The Christian News
5.03K subscribers
3.01K photos
23 videos
710 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ጠቢባን እንደኖህ ቤታቸውንና ትውልዳቸውን ከዘመናችን የጥፋት ውሃ የሚያስመልጥ መርከብ በእግዚአብሔር ቃል ንድፍ መሰረት እየሰሩ ነው። 

ፈጥኖ መቀላቀል ከጠቢባን መካከል መሰለፍ ነው።
"አርቤን ለትዳሬ" ምን ማለት ነው?

ለሥራ ፣ ለትምህርት ወይም ለተለያየ ተግባሮቻችን እና የህይወታችን ክፍል ጊዜ እንሰጣለን።

ትዳራችን ግን በህይወት ሩጫ መካከል ሲሸፈን ይታያል። ስለዚህ ይህ እንዳይሆን በሳምንት አንድ ቀን ማለትም "አርብን" ትዳራችንን ፣ ራሳችንን (ከትዳር አንፃር) ፣ የትዳር አጋሪችንን እና ልጆቻችንን በአስተውሎት ልናጤን ይገባናል። "አርቤን ለትዳሬ" ማለት ይህ ነው።

ዓላማው ምንድነው?
👉ባለትዳሮች ትዳራቸውን በእውቀት ፣ በማስተዋልና በጥበብ እንዲመሩ ማገዝ፤
👉ስለጋብቻና ልጆች አስተዳደግ ቁጭ ብሎ የመማርን ልምድ ማስረፅ፤
👉"አርብን" የቤተሰብ ቀን የማድረግ ባህልን ማስተዋወቅ ፤

ይህንን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ።
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
#ጤናማ_ቤተሰብ_ጤናማ_ሀገር
#የቤተሰብ_ቅጥር_አዳሽ
#ወደ ሚወደዉ ጌታ ሄዷል። #ዜና 😭😭

ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ወደሚወደው ጌታ ሄዷል።

የሄደው ወደጌታ ቢሆንም የሚወዱት ሲለይ ያሳዝናልና The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን.... 🙏🙏🙏
#የኢየሱስ ወታደር ነኝ ... #ወደ አምላኩ ሄደ 😭
ከ40ዓመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቷል...

#ሄደ #ወደ አምላኩ ሄደ ...
ኢየሱስን ብሎ አለምን የካደ ሄደ ..😭

ከ1945 - 2016 ...

ሙሉቀን በ1960ና 70ዎቹ ብዙዎች በኢትዮጵያ ወርቃማ በሚባለው የሙዚቃ ዘመን፣ ቁንጮ ከነበሩት መካከል ነዉ ይሉታል። ኋላ ላይም ወደ ጌታ #ኢየሱስ መጥቷል።

ሙሉቀን በ1945 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተወለደ። በልዩ ተሰጦው ምክንያት በ12 አመቱ ሙዚቃን የጀመረው ሙሉቀን፣ በለጋ እድሜው ነበረ በመሸታ ቤቶች ውስጥ “እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በሚለው ሙዚቃ የጀመረው።

ሙሉቀን የዘፈኑ አለም በቃኝ ብሎ ወደ ጌታ ከመጣበት 1970ዎቹ ማገባደጃ አካባቢ ጀምሮ በዝማሬ ማገልገሉን ቀጥሏል። በየጊዜው የቀድሞ የዘፈን ወዳጆቹ የእንዝፈን ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥሎበታል።

ህመሙ በጠናበት ጊዜም እነ ታማኝ በየነ ልህክምና ወጪ የዘፈን ድግስ እናዘጋጅ ሲሉትም በኔ ስም አይዘፈንም ብሎ በቅድስና የኖረ ጀግና ክርስቲያን ነው።

ሙሉቀን ወደ ክርስቲያኖች ካደረሳቸው መዝሙሮች መካከል “ስለ ውለታህ”፣ አድራሻ ቢስ ሆኜ በዓለም ውስጥ ስጨነቅ”፣ “ሃሌሉያ”፣ “አቤኔዜር” እና ሌሎችንም መዝሙሮችን ከሃሌሉያ አልበሙ አስመቶናል።

በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ መታሰቢያ በEBS Tv ላይ "ከኢትዮጵያ ከወጣህ 38 ዓመት ሆኖሃል አትናፍቅህም?" የሚል ጥያቄ ብትሰነዝርለትም ሙሉቀን መለሠ ግን አትናፍቀኝም! ... ኢየሱስን ማየት ነው የናፈቀኝ ማለቱ የቅርብ ዓመች ትዝታ ነዉ።

#ዘማሪ #ሙሉ #ቀን ኑሮውን በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ከባለቤቱ ጋር አድርጎ በኖረበት በ71 ዓመቱ ወደ ሚወደውና ወዳገለገለው #ጌታ ሄዷል።

በነገራችን #ላይ ሙሉቀን መለሰ በዓለም የሙዚቃ ስራ ዉስጥ ለ14ዓመት ብቻ ከ13 ዓመቱ እስከ 27ዓመቱ ብቻ ነዉ የቆየው ዘፈን አቁሞ ወደ ጌታ ከመጣ ደግሞ 43 አመታትን አስቆጥሯል።

ከበርካታ ዝማሬዎቹ መካከል
አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም
አምላክ ከእኔ ጋር ነው አታሸንፊኝም

እንዲሁም
ከኢየሱስ ጋራ ሲሄዱ
ከጌታ ጋራ ሲሄዱ
እንዴት ያምራል ጎዳናዉ
እንዴት ያምራል መንገዱ

በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀዉ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
እዋጋለሁኝ አልሽነፍም
ለጠላት እጅን አልስጥም

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ ...

ለሙሉቀን መለሰ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ መጽናናትን ይመኛል።
ለ3 እናቶች #እዉቅና ተሰጣቸዉ።

ላለፋት 12 ዓመታት ለቀደምት የወንጌል አርበኞችን በግምባር ቀደምነት እውቅና በመስጠት የሚታወቀው የምርጦቹ 7000 #ቤተክርስቲያን ለሦስት እናቶች እውቅና ሰጥቷል።

መረሃ ግብሩ ለትውልድ ወንጌልን ስላደረሱ ማመስገን የሚል ዓላማ ያለዉ እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም ቀጣዩን ትውልድ እንዲባርኩ ነው።

የበረከቱ ትሩፋት ምን እንደሆነ የቤተክርስቲያኒቷ ዋና መጋቢ አቢ እምሻው "የእናቶች በረከት የሚስጥር መዝገብ በሙላት ሲፈታ ብዙ ዘመን አሻጋሪ አቅሞች ይለቀቃሉ ፣ኃያላንም ይንቀሳቀሳሉ የትውልድን እስራት እየፈቱ ፣ "የዘመንን ስብራት እየፈወሱ ፣ ለቤተክርስቲያን መታደስና ለአገር መፈወስ ምክንያት ይሆናሉ፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።

በመረሀግብሩ እውቅና የተሰጣቸው እናቶች፦

👉 የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ መስራች የነበረው የተማሪዎች ህብረት እና የሴሎ መጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤት የመጀመሪያ ዳይሬክተር እትዬ እናጉ ደሴ፣

👉የኢትዮጵያ ገነት ቤ/ክ አገልጋይ እና የዴቦራ የሴቶች አገልግሎት መስራች ወ/ዊ መዓዛ በቀለ፣

👉የኒው ላይፍ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል መስራች ሲ/ር ይርገዱ ሀብቴ ናቸው።
#ሙሉቀን_መለሰን_ወደጌታ_ያመጡት_ሰው....

እኝህ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ሐዋሪያው ዳንኤል መኮነን ይባላሉ፡፡

በ1960ዎቹ እና በ70ዎቹ እጅግ አስገራሚ ነገር ጌታ ገልጦባቸዋል፡፡

ሽባ ሲተረተር፣ እብዶች ሲፈወሱ፣ አይድንም የተባለ በሽታ ሲድን፣ የሚታዮ የሚጨበጡ የሚዳሰሱ ተአምራቶች ሲሆኑ ብዙ ሰዎችም ጌታን ሲቀበሉ ነበር፡፡

ካሜራ ያልነበረበት ዘመን ሆኖ እንጅ እውነተኛው ሪቫይቫል በምድራችን የተገለጠበት ጊዜ ነበር፡፡

በጊዜው ፍላሚንጎ አካባቢ የነበረችውን መሰረተክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሚያስታውሳት ሁሉ ይሄንን እውነት ያውቀዋል፡፡

ጊዜው የደርግ መንግስት ቤተክርስቲያን ላይ ስደት ያወጀበት ፣ የወንጌላውያን ቸርቾች እየተዘጉ ያሉበት አስጨናቂ ጊዜ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን ታማኙ እግዚአብሔር በልጆቹ እያለፈ ብዙዎቹን ያሳርፍ፣ ብዙዎችን ይፈታ ነበር፡፡

በዛን ዘመን በእሳቸው እጅ ወደጌታ ከመጡ ብዙ ሰዎች መሀል በትናንትናው ዕለት ወደጌታ የሄደው የቀድሞው ታዋቂ ዘፋኝ የአሁኑ ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ይገኛል።

ዳንኤል መኮነን መድረክ ላይ እየሰበኩ እኔ ኢየሱስን አገኘሁት እስከመጨረሻው አለቀውም ብዬ ወሰንኩ ይላል።

ሙሉቀን....

ክርስቲያን ቲዩን እንደከተበዉ .. 🙏🙏🙏
#እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏

ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
ሮሜ 12:9

#FBI #church (ፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል #ቤተክርስቲያን) በአንድ #አመት ውስጥ #በአዲስ አበባ በሁለት ክፍለ ከተሞች የአምስት አቅም የሌላቸውን ቤተሰቦች #ቤት ሰርተን አስረክበናል።

የረዳን #እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው::
ኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች ያሏቸው ወላጆች ከቤታቸው ሳይወጡ እስከ ሁለት እና ሶስት አመታት ይቆያሉ። እነዚህ ልጆች ግን አስፈላጊውን ክትትልና እንክብካቤ ከተደረገላቸው እንደማንኛውም ልጅ ትክክለኛ እድገት ማደግ እና ምርታማ ዜጋ መሆን እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ቻምፒየንስ አካዳሚ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሄደ። ትምህርት ቤቱ ለልዩ ፍላጎት ልጆች ልዩ የትምህርት ክፍሎችን በማዘጋጀት፣ በአዲሰ አበባ ከተማ አገልግሎትን እየሰጥ ይገኛል።

አካዳሚው ይሄንን የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር ሲያዘጋጅ ይህ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው።
በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሩ፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች መዝሙሮች፣ እንቆቅልሽ፣ ድራማ እና ሌሎችም የመድረክ ላይ ዝግጅቶች አቅርበዋል። ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች ወላጆችና በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ አዋቂዎችም ልምድ አካፍለዋል።

የመርሃ ግብሩ አዘጋጅ መዓዛ መንክር፣ በክርስቲያኖች ዘንድ ኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ልጆች እንደ መንፈስ እና እርግማን የመቁጠር የተሳሳተ ግንዛቤ አለ፣ ይሄንንም ወደ ባለሙያ በመምጣትና በማማከር የልጆችን ጊዜ መቆጠብና ቀድመው ክትትል በማድረግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ብለዋል።

ለክርስቲያን ዜና ሃሳባቸውን የሰጡ ወላጆች፣ ምንም እንኳን በኦቲዝም ጥላ ስር ያለ ልጅ ማሳደግ ከባድ ቢሆንም፣ በቂ ክትትል እና እንክብካቤ ሲደረግላቸው ልጆቻችንን ይበልጥ እንድንወዳቸው እና ሁኔታቸውን የሚመስል እንክብካቤ እያደረጉ ሁኔታውን ማሸነፍ መቻላቸውን ገልጸዋል።

መዓዛ መንክር “ሁሉም በአንድ” የሚል ስለ ኦቲዝም እና ሁኔታው የሚያስረዳ መጽሃፍ ጽፋለች።

በአለማችን ላይ ድከሚወለዱ 100 ህጻናት አንዱ በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖር መሆኑን WHO መረጃ ያሳያል።
ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በአገልግሎት ላይ ሳሉ ጥቃት ተፈፀመባቸው

በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በሚዘዋወር ስብከታቸው የሚታወቁት ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በአገልግሎት ላይ ሳሉ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተገለጸ !

በአሦርያውያን ቤተ ክርስቲያን የአውስትራሊያ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በእንግሊዝኛ እና ዐረብኛ ቋንቋዎች በሚያስተላልፉት ስብከት የሚታወቁ ሲሆን በሲድኒ በሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ሳሉ በአንድ ግለሰብ አማካይነት በስለት መወጋታቸው ተገልጿል።

የኒው ሳውዝ ዌልስ ፖሊስም ጥቃቱን የፈፀመውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተናግሯል። የኒው ሳውዝ ዌልስ የአምቡላንስ አገልግሎት በዕለቱ ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት አራት ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።

ሊቀ ጳጳሱ የሕክምና እርዳታ ተደርጎላቸው በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

በዕለቱ በሠላሳዎቹ ውስጥ ከሚገኝ ወጣት በተጨማሪ በከባድ ሁኔታ ወደ ሆስፒታል የተወሰደው በሀምሳዎቹ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው መኖሩንና በርካታ ቦታዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ለመገንዘብ ተችሏል።

