አትሮኖስ
228K subscribers
104 photos
3 videos
41 files
303 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቢ


‹‹በማግስቱ ሰራ መሄድ አልቻለችም…ኸረ እንደውም ከተኛችበት መንቀሳቀስም አልቻለችም፡፡ ሀሳብ እንዲህ ድቅቅ አድርጎ እንደሚያደክም ይሄ በህይወቷ የመጀመሪያው ልምዷ ነው፡፡ ዝልፍልፍ ነበር ያለችው…ስጋትና ጉጉት..ፍራቻና ድፍረት..
‹‹ለአለቃዋ በጣም ስላመመኝ መምጣት አልቻልኩም›› ብላ በሚሴጅ መልዕክት ላከችለት፡፡
‹‹ሳምንቱን ሙሉ ስታወርድና ስታወጣ ስታስብና ስታሰላስል ቆይታ ቅዳሜ ዕለት ወደማታ ለትብለጥ ደወለችላትና እሁድ እንድምትመጣ ነገረቻት፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት መኪና እንደምትልክላት ነገረቻት፡፡
ስትደውልላት ወስና አይደለም….አግኝታት… የበለጠ ማብራሪያ፤የበለጠ ገለፃ እንድታደርግላት ፈልጋ እንጂ...አዎ በሳምንት ውስጥ ከአንድ ሺ በላይ ጥያቄዎች ወደ እዕምሮዋ ተግተልትለው ገብተው መልሰው ወጥተዋል..ታዲያ ቢያንስ መሰረታዊ የሆኑ እንዲመለሱላት የምትፈልገው አስራ ምናምን የሚሆኑ ጥያቄዎች አሉ…የስራውን እድል የምትቀበለውም  አሻፈረኝ የምትለውም  እነሱ ላይ ተንተርሳ እንደሆነ ከራሷ ጋር ባደረገችው ውይይት ውሳኔ ላይ ደርሳለች፡፡

ለምሳሌ ጥያቄ ቁጥር አንድ የተባለውን ያህል ብር በወር እስከ 100ሺ ብር ታገኛለች?100ሺ ብሩ ይቅር እሺ 50ሺ ብር እንኳን እንደምታገኝ ማረጋገጫዋ ምንድነው…?ይሄ ተስፋ የውሸት ቢሆንስ?
‹በሶስት ወር ስልጠና የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ ባትሆንስ…?ተጨማሪ ስልጠና ይሰጣታል ወይስ ትባረራለች?፡፡›
‹‹ከማሳጅ ሙያ ውጭ እንድትሰጥ የሚጠበቅባት አገልግሎት ምንድነው..?

‹‹እንደ ተነገራት ዋናው የደንበኞቿን ፍላጎት ያለምንም መሸራረፍ 100 ፐርሰንትእንድታሟላና ፍፁም ደስተኛ ሆነው እንዲመለሱ ማድረግ ነው…ይሄ የወሲብ ጥያቄንም ያጠቃልላል….?››
‹‹ደንበኞቿ ወንዶች ብቻ ናቸው ወይስ ሴትም ወንድም….? የተመረጡ  ሰዎች ናቸው ወይስ  ማንም  አገልግሎቱን  የፈለገና  መክፈል  የሚችል  ሰው  ሁሉ መገልገል ይችላል?››
‹‹በስራ ላይ እያለች በደንበኞቿ ጥቃት ቢደርስባት ድርጅቱ እስከምን ድረስ ይከላከልላታል››…ወዘተ
እነዚህን አንድ በአንድ በማንሳት በዝርዝር እንድታስረዳት ካደረገች በኃላ ከዛ በስራው ለመቀጠልና ወደስልጠና ለመግባት ትወስናለች፤ካለበለዚያም እስከአሁን

ላደረገቸላት.እንክብካቤና ቀናነት አመስግናት ወደ ድህነት ስራዋ ትመለሰላች.. አዎ እንደዛ ወስና ነው የደወለችላት፡፡

እሁድ በተመሳሳይ  ሰዓት  በተመሳሳይ  ቁጥር  ተመሳሳይ ስልክ  ተደወለላት
..ተዘጋጅታ ስትጠብቅ ስለነበረ ቦርሳዋን አነሳችና ወጣች፡፡ ዛሬ እንደባለፈው ሳምንት ፍፁማዊ በሚመስል መሽቀርቀር አይደለም፤ጉጉቷም የተለየና በስጋት የተሞላ ነው፡፡
ካዛንቺስ ደርሰው መኪናውን እንደተለመደው ግቢው ውስጥ አስገብቶ  አቆመና ከፍቶ አስወረዳትና እጇን ይዞ ወደሳሎን ወሰዳት….በተመሳሰይ ለሰራተኛዋ አስረከባት..ሰራተኛዋ ቤተኛነትን በሚያሳይ የጋለ ሰላምታ ከተረከበቻት በኋላ ይዛት ወደውስጥ ገባች..ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ስትጠብቃት የነበረችው ግን ትብለጥ አልነበረችም…ሌላ በእሷ ከእድሜ አራት ወይም አምስት  አመት  የምትበልጥ ጠይም ረጅም ሞዴል መሳይ ቆንጆ ሴት ነች፡፡ ከመቀመጫዋ ተነሳችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋችላት..
‹‹ይህቺም እንደእኔ በስራው ተመልምላ  ይሆን  የመጣችው..? አንድ  ላይ ልታናግረን ይሆናል አንድ ላይ የጠራችን ?››ስትል አሰበችና ቅር አላት…
ያ ሁሉ ጥያቄ ሌላ ሰው ፊት እንዴት አድርጋ ትጠይቃታላች...ሀሳቧን ዘርዝራ ሳትጨርስ…ልጅቷ‹‹ሰገን እባላለሁ..ካልተሳሳትኩ አንቺ ሳባ ነሽ››አለቻት
ለሰላምታ የሰነዘረችውን የሚቀነጠስ የሚመስለውን ጣቷን አየጨበጠች…‹‹አዎ አልተሳሳትሸም››አለቻት
‹‹እትዬ በቃ እናመሰግናለን..የምንፈልገው ነገር ካለ እንጠራሻለን››አለችና ሰራተኛዋን ወደ ውስጥ ሸኘቻትና ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ ሳባንም

ከፊት ለፊቷ እንድትቀመጥ ጋበዘቻት...ሳባ ግራ በመጋባት ከስር እስከ ላይ ብትቃኛትም ምንም መገመት አልቻለችም…ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ በዛ ያሉ ወረቀቶች ይታያታል፡፡ ፊቷ ያያችው ሰገን እባላለሁ ያለቻት ልጅ መናገር ጀመረች፡፡
‹‹እንግዲህ ስለስራው መጀመር ማለቴ ስለ ስልጠናው ሁኔታ አንዳንድ ቅድመ ዝግጅቶችና የተወሰኑ የሚፈረሙ ውሎች አሉ… ስለዛ እንድንነጋገርና እንደንጨርስ ነው፡፡››
‹‹ግን እኮ››

‹‹ምነው…ችግር አለ?››

‹‹ማለቴ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ደርሼ አይደለም የመጣሁት  …አሁንም  እትዬ ትብለጥን ጠይቄ መረዳት የሚገባኝ ጥያቄዎች ነበሩኝ..››

‹‹ግን የተነገረኝ እንደተስማማሽ ነበር፡፡ትብለጥ ያለችኝ እንደዛ ነበር››

‹‹አዎ እርግጥ ለእሷ ያልኳት እንደዛ ነው…ማለት በአካል ሳገኛት ላስረዳትና ጥያቄዎቼን ላቀርብላት ነበር የፈለኩት...እና የማላስቸግርሽ ከሆነ ከእሷ ታገናኚኛለሽ?››
‹‹አይ አሁን በቅርብ ስሌለች አልችልም››

‹‹ውይ ያሳዝናል. በቃ ንገሪልኝና በተመቻት ቀን ቀጠሮ ትያዝልኝ እመጣለሁ፡፡››

‹‹ይቻላል….እነግራታለሁ..ግን ከስድሰት ወር በኃላ ነው እሷን የምታገኚያት፡፡››

ልቧ ምንጭቅ ብሎ ወደታች ዝቅ  ያለ  መሰላት…ወይንም  የሆነ  ነገር  ከቤቱ ኮሪኒስ ላይ ተላቆ ጭንቅላቷ ላይ የወደቀ አይነት ስሜት ነው የተሰማት
‹ስድስት ወር….?››

‹‹አዎ..ዛሬ ወደ አሜሪካ በራለች…አሁን ያለሽ ምርጫ ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄዎችሽን ለእኔ አቅርበሽ ስለስራው በመረዳት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተሸ ወደስራ መግባት ወይም ሁለተኛው ምርጫሽ ይቅርብኝ ብለሽ ወደ ተለመደው ኑሮሽ መመለስ…››
‹‹በቃ?››

‹‹አዎ..አየሽ አንቺ የተፈለግሺበት ዋናው  ምክንያት  የእኔን  ቦታ  ለመተካት ነው፡፡››
አሁን ተነቃቃች…ቢያንስ ስራውን በጥልቀት የሚያውቀው ሰው  ነው ከፊት ለፊቷ ያለው
‹‹ያንቺን…?አንቺ ልታቆሚ ነው፡?፡››
‹‹አይ በፍፁም… እንደነገርኩሽ እሷ አሜሪካ ለሚቀጥሉት ስድስት  ወራት ስለምትቆይ የእሷን ቦታ ለመተካት ነው….ማለት ድርጅቱን  ለማስተዳደር..የእሷ ነገር ሆኖብኝ እንጂ እኔስ አዛው ስራዬን ብሰራ ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹እኔም ስራውን እፈልገዋለሁ እኮ…ግን ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች በውስጤ እየተጉላሉ እየረበሹኝ ስለሆነ ነው፡፡››
‹‹እሺ ትብለጥ…አንቺን በተመለከተ አደራ ስላለቺኝ ስለስራው  ከእኔ ታሪክ አንስቼ ላስረዳሽ››
‹‹በፈጠረሽ…ደስ ይለኛል፡፡››

‹‹የዛሬ ስድስት አመት ነው፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2ተኛአመት የማኔጅመንት ተማሪ ነበርኩ፡፡እናቴ በድንገት ታማ ከክፍለ ሀገር አጎቶቼ አመጧትና ሚኒሊክ አስተኞት...ያው አባቴ በልጅነቴ ነበር የሞተብኝ..አጎቶቼ ሲመጡ ለቀናት  ቢበዛ ለአንድ ሳምንት ህክምና ብለው ነበር…ግን በሽታዋ  እንዲህ  በቀላሉ  የሚድን አይነት አልነበረም….ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ሁሉም ተራ በተራ ወደ ሀገራቸው

ተመለሱ፤ምክንያቱም ሁሉም የየራሳቸው ልጆችና ቤተሰቦች ያሏቸው ከእጅ ወደአፍ የሆነ ኑሮ የሚኖሩ ድሆች ስለነበሩ ከዛ በላይ  ለእናቴ  የሚያደርጉላት ምንም ነገር አልነበረም..ሆስፒታል አንድ ወር ከ15 ቀን ተኛች….
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ‹‹ወደ ትምህርትሽ ለመመለስ አልፈልግሺም ነበር….?››መሀከል ገብታ ጥያቄ ጠየቀቻት
ምን ሊያደርግልኝ…ተምሬ ስንት ልቀጠር..ሶስትና አራት ሺ ብር…ምን ላደርግበት.?ነገ ብታመም እንደእናቴ ባዶ ቤት ማቅቄ ልሞት? ነገ ልጅ ብወልድ በድህነት ውስጥ ላሳድገው….?አይ ምንም ሰርቼ ምንም ሀብታም መሆን ብቻ ነው የፈለኩት….ለምሳሌ መስረቅም ቢሆን ፤መሸርሞጥም ቢሆን፤ሀሺሽ ማከፋፈልም ቢሆን… ብቻ ዋናው ጠቀም ያለ ገንዘብ ያስገኝ እንጂ የስራው አይነት ላይ ምንም አይነት ምርጫ እንደማላደርግ ለራሴ ቃል ገባሁ….በአጋጣሚ ያ ያልኩሽ ሰውዬ እቅዴን ስነግረው ከትብለጥ ጋር አስተዋወቀኝና ‹‹እባክሽ እርጂያት››አላት…ተገናኝን..አየቺኝ ልክ አሁን  አንቺን  እንደወደደችሽ ወደደቺኝ..ታዲያ እኔ እንደአንቺ መወዛገብ ውስጥ አልገባሁም እንዴትስ ልገባ እችላለሁ…? እሺ ብላ ተረከበቺኝ፡፡ ወደስልጠና ገባሁ…ስልጠናው ዛሬ እንደምንሰጠው በጣም የተደራጀ አልነበረም…ግን ለአንድ ወር ሰለጠንኩ…ይበልጥ ወደድኩት…እና ይሄው ስድስት አመት እሱኑ እየሰራሁ ነው፡
ስልኳን  ከኪሶ  አወጣችና  ከፈተች፤ከባንክ የተላከላትን የሂሳብ ዝርዝር.ላይ ያለውን ብር አሳየቻት 6,354,450 ይላል
‹‹6 ሚሊዬን ነው የሚለው?››

‹‹አዎ›› አለችና ጋላሪ ውስጥ በመግባት አንድ ፎቶ አወጣች ‹‹ይሄ በቅርብ እያሰራሁት ያለ ጅምር ቤት ነው..ከሶስት ወር  በኃላ  ይጠናቀቃል፤ይህቺኛዋ መኪናዬ.ነች፤ቢያንስ ከአስር የሚበልጡ የዘመዶቼን ልጆች አስተምራለሁ…፡፡
‹‹ይገርማል›› አለች ሳባ

‹‹አዎ ይገርማል…  .እንግዲህ አስከአሁን የነገርኩሽ መግቢያውንና.መደምደሚያውን ብቻ ነው፡፡ማለቴ እንዴት ስራው ውስጥ እንደገባሁና በመግባቴ ያገኘሁትን ውጤት….››

‹‹አዎ ..››

መሀከሉ የህይወትሽን የአስተሳሰብሽን፤ለሰው ልጅ  የምትሰጪውን  አጠቃላይ ትርጉም ሙሉ በሙሉ የሚገለባብጥ ተግባርና ስራ  ነው  የሚያጋጥምሽ…አስር ዲግሪ ብትማሪ የማታገኚውን የህይወት ልምድ ነው የምታገኚው..ሀገር በእነማን አንደምትመራ፤የምናደንቃቸውና.ለአምልኮ በተጠጋ ፍቅር የምንከተላቸው አርቲስቶች እና ዘፋኞች ያላቸው ስብእና..ብር ለሀብታሙና ብር ለደሀው ያለው የትርጉም ልዩነት …ብዙ ብዙ ነገር ትማሪበታለሽ….መማር ብቻ አይደለም…እያንዳንዷን እውቀትም ሆነ እያዳንዷን ገንዘብ ስትቀበይ ለዛ  የምትከፍይው ስቃይና ህመም አለ…አንዱ ደንበኛ እንደ አሻንጉሊት ያይሻል፤ ሌላ ንግስት አድርጎ ያንቆጦቁጥሻል አንዱን ሰውነቱን ከላይ እስከታች ታሺለታለሽ፤ ሌላውን ደግሞ አእምሮውንና የውስጥ የስነልቦና ጥዝጣዜውን ውስጡ ገብተሸ እንድታክሚው ይጠበቅብሻል… አንዱን በወሲብ ስታስደስቺው…ሌላውን ደግሞ ለሊቱን ሙሉ ቁጭ ብለሽ እንድታዳምጪው ብቻ ይፈልግ ይሆናል…፡፡
በዚህ የስራ ባህሪ የማያጋጥምሽ ነገር የለም…እርግጥ ከፍላጎትሽ ያፈነገጠ አካላዊ ጥቃት አያጋጥምሽም፤ ድርጅቱ ለዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ  ያደርጋል…እዚህ የሚመጡት ደንበኞቻችን ለስማቸው አብዝተው ስለሚጨነቁ በዛ ብዙም አያስቸግሩም፡፡ በተረፈ ግን  ዋና ታርጌትሽ በመጪዎቹ  አምስትና ስድስት አመታት ለእድሜ ልክሽ የሚበቃሽን ብር ለማግኘት ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ቁርጠኛ ነሽ ወይ…ነው..ለዛ አዎ ቁርጠኛ ነኝ… ከሆነ መልስሽ ያንን እንድታደርጊ የሚያግዝሽ በቂ ስልጠናና ዝግጅት እንዲኖርሽ ወደስልጠና ትገቢያለሽ…አይ እኔ የገንዘብም ችግር የለብኝም.. ቤተሰቦቼ ደህና የሚባል አቅም አላቸው እኔም እየሰራሁት ያለሁት ስራ በቂ ነው የምትይ  ከሆነ  ግን  ልገፋፋሽ አልፈልግም ቢቀርብሽ ይሻላል››
የተወሰነ ደቂቃ ዝም አለች…ሰገንም በዝምታ የማሰላሰያ ሰዓቱን ፈቀደችላት
‹‹ችግሯን አሰበች…ቤተሰቦቿ ያሉበትን ሁኔታ አሰበች…ሁለት እግሮቹን  አጥቶ ቤቱ የቀረውን ተወዳጅ አባቷን አሰበች፤የብቸኛ ታናሽ ወንድሟን የወደፊት ህይወቱን አሰበች በወቅቱ በኩርፊያ የተለያየችውን ፍቅረኛዋን አሰበች.. ሰገን ያሳየቻትን በስድስት አመት ውስጥ ሰርቼ አገኘሁት ያለችውን ብር መጠን አሰላች.እያሰራች ያለውን ቤትና የምትነዳውን መኪና አሰበች…በመጎምዠት በአፏ ምራቅ ሞላ ‹‹አይ እሞክረዋለሁ››አለቻት፡፡
‹‹እሞክረዋለሁአይሰራም..አደርገዋለሁ.ወይም ይቅርብኝ..መልስሽ ከሁለት. አንዱ ነው መሆን ያለበት››
‹‹አደርገዋለሁ፡፡››
እጇን ዘረጋችላትና ‹እንኳን ደስ አለሽ… የቤተሰባችን አባል ለመሆን ስለወሰንሽ ደስ ብሎኛል...ከእኔ በተሻለ ብልህ ሆነሽ ስኬታማ እንደምትሆኚ አምናለሁ›በማለት ጨበጠቻትና ፊት ለፊቷ ያለውን ወረቀት አነሳችና ከመካከሉ ሁለት ፎርም በማንሳት ከእስኪርፕቶ ጋር አውጥታ እየሰጠቻት አንብቢውና ፈርሚበት..ያው በእኛ መካከል ዋናው የወረቀት ውል ሳይሆን የደም ውል ነው...አንዴ ቤተሰብ ሆነሽ ወደውስጥ ከገባሽ በህይወት ጭምር እንታመንሻለን ፤በህይወትሽ ጭምር ትታመኚናለሽ ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም እስክትጨርሺ መጣሁ ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደውስጥ ገባች…ሳባም ማንበብ ጀመረች…
አሰሪውና ሰራተኛውን ማክበር የሚገባቸውን ኃላፊነትና ያላቸውን መብት የሚደነግግ ነው፡፡
ለምሳሌ፡
ሰራተኛው..በስራ ሂዳት የሚያጋጥሙትን ሰዎች ማንነት  ሆነ  ከእነሱ  ጋር ያሳለፈውን ማንኛውንም ምስጢራዊም ሆኑ ቀላል ነገሮችን ከማንም ጋር አንስቶ ማውራትም ሆነ መወያየት በጥብቅ የተከለከለ ነው፤ከቤተሰብ  ከእናት  ጋር ቢሆንም፡፡ ይሄንን መተላለፍ ሚስጥሩ እንደሚያስከትለው ጉዳት መጠን    መረር ያለ ቅጣት ያስከትላል፡፡
ህመም ወይም የታወቀ ከባድ ችግር ካልገጠመ በስተቀር ደንበኛ በቀጠሮ በተገኘበት ጊዜ ከስራ ቦታ ላይ አለመገኘትም ሆነ ማርፈድ ፈፅሞ የማይፈቀድና ይቅርታ የማያሰጥ ስህተት ነው፡፡
ከደንበኞች የሚሰጥ ማንኛውንም የብር ስጦታ፤የጌጣጌጥ ስጦታ፤ከዛም ከፍ ያለ እስከ ቤት ስጦታ ድረስ ቢሰጥ ሙሉ በሙሉ የሰራተኛው የግል ሀብት ነው፡፡
ድርጅቱ ሰራተኞቹ በደንበኞች አካላዊ ጥቃት ድብደባም ሆነ መሰል ጥቃት ቢደርስባቸው ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ እስከ ውጭ ሀገር በመላክ ሙሉ ህክምና እንዲያገኙ የማድረግ ጥቃት አድራሹ ደንበኛ ጋር በህግም ሆነ በሌሎች ዘዴዎች በመጠቀም በቂ ካሳ እንዲያገኙ የማስደረግ ኃላፊት ይወስዳል፡፡ቅድሚያ ግን አንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ ደንበኞች መረጣ ላይም ሆነ በሂደት ክትትል ያደርጋል…የራሱን ዘዴ በመጠቀም በስውርና በግልጽ ደህንነታቸውን ይከታተላል፤ ይጠብቃል፤ከስራ ሰዓት ውጭ የፈለጉበት ቦታ መሄድ፤ቤተሰቦቻቸውን የመጠየቅ ከጓደኞቻቸው ጋር መዝናናት ሙሉ መብት ያላቸው   ቢሆንም  ለደህንነታቸው ሲባል እንቅስቃሴያቸውን በተለያዩ ዘዴዎች ክትትል ይደረግባቸዋል፡፡ የስራቸው ፀባይ ከሀገሪቱ ትላልቅ ሰዎች ጋር   ስለሚያገናኛቸው በተቻለ መጠን የሚሄዱበቸው ቦታዎች የተመረጡ የሚያገኟቸው ሰዎች ወደአደጋ የማያስገቡ መሆን እንዳለባቸውም የሚያብራራ አንቀጽ አለበት.በአጠቃላይ እነዚህንና መሰል መመሪያዎች ነው ያሉት

‹‹አንዴ ገብቼበታለሁ የራሱ ጉዳይ፤ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም›› አለችና እስኪሪፕቶውን አነሳችና ሁለቱም ወረቀት ላይ ፈርማ በእፎይታ ከመቀመጫዋ ተነስታ ስትንጠራራ ሰገን ከሄደችበት በፈገግታ መጣች፡፡ የፈረመችውን ወረቀት ከጠረጴዛ ላይ በማንሳት አንዴ በስሱ አየችና ወደቦታው መልሳ በማስቀመጥ ቦርሳዋን አነሳችና ከፈተች….አንድ በካኪ የተጠቀለለ ነገር አነሳችና እጆ ላይ አስቀመጠች
ሳባ‹‹ምንድነው?›› ጠየቀቻት
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዛሬ ላይ

ሳባ  ሊቱን  ሙሉ  በትዝታ  ከወዲህ  ወዲያ  ስትዋዥቅ  ነው  ያደረችው…ለሰከንድ እንኳን እንቅልፍ በአይኗ አልዞረም…አሁን የትዝታ ጉዞዋን መሀከል ላይ ሳትቆጭ
ያቆመችው ታናሽ ወንድሟ ራጂ የተኛችበት ክፍል ደረስ መጥቶ በእናቱና በእሷ መካከል ሰርስሮ መሀከላቸው ሲገባ ነው፡፡

‹‹አንተ ጓረምሳ ሴቶች ክፍል ምን ትሰራለህ?››

‹‹እህቴ ናፍቃኝ ነዋ››

‹‹ወደራሷ ልጥፍ አድርጋ በማቀፍ  ግንበሩን ሳመችው፡፡››

‹‹እህቴ ዛሬም ታድሪያለሽ አይደል?›

‹‹ማደር አላድርም …ግን አሁን እንነሳና ከተማህን ዞር ዞር አድርገህ አሳየኝ..ከዛ ትንሽ ዘና ብለን ከሰአት በኃላ እሄዳለሁ፡፡››
ስንዱ(እማሆይ  አፀደ)  ከአልጋዋ  እየወረደች‹‹  ምነው  ዛሬ  አድረሽ  ነገ  በጥዋቱ     -ብትሄጂ አይሻልም?››ስትል ሀሳብ አቀረበችላት፡፡
‹‹አይ..  ቢያንስ  ነገ  በጥዋት  ሀኪሜ  ጋር  ተመልሼ  በመሄድ  ስላቋረጥኩት  -መድሀኒት ነገሬው የሚለኝን መስማት አለብኝ፡፡››

‹‹በቃ እንደዛ ከሆነ ተነሱ እስከዛ እኔ ቁርስ ልስራ፡፡››

‹‹አይ አንቺም ተነሺና አብረን ውጭ ነው ቁርስ ምንበላው፡፡››

‹‹ባይሆን እናንተው ሂዱና  ስትመለሱ  ከእኔ  ጋር  ሆነን  የሆነ  ቦታ እንሄዳለን፡፡ ማለቴ ብዙም ጊዜ የሚፈጅ አይደለም፡፡እዚሁ ቅርብ ነው፡፡15 ደቂቃ ቢወስድብን ነው፡፡››

