውም ለቡድኑ ተጨማሪ ኃይል ይሆነዋል።
ምንም እንኳን ከተጋጣሚው በራሱ ሜዳ ከፍ ያለ ጫና ሊደርስበት እንደሚችል ቢገመትም ያንን የሚያልፍበት ጥሩ ዕቅድ ከኖረው የጊዮርጊስን የአማካይ ክፍል ተጋፍጦ የመጨረሻ ኳሶችን ለማድረስ የተሻለ ዕድል ይኖረዋል።
ይህን ለማድረግ ግን ተደጋጋሚ ለውጦች የተደረጉበት የቡድኑ የተከላካይ አማካይ ተሰላፊ ሚና ከፍ ያለ ነው።

ፊት መስመር ላይ ያሉት የቡድኑ ተሰላፊዎችም እንዲሁ ከግብ አስቆጣሪነቱ ሳይቦዝኑ ለጨዋታው መድረሳቸው ለአሰልጣኝ #ካሳዬ ቡድን ጥንካሬን የሚያላብስ ነው።
ቡድኑ ከኋላ ያለከፍተኛ ጫና ሲሰራቸው እና ዋጋ ሲያስከፍሉት የሰነበቱት ስህተቶች ግን ነገ ከበድ ባለ ጫና ዳግም የመፈተሻቸው ነገር ስጋት የሚጭር ይሆናል።

በቡድኖቹ የተሻለ የማጥቃት ተሳትፎ ያላቸው ተከላካዮች #ሄኖክ_አዱኛ እና #ኃይሌ_ገብረትንሳይ ወደ ፊት ለመሄድ ከተቃራኒ ቡድን የመስመር አጥቂዎች የሚገጥማቸው ፈተና ፣ #ታፈሰ_ሰለሞንን ከሙላለም መስፍን ያሚያጋፍጡ ቅፅበቶች ፣ የጊዮርጊሶቹ አቤል ያለው እና አዲስ ግደይ ከቡና የተከላካይ መስመር ፊት እና ኃላ ያሉ ቦታዎች ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ ፣ የቡና መስመር አጥቂዎች በጊዮርጊስ መሀል እና መስመር ተከላካዮች መሀል ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት እንዲሁም የጌታነህ ከበደ እና የ#አቡበከር_ናስር ከተከላካይ መስመር ጋር የሚኖራቸውን ግብግብ በነገው ሸገር ደርቢ የምንጠብቃቸው የሜዳ ላይ ፍልሚያዎች ይሆናሉ።

ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ የቡድን ዜናዎችን ለማካተት ያደረግነው ጥረት በሁለቱም ክለቦች በኩል መረጃ ባለማግኘታችን አልተሳካም።

እርስ በእርስ ግንኙነት
– ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ 40 ጊዜ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 ጨዋታ ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያ ቡና 6 ድል አሳክቷል። በ16 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
– የሸገር ደርቢ ምንም እንኳ አሁን አሁን ያለ ግብ የሚጠናቀቅባቸው ጨዋታዎች በርከት ቢሉም ባለፉት 40 ግንኙነቶች 73 ጎሎች ተቆጥረዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ 49፤ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 24 ጎሎች ማስቆጠር ችለዋል።

ግምታዊ አሰላለፍ
ቅዱስ ጊዮርጊስ (4-2-3-1)
ፓትሪክ ማታሲ
ሄኖክ አዱኛ – ምንተስኖት አዳነ – አስቻለው ታመነ – ፍሪምፖንግ ሜንሱ
ሀይደር ሸረፋ – ሙሉዓለም መስፍን
አቤል ያለው – ሮቢን ንጋላንዴ – አዲስ ግደይ
ጌታነህ ከበደ

ኢትዮጵያ ቡና (4-3-3)
ተክለማሪያም ሻንቆ
ኃይሌ ገብረትንሳይ – ወንድሜነህ ደረጄ – አበበ ጥላሁን – አሥራት ቱንጆ
ታፈሰ ሰለሞን – ረመዳን ናስር – ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን
አቤል ከበደ – ሀብታሙ ታደሰ – አቡበከር ናስር
© ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ኢትዮጵያ ቡና የዛሬ አሰላለፍ

1 ተክለማርያም ሻንቆ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
16 ሬድዋን ናስር
13 ዊልያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
10 አበበከር ናስር
25 ሀብታሙ ታደሰ
17 አቤል ከበደ

አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ በሰበታው ጨዋታ ድል ያደረገውን ቡድን ሳይቀይር ጨዋታውን ይጀምራል ወጣቶቹ #ሬድዋን_ናስር እና #ዊልያም_ሰለሞንም በድጋሚ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ የመካተት ዕድልን አግኝተዋል።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ሪፖርት | የአቡበከር ናስር ሐት-ትሪክ ቡናን ባለድል አድርጓል

ከአስር ዓመታት በኋላ ከሦስት በላይ ግቦችን ባስተናገደው ሸገር ደርቢ ቡና ጊዮርጊስን 3-2 አሸንፏል።
ሁለቱ ቡድኖች ሰበታን ከገጠሙባቸው ጨዋታዎች አንፃር ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ ግደይን በጋዲሳ መብራቴ በመተካት ጨዋታውን ሲጀምር ኢትዮጵያ ቡና ግን የተጠቀመበትን የመጀመሪያ አሰላለፍ ሳይለውጥ ቀርቧል።
ተጠባቂነቱን በሚመጥን ግለት የጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ግቦችን ለማስተናገድ ብዙም አልቆየም።
ከጅምሩም ሁለቱም ቡድኖች ወደ ተጋጣሚ ሳጥን እየቀረቡ ራቅ ያሉ ሙከራዎችን ማድረግ ጀምረዋል።
ከተከላካይ ጀርባ የመግባት ምልክት ያሳዩ የነበሩት ቡናዎችም ቀዳሚውን ጎል ማግኘት ችለዋል።
15ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታው በጀመረበት ደቂቃዎች አካባቢ እንደሆነው ሁሉ አቡበከር ናስር ከተካላካዮች አምልጦ ሳጥን ውስጥ በገባበት ቅፅበት በፓትሪክ ማታሲ ጥፋት ተሰርቶበት ማታሲ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ሲወጣ አቡበከር የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት ሮቢን ንጋላንዴን ለውጦ በገባው ለዓለም ብርሀኑ ላይ አስቆጥሯል።

ከግቡ በኋላ ቡናዎች ተረጋግተው ኳስ በመያዝ ከጊዮርጊሶች የፊት መስመር ጫና ለመውጣት ጥረት ላይ ሳሉ ግን ስህተት ሰርተዋል።
በራሳቸው ሜዳ ኳስ በማንሸራሸር ላይ ሳሉ #ሬድዋን_ናስር ወደ ኋላ ለግብ ጠባቂው #ተክለማርያም_ሻንቆ የላካው ኳስ ከመረብ አርፏል።
በዚህ የተነቃቁት ጊዮርጊሶች ተጨማሪ ጎል ለማግኘት ወደ ፊት ገፍተው መጫወት ሲጀምሩ እንደመጀመሪያው ሁሉ ቡናዎች ክፍተት አግኝተዋል።
የታፈሰ ሰለሞን ተከላካይ ሰንጣቂ ኳስ ተከትለው በድጋሚ በጊዮርጊስ የግራ መከላከል ክፍል በኩል #አቤል_ከበደ እና #አቡበከር_ናስር ሰብረው ገብተው አቤል አመቻችቶለት #አቡበከር 25ኛው ደቂቃ ላይ እንደገና ቡድኑን መሪ አድርጓል።

በጎዶሎ የተጫዋች ቁጥር ለመጫወት ከተገደዱበት ደቂቃ ጀምሮ ይበልጥ ቀጥተኛነት የታየባቸው ጊዮርጊሶች ከአምስት ደቂቃ በኋላ በሰጡት ምላሽ አቤል ያለው ከሄኖክ አዱኛ የተቀበለውን ኳስ ከቀኝ አቅጣጫ ይዞ በመግባት ሳጥኑ ጠርዝ ላይ ይገኝ ለነበረው ጋዲሳ መብራቴ አመቻችቶለት ጋዲሳ ጨዋታውን ወደ አቻነት የቀየረች ግብ አስቆጥሯል።
ቀሪዎቹ የአጋማሹ ደቂቃዎች በንፅፅር ጨዋታው ቀዝቀዝ ብሎ ሲታይ ቡናዎች በጊዮርጊስ ሜዳ ላይ ብዙ ሰዓቱን ኳስ ይዘው ቆይተዋል።
በለዓለም ከዳነው የኃይሌ ገብረትንሳይ የርቀት ሙከራ ውጪ ግን ሌላ የግብ ዕድል ሳያገኙ ጨዋታው ወደ ዕረፍት አምርቷል።

ሁለተኛውም አጋማሽ እንደመጀመሪያው ሁሉ በክስተት ጀምሯል።
47ኛው ደቂቃ ላይ #የዊልያም_ሰለሞንን ኳስ ተከትሎ አሁን ደግሞ በጊዮርጊስ የቀኝ ተከላካይ ክፍል መሀል የገባው #አቡበከር _ናስር በአስቻለው ታመነ ጥፋት ተሰርቶበት ሌላ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝቶ ቢመታም ስቶታል። አቡበከር 54ኛው ደቂቃ ላይም ከአሥራት ቱንጆ የተላከለትን ኳስ ይዞ በተመሳሳይ ሩጫ የጊዮርጊስን ተከላካዮች አምልጦ ገብቶ ለማስቆጠር ቢቃረብም ሙከራውን ለዓለም አድኖበታል።
በራሳቸው ሜዳ ላይ መቆየትን የመረጡት ጊዮርጊሶች ሳጥናቸው ዙሪያ ድረስ ለሚቀርቡትን የተጋጣሚያቸው ቅብብሎች ክፍተት ላለመስጠት በረጃጅም ኳሶች ወደፊት ለመሄድ ጥረት ሲያደርጉ ይታይተጠናቋል።

በተቀዛቀዘ መልኩ በቀጠለው ጨዋታ ቡናዎች በጊዮርጊስ የግብ አፋፍ በደረሱበት 74ኛው ደቂቃ ላይ ታፈሰ ከኃይሌ የተቀበለውን ኳስ ወደ ውስጥ ጥሎት ሲመለስ አቡበከር መትቶት ሄኖክ አዱኛ ከመስመር ላይ በደረቱ አውጥቶታል።
በቡናዎች ክፍተት ማፈላለግ እና በጊዮርጊስ ጥንቃቄ እስከመጨረሻው የዘለቀው ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃ በተሰራ ስህተት ጎል ተቆጥሮበታል።
90ኛው ደቂቃ ላይ ፍቅረየሱስ ከሳጥኑ መግቢያ ላይ የመታውን ኳስ ለዓለም ብርሀኑ በአግባቡ መቆጣጠር ሳይችል ቀርቶ አቡበከር_ናስር ለራሱ እና ለቡድኑ ሦስተኛውን ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው በቡና 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ | 16ኛ ሳምንት ምርጥ 11

በባህር ዳር የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ በመመስረት ሶከር ኢትዮጵያ ተከታዩን ስብስብ በሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ አካታለች።

አሰላለፍ (4-1-4-1)

አሰልጣኝ – ካሣዬ_አራጌ

የኢትዮጵያ ቡናው አለቃ ለሦስተኛ ጊዜ የድረገፃችን የሳምንቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል።

ከሽንፈት የተመለሰውን እና በመጀመሪያ ተሰላፊዎቹ ላይ ጉዳቶች ያስተናገደውን ቡድን አዋቅረው ጥሩ መነቃቃት ላይ በመሆኑ ሊፈትናቸው ይችላል ተብሎ የነበረው ድሬዳዋ ከተማን ያለብዙ ችግር ማሸነፍ ችለዋል።

ከዚ ዉስጥ ኢትዮጵያ ቡና
ሁለት ተጫዎቾች በቆሚ አስመርጦል

#አስራት_ቱንጆ በተከላካይ

የብሔራዊ ቡድን ተመራጩ የግራ መስመር ተከላካይ እንደወትሮው ሁሉ በድሬዳዋው ጨዋታም የማጥቃት ድፍረቱን ደጋግሞ አሳይቷል።

በዚህ ጥረቱም የቡድኑ ቀዳሚ ጎል እንዲቆጠር ምክንያት የሆነውን ጥቃት ሲያስጀምር ወደ ተጋጣሚው ሳጥን ዘልቆ መግባት በቻለበት አጋጣሚም የቡድኑን ሁለተኛ ግብ የአጥቂ በሚመስል አጨራረስ ማስቆጠር ችሏል።

#ዊሊያም_ሰለሞን በአማካይ

ወጣቱ አማካይ ልዩ ብቃቱን ካሳየባቸው ጨዋታዎች የዚህ ሳምንቱ የድሬዳዋው ጨዋታ ቀዳሚው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

የቴክኒክ ብቃቱ እና እይታው ለተጋጣሚዎቹ ፈተና ሆኖ በታየበት በዚህ ሳምንት ለአቡበከር ናስር ሁለት ያለቀላቸው ዕድሎች መፍጠር ችሎ አንዱ ወደ ግብ ሲቀየር ለሦስተኛው ግብ መገኘት መነሻ የነበረውን ተንጠልጣይ ኳስ ወደ ሳጥን በማድረስም የበኩሉን አድርጓል።

ሁለት በተጠባባቂነት ተካተዋል
#አቡበከር_ናስር
#ሬድዋን_ናስር
©️ ሶከር 

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
🔹የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች በግራንድ ኤሊያና ሆቴል ደምቀው አመሹ!

◾️የቡና ሠማይ ሥር ሦስትኛው ዙር የኮኮቦች ሽልማት እጅግ ደማቀ በሆነ ሥነ ስራአት ትላንት ምሽት በኤሌያና ሆቴል ተደርጓል።

1➡️ የህይወት ዘመን የክብር ተሸላሚ #መቶ_አለቃ_ፍቃድ_ማሞ

2➡️ የቡና ሠማይ ሥር በደጋፊዎች ምርጫ የዓመቱ ኮኮብ ተጨዋች #አቡበከር_ናስር

3➡️የቡና ሠማይ ሥር አዘጋጆች ኮከብ ተጨዋች #አስራት_ቶንጆ

4➡️የ2013 ወድድር የኢትዮጽያ ቡና ደንቅ ጎል #ሚኪያስ_መኮንን

5➡️ በርከታ ለጎል የሚሆኑ ኳስ ያቀበለ #ታፈሰ_ሰለሞን

6➡️ተስፈኝ ታዳጊ ተጨዋቾች #ዊሊያም_ሰለሞን እና #ሬድዋን_ናስር ...በመሆን በርካታ ታዲሚያን ፤ ጥሩ የተግደረገላቸው የቡና ደጋፊዎቻ እና አርቲስቶች በተገኙበት ተሸላሚ በመሆን ደምቀው አምሽተዋል።

ዊሊያም እና ሬድዋን የቤሄራዊ ቡድን ጥሪ ላይ ሲሆኑ ከሆቴል ለመውጣት ፍቃድ ባለ ማግኘታቸው በአማኑኤል እና በኢያሱ በአማካኝነት ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ሬድዋን_ናስር
በ2014 አጋማሽ ላይ #በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ ከሱ ማግኘት የሚገባንን #ግልጋሎት ሳናገኝ መቅረታችን ይታወሳል #አሁን ላይ ሬድዋን ወደ ሜዳ ለመመለስ የተለያዮ እንቅስቃሴዎችን #በግሉ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን #ጥቅምት አጋማሽ ላይ ወደ ሜዳ ላይ #ልምምድ የሚመለስ ይሆናል።
#የሱ መመለስም #ለክለባችን በመሃል ሜዳው ላይ #ተጨማሪ አማራጭ የሚፈጥርልን ይሆናል
#በቶሎ_አገግመህ_ወደ_ሜዳ_እንድትመለስ_እንመኝልሃለን_በርታልን
#የኢትዮጵይ_ቡና_ዋናው_ቡድን_ልምምዱን_ጀመረ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ልምምዱን ለቡ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቡና የተጫዋቾች መኖሪያ ካምኘ አድርጎ ከባለፈው ማክሰኞ 26/04/2015 ዓ.ም ልምምዱን እያደረገ ይገኛል፡፡

🎯 ለዕረፍት ወደ ሀገራቸው ከሄዱት ኩዋኩ ዱሀ፣ ሕዝቄል ሞራክ እና ሮቤል ተ/ሚካኤል እንዲሁም ለብሔራዊ ቡድን ከተመረጡት በረከት አማረ እና ገዛኽኝ ደሳለኝ ውጪ ሁሉም በልምምዱ ስፍራው ተገኝተዋል፡፡

👉 ጉዳት ላይ ያሉ ተጫዋቾች የክለባችን አንደኛ እና ሁለተኛ አምበል የሆኑት አማኑኤል ዮሐንስ እና አስራት ቶንጆ እንዲሁም ወንድሜነህ ደረጀ አሁንም ወደ ልምምድ ያልተመለሱ ሲሆን የመሀል አማካኝ ተጫዋች #ሬድዋን_ናስር ከጉዳቱ አገግሞ መጠነኛ ልምምድ ከቡድኑ ጋር ማድረግ ጀምሯል፡፡

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ዜና_የኢትዮጵያ_ቡና
👉 የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከነሐሴ 4/2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በቀን ሁለት ጊዜ የቅድመ-ውድድር ዝግጅት ማድረጉን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ለዚህ ይረዳው ዘንድ የተለያዩ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው ክለባችን ዛሬ ከሐድያ ሆሳዕና ጋር ከቀኑ 10:00 ሰዓት በዩኒቨርስቲው ስታዲየም የሚያደርግ ይሆናል።

👉 #በቀጣይ
የፊታችን ማክሰኞ ከመቻል እንዲሁም ሐሙስ ከኢትዮጵያ መድን የእግር ኳስ ቡድኖች ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል።

👉 ሁሉም የክለባችን ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ ያሉ ሲሆን፤ በጉዳት ከቡድኑ ተለይቶ የነበረው የአማካኝ ቦታ ተጫዋቹ #ሬድዋን_ናስር ከህመሙ በማገገሙ ፤ የፊታችን ሰኞ ቡድኑን በመቀላቀል ልምምዱን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛🤎 
@coffeefc 💛🤎
💛🤎
@coffeefc  💛🤎