ጥቃቱን የሚያሳየው ቪዲዬ >>>>> https://vm.tiktok.com/ZMMCA7PVT/
#የወንጌል ዘመቻ ሊካሄድ ነዉ።

ጋፕስ አለም አቀፍ አገልግሎት
አንጾኪያ የወንጌል እንቅስቃሴ

ጋፕስ ያለፉትን 14 ዓመታት የአገልጋዮችን የኑሮ ክፍተት መሙላት፡ የመንፈሳዊ ክፍተት መሙላት (ማጎልበት፡ ማስተማር) ላይ ሲሰራ ቆይቷል።

አንጾኪያ የወንጌል እንቅስቃሴ የ10 ቀናት የወንጌል ዘመቻ በነገው እለት ጀምሮ ከሚያዝያ 9-19 ድረስ ይካሄዳል።

ዘመቻው፡ የቡና #ሻይ ሰዓትን ለወንጌል፡ ሙስሊም ኢቫንጀሊዝም፡ የደም ልገሳ፡ የጎዳና ወንጌል፡ #አንድ #ሰው ለኢየሱስ፡ ማህበራዊ ሚድያን ከወንጌል፡ አርትን ለወንጌል፡ በመርዳት ወንጌል መስበክ፡ ሙዚቃን ለወንጌል፡ የርህራሄ አገልግሎት በዘመቻው በየእለቱ የሚሰሩ ስራዎች ናቸው።

የጋፕስ ሚኒስትሪ መስራችና መሪ መጋቢ ዳንኤል ዋለልኝ ሁሉም ሰው የተልዕኮ ሰራተኛ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡ በእነዚህ 10 ቀናት ሁሉም #ክርስቲያን አንጾኪያ በሚያደርገው የወንጌል ዘመቻ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የክርስቲያን መገናኛ ብዙሃንም በዚህ የወንጌል ዘመቻ በትልቅ ተሳትፎ እንዲሰራ፡ የክርስቲያን ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዘሪሁን ግርማ ጥሪ አቅርበዋል።

አንጾኪያ ሙቭመንት #አዲስ የወንጌል ተኮር አገልግሎት ነው። አላማው በሐዋ ስራ 11 እንደተገለጸው፡ የአንጾኪያ ቤ/ክ የወንጌል አካሄድ መድገም ነው።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና መግለጫውን በስፍራዉ በመገኘት አሰናዳንላችሁ።
#አስደሳች #ዜና ካህን #የክርስቲያን ባዛር ሊደረግ ነው።

በመልህቅ ፕሮዳክሽን እና ኢቨንት አዘጋጅነት "ካህን" የተሰኘ እና ጀማሪ እና መካከለኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ #ክርስቲያን ነጋዴዎች የሚሳተፉበት የክርስቲያን ባዛር ሊካሄድ ነው።

ሚያዝያ 12/2016ዓ.ም ቅዳሜ በሚደረገው ፕሮግራም ላይ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፤ ታዋቂ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፤ ወጣት እና አንጋፋ ዘማሪዎች በክብር እንግድነት ተገኝተው በድምቀት እንደሚከፍቱት አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።

በመረሃ ግብሩ የክርስቲያን ባዛር የአምልኮ #ጊዜ የተለያዩ ጨዋታዎች የሚዲያ ሽፋን እንዲሁም ለክርስቲያን ቲክቶከሮች ማበረታቻ የሚሰጥበት ጊዜ እንደሚኖር ታውቋል።

#ቦታ ብሔራዊ ትያትርን ተሻግሮ በከተማና ልማት አዳራሽ ከማለዳው 2:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 2:00ሰዓት ይከወናል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። ይጎብኙ ፤ ይሸምቱ ፤ አብረውን ያምልኩ።
ሕብረቱ በአድዋ ሙዝየም ፕሮግራም ሊያካሂድ ነዉ።

ፓስተር ጻድቁ አብዶ አድዋ 00 ስለሚካሄደው ስብሰባ መግለጫ ሰጡ!

የኢትዮጵያ ወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ለ5300 የቤ/ክ መሪዎች ከሚያዝያ15-17 በአድዋ 00 ሙዚየም አዳራሽ ውስጥ ነው ስልጠናው የሚሰጠው።

ስልጠናው "የወንጌል ተልዕኮና የእርቅ መንገድ ለኢትዮጵያ ቤ/ክ" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

ሮሜ 14ን መሰረት አድርጎ፡ ሰላምና እርቅ፡ ወንጌል ተልዕኮ፡ መንፈሳዊ ስምረት እና ጽኑ አመራርነት ላይ ትኩረት ያደርጋል ብለዋል የህብረቱ ስነ መለኮት መምሪያ ሃላፊ ፓስተር ደረጀ።

የስልጠናው ወጪ ከአባል ቤተ እምነት እና ሚኒስትሪዎች በተገኘ ድጋፍ ነው የተሸፈነው። በስፍራው ምዝገባ ያደረጉ ሰዎች ብቻ መገኘት የሚችሉ መሆኑ በመግለጫ ተነስቷል።

ህብረቱ በቀጣይ 10 ዓመታት መንፈሳዊ ተሃድሶ፡ መንፈሳዊ መነቃቃትና እርቅና ተሃድሶ የትኩረት አቅጣጫዎቹ ናቸው።

ከዚህ ቀደም ህብረቱ መሰል ስልጠና በኤልያና ሆቴልና ሚሊኒየም አዳራሽ መሰጠቱ ይታወሳል።
#አፍሪካ

አፍሪካ ባለፉት 150 አመታት በርካታ ክርስቲያናት ያሉባት አህጉር ሆናለች።

በ1900 #ላይ በአለም ካለው #ክርስቲያን 82 በመቶው፣ በሰሜን የአለም ክፍል፣ አውሮፓ እና #አሜሪካ ይገኝ ነበረ። በተቃራኒው ደቡባዊ የአለም ክፍል አፍሪካ፣ እስያና ላቲን አሜሪካ ደግሞ 18 በመቶ ብቻ ነበረ።

#አንድ #መቶ አመታትን #ወደ ፊት፣ ሰሜኑ አለም 33 በመቶው #ብቻ ክርስቲያን ሲሆን፣ ደቡቡ የአለም ክፍል ደግሞ 67 በመቶ ክርስቲያን ነው።

በጋና አክራ፣ በተካሄደ አለም አቀፍ የክርስቲያኖች ፎረም፣ በአለም ላይ የክርስትና ህዝብ ነክ ቁጥር ትልቅ ለውጥ ማሳየቱ ተነስቷል። ከኤፕሪል 16-20 በነበረው በዚህ ፎረም ከ60 የተለያዩ ሃገራት የተወጣጡ ከ240 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በዚህ ለውጥ ውስጥ ሴቶች ያላቸው ሚና እጅግ ታላቅ ነው ተብሏል። ወደፊት በተቀመጠ ትንበያ መሰረት ደግሞ በ2050፣ 77 በመቶ ክርስቲያኖች በደቡቡ የአለም ክፍል የሚኖሩ ይሆናል።

እነዚህ የአሃዝ ለውጦችና ትንበያዎች ወደፊት የክርስትና ማዕከል የትኛው የአለም ክፍል እንደሚሆን ያሳያል ተብሏል።

ለአብነት በአውሮፓና አሜሪካ የክርስትና ቁጥር በፍጥነት እየቀነሰ ሲሆን፣ በተቃራኒው በአፍሪካና እስያ ደግሞ በፍጥነት እያደገ
#ሬማ በድምቀት #ተመረቀ

ለዝማሬ አገልግሎት ከፍተኛ አሶተዋፅኦ የሚሰጥ ሬማ ሪከርዲንግ ስቱዲዮ ሚያዚያ 12 ቀን 2016ዓ/ም ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ።

የስቱዲዮዉ ባለቤት ሙዚቀኛ ዳዊት ወርቁ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ለረዥም አመታት ያገለገለ #ወጣት አገልጋይ ሲሆን ሬማ ሪከርዲንግ ስቱዲዮ ለትርፍ ያልተቋቋመ እና በዋነኝነት ተማሪዎችን እና የዝማሬ ፀጋ ያላቸዉን ለማገልገል የተዘጋጀ መሆኑን ገልፃል።

በምረቃ ስነስረአቱ ላይ ስቱዲዮዉን በፀሎት የመረቁት አፖስትል ብስራት ብዙአየን(ጃፒ) “አሁንም ቤተክርስቲያን ለሙዚቀኞች ትኩረት ልትሰጥ ይገባል የቤተክርስቲያን ሙዚቃ የአለምን ሙዚቃ መዋጥ አለበት” ሲሉ ተናግረዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለወንድማችን ሙዚቀኛ ዳዊት የተሰማን ደስታ እንገልፃለን።