አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
183K subscribers
4.94K photos
156 videos
14 files
750 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
ቅድመ ዳሰሳ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና

የስድስተኛ ሳምንት መክፈቻ የሆነውን የሸገር ደርቢ የተመለከተው ዳሰሳችንን እነሆ።

የመዲናይቱ ሁለት ክለቦች ከድል መልስ የሚገናኙበት ተጠባቂ ጨዋታ ነገ ረፋድ ላይ ይከናወናል።

በእርግጥ ባለፉት ዓመታት የሸገር ደርቢ በሜዳ ላይ የታሰበውን ያህል ፉክክር ሳያሳየን የጎል ድርቅም እየመታው ሲጠናቀቅ ቆይቷል።

ይህ መሆኑ ተጠባቂነቱን ባይቀንሰውም ጓጉቶ ለሚጠብቀው የስፖርት ቤተሰብ የሚጠበቀውን ያህል አዝናኝ አለመሆኑ ቅሬታን የሚፈጥር ነው።

ለዚህ እንደአንድ ምክንያትነት የሚነሳው የሜዳ ላይ ጡዘቱ ወደ ደጋፊዎች ግጭት እንዳያመራ የመሰጋቱ ነገር ዘንድሮ በኮቪድ 19 ምክንያት ጨዋታዎች በዝግ በመካሄዳቸው የማይኖር በመሆኑ ጨዋታው ከፍ ያለ ፉክክር እንዲኖረው በር ሊከፍት እንደሚችል ይገመታል።

የቡድኖቹ ተጨዋቾችም ቀለል ባለ ጫና ውስጥ ሆነው ሲገናኙ የተሻለ ብቃታቸውን አውጥተው ለመጨወት ዕድል እንደሚያገኙም ይታሰባል።

ከሰባት ቀናት በኋላ ወደ ጨዋታ የሚመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስት ተከታታይ ድሎችን በማሳካት መልካም አቋም ላይ ይገኛል።

ከማሸነፍ በዘለለ በየጨዋታዎቹ ያስቆጠራቸው ግቦች ቁጥር ከፍ ማለትም ከእንደነገው ዓይነት ጨዋታ በፊት የቡድኑን በራስ መተማመን ከፍ ለማድረግ የሚረዳ ሌላው በጎ ነጥብ ነው።

ወደ ቀደመ የቀጥተኛነት አጨዋወቱ የማዘንበል ባህሪ እየታየበት ያለው ጊዮርጊስ ከተከላካይ ጀርባ የሚገኙ ክፍተቶችን በአግባቡ በመጠቀም ጥንካሬውን ማሳየት ችሏል።

ነባሮቹም ሆኑ አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ግብ በማስቆጠር እና ጨዋታ ለዋጭ ተፅዕኖዎችን በመፍጠር እያሳዩ ያሉት ብቃት ቡድኑ አማራጮች እንዲሰፉለት ጨዋታው ቢከብደው እንኳን በተጫዋቾች የግል ብቃት የሚገኙ ግቦችን ለማስቆጠር የሚረዳው ጉዳይ ነው።

በተለይ ኢትዮጵያ ቡና ከኃላ መስመር ላይ ከሚሰራው ተደጋጋሚ ስህተት አንፃር የፈረሰኞቹ ቀጥተኝነት እና ፊት ላይ ያሉ ተሰላፊዎቻቸው ፍጥነት ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይገመታል።

ቡድኑ መሀል ሜዳ ላይ ኳስን የማቆየት ሀሳብ ካለው ግን የተሻለ ውህደት ባለው ተጋጣሚው መፈተኑ የሚቀር አይመስልም።
ኢትዮጵያ ቡና እንደተጋጣሚው ረዘም ያለ የማገገሚያ ጊዜ ባይኖረውም ከኋላ ተነስቶ ያሸነፈበት የሰበታው ጨዋታ ትዝታ ትኩስ መሆኑ የቡድኑ ጉልበት ላይ የሚጨምርለት አዕምሯዊ ጥንካሬ ይኖራል።

የኳስ ቁጥጥር የበላይነትን አብዝተው የሚፈልጉት ቡናማዎቹ እንደ ሰበታው ጨዋታ ታታሪነት የታከለበት እና የፊት መስመር ተሰላፊዎች እገዛ ያልተለየው እንቅስቃሴ የመሀል ሜዳውን ጦርነት ለማሸነፍ ትልቅ እገዛ ያደርግላቸዋል።

እንደ #ዊሊያም_ሰለሞን እና #ሬድዋን_ናስር ዓይነት ወጣት ተጫዋቾቻቸው ጭምር ቡድኑ ለሚፈልገው አካሄድ በጨዋታ ጭምር ተፈትነው ለደርቢው መድረሳቸውም ለቡድኑ ተጨማሪ ኃይል ይሆነዋል።
ምንም እንኳን ከተጋጣሚው በራሱ ሜዳ ከፍ ያለ ጫና ሊደርስበት እንደሚችል ቢገመትም ያንን የሚያልፍበት ጥሩ ዕቅድ ከኖረው የጊዮርጊስን የአማካይ ክፍል ተጋፍጦ የመጨረሻ ኳሶችን ለማድረስ የተሻለ ዕድል ይኖረዋል።
ይህን ለማድረግ ግን ተደጋጋሚ ለውጦች የተደረጉበት የቡድኑ የተከላካይ አማካይ ተሰላፊ ሚና ከፍ ያለ ነው።

ፊት መስመር ላይ ያሉት የቡድኑ ተሰላፊዎችም እንዲሁ ከግብ አስቆጣሪነቱ ሳይቦዝኑ ለጨዋታው መድረሳቸው ለአሰልጣኝ #ካሳዬ ቡድን ጥንካሬን የሚያላብስ ነው።
ቡድኑ ከኋላ ያለከፍተኛ ጫና ሲሰራቸው እና ዋጋ ሲያስከፍሉት የሰነበቱት ስህተቶች ግን ነገ ከበድ ባለ ጫና ዳግም የመፈተሻቸው ነገር ስጋት የሚጭር ይሆናል።

በቡድኖቹ የተሻለ የማጥቃት ተሳትፎ ያላቸው ተከላካዮች #ሄኖክ_አዱኛ እና #ኃይሌ_ገብረትንሳይ ወደ ፊት ለመሄድ ከተቃራኒ ቡድን የመስመር አጥቂዎች የሚገጥማቸው ፈተና ፣ #ታፈሰ_ሰለሞንን ከሙላለም መስፍን ያሚያጋፍጡ ቅፅበቶች ፣ የጊዮርጊሶቹ አቤል ያለው እና አዲስ ግደይ ከቡና የተከላካይ መስመር ፊት እና ኃላ ያሉ ቦታዎች ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ ፣ የቡና መስመር አጥቂዎች በጊዮርጊስ መሀል እና መስመር ተከላካዮች መሀል ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት እንዲሁም የጌታነህ ከበደ እና የ#አቡበከር_ናስር ከተከላካይ መስመር ጋር የሚኖራቸውን ግብግብ በነገው ሸገር ደርቢ የምንጠብቃቸው የሜዳ ላይ ፍልሚያዎች ይሆናሉ።

ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ የቡድን ዜናዎችን ለማካተት ያደረግነው ጥረት በሁለቱም ክለቦች በኩል መረጃ ባለማግኘታችን አልተሳካም።

እርስ በእርስ ግንኙነት
– ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ 40 ጊዜ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 ጨዋታ ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያ ቡና 6 ድል አሳክቷል። በ16 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
– የሸገር ደርቢ ምንም እንኳ አሁን አሁን ያለ ግብ የሚጠናቀቅባቸው ጨዋታዎች በርከት ቢሉም ባለፉት 40 ግንኙነቶች 73 ጎሎች ተቆጥረዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ 49፤ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 24 ጎሎች ማስቆጠር ችለዋል።

ግምታዊ አሰላለፍ
ቅዱስ ጊዮርጊስ (4-2-3-1)
ፓትሪክ ማታሲ
ሄኖክ አዱኛ – ምንተስኖት አዳነ – አስቻለው ታመነ – ፍሪምፖንግ ሜንሱ
ሀይደር ሸረፋ – ሙሉዓለም መስፍን
አቤል ያለው – ሮቢን ንጋላንዴ – አዲስ ግደይ
ጌታነህ ከበደ

ኢትዮጵያ ቡና (4-3-3)
ተክለማሪያም ሻንቆ
ኃይሌ ገብረትንሳይ – ወንድሜነህ ደረጄ – አበበ ጥላሁን – አሥራት ቱንጆ
ታፈሰ ሰለሞን – ረመዳን ናስር – ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን
አቤል ከበደ – ሀብታሙ ታደሰ – አቡበከር ናስር
© ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
አሠልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ በየዛሬው ጨዋታ ለዋንጫው ወሳኝ መሆኑን ተናግረው ከባለፈው የወልቂጤ ጨዋታ መጠነኛ ለውጦችን አድርገው ወደ ሜዳ እንደገቡ ገልፀዋል። በዚህም #ኃይሌ_ገብረትንሳይ#ምንተስኖት_ከበደ እና #እያሱ_ታምሩን በአስራት ቱንጆ፣ ወንድሜነህ ደረጄ እና ዊሊያም ሰለሞን ተክተው ለጨዋታው ቀርበዋል።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሃን ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።
የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ኢትዮጵያ ቡና
99 አቤል ማሞ
11 አስራት ቱንጆ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
8 አማኑኤል ዮሃንስ
13 ዊሊያም ሰለሞን
15 ሬድዋን ናስር
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
7 ሚኪያስ መኮንን

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
ቅድመ ዳሳሳ | ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

በባህር ዳር ከተማ አስተናጋጅነት የሚደረገውን የመጨረሻ ጨዋታ በዳሰሳችን እንዲህ ተመልክተነዋል።

ድል ካደረጉ አምስት የጨዋታ ሳምንታት ያለፋቸው ድሬዳዋ ከተማዎች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለ ጎል አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ያሳዩትን መሻሻል በውጤት ለማሳጀብ እና ከአስጊው ቀጠና ለመራቅ ነገ ወደ ሜዳ ይገባሉ።
በፋሲል ከነማ አንድ ለምንም ተረተው ለዚህኛው ጨዋታ እየተዘጋጁ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች በበኩላቸው ዳግም ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እና ከሊጉ መሪ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት በስምንት ለማስቀጠል ድልን አልመው ጨዋታውን ይቀርባሉ።
በአሠልጣኝ ዘማርያም የሚመራው ድሬዳዋ ከተማ በጊዮርጊሱ ጨዋታ በእንቅስቃሴ ደረጃ እጅግ ተሻሎ ቀርቦ ነበር።
በተለይም ግብ የማስተናገድ አባዜ ይዞት የነበረው የቡድኑ የኋላ መስመር እርጋታ በተሞላበት ሁኔታ የተጋጣሚን ቡድን አጥቂዎች ተቆጣጥሮ ሲጫወት ተስተውሏል።
በተጨማሪም ቡድኑ ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴዎችን በመስመር በኩል በማፋጠን ተጋጣሚን ሲረብሽ ታይቷል።
በዋናነት ደግሞ አስቻለው ግርማ ፍጥነቱን ተጠቅሞ የሚያደርጋቸው ሩጫዎች ለተጋጣሚ አደጋን የሚያመጡ ነበሩ።
ወደ መሐል ሜዳው ተጠግቶ መከላከል የሚያዘወትረው የቡና የተከላካይ መስመርም ነገ አስቻለውን ጨምሮ ሌሎች የቡድኑን የወገብ በላይ ተጫዋቾች በአግባቡ የማይቆጣጠር ከሆነ ከባድ ጊዜን ሊያሳልፍ ይችላል።
ካለፉት ሦስት ጨዋታዎች ሁለት ጎሎችን ብቻ ያስተናገደው የቡድኑ የተከላካይ መስመር ለቡናዎች ከባድ ቢሆንም ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ሦስት ግቦችን ብቻ ተጋጣሚ ላይ ያስቆጠረው የፊት መስመሩ መሻሻሎች ያስፈልጉታል።
ከላይ እንደተጠቀሰውም በግል ብቃት ከሚገኙ አጋጣሚዎች ውጪ ቡድኑ በተደራጀ እና መደገም በሚችል መልኩ ጥቃቶችን ለመፍጠር ይቸገራል።
ከዚህ መነሻነትም ቡናዎች የፊት መስመር ተጫዋቾቹን ፍጥነት የሚቆጣጠር ከሆነ ድሬዳዋ የማጥቂያ ሀሳብ ሊያጥረው ይችላል።
ብርትካናማዎቹ በነገው ጨዋታ የሱራፌል ጌታቸውን ግልጋሎት በጉዳት ምክንያት አያገኙም።
ከኳስ ጋር አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ ማሳለፍ ተቀዳሚ ምርጫው የሚያደርገው ኢትዮጵያ ቡና በነገውም ፍልሚያ የጨዋታውን የኃይል ሚዛን ወደ ራሱ አድርጎ እንደሚጫወት ይገመታል።
በዋናነት ግን የአማካይ መስመሩ ላይ ያሉትን የተጫዋቾች የቴክኒክ ብቃት ተንተርሶ ከሚደረግ የመሐል ለመሐል ጥቃት በበለጠ ቡድኑ የመስመር ላይ አጨወቱን አስሎ ወደ ሜዳ ሊገባ ይችላል።
በዚህም ለመከላከል ቅድሚያ ይሰጣል ተብሎ የሚገመተውን የድሬዳዋ የተከላካይ መስመር ለመዘርዘር በመስመር ላይ ያተኮሩ እንቅስቃሴዎችን ሊተገብር ይችላል።
የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የያዘው ቡና
(አቡበከር) ከኳስ ጋር አስፈሪ ቢሆንም ከኳስ ውጪ ያለው አደረጃጀት ግን ጠጣርነት ይጎድለዋል።
በተለይም ቡድኑ የሚያደርጋቸው ከማጥቃት ወደ መከላከል ሽግግሮች ጊዜያቸው የረዘመ ሲሆን ይታያል።
ይህም ቡድኑን ለመልሶ ማጥቃት ሲያጋልጠው ይስተዋላል።
ስለዚህም ነገ ድሬዳዋዎች ቡድኑ ከኋላ ኳስ ሲጀምር ተጭነው ለመቀበል ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪ የመልሶ ማጥቃት አጋጣሚዎችን በአትኩሮት መጠበቅ ጠቀሜታን ሊያስገኝላቸው ይችላል።

➡️አሠልጣኝ ካሳዬ አራጌ በነገው ጨዋታ ጉዳት አጋጥሟቸው ከቡድኑ ጋር ልምምድ ያልሰሩትን #ኃይሌ_ገብረትንሳይ እና #ታፈሰ_ሰለሞንን የማያገኙ ይሆናል።

የእርስ በእርስ ግንኙነት

– ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ለ17 ጊዜያት ያህል ተገናኝው ኢትዮጵያ ቡና 9 ጊዜ በማሸነፍ የበላይ ሲሆን ድሬዳዋ 3 ጊዜ ድል ቀንቶታል ፤ 5 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። በጨዋታዎቹ 27 ጎሎች በኢትዮጵያ ቡና 14 ጎሎች ደግሞ በድሬዳዋ ከተማ ተቆጥረዋል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ድሬዳዋ ከተማ (4-2-3-1)
ፍሬው ጌታሁን
ዐወት ገብረሚካኤል – ያሬድ ዘውድነህ – ፍሬዘር ካሳ – ሄኖክ ኢሳይያስ
ዳንኤል ደምሴ – ሄኖክ ገምቴሳ
አስቻለው ግርማ – ሙኸዲን ሙሳ – ኢታሙና ኬይሙኒ
ጁኒያስ ናንጄቦ

ኢትዮጵያ ቡና (4-3-3)

አቤል ማሞ
እያሱ ታምሩ – ወንድሜነህ ደረጄ – አበበ ጥላሁን – አሥራት ቱንጆ
ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን – ረመዳን ናስር – ዊሊያም ሰለሞን
ሚኪያስ መኮንን – አቡበከር ናስር – አቤል ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