አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
772 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
💚💛 @coffeefc 💚💛


#ያንን_ቡድን_ከቶ_ማን_ይረሳዋል

ጠንካራው ኤልፓን አሸንፎ የጥሎማለፍ ዋንጫ የበላ

አሸናፊ ግርማ ኮኮብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠለት

የቡና ደጋፊ እንደ አሸን የፈላበት

ቢራን አዝረክርኮ ከጎል እስከ ጎል ተቀባብሎ ግብ ያስቆጠረበት

ሳሚ ዮርዲ አሸናፊ ምርጥ ጥምረት የፈጠሩበት
#ካሊድ#ደብሮም#አንተነህ#ባርያው በምርጥ ብቃት የቡድኑን ባላንስ የጠበቁበት

#ሸበላው#ኪንጉና #ኩኩሻ የብረት አጥር የሰሩበት

#ለሚ#ኮል#ጋና#አስፕሬላ#ቤቢ#ባሴ አሻራቸውን ያሳረፉበት

በክለቦች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሲዲ መዝሙር የታተመለት

ሪከርድ የሆነ የስታድዮም ገቢ የተመዘገበለት።

♨️ የአልዛይመር ታማሚ ሁሉ ሊረሳው የማይችል ድንቅ ...

▪️ ያንን አስማት የሆነ ቡድን በእጁ ጠፍጥፎ የሰራው የኳስ ሜዳው #ኢንጅነር_ካሳዬ_አራጌ ወደ ቡና ሊመለስ መሆኑን ሰማን እጅግ በጣምም ደስ አለን ።

#ካሳዬ_is_back ❗️❗️
©EthiopianCoffeesportclup

@coffeefc @bunnafc @coffeefc


#ካሳዬ_አራጌ ማክሰኞ ወደ ሀገሩ #ኢትዮጵያ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል

ቀጣዮቹን አመታት ኢትዮጵያ ቡናን በዋና አሰልጣኝነት ይመራል ተብሎ የሚጠበቀው ካሳዬ አራጌ ወደ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ)
#ማክሰኞ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

በሚኖርበት #አሜሪካን ( #ቬጋስ ) በጔደኞቹ በቤተሰቦቹ እና በአሜሪካ በሚኖሩ #የኢትዮጵያ_ቡና ደጋፊዎች አሸኛኘት እና መልካም ምኞታቸውን የመግለፅ ፕሮግራም ተደርጎለታል።

ከወዲሁ መልካሙን ሁላ እንመኝልካለን መልካም መንገድ




👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆

👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
መልካም አዲስ አመት!!!

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆


#ኢትዮጵያ_ቡና ለ 2012 የውድድር አመት ቡድኑን ከአሰልጣኝ ጀምሮ እንዳዲስ እያዋቀረ መቆየቱ ይታወቃል። አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ ሲጫወትም ሲያሰለጥንም አብዛኛዎቻችን ባናየውም ስለሱ በጣም ብዙ ሰምተናል። ያንንም ለማየት ጓግተናል ቡድኑ ከአሰልጣኝ በተጨማሪ በርከት ያሉ #ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛል ከሌላው ጊዜ በተለየ ደስተኛ የሆንበት ዝውውር ነው ብለን እናምናለን።

ሁላቹም አዲስ የተቀላቀላቹን ተጨዋቾች እንኳን ፍቅር ወደ ሆነው ክለብ በሰላም መጣቹልን።

የቅድመ ዝግጅት ጊዜ ነባሮቹን ከአዳዲሶቹ ጋር በማጣመር #ከመስከረም 3-5 እንደሚጀምር ሰምተናል። መልካም የቅድመ ዝግጅት ግዜ እንዲሆን ተመኘን።

2011 አመት አብራቹን ያሳለፋቹ አሁን የተለያቹን በሄዳቹበት ይቅናቹ መልካም ጊዜ ተመኝተናል ።



👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#አዲስ_ፍሰሃ_ተመልሷል
ከኢትዮጵያ ቡና የተስፋው ቡድን ነው ያደገው (#እድሉ_ደረጄ እና #ዮሴፍ_ተስፋዬ #አሰልጥነውታል) የተስፋው ቡድናችንንም በአምበልነት መምራት ችሎ ነበር

➡️ ዲዲየር ጎሜዝም ወደ ዋናው ቡድን አሳድጎት 2010 ከወልዲያ ጋር ሰበታ ላይ በተደረገው ጨዋታም ላይ ቋሚ አሰላለፉም ውስጥ መግባት ችሎ ነበር ያሳለፍነው አመትም ከቡና ተለያይቶ ነበር #ካሳዬ_አራጌ ባዘጋጀው የሙከራ ጊዜም በመታየት ዳግም ወደ ቡና በመመለስ በዝዋይ የዝግጅት ግዜን በማድረግ ላይ ይገኛል ።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#ካሳዬ_አራጌ
family time ❤️

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
#ካሳዬ_አራጌ
Family time ❤️

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
👉 አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል !

🇪🇹☕️ የኢትዮጵያ ቡናው ዋና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ፕርሚየር ሊጉ #በኮቪዲ_19_ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መቋረጡን ተከትሎ ቤተሰቦቹ በሚገኙበት አሜሪካ ማቅናታቸው ይታወሳል ።

👉 ይህንንም ተከትሎ በመጪው #ነሐሴ_20_2012 ( ሰኞ ) ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የክለቡን ስራዎች ዳግም እንደሚቀጥሉ ለማረጋገጥ ተችሏል ::

© #Hatric_sport

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
👉 አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል !

🇪🇹☕️ የኢትዮጵያ ቡናው ዋና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ፕርሚየር ሊጉ #በኮቪድ_19_ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መቋረጡን ተከትሎ ቤተሰቦቹ በሚገኙበት አሜሪካ ማቅናታቸው ይታወሳል ።

👉 ይህንንም ተከትሎ ዛሬ #ነሐሴ_1_2012 ( አርብ ) ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የክለቡን ስራዎች ዳግም እንደሚቀጥሉ ለማረጋገጥ ተችሏል ::

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ቅድመ ዳሰሳ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና

የስድስተኛ ሳምንት መክፈቻ የሆነውን የሸገር ደርቢ የተመለከተው ዳሰሳችንን እነሆ።

የመዲናይቱ ሁለት ክለቦች ከድል መልስ የሚገናኙበት ተጠባቂ ጨዋታ ነገ ረፋድ ላይ ይከናወናል።

በእርግጥ ባለፉት ዓመታት የሸገር ደርቢ በሜዳ ላይ የታሰበውን ያህል ፉክክር ሳያሳየን የጎል ድርቅም እየመታው ሲጠናቀቅ ቆይቷል።

ይህ መሆኑ ተጠባቂነቱን ባይቀንሰውም ጓጉቶ ለሚጠብቀው የስፖርት ቤተሰብ የሚጠበቀውን ያህል አዝናኝ አለመሆኑ ቅሬታን የሚፈጥር ነው።

ለዚህ እንደአንድ ምክንያትነት የሚነሳው የሜዳ ላይ ጡዘቱ ወደ ደጋፊዎች ግጭት እንዳያመራ የመሰጋቱ ነገር ዘንድሮ በኮቪድ 19 ምክንያት ጨዋታዎች በዝግ በመካሄዳቸው የማይኖር በመሆኑ ጨዋታው ከፍ ያለ ፉክክር እንዲኖረው በር ሊከፍት እንደሚችል ይገመታል።

የቡድኖቹ ተጨዋቾችም ቀለል ባለ ጫና ውስጥ ሆነው ሲገናኙ የተሻለ ብቃታቸውን አውጥተው ለመጨወት ዕድል እንደሚያገኙም ይታሰባል።

ከሰባት ቀናት በኋላ ወደ ጨዋታ የሚመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስት ተከታታይ ድሎችን በማሳካት መልካም አቋም ላይ ይገኛል።

ከማሸነፍ በዘለለ በየጨዋታዎቹ ያስቆጠራቸው ግቦች ቁጥር ከፍ ማለትም ከእንደነገው ዓይነት ጨዋታ በፊት የቡድኑን በራስ መተማመን ከፍ ለማድረግ የሚረዳ ሌላው በጎ ነጥብ ነው።

ወደ ቀደመ የቀጥተኛነት አጨዋወቱ የማዘንበል ባህሪ እየታየበት ያለው ጊዮርጊስ ከተከላካይ ጀርባ የሚገኙ ክፍተቶችን በአግባቡ በመጠቀም ጥንካሬውን ማሳየት ችሏል።

ነባሮቹም ሆኑ አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ግብ በማስቆጠር እና ጨዋታ ለዋጭ ተፅዕኖዎችን በመፍጠር እያሳዩ ያሉት ብቃት ቡድኑ አማራጮች እንዲሰፉለት ጨዋታው ቢከብደው እንኳን በተጫዋቾች የግል ብቃት የሚገኙ ግቦችን ለማስቆጠር የሚረዳው ጉዳይ ነው።

በተለይ ኢትዮጵያ ቡና ከኃላ መስመር ላይ ከሚሰራው ተደጋጋሚ ስህተት አንፃር የፈረሰኞቹ ቀጥተኝነት እና ፊት ላይ ያሉ ተሰላፊዎቻቸው ፍጥነት ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይገመታል።

ቡድኑ መሀል ሜዳ ላይ ኳስን የማቆየት ሀሳብ ካለው ግን የተሻለ ውህደት ባለው ተጋጣሚው መፈተኑ የሚቀር አይመስልም።
ኢትዮጵያ ቡና እንደተጋጣሚው ረዘም ያለ የማገገሚያ ጊዜ ባይኖረውም ከኋላ ተነስቶ ያሸነፈበት የሰበታው ጨዋታ ትዝታ ትኩስ መሆኑ የቡድኑ ጉልበት ላይ የሚጨምርለት አዕምሯዊ ጥንካሬ ይኖራል።

የኳስ ቁጥጥር የበላይነትን አብዝተው የሚፈልጉት ቡናማዎቹ እንደ ሰበታው ጨዋታ ታታሪነት የታከለበት እና የፊት መስመር ተሰላፊዎች እገዛ ያልተለየው እንቅስቃሴ የመሀል ሜዳውን ጦርነት ለማሸነፍ ትልቅ እገዛ ያደርግላቸዋል።

እንደ #ዊሊያም_ሰለሞን እና #ሬድዋን_ናስር ዓይነት ወጣት ተጫዋቾቻቸው ጭምር ቡድኑ ለሚፈልገው አካሄድ በጨዋታ ጭምር ተፈትነው ለደርቢው መድረሳቸውም ለቡድኑ ተጨማሪ ኃይል ይሆነዋል።
ምንም እንኳን ከተጋጣሚው በራሱ ሜዳ ከፍ ያለ ጫና ሊደርስበት እንደሚችል ቢገመትም ያንን የሚያልፍበት ጥሩ ዕቅድ ከኖረው የጊዮርጊስን የአማካይ ክፍል ተጋፍጦ የመጨረሻ ኳሶችን ለማድረስ የተሻለ ዕድል ይኖረዋል።
ይህን ለማድረግ ግን ተደጋጋሚ ለውጦች የተደረጉበት የቡድኑ የተከላካይ አማካይ ተሰላፊ ሚና ከፍ ያለ ነው።

ፊት መስመር ላይ ያሉት የቡድኑ ተሰላፊዎችም እንዲሁ ከግብ አስቆጣሪነቱ ሳይቦዝኑ ለጨዋታው መድረሳቸው ለአሰልጣኝ #ካሳዬ ቡድን ጥንካሬን የሚያላብስ ነው።
ቡድኑ ከኋላ ያለከፍተኛ ጫና ሲሰራቸው እና ዋጋ ሲያስከፍሉት የሰነበቱት ስህተቶች ግን ነገ ከበድ ባለ ጫና ዳግም የመፈተሻቸው ነገር ስጋት የሚጭር ይሆናል።

በቡድኖቹ የተሻለ የማጥቃት ተሳትፎ ያላቸው ተከላካዮች #ሄኖክ_አዱኛ እና #ኃይሌ_ገብረትንሳይ ወደ ፊት ለመሄድ ከተቃራኒ ቡድን የመስመር አጥቂዎች የሚገጥማቸው ፈተና ፣ #ታፈሰ_ሰለሞንን ከሙላለም መስፍን ያሚያጋፍጡ ቅፅበቶች ፣ የጊዮርጊሶቹ አቤል ያለው እና አዲስ ግደይ ከቡና የተከላካይ መስመር ፊት እና ኃላ ያሉ ቦታዎች ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ ፣ የቡና መስመር አጥቂዎች በጊዮርጊስ መሀል እና መስመር ተከላካዮች መሀል ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት እንዲሁም የጌታነህ ከበደ እና የ#አቡበከር_ናስር ከተከላካይ መስመር ጋር የሚኖራቸውን ግብግብ በነገው ሸገር ደርቢ የምንጠብቃቸው የሜዳ ላይ ፍልሚያዎች ይሆናሉ።

ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ የቡድን ዜናዎችን ለማካተት ያደረግነው ጥረት በሁለቱም ክለቦች በኩል መረጃ ባለማግኘታችን አልተሳካም።

እርስ በእርስ ግንኙነት
– ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ 40 ጊዜ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ 18 ጨዋታ ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያ ቡና 6 ድል አሳክቷል። በ16 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።
– የሸገር ደርቢ ምንም እንኳ አሁን አሁን ያለ ግብ የሚጠናቀቅባቸው ጨዋታዎች በርከት ቢሉም ባለፉት 40 ግንኙነቶች 73 ጎሎች ተቆጥረዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ 49፤ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 24 ጎሎች ማስቆጠር ችለዋል።

ግምታዊ አሰላለፍ
ቅዱስ ጊዮርጊስ (4-2-3-1)
ፓትሪክ ማታሲ
ሄኖክ አዱኛ – ምንተስኖት አዳነ – አስቻለው ታመነ – ፍሪምፖንግ ሜንሱ
ሀይደር ሸረፋ – ሙሉዓለም መስፍን
አቤል ያለው – ሮቢን ንጋላንዴ – አዲስ ግደይ
ጌታነህ ከበደ

ኢትዮጵያ ቡና (4-3-3)
ተክለማሪያም ሻንቆ
ኃይሌ ገብረትንሳይ – ወንድሜነህ ደረጄ – አበበ ጥላሁን – አሥራት ቱንጆ
ታፈሰ ሰለሞን – ረመዳን ናስር – ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን
አቤል ከበደ – ሀብታሙ ታደሰ – አቡበከር ናስር
© ሶከር ኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ኢትዮጵያ ቡና የዛሬ አሰላለፍ

1 ተክለማርያም ሻንቆ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
16 ሬድዋን ናስር
13 ዊልያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
10 አበበከር ናስር
25 ሀብታሙ ታደሰ
17 አቤል ከበደ

አሰልጣኝ #ካሳዬ_አራጌ በሰበታው ጨዋታ ድል ያደረገውን ቡድን ሳይቀይር ጨዋታውን ይጀምራል ወጣቶቹ #ሬድዋን_ናስር እና #ዊልያም_ሰለሞንም በድጋሚ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ የመካተት ዕድልን አግኝተዋል።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
የአሁኑ አሰልጣኛችን የቀድሞው ተጫዋቻችን #ካሳዬ አራጌ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉 የሰከኑት #ካሳዬ_አራጌ #Gk

➡️አሰልጣኞች እንደ ማንኛውም ሰው በህይወት ጉዟቸው የስሜት ከፍታ እና ዝቅታ ማስተናገዳቸው ብሎም እነዚሁን ስሜቶች የሚያፀባሩቁባቸው ተለዋዋጭ ግብረ መልሶችን በስራቸው ላይ ማሳየታቸው የሰውነታቸው መገለጫ ተደርገው ይወሰዳሉ። ታዲያ ይህን የህይወታችን አንዱ አካል የሆነውን የስሜት መለዋወጥ ግን በኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ላይ መመልከት እጅግ አዳጋች ይመስላል።

➡️አሰልጣኙ ብዙዎቻችን በምናውቀው ከካሜራ ፊት እና በሜዳው ጠርዝ ቡድኑን ሲመሩ የሚታይባቸው የስሜት ወጥነት እጅግ አስደናቂ ነው።

➡️ቡድኑ ቢመራም አልያም ብልጫ ቢወሰድበት አሰልጣኝ ካሳዬ ግን እንደተለመደው እጅጉን ተረጋግተው በሜዳው ጠርዝ ላይ ይታያሉ እንጂ ሲቅበጠበጡ እና በስሜት መዋዥቅ ውስጥ ሆነው አናያቸውም።

➡️እንደ አብዛኞቹ የሊጉ አሰልጣኞች ከቡድኑ በተቃራኒ የሚወሰኑ የዳኝነት ውሳኔዎችን ተከትሎ እንኳን ተቃውሞዎችን ስያሰሙ አይስተዋልም።

➡️ታድያ ይህ የሰከነ ስብዕና አያስገርምም ትላላችሁ ?

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