አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
196K subscribers
5.06K photos
159 videos
14 files
760 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
#ዜና_ኢትዮጵያ_ቡና

ከንግድ ባንክ ጋር በተደረገው ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ተከላካዩ #ራምኬል_ጀምስ ለአንድ ሳምንት ከሜዳ የሚርቅ ሲሆን

#አብዱልሐቪዝ በጆሮ ህመም፣ እንዲሁም ለወራት ከሜዳ ከራቀ በኋላ ከጉዳት መልስ ቡድኑን በተቀላቀለበት ዕለት በእግሩ ላይ የፈላ ውሃ በመደፋቱ ምክንያት ከቅድመ-ውድድር ዝግጅቱ የተገለለው አጥቂው

#መሐመድኑር ከነገ ጀምሮ ቡድኑን ይቀላቀላሉ። በተያያዘ ዜና ለረጅም ወራት ከሜዳ ተገልሎ የነበረው

#አስራት_ቶንጆ የጂም ውስጥ እንቅስቃሴ እያደረገ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የሜዳ ላይ ልምምዶችን እየሰራ ይገኛል።

ከህክምና ክፍላችን ባገኘነው መረጃ መሰረት በዚህ ወር መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ከቡድኑ ጋር ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛🤎 
@coffeefc 💛🤎
💛🤎 
@coffeefc  💛🤎
🆘 ዜና የኢትዮጵያ ቡና

📌 የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የ2016 ዓ.ም የውድድር ዘመን  ከሲዳማ ቡና አድርጎ በኤርሚያስ ሹምበዛ ድንቅ ጎል የመጀመሪያ ጨዋታውን በአሸናፊነት መጨረሱ ይታወቃል። ቀጣይ ጨዋታውን ከድሬዳዋ ከተማ ጥቅምት 1/2016 ዓ.ም የሚያደርግ ይሆናል።

📌 መቀመጫውን አዳማ ከተማ ያደረገው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለተወሰኑ ቀናቶች በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ልምምዱን ሲያደርግ የነበረውን የመለማመጃ ቦታ ወደ ወንጂ ስታዲየም በመቀየር ልምምዱ በተጠናከረ መልኩ እያደረገ ይገኛል። በአዲስ አበባ ያለው የዝናብ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ከቆመ መቀመጫውን በራሱ የተጫዋቾች የመኖሪያ ካንፕ በማድረግ ልምምድኑ የሚያከናውን ይሆናል።

📌 ከዚህ ጋር ተያይዞ አሰልጣኝ ኮቫዞቪች ኒኮላ በህመም እና ከብሔራዊ ቡድን ጥሪ ጋር በተያያዘ ሙሉ የቅድመ-ውድድር ዝግጅት የልምምድ ጊዜያቸው ያላከናወኑ ተጫዋቾች ሙሉ ለሙሉ ወደ ቡድኑ የሚቀላቀሉበትን ጊዜ አሳውቀዋል።

➡️ በዚህም መሰረት

📌 በተለያዩ ምክንያቶች ከቡድኑ ጋር ልምምድ ያላደረገው አማካኙ #አማኑኤል_ዮሐንስ መስከረም 29/2016 ዓ.ም ሙሉ የልምምድ ዝግጅቱን የሚያጠናቅቅ በመሆኑ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ሲጠበቅ

📌 በተመሳሳይ #መሐመድኑር_ናስር ከሦሥት ሳምንት በኋላ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም እንዲሁም አብዱልሐቪዝ ቶፊቅ መስከረም 27/2016 ዓ.ም  በተመሳሳይ የተያዘላቸውን የልምምድ ጊዜ እንዳጠናቀቁ ለውድድሩ ብቁ ሆነው ቡድኑን የሚቀላቀሉ ይሆናል።

📌 ከጉዳት ጋር በተያያዘ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው አንበሉ #በረከት_አማረ ከዛሬው የልምምድ ፕሮግራም ውጪ ቢሆንም ከነገ ጀምሮ ወደ ልምምድ የሚመለስ ይሆናል።

📌 በተመሳሳይ በሲቲ ካፑ ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ተከላካዩ #ራምኬል_ጀምስ መጠነኛ ልምምድ ማድረግ ጀምሯል።

📌 በተመሳሳይ በጉዳት ከቡድኑ ተለይቶ የነበረው #ሬድዋን_ናስር ቡድኑን ተቀላቅሎ መጠነኛ ልምምድ ማድረግ ጀምሯል።



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
➡️ ዜና የኢትዮጵያ ቡና

➡️ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋናው ቡድን ዝግጅቱን በራሱ የመለማመጃ ሜዳ አጠናክሮ ቀጥሏል። ያለፉትን እሁድ እና ሰኞ በቀን ሁለት ጊዜ ልምምዱን አድርጎ ከትላንት ጀምሮ በቀን አንድ ጊዜ  ልምምዱን ሲሰራ የነበረው ክለባችን፤ የሦሥተኛ ሳምንት ጨዋታውን እሁድ ጥቅምት 11/2016 ዓ.ም ምሽት 12:00 ስዓት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ለማድረግ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም ወደ አዳማ ያቀናል።

➡️ የኢትዮጵያ ቡና በጉዳት ምክንያት እስከ አሁን ግልጋሎታቸውን ያላገኘው #ራምኬል_ጀምስ እና #ኃይለሚካኤል_አደፍርስ ቡድኑን ተቀላቅለው እየሰሩ ሲገኝ በቅርቡ ከጉዳት መልስ የተቀላቀሉት #አስራት_ቶንጆ #መሐመድኑር_ናስር እና #ሬድዋን_ናስር በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት ዝግጅታቸውን እየሰሩ ይገኛሉ።

➡️ በ2015 ዓ.ም የውድፍር ዘመን በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር ተመዝግቦ ውድድሩን ሲያከናውን የነበረው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የሴቶች ቡድን አንደኛ መውጣቱ ይታወሳል። የዋንጫ ርክክቡን የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 10/2016 ዓ.ም እንደሚያደርግ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

➡️ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ተስፋ(U-20) ቡድን  በክለባችን የመለማመጃ ሜዳ ልምምዱን አጠናክሮ ቀጥሏል። በአሰልጣኝ አብይ ካሳሁን የሚመራው የተስፋ ቡድናችን ዋነኛ አላማው አድርጎ ዝግጅቱን የጀመረው ተጫዋቾችን በመልካም ባህሪ፣ በአካል ብቃት እና የአእምሮ ዝግጅት በማድረግ በቀጣይ ለዋናውን ቡድን ግብዓት እንዲሆኑ ለማብቃት ነው።

➡️ ምልመላው የተደረገው በአምናው የውድድር ወቅት ከተለያዩ ክለባት (U-20) ጥሩ ብቃት ያሳዩ ተጫዋቾችን፣ ከአዲስ አበባ አንደኛ ዲቪዚዮን፣ ከባለፈው ዓመት ነባር የክለባችን ተስፋ ቡድን ተጫዋቾች እና ከ U-17 ወደ ተስፋው ቡድን በተዋቀሩ ተጫዋቾች ነው።

➡️ የቅድመ-ውድድር ዝግጅቱን መስከረም 30/2016 ዓ.ም የጀመረው የተስፋው ቡድን ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ለስድስት ሳምንታት ያክል ዝግጅት የሚያደርግ ሲሆን፤ በዚህ የዝግጅት ወቅትም ከአምስት በላይ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM