አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
772 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
🔹የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች በግራንድ ኤሊያና ሆቴል ደምቀው አመሹ!

◾️የቡና ሠማይ ሥር ሦስትኛው ዙር የኮኮቦች ሽልማት እጅግ ደማቀ በሆነ ሥነ ስራአት ትላንት ምሽት በኤሌያና ሆቴል ተደርጓል።

1➡️ የህይወት ዘመን የክብር ተሸላሚ #መቶ_አለቃ_ፍቃድ_ማሞ

2➡️ የቡና ሠማይ ሥር በደጋፊዎች ምርጫ የዓመቱ ኮኮብ ተጨዋች #አቡበከር_ናስር

3➡️የቡና ሠማይ ሥር አዘጋጆች ኮከብ ተጨዋች #አስራት_ቶንጆ

4➡️የ2013 ወድድር የኢትዮጽያ ቡና ደንቅ ጎል #ሚኪያስ_መኮንን

5➡️ በርከታ ለጎል የሚሆኑ ኳስ ያቀበለ #ታፈሰ_ሰለሞን

6➡️ተስፈኝ ታዳጊ ተጨዋቾች #ዊሊያም_ሰለሞን እና #ሬድዋን_ናስር ...በመሆን በርካታ ታዲሚያን ፤ ጥሩ የተግደረገላቸው የቡና ደጋፊዎቻ እና አርቲስቶች በተገኙበት ተሸላሚ በመሆን ደምቀው አምሽተዋል።

ዊሊያም እና ሬድዋን የቤሄራዊ ቡድን ጥሪ ላይ ሲሆኑ ከሆቴል ለመውጣት ፍቃድ ባለ ማግኘታቸው በአማኑኤል እና በኢያሱ በአማካኝነት ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
#ዜና_የኢትዮጵያ_ቡና

👉 የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የቅድመ-ውድድር ዝግጅቱን ለማድረግ የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 4/2015 ዓ.ም አዳማ ከተማ ላይ የሚከትም ሲሆን ቡድኑ ከአርብ ነሐሴ 05/2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ልምምዱን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

👉 ዘጠኝ የአሰልጣኝ ቡድን እና 29 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ አዳማ ከተማ የሚያቀናው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከወዲሁ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችንም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

👉 በ2015 ዓ.ም የውድድር ዓመት ጉዳት የገጠማቸው #ሮቤል ተ/ሚካኤል፣ #አስራት ቶንጆ እና #መሐመድኑር ናስር ከቅድመ-ውድድር ዝግጅቱ ውጪ መሆናቸው ሲታወቅ የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር መጀመሪያ ላይ ቡድኑን የሚቀላቀሉ ይሆናል። ባንፃሩ ለረጅም ጊዜ በጉዳት ላይ የነበረው ተከላካዩ #ወንድሜነህ ደረጄ ሙሉ ለሙሉ ከጉዳት በማገገሙ ቡድኑን ይቀላቀላል።

👉 ሁለት የውጭ ተጫዋቾች በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ቡድኑን የሚቀላቀሉ ሲሆን የመጫወቻ ቦታቸውም የፊት አጥቂ እና ተከላካይ ቦታ ላይ ነው ።

👉 ለ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት አዲስ ሁለት የውጭ አሰልጣኞችን ወደ ቡድናችን ሲቀላቀሉ ዋናው አሰልጣኝ #Kavazovic_Nikola እና የአካል ብቃት አሰልጣኙ #Vasiljevic_Marko ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ሲጠበቅ፤ ነገ ወደ አዳማ ከተማ የሚያቀኑ ይሆናል።

በሁለቱ አሰልጣኞች የውል ዘመን፣ እና በውል ውስጥ የተካተቱ ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣይ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።
አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና-አደገኛ
💛🤎@coffeefc💛🤎
💛🤎@coffeefc💛🤎
#ዜና_ኢትዮጵያ_ቡና

ከንግድ ባንክ ጋር በተደረገው ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ተከላካዩ #ራምኬል_ጀምስ ለአንድ ሳምንት ከሜዳ የሚርቅ ሲሆን

#አብዱልሐቪዝ በጆሮ ህመም፣ እንዲሁም ለወራት ከሜዳ ከራቀ በኋላ ከጉዳት መልስ ቡድኑን በተቀላቀለበት ዕለት በእግሩ ላይ የፈላ ውሃ በመደፋቱ ምክንያት ከቅድመ-ውድድር ዝግጅቱ የተገለለው አጥቂው

#መሐመድኑር ከነገ ጀምሮ ቡድኑን ይቀላቀላሉ። በተያያዘ ዜና ለረጅም ወራት ከሜዳ ተገልሎ የነበረው

#አስራት_ቶንጆ የጂም ውስጥ እንቅስቃሴ እያደረገ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የሜዳ ላይ ልምምዶችን እየሰራ ይገኛል።

ከህክምና ክፍላችን ባገኘነው መረጃ መሰረት በዚህ ወር መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ከቡድኑ ጋር ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛🤎 
@coffeefc 💛🤎
💛🤎 
@coffeefc  💛🤎
📌 የኢትዮጵያ ቡና የተቀላቀለው በ2010 ዓ.ም በአሰልጣኝ ፖፓዲች ቡድን ውስጥ ነበር። በ2009 የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊግ ይጫወት የነበረውን ጅማ አባጅፋርን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲያድግ ትልቅ አስተዋፅዖም አድርጓል።

📌 በኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እና የእግር ኳስ ተመልካቾች በሜዳ ላይ እንቅስቃሴው ታታሪ፣ አይደክሜ እና በተለይም በጥሩ ስነ-ምግባር ከሚጠቀሱ የእግር ኳስ ተጫዋቾች አንዱ እንደሆነ ይመሰክሩለታል።

📌 ለብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጥሪ በአሰልጣኝ አብርሐም መብራቱ ጥሪ ከቀረበለት ጀምሮ በጉዳት ከሜዳ እስከራቀበት ጊዜ በቋሚነት ብሔራዊ ቡድኑን አገልግሎት የሰጠው 11 ቁጥር ለባሹ #አስራት_ቶንጆ ከሜዳ ከራቀ አንድ የውድድር ዓመት ሊሞላው ነው።

📌 ለመሆኑ አስራት አሁን ያለበት የጤና ሁኔታ ምን ይመስላል በሚለው ዙሪያ አነጋግረነው መልስ ሰጥቶናል።

📌 ወደ አንድ ዓመት የሚጥጋ ጊዜ ከውድድር ያራቀህ ጉዳት ምንድነው ያደረገውስ ህክምና ምን ይመስላል?

🗣 አስራት፦ የጉልበት ህመም ሲሆን የ'ሌጋሜንት' መበጠስ ነበር ያጋጠመኝ። ለዚህም ጉዳት የቀዶ ጥገና አድርጊያለሁ። ከህመሙ ለማገገም እና  እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ከ6-9 ወር ጊዜ ይፈጃል። እነዚህ ጊዜያት በቶሎ ማገገም የሚቻልበት ወቅት ነው። ከዚህም በላይ የሚፈጅበት ጊዜ አለ። እኔ አሁን እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ። አሁን ላይ ህክምና ባደረኩበት ተቋም ፊዚዮቴራፒ እያደረኩ የነበረው ጨርሻለሁ። በመሆኑም ወደ ሜዳ መመለስ እንደምችል ከሐኪሙ ተነግሮኛል።

📌 ወደ ሜዳ ለመመለስ አሁን ላይ እያደረክ ያለኸው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?

🗣 አስራት፦ ህክምና ካደረኩኝ በኋላ ፊዚዮቴራፒስቷ በምትለኝ መሰረት ነበር እንቅስቃሴ የማደርገው የነበረው። ይህ ማለት ጉልበቴን መታሸት ሳይሆን የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እና የጡንቻ ማጠንከሪያ ስራዎችን ነበር የምሰራው። እነዚህን እንቅስቃሴዎች በጂም ውስጥ ከ3ወር ጀምሮ ነው መስራት የጀመርኩት ። ከስድስት ወር በኋላም ከጂም በተጨማሪ  ሜዳ እንድለምድ  በሳምንት ሁለት ቀን ሜዳ ላይ ሩጫዎችን አደርጋለሁ። አሁን ያለሁበት ሁኔታ ይህንን ይመስላል። በቅርቡም ክለባችን ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ ቡድኑን ተቀላቅዬ ልምምድ እጀምራለሁ።

📌 ሜዳው ....ደጋፊው አልናፈቀህም?

🗣 አስራት፦ ይሄንንማ እንዴት መግለፅ እንደሚቻል አላውቅም። አንዳንድ ጊዜ ሜዳ ውስጥ ሆነህ የማይሰማህ ነገሮች አሉ። ግን ከሜዳ ስትወጣና ስትርቅ ያኔ ነው ሁሉም ነገር የሚናፍቅህ።  እናም በድንቆቹ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ዝማሬ ጋር ሆኜ ሜዳ ላይ መጫወት እጅግ ናፍቆኛል። እናም ከእግዚያብሔር ጋር በቶሎ ወደ ሜዳ ተመልሼ በቃላት በማልገልፃቸው ደጋፊዎች እና የቡድን አጋሮቼ ጋር ለመጫወት በጣም ጓጉቻለሁ።

📌በጣም አመሰግናለሁ

🗣 አስራት፦ እኔም ከልብ አመሰግናለሁ።‌‌



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
➡️ ዜና የኢትዮጵያ ቡና

➡️ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋናው ቡድን ዝግጅቱን በራሱ የመለማመጃ ሜዳ አጠናክሮ ቀጥሏል። ያለፉትን እሁድ እና ሰኞ በቀን ሁለት ጊዜ ልምምዱን አድርጎ ከትላንት ጀምሮ በቀን አንድ ጊዜ  ልምምዱን ሲሰራ የነበረው ክለባችን፤ የሦሥተኛ ሳምንት ጨዋታውን እሁድ ጥቅምት 11/2016 ዓ.ም ምሽት 12:00 ስዓት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ለማድረግ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም ወደ አዳማ ያቀናል።

➡️ የኢትዮጵያ ቡና በጉዳት ምክንያት እስከ አሁን ግልጋሎታቸውን ያላገኘው #ራምኬል_ጀምስ እና #ኃይለሚካኤል_አደፍርስ ቡድኑን ተቀላቅለው እየሰሩ ሲገኝ በቅርቡ ከጉዳት መልስ የተቀላቀሉት #አስራት_ቶንጆ #መሐመድኑር_ናስር እና #ሬድዋን_ናስር በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ዝግጅታቸውን እየሰሩ ይገኛሉ።

➡️ በ2015 ዓ.ም የውድፍር ዘመን በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር ተመዝግቦ ውድድሩን ሲያከናውን የነበረው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የሴቶች ቡድን አንደኛ መውጣቱ ይታወሳል። የዋንጫ ርክክቡን የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም እንደሚያደርግ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

➡️ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ተስፋ(U-20) ቡድን  በክለባችን የመለማመጃ ሜዳ ልምምዱን አጠናክሮ ቀጥሏል። በአሰልጣኝ አብይ ካሳሁን የሚመራው የተስፋ ቡድናችን ዋነኛ አላማው አድርጎ ዝግጅቱን የጀመረው ተጫዋቾችን በመልካም ባህሪ፣ በአካል ብቃት እና የአእምሮ ዝግጅት በማድረግ በቀጣይ ለዋናውን ቡድን ግብዓት እንዲሆኑ ለማብቃት ነው።

➡️ ምልመላው የተደረገው በአምናው የውድድር ወቅት ከተለያዩ ክለባት (U-20) ጥሩ ብቃት ያሳዩ ተጫዋቾችን፣ ከአዲስ አበባ አንደኛ ዲቪዚዮን፣ ከባለፈው ዓመት ነባር የክለባችን ተስፋ ቡድን ተጫዋቾች እና ከ U-17 ወደ ተስፋው ቡድን በተዋቀሩ ተጫዋቾች ነው።

➡️ የቅድመ-ውድድር ዝግጅቱን መስከረም 30/2016 ዓ.ም የጀመረው የተስፋው ቡድን ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ለስድስት ሳምንታት ያክል ዝግጅት የሚያደርግ ሲሆን፤ በዚህ የዝግጅት ወቅትም ከአምስት በላይ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM