አትሮኖስ
224K subscribers
104 photos
3 videos
41 files
304 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ማኅደረ ጋር ስልክ ተቀያይረን ከተለያዬን ከሦስት ቀን በኋላ ይመስለኛል ደወለችልኝ፤ መቼ እረፍት እንደምትሆን ስላላወቅሁ የእርሷን ስልክ ስጠብቅ ነበርና ደስ አለ፡፡ በቀጣዩ ቀን ቅዳሜ ምሳ ልንበላ ተቀጣጠርን፡፡ ሳገኛት እንደመጀመሪያው ቀን ፍንድቅድቅ አላለችም ትንሽ ቁጥብ ሆና ነበር፤ ቢሆንም ብዙ አወራን። የሚበዛውን ያወራሁት እኔ ብሆንም እሷም ትምህርት አቋርጨ ከሄድኩ በኋላ የተወራውን፣ እዚያች ፎቶ ኮፒ ቤት ሄዳ ጓደኛዬን ምን ሆኜ እንደጠፋሁ እንደጠየቀችው ነገረችኝ፤ በዚህ ንግግሯ ውስጤ ተደሰተ፡፡ የሆነ የመፈለግ ስሜት ተሰማኝ፡፡ እንዲሁ የኮሌጅ የጓደኝነት ቅርርባችን የፈጠረው በሚመስል ግልጽነት ሕይወት እንዴት ነው? አልኩ፡፡ የዚያን ቀን እጄን ታጥቤ ልምጣ ብላ ሄዳ ከሩቅ ለአስተናጋጁ ሒሳብ ስትከፍል አዬኋት፡፡ አንዳንድ ዓመል ዕድሜ ልክ አይለቀም፡፡ ከዚያን ቀን በኋላ ግንኙነታችን አስገራሚ ነበር፡፡ረፍቴን ጨርሼ ወደ አሜሪካ እስክመለስ ድረስ በየቀኑ በሚባል ሁኔታ እንገናኝና ሻይ ቡና ብለን እንለያያለን፡፡ አልፎ አልፎም ራት እንበላለን፡፡ ስፈራ ስቼር… “ይቅርታ በግል ጉዳይሽ ከገባሁ እንዲሁ የጓደኝነት ጥያቄ ነው፤ አላገባሸም?'' አልኳት፡፡

“እምምምምም! በክኽ የኔ ነገር ትንሽ ግራ የገባው ነው፣ ስለ አንተ እናውራ.. እንተስ?" "እላገባሁም!" "ምነው በሰላም?" “እውነቱን ለመናገር በቁም ነገር አስቤበት አላውቅም፣ በዚያ ላይ ፋታ የሌለው ሕይወት ነው ያሳለፍኩት... ስልሽ እንኳን ስለሌላ ሰው ማሰብ ራስሽን የሚያስረሳ...እኔ እንጃ! ምናልባትም ይኼ አስቀያሚ መልኬ የሚስባት ሴት ጠፍታ ይሆናል” ተሳሳቅን። ከሦስት ወር ረፍቴ የሚበዛውን ማኅደረ ጋር ጥሩ ጊዜ አሳለፍን፡፡ አንድ ነገር እየገረመኝ ነበር፤ አንድም ቀን በቀጠርኩባት ሰዓት አይመቼኝም ብላኝ አታውቅም፤ ይኼ አደፋፍሮኝ ነበር ወደ አሜሪካ ልመለስ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ ከከተማ እንድንወጣ የጠዬቅኋት፤ አንገቷን እንዳቀረቀረች “ደስ እንዳለህ'' አለችኝ፡፡ የነገሮች ፍጥነት ገረመኝ። መታበይ መሆኑ ቆይቶ ቢገባኝም “አሜሪካና ሴት" የሚል አጉል ሃሰብ ውልብ ብሎብኝ ነበር፡፡ ያቺ ኮስታራ ለሰላምታ እንኳን ደጅ የምታስጠና ሴት፤ እንዲህ ስስባት የምትሳብ ስገፋት የምትገፋ ሆና ሳገኛት ምን ላስብ?! የት ከርሞ እንኳን እንደመጣ በወጉ ላላወቀችው ሰው ራሷን ጣል ስታደርግ ምን ልበል? ቢሆንም ይኼነው ብዬ በማልገልጸው ምክንያት ውስጤ ጨዋነቷን ይለፍፍ ነበር፡፡ ሀዋሳ ሄድን። እጅግ ውብ የሆነ ቀን ነበር ያሳለፍነው፡፡ በጀልባ ሐይቆቹ ላይ ቀዘፍን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን በእግራችን ብዙ ዞርን፣ ውስጤ እያደረግን ባለው ነገር ቢደሰትም... ውሃ፣ ጀልባ እና ዓሣ ሳይ ግን ከዚያ አካባቢ ሩጥ ሩጥ ብሎኝ ነበር፡፡ የሞሮኮ መከራዬ፣ ደስታዬ መኻል ዘብረቅ ብሎ እየገባ ያስቸግረኝ ነበር፡፡

የእግር መንገዳችን አድክሞን፤ ከሐይቁ ዳርቻ ያገኜነው አግዳሚ የድንጋይ ወንበር ላይ አረፍ አልን። ፀሐይ እየጠለቀች ነበር። ምን ላወራት እንደነበር እንጃ ብቻ ዞሬ ማኅደረን አዬኋት፤ ያ ምስሏ ዘላለማዊ ትዝታዬ ሆኖ በውስጤ ታተመ። ያ የምሽት ጀምበር ያረፈበት ጸጉሯ፤ በነፋስ በቀስታ እየተተራመሰ ተበታትኖ ፊቷን ከቦታል፤ ወርቃማዋ የምሽት ጀምበር እንደ ቲያትር ቤት መብራት ማኅደረ ጠይም ፊት ላይ ብቻ የበራች መሰለኝ። ፊቷ ከነተከበበት ውብ ጸጉሯ ሲታይ በጥቁር ሐር የተከበበ የወርቅ ዕንቁላል ይመስል ነበር። ከንፈሯ ጠብ ሊል የተንጠለጠለ ውብ ጤዛ!! ጀምበር እዚያ አድማሱ ላይ ሳይሆን ፊቷ ላይ የምትጠልቅ ነበር የሚመስለው። ድምቀቱ፣ ብነካው የሚያቃጥል የሚመስል ፍም ጠይምነት፣ ዓይኔን ሳልነቅል አዬኋት፤ አሻግራ አድማሱን ትመለከት ነበር። ወደ እኔ ዞራ ዓይናችን ሲገጣጠም በኃፍረት ፈገግ አለች፡፡ ድንገት “ለምን አንጠጣም?'' አልኳት፡፡ ሐሳቡ ከዬት እንደመጣልኝ አላውቅም። “እንጠጣ?” “...ስልሽ እንስከር!" “እንስከር?'' ብላ ምንቼገረኝ በሚል ስሜት ትከሻዋን ወደ ላይ ሰበቀች። ዝም ብዬ አዬኋት፡፡ ሳቀችና በኃፍረት አቀረቀረች፡፡ እጄን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጌ በኮንትራት የያዝነውን ሾፌር ጠራሁና ጥሩ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደን ጠዬቅሁት፡፡ አንድ ሰፊ ግቢ ያለው ቪላ የሚመስል ቤት ወሰደን፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ፣ አዳራሹ አለባበስና ወዘናቼው ምቹ ኑሯቼውን በሚያሳብቅ ወንዶችና ሴቶች ተሞልቷል፡፡ ከመድረኩ አንድ ድምፃዊ የጥላሁን ገሠሠን ዘፈን በሙሉ ባንድ ታጅቦ ይዘፍናል። ድባቡ ደስ የሚል ነበር። ከዚያ የሆነው ነገር ሁሉ እብደት ነበር፡፡ ሳናቋርጥ ጠጣን፣ተያይዘን ሰፊው መደነሻ ላይ በእነዚያ ለስላሳ ሙዚቃዎች ተወዛወዝን፣ ጥልቅ የሆነ ዝምታና መተቃቀፍ ውስጥ ሆነን ነበር የምንወዛወዘው፤ በሰዓቱ እኔ አልሰከርኩም ነበር፡፡ ማሂ ግን ትንሽ ሞቅ ያላት ይመስለኛል፡፡ አልፎ አልፎ ትንሽ ሚዛኗን እንደመሳት ያደርጋት

ነበር። በዚህ ዝምታ ውስጥ ነፍሴ እነዚያ ባሕር ዳርቻ ላይ የነበሩ መሸታ ቤቶች ውስጥ ዛናታ ጋር ያሳለፈቸውን ጊዜ ታስባለች። “ለምንድን ነው ሄድኩኝ ሳትለኝ የሄድከው?'' አለች ማኅደረ ከንፈሯ ጆሮዬን እስኪነካኝ ተጠግታኝ። “የት?'' ግራ ገብቶኝ ጠዬቅኋት። “ሱዳን…. ኬኒያ... እኔ እንጃ...አሜሪካ..." “ኦ!” ብዬ የምመልሰውን ሳስብ፣ “ትወደኝ ነበር አይደል?'' አለች፡፡ ሰክራለች፡፡
"በጣም"
“እዚያ ሆነህ አስታውሰኸኝ ታውቃለህ?” “ብዙ ጊዜ” ብዬ ዋሸኋት፡፡ “አሁንም ትወደኛለህ?'' አልመለስኩላትም ወደ ራሴ ስቤ አጥብቄ አቀፍኳት። ዘፋኙ ጨርሶ የዳንስ ወለሉ ላይ የነበሩት ሰዎች ወደየወንበራቼው መመለስ ጀመሩ። እዚህ ላይ ነበር እስከ ዛሬ የሚገርመኝ ነገር የተፈጠረው። ወደ ጠረጴዛችን ለመመለስ እጇን ይዠ በሰው መኻል መንገድ ስጀምር፣ ማሂ እጇን በቀስታ አስለቅቃኝ ተመለሰች፡፡መጀመሪያ ወደ መታጠቢያ ቤት የምትሄድ ነበር የመሰለኝ፡፡ ወደ መድረኩ ተጠግታ የባንዱ መሪ የሚመስለውን ጊታር ተጫዋች ጎልማሳ በምልክት ስትጠራውና በአክብሮት ወደ ፊት መጥቶ አጎንብሶ ሲያዋራት የሆነ ሙዚቃ እንዲጫወቱላት ልትጠይቅ ነው አልኩ። እንዲያውም የምትመርጥልኝን ሙዚቃ ለመስማት ሳልጓጓ እቀራለሁ?

የሆነው ነገር ግን በውኔም በሕልሜም ያላሰብኩት ነገር ነበር። ጊታር ተጫዋቹ እራሱን በፍጥነት ነቅንቆ በደስታ ፈገግ አለ። ወደ ደረጃው ጠቁሟት ቀድሟት ሄዶ ቆመ። በደረጃው በኩል ወደ መድረኩ ስትወጣ ራመድ ብሎ በአክብሮት እጇን ይዘ ደገፋት። ሁለቱም ወደተደረደሩት የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች ሄዱና የሆነ ነገር ሲነግራቼው በፈገግታ እራሳቼውን እየነቀነቁ ተስማሙ። እንዲያውም ጊታር ተጫዋቹ ወደ ፊት ራመድ አለና ማይክ አንስቶ ለማኅደረ አቀበላት፤ ተቀብላው ቆመች:: ሙዚቀኞቹ ጎን ለጎን በሹክሹክታ ተነጋግረው በስምምነት አውራ ጣታቼውን ከፍ እያደረጉ ምልክት ከተሰጣጡ በኋላ ለመጀመር ተዘጋጁ። ያኔ ደነገጥኩ! ወደ መድረክ ሮጨ እባካችሁ ትንሽ ሞቅ ብሏት ነው፤ ይቅርታ ለማለት አንድ ሁለት ጊዜ እግሬን ካነሳሁ በኋላ ግራ ገብቶኝ ቆምኩ። በጭንቀት ተውጨ አዳራሹን በዓይኔ ቃኜሁት ሁሉም ሰው ወደ መድረኩ ይመለከታል። ሙዚቃው ረጋ ብሎ ሲጀምር ማኅደረ ወደ ተመልካቹ ፊቷን አዞራ መሬት መሬት እያዬች ቆመች። ግንባሬን እዬፈተግሁ በኃፍረት አቀርቅሬ እንደቆምኩ ፈጽሞ ከማኅደረ ይወጣል ብዬ ያልጠበቅሁት ስርቅርቅና ውብ ድምፅ አዳራሹ ውስጥ ሲናኝ ባለማመን ቀና ብዬ አዬኋት። ድምፅዋ ውስጥ የሆነ መግለጽ የማልችለው የሚነዝር ስሜት ነበር፡፡ ብዙ ዓመት እንደዘፈነ የመድረክ ሰው ዓይኖቿን ከድና በእርጋታ ነበር
የምትዘፍነው። ሙዚቀኞቹም እንደ እኔው ጨንቋቼው ነበር መሰል ስትዘፍን በፈገግታ ተያዩ፡፡ አዳራሹ ጸጥ ብሎ ሙዚቃውና የማሂ ድምፅ ብቻ ሲንቆረቆር ምን አደረግሁ!?... አለቀስኩ!! ድብልቅልቅ አለብኝ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያንን ዘፈን ስንት ጊዜ እንደሰማሁት እግዜር ይወቅ፡፡ ደግሞ የወንድ ዘፈን'ኮ ነው። ተሸመ አሰግድ የተባለ አንጋፋ ድምፃዊ የድሮ ዘፈን፡፡ ከዚያ በፊት በሴት ሲዘፈን አልሰማሁም። "የኔ አካል የኔው ነህ ምን አወርስሃለሁ... አንጀቴና ልቤን ያው ትቸልሃለሁ። በሃሳብ በርሃ ብቃጠል ብቀልጥም... የመውደድን ርሃብ... የፍቅርን ውሃ ጥም... ካንተ ትንፋሸ በቀር... በምንም አልቆርጥም። ደምም ባልቋደስ ከወንድም ከእህትህ...

ካንጀቴም በማዘን ባልሆን እንደናትህ...ከኔም ሆድ በፍቅር ተቀምጠሃል- እንደቅንነትህ.. ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻለችም፤ ሳግ ተናነቃት፡፡ ማይኩን በሥርዓት አስቀምጣ ከመድረኩ በፍጥነት ወረደች፡፡ አዳራሹ ውስጥ የነበረው ሰው ረዥም ጭብጨባ እጅቧት ወደ እኔ መጣች፡፡ እያለቀሰች ነበር። ወደ ፊት ሄጄ አቀፍኳት። “እንሂድ!'' አለች፡፡ ተያይዘን ወጣን፡፡ ወደ ያዝነው ሆቴል ነበር በዝምታ የሄድነው፡፡ ቀን ላይ ለዬራሳችን ሁለት የተለያዩ ክፍሎች ብንይዝም በዚያ ምሽት ግን ወደ እኔ ክፍል ስንገባ ምንም አላለችም። ሌላ ክፍል መያዟንም የረሳችው ነበር የምትመስለው፡፡ ፍዝዝ ብላ ነበር፤ መጠጡ ይሆናል ብዬ አሰብኩ፡፡ በዝምታ ተጠጋኋት፣ ዝም! አቀፍኳት፣ ዝም! መሳሳም ጀመርን፤ ድንገት ዕንባዋ ተዘረገፈ “ማሂ ደሀና ነሽ? ወደ ክፍልሽ ልውሰድሽ?'' አልኳት ከልቤ ነበር፡፡ እራሷን በአሉታ ነቅንቃ በደከመ ድምፅ “እንተኛ'' አለችኝና ቀድማ ወደ አልጋው ተራመደች። ልብሶቻችንን አወላልቀን በጨለማው ውስጥ ስንተቃቀፍ ምን ገረመኝ? የሰውነቷ ልስላሴ፡፡ በሕይወቴ የመጀመሪያ ከሆነችው ዛናታ ጀምሮ አሜሪካ ከገባሁ በኋላ አልፎ አልፎ አብሪያቼው እስከወጣሁት ሴቶች ከማንኛቼውም እንደ ማኅደረ ገላ የሚለሰልስ ሰውነት አላጋጠመኝም፡፡ የሕፃን ልጅ ሰውነት እንኳን እንደዚህ አይለሰልስም። በዚያ ጨለማ ውስጥ የለቅሶ ሲቃ በሚተናነቀው ድምፅ ማኅደረ ደጋግማ የምትለው... “አፈቅርሻለሁ በለኝ!'' ነበር፡፡ “አፈቅርሻለሁ በለኝ!'' በዚያች ሌሊት ነበር ላገባት ውስጤ የወሰነው፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ይህን አባባሏን ፈጽሞ በተሳሳተ መንገድ ስለተረጎምኩት ነበር፡፡ በትክክል የመሰለኝ ማኅደረ ኮሌጅ እያለን ያፈቀረችኝና በመሄዴ የተጎዳች፣ ለዓመታት ፍቅሯ ውስጧ ቆይቶ ስታገኜኝ የፈነዳ ዓይነት ነበር፡፡ ለምን ፎቶ ኮፒ ቤት ሄዳ የት እንደሄድኩ ጠየቀች? ለምንስ ሳትነግረኝ ሄድክ ብላ ወቀሰችኝ? ጓደኝነታችን በግሩፕ ነበርና እንደ ጓደኛ ካወራች

“ለምን ሳትነግረን ሄድክ?” ነበር ማለት የነበረባት። ለምን መታወሷን ማወቅ ፈለገች? በግሏ ነበር ያዘነችው አልኩ፡፡ እንዲያውም ይኼን ያኽል ዓመት ብቻዋን እያሰበችኝ አስታውሻት ባለማወቄ ጸጸት ቢጤም እንደተሰማኝ ትዝ ይለኛል። ምንም እንኳን ከአሜሪካ ነቅዬ ለመምጣትና አገሬ ላይ ለመኖር ካሰብኩ ቆይቼ የነበረ ቢሆንም ከፉከራ ያለፈ ቁርጥ ያለ ጊዜ አላስቀመጥኩም ነበር። ማኅደረን ካገኜሁ በኋላ ግን ወሰንኩ። ተመልሼ የምሄደው ነገሮችን ለማስተካከል ቢሆንም ይኼንን ግን ለማንም አልተናገርኩም ነበር፤ ለእርሷም ጭምር፡፡ እንዲያውም ሥራዋን እንድታቆም ያሳመንኳት አሜሪካ ከሄድን ምን ያደርግልሻል? ብዬ ነበር። በቀጣዩ ቀን እዚያው ሀዋሳ ራት ላይ ላገባት እንደምፈልግ ነገርኳት መልሷ እስካሁን ይገርመኛል። “ከፈለግህ እሺ!” “ማኅደረ! እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ! ሚስቴ እንድትሆኚ በጣም ነው የምፈልገው" አልኳት ከልቤ ነበር፡፡ ዕንባዋ ድንገት ተዘረገፈ። ምንም ሊገባኝ አልቻለም ለምንድን ነው የምታለቅሰው?! እስከአሁን ያ ለቅሶዋ አልገባኝም፡፡ እንዲህ ባለ የቁልቁለት ሩጫ ነበር ወደ ትዳር የገባነው፡፡ ማኅደረ ጋር ከተጋባን በኋላ፣ ስለ ቤተሰቧም ሆነ ስላለፈ የፍቅር ሕይወቷ፣ ከእራሷ አንደበት ምንም ነገር ሰምቼ አላውቅም። አታወራም፤ በእርግጥ ጠይቂያት አላውቅም፡፡ በተለይ ስለ ፍቅር ሕይወቷ ላለማንሳት እጠነቀቅ ነበር። በደፈናው የሆነ ሰው ወይም ሰዎች እንደነበሯት ይገባኛል፡፡ እኔ ራሴ በፍቅር ስለከነፍኩላት ዛናታ ለማን ተነፈስኩ? ያውም እንደ ትዳር አብረን ኖረን፡፡ እንደ ዘላለም ከረዘመውና ሰው እስኪሰለች ከምዘረዝረው ታሪኬ ውስጥ ለምን ዛናታ ጋር ያሳለፍኳቼውን ሰባት ውብ ወራት ቆርጨ እዘላቼዋለሁ? በአፍሪካና አውሮፓ መካከል ለእኔ ጀልባም፣ ደላላም ሳይሆን ያቺ ሴት ነበረች ድልድይ የሆነችኝ፡፡ ያውም ስለ እሷ

በሰብኩ ቁጥር የፍቅራችን ሙቀቱና ትዝታው እስከ ዛሬም በልቤ ወላፈኑ እየተሰማኝ።... እናም ማኅደረ ያለፈ የፍቅር ታሪኳን ካልነገረችኝ ብዬ እልተቀዬምኳትም:: ግን አንዳንድ ውልብ የሚሉ ጉዳዮች ያለፈውን ለማወቅ እንድጓጓ የሚያደርጉብኝ ጊዜ አለ፡፡ ለምሳሌ፣ ያቺ ሃይማኖት የምትባል ጓደኛዋ ቤታችን መጥታ በሄደች ቁጥር ማኅደረ ዓይኖቿ ያባብጣሉ፤ ስታለቅስ ባላያትም እንዳለቀሰች ግን ይገባኛል። ለቀናት የሚቆይ ድብርት ይጫጫናታል። ምን እያወራቻት ብትሄድ ነው እንደዚያ ስሜቷ የሚረባበሸው? እላለሁ። ቤተሰቦቿን አውቃለሁና ስለ ቤተሰብ ጉዳይ እንደማይሆን ግልጽ ነው። እንግዲህ ሁለቱ ብቻ የሚያውቁት የሚያስለቅስ ጉዳይ ምን ሊሆን ይችላል?

አለማወቅ ደጉ!

የሚስቴን ገላ ከእኔ በፊት ማን እና እንዴት እንዳቀፈው የመስማት ፍላጎት የለኝም። ድንግልና ለእኔ የሥጋ ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ አንዲት ሠላሳ ዓመት ያለፋት ሴት ለምን ድንግል ሆና አላገኜኋትም የምል ጅልም አይደለሁም። ቅሬታዬ የሚመነጨው እየገፋችኝ ያለችው እሷ ናት ወይስ ውስጧ ያለ ሌላ ሰው? የሚለውን ሳስብ ነው፡፡ ይኼንንም ግን አልጠዬቅሁም... ለምን? የማናውቀውን ታሪክ በግልጽነት ስም በማውራት የትዝታ ሥጋ ማልበስ፤ ነገሩ ከሆነው በላይ በሐሳባችን ሲሆን እንዲኖር መፍቀድ ነው፡፡ አጠቃላይ ዕውቀት የዝርዝሩን ያኽል አያበሳጭም፣ አያስቀናም፣ አያሳዝንም፤ የሆነ ፍቅረኛ ነበራት ወይም ፍቅረኞች ነበሯት፤ በቃ! ካወራንበት ያ የሆነ የማይታወቅ ሰው፤ መልክ፣ ስም፣ ባሕሪ፣ ሥራ፣ ሐብት እና በፍቅር ያሳለፉበት ጊዜ ሁሉ ዕውቀታችን ይሆናል፤ ያወቅነው ነገር ነው በመረጃ እየተደገፈ የሚያበሳጨን እና የሚያስቀናን፡፡ የማወቅ ጉጉታችን ቢገፋን እንኳን፣ መተውን የመሰለ ፈውስ የለም። በአንዳንድ ጉዳዮች አለማወቅን የመሰለ ዕውቀት የለም። አዎ! ማን ጋር ምን እንዳደረገች ከግምት ባለፈ አላውቅም፤ ስለማላውቅ አላስታውስም፤

ስለማላስታውስ ምንም አላደረገችም፤ ስለዚህ በድንግልናዋ ያገኜኋት የምወዳት ሚስቴ ናት እለዋለሁ ለራሴ፡፡ ሁላችንም ልናወራው የማንፈልገው ታሪክ ይኖረናል፡፡ ምናልባትም ዋናው ታሪካችን ያ ልናወራው የማንፈልገው ታሪክ ይሆናል፡፡ መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ዛፍ ሥር አለው፡፡ የደበቅነው ታሪካችን እንደ ዛፍ፣ አላፊ አግዳሚ ለሚያዬው ሕይወታችን የማይታይ ሥር ነው። አወራነውም- አላወራነውም፣ ታዬም- አልታዬም እዚያ የተደበቀ የታሪክ ሥራችን ላይ ነው የምንቆመው። ወደ ፊት እስከቀጠልን ድረስ ተመልሶ መነካካቱ፣ ምናልባትም ዛሪያችንን ሊረብሽ ይችላልና ባለቤቱ ፈቅዶ እስኪተነፍሰው መተው ይሻላል ባይ ነኝ፡፡ ያለፈ ነገራችን እየተመለሰ ዛሪያችንን እስካልረበሼ ድረስ፣ ሥራችንን በነበረበት ትተን በሚታዩ ፍሬዎቻችን፣ በሚስቡ አበቦቻችን፤ መፋቀር፣ መዋደድ፣ መከባበር አንችልም ወይ? እንዲሀም ባስብም ግን የማኅደረን የበዛ ዝምታ ውስጤ ይሁን ብሎ
ተቀብሎታል ማለት አይደለም፡፡ ባልጠይቃትም ላገቡት ሰው ይቅርና ለጓደኛ እንኳን ስለራሳችን የሆነ ነገር እንላለን'ኮ! ሰዎችን አወቅን ስንል አብረናቼው በመኖር ካዬነው ባሕሪያቼው፤ ራሳቼው ከነገሩን ታሪካቼው፤ ፍላጎትና ስሜታቼው ተነስተን የምንገነባው ማንነታቼውን አወቅን ማለታችን አይደለም እንዴ? እከሌ እንዲህ ነው ስንል፣ ከእነዚህ ምንጮች ከሰበሰብነው መረጃ ተነስተን ነው መቼስ! እና ማንን ነው ያገባሁት? ስል የማገኜው መልስ ከአንድ ዓረፍተ ነገር አይዘልም፡፡ ያገባሁት ንግድ ሥራ ኮሌጅ ስንማር አውቃት የነበረች፣ በኋላ አካውንታት የሆነች ማኅደረ ሰላም ዓምደ ሚካኤል የምትባል ሴት ናት፡፡ ስለ እርሷ ከማውቀው ታሪኳ ይልቅ ስሟ ይረዝማል፡፡ አገሬ ላይ በወግ በማዕረግ አግብቼ፣ ልጅ ወልጄ በመኖሬ ፍጹም ደስተኛ ብሆንም፤ አንዳንዴ እንዲህ ዓይነት ስሜቶች ዘብረቅ እያሉ ሕይወቴን ያጠያይሟታል፡፡ ሙሉ ጨለማ ወይም ሙሉ ብርሃን የሚባል ሕይወት በዚህ ምድር ላይ የለም፡፡ ጠይምነትም ቢሆን መተላለፊያ ድልድያችን እንጂ ሕያው የሕይወት ቀለም

አይደለም፡፡ የማኅደረ_ ዝምታና ቀዝቃዛነት ሲበዛብኝ፣ ለዓመታት ከእጄ ላይ ያላወለቅሁትን ብራዝሌት' በትካዜ እነካካለሁ። ሙቀት፣ ስሜት፣ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ መላፋት፣ ቀልድ፣ ሕልም የተሞላባት ትንሽ የደሃ ጎጆ በአእምሮዬ ውልብ ትላለች፡፡ የአንድኛችንን ወሬ / ሌላኛችን በጉጉት የምናዳምጥ ነፍሳት በዚያች ጎጆ ውስጥ ነበርን፡፡ አንዳንዴ አንዲት ሴት አግብቼ የሌላ ሴት ማስታወሻ እጄ ላይ ማስቀመጥ ነውር እየሆነብኝ፣ አውልቄ ልጥለው አስብና “ግዴለም ባይመለሱበትም የተሻገሩበትን ድልድይ መስበር ግዴታ አይደለም!” እላለሁ - ለራሴ!! ማንም የማያስታውሳቼውን ሰዎች፣ ማንም ከነማይዘክረው ታሪካቼው፤ በዚህ ምድር እንደሌሉ፣ እንዳልተፈጠሩ ከመርሳት፤ ትንሽ ሐውልት (በአደባባይም ባይሆን) ውለታቼው ባረፈበት ሰው ልብ ቢቀር ምኑ ነው ክፋቱ!? ይህች 'ብራዝሌት' ሌላ ትርጉም የላትም... የአንዲት ውብ ነፍስ ማስታወሻ ናት!!

ተፈፀመ።

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ማታ ቤት ገብታም ስለሴትዬዋ ማሰቧን አላቋረጠችም ነበር፡፡ ወንድ ብትሆን "ፍቅር ያዘኝ እንዴ?ብላ ራሷን መጠራጠር ትጀምር ነበር...ሴትዬዋ የማሳጅ ቤት ባለቤት መሆኗን ከቢዝነስ ካርዷ ብትረዳም ‹‹የፈለገችኝ ለሌላ ስራ ቢሆንስ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት።

እንደምንም ራሷን   ተቆጣጠረችና አራት ቀን በመቆየት በአምስተኛው ቀን ደወለችላት፡፡

"ሳባ  እባላለሁ...በቀደም  ለታ  ቢዝነስ  ካርድሽን  ሰጥተሽኝ  ነበር..."ብላ.ቦታውንና ሁኔታውን ልትዘረዘርላት ስትጀምር አቋረጠቻት

"አውቄሻለሁ...ስለደወልሽ ደስ ብሎኛል..." የሚል መልስ ሰጠቻት
ትብለጥ፡

"አመሰግናለሁ"

"እሺ.ተገናኝተን.እናውራ፡

"ይቻላል"

"መቼ ይመችሻል?"

"ያው ያንቺን አላውቅም እንጂ እኔ ዛሬ እሁድ ስለሆነ  ይመቸኛል...ካልሆነ ግን በማንኛውም ቀን ከ11.30 በኃላ መሆን ይችላል።››

"ግድ የለም ይመቸኛል...ሰፈርሽ የት ነው፡፡"

"ላንቻ....ግሎባል አካባቢ፡፡"

‹‹በቃ ስምንት ሰዓት መኪና ልክልሻለሁ...ቁጥርሽን እሰጠዋለሁ… ይደውልልሻል።"
‹‹እረ  አያስፈልግም  ቦታውን  ንገሪኝና  በላዳ  መጣለሁ፡፡"አለቻት  ያልጠበቀችውን ነገር በመስማቷ ግራ ተጋብታ፡፡

"አይ እሱ  አሳሳቢ ጉዳይ አይደለም...ቻው በቃ፡፡ ስምንት ሰአት ይመጣልሻል፡፡ በኃላ እንገናኝ።››ስልኩ ተዘጋ።

ይበልጥ ገረማት። ለእሷ እቤት  ድረስ  መኪና? መደመም  ውስጥ  የሚከት  ነው፡፡ቢሮዋ እንኳን ጉዳይ እንድታስፈፅም የሆነ ቦታ ሲልካት..አለቃዋ ቀብረር ብሎ‹‹እስከ እዛ በታክሲ ሄደሽ ..ከዛ በእግር ተሻግረሽ ወደዚህ ተጠምዝዘሽ ከዛ ሌላ ታክሲ ተሳፍረሽ....›› ብሎ ነው የሚያዛት። አሁን ግን መኪና ከሹፌር ጋር ለዛውም ቤቷ ድረስ?ለዛውም ለራሷ ጉዳይ፡፡

‹‹ይሄ  ነገር  የእውነት  ህይወቴን   የሚቀይር   አጋጣሚ   ይሆን   እንዴ?..›› ስትል አሰበችና ሰዓቷን ተመለከተች …5 ሰዓት ሆኗል።ፒጃማዋን አውልቃ ልብስ ቀየረችና ቦርሳዎን ይዛ አንድ ክፍል  ቤቷን  ቆልፋ  ግቢውን  ለቃ  ወጣች። ያመራችው እዛው ሰፈር ወደሚገኝ አንድ ፀጉር ቤት ነው።‹‹አዎ የተለየ ሰው ጋር ለተለየ አገጣሚ የተለየ ሆኜ መሄድ አለብኝ፡፡"ብላ ወስናለች፡፡ባላት ሶስት ሰዓት ወስጥ በተቻላት እና አቅሟ በፈቀደላት መጠን አምራና ዘንጣ የሚላክላትን ሹፌር መጠበቅ እንዳለባት ተሰምቷታል። ዝግጅቷን ጨርሳ 10  ደቂቃ  ያህል  እንኳን ሳታርፍ ነበር ስልኳ ያንጫረረው። ስልኳ እጇ ላይ ስለነበረ ፈጥና አነሳችው።

‹‹ሄሎ፡፡››

‹‹የእኔ እመቤት ጤና ይስጥልኝ፡፡ ደምሳሽ እባላለሁ፤አንቺን ወደ ቤት ለመውሰድ ተልኬ ነበር?››

‹‹ወደ ቤት?›› አለች ደንግጣ...የደነገጠችበት ምክንያት ፈፅሞ ቤት  የሚባል በምናቧ ስላልነበረ ነው... የጠበቀችው ሆቴል ወይም ካፌ..ወይም የሆነ  መዝናኛ ቦታ ነበር፡፡"

ደዋዩ  ፀጥ  ስትልበት  ግራ  ተጋብቶ "ምነው  እመቤቴ  ችግር  አለ.እንዴ?"ሲል ጠየቃት።
"እረ ምንም ችግር የለም...በቃ እየወጣሁ ነው"
"ግሎባል ጋር ቆሚያለሁ አቅጣጫውን ንገሪኝና ልቅረብልሽ"

"ቅርብ ነኝ ...እዛው እመጣለሁ"ብላ ስልኩን አቋረጠችና ቤቱን በመዝጋት ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ እንግዳና የማይገመቱ ነገሮች ናቸው እየገጠሟት የነበረው፡፡ ደግሞ የሹፌሩ ትህትና "ማን ነች ብላ ብትነግረው ነው እንዲህ እመቤቴ እያለ ቅንጥስጥስ የሚለው?" በማለት እያጉረመረመች ዋናው አስፓልት ላይ ወጣች። ወደ ግሎባል ተጠጋች፡፡ ወዲህ ማዶም ሆነ ወዲያ ማዶ ምንም መኪና አይታያትም...ስልኳን አወጣችና ደወለች፤ከአጠገቧ ከ5 ሜትር ርቀት አካባቢ በእጅ ምልክት ሲሰጣት አየችው፡፡ሰውዬውን ከዚህ በፊት አይታዋለች፤ በቀደም ከሴትዬዋ ጋር የእሷ ጋርድ ሆኖ ቢሮዋ ድረስ መጥቶ ነበር፡፡ የመኪና በራፍ ይዞ ቆሟል፡፡መጥታ እስክትገባ እየጠበቀ ነው፡፡ ትህትናው ከሰውነት ግዝፈቱና ከመወጣጠሩ ጋር ፈፅሞ አብሮ የማይሄድ ነው የሆነባት።መኪናዋ እጅግ ዘመናዊ ከመሆኗ የተነሳ ከዚህ በፊት እንኳን ልትቀመጥበት በአስፓልቱ ላይ እራሱ ሲነዳ የምታየው በጣም አልፎ አልፎ ነው።ለዛ ነው ገና ከቤቷ ቅያስ ወጥታ አስፓልቱን እንደያዘች አይኗ የገባው የመጀመሪያው መኪና ቢሆንም  ለእኔ የተላከ ይሆናል ብላ ስላልገመተች ትኩረት ያልሰጠቸው፡፡ እየፈለገች የነበረው ሌላ ቪታራ ወይም ቪትስ አይነት መኪና ነበር።

በደመነፍስ እየተንሳፈፈች ሄደችና ተጠጋችው፡፡በአንድ እጅ የመኪናውን በራፍ እንደያዘ ጎንበስ ብሎ በሌላ እጅ ወደውስጥ እንድትገባ አመለከታት.. ገባች። የመኪናው መቀመጫ ራሱ የተለየ ነው። ሁሉ ነገሩ የተሟላለት የሀብታም ወንደላጤ ሳሎን ነው የሚመስለው፡፡ ዙሪያውን የተገጠገጠው በሚያብረቀርቅ ቡኒ ቆዳ የተለበጠው ምቹ መቀመጫ ፊት ለፊት የሚታየው አነስተኛ ፍሪጅ፤ ከዛ ከፍ ብሎ ዘመነኛ የፈረንጅ ክሊፕ እያጫወተ ያለ ቲቪ...ሁሉም  ያምራል።‹‹አሁን ይሄን ያለው ሰው ቤት ምን ያደርግለታል?››። ስትል  በውስጧ እያልጎመጎመች ፈራ ተባ በሚል ስሜት ኮርነር ላይ ሄደችና ተቀመጠች።

ሹፌሩም ‹‹እመቤቴ የሚጠጣ ነገር ከፈለግሽ ፍሪጅ ውስጥ አለልሽ ፤ሌላ የሚያስፈልግ ነገር ካለ ጠይቂኝ›› አለና በራፉን ዘግቶ በፊት ለፊት ዞሮ ሄደና የሹፌሩን ቦታ ይዞ ማሽከርከር ጀመረ፡፡...ትንሽ  እንደተጓዙ  በእሷ  እና  በእሱ መካከል  ያለውን  ክፍተት  በተንሸራታች ጥቁር መስታወት  ዘጋው። ተንፈስ  አለች.. የተሻለ ነፃነት ተሰማት፡፡ ከ20 ደቂቃ በሀሳብ የሚያናውዝ ጉዞ በኋላ ካዛንቺስ ደረሱ፡፡ ከስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ቢሮ ቀጥሎ ባለው ቅያስ ተጠምዝዞ ገባና የተወሰነ ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ አንድ ግዙፍ ግቢ ውስጥ ይዟት በመግባት ጋራዥ  አቁሞ በፍጥነት ዞሮ በመምጣት በክብር እንዳስገባት በክብር እጇን ይዞ አወረዳት፡፡ እየመራት ወደ ግዙፉ ቪላ ቤት ይዟት ገባ። በእውነት መኖሪያ  ቤት  ሳይሆን የነገስታት የእልፍኝ አዳራሽ  ነው ሚመስለው፡፡ድባቡ ያስፈራል፤ በራፉን አልፈው ወደውስጥ አንድ ሶስት እርምጃ ዘልቀው እንደገቡ  የሆኑ  ደልደል  ያለች ነጭ ሽርጥ ያደረገች ሴትዬ  ከግራ  በኩል  ካለው  ኮሪደር  ድንገት ወጣችና.

.."እመቤቴ እንኳንም በሰላም መጣሽ"በሚል ቃል የታጀበ በሞቀ ፈገግታ ካመጣት ሹፌር ተቀብላት ወደ ውስጥ ይዛት ዘለቀች፡፡ሹፌሩ ቀኝ  ኃላ ዞሮ ተመልሶ ወጣ፡፡

ሴትዬዋ እየመራች ወስዳ ግዙፉ እና ባለግርማ ሞገሱ ሶፋ ላይ እንድትቀመጥ ካደረገች በኋላ"የሚጠጣ ምን ላምጣ?"ስትል ከአንገቷ ጎንበስ ብላ በትህትና ጠየቀቻት፡፡

‹‹አይ ግድ የለም…ምንም አያስፈልግም፡፡››ስትል መለሰችላት፡፡

‹‹አንድ ነገርማ ያዢ"

‹‹እንግዲያው ውሀ ይሁንልኝ›› አለች።እውነት ውሀ ጠምቷት ሳይሆን በህይወቷ እንዲህ አይነት ግራ የገባው ነገር ገጥሟት ስለማያውቅ በደመነፍስ  ነው ያዘዘችው።
//
ከ10 ደቂቃ ጥበቃ በኋላ ሴትዬዋ በቀደም ካየቻት የተለየች ሆና መጣች፡፡ የሆነ የደቡብ አፍሪካ ወይም የታንዛኒያ የባህል አምባሳደር ነው የምትመስለው…ከላይ ከሻሽ አስተሳሰሯ እስከ ተጫማችው ጫማ ልዩ ኦሪጅናል አፍሪካዊ መስላ ነው የጠበቀቻት፡፡ ያው የሴትየዋ አለባበስ ለሳባ አዲስ ሆነባት እንጂ ለእሷ የተለመደና በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን የምትጠቀምበት ነው፡፡፡የሞቀና የጋለ ሰላምታ ሰጥታት ከተቀመጠችበት ሶፋ ላይ ልክ ለረጅም አመት እንደምታውቃት ታላቅ እህቷ አንድ እጇን ትከሻዋ ላይ ጥላ በፍቅርና በፈገግታ   እያወራቻት ወደሚቀጥለው ክፍል
ይዛት ገባች…፡፡

ከሳሎኑ በመጠኑ ጠበብ ያለ መለስተኛ የምግብ አዳራሽ የሚመስል ክፍል ነው፡፡ አንድ አስራ ምናምን ሰዎች በዙሪያው የሚያስቀምጥ ግዙፍ የምግብ ጠረጴዛ ሲኖር በሌላው ጥግ ደግሞ ሶስትና አራት ሰው የሚያስተናግድ ጠረጴዛ አለ...ያ ሰፊ ጠረጴዛ ጎን ያለ ሌላ አነስተኛ ጠረጴዛ ሲኖር ሙሉው በምግብ ተሞልቷል፡፡ ወደእጅ መታጠቢያው ይዛት ሄደችና ከታጠቡ በኋላ ፊት ለፊት በምግብ የተሞላው አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ ተቀመጡ….ከጥዋት ጀምሮ ምንም እንዳልቀመሰችና በጣም እርቧት እንደነበረ ያወቀችው አሁን ምግቡ ፊት ለፊት ስትቀመጥና አንጀቷ በምግብ አምሮት ድምፅ አውጥቶ ሲንጓጓ ነው፡፡

እንግዲህ የምትወጂውን የምግብ አይነት ስለማላውቅ በግምት ነው ያሰራሁት.. ከመሀከሉ የሚመችሽን ራስሽ ምረጪ››አለቻት…
እሷም በውስጧ‹‹አይ አለማወቅ…አሁን እዚህ ጠረጴዛ ላይ ካለው ምግብ አልበላለት የሚል ሰው ይኖር ይሆን?›› አለችና…እሷ ፊት ለፊት እንደተቀመጠችው ሴትዬ አይነት ጥቂቶች ቢሆኑም እንደማይጠፉ አሰበችና ከየምግቡ እየቆነጣጠረች በምግብ ሰሀኑ ላይ ማድረግ ጀመረች…ያው ትዝብት ላይ ላለመውደቅ በማሰብ ከምትፈልገው ግማሹን ያህል ብቻ ነው ያነሳችው….ቀላል ወሬ እየወሩ ለእሷ ከባድ የሚባል ምሳ ከተመገቡ በኋላ አጃቸውን ተጣጥበው ወደ ሳሎን ተመለሱ..ለዋናው ውይይት ጎን ለጎን ተቀመጡ፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ማታ ቤት ገብታም ስለሴትዬዋ ማሰቧን አላቋረጠችም ነበር፡፡ ወንድ ብትሆን "ፍቅር ያዘኝ እንዴ?ብላ ራሷን መጠራጠር ትጀምር ነበር...ሴትዬዋ የማሳጅ ቤት ባለቤት መሆኗን ከቢዝነስ ካርዷ ብትረዳም ‹‹የፈለገችኝ ለሌላ ስራ ቢሆንስ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት። እንደምንም ራሷን   ተቆጣጠረችና አራት ቀን በመቆየት…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቢ


‹‹እሺ ሳባ ህይወት እንዴት ነው?››

‹‹አሪፍ ነው…ምንም አይል?››

‹‹ማለቴ የስራ ህይወትሽ እንዴት ነው..ደስተኛ ነሽ?››

‹‹አዎ በስራው ደስተኛ ነኝ….ግን ክፍያው በቂ አይደለም…ማለቴ  በቂ  ሊሆን ይችላል ለእኔ ግን እየበቃኝ አይደለም፡፡›› ስትል በምሬት መለሰችላት፡፡
‹ይገባኛል…አየሽ አንቺ የተማርሽ ቆንጆና ማራኪ ወጣት ብትሆኚም በዕድሜ ግን ገና ለጋ ወጣት ነሽ…ገና ብዙ ብዙ ዕድል ይጠብቅሻል.. በህይወት የተሰጠሸን እድል ትጠቀሚበታለሽ ወይስ ታባክኚዋለሽ….ዋናው ጥያቄ ይሄ ነው፡፡››

‹‹ማለት አልገባኝም፡፡››አለቻት..እውነትም አለመግባትም ብቻ ሳይሆን  ይባስ ብሎም ግራ ገብቷታል፡፡
ስለጀመረችላት ወሬ ይበልጥ ማብራሪያ ትሰጠኛለች ብላ ስትጠብቅ አሷ ‹‹እስኪ ተነሽ አንድ ቦታ ሄደን እንምጣ›› ብላት ቀድማት ከመቀመጫዋ ተነሳች...ሳባም ያለምንም ማቅማማት ተከትላት ተነሳችና ከኋላዋ ተከተለቻት፡፡
በፊት ለፊት በር ትወጣለች ብላ ስትጠብቅ ወደኋላ በር አመራች ..ረጅም ኮሪደር ሰንጥቀው ካቋረጡ በኋላ ወደውጭ ወጡ፡፡ በፅድና በተለያዩ አበቦችና አትክልቶች የተሞላ ውብ ግቢ ነው፡፡በረንዳውን ወርዳ ወደጓሮ ዘልቃ ገባች… ‹‹ይህቺ ሴትዬ ጓሮዋን ልታስጎበኘኝ ነው እንዴ?››እያለች  በማልጎምጎም  ተከተለቻት፡፡ግን ተሳስታ ነበር…፡፡እስከመጨረሻ ጓሮውን ሰንጥቀው ከጨረሱ በኋላ ሰማይ ጠቀስ በሆነው የብሎኬት አጥር መሀከል የሚያብረቀርቅ ወርቅ  ቅብ  አይነት  ቀለም የተቀባ የላሜራ ግዙፍ በር አለ..በራፉ ጋር አንድ ጥቁር  ሱፍ  የለበሰ  መልኩም ጥቁር የሆነ ወጠምሻ ሰው ቆሟል ፡፡
የኋላ ቤት የኋላ በራፍ በመኖሩ ተገርማ ሳትጨርስ ጭራሽ ጠባቂ ስታይ‹‹ይሄ ምን ጉድ ነው?››ስትል ነበር በውስጧ የጠየቀችው
‹‹….ሴትዬዋ ሀሽሽ አከፋፋይ ትሆን አንዴ?››መልስ ባታገኝም በውስጧ የጠየቀችው ጥያቄ ነበር፡፡ወጠምሻው ጠብ እርግፍ በማለት በትህትና እጅ ነሳና በራፉን ከፈተላቸው፡፡ተያይዘው በራፉን አልፈው ወጡ፡፡የወጡት ግን ወደ አስፓልት አይደለም ወይም ኮረኮንች መንገድ ላይ ወስዶ የሚጥልም አይደለም…ወደ ሌላ ግቢ እንጂ፡፡ ግቢው በግምት አንድ ሺ ካሬ ስፋት ያለው

ሲሆን የሎጅ አይነት አሰራርና አደረጃጀት የተከተለ ነው….ራቅ ራቅ ብለው አንደኛው ከአንደኛው በራፍና መግቢያ ተቃራኒ እንዲሆን ተደርጎ በቁጥር አስር በጎጆ ቅርፅ የተሰሩ ግድግዳቸው ባህላዊ ይዘት ኖሮት በተጠረበ ድንጋይ በጥንቃቄ የተሰሩ ቤቶች ዙሪያቸውን በተክሎች፤በአበባና፤በሀረጎች የተሸፈነና   የተከለለ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
ትብለጥም‹‹ይሄ አንደኛውና ዋነኛው የስራ ቦታችን ነው…ሌሎች ሁለት ቦታዎችም አሉን…ዋናው ግን ይሄ ነው፡፡››በማለት ወደ አንዱ እየመራች ወሰደቻት፡፡
የተዘጋውን በራፍ እጄታውን ጫን አለችና ገፋ አድርጋ ከፈተችው..ሶስት ክፍል አለው፡፡አንዱ ሻወር ቤት…ሁለተኛው ከሻወር  ቤቱ የተያያዘ  መልበሻ  ክፍል፤ሲሆን ሌላው ዋናውና ሰፋ ያለው ክፍል ነው፡፡ ሰፊውና ዋናው ክፍል ውስጥ አንድ ቁም ሳጥን ሁለት ደረቅ ወንበሮች፤ከአንድ አነስተኛ ጠረጴዛ ጋር አንድ መካከለኛ ቁመት ያለው ሰው በምቾት ማስተኛት የሚችል ረዘም ያለ በነጭ ቆዳ የተለበጠ ሶፋ ሲኖር ወለሉ መካከል ላይ ሰፊና ረጅም የማሳጅ  ጠረጴዛ አለ፡፡ዙሪያውን ቃኝታ ሳትጨርስ ደረቅ ወንበሩ ላይ ቁጭ ብሎ የነበረ አንድ የተወጣጠረ ጡንቻ ያለው ወጣት ከተቀመጠበት በፍጥነት ተነሳና ወደ እነሱ በመቅረብ  ‹‹እንኳን በሰላም መጣችሁ ›› ሲል መጀመሪያ ትብለጥን ከዛ ደግሞ ሳባን ጨበጣቸው…
ሳባ ሲጨብጣት የእጁ ልስላሴና ጥንካሬ ውስጧ ድረስ ተሰማት፡‹‹እንዴት በዚህ መጠን ለስላሳና ጠንካራ ሊሆን ቻለ..?››ስትል ተገረመችበት፡፡‹‹አይ  እንደዛማ ሊሆን አይችልም…እኔ ተሳስቼ ነው፡፡›› አለችና ትኩረቷን ለመሰብሰብ ሞከረች፡፡
‹‹ሶፈኒያስ ይባላል እሷዋ ደግሞ ሳባ ትባላለች…ዘመዴ ነች፡፡ሰሞኑን  ከተጨናነቀ ስራ ላይ ነበረች፤ከዛ አስነስቼ ነው ያስመጣኋት፤ትንሽ ዘና ማለት ይገባታል

…አንተን ደግሞ እተማመንብሀለሁ….ልከ ለእኔ እንደምታዳርገው ለእሷም እንደዛው፡፡›› የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈችለት፡፡
‹‹እረ ችግር የለውም…ግቢና ልብስሽን ቀይሪ…››ብሎ ፊቱን አዙሮ ወደ ጠረጴዛው ሄደና ለስራ የሚገለገልባቸውን ቅባቶችና የማሳጅ መገልገያ ዕቃዎች ማዘጋጀት ጀመረ፡፡ሳባ የምትለውና የምታደረግው ግራ ገብቷት በተገተረችበት ፈዛ ትብለጥን በትኩረት ትመለከታት ጀመረ፡፡
ገባትና ልትቀመጥ ወደሶፋው መራመድ የጀመረችውን እርምጃ ገትታ እጇን በመያዝ እየጎተተቻት ወደልብስ መቀየሪያው አነስተኛ ክፍል ይዛት ገባች.. የክፍሉ ሁለት የግድግዳው ክፍል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመስታወት የተሸፈነ ነው፡፡በአንደኛው ግድግዳ ተደግፎ የቆመ ለክፍሉ እንዲስማማ ተደርጎ የተሰራ አነስተኛ ቁምሳጥን አለ…አንድ መቀመጫ መግቢያው ላይ አለ‹‹…በይ ልብስሽን አውልቂና ይሄንን ፎጣ አገልድመሽ ነይ…››
‹‹ልብሴን አውልቄ…? ማለት ለምን..?››

‹‹እንዴት ለምን ?ማሳጅ ተሰርተሸ አታውቂም?››

‹‹በፍፁም አላውቅም፡፡››

‹‹እንግዲያው እመኚኝ በጣም ትወጂዋለሽ፡፡›

‹‹እረ ይቅርብኝ..እኔ ወንድ ፊት እርቃኔን ቆሜ አላውቅም..››

‹‹እንዴ ምን ነካሽ የተማርሽና ዘመናዊ ሴት አይደለሽ እንዴ…? እንዳልሽ በወንድ ፊት ልብስሽን አውልቀሽ የማታውቂ ከዛም በላይ የወንድ እጅም ሰውነትሽ ላይ አርፎ የማያውቅ ሊሆን ይችላል…ግን ያ ማለት እስክትሞቺ   አንዲህ  ሆኖ ይቀጥላል ማለት እንዳልሆነ መቼስ በደንብ ታውቂያለሽ…አንድ ቀን በየተራ አድርገሽ የማታውቂያቸው ነገሮችን ቀስ በቀስ ማድረግሽ የማይቀርና የሚጠበቅ
ነው..አሁን በይ ልብስሽን አውልቂና ነይ…ደግሞ እኮ ብቻሽን አይደለሽም እኔ በክፍሉ ውስጥ ከፊት ለፊትሽ ቁጭ እላለሁ፡፡››
ምንም ማምለጫ መንገድ ልታገኝ አልቻለችም፡‹‹እሺ በቃ››

‹‹አዎ እንደዛ ነው የሚባለው..በይ አውልቂና ነይ .››ብላት ክፍሉን ጥላላት ወጥታ ሄደች…ሳባ የለበሰችውን ቀሚስ አወለቀችና ቀኑን ሙሉ ስትለፋበት የዋለችውን አዲስ የተሰራ ጸጉሯን አንድላይ ጠቅላላ በማያያዝ ፎጣውን አገልድማ ልክ ለዘመናት ሲያልመውና ሲመኘው ወደከረመው መድረክ   አድል ቀንቶት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚወጣ አማተር  አርቲስት በፍራቻና   በሚንቀጠቀጡ እግሮቿ ወደ ውስጥ ገባች…ሁለቱም ቀና ብለው አዯት እና እርስ በርስ ተያዩ
…ፈገግ አለች ትብለጥ

‹‹ምነው?ምን አጠፋሁ?››

‹‹ምንም…ግን በማሳጅ ምንም አይነት ልብስ አይፈቀድም…››

‹‹እንዴ ፓንትም?››

‹‹እሺ ለዛሬ ፓንቱን ይሁን ተይው…ጡት ማስያዣውን ግን አውልቂው…››

‹‹ሴትዬዋ ጉድ ልትሰራኝ ነው እንዴ? ያን  ሁሉ  እንክብካቤና  ጠብ  እርግፍማ ለጤና አይደለም›› እያለች ተመልሳ  ወደክፍሉ  ገባችና  ጡት  ማስያዣዋን አወለቀችና ተመለሰች…ወደ ጠረጴዛው ቀረበች…
‹‹ዘና በይና ጠረጴዛው ላይ በደረትሽ ተኚ ››አላት…

ከፍራቻዋ ጋር እየታገለች እንዳላት አደረገች..ቅባቱን በእጆቹ አፈሰና  ከትከሻዋ አካባቢ እጆቹን አሳረፈ፡፡ ሰውነቷ ሽምቅቅ  አለ…ቀስ  እያለ  መገጣጠሚያዋን እየነካካ እያፍታታት፤ወደታች ወደ ጀርባዋ ወረደ…አንዳንዴ ላላና ለስለስ ብሎ
በሰውነቷ ላይ እጆቹን እያንሳፈፋቸው...ድንገት ደግሞ የሆነ አጥንቷንና  የሆነ ቦታ ያሉ ስሮቿን ጨመቅና ጠምዘዝ እያደረገ አንዲሰማትና እንዲያማት ያደርጋል…ግን ደግሞ አመመኝ ማለት እንኳን አትችልም..ፈፅሞ ያለችበትን ቦታ እየረሳችና እየተንሳፈፈች መጣች.. እጆቹን በቅባት አርሶ እታች ወደ እግሯ ተረከዞች ወረደ.. እያፈራረቀ ውስጥ እግሯንና ቁርጭምጭሚቷን ሲያሻት ላይ ጭንቅላቷ ድረስ ተሰማት ‹‹…እንዴት ነው እግሮቼን ላሸኝ ጭንቅላቴ ላይ እንዲህ አይነት የኤሌክትሪክ ንዘርት የሚረጨው›› ይህንን ጭልጭል በሚል አቅሟ ነው ለማሰብ የሞከረችው..ቀስ እያለ ፎጣውን   ወደላይ ወደመቀመጫዋ ሰበሰበና እጆቹን ወደላይ ቀስ እያለ እያስጠጋ ወደ ጭኗ እየቀረበ እየቀረበ እንድትንሰፈሰፍ አደረጋት..
ከዛ ወደ ጆሮዋ ጎንበስ አለና ‹‹አሁን ቀስ ብለሽ ተገልበጪልኝና በጀርባሽ ተኚ›› አላት….ድምፁ ከሩቅ አየሩን ሰንጥቆና አድማሱን አቋርጦ የሚመጣ ነው የሚመስለው፡፡ ግን ደግሞ ስምታዋለችና በዝግታ ታዘዘችው..አይኖቿን እንደጨፈነች ያለምንም ማቅማማት ልክ ገዳዮቹ እጅ ድንገት ገብቶ እንደተማረከ የጦር ምርኮኛ ታዛዥ ሆነችለት..ጥቁር አነስተኛ ፎጣ አመጣና አጣጥፎ አይኖቾ ላይ ጣል አደረገላት...ስራውን ቀጠለ…ከላይ ከአንገቷ አንስቶ ወደደረቷ እየወረደ በቅባት በወረዛና በለሰለሰ እጆቹ ጡቶቿ ዙሪያ እየተሸከረከረ ደግሞም ታች እምብርቷ አካባቢ እየደረሰ…ደግሞም ወደላይ እየተመለሰ እንድትቃትት አደረጋት…የሆኑ አጥንቶቿ ሲላቀቁ የሆኑ ስሮቿ ሲሳሳቡ..የሆኑ ደም ሰሮቿ ሲለጠጡና ሲሰፉ በዛ ውስጥ ደሟ እተንፏለለ በመፍሰስ በመላ  ሰውነቷ  ላይ  ጭንቅላቷ  እና  ታች እግሯ ጥፍር ድረስ ፏ ብሎ ሲራወጥ ተሰማት…ሰውዬው ቀጥሏል …እሁን ግን አጓጉል  ቦታዎች  እየነካካት ነው..እጆቹ ፓንቷ ላይ አርፈዋል…አሁን መወራጨት ሁሉ ጀምራለች…የትብለጥን ክፍሉ ውስጥ መኖሯን ሆነ የሚያሻት ሰውዬን ምንነትና ማንነት ሁሉ ከአእምሮዋ እየደበዘዘ  እየጠፋባት  ነው..  በአየር ላይ እንደመንሳፈፍና እንደመሰወር እያደረጋት ነው..፡፡

ከዛ የሰውየው እጅ ከሰውነቷ ላይ ተነሳ…‹‹.ምን ነካህ  ቀጥል  እንጂ..››  ልትለው ፈልጋ ነበር..ግን ያንን ለማለት አንደበቷን መክፈት  አልቻለችም…እ..እ ግን ‹‹እመቤቴ አሁን ጨርሰናል…መነሳት ትችያለሽ ››አላት…እንደዛ ያደረገው ከትብለጥ እንዲያቆም በምልክት ስለተነገረው ነው…ከዚህ በላይ ከቀጠለ.. ስሜቷን ሙሉ በሙሉ ፈንድቶ ወጥቶ  ያልሆነ  ነገር ይከሰትና ለእፍረት  ልትዳረግ ትችላለች፡፡ያ ደግሞ ለቀጣይ ንግግራቸውና ድርድራቸው ጥሩ አይሆንም የሚል ግምት ስለወሰደች ነው፡፡ ለዛ ነበር ያስቆመችው.. ደቂቃዎችን ወስዳ እንደምንም ከገባችበት ሰመመን ወጣችና ፎጣውን አስተካክላ ለብሳ ከጠረጴዛው ላይ በመነሳት ቆመች…‹‹ሻወር ውሰጂና ልብስሽን ለብሰሽ ነይ..እጠብቅሻለሁ››አለቻት…10ደቂቃ ፈጀባት..
ስትመጣ ትብለጥም እያነበበች የነበረችውን መፅሄት አስቀምጣ ቦርሳዋን ይዛ በመነሳት ቆመች፡፡ ቦርሳዋን ከፈተችና ሳባ እያየቻት የታሰረ ብር በማውጣት ቆጠረች..ሁለት ሺ ብር ቀነሰችና ‹‹እናመሰግናለን እንካ እቺን›› ብላ ዘረጋችለት
‹‹አረ እትዬ ትብለጥ ይሄንንማ አልቀበልም…በእኔ ነው››

‹‹ግዴለህም ተቀበል››

‹‹አረ አይሆንም..ያንቺ ዘመድ የእኔ ዘመድ ማለት ነች..ለዛውም እኮ ግማሽ ስራ ነው፡፡››
‹‹እኮ ጉርሻውም እኮ ግማሽ ነው…በል ያውልህ ብላ የተነሳችበት ሶፋ ላይ ብሩን ወርውራለት ሳባን ይዛት ወጣች….ሳባ ሁሉ ነገር ግራ ቢገባትና መአት ጥያቄ ቢኖራትም ምንም መጠየቅ ሳትችል ዝም ብላ ተከተለቻት…

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቢ ‹‹እሺ ሳባ ህይወት እንዴት ነው?›› ‹‹አሪፍ ነው…ምንም አይል?›› ‹‹ማለቴ የስራ ህይወትሽ እንዴት ነው..ደስተኛ ነሽ?›› ‹‹አዎ በስራው ደስተኛ ነኝ….ግን ክፍያው በቂ አይደለም…ማለቴ  በቂ  ሊሆን ይችላል ለእኔ ግን እየበቃኝ አይደለም፡፡›› ስትል በምሬት መለሰችላት፡፡ ‹ይገባኛል…አየሽ አንቺ የተማርሽ ቆንጆና ማራኪ…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቢ


‹‹በማግስቱ ሰራ መሄድ አልቻለችም…ኸረ እንደውም ከተኛችበት መንቀሳቀስም አልቻለችም፡፡ ሀሳብ እንዲህ ድቅቅ አድርጎ እንደሚያደክም ይሄ በህይወቷ የመጀመሪያው ልምዷ ነው፡፡ ዝልፍልፍ ነበር ያለችው…ስጋትና ጉጉት..ፍራቻና ድፍረት..
‹‹ለአለቃዋ በጣም ስላመመኝ መምጣት አልቻልኩም›› ብላ በሚሴጅ መልዕክት ላከችለት፡፡
‹‹ሳምንቱን ሙሉ ስታወርድና ስታወጣ ስታስብና ስታሰላስል ቆይታ ቅዳሜ ዕለት ወደማታ ለትብለጥ ደወለችላትና እሁድ እንድምትመጣ ነገረቻት፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት መኪና እንደምትልክላት ነገረቻት፡፡
ስትደውልላት ወስና አይደለም….አግኝታት… የበለጠ ማብራሪያ፤የበለጠ ገለፃ እንድታደርግላት ፈልጋ እንጂ...አዎ በሳምንት ውስጥ ከአንድ ሺ በላይ ጥያቄዎች ወደ እዕምሮዋ ተግተልትለው ገብተው መልሰው ወጥተዋል..ታዲያ ቢያንስ መሰረታዊ የሆኑ እንዲመለሱላት የምትፈልገው አስራ ምናምን የሚሆኑ ጥያቄዎች አሉ…የስራውን እድል የምትቀበለውም  አሻፈረኝ የምትለውም  እነሱ ላይ ተንተርሳ እንደሆነ ከራሷ ጋር ባደረገችው ውይይት ውሳኔ ላይ ደርሳለች፡፡

ለምሳሌ ጥያቄ ቁጥር አንድ የተባለውን ያህል ብር በወር እስከ 100ሺ ብር ታገኛለች?100ሺ ብሩ ይቅር እሺ 50ሺ ብር እንኳን እንደምታገኝ ማረጋገጫዋ ምንድነው…?ይሄ ተስፋ የውሸት ቢሆንስ?
‹በሶስት ወር ስልጠና የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ ባትሆንስ…?ተጨማሪ ስልጠና ይሰጣታል ወይስ ትባረራለች?፡፡›
‹‹ከማሳጅ ሙያ ውጭ እንድትሰጥ የሚጠበቅባት አገልግሎት ምንድነው..?

‹‹እንደ ተነገራት ዋናው የደንበኞቿን ፍላጎት ያለምንም መሸራረፍ 100 ፐርሰንትእንድታሟላና ፍፁም ደስተኛ ሆነው እንዲመለሱ ማድረግ ነው…ይሄ የወሲብ ጥያቄንም ያጠቃልላል….?››
‹‹ደንበኞቿ ወንዶች ብቻ ናቸው ወይስ ሴትም ወንድም….? የተመረጡ  ሰዎች ናቸው ወይስ  ማንም  አገልግሎቱን  የፈለገና  መክፈል  የሚችል  ሰው  ሁሉ መገልገል ይችላል?››
‹‹በስራ ላይ እያለች በደንበኞቿ ጥቃት ቢደርስባት ድርጅቱ እስከምን ድረስ ይከላከልላታል››…ወዘተ
እነዚህን አንድ በአንድ በማንሳት በዝርዝር እንድታስረዳት ካደረገች በኃላ ከዛ በስራው ለመቀጠልና ወደስልጠና ለመግባት ትወስናለች፤ካለበለዚያም እስከአሁን

ላደረገቸላት.እንክብካቤና ቀናነት አመስግናት ወደ ድህነት ስራዋ ትመለሰላች.. አዎ እንደዛ ወስና ነው የደወለችላት፡፡

እሁድ በተመሳሳይ  ሰዓት  በተመሳሳይ  ቁጥር  ተመሳሳይ ስልክ  ተደወለላት
..ተዘጋጅታ ስትጠብቅ ስለነበረ ቦርሳዋን አነሳችና ወጣች፡፡ ዛሬ እንደባለፈው ሳምንት ፍፁማዊ በሚመስል መሽቀርቀር አይደለም፤ጉጉቷም የተለየና በስጋት የተሞላ ነው፡፡
ካዛንቺስ ደርሰው መኪናውን እንደተለመደው ግቢው ውስጥ አስገብቶ  አቆመና ከፍቶ አስወረዳትና እጇን ይዞ ወደሳሎን ወሰዳት….በተመሳሰይ ለሰራተኛዋ አስረከባት..ሰራተኛዋ ቤተኛነትን በሚያሳይ የጋለ ሰላምታ ከተረከበቻት በኋላ ይዛት ወደውስጥ ገባች..ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ስትጠብቃት የነበረችው ግን ትብለጥ አልነበረችም…ሌላ በእሷ ከእድሜ አራት ወይም አምስት  አመት  የምትበልጥ ጠይም ረጅም ሞዴል መሳይ ቆንጆ ሴት ነች፡፡ ከመቀመጫዋ ተነሳችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋችላት..
‹‹ይህቺም እንደእኔ በስራው ተመልምላ  ይሆን  የመጣችው..? አንድ  ላይ ልታናግረን ይሆናል አንድ ላይ የጠራችን ?››ስትል አሰበችና ቅር አላት…
ያ ሁሉ ጥያቄ ሌላ ሰው ፊት እንዴት አድርጋ ትጠይቃታላች...ሀሳቧን ዘርዝራ ሳትጨርስ…ልጅቷ‹‹ሰገን እባላለሁ..ካልተሳሳትኩ አንቺ ሳባ ነሽ››አለቻት
ለሰላምታ የሰነዘረችውን የሚቀነጠስ የሚመስለውን ጣቷን አየጨበጠች…‹‹አዎ አልተሳሳትሸም››አለቻት
‹‹እትዬ በቃ እናመሰግናለን..የምንፈልገው ነገር ካለ እንጠራሻለን››አለችና ሰራተኛዋን ወደ ውስጥ ሸኘቻትና ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ ሳባንም

ከፊት ለፊቷ እንድትቀመጥ ጋበዘቻት...ሳባ ግራ በመጋባት ከስር እስከ ላይ ብትቃኛትም ምንም መገመት አልቻለችም…ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ በዛ ያሉ ወረቀቶች ይታያታል፡፡ ፊቷ ያያችው ሰገን እባላለሁ ያለቻት ልጅ መናገር ጀመረች፡፡
‹‹እንግዲህ ስለስራው መጀመር ማለቴ ስለ ስልጠናው ሁኔታ አንዳንድ ቅድመ ዝግጅቶችና የተወሰኑ የሚፈረሙ ውሎች አሉ… ስለዛ እንድንነጋገርና እንደንጨርስ ነው፡፡››
‹‹ግን እኮ››

‹‹ምነው…ችግር አለ?››

‹‹ማለቴ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ደርሼ አይደለም የመጣሁት  …አሁንም  እትዬ ትብለጥን ጠይቄ መረዳት የሚገባኝ ጥያቄዎች ነበሩኝ..››

‹‹ግን የተነገረኝ እንደተስማማሽ ነበር፡፡ትብለጥ ያለችኝ እንደዛ ነበር››

‹‹አዎ እርግጥ ለእሷ ያልኳት እንደዛ ነው…ማለት በአካል ሳገኛት ላስረዳትና ጥያቄዎቼን ላቀርብላት ነበር የፈለኩት...እና የማላስቸግርሽ ከሆነ ከእሷ ታገናኚኛለሽ?››
‹‹አይ አሁን በቅርብ ስሌለች አልችልም››

‹‹ውይ ያሳዝናል. በቃ ንገሪልኝና በተመቻት ቀን ቀጠሮ ትያዝልኝ እመጣለሁ፡፡››

‹‹ይቻላል….እነግራታለሁ..ግን ከስድሰት ወር በኃላ ነው እሷን የምታገኚያት፡፡››

ልቧ ምንጭቅ ብሎ ወደታች ዝቅ  ያለ  መሰላት…ወይንም  የሆነ  ነገር  ከቤቱ ኮሪኒስ ላይ ተላቆ ጭንቅላቷ ላይ የወደቀ አይነት ስሜት ነው የተሰማት
‹ስድስት ወር….?››

‹‹አዎ..ዛሬ ወደ አሜሪካ በራለች…አሁን ያለሽ ምርጫ ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄዎችሽን ለእኔ አቅርበሽ ስለስራው በመረዳት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተሸ ወደስራ መግባት ወይም ሁለተኛው ምርጫሽ ይቅርብኝ ብለሽ ወደ ተለመደው ኑሮሽ መመለስ…››
‹‹በቃ?››

‹‹አዎ..አየሽ አንቺ የተፈለግሺበት ዋናው  ምክንያት  የእኔን  ቦታ  ለመተካት ነው፡፡››
አሁን ተነቃቃች…ቢያንስ ስራውን በጥልቀት የሚያውቀው ሰው  ነው ከፊት ለፊቷ ያለው
‹‹ያንቺን…?አንቺ ልታቆሚ ነው፡?፡››
‹‹አይ በፍፁም… እንደነገርኩሽ እሷ አሜሪካ ለሚቀጥሉት ስድስት  ወራት ስለምትቆይ የእሷን ቦታ ለመተካት ነው….ማለት ድርጅቱን  ለማስተዳደር..የእሷ ነገር ሆኖብኝ እንጂ እኔስ አዛው ስራዬን ብሰራ ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹እኔም ስራውን እፈልገዋለሁ እኮ…ግን ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች በውስጤ እየተጉላሉ እየረበሹኝ ስለሆነ ነው፡፡››
‹‹እሺ ትብለጥ…አንቺን በተመለከተ አደራ ስላለቺኝ ስለስራው  ከእኔ ታሪክ አንስቼ ላስረዳሽ››
‹‹በፈጠረሽ…ደስ ይለኛል፡፡››

‹‹የዛሬ ስድስት አመት ነው፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2ተኛአመት የማኔጅመንት ተማሪ ነበርኩ፡፡እናቴ በድንገት ታማ ከክፍለ ሀገር አጎቶቼ አመጧትና ሚኒሊክ አስተኞት...ያው አባቴ በልጅነቴ ነበር የሞተብኝ..አጎቶቼ ሲመጡ ለቀናት  ቢበዛ ለአንድ ሳምንት ህክምና ብለው ነበር…ግን በሽታዋ  እንዲህ  በቀላሉ  የሚድን አይነት አልነበረም….ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ሁሉም ተራ በተራ ወደ ሀገራቸው

ተመለሱ፤ምክንያቱም ሁሉም የየራሳቸው ልጆችና ቤተሰቦች ያሏቸው ከእጅ ወደአፍ የሆነ ኑሮ የሚኖሩ ድሆች ስለነበሩ ከዛ በላይ  ለእናቴ  የሚያደርጉላት ምንም ነገር አልነበረም..ሆስፒታል አንድ ወር ከ15 ቀን ተኛች….
ከዛ ውጭ ወጥታ በሳምንት አንድ ቀን አንዴ በተመላላሽ ህክምናዋን እንድትከታተል ተወሰነ...ምን ላድርግ በወቅቱ ምንም የማላውቅ የ21 ዓመት ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ…ወር ከ15ቀን ሆስፒታል ስኖር ወጪውን ሁሉ የተሸፈነው ጓደኞቼ ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለምነውልኝ በሰጡኝ ብር ነው፡፡ ከዛ በላይ ምንም ሊያደርጉልኝ አልቻሉም አስበሽዋል በምኔ ቤት እከራያለሁ..?በምኔ.የምንተኛበት ፍራሽና የምንለብሰው ልብስ እገዛለሁ..?.በምኔ ቀለባችንን አሟላለሁ….?በምኔ የላዳ እየከፈልኩ እናቴን ከተከራየሁበት ቤት ሆስፒታል.ድረስ.አመላልሳታለሁ…?ትምህርቴንስ.ምንድነው.የማደርገው…?
ጭንቅላቴ ብቻ ሳይሆን ነፍሴም ተወጣጠረች.. በመጀመሪያ ትምህርቴን ዊዝድሮዋል በመሙላት አቋረጥኩ…ከዛ ዘመዶቼ ሰባስበው በላኩልኝ ጥቂት ገንዘብ አንድ አነስተኛ ቤት ተከራየሁና አንድ አነስተኛ ፍራሽና አንድ ብርድ ልብስ ገዝቼ እናቴን ከሆስፒታል በማውጣት ወደ ተከራየሁት ቤት ወሰድኳት..ከዛ ምን ላድርግ? ስራ ለመፈለግ በየደላላው ቤት ኳተንኩ.. ከዛ እንደ ምንም በአንድ ሺ ብር የአስተናጋጅነት ስራ አገኘሁ…
የአስተናጋጅ ስራ ቀኑን ሙሉ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ማታሁለት ሰዓት ነው የምሰራው..እንደልቧ መንቀሳቀስ የማትችል በሽተኛ እናቴን ባዶ  ቤት  ዘግቼባት ቀኑን ሙሉ ስራ ላይ ውላለሁ….አማራጭ አልነበረኝም… በሳምንት  አንድ ቀን ባለችኝ የረፍት ቀን እሷን  ሆስፒታል  ወስጄ  አሳክማለሁ..ደሞዜ አንድ ሺ  ብር ነው …የቤት ኪራይ ሁለት ሺ ብር ከፍላለሁ.ለእናቴ ህክምና መድሀኒት በወር በትንሹ አንድ ሺ ብር ያስፈልገኛል….ለምግባችን ለታክሲ …በጣም ተቸግረንና ተሳቀንም ቢሆነ ከ5 ሺ ብር በላይ ያስፈልገኛል፡፡አንድ ደንበኛ መጥቶ ተስተናግዶ ሂሳብ ከፍሎ ሲወጣ ተንደርድሬ የተውልኝን ዝርዝር ሳንቲሞችና ብሮች ነው

የማየው..እነዛን ሳንቲሞች በስጋዬም ብቻ ሳይሆን በነፍሴ ጭምር ነበር የምፈልጋቸው የነበረው.አንዳንዴ ባዶ--ትተውልኝ ሲሄዱ ልክ እንደመብቴ እብሳጫለሁ፡፡ጥሪና ስደቢያቸው የሚልስሜት   ሁሉ   ይፈታተነኛል፡፡ እንደዛም ተሳቅቄ የሰበሰብኩት ቲፕና የወር ደሞዜ ወጪአችንን   ስለማይሸፍንልን አልፎ አልፎ ሶስት መቶ እና አራት  መቶ   ከሚወረውሩልኝ   ወንዶች   ጋር እወጣ ነበር…ይሄ ለእኔ እንዴት ከባድ እንደነበረ ምን አልባት አብረን የምንዘልቅ ከሆነ ከነምክንያቱ ሌላ  ቀን  እነገርሻለሁ፡፡ አልፎ  አልፎም  እንባዬ ያለ ፍቃዴ ይንጠባጠባል…ታዲያ ምን ሆነ መሰለሽ፤በዚህ አይነት ሁኔታ ለ4 ወር ከቀጠልኩ በኃላ አንድ ቀን ስራ ላይ ቆይቼ ወደቤት ልሄድ ከካፌያችን እንደወጣሁ አንድ ደንበኛችን በራፍ ላይ መኪና ውስጥ ቁጭ ብሎ ሲጠብቀኝ ነበር..አስቆመኝና አናገረኝ ነገሬም ሳልል ሰላምታ ሰጥቼው ላልፍ ስል ልሸኝሽ ብሎ የገቢናውን በራፍ ከፈተልኝ
ወሬዋን አቆመችና ፊት ለፊቷ ባለው ውሀ የደረቀ ከንፈሯን  በማርጠብ‹‹ውይ ነገሩን በጣም አርዝሜ አንዛዛሁት አይደል?››ስትል ሳባን ጠየቀቻት፡፡
‹እረ በፈጠረሽ በጣም ተመስጬ እያዳመጥኩሽ ነው…ደግሞም ታሪኩ ከውይይታችን ጋር ይገናኝም አይገናኝም አያስጨንቀኝም…..ይልቅ ቀጥዬ….ምንም የሚያስቸኩልም የምሄድበትም ቦታ የለኝም፡››
‹‹እሺ ካልሽ.. እና እንደነገርኩሽ ሰውዬው መኪና ውስጥ ገባሁና ወደ ቤቴ አቅጣጫ እያዋራኝና እያጫወተኝ ጉዞ ጀመርን….መሀከል ላይ አብሬው ካደርኩ 2 ሺ ብር እንደሚከፍለኝ ነገረኝ‹‹…ሁለት ሺ ብር በአንድ ቀን የእውነት ሎቶሪ ነው››ስል በውስጤ አሰብኩ…ግን እናቴን ምን እላታለሁ..? ለሊት  ቢያማት  ምን አደርጋለሁ? ልክ አሁን አንቺ እንዳለሽበት ሁኔታ እሺም እንቢም ማለት

አልቻልኩም… እዕምሮዬን አሰራሁት…ድንገት ‹‹300 ብር  አሁን  ስጠኝ›› አልኩት፡
‹‹ምነው ተስማማሽ ማለት ነው፡፡››

‹‹አዎ..ሱፐር ማርኬት ያለበት አካባቢ ስትደርስ አቁምልኝ…ለእናቴ የሚያስፈልጋትን ነገር ገዝቼ  አደርስላትና  ከዛ እንሄዳለን….አይደብርህም አይደል?››
‹‹አረ ችግር የለውም….ዋናው መስማማትሽ ነው እናም ደግሞ ባትስማሚም 300 ብሩን እሰጥሻለሁ››አለና ሱፐር ማርኬት ሲያገኝ እንዳልኩት አቆመልኝና እጁን ወደኪሱ ሰዶ የጠየኩትን ብር ይሰጠኛል ብዬ ስጠብቅ ሞተሩን አጠፋና ከመኪና በመውረድ አብሮኝ ሱፐር ማርኬት ገባ…ሰውዬው ትንሽ ጉራና  ብዙ  ደግነት ያለው ዘመናዊና ሀብታም ሰው ስለሆነ የሶስት መቶ  ብር እቃ  ልገዛ የገባሁት የአንድ ሺ ምናምን ብር ቤት ውስጥ ለእኔና ለእናቴ ያስፈልጋል  ያልኩትን እቃ ሁሉ ገዛልኝ…ይሄ በእኔ ነው እያለ ሲጨምር ይሄ  በኔ  ነው  አያለ ሲጨምር ሁለት ኩርቱ ፌስታል ዕቃ ገዛንና ወደቤት መሄድ ቀጠልን
ያሰብኩት ከእኛ ቤት ጎን ተከራይታ ከወንድሟ ጋር የምትኖር ጎረቤታችን አለች..አንድ መቶ ብር ሰጥቼያት  ከእናቴ  ጋር እንድታድርልኝ አድርጌ  ከሰውየው ጋር ለመሄድ ነው ደረስን ..እንግዲህ 15ደቂቃ አቆይሀለሁ.›አልኩትና እቃዬን ይዤ ከመኪናው ወረድኩ

‹‹ችግር የለውም….›አለኝ  ሁለቱን  ፌስታል  በግራና  ቀኝ  እጀቼ  ይዤ እየተንገዳገድኩ ደረስኩ ፤የቤታችንን ቁልፌን አወጣሁን ከፍቼ  ወደወስጥ  ስገባ እናቴ ጥቅልል ብላ ተኝታለች..ማለቴ እንቅልፍ ወስዷታል፡፡ ገባሁና ፌስታሉን በማስቀመጥ ተመልሼ ወጣሁ፤የጎረቤቱን በራፍ አንኳኳሁ ወጥታ

ከፈተችልኝ፡፡ስቤ ወደ ውጭ አወጣኋትና ለነገ ጥዋት የሚደርስ ስራ ካፌያችን ስለታዘዘ አድሬ እንድረዳቸው ስላስገደዱኝ ተመልሼ መሄዴ ስለሆነ…እናቴ ጋር እንድታድርና ሁለት መቶ ብር አበል ስለሚከፈለኝ መቶ ብሩን ጠዋት እንደምሰጣት ስነግራት እንደ እኔው ደሀ እና ሳንቲም ብርቋ የሆነባት ልጅ ስለሆነች በደስታ ተስማማች፤ ለወንድሟ በአጭሩ አስረድታው፤በራፉን  እንዲቀረቅር ነግራው፤ተከትላኝ ወደ  እኛ  ቤት  ገባች… ከገዛሁት  እቃዎች  የተወሰኑትን በመቀነስ ሰጠኋት እና ለእናቴ ቆንጆ እራት እንድትሰራላትና ከእንቅልፏ ስትባንን እሷን አብልታ ለራሷም እንድትበላና፤ ወዴት  እንደሄድኩ እንድታስረዳልኝ አደራ ብያት ወጥቼ ውጭ ወደሚጠብቀኝ ሰውዬ ሄድኩ፡፡
የሰውዬው ቤት ደርሰን የቀረበልንን  እራት በልተን፤የቀረበልንን ወይን እየተጎነጨን ለቀጣዩ የአልጋ ጨወታ እየተሟሟቅን ባለንበት ቅፅበት ኪሴ ውስጥ ያለችው የወላለቀች ኤርገንዶ ስልኬ ተንጫረረች..ድምጿ ከአቅሟ በላይ ነው ሲያስደነግጥ..አየሁት…እናቴን አደራ ያልኳት ልጅ ቁጥር ነው… ደነገጥኩና ቶሎ ብዬ አነሳሁት…የሆነ እቃ ፈልጋ ያጣችና ያለበትን ልትጠይቀኝ ወይንም እናቴ አገናኚኝ››ብላት እንደሆነ ነበር የገመትኩት…እንዳነሳሁት ልጅቷ ታንቧርቃለች፡፡
‹‹ምነውአንቺ….? ግ ልሁን ባልኩ እንዴት እንዲህ ትሰሪኛለሽ…..?እናትሽ አይደለችም .እንዴት እንዲህ ይደረጋል?›
‹‹ምንድነው ተረጋግተሸ ንገሪኝ ..?››
‹‹ምንድ ነው የምነግርሽ…በድን  ሬሳ  አስታቅፈሺኝ  ትሄጂያለሽ…እኔ  ያንቺው ቢጤ ደሀ ነኝ…ልታሳስሪኘ ነው.እንደዛ አድርገሽ ምን ትጠቀሚያለሽ..›
በወቅቱ አለም እየከዳችኝ መሰለኝ‹‹ምን እያወራሽ ነው.?››
ከዛ ውጭ ወጥታ በሳምንት አንድ ቀን አንዴ በተመላላሽ ህክምናዋን እንድትከታተል ተወሰነ...ምን ላድርግ በወቅቱ ምንም የማላውቅ የ21 ዓመት ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ…ወር ከ15ቀን ሆስፒታል ስኖር ወጪውን ሁሉ የተሸፈነው ጓደኞቼ ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለምነውልኝ በሰጡኝ ብር ነው፡፡ ከዛ በላይ ምንም ሊያደርጉልኝ አልቻሉም አስበሽዋል በምኔ ቤት እከራያለሁ..?በምኔ.የምንተኛበት ፍራሽና የምንለብሰው ልብስ እገዛለሁ..?.በምኔ ቀለባችንን አሟላለሁ….?በምኔ የላዳ እየከፈልኩ እናቴን ከተከራየሁበት ቤት ሆስፒታል.ድረስ.አመላልሳታለሁ…?ትምህርቴንስ.ምንድነው.የማደርገው…?
ጭንቅላቴ ብቻ ሳይሆን ነፍሴም ተወጣጠረች.. በመጀመሪያ ትምህርቴን ዊዝድሮዋል በመሙላት አቋረጥኩ…ከዛ ዘመዶቼ ሰባስበው በላኩልኝ ጥቂት ገንዘብ አንድ አነስተኛ ቤት ተከራየሁና አንድ አነስተኛ ፍራሽና አንድ ብርድ ልብስ ገዝቼ እናቴን ከሆስፒታል በማውጣት ወደ ተከራየሁት ቤት ወሰድኳት..ከዛ ምን ላድርግ? ስራ ለመፈለግ በየደላላው ቤት ኳተንኩ.. ከዛ እንደ ምንም በአንድ ሺ ብር የአስተናጋጅነት ስራ አገኘሁ…
የአስተናጋጅ ስራ ቀኑን ሙሉ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ማታሁለት ሰዓት ነው የምሰራው..እንደልቧ መንቀሳቀስ የማትችል በሽተኛ እናቴን ባዶ  ቤት  ዘግቼባት ቀኑን ሙሉ ስራ ላይ ውላለሁ….አማራጭ አልነበረኝም… በሳምንት  አንድ ቀን ባለችኝ የረፍት ቀን እሷን  ሆስፒታል  ወስጄ  አሳክማለሁ..ደሞዜ አንድ ሺ  ብር ነው …የቤት ኪራይ ሁለት ሺ ብር ከፍላለሁ.ለእናቴ ህክምና መድሀኒት በወር በትንሹ አንድ ሺ ብር ያስፈልገኛል….ለምግባችን ለታክሲ …በጣም ተቸግረንና ተሳቀንም ቢሆነ ከ5 ሺ ብር በላይ ያስፈልገኛል፡፡አንድ ደንበኛ መጥቶ ተስተናግዶ ሂሳብ ከፍሎ ሲወጣ ተንደርድሬ የተውልኝን ዝርዝር ሳንቲሞችና ብሮች ነው

የማየው..እነዛን ሳንቲሞች በስጋዬም ብቻ ሳይሆን በነፍሴ ጭምር ነበር የምፈልጋቸው የነበረው.አንዳንዴ ባዶ--ትተውልኝ ሲሄዱ ልክ እንደመብቴ እብሳጫለሁ፡፡ጥሪና ስደቢያቸው የሚልስሜት   ሁሉ   ይፈታተነኛል፡፡ እንደዛም ተሳቅቄ የሰበሰብኩት ቲፕና የወር ደሞዜ ወጪአችንን   ስለማይሸፍንልን አልፎ አልፎ ሶስት መቶ እና አራት  መቶ   ከሚወረውሩልኝ   ወንዶች   ጋር እወጣ ነበር…ይሄ ለእኔ እንዴት ከባድ እንደነበረ ምን አልባት አብረን የምንዘልቅ ከሆነ ከነምክንያቱ ሌላ  ቀን  እነገርሻለሁ፡፡ አልፎ  አልፎም  እንባዬ ያለ ፍቃዴ ይንጠባጠባል…ታዲያ ምን ሆነ መሰለሽ፤በዚህ አይነት ሁኔታ ለ4 ወር ከቀጠልኩ በኃላ አንድ ቀን ስራ ላይ ቆይቼ ወደቤት ልሄድ ከካፌያችን እንደወጣሁ አንድ ደንበኛችን በራፍ ላይ መኪና ውስጥ ቁጭ ብሎ ሲጠብቀኝ ነበር..አስቆመኝና አናገረኝ ነገሬም ሳልል ሰላምታ ሰጥቼው ላልፍ ስል ልሸኝሽ ብሎ የገቢናውን በራፍ ከፈተልኝ
ወሬዋን አቆመችና ፊት ለፊቷ ባለው ውሀ የደረቀ ከንፈሯን  በማርጠብ‹‹ውይ ነገሩን በጣም አርዝሜ አንዛዛሁት አይደል?››ስትል ሳባን ጠየቀቻት፡፡
‹እረ በፈጠረሽ በጣም ተመስጬ እያዳመጥኩሽ ነው…ደግሞም ታሪኩ ከውይይታችን ጋር ይገናኝም አይገናኝም አያስጨንቀኝም…..ይልቅ ቀጥዬ….ምንም የሚያስቸኩልም የምሄድበትም ቦታ የለኝም፡››
‹‹እሺ ካልሽ.. እና እንደነገርኩሽ ሰውዬው መኪና ውስጥ ገባሁና ወደ ቤቴ አቅጣጫ እያዋራኝና እያጫወተኝ ጉዞ ጀመርን….መሀከል ላይ አብሬው ካደርኩ 2 ሺ ብር እንደሚከፍለኝ ነገረኝ‹‹…ሁለት ሺ ብር በአንድ ቀን የእውነት ሎቶሪ ነው››ስል በውስጤ አሰብኩ…ግን እናቴን ምን እላታለሁ..? ለሊት  ቢያማት  ምን አደርጋለሁ? ልክ አሁን አንቺ እንዳለሽበት ሁኔታ እሺም እንቢም ማለት

አልቻልኩም… እዕምሮዬን አሰራሁት…ድንገት ‹‹300 ብር  አሁን  ስጠኝ›› አልኩት፡
‹‹ምነው ተስማማሽ ማለት ነው፡፡››

‹‹አዎ..ሱፐር ማርኬት ያለበት አካባቢ ስትደርስ አቁምልኝ…ለእናቴ የሚያስፈልጋትን ነገር ገዝቼ  አደርስላትና  ከዛ እንሄዳለን….አይደብርህም አይደል?››
‹‹አረ ችግር የለውም….ዋናው መስማማትሽ ነው እናም ደግሞ ባትስማሚም 300 ብሩን እሰጥሻለሁ››አለና ሱፐር ማርኬት ሲያገኝ እንዳልኩት አቆመልኝና እጁን ወደኪሱ ሰዶ የጠየኩትን ብር ይሰጠኛል ብዬ ስጠብቅ ሞተሩን አጠፋና ከመኪና በመውረድ አብሮኝ ሱፐር ማርኬት ገባ…ሰውዬው ትንሽ ጉራና  ብዙ  ደግነት ያለው ዘመናዊና ሀብታም ሰው ስለሆነ የሶስት መቶ  ብር እቃ  ልገዛ የገባሁት የአንድ ሺ ምናምን ብር ቤት ውስጥ ለእኔና ለእናቴ ያስፈልጋል  ያልኩትን እቃ ሁሉ ገዛልኝ…ይሄ በእኔ ነው እያለ ሲጨምር ይሄ  በኔ  ነው  አያለ ሲጨምር ሁለት ኩርቱ ፌስታል ዕቃ ገዛንና ወደቤት መሄድ ቀጠልን
ያሰብኩት ከእኛ ቤት ጎን ተከራይታ ከወንድሟ ጋር የምትኖር ጎረቤታችን አለች..አንድ መቶ ብር ሰጥቼያት  ከእናቴ  ጋር እንድታድርልኝ አድርጌ  ከሰውየው ጋር ለመሄድ ነው ደረስን ..እንግዲህ 15ደቂቃ አቆይሀለሁ.›አልኩትና እቃዬን ይዤ ከመኪናው ወረድኩ

‹‹ችግር የለውም….›አለኝ  ሁለቱን  ፌስታል  በግራና  ቀኝ  እጀቼ  ይዤ እየተንገዳገድኩ ደረስኩ ፤የቤታችንን ቁልፌን አወጣሁን ከፍቼ  ወደወስጥ  ስገባ እናቴ ጥቅልል ብላ ተኝታለች..ማለቴ እንቅልፍ ወስዷታል፡፡ ገባሁና ፌስታሉን በማስቀመጥ ተመልሼ ወጣሁ፤የጎረቤቱን በራፍ አንኳኳሁ ወጥታ

ከፈተችልኝ፡፡ስቤ ወደ ውጭ አወጣኋትና ለነገ ጥዋት የሚደርስ ስራ ካፌያችን ስለታዘዘ አድሬ እንድረዳቸው ስላስገደዱኝ ተመልሼ መሄዴ ስለሆነ…እናቴ ጋር እንድታድርና ሁለት መቶ ብር አበል ስለሚከፈለኝ መቶ ብሩን ጠዋት እንደምሰጣት ስነግራት እንደ እኔው ደሀ እና ሳንቲም ብርቋ የሆነባት ልጅ ስለሆነች በደስታ ተስማማች፤ ለወንድሟ በአጭሩ አስረድታው፤በራፉን  እንዲቀረቅር ነግራው፤ተከትላኝ ወደ  እኛ  ቤት  ገባች… ከገዛሁት  እቃዎች  የተወሰኑትን በመቀነስ ሰጠኋት እና ለእናቴ ቆንጆ እራት እንድትሰራላትና ከእንቅልፏ ስትባንን እሷን አብልታ ለራሷም እንድትበላና፤ ወዴት  እንደሄድኩ እንድታስረዳልኝ አደራ ብያት ወጥቼ ውጭ ወደሚጠብቀኝ ሰውዬ ሄድኩ፡፡
የሰውዬው ቤት ደርሰን የቀረበልንን  እራት በልተን፤የቀረበልንን ወይን እየተጎነጨን ለቀጣዩ የአልጋ ጨወታ እየተሟሟቅን ባለንበት ቅፅበት ኪሴ ውስጥ ያለችው የወላለቀች ኤርገንዶ ስልኬ ተንጫረረች..ድምጿ ከአቅሟ በላይ ነው ሲያስደነግጥ..አየሁት…እናቴን አደራ ያልኳት ልጅ ቁጥር ነው… ደነገጥኩና ቶሎ ብዬ አነሳሁት…የሆነ እቃ ፈልጋ ያጣችና ያለበትን ልትጠይቀኝ ወይንም እናቴ አገናኚኝ››ብላት እንደሆነ ነበር የገመትኩት…እንዳነሳሁት ልጅቷ ታንቧርቃለች፡፡
‹‹ምነውአንቺ….? ግ ልሁን ባልኩ እንዴት እንዲህ ትሰሪኛለሽ…..?እናትሽ አይደለችም .እንዴት እንዲህ ይደረጋል?›
‹‹ምንድነው ተረጋግተሸ ንገሪኝ ..?››
‹‹ምንድ ነው የምነግርሽ…በድን  ሬሳ  አስታቅፈሺኝ  ትሄጂያለሽ…እኔ  ያንቺው ቢጤ ደሀ ነኝ…ልታሳስሪኘ ነው.እንደዛ አድርገሽ ምን ትጠቀሚያለሽ..›
በወቅቱ አለም እየከዳችኝ መሰለኝ‹‹ምን እያወራሽ ነው.?››
​​‹‹በይ ነይ የእናትሽን በድን እንደምታረጊ አድርጊያት››አለቺኝ የእሷን የምትለኝን ነገር በደነዘዘ ሁኔታ እየሰማኋት ነው…ከጀርባው ደግሞ ለቅሶ ይሰማኛል..ሰውየው በድንጋጤ ዙሪያዬን እየተሸከረከረ ምን እንደተፈጠረ  ለማወቅ ይጠይቀኛል፡፡…ጅው ብዬ ባለሁበት ወደኋላ ወደቅኩ….ከደቂቃዎች በኋላ ውሀ ተደፍቶብኝ ተንፍሼ ነቃሁ..ሰውየውም ስሜቱን ለማርካት የተወጣጠረ እንትኑ ተኮማትሮ ከእንደገና በዛ ለሊት እኔን ይዞ ወደቤቴ መለሰኝ፡፡ ስደርስ ያው ሁሉ ነገር አክትሞ ነበር.ለካ ከስራ እንደገባሁ እናቴ ኩርምትመት ብላ የተኛች የመሰለኝ ሞታ ነበረ...ሳትሰናበተኝ..ምንም ነገር ሳትለኝ ባዶ ቤት እናቴን አጣሁ ሳንቲም ለቀማ ሄጄ….፡፡ ያው ሰውዬው በማግስቱም ከእኔ አልተለየም፤በእሱ እገዛ እናቴን ቀበርኩ…ከዛ ፈፅሞ አምርሬ ድህነትን ጠላሁ…ምንም ሰርቼ ምንም ቀድጄ ቢሆን የማልጨርሰው ገንዘብ ማግኘት እንዳለብኝ ወሰንኩ.፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ‹‹ወደ ትምህርትሽ ለመመለስ አልፈልግሺም ነበር….?››መሀከል ገብታ ጥያቄ ጠየቀቻት
ምን ሊያደርግልኝ…ተምሬ ስንት ልቀጠር..ሶስትና አራት ሺ ብር…ምን ላደርግበት.?ነገ ብታመም እንደእናቴ ባዶ ቤት ማቅቄ ልሞት? ነገ ልጅ ብወልድ በድህነት ውስጥ ላሳድገው….?አይ ምንም ሰርቼ ምንም ሀብታም መሆን ብቻ ነው የፈለኩት….ለምሳሌ መስረቅም ቢሆን ፤መሸርሞጥም ቢሆን፤ሀሺሽ ማከፋፈልም ቢሆን… ብቻ ዋናው ጠቀም ያለ ገንዘብ ያስገኝ እንጂ የስራው አይነት ላይ ምንም አይነት ምርጫ እንደማላደርግ ለራሴ ቃል ገባሁ….በአጋጣሚ ያ ያልኩሽ ሰውዬ እቅዴን ስነግረው ከትብለጥ ጋር አስተዋወቀኝና ‹‹እባክሽ እርጂያት››አላት…ተገናኝን..አየቺኝ ልክ አሁን  አንቺን  እንደወደደችሽ ወደደቺኝ..ታዲያ እኔ እንደአንቺ መወዛገብ ውስጥ አልገባሁም እንዴትስ ልገባ እችላለሁ…? እሺ ብላ ተረከበቺኝ፡፡ ወደስልጠና ገባሁ…ስልጠናው ዛሬ እንደምንሰጠው በጣም የተደራጀ አልነበረም…ግን ለአንድ ወር ሰለጠንኩ…ይበልጥ ወደድኩት…እና ይሄው ስድስት አመት እሱኑ እየሰራሁ ነው፡
ስልኳን  ከኪሶ  አወጣችና  ከፈተች፤ከባንክ የተላከላትን የሂሳብ ዝርዝር.ላይ ያለውን ብር አሳየቻት 6,354,450 ይላል
‹‹6 ሚሊዬን ነው የሚለው?››

‹‹አዎ›› አለችና ጋላሪ ውስጥ በመግባት አንድ ፎቶ አወጣች ‹‹ይሄ በቅርብ እያሰራሁት ያለ ጅምር ቤት ነው..ከሶስት ወር  በኃላ  ይጠናቀቃል፤ይህቺኛዋ መኪናዬ.ነች፤ቢያንስ ከአስር የሚበልጡ የዘመዶቼን ልጆች አስተምራለሁ…፡፡
‹‹ይገርማል›› አለች ሳባ

‹‹አዎ ይገርማል…  .እንግዲህ አስከአሁን የነገርኩሽ መግቢያውንና.መደምደሚያውን ብቻ ነው፡፡ማለቴ እንዴት ስራው ውስጥ እንደገባሁና በመግባቴ ያገኘሁትን ውጤት….››

‹‹አዎ ..››

መሀከሉ የህይወትሽን የአስተሳሰብሽን፤ለሰው ልጅ  የምትሰጪውን  አጠቃላይ ትርጉም ሙሉ በሙሉ የሚገለባብጥ ተግባርና ስራ  ነው  የሚያጋጥምሽ…አስር ዲግሪ ብትማሪ የማታገኚውን የህይወት ልምድ ነው የምታገኚው..ሀገር በእነማን አንደምትመራ፤የምናደንቃቸውና.ለአምልኮ በተጠጋ ፍቅር የምንከተላቸው አርቲስቶች እና ዘፋኞች ያላቸው ስብእና..ብር ለሀብታሙና ብር ለደሀው ያለው የትርጉም ልዩነት …ብዙ ብዙ ነገር ትማሪበታለሽ….መማር ብቻ አይደለም…እያንዳንዷን እውቀትም ሆነ እያዳንዷን ገንዘብ ስትቀበይ ለዛ  የምትከፍይው ስቃይና ህመም አለ…አንዱ ደንበኛ እንደ አሻንጉሊት ያይሻል፤ ሌላ ንግስት አድርጎ ያንቆጦቁጥሻል አንዱን ሰውነቱን ከላይ እስከታች ታሺለታለሽ፤ ሌላውን ደግሞ አእምሮውንና የውስጥ የስነልቦና ጥዝጣዜውን ውስጡ ገብተሸ እንድታክሚው ይጠበቅብሻል… አንዱን በወሲብ ስታስደስቺው…ሌላውን ደግሞ ለሊቱን ሙሉ ቁጭ ብለሽ እንድታዳምጪው ብቻ ይፈልግ ይሆናል…፡፡
በዚህ የስራ ባህሪ የማያጋጥምሽ ነገር የለም…እርግጥ ከፍላጎትሽ ያፈነገጠ አካላዊ ጥቃት አያጋጥምሽም፤ ድርጅቱ ለዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ  ያደርጋል…እዚህ የሚመጡት ደንበኞቻችን ለስማቸው አብዝተው ስለሚጨነቁ በዛ ብዙም አያስቸግሩም፡፡ በተረፈ ግን  ዋና ታርጌትሽ በመጪዎቹ  አምስትና ስድስት አመታት ለእድሜ ልክሽ የሚበቃሽን ብር ለማግኘት ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ቁርጠኛ ነሽ ወይ…ነው..ለዛ አዎ ቁርጠኛ ነኝ… ከሆነ መልስሽ ያንን እንድታደርጊ የሚያግዝሽ በቂ ስልጠናና ዝግጅት እንዲኖርሽ ወደስልጠና ትገቢያለሽ…አይ እኔ የገንዘብም ችግር የለብኝም.. ቤተሰቦቼ ደህና የሚባል አቅም አላቸው እኔም እየሰራሁት ያለሁት ስራ በቂ ነው የምትይ  ከሆነ  ግን  ልገፋፋሽ አልፈልግም ቢቀርብሽ ይሻላል››
የተወሰነ ደቂቃ ዝም አለች…ሰገንም በዝምታ የማሰላሰያ ሰዓቱን ፈቀደችላት
‹‹ችግሯን አሰበች…ቤተሰቦቿ ያሉበትን ሁኔታ አሰበች…ሁለት እግሮቹን  አጥቶ ቤቱ የቀረውን ተወዳጅ አባቷን አሰበች፤የብቸኛ ታናሽ ወንድሟን የወደፊት ህይወቱን አሰበች በወቅቱ በኩርፊያ የተለያየችውን ፍቅረኛዋን አሰበች.. ሰገን ያሳየቻትን በስድስት አመት ውስጥ ሰርቼ አገኘሁት ያለችውን ብር መጠን አሰላች.እያሰራች ያለውን ቤትና የምትነዳውን መኪና አሰበች…በመጎምዠት በአፏ ምራቅ ሞላ ‹‹አይ እሞክረዋለሁ››አለቻት፡፡
‹‹እሞክረዋለሁአይሰራም..አደርገዋለሁ.ወይም ይቅርብኝ..መልስሽ ከሁለት. አንዱ ነው መሆን ያለበት››
‹‹አደርገዋለሁ፡፡››
እጇን ዘረጋችላትና ‹እንኳን ደስ አለሽ… የቤተሰባችን አባል ለመሆን ስለወሰንሽ ደስ ብሎኛል...ከእኔ በተሻለ ብልህ ሆነሽ ስኬታማ እንደምትሆኚ አምናለሁ›በማለት ጨበጠቻትና ፊት ለፊቷ ያለውን ወረቀት አነሳችና ከመካከሉ ሁለት ፎርም በማንሳት ከእስኪርፕቶ ጋር አውጥታ እየሰጠቻት አንብቢውና ፈርሚበት..ያው በእኛ መካከል ዋናው የወረቀት ውል ሳይሆን የደም ውል ነው...አንዴ ቤተሰብ ሆነሽ ወደውስጥ ከገባሽ በህይወት ጭምር እንታመንሻለን ፤በህይወትሽ ጭምር ትታመኚናለሽ ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም እስክትጨርሺ መጣሁ ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደውስጥ ገባች…ሳባም ማንበብ ጀመረች…
አሰሪውና ሰራተኛውን ማክበር የሚገባቸውን ኃላፊነትና ያላቸውን መብት የሚደነግግ ነው፡፡
ለምሳሌ፡
ሰራተኛው..በስራ ሂዳት የሚያጋጥሙትን ሰዎች ማንነት  ሆነ  ከእነሱ  ጋር ያሳለፈውን ማንኛውንም ምስጢራዊም ሆኑ ቀላል ነገሮችን ከማንም ጋር አንስቶ ማውራትም ሆነ መወያየት በጥብቅ የተከለከለ ነው፤ከቤተሰብ  ከእናት  ጋር ቢሆንም፡፡ ይሄንን መተላለፍ ሚስጥሩ እንደሚያስከትለው ጉዳት መጠን    መረር ያለ ቅጣት ያስከትላል፡፡
ህመም ወይም የታወቀ ከባድ ችግር ካልገጠመ በስተቀር ደንበኛ በቀጠሮ በተገኘበት ጊዜ ከስራ ቦታ ላይ አለመገኘትም ሆነ ማርፈድ ፈፅሞ የማይፈቀድና ይቅርታ የማያሰጥ ስህተት ነው፡፡
ከደንበኞች የሚሰጥ ማንኛውንም የብር ስጦታ፤የጌጣጌጥ ስጦታ፤ከዛም ከፍ ያለ እስከ ቤት ስጦታ ድረስ ቢሰጥ ሙሉ በሙሉ የሰራተኛው የግል ሀብት ነው፡፡
ድርጅቱ ሰራተኞቹ በደንበኞች አካላዊ ጥቃት ድብደባም ሆነ መሰል ጥቃት ቢደርስባቸው ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ እስከ ውጭ ሀገር በመላክ ሙሉ ህክምና እንዲያገኙ የማድረግ ጥቃት አድራሹ ደንበኛ ጋር በህግም ሆነ በሌሎች ዘዴዎች በመጠቀም በቂ ካሳ እንዲያገኙ የማስደረግ ኃላፊት ይወስዳል፡፡ቅድሚያ ግን አንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ ደንበኞች መረጣ ላይም ሆነ በሂደት ክትትል ያደርጋል…የራሱን ዘዴ በመጠቀም በስውርና በግልጽ ደህንነታቸውን ይከታተላል፤ ይጠብቃል፤ከስራ ሰዓት ውጭ የፈለጉበት ቦታ መሄድ፤ቤተሰቦቻቸውን የመጠየቅ ከጓደኞቻቸው ጋር መዝናናት ሙሉ መብት ያላቸው   ቢሆንም  ለደህንነታቸው ሲባል እንቅስቃሴያቸውን በተለያዩ ዘዴዎች ክትትል ይደረግባቸዋል፡፡ የስራቸው ፀባይ ከሀገሪቱ ትላልቅ ሰዎች ጋር   ስለሚያገናኛቸው በተቻለ መጠን የሚሄዱበቸው ቦታዎች የተመረጡ የሚያገኟቸው ሰዎች ወደአደጋ የማያስገቡ መሆን እንዳለባቸውም የሚያብራራ አንቀጽ አለበት.በአጠቃላይ እነዚህንና መሰል መመሪያዎች ነው ያሉት

‹‹አንዴ ገብቼበታለሁ የራሱ ጉዳይ፤ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም›› አለችና እስኪሪፕቶውን አነሳችና ሁለቱም ወረቀት ላይ ፈርማ በእፎይታ ከመቀመጫዋ ተነስታ ስትንጠራራ ሰገን ከሄደችበት በፈገግታ መጣች፡፡ የፈረመችውን ወረቀት ከጠረጴዛ ላይ በማንሳት አንዴ በስሱ አየችና ወደቦታው መልሳ በማስቀመጥ ቦርሳዋን አነሳችና ከፈተች….አንድ በካኪ የተጠቀለለ ነገር አነሳችና እጆ ላይ አስቀመጠች
ሳባ‹‹ምንድነው?›› ጠየቀቻት
የመጀመሪያ ወር ደሞዝሽ ነው…አንደንድ ነገሮችን ማስተካከል ስላለብሽ ብር እንዳይቸግርሽ ነው ቅድሚያ የምንከፍልሽ..ከአሁን ሰዓት ጀምሮ የእኛ ቤተሰብ ነሽ፡፡የምትኖሪበት ቤት የኪራይ ከሆነ  መልቀቅና  እቃዎችሽን  ቤተሰቦችሽ  ጋር ወይም ሌላ የሚመችሽ ቦታ ማስቀመጥ ይኖርብሻል ፤ቦታ ማይኖርሽ ከሆነ ደግሞ ንገሪኝና በጥንቃቄ እኛ መጋዘን ውስጥ ሊቀመጥልሽ ይችላል... ከስራ ለመልቀቅና ሁኔታዎችን ለማስተካከል አንድ ሳምንት ብቻ ነው ያለሽ...ልክ  የዛሬ  ሳምንት ከጥዋቱ አራት ሰዓት ደምሳሽ  ያለሽበት  ቦታ  ድረስ መጥቶ ይወስድሻል፡፡ ሻንጣሽን ዝግጁ አድርገሽ ጠብቂው›የሚል የተቀጣጠለ ረጅም ትዕዛዝ አስተላለፈችላት ፡፡
ሳባ ትዕዛዙን በትክክል እንደሰማች አረጋግጣ በተነገራት መሰረት እንደምትተገብረው ጭንቅላቷን ላይ ታች እየነቀነቀች አረጋገጠችና የተሰጣትን ብር ቦርሳዋ ውስጥ በመክተት ለመሄድ ዝግጁ ሆነች..
‹‹እንግዲህ በርቺ…በራፍ ድረስ ልሸኝሽ›› ብላት ተከትላት ወደሳሎኑ መውጫ መራመድ ጀመሩ ልክ ቤቱን ለቀው ወጥተው በረንዳ ላይ እንደደረሱ…‹‹ይቅርታ አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ››አለች ሰገን
ሳባም ለመሰማት ዝግጁ ሆና ትኩረቷን ሰጠቻት

‹‹ፍቅረኛ አለሽ?››

‹‹አዎ ግን አሁን ላይ ብዙም ጥሩ አይደለንም››

‹‹እንደዛ ከሆነ ጥሩ ነው፡፡››

‹‹እንዴት?››ስትል ጠየቀች ገርሟት…‹‹እንዴት ነው ሰው ከፍቅረኛው ጋር ጥሩ አለመሆኑ ጥሩ ሊሆን የሚችለው፡፡››በውስጧ ነው ያሰበችው
‹‹ስራው ፍቅረኛ ባይኖርሽ ተመራጭ ነው…ማለት ቢያንስ የስራውን ባህሪ በጣም እስክትለምጂውና እዕምሮሽ እስኪጎለበት ስራውንና የፍቅር ህይወትሽን አስማምቶ ማስኬድ በጣም ፈተና ነው የሚሆንብሽ..ለዛ ነው ጥሩ ነው ያልኩት፡፡››
‹‹ገባኝ›› አለች ሳባ

‹‹ይቅርታ በጣም ፐርሰናል ጥያቄ ልጠይቅሽ››

‹‹ችግር የለም ..ጠይቂኝ፡››

‹አይ እንደውም ጥያቄ ሳይሆን ምክር ነው.. አጭር ምክር…የዛሬ ሳምንት ወደእኛ ስትመጪ ሴት ሆነሽ ብትመጪ መልካም ነው››

‹‹አልገባኝም›አለቻት  የእውነትም  ስላልገባት‹‹እንዴ  ምን  ለማለት  ፈልጋ
ነው.? አሁንስ    አይደለሁም  እንዴ…? 
‹‹ማለቴ ድንግል ከሆንሽ ለምትፈልጊው ሰው ሰጥተሸ ብትመጪ  ለማለት ነው..አንደዛ ቢሆን ለእኛም ለአንቺም ቀላል ይሆናል…ማለት ያው እኛ ሴቶች ድንግልናችን ከፋም ለማም ትርጉም ባለው መንገድ ሲወገድ ደስ  ይለናል…ለዛ ነው እንዲህ ያልኩሽ..በይ ቻው..ደምሳሽ እየጠበቀሽ ነው…ቤትሽ ወይም የምትፈልጊው ቦታ ድረስ ያደርስሻል፡››፡ብላት ጉንጯን ሳመችና ፊቷን  አዙራ ወደቤት ተመልሳ ገባች ሳባም እግሯን  የመጎተት ያህል እየሳበች  ቆሞ ወደሚጠብቃት ወጠምሻ ሹፌርና መኪና ተጓዘች፡፡


💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ሳባ‹‹ወደ ትምህርትሽ ለመመለስ አልፈልግሺም ነበር….?››መሀከል ገብታ ጥያቄ ጠየቀቻት ምን ሊያደርግልኝ…ተምሬ ስንት ልቀጠር..ሶስትና አራት ሺ ብር…ምን ላደርግበት.?ነገ ብታመም እንደእናቴ ባዶ ቤት ማቅቄ ልሞት? ነገ ልጅ ብወልድ በድህነት ውስጥ ላሳድገው….?አይ ምንም ሰርቼ ምንም ሀብታም መሆን ብቻ ነው የፈለኩት….ለምሳሌ…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዛሬ ላይ

ሳባ  ሊቱን  ሙሉ  በትዝታ  ከወዲህ  ወዲያ  ስትዋዥቅ  ነው  ያደረችው…ለሰከንድ እንኳን እንቅልፍ በአይኗ አልዞረም…አሁን የትዝታ ጉዞዋን መሀከል ላይ ሳትቆጭ
ያቆመችው ታናሽ ወንድሟ ራጂ የተኛችበት ክፍል ደረስ መጥቶ በእናቱና በእሷ መካከል ሰርስሮ መሀከላቸው ሲገባ ነው፡፡

‹‹አንተ ጓረምሳ ሴቶች ክፍል ምን ትሰራለህ?››

‹‹እህቴ ናፍቃኝ ነዋ››

‹‹ወደራሷ ልጥፍ አድርጋ በማቀፍ  ግንበሩን ሳመችው፡፡››

‹‹እህቴ ዛሬም ታድሪያለሽ አይደል?›

‹‹ማደር አላድርም …ግን አሁን እንነሳና ከተማህን ዞር ዞር አድርገህ አሳየኝ..ከዛ ትንሽ ዘና ብለን ከሰአት በኃላ እሄዳለሁ፡፡››
ስንዱ(እማሆይ  አፀደ)  ከአልጋዋ  እየወረደች‹‹  ምነው  ዛሬ  አድረሽ  ነገ  በጥዋቱ     -ብትሄጂ አይሻልም?››ስትል ሀሳብ አቀረበችላት፡፡
‹‹አይ..  ቢያንስ  ነገ  በጥዋት  ሀኪሜ  ጋር  ተመልሼ  በመሄድ  ስላቋረጥኩት  -መድሀኒት ነገሬው የሚለኝን መስማት አለብኝ፡፡››

‹‹በቃ እንደዛ ከሆነ ተነሱ እስከዛ እኔ ቁርስ ልስራ፡፡››

‹‹አይ አንቺም ተነሺና አብረን ውጭ ነው ቁርስ ምንበላው፡፡››

‹‹ባይሆን እናንተው ሂዱና  ስትመለሱ  ከእኔ  ጋር  ሆነን  የሆነ  ቦታ እንሄዳለን፡፡ ማለቴ ብዙም ጊዜ የሚፈጅ አይደለም፡፡እዚሁ ቅርብ ነው፡፡15 ደቂቃ ቢወስድብን ነው፡፡››

‹‹ሳባም …እሺ በቃ›› ብላ ለባብሳ ከወንድሟ ጋር ተያይዘው ከግቢ ወጡ፡፡ቀጥታ የሄዱት ሻለቃ ደራርቱ  ቱሉ  ሆቴል  ነው፡፡  እዛ  እየተዝናኑና  ቁርስ  እየበሉ እተጫወቱ   አራት ሰዓት  ሆነ ፡፡ ከዛ ወጡና ወደስጦታ መሸጫ ሱቅ እየሄዱ ሳለ ስልኳ ጠራ፡፡አየችው ..በጣም የምትፈልገው ስልክ ነው፡፡አነሳችው፡
‹‹እሺ ደራሲ ጳውሎስ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁ.. ሰላም ነኝ››
‹‹እሺ እንዴት እየሆነልህ ነው…?›
‹‹ጨርሼለሁ..ዛሬ ወደአዲስአባ ልንመጣ ነው…ከመነሳቴ በፊት ልደውልልሽ ብዬ ነው፡፡››
‹‹በእውነት  በጣም  አስደሳች  ዜና  ነው  የነገርከኝ…በቃ  እኔም  አሁን  አሰላ ነኝ…ከሰአት እነሳለሁ..ነገ እንገናኛለን፡፡››
‹‹እሺ በቃ ቸው››
‹‹ደግሞ የጉዞውም ነገር መስመር ይዞል..በአስራአምስት ቀን ውስጥ የሚጠናቀቅ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ደስ ይላል፡፡በቃ ነገ አንገናኝ፡፡››ብሏት   ስልኩን   ዘጋው፡፡እሷም   ስልኳን   ወደኪሷ መልሳ በደስታ ፈጋ ወንድሟን እንዳቀፈች ወደ ሱቅ ገባች፡፡ ትኩስ አበባ ከገዙ በኃላ ቀጥታ ወደቤተክርስትያን ነው ተያያዘው የሄዱት፡፡ ሁለቱም አባታቸው መቃብር ላይ የያዙትን አበባ አስቀመጡና ሀውልቱ ስር ጎን ለጎን ቁጭ አሉ፡፡ ሁለቱም በዝምታ ተሸብበው በየራሳቸው ትዝታ መዳከር ጀመሩ፡፡ሳባ ትዝ ይላታል፡፡የዛሬ ሰባት አመት በፊት የአባቷ አሟሟት፡፡ 
አዎ   ሙሉ   በሙሉ በእሷ ጣጣ እንደሞተ ነው የምታምነው፡፡በዛ ምክንያት ደግሞ በቀል በውስጧ በቅሎ ሰው እስከመግደል ደርሳለች፡፡እርግጥ ቀጥታ የሽጉጥ ቃታ ስባ…ወይም ጩቤ በሰው ልብ ሰክታ አልነበረም ግድያውን የፈፀመችው፡፡ግን የአባቴ ዋነኛ ገዳይ ነች የምትላትን ሴት ያላትን ሁሉ አንድ በአንድ እንድታጣ አድርጋ ባዶዋን በማስቀረት በራሷ እጅ አንገቷን ገመድ ውስጥ አስገብታ ከዚህች አለም ህይወት እራሷን እንድትገላግል አድርጋለች፡፡አሁን ሌላ አንድ ትቀራታለች….ለእሷም የመጨረሻውን ቦንብ አጥምዳ ወደማጠናቀቁ ላይ ነች…ከዛ የሴትዬዋ እግሮች ቦንቦቹን ረግጠው ሲነሱ ሁሉ ነገሯ ቡም ብሎ ይበታተናል... ያ ወጥመድ….ደራሲ ጳውሎስ ፅፎ ያጠናቀቀው መፅፈህ ነው፡፡ያ መፅሀፍ ቦንብ ሆኖ ቀሪዋንና ኃያሏን ሴት ያስወግዳታል..‹‹አባዬ አይዞህ ..አንድ በአንድ እበቀላቸዋለሁ››አለች ሳባ፡፡
‹‹ምን አልሽ እህቴ …?አናገርሺኝ?››አላት ታናሽ ወንድሟ፡፡
‹‹አይ…. ከአባዬ  ጋር  እያወራሁ  ነበር፡፡››አለች  ደንግጣ፡፡ ራጂም ‹‹እህቴ …አባዬ እኮ በጣም ነው የሚናፍቀኝ፡፡›› አላት፡፡
‹‹እኔም በጣም ነው የሚናፍቀኝ…..በየጊዜው እናንተ ጋር የማልደውለው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ ?እንተን ሳወራ አባዬ ትዝ ስለሚለኝና እሱ ትዝ ሲለኝ ደግሞ ሀዘን ውስጤን ስለሚሸረካክተው ነው፡፡አባዬ በጣም ጀግናና ስማርት የሆነ አባት ነበር… ሲሞት አንተ ልጅ ስለነበርክ በደንብ ልብ ላትለው ትችችለህ…በተለይ ከአደጋው በፊት ሮጦ ልረፍ የማይል፤ ሰርቶ ደከማኝ የማያውቅ፤ ለቤቱ  ድንቅ አባወራ ለእኔና ለአንተ ድንቅ አባት ፤ለሰፈርና በቄሄው የተከበረ ልዩ ሰው ነበር…አባዬን ሳስብ ሁል ጊዜ ከአደጋው በፊት ስለነበረው ሁኔታ ነው ማሰብ የምፈልገው…››
‹‹እህቴ እኔ አንቺ ከምታስቢው በላይ አባዬን  አውቀዋለሁ.እርግጥ አምስት  አመቴ ላይ ነው የሞተው…ቢሆንም አምስት አመት  ሙሉ እኔን ከማሳደግ ውጭ ሌላ ስራም ሆነ ፍላጎት እልነበረውም…እማዬ  እናቴ  መሆኗን  በትክክል  ያወቅኩት እንኳን   እሱን   በሞት   ካጣሁ   በኃላ   ነው፡፡ከዛ   በፊት   ምተኛው   ከእሱ   ጋር
፤የሚያጥበኝ እሱ፤ ምግብ እራሱ የሚያጎርሰኝ እሱ ነበር..እስኪሞት ድረስ በእጆቼ ምግብ ቆርሼ መጉረስ አልችልም ነበር ፡፡እሰከዛ ድረስ በእሱ እጅ ካልሆነ ምግብ ወደአፌ አይገባም ነበር…በየቀኑ የሚነግረኝ ተረቶች የሚያነብልኝ መፅሀፎች ትዝታው  ዛሬ  የተከወነ  ያህል  ነው የማስታውሰው    ፡፡አንድ አይነት ተረት በቀን
ለ10 ጊዜ ደጋግመህ ንገረኘኝ ስለው አይሰለችም…በደስታ ያደርገዋል፡የአባዬ ጣፋጭ ድምፅ ዛሬም በጆሮቼ ውስጥ ሲንቆረቆር ማደመጥ እችላለሁ፡››
በታናሽ ወንድሟ ልብ የሚነካ ንግግር እንባዋ በጉንጮቾ ተንኳለለ፡፡
ወንድሟ ቀጠለ‹‹…እህቴ የዛን ያህል እያስታወስኩት በዛ መጠን እየናፈቀኝ እንኳን ለምን አንዳማላማርር ታውቂያለሽ?››
መልሱን ለመስማት ተነቃቃች‹‹ለምንድን ነው?››
‹‹አንቺ ስላለሺኝ ነዋ…አንቺ እኮ ልክ እንደአባቴ ነሽ..አይደለም አሁን ላለሁበት ለወደፊት ህይወቴ እንኳን ትጨነቂያለሽ…ጀግና እህት ስላለኝ በአንቺ እፅናናለሁ..አባዬ ሲናፍቀኝ እዚህ እመጣና አንቺ ለእኔ  እና  ለእናቴ  ምታድርጊልን ነገር ሁሉ እነግረዋለሁ…ከዛ ደስ ሲለው አይቼ ወደቤቴ እምለሳለሁ.፡››
ከተቀመጠችበት ተንደርድራ ሄዳ አቀፈችው …ጭምቅ አድርጋ አቀፈችው.. እያገላበጠች ሳመችው…እሱ በእሷ ላይ ያለውን መመካት እሩብን   ያህል   እሷ በራሷ ላይ ኖሯት ቢሆን እጅግ ደስ ይላት ነበር፡፡ግን እሷ በውስጧ ትንሽነት ነው የነገሰው.. ፤ባዶነት ነው ልቧን የሞላው ፤ስጋት ነው እየናጣት   ያለው፤ተስፋ መቁረጥ ነው ዙሪያዋን የከበባት፣
እህትና ወንድም ተመልሰው  እቤት  ሲደርሱ  ስድስት  ሰዓት  አልፎ  ነበር… እናትየው ምርጥ  የተባለ  ምሳ  ሰርታ  ቡና  አፍልታ  ፤እቤቱን  አሟሙቃና አጫጭሳ ነበር የጠበቀቻቸው…የተዘጋጀውን ምግብ ከበሉና ከቡናውም አቦሉን ከጠጡ በኃላ ስንዱና ሳባ በተራቸው ተያይዘው ወጡ..
‹‹ስንድ የት እንደምትወስጂኝ ለማወቅ ጓጉቼያለሁ?››
‹‹ትንሽ ታገሽ ደግሞ አስደሳች ቦታ የምወስድሽ እንዳይመስልሽ››
‹‹እናስ..?››
‹‹ያው አስፈላጊ ቦታ ነው…. በተለይ ለእኔ?››
‹ለነገሩ ዝም ብዬ ነው የጠየቅኩሽ…መቼስ መዝናኛ ቦታ ይዘሽኝ ትሄጃለሽ ብዬ አላስብም…›
​​በዚህ ጊዜ የሆነ የቆርቆሮ በር ያለው ግቢ ደርሰው ነበር..ስንዱ እጇን  አሻግራ ከውስጥ የተሸነጎረበትን እንጨት ሳበችና በራፉን ከፈተች.. ተያይዘው ወደውስጥ ሲገቡ አንድ ጠና ያሉ ሴት ከበረንዳ ላይ ተቀበሏቸው
‹‹እንዴት ዋልሽ ልጄ..?ደህና ዋልሽ….?››ለሁለቱም የሞቀ ሰላምታ ሰጣቸው፡፡‹‹ግቡ  ግቡ …››ወደውስጥ ዘልቀው ሲገቡ ሶስት ክፍል ያለው ያረጀ ቤት ነው ፡፡ሰፋ ያለው ሳሎን መሰል ክፍል ውስጥ ሶስት አልጋ ተዘርግቷል፡
አንዱ አልጋ ባዶ ሲሆን ሁለቱ አልጋ ላይ አንድ አንድ ሰው ቁጭ ብለዋል፡፡አንዱ አልጋው ጠርዝ ላይ  ተቀምጧል  ፡፡ሙሉ  ፀጉረ  በረሀ  ነው…እድሜው  ከሀምሳ ትንሽ ከፍ ይላል፡፡አንድ እግሩ መሬት ረግጧል… ሌለኛው እግሩ ግን ግማሽ ነው.. በፋሻ ተጠቀልሎ ክራንች ላይ ተንጠልጥሏል፡ቀጣዩ አልጋ ላይ ያለውን ስታይ ጭራሽ ሁለቱ እግሮቹ ከጉልበቱ በታች ተጎምደዋል..ልክ እንደአባቷ..በተጨማሪም የግራ እጁ እጣት አልባ ነው፡፡
ስንዱ ሁለቱንም በስማቸው እየጠራች ስለጤናቸው ትጠይቃቸዋለች፡፡
‹‹አንቺ  እያለሽልን   ምን   እንሆናልን…?እግዚያብሄር   ከክፉ   ሁሉ   ይጠብቅሽ፣..ከእነቤተሰብሽ ክፉ አያግኝሽ..› በየተራ እየተፈራረቁ ይመርቋታል….ሳባ ባለችበት ደንዝዛ ቆማለች፡፡
ተዋወቋት ሳባ እያልኩ የማወራችሁ ልጄ እሷ ነች ››ሁለቱም በየተራ ለሰላምታ እጃቸውን ዘረጉላት፡፡ በደመነፍስ ጨበጠቻቸው፡፡ይዛት ወደሚቀጥለው ክፍል ስትገባ ሌሎች የተለያየ ጉዳት የተጎዱ ሁለት ሴቶች አሉ፡፡ በአጠቃላይ እዛ ቤት ውስጥ  እራሳቸውን  ሙሉ  በሙሉ  መርዳት  የማይችሉ  ከጉዳታቸው  ያላገገሙና  በህክምና እርዳታ ላይ የሚገኙ ሰባት ሰዎች ነበሩ…፡፡
ከ30 ደቂቃ ቆይታ በኃላ ምንም ሳይነጋገሩ በዝምታ እንደተሸበብ ወደ ቤት ተመለሱ፡፡
..ሳሎን  ባለ  ሶፋ  ላይ  ጎን  ለጎን  እንደተቀመጡ  ነው  ሰባ  ንግግሩን  በጥያቄ  የከፈተችው፡፡
‹‹ስንድ አልገባኝም…ምንድነው ያሳየሺኝ?››
‹‹ካየሻቸው ጉዳተኞች መካከል ሶስቱ በአሁኑ ጦርነት የተጎዱና ጡረታ ወጥተው ወደቤተሰባቸው የተመለሱ ቢሆን በጣም ዝቅተኛ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ በመሆናቸው በከፋ ሁኔታ ስቃይ ላይ ሆነው ስላየኋቸው ነው አሁን ወዳሉበት ቦታ ያመጣዋቸው ፡፡ሌሎቹም ሁለቱ በመኪና አደጋ  የተጎዱ  ሲሆን  የተቀሩት በተለያየ መንገድ አካላቸውን አጥተው አሁን ህክምና ክትትል ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ይሄንን ቤት ተከራይቼ ያየሻትን አስታማሚና ተንከባካቢ ቀጥሬላቸው በተቻለኝ አቅም ላሳክማቸውና የኑሮ ሸክማቸውን ለቃልልላቸው እየሞከርኩ ነው፡፡››
‹‹ይሄ ሁሉ ከመቼ ጀምሮ ነው?››
‹‹አመት ሊሆነኝ ነወ….እርግጥ ሰባቱንም በአንዴ አይደለም የተቀበልኳቸው.. በተለያየ ጊዜ ነው፡፡ ድነውና የተሻለ አማራጭ አግኘተው የሄዱም  ሁለት  ሌሎች ነበሩ..››
እንባ ያቀረዘዙ አይኖቾን በናብኪን እያበሰች፡፡‹‹ስንድ በጣም የሚገርም ስራ ነው››አለቻት፡፡
‹‹ሳቢ ይሄንን ለምን እንደማደርግ ታውቂያለሽ?››ስትል ስንዱ ጠየቀች፡፡
‹‹አዎ አውቃለሁ....የአባቴን መንፈስ ደስ ለማሰኘት ነው..እሱ በምድር ላይ የመጨረሻዎቹን የጉዳትና የህመም አመታትን ባሳለፈው አይነት ስቃይ ውስጥ
እያሳለፉ ያሉትን ሰዎች በመርዳት ነፍሱን ማሳረፍና ማስደሰት ስለፈለግሽ ነው፡፡››በእርግጠኝነት መለሰች፡፡
‹‹አይደለም..ለእሱ ብዬ አይደለም››
ሳባ ያልጠበቀችውን መልስ ስላገኘች ደነገጠች‹‹እና ታዲያ ለምንድነው?›
‹‹ለአባትሽ ራሱ በህይወት ሳለ በተቻለኝ መጠን ተንከባክቤው አስታምሜውና ብቸኝነት እንዳይሰማው አድርጌ ስለሸኘሁት ይሄንን ባደረኩለት ኖሮ ብዬ የሚቆጨኝ ነገር የለም…ይሄንን እያደረኩ ያለሁት ለአንቺ ብዬ ነው››
ሳባ አስፈሪ ድንጋጤ ደነገጠች‹‹አልገባኝም ለእኔ እንዴት?›
‹‹አንቺ አባትሽን ካጣሽ በኃላ ምን አይነት ስቃይ ላይ እንዳለሽ አውቃለሁ…ፈፅሞ መቀበል አልቻልሽም ...በመጀመሪያ አባትሽን ያሳጣሽ ድህነት መስሎሽ ቀንና ሌት በመስራትና የማትፈልጊያቸውን ነገሮች ሁሉ በማድረገ ገንዘብን ሰበሰብሽ … ሀብታም ሆንሽ… ግን ሀዘንሽን ሊያረግብልሽ አልቻለም…አሁን አሁን  ደግሞ  የአባትሽ  ሞት ሰበብ ራስሽ እንደሆንሽ በማሰብ ነፍስሽን እየተጠየፍሽ ራስሽንም እየቅጣሽ ነው፡፡በዚህ መንገድ ከቀጠልሽ እመኚኝ አንቺም ብዙ እድሜ የለሽም..እና ከአባትሽ መንፈስ የተጣላሽና የተቀያየምሽ ምስሎ ይሰማሻል››
‹‹ስንድ ልፊ ቢልሽ እኮ ነው …ያማ ምን ሚያጠራጥር ነገር አለው?››
‹‹እሱ ላይ ልከራከርሽ አልፈልግም..አንቺ በራስሽ በምታውቂም ምክንያት አባትሽ ቅር እንደተሰኘብሽ ወስነሽ ቢሆን እንኳን ከእሱ መታረቂያ መንገዱ አሁን አንቺ እየተጓዝሸበት ያለው የጥፋትና የውድመት መንገድ አይደለም…ይሄ አሁን እኔ ያሳየሁሽ መንገድ ነው ትክክለኛው፡፡የአዲስአባ ህይወት ይብቃሽ…እየዋጠሸና እያሰመጠሸ ነው….እኔና ልጄ በጣም ነው የምንወድሽ…ለእኛ  ስስታችን ነሽ…ከአባትሽ ሀዘን የተፅናናንብሽ የህይወት  ተስፋችን  ነሽ፤እባክሽ  እዚህ  ነይ አብረን አንኑር..እነዚህን ሰዎች ተንከባከቢያቸው.. ልክ እንደአባትሽ እያየሽ እርጂያቸው ፤እኔም ከጎንሽ ነኝ…እዳ ምናምን ካለብሽ እዛ  ያለውን  ቤትሽን ሽጭውና ከፋፍለሽ ነፃ ሆነሽ ባዶ እጅሽን ነፍስሽን ብቻ ይዘሽ ነይ..እዚህ ለሁለችንም የሚበቃ ነገር አለ …እኔ እናታችሁ መቼም አንገታችሁን እንድትደፉ አላደርግም..፡፡››
‹‹ስንድ ቆይ ግን እቤቱን ለምን ተከራየሽ…ፍቅር ቤቱን አላከራየሽውም ወይ  አልኖረሽበት..?
‹‹አስቤ ነበር.. ግን ይህ ቤት የአንቺና የወንድምሽ  ንብረት  ነው...ፍቃዳችሁን ሳልጠይቅ እናንተን ቅር የሚየሰኝ ነገር ማድረግ አልፈልግም..፡፡››
‹‹አይ ስንድ .ይሄ ቤት የእኛ ሳይሆን የአንቺ ነው...እናም ምንም ነገር ለማድረግ የእኛ ፍቃድ አያስፈልግሽም››
‹‹..እኔ ለአባቴ አልገባውም፡፡››
‹‹ለምን  አንዲህ አይነት ጨለማ ሀሳብ ከአእምሮሽ ማስወጣት እንዳቃተሸ ታውቂያለሽ ? የህመምሽ ዋና መንስኤ ይሄ መጥፎ ሀሳቦችን ወደራስሽ የመሰብሰብ አባዜ ስለተፀናወተሸ እንደሆነ ታውቂያለሽ››
‹‹እኔ እሱን አውቃለሁ…አንቺ ግን አባቴን እንደገደልኩት አታውቂም››
‹‹አባትሽን የወሰደው ፈጣሪ ነው ማንም አልገደለውም….እስትንፋሱ ስትወጣ እንኳን   አንቺን እየመረቀና እያመሰገነ ነበር የሞተው፡፡››
‹‹ለምን  እንዳዛ  እንዳደረገ  ታውቂያለሽ.?.በስተመጨረሻ  ልጁ  የማትረባ  ውዳቂ መሆኗን ስላወቀ እፍረት ተስመቶት ነው፡፡››
‹‹ስለምንድነው የምታወሪው?››
‹‹ለማንኝውም እርሺው…››አለችና…ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደመኝታ ቤት በመሄድ ይዛ የመጣችው ቦርሳ አንጠልጥላ ወደ ሳሎን ተመለሰች…ከቦርሳ ውስጥ  ቼክ አወጣችና አምሰት መቶ ሺ ብር ፃፈችበት፡፡
ስንድ እንደአንቺ አይነት እናት እና ጓደኛ ስላለኝ በጣም እድለኛ ነኝ...እኔ የማረባና ከንቱ ሰው ስለሆንኩ አይገባኝም እንጂ አንቺና ወንድሜ ለእኔ ያላቸሁን ፍቅር ብቻ ቢሊዬን ብር አይገዛውም..አሁን ልሂድ አንድ ሁለት  ወር  ላስብበት..ከዛ ተመልሼ እመጠና እናወራበታለን.እስከዛ ይህቺን ያዣት፡፡››
‹‹እኔ እኮ ብር አልጠየቅኩሽም.ብርም አልተቸገርኩም››
‹‹አውቃለሁ..ካለሽ አስቅምጪው…ሲቸግረኝ መልሼ ወስዳለሁ›› አለቻት ፡፡›››
‹‹‹ ፣እሺ ካልሽ ብላ መኪናዋ ድረስ ሸኘቻት፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ዛሬ ላይ ሳባ  ሊቱን  ሙሉ  በትዝታ  ከወዲህ  ወዲያ  ስትዋዥቅ  ነው  ያደረችው…ለሰከንድ እንኳን እንቅልፍ በአይኗ አልዞረም…አሁን የትዝታ ጉዞዋን መሀከል ላይ ሳትቆጭ ያቆመችው ታናሽ ወንድሟ ራጂ የተኛችበት ክፍል ደረስ መጥቶ በእናቱና በእሷ መካከል ሰርስሮ መሀከላቸው ሲገባ ነው፡፡ ‹‹አንተ ጓረምሳ ሴቶች ክፍል ምን…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሳባ የአሰላን ከተማ ለቃ እንደወጣች በደመነፍስ ነበር ስትነዳ የነበረው፡፡ ሀሳቧ ሁሉ ወደኃላ ተመልሷል..ያንን የተረገመ ስራ እንዴት እንደ ጀመረች አስር  አመት ወደኃላ ተመልሳ ማብላላት ጀመረች፡፡
ከ10 ዓመት በፊት
ያኔ በዛ ዘመን አዲሱን ስራዋን ለመጀመር ከሰገን  ጋር የመጨረሻ ድርድር ስታደርግ እና ሲለያዩ አንድ ምክር ሰጥታት ነበር…‹‹ድንግል ከሆንሽ ለምትወጂው ሰው ስጪው፡፡››ነበር ያለቻት…ግን በፍጥነት ማድረግ አልቻለችም ነበር…በወቅቱ የምትወደው ሰው ልቧን ሰብሮ ካሳዘናት ሰነባብቷል….‹‹ለእሱ ድንግልና ሳይሆን ከተቻለ በቀል ነው የሚገባው››ስትል  በማሰብ….ስለድንግልናዋ ማሰብና መጨነቅ ትታ…ዕቃዋን በየካርቶኑ እያስገበባች አሸገች፤ልብሶቿን በሁለት ሻንጣ ጠቅጥቃ አሳሰረች…የምትተኛበት ፍራሽ ብቻ እንደተዘረጋ ቀረ…ቀጥሎ ምን እንደምታደርግ ግራ ገባት፡፡መቼስ ይሄን ሁሉ ኮተት ይዛ በህዝብ ትራንስፖርት ተጠቅማ አሰላ ድረስ ማጓጓዝ አትችልም...እንዴት አድርጋ…‹‹ደግሞ ስኖርበት ባዶ የነበረው ቤት  አሁን ልለቅ ስል እንዴት ነው እንዲህ ሜዳውን የሞላው?››ሥትል በማሰብ ተገረመች፡፡‹‹ግን አሁን ይሄንን ሁሉ ኮተት ብረት ድስት፤ሰሀን፤ብርጭቆ ምድጃ ለምንድነው የሰበሰብኩት? ለምን ለተቸገረ አላከፋፍለውም?››ራሷን በትዝብት ጠየቀች፡፡
  ግን ደፍራ ነገ ሀብታምና  ሁሉ  ነገር  የተረፈው  እንደምትሆን  ተማምና ‹‹አይ ይሄን ኮልኮሌ አልፈልግም ላከፋፍለው››ልትል አልቻለችም…
ወሰነች.‹‹አዎ ብር አለኝ… አሰላ ድረስ የሚወስድልኝ መኪና ብፈልግ ይሻላል››ስትል አሰበች…‹‹አዎ መርካቶ ብሄድ ጭነት መኪና አላጣም….ጭነው ሲጨርሱ በዚሁ ጎራ ቢሉ ከላይ ጣል ጣል አድርገው ይወስዱልኛል….››ብላ ስሌት ሰራችና ወደመርካቶ ለመሄድ ካሰበች በኃላ ሌላ የተሻለ ያለችው ሀሳብ ብልጭ አለላት፡
ደምሳሽ ትዝ ኣላት….እርግጥ በወቅቱ ለዚህ የሚያበቃ ትውውቅም ሆነ ንግግር.አልነበራቸውም...ቢሆንም.ያው‹‹ቤተሰብ ሆነናል››ብሏት የለ. ብትጠይቀው ምንም ክፋት እንደሌለው አሰላች…ሸፌር ስለሆነ ሌሎች ሹፌሮችን ስለሚያውቅ ወደአሰላ የሚሄድ የጭነት መኪና ብዙም ሳይለፋ በስልክ ሊጨርስላት ይችላል…ስልኳን አወጣችና ደወለችለት..ከሶስት ጥሪ በኋላ ተነሳ..
‹‹ጤና ይስጥልኝ የእኔ እመቤት››

‹‹አቶ ደምሳሽ ሳባ ነኝ .አወቅከኝ?በቀደም…››

‹‹እመቤቴ አውቄሻለሁ..ማብራራት አይጠበቅብሽም…አንቺን እንዴት ልዘነጋ እችላለሁ፡፡ለዛውም ቤተሰብ ሆነን?››ነበር ያላት…
‹‹በእውነት ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ነው ያደረከው››አለችው ከምሯ፡፡
‹‹አረ ምንም የተለየ ነገር አልተናገርኩም…ለማንኛውም ምን ልታዘዝ?››

‹‹እየፈራሁ  ነው  የደወልኩት..ሌላ  ላስቸግረው  የምችል  ሰው  ስለሌለ  ነው እባክህ ከድፍረት አትቁጠርብኝ››

‹‹በነገራችን ላይ  አልተነገረሽም መሰለኝ?››

‹‹ምኑን?››

‹‹ከዛሬ ጀምሬ በማንኛውም ነገር አንቺን እንድጠብቅ፤እንድታዘዝና የምትፈልጊውን ነገር ሁሉ እንዳሟላልሽ ታዝዣለሁ…ስለዚህ እኔን  ማዘዙን ከዛሬው ተለማመጂው…ለአንቺ መታዘዝ ስራዬ ነው›› አላት፡፡
‹‹ማዘዙን?››

‹‹አዎ ማዘዙን››

‹‹አይ እንዳልጠየቅህ አደረከኝ…በቃ ይቅርብኝ ሌላ አማራጭ እፈልጋለሁ፡፡››

‹‹አረ ተይ ቀለል አድርጊውና የምትፈልጊውን ንገሪኝ..ካለበለዚያ አሁኑኑ ሰፈርሸ እመጣለሁ››አላት
‹‹ኸረ ተው…እሺ ያው ሹፌር  ስለሆንክ ሹፌሮችን ታውቃለህ ብዬ ነው››

‹‹አዎ በደንብ አውቃለሁ…ምን ፈለግሽ?››

‹‹የፈለኩትማ ያው ሰሞኑን ስልጠና ጠቅልዬ ስለምገባ የምኖርበትን ቤት ለቅቄያለሁ….ቤተሰቦቼ ያሉት አሰላ ነው…እቃዎቼን ወደእዛ ለመውሰድ  ፈልጌ ነበር…እና ወደዛ የሚሄድ የጭነት መኪና ፈልጌ ነበር..እንዴት እንደማገኝ  ግራ ገብቶኝ ነው››
‹‹ወይ ለዚህች ነው እንዴ..?ለመቼ ነው..?››

‹‹ከተቻለማ ለዛሬ ነው…ካልሆነም ለነገ ጠዋት…››

‹‹ስልኬን ጠብቂ…መልሼ እደውላለሁ፡፡››

‹‹በእውነት ከልቤ ነው የማመሰግነው››

‹‹በይ ቻው በቤተሰቦች መካከል መመሰጋገን የለም ››ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡

ከ8  ደቂቃ  በኃላ  ነበር  ስልኳ  መልሶ  የጠራው…ስታየው  ደምሳሽ  ነው..በዚህ ፍጥነት አልጠበቀችም.
አነሳችውና ‹‹ሄሎ አገኘህልኝ?››አለችው፡፡

አዎ እቃሽ ብዙ ነው እንዴ ?ማለት ፒካፕ መኪና አይችለውም..?››

‹‹አረ በደንብ ነው ሚችለው››

‹‹እንግዲያው አሁን 5 ሰዓት ሆኗል 7 ሰዓት ሰፈር ደርሶ ይደውልልሻል..እስከዛ የቀረሽ ነገር ካለ  አስተካክይ››
በደስታ ስልኩን ዘጋችና የመጨረሻውን ዝግጅት ማድረግ ጀመረች፡


ለ7 ሩብ ጉዳይ ደወለላት...ፈጥና አነሳችው

‹‹ሄሎ ደምሳሽ...እንዴት ሆነልህ?››

‹‹ያው ግሎባል ጋር ሰማያዊ ደብል ፒካኘ ቲዬታ መኪና ይዞ እየጠበቀሽ ነው።››ስልኳን እያወራች ቤቱን ለቃ ወጣች‹‹እንዴት እንደማመሰግንህ አላውቅም"
"ችግር የለውም… ስትመጪ ምሳ ትጋብዢኛለሽ"
‹‹አረ  ችግር  የለውም...ግን  ክፍያውን  እንዴት  ነው  የማደርገው  ማለቴ
ነግሮሀል?"

‹‹ዋጋው ችግር የለውም...ወላጆችሽ ምሳና ቡና ከጋበዙት ይበቃዋል››
‹‹እውነቴን እኮ ነው...ትቀልድብኛለህ አይደል?››
በዚህ ጊዜ ግሎባል ጋር ደርሳ ነበር ...በምልክት የነገራትን ፒካፕ ወዲያው አየቻት...ለሹፌሩ ወደእሷ እንዲመጣ በእጇ ምልክት ጠራችውና መኪናዋን ማንቀሳቀሱን ካየች በኃላ ፊቷን አዙራ ወደቤቷ ተንቀሳቀሰች፡፡
‹‹ሰውዬውን አግኝቼዋለሁ" ‹‹እ..ታዲያ አናገርሽው?"  ‹‹አይ አላናገርኩትም"
"ታዲያ ልደውልለትና ልጠይቅልሽ ወይስ አንቺው እዛው ትከራከሪዋለሽ?"
‹‹አይ አመሰግንሀለሁ...ከዚህ በላይማ ላስቸግርህ አልፈልግም...በቃ ቻው።››
‹‹ቻው በቃ ሚቸግርሽ ነገር ካለ ደውይ››
እሷ የቤቷ በራፍ ጋር ስትደርስ ፒካፗ አጠገቧ  ደርሳ  በስሱ  ክላክስ  ሲያደርግላት ስልኩን ፈጠን ብላ ዘጋችና ወደግቢ ገብታ የመኪና መግቢያ በራፍ ከፈተች… መኪናዋ ወደውስጥ ዘልቃ ገባችና የግቢው መሀል አካባቢ ቆማ ከገቢናዋ  ሹፌሩ ዱብ ብሎ ወረደ...በድንጋጤ እጇን አፏ ላይ ከደነች።
‹‹ምነው አስደነገጥኩሽ እንዴ?››
"እዚህ ሆነህ ነው እንዴ የምታስለፈልፈኝ...?ባለመኪናው የት አለ?"
‹‹መኪናው የድርጅቱ ነው...ሹፌሩም ደግሞ እኔ ነኝ.."
‹‹ኸረ  ደምሳሽ  እንዲህ እኮ   መቸገር  አልነበረብህም።አሰላ  ድረስ  እኮ  ነው።

"ይሄ የእኔ ሀሳብ አይደለም..ታዝዤ ነው...መኪና እየፈለግሽ እንደሆነ ለሠገን ስነግራት...ራስህ አድርስላት ብላ አዘዘቺኝ...ይልቅ አሁን ሰዓቱ እየነጎደ ስለሆነ እቃሺን ቶሎ ጫን ጫን አድርገን እንውጣ›› አላት። እየከበዳት እቃዋን ወደ ተቆለለበት ክፍል ይዛው ገባች..እቃውን ጭነው ከግቢው ለመውጣት 20 ደቂቃ ብቻ ነበር የወሰደባቸው።
///
11 ሰዓት ላይ ቤት ደረሱ እቃው እስኪወርድ፤ መክሰስ በልተው የተፈላውን ቡና ጠጥተው እስኪያጠናቅቁ ለአንድ ሰአት ሩብ ጉዳይ ሆነ...ሳባ    ከቤተሰቦቿ ጋር ስትጫወት አድራ በማግስቱ ረፈድፈድ ሲል ነበር መመለስ   የፈለገችው። ያንን ዕቅድ ያወጣችው ሹፌሩ ደምሳሽ መሆኑን ከማወቋ በፊት ነበር። በኋላ ግን ለእሷ ብሎ አሰላ ድረስ መጥቶ እንዴት ብቻውን እንዲመለስ ትተወው?ያ ነው የጨነቃት፡፡ እርግጥ እርሱም በእንግድነት እነሱ ቤት እንዲያድርና ጥዋት አብረው እንዲመለሡ ጠይቃው ነበር። እሱ በማግስቱ 12 ሰዓት አዲስ አበባ ላይ የሚሰራው ስራ ስላለ እንደማይችል ስለነገራት አብራው ለመመለስ ወሰነች። ሁሉን