‹‹ሳባም …እሺ በቃ›› ብላ ለባብሳ ከወንድሟ ጋር ተያይዘው ከግቢ ወጡ፡፡ቀጥታ የሄዱት ሻለቃ ደራርቱ  ቱሉ  ሆቴል  ነው፡፡  እዛ  እየተዝናኑና  ቁርስ  እየበሉ እተጫወቱ   አራት ሰዓት  ሆነ ፡፡ ከዛ ወጡና ወደስጦታ መሸጫ ሱቅ እየሄዱ ሳለ ስልኳ ጠራ፡፡አየችው ..በጣም የምትፈልገው ስልክ ነው፡፡አነሳችው፡
‹‹እሺ ደራሲ ጳውሎስ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁ.. ሰላም ነኝ››
‹‹እሺ እንዴት እየሆነልህ ነው…?›
‹‹ጨርሼለሁ..ዛሬ ወደአዲስአባ ልንመጣ ነው…ከመነሳቴ በፊት ልደውልልሽ ብዬ ነው፡፡››
‹‹በእውነት  በጣም  አስደሳች  ዜና  ነው  የነገርከኝ…በቃ  እኔም  አሁን  አሰላ ነኝ…ከሰአት እነሳለሁ..ነገ እንገናኛለን፡፡››
‹‹እሺ በቃ ቸው››
‹‹ደግሞ የጉዞውም ነገር መስመር ይዞል..በአስራአምስት ቀን ውስጥ የሚጠናቀቅ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ደስ ይላል፡፡በቃ ነገ አንገናኝ፡፡››ብሏት   ስልኩን   ዘጋው፡፡እሷም   ስልኳን   ወደኪሷ መልሳ በደስታ ፈጋ ወንድሟን እንዳቀፈች ወደ ሱቅ ገባች፡፡ ትኩስ አበባ ከገዙ በኃላ ቀጥታ ወደቤተክርስትያን ነው ተያያዘው የሄዱት፡፡ ሁለቱም አባታቸው መቃብር ላይ የያዙትን አበባ አስቀመጡና ሀውልቱ ስር ጎን ለጎን ቁጭ አሉ፡፡ ሁለቱም በዝምታ ተሸብበው በየራሳቸው ትዝታ መዳከር ጀመሩ፡፡ሳባ ትዝ ይላታል፡፡የዛሬ ሰባት አመት በፊት የአባቷ አሟሟት፡፡ 
አዎ   ሙሉ   በሙሉ በእሷ ጣጣ እንደሞተ ነው የምታምነው፡፡በዛ ምክንያት ደግሞ በቀል በውስጧ በቅሎ ሰው እስከመግደል ደርሳለች፡፡እርግጥ ቀጥታ የሽጉጥ ቃታ ስባ…ወይም ጩቤ በሰው ልብ ሰክታ አልነበረም ግድያውን የፈፀመችው፡፡ግን የአባቴ ዋነኛ ገዳይ ነች የምትላትን ሴት ያላትን ሁሉ አንድ በአንድ እንድታጣ አድርጋ ባዶዋን በማስቀረት በራሷ እጅ አንገቷን ገመድ ውስጥ አስገብታ ከዚህች አለም ህይወት እራሷን እንድትገላግል አድርጋለች፡፡አሁን ሌላ አንድ ትቀራታለች….ለእሷም የመጨረሻውን ቦንብ አጥምዳ ወደማጠናቀቁ ላይ ነች…ከዛ የሴትዬዋ እግሮች ቦንቦቹን ረግጠው ሲነሱ ሁሉ ነገሯ ቡም ብሎ ይበታተናል... ያ ወጥመድ….ደራሲ ጳውሎስ ፅፎ ያጠናቀቀው መፅፈህ ነው፡፡ያ መፅሀፍ ቦንብ ሆኖ ቀሪዋንና ኃያሏን ሴት ያስወግዳታል..‹‹አባዬ አይዞህ ..አንድ በአንድ እበቀላቸዋለሁ››አለች ሳባ፡፡
‹‹ምን አልሽ እህቴ …?አናገርሺኝ?››አላት ታናሽ ወንድሟ፡፡
‹‹አይ…. ከአባዬ  ጋር  እያወራሁ  ነበር፡፡››አለች  ደንግጣ፡፡ ራጂም ‹‹እህቴ …አባዬ እኮ በጣም ነው የሚናፍቀኝ፡፡›› አላት፡፡
‹‹እኔም በጣም ነው የሚናፍቀኝ…..በየጊዜው እናንተ ጋር የማልደውለው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ ?እንተን ሳወራ አባዬ ትዝ ስለሚለኝና እሱ ትዝ ሲለኝ ደግሞ ሀዘን ውስጤን ስለሚሸረካክተው ነው፡፡አባዬ በጣም ጀግናና ስማርት የሆነ አባት ነበር… ሲሞት አንተ ልጅ ስለነበርክ በደንብ ልብ ላትለው ትችችለህ…በተለይ ከአደጋው በፊት ሮጦ ልረፍ የማይል፤ ሰርቶ ደከማኝ የማያውቅ፤ ለቤቱ  ድንቅ አባወራ ለእኔና ለአንተ ድንቅ አባት ፤ለሰፈርና በቄሄው የተከበረ ልዩ ሰው ነበር…አባዬን ሳስብ ሁል ጊዜ ከአደጋው በፊት ስለነበረው ሁኔታ ነው ማሰብ የምፈልገው…››
‹‹እህቴ እኔ አንቺ ከምታስቢው በላይ አባዬን  አውቀዋለሁ.እርግጥ አምስት  አመቴ ላይ ነው የሞተው…ቢሆንም አምስት አመት  ሙሉ እኔን ከማሳደግ ውጭ ሌላ ስራም ሆነ ፍላጎት እልነበረውም…እማዬ  እናቴ  መሆኗን  በትክክል  ያወቅኩት እንኳን   እሱን   በሞት   ካጣሁ   በኃላ   ነው፡፡ከዛ   በፊት   ምተኛው   ከእሱ   ጋር
፤የሚያጥበኝ እሱ፤ ምግብ እራሱ የሚያጎርሰኝ እሱ ነበር..እስኪሞት ድረስ በእጆቼ ምግብ ቆርሼ መጉረስ አልችልም ነበር ፡፡እሰከዛ ድረስ በእሱ እጅ ካልሆነ ምግብ ወደአፌ አይገባም ነበር…በየቀኑ የሚነግረኝ ተረቶች የሚያነብልኝ መፅሀፎች ትዝታው  ዛሬ  የተከወነ  ያህል  ነው የማስታውሰው    ፡፡አንድ አይነት ተረት በቀን
ለ10 ጊዜ ደጋግመህ ንገረኘኝ ስለው አይሰለችም…በደስታ ያደርገዋል፡የአባዬ ጣፋጭ ድምፅ ዛሬም በጆሮቼ ውስጥ ሲንቆረቆር ማደመጥ እችላለሁ፡››
በታናሽ ወንድሟ ልብ የሚነካ ንግግር እንባዋ በጉንጮቾ ተንኳለለ፡፡
ወንድሟ ቀጠለ‹‹…እህቴ የዛን ያህል እያስታወስኩት በዛ መጠን እየናፈቀኝ እንኳን ለምን አንዳማላማርር ታውቂያለሽ?››
መልሱን ለመስማት ተነቃቃች‹‹ለምንድን ነው?››
‹‹አንቺ ስላለሺኝ ነዋ…አንቺ እኮ ልክ እንደአባቴ ነሽ..አይደለም አሁን ላለሁበት ለወደፊት ህይወቴ እንኳን ትጨነቂያለሽ…ጀግና እህት ስላለኝ በአንቺ እፅናናለሁ..አባዬ ሲናፍቀኝ እዚህ እመጣና አንቺ ለእኔ  እና  ለእናቴ  ምታድርጊልን ነገር ሁሉ እነግረዋለሁ…ከዛ ደስ ሲለው አይቼ ወደቤቴ እምለሳለሁ.፡››
ከተቀመጠችበት ተንደርድራ ሄዳ አቀፈችው …ጭምቅ አድርጋ አቀፈችው.. እያገላበጠች ሳመችው…እሱ በእሷ ላይ ያለውን መመካት እሩብን   ያህል   እሷ በራሷ ላይ ኖሯት ቢሆን እጅግ ደስ ይላት ነበር፡፡ግን እሷ በውስጧ ትንሽነት ነው የነገሰው.. ፤ባዶነት ነው ልቧን የሞላው ፤ስጋት ነው እየናጣት   ያለው፤ተስፋ መቁረጥ ነው ዙሪያዋን የከበባት፣
እህትና ወንድም ተመልሰው  እቤት  ሲደርሱ  ስድስት  ሰዓት  አልፎ  ነበር… እናትየው ምርጥ  የተባለ  ምሳ  ሰርታ  ቡና  አፍልታ  ፤እቤቱን  አሟሙቃና አጫጭሳ ነበር የጠበቀቻቸው…የተዘጋጀውን ምግብ ከበሉና ከቡናውም አቦሉን ከጠጡ በኃላ ስንዱና ሳባ በተራቸው ተያይዘው ወጡ..
‹‹ስንድ የት እንደምትወስጂኝ ለማወቅ ጓጉቼያለሁ?››
‹‹ትንሽ ታገሽ ደግሞ አስደሳች ቦታ የምወስድሽ እንዳይመስልሽ››
‹‹እናስ..?››
‹‹ያው አስፈላጊ ቦታ ነው…. በተለይ ለእኔ?››
‹ለነገሩ ዝም ብዬ ነው የጠየቅኩሽ…መቼስ መዝናኛ ቦታ ይዘሽኝ ትሄጃለሽ ብዬ አላስብም…›
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሳባ የአሰላን ከተማ ለቃ እንደወጣች በደመነፍስ ነበር ስትነዳ የነበረው፡፡ ሀሳቧ ሁሉ ወደኃላ ተመልሷል..ያንን የተረገመ ስራ እንዴት እንደ ጀመረች አስር  አመት ወደኃላ ተመልሳ ማብላላት ጀመረች፡፡
ከ10 ዓመት በፊት
ያኔ በዛ ዘመን አዲሱን ስራዋን ለመጀመር ከሰገን  ጋር የመጨረሻ ድርድር ስታደርግ እና ሲለያዩ አንድ ምክር ሰጥታት ነበር…‹‹ድንግል ከሆንሽ ለምትወጂው ሰው ስጪው፡፡››ነበር ያለቻት…ግን በፍጥነት ማድረግ አልቻለችም ነበር…በወቅቱ የምትወደው ሰው ልቧን ሰብሮ ካሳዘናት ሰነባብቷል….‹‹ለእሱ ድንግልና ሳይሆን ከተቻለ በቀል ነው የሚገባው››ስትል  በማሰብ….ስለድንግልናዋ ማሰብና መጨነቅ ትታ…ዕቃዋን በየካርቶኑ እያስገበባች አሸገች፤ልብሶቿን በሁለት ሻንጣ ጠቅጥቃ አሳሰረች…የምትተኛበት ፍራሽ ብቻ እንደተዘረጋ ቀረ…ቀጥሎ ምን እንደምታደርግ ግራ ገባት፡፡መቼስ ይሄን ሁሉ ኮተት ይዛ በህዝብ ትራንስፖርት ተጠቅማ አሰላ ድረስ ማጓጓዝ አትችልም...እንዴት አድርጋ…‹‹ደግሞ ስኖርበት ባዶ የነበረው ቤት  አሁን ልለቅ ስል እንዴት ነው እንዲህ ሜዳውን የሞላው?››ሥትል በማሰብ ተገረመች፡፡‹‹ግን አሁን ይሄንን ሁሉ ኮተት ብረት ድስት፤ሰሀን፤ብርጭቆ ምድጃ ለምንድነው የሰበሰብኩት? ለምን ለተቸገረ አላከፋፍለውም?››ራሷን በትዝብት ጠየቀች፡፡
  ግን ደፍራ ነገ ሀብታምና  ሁሉ  ነገር  የተረፈው  እንደምትሆን  ተማምና ‹‹አይ ይሄን ኮልኮሌ አልፈልግም ላከፋፍለው››ልትል አልቻለችም…
ወሰነች.‹‹አዎ ብር አለኝ… አሰላ ድረስ የሚወስድልኝ መኪና ብፈልግ ይሻላል››ስትል አሰበች…‹‹አዎ መርካቶ ብሄድ ጭነት መኪና አላጣም….ጭነው ሲጨርሱ በዚሁ ጎራ ቢሉ ከላይ ጣል ጣል አድርገው ይወስዱልኛል….››ብላ ስሌት ሰራችና ወደመርካቶ ለመሄድ ካሰበች በኃላ ሌላ የተሻለ ያለችው ሀሳብ ብልጭ አለላት፡
ደምሳሽ ትዝ ኣላት….እርግጥ በወቅቱ ለዚህ የሚያበቃ ትውውቅም ሆነ ንግግር.አልነበራቸውም...ቢሆንም.ያው‹‹ቤተሰብ ሆነናል››ብሏት የለ. ብትጠይቀው ምንም ክፋት እንደሌለው አሰላች…ሸፌር ስለሆነ ሌሎች ሹፌሮችን ስለሚያውቅ ወደአሰላ የሚሄድ የጭነት መኪና ብዙም ሳይለፋ በስልክ ሊጨርስላት ይችላል…ስልኳን አወጣችና ደወለችለት..ከሶስት ጥሪ በኋላ ተነሳ..
‹‹ጤና ይስጥልኝ የእኔ እመቤት››

‹‹አቶ ደምሳሽ ሳባ ነኝ .አወቅከኝ?በቀደም…››

‹‹እመቤቴ አውቄሻለሁ..ማብራራት አይጠበቅብሽም…አንቺን እንዴት ልዘነጋ እችላለሁ፡፡ለዛውም ቤተሰብ ሆነን?››ነበር ያላት…
‹‹በእውነት ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ነው ያደረከው››አለችው ከምሯ፡፡
‹‹አረ ምንም የተለየ ነገር አልተናገርኩም…ለማንኛውም ምን ልታዘዝ?››

‹‹እየፈራሁ  ነው  የደወልኩት..ሌላ  ላስቸግረው  የምችል  ሰው  ስለሌለ  ነው እባክህ ከድፍረት አትቁጠርብኝ››

‹‹በነገራችን ላይ  አልተነገረሽም መሰለኝ?››

‹‹ምኑን?››

‹‹ከዛሬ ጀምሬ በማንኛውም ነገር አንቺን እንድጠብቅ፤እንድታዘዝና የምትፈልጊውን ነገር ሁሉ እንዳሟላልሽ ታዝዣለሁ…ስለዚህ እኔን  ማዘዙን ከዛሬው ተለማመጂው…ለአንቺ መታዘዝ ስራዬ ነው›› አላት፡፡
‹‹ማዘዙን?››

‹‹አዎ ማዘዙን››

‹‹አይ እንዳልጠየቅህ አደረከኝ…በቃ ይቅርብኝ ሌላ አማራጭ እፈልጋለሁ፡፡››

‹‹አረ ተይ ቀለል አድርጊውና የምትፈልጊውን ንገሪኝ..ካለበለዚያ አሁኑኑ ሰፈርሸ እመጣለሁ››አላት
‹‹ኸረ ተው…እሺ ያው ሹፌር  ስለሆንክ ሹፌሮችን ታውቃለህ ብዬ ነው››

‹‹አዎ በደንብ አውቃለሁ…ምን ፈለግሽ?››

‹‹የፈለኩትማ ያው ሰሞኑን ስልጠና ጠቅልዬ ስለምገባ የምኖርበትን ቤት ለቅቄያለሁ….ቤተሰቦቼ ያሉት አሰላ ነው…እቃዎቼን ወደእዛ ለመውሰድ  ፈልጌ ነበር…እና ወደዛ የሚሄድ የጭነት መኪና ፈልጌ ነበር..እንዴት እንደማገኝ  ግራ ገብቶኝ ነው››
‹‹ወይ ለዚህች ነው እንዴ..?ለመቼ ነው..?››

‹‹ከተቻለማ ለዛሬ ነው…ካልሆነም ለነገ ጠዋት…››

‹‹ስልኬን ጠብቂ…መልሼ እደውላለሁ፡፡››

‹‹በእውነት ከልቤ ነው የማመሰግነው››

‹‹በይ ቻው በቤተሰቦች መካከል መመሰጋገን የለም ››ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡

ከ8  ደቂቃ  በኃላ  ነበር  ስልኳ  መልሶ  የጠራው…ስታየው  ደምሳሽ  ነው..በዚህ ፍጥነት አልጠበቀችም.
አነሳችውና ‹‹ሄሎ አገኘህልኝ?››አለችው፡፡

አዎ እቃሽ ብዙ ነው እንዴ ?ማለት ፒካፕ መኪና አይችለውም..?››

‹‹አረ በደንብ ነው ሚችለው››

‹‹እንግዲያው አሁን 5 ሰዓት ሆኗል 7 ሰዓት ሰፈር ደርሶ ይደውልልሻል..እስከዛ የቀረሽ ነገር ካለ  አስተካክይ››
በደስታ ስልኩን ዘጋችና የመጨረሻውን ዝግጅት ማድረግ ጀመረች፡


ለ7 ሩብ ጉዳይ ደወለላት...ፈጥና አነሳችው

‹‹ሄሎ ደምሳሽ...እንዴት ሆነልህ?››

‹‹ያው ግሎባል ጋር ሰማያዊ ደብል ፒካኘ ቲዬታ መኪና ይዞ እየጠበቀሽ ነው።››ስልኳን እያወራች ቤቱን ለቃ ወጣች‹‹እንዴት እንደማመሰግንህ አላውቅም"
"ችግር የለውም… ስትመጪ ምሳ ትጋብዢኛለሽ"
‹‹አረ  ችግር  የለውም...ግን  ክፍያውን  እንዴት  ነው  የማደርገው  ማለቴ
ነግሮሀል?"

‹‹ዋጋው ችግር የለውም...ወላጆችሽ ምሳና ቡና ከጋበዙት ይበቃዋል››
‹‹እውነቴን እኮ ነው...ትቀልድብኛለህ አይደል?››
በዚህ ጊዜ ግሎባል ጋር ደርሳ ነበር ...በምልክት የነገራትን ፒካፕ ወዲያው አየቻት...ለሹፌሩ ወደእሷ እንዲመጣ በእጇ ምልክት ጠራችውና መኪናዋን ማንቀሳቀሱን ካየች በኃላ ፊቷን አዙራ ወደቤቷ ተንቀሳቀሰች፡፡
‹‹ሰውዬውን አግኝቼዋለሁ" ‹‹እ..ታዲያ አናገርሽው?"  ‹‹አይ አላናገርኩትም"
"ታዲያ ልደውልለትና ልጠይቅልሽ ወይስ አንቺው እዛው ትከራከሪዋለሽ?"
‹‹አይ አመሰግንሀለሁ...ከዚህ በላይማ ላስቸግርህ አልፈልግም...በቃ ቻው።››
‹‹ቻው በቃ ሚቸግርሽ ነገር ካለ ደውይ››
እሷ የቤቷ በራፍ ጋር ስትደርስ ፒካፗ አጠገቧ  ደርሳ  በስሱ  ክላክስ  ሲያደርግላት ስልኩን ፈጠን ብላ ዘጋችና ወደግቢ ገብታ የመኪና መግቢያ በራፍ ከፈተች… መኪናዋ ወደውስጥ ዘልቃ ገባችና የግቢው መሀል አካባቢ ቆማ ከገቢናዋ  ሹፌሩ ዱብ ብሎ ወረደ...በድንጋጤ እጇን አፏ ላይ ከደነች።
‹‹ምነው አስደነገጥኩሽ እንዴ?››
"እዚህ ሆነህ ነው እንዴ የምታስለፈልፈኝ...?ባለመኪናው የት አለ?"
‹‹መኪናው የድርጅቱ ነው...ሹፌሩም ደግሞ እኔ ነኝ.."
‹‹ኸረ  ደምሳሽ  እንዲህ እኮ   መቸገር  አልነበረብህም።አሰላ  ድረስ  እኮ  ነው።

"ይሄ የእኔ ሀሳብ አይደለም..ታዝዤ ነው...መኪና እየፈለግሽ እንደሆነ ለሠገን ስነግራት...ራስህ አድርስላት ብላ አዘዘቺኝ...ይልቅ አሁን ሰዓቱ እየነጎደ ስለሆነ እቃሺን ቶሎ ጫን ጫን አድርገን እንውጣ›› አላት። እየከበዳት እቃዋን ወደ ተቆለለበት ክፍል ይዛው ገባች..እቃውን ጭነው ከግቢው ለመውጣት 20 ደቂቃ ብቻ ነበር የወሰደባቸው።
///
11 ሰዓት ላይ ቤት ደረሱ እቃው እስኪወርድ፤ መክሰስ በልተው የተፈላውን ቡና ጠጥተው እስኪያጠናቅቁ ለአንድ ሰአት ሩብ ጉዳይ ሆነ...ሳባ    ከቤተሰቦቿ ጋር ስትጫወት አድራ በማግስቱ ረፈድፈድ ሲል ነበር መመለስ   የፈለገችው። ያንን ዕቅድ ያወጣችው ሹፌሩ ደምሳሽ መሆኑን ከማወቋ በፊት ነበር። በኋላ ግን ለእሷ ብሎ አሰላ ድረስ መጥቶ እንዴት ብቻውን እንዲመለስ ትተወው?ያ ነው የጨነቃት፡፡ እርግጥ እርሱም በእንግድነት እነሱ ቤት እንዲያድርና ጥዋት አብረው እንዲመለሡ ጠይቃው ነበር። እሱ በማግስቱ 12 ሰዓት አዲስ አበባ ላይ የሚሰራው ስራ ስላለ እንደማይችል ስለነገራት አብራው ለመመለስ ወሰነች። ሁሉን
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁለት  ተኩል  ላይ  ወሎ  ሰፈር  የያዘላት  ሆቴል ጋር  ደረሱ፤ክፍልአስገባት።
‹‹ሌላ የምትፈልጊው  ነገር አለ ?›
"ኧረ ቤተ- መንግስት ነው የተከራየህልኝ...ካልደበረህ ሆቴል የሆነ ነገር እየተጠቀምክ ትጠብቀኛለህ...ምቾት እየተሠማኝ ስላልሆነ ሻወር ለመውሰድ 10 ደቂቃ ይበቃኛል።
‹‹እንዴ አመረርሽ እንዴ…?እኔ እኮ ደህና እደሪ ብዬሽ ወደቤት ልሄድ ነበረ"
‹‹ምነው ቤት ይጠብቁሀል እንዴ?"
"አዎ አጥሩን ስከፍት እያንቧረቀ የሚቀበለኝ አንድ ውሻ አለኝ" "በቃ?"
"አዎ...በቃ...ለማንኛውም ታች እንገናኝ።" ብሏት ወጥቶ በሩን ዘጋና ሄደ፡፡ እሷም እየቀነቀነ ያስቸገረትን ሰውነቷን ለመታጠብ ወደ ሻወር አመራች። ሰውነቷን ታጥባ ጨርሳ በሻንጣዋ ከያዘችው ቅያሪ ቀሚስ ምርጥ ያለችውን ቀሚስ ለብሳ የብር ቦርሳዋን ይዛ ክፍሏን ቆለፈችና ወደታች ወደ ሆቴሉ ወረደች፡፡
ምግብ አዳራሹ ውስጥ ገብታ ዞር ዞር እያለች ብትፈልገው ልታገኘው አልቻለችም።ወደ ባሩ ስትገባ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጦ መጠጡን ይልፋል፡፡ እንዳየችው ፈራ ተባ እያለች ወደ እሱ ቀረበች።መምጣቷን ሲያይ ከመቀመጫው ላይ ተንሸራቶ በመውረድ ተቀበላት።

‹‹ቆየሁብህ እንዴ?›

"አይ እንደውም ፈጠንሽ...ነይ መጀመሪያ እራት እንብላ"

ተከተለችው...፡፡ ሲገቡ አስተናጋጇ ወደተያዘላቸው ወንበር እየመራች ወሰደችና አሰቀመጠቻቸው። ሜኑ መጣና አዘዙ ፡፡ቆንጆ እራት በሉ፡፡ሂሳብ ለመክፈል እሷ ወደቦርሳዋ እጇን ከመስዳዷ በፊት እሱ ቀድሞ ዘጋ"የከፈለውን  ብር  ገርመም አድርጋ ስታየው ተገረመች..
‹‹ይሄ ሰውዬ  እውነት  ሹፌር  ብቻ  ነው?››ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡  መልስ ሳታገኝ ወደባር ይዟት ገባ ።ሁለቱም የየምርጫቸውን አዘው አየተጎነጩና በጫወታ እያዋዙ ጊዜውን መግፋት ጀመሩ።ሳባ በማታውቀው ምክንያት ደስ እያለት መጣ ...ሞቅ እያላት ሲመጣ እያቅበጠበጣት መጣ..በቀደም ሰገን ስትሸኛት የተናገረቻት የመጨረሻ ምከር ከምናቧ ሊጠፋ አልቻለም። እንደዛ ብታደርጊ ይሻላል ...እዚህ አንፈልገውም"አዎ ቃል በቃል ባይሆንም እንደዛ ነበር ያለቻት፡፡ እናም ምክሩን ተቀብላ በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ውስጥ ለወራት ከተኳረፈችው ፍቅረኛዋ በመታረቅ ምክሯን ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ነበራት። ግን አሁን አላስቻላትም።በዛን ሰዓት ከኮተቤ ተነስቶ ወሎሰፈር መምጣት እንደማይችል ብታውቅም ቢያንስ ድምፁን ለመስማት ፈለገች...ለወራት ሲደውልላትና ይቅር እንድትለው በአማላጅ ጭምር ሲማፀናት ነበር..ተስፋ ቆርጦ ግንኙነታቸውን ሁሉ እርግፍ አድርገው  ያቆሙ ከመሰሉ ወር ደፍኖ ነበር "መቼስ አሁን ስደውልለት በርሬ ካልመጣሁ ብሎ ያስቸግረኛል" ስትል ተስፋ አደረገች፡፡
  "ጨክኖ ካልመጣሁ ካለ መቼስ ምን አደርጋለሁ...ለማንኛውም  ልደውልለት" በማለት ወሰነችና"ቶይሌት ደርሼ ልምጣ?"ብላ ለደምሳሽ በመናገር ከተቀመጠችበት ተነሳች።
"ድረሺና ነይ..ሰዓት እየሄደ ስለሆነ ስትመጪ ወደክፍልሽ አድርሼሽ እሄዳለሁ"አላት።
    እሷም ከቦርሳዋ ገንዘብ ዛቅ አደረገችና ጠረጴዛ ላይ ወርወራ‹‹..እንግዲያው ሂሳብ ዝጋና ጠብቀኝ...ራስ ወዳድ ሆኜ አስመሸሁብህ አይደል..?››ብላ ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ ቦርሳዋን እዛው ጠረጴዛ ላይ ጥላ ስልኳን ብቻ  በእጇ  ይዛ እየተውረገረገች በሆቴሉ የኋላ፣በር ወደውስጥ ገባች...ወደ ቶይሌት እየተራመደች ደወለች...መጥራት ሲጀምር ሰውነቷን ፍርሀት ወረራት
"አሁን ምን እለዋለሁ?"ጨነቃት...ደግነቱ ስልኩ አልተነሳም...
ጥሪውን ጨርሶ ተቋረጠ። የምታደርገው ግራ ገባት፡፡ ሰዓቱን አየች። ለአምስት ሰዓት አስር ጉዳይ ይላል።

‹‹ያ እንቅልፋም በዚህ ሰዓትማ  ሀይለኛ  ህልም  እያለመ ነው"ስትል  አሰበች ቶይሌት ገባችና የከፈተችውን በራፍ መልሳ ዘግታ ቀሚሷን ገልባ ፓንቷን ወደታች አንሸራታ ቁጭ አለች። ሽንቷ ወጥሯት ተጨናንቃ ነበር...
ሿሿሿ ብሎ መውረድ ጀመረ.. በዚህ መሀል ስልኳ ጠራ…አየችው።ራሱ ነው።

‹‹ይሄ  እንቅልፋም  ነቃ  ማለት  ነው....ልታነሳ  ፈለገች ...የሽንቷ  የሿሿታ  ድምፅ እሱ ጆሮ ደርሶ እንዳይረብሸው እስክትጨርስ መጠበቀ ወሰነች  ...ሽንቷን ከማጠናቀቋ በፊት ስልኩ ተቋረጠ...""ከሁለት ደቂቃ በኃላ ራሷ ደወለች።ተነሳ።
   ጆሮዋ ላይ ለጥፋ ፀጥ አለች።‹‹አዎ እኔ የመናገር እድሉን ካመቻቸሁለት ይበቃል..ይቅርታ የመጠየቅ ጥፋቱን እየተናዘዘ የመለማመጥና የመለመን ድርሻው የእሱ መሆን አለበት።አዎ  እኔ መልስ  የመስጪያ  ጊዜዬ እስኪደርስ በኩራት መጠበቅ ነው ያለብኝ›› ብላ በዝምታዋ ፀናች።ክፋቱ ከዛም ወገን ፈጣን መልስ አላገኘችም፡፡

ከረጅም ጥበቃ በኋላ "ሄ....ሎ"የሚል ድምፅ ከወዲያኛው ጫፍ እየተንሳፈፈ መጥቶ ጆሮዋ ውስጥ ተሰነቀረ....ውርር አደረጋት።ቶሎ ብላ ከጆሮዋ አነሳችና ወደ አይኗ አቀረበችው፤አፍጥጣ እና አትኩራ አየችው።አልተሣሣተችም ስሙም  ቁጥሩም የራሱ ነበር።
"ሄሎ የእሱባለው ስልክ አይደለም እንዴ?"
"ትክክል ነሽ..አልተሳሳትሽም...ግን አንቺን ማን ልበል?"
"አይ አታውቂኝም...እሱን ልታቀርቢልኝ አትቺይም...ነው ወይስ ተኝቷል?"ስትል ጠየቀቻት
‹‹አዎ ቁጥሩን ካልተሳሳትኩ የምታናግረኝ እህቱ ነች ማለት ነው›› ስትል ነበር በእርግጠኝነት የወሰነችው።ከልጅቷ የሰማችው መልስ ግን የሚያጥወለውል አይነት ነበር።
"አይ አልተኛም ልጅ እያባበለ ነው?"
‹‹እንዴ የምን ልጅ?"
"የምን ልጅ ማለት ምን ማለት ነው..?የራሱን ልጅ ነዋ..የወለደውን" "ይቅርታ አንቺን ማን ልበል...?"
"ባለቤቱ ነኝ...በጣም አስቸኳይ ካልሆነ  "
ልጅቷ ተናግራ ሳትጨርስ ስልኩ ከእጇ ተንሸራቶ ወለሉ ላይ   ወደቀ፡፡ከውጭ‹‹ሳባ..የት.ነሽ....?"የሚል ተደጋጋሚ ጥሪ ስትሰማ ነበር ከድንዛዜዋ የባነነችው፡፡
"እ....መጣሁ"አለችና ከሽንት  ቤቱ ሰሀን ተነሳችና  ፓንቷን  ወደ ላይ ጎትታ የነበረበት ቦታ በመመለስ ቀሚሷን ወደታች ለቀቀች።ጎንበስ አለችና የወደቀውን ሞባይል አነሳች።ስክሪኑ ከዳር ሰንጠቅ ብሏል።በክህደት ምክንያት ልቡ ከመሀል ለተሠነጠቀ ሰው የሞባይሉ መሰንጠቅግድ   ይሰጠዋል?።የሽንት ቤቱን በራፍ ከፍታ ስትወጣ ደምሳሽ ግራ በመጋባት በራፍ ላይ ቆሞ ሲጠብቃት አገኘችው።
   እንዳያት "እንዴ ምነው...?አመመሽ እንዴ?"ሲል ጠየቃት
ፍርጥም ብላ ‹‹ምነው"
   አይ ቆየሽ...ደግሞ ፊትሽ ተቀያይሯል...ይሄው ቦርሳሽ...ነይ ክፍልሽ ላድርስሽ"
    "አይ ወደ ክፍሌ መግባት አልፈልግም"ያልጠበቀው መልስ ስለነበረ ግራ ገባው "እ ምነው? በሰላም?"
ቦርሳዋን ተቀበለችውና ወደባር እየተመለሰች..."መጠጣት ፈልጋለሁ...ለዛውም በጣም"አለችው። ከኋላ ተከተላት...ከተነሱበት ቦታ ተመልሳ ተቀመጠችና አስተናጋጁን በእጇ ጠራችው።አስተናጋጁ ተንደርድሮ ስራቸው ሲደርስ ደምሳሽም ደርሶ ለመቀመጥ ወንበር እየሳበ ነበር...የቤቱን ምርጥ የተባለ ወይን አምጣልኝ...ደግሞ የሚያሰክር መሆን አለበት"አስተናጋጁ  ትዕዛዙን  ተቀበለና  በፍጥነት ተመልሶ ሄደ ።››
‹‹ይቅርታ ትንሽ መጠጣት ስለምፈልግ ነው።አንተ ሂድ...እዚሁ ጠጥቼ እዚሁ ክፍሌ መግባት የሚከብደኝ ይመስልሀል?።"

"ለእኔ.አታስቢ..እኔ.በማንኛውም.ሰዓትመሄድ.እችላለሁ...ለምጄዋለሁ"
እንግዲያው እንዳልክ"
"መጠጡ መጣና ተቀዳላት...እሱ ግን የጀመረውን  ቢራ አስመጣና  በመጠጣት የእሷን ሁኔታ በንቃት መከታተል ቀጠለ።
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለሊት 10 ሰዓት  ነበር የባነነችው። ራስ ምታት  እየወቀራት  ነበር።  አይኗን እንኳን መግለጥ አቅቷታል።"የት ነው ያለሁት ?"እጇን ወደአይኖቿ ላከችና እያሻሸች ከመኝታዋ ተነሳች።...ሽንቷ  ነው  ከእንቅልፏ  የቀሰቀሳት፡፡ከአልጋዋ   ወረደችና ቀጥታ ወደሽንት ቤት ሄደች። ጨርሳ ስትመለስ ከእንቅልፏ ድባቴ ሙሉ በሙሉ ነቃታ.. አይኖቿም ተከፍተው ነበረ...መኝታ ክፍሏ  ውስጥ ባለው  ሶፋ ላይ የተኛ ሰው አለ..አፍጥጣ አየችው…አልጋ ልብስም ሆነ ሌላ ስላለበሰ ወዲያው ነው ማንነቱን የለየችው። እሱም ነቅቶ በዝምታ እያያት ነው።

"እንዴ ደምሳሽ...?"አለችው በመገረም

"ይቅርታ በእንደዛ አይነት ሁኔታ ብቻሽን  ጥዬሽ  መሄድ  አልቻልኩም...ምን አልባት ለሊት ካመመሽ ብዬ ሰጋሁ››
"ታዲያ ቢያንስ አልጋ ልብሱን ወስደህ አትለብስም ነበር?"አለችው አልጋው  ጠርዝ ላይ ተቀምጣ።

"አይ ችግር የለውም...በእንደዚህ አይነት ሁኔታ የመተኛት  የብዙ  ጊዜ  ልምድ አለኝ"

"ቢሆንም ለእኔ ስትል እንዲህ  በብርድ  መመታት የለብህም ››አለችና  አልጋ ልብሱን ከላይ በማንሳት አልብሳው ስትመለስ ማታ ለብሳው የነበረውን ቀሚስ በስርአት ተጣጥፎ ተቀምጦ አየች። ለመጀመሪያ ጊዜ  የለበሰችውን  ቢጃማ አስተዋለች

"መቼ ነው ቢጃማዬን የቀየርኩት?"ራሷን ጠየቀች...ለማስታወስ ሞከረች...ትዝ ያላት ነገር የለም...ደግሞ ቀሚስ አስተጣጠፏ የእሷ አይደለም። እንኳን ሰክራ በሰላሙም ቀን እንዲህ አይነት ነገር ላይ ሰነፍ ነች።አልጋ ላይ ወጥታ በተገለጠው ብርድ ልብስ ወደውስጥ ገብታ እየተኛች"ደምሳሽ"ስትል ተጣራች።
"አቤት"
"ልብሴን ማን ነው ያወለቀልኝ?" "ምነው የተበላሸ ነገር አለ እንዴ?"
"አይ ማለቴ..."የምትለው ጠፋት
"በይ ወደ እንቅልፍሽ ተመለሺ ...ለሊት ነው"

"እሺ ደህና እደር"አለችውና ሙሉ በሙሉ ተሸፈነች፤እንቅልፍ ግን ሊወስዳት አልቻለም።ማታ በፍቅረኛዋ ልብ ሰባሪ ድርጊት ልቧ እስኪሰባበር ድረስ አዝናና ተበሳጭታ ነበር።በዛም የተነሳ አቅሏን እስክትስት ጠጥታ ይሄው ለሳምንት ብቻ የምታውቀው ባዕድ ሰው ልብሷን አውልቆ መላ እርቃኗን አገላብጦ አይቶ ሌላ ልብስ አልብሶ እስኪያስተኛት የምታውቀው  ነገር  አልነበረም።  በቀጣይነት  ከእሱ ጋር እንዴት አድርጋ ነው ስራ የምትሰራው?። እሷን ባያት ቁጥር እርቃኗ ነው የሚታየው።"ቆይ ግን ሌላ ነገር አድርጎኝ ይሆን እንዴ?"
ይሄ ሀሳብ ወደምናቧ በመጣበት ቅፅበት በርግጋ ከመኝታዋ ተነስታ ቁጭ አለችና ብርድ ልብሱን ከላዯ በመግፈፍ እግሯን አንፈርክካ ጭኗ መካከል አይኖቿን ተክላ ቀኝ እጇን በፓንቷ ስር ሰዳ መዳበስ ጀመረች...በዚህ ቅፅበት ደምሳሽ ከተኛበት በርግጎ እና ተንደርድሮ ስሯ ቆመና"ምን ሆንሽ ...ምን ነካሽ?" እያለ ይጠይቃት ጀመር…በሌላ ድንጋጤና እፍረት ቶሎ ብላ እጇን ከፓንቷ መዛ አወጣችና ቢጃማዋን ወደታች መልሳ .."እኔ እንጃ የሆነ አውሬ ማለቴ ትንኝ ምናምን ነገር መሠለኝ"አንደበቷ ላይ   የመጣላትን ቀባጠረች።

"አውሬ..እዚህ  አውሬ...እንዴት ተደርጎ...?እስኪ ተነሽ…ከአልጋ ውረጂ" እውነታውን  ብታውቅም    ትዕዛዙን  ተቀብላ  ወረደች    ..ልብሷን      ከአልጋው  ላይ በየተራ    በማንሳት  ማራገፍ  ጀመረ።ሳቋ    አፈናትም..አሳዘናትም። እየተንደረደረች ወደሻወር ቤት ገባች። ፓንቷን አወለቀችና ሙሉ በሙሉ በነፃነት ብልቷን ማየትና መፈተሽ ጀመረች...እና በሞኝ ድርጊቷ በራሷ ሳቀች።‹‹የሆነ ነገር አድርጎ ቢሆን በቀላሉ አላውቅም ነበር...?ለመጀመሪያ  ጊዜ  ያደረኩት ወሲብ  እንዴት   እንዲህ ቀላልና  ህመም  አልባ  ይሆናል?ብዬ  ላስብ  ቻልኩ….  ደግሞስ  ….አድርጎስ ቢሆን ምን ነበር የማደርገው?" ለራሷ ጥያቄ እራሷ መመለስ ጀመረች"አዎ በጣም ነበር የምበሳጨው "ስትል ለራሷ መልስ ሰጠች።
ደግሞ ሌላ ጥያቄ ‹‹ግን ለምንድነው የምበሳጨው?"

"ዋናው በህይወት ዘመኔ አንዴ ብቻ የማገኘውን ሳላጣጥመው ማጣቴ ያበሳጨኛል...ሁለተኛው  ያለፍቃዴ  ተሸውጄ  መሆኑ… ሶስተኛው... ››አለችና  ሀሳቧን  ገታች‹‹ሶስተኛ ለማላፈቅረው ሰው በመሆኑ››ልትል ነበር...ግን ልቧ እንቢ አላት…::በተወሰነ ደረጃማ ቢሆን ወዳው ነበር...በፍጥነት ወደውስጧ እየገባ ነበር። እና እሱ በመሆኑ የሚከፋት መስሎ አልተሰማትም..ከሀሳቧ ያወጣት  የሻወር ቤቱ መንኳኳት ነበር፡
"አቤት"አለች "ሰላም.ነሽ?"
በእጇ አንጠልጥላው የነበረውን ፓንት መልሳ በማጥለቅ  ፋንታ  ማንጠልጠያው ላይ ሰቀለችና.."ሰላም ነኝ …ሰላም ነኝ"እያለች በራፍን ከፈተችና ወጣች። ሰላም መሆኗን ለማረጋገጥ አይኖቹን ከላይ እታች አንከባለለባት።
"ትንሽ  ሲያሸልበኝ  ቃዠቼ  መሠለኝ"አለችና  ወደአልጋው  ስትሄድ  እንደአዲስ አስተካክሎ አንጥፎት ነበር ።
"አስቸገርኩህ አይደል?"
ወደ ሶፋው እየሄደ”አረ ችግር የለውም ዋናው ያንቺ ደህንነት ነው።” አላት "ለምን እዚህ አትተኛም… ይበቃናል"
የእሷን ግብዣ ችላ አለና አዲስ የወሬ ርዕስ ከፈተ "የሆነው ነገር ምን አልባት በምክንያት ነው"
"ምኑ?"
"ከምታፈቅሪው ሰው መለያየትሽ ..."አላት፡፡
"የማፈቅረውን  ሰው  በዚህ  መልክ  ማጣቴ  እንዴት  ነው  ጥሩ  የሚሆነው?"ግራ ተጋብታ ጠየቀችው።
"አየሽ ...እሱ ባይከዳሽም ውለሽ አድረሽ አንቺ ትከጂው ነበረ"
"አረ...እንደዛ አይነት ሰው እመስላለሁ?።››
"አንቺ በፍፁም አትመስይኝም...የጀመርሽው ስራ ባህሪ ግን እንደዛ ነው። በጥቂት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይቀይርሻል። ሌላ አመለካከት፤የተለየ    ስነልቦና ያለሽ አዲስ ሰው ነው የምትሆኚው። እና በምንም  አይነት   ፍቅረኛሽ እንደሚፈልግሽ አይነት ሰው ፍፁም ልትሆኚ አትችይም። ለተወሰነ ጊዜ ተጨቃጭቃችሁ ከዛ   መለያየታችሁ   አይቀሬ   ነበር..ልዩነቱ   አሁን   እሱ   ነው ልብሽን የሠበረው...ቢቆይ ኖሮ አንቺ ነበርሽ ልቡን የምትሰብሪው።››
"እንድፈራ እያደረከኝ ነው"
"ይቅርታ....እውነቱን እየነገርኩሽ እና ለሚመጣው ነገ እያዘጋጀሁሽ ነው"
"ለመሆኑ አንተ ፍቅረኛ የለህም?"
"ፍፁም.የለኝም...ወደፊትም አይኖረኝም" "እንዴ ለምን?"
‹‹እየነገርኩሽ  እኮ  ነው...እዚህ  ስራ  ውስጥ  ከአንድ  አመት  በላይ  ከቆየሽ ፍቅር...እምነት...ጋብቻ....ቤተሰብ የሚሉት ነገሮች ትርጉም ያጡብሻል።››

"በምን ምክንያት? "
"ልታይው አይደለ...ምን አስቸኮለሽ?...አሁን በይ ተኚ"
"እሺ ግን ነገ ካቆምንበት እንቀጥላለን"
"ችግር የለውም"
"ጥዋት ሁለት ሰዓት ከእንቅልፏ ስትባንን ክፍሉ ባዶ ነበር። መጀመሪያ  ወደሻወር ቤት የገባ መስሏት ነበር ...ግን ኮመዲኖ ላይ  በተወላት ማስታወሻ  ትቷት ወደጉዳዩ እንደሄደ ተረዳች።
የተወላት ማስታወሻ‹‹ሳባ...የሆነች ስራ ስላለችኝ ሄጄያለሁ።ስራዬን እስከ አራት ሰዓት እጨርሳለሁ።ከዛ በኋላ በፈለግሺኝ ሰዓት ደውይልኝ"ይላል።
//
አሁን…ዛሬ ላይ
አዲስ አበባ ሰፈሯ ስለደረስች ከትዝታዋ ወጣችና በራፉ እንዲከፈትላት የመኪናዋን ክላክስ አስጮኸች…አንድ ሰዐት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ዘበኛው ከፈተላት መኪናዋን ወደውሰጥ አስገባችና አቁማ ወረደች…፡፡
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


…..የሰላም እንቅልፍ አልተኛችም እንቅልፏ ያው እንደተለመደው በስቃይ እና በቅዠት የተሞላ እንቅልፍ ነበር…ስምንት ሰዓት ላይ ሙሉ በሙሉ ከእንቅልፏ ተነስታ ወደ በረንዳ ወጣች….ግቢዋ በፓውዛ መብራት ድምቅ ብሎ ነበር፤ግን ፀጥ ያለ ነው..ፀጥታው ደስ ያሰኛል፡፡ግን አየሩ ይቀዘቅዛል ..ወደውስጥ ተመለሰችና በለበሰችው የለሊት ፒጃማዋ ላይ ከአመት በፊት ስንዱ አሰርታ የሰጠቻትን ወፍራም ጋቢ ከቁም ሳጥኗ አውጥታ ለበሰችና ተመልሳ ወጥታ ወንበር ላይ ቁጭ አለች፡፡

እና ቅድም ከአሰላ ስትመጣ በመንገዷ ሁሉ ስታመነዥገው የነበረው ትዝታና በራፏ ጋር ስትደርስ አቁማ ነበር፡፡ከሰአታት.እረፍት በኋላ አሁን በእኩለ ለሊት ካቆመችበት ቀጠለች፡፡
ትዝታ…ከአስር አመት በፊት
ከዛሬ አስር አመት በፊት የነበረችው ሳባ ናፈቀቻት፡፡ እስከዚያ  ጊዜ  ድረስ የዋህ፤ንፁህ ግን ደግሞ ጉጉና ደፋር ወጣት ነበረች፡፡ለአባቷ ያላት ፍቅር በወቅቱ ምንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል እንዳታመነታ አድርጓታል፡፡ ቢሆንም በወቅቱ የነበራት ምልከታ በአስር አመት ውስጥ ከሆነው ፍፁም  የተለየ  እና የምድር እና የጨረቃን ያህል ርቀት ያለው ነው፡፡ በወቅቱ ሀሳቧም ግልፅ ምኞቷም ቅልብጭ ያለ ነበር፡፡ምንም አይነት ስራም ቢሆን ሰርታ ገንዘብ በማግኘት ለአባቷ ዘመናዊ ዊልቸር መግዛት ከዛም አሪፍ መኪና ገዝቶ ምቹ ህይወት እንዲኖር ማድረግ…ከዛ በቃ ወደኃላ ተመለሳ እንደቀድሞ ንፁህ ቀላልና የተለመደ አይነት ህይወት መኖር…እንደዛ ነበር እቅዷ….ግን ለካ ወደኋላ መመለስ ወይንም ባሉበትም ቢሆን ቆሞ የህይወትን  ፍሬን  በመያዝ  ከገቡበት ማጥ መውጣት ቀላልስራ.አልነበረም…ይሄው አስር አመት ፈጀባት፡፡
በወቅቱ ከደምሳሽ ጋር አንድ ቤርጎ ውስጥ ካደሩና ጠዋት  እሱ  በተኛችበት ማስታወሻ ትቶላት ከሄደ ቡኃላ አልጋዋን ለቃ በመውረድ ልብሷን በጥንቃቄ ለብሳ እዛው ሆቴል ቁርሷን  በልታ  ወደለቀቀችው  መስሪያ  ቤቷ  ነበር የሄደችው፡፡ቀኑን ሙሉ እጇ ላይ ያሉትን የድርጅቱን ንብረቶች ስታስረክብ...ከዛም ክሊራንስ በየዲፓርትመንቱ እየዞረች ስታስፈርም...እንዲሁ ስትባክን ነው የዋለችው፡፡ እዛው እያለች ከቀኑ 10 ሰዓት ሞላ። ሰዓቱን ያየችው እየጠራ ያለውን ስልኳን ለማንሳት ከቦርሳዋ ስታወጣ ነበር።
"ሄሎ ደምሳሽ...እንዴት ዋልክ?"

"ደህና ነኝ...ነፃነትሽን ላለመጋፋት ነበር እስከአሁን ያልደወልኩልሽ...ግን ስጠፊ አላስቻለኝም፡፡"

"አረ ሰላም ነኝ፤መስሪያ ቤት ነው ያለሁት…ክሊራንስ ለመጨረስ እየተሯሯጥኩ ስለነበረ ነው...ለመደወል ምንም ጊዜ አልነበረኝም"
"እና አሁንም አልጨረስሺም?"
"አይ አሁን እንኳን ወደመጨረሱ ነኝ..የሥራ ልምድ ተፅፎልኛል...መዝገብ ቤት ገብቶ ወጪ እስኪሆን ነው እየጠበቅኩ ያለሁት።››
"እንደዛ ከሆነ በቃ መጣሁ...ቅርብ ቦታ ነኝ..አንድ 15ደቂቃ ቢፈጅብኝ ነው።"ብሎ ስልኩን ዘጋው።ደስ የሚል ስሜት ሰውነቷን ወረራት።እንዲህ የሚያስብላት፤እንዲህ የሚንከባከባት ሰው ከጎኗ በመኖሩ ተደሰተች። እርግጥ ስራው ነው…ታውቃለች፡፡እሱም ደጋግሞ ነግሯታል። እሷ ግን እንደዛ እየተሠማት አይደለም። አሳቢነቱ ከልብ የመነጨ፤እንክብካቤው.ፍቅር የተቀየጠበት እንደሆነ ነው እየተረዳች የነበረው። ውስጧ በሰው ሲተማመን ከአባቷ ቀጥሎ የመጀመሪያው ሰው ነው። የምታፈቅረው የነበረውንና ልቧን የሰበራት ሰው ራሱ አብራው ባለችበት ጊዜ ሳይቀር እንደዚህ እንዲሰማት አድርጎ አያውቅም።
መኪና ውስጥ ገቢና ከጎኑ ተቀምጣ እያወሩና እየተጫወቱ እየተጓዙ ነው። "አሁን የምትሄጂበት ቦታ አለ?"ሲል ነበር የጠየቃት፡፡
"አይ የትም አልሄድም...በእለቱ  መስራት  የምፈልገውን.ስራ ጨርሼያለሁ...የምትሄድበት ቦታ ካለህ ሆቴል ጣል አድርገኝና መሄድ ትችላለህ፡፡"
"አይ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም..የማትቸኩይ ከሆነ ቤቴ በሚቀጥለው ቅያስ አጠፍ ብሎ ስለሆነ ጎራ ብለን ልብስ ብቀይር ብዬ ነው"
"ታዲያ ምን ችግር አለው"
‹‹እንግዲያው እሺ››አለና መኪናዋን ወደ ግራ ጠመዘዘና በጠባብ ኮብል መንገድ ገባ…ትንሽ ከተጓዘ በኋላ ባለጥቁር ቀለም የብረት በራፍ ቪላ ቤት የመኪናዋን አፍንጫ አስጠጋና ጡሩንባዋን አስጮኸ...በፍጥነት በዘበኛው አማካይነት በሩ ተከፈተለትና ወደውስጥ ገባ..፡፡
"እዚህ ተከራይቶ ነው የሚኖረው ማለት ነው?"ብላ አሰበች፡፡ የዘበኛው መሽቆጥቆጥ ግን ግራ አጋባት፤ ከመኪና እንደወረደ ግዙፍ ሰንሰለት አንገቱ ላይ የተጠለቀለት ውሻ ሰንሰለት ለመበጠስ በሚፈልግ አይነት እየቦረቀ እና እየዘለለ ወደ ደምሳሽ አቅጣጫ ይዘል ጀመር..ሳባ በፍራቻ ወደ ኃሏ ሸሸች...ደምሳሽ በፈገግታና በደስታ ወደውሻው ተራመደ ስሩ ደረሰና፣ ጭንቅላቱን ሲያሻሽለት ውሻው ከድምፁ ቀነስ ከዝላዩ ሰከን እያለ መጣና እግሩ ስር ውልምጥምጥ ብሎ ተኛ…ከዛ የደምሳሽን እግር በረጅም ምላሱ ይልስ ጀመር፡፡
"መክሰሱን.ሰጠኸው?"
‹‹አዎ ጌታዬ አሁን በላ››
"በል  ጌታው  እንግዳ  አለብኝ"አለና  ከስሩ  ተነስቶ  ሳባን አስከትሎ  ወደግዙፉ  ቪላ ቤት ይዟት ገባ...
ቤቱ ቢያንስ 10 አባላት ያሉትን ቤተሰብ ዘና ባለ ሁኔታ ማኖር የሚያስችል ሁሉ ነገር የተሟላለት ባለብዙ ክፍል ግዙፍ ቤት ነው።

ወደ ሶፋው በእጁ እያመለከተ "ቁጭ በይ" አላት...በዝምታ የቤቱን ዙሪያ ገባ እየቃኘች ወደ አመለከታት ቦታ ሄዳ ቁጭ አለች።
"የሚጠጣ ምን ላምጣልሽ?"
"ያለውን.."
ተራመደና ሳሎን  ውስጥ ያለውን ግዙፍ ፍሪጅ ከፈተ...እንደ ሱፐርማርኬት ፍሪጅ ጥቅጥቅ ብሎ በመጠጥ አይነቶች፣በፍራፍሬና፣በታሸጉ ምግቦች ተሞልቷል። ሁለት ቢራ አነሳና ከመክፈቻ ጋር በማምጣት ከፍቶ አንድ ለእሷ አቀረበላትና ሌላውን በመክፈት ገርገጭ ገርገጭ በማድረግ ሩቡን ያህል ከላፈለት በኋላ ጠረጴዛው ላይ በማስቀመጥ ሪሞት በማንሳት ቲቪ ከፍቶ ሪሞቱን ለእሷ አቀበላትና፡፡ "ጥቂት ደቂቃ...ልብስ ቀይሬ ልምጣ፡፡"አላት፡፡
"ችግር የለውም…ኸረ ...ዘና ብለህ ቀይር፡፡ "ስትለው ወደ ውስጠኛ ክፍል አመራ...ከ10 ደቂቃ በኃላ ለብሶት የነበረውን ጥቁር ሱፍ አውልቆ ሰማያዊ ጅንስ ሱሪ በነጭ ቲሸርትና ከቡኒ ሌዘር ጋር ለብሶ ይበልጥ ፈርጣማና ጎረምሳ መስሎ ወጣ፡፡
"አልደበረሽም አይደል?"እያለ ከፊት ለፊቷ ተቀመጠና ጀምሯት የነበረውን ቢራ አንስቶ ተጎነጨ‹‹ኸረ የምን መደበር....ቤትህን  ገና መቼ አይቼ ጨረስኩት"
"እንዴት ነው ቤቴ ያምራል?"
"ያምራል...ቤተመንግስት አይደል እንዴ የሚመስለው...ግን እርግጠኛ ነህ ብቻህን ነው የምትኖረው?"
"አይ እንዳየሽው ዘበኛዬ አለ...ውሻዬም አብሮኝ ነውየሚኖረው  ..በየሁለት ቀን እየመጣች ቤት የምታፀዳልኝና ሌሎች ስራዎች የምትሰራልኝ ልጅም አለች፡"

"በቃ?"
"ምነው….ካነሰ እያየን እንጨምራለን፡፡" "የእውነት.ይገርማል...ግንኪራዩን ትችለዋለህ"
"የራሴ እኮ ነው"
"ዋው...!!"
"ይገርማል"
"አዎ..በጣም ያስገርማል....ብታከራየው እኮ በወር ከ50 ሺ ብር በላይ ያስገኝልሀል"
"ነው ግን...እኔ እንዲህ ዝግጁ ሆኖ እንዲቀመጥ ነው የምፈልገው …አንድ ቀን የማገባት ልጅ አግኝቼ ልቤ ሲፈቅድ ቶሎ ብዬ ሀሳቤን ሳልቀይር ጎትቼ ማስገባት ነው የምፈልገው።
"በንግግሩ ሳቋን ለቀቀች ‹‹ለመሆኑ እዚህ ስራ ላይ ስንት አመት ቆየህ?"
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


"ውይ ለመክሰስ ሆቴል...?ሰርቼ ልጋብዝሽ የምትለኝ መስሎኝ ነበር።"
‹‹ደስ ይለኝ ነበር...ግን ካገዝሽኝ ነው..."

"ይቻላል"
ሁለቱም  የየራሳቸውን  ቢራ  ይዘው  በእሱ  መሪነት  ወደ  ኪችን.አመሩ።
ኪችኑ በእጅጉ የተደራጀና የሚያምር ነው። ፍሪጁን ከፈተና ተመለከተ...
"ምን እንስራ"በራሱ መወሰን አቅቶት ጠየቃት።
"እኔ እንጃ...ምን አለህ?"አለችና ወደእሱ ተጠግታ ያለውን ነገር ተመለከተች...ብዙ ምርጫ አላቸው...የምትፈልገውን ነገር እየመረጠች ከፍሪጁ ማውጣት ጀመረች፡፡ እሱም ወደውጭ ሊወጣ አስቦ የለበሰውን ጃኬት አወለቀና ሽርጥ ለበሰ..ለእሷም ተመሳሳይ ሽርጥ ሰጣት።በ30 ደቂቃ ውስጥ ሶስት የተለያየ የምግብ አይነት ተጋግዘው በመስራት ሳሎን የምግብ ጠረጴዛ  ላይ  አቀረቡ..በልተው  ሲጨርሱ አንድ ሰዓት አልፎ ነበር።

"አሁን በላሁ ጠጣሁ...ወደማድርበት ቤርጎዬ ልትመልሰኝ ትችላለህ?›› አለችው። ሞባይሉን በማውጣት ሰዓቱን አየና"እንዴ ገና አንድ ሰዓት  እኮ  ነው...ባይሆን አንድ ወዳጄ ከፈረንሳይ ያመጣልኝ ልዩ ወይን አለኝ...እሱን ላምጣና መጠጥ እንቀይር››አለና እሺታዋንም ሳይጠብቅ መቀመጫውን ለቆ ወደመኝታ ቤቱ በመሄድ ይዞ መጣና የቢራ ጠርሙሶችን ከፊታቸው በማንሳት በወይን ብርጭቆ ተካውና ተደላድሎ ቁጭ አለ፡፡:

"በቀደም  ለታ  ግን  ማደሪያ  ቦታ  ስጠይቅህ  ለምን  ቤትህን  አራተኛ  ምርጫ አድርገህ አላቀረብክልኝም ነበር?"ስትል.ያላሰበውን ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቀችው።
"እኔ  እንጃ...ምን  አልባት  እንደዛ  ብልሽ  ሌላ  ነገር  ታስቢያለሽ  ብዬ.ፈርቼ ይሆናል"አላት፡፡
"እንዴት ሌላ ነገር አስባለሁ?"
"ብታስቢም እኮ አይፈረድብሽም...በጥልቀት አታውቂኝም"
"ለነገሩ እውነትህን ነው፤እሺ አሁን ብዙ ብር ከምትዝቅበት የማሳጅ ስራ ራስህን ለምን እንዳገለልክ ንገረኝ? "ቅድም ጀምረው ወዳቋረጡት የጫወታ ርእስ መለሰችው፡፡
የወይኑን ብርጭቆ አነሳና ውስጡ ያለውን ከጨለጠ በኃላ መልሶ አስቀምጦ አንገቱን አቀረቀረ፡፡››
"ምነው ከባድ ጥያቄ ነው እንዴ የጠየኩህ?" በረጅሙ ተነፈሰ፡፡
"ከከባድም በላይ..አየሽ ቅድም ስለስራው ሳስረዳሽ ልክ እንደሀሺሽ ነው ብዬሽ ነበር አይደል። በመጀመሪያ ሁሉ ነገር አስደሳችና ልብን ስውር የሚያደርግ ነበር። አገልግሎቱን ለማግኘት የሚመጡት ሴቶች ሊነኳቸው የሚያሳሱ  የሰውነታቸው ቆዳ እንደሀር ጨርቅ የለሠለሠ፤ የፊታቸው ውበት የመላእክት የመሰለ ፤ጠረናቸው ጭንቅላት አዙሮ ጭናቸው ስር የመድፋት ኃይል ያለው፤ የህልም አለም ንግስቶች ናቸው። ታዲያ እነሱን እርቃን አስወልቀሽ ከላይ ከጭንቅላታቸው እስከታች የእግር ጥፍራቸው መላ ሰውነታቸውን አፍተልትለሽ ዳብሰሽና አሽተሽ፤በስሜት ሲወራጩና በደስታ እንባቸው ሲንጠባጠብ አይተሽ...ለምነውና በአይናቸው ተለማምጠው እርቃንሽን ከእርቃናቸው እንድታዋህጂ ለምነውሽ...አርክተሻቸውና.ረክተሽ፤አስደስተውሽና ተደስተሽ፤ አስለቅሰሻቸውና አልቅሰሽ  ከዛ  ደግሞ  ረብጣ ብር የእጅሽ መዳፍ ላይ አስጨብጠው..በመፍለቅለቅ ጉንጭሽን ወይም ከንፈርሽን ስመው በሳምንቱ እንደሚመለሱ ምለውና ተገዝተው ይሄዳሉ...;
‹‹ስራው እስከዚህ ይሄዳል ማለት ነው"

"አዎ ምነው የፈረምሽውን ውል በቅጡ አላነበብሽውም እንዴ...ደንበኛ ምንም ነገር ጠይቆ መከልከል የለበትም ይላል እኮ.ያ ማለት ደግሞ ስራው ከነገርኩሽም በላይ ይሄዳል ማለት ነው.."
"እና አሁን አንድ የማላውቀው ሰው መጥቶ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ  ካለኝ..ዝም ብዬ እከፍትለታለሁ ማለት ነው።"

‹‹አይ ዝም ብለሽማ አትከፍቺለትም ...አንቺ ያለሽበት ቦታ አገልግሎትሽን ፈልጎ የሚመጣው ግለሰብ በየሄደበት ዝም ብለው የሚከፍቱለት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አንዳንዴም ካንቺ በላይ ለጋ፤ ካንቺ በላይ ፀሀይ የመሰሉ ውብ የሆኑ ሴቶች አሉት...እንደዛ ካደረግሽ ደብሮት የመጣውን ሰውዬ ጭራሽ አሳብደሽ ነው የምትልኪው››

‹‹እና ምንድነው ማድረግ የሚጠበቅብኝ ?››በከፍተኛ መገረም ጠየቀችው።
እጅሽ ሰውነቱ ላይ ሲያርፍ ልስላሴውና ሙቀቱ ቆዳውን ሳይሆን ልቡ ላይ ሊሰማው ያስፈልጋል....መሳም ኖሮብሽ ከሳምሽው ከከንፈሮችሽ የሚመነጨው ሙቀት ወደ ጭንቅላቱ ሄዶ በቢሊዬን የሚቆጠሩትን የኒሮን ሴሎችን ከተኙበት መቀስቀስና መደነስ እንዲችሉ ማድረግ አለብሽ... ልብሶችሽን  ፊቱ  ስታወልቂ አይኖቹ ቆዳሽን ሰንጥቀው ውስጥሽ በመግባት ነፍስሽን ጭምር ለመቆረጣጠም እስኪመኝ መቃተት መቻል  አለበት። ጭንሽን  ከፍተሽለት  ብልቱ ብልትሽን ሰንጥቆ ከገባ አካሉ መጥፋት፤አእምሮ መሰወር፤ነፍሱ በአየር ላይ እየተንሳፈፈች ትዕይንቱን መታዘብ አለባት።ሰውዬው ካንቺ በፊት ከመቶ ሴቶች ጋር ለአንድ ሺኛ ጊዜ ወሲብ አድርጎ የሚያውቅ ከሆነ .. እንዴ ከዚህ በፊት ወሲብ አድርጌ አውቅ ነበር እንዴ ..?ብሎ እስኪጠይቅና እስኪወነባበድ ድረስ ህልም ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ይጠበቅብሻል... የስራው ከባድነት ደግሞ ሰውዬው በሳምንት ወይም በወራት ልዩነት ደጋግሞ ቢመጣ በተመሳሳይ ብቃት ግን ደግሞ ፍፁም ባልተደጋገመ 10 የተለያየ መንገድ ማስተናገድ ይጠበቅብሻል፡፡
"የሚያወራውን ሁሉ የምታዳምጠው ሁሉንም የስሜት ህዋሳቶቿን ከፋፍታ ነበር...እየጠጣችው ያለው መጠጥ እየሠማችው ካለው ወሬ ጋር ተዳምሮ ሙቀትና ንዝረት ለቀቀባት
"የምትነግረኝ ነገር ሁሉ ግን እውነት ነው?ማለቴ እንደዚህ አይነት ነገር አለ?"
"አዎ አለ"
"ወይ በፈጣሪ..ታዲያ እኔ ምን  ላደርግ  ነው?  እንደው  ፍቃደኛ  ሆኜ የተጠየቅኩትን ለማድረግ ፈለኩ ልበል…ግን በየትኛው ብቃቴ ነው አንተ ባወራህልኝ መጠን በአየር ላይ የሚያንሳፍፍ ወሲብ መፈፀም የምችለው..?
"አይዞሽ ...አንቺ ብቻ ከልብሽ ተቀባይ ሁኚ እንጂ…በቂ ስልጠና ይሰጥሻል...ከዛ የተወሰነ የስራ ልምድ በኋላ እርግጠኛ ነኝ ከነገርኩሽም በላይ የተካንሽ ትሆኚያለሽ"
"እንዴት እርግጠኛ ሆንክ?"ብላ ልትጠይቀው ፈለገችና ብዙ በተናገረች  ቁጥር ይበልጥ ራሷን እያጋለጠችና ወደ ሽብር ውስጥ እየገባች ስለመጣች መልሳ ዋጠችው።
"እሺ ይሄን ለጊዜው ተውና ..የጀመርክልኝን የራስህን ታሪክ ቀጥልልኝ"
"አጠር ላድርገውና በተደጋጋሚ ጊዜ ከሚመላለሱ ደንበኞቼ መካከል ከአንዷ ጋር የተለየ ግንኙነት ነበረኝ፣ለነገሩ ከአንዷ ጋር ብቻ አልነበረም ከአምስት ከስድስቱ ጋር በይው። ግን ስራ እንዳቆም ስላስገደደቺኝ አንዷ ብቻ ላውራሽ።
የባለስልጣን ሚስት ነች። ባሏ የሆነ መስሪያ ቤት ሚኒስትር ዲኤታ ነው። ያው በስራውም በራሱ ጉዳይም በጣም እረፍት የሌለው ከወር ውስጥ ግማሹን ቤቱ
የማያድር...በሚያድርባቸው ጥቂት ቀናትም እኩለ ለሊት ገብቶ ወፍ ሲንጫጫ የሚወጣ አይነት አባወራ ነው። ሚስቱ የፈለገችውን ያህል ብር ይሰጣታል። በዛ ላይ በእሷ ስም የተከፈተ ግዙፍ ድርጅት አላቸው። የት ገባህ የት   ወጣህ እንዳትለው ያንን በማስተዳደር ቢዚ ሊያደርጋት ሞክሮ ነበር። ይሄ  እቅድ ለተወሰነ አመት ቢሰራለትም ቀስ በቀስ ሴትዬዋን ለድብርትና   ለጭንቀት እያጋለጣት መጣ ...ከዛ በአንድ ወዳጇ ገፋፊነት እኛ ጋር ትመጣለች..አጋጣሚ ሆኖ እኔ ጋር ተላከች። በመጀመሪያዎቹ ሶስት አራት   ዙሮች እንደማንኛውም ኖርማል  ማሳጅ  የተለመደውን  አገልግሎት  እያገኘች   ነበር የምትሄደው...ከዛ ነገሮች በሂደት እድገት ሲያሳዩ ከስድስት ወር የደንበኝነት መመላለስ በኃላ ጥልቅ የሆነ ፍቅር ውስጥ ገባች...
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳምንት ሙሉ ታገስኩ….ላብድ ደረስኩ…ስራ ሁሉ መስራት አቃተኝ….ከ15ቀን  በኋላ ሰውዬውን የሆነ ስብሰባ ሲመራ በቲቪ አየሁት….ደስ አለኝ፡፡ልክ እሷን ያገኘሁ ነው የመሰለኝ…..በቃ እሷም መጥታለች ማለት ነው ስል አሰብኩ….ማንንም እንዳታገኝ ቤት ውስጥ ቆልፎባታል ስል በማሰብ እርግጠኛ ወደመሆን ተሸጋገርኩ እሷን ነፃ ለማውጣት ወሰንኩ፡፡ ጓደኞቼን እንዲረዱኝ ጠየቅኩ፡፡ የሰውየውን ቤት ቀንና ሌሊት ማጥናትና መሰለል ጀመርን፤የሚገባውንና የሚወጣውን ሁሉ መከታተል ቀጠልን…በአራተኛው ቀን ቤቱ ያሉት አንድ የቤት ሰራተኛ አንድ ነርስ እና አንድ ህፃን ልጅ ብቻ እንደሆኑ አረጋገጥን›› የምሆነውም የማደርገውም ነገር ግራ ገባኝ…ሰራተኛዋ እቃ ለመግዛት ከቤት ስትወጣ ጠብቀን አገትናትና አስፈራርተን መረጃ ጠየቅናት..ሴትዬዋም ፈርታ  ስለነበረ የምታውቀውን ሁሉ ምንም ሳታስቀር ዘረዘረችልን፡፡

‹‹ምን አለቻችሁ ?ምን ሆና ነው?››ሳባ የተፈጠረውን ለማወቅ በጉጉት ጠየቀች፡፡

‹‹ሚስቱ ከአሜሪካ ወደሀገሬ አልመለስም ብላ አንደኛውን ልጅ ይዛበት እንደተሰወረች..ለ15 ቀን ከዛሬ ነገ ተመልሳ ትመጣለች ብሎ ሲጠብቃትና ሲያስፈልጋትም ከቆየ በኋላ ተስፋ ቆርጦ የተወችለትን አንደኛውን ልጁን ይዞ ወደ ሀገር እንደተመለሰ እንደነገራቸው፣…እና ሁልጊዜ ወደቤት ሲገባ እሱን እያሰበ እንደሚያዝንና እንደሚተክዝ ነገረችን….ላምን አልቻልኩም፡፡

በሰማሁት ዜና በጣም ተረበሽኩ..ላብድ ደረስኩ‹‹እሷ በፍፁም እንደዛ አታደርግም..አንደዛ ብታደርግ ኖሮ ቢያንስ ካለችበት ቦታ ለእኔ የሆነ መልዕክት ትልክልኝ ነበር…ኢሜሌንም ሁለቱንም ስልክ ቁጥሬን በቃሏ ልክ እንደገዛ ስሟ ነው የምታውቀው….እና የሆነ ነገር እንደሆነች ገባኝ፡፡ በህይወቴ ወሰንኩና እሷ ምን እንደሆነች ለመረዳት አንድ አደገኛ ነገር ለማድረግ ወሰንኩ በሁለት ቦዲጋርድ እየታጀበ ወደቤቱ የሚመጣውንና የሚሄደውን ሚኒስቴር ዲኤታ በጓደኞቼ እገዛ ቤት ውስጥ ገብቼ በገዛ መኝታ ቤቱ ለመተኛት ሲገባ ጠበቅኩና ሽጉጥ ግንባሩ ላይ ደቅኜ እጆቹንና እግሮቹን ጠፍሬ ከወንበር ጋር አሰርኩትና እውነቱን እንዲነግረኝ ጠየቅኩት››

‹አንተ ነህ ማለት ነው ውሽማዋ?››ሲል ጠየቀኝ፡፡

‹‹ሚስትህን  እንደዛ  አይነት  ስህተት  ውስጥ  እንድትገባ  የገፋፋሀት  አንተው  ነህ
…ምንም አይነት ለአሷ የሚሆን ጊዜ አልነበረህም….››አልኩት፡፡

‹‹እና በእኔ ላይ መሸርሞጧ ትክክል ነው ትላለህ?››

‹‹አንተም እኮ ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ሴቶች ጋር በየሆቴሉና ሎጁ ስትቀብጥና ስትሸረሙጥ መኖርህን አውቃለሁ…ከፈለክ መረጃው አለኝ….አልኩና ሞባይሌ ላይ ከነበሩት አንድ ሶስት መረጃዎች ውስጥ ከፈትኩና አሳየሁት›

‹‹እና እኔ ስላደረኩት እሷ ማድረግ አለባት እያልክ ነው…?ደግሞ ቢያንስ እኔ እኮ ልጅ ወልጄ አላመጣሁባትም››

‹‹አይ አንተም ንፁህ አይደለህም ስለዚህ ይቅርታ ይገባታል እያልኩህ  ነው…አሁን የት ነው የቆለፍክባት?››
‹‹የምን መቆለፍ…ጉዷ ተፍረጥርጦ ሲወጣ እዛው  አሜሪካ  ነው  አንደኛውን ልጇን ይዛ የተሰወረችው›› ብሎ ሊያታልለኝ ሞከረ….ብዙ ሞከርኩ ሲያስቸግረኝ አፉን አፈንኩትና ገልብጬ እግሩ እስኪተለተል ወፌ ላላ ስገርፈው…በመጨረሻ አመነልኝ፡፡ ሲጨቃጨቅ ድንገት እንደመታትና እንደሞተችበት…ከዛ ለአሜሪካ ጋንግስተሮቸ ብዙ ብር ከፍሎ እሬሳዋ እንዲወገድ እንዳደረገ እና የእሱ ያልሆነውን ልጁም ነጥሎ ለማደጎ ድርጅቶች እንደሰጠ አፉን ሞልቶ ነገረኝ….ልጁን የሰጠበትን የማደጎ ድርጅት አድራሻ ተቀበልኩትና ልገድለው ፈለኩ፤ከራሴ ጋር ለበርካታ ደቂቃዎች ተሟገትኩ ግን የልጄ ወንድም አባት ነው…እንዴት ምንም ያማያውቀውን ህፃን ያለእናት መቅረቱ ሳያንስ ያለአባት አስቀረዋለሁ? ብዬ አሰብኩ….፡፡

ከዛ ስለእኔ ለሌላ ሰው ቢያወራ ሊበቀለኝ ሙከራ ቢያደርግ እሱንም አሳልፌ እንደምሰጠው ስልጣኑንም ክብሩንም አጥተን እስር ቤት እንዲበሰብስ እንደማደርገው ነግሬ በገባሁበት ቦታ ጋርዶቹ ሳያዩኝ ጥዬው ወጣሁ፡፡
‹‹እና አላሳሰርከውም?››
‹‹ባሳስረው ምን ይጠቅመኛል…?አራስ ልጅ እኮ አለው...ልጁ ደግሞ ምንም ቢሆን የእሷ ነው››
‹‹ከዛ በኋላ ሊያጠቃህ አልሞከረም?››
‹‹በፍፁም ስሬ ድርሽ አላለም፡፡››
‹‹እና ልጅህን የምታስመልስበት ምንም መንገድ አላገኘህም?.››
አሜሪካ  በሚገኙ  ወዳጆቼ  አማካይነት  ለረጅም  ጊዜ  ካፈላለኩ  በኃላ  የዛሬ  ወር አካባቢ ትክክለኛ አድርሻውን አገኘሁ፡፡››
‹‹በእውነት ደስ ሲል..››
‹አዎ ደስ ይላል.. እሱ ለማደጎ ድርጅት ቢያስረክበውም .ማደጎ ድርጅቱ  ደግሞ አሳዳጊ አግኝቶ ለአንድ አሜሪካዊ ጥንዶች አስተላልፈው ስለሰጡት አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማወቅ ችያለሁ…..እግዜር ካለ በቅርብ ሄጄ እንደማየውና ከተቻለ ይዤው እንደምመጣ ከልሆነ እንኳን ከወላጆቹ ጋር  ተዋውቄ  ልጄንም አይቼ መምጣት ፈልጋለሁ..፡፡
‹‹በጣም ነው የማዝነው ሰው ሁሉ ለካ የራሱን ቁስል ይዞ ነው የሚዞረው››ስትል አሰበች፡፡
አዎ..ይሄንን ታሪክ የሚያውቁ በጣም የቅርቤ የሆኑ ጥቂት ሰዎች ናቸው..እና ከዛ በኋላ የማሳጅ ስራ እንዴት መስራት እችላለሁ...? ገና የማሳጅ ጠረጴዛው ላይ የሆነ ሴት መጥታ ስትተኛ ፊቴ ድቅን የምትለው እሷ ነች…..ልክ በገዛ እጄ አንቄ እንደገደልኳት ወይም በገመድ አንጠልጥዬ ነፍሷን እንደነጠቅኳት ይታሰበኝና እጄ ሆነ መላ ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል…ከዛ አቃተኝና ይብቃኝ አልኩ…ትብለጥም ከመጀመሪያው ጀምሮ ታሪኩን ታውቅ ስለነበረ ወዲያው ጥያቄዬን ተቀበለችና ይሄንን አሁን የምሰራውን ስራ እንድሰራና ድርጅቱን ልክ እንደቤተሰብ ድርጅት እንዳገለግል ጠየቀችኝ ..እኔም ተቀበልኳት…እና ይሄው ሁለት አመት ድርጅቱ በሚፈልገኝ በማንኛውም ቦታ እየገባሁ ያለውን ስራ ሁሉ እሰራለሁ…በጣም ጥሩ የሚባል ደሞዝም ይከፈለኛል…እና ታሪኩ እንደዛ ነው እልሻለሁ ፡፡
‹‹በጣም ያሳዘናል፡፡››…አለች የእውነትም ከልቧ አዝና…ከመጠጡ ጋር ወደ ውስጧ ያስገባችው አሳዛኝ ታሪክ በሰውነቷ ሙቀት ለቀቀባት…ስትቁነጠነጥ አየና‹‹ ምነው ምን ፈለግሽ?››ሲል ጠየቃት፡

‹‹እኔ እንጃ… ሞቀኝ …ሰውነቴን ለቅለቅ ብል ደስ ይለኛል፡፡››አለችው፡፡

የጠበቀው‹‹መሸ ወደ ሆቴሌ አድርሰኝ›› የምትለው ነበር የመሰለው፡፡ቶሎ ብሎ ተነሳና‹‹ተነሽ ምን ችግር አለው..እንደቤትሸ ቁጠሪው››አለና እየመራ ወደ ውስጠኛው ክፍል ይዟት ሄደ…አንዱን ክፍል ከፍቶ ገባ ተከተለችው፡፡መኝታ  ክፍሉ ከሳሎኑ ብዙም የማይተናነስ ሰፊ ክፍል ነው፡፡መሀከል ላይ ነጭ  አልጋ  ልብስ በስርዓት የተነጠፈበት ነጭ ግዙፍ አልጋ ይታያል…በአንደኛው  የግድግዳ ሙሉ ቁም ሳጥን የተገጠመለት ነው፡፡
‹‹ይሄ ሁሉ ቁም ሳጥን ልብስ ካለበት ይገርመኛል››አለች፡፡
ወደ ቁም ሳጥኑ አመራና አንዱን በራፍ ከፍቶ ከተደረደሩት በርካታ አንሶላና ፎጣዎች ውስጥ አንድ ነጭ ፎጣ አወጣና እያቀበላት
‹‹ያው ግቢና ታጠቢ ሳሎን እጠብቅሻለሁ››አላት፡፡
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዛሬ ላይ…አሁን

ሳባ ከሰመጠችበት የአመታት ትዝታ ወጥታ…ወዳለችበት ስትመለስ  ከታላቅ መገረም ጋር ነው፡፡በዛን ወቅት በዛን ለሊት በወሲብ የረካችውን እርካታ በህይወቷ ሙሉ ድጋሚ አግኝታው አታውቅም..እናም ደግሞ ፈፅሞ  አትዘነጋውም..እርግጥ ሴት ሆና የመጀመሪያ ቀን የወሲብ ገጠመኟን  በመጥፎም ሆነ በክፉ የማታስታውስ የለችም…የእሷ ግን ከነጣዕምና ከነቃናው ዕድሜ ልኳን ይሄው እንዲህ ስብርብር ብላ አቅሏን  አጥታ ደንዝዛ እንኳን  ምንም የደበዘዘ ነገር የለም፡፡ እንደምንም ከተቀመጠችበት ተነስታ ለመቆም ስትሞክር እግሯ የእሷ መሆኑ እስኪጠፋት ድረስ ደንዝዞ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኗል ..እንደምንም ፈጠን አለችና የበረንዳውን ብረት በመያዝ ቆመች….ከድንዛዜዋ እስክትወጣ ከ5 ደቂቃ በላይ ወስደባት…
ትዝ ይላታል እዚህ ቦታ ስትቀመጥ ከለሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ነበር..አሁን  ግን ነግቶ..ወፎች ግቢ ውስጥ ያሉ ሁለት ዛፎች ላይ ሰፍረው ጭጭጭ እያሉ መንፈስ የሚያንሰፈስፍ ሚስጥራዊ መዝሙር አየዘመሩ ነው…ግቢ ውስጥ ከወዲህ ወዲያ ስትንጎራድድ ዘበኛዋ ለኦሎምፒክ እንደሚዘጋጅ አትሌት በዛ  ለሊት የስፖርት ቱታ ለብሶ ግቢው  ውስጥ  ባለ  ከፍት ቦታ ስፖርት  እየሰራ ነው….በርከት ላሉ ደቂቃዎች ቆማ ተመለከተችው…አንዴ ፑሻፕ ይሰራል፤ደግሞ ክብደት ያነሳል፤ደግሞ ቁጭ ብድግ ይላል፡፡
‹ታድለህ..››አለችና ወደውስጥ ገባች፡፡
…ቀጥታ ወደሻወር ቤት ነው ያመራችው…ሰውነቷን ታጠበች..ለመታጠብ ረጅም ሰዓት ነው የፈጀባት.. ምን አልባትም ከአንድ ሰዓት በላይ....ከዛ ልብሷን ቀየረች..የተወሰነ ሜካፕ በመጠቀም ራሷን አሰማመረችና መድሀኒቷን ወደቦርሳዋ በማስገባት መኝታ ቤቷን ለቃ ለመውጣት ዝግጁ ስትሆን ሁለት ሰዓት ከሩብ ሆኖ ነበር….ቀጥታ ወደሆስፒታል ነው የምትሄደው…እርግጥ ለቀጠሮዋ ሶስት ቀን ይቀረዋል..ግን ደግሞ ላለፉት ሶስት ቀን መድሀኒቷን  አልተጠቀመችም..ያንን ለሀኪሟ ተናግራ መፍትሄ የሚለውን እንዲነግራት ትፈልጋለች….እርግጥ ልታገኘው የፈለገችው ለዚህ ብቻ አይደለም…ከእሱ ጋር መነጋገር ሰላም እንዲሰማት ስለሚያደርጋት ነው፡፡ ፎቅ ላይ ካለው መኝታ ቤቷ ወደሳሎን ስትወርድ ፊት ለፊቷ ባለው የምግብ ጠረጴዛ በምግብ ተሞልቶ አየች…ግራ ገባት…ሞባይሏን አወጣችና ሰዓቷን መልሳ አየችው  2.20 ነው፡፡ተመላላሽ ሰራተኛዋ ከ3 ሰዓት በፊት ስትገባ  አይታት  አታውቅም  …እንደዛ አይነት ንግግርም የላቸውም
‹‹…ታዲያ አንዴት ዛሬ ልታደርገው ቻለች?››በማለት ቦርሳዋን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችና ወደኪችን ስትሄድ፤ባዶ ነው፡፡ ኪችኑ ሁሉ ነገር ፅድት ብሎ እቃዎች ሁሉ በየቦታቸው ስለተቀመጡ ከነጋ ሰው የገባበትም አይመስልም፡፡ ቀጥታ ወደምግቡ ተመለሰችና እየጣፈጣት የምትፈልገውን ያህል ከተመገበች በኃላ እጇን ተጣጥባ ቦርሳዋን ይዛ ወጣችና ቀጥታ ወደ መኪናዋ ስትሄድ ትናንት ከአሰላ ስትመጣ አልብሷት የነበረውን አቧራና ጭቃ ከላዩ ላይ ተወግዶ ፏ ብላ ፀድታለች፡፡ደስ አላት፡፡ገባችና ቁልፏን አሽከርክራ ሞተሩን ማሞቅ ጀመረች በዚህን ጊዜ  የመኪናውን ድምፅ ሰምቶ ከዘበኛ ቤት ወጣና በራፉን ከፈተላት..መኪናዋን አንቀሳቀሰችና .ስሩ.ስትደርስ.አቆመች አንገቷን በመስኮት አወጣችና..‹‹መኪናዬን ንፁህ ስላደረክልኝ አመሰግናለሁ››አለችው
‹‹አረ ችግር የለውም…ቁጭ ከምል ብዬ ነው››

‹‹ሳሎን ቁርስ አለልህ.. ግባና ብላ ››

‹‹እሺ እበላለሁ››

‹‹እሺ  ቻው›ብላ መኪናዋን አንቀሳቀሰችና  ወዲያው መልሳ አቆመችው፡፡

‹‹ይቅርታ ስምህ አይያዝልኝም››

‹‹ቀናው››

‹‹ያልተለመደ ስም ነው…ቆይ አለም መጥታ ነበረ አይደል.?ታዲያ.የት ሄደች?››
‹‹መቼ? ዛሬ ከሆነ አልመጣችም፡፡››

‹‹ታዲያ ቁርሱን ማን ነው የሰራው?››አቀረቀረ…

‹‹ምነው መልስ የለህም?››ኮስተርተር ብላ ጠየቀችው፡፡

‹‹ምነው የማይሆን ነገር ሰራሁ እንዴ?››

የምትመልሰው  ግራ  ገባት ‹‹እኔ እንጃ.. ለማንኛውም  በጣም ይጣፍጣል›› አለችውና ከመገረም ውስጥ ሳትወጣ መኪናውን አስነስታ ተፈተለከች፡፡
ከዶክተሩ ጋር ተገናኝታ ፊት ለፊት ተቀምጣለች…የሆነውን ነገር ሁሉ  ነግራው ምክር እየሰጣት ነው፡፡
ይሄውልሽ ሳባ .ይሄንን ነገር ሲሪዬስ አድርገሽ እንድትወስጂው እፈልጋለሁ››
‹‹እሺ ዶ/ር ሁለተኛ አይለመደኝም፡፡››
‹‹ቤተሰቦችሽም ሊረዱሽ ይገባል፡፡››

‹‹ቤተሰቦቼ አሰላ ነው ያሉት‹‹ያንን ማድረግ አይችሉም፡፡››

‹‹ሳባ ከእኔ በተጨማሪ በቅርብሽ ሆኖ ሁሉን ነገር እየተከታተለ ሊረዳሽ   የሚችል ሰው ማግኘት አለብሽ.››.
‹‹አይ ዶ/ር እንዲሁ እድሜ ለመግፋት ካልሆነ በስተቀር የእኔ ነገር ተስፋ.ያለው........ .አይመስለኝም…በአጠቃላይ.መኖርደክሞኛል..መጨረሻ.መዳረሻዬ.
መቃብር ቤት፤
   ከዛ  ካመለጥኩ  በሰንሰለት  ታስሬ  አማኑኤል…በጣም  እድለኛ  ከሆንኩ  ደግሞ እስር ቤት የሚሆን ይመስለኛል››

‹‹ከእንደዚህ አይነት አሉታዊ አስተሳሰቦች ራስሽን ማራቅ አለብሽ..አሉታዊ ሀሳብ ቀስ በቀስ በመጀመሪያ በአዕምሯችን ስሩን እየሰደደ ይሄዳል.. ከዛ የምናስብበትን መንገድ ይቀይራል፡፡ እኛ ደግሞ የሀሳባችን ውጤት ስለሆንን በሂደት በአላስፈላጊ መንገድ እንድንጓዝ እየቀየረን ይሄዳል፡፡ ቀድሞ የማናውቀው አይነት ሰው ከውስጣችን ይበቅላል››

    ‹‹.ይበቅላል አልክ…በቅሎ አድጓል እኮ…ብቻ ዶ/ር ሁሉ ነገር ይጨንቃል››

   እኮ የምልሽ እሱን ነው.መድሀኒቱ ብቻውን ብዙም ውጤታማ  አይሆንም፤ አንቺም በተስፋ መታገል አለብሽ፡፡ ከዚህ ውጥረት በአፋጣኝ እራስሽን ማላቀቅ አለብሽ ምን መሰለሽ ውጥረት ከቁጥጥራችን ውጭ ከወጣ ወደ ስራ ህይወታችን ይሄድና ስህተት የሆነ ውሳኔ እንድንወስን ያደርገናል፡፡ ከዛም አልፎ የቤተሰብ ህይወታችን ላይ ጫና ያሳድራል፡፡ውጥረት ያመጣብንን ችግር በወቅቱና በሰዓቱ ካልተቆጣጠርነው እዕምሯችንና አካላችንን ይቆጣጠርና የጤና ችግር ከማስከተሉም በላይ አካላዊ በሽታና አእምሮአዊ በሽታ ያስከትልብናል..በሂደትም ለባህሪ ለውጥ ይዳርገናል፡፡ የባህሪ ለውጥ ማለት ደግሞ የምናስብበት መንገድ ነገሮችን የምናይበትና የምንመዝንበት ሚዛን እየተቀየረና እየተዛባ ይሄዳል ማለት ነው፡፡ ያ ደግሞ በውሳኔያችን ላይ ለውጥ ያመጣል፡፡ በስተመጨረሻም የሕይወታችንን መስመር ሙሉ ለሙሉ የመቀየር አቅም ይኖረዋል፡፡ስለዚህ በአእምሮችን ላይ የሚከሰት ማንኛውንም ውጥረት በጊዜና በሰአቱ ማከም ይጠበቅብናል፡፡ ለዛ ነው የምጨቀጭቅሽ››

‹‹እሺ ዶ/ር እሞክራለሁ..ማለቴ ለጤናዬ እፋለማለሁ››

አዎ እንደዛ ማድረግ አለብሽ…አየሽ ራሳችን ከውስጣችን ጋር ስናጣምር ህይወት ምን ያህል ንፁህ በደስታ የተሞላችና ህመም አልባ እንደሆነች  እንረዳለን፡፡ለአዕምሯችን ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ብናቀርብለት ያለማቅማማት መልስ ይሰጠናል፡፡ ጥያቄው ብዛትም ሆነ ክብደት ችግር የለውም ብቻ ሁሌ መልስ አያጣም፡፡ ችግሩ መልሱ ትክክል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል..ስለዚህ እኛም ራሳችንን የምንጠይቅበት ሆነ ሌሎች የሚጠይቁንን ጥያቄዎች  መጠንቀቅ አለብን፡፡ ምክንያቱም አዕምሯችን የሚሰጠን መልስ በምናቀርብለት የጥያቄ ይዘት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለምሳሌ ይህች ሀገር ወዴት እየሄደች ነው? የሚል ጥያቄ ለአዕምሯችን ቢቀርብለት ቀድሞ የሚመጣለት መልስ ስለጦርነት፤ስለኑሮ ውድነትና፤መሰል ነገሮች ነው...መልሱም በዛ ዙሪያ የሚሽከረከር ነው የሚሆነው፡፡ በተለየ መንገድ ደግሞ ኢትዬጵያ ላንቺ ምንሽ ነች? ቢሆን ጥያቄው...ስለውበቷ፤ ስለ