አትሮኖስ
223K subscribers
103 photos
3 videos
41 files
304 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

..በህይወቷ እንዲህ አይነት ድንዛዜ ውስጥ ገብታ አታውቅም...የአባቷን  የሙት አመት መታሰቢያ ቀን መርሳት ማለት ..በቃ እያበቃላት መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ያለፉትን ስድስት አመታት እሷ ነበረች  ቀድማ  ለእንጀራ  እናቷ የምታስታውሳትና ለድግስ የሚያስፈልገውን ነገር ቀድማ የምታሟላው።ሳምንት ሲቀረው ጓዟን ጠቅልላ ወደአሰላ ትሄዳለች።የአባቷን ሀውልት ታሳድሳለች..አካባቢውን ታፀዳለች..በሀውልቱ ላይ ደርቀው የከሰሙ አበቦችን አስወግዳ በምትካቸው አዲስ ትተክላለች..ያሉትንም ውሀ  ታጠጣለች...ቤት ውስጥ በድግሱ የእንጀራ እናቷን ትረዳለች...በዕለቱ ታዲያ አንድም ችግረኛና የኔ ቢጤ በከተማው አይቀርም፤ ቀኑን ሙሉ ወደእነሡ ቤት ሲጓዙና ከድግሱ በልተው ወደቤት ይዘው የሚሄዱትን በፌስታል ተቋጥሮላቸው የሞተውንም ነፍስ ይማር ብለው እነሱንም መርቀው ይሄዳሉ።ይሄ መታሰቢያ ባለፉት ስድስት አመታት በጠቅላላው በአሰላ ከተማ የታወቀ ነው። እሷ ግን ይሄው የዘንድሮውን ረሳችው፡፡ከአይኖቿ የሚንጠባጠበውን እንባ እያበሰች "አባዬ በጣም ይቅርታ፡፡›› አለች፡፡

በዚህ ጊዜ ቱሉ ዲምቱ የክፍያ ጣቢያ ደርሳ የክፍያ ትኬት ለመቀበል መኪናዋን አቁማ ነበር።ታናሽ ወንድሟን ካወራች በኃላ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም።ወደቤቷ ሄዳ እንኳን ቅያሪ ልብስ ለመያዝ አልሞከረችም።ጭራሽ በሀሳቧም አልመጣ፡፡ቀጥታ መኪናዋን አዙራ ወደአሰላ መሄድ ብቻ ነበር የታያት፤እያደረገች ያለውም ያንን ነው።የቤታቸው የውጭ በራፍ ጋር የመኪናዋን አፍንጫ አስጠግታ የመኪናዋን ክላክስ ስታስጓራ አስር ሰዓት  ተኩል  ሆኖ  ነበር። ከሰፈሩ  በግርማ  ሞገሡ  አንደኛ የሆነውን ፊት ለፊቷ የሚታያትን የግንብ አጥር እና ፍረንች ዶር ያሰራችው እሷ ነበረች...አጥሩን ብቻ ሳይሆን ከድሮ ቤታቸው ማለት እትብቷ ከተቀበረበት እና ካደገችበት ቤት ፊት ለፊት ያለውን ቪላ ቤት ያሰራችው እሷ ነች።ግን ይህን ሁሉ ያደረገችው ውድ አባቷ ከሞተ በኋላ ነው።በህይወት እያለ የሚወደውንና መላ ህይወቱን የለፋበትን ግቢ እንዲህ አሳምራውና ቀይራው ቢያይላት ኖሮ እንዴት ይደሰት እንደነበረ ትገምትና የብስጭት እንባዋን  ትዘራለች።ሁሌ ስለእንደዚህ አይነት ጉዳይ አንስተው ከስንዱ ጋር ሲያወሩ"አሁንም  እኮ መንፈሱ ያይሻል...ለእኔና ለወንድምሽ በምታረጊው ነገር ባለበት ሆኖ ይመርቅሻል..ልክ በህይወት እያለ ይኮራብሽ እንደነበረው  አሁንም  ይኮራብሻል..››እያለች ልታፅናናትና ከገባችበት ሀዘን መንጭቃ ልታወጣት  ትሞክራለች።ግን ይህ አይነቱ  የእንጀራ እናቷ የማፅናኛ ንግግር እሷን ይበልጥ ጥልቅ ወደሆነው ሀዘን ውስጥ ነው ጎትቶ የሚሸጉጣት

‹‹አባቴ ባለበት ሆኖ እኔን የሚያየኝ ከሆነማ በጣም ነው የሚያፍርብኝ...በእውነት ይህቺ ልጅ እኔ ያሳደኳት ከአብራኬ የወጣች ልጅ ነች ?››ብሎ መጠየቁ አይቀርም...ምክንያቱም በትክክልም ባለበት ሆኖ ስራዬን የሚያይ ከሆነ ቤቱን ማሳመሬን ብቻ አይደለም የሚያየው..ሚስቱን እና ልጁን መንከባከቤንና መርዳቴን ብቻ አይደለም የሚያየው አመት እየጠበቅኩ በስሙ የአሰላን ድሆች ማብላቴን ብቻ አይደለም የሚያየው...እርግጥ እነዚህን ስራዎቼን ባየ ቁጥር ፈገግ ሊል ይችል ይሆናል፡፡ግን ደግሞ በየዕለቱ በስራ  ህይወቴ  የማሳልፈውን ነገሮች ካየስ..?.በእየዕለት ህይወቴ የሆንኩትንና እየሆንኩ ያለሁትን የሚያይ ከሆነስ..?ልጁ አጨበርባሪ እንደሆነች ሲያይስ.?ልጁ እልል ያለች ፕሮፌሽናል ሸርሙጣ መሆኗን ሲያይስ? ከዛም  አልፎ  ገዳይና  ቂመኛ  መሆኗን ሲያይስ?››እኚህንና መሠል ነገሮችን በውስጧ እያሰበች ሽምቅቅ ትላለች።አባቷ በሄደበት በዛው እንዲመቸውና ፊቱን ወደኃላ ዞሮ እንዳያያት ዘወትር ትፀልያለች።አዎ አባቷም  ሆነ  ሌሎች የሚወዷት ሰዎች ከዛሬ አስር አመት በፊት የነበረችውን ሳባን ብቻ አውቀው በዛ ትዝታ እንዲኖሩ እንጂ ካዛ ወዲህ እንደ አዲስ በውስጧ በቅላ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረቻትን አውሬዋን ሳባን እንዲያውቁ ፈፅሞ አትፈልግም...

የአሁኗን ሳባ ከእነሱ ለመደበቅ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም።
በሀሳብ ጭልጥ ካለችበት የበራፍ መከፈት ነው ያባነናት፡፡ራጂ ነበር ..የከፈተላት።መኪናዋ አዲስ ስለሆነች አይቷት አያውቅም።ማንነቷን ስላለየ  ወጣና ቀረባት፤እህቱ መሆኗን ሲያውቅ እየፈነጠዘ ሰላምም ሳይላት  ወደውስጥ ሮጠ.‹‹..እናቴ ማን እንደመጣ እይ ? እናቴ አላልኩሽም እህቴ  መጣች...እህቴ መጣች" ደስታውንና ፈንጠዝያውን ስታይ ውስጧ ርብሽብሽ አለባት፡፡
‹‹እንደዚህ የሚንሰፈሰፉልኝ ቤተሠቦች እያሉኝ ለምንድነው ብቸኝነት ውስጤን የሚከታትፈው? ›› ስትል እያሠበች ከገቢናው ከፍታ ወረደችና ወንድሟ  ክፍት ጥሎት በሄደው ትንሹ በር ገብታ እራሷ የመኪናውን መግቢያ በራፍ ከፈተችና መኪናዋን ወደ ግቢ ውስጥ አስገብታ ገና በቅጡ ሳታቆም ስንዱ ልጇን አስከትላ እጇን እንደ ክንፍ እያርገፈገፈች ስትመጣ አየቻትና ፈጠን ብላ  መኪናዋን በማቆም ወረደችና… ወደእሷ ተንደረደረች፡

አይን  ለአይን  ሳይተያዩ ገና ሁለት ወርም በቅጡ ያልደፈነ ቢሆንም አሁን በሰላምታ ተቃቅፈው ሲላቀሱ ላያቸው ባለፈው ሁለት አመት ጭራሽ ያልተገናኙ ነው የሚመስለው፡፡

‹‹ለመሆኑ.አለሽ…?ምነው.ከሳሽ?››ፊቷን.እየዳበሰች.በመንሰፍሰፍ.ጠየቀቻት…ስንዱ የሳባ እኩያ ብትሆንም አባቷን በማግባቷና  በዛም  ምክንያት እናቷ መሆን በመቻሏ  ሁሌ  ንግግራቸው የሀያ አመት ልዩነት በመሀከላቸው ያለ ነው የሚመስለው፡፡

ቤት እንደገባች ምግብ ተሰርቶ በልታ ቡና ተፈልቶላት ጠጥታ  ለነገው  ድግስ የሰፈር ሰው ሁሉ ቤታቸው ስራ ላይ  ስለነበረ  እነሱን  ተቀላቅላ  ማገዝ ብትፈልግም ራስ ምታቷ ስለተቀሰቀሰባትና ከሰው ተቀላቅላ ሆይ ሆይታ ውስጥ መሳተፉን ስላልቻለች በስንዱ ገፋፊነት እሷ መኝታ  ቤት  ገብታ እንድትተኛ አድርጋት ወንድሟም እየመጣ እንዳይረብሻት አስጠንቅቃው በራፉን ከውጭ ዘገታባት ወደስራዋ ሄደች፡፡

ሳባም የድሮ የአባቷ መኝታ  ክፍል  አባቷ ይተኛበት የነበረ አልጋ ላይ ወጥታ ኩርምት ብላ ተኛች የተወሰነ  ድካም  ቢኖርባትም እንቅልፍ ሊወስዳት ግን አልቻለም፡፡እስከአሁን ሁለት ጊዜ በዶክተሩ የታዘዘላትን ለሳምንት ያህል በተከታታይ ስትወሰደው የነበረውን መድሀኒት መውሰድ ነበረባት..ጥዋት ለህክምና ብላ ከቤት እንደወጣች ስላልተመለሰች አልያዘችውም ዛሬ የታዘዘላትንም ተጨማሪ መድሀኒት  ወደፋርማሲ  ጎራ  በማለት  ልትገዛ አልቻለችም..ጭራሽ ትዝም አላላት፡፡

‹‹የራሱ ጉዳይ አለችና ››ወደሀሳቧ ተመለሰች፡፡
እዚህ ቤት መምጣት .ከዛም በላይ እዚህ ክፍል መግባት… ከዛም በላይ  እዚህ አልጋ ላይ ተኝቶ ስለአባቷ  ማሰብ  አንኳን  አሁን  እንደዚህ  አእምሮዋ  በጭንቀት እና በድባቴ ምስቅልቅል ባለበት ጊዜ ይቅርና በፊትም ራሷን መግዛትና ስሜቷን ማረቅ በምትችል ጊዜ በጣም ነበር የሚረብሻት…በጣም ነበር ሀዘን ውስጥ የሚጨምራት፡፡ይሄ ቤት የተወለደችበት ነው፡፡እናቷ የሞተችው እሷ ከተወለደች ከአንድ አመት በኃላ ነበር፡፡አዎ  የአንድ  አመት  የልደት  በዓሏ  ሊከበርላት  አንድ ቀን በቀረበት ጊዜ ነው፡እናትዬው ከመሞቷ በፊት ለእሷ የልደት ክብረበዓል የሚሆኑ ሁሉንም ዝግጅት አሰናድታ ጨርሳ ነበር.በድንገተኛ በሽታ ማታ ሁለት ሰዓት አመማት..ወዲያው አፋፍሰው አሰላ ሆስፒታል አስገቧት…አምስት ሰዓት ህይወቷ አለፈ፡፡ ከዛ አባትዬው ለብቻው ሆኖ ነጭ ላቡን ጠብ በማድረግ ምንም እንዳይጎልባት አድርጎ አሳደጋት፡፡ታዲያ ሁል  ጊዜ  የእሷ  ልደት 
​​ሲደርስ  አባትዬው ፊት ላይ የሚፈራረቀው ስሜት አሁንም ድረስ ስታስበው ይዘገንናታል.በዚህ የሚወዳት ብቸኛ ልጁ የተወለደችበት የህይወቱ በጣም አስደሳቹ ቀን ነው.በሌላ ጎኑ ደግሞ የልቡ ሰው የነበረችው የልጅነት ፍቅሩና የሚወዳት ሚስቱን የተቀበረችበት ቀን ነው ይሄ ስሜት ውድ አባቷን እስከ እለተ  ሞቱ  ድረስ በተፈራራቂ ስሜት ሲያንገላታውና ሲፈታተነው  የኖረ  የህይወቱ አንዱ ክፍል ነበር፡፡
አባቷ እሷ አድጋ ትምህርት ቤት ገብታ ተምራ፤ ትምህርቷን ጨርሳ ዩኒቨርሲቲ እስክትገባ ድረስ ሚስት አላገባም ነበር..ጭራሽ  በህይወት  ዘመኑ  ሙሉ የማግባትም እቅድ የለውም ነበር..በመጀመሪያ እንደዛ ያደረገው ለልጄ የእንጀራ እናት አላመጣባትም በሚል እሳቤ ቢሆንም ዘመናት እያለፉ ሲመጡ ደግሞ ከነጭራሹ ዳግመኛ ማግባት አያስፈልገኝም ብሎ ድምዳሜ ላይ ደረሰ፡፡ ግን ያንን ውሳኔውን ሽሮ በተአምራዊ ሁኔታ ሊያገባ ቻለ፡ለዛውም የገዛ የልብ ጓደኛዋንና የእድሜ እኩያዋን ስንዱን፡
ስንዱ ለሳባ እንዲሁ አባቷን ስላገባች ብቻ የእንጀራ እናቷ ትባል እንጂ ከዛ ይልቅ ጓደኝነቷ የበለጠ ትርጉም አለው፡ከታዳጊነት እድሜያቸው ጀምሮ አብረው ያደጉ በጣም የሚቀራረቡ በሁለት አመት ያህል ብቻ የሚበላለጡ የልብ ጓደኛሞች ነበር

ስንዱም ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ አሰላ ዙሪያ ካለ ገጠር መጥታ እነ ሳባ ሰፈር በመከራየት ትምህርት ስትጀምር እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከሳባ ጋር አንድ ክፍል ስለደረሳቸው ትምህርት ቤት አብሮ መሄድና አብሮ መምጣት ከዛም ሚስጥር መቀያየር ጀመሩ፤ ከዛም የልብ ጓደኛሞች ሆኑ፡የስንዱ ለደንቡ ያህል ቤት ትከራይ እንጂ ከትምርት ቤት ውጭ ያለውን አብዛኛውን ጊዜዋን የምታሳልፈው እነሳባ ቤት ሆነ፡፡አቶ በአምላክም በሂደት እየለመዷትና የልጃቸው ጓደኛ ከዛም አልፎ እንደእህት ስለሆነችላት ደስተኛ ሆኑ.እሷንም ልክ እንደልጃቸው ማየት ጀመሩ፡፡ለልጃቸው ልብስ ሲገዙ ለእሷም መግዛት፤ለልጃቸው መፅሀፍ ሲገዙ ለእሷም መግዛት ጀመሩ፡ሁለቱንም መልካም ስራ ሲሰሩ ማሞገስ  ሲያጠፉ  እኩል መቆጣት ከዛም አልፎ  እውቂያቸው ገጠር ወደሚኖሩት የስንዱ ቤተሰብ ድረስ ዘለቀ‹‹ሀይስኩል ስትገባ የቤት ኪራይ መክፈልስ ለምን አስፈለገ?››ተባለና ወደእነ ሳባ ቤት ተጠቃላ ገባች፡ልክ እንደቤቱ አንድ ልጅ የሳባን ክፍል እየተጋራች በመኖር አብረው እየተረዳዱና እያነበቡ በትምህርታቸው ቀጠሉ፡፡
አስራ ሁለተኛ ክፍል ማትሪክ ተቀበሉ፤ሳባ ጥሩ ዉጤት አምጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላትን እድል ስታገኝ ስንዱ አልተሳካላትም፡፡በዛን ወቅት ከቤተሰቦቿ በላይ ያዘነውና ያፅናኗት የሳባአባት አቶ በአምላክ ነበረ፡፡ምክንያቱም ስንዱ ከሳባም በላይ በትምህርቷ ጎበዝ እንደሆነች ነበር የሚረዳው፤እንዴት እንዲህ እንደተበላሸባት አልገባውም...ምን አልባት ከቤተሰብ ተነጥሎ መኖር ያመጣባት የስነ-ልቦና ጫና ይሆናል ሲሉ ደመደመ
ከዛ ቀኑ ሲደርስ እዛው  አሰላ  በግል  ኮሌጅ  እንድትማር  አሳምኗት  ልጁን ዩኒቨርሲቲ.ሊሸኝ.ሄደ፡አዲስ.አበባ. አድርሷት፤ መመዝገቧን አጠናቃና ..የዩኒቨርሲቲውን ዶርም ተረክባ መረጋጋቷን ካረጋገጡ በኋላ ወደአሰላ ሲመለስ መንገድ ላይ በተፈጠረ የመኪና ግጭት አደጋ ደረሰበትና በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተወሰደ.. በጣር ላይ  ሆኖ  ሲሰቃይ  ከጎኑ ማንም አልነበረም፡
በወቅቱ ስልኩንና ሌሎች እቃዎቹን የሰበሰበው ፖሊስ ቅድሚያ የደወለው  ስንዱ ስልክ ላይ ነበር…ምክንያቱም በመጨረሻ በስልኩ የተደወለው ለእሷ ነበር…የደወለላት ወደአሰላ እየመጣ መሆኑን ሊነግራት ነበር ግን ስልኩን ከዘጋ ከ25 ደቂቃ በኃላ ነበር አደጋው የደረሰው.እሷም ይመጣል ብላ ቤቱን አሰማምራና፤ ቆንጆ ምግብ ሰርታ፤ቡና አቀራረባና ቤቱን አጫጭሳ ስትጠብቅ ስለዘገየባት ስትጨነቅ ከ2ሰዓት በኃላ ተደውሎ ሲነግራት ዜናውን ማመን አቅቷት ራሷን ስታ ወደፊቷ ተዘርራ የጠረጴዛው ጠርዝ ጋር ተጋጭታ እስከመፈንከት ደርሳ ነበር
እና ከዛ አደጋ በአራት ወር አታካች ህክምና  ክትትል  በኃላ  የሳባ  አባት  አቶ በአምላክ ሁለት እግሩን አስቆርጦ በዊልቸር እየተገፋ ወደቋሚ  መኖሪያ  ቤቱ ከሁለት ልጆቹ ጋር ተመለሰ፡ሳባም በዛ አመት ትምህርቷን የምትቀጥልበት አእምሮም ሆነ ዝግጅነት ሰላልነበራት ዊዝድሮዋል ሞልታ ነበር ከስንዱ ጋር በመተጋገዝ አባቷን ስታስታምመው የቆየችው፡፡ስንዱም እዳዛው ኮሌጅ የመማሩን ፍላጎት ሙሉ  በሙሉ  ጥላ ሁለቱም እሱን መንከባከቡ ላይ አተኮሩ፡

ከዛ አመቱ አልቆ መስከረም ጠባ፡፡ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ሰዓት ሲደርስ ቤት ውስጥ ጭቅጭቅ ተፈጠረ፤ሳባ አባቴን እንዲህ  ባለ  ሁኔታ ጥዬ አልሄድም  ብላ አሻፈረኝ አለች
አቶ በአምላክ የሱ ህይወት ገና በጎልማሳነት ዕድሜው ላይ ባልታሰበ  አደጋ ስንክልክል ማለቱ ሳይበቃ የልጁ የወደፊት ህይወት ሲሰነካከል ቁጭ ብሎ መታዘብ አልቻለም የሆነ ነገር አድርጎ ልጁን ማሳመንና ወደዩኒቨርሲቲ ሄዳ ያቋረጠችውን ትምህርት እንድትቀጥል ማድረግ አማራጭ የሌለው ግዴታው እንደሆነ ተረዳ.. በወቅቱ.ሳባን ወደከተማ ላካትና ስንዱን አስጠርቶ ፊቱ አስቀምጦ ማዋራት ጀመረ

‹‹ምነው ጋሼ አመመህ እንዴ?››

‹አይ በጣም ደህና ነኝ ግን ልጄ አንድ ውለታ ልጠይቅሽ ነው››

‹‹ጋሼ አንተ አባቴ ነህ የሞተብኝ አባቴ  ምትክ  ነህ ሚቻል  ቢሆን  እግሬን ቆርጬ እሰጥህ ነበር.እና ምንም ነገር አድርጊልኝ በለኝ አደርግልሀለሁ፡›› አለችው.አቶ በአምላክ በስንዱ ንግግር ልቡ ተነካና አይኖቹ እንባ አቀረሩ፡፡ልጅቷ ከራሷ ቤተሰቦች በላይ እሱንና ልጁን እንዲህ አምርራ ለምን እንደምትወድ ግራ ይገባዋል፡እንደምንም ሰሜቱን ተቆጣጠረና ንግግሩን ቀጠለ
‹‹ልጄ እኔም ልክ እንደልጄ ነው የማይሽ የሳባ ህይወት እንደሚያሳስበኝ ያንቺም የነገ ህይወት ያሳስበኛል..ስለዚህ ሁለት ነገር እንድታደርጊልኝ እፈልጋለሁ››

‹‹ዝም ብለህ ንገረኝ.ምንና ምን?››አለችው ስንዱ የሚጠይቃትን ሁሉ ያለማቅማማት ለመፈፀም ለራሷም ጭምር ቃል በመግባት፡በመጀመሪያ ከትራሱ ስር ሁለት ሺ ብር መዘዘና እጇ ላይ አስቀምጠው
‹‹ምንድነው ጋሼ?››
‹‹ነገ ሄደሽ ዶክመንትሽን በመያዝ ኮሌጅ ለመማር ትመዘገቢያለሽ››

‹እንዴ ጋሼ ምን እያልክ ነው…?አሁን ያንተ ጤንነት እንጂ የእኔ ትምህርት ያሳስባል?ገና ልጅ እኮ ነኝ ቀስ ብዬ እማራለሁ..አሁን አንተን መንከባከብ ነው የምፈልገው፡፡ባይሆን ሁለታችንም ተባብረን ሳባ ወደአዲስ አበባ ሄዳ እንድትማር ማሳመን ነው የሚገባን፡››ስትል ነበር የመለሰችለት፡

‹‹እኔም እኮ ለዛ ነው አንቺ ለመማር በመመዝገብና ትምህርትሽን እየተማርሽ እኔንም እንደምትንከባከቢኝ በተግባር ብታሳያት ታምናለች የልጆቼ የወደፊት ህይወት እንዲስነካከል አልፈልግ.እንደዛ ከሆነ በቃ ለሁለተኛ ጊዜ እርባና ቢስ እንደሆንኩ ነው የሚሰማኝ››

‹‹ጋሼ እኔ ኮሌጅ ለመማር ስለተመዘገብኩ እሷ ልማር ብላ አትሄድም እንደውም በተቃራኒው አንቺ ትምህርት ቤት በምትሆኚበት  ሰዓት አባቴን ማን ይንከባበዋል ብላ በማሰብ ተቃራኒውን ነው የምታደርገው
‹እና ምን ይሻላል? ያንቺም ትምህርት የሚቀር አይደለም፡እንዴ ሰው መቅጠር እንችላለን…ሰራተኛ ከአሁኑ.ፈልጊ አዎ ያንን ንገሪያት››
‹‹ጋሼ እኔ የተሻለ ዘዴ አለኝ››ነበር ያለችው
‹‹ምን አይነት ዘዴ? ››በጉጉት ጠየቃት፡፡

💫ይቀጥላል💫
ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ..በህይወቷ እንዲህ አይነት ድንዛዜ ውስጥ ገብታ አታውቅም...የአባቷን  የሙት አመት መታሰቢያ ቀን መርሳት ማለት ..በቃ እያበቃላት መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ያለፉትን ስድስት አመታት እሷ ነበረች  ቀድማ  ለእንጀራ  እናቷ የምታስታውሳትና ለድግስ የሚያስፈልገውን ነገር ቀድማ የምታሟላው።ሳምንት ሲቀረው ጓዟን ጠቅልላ ወደአሰላ ትሄዳለች።የአባቷን…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰባት


ደራሲ-ዘሪሁንገመቹዋቤ


‹‹አሁን አልነግርህም...ግን ለወራት ያስብኩበት አንድ ነገር አለ፡፡››

‹‹እኮ ንገሪኛ?››

‹‹አይ መጀመሪያ ከእሷ ጋር ልነጋገር…ግን አንተ ምንም አታስብ እሷን በምንም ዘዴ ቢሆን በምንም አሳምናታለሁ..በእኔ ጣለው…ትሄዳለች፡፡››

‹‹አንቺስ?››

‹‹ጋሼ እኔ እዚሁ ነኝ…የግል ኮሌጆች ምዝገባቸው ለወራት የሚዘልቅ ነው…ጊዜ አለን…ለማንኛውም ብሩ አንተው ጋር ይቀመጥ..ልመዘገብ ስሄድ እወስደዋለሁ›› ብላ ነበር ብሩን መልሳለት የወጣች፡፡

ሳባ በደንብ ትዝ ይላታል..በዛን ቀን ማታ እራት ተበልቶ ቡና ተጠጥቶ እንዳለቀ የሚፈልገውን ነገር ለአባታቸው አቀራረቡና ተያይዘው ወደመኝታ ቤታቸው ሄዱ፡፡ክፍላቸውን ዘጋግተው አልጋቸው ላይ ወጡና ወሬ ጀመሩ፡፡

‹‹ሳቢ አርብ ነው ወይስ ሰኞ የምትሄጂው?››አለቻት ስንዱ

ሳባ ግራ በመጋባት‹‹የት ነው የምሄደው ?›ስትል መልሳ ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዲስ አበባ ነዋ….ምዝገባው እኮ ከአርብ እስከ ማክሰኞ ነው፡››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ?የምን ምዝገባ ነው?ዕድሜ ልኩን ወጥ እየወጠወጠና ልብሶቼን እያጠበ፤ንፍጤን እየጠረገና  ለሀጬን  እያበሰ  ያለእናት  ያሳደገኝን አባቴን እግር አልባ ሆኖ አልጋ ላይ ቀርቶ እያየሁ፤ እኔ  ገና  ለገና  ነገ  ባለድግሪ ለመሆን ብዬ ጥዬው የምሄድ ይመስልሻል…?እንደውም ስለትምህርት ሲጠራ እንዴት እንደሚቀፈኝ ብታውቂ ››
‹‹እንዴት ?ለምንድነው ትምህርት ሊቀፍሽ ሚችለው?›

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..?እንደአንቺ ማትሪክ ሳይመጣልኝ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ አባቴ ልሸኝሽ ብሎ በዛን ጊዜ  አዲስ  አበባ  ይሄድ  ነበር?.ባይሄድ  ደግሞ  ለዛ አደጋ ይጋለጥና እንደዛ ኩሩና ሀገር የማይበቃው  የነበረው  አባቴ  እንዲህ  ተቆራምዶ ቤት ይቀር ነበር…?››

‹‹ምን ነካሽ…..ያ የእግዚያብሄር ፍቃድ ነው፡፡ ደግሞ  አባታችን  በህይወት ስለተረፈልንና ዛሬም በእጆቹ እየዳበሰን ስለሆነ... ዛሬም በአንደበቱ እየመከረንና እየገሰፀን ስለሆነ ማመስገን ነው ያለብን፡፡ዛሬም ስለነጋችን እየተጨነቀና
መንገድ  እያሳየን  በመሆኑ  እድለኞች  ነን፡፡ከእሱ ጋር በመኪና ውስጥ የነበሩት ሰዎች እኮ ግማሹ ወዲያው ነው የሞቱት፡፡››

‹እሱስ  እውነትሽን  ነው…ተመስገን  ነው…አባቴን  ባጣ  ምን  ይዉጠኝ.ነበር?ግን አትልፊ…እኔ የትም አልሄድም፡፡››

‹‹ቆይ ጋሽ በአምላክ.. ለእኔም አባቴ እንደሆነ ታምኛለሽ?››

‹‹ምን ማለትሽ ነው…በጣም እንጂi አንቺ እኮ እህትና ወንድም ስለሌለኝ በውስጤ የነበረውን ቁጭትና ሀዘን ያጠፋሺልኝ ምርጥ እህቴ ነሽ››

‹‹ይሄን  በመስማቴ  ተደስቼያለሁ..ታዲያ  አሁን  ዩኒቨርሲቲ  ብትገቢ  እኔ.አንቺ እዚህ ሆነሽ ከምትንከባከቢው በታች ትንከባከበዋለች ብለሽ ታስቢያለሽ?››

‹‹በፍፁም… እንደውም እሱን በመንከባከብ አንቺ ከእኔ የተሻልሽ ነሽ፡፡››

‹‹እና ታዲያ በእኔ እምነት ይኑርሻ፡፡››

‹‹ባንቺ  እምነት  ሳይኖረኝ  ቀርቶ  እኮ  አይደለም፡፡አመታቱ  ረጅም.መሆናቸው አሳስቦኝ ነው..አራት አመት…››

‹‹አራት አመት ምን አላት? አርባ አመትስ ቢሆን?››

‹‹ምን ነካሽ አንቺም እኮ የራስሽ ህይወት አለሽ…ችላ ብለሽ ልታልፊው የማትችይው የስራ ዕድል ሊያጋጥምሽ ይችላል..?ልታፈቅሪ  ትችያለሽ…ባል ማግባትም ልትወስኚ ትችያለሽ…አንቺ ባትፈልጊ እንኳን ቤተሰቦችሽ ሊያስገድዱሽ ይችላሉ፡፡ያኔ እንዴት ሊሆን ነው…?ትምህርቴን ለሁለተኛ  ጊዜ መልሼ ላቋርጥ ነው…?፡፡የማልወጣውን ነገር መነካካት አልፈልግም፡፡ግድ የለም ይቅርብኝ፡፡እዚሁ የተዘጋውን የአባቴን ሱቅ ከፍቼ እሱን እየሰራው ብንከባከበው ይሻላል፡፡››

‹‹አይ እንደዛ ማደርገው እኔ ነኝ፡፡አንቺ ወደ ትምህርትሽ ነው የምትሄጂው፡፡ ብታፈቅሪስ ላለሽው ቆየሁኮ አፍቅሬያለሁ፡፡››
‹‹ባክሽ ቀልዱን አቁሚ፡፡››

‹‹እየቀለድኩ እኮ አይደለም ..እውነቴን ነው፡፡››

‹‹እንዴ አንቺ…?ከመቼ ጀምሮ...?ትራሷን ከፍ አደረገችና ከአንገቷ ቀና ብላ አፋጠጠችባት››
‹‹ቢያንስ ሶስት አመት…፡፡››

‹‹አንቺ ሶሰት  አመት  ሙሉ  አፍቅረሽ  ለእኔ  ሳትነግሪኝ..?እኔ  እኮ  በህልሜ ያናገረኝን ወንድ ማንነት ሳይቀር ነው የምነግርሽ፡፡››
‹‹እንደምታስቢው ለመናገር ቀላል አልነበረም፡፡››

‹‹…እውነትሽን ነው ቀላል አልነበረም….?››ሳባ ተበሳጨች… ከዛ በላይ ማውራት አልፈለገችም፡፡ትራሷን ወደታች አወረደችና ብርድ ልብሱን ተከናንባ ተኛች፡
‹‹እንዴ ጥለሺኝ እየተኛሽ ነው…?ማን ነው ያፈቀርሺው ብለሽ አትጠይቂኝም?››
‹‹ምን ሊያደርግልኝ… ሶስት አመት ሙሉ የደበቅሺኝን ዛሬ ብሰማው  ምን ይረባኛል… ?.እንደውም ከማያምነኝ ሰው ጋር መተኛት አልፈልግም፡፡›› ብላ ነበር መኝታዋን ለቃ በመውረድ ከላይ ያለውን አልጋ ልብስ ገፋ ስሊፐሯን ተጫምታ ከክፍሉ ለመውጣት ወደበራፍ መራመድ የጀመረች...ለመክፈት እጇን ወደ እጀታው ስትዘረጋ ከስንዱ አንደበት እጅግ አስደንጋጭ መንፈሰን የሚያርድና የሚያደነዝዝ ቃል ነበር የወጣው ፡፡

‹‹ያፈቀርኩት አባትሽን ነው፡፡››

በቆመችበት ደንዝዛ ለደቂቃዎች ቆመች...እንደምንም ፊቷን አዞረችና
‹‹አልሰማሁሽም››ነበር ያለቻት፡፡እውነታው ግን የተናገረችውን ሶስት ቃላት በትክክል ሰምታለች…ግን.አልገባትም.ወይም.ሊታመን የሚችል ዜና ሆኖ አላገኘችውም፡፡

‹‹አዎ ለዛ ነው ሶስት አመት መሉ ሳልነግርሽ በውስጤ አፍኜ የኖርኩት..አባትሽን ስላፈቀርኩ በራሴ አፍሬያለሁ፡፡››

‹‹ቀስ ብላ እግሮቿን እየጎተተች ወደውስጥ ተመለሰችና አልጋ ልብሱን እንደተከናነበች አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡በሰማችው ዜና ደስታ ይሰማት ወይስ ሀዘን ማወቅ አልቻለችም…..አባቷን እኩያዋ የሆነች ልጅ ለዛውም አብራት የምትኖር የገዛ ጓደኛዋ ስታፈቅረው ፡፡

‹‹እርግጠኛ ነሽ ግን?››

‹‹እስከ ዛሬ አመት ማለቴ ጋሼ አደጋ እስኪደርስበት ድረስ እርግጠኛ አልነበርኩም…እንዲሁ ውስጤ የተፈጠረ ቅዠት አድርጌ  በማሰብ ራሴን በመገሰፅ ነገሮችን አዳፍኜ መቀጠልን ነበር የወሰንኩት፡፡ጋሼ የተጎዳ  ጊዜ  ግን በተለይ ዜናውን ፖሊሶች ደውለው ሲነግሩኝ የተሰማኝ ስሜት፤የፈራሁት ፍርሀት፤ላፈቀርሽውና ህይወትሽን ሳይቀር ልትሰጪው ፍቃደኛ ከሆንሺለት ሰው ውጭ ለሌላ ሰው የሚሰማሽ እንዳልሆነ ገባኝ..እውነትም አፍቅሬዋለሁ ብዬ ሙሉ በሙሉ የደመደምኩት የዛኔ ነው››

በወቅቱ ሳባ ምንም ልትላት አልቻለችም….

‹‹ምነው አላመንሺኝም አይደል..?አልፈርድብሽም እኔ ለራሴ  የልቤን  ጩኸት አምኖ ለመቀበል አመታት ከወሰደብኝ አንቺ እንዴት እንዲህ በፍጥነት ትረጂዋለሽ ብዬ አስባለሁ?፡፡››

‹‹አይደለም እኮ …ማለት አባዬ ለአንቺም እንደአባትሽ ነው፤ለእሱ ካለሽ ክብርና መውደድ የተነሳ ምን አልባት ተምታቶብሽ እንዳይሆን ብዬ ነው እኮ…?›

‹‹ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር እኮ..ግን አይደለም..ጋሼ አባቴ ሳይሆን ባሌ እንዲሆን ነው የምፈልገው፡፡›

‹‹አባዬ እኮ 42 አመቱ ነው ፤ከአንቺ  በ22 ዓመት ይበልጣል፡፡››

‹‹አውቃለሁ… ግን ያ  ግድ አይሰጠኝም..››

‹‹እሺ አሁን ያለበት  ሁኔታስ…?››

‹‹እሱም  ጉዳዬ  አይደለም…እኔን የሚያስጨንቀኝ ብቸኛው ምክንያት አንቺ ስለነገሩ ምን ታስቢያለሸ ?የሚለው ነው…፡፡››

‹‹እኔ ደግሞ ምን?››
​​‹‹አባትሽን በማፍቀሬ የምትከፊና እንደከዳተኛ የምትቆጥሪኝ ከሆነ ውስጤ በጣም ነው የሚሰበረው…አባትሽን እንዳገባ የማትፈልጊ ከሆነ ዛሬውኑ ማወቅ እፈልጋለሁ…ከዛ ማንም ወደ ማያገኘኝ ቦታ ለዘላለም እጠፋለሁ….ከአባትሽ ሚነጥለኝ ብቸኛው ምክንያት ያንቺ ተቃውሞ ብቻ ነው….››

ሳባ እንባ በአይኖቿ ሞላ….ከተከናነበችው አልጋ  ልብስ  ውስጥ  እጆቿን አወጣችና ወደእሷ ተጠጋች፡፡አቀፈቻት…ጭምቅ አድርጋ አቀፈቻት፡፡

‹‹የእኔ ውድ እኔ እኮ በጣም ነው የምወድሽ….መቼም አንቺን ማጣት አልፈልግም…እኔ ይሄን ነገር ባይሆን ደስ ይለኛል…ምክንያቱም እኔ ለአንቺ የምመኝልሽ በጣም ትልቅ ነገር ነው….ታውቂያለሽ አባቴ ለእኔ ሁለነገሬ ነው.የአለም ጥሩ ነገር ሁሉ ተጠራርጎ ለእሱ  ቢሰጥ  ደስታውን  አልችልም፤ ቢሆንም አሁን ባለበት ሁኔታ እንክብካቤና እርዳታ የሚፈልግ ሰው ነው..እሱን አገባሽ ማለት ሙሉ ህይወትሽን ነው ለእሱ.መስዋዕት የምታደርጊው… መዝናኛ ቦታ ወገብሽን አቅፎ አያንሸራሽርሽም ….ከምትወልጂለት ልጅ ጋር ኳስ አይጫወትም…ሰርግ ቤት ስትጠሪ አብሮሽ ላይሄድ ይችላል…››

ስንዱም እንባዋን ከአይኗ እያበሰች ከእቅፏ ወጣችና  አይን  አይኗን  በስስትና በፍቅር አየተመለከተቻት‹‹እነዚህ የዘረዘርሻቸው ነገሮች ሁሉ ትርፍ ናቸው..ለእኔ.ዋናው ከእሱ ጋር አብሮነትን መጋራት ነው የምፈልገው…አብሮኝ  መኖሩንና አብሬው መኖሩን ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹በእውነት የሚገርም ነገር  ነው..እንዲህ  አይነት  በሚያደነዝዝ  ፍቅር  ውስጥ ያለሽ መሆንሽን ባለማወቄ በራሴ አፍሬያለሁ…ለመሆኑ ይህንን ጉዳይ አባቴ ሲሰማ ምን አለሽ?››
ስንዱ ደነገጠች‹‹እንዴ ምን ነካሽ  ?ጋሼ  ምንም  አያውቅም…..ለእሱ  ዛሬም  እኔ ልጁ ነኝ፡፡››

‹‹እርፍ….ታዲያ  እንዴት ልታደርጊ ነው…?››

‹‹እሱን ለእኔ ተይው…ዋናው ለእኔ  አስጨናቂው የአንቺን  ፍላጎት  ማወቅ ነው፡፡፡››

‹‹እኔማ አንቺን የመሰለች  እናት አግኝቼ ነው፡፡››

‹‹እንግዲያውን ሌላውን ለእኔ ተይና አንቺ ቀጥ ብለሽ ወደትምህርትሽ››

‹‹ከዛ ምን ልታደርጊ?››
‹‹እኔ ትክክለኛው ሰዓት እና አጋጣሚ ሳገኝ እነግረዋለሁ ...ከተሰማማ ደስ ይለኛል..እናት  አገኘሽ  ማለት  ነው...?ካልሆነም  ለእኔ  ችግር  የለውም.  ልጁ  እንደሆንኩ ለአንቺም  እህትሽ  እንደሆንኩ  እቀጥላለሁ ማለት  ነው….ለእኔ  ዋናው  ነገር እሱ በህይወት እስከአለ ድረስ አብሬው መኖሬ ነው..››

‹‹ይገርማል..››

‹‹ምኑ ነወ የሚገርመው?››

‹‹እኔም  እንደአንቺ  አይነት  ፍቅር  አንድ  ቀን  ይይዘኝ  ይሆን  ?ብዬ  አስቤ ነው የተገረምኩት፡›
‹‹ይሄ የእኔ እኮ ልክፍት ነው..ይቅርብሽ…አሁን በይ ከመንጋቱ በፊት እንተኛ››
ተቃቅፈው ተኙ…ከዛ በሶስተኛው ቀን ሳባ በተረጋጋ መንፈስና ሻንጣዋን  ሸክፋ አባቷን በሳቅና በለቅሶ ድብልቅ ሰሜት ተሰናብታና አደራዋን ሁሉ ለስንዱ ሰጥታ ወደ አዲስ አበባ ትምህርቷን ለመቀጠል ሄደች፡፡ስንዱም በአንድ አመት የጊዜ ሂደት አባቷን በከፍተኛ ጥረትና ትጋት አሳምና ማግባት  ቻለች  ፡፡አገር ጉድ እያለ በአመቱ ልጅ ወለደችለት፡፡ይሄው ያ  ልጅ  ዛሬ  12  ዓመት ጎረምሳና የክፉ ቀን አይን ማረፊያዋ ከአንጀቷ ፍቅፍቅ ብላ እንድትስቅ የማድረግ  ችሎታ  ያለው ብቸኛው ወንድሟ ሆነ፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁንገመቹዋቤ ‹‹አሁን አልነግርህም...ግን ለወራት ያስብኩበት አንድ ነገር አለ፡፡›› ‹‹እኮ ንገሪኛ?›› ‹‹አይ መጀመሪያ ከእሷ ጋር ልነጋገር…ግን አንተ ምንም አታስብ እሷን በምንም ዘዴ ቢሆን በምንም አሳምናታለሁ..በእኔ ጣለው…ትሄዳለች፡፡›› ‹‹አንቺስ?›› ‹‹ጋሼ እኔ እዚሁ ነኝ…የግል ኮሌጆች ምዝገባቸው ለወራት የሚዘልቅ ነው…ጊዜ…»
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ አራት

ብር፣ አምባር...ሰበረችልዎ!

ትንሸ ስረጋጋ እና አገሩን ስለምድ፣ እኔም ሰው ነኝና ስፈራ ስቼር አልፎ አልፎ ወደ እነዚያ መሸታ ቤቶች ጎራ ማለት ጀመርኩ፡፡ በሕይወት ዘመኔ ከእናቴ ጠላ ውጭ አልኮል መቀማመስ የጀመርኩት እዚያ ነበር፡፡ እንደ እኔ ሊሰደዱ ሞክረው ገንዘብ ያጠራቼው፤ ወይም በማይወጡት ሱስና ዕዳ የተዘፈቁ፤ ያቺን ለማሟላት ሴተኛ አዳሪ የሆኑ የበርካታ አገራት ሴቶች በመሸታ ቤቶቹ ውስጥ ነበሩ፡፡ የሚበዙት ተስፋ ቆርጠው እዚያው በሴተኛ አዳሪነት ሕይወታቼውን የሚገፉ ናቸው፡፡ ከብዛታቼው

የተነሳ አንድ ዓሣ- ዓሣ የሚሸት ጎስቋላ ወንድ ወደ ቡና ቤቶቹ ሲገባ እምስት - ስድስት ሴቶች ይከቡታል፡፡ እነዚያ በሌላው ዓለም ቢሆን እግራቼው ተስሞ ለጋብቻ የሚጠየቁ ቆነጃጅቶች እንዲሀ ሲሆኑ ማዬት፣ እስኪለምዱት አንዳች ግርምት ያጭራል። እኔም ይኼው ነበር የገጠመኝ፡፡ ሴቶች አንዳች አስማተኛ ፍጡራን ናቸው። በዚያ ሲኦል ውስጥ እንኳን ወንድነት፣ ሰው የመሆን፣ የመፈቀር ስሜት፣ እንዲሰማን ያደርጉናል፡፡ ለሕይወት እንድንሳሳ ያደርጉናል፡፡ የቆረጥናትን ተስፋ በሴቶች ፈገግታና የሽቶ ጠረን መልሰን እንቀጥላታለን፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነበር ዛናታ የምትባል ሴት ጋር የተዋወቅሁት፡፡ መጀመሪያ እንዳዬኋት ኢትዮጵያዊ መስላኝ ነበር፡፡ የቀይዳማ መልኳ፣ የሚዘናፈል ጸጉሯ እና በዚያ ሥራ ውስጥ ሆና እንኳን የሚያስታውቅበት ዓይን አፋርነት የኢትዮጵያ ሴቶች ዓይነት ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ እዚያ ቤት ስመላለስ ሴቶቹ አይተውኝ ምንም ጠብ እንደማይለኝ ስላወቁ ለብቻዬ ትተውኝ ነበር፡፡ የዚያን ቀን ግን ማፍጠጤ ጠርቷት መሰለኝ ፈገግ ብላ ወደተቀመጥኩበት መጣች፡፡ ለዚያ ሥራ በተለማመደችው የወንዶችን ስሜት የሚያነሳሳ አረማመድ ሰበር ሰካ ስትል ትልቅ መቀመጫዋና መካከለኛ ጡቶቿ የተለዬ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። በተለይ ግን ጥርሷ! እንደዚያ ዓይነት የጥርስ ንጣት የትም ዓይቼ አላውቅም፡፡ የማላውቀው አገር ልሳን በሚጫነው እንግሊዝኛ... “ምነው ብቻህን?'' አለችኝ፡፡ እንደ ቀልድ ፈገግ ብዬ “እግዚአብሔር_ከነፍጥረቱ ብቻዬን ተወኝ” አልኳት፡፡ አልሳቀችም፤ ዝም ብላ አዬችኝና ኮስተር እንዳለች በማላውቀው ቋንቋ የሆነ ነገር ተናገረች። ግራ መጋባቴን አውቃ በእንግሊዝኛ "እግዚአብሔር_እኔን ልኮልኻል የምትፈልገውን ተናገር" ብላ ባንዴ መኮሳተሯ ወደ ሳቅ ተቀዬረ፡፡ “ምንኛ ነው መጀመሪያ የተናገርሽው?'' “ፈረንሳይኛ፡፡”

“ትችያለሸ?” “ከአረብኛ ቀጥሎ አፌን የፈታሁበት ነው።” “አረብኛም ትናገሪያለሸ?!'' “እንደ ትልቅ ዕውቀት አትዬው፣ በሁሉም ቋንቋ አንድ የረባ ነገር ተናግሬበት አላውቅም!” ተሳሳቅን፡፡ ቢራ እንድትጠጣ ጋበዝኳት፤ አልኮል እንደማትጠጣ ነገረችኝ እና ለእኔ ቢራ፣ ለእርሷ ቀዝቃዛ የሎሚ ጭማቂ ይዛ መጣች፡፡ ከተፋፈገው ክፍል ወጥተን፣ ነፋሻው የቡና ቤቱ አሮጌ የእንጨት በረንዳ ላይ ተቀመጥን። ስትቀመጥ አያታለሁ፣ ቀሚሷን ሰብሰብ አድርጋ በሥርዓት ነበር የተቀመጠችው። ሁለታችንም ዝም ብለን ተቀመጥን፡፡ ጨለማ በዋጠው ውቂያኖስ ላይ አልፎ አልፎ ቀይ መብራቶች ቦግ እልም ይላሉ፤ የባሕር ላይ ድንበር ጠባቂ ጀልባዎች ናቸው: ከመራቃቸው የተነሳ ድምፃቼው የማይሰማ አውሮፕላኖች በጥቁሩ ሰማይ ላይ አብሪ ኮከብ መስለው ያልፋሉ። ዛናታ እንደ ዓመታት ፍቅረኛ ራሷን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ፣ በዝምታ ተቀምጣለች፡፡ ጠረኗ ደስ የሚል የሽቶ፣ የሎሚና የዚያ አገር ሜንት ሲጋራ ድብልቅ ጠረን ነበረው። በቀስታ አቅፌ ጸጉሯን መነካካት ጀመርኩ፣ ልቤ ደረቴን ቀዳ ልትወጣ ደርሳለች... ድንገት ቀና ብላ “ቤቴ ቅርብ ነው ከፈለግህ መሄድ እንችላለን” አለችኝ፡፡ በአክብሮት እንደማልፈልግ ነግሪያት ተሰነባብተን ወደ ዋሻዬ አመራሁ። ዞሬ ሳያት ቆማ እያዬችኝ ነበር። እስከዚያ ዕድሜዬ ሴት ጋር ሄጄ አላውቅም ነበርና ክፉኛ ፈርቼ ነበር፡፡ በዚያ ልክ ሴት ጋር ስጠጋጋም የመጀመሪያዬ ነበር። ከዚያች ምሽት በኋላ ወደዚያ መሸታ ቤት እግር አበዛሁ፡፡ ዛናታ ባዬችኝ ቁጥር እየተፍለቀለቀች ትመጣለች፤ ቢራዬን ይዠ የሎሚ ጭማቂዋን እየተጎነጨች እናወራለን፡፡ የሆነ ነገር ገብቷታል፤ እንደ እንስሳ በሚያደርጋቼው ወንዶች መኻል ሰው ሰው ሳልሸታት አልቀረሁም፡፡ የሰውነት ሽታ፣ ከሚቀረናው የዓሣ ሽታም በላይ የሰውን

ነፍስ ዘልቆ ይሰማል መሰለኝ!? ብቻ በየምሽቱ እየተገናኜን ወዳጅነታቸንም እየጠነከረ ሄደ፡፡ አንድ ማታ መጠጋጋታችን ወደ ድንገተኛ መሳሳም አለፈ፡፡ እጅግ ጥልቅና ረዥም መሳሳም ነበር። ሎሚ-ሎሚ የሚል መሳሳም። እናም በሚስለመለሙ ውብ ዓይኖቿ እያባበለች ወደ ቤቷ ስትጋብዘኝ እንቢ የማለት ወኔዬ ከዳኝ፡፡ የሴት ልጅ ሰውነት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የዚያን ሌሊት ተዋወቅሁ፡፡ “እኔ አላምንም የመጀመሪያህ ነው?'' አለች እየተፍለቀለቀች! ዝም ብዬ አዬኋት። “እንዳትዋሽ!'' አለች ሊፈነዳ ያሰፈሰፈ ሳቋ ፊቷ ላይ እንደተዘጋጁ፤ በአወንታ ራሲን ነቀነቅሁ፤ ከንፈሬን ስማኝ... አውቄ ነበር፤ _ አውቄ ነበር.... እያለች በሳቅ ተፍለቀለቀች። ድንገት ሳቋን አቁማ... “አገራችሁ ሴት የለም?'” አለችና የሚያምሩ ጥርሶቿ ብርሃናቼውን ረጩ፤ እንደ ተአምር አዬችኝ፡፡ ልክ እንደ ሕፃን ልጅ በዝምታ ጉንጯን ጉንጨ ላይ ለጥፋ ቆዬችና “ሲገርም” አለች ለራሷ፤ ምን እንደገረማት አልገባኝም፡፡ እናም ዛናታ ጋር ያበደ ፍቅር ውስጥ ገባሁ፡፡ አንድ እሷ ነበረች ሙሉ ከተማውን፣ ውሃውን፣ መንገዱን የሞላችው- ለእኔ፡፡ እሷ ጋር ስሆን በስደት አገር ውስጥ ለብቻዬ የተከለለ ሕጋዊ ደሴት ላይ ያረፍኩ መስሎ እስኪሰማኝ ሰላም እሆን ነበር፡፡ እቤቷ _ በሄድኩ ቁጥር ከእሷ እኩል ቤቷ ይገርመኛል፡፡ እግሬ ከኢትዬጵያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥርዓት የተደራጄ ቤት ውስጥ ስገባ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ የቤቷ ንጽህና ገረመኝ፡፡ የቤት ዕቃዎቹ ወደ ሆነ ሕይወት መለሱኝ፡፡ ትንሽ ሕያው ሙዚዬም ነገር። የምኖረው ሌሎች ዘጠኝ ስደተኞች ጋር በምጋራው ጠባብ አሮጌ ክፍል ውስጥ የተገኜውን ነገር እያነጠፍኩ ነበርና የተሰማኝ ስሜት ልዩ ነበር፡፡ የእኔን እንኳን መኖሪያ ከማለት መደበቂያ ዋሻ ማለት ይቀላል፡፡ ማንኪያ፣ ሹካ፣ መጥበሻና ብርጭቆ ዝም ብለው ቁስ አይደሉም። ከነመኖራቼውም ትዝ የማይሉን የቤት እቃዎች ሰውን ተከትለው ባረፈበት የሚረጉ፣ ሰውን በክብር ለማስተናገድ የተሰለፉ፣ ሕያው ቁሶች ናቸው፡፡ ቤት እንዲህ የሚናፈቅ ነገር ነው ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ የተደረደሩትን እቃዎች እያዬሁ ዕንባዬ በዓይኖቼ እንደሞላ ትዝ

ይለኛል።ይኼ እንዴት ሊገለጽ ይችላል!? ከአንድ ወር በኋላ ይመስለኛል፣ ዘናታ ጠቅልዬ ከእሷ ጋር እንድኖር ጠዬቀችኝ፤ አላንገራገርኩም!! ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ... ተማርኩ ሰለጠንኩ ብዬ “የአበሻ ወንዶች አምባ ገነን ባሕሪ የፈጠረው ተረት!” እያልኩ ያጣጣልኩት አባባል ነበር። ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ ሲሉ። የዚያችን ቀን ምሽት ገጠመኝ ባስታወስኩ ቁጥር ግን አባባሉ እንደ በዓል መድፍ አርባ ጊዜ ይጮኸብኛል። ዛናታ ቤት ጠቅልዬ የገባሁ ሰሞን ሁለታችንም ዓለምን ረሳን፤ ራሳችንን ረሳን፤ ስደተኝነታችንን ረሳን፤ ፖሊስ ጋር የአይጥና ድመት ድብብቆሸ እየተጫዎትን የምንኖር ምስኪኖች መሆናችንን ረሳን፤ ፍቅር _ ነፃነት ነው...
ፍቅር _ የባርነት ሰንሰለትን እንዳጠለቁ መደነስ ነው። ከምሠራበት ቦታ ዓሣ ይዤ ወደ አዲሷ ጎጆዬ ስገባ የሚሰማኝ የአባወራነት ስሜት ልዩ ነበር፡፡ የኔ ቆንጆ ዛናታ በረከሰ ሥራ ውስጥ የከበረ ነፍስ የነበራት ውብ ሚስት ነበረች። ሚስትነትን በቀለበትና በሰርግ ሳይሆን ከልብ በመነጨ ፍቅር መኖር ጀምራ ነበር። አብረን መኖር በጀመርን በወሩ ይመስለኛል፣ ክፍያዬን ከሦስት አሠሪዎቼ ተቀብዬ ወደምትሠራበት ቡና ቤት በኩራት አመራሁ፤ ስታዬኝ ተንደርድራ መጥታ እቅፌ ላይ ወደቀች፡፡ ወደተለመደው በረንዳችን ሄደን እንደተቀመጥን “ዛሬ ክፍያ ተቀብያለሁ” አልኩና የተቀበልኩትን ብር በሙሉ እጇ ላይ አስቀመጥኩላት። እዬሳቀች ታዬኛለች “እስኪ ዛሬ በነፃነት ሌላ ቦታ እንሂድ? የምታውቂው ቆንጆ ቦታ” ብዙ አላሰበችም እየተፍለቀለቀች “ውጭ ጠብቀኝ እንደወጣሁ ነግሪያቼው መጣሁ'' ብላኝ እየተፍለቀለቀች ሄደች። ስትመለስ በትልቅ የጨርቅ ዘንቢል ቢራ፣ ድፍን ሐብሃብ፣ የሎሚ ጭማቂ፣ የተጠበሱ ዓሣዎች ይዛ መጣች። ከብዷት ስለነበር ግራና ቀኝ በማንጠልጠያዎቹ ለሁለት ያዝነው። የዚያን ቀን ምሽት ተያይዘን በባሕሩ ዳርቻ የተሠራውን ዋና

መንገድ ወደ ግራ በመተው ወደ ሰፊው አሸዋማ የባሕር ዳርቻ አቀናን፡፡ መ74. ጨለም ያለና ሰዎችም ብዙ የማይጠቀሙበት ነበር። በሕሩ ዳርቻ ላይ ወዳሉ የጀልባ ላይ ጎጆዎች ነበር ለመሄድ ያሰብነው: እኔ ከምኖርባት ሰፈር ስወጣ የመጀመሪያ ነበር፤ ዘናታ ግን በተደጋጋሚ ትሄድባቸው ስለነበር መንገዱን የምትመራኝ እሷ ነበረች። ጀልባዎቹ በተለይ ለጥንዶች የሚዘጋጁ ሲሆኑ የራሳቼው ትንሽ መኝታ ቤት እና መጸዳጃ ቤት ያላቼው ተንሳፋፊ ጎጆዎች ነበሩ። በዋጋም ርካሽ ናቸው። ወደ እኩለ ሌሊት ስለነበር በመንገዳችን የሰው ዘር አልነበረም። ሁለታችንም ሕገወጥ ነዋሪዎች ነንና ይኼን ወደነዋል። በዚያ ሰዓት ፖሊሶች ሙሉ ትኩረታቼው ጠረፉ አካባቢ በሌሊት ድንበር በሚሻገሩ ስደተኞች ላይ ስለሚሆን አካባቢው ነፃ ይሆናል። ከሩቅ የሚብለጨለጨውን የጀልባዎቹን ብርሃን እያዬን፣ እያወራንና እየተሳሳቅን በየመኻሉም እየተሳሳምን ምድሩም ሰማዩም _ ጠቦን እንደ አገረገዥ በኩራት ስንጓዝ፤ ድንገት ከቀኝ በኩል ከተደረደሩት የዘንባባ ዛፎች ውስጥ የመኪና መብራት ቦግ ብሎ አካባቢውን በሰማያዊ ብርሃን አጥለቀለቀውና መልሶ ጠፋ። ሁለታችንም የጨው ዓምድ ሆነን ቀረን። ያንን መብራት ማንም ስደተኛ የሚያውቀው መብራት ነበር። ሕገወጥ የሰው ዝውውርና አደንዛዥ ዕፅ ተቆጣጣሪ ፖሊሶች መኪና መብራት ነው። ምልክቱ ቁሙ ነበር። ብዙዎች ከዚህ መብራት ማስጠንቀቂያ ለማምለጥ ሲሮጡ በጥይት ሩምታ ተገድለዋል። ማንም ወረቀት የሌለው ስደተኛ ለምን ገደላችሁ የሚላቸው የለም። ባለንበት ቀጥ ብለን ቆምን። ሁለት ፖሊሶች ትንሽ ተራርቀው የእጅ ባትሪ ፊታችን ላይ እያበሩ ቀረቡንና በአረብኛ የሆነ ነገር ተናገሩ፤ ዛናታ የያዝነውን ዘንቢል እንድናስቀምጥና ወደ ፊት እንድንራመድ ነገረችኝ። እንዳለችኝ አደረኩ። ረዘም ያለና ቁጣ የተቀላቀለበት ነገር ሲናገሩ ዛናታም ኮስተር ብላ መለሰችላቼው፤ ጭቅጭቅ ተፈጠረ። በመጨረሻም አንደኛው ወደ እኔ ራመድ ብሎ ክንዴን አፈፍ አደረገና ወደ መኪናው እንድሄድ ጎተተኝ፤ ዛናታ የሆነ ነገር ስትናገር መጎተቱን አቆመና ወደ ኋላዬ ገፋ አድርጎኝ እሷን በምልክት ወደ መኪናው እንድትቀድም አሳያት።

በአንድ ነገር እንደተስማሙ ገብቶኛል። ወደ እኔ ዞራ በተረጋጋ ድምፅ «በቀጥታ ተመልሰህ እቤት ሂድ፤ ጠብቀኝ ቶሎ እመጣለሁ!» አለችኝ፡፡ ግራ እንደተጋባሁ ሳያት ቆጣ ብላ “ሂድ! የምልህን ስማኝ! ካልሰማኻኝ ሁለታችንንም ችግር ውስጥ እንገባለን ሂድ!'' ብላኝ ወደ መኪናው ተራመደች፡፡ ወደ ኋላ ተመልሼ መንገድ ከጀመርኩ በኋላ ትንሽ ራቅ እንዳልኩ አቅጣጫዬን ቀይሬ ከአንዱ ዘንባባ ዛፍ ሥር ቆምኩ፡፡ ይቺን ድርጊት ምነው ባላደረግኋት እላለሁ እስከ ዛሬ። መኪናው ውስጥ ከኋላ አስገብተዋት ሁለቱም ወደጋቢና ገብተው በሩን ሲዘጉ ወደ ሆነ ቦታ ሊሄዱ መስሎኝ ነበር። መኪናው ግን አልተነሳም። ትንሽ ቆይተው አንዱ ፖሊስ ወጣና ሲጋራ ለኩሶ ከመኪናው ወደ ፊት አለፍ ብሎ እያጨሰ ቆመ፤ ሌላኛው ከጋቢና ወጥቶ ዛናታ የገባችበትን የኋላ በር ከፍቶ ገባና ዘጋው፤ ትንሸ ቆይቶ መኪናዋ በቃስታ ከፍ ዝቅ ስትል ትታዬኝ ነበር፡፡ ወደ ፊት ሩጥ ሩጥ የሚለኝን ስሜት የዘንባባ ዛፉን በብስጭት አንቄ ተቆጣጠርኩት፡፡ የራሴን እጅ ነክሼ በምሬት ቆምኩ። የመጀመሪያው ፖሊስ ወጥቶ ቀበቶውን ሲያስር ሁለተኛው በጥድፊያ ወደ መኪናው ተጣደፈ። መኻል ላይ ቆም ብለው ሲጋራ ተቀባበሉ። ሁለተኛው ፖሊስ የመጀመሪያው በወጣበት በዚያው በር ገባና ዘጋው፡፡ ከዚያ በላይ ማዬት አልቻልኩም፤ ፊቴን አዙሬ ወደ ቤታችን ተጣደፍኩ። ዋጋ ቢስነት፣ ረዳት አልባነት ውስጤን ሞላው። ሰውነቴ በእልኅ ይንቀጠቀጥ ነበር። ደግሞም ራስ ወዳድነቴ ሕይወትን መውደዴ እንጂ እነዚያን ቆሻሾች አጥፍቻቼው ብጠፋስ እላለሁ፡፡ _ ከእህቶቼ አንደኛዋ ላይ ቢሆን የማደርገው ይኼንኑ ነበር?...መሸሽ!? ተንገበገብኩ፤ መንገዴ ላይ ያገኜሁትን ነገር ሁሉ በእግሬ እየጠለዝኩ እንደ እብድ ብቻዬን ለፈለፍኩ፣ ፖሊሶቹን ረገምኩ፣ ከተማዋን ረገምኩ፣ መንግሥትን ረገምኩ፣ አገሪቱን ረገምኩ! ራሴንም ጭምር ረገምኩ፡፡ አእምሮዬ ወደ ኋላ ብዙ ዓመታት ተጉዞ አባቴን አስታወሰ፡፡ አንድ ጧት አባትና እናቴ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ግቢያችን በር ላይ ልጋጉን የሚያዝረበርብ ውሻ አጋጠማቸው። ውሻው እንዳያቸው ወደ እናቴ ሊነክሳት ሮጠ፤ ከውሻው ፍጥነት የተነሳ አባባ ረዥም መቋሚያውን እንኳን መጠቀም አልቻለም፤ ዘሎ ከእናቴ ፊት

ቆመና ለእናቴ የተሰነዘረው የውሻ ጥርስ የአባቴ ክንድ ላይ ተሰገሰገ። እናቴ ዘላ ወደ ግቢ ተመልሳ በጩኸት እስክትቀሰቅሰን አባባ ውሻው ጋር እየታገለ ነበር። ያ ውሻ የእብድ ውሻ በሽታ በሚሉት የተለከፈ ነበር። አባባ በዚያ ጠንቅ ለወራት በዘለቀ ሕክምና ከሞት አፋፍ ተመልሷል። እኔ ልጁ ግን አንዲት ምስኪን በዝሙት ላበዱ ዉሾች አስረክቤ ወደ ቤት ተመለስኩ። ከሁለት ሰዓት በኋላ ይመስለኛል ዛናታ መጠች። በዝምታ ገብታ ከቤታችን ኋላ ወዳለች ገላ መታጠቢያ ሄደችና ብዙ ቆይታ ተመለሰች፡፡ ትንሿን የኤሌክትሪክ ምድጃ ለኩሳ ሻይ ጣደች፡፡ አልጋችን ጫፍ ላይ ተቀምጨ በዝምታ አያታለሁ። ሻዩ ሲፈላ ቤቱ በቅመሙ ሸታ ተሞላ። በሁለት ብርጭቆዎች ቀዳችና አንዱን ለእኔ አቀብላኝ የራሷን በዝምታ ጠጥታ ጨረሰች።ዕቃዎቹን አጣጥባ “እንተኛ?' አለችኝ። ትንሽ ከእኔ ራቅ ብላ ፊቷን ወደ ግድግዳው አዙራ ተኛች። መብራቱን አጥፍቼ ወደ እሷ ዞሬ ከኋላዋ ሳቅፋት ሰውነቷ በሳግ እየተናጠ እያለቀሰች ነበር። አጥብቄ አቀፍኳት። በዚያች ጎጆ ውስጥ ረዳት አልባ የተረሱ ፍጡሮች ነበርን። ሁለታችንም ስለዚያች ቀን እስከመጨረሻው እንደገና _ አላነሳንም። ይሁንና በውስጤ የኔ የምላቼውን መከላከል የማልችል ደካማ የመሆን ስሜት በየጊዜው እዬተሰማኝ ስሰቃይ ኖሪያለሁ። አውቃለሁ ዛናታ ሴተኛ አዳሪ ነበረች፤ እኔም ጋር ሆነን ብዙ ወንዶች ጋር ትወጣ ነበር፤ ያቺ ምሽት ግን...
ለሰባት ወራት አብረን ኖርን፡፡ ለወራት በዘለቀ የነፍስ ግንኙነታችን ስለ ራሴ ያልነገርኳት፣ _ ስለ _ እርሷም _ ያልነገረችኝ _ ነገር _ አልነበረም፡፡ እናትና አባቷን እታውቃቼዉም፣ የተወለደችው ሞሪታኒያ የምትባል አገር ነው፡፡ እስከ ዐሥራ አንድ ዓመቷ ያሳደጋት ፈረንሳዮች የሚያስተዳድሩት የማደጎ ድርጅት ነበር፡፡ ዕድሜዋ ዐሥራ አንድ ሲደርስ ግን የአገራቼው መንግሥት ከቀድሞ ቀኝ ገዣቼው ፈረንሳይ መንግሥት ጋር ባለመግባባቱ፣ ፈረንሳዮች ማሳደጊያውን ዘግተው፣ ልጆቹንም በትነው ሄዱ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኑሮዋ የመከራ ሆነ፡፡ በዋናነት ለቱሪስቶች በእጅ

የተሠሩ ባህላዊ ጌጣጌጦች በመሸጥ፣ በመላላክ፣ልብሳቼውን በማጠብ በኋላም አንዳንድ ታሪካዊ ቦታዎችን በማስጎብኜት ኑሮዋን መግፋት ጀመረች፡፡ ዕድሜዋ 16 ሲደርስ አንድ እንግሊዛዊ ጋር ተኛች፡፡ እርሷ ሰውዬውን ወዳው ነበር። በወቅቱ ብር ሲሰጣት ለእርሷ የፍቅር መግለጫ ነበር የመሰላት፤ ሲቆይ ግን ሌሎችም ጋር ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግ ደረሰችበት፡፡ የፍቅር ታሪኳ ባጭሩ ተቀጨ፡፡ ሌሎች ቱሪስቶችም ብር እየከፈሏት በድብቅ ይወስዷት ጀመሩ። ያለፈችበትን የድህነት ሕይወት በዚህ መንገድ ማለፍ እንደምትችል አሰበች ዓይታው የማታውቀው ብር ማግኜት ጀመረች፤ እናም ሙሉ ለሙሉ የሴተኛ አዳሪነት ሥራ ውስጥ ገባች፡፡ በሞሪታኒያ ሕግ ሴተኛ አዳሪነት በጥብቅ የተከለከለና በእስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ በአንድ ዕድለ ቢስ ምሽት ተደረሰባትና ተያዘች። ለፖሊሶች ያላትን ገንዘብ ገላዋንም ጉቦ ሰጥታ ከእስር ቤት ካስወጧት በኋላ ወደ ሞሮኮ ተሰደደች፡፡ በአንድ በሚያውቃት ፈረንሳዊ ቱሪስት ተረድታ ነበር ወደዚያች ከተማ የደረሰችው። ሰውዬው ወደ ፈረንሳይ እንደሚያሻግራት ቃል ገብቶላት ሞሮኮ እንደደረሱ በአንድ ቅንጡ ሆቴል ለአንድ ሳምንት ያኽል ተዝናንቶባት እንደ ወጣ ቀረ። ከዚያ በኋላ ኑሮዋን በሴተኛ አዳሪነት መግፋት ቀጠለች። ውብ ሰውነቷ ወንዶች የሚሻሙበት ሴት አደረጋት፡፡ እርሷም ገንዘብ ይዘው ጎራ የሚሉ ወንዶችን ከሌሎች ሴቶች ጋር ተሻምታ የምትኖር ሴት ሆነች፡፡ ከዚያ የተረገመ ምሽት በኋላ የምትሠራበት መሸታ ቤት እንዳልሄድ ከለከለችኝ፡፡ ያንን ሥራ ስትሠራ እንዳያት አትፈልግም ነበር፡፡ ሥራዋ ላይ በጣም ቁጡ እና ሞገደኛ ነበረች፡፡ ጋጠወጥ ወንዶች በሚበዙበት በዚያ ጋጠወጥ መሸታ ቤት፣ በቢራ ጠርሙዝ የፈነከተቻቼው፣ እንጀራ ነውና በወንድ ተጣልታ ፊታቼውን በጥፍሯ የተለተለቻቼው ብዙ ነበሩ፤ ራሷ ናት የነገረችኝ፡፡ ለአንተ ብቻ ነው ጨዋ የሆንኩት ትለኛለች፡፡ ድንገት ሰዎች ጋር በእርሷ ምክንያት እንዳልጣላ ትፈራ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ግን እኔ ፊት ሌሎች ወንዶች ጋር ስትወጣ እንዳይ አትፈልግም ነበር። በእርግጥ እኔም ያንን ቦታ ሳስበው ይቀፈኛል፤ ይቀፈኛል ብቻ አይደለም ቅናት

ያንገበግበኛል፡፡ ሥራውን ተይው ልላት አስብና “የማያዋጣ በል ቅንድብ ይስማል እንደሚባለው” ይሆንብኛል፡፡ ሰው ቤት ተቀጥራ ለመሥራት ብዙ ሞክራ ነበር፤ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላት ሴት መቅጠር አልፈለጉም። ይህች ሴት ጋር በባህልም ሆነ በቋንቋ አንገናኝም፡፡ ሞሪታኒያ ከምትባል አገር የተገኜች ሴት አፈቅራለሁ ብዬ ላስብ ይቅርና ከዚያ በፊት ሞሪታኒያ የምትባል አገር የት ናት? ቢሉኝ እምላለሁ! አላውቃትም ነበር፡፡አንድ ቀን የት ነች ሞሪታኒያ? ብዬ ጠዬቅኋት “እዚሀ ነች'ኮ” አለችኝ በአገጯ እየጠቆመች፡፡ እውነትም እዚያው ነበረች፡፡ ሰው አገሩን ይመስላል እንዴ? ሞሪታኒያ በምዕራብ በኩል አትላንቲክ ውቂያኖስ የሚያዋስናት፤ በሰሜን ደግሞ ንዳዳሙን የሰሃራ በርሃ ተንተርሳ የከተመች አገር ናት። በእሳትና ውሃ መኻል ያለች አገር የፈጠረቻት፤ እሳትና ውሃ የሆነች ልጅ ጋር ነበርኩ።

ሞሮኮና ሞሪታንያ ነገረ ሥራቼው እንደ ኢትዮጵያና ኤርትራ ነው። ሲላቼው ታሪክ አጣቅሰው፣ አንዱ የአንዱን ድንበር ይገባኛል ይላሉ፡፡ እንዲያውም ሞሮኮ የሚለያቼውን በርሃ ተሻግራ ሙሉ ሞሪታኒያ የታላቋ ሞሮኮ አካል ነበረች ትል ነበር፤ ማለት ብቻ አይደለም ሞሪታኒያን እንደ አገር እውቅና ሳትሰጣት ቆይታለች፡፡ ቅኝ ገዥዎች በመኻል _ ገብተው ከናካቴው አለያዩዋቼውና _ አረፉት፡፡ ከቅኝ ግዛት ፈረንሳይኛ ቋንቋና ድህነት የተረፋቼው ሕዝቦች የሚኖሩባት አገር ናት፡፡ ይህች ከድፍድፍ ነዳጅ እስከ ወርቅ፣ ከብረት እስከ ዩራኒዬም፣ የተቼራት አገር ሕዝቦቿ ባገኙት ቀዳዳ እንደቀረው አፍሪካዊ ሁሉ የስደትን ጽዋ ይቀምሳሉ፤ ርግማን ነው። ስደት የሚባለው ነገር ምኑን ከምኑ እንደሚቀላቅለው ሳስብ፣ የሆነ ጢማም ተንኮለኛ ሳይንቲስት ይመስለኛል፡፡ ቁጭ ብሎ ዓለምን እንደ ላብራቶሪ ብልቃጥ ፊቱ አቅርቦ፣ እኛን ነዋሪዎቿን ከዚያና ከዚህ እያነሳ የሚጨምረን እና እስክንዋሃድ የሚወዘውዘን፤ የሚበጠብጠን፡፡ ስደት ትርምስ ነው፡፡ ስደት መለያዬት ነው። ደግሞም ስደት መቀላቀል

የሆነ ሆኖ እንደዚያ ስወድቅ ስነሳ አልሳካ ያለኝን ወደ አውሮፓ የመሸገር ሕልም፤ ገላዋን ሸጣ፣ ያጠራቀመቻትን ጥሪት አሟጣ፣ ስደቴን ባላሰብኩት ፍጥነት ያሳካችልኝ ይቺ ሴት ነበረች ብል ማን ያምናል?! የአገሬ የሰርግ ቤት ዘፋኝ “ምን ያለው አማጭ ነው የተክለፈለፈ ማሩን ከወተቱ ቀላቅሎት አረፈ!'' ያለው እንዲህ ያለ ነገር ቢገጥመው ይመስለኛል፡፡ ራስህን ወተት እልክ አልባልና፣ ብልም ግን እውነት አለኝ - ወተትም እንደ እኔ አልተናጠ!! አጥባቂ ሃይማኖተኛ ቤተሰብ ውስጥ ነው ያደግሁት፡፡ እንኳን ሴተኛ አዳሪነትን የቤት ልጆች ነን የሚሉ ሴቶች ጋር በፍቅር መቀራረብ በሩቅ የምፈራ ነበርኩ፤ ግን ሕይወት እንዲህ ነውና እዚች ልጅ ጋር የጦፈ ፍቅር ውስጥ ወደቅሁ። ከቀለበት ውጭ ልክ እንደ ባለ ትዳር ነበር አኗኗራችን፡፡ ዛናታ ሕልም አልነበራትም፣ የመሰደድም ወደ አገሯ የመመለስም ዕቅድ አልነበራትም፣ በአገሯ ይኼ ሥራ ነውር ነው፤ ግን ደግሞ ሕይወት ነውር አታውቅም፡፡ ያቺ መልካም ሴት እኔ ጋር እስክንገናኝ ምንም ዕቅድ አልነበራትም፤ በቃ ሴተኛ አዳሪ ናት...ትሠራለች ትኖራለች፡፡ እኔን ካገኜች በኋላ ግን ተስፋ ጀመረች፡፡ መጀመሪያ እኔ ከወጣሁ በኋላ ልትከተለኝና አውሮፓ ልንኖር አቀድን፡፡ ስለምንወልዳቼው ልጆች አወራን ... የመጨረሻ ቀን ምሽታችን፣ አሳዛኝ ግን ደግሞ በተስፋ የተሞላ ነበር፡፡ በሌሊት ባሕር ወደምንሻገርባት ጀልባ የሄድነው አብረን ነበር። የመጨረሻ ቃሏ ምን ነበር “ፈጣሪ ይከተልህ!" ብላ ከብር የተሠራ ጫፍና ጫፉ እንደ እባብ ጭንቅላት የተድበለበለ ቀጭን “ብራዝሌት' ግራ እጄ ላይ አጠለቀችልኝ፡፡ “በእኔ አገር ባህል ይኼ ከክፉ መንፈስ ይከላከላል ብለን እናምናለን” አለችኝ፡፡ የእናቴ አምላክ እና የዚች የሰው አገር ሰው አምላክ ተባብረውም ቢሆን አንድ እኔን አንከብክበው ይህችን ውሃ ማሻገር ያቅታቼዋል!? እያልኩ ነበር አርባ ሰባት ስደተኞች በጫነች አሮጌ ጀልባ ባሕር የቀዘፍኩት። እንዲህ ነበር ዛናታ ጋር የተለያዬነው። ብሯን ለመሳፈሪያ፣ አምባሯን ለማስታወሻ፣ ሰውነቷን ለወንድነቴ መጀመሪያ አድርጋ በብዙ ፍቅር ሸኜችኝ።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
​​#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከምሽቱ 5 ሰዓት ስንዱ ስራዋን ጨርሳ ለመተኛት ወደመኝታዋ መጥታ ከውጭ ቀርቅራ የሄደችውን መኝታ ቤት ስትከፍት ነበር..ሳባ 14 ዓመት ወደ ኋላ የተጓዘችበትን ረጅም የትዝታ ጉዞ አቋርጣ የተመለሰችው፡፡ስንዱ ቀስ ብላ ከፍታ ገባች ስታያት ጭብጥብጥ ብላ በተኛችበት አይኗን ቁልጭ ቁልጭ ታደርጋለች፡

‹‹ውይ ቀሰቀስኩሽ እንዴ?››

‹‹አይ አረ አልተኛሁም ነበር?››

‹‹ምነው እስከአሁን?አመመሽ እንዴ?››

‹‹አይ ምንም አልል..እንዲሁ የባጥ የቆጡን ሳስብ ነው?››

‹‹ካልተኛሽማ እራት ላምጣልሽ?››

‹‹አረ እኔ ነገም አልበላ..ቅድም እኮ ጠቀጠቅሸብኝ.ይልቅ. ስትደክሚ ነው የዋልሽው ነይና ተኚ›› ‹‹ካልሽ እሺ››
አለችና..ወደቁምሳጥኑ.ሄዳ ከፈተችና ለብሳ ስትሰራበት የቆየችውን ቀሚስ አውልቃ ሌላ ፒጃማ ከውስጥ አውጥታ ስትለብስ ከተደረደሩት ልብሶች መካከል የሆነ ቢጫ ልብስ ከቁምሳጥኑ ተንሸራቶ አልጋው ጠርዝ ላይ ወደቀ…ሳባ ጨርቁ ሳታስበው ትኩረቷን ሳበውና እጇን ዘረጋች…ወደራሷ ጎተተችው፡፡

‹‹እንዴ ስንድ ይሄ ምንድነው?››

‹‹የመነኩሴ ልብስ ነዋ››

‹‹የመነኩሴ?…እትዬ ልትመለኩስ ነው.እንዴ?››እትዬ ያለችው የስንዱን እናት ነው፡፡

‹‹አይ እሷ ገና ሌላ ለማግባት ሁሉ ሳታስብ አትቀርም››ስትል ቀለደች

‹‹እና የማን ነው?››

‹‹የእኔ?››

ሳባ ቆሌዋ ነው ተገፈፈው

‹‹ምን?›ከተኛችበት  ብርግግ ብላ ተነሳችና ቁጭ አለች፡፡

‹‹ምነው ?ይሄን ያህል ያስጨንቃል እንዴ?››

‹‹እኔ እኮ ደረቅነትሽን ስለማውቅ ነው እስከዛሬ ዝም ያልኩሽ…ሰባት አመቱ ካለፈ ግን ግድ አናግራታለሁ ብዬ እቅድ ነበረኝ››
ስንዱ ፒጃማውን ለብሳ ጨርሳ ወደአልጋው ወጣችና ከጎኗ ቁጭ ብላ‹ምን የምታናግሪኝ ነገር አለ.?ምንም እኮ የለም›አለቻት
‹ለምን የለም…?ገና እኮ 34 አመትሽ ነው….ሰላሳ አራት አመት ማለት ደግሞ ገና ሙሉ ወጣት ነሽ ማለት ነው.አብዛኛው የአዲስ አበባ ሴት በዚህ እድሜዋ ከእናቷ እቅፍም አትወጣም..ገና በዚህ እድሜያቸው ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ስለማግባት ራሱ የሚያስቡት››

‹‹እና ታዲያ እኔ ስለምን ላስብ..በህይወቴ በጣም የማፈቅረውን ሰው አግብቼ ልዩ የሆነ የትዳር ጊዜ አሳልፌያለሁ፤በህይወቴ በጣም የምወዳቸው አንድ ሴትና አንድ ጎረምሳ ወንድ ልጅ አለኝ…እና ከዚህ በላይ ምን ለማግኘት ብዬ ስለዚህ ጉዳይ አስባለሁ?›

‹‹ተይ እንጂ ስንዱ..አባዬስ በዚህ ውሳኔሽ  ደስ  የሚለው ይመስልሻል?  በዛ  ላይ እኔም እህት ራጂም ወንድም ይፈልጋል፡››

‹‹አይ እንደዛ ከሆነ አንቺ የምትወልጂውን ልጅ ወንድም አድርጎ መቀበል ይችላል አንቺም እንደዛው.እኔ ባሌን ሳገባው በህይወት እስካለህ ድረስ ሳይሆን በህይወት እስካለሁ ድረስ ለአንተ ታምኜ ያንተ ሚስት ሆኜ እኖራለሁ ብዬ  ነው ቃል የገባሁለት… ይሄንን ቃሌን ከማጥፍ ደግሞ ዛሬውኑ ብሞት  ይሻለኛል..በይ አሁን ተኚ›› ብላ ከጭንቅላቷ በላይ ያለውን ማብሪያ  ማጥፊያ  ተጭና  አጠፋችና ትራሷን አስተካክላ ተኛች…ሳባም  እሷ  እንዳደረገችው  አደረገችና  እቅፍ አደረገቻት…፡፡

‹‹ስንድ››

‹‹ወይ ሳባ››

‹‹ከድሮም ጀምሮ ባንቺ የማፍቀር ፀጋ እንደቀናሁ ነው..እኔም በህይወቴ ያንቺ አይነት ፍቅር ማፍቀር ብችል አንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰለሽ?››

‹‹ትቺያለሽ አንድ ቀን እንደዛ የምታፈቅሪውን ሰው አምላክ ይሸልምሽ ይሆናል፡፡››

‹‹ያ ቀን ሳይመጣ አረጀሁ እኮ ››

‹‹ሳቢ እኔ ካንቺ ባላውቅም እስትንፋስሽ በውስጥሽ እስካለ ድረስ ለምንም ነገር አይረፍድም…እንደውም አንዴ የነፍስ አባቴ የነገሩኝን አጭር ታሪክ ልንገርሽ››

‹‹እሺ ንገሪኝ››

‹‹ሰውዬው ነፍስ ካወቀ ጀምሮ በራዕይ አንድ ዛፍ ስር የተቀመጡ አዛውንት መምህር ሲያገኝና የእሳቸው ደቀ መዝሙር በመሆን ጥበብንና እውቀትን ሲያስተምሩት በተደጋጋሚ ያያል።ከዛም እድሜው ሲጎለብትና ሙሉ ወጣት ሲሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ቆርጦ ይነሳል።ሰውዬው እኛን እድሜውን ሙሉ በራዕይ ሲመለከታቸው የኖረውን መምህር ፍለጋ አለምን ለመዞር ቁርጠኛ ነበር።ከዛም ስንቁን ሸክፎ ጉዞ ጀመረ።ከመንደሩ ወጣ እንዳለ ከአንድ ሽማግሌ ጋር ተገናኘ።ሽማግሌው በሚያስደነግጥ ግርማ ሞገስና በፍፁማዊ ፀጥታ ዛፍ ስር ቁጭ ብለዋል።

ወደእሳቸው ጠጋ አለና"ሲታዩ ተጓዠ ይመስላሉ?"ሲል ጠየቃቸው

"አዎ:-እኔ ተጓዥ ነኝ፡፡ በዚህ እድሜዬ ሙሉ ዓለምን በጠቅላላ ዞሬያለሁ ማለት ይቻላል።"ሲሉ መለሱለት።

"እርሷ ትክክለኛው ሰው ኖት...እኔ ፍፁማዊ ለሆነ መምህር ደቀመዝሙር መሆን ታላቁ ምኞቴ ነው።ቤቴንና መንደሬን ለቅቄ የህልሜ ሰው የሆነውን
በዕውቀት የበሰለና በጥበብ የመጠቀ መምህር ፍለጋ እየወጣሁ ነው።እባክዎ በየት ብሄድ የምፈልገውን አይነት መምህር  ላገኝ  እና  የእሱ የዘላለም ደቀመዝሙር መሆን እንደምችል ሊጠቁሙኝ ይችላሉ?"ሲል ጠየቃቸው። ሽማግሌውም የተወሰነ አድራሻዎች ሰጡት...ወጣቱም አመስግኖ ተለያቸውና በጉጉትና በተስፋ ጉዞውን ቀጠለ።
ወጣቱ እንዳሰበው ሳይሆን ከአንድ መምህር ወደሌላው እየዞረ  ለ30  አመት ምድርን ካሰሳት በኃላ የሚፈልገውን አይነት ጥበብና እውቀት  ኖሮት  ልብን ሊያሸንፍ የሚችል መምህር  ሊያገኝ  ስላልቻለ  ተስፋ ቆርጦ አዝኖና  በጣም ተከፍቶ ወደመንደሩ የመልስ ጉዞ ጀመረ፤በሚገርም አጋጣሚ ወደመንደሩ ሲቃረብ ከሰላሳ አመት በፊት አግኝቶና አውርቷቸው የነበሩት አዛውንት ሰውዬ ይበልጥ አርጅተው እዛው ዛፍ ስር እንደተቀመጡ አገኛቸው።ወዲያው  እንዳያቸው ተገለፀለት፤ግማሽ እድሜውን ፈጅቶ ሲፈልጋቸው የነበሩት መምህር እራሳቸው እንደሆኑ አመነ፤ የተቀመጡበትም ዛፍ ልጅ ሆኖ በተደጋጋሚ በህልሙ ሲያየው የነበረው እንደሆነ እርግጠኛ ሆነ። እናም ተንደርድሮ ወደ እሳቸው ቀረበ።እግራቸው ስር ተደፋና"ከሰላሳ አመት በፊት ስጠይቆት ለምን እርሶ እንደሆኑ አልነገሩኝም?"ሲል ጠየቃቸው

"ልጄ በወቅቱ ለአንተ ጊዜው አልነበረም።ለዛ ነው ሊገለፅልህና ልትለየኝ ያልቻልከው።አለምን በመዞር የተወሰነ ልምድ ማግኘት እና  የተወሰነ መብሰል ነበረብህ።አሁን በብስለት ማየት ችለሀል።ከሰላሳ አመት በፊት ግን እንዲህ አልነበርክም።አግኝተኸኝ ነበር ግን ልታየኝ አልቻልክም።አውርተኸኝ ነበር ግን እያዳመጥከኝ አልነበረም።እና በጠየቅከኝ መሠረት የተወሰኑ አድራሻዎችን ሰጠሁህ ፡፡ አድራሻዎቹ የተሳሳቱ ቢሆንም ግን ተምረህባቸዋል...እኔም ይሄው.ሰላሳ አመት ሙሉ ከዚህ ዛፍ ስር አልተንቀሳቀስኩም ፡፡አንተን ተመልሰህ እስክትመጣ እየጠበቅኩህ ነበር አሉት።

‹‹እሺ ምን ለማለት ነው?››አለቻት ሳባ

‹‹ምን አልባት እስከዛሬ ፍለጋሽ የራቀ ቦታ ሆኖ እየኳተንሽ ይሆናል የኖርሽው…ለአንቺ የሚሆነው ነገር በእግዜር ተዘጋጅቶልሽ  በቅርብሽ  በቀላሉ  በምታገኚበት ቦታ ተቀምጦ ሳለ ሳታይው ቀርተሸ እንዳይሆን ብዬ እሰጋለሁ፡፡እና ቀኑ ደርሶ በማስተዋል አይንሽ ተገልጦ ያንቺ  የሆነውን  አንድምታይ  እርግጠኛ ነኝ …በይ አሁን ደህና እደሪ ለሊት መነሳት አለብን፡፡››
ሳባ እሷን ላለመረበሽ ስትል የተኛች መስላ አደፈጠች..እናም.ቅድም ወዳቋረጠችው ትዝታ ተመልሳ ገባች፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ እሷን ላለመረበሽ ስትል የተኛች መስላ አደፈጠች..እናም.ቅድም ወዳቋረጠችው ትዝታ ተመልሳ ገባች፡፡

ከ11 አመት በፊት ጥቅምት- 2004

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተምራ ለመመረቅ ቸኩላ ነበር፡የቸኮለችው ግን ለግል ደስታዋና እራሷን ለመቻል ካላት ጉጉትና ፍላጎት ብቻ አልነበረም፡፡ዋናው ለአባቷ ስትል ነበር፡፡ለአባቷ ምቹ  ሁኔታ መፍጠር እንዳለባት ፅኑ እምነት  ስላላት ነበር፡፡ቀና ብሎ እንዲኖር፤ቢያንስ ከጓደኞቹ ጋር ውጭ ውሎ እንዲገባ..ከጓደኞቹ ጋር ቀብር ሲሄድ፤ሰርግ ቤት ወዳጆቹ ሲጠሩት ብድግ ብሎ ሄዶ ከሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ውሎ ስቆና ተደስቶ አንዲመጣ፡፡አዎ ለእሱ ለሁለት እግሮቹ የሚሆኑ ዘመናዊ አርቴፊሻል እግሮች እና እሱ ሊነዳት የሚችል አንድ መኪና ልትገዛለት፡፡ይሄ የህይወቷ ትልቁ ምኞቷ ነበር፡፡ግን ማይታሰብ ነው የሆነባት፤በወቅቱ ጭራሽ እራሷንም ማኖር እየከበዳት ነበር ፡፡ይባስ ብሎ በዛው ወር   አባቷን ልታየው ወደ ትውልድ ከተማዋ አሰላ ሄዳ ነበር፡፡አባቷም ትንሹ  ወንድሟም ስለናፈቋት ተነሳችና ሄደች፡፡ስትደርስ  አባቷ  ሳሎን በእጅ የሚገፋ ማንዋል ዊልቸሩ ላይ ቁጭ ብሎ ነጭ ጋቢ ተከናንቦ ፊት ለፊቱ ያለ ቴሌቪዥን ላይ አይኖቹን ተክሎ እያየ ነበር፡፡ የበራፉ መንገጫገጭ  ድምፅ አነቃውና ፊቱን ወደበራፉ ዞር አደረገ..ፊቱ በአንዴ እንደ ጠዋት ፀሀይ ብርሀን ረጨ…ቦርሳዋን እዛው በራፍ ላይ ጥላ ተንደርድራ በመሄድ ሶፋው ላይ ሙሉ በሙሉ ዘላ ወጣችና አባቷ አንገት ላይ  ተጠመጠመችበት…እጁን  ዘረጋና ግራና ቀኝ ፊቷን እያገላበጠ ጉንጮቿን ሳማት፡፡
‹‹የእኔ እንቁ..በሰላም ነው…?እንዴት መጣሽ?››

‹‹ምን ማለት ነው?አልናፈቅኩህም እንዴ…?እንደዛ ከሆነ ተመልሼ መሄድ እችላለሁ››አለች የውሸት እንደማኩረፍ ብላ..፡፡
‹‹አንቺ እኮ ፀሀዬ ነሽ..ማነው ፀሀይ ጥዋት ስለወጣችለትና ስለነጋለት የሚከፋው…እንዲሁ ሳትደውይ ድንገት ብርት በማለትሽ ምን ገጥሟት ይሆን ብዬ ነው?››

‹‹አይ ደህና ነኝ…ሰርፐራይዝ ላድርጋችሁ ብዬ ነው፡፡››ስትል እንጀራ እናቷ ከኋለኛው ክፍል ውስጥ ተወዳጁን ታናሽ ወንድሟን እጁን እየጎተተች  መጣች፡፡‹‹እንዴ አባትና ልጅ በምስጢር ተጠራርታችሁ ትገናኙ ጀመር?››አለቻት  የእንጀራ እናቷ ስንዱ፡፡
‹‹ምነው ቀናሽ እንዴ?››

‹‹ብቀናስ…መብት የለኝም?›እያለች ወደ እሷ ተጠጋችና ጉንጭ ለጉንጭ  በመሳሳም የሞቀና የደመቀ ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡

አዎ የዛን ጊዜ አባትዬውን ልትጠይቅ አሰላ በሄደች ጊዜ በማግስቱ  አባትዬውን ልታዝናና ወደከተማ ይዛ ለመውጣት ፈልጋ ልብስ እየቀየረችለት ነበር…
‹‹አባዬ ይሄኛው ጃኬት ይሻልሀል?››

‹‹ልጄ አሁን ቤታችን ብናሰልፍስ..?ይሄ እኮ የተወለድሽበትና ያደገሽበት ሀገር ነው፤ብዙ የምታውቂያቸው ሰዎች ብዙ ጓደኞች አሉሽ.››.

‹‹እና? ››

‹‹እናማ እኔን እያንጓተቱ በአስፓልት ላይ መሄድ …››

‹‹አይ አባዬ..ትቀልዳለህ እንዴ.?አንተ እኮ ሁለ ነገሬ ነህ..አይቻልም እንጂ ቢቻል አንገቴ ላይ አንጠልጥዬ በየሄድኩበት ይዤህ ብዞር  በደረስኩበት  ሁሉ  ከጎኔ ብትኖር ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አባዬ አንተ እኮ ጌጤ ነህ…አለሜ፡፡››

‹‹ይሁንልሽ ልጄ …››ሲል ተሸነፈላት፡፡

ቤተክርስቲያን ይዛው ሄደች..ከዛ ሆቴል ይዛው ገባች፡፡ አዝናናችው..፡፡ ወደማታ ሲሆን ወደቤት ይዛው ገባች፡፡ ከቤተሰብ ጋር ስትስቅና ስትደሰት አመሸች፡፡ በበፊት መኝታ ክፍሏ ትንሹ ወንድሟን አቅፋ ተኛች፡፡

ለሊት በመነሳት ባልና ሚስቱን ቀሰቀሰችና አባቷን ወደ ቤተክርስቲያን ይዛው ሄደች፡፡ ሶስት ሰዓት ሲመለሱ ቁርስ ተዘጋጅቶ በልተው እስከ  ስድስት  ሰዓት  ቆየችና በማግስቱ ስራ ለመግባት ወደአዲስ አበባ ለመሄድ ተነሳች፡፡ በዚህ  ጊዜ ስንዱ በኩርቱ ፌስታል ሙሉ እቃ ይዛ ከጓዳ ወጣችና ወለሉ መሀከል ከሻንጣዋ ጎን አስቀመጠችው፡፡

‹‹ምንድነው ይሄ ደግሞ? አንቺ መቼስ ዘላለምሽን ኮተት አታጪም..ተማሪ  ሆኜ እሺ፤አሁንም አታቆሚም?››ነበር ያለቻት፡፡
‹‹አንቺ የእናት እጅ ለዘላለም እምቢ አይባልም››

ተከራክራ እንደማታሸንፋት ስለምታውቅ ወደአባቷ ሄደችና..አገላብጣ ስማ ተሰናበተችው፡፡ በቀጣይ እንጀራ እናቷን ተሰናብታ 500 መቶ ብር እጇ ላይ አስቀመጠችና ወንድሟን ወደላይ አንስታ አገላብጣ ስማው ለመሄድ ተዘጋጀች፡፡
የእንጀራ እናቷ ስንዱ ብሩን ለመመለስ ጣረች ‹‹ኸረ አይሆንም .አንቺ ከየት ታመጪዋለሽ?፡››ብላ ብትከራከራትም አልሰማቻትም፡፡ ብሩን የምትመልሺ ከሆነ እኔም የቋጠርሽልኝን ነገር ጥዬ ነው የምሄደው ብላ ስታስፈራራት ነበር በሃሳቧ የተስማማችው፡፡

አባትዬው መሀል ሳይገባ በትዝብት ሁለቱንም ይመለከት ነበር.እውነት ሳባ ከልቧ ለቤተሰቡ ብዙ ነገር ለማድረግ ፍላጎትም ምኞትም ነበራት…ግን  በወቅቱ ሁሉ ነገር ከአቅሟ በላይ ነበር፡በአራት ሺ ብር የወር ደሞዝ እራሷንም ማኖር በጣም እየከበዳት ነበር፡፡እነሱን ለመጠየቅ ለምትመጣበት እና ያንን ብር እንጀራ እናቷ እጅ ላይ ለማስቀመጥ አንኳን ብዙ ፍላጎቶቿን መግደልና ምቾቶቿን መስዋእት ማድረግ ነበረባት..አንባዋ እንዳቀረረ አባቷን በድጋሚ ስማ ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ ከበራፍ ላይ ባጃጅ አስቆመችና መናኸሪያ ድረስ አደረሳት፡፡

ወደአዲስ አበባዋ ተመለሰች…ማታ ከመተኛቷ በፊት ስንዱ የቋጠረችላትን ፌስታል ከፈተች፡፡ ውስጥ ያሉትን ቋጠሮዎች ዘረገፈችና…ተራ በተራ ማየት ጀመረች ሽሮ፤በርበሬ፤ምስር ክክ፤አተር ክክ የቀረ ነገር የለም፡፡
‹‹ይህቺ እኮ ከእናትም በላይ ነች››አለችና በጉንጮቿ ያለፍቃዷ   የሚንኳለለውን ዕንባ አበሰችና ፒጃማ ፈልጋ ቦርሳዋን ከፈተች፡፡ የተጣጠፈ ካኪ ወረቀት አገኘች፡፡

ግራ ገብቷት አነሳችውና ውስጡን ስትከፍት የተጠቀለለ በዛ ያለ ብር አገኘች. ወረቀቱን ዳግመኛ አነሳች፤ውስጡን ገለጠችው፤የአባቷ የእጅ ፅሁፍ ነበር፡፡

‹‹ለታክሲ ትሆንሻለች ብዬ ነው፡፡እንደሚቸግርሽ  አውቃለሁ  ግን ታውቂያለሽ እንደልቤ መሻት ላግዝሸ አልቻልኩም፡፡ አይዞሽ  ትንሽ  ወር  ነው  ነገሮች ይስተካከላሉ እስከዛው እንደምንም በርቺልኝ...ደግሞ አንቺ የእኔ ልጅ ነሽ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ትችያለሽ››ይላል፡፡

ደብዳቤውን ጨምድዳ ወለሉ ላይ ወረወረች…በእንጀራ እናቷ ገደብ  በሌለው ደግነት ተነክታ የጀመረችውን ለቅሶ በሰፊው ለቀቀችው..ብሩን አነሳችና ቆጠረችው…ሶስት ሺ ብር ነው፡፡
‹‹አሁን እኔ ሰው ነኝ....ተማሪም ሆኜ የቤተሰቦቼ ሸክም….አሁንም  ስራ  ይዤ ለዛውም አባቴ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እያለ ከእነሱ ብር መቀበል…››በዛን ቀን ሁሉ ነገር ነበር ያስጠላት …ህይወት እራሱ አስጠላቻት…የሆነ ነገር መቀየር እንዳለባት ተሰማት…አዎ የህይወቷን መስመር ማስተካከል እንዳለባት ወሰነች፡፡ አዎ እንደዛ ነው የተሰማት…‹‹ወይ እንደምንም ቀልጠፍጠፍ ብዬ የተሻለ ደሞዝ የሚያስገኝ የተሻለ ሰራ ማግኘት አለብኝ፡፡ አልያም ደግሞ ረከስ ያለ ኑሮ የሚገኝበት ክፍለሀገር ሄጄ መኖር.›ስትል ነበር የወሰነችው፡፡
​​​​ቢያንስ ከአዲስ አበባ በቤት ኪራይና በታክሲ ሂሳብ የማይሻል የክፍለሀገር ከተማ የለም..ቢያንስ ከዛ በሚገኝ ትርፍ ቤተሰቦቿን መርዳት  ትችላለች…ግን ችግሩ ቤተሰቦቿ የሚፈልጉት እርዳታ  ትንሽ  እርዳታ  አይደለም...ችግራቸው የእለት ጉርስ እና ለአመት ልብስ አይደለም…ለዛ መቼም አይቸግራቸውም፡፡ የእሷ ሀሳብ ማደረግ ያለባትና ማድረግም የምትፈልገው ግን ከዛ በላይ ነው፡፡ ለአባቷ ዘመናዊ ዊልቸርና ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀስበት መኪና የመግዛት ህልም  አላት፡፡..ይሄ ተማሪ እያለች ጀምሮ በአእምሮዋ  ሲጉላላ  የኖረ  ምኞት  ነበር፤ቆይቶ  ስራ ከተቀጠረች ከአመት በኋላ ግን ያንን መቼም ማድረግ እንደማትችል እየተሰማት አና ተስፋ እየቆረጠች ሄደች፡፡
ትዝታዋን ሳትጨርስ ነበር እንቅልፍ ያሸነፋት፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ሳባ እሷን ላለመረበሽ ስትል የተኛች መስላ አደፈጠች..እናም.ቅድም ወዳቋረጠችው ትዝታ ተመልሳ ገባች፡፡ ከ11 አመት በፊት ጥቅምት- 2004 በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተምራ ለመመረቅ ቸኩላ ነበር፡የቸኮለችው ግን ለግል ደስታዋና እራሷን ለመቻል ካላት ጉጉትና ፍላጎት ብቻ አልነበረም፡፡ዋናው ለአባቷ ስትል ነበር፡፡ለአባቷ ምቹ  ሁኔታ መፍጠር…»
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ አምስት

ድቅድቅ ባለው ጨለማ ከጀልባዋ የሞተር ድምፅ እና ከውሃው መንቦራጨቅ በስተቀር ምንም ነገር በማይሰማበት ባሕር ላይ ለሦስት ሰዓታት ያኸል ተጉዘን፣ የታሪፋ ወደብ የሚባለው የስፔን ግዛት ስንቃረብ፣ ጀልባችንን የሚነዳት ስደተኛ ሞተሯን አጠፋት፤ ልምድ ያለው ሰው ይመስላል፡፡ ጨለማው ውስጥ ከሩቅ የወደቡን መብራት እያዬን በዝምታ በመዓበሉ እየተገፋን ስንጠጋ፣ ከወደቡ አካባቢ ድንገተኛ የሆነ ከባድ የተኩስ ድምፅ ተሰማ፤ ወዲያው በሰማዩ ላይ እንደ ጅራታም ኮከብ የሚበር _ ነገር እየተምዘገዘገ ወደ እኛ አቅጣጫ መጥቶ ሰማዩ ላይ እንደ ርችት ፈነዳና የብርሃን ዝናብ በላያችን ላይ ዘነበ፡፡ እካባቢው በደማቅ ብርሃን ሲጥለቀለቅ ዓይኖቻችንን ጨፍነን መንጫጫት ጀመርን፡፡ በበኩሌ ያለቀልን ነበር _ የመሰለኝ። ወዲያው ሌላ ተኩስ ተከተለ፣ ይኼንኛው ለደቂቃዎች እንደ ፀሐይ ከበላያችን ቆሞ ባሕሩን ቀን አስመሰለው። ወዲያው ሁለት ትልልቅ ደማቅ ብርቱካናማ ቀለም ያላቼው የሞተር ጀልባዎች ውሃውን እየሰነጠቁ ወደ እኛ በፍጥነት ሲበሩ ተመለከትን፡፡ የእኛን ጀልባ ሲቆጣጠር የነበረው ስደተኛ “ማንም ሰው እንዳይንቀሳቀ የስፔን ድንበር ጠባቂ ፖሊሶች ናቸው ጀልባችን ተበላሽቷል በሉ” አለና ከጀልባዋ ኋላ የተንጠለጠለውን መቅዘፊያ ሞተር ነቅሎ ወደ ውሃው ውስጥ ወረወረው፤ ከዚያም መኻላችን ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ጀልባዎቹ እንደደረሱ በድምፅ ማጉያ ፖሊሶቹ መናገር ጀመሩ፡፡ “ፖሊሶች ነን፣ ማንም ሰው ወደ ውሃው እንዳይዘል ጥልቅና ቀዝቃዛ ነው!''
“ጀልባው ላይ ሕፃናት አሉ?''

"እርጉዝ ሴቶች ...?"
“የታመመ ?"
“አካል ጉዳተኛ. . .?"
“የጦር መሣሪያ የያዘ. . .?"

ጀልባችሁ ውስጥ ውሃ ገብቷል?... ከጥያቄው በኋላ ወፍራምና ረዥም ገመድ ቁልቁል ወረወሩልን፤ ጀልባችን ከእነሱ ዘመናዊና ግዙፍ ጀልባ ጋር አቆራኜናት፤ በቀስታ እየተጎተትን ወደ ወደቡ ተጓዝን። በዚህ ሁኔታ የአውሮፓን ምድር ለመርገጥ በቃሁ።

ስሄድ አገኜኋት ስመለስ አጣኋት...

አውሮፓ ገብቼ ስዳክር፣ በኋላም በብዙ ውጣ ውረድ ወደ አሜሪካ ስሻገር፣ ዘናታን በልቤ ተሸክሚያት ነበር፡፡ ያኔ ስፔን መድረሴን በስልክ ሳሳውቃት ደስታዋ በቃል የሚገለጽ አልነበረም፡፡ ለአራት ወራት አካባቢ በሰጠችኝ ስልክ ተገናኝተን የደረስኩበትን ስናወራ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን ያ እንደዋወልበት የነበረው ስልክ መሥራት አቆመ። ብዙ ደከምኩ፡፡ ብዙ ቀናት፣ ወራት፣ ዓመታት ነጎዱ... ዛናታ የውሃ ሽታ ሆነች፡፡ ከሞሮኮ መጣ የተባለን ስደተኛ ሁሉ እያሳደድኩ ስለ ዛናታ ያልጠዬኩበት ጊዜ አልነበረም። ሰው ነን እና ከዓይናችን የራቀን ምስል ልባችን ቢያደበዝዝብንም በሆነ በሆነ ቀላል የሚመስል ትዝታ፤ ፍቅር የራሱን ቀለም የሚያድስበት የሚደምቅበት ጊዜ አለ፡፡ ከአምስት ዓመታት የአሜሪካ ኑሮ በኋላ የዛናታ ነገር እንደገና ውስጤን ያንገበግበው ጀመረ፡፡ ምናልባት በገንዘብም፣ በስሜትም ስረጋጋ፤ ሁሉ ነገር ሞልቶ ሰው ሰው የሚሸት ነገር ሲጠፋ፤ ባዶነት በውስጤ እንደ ውቂያኖስ ተንጣሎ መንፈሴ የሆነ አድማስ ማረፊያ መሬት ስትፈልግ ያኔ ትናንቴን ፍለጋ ውስጤ ተነሳስቶ ይሆናል፡፡ አገራት ጦርነት ላይ ሲሆኑ ከታሪክ ይልቅ የቅጽበቱ ውጊያ እንደሚያሳስባቼው፣ ግለሰብም በሕይወት ጦርነት ሲዘፈቅ ታሪኩን ለጊዜው ዘንግቶ ይቆያል፡፡ ድል ሲያደርግ ወደ ነበረው ይመለሳል፡፡ ወደ ትዝታዬ... ፍቅር፣ በጎነት ወዳሳዬችኝ ያቺ ሴት በትዝታ ተመለስኩ። ወደ ኢትዮጵያ መጥቼ ቤተሰቦቼን ካዬሁ በኋላ ያቀናሁት ወደ ሞሮኮዋ ታንጂር ነበር፡፡ ያለ ስጋት በቱሪስት 'ቪዛ' በእነዚያ መንገዶች ስራመድ "መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ አይባልም ደርሶ...!" የሚሉት ብሒል ነበር ግዝፈቱ የሚሰማኝ፡፡ ከተማዋ

ስሄድ እንደነበረችው እንደዚያው ናት፡፡ ሁሉም ነገር እንዳለ ነበር፡፡ ወደ እነዚያ መሸታ ቤቶች ሰቀና፣ እግሮቼ እየተንቀጠቀጡ ሐሴት፣ ናፍቆት እና ፍርኃት በተቀላቀለበት ስሜት ነበር። የመሸታ ቤቶቹ ቁጥር በጣም ጨምሯል። ሰውም የዚያኑ ያህል በዝቶ ነበር። ይሁንና የዚያን ምሽት አንድም ዛናታን እውቃታለሁ የሚል ሰው ማግኘት አልቻልኩም፡፡ እነዚያ በዓይን የማውቃቼው ሴቶች አንድኛቼውም አልነበሩም። እንኖርበት ወደነበረው ቤት አቀናሁ፣ ሰፈሩ በሙሉ ፈርሶ ትልቅ መጋዘን የሚመስል ነገር ተሰርቶበታል፡፡ በብዙ ፍለጋ፣ ከሦስት ቀናት በኋላ አብራት ትሠራ የነበረች ናይጀሪያዊት ሴት አገኜሁ፤ አላስታወሰችኝም፡፡ ሴትዮዋ በዚህ ፍጥነት ትልቅ ሴትዮ መስላለች፡፡ ጥያቄዬ አሰልችቷት ነበር፡፡ መጠጥ ስገዛላት ተረጋጋች። ከብዙ ምልክትና ማብራሪያ በኋላ ግን ትዝ አላት፡፡ ሞቅ ብሏት ንግግሯ እየተደነቃቀፈ ስለነበር ማስታወሷን ተጠራጥሬ ነበር፡፡ ሊያልቅ የተቃረበ ሲጋራዋን በላይ በላዩ እየሳበች ጭሱን አንዴ ወደ ላይ፣ አንዴ ወደ ጎን በዘፈቀደ ታንቦለቡለዋለች። በጭሱ ውስጥ በቸልታ አዬችኝና፣ በረዥሙ ተንፍሰ "ያቺ ቆንጆ ልጅ... አስታወስኳት ቆንጆ ጥርሶች የነበሯት...ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ አረብኛ ትናገር ነበር ... ወንዶች በጣም ይወዷት ነበር፤ አስታወስኳት። እንደገና ፊቷ የተቀመጠውን ብርጭቆ አንስታ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠችውና በመጠጡ ምሬት ፊቷን አጨፈገገች፡፡ ትዕግስት በሚፈታተን እርጋታ አዲስ ሲጋራ አዉጥታ ለኮሰች፡፡ “የሆነ ጊዜ ተጣልተን አሮጊት ብላ ሰድባኛለች...ሁሉም እንደዚያ ነው የሚለኝ፡፡ ዕድሜዬን ላቆመው አልችልም!" አለች በቅሬታ፡፡ ድንገት ኮስተር አለችና "ምኗ ነህ ግን?'' አለችኝ፡፡ “ጓደኛዋ ነበርኩ ከተለያዬን ቆዬን፣ ላገኛት ከሩቅ ቦታ ነው የመጣሁት”

“ከየት”
ፈራ ተባ እያልኩ “ከአሜሪካ”

ሁለት እጇን ወደ ሰማይ ዘርግታ “ዕድለኛ ልጅ ነች፤ ሞታ እንኳን የምትፈለግ! እኔ ቆሜ ፈላጊ የለኝም'' አለች። “ሞታ ነው ያልሽው?'' አልኩ በድንጋጤ። ሲጋራ በያዘ እጇ ወደተንጣለለው ባሕር እየጠቆመችኝ “ከአራት ይሁን አምስት ዓመት በፊት ተገድላ እስከሬኗ ውሃ ላይ ተጥሎ ተገኜ፡፡ በዚያ ምክንያት እነዚያ ውሻ ፖሊሶች ሰብስበው አስረውን ነበር። ብዙ ሰው ጋር ትጣላ ነበር በጣም ወጣት ነበረች ደግሞ...' አለች፡፡ ሁኔታዋ ተራ ነገር ያወራች ነበር የሚመስለው፣ የያዝኩት የቢራ ጠርሙዝ ከእጄ አምልጦኝ መሬት ላይ ሲወድቅ፣ ናይጀሪያዊቷ ሴት ምንም ሳይመስላት “መሄድ አለብኝ! አሮጊት ብሆንም ቀድማኝ ሞተች...ይቅርታ ደነገጥክ መሰለኝ?''ብላኝ ተነስታ ሄደች:: በቃ! ያቺ ውብ እና ለእኔ ብቻ ደግ አድርጎ የፈጠራት ሴት መጨረሻዋ እንደዚያ ሆነ፡፡ የቀረኝ ብቼኛ ነገር ትዝታዋ እና ከእጄ ላይ አውልቄው የማላውቀው የሰጠችኝ 'ብራዝሌት' ነበር፡፡ ናይጀሪያዊቷ ተነስታ ስትሄድ፣ አዳዲስ ወጣት ሴተኛ አዳሪዎች መጥተው ከበቡኝ። ተነስቼ በመካከላቸው አለፍኩና ከቡና ቤቱ ወጥቼ ቁልቁል ወደ ባሕሩ ዳርቻ ተጓዝኩ... ጀልባዎች ወደሚቆሙበት፣ አሁንም ጀልባዎች በመደዳ ታሥረው ይወዛወዛሉ፡፡ ሁለት ሰዎች መረብ ይጠቀልላሉ፣ መልካቼው በደንብ አይታዬኝም፡፡ ባሕሩ ዳርቻ ላይ ቆሜ እስኪበቃኝ አለቀስኩ! ከንቱ ዓለም!! ምናልባት እርሰ በእርስ እየተቀናኑ ለዱርዬ ትንሽ ሳንቲም ሰጥተው እህቶቻቼውን የሚያስገድሉ ሴቶች ሲሳይ ሆና ይሆናል፡፡ ወንጀል፣ ወሲብ፣ ሕገወጥ የሰው ዝውውር፣ ዕፅ፣ ባጥለቀለቃት በዚያች ትንሽ መንደር እንዲህ ዓይነት ነገር የተለመደ ::חל ከዚያ ሁሉ መንከራተት በኋላ አሜሪካ እጇን ዘርግታ አልተቀበለችኝም ነበር፡፡ ቢሆንም የመንከራተት ታሪኬ አብቅቶ እንደ ሰው የምታይበት ኑሮ መጀመሬ ልዩ
ተስፋ ጫረብኝ፡፡ አውሮፓ ካሳለፍኩት አሰልች የጥበቃ ሕይወት ይልቅ ያ መረብ

መጠቅለልና ዓሣ መሸከም ቢቆይም ከውስጤ ያልጠፋ ስቃይ ነበርና፤ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት የአሜሪካ ሥራዬ 7ነት መስሎ ነበር የታዬኝ፡፡ ቆይቶ የአሜሪካ ኑሮ ሲገለጥልኝ መረብ ከማጠብ ወጥቼ እኔ ራሴ መረብ ውስጥ መግባቴ ገባኝ፡፡ ሁለት ዓይነት እስር ቤቶች አሉ፤ አንዱ አጥር ውስጥ ያስቀምጠናል፣ ሌላኛው አጥሩን ውስጣችን ያስቀምጠዋል- አሜሪካ ሁለተኛዋ እስር ቤት ነበረች፡፡ ካቴናው ነፍስ ላይ ነበር የሚከረቼመው፡፡ በዚች ምድር፣ የነፃነት ቁንጮ ማለት አገርህ ላይ ከፋም ለማም ሕዝብህ መኻል ተሳክቶልህ መኖር መቻል ነው፡፡ ተራራው ሥር ሆኖ ይኼን ማሰብ አይቻልም፤ ለዓመታት ለፍተው- ደክመው ተራራው ጫፍ ላይ ሲቆሙ ብቻ ነው፣ አገር ከነድህነት እና ከነሰቆቃዋ የነፍሳችን ሐቅ መሆኗ የሚገለጥልን፡፡ በወጣ ገባ ጉዞዬ ሰዎችን ከነፍሴ ይቅር ማለት ተማርኩ፡፡ በቃ ሰዎች ተረገምንም፣ ተመረቅንም በዚች አጭር ሕይወት የምንከፍለው መከራ በቂያችን ነው፡፡ በቀል፣ እርስ በእርስ መፋተግ የከንቱ ከንቱ...ሁሉን ነገር ተውኩት፡፡ አንገቴን ደፍቼ ቀን ከሌት መሥራት ሆነ ኑሮዬ... መሥራት... መሥራት... መሥራት፡፡ ከቤተሰቦቼ ሕይዎት ጀምሮ ሁሉን ነገር በመሥራት ቀዬርኩ። ዐሥራ አራት ዓመታት ግራ ቀኝ ሌላ ሕይወት ሳልመኝ፣ ሁለት ሥራ እየሠራሁ ከመረቤ ለመውጣት ተጋሁ፤ በእርግጥም የተሳካልኝ ይመስለኛል፡፡ ከ21 ዓመቴ የጀመረ መንከራተት አርባ ልደፍን አንድ ዓመት ሲቀረኝ እግዚአብሔር በቃህ አለኝ መሰል ጠቅልዬ አገሬ ገባሁ፡፡ ዕድል ከብዙ ጀርባ መስጠት በኋላ ፊቷን አዙራልኝ አሜሪካ በምትባል ግዙፍ ዓሣ ነባሪ ተውጨ ተተፋሁ፡፡ የስሜ አንድምታ ቆይቶ ገረመኝ! ዓሣ ነባሪ ውጦ የተፋው ዮናስ አሜሪካ ውጣ ከተፋችኝ እኔ ጋር ስም ተጋራን፡፡ ሁለቱም አንዴ የዋጥቱን አጽሙን ካልሆነ አይተፉም ይባላል፤ እውነት ነው፡፡ የሕይወት አጋጣሚ ዓሣ ነባሪውንም አሜሪካንም እንዴት እንደሚውጡና እንዴት እንደሚተፉ አሳይቶኛልና ሕያው ምስክር ነኝ። እናም አዋዋጡ አንድ ዓይነት ባይሆንም እኔ ዮናስ ጥላሁን እንዲህ ለዓመታት በስደት ጥርስ ታኝኬ ተተፋሁ፡፡ ነፍሴ ላይ የመረረ የጥርስ ማኅተም _ ቢኖርም _ እነዚያን ጠባሳዎች ሕይወት ጋር ተፋልሜ ድል በመንሳቴ

ያገኘኋቼው ኒሻን አድርጌ አያቼዋለሁ እንጂ አልማረርም፡፡ በአዲስ ሕይወት እንደምፈወስም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሕይወት ተአምር አያልቅባት መቼስ!! ቢሆንም ተስፋ ራሱ ሕመም እንዳለዉ አልዘነጋም፡፡

የተስፋ ሕማማት!

ከረዥም ጊዜ የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ጠቅልዬ ለመኖር ወደ ኢትዮጵያ ስመለስ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጓደኛዬ ካሌብ ጋር የምሰ ቀጠሮ ያዝን። ዝምተኛ ልጅ ነበር። ሠዓሊ ነው። ገና ያኔ ተማሪ እያለንም በሥዕል ፍቅር ያበደ ልጅ ነበር። ዐሥረኛ ክፍል ሆነን ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን ራት ሲበላ የሚያሳይ ቆንጆ ሥዕል ስሎ ሰጥቶኝ እስከ አሁን እማማ መኝታ ቤት በፍሬም ተሰቅሎ አለ። እማማ ሥዕሉን ባዬችው ቁጥር ከንፈሯን ትመጥና “የኔ ጌታ! ለኛ ብሎ'ኮ ነው እንዲህ የጠቋቆረ እንጂማ የብርሃን ፀዳሉ ከጠሐይ ሰባት እጅ የሚያበራው የት ሂዶበት?! እንኳን ለራሱ ለኛስ ብርሃኑ ተርፎ የለ?!'' ትላለች በሐዘን። በእርግጥ ሥዕሉ የጠቆረው ካሌብ “ቻርኮል' በሚለው ነገር ስለሳለው ነበር። በኋላ እኔ ወደ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ስገባ ካሌብ ሥዕል ለመማር “አርት ስኩል” ገባ። አሁን ታዋቂ ሠዓሊ ሆኗል። ታዲያ ተገናኝተን ስላሳለፍኩት አንዳንድ ነገር እያጫዎትኩት ድንገት የሆነ ሐሳብ አሰብኩ። “እኔ የምልህ ... አንድ ነገር ብነግርህ ልክ እንደነገርኩህ አድርገህ ትሥልልኛለህ?'' “ራፖርት ጸሐፊ እንደሚባለው ራፖርት ሠዓሊ ልታደርገኝ ነዋ?'' ብሎ ሳቀና “ምንድን ነው?'' አለኝ። በሞሮኮና ስፔን ድንበር መካከል ስላጋጠመኝ ነገር ከመጀመሪያ ጀምሮ ነገርኩት፤ እና አጥሩን፣ አጥሩ ላይ በነፋስ ድምፅ የሚፈጥሩትን ብጭቅጫቂ ጨርቆች፣ ከአጥሩ ወዲያ ያለው መብራትና በዚህ በኩል ስለነበረው ጨለማ . . . ጭንቀቱ፣ ተስፋው... ተመስጦ ሲያዳምጠኝ ቆዬና ፊቱ ላይ ሐዘን ረበበት “ለምን ማሣል ፈለግህ?'' አለኝ።

ያ አጥር ለእኔ በሁለት አገራት መካከል የተቀመጠ የድንበር መከለያ ብቻ አልነበረም፤ በሞት እና በሕይወት መካከል ያለ መለያ መስመር እንጂ። ስንቶች ከስንቱ ኣፍሪካዊ አምባገነን፣ ርሃብና ጦርነት ነፍሳቼውን ሊያድኑ በዛ አለፉ?! ጥለውት የሄዱት ፎቶና ዕቃቸው ምሰክር ነው። ያ አጥር ለእኔ በአገራት መካከል ያለ ጥቂት ኪሎሜትሮች ልዩነት ብቻ ሳይሆን የዘመን መለያ መስመር ነበር። ከአጥሩ ወዲህ ባለቸው አፍሪካና ከአጥሩ ወዲያ ባለው አውሮፓ መካከል በኑሮ፣ በስልጣኔ፣ በሰብአዊነት የብዙ ክፍለ ዘመን ልዩነት ነበር። ያ አጥር ለእኔ ከገራገር ልጅነት ወደ ጥልቅ ሰውነት የቀየረኝ አስማተኛ በር ነበር። ያ አጥር ከአጥር ወጥቼ ስለ እውነተኛዋ ሕይወት እንዳስብ ያደረገኝ መገለጥ ነበር– ለእኔ፡፡ ከአጥሩ ወዲያ ለተቀመጠው ተስፋ እኔን ጨምሮ ሰዎች የሚከፍሉት ዋጋ እንደዚያ ይመራል ብዬ አላሰብኩም ነበር። አጥሩ ከሚቦጨቀው ሥጋ በላይ ተስፋ ነበር ሕመም የሆነብን። ተስፋ እዚህ ልብ ላይ የሚፈጥረው ሕመም አለ። ተስፋ ሕመም አለው። ይኼን ሁሉ የሆነውን አጥር በጎበዝ ሠዓሊ ለማሣል ፈለግሁ። ታሪኬ የጀመረው እዚህ ነው ብዬ የማሳዬው ነገር ፈለግሁ። በእርግጥ ያልነገርኩት አንድ ነገርም ነበር። ለዛናታ ስለዚያ አጥር ስነግራት ራቁት ደረቴ ላይ ዕንባዎቿ ተንጠባጠቡ፤ ቀዝቃዛ የዕንባ ዘለላዎች። እና ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ያላለችውን አንድ ነገር አለች። “የትም አትሂድብኝ!?'' በረዥሙ ተነፈሰና “ችግር የለዉም ዕሥልልሃለሁ! እንደጨረስኩ እደውልለሃለሁ፣ እንዳትጨቀጭቀኝ'' አለኝ፣ ካሌብ። ልቤ በደስታ ዘለለች። ይሀን ካለኝ በኋላ ግን ካሌብ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። እኔም ያን ያኽል አልተከታተልኩትም። በመኻል ወደ አሜሪካ ተመልሼ ስለቆዬሁ አልተገናኘንም። ስሜቱም ድንገት ብልጭ ያለብኝ ነገር ስለነበር ሲቆይ እንኳን ሥዕሉን ሠዓሊውን ረሳሁት። አንድ ቀን ብሔራዊ ቲአትር አካባቢ ሰው ቀጥሬ ቡና እዬጠጣሁ አንድ ጋዜጣ አዟሪ ፊቴ ያስቀመጠውን ጋዜጣ ገለጥ ገለጥ እያደረኩ አያለሁ። ድንገት የኪነጥበብ አምዱ ላይ የጋዜጣውን ገጽ ግማሽ የሞላ ሥዕል ጋር ተፋጠጥኩ። የድንበር አጥሩ ላይ በቁርጥራጭ ጨርቆቹ ምትክ ብዙ ሰዎች እንደ ኢየሱስ ተሰቅለው የድንበር

ጠባቂዎቹ እንደ ክርስቶስ ሰቃዮች ዓይነት የጥንት የሮማ ወታደሮች የሚለብሱትን ጡሩር ለብሰው ይታያሉ። ከፍ ብሎ ሰማዩ ላይ ልክ እንደ ፀሐይ ብርሃን የሚረጭ ዶላር ይታያል። ዓይኔን ወደ ርዕሱ አቃበዝኩ "the passion of hope" በሚል ርዕስ በሒልተን ሆቴል የተካሄደው የታዋቂው ሠዓሊ ካሌብ ፍሰሐ የሥዕል ዓውደ ራዕይ ከፍተኛ አድናቆትን አግኝቷል'' ይላል። ዝቅ ብሎ ጋዜጠኛ ይጠይቃል፣ “ሐሳቡ እንዴት መጣልህ?'' ይመልሳል ወዳጄ ካሌብ “አንድ ቢቢሲ የሰራው ዶክሜንተሪ ላይ ስደተኞች በሞሮኮና ስፔን ቦርደር የሚገጥማቼውን ችግር ሲናገሩ ካዬሁ በኋላ ሐሳቡ ከውስጤ አልወጣ አለ... ከምንም በላይ የሚጎዳን ኤክስፔክቴሽናችን ነው በተስፋ ውስጥ ያለውን ሕመም ነው ለማሳዬት የፈለግሁት..." “ተሳክቶልኛል ትላለህ?” ...
ጋዜጣውን በቀስታ አጣጥፌ አስቀመጥኩና ተከዝኩ! እንደ ልምጭ ግርፊያ ቆዳዬን ዘልቆ አመመኝ፡፡ ተስፋ ያደረግሁት ወዳጄ ለተስፋ ሕመም ዳረገኝ። በአገሮች መካከል ብቻ አይደለም የእሾህ አጥር ያለው፤ በእኛና በታሪካችን መካከልም ለራሳቼው ዕውቅና ለመቃረም እንዲህ የሚሰነቀሩ የእሾህ አጥሮች አሉ፡፡ ስደቴን ሳይሰደድ፣ እይታዬን ሳያይ፣ ሕልሜን ሳያልም፣ ሕመሜን ሳይታመም፣ ናፍቆቴን ሳይናፍቅ፣ በመሰናክሌ ሳይሰናከል፣ ታዋቂው ወዳጄ የማያውቀውን ትላንቴን በብሩሹ ቀማኝ። ነገሩ በልኬ እንዲያስተካክልልኝ የሰጠሁትን የሐዘን ልብስ፣ ልብስ ሰፊዉ በአደባባይ ዘንጦበት ሲደሰት እንደማዬት ነበር፡፡ የአንዱ ሕማማት ለሌላዉ ሰርጉ ነዉ! ተውኩት።

ሕይወት...ሲጠያይም!

ባለቤቴ ማኅደረ ሰላም ወሬ የሚሰለቻት ሴት ናት፡፡ ሲበዛ ዝምተኛ፣ ካወራችም በአጭሩ ተናግራ ወደ ዝምታዋ የምትመለስ ሴት፡፡ አንዳንዴ ወሬዋ ከማጠሩ የተነሳ የተቋረጠ ስለሚመስለኝ ትቀጥላለች ብዬ ዓይን ዓይኗን ሳያት "አለቀ!" ትለኛለች እስቃለሁ፡፡ ምንም እንኳን ዝምተኛነቷን ገና የኮሌጅ ተማሪዎች እያለን የማውቀው

ቢሆንም ከተጋባን በኋላ ግን ብሰባት ነበር። ወይም በዚህ ቅርበት ስታዘበው ተጋኖብኝ ይሆናል፡፡ እኔ ደግሞ ለረዥም ዓመታት በሰው አገር ታፍኜ በመኖሬ ይሁን አልያም የፈረንጆቹ ትንሽ ትልቁን በዝርዝር የማውራት ልማድ ተጋብቶብኝ፣ ብቻ ብዙ የማወራ ይመስለኛል፡፡ የእርሷ ዝምተኛነት የበለጠ ወሬኝነቴን ያጋንነውና ብቻዬን የምኖር እስኪመስለኝ እንዳንዴ የራሴ ድምፅ ያስተጋባብኛል፡፡ አለ አይደል በጨለማ ውስጥ ለሆነ ሰው እያወራን ድምፁ ሲጠፋብን ተኛህ እንዴ? እንደምንለው ዓይነት፣ ማኅድረ ጋር ሳወራ በየመኻሉ “እዬሰማሽኝ ነው?” ማለት አበዛለሁ፤ ብዙ ጊዜ ራሷን በአዎንታ ከፍ ዝቅ ከማድረግ ባለፈ “አዎ!'' የሚል ቃል እንኳን ለመናገር 오ナカナナ ታዲያ መጀመሪያ ከአሜሪካ ወደ ኢትዬጵያ መጥቼ እንደተገናኜን ሰሞን፤ በወሬ ወሬ “በሕፃንነቴ ጥቁር ነበርኩ እያደግሁ ስኼድ መልኬ ጠየመ፤ ወደ ፊት ፈረንጅ እንዳልመስል እፈራለሁ'' አለችኝ... እንደ ቀልድ! እንዲያው ያን ያኽል ቁም ነገር ሆኖ ሳይሆን አባባሏ የራሴን ሕይወት የሚገልጽ መስሎኝ ነበር ያኔ። ብዙ ብዙ የጠቆሩ የስደት ጊዚያትን አሳልፌ በስተመጨረሻ ሕይወት መልኳ እየጠዬመልኝ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ማኅድረን ማግባቴ ደግሞ ሕይወትን እንደ ፀሐይ ያደምቃታል የሚል ተስፋ ሞልቶኝ ነበር፡፡ መቼስ ለሕይወት ተምሳሌት _ ካደረግነው _ መጠዬም፣ በመጨለምና _ በመንጋት መኻል ያለ መካከለኛነት ምሳሌ ነውና ፍጹም ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ግን ደግሞ ከተጋባን በኋላ ከዚያ ሁሉ _ መራር የስደት ታሪክ ሳገግም _ ነው መሰል አንዳንድ ጥያቄ በውስጤ ሳይፈጠር አልቀረም፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ቀደም ሲል በቼልታ ያለፍኳቼው ቢሆኑም እየቆዩ ይከነክኑኝ ጀመር። ብዙ የማይገቡኝ ነገሮች አሉ። ከድሮውም ግድ ካልሆነብኝ በስተቀር የሕይወትን ሚስጥር ካልመረመርኩ ብዬ ችክ የምል ሰው አይደለሁም፡፡ ያልገባኝን ነገር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ዞሬው አልፋለሁ፡፡ አላሳልፍ ካለኝም ወደ ኋላ እመለሳለሁ፡፡ ንዝንዝ

አልወድም። በሥራ ቦታዬም ይሁን የትም ሰዎች ጋር በገባኝም፣ ባልገባኝም ጉዳይ ክፉ ነገር ከተነጋገርኩ፣ ከቀኝ ጆሮዬ ከፍ ብሎ ጨምድዶ የሚይዝ ራስ ምታቲ ይነሳብኛል፡፡ ይኼ እንኳን ከጊዜ በኋላ የመጣ ሕመም ነው፡፡ ከነገር እሸሻለሁ፣ ከጥል እሸሻለሁ፣ ሰላም፣ ሳቅ እና ጨዋታ ብቻ እወዳለሁ...ግን ሁልግዜ ፋሲካ የለም። አንዳንድ ጉዳይ ቢሸሽቱም የማይሸሽ ነው፡፡ ለምሳሌ ይኼው የባለቤቴ ማኅደረ ሰላም ነገር፡ በሕይወቴ ስኬት ከምላቼው ታላላልቅ ጉዳዮች አንዱ ትዳር መመሥረቴ ሲሆን፤ በተለይም ማኅደረን ማግባቴ ስኬቴን ከፍ ያለ አድርጎት ነበር፡፡ ፈጣሪ በምን ተአምር ጠብቆ ለእኔ እንዳስቀመጣት በግርምት አስባለሁ። መታበይ እንዳይመስልብኝ ባልነግራትም ገና ያኔ ንግድ ሥራ ኮሌጅ እያለን ነበር የወደድኳት፤ የወደድኩባት ምክንያት እንደ ብዙኃኑ የግቢው ወንድ በቁንጅናዋ ተስቤ አልነበረም፤ በጭራሽ! እንዲያውም እኔ የማኅደረ ቁንጅና አይገባኝም፡፡ በእርግጥ የሆነ ለመግለጽ የሚከብድ የፊት ቀለም ነበራት፡፡ በድፍን ግቢው ጥይምና ለእርሷ ብቻ የተሰጠ ይመስል “ጠይሟ ልጅ” ነበር ብዙዎች የሚሏት፡፡ እሱም ያን ያኽል ተጋኖ እይታዬኝም ነበር፡፡ ያ የተወለወለ የሚመስል ጠይምነቷ እንደ ሆነ ልዩ ምልክት ከመሆን ባለፈ ያን ያኽል የተለዬ ስሜት አያሳድርብኝም ነበር፡፡ ማኅደረ ለእኔ ቀጥ ያለ አቋምና ረዥም ጸጉር ያላት ጠይም ሴት ናት፡፡ ቆንጆ ተብሎ የሚዳነቅ ሳይሆን፣ የተስተካከለ ምንም እንከን የማይወጣለት መደበኛ መልክ ያላት ነበረች፡፡ ልክ እንደ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ሴቶች፡፡ እንግዲህ ቁንጅና የመለዬት ጸጋዬ ከሕዝብ ተለይቶ ተገፎ ካልሆነ በስተቀር የማኅደረ ውበት ሥርዓቷና ጥልቅ ዝምተኝነቷ ነበር ባይ ነኝ፡፡ያኔ ማኅደረና ጓደኛዋን ጨምሮ አምስት የምንሆን ልጆች ጥሩ ቅርርብ ነበረን፡፡ ነገሩ እንደ “ግሩፕ” ነገር ነበር። ታዲያ ሁላችንም በማኅደረ ዙሪያ የተለያዬ ርቀት ያለው ምህዋር ነበረን፡፡ እኔ ጥሩ ልጅነቷ ስለሚስበኝ ወድጃት ነበር፤ አብሪያት መሆን እፈልግ ነበር፡፡ ያ ነገር ልብስ የሚያስጥል ፍቅር አልነበረም፤ ይልቅ ሁኔታው ቢመቻችለት ወደ ፍቅር ለመቀዬር ጫፍ ላይ የቆመ ለስላሳ ስሜት ነበር።

የኮሌጅ ትምሀርቱን አቋርጨ ከተሰደድኩ በኋላ ማኅደረን ያስታወስኩበት ጊዜ ትዝ አይለኝም ነበርና አሁንም ያ ነገር ፍቅር ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ።ያኔ አፈሙሌና ማኅደረ ጋር ረዘም ያለ ጊዜ ለብቻችን የተገናኜንበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም (ቆይቶ ተጨዋች የነበርኩ ቢሆንም፣ እዚህ ነገር ላይ ግን አንዳች ነገር አፌን የሚቆልፈው ዓይን ኣፋር ነበር በርኩ። ከውጭ ለሚያዬኝ ግን እንደዚያ መገመቱን እንጃ ካልረሳሁት በስተቀር) ሲጀመር ብቻዋን ማግኘት አስቸጋሪ ነበር። ሃይማኖት ከምትባል መንጠቆ የመሰለች ጓደኛዋ ጋር ነበር ተያይዘው የሚጓተቱት ፡፡ ታዲያ ማኅደረን ለመቅረብ በሞከርኩ ቁጥር ሃይማኖት የምትባል ጓደኛዋ እንደ ሽቦ እጥር ከፊቱ ትጋረጣለች፡፡ ከዚህ ጋሬጣነቷ ብዛት ከማኅደረ ይልቅ ሃይማኖት ጋር በጠም ተቀራርበን ነበር። ከኮሌጁ የተማሪዎች ካፍቴሪያ በናልፍም፣ ብቻችንን አልፎ አልፎ ሸይ ቡና እንል ነበር፡፡ በዚህ ቅርርባችን ታዲያ ጉራ እንዳይመስልብኝ እንጂ፣ ሃይማኖት አጉል ፍላጎት አድሮባት እንደነበር ከሁኔታዋ ገብቶኝ ነበር፡፡ እንዲውም አንዴ በጣም ደስ የማይል ነገር ማድረጓ ትዝ ይለኛል። ልሰደድ ቀናት አንደቀሩኝ ነበር፤ አጠቃላይ ዝርዝሩን አላስታውስም፤ ብቻ ወደ ማታ አካባቢ እሷና እኔ እዚያው ኮሌጅ አካባቢ የሆነ ቦታ ቆመን ነበር፤ ስንሰነባበት ሁልጊዜ ጉንጭ ለጉንጭ ተሳስመን ነው። የዚያን ቀን ግን ሆነ ብላ ዞረች እና ከንፈሯ ከንፈሬን ቦርሾት አለፈ፤ ነገሩ ስለደበረኝ ተሰናብቻት ሄድኩ። ሴት ልጅ እንደዚህ ስትሆን ደስ አይለኝም። እስካሁን ሳያት ይቀፈኛል፡፡ ታዲያ ለራሴ ስቀልድ በዚያ ገደ ቢስ ከንፈሯ ሸኝታኝ ነው ፍዳዬን የበላሁት፤ የማኅደረ ከንፈር ቢሆን ኖሮ በብርሃን ሰረገላ ነበር አሜሪካ የምገባው እላለሁ። ታዲያ ስለ ማኅደር በወሬ ወሬ ጣልቃ እያስገባች አንዳንድ ነገር ትነግረኝ ነበር። ያዘነች አስመስላ ታውራው እንጂ የሚበዛውን የማኅደረን ጉድለት የሚመስል ታሪክ የሰማሁት ከዚቹ ጓደኛዋ ነው፡፡ ይቺ ሃይማኖት የምትባል መልክም፣ አመልም የነሳት ልጅ ስንጋባ የማኅደረ ሚዜም ነበረች፡፡ በግልጽ ፊቴ ላይ እንዳያስታውቅ ብጠነቀቅም እስከ አሁን ቤታችን በመጣች ቁጥር ደስ
የማይል ስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡

አንዱ ሲቆይ የሚከነክነኝ ነገር ስለማኅደረ እናት የነገረችኝ ነገር ነው “እናቷ አገር ያወቃት ቁሌታም ነበረች (ቃል በቃል እንደዚያ ነበር ያለችኝ) አለሌ ነገር ነበረች፡፡ ግን ደግሞ ብታያት እንዴት እንደምታምር፤ አባቷን ከሦስት ልጆቻቼው ጋር ጎልታቼው ሌላ ወንድ ጋር ተያይዛ ጠፋች'' አለችኝ። ዛሬ ላይ ሳስበው ስለጓደኛዋ ገመና ያውም ማኅደረን ለወደዳትና አብሯት ለሚማር ልጅ በዚያ ልክ ማውራት ለምን አስፈለገ? ብልም፤ ያኔ ግን ምነው ሦስት ልጅ ከወለዱ በኋላ? ብያለሁ፡፡ ያንን ከሩቅ የሚሸሹት ፊቷን ወደ እኔ አስጠግታ “ልጆቹን የወለደቻቼው ከሰውዬው አይደለም እየተባለ ይታማል፡፡ እንዲያውም ሰውዬው አልጋ ላይ ችግር ስላለባቼው ነው ወንዶች ጋር የምትሄደው እየተባለ ይወራል፡፡ ደግሞ ልጆቹን ስታያቼው ሐሜቱን ወደማመን የሚገፋ መልክ ነው ያላቼው ሦስቱም በመልክ አይመሳሰሉም፡፡ ብቻ እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው።" በእርግጥ ከዚያ በፊት ባላውቃቼውም ከአሜሪካ ተመልሼ ማኅደረ ጋር ጋብቻ ካሰብን በኋላ ቤተሰቦቿ ጋር አስተዋውቃኝ ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን፣ ወንድሞቿን ባየኋቸው ቁጥር ሁልጊዜ ይኼ ነገር ትዝ እያለኝ እቼገራለሁ፡፡ የማኅደረ ተከታይ ኤፍሬም ይባላል፤ ለስላሳ ጸጉሩ ውሃ ሲነካው የሚተኛ ወደ ቢጫ የሚወስደው ቅላት ያለው ልጅ ነበር፡፡ በዚያ ላይ ረዥም፣ የሁሉም ታናሽ መስፍን ደግሞ ጥቅጥቅ ያለ ከርዳዳ ጸጉርና ጠይም ቆዳ ያለው እንደ ዕድሜው በቁመቱም ከሁሉም የሚያንስ ልጅ ነው፡፡ ሁሉንም የሚያመሳስላቼው አንድ ነገር ሲበዛ ትሁቶች መሆናቼው ብቻ ነው፡፡ ወሬው እውነት ነው ብዬ ብቀበለው እንኳን ይኼ ትህትና የአስተዳደግ ውጤት ነውና አባታቼው ምን ያኽል ጥሩ አባት እንደሆኑ የሚያሳይ ምልክት ነበር -ለእኔ፡፡ በእርግጥም የበለጠ እያወቅኋቼው በሄድኩ ቁጥር የማኅደረ አባት ምን ያኽል ብርቱና ጨዋ ሰው እንደነበሩ መረዳት ችያለሁ፡፡ እንዲያውም አልፎ አልፎ ውጭ እየተገናኜን አንድ ሁለት ማለታችን አልቀረም፤ ይኼ ነገር ማኅደረ ፊት ላይ ፈገግታ ሲፈጥር ተመልክቻለሁ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
​​#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስር


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
ዛሬ ላይ..
ለሊት 11 ሰዓት ተነስተው ቤተክርስቲያን ሄዱ፤ለአባትየው ሰባት ዓመት ፍትሀተ-ፀሎት ከመደረጉ በተጨማሪ የስንዱም የምንኩስና ስርዓት ፀሎት ተደርጎ እማሆይ አፀደማርያ ተብላ ቆብ ደፋች.ይሄ ድርጊት በአብዛኛው  ሰው  ዘንድ መደነቅን ለጥቂቱ ደግሞ ለሀሜት አሳልፎ ሰጣት…ከቅዳሴ በኋላ ከቤት ተዘጋጅቶ የመጣውን ፀበል ፃዲቅ ሰንበቴ ቤት በመታደም ከተቋደሱ በኋላ ቤት ላለው ዝግጅት ተመለሱ ቀኑን  ሙሉ ባለፉት 6  ዓመታት እንደተደረገው  ችግረኞችና  የኔ ቢጤዎች ሲመላለሱበት ዋሉ…ሳባ በዕለቱ አብዛኛውን ፕሮግራምና ሽር ጉዱን ብትሳተፍም ከአስር ሰዓት በኃላ ግን ደከማት፡፡  ተዝለፍልፋ ሰው መሀል ከመውደቋ በፊት እየተጎተተች ወደመኝታ ቤት ገባችና አልጋ ላይ ወጥታ ተዘረረች..ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰዳት…እንቅልፏ ግን እጅግ  ሰቅጣጭ  የሆነ ቅዠት የሞላበት ነፍስ አስጨናቂ ነበር…ደግሞ የሚገርመው  ሕልሙ  እንደ ሆረር ፊልም ከአንዱ አሰቃቂ ትዕይንት ወደሌላ በተሸጋገረ ቁጥር ጭንቀላቷ ውጥርጥር እያለ ሲለጠጥ በትክክል ይታወቃታል…በተለጠጠ ቁጥር ደግሞ ውጥረቱ የሆኑ ነርቮቿን እንደሚበጣጥስ ይሰማትና ከህመሙ ራሷን ለማዳን ከእንቅልፏ ለመንቃት እየጣረች ነው.. አዎ ይታወቃታል..በደንብ ከልቧ እየጣረች ነው…ግን አልቻለችም፡፡ ስንዱ እቃ ለመውሰድ ወደመኝታ ቤት ስትገባ ሳባ በላብ ተደፍቃ ስትወራጭ በማየቷ ወዝውዛ ነበር ከእንቅልፏ ያነቃቻት..

‹‹ወይ ስንድ..ገላገልሺኝ.. እመሰግናለሁ›አለችና ተጠመጠመችባት፡፡
ስንዱም ጭንቅላቷን እያሻሸቻት‹‹ምንድነው ይሄ ሁሉ ላብ? አሞሻል እንዴ አንቺ ልጅ?›ስትል ጠየቀቻት፡

‹‹አይ ሰሞኑን ትንሽ አሞኝ የታዘዘልኝ መድሀኒት ነበር..ስመጣ ግን  ረስቼው መጣሁ››

‹‹ታዲያ ለምን ከዚህ አይገዛልሽም?››
‹‹አይ እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አይነት አይደለም..ማዘዣው ስለሌለኝ አይሸጡልኝም፡፡ግዴለሽም አሁን ትንሽ ስለተኛሁበት ይሻለኛል..ወደ እንግዶችሽ ተመለሺ››

‹‹እሺ በቃ መለስ መለስ እያልኩ አይሻለሁ..››ብላ ግንባሯን ሳመችና በራፉን ዘግታላት ወጥታ ሔደች፡፡
ሳባም መልሶ እንቅልፍ እንዳይወስዳትና ወደተመሳሳይ ቅዠት ገብታ ስቃይ ውስጥ ላለመግባት ስትል ወደሀሳብ ውስጥ ገባች ወደ ትናንቷ ተመለሰች፡፡ትዝ ይላታል የዛን ሰሞን አሰላ ሄዳ ቤተሰቦቿን ጠይቃ ከተመለሰች በኋላ እና አባቷ ደብቆ ሻንጣዋ ውስጥ ያስቀመጠላትን 3ሺብር ካገኘች በኋላ ምንም ሰላም ማግኘት አልቻለችም ነበር፡፡ ቀንና ለሊት ሕይወቷን እንዴት ማስተካከል እንደምትችልና ከቤተሰቧ ድጎማ እራሷን አላቃ በተራዋ ለቤተሰቦቿ ተገቢውን ድጋፍ እንዴት ልታደርግ እንደምትችል ማሰብ ነበር ቋሚ ስራዋ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን ተዓምር ተከሰተ፡፡፡:

ትዝ ይላታል ማክሰኞ ቀን ነው፡፡ ስራ ገበታዋ ላይ ሆና  በተለመደ  መልኩ ባለጉዳዬችን እያስተናገደች ሳለ ረፋድ ላይ አንድ እጅግ ዘመናዊ ጥራት ያላቸው ብራንድ ልብሶች የለበሰች፤ውድ የሆኑ አብረቅራቂ ጌጣጌጦችን ጆሮዎቿና እጆቿ ላይ የደረደረች ሴት ወደ ቢሮዋ የገባችው፡፡ልክ እንዳየቻት ነው  ልቧ የደነገጠላት..በሁለመናዋ ነው የቀናችባት….አየሩን ሞልቶ ወደ አፍንጫዋ ሰርጎ በገባው ውድ ሽቶዋ ሳይቀር ቀናችባት፡፡እናም ሳታስበው ከወትሮ በተለየ አይነት ፈግታና ቅልጥፍና ሴትዬዋን ማስተናገድ ጀመረች፡፡ እሷ የምትጨርሳቸውን ስራዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ቢሮዎች የሚሰሩ እና የሚፈረሙ ፊርማዎችን  ሳይቀር ሴትዬዋን  የራሷ  ቢሮ አስቀምጣ እሷ (ልክ ጉቦ ይሰጥሀል እንደተባለ ኤክስፐርት) ተዟዙራ አስጨረሰችላትና ሰጠቻት፡፡
ከዛም ሴትዬዋ..ወረቀቷን ተቀብላ ትሄዳለች ብላ  ስትጠብቅ  ተመቻችታ  ፊት ለፊቷ ተቀመጠችና….‹‹ስሜን መቼስ ከሰነዱ አንብበሻል…ትብለጥ እባለለሁ…››

‹‹እኔ ደግሞ ሳባ››ስትል የራሷንም ነገረቻት፡፡

‹‹ሳባ ዋው…ስምሽም እንደመልክሽያምራል››አለቻት፡፡የሴትዬዋ ንግግር ቀጥታ ልቧ ላይ አርፎ ነበር ቅልጥ ያደረጋት፡፡ አንድ ጎረምሳ ወንድ እንኳን እንደዛ አይነት አስተያየት ቢሰጣት የዛን አይነት ስሜት በውስጧ አያጭርባትም፡

‹‹አመሰግናለሁ….›› አለች ሌላ ምትለው ነገር ስለጠፋት፡፡

ሴትዬዋ ቀጠለች‹‹ስራ እንዴት ነው?››

‹‹ያው እንደምታይው ነው…ምንም አይልም››

‹‹ምንም አይልም ነው ወይስ ጥሩ ነው ነው?›

‹‹አይ ምንም አይልም…ጥሩ የሚባል ስራ እንዲህ በቀላሉ ይኖራል ብለሽ ነው?›› አለቻት ሰሞኑን ስላለችበት ብሶት እያሰላሰለች፡

‹‹እንደ አንቺ ቆንጆ፤መለሎ ቁመና የተስተካከለ የሰውነት ቅርፅ ያላትና በዛ ላይ የተማረች ሴትማ በጣም ጥሩ የተባለ ስራ ሊኖራት የግድ ነው…››አለችና እጇን ወደ ቦርሳዋ ሰዳ የቢዝነስ ካርዷን አወጣችና ጠረጴዛዋ ላይ እያስቀመጠችላት
‹‹ይሄውልሽ ሳባ ለምን እንደሆነ አላውቅም ወድጄሻለሁ ምን አልባት ጥሩ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ በምትፈልጊበት ቀን ደውይልኝ….በይ ቻው  ለመስተንግዶሽ አመሰግናለሁ፡፡››ብላ ጉንጯን ሳመችና ቢሮዋን ለቃ ወጣች፡፡ ሳባም በተቀመጠችበት መቀመጫ ደንዝዛ በፈዘዙ አይኖቿ ከኋላዋ ተከተለቻት ሴትዬዋ እየተሞናደለች ቢሮውን ለቃ ስትወጣ በራፍ ላይ ሁለት ወጠምሻና ባለጡንቻ ወጣቶች እየጠበቋት.ነበር….መሀከል አስገብተዋት ይዘዋት ሄዱ…፡፡

‹‹ይህቺ ባለስልጣን ነች ወይስ የባለስልጣን ሚስት?› ስትል ራሷን ጠየቀች….ብንን እንደማለት አለችና ትታላት የሄደችውን ቢዝነስ ካርድ አነሳችና…አየችው..
ትብለጥ ግዛው፡፡

‹‹ቤርሙዳ ማሳጅ ቤት›› ይላል፡፡

‹‹እንዴ ባለማሳጅ ቤት ነች ግን አስመጪና ላኪ  ነው  የምትመስለው›› ስትል የስራዋ አይነት ከግምቷ ውጭ ሰለመሆኑ አብሰለሰለች፡፡ሌላ ባለጉዳይ ገባባት፡፡ሳትወድ.በግዷ.ሀሳቡን ለጊዜው በልቧ ሸሸገችውና ወደስራዋ ተመለሰች፡፡ማታ ቤት ገብታም ስለሴትዬዋ ማሰቧን አላቋረጠችም ነበር፡፡ ወንድ ብትሆን "ፍቅር ያዘኝ እንዴ?ብላ ራሷን መጠራጠር ትጀምር ነበር...ሴትዬዋ የማሳጅ ቤት ባለቤት መሆኗን ከቢዝነስ ካርዷ ብትረዳም ‹‹የፈለገችኝ ለሌላ ስራ ቢሆንስ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት። እንደምንም ራሷን   ተቆጣጠረችና አራት ቀን በመቆየት በአምስተኛው ቀን ደወለችላት፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «​​#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ : : ዛሬ ላይ.. ለሊት 11 ሰዓት ተነስተው ቤተክርስቲያን ሄዱ፤ለአባትየው ሰባት ዓመት ፍትሀተ-ፀሎት ከመደረጉ በተጨማሪ የስንዱም የምንኩስና ስርዓት ፀሎት ተደርጎ እማሆይ አፀደማርያ ተብላ ቆብ ደፋች.ይሄ ድርጊት በአብዛኛው  ሰው  ዘንድ መደነቅን ለጥቂቱ ደግሞ ለሀሜት አሳልፎ ሰጣት…ከቅዳሴ በኋላ ከቤት ተዘጋጅቶ የመጣውን ፀበል ፃዲቅ…»
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ ስድስት

እንግዲህ አንደ ጓደኛዋ ሃይማኖት አባባል ከሆነ፤ የማኅደረ ዝምተኝነት እና ከሰው መለዬት እንደ በሽታ የተጠናዎታት እናታቼው ትታቼው ከሄደች በኋላ ነበር። ከወንድሞቿም በላይ በእናቷ መጥፋት ክፉኛ የተጎዳቸው ማኅደረ ናት እንጂ ከዚያ በፈት ተጫዋች፣ ተግባቢ እንዲያውም የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እያሉ አስተማሪ ወጣ ሲል፣ ተማሪዎች ፊት ቆማ ካልዘፈንኩላችሁ የምትል ደፋር ልጅ ነበረች፡፡ የእናቷ መጥፋት መንፈሷን ሰበረው፡፡ ጓደኛዋ ይኽን ነገር ለምንም ትንገረኝ ለምን፣ ቤተሰብ የሚለው ነገር የሁሉ ነገሬ አልፋና አሜጋ ነውና ለማኅደረ ልክ የሌለው ሐዘን ተሰማኝ፡፡ እናቷ ትታት የጠፋችና በዚህች ምድር አባት ብላ በሙሉ ልቧ የተደገፈቻቼው ሰው ምናልባትም ትክክለኛ አባቷ ያልሆኑ ምስኪን። ጓደኛዋ እንኳን የእውነት ጓደኛዋ አይደለችም፡፡ ለማኅደረ የነበረኝ ስሜት ከልክ ያለፈ ሐዘን ነበር። ከመጀመሪያውም ከወደድኩት ባሕሪዋ ጋር ምናልባት ይኼ ይኼ ነገር ተደማምሮ ማኅደረን እንደ ጓደኛዬ ማዬት እና መቅረብ የጀመርኩበት ጊዜ ነበር፡፡ ያውም በራሴ የቤተሰብ ጉዳይ በተጨናነቅሁበት ለራሴ የሚታዘንልኝ በነበርኩበት ወቅት፡፡ በሴት ጉዳይ ይዘፈንበት ይለቀስበት የማላውቅ ወጣት ነበርኩና ደፍሬ አልገፋሁም፤ ጨክኜም አልራቅኋትም፡፡ አንዳንድ ማኅደረ ጋር ለመቀራረብ የማደርጋቼው ነገሮች ነበሩ። ከጓደኞቼ ፎቶ ኮፒ ቤት የሚያስፈልጋትንም የማያስፈልጋትንም ሁሉ በነፃ ኮፒ እያደረግሁ እወስድላት ነበር፡፡ እሷ ግን እያንዳንዷን ሳንቲም አስባ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ትመልስልኝ ነበር፡፡ ያው ተዘዋዋሪው እዚያ የተማሪዎች ካፌ ላይ ስንጠጣ የእኔን ሒሳብ ተንደርድራ የምትከፍለው ነገር መሆኑ ነው፡፡ ለምን ቀድማ ሒሳብ እንደምትከፍል ለእኔ ቢገባኝም፣ ለሌሎቹ ጓደኞቻችን ግን በመካከላችን የተለዬ ቅርበት የተፈጠረ የሚያስመስል ነገር ነበር፡፡ በአሽሙር ፈገግታ፣ በጥቅሻ፣ በክንድ ጉሸማ፣ ወዘተ፣... ግፋበት የሚሉኝ ጓደኞቼ በወቅቱ እንደዚያ ስታደርግ ደስ የማይል ስሜት እንደሚሰማኝ አያውቁም ነበር፡፡ማኅደረ ጋር አሳለፍኩ የምለው ረዥም ጊዜ አሁን ጨርሶ በማላስታውሰው ምክንያት ሰፈሯ ድረስ የሸኜሁባትን ቀን ነው። ምን እንዳወራን አላስታውስም፣ ሰዓቱ እንኳን ትዝ አይለኝም፣

የማስታውሰው ብቼኛ ነገር አንድ ዙሪያውን በወዳደቀ አሮጌ መኪናና የመኪና 19 የተሞላ አሮጌ ጋራዥ ጋ ስንደርስ መለያዬታችንን ነው። መንገዱ ከዚያ ጋራዥ በሚወጣ የተቃጠለ ዘይት የተበከለ ከባድ የብረት ቅጥቀጣ ድምጽ የነበረበት፣ አካባቢውም የሚቀፍ ዓይነት ነበር፡፡ ከጋራዡ አለፍ ብለው፣ እንደሱቅ መንገዱን ተከትለው የተሠሩ ግቢ የሌላቼው የቁጠባ ቤቶች ነበሩ። ከእነዚያ ምርጊታቼው የረገፈና የጣራቼው ቆርቆሮ የዛገ አሮጌ የቁጠባ ቤቶች መካከል ማኅደረ ወደ አንደኛው ስትገባ አስታውሳለሁ፡፡ ለምን እንደሆን እንጃ ያም እይታ አሳዝኖኛል፡፡ ከሁለት ዓመታት በላይ በዚያ ስሜት ውስጥ ቆይቻለሁ። በመጨረሻ አቅሌን ስቼ ለስደት ስዘጋጅ ከእነዚያ ሁሉ ጓደኞቼ ይልቅ ማኅደረ የጠዬቀችኝን ዛሬ ላይ አስታውሰዋለሁ። ወደ አምስት የምንሆን ልጆች ከክላስ በፊት ሰብሰብ ብለን ተቀምጠን በየአፋችን ስናወራ፤ ከጎኗ ነበር የተቀመጥኩት፣ ዞር ብላ አይታኝ፣ “ዮኒ ሰሞኑን ልክ አትመስልም ደህና ነህ?'' “ደህና ነኝ” አልኩ፤ እየሳቅሁ! ለቅጽበት ትክ ብላ አይታኝ ወደ ሌሎቹ ጨዋታ ተመለሰች፡፡ ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ይመስለኛል ተሰደድኩ፡፡ የማኅደረ ነገር በዚያው አለቀለት፡፡ እንደው በሆነ በሆነ አጋጠሚ ለቅጽበት አስታውሻት ካልሆነ በስተቀር ሙሉ መልኳ ጭምር ከአእምሮዬ ጠፍቶ ነበር፡፡ እንደገና ማኅደረን ያገኜኋት ከ14 ይሁን 15 ዓመታት በኋላ ነበር፡፡ ሌላ ሰው ሆኜ ሌላ ሰው ሆና፡፡ የዛሬ ሰባት ዓመት ቤተሰቦቼን ጥዬቃ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ ነበር። በዚያውም አባታችን ያወረሰን ቦታ ላይ ወደ አገሬ ስመለስ የምኖርበት ያልኩትን ቤት እያሠራሁ ስለነበር ምን እንደደረሰ ለማዬት። የተወሰነ ጊዜ እንደቆዬሁ ታናሸ እህቴ ማሪያም ሰምራ ጋር የሆነ ውክልና ጋር የተያያዘ ነገር ለመጨረስ ስድስት ኪሎ ወደሚገኝ አንድ መሥሪያ ቤት ሄድን፤ ሁሉም ነገር ግራ ስለሚገባኝ እህቴ እንሂድ ያለችብኝ ቦታ ሁሉ እንደ ሕፃን ልጅ እየተከተልኩ ከመሄድና ፈርም ስትለኝ ከመፈረም ውጭ ሌላ ሥራ አልነበረኝም፡፡ ቢሮክራሲው ያሰለቼኝ ነበር፡፡

የዚያን ቀን እህቴ የምታደርገውን አድርጋ ለፊርማ እስክትጠራኝ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጨ ከዚያ ከዚህ ስትሯሯጥ አያታለሁ፡፡ የትላንትና ማሪያም አድጋ እንዲህ ከሩቁ ሳያት ግርምት ይሞላኛል፡፡ መኻል ላይ ዐሥራ አራት ዓመታት ክፍተት ስለነበር ያች ትንሿ እህቴ አድጋ ሳይሆን በትልቅ ቆንጆ ወጣት ሴት ቀይረው የጠበቁኝ እስኪመስለኝ፣በግርምትና በስስት አያታለሁ፡፡ ትርምሱን እታዘባለሁ፡፡ በጫጫታው እገረማለሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ ሁሉ ነገር እንደነበረ መሆኑ እየገረመኝ ይኼን ትርምስ የናፈቀ አእምሮዬ በጉጉት እያንዳንዱን ነገር ይቃርማል፡፡ በዚህ ቅጽበት ነበር ፊት ለፊ ከቆመው የመስተዋት ግርዶሸ ጀርባ ካሉት በርካታ ቢሮዎች የአንዱ በር ተከፍቶ በወረቀት የተሞላ ቢጫ ፋይል ያቀፈች ሴት ብቅ ያለችው፡፡ አእምሮዬ ለቅጽበት የት እንደሚያውቃት ከማሰብ ውጭ ለማስታወስ ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም፡፡ ረዘም ያለች ፣ረዥም ጸጉሯ ወደ ኋላ ታሥሮ የተለቀቀ ጠይም ሴት፤ ለራሴ ማኅደረ አልኩ፡፡ ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ እንኳን ከልጅነት ወደ አዋቂነት ከተሸጋገረ አጠቃላይ ለውጥ ውጭ የተጋነነ ለውጥ አልነበራትም፤ ውስጤ በደስታ ሲዘል ይታወቀኛል፡፡ ተነስቼ ወደ ፊት ሄድኩና ደንበኛ ለማስተናገድ በተሠራው የመስተዋቱ ክብ ቀዳዳ በኩል ጎንበስ ብዬ በጎላ ድምፅ ጠራኋት “ማኅደረ!'' ድንገት ዞረችና ወደ እኔ ሳይሆን ወደሚተራመሰው ሕዝብ የጠራትን ሰው ፍለጋ ዓይኞቿን አንከራተተች። እጄን አውለበለብኩላት፣ ግራ በመጋባት አዬት አደረገችኝና ወደ እኔ መጥታ በትህትና “አቤት!” አለችኝ፡፡ ፊቷ ላይ ምንም ዓይነት ማስታወስ አይታይባትም ነበር (በዚህ ትንሽ ቅሬታ እንደተሰማኝ አስታውሳለሁ ያን ያኽል አርጅቼ ይሆን? ከሚል ሐሳብ ጋር ) ካጎነበስኩበት ቀና ብዬ በፈገግታ ጠፋሁብሸ? አልኳት፡፡ ትንሽ የኃፍረት ፈገግታ ፊቷ ላይ እየታዬ ወደ ቀኝ በኩል ተራመደች፣ በዚያ በኩል መስተዋት ስላልነበር በግልጽ መተያዬት እንችል ነበር። እናም ትንሽ አዬችኝና “እምምም ዮኒ እንዳትሆን ብቻ?'' ብላ በሳቅ ስትፍለቀለቅ ነፍሴ በሐሴት ተሞላች። ከሆነ ዓይነት ሞት በኋላ የሚያውቁኝ ሰዎች ወዳሉበት ዓለም በትንሣኤ የተመለስኩ

እስኪመስለኝ ውስጤ በደስታ ዘለለ፡፡ ያቀፈችውን ፋይል የሆነ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችና፣ ሌላ በር ከፍታ ወደ እኔ መጣች ተቃቅፈን በሳቅ አውካካን፡፡ ከውስጥ መስተዋቱ ያንጸባርቃል ለዚያ ነው፤ አለች ይቅርታ ባዘለ ድምጽ። አንተ! አንቺ! እየተባባልን በግርምት ስንተያይ ቆዬን፡፡ እንዲህ ነበር ከጸጉር በቀጠነች አጋጣሚ ማኅደረን ዳግም ያገኜኋት፡፡ የዚያን ቀን እህቴ ጋር አስተዋወቅኋቼው፡፡ ታዲያ ስንወጣ እህቴ ምን አለችኝ?... “የፊቷ ጥራት ሲገርም!... ንኪው ንኪው ብሎኝ ነበር...'' ወይ ይኼ ፊት! አልኩ በውስጤ።