አትሮኖስ
228K subscribers
104 photos
3 videos
41 files
303 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ዘጠኝ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...ወንበር ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠና እግሩን ወፍራሙና ክብ የሆነው የወንበሩ መደገፊያ ላይ አድርጎ የሚያነበው መፅሀፍ ከፈተ፡ እኔም ብቸኛው ባዶ አልጋ ላይ ጋደም ብዬ ስለ ንጉስ አርተር ማንበብ ጀመርኩ። አመናችሁም
አላመናችሁ ከዚህ በፊት መኖሩን የማላውቀው በር ተከፈተልኝ እጅግ ውብ አለም ጀብደኝነት ያለበት፣ ፆታዊ ፍቅር ያለበትና ስርዓት ያላቸው ሴቶች እንደምሰሶ ቆመው ከሩቅ የሚመለኩባት ናት። ለእኔ የመካከለኛው ዘመን የፍቅር ግንኙነት የተጀመረው የዚያን ቀን ነው። ከሁሉም በላይ ብዙ
የባሌት ዳንሰኞች መሰረታቸው ተረት ነው፣ አይደል? ሁሉም ተረቶች ደግሞ በመካከለኛው ዘመን ካሉ ተረትና ምሳሌዎች አይደል የመጡት።

እኔ ሁልጊዜ ተረት ላይ ያሉ አስማተኛ ፍጡራን ሳር ላይ ሲደንሱ ማየት የምፈልግ ልጅ ነኝ፡ በጠንቋዮች፣ በድግምት፣ በአስማት፣ በጭራቅ ማመን
እፈልግ ነበር፡ አስማቶች ሁሉ በሳይንሳዊ ማብራሪያ ከአለም ላይ እንዲጠፉ አልፈልግም: የዚያን ጊዜ ግን በጠንቋይና በጭራቅ በሚተዳደር ጠንካራና
ጨለማ ቤተመንግስት ውስጥ ለመኖር እንደምመጣ አላውቅም ነበር አንዳንድ የሰለጠነው ዘመን ጠንቋዮች ድግምት ለመስራት ገንዘብ ይጠቀማሉ ብዬ ገምቼም አላውቅም።

የቀኑ ብርሃን ከከባድ መጋረጃዎቹ ጀርባ ሲሸሽ ትንሽዋ ጠረጴዛችን ላይ ለእራት ተቀመጥን፡፡ እኔና ክሪስ ቀዘቀዘም አልቀዘቀዘም ምግባችንን እንበላለን። መንትዮቹ ግን ገና ምግባቸውን ሲያዩት ሁልጊዜ አይጣፍጥም
ብለው ይነጫነጫሉ ኬሪ የምትነጫነጭ ባይሆን ኖሮ ኮሪ የተሻለ ይመገብ እንደነበር ይሰማኛል።

“ብርቱካኖቹ የሚያስቅ መልክ ነው ያላቸው" አለ ክሪስ ብርቱካን እንድልጥ እየሰጠኝ፡ “ፈሳሽ የፀሀይ ብርሀን ናቸው":: አሁን ትክክለኛ ነገር ተናገረ።
መንትዮቹ በደስታ ሊበሉት የሚችሉት ነገር አገኙ: “ፈሳሽ የፀሀይ ብርሀን”።

አሁን መሽቷል። ክፍሉ ግን ቀን ከነበረው የተለየ አልሆነም አራቱንም መብራቶች አበራናቸው፡፡ እናታችን ይዛት የመጣችውን ትንሽዬ የራስጌ
መብራት ደግሞ ጨለማ ለማይወዱት መንትዮች አደረግንላቸው:ከእንቅልፋቸው ሲነቁ እንደገና ንፁህ ልብስ አልብሰን ፀጉራቸውን አበጥረንና
ፊታቸውን አጥበን እንቆቅልሽ እንዲጫወቱ ወለሉ ላይ አስቀመጥናቸው በጣም ቆንጆ ሆነው ነበር። ምስል የመገጣጠሙን እንቆቅልሽ ለእነሱ አዲስ ስላልነበር የትኛው የቱጋ እንደሚገጠም ማወቅ ቀላል ሆኖላቸው ነበር በውድድር መልክ እንዲያደርጉት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰላቹ ከዚያ አልጋ
ላይ አስቀመጥናቸውና ራሳችን የፈጠርናቸውን ታሪኮች እንነግራቸው ጀመር
ያም አሰለቻቸው እኔና ወንድሜ ምን ማድረግ እንዳለብን አላወቅንም: ቀጥሎ ክሪስ ከሻንጣ ውስጥ የመጫወቻ መኪናዎች አወጣና እየገፉ እንዲጫወቱ ነገራቸው።
በጠረጴዛው ስር በአልጋው ስር እየገቡ እንደገና እስኪቆሽሹ ድረስ መጫወት ጀመሩ።

ሲደክመን ክሪስ ቼከርስ እንድንጫወት ሀሳብ አቀረበና መንትዮቹ የብርቱካን
ልጣጮቹን በመኪናቸው ጭነው ወስደው ፍሎሪዳ ላይ እየደፉ ነበር። ያም ጥግ ላይ የተቀመጠው የቆሻሻ ቅርጫት ነበር።

“በቀያዮቹ መጠቀም ትችያለሽ እኔ እንዳንቺ ጥቁር ተሸናፊ ቀለም ነው ብዬ አላምንም” አለ ግንባሬን አጨፈገግኩት በቀንና በማታው መካከል ዘለአለም የሚመስል
ጊዜ አልፏል፤ ይህም እንደገና እንዳልመለስ አድርጎ ለውጦኛል። “ቼከርስ መጫወት አልፈልግም” አልኩት።

ሊመጣ ካለ ነገር ፍራቻና ውስጤን ከሚያሰቃዩኝ ጥርጣሬዎች ለመገላገል
እናታችን ሁሉንም እውነት ብትነግረን ኖሮ የሚለውን ማለቂያ የሌለውን ፀሀሳቤን ተውኩት ነገር ግን አራታችንም እናታችን እንድትመጣ እየጠበቅን
ሳለ ሀሳቦቼ ያልዳሰሱት ቦታ አልነበረም: አብዛኛው ፍራቻዬ እሳት፣ ጣዕረሞትና ሌሎች ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ውስጥ ያሉ አስፈሪ ነገሮች ነበሩ። ከሁሉም በላይ ትልቁ ፍራቻዬ በተቆለፈ ክፍል ውስጥ ሊነሳ የሚችል እሳት ነበር።

ጊዜው በዝግታ አለፈ ክሪስ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ እያነበበ አልፎ አልፎ ሰዓቱን ይመለከታል፡ መንትዮቹ የብርቱካን ልጣጮቻቸውን እያመላለሱ
መጫወት ሰለቻቸው:
ሲኦልንና በሲኦል ያሉ ቅጣቶችን የሚያመለክተውን ስዕል ስመለከት አያታችን ምን ያህል ብልጥና ጨካኝ እንደሆነች እያሰብኩ ነበር ለምንድነው ስለ ሁሉ ነገር ማሰብ ያለባት? እግዚአብሔርም ራሱ ውጪ ስንትና ስንት መጥፎ
ነገሮች የሚሰሩ እያሉ ተቆጣጣሪ አይኖቹን በአራት ትንንሽ ልጆች ላይ ማድረጉ ፍትሀዊ አይደለም እኔ በእግዚአብሔር ቦታ ብሆን ኖሮ ሁሉንም ነገር ማየት የምችል ከመሆኔ አንፃር፣ የተቆለፈባቸውን አባት የሌላቸውን አራት ህፃናት በመቆጣጠር ጊዜዬን ከማጠፋ ሌላ በጣም የሚያዝናና ነገር ላይ
ትኩረት አደርግ ነበር በዛ ላይ አባታችን ያለው እዛው ከእግዚአብሔር ጋር ስለሆነ፣ እግዚአብሔር በደንብ እንዲንከባከበንና አንዳንድ ስህተቶቻችንን አይቶ እንዲያልፍ ሊነግረው ያስፈልጋል።

ክሪስ አኩራፊና ተቃዋሚነቴን ችላ ብሎ መፅሀፉን አስቀመጠና የመጫወቻውን ሳጥን አነሳ፡

“ምን ሆነሻል?” ሲል ጠየቀኝና የመጫዎቻውን ሠሌዳ ዘርግቶ ጥቁሩን በጥቁሩ፣ ቀዩን በቀዩ መደርደር ጀመረ፡ “ለምንድነው ፀጥ ብለሽ የተቀመጥሽው?
ለምንድነው የፈራሽ የመሰልሽው? እንደገና እንዳላሸንፍሽ ነው?”

ስለ እሳት ያሰብኩትን ለክሪስ ነገርኩት ከዚያ ልክ የድሮ ፊልም ላይ እንዳየሁት ከእሳቱ ለማምለጥ መሬት ላይ እንዲያደርሰን አንሶላውን ተልትለንና ቋጥረን
እንደመሰላል መስራት እንደምንችል አወራሁት “ምናልባትም ዛሬ ማታ እሳት ከተነሳ መስኮቱን ከስበርን በኋላ መሬት የምንደርስበት መንገድ ይኖረናል ማለት ነው እና እያንዳንዳችን መንትዮቹን አንድ አንድ ተካፍለን ጀርባችን ላይ
እናስራቸዋለን” አልኩት።

ሰማያዊ አይኖቹ በአድናቆት በሩ እንደዚህ አይነት አክብሮት ሲያሳዩኝ አይቼ አላውቅም፡ “ዋው ካቲ እንዴት የሚገርም ሀሳብ ነው! አስደናቂ ነው! ልክ ነሽ እሳት ቢነሳ ማድረግ ያለብን አሁን እንዳልሽው ነው ግን አይነሳም ከአሁን
በኋላ አልቃሻ ህፃን አለመሆንሽን ማወቄ በጣም ጥሩ ነው ስለ ወደፊት አስብሽ ሳይጠበቅ ለሚመጣ ነገር እቅድ ካወጣሽ አድገሻል ማለት ነው እናም
ወድጄዋለሁ” አለኝ።

ከአስራ ሁለት አመታት ከባድ ሙከራ በኋላ፣ ማግኘት ይቻላል ብዬ የማላምነውን የክሪስን አድናቆትና ማረጋገጫ የማግኘት ግቤን በመጨረሻ አሳካሁ በዚያች ደቂቃ በተለዋወጥናቸው ፈገግታዎች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ አብረን መዝለቅ እንደምንችል ቃል ገባን።

እናታችን እንግዳ ገፅታ ተላብሳ በሚያስቅ ሁኔታ እየተራመደች ወደ ክፍሉ መጣች መምጣቷን ለረጅም ሠዓታት እየጠበቅን የነበረ ቢሆንም፣ እንደገና
ከእሷ ጋር መሆናችን ግን የገመትነውን ያህል ደስታ አልሰጠንም ምናልባት
አብራት ተከትላ የመጣችው አያታችን በክፉ ግራጫ አይኖቿ ስትመለከተን ጉጉታችንን ገድላው ይሆናል።

አንድ ልክ ያልሆነ ነገር ተፈጥሯል፡ ምን ይሆን? ክሪስና እኔ አልጋ ላይ
ተቀምጠን ቼከርስ ስንጫወት የአልጋ ልብሱን በማጨማደድ የሰራነው ጥፋት የአያትየውን እይታ ስቧል።

አንድ ህግ ተጥሷል አይ ሁለት... መተያየትም የአልጋ ልብሱን እንደማጨማደድ ሁሉ የተከለከለ ነው።

መንትዮቹ ደግሞ ሲጫወቱ የነበረው የመገጣጠም እንቆቅልሽ እዚህና እዚያ
ተበታትኗል፡ የመጫወቻ መኪናዎቻቸውም በየቦታው ተዝረክርከዋል ክፍሉ ንፁህ አልነበረም

ሶስት ህጎች ተጥሰዋል።
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


የጀርመንን ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ለማሳሳት በርካታ ትላልቅ ብርማ
ቀለም ፊኛዎች ሰማዩ ላይ ያንዣብባሉ፡ ሱቆችና የመንግስት ህንፃዎች
ከቦምብ ናዳ ለመጠበቅ በአሸዋ በተሞሉ ጆንያዎች ዙሪያቸውን ተከበዋል፡
በየመናፈሻው የቦምብ
መከላከያ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም ሰው በእጁ የጋዝ
ጭስ መከላከያ ጭምብል አንጠልጥሏል ሰዎች በማንኛውም ደቂቃ በቦምብ
ናዳ እንደሚያልቁ ያስባሉ፡፡

ሄሪ ስለ አንደኛው የአለም ጦርነት ምንም ትዝታ የለውም፡ ጦርነቱ
ሲያልቅ የሁለት አመት እምቦቃቅላ ነበር፡፡ ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ጦርነት
ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ አወቀ፡፡ በኋላም ፋሺስቶች በለንደን መንገዶች
ያደረጉትን ወታደራዊ ሰልፍ አዛውንት ይሁዳውያን በፍርሃት ሲመለከቱ
ሲያይ የጦርነትን አስፈላጊነት ተረዳ፡ሆኖም ሂትለር ሶቭየት ህብረትን
ይደመስስልኛል ብሎ የአንግሊዝ መንግስት የሆነውን ሁሉ እንዳላየ ሲያልፍ ጥላቻው ነገሰ፡፡

ሄሪ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ቤቱ መሄድ እንደሌለበት ወስኗል።
ፖሊሶች በዋስ በመለቀቁ ስለተበሳጩ በማንኛውም አጋጣሚ ሊያስሩት
አቆብቁበዋል፡፡ ለትንሽ ጊዜ መደበቅ ያዋጣዋል፡፡ ተመልሶ እስር ቤት መግባት
አይፈልግም፡፡ ታዲያ ስንት ጊዜ ፖሊስ መጣ እያለ ሲበረግግ ሊኖር ነው?
ሁልጊዜስ ፖሊስን መሽወድ ይቻላል? ካልሆነስ ምን ማድረግ ይኖርበታል?

እናቱ በሃዘን ፊታቸው ጠቁሯል፡ ገንዘብ እንዴት እንደሚያገኝ ቢያውቁም አንስተውበት አያውቁም፡፡ ‹‹በእናትነቴ ምንም አድርጌልህ አላውቅም›› አሉት ‹‹እማማ ያለሽን አድርገሽልኛል›› ሲል መለሰላቸው፡፡

‹ሃሰት፤ ምንም አላደረኩልህም፤ ለዚህ አይደለም መስረቅህ››
ሄሪ ለዚህ መልስ አጣ፡፡

ከአውቶብስ እንደወረዱ ጋዜጣ ሻጩ በርኒን እናቱን በስልክ ስለጠራለት
እንደውለታ ቆጥሮት ጋዜጣ ገዛው፡፡ የጋዜጣው የፊት ሽፋን ጀርመን ፖላንድን በቦምብ ደበደበች ይላል፡ ወዲያውም አንድ ፖሊስ በብስክሌት ሲመጣ ተመልክቶ በደመነፍስ ተርበተበተ፡፡ እግሬ አውጪኝ ሊል ሲያስብ ሰው ለማሰር ሁለት ሆነው የሚመጡ መሆኑን ሲያውቅ አደብ ገዛ፡፡

እንደዚህ እየሰጋሁማ እንዴት እኖራለሁ› ሲል አስበ፡፡

እቤት ሲገባ እናቱ ሻይ ጥደው ‹‹ሰማያዊ ሱፍ ልብስህን ተኩሼልሃለሁ፤ መለወጥ ትችላለህ›› አሉት

እስካሁንም ልብሱን የሚያጥቡለትና የሚያዘገጃጁለት ካልሲውንም የሚሰፉለት እናቱ ናቸው፡፡ ሄሪ መኝታ ቤት ገባና ከአልጋው ስር ሻንጣውንዐአውጥቶ ገንዘቡን ቆጠረ፡፡ ሁለት ዓመት በስርቆት ተሰማርቶ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ፓውንድ አጠራቅሟል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት እጁ ገብቷል በሃሳብ ተውጦ ፓስፖርቱን እያገላበጠ ተመለከተው፡፡ ከአንድ አሜሪካዊ ላይ እንደመነተፈው አስታወሰ፡ የሰውየው ስም ሃሮልድ መሆኑን ሰውየውም
እሱን እንደሚመስል ተገነዘበና ኪሱ ከተተው፡

የአሜሪካውያንን የአነጋገር
ቅላጼ ይችላል፡፡ በአሜሪካ ውስጥ የእንግሊዛውያን የአነጋገር ቅላጼ ካለህ የከበርቴ መደብ አባል እንደሆንክ ተደርጎ ይቆጠራል፡ አሜሪካ ውስጥ በርካታ በፍቅር ልታሳብዳቸው የምትችላቸው ኮረዶች አሉ፡፡

እንግሊዝ ውስጥ የሚቀርበት እስር ቤትና ውትድርና ብቻ ነው፡፡
አሁን ፓስፖርትና ኪሱ ሙሉ ገንዘብ አለው፡ እናቱ ቁም ሳጥን ውስጥ ንፁህ ሱፍ ልብስ ያለው ሲሆን አንድ ሁለት ሸሚዝ መግዛት ይችላል።

ከሳውዝ ሃምፕተን 75 ማይል ነው የሚርቀው

ዛሬውኑ መሄድ ይችላል።

ሁሉም ነገር እንደ ህልም መሰስ ይላል።

እናቱ ‹‹ሄሪ ሳንድዊች ትፈልጋለህ?›› ሲሉ ጠየቁት

‹‹እሺ እማ››

ኩሽና ሄዶ ተቀመጠ፤ እናቱ ሳንድዊቹን ፊቱ ቢያደርጉለትም ንክች
አላደረገውም፡፡‹‹እማ አሜሪካ እንሂድ›› አላቸው
እናቱ በሳቅ ፈነዱ ‹‹እኔ አሜሪካ?!››
‹‹እውነቴን ነው፡ እኔ ልሄድ ነው፡››
አሁን ፈገግታቸው ጠፋ ‹‹ለኔ አይሆንም ልጄ፡፡ በዚህ እድሜዬ ስደት
ለኔ አይሆንም››

‹‹እዚህ እኮ ጦርነት ሊጀመር ነው፡፡››

‹‹አንድ ጦርነት፣ የስራ ማቆም አድማና የኢኮኖሚ መዳሸቅ አሳልፌያለሁ፡››

ጠባብዋን ማድቤት አማተሩና ‹‹የኔ ዓለም ይሄ ነው›› አሉ።

ሄሪ እናቱ በዚህ እንደማይስማሙ ቢያውቅም ቁርጡን ሲነግሩት ተስፋው ተሟጠጠ፡፡

በዚህ አለም ላይ ያሉት እናቱ ብቻ ናቸው፡፡

‹‹እዚያስ ምን ልትሰራ አስበሃል?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡

‹‹የሌብነት ስራዬ ያሳስብሻል?››

‹‹ሌብነት የትም አያደርስም፡ በሌብነት ያለፈለት ሰው አላውቅም›› አሉት፡፡

‹‹እዚያ አየር ኃይል ገብቼ አብራሪ መሆን እፈልጋለሁ፡ አሜሪካ ውስጥ ጭንቅላት ካለሽ የሰራተኛው መደብ ብትሆኝም ግድ የላቸውም።››

እናቱ በመጠኑ ፈገግ አሉ፡ እሳቸው ሻይ ሲጠጡ እሱ ሳንድዊቹን ይገምጣል።

በልቶ እንደጨረሰ ገንዘቡን ከኪሱ አወጣና ሃምሳ ፓውንድ ቆጥሮ ለየ
‹‹ይሄ ለምንድን ነው?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡ ይህ ገንዘብ ሁለት አመት ልብስ አጥበው የሚከፈላቸውን ገንዘብ ያክላል

‹‹ይጠቅምሻል እማ ውሰጂው›› አለ፡፡

እናቱ ገንዘቡን ተቀበሉና

‹‹እውነት ልትሄድ ነው?›› ሲሉ ጠየቁት።

‹‹ወደ ሳውዝ ሃምፕተን በሞተር ሳይክል እሄድና መርከብ ላይ እሳፈራለሁ»
እጃቸውን ሰደዱና የልጃቸውን እጅ ለቀም አደረጉ፡፡ ‹‹ልጄ መልካም
ዕድል ይግጠምህ፡››

እሱም የእናቱን እጅ ጨበጥ አደረገና ‹‹ከአሜሪካ ገንዘብ እልክልሻለሁ አለ።

‹‹አያስፈልግም፡፡ ከዚያ ደብዳቤ ቶሎ ቶሎ ስደድልኝና ጤንነትህን
ልወቅ፡፡››

‹‹እሺ እፅፍልሻለሁ፡››

አይናቸው በእንባ ተቆረዘዘ ‹‹አንድ ቀን ናና አሮጊት እናትህን እያት››

እጃቸውን ጨበጥ አደረገ፡፡ ‹‹እመጣለሁ እንጂ እማ፡፡ እመለሳለሁ፡››
ሄሪ በመስታወት ከላይ እስከ ታች ራሱን አየ፡፡

ሰማያዊው ሱፍ ልብስ ያማረበት ሲሆን ከሰማያዊው የአይኑ ቀለም ጋ ሄዷል፡፡

ሸሚዙ የአሜሪካ ሽሚዝ ይመስላል፡ ፁጉር አስተካካዩ የባለ ሁለት
ደረት ኪስ ኮቱን ትከሻ በቡሩሽ ሲጠርግለት ሄሪ ጉርሻ ሰጠውና ወጣ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሳውዝ ሃምፕተን ወደብ በሰው ተጥለቅልቋል። ከዚህ ቦታ ነው የአትላንቲክ አቋራጭ ጉዞ የሚነሳው፡፡ በመሆኑም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች
ከእንግሊዝ ለመውጣት ይተራመሳሉ፡፡

ሄሪ መርከብ ለማግኘት ሲጠያይቅ የሁሉም መርከቦች ቦታ ለመጪዎቹ
ሳምንታት ጉዞ አስቀድመው እንደተያዙ አወቀ፡ አንዳንዶቹ የመርከብ ትራንስፖርት ድርጅቶች ባዶ ቢሮ ታቅፈው ለሰራተኛ ደመወዝ ከመክፈል በራቸውን ዘግተዋል፡ ለተወሰነ ጊዜ ምንም ቦታ የማይገኝ መሰለው።

በመርከብ መሄዱን ትቶ ሌላ አማራጭ መጓጓዣ ሲያፈላልግ አንድ የጉዞ ወኪል ባህር ላይ የሚያርፍና ከባህር ላይ የሚነሳ የፓን አሜሪካን
አውሮፕላንን እንዳለ
አበሰረው፡፡ ስለዚህ አይሮፕላን በየጋዜጣው ላይ
አንብቧል፡ መርከብ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ለመሄድ አራትና አምስት ቀን
የሚፈጅበት ሲሆን አይሮፕላኑ ከ30 ሰዓት ባነሰ ይደርሳል፡ ታዲያ የአንድ
ጊዜ ጉዞ ትኬት ዋጋ 90 ፓውንድ አዲስ መኪና ይገዛል።

ሄሪ በርካታ ገንዘብ አባክኗል፡፡ እብደት ነው፡፡ ታዲያ ከአገር ለመውጣት
ሲል የፈለገውን ያህል ዋጋም ቢሆን ለመክፈል ወስኗል፡፡ አይሮፕላኑ ምቾቱ
ያጓጓል፡ ኒውዮርክ እስክትደርስ ድረስ ሻምፓኝ መጨለጥ ነው፡፡ እንዲህ
አይነት ቅንጦት ደግሞ ለሄሪ ነፍሱ ነው፡፡

ፖሊስ ባየ ቁጥር መደንበሩ ሊቀር ነው፡፡ ሳውዝ ሃምፕተን ውስጥ
ደግሞ ስለ እሱ ሌብነት የሚያውቅ ፖሊስ የለም፡፡ ከዚህ ቀደም በአይሮፕላን
በርሮ ስለማያውቅ ግን አዕምሮው ተረብሿል፡፡

ሰዓቱን አየ፤ከቤተመንግሥት አንጋች ላይ የመነተፈው ነው፡፡
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የሐመር ዕጽዋት ለምልመው፣ ንቦች ከአበባ ወደ አበባ እየተዘዋወሩና እየዘመሩ ሲቀስሙ፣ ከብቶች ጨሌ ሳራቸውን እያመነዠኩ ሲያገሱ፣ እንቦሶች ቃጭላቸውን እያቅጨለጨሉ ሲቦርቁ፣
ልጃገረዶችም ማሳውን እያረሱ ሲያዜሙ፣ ልጆች እራቁታቸውን ሆነው በቀስት ጫካ ለጫካ ተሪ ለመግደል ሲሯሯጡ በሚውሉበት፣
ጎረምሶች ሹልሹላ፣ ሹርባ...ጸጕራቸውን እየተሠሩ «አኖ» በተባለው አፈር ሰውነታቸውን በማዥጐርጐር ለማታው ጭፈራና ድሪያ ሲዘጋጁ፣ የብልታቸውን ጸጕር እየተላጩ በመኸር ጊዜ የሚዘፍኑትን ዘፈን ሲያዜሙ በሚውሉበትና ሐመር የክቱን የተፈጥሮ ሕይወት
ለብሳ ኗሪዎቿን በምታስፈነጥዝበት ወቅት ድንገተኛ ሁኔታ ታየ።

ካርለት አልፈርድ ሰቀላ ቤት አሠርታ መኖር ከጀመረች ዘጠኝ ወር አለፋት። ከሷ በስተግራ ከሃያ ሜትር ላይ የከሎ ክብ ጎጆ አለ።
በግቢያቸው የዱር አበባ፣ ቦዬ፣ ጉደሬ በቅሏል። ከነሱ ግቢ ራቅ ብሎ አለፍ አለፍ በማለት የሐመሮች መኖሪያ ይታያል። ካርለት ቤቷ ሆና
ፀሐይ ስትወጣ ከፊት ለፊት፣ ስትገባ ደግሞ ከበስተኋላ ሆና ልታያት
ትችላለች"

በእርግጥ በፖስት ካርድ ፀሐይ ስትወጣና ስትገባ አስደናቂ ፎቶዎችን ተመልክታለች። ሕይወት ያላት የሐመሯ ፀሐይ ግን ምሽት ላይ በተለያዩ ቀለማት ተውባ እንደ ዕንቁ እያንፀባረቀች አካባቢውን
ቀይ፣ ቢጫ ሐምራዊ ድብልቅልቅ ቀለማትን ስትለዋውጥ ስታያት
ግን በሕይወቷ ካየችው ውብ ነገር ይልቅ፣ በሐሳቧ የቀረፀችው የገነት
ውበት ይታያታል።

ታዲያ፣ በጣም ተመስጣ የአካባቢውን ውበት ስትመለከት ውበትን በትክክል ለማስቀመጥ፣ መጨመር የምትፈልገውንም
ጨምራ ለመርካት፣ ከአንትሮፖሎጂስትነቷ ይልቅ ባለቅኔ ወይንም
ሠዓሊ መሆን ያምራታል
ካርለት ያጣችው ነገር የለም አይባል" የዋና ቦታ አላገኘችም ኑሮዋ ዘመናዊ አይደለም" ያም ሆኖ ግን በሚያውዳት የተፈጥሮ
መዓዛ፣በስሜት በምትውረገረገው የምሽት ጭፈራ፣ ባየችውና
በቀረበችው ቍጥር ጥልቅ እሳቤን የሚጠይቃት የተፈጥሮ ምሥጢር፣ በንጹሕ ሕሊና የምታነባቸው መጻሕፍት የደስታ ሚዛኗን
ይጠብቁላታል።

አሸጋግራ የምታየው የሐመር ሰንሰለታማ ተራራ፣ መሸት ሲል ከየዋሉበት ብቅ ብቅ የሚሉት ሰዎችና እንስሳት፣ ስታንቀላፋ
የዋለችው መንደር፣ ሞቅ ሞቅ ደመቅ ስትል፣ ሁሉም ከፀሐይ ውበት ጋር ውሕደት፣ ቅንብር ሲፈጥሩ ስሜቷ ይረካል» እንዲያውም ከዚህ
ለየት ላለ ያልተበረዘ ተፈጥሮ ያላት ፍቅር «ምነው እናቴ፣ ወንድሜ፣ እኅቴና ስቲቭ ይህን ባዩ» ብላ፣ ቅን ሐሳብ እንድታልም
ያደርጋታል"

አንድ ቀን ግን፣ የተለመደ ትርዒቷን ስትመለከት፣ በግምት የአሥራ አምስት ዓመት ልጃገረድ፣ ከጥቁር ፍየል ለፍቶ የተሠራውን
ቆዳ ዙሪያዋን በነሐስና ጨሊ አስጊጣ ለብሳ፣ አንገቷ ላይ በደረደረችው ጨሌ ራሷን አሰማምራ፣ ዳሌዋንና ቀጥ ብለው ግጥም ያሉ ማራኪ የእግር ቅርፅዋን ስታይ ካርለት አፏን በአድናቆት ከፈተች
«በእርግጥ በጣም ቆንጆና ለየት ያለች ነች መቼም አይቻት እንደማላውቅ እርግጠኛ ነኝ» እያለች በባለ ሌንሱ ካሜራዋ ደጋግማ
ከርቀት አነሣቻት" ልጃገረዷ ካለምንም ሥጋት ወደ ካርለት ሰቀላ ቀርባ ሰላም ብላ ካርለትን ቆም ብላ ካየቻት በኋላ ጸጕሯን በጣቶቿ እሷም በተራዋ እየነካካች አድናቆቷን በሣቋ ገልጣ ልትሄድ ስትል
ካርለት «ወይ አምላኪ፣ አምላኬ! ኧረ ጥርሶቿስ እንዴት ያምራሉ!» አለችና እንድትቀመጥ ጋበዘቻት" ልጃገረዷ ግን፣ ካርለትን የቤት ውስጥ ሁኔታ አንገቷን አስገብታ ቃኝታ በድጋሜ
ፈገግ ብላ፣ «ደህና ሁኝልኝ» ብላ ሄደች"

ከሎ ሆራ የሐመሯን ውብ ቀደም አድርጎ ይመለከታት ነበርና ውበቷ ደንቆታል" በተለይ ወደ እሱ ቤት አቅጣጫ ስትመጣ ልቡ
መዝለል፣ ሐሳቡ መተረማመሱን ጨመረ። ከሎ ሆራ እስh ዛሬ
ታይቶበት የማያውቅ መርበትበትና ድንጋጤ ታየበት"

ልጃገረዷ፣ «ደህና ዋልህ» ብላው፣ ከተከፈተው የጎጆ ቤት መስኮት ላይ ተንጠልጥላ ስታይ እግሮቿ፣ ጭኗ፣ ዳሌዋና የሚሳበው
| ወገቧ ከሎን በሲቃ አፈኑት። ልጃገረዷ፣ የሚተኛበትን መኝታና
ዕቃዎቹን ተመልhታ ስትወጣ የሱም ልብ አብሮ ተከተላት እሷ እንደምታውቀው በማንኛውም የሐመር ቤት የሚገኝ ለመተኛ ቁርበት፣ ለመመገቢያና ለመጠጫ ሾርቃ (ከቅል የተሠራ)
እንስራ (ለሸፈሮ ቡና ማፍያ) ነው" ከነጯ ቤትና እንደ ሐመሮች መልክ ያለውና ጨርቅ ለባሹ ቤት ግን አይታው የማታውቀው ዕቃ
አለ" በኮተቱ ብዛት ትገረም እንጂ አልተደነቀችም“ እንዲያውም ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑት ቁርበት፣ ሾርቃ፣ እንስራ ቤታቸው
ውስጥ ባለመኖሩ ተደንቃለች።

ከሎ ቤቱ በር ፊት ለፊት ሆኖ ጠበቃት በሐመር ባህል ደንብ ልጃገረድ ከቡር ናት ካለፍላጎቷና ሳያግባባ መታገል የውርደት
ውርደትና ነውር ነው" ልጃገረድ እንደሚሰበር ዕቃ የሚጠነቀቁላት፣ እንደ ሕፃን ልጅ ፍላጎቷን የሚያከብሩላት መሆን ይገባል"ልጃገረድ የምትፈልገውን ወንድ ቀጠሮ ትሰጠዋለች" ያውም
ከተመቻት ነው" ካለበለዚያ፣ ካለ እሷ ትብብር አፈቀርኩ፣ ወደድኩ፣ በዚህ ወጥቶ በዚያ ወርዶ፣ ምን ሲባል ያን አይተሽ፣ እያሉ መሟዘዝ በባህሉ አይታወቅም
በሐመር ማኅበረሰብ ልጃገረድ ቀሳሚ ንብ፣ ወንዶች አበባ ናቸው" ባል ካገባች በኋላ ግን ሴት የባል ዕቃና ንብረት ናት።

ስለዚህ ልጃገረዷ ካለፍላጎቷ የሚደርስባት ችግር እንደሌለ
ስለምታውቅ ከሎን አልፈራችውም ከሎ ሆራ ግን ድንገት «እጅ ወደ ላይ» እንደተባለ ሰው ደንዝዟል" ካርለት የሁለቱን ሁኔታ
ከርቀት በጕጕት ትመለከታለች" ልጃገረዷ ሰላምታ አቅርባለት
መንገዷን ሰትቀጥል፣ ከሎ በባህሉ ኰራ ብሎ መታየት ሲገባው ተርበተበተ"

ሰንበት ብሎ ሲያስበው ራሱን ቢታዘብም በሕይወቱ በጣም አደገኛ ወጥመድ ላይ የወደቀበት ጊዜ ያ መሆኑን ራሱ ለራሱ አመነ"
ልጃገረዷ ግን ዳግመኛ ወደ መንደሩ አልተመለሰችም።

ሆኖም ከሎ፣ «ከየትኛው መንደር ይሆን የመጣችው? እጮኛ አላት ይሆን?» እያለ፣ በሐሳቡ መዋለሉ አልቀረም።

«...የሐመር ወንዶች ቢያፈቅሩም ፍቅራቸውን በግልጽ ማሳየት
ነውር ነው። ቢሆንም ልጃገረድን መዳራት ነውርነት የለውም» ብሎ፣
ከሎ የነገራትን ካረለት አስታወሰች"

ከሎ ሲቆዝምና ሐሳብ ሲያበዛ፣ ካርለት በፍቅር ሰመመን መዋጡን በመረዳቷ፥ «ከሎ ያችን ልጃገረድ እውን አፍቅሮ ይሆን? ፍቅሩንስ በምን መልክ ይገልጽ ይሆን? ባህላዊውን ወይስ ዘመን
አመጣሹን ይሆን የሚጠቀመው? ኧረ ኅብረተሰቡስ ምን ይሰማው
ይሆን?» በማለት፣ ካርለት በጥንቃቄና በተመስጦ ማሰቧን ቀጠለች።

«ምን ዓይነት ድንቅ ነገር ነው!» ሁሉም ነገር ምሥጢር ሆኖባት
ተገረመች። ስሜት ረቂቅ ነው፤ አይጨበጥም። ስሜት በአካባቢ ላይ
ተፅዕኖ ቢኖረውም፣ አካባቢም በስሜት ላይ ጫናው ከባድ ነው"
ማፍቀርና መፈቀር ተፈጥሯዊ ነውና ማንም ከዚህ ስበት ሊያመልጥ
አይችልም" ችግሩ ከፍቅር ቀጥሉ ግንኙነቱ በምን መልክ መሆን ይኖርበታል ነው። እኒህ ሁለት ሥረ ግንዳቸው አንድ የሆኑ፣ አካባቢያቸው ግን ለውጥ ያለው ሰዎች እውነት እንዳሰቡት ቢፋቀሩስ?»

አዲሱን ምርምሯን በተለያዩ መንገዶች ተጠቅማ ማወቅ
ይኖርባታል" «ከሎ ከልጃገረዷ ጋር ፍቅር ቢይዘው ልብስ በመልበሱ
ትንቀው ትችል ይሆን? አውሬ ወይንም የጎሳው ጠላት የሆነውን ሰው አልገደለም ከብት የለውም ስለዚህ ዘመናዊዋም ሆነች ቆዳ ለባሿ ሴት ክብርና ዝናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈላጊ ስለሆነች
ላትቀርበው ትችላለች"»

«ከሎም ቢሆን ልጃገረዷን ለማግባት ኡክሊ ሆኖ በየዘመዶቹ መዞር፣ ከብት መዝለልና ለኮይታ (ጥሎሽ) የሚሰጠው ከብት፣
ፍየል፣ በግና ማር ማግኘት አለበት"
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ጊዜው የበጋ ወቅት እንደመሆኑ መጠን የሁዌልቫ አየር እጅግ ማራኪ ነበር።

ሁዌልቫ ሶራ ከወር በፊት ብርዳማው የክረምት ወቅት
ከመውጣቱ አስቀድሞ ካፖርቱን ከጥጥ የተሰራ የአንገት መጎናፀፊያውንና የሱፍ ቆቡን እያደረገ ወደ “ኢስላእ ክርስቲናእ"
ወደብ በመሄድ የአሳ ማጥመጃ ጀልባዎች በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ
ሲንሳፈፉ ዲካ አልባውንም የአትላንቲክ ውቅያኖስ አድማስ... ማየት
የመኪናውን ሙቀት መስጫ እንደከፈተም ከኮሎምበስ ሐውልት ስር ከተደረደሩትና የፍቅር አላማቸውን ከሚቀጩት ስፔናውያን ጎን
አቁሞ እያሸጋገረ የጠፋው ነገር እንዳለ ሁሉ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ማፍጠጥ ያዘወትር ነበር።

የአገሩን አፈር የአገሩን ባንዲራ ከኮለምበስ ሐውልት ሙዚየም ውስጥ አይቷል። ያ ጠንካራው የውሀ ጀግና ከዘመናት
በፊት ዘግኖ ያመጣውን የአገሩን አፈር ከግዙፉ ሐውልት ስር ካለው
ሙዚየም መስታዋት ውስጥ ተመልክቷል: አፈሩ ከወርቅና እንቁ
በላይ እንደሆነ ሁሉ አፍሶ ቢያሸተው ዘግኖ ቢጨብጠው እንደስኳር
ቢቅመው ተመኝቷል: ግን አልቻለም:: በመካከላቸው ጠንካራ መስታዋት አለ: የአፈሩን ጠረን ባፍንጫው ማሽተት እንኳን
ተመኝቶ አልተሳካለትም።

የአገሩ ባንዲራ የአቢሲኒያ ባንዲራ" ይላል አንጂ ቀለሙ ለቋል: ትክ ብሎ ሲመለከተው ግን ያ የቀስተ ዳመና ቀለም ያ ከህፃንነቱ ጀምሮ “የማሪያም መቀነት ለኔ..." እያለ ጮቤ የረገጠለት
ትምህርት ሲማር እንደገባ በጮርቃ አስተሳሰቡ በእንቦቀቅላነቱ.
አንጋጦ እያየ ያዜመለት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ባንዲራው ታየው ያኔ እጆቹን ዘርግቶ እንባው ከአይኖቹ እየፈሰሰ መስታዋቱ
ላይ ተደፋ።

“መለያዬ መታወቂያዬ...
የጥቁርነቴ አርማ... የነፃነቴ
ምልክት” ብሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለው ባንዲራ ንፋሱ “ጧ" እያደረገው "ሰማዩ ላይ ሲውለበለብ
ታየውና ሆድ ባሰው ባይተዋርነት ተሰማው ማንነቱን ያጣ ሆነ
ብቸኝነት ስለት ጥፍሩን አሹሎ መላ አካሉን ቧጠጠው: ውስጡ
ደማ በብሶቱ ህሊናው ደረቀ ስሩ እንደተቆረጠ እፅዋት ሲጠወልግ ሲወይብ እራሱን ተመለከተው: ስለዚህ ብሶቱን በእንባው ለውሶ
ወፍራሙ እንባው እንደጎርፍ የተሰበረ ልቡን እየሸረሸረው ወደ ውጭ ተደፋ። ማንነቱን ከአጣ ቆይቷል። ከርሱ ቢሞላም ህሊናው ግን
በፍርፋሪ ማንነት ሊጠግብ አልቻለም: እየሄደ ይቆማል እየሰራ ይቃዣል ሲስቅ እንባው ከየት መጣ ሳይባል በአይኖቹ ይሞላል...
“ማነህ?” ሲሉት እውነት ማን ነኝ! የማንነቴስ መለያ ምንድን ነው?  ለምንስ ዓላማ እኖራለሁ? ቅዠቴስ ለምን በረከተ? እውን የምበላውን የሚያፈራ አፈር የለኝም? የሚለበስ በታሪኩ
የሚያኮራ ባንዲራስ የለኝም..." ይልና በሃዘን ይንዘፈዘፋል።

ከወር በፊትም ያጋጠመው ይኸው ነው: የማንነት ረሃቡ
አይሎ ብቸኝነት በዚያ ስለታም አካፋው ህሊናውን እየሰቀሰቀ አንጎሉን ሲያቦካበት ህመሙ እየለበለበ ሲያቃጥለው ልቡ ሲደማ መስታዋቱ ላይ ተደፍቶ ኮሎምበስ ከዘመናት በፊት ያመጣውን
የአገሩን አፈርና ባንዲራ ተማፀነ።

“ምነው አምላኬ መግባባትንና መቻቻሉን ነፈግኸን። ምነው
የርሃብተኞች ምሳሌ አደረግኸን...” ሳግ ተናነቀው እንባው እንደ
ዶፍ ዝናብ ወረደ ንፍጡ ተዝረከረከ፡ በዚህ አጋጣሚ የሆነ ሰው ከተደፋበት ቀስ አድርጎ ቀና አደረገው: ሶራ ከሙዚየሙ ክፍል
ወጥቶ የአትላንቲክ ውቅያኖስ የማዕበል ነፋስ አካሉን ሲዳስሰው
የተለያየ ሃሳብ ተፈራረቀበት።
ከተደፋበት ያቃናው ግን ማን እንደሆነ ለምንስ ከሐዘኑ  እንዳናጠበው ለምን አብሮት
እንደሚራመድ አሰበ
ነፋሱ እየበረታበት ሀሊናው እየተስተካከለ ማሰብ ሲጀምር የያዘውን ሰው
ማንነት ለማየት ሞከረ።

ወፍራም ሰማያዊ ሹራብ
የፈረንሳዮችን ቡትስ ጫማ
የተጫማች ካፖርት ለብሳ ፀጉሯን በሱፍ ኮፍያ ብትሸፍንም በእንቢታ  ያፈነገጡ ፀጉሮችዋ ፊቷ ላይ ብን ብን እያሉ በሚያምረው ጠይም የፊት ቅርጿ ላይ የሚራወጡ፣ በግራ ትከሻው በኩል ወገቡን በእጆችዋ አቅፋው ተመለከተ።

ጡቷ ብብቱን ሊነካካው
ተገርሞ ትክ ብሉ አያት: ፈገግ አለችና አይኗን ሰበር አደረገች። በእርግጥ እርዳታዋ ራሱን መቆጣር እስከሚችልበት ድረስ በመሆኑ እስኪረጋጋ ጠበቀችው። ከዚያ

“ግራሊያስ” አላት በስፓንሽ አመሰግናለሁ ለማለት።

“ዴናዳ...” አለች ምንም አይደል ለማለት። ለቀቅ አድርጋው! አሁን የተረጋጋህ ይመስለኛል። ስለዚህ ብሄድ ይከፋሃል?" አለችው።
በዚህ ግላዊ ህይወት ጥልቅ መሰረት ያለው ፎቅ እየሰራ ባለበት ዓለም አፓርታማው ውስጥ የሚኖረውን ኗሪ በግል ህይወቱ ገብተው
“ለምን  ሳቅህ?... እያሉ መጠየቅ የግል ነፃነቱን እንደመዳፈር ስለሚቆጠር መርዳትና መተባበር የሚችሉትን ፈፅሞ ሌላውን ጣጣ ለባለቤቱ ትቶ ዘወር ማለት ተገቢ በመሆኑ ልጅቷ ካለምንም ጥያቄ፡-

“ደህና ሁን” ብላው ስትሄድ ከወገቡ በፊት እጥፍ ብሎ
አጆቹን ዘርግቶ እጅዋን ያዛት: በግርምታ ዘወር ብላ አየችው አያት እሱም: ወዲያው ሃፍረት ተሰማው ወንጀለኝነት ስሜት አደረበት።የያዛት እጁ እጅዋን አለቀቀም። እሷም ለማስለቀቅ አልሞከረችም።
እጁ ግን ሲንቀጠቀጥ ይሰማታል። ስሜቱም ሲለዋወጥ ተመልክታዋለች። ስለዚህ ልታፈጥበት ልትገስፀው አልፈለገችም:

“አዝናለሁ" አላት ፈገግ
ለማለት ቢሞክርም ቅንድቡ
እየተንቀጠቀጠ እያሳጣው።

“ለምን?” አለችው በፅሞና።

“ትንሽ እንድትቆይ መጠየቅ በመፈልጌ..." አላት ቀስ ብሎ እየተጠጋ።

“ማዘን አያስፈልግህም! ቶሎ መሄድ ስላሰብኝ ግን አሁኑኑ መሄድ አለብኝ።" እጆቹን ኪሱ ከተተና አድራሻውን የያዘውን ካርድ
እየሰጣት “ብትችይ ደውይልኝ አላት በትህትና።

“አዝናለሁ” ትከሻዋን ሽቅብ ሰበቅ አድርጋ “ወደ አፍሪካ
መሄድ ስለምፈልግ ጊዜ የለኝም።''

“አፍሪካ...” ከነበረበት ቅዠት ሙሉ ለሙሉ ነቃ።

“አፍሪካ የት?" አላት ፊቱ ላይ ደስታ እየታዩ፡

“አያቴ አገር... ኢትዮጲያ”  ስትለው  አለከለከ: ድንጋጤ
አይሉት ደስታ ላብ እስኪያሰምጠው ድረስ ተሸበረ:

“ኢትዮጵያ!... ኢትዮጵያ... ኦ! አምላኬ እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ። የሃዘኔም ጦስ ናፍቆት ነው..." ሲል ልጅቷ አይኖችዋን አጥብ
ተመለከተችውና

“ኮንችት”

“ምን?”

“ፔሶ ቤኒ ኮንቺት እባላለሁ። ነገ በአስር ሰዓት እዚሁ እንገናኝ አለችውና ሄደች።
በግርምታ ከአይኑ እስክትጠፋ ተመለከታት።

“…አያቴ አገር ኢትዮጲያ... ያለችው እንደገና ጆሮው
ላይ አቃጨለበት ደስ አለው። ስለ ኢትዮጵያ አብሮት የሚያወራ
አግኝቷል፡ ከጉጉቱ የተነሳ ግን ነገ ራቀበት: ያን ሩቁን ነገ እንግዳውን ነገ. መጠበቅ ግን ግዴታው ነበር።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሶራ መኪናው ውስጥ ሆኖ በሃሣብ ፈረስ ከርቀት ደረቱን እንደ ጎረምሳ ገልብጦ ከሚመጣው የአትላንቲክ ውቅያኖስ ማዕበል ይገባና አብሮ ብቅ ጥልቅ እያለ እየሰጠመ እየተንሳፈፈ ወደ ዳር
ይመጣና ካለው የሲሚንቶ ግንብ ጋር እየተጋጨ እንደ ጥይት ጮሆ.አረፋ ሲደፍቅ... እራሱን እያዬ መሪው ላይ ተደፍቶ ሲጨነቅ ተመልሶ ደግሞ አይኖቹን ውቅያኖሱ ላይ ተክሎ በሃሣብ ለረጅም ጊዜ ሲንቦራጨቅ በምናቡ አለም መግቢያ ጠፍቶት ሲዛክር ቆዬ:

ቶዮታ ኮሮላ መኪና ቀስ እያለች አልፋ ክፍቱ የመኪና
ማቆሚያ ላይ ተስተካክላ ቆመችና ሞተሯ ጠፋ: ለተወሰነ ጊዜ ፀጥታው እንደገና ሰፈነ። ከዚያ የአስር ሰዓት ደወል ተሰማ።
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ዘጠኝ

ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው፡፡የምሰራበት ሆቴል ቤርጎ ይዛለች፡፡ስራ እንደጨረስክ ና ብላኝ ስለነበረ ስራዬን ጨርሼ ወደእሷ ለመሄድ እየተዘጋጀው ነው፡፡ስደርስ በረንዳ ላይ ባለ ወንበር ላይ ኩርምት ብላ ቁጭ ብላለች አይኖቾን ሰማይ ላይ ሰክታ ፈዛለች፡፡ከጎኗ ቁጭ አልኩና‹‹ጨረቃን እያየኋት ነው እንዳትይኝ?››አልኳት፡፡

‹‹አልኩህ››

‹‹እራስሽን ምን አሳየሽ?››

‹‹ማለት? ››

‹‹ያው እንቺም ጨረቃ ነሽ ብዬ ነዋ...››

‹‹ጨረቃ ነሽ ስትል በቀጥታ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››

"ከዚህ ንግግሬ ምን የማይገባ ነገር አገኘሽበት... ጨረቃ ነሽ ስል አደንዛዥ የሆነ ውበት ባለቤት ነሽ ማለቴ ነዋ።"

‹‹ጨረቃ እውነትም እንደምትለው አደንዛዥ ውበት አላት ?››

" የላትም እንዴ?"

‹‹እኔ ምን አውቄ እንደዛ ስላልከኝ ነው..ይህቺን አባባል ሁሉም ሰው ይጠቀማታል …ግን በትክክል በምሽት ስራዬ ብሎ የቤቱን በራፍ ከፍቶ በረንዳ ላይ ወጥቶ አንገቱን ወደ ሰማይ አንጋጦ፤ አይኖቹን ጨረቃ ላይ ተክሎ፤ ውበቷን ያስተዋለ ድምቀቷን ያጣጣመ..  ከመቶ ሺ አንድ ሠው ይገኝ ይመስልኸል...ግን ዝም ብሎ ስለሚባል ብቻ ትክክል ይሁን አይሁን ሳያውቅ ሁሉም ይደሰኩራል....

"እና ማጠቃለያሽ ጨረቃ ቆንጆ አይደለችም ነው?›

"አይ ነችምም አይደለችምም..ለምሳሌ እኔ ቆንጆ ነኝ?"

"ግጥም አድርጎ ...በጣም ውብ ነሽ"

"ከዚህ በፊት ሁለት ሰዎች ቀጥታ አሁን አንተ እንደቆምከው ፊቴ ቆመው ምንሽም የማያምር አስቀያሚ ሴት ነሽ ብለውኝ ያውቃሉ።እንደውም እንደዛ አይደለም.አስቀያሚ ወንዳወንድ ነገር ነሽ ነው ያሉኝ፡፡››

"እና ማንኛችንን አመንሽ?"

"ሁለታችሁኑም"

"ሁለታችንንማ ልታምኚ አትችይም ..አንቺ ወይ ቆንጆ ወይ አስቀያማሚ ነሽ.."

"አይ እንደየሁኔታው ቆንጆም አስቀያሚም ልሆን እችላለሁ...ውበት እንደየተመልካቹ ነው በሚለው ንግግር አምናለሁ...ለዚህ ነው ቆንጇ ነሽ ሲሉኝ ብዙ የማልፈነጥዘው አሰቀያሚም ሲሉኝ አንገቴን የማልደፋው።"

‹‹እና ማየቴን ላቁም?››

‹‹እንዳሰኘህ…ግን ጨረቃ በትከክልም  ምን ግዜ ውብ እንደምትሆን ታውቃለህ?››
‹‹አላውቅም ንገሪኝ ››
ጦር ሜዳ ፊት ለፊት ግምባር ላይ እያለህ የሆነ ግዳጅ  ተሰጥቶህ ከጓደኞችህ ጋር ድቅድቅ ባለ ጨለማ እየተጓዝክ መንገድ ጠፍቶህ ከጠላት ምሽግ ሰተት ብዬ ገባሁ ወይስ የጠላት ደጋፊ ከሆኑ ህብረተሰብ እጅ ወደቅኩ እያልክ አቅጣጫህን እንዴት እደምታስተካክል ግራ ገብቶህ እያለ ድንገት ብልጭ ብላ ስትወጣ…ከዛ እየደመቀች ስትሄድ….በቃ ውብ መሆኗ የሚገባህ የዛን ጊዜ ነው፡፡ምክንያም ህይወትህ የምታድንበት ጭላንጭል እድል ሰጥታሀለችና፡፡
‹‹ወይም ደግሞ›› ብዬ እኔ ቀጠልኩላት
‹‹ወይ ደግሞ.. በጣም የምትወጃትን ማለቴ የምታፈቅሪያት ልጅ  አባትዬው ከእቅፍሽ ነጥቀው ለሌላ ሊድሩብሽ መሆኑን ስትሰሚ እሷን በጠፍ ጨረቃ ከቤት አስኮብልለሻት በየጫካው ይዘሻት ስትጠፊ በዛን አስደሳችና ጭንቀት በተቀላቀለበት ወሳኝ ሰዓት ለመንገድሽ ብርሀን ሆና ከፊት ለፊትሽ ቦግ ስትል .. በዛን በክፉና በደስታ ቀን የመንገድሽ አጃቢና መሪ ብሎም  ለፍቅርሽም ድምቀት ስትሆን…አዎ የዛን ቀን ነው ጨረቃ ከውብም ውብ መሆኗን በደንብ የሚገባሽ››
‹‹አየህ ጨረቃን እንደየልምዳችን ነው ለውበቷ ትርጉም የሰጠነው..››
‹‹እንደልምዳችን  ማለት?አንቺ ወታደር ነሽ እንዴ?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኳት፡፡
‹‹አይ ማለቴ ጓደኛዬ ወታደር ነው….ታውቃለህ አይደል?››
‹‹አዎ የበቀደምለታው ጄኔራል አይደል?››
‹‹አዎ ..እሱ ነው››
‹‹ግን…እንዲህ ከሌላ ሰው ጋር በምትሆኚበት ጊዜ ችግር አይፈጥርብሽም?››
አይኖቾ በንዴት ግልብጥብጥ አሉ….‹‹እንደዚህ ከማን ጋር ስሆን አይተኸኛል?›አፋጠጠችኝ፡፡
‹‹አረ አረጋጊው…ከእኔ ጋ ለማለት ፈልጌ ነው›
‹‹ካንተ ጋርስ ምን አድረግናል?››
‹የባሰ አለ ሀገርህን አትልቀቅ› ይላል የሀገሬ ሰው..ድንብርብሬ ወጣ…ምን ብዬ በንዴት ወደላይ የተመነጠቀ ስሜቷን  ልመልሰው?‹‹ምንም አለማድረጋችንን እኮ የምናውቀው እኔና አንቺ ብቻ ነን…ቢያንስ ሁለት ቀን አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ አድረናል…››
‹እ..እሱስ እውነትን ነው….ግን ያ ምንም ችግር የለውም..እሱም አመቱን ሙሉ ከሚስቱ ጋ ሲተኛ እኔ ምንም ብዬው አላውቅም፡፡››
‹‹ሚስቱ?›
‹‹አዎ ሚስቱ….ሚስትና ሶስት ልጆች አሉት››
‹‹ከባድ ነው››
‹‹አዎ ፍቅር ምን ጊዜም ቀላል ሆኖ አያውቅም››
‹‹ግን ምንድነው ስራሽ..?››
‹‹እሱን ማፍቀር?››
‹‹አይ ስራ መትተዳደሪበትን  ነው የጠየቅኩሽ..?››
‹‹ነገርኩህ ስራዬ እሱን ማፍቀር ነው….ገንዘብ ማገኝበትን ከሆነ የጠየቅከኝ ሌላ ጊዜ ነግሀለሁ…ግን ለራሴ የሚበቃ በቂ ገቢ አለኝ፡፡››
‹‹አይ ጥሩ ነው‹‹
‹‹ጥሩ ባይሆንስ ምን ምርጫ አለኝ....በል አሁን ይብቃን ገብተን እንተኛ››
‹‹አዎ ተነሽ.. ግን እኔ ወደቤቴ ልሂድ››
ፈገግ አለች‹‹ምነው ምን አሳቀሽ?››
‹‹አይ ወደቤት ልሂድ አባባልህ እራሱ ያስቃል..ምነው የጄኔራሉ ሽጉጥ ፊትህ ላይ ሲደቀንብህ በምናብህ አየህ እንዴ ››
‹‹ቀላል…ትቀልጂያለሽ እንዴ…?ገና በቅጡ እንኳን ያላየኋት እና ያላሰደኳት ልጅ አለችኝ..ድፍት ቢያደርገኝ ምን እላለሁ፡?፡››
ከተቀመጠችበት ተነስታ እጄን ይዛ ወደክፍሏ እያመረን ነው.. በራፍ አካባቢ ስንደርስ ነው ስለልጄ የነገርኳትን …ስትሰማ በድንጋጤ እጄን ለቀቀችና ባለችበት በመቆም አፍጥጣ አየችኝ፡፡
‹‹አንተ የእውነትን እንዳይሆን?››
‹‹ግራ ገባኝ ..ስለፍቅረኛዬ እያወራኋት ቢሆን ልሸመጥጣት እችል ነበር ..የልጅ ነገር ግን እንዴት አድርጌ…?መጀመሪያ አዳልጦኝ የተናገርኩ ቢሆን ወደኃላ ልመልሰው ግን እልፈለኩም …ቀጠልኩበት፡፡
‹‹አዎ ልጅ..አለቺኝ..የ7 አመት ልጅ..ተአምር ትባላለች››
‹‹ከዚህ በፊት ግን ፍቅረኛም ሚስትም እንደሌለህ የነገርከኝ መሰለኝ››
ይሄን ደግሞ መች ይሆን የቀባጠርኩላት…ማስታወስ አልቻልኩም፡፡አሁን ወደፊት ተንቀሳቅሰን በራፍ ጋር ደርሰናል….በእጇ ያንጠለጠለችውን ቁልፍ በማስተካከል በራፉን እየከፈተች ነው‹‹አዎ አሁንም  ሚስትም ፍቅረኛም የለኝም ….እውነቴን ነው››
ወደውስጥ ገባች…ሄዳለሁ ያልኩት ሰውዬ ተከትያት ወደውስጥ ገባሁ ..መልሳ በራፉን ከውስጥ ቆለፈችው፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡ከጎኗ ተቀመጥኩና ወሬዬን ቀጠልኩ፡፡
‹‹ነገሩ ውስብስብ እና የድሮ ታሪክ ነው… ሀይስኩል ተማሪ እያለው ነው የልጅ አባት የሆንኩት››
‹‹ታድለህ….ምን አለ እኔም ከእናቴ ቤት ሳልወጣ አንድ ዲቃላም ቢሆን ወልጄ በሆነ››
‹‹እውነትሽን ነው?፡፡››
‹አዎ..እውነቴን ነው…..የህይወቴ አንዱ ህመም የልጅ እናት ካለመሆኔ ጋ የተያያዘ ነው…››አይኖቾ በእንባ ተሞሉ…አረ ዘረገፈችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ አሁንም  ይቻላል.. ገናነው አልረፈደም…ሶስትም አራትም ልጅ መውለድ ትችያለሽ››
ኩስትርትር ብላ‹‹መቻሌን በምን አወቅክ?››በሚል ጥያቄ አስበረገገችኝ፡፡
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ዘጠኝ

"ይእ!ጥሩ ነው እንጂ ካርለቴ  ባልሽ በመታሽ ቁጥር የፍቅር ጥገትሽ ይጨምራል ለባልሽ የሚያስገሳውን ፍቅር ትሰጭዋለሽ እሱም እንደ ክረምት ዝናብ በፍቅሩ ያርስሻል ያን ጊዜ ይበልጥ
ትቀራረባላችሁ
በሐመር ሴት ሁለት ሶስት እስት ትወልድ ድረስ ባሏ
እንዲመታት ሰበብ ትፈጥራለች ልጃገረድ እያለሽ በኢቫንጋዲ
ላይ ዘመድሽ አብረሽኝ አልደነስሽም ብሎ ወይ ሌላ ምክንያት ፈጥሮ ይገርፍሻል" ዝምድናውን ለማጥበቅና አንድትግባቡ መፈለጉን ስለምታውቂ አትቀየሚውም ዘመድሽ ካልገረፈሽ ጠልቶሻል ወይንም ተቀይሞሻል ማለት ነው" ችግር ቢመጣ አይደርስልሽም

"ዘመድሽ ከብት ሲዘል እየፎከርሽ የምትገረፊውም የእሱን ዝምድና ለመግለፅ ሲሆን ያን አይቶ መከታሽ ይሆናል" ባልሽ ዘንድ
ስትሄጂም እንዲቀርብሽ:
ዘመድ እንዲሆንሽ
እንዲመታሽ ታደርጊያለሽ ያኔ ይመታሽ ይመታሽና

የኔ ሸጋ ... የኔ ወለላ
አርጊ ያልኸኝን ከአሁን ጀምሮ አንተን
አደርጋለሁ ስጭኝ ያልኸኝን እሰጥሃለሁ ማስደሰትና ልጅ መውለድ ይሆናል ስራዬ ስትይው እንደ ማሽላ
ዱቄት አፍሶ ደረቱ ላይ ነስንሶሽ ጫካ ውስጥ ይገባል አንች ደግሞ
እንደ አለቅት ደረቱን እየበሳሽ ሙቅ ልቡ ወስጥ ትገቢና ጎዝጉዘሽ
ትተኛለሽ ልቡ ውስጥ ሆነሽ ጡትሽን ሲዳስሰው ሁለመናሽን ሲያሸው
ለሴት ልጅ ከዚህ የበለጠ ምን ደስታና ጣእም ያለው ህይወት ይኖራታል!" አለች ጎይቲ ያቆመችውን ፀጉር መስራት ለመጀመር ካርለትን ወደ ጉያዋ ሳብ እያደረገቻት።

"ጎይቲ ታዲያ ዱላ ለሐመር ሴት የፍቅር መግለጫ ነው?"

"ይእ! ልጃገረድ ሆነሽ ዳንስ ቦታ የለመድሽው ፍቅር ባልሽ ዘንድ ስትሄጂም የሚጠብቅሽ ፍቅር  ዱላ ነው"

"እናንተ አገር የፍቅር መግለጫችሁ ምንድን ነው?"

"መተሳሰብ: መሳሳም …"

"ይእ! ታለ ግርፊያ መተሳሰብ የተኮመታተረው ስሜትሽ ተመታቶ ሳይፍታታ መሳሳም በአፍንጫዬ ይውጣ! ምን ኑሮ ነው
እቴ!"

"ስላለመድሽው እንጂ …"

"ይእ! በይ ዝምበይ
እኔ የሌሎችን ነገርሁሽ እንጂ እኔማ ልምዴን ተገፍፌ እንደ ምትታለብ ላም ዳሌየንና ጡት ስሬን
የሚያሽ ባል አግብቻለሁ" እንዲያው ግን ካርለቴ  ከሎ የልምዴን ሰጥቶኝ እንዲህ ማህፀኔ ቢደርቅ እኮ አይከፋኝም  ነበር, ከዛሬ ነገ
ወንድ ወንድ ይሸተኛል ስል ከዛሬ ነገ የወንዶችን ለበቅ ያነሳል ስል ዕጣ ፋንታዬ እንዲህ ይክፋ  ካርለቴ!" ብላ ምርር ብላ አዘነች

"አዝናለሁ ጎይቲ
ግርፊያ ለሐመር ልጃገረድ እንዲህ እንደ ውቅያኖስ ወለል የጠለቀ ትርጉም ያለው አይመስለኝም  ነበር!
ስትላት ጎይቲ ውቅያኖስ ያለችው ባይገባትም

"ይእ! የአባት ደንብ አይደል ካርለቴ እናትሽ ባልሽ ዘንድ
ከመሄድሽ በፊት ባልሽ ሲመታሽ አታልቅሽ የባልሽ ጓደኞች ወደ ቤትሽ ሲመጡ ከጎሽ ቆዳ የተሰራ ጫማቸውን ጠመንጃቸውን ተቀብለሽ ተቀብለሽ ቤት አስገቢ ቀጥለሽ ከውጭ ቁርበት አንጥፈሽ ሸፈሮ ቡና አፍይላቸው" የባልሽን የአደን ጓደኛ ሚሶ'
የዝላይ ወቅት ጓደኛውን ባርግያ በይ በባራዛ አርጩሜ ገርፈው
ምን ተሰማሽ?  ሲሉሽ ፈገግ ብለሽ ምንም በያቸው ያን ጊዜ በማርና ወተት ያደገች ተጨዋች ናት ብለው ይግባቡሻል" ለባልሽም
አንችን አሞጋግሰው ስለሚነግሩት ይቀርብሻል"

"ሲመቱሽ ካለቀስሽና አንገትሽን ከደፋሽ ግን ከብትና ፍየል አልጠበቀችም ቀፎ አልሰቀለችም ድሀ አደግ ጨዋታ የማታውቅ
እንደ አነር ቁጡና ክፉ ናት ብለው ይጠሉሻል" ያን ሲሰማ ደግሞ ባልሽም ይጠላሻል ይርቅሻል ውሎው ከሌላ ሴት ጋር ይሆናል እያሉ ዘመዶችሽ መክረውሽ አለት ድንጋይ ልብሽ ውስጥ ጨምረሽ
ጠንካራ እሆናለሁ ብለሽ ባልሽ ዘንድ ሄደሽ  የጠበቅሽውን  ሁሉ
ስታጭው ምነው አትራቢ ምነው አታዝኝ!" ብላ ጎይቲ እንባዋን ፀጥ ብሎ እንዲፈስ ከፈተችው

ካርለትም ዐይኖችዋ በእንባ እንዳቀረዘዙ ጎይቲን እያባበለች አንድ ቃል በህሊናዋ ብልጭ ብሎ ድርግም አለ ፈለገችው
ያን ቃል ፈረንሳዮች ፍላጀላሲዬን ይሉታል እንግሊዞች ደሞ
ፍላጄሌሽን  ደስ አላት ህሊናዋ ከትውስታው ክፍል ጀባ ያላትን ቃል ወደ ኖረበት ተመልሶ ሳይገባ አፈፍ አድርጋ ስለያዘችው

ፍላጀላሲዬን ስርዓት ባለው ወይንም ሃይል በተሞላበት
መንገድ በሃይማኖት ተከታዮች የሚፈፀም ግርፊያ ነው" በብዙ
የሃይማኖት ተቋማት ፍላጀላሲዬን በመባል የሚታወቀው ግርፊያ
የርኩስ መንፈስ የማስወጫ ስልትና መፈወሻ ዘዴ ተደርጎ ይቆጠራል"በጥንት "ዘመን የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በግርፊያ መሰቃየትን እንደ
አምልኮዋዊ ፀጋ ይቆጥሩት ነበር በነዚህ ህዝቦች እምነት መገረፍ ወይን በአካላዊ ጉዳት መሰቃየት ከሃጢያታቸው መንፃታቸውን፥ከመቅሰፍት
መዳናቸውን የሚያረጋግጡበት
ሆኖ ሲታመንበት ቆይቷል

በሰሜን አሜሪካ ህንዶች: በስፖርታዎችና በሮማውያን
ግርፊያ የአማልክትን ወይንም የቅድመ አያቶችን
ምስል ጭንብል
ባጠለቀ ገራፊ የሚፈፀም ነበር" ይህ ድርጊት በአስራ ሶስተኛው ክፍለ
ዘመን አጋማሽና በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመንም ቀጥሎ እንደ ጀርመን: ሆላንድ በመሣሰሉት አገሮችም ተስፋፍቶ ቆይቷል በብዙ አገሮች በበዓላት ቀን ወንዶች ጀርባቸውንና ደረታቸውን በአለንጋ
ይገረፋሉ።

ይህ አምልኮዋዊ እምነት እ.ኤ.አ. በ1349 ዓ.ም እንደነበሩት ፓትሪያርክ ክሌመንት በመሳሰሉ  የሃይማኖት አባቶች ከረር ያለ ተቃውሞ ግርፊያ እየቀነሰ ቢመጣም በአሁኑ ዘመንም በደቡብ
የአውሮፓ ሀገሮች በላቲን አሜሪካውያንና በመካከለኛውና ሩቅ
ምስራቅ አገሮች የተለመደ ነው ለምሳሌ በታይዋን የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በየአመቱ በስቅለት ቀን እንደ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መገረፍ: መሰቃየት: እጅና እግርን በሚስማር መቸንከር
የእየሱስ ክርስቶስን ፍቅር እንደ ማግኘት ምድራዊ ሃጢያትን እንደ መቀነስና ለሰማያዊው ህይወት በክብር መዝገብ እንደመመዝገብ
ይቆጠራል

ከዚህ ውጭ ግን ዘመንሁ በሚለው ህብረተሰብ በሁለቱም ፆታ ግርፊያ በብዙ ግለሰቦች የወሲብ ስሜት መቀስቀሻ ወይንም የወሲብ ስሜት ማርኪያ ስልት እንደሆነና የገራፊ ልብሶችና የመግረፊያ
አለንጋዎች የሚሸጡባቸው የወሲብ ሱቆች
በርካታ እየሆኑ
መጥተዋል እኒህ ግርፊያን እንደ ወሲባዊ የችግር መፍትሔ የሚቆጥሩ
ሰዎችን የስነ አዕምሮ ጠቢባን የስነ-አዕምሮ
ችግር ያለባቸው እንደሆኑ በመቁጠር ብዙ መላ ምቶችን እየደረደሩ ቢሆንም
የመገረፍ ፍላጎት ወይንም ሱስ ግን አንድም የተፈጥሮ ባህሪ ውጤት ወይንም እምነት የፈጠረው ፍላጎት ስለመሆኑ አያጠራጥርም ብላ አሰበችና የሐመሩ ግርፊያም ባህላዊ እምነት የፈጠረው የህሊናና
የአካል ዝግጁነት ውጤት ነው ብላ ደመደመች።

እየጨለመ ሲመጣ የእሳቱ ወጋገን ይበልጥ እየጎላ  እየጎላ መጣ ወጣቶች ለስነ-ስርዓቱ ከሰበሰቡት እንጨት በተጨማሪ ከጫካ
ግንዲላውን: ጭራሮውን እየተሸከሙ እያመጡ ይከምራሉ ጥቂት ጎረምሶች ደግሞ ለወጠሌ ጥብስ የሚሆነውን ችካል በጩቤያቸው ይጠርባሉ  ሌሎች የእድሜ ጓደኛ ጎረምሶች ደግሞ ከሳቱ ርቀው ተሰብስበው ያወጋሉ፤ አንዳንዴም
በተቀቡት ዥንጉርጉር የአኖ ቀለም ከሹልሹላቸው
ለዳንሱ ዝግጅት
የሰጎን ላባ ሰክተው
ጨሌያቸውን አንገታቸው
ላይ ደርድረው ግንባራቸው ላይ የጨሌ ገመድ
ቋጥረው ዳንሱንና ድሪያውን ናፍቀው ውስጥ ለውስጥ ይቋምጣሉ አልደርስ ብሏቸው"

"ሚሶ!" አለ አንዱ
አለ አንዱ ከመሀላቸው የአደን ጓደኞቹን የሰአት ማሳለፍያ ጨዋታ ሊያወጋቸው።
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ስትባንን በመስኮቱ ሾልካ የገባችው ፀሀይ ልክ አልመው የለቀቋት ይመስል ደረቷ ላይ በጡቶቾ መካከል የአካፋዩ መጀመሪያ ላይ አርፋለች.. ከተኛችበት ቦታ ንቅንቅ ሳትል ነው የነቃችው…አንገቷን ጠምዝዛ ወደጀርባዋ ስትመለከት አልጋው ባዶ ነው…
‹‹እንዴ የት ሔደ…?››ብላ ዞር ስትል
‹‹አለሁ እዚህ ነኝ››አላት… ወደ እዛኛው ክፍል በሚወስደው በራፍ ዳፍ ላይ ፊቱን ወደእሷ ዞሮ በትኩረት እየተመለከታት ነበር፡፡
‹‹ውይ ስንት ሰዓት ሆነ?››ጠየቀችው፡፡

‹‹3፡10፡፡››

‹‹እየቀለድክ ነው?››

‹‹በፍፅም..ምነው የምትሄጅበት ቦታ ከሌለሽ ዛሬ እኮ እሁድ ነው..የእረፍት ቀን ነው?››

‹‹አይ እኔ እንኳን ስራ ፈት ነኝ ..አንተን ስራ ካስፈታሁህ ብዬ ሰግቼ ነው፡፡››

‹‹አይ በፍፁም እኔን ስራ አታስፈቺኝም…ጉዳይ ቢኖርብኝ  እኮ መልዕክት ጥዬልሽ ሄድ ነበር፡፡››

‹‹ዳግመኛማ እንደዛ አታደርግም…፡፡››

‹‹ለምን?›› አለ ግራ በገባው ፊት፡፡

‹‹እንደዛ አድርገህ እኮ በቀደም ላፕቶፕህን ይዤብህ ሄድኩ …ዛሬ ብትደግመው ጠቅላላ ቤትህን አስጭኚ ልወስደው እችላለሁ፡፡››

‹‹እሱ አያሳስበኝም..ይልቅ አሁን ታጠቢና ወደሳሎን ነይ.. የሰራሁትን ቁርስ እንዲቀዘቅዝ አታድርጊ..፡፡››አላት..ለመመፃደቅ ሳይሆን እውነቱን ነው የነገራት…

አሁን እሱ ለቁሳቁስ የሚጨነቅበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው….በቅርብ በዙርያው የኮለኮላቸውን መገልገያ ዕቃዎቹን በጠቅላላ እርግፍ አድርጎ ትቶቸው እንደሚሄድ ያውቃል..ምን አልባት እሷ እንዳለችው  ዛሬውኑ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ ጫጭና ብትወስድ መሄጃ ቀኑን ከማፍጠኗ ውጭ ሌላ የምታደርስበት ጉዳት ወይም የኑሮ መፋለስ የለም፡፡አሁን እዚህ ቦታ እዚህ ከተማ ውስጥ አስሮ ያቆየው አንድ ጉዳይ ብቻ ነው…የፍቅረኛው ጉዳይ…የእሷን የወደፊት ህይወት መሰረት ካስያዘ በቃ ሌላ የሚቀረው ነገር የለም፡፡

  ልዩ ስለምግብ ሲያወራት በቀደም የበላችውን ምግብ አይኖቾ ላይ  ድቅን  አለ…  እናም በዛው ቅፅበት እስከአሁን ልብ ያላለችው የሚያውድ የምግብ ሽታ አፍንጫዋን ቆጠቆጣት…ቶሎ ብላ ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች…5 ደቂቃ ያህል    ነው የወሰደባት፡፡፡ሳሎን ስትገባ ቀለል ያለ ቆንጆ ቁርስ ተሰናድቶ ጠበቃት…ልክ አስደሳች ጀብዱ እንደሰራ ማራኪ ፍቅረኛ እየተፍለቀለቀች ለቁርስ ቀረበች፡፡ከፊት ለፊቷ ሆኖ እጁን ወደምግቡ ይዘረጋል ስትል  ሁለቱንም እጆቹን አንድ ላይ በማጣመር ወደግንባሩ ወሰደና ወደላይ አንጋጠጠ..፡፡ሊፀልይ መሆኑ ገባትና አብራው መፀለይ ባትችልም በዝምታ መከታተል ጀመርች‹‹….ጴንጤ ይሆን እንዴ ይሄ ልጅ;?›› በውስጧ እራሷን ጠየቀች እሱ ከንፈሩን በማነቃነቅ ሚሰሙ ቃላቶችን ከአንደበቱ እያወጣ ፀሎቱን ቀጠለ…
‹‹ለውስጣችን  የሚስፈልገንን ኃይል በትክክለኛው መንገድ እድናገኝ እርዳን….ይሄ ምግብ የተቀደሰ ይሁን…ይህ ምግብ ያለውን ኃይል አሞጦ ለእኛ እንዲሰጥ በፍቅርና በትህትና እጠይቃለሁ…ኃይሉም ለውስጣችን ጉልበት፤ ለአካላታችን ጤና እና ለመንፈሳችን ብርታትን ለአእምሮአችን ደግሞ  በጎ በጎውን  የማስብ ብቃትን እዲያጎናፅፈን ይሁን፡፡
አሜን
ጨረሰና‹‹..ብይ››አላት
ከመደነቋ ሳትወጣ‹‹..እሺ›› ብላ ለመብላት እጇን ዘረጋች..እንዲህ አይነት ፀሎት የትም በማንም ሲፀለይ ሰምታ አታውቅም‹‹….ከምን አይነቱ ተአበኛ ሰው ጋ ነው ፈጣሪ ያገናኘኝ፡፡››ስትል በውስጧ አብሰለሰለች፡፡
ማሰቧን ለሰከንድም ሳትገታ ቁርሷን ግን ጥብስቅ አድርጋ  በላች…የእሱ አበላል በጣም የተለየ ሆኖ ነው ያገኘችው ….በጣም ስርአት ያለው በፅሞና የታጀበ .ረዘም ያለ ማላመጥ ያለበት ነው፡፡
‹‹…የዚህ ልጅ ፍቅረኛ እንዴት ታድላለች?››

‹‹ምን አልሺኝ?››
ለካ ድምጻን ከፍ አድርጋ ነበር ያጉረመረመችው
በእፍረት አይኖቾን ከወዲህ ወዲያ እያቁለጨለጨች፡ ‹‹ማለት… ያው ለማድነቅ ፈልጌ ነው፡፡››አለችው..
‹‹አይ ምንም የሚደነቅ ነገር የለውም..እኔ በተቻለኝ መጠን የሚጣፍጥ ምግብ መመገብ እፈልጋለሁ…ምን አልባት መጠኑ ካልሆነ በስተቀር አንቺም ባትኖሪ ማበስለው እንደዚሁ ነው..እና ሌላ እንግዳም ቢሆን…››
‹‹እና ላንቺ ብዬ ያደረኩት ምንም የተለየ ነገር የለም ለማለት ነው?››
‹‹በትክክል፡፡››
‹‹እና እስከአሁን እኔን በተመለከተ ያደረካቸው በጎነቶችና ትእግስቶች …ለሌላም ታደርገዋለህ ማለት ነው፡፡››ስትገረምበት የሰነበተችውን ጥያቄ አጋጣሚውን ስታገኝ ጠየቀችው፡፡

ለዚህ ጥያቄ በተወሰነ መጠንም ቢሆን የተሳሳተ ወይም የተጋነነ መልስ ሊሰጣት ወሰነ.. ‹በተቻለኝ መጠን አዎ…ግን አስቤበት ለእከሌ እንዲህ ላድርግ ብዬ አይደለም…በእየእለት ገጠመኜ ፊት ለፊቴ የሚደነቀሩትን ማንኛውንም አጋጣሚዎች አእምሮዬና ልቤ ተጋግዘው በሚወስኑት ውሳኔ በመገዛት ላልፋቸው እሞክራለሁ..በዛ ሂደት ውስጥ እንግዲህ ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር በሌላው ሰው ላይ  ልሰራ እችላለሁ…..በእኔ ምክንያት ግን ሰው  ፊቱን ባያጨማድድ ደስ ይለኛል፡፡››አላት…ያለው ሁሉ እውነትነት ያለው ቢሆንም እሷ ላይ ግን የተለየ አቀራረብና ልዩ የሆነ ትኩረት አደርጓል…ይሄንን ግን ሊነግራት አልፈለገም…ለመዋሸት ፈልጎ ሳይሆን ለምን ብትለው ሚመልስላት የተዘጋጀ መልስ በውስጡ ስለሌለ ነው፡፡
‹‹አእምሮዬና ልቤ የተስማሙበትን ነው ያልከው..እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው..እስኪ ትንሽ አብራራልኝና   ከረዳኝ እኔም ልጠቀምበት፡፡››
‹‹አእምሮሽን ብቻ ስተጠቀሚ እኔነት ያጠቃሻል ….እኔነትን መሰረት አድርገሽ ምትወስኚው ውሳኔ ደግሞ ወደ ራስ ማዳላቱና ከሌላው መብት ላይ የተወሰነ ድርሻ  መስረቁ አይቀሬ ነው..ልብሽን ስትጠቀሚ ደግሞ ስሜት ያጠቃሻል ፡፡በወቅቱ በሚሰማሽ ስሜት ብቻ ሙሉ በሙሉ ተስበሽ ውሳኔ  ላይ ትደርሻለሽ….ብዙን ጊዜ ደግሞ በመጀመሪያው እይታ አይተው የሆነ ስሜት የሚቀሰቅሱ ነገሮች ጠለቅ ብለሽ ሰታጠኛቸው ሌላ ታሪክ በጀርባቸው አዝለው ይገኛሉ….ሁለቱንም ማለቴ ልብሽንና አእምሮሽን በጥምረት መጠቀም ግን ወደእውነታው የበለጠ መቅረቢያ የተሻለው መንገድ ነው፡፡ልብህ ወደሚመራህ ቦታ ተጓዝ እምሮህንም ግን ይዘህ ሂድ ያለው ማን ነበር ››አላት
‹‹ሰው ግን በምኑ ነው የሚያስበው?››ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ ሰው በአእምሮው እንደሚያስብ ነው የሚታወቀው..እኔ ግን በአእምሮችን ብቻ ሳይሆን በልባችንም እናስባለን ብዬ አምናለሁ… በኩላሊትም እንደሚያስቡ የሚያምኑ ማህበረሰቦች አሉ፡፡››
‹‹እንዴ ምን ነካህ ልብ እኮ በደም የተሞሉ የተለያዩ የደም ቱቦሆች ቅጥልጥል ነው … እንዴት ማሰብ ይችላል?››
‹‹አእምሮም ደግሞ እሱንም የለውም….አእምሮ ጭንቅላት ውስጥ ሚካሄድ የሀሳብ ስርአት ነው….ጭንቅላትም ደግሞ በቢሊዬን የሚቆጠሩ የተለያዩ ኒውሮኖች ቅጥልጥል ነው፡፡ እንዴት አድርጎ ነው የሚያስበው..ስታስቢስ በአእምሮሽ ታስብ በኩላሊትሽ፣በልብሽ ታስቢ በጉልበትሽ በርግጥ መለየት ትቺያለሽ?›› መልሶ ጠየቃት፡፡  
  
‹‹አልችልም፡፡››

ከእሱ ጋር ረዘም ያለ ጊዜ ማሳለፍ ስለፈለገች‹‹አሁን የሆነ ቦታ እንሂድ››አለችው፡፡

‹‹ደስ ይለኛል …ግን የት?››

‹‹የፈለክበት ቦታ..ሲኒማ ቤት…ትያትር ቤት.. መጠጥ ቤት…››
‹‹ካልደበረሽ እኔ አንድ ቦታ ልውሰድሽ፡፡›› አላት…
#ህያብ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በኤርሚ

የሆነ እንደመልዓክ የቆጠራችሁት ሰው ከሆነ ጊዜ በኋላ ውስጡ ያለውን የሚያስፋራ አውሬ አውጥቶት ሊበላችሁ እየገሰገሰ ሲመጣ ምን ይሰማችኋል። ትሸሻላችሁ ወይስ ቆማችሁ ትበላላችሁ። እኔ ግን ብዙ ነገሬ እስከሚያልቅ ቆሜ ነበር የተበላሁት

የልቤ ንጉስ  ብዬ የፍቅር ማማ ላይ የሰቀልኩት ሰው ልክ የዛን ቀን ትክክለኛ ማንነቱን አየሁት። ማንኛውም ሰው ሲናደድ ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል የሱ ግን ከዛ የተለየ ነበር። ነገሮችን ለመስማትም ለመረዳትም ፈቃደኛ አልነበረም ያነበበው ደብዳቤ ሳይቀር ቢኒ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅሩን እንደገለፀልኝ እየነገረው እሱ ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ ፍቅረኛሞች ነበራችሁ ብሎ ደመደመ።

"ጯ ጯ" ይህ በማፈቅረው ሰው የተመታሁት የጥፊ ድምፅ ነው። የቦክስን ድምፅ ደግሞ በቃል መግለፅ ይከብዳል እንጂ እኔን እንደመታኝ ቢኒ ዘሎ ተነስቶ ያቀመሰውን ቦክስ ከዛም አንዴ ቢኒ አንዲ ዮኒ ገላጋይ እስኪመጣ የተደባደቡትን በቃል እገልፅላችሁ ነበር።

ከድብድቡ በኋላ ሁለቱንም ሰው ይዟቸው

"አንተ ውሻ አላፈቅራትም ብለህ ያጣበስከኝ ፍቅረኛህን ነበር አይደል?(ደም ያዘለ ምራቅ ከአፉ እየተፋ) አትረባም ወንድ አይደለህም እሺ... ቀሚስ ልበስ"

ቢኒ ደግሞ ሌላ ትዕይንት ነው ከድብድቡ በኋላ እሱንም ሰዎች ቢይዙትም ለመወራጨትም ሆነ ለመሳደብ አልሞከረም የንዴት ትንፋሽ እየተነፈሰ ዝምም ብሎ ዳር ላይ ቆሜ አንዴ እሱን አንዴ ዮኒን እያፈራረቅሁ የማየውን እኔን ያየኛል

"እባካችሁ ልቀቁኝ ምንም አይፈጠርም እሷን ግን ሊጎዳት ይችላል። ሚስቱ ናት ግን እባካችሁ እንዳይጎዳት አድርጉ" አወራሩ ያሳዝን ነበር። ለቀቁትና ወደኔ መጣ

"ይሄ ውሻ ሚስቴ አጠገብ እንዳይደርስ እንዳትነካት አትጠጋት"
ብዙም ሳይቀርበኝ ቆመ

"ከሳምንት በኋላ እበራለሁ እስከዛ ግን ችግር ካለ ደውይልኝ እዛ ስሄድ ደግሞ እኔ እደውልልሻለሁ" አለኝና መልሴን ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ ከመናፈሻው ወጣ

።።።። ።።።።። ።።።። ።።   ።።። 
ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት ብዬ ተቀምጫለሁ። ዮኒ ደግሞ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ ያለማቋረጥ እየተመላለሰ ይለፈልፋል

"ንገሪኝ እስኪ ስንት ጊዜ ሆናችሁ?" መልሴን ሳይጠብቅ ደግሞ

"የትናዬት ልክ ነበረች አይደል" ለመናገር አፌን እንደከፈትኩ

"ዝምምም በይ ምንም አትናገሪ ባትነግሪኝም አውቄዋለሁ። ግን ከመች ጀምሮ ነው ፍቅረኛ የሆናችሁት አንደኛ አመት እያለሽ"

"ኧረ እኔ ከቢኒ ጋር"
" ዝምም በይ አትንገሪኝ መገመት አይከብደኝም" ለመናገር መሞከሬን አቆምኩና ንዴቱ ሲበርድለት እነግረዋለሁ ብዬ አሰብኩ ግን በፍፁም ያሰብኩት አልሆነም። በውስጡ ያመነበትን የመከዳት፣ የመቀደምና የመሸወድ ስሜት ከውስጡ እንዳስወግድለት እድል ሊሰጠኝ አልቻለም። በራሱ ጭንቃላት ታሪክ ፈጠረና በፈጠረው ታሪክ ደግሞ አመነበት። ህያብ ከቢኒያም ጋር የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው ፍቅር የጀመረችው። እኔ ላይ ተመካክረው ነው የተጫወቱብኝ ይህን እና ሌሎች ነገሮችን በጭንቅላቱ ውስጥ ሞላቸው የሚያውቀውን እውነት ሳይቀር ካደ። ከዛ በኋላማ ያሳለፍኩትን እንዴት ልገልፀው እችላለሁ በአጠቃላይ ህይወቴ ሲኦል ሆነ።

ተመስገን ይህን ሰሞን በፍቅር የተሞላ ጊዜ አሳለፍን ብዬ አመስግኜ ሳልጨርስ ሌላ ታሪክ ይፈጠራል። በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን ለሱ ያለኝ ፍቅር እንደድሮው ነበር። ትቼው እንኳን ለመሄድ አቅም አልነበረኝም። በእርግጥ ትቼው ብሄድ ከሱ የተሻለ ደሞዝ ያለኝ ራሴንም ሆነ ልጄን እና እናቴን ቀጥ አድርጌ ማስተዳደር የምችል ሰው ነበርኩ። ግን አፈቅረዋለሁ አንድ ቀን እውነቱን ለመረዳት እንደሚሞክርም አምናለሁ። እምነቴ ከምንም በላይ ለሱ ያለኝ ፍቅር በደልን ችዬ እንድኖር አደረገኝ

ይህ ከተፈጠረ ከአመት በኋላ እናቴ በፀና ታማ ሆስፒታል ገባች። እኔ የምሰራበት ሆስፒታል ነበር።  እንደማትተርፍ እያወቅሁ ብዙ ጣርኩ ግን ልመልሳት አልቻልኩም።

እናቴ ጥላኝ ሄደች እንደሚሰበር እንቁላል የምትጠነቀቅልኝ እናቴ እንደ አይኗ ብሌን የምትጠብቀኝ እናቴ ለኔ እንደኖረች ተምሬ ደርሸላት ትንሽ እንዳሳረፍኳት ገና ውለታዋን ሳልመልስ በደንብ እፎይይይ ብላ መኖር ሳትጀምር ሞት ነጠቀኝ። አመመኝ.... እጅግ በጣም አመመኝ። ከኔ የበለጠ እንቁን ማፅናናት ከባድ ነበር። እማዬ ሁሉ ነገሯ ነበረች።

ለአንድ ቀን መዓድ የተጋራሀውን ሰው እንኳን በሞት ማጣት ከባድ ነው። እማ ከዛም በላይ አለሜ ነበረች፤ የራሴን ውብ አለም ፈጥራ ከፍራቻዬ የሸሸገችኝ፣ ጓደኛዬ፣ ስታመም ሀኪሜ፣ ስጨነቅ አማካሪዬ፣ ተቆጪ መካሪዬ፣ ዘጠኝ ወር በሆዷ ተሸክማ ሶስት አመት ጡቷን አጥብታ ያሳደገችኝ እናቴ ለሰው አንድ ለኔ ግን ብዙዬ ነበረች።
ይገርማል አይደል ነው ከመባል ነበር ወደመባል የምንሸጋገርባት የሽርፍራፊ ሰከንዶች ሞት....

አስፈላጊ ያልናቸውን እቃዎች ሰብስበን ወደኔ ቤት ካመጣን በኋላ ቤቱን አፅድተን ለአከራይዋ ቁልፉን አስረከብን።

አከራይዋን ቻው ብለናቸው ልንወጣ ስንል እንቁ
"ማሚ እዚሁ ነው መኖር የምፈልገው እማዬን ትቼ የትም አልሄድም" እየተንሰቀሰቀች የተቆለፈው በር ስር ሄዳ ቁጭ አለች። አጠገቧ ሄጄ ቁጭ አልኩና አቀፍኳት.... ለረጅም ደቂቃ አብረን ተላቀስን።

አከራይዋ ወ/ሮ ትርንጎ ከቤት ሲወጡ ተቃቅፈን ስንላቀስ አዩንና  ወደኛ መጡ

" ምነው ልጆቼ ተነጋግረን አውርተን... ተው እንጂ እኔንም ሆድ አታስብሱኝ እናታችሁንም አትረብሿት ነብሷ በሰላም ትረፍ። በእናንተ እንደዚህ መሆን ደስተኛ የምትሆን ይመስላችኋል በሉ ልጆቼ ኑ ተነሱ" እጇችንን ይዘው ካነሱን በኋላ እንባችንን ጠራረጉልንና መክረውንና አፅናንተውን በር ድረስ ሸኙን።

"በቃ ቻው እማማ ትርንጎ እየመጣን እንጠይቆታለን ብዬ ቃል አልገባልዎትም ግን ቤተ ክርስቲያንም ቢሆን መገናኘታችን አይቀርም። የምሰራበትንም ሆስፒታል ያውቁታል አይደል ለጤናዎትም ብቅ ማለት ይችላሉ። ቤትም ይምጡ አይጥፉ። በሉ ቻው... ከዚህ በላይ አይቸገሩ" ተሳስመን መኪና ውስጥ ገባንና ወደ ቤት ሄድን።

እንቁ ሙሉ ለሙሉ እኛ ቤት መኖር ከጀመረች በኋላ የዮኒ ፀባይ ተስተካክሏል። ቶሎ ወደ ቤት ይገባል ትምህርት ቤት ያደርሳታል እልፎ አልፎ አብረው ይዝናናሉ። እኔ ብዙውን ጊዜ በስራ ስለማሳልፍ ባልቀላቀላቸውም የልጄ የአባትነት ክፍተት ሲሞላ በማየቴ ደስተኛ ነበርኩ። ሁልጊዜ አባቴ ማነው የሚለው ጥያቄዋ ሊያሳብደኝ ነበር የሚደርሰው.... ለጊዜውም ቢሆን ጥያቄዋን ትታ ዮኒን እንደ አባት ስታየው ማየቴ እፎይታን ሰጥቶኛል።

ትልቅ ልጅ እየሆነች ነው። አንዳንዴ እማዬ እየሳቀች "መልኳ እኮ አንቺን አስደግፈው የሳሏት ነው የምትመስለው። አንቺም ልጅ ሆነሽ እንደሷ እኮ ነው መልክሽ ካላመንሽ  ያንን አልበም አምጪና ፎቶሽን እና እሷን አስተያይ" ትለኝ ነበር።

ልጅ ሆና ብቻ ሳይሆን እያደገች ስትመጣም የኔኑ መልክ ያዘች።

ከዮኒጋ አልፎ አልፎ ጭቅጭቅ እንደ ቅመም ጣል ጣል ያለበት ራት በልተን እንገባለን። ቢሆንም ግን ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር ተመስገን ያስብላል። ትንሽም ቢሆን ቤቴ ትዳሬ ማለት ጀምሯል ያ ለኔ ትልቅ ነገር ነበር።

ቢኒ ከሄደ ጀምሮ ሶስቴ ነው የደወለልኝ። አንደኛው ከእናቴ ሞት በኋላ እግዜር ያፅናሽ ለማለት ነበር። ከዛ በፊት ሁለቴ ደውሎ ቢያውቅም ያን ያክል ግን አላወራንም ነበር ሌላው ቢቀር ስለመጫረሻው ቀናችን ደፍሮ የጠየቀ እንኳን አልነበረም።
ቻው ከማለቱ በፊት
" ግን ደስተኛ ነሽ" ይለኛል።
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
‹‹እና ታዲያ አሁን ምንድነው የሚሆነው.?›› 

‹‹አንቺን ከዚህ ማውጣት እና ወደመሬት ማለቴ ወደቤትሽ መመለስ አለብኝ፡፡››

‹‹አንተስ...?››

‹‹እኔን እርሺኝ፡፡››አለና ሰውነቱን ወጣጠረ …ጭራው ወደላይ ወደወገቡ ሄደና ሰውነቱን እየሰረሰረና ቅርፅን እየቀየረ መጣና በደቂቃ ውስጥ አብረቅራቂ ክንፍ ሆነ..የሰውነቱ ጠቅላላ ገፀ-መልኩ ተቀየረ …የሚያበራና የሚንፏለለ አንጸባራቂ ብርሀን ከውስጡ ይፈስ ጀመር.. እጁን ወደ አንገቷ ስር ሰዶ  ጥፍር በመሰለ ነገር ወጋት..የሆነ የመርፌ ውግ አይነት ስሜት ነው የተሰማት …ወዲያው ድንዝዝ ነው ያላት …ከዛ በኃላ የሆነውን ነገር አላወቀችም….

ስትነቃ…. ያዶት ወንዝ ዳር እራሷን ስታ እርቃኗን ጥቅልል ብላ ተኝታ ነው  ሰዎች ያገኟት….አፋፍሰው ወስደው ለቤተሰቦቾ አስረከቧት…ከዛ በቤታቸውና በጠቅላላ መንደሩ አስፈሪ ትርምስ ተፈጠረ…ሁኔታዋ ሲታይ ተደፍራለች… ነፍስ እንደዛራች ያለችበትን እና የሆነውን ነገር ማመን ነው ያቃታት…ምን እንደሆነች በቤተሰቦቾም ብትጠየቅም የሚጨበጥ ነገር መናገር አልቻለችም‹‹ሴይጣን ደፍሯት ነው›› ተባለ..ተከራክራ ልታሳምናቸው አልቻለችም …እሷ ‹‹ተደፍሬ ሳይሆን በፍቃዴ  ነው›› ብትልም ሰሚ አልነበረም… ያንን የሰይጣን እና መላአክ ድብልቅ የሆነ ፍጡር ለማግኘት ከቤተሰቧ እየተደበቀች  ለወራት ያዶት ወንዝ ላይ በለሊት በመሄድ ወንዙን ብታስስም በለቅሶ እየታጠበች በልመና ብትጣራ.. ብትፈልግ ብትጠብቅ ከየት ታምጣው .?
‹‹ወገኖቹ ምን አድርገውት ይሆን...?ምን አለ ለአንድ ሰከንድ እንኳን ተመልሶ ቢመጣና  ቢገለፃልኝ .?እና ሰላም መሆኑን ባውቅና ብረጋጋ..!!!› የዘወትር ምኞቷ ነበር..ግን ምንም መፍትሄ አልነበረውም፤ዳግመኛ ልታገኘው አልቻለችም..ግን ልትረሳውም አልቻለችም..ምክንያቱም አርግዛለታለች.. ስላረገዘችለትም ደስ ነበር ያላት ..ማንም ምንም ቢላት ግድ አልነበራትም ነበር…ቢያንስ በልጁ ውስጥ  እሱን በማየት ነው ለዓመታት የተፅናናችውና..የተረጋጋችው፡፡ ..እርግዝናዋ ከባድ ነበር ፤በአመት ከስድስት ወሯ ነበር መውለድ የቻለችው..የሰውነቷ አወቃቀር እና መላ ተፈጥሮዋ ልክ እንደ እሷ የሆነ እና ከአንገቷ በላይ ያላት መልክ እና  ነገረ ስራዋ የእሱን የምትመስል ልጅ ወለደች…፡፡ከተአምረኛው ፍጡር ተአምረኛ ልጅ ወለደች..ሰው ሁሉ ግን  የገዛ ዘመዶቾንም ጨምሮ  ከዳቢሎስ  ወለደች ነበር ያሏት .‹‹. ይሁን እንኳንም ወለድኩለት   ፡፡›አለች፡፡ስሟንም ኬድሮን  አለቻት፡፡ ይሄም አባቷ የሚኖርበትን ስውር ፕላኔት ለማስታወስ አስባ ነው፡፡የበሬዱ ታናሽ ወንድሞ ደግሞ ሰውን ግራ አታጋቢ አለና ‹‹ሶፊያ›› አላት፡፡በዚህ የተነሳ ‹ኬድሮን› እና ‹ሶፊያ› የተባለ ሁለት ስም ኖራት፡፡
የበሬዱ ዲንቃ ፍቅር….ምናባዊ አይነት ነው ቢባልም…..ግን ደግሞ ምናባዊ ብቻ ነው ተብሎም ድምዳሜ የሚሰጠው አይደለም… ታሪኩ በአጠቃላይ ተአማኒነት የሚጎድለው ልብ አንጠልጣይ ልብ ወለድ ከሚመስል ታሪክ ውስጥ እውነተኛ የምትጨበጥና የምትታቀፈ ልጅ ተገኝታለች፡፡

….ህልም እና ቅዣት ከሚመስለው የፍቅር ግንኙነት ተጨባጭ ኬድሮን አሁን አለች … መቼስ ልጅቷም እራሷ ከተአምራዊ ነገር የታጠረ የወደፊት ታሪክ እንደሚኖራት እንዲሁ የልጅነት ገፅታዋን ብቻ አይቶ መተንበይ ከባድ  አይደለም፡፡
የፍጥረት ምንጩ ከማይታወቅ አባትና ሰው ከሆነች እናት የተወለደችው ኬድሮን ከውልደቷ ጀምሮ  ልዩ ክስተት ሆና ነው በዚህ ምድር የተከሰተችው፡ሁሉ ነገሯ ከሰው የማይገጥም እና ተለየ የሆነው ገና ከውልደቷ  ጀምሮ ነው፡፡የተወለደችው  እንደማንም የሰው ልጅ በዘጠኝ ወሯ አይደለም..አንድ አመት ከስድስት ወር በእናቷ ማሀፀን ውስጥ ዘና ብላ ኖራለች…ምን አልባት በሰው ልጅ የህይወት ታሪክ በእናቱ ማህጻን  ከበቂ በላይ ለሆነ ጊዜ በመንደላቀቅ እና በምቾት በመኖር ሪከርዱ በእጇ  ሳይሆን አይቀርም…
እርግጥ ብዙዎቹ ይሄንን ታሪክ ሲሰሙ ባለማመንና በመጠራጠር ክርክር ውስጥ ይገባሉ‹..እናቷ እሷን የፀነሰችበትን ቀን ተሳስታ ነው፡፡ ›የአብዛኞቹ መላምት ነው..ግን ይሄ እንዳልሆነ ከመጀመሪያ ሳምንት የጽንሰቷ ጊዜ አንስቶ እስክትገላገል ድረስ የሀኪም ክትትል ውስጥ ስለነበረች ትርክቷ በሳይንስ መረጃ የተደገፋ ነው…ይሄም በተወለደችበት ሳምንት በኢትዬጴያ ሬዲዬ የቀትር ዜና ላይ‹‹በባሌ ክፍለሀገር በደሎ መና ከተማ ኑዋሪ የሆነች በሬዱ ዲንቃ የምትባል ወጣት ሴት በአንድ አመት ከስድስት ወር ጤነኛ የሆነች ሴት ልጅ መገለገሏን ከከተማው ጤና ጣቢያ በደረሰን ዜና ማወቅ ተችሏል፡፡…››የሚል ዜና ተነግሮ ስለነበረ ከመወለዷ የከተማዋ ዝነኛ እና ታወቂ እንድትሆን ተገዳለች፡፡

የኬድሮን ተአምራዊነት በዚህ ብቻ አልተገታም ፤እራሷን ችላ መቀመጥ የጀመረችው በሶስት ወሯ ነው…በስድስተኛ ወሯ መራመድ ጀመረች፤ በአንድ አመቷ በእቤታቸው ውስጥ በኩል ደረጃ ይነገሩ የነበሩትን አማርኛ እና ኦሮሚኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፋ ማውራት ቻለች፡፡
ይሄ ሁኔታዋ  ሰው ሁሉ እንዲፈራትና እንደሌላ ፍጡር እንዲቆጥራት አደረገ፡፡አንዳንዴ እሷ ራሷ ስለራሷ ስታስብ  ያው በአንድ አመት ከስድስት ወር እናቷ ማህፀን ስትቆይ ብዙ ነገር ተምራ ብዙውን ነገር እዛው ጨርሳ የወጣች ይመስላታል…እሷ ምትለው እውነት ከሆነ ደግሞ በዘጠኝ ወራቸው የሚወለዱ የሰው ልጆች እድገታቸውን ሳይጨርሱና ማወቅ ሚገባቸውን ጠንቅቀው ሳያውቁ ፤እራሳቸውን የመርዳት አቅሙ ሳያዳብሩ ቸኩለው እንደሚወለዱ ፍንጭ የሚሰጥ ክስተት ነው ማለት ይቻላል፡፡ለምሳሌ ከሰው ልጅ ውጭ ያለ ሌላ እንስሳት ተመልከቱ…ገና ከመወለዳቸው በራሳቸው ለመቆም ይፍጨረጨራሉ..በቀናት ውስጥ የራሳቸውን ምግብ በራሳቸው ቃርመው መመገብ ይጀምራሉ፡፡ከእናታቸው የሚፈልጉት የተወሰነ የደህንነት ጥበቃ እንድታደርግላቸውና መንገድ እንድታሳያቸው ብቻ ነው  ..የሰው ልጅ ግን ልፍስፍስ ነው…በእናቱ ማህፀን ዘጠኝ ወር አሳልፎ ከተወለደ በኃላ ሌላ ዘጠኝ አመት እናቱ ጉያ ውስጥ ተወትፎ በመነፍረቅ ሲልወሰወስ ይገኛል..በሀያ አመቱ  እንኳን እራሱን ችሎ ከቆመ ጠንካራ ና ጀግና ተብሎ  ይሞገሳል..ሰው እራሱን ለመቻል ለሃያ ረጅም አመታት ማደግ… መማር… መሰልጠን ..መጠንከር ይጠበቅበታል፡፡እሷ ግን እንዲ እንዳልሆነች ገና በጥዋቱ ነው የምታውቀው …፡፡
የእሷ ልዩ መሆነ ከውልደቷ ነው የሚጀመረው ቢባልም እውነታው ግን ከዛም ሳብ ይላል ..ከጽንሰቷ ነው የሚጀምራው…ከአባቷ  ማንነት….

ይቀጥላል
#ትንግርት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


...‹‹ስሚ አሁኑኑ ጨርቅሽን ይዘሽ ከቤቴ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼን ላሳድግበት፡፡ ከፈለግሽ ሽርሙጥና ቤት ግቢና እንደፈለግሽ ሁኚ፤አልፈልግሽም፡፡>> በማለት ጨርቄንና ደብተሮቼን ሠብስባ አስታቅፋኝ እየገፈተረችኝ ከቤቷ አውጥታ አባረረችኝ፡፡

በእንደዚህ ሁኔታ ነበርሰ ታሪኳን ያስረዳችው፡፡ ከዛም እንደ እህቱ አድርጎ ተቀበላት፡፡."

ትምህርቷንም እንድትቀጥል አደረጋት፡፡ በወቅቱ እሱ ጋር ስትመጣ የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ አሁን በዲፕሎማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሦስተኛ አመት ተማሪ ነች፡፡

....ሁሴን የሀሳብ ውቅያኖስ ተንፈራግጦ ሲወጣ እቤቱ ሞቆና ተጫጭሷ ነበር፡፡ ፎዚያ ቅድም የለበሠችውን ልብስ አውልቃ ድርያ ለብሳለች፡፡ ብዙውን ጊዜ የምትሸፍነውን ፀጉሯን በነፃነት ለቃዋለች፡፡ አጭር ቢሆንም ሉጫ ስለሆነ ለውበቷ ልዩ ድምቀት ለግሷታል፡፡

‹‹እሺ ፎዚያ ትምህርት እንዴት ነው?›› አላት፡፡

‹‹አሪፍ ነው፡፡አሁንማ ልጨርስ አራት ወር ብቻ ቀረኝ እኮ!››

‹‹በጊዜ ስራ ፈልጉ ማለትሽ ነው?››

‹‹ለስራው እንኳን ብዙም ጉጉት የለኝም፡፡ ዋናው ተምሬ እዚህ ደረጃ መድረሴ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ዕቅዴ አንተን በተሻለ መንገድ መንከባከብ ነው፡፡››

‹‹እንዴት ባክሽ? እኔን ለመንከባከብ እኮ ሦስት ዓመት ሙሉ ኮሌጅ ገብቶ መማር አያስፈልግሽም ነበር

‹‹...እንዲህ ብለህ አታሳምነኝም...አንተ ለእኔ ምርጥ ወንድሜ ብቻ ሳትሆን አባቴም ጭምር ነህ ፡፡ብዙ ነገር አድርገህልኛል፡፡አላህ አንተን ባይጥልልኝ ኖሮ ዛሬ ዕጣ ክፍሌ የሰው ቤት ግርድና ካልሆነም ሽርሙጥና ነበር፡፡ስለዚህ የእኔ አንተን ለመንከባከብ መወሰን ያንስብሀል እንጂ አይበዛብህም፡፡››

‹‹...ፎዚ ለእኔም እኮ ምርጥ እህት ሆነሽኛል፡፡ ይሁን እንጂ እህትም አንድ ቀን የታለቅ ወንድሟን ቤት ጥላ የራሷን ቤት ትገነባለች፡፡ የወንድም ኃላፊነት ደግሞ እህቱ እዚህ ደረጃ እንድትደርስለት ማበረታታትና መደገፍ ነው፡፡ እርግጥ ነገሮች ቀላል አይደሉም፡፡ እኔም እኮ አንድ ቀን ስራ ይዘሽ ፣የፍቅር ጓደኛ አበጅተሸና ትዳር መስርተሸ ጥለሺኝ እንደምትሄጂ ሳስብ በጣም ይጨንቀኛል፤ ቢሆንም ግን የግድ መቀበል እንዳለብኝ አምናለሁ፡፡

የፈላውን ቡና በመቅዳት ስኳር ጨምራ በማማሰል አቀበለችውና ለራሷም ቀድታ ንግግሯን ቀጠለች፡፡

‹‹እንግዲህ ውሳኔዬ የማይቀየር ነው፡፡ ምን አልባት አግብተህ ባለቤትህ ቤቱን ከተረከበችኝና ከልብ እንደምትንከባከብህ እርግጠኛ ከሆንኩ.. ያኔ ያልከውን አደርግ ይሆናል፡፡›

‹‹ዝም ብለን በባዶ ሜዳ እኮ ነው የምንጨቃጨቀው፡፡>>

‹‹እንዴት ማለት?›› ሁሴን ሊላት የፈለገው ምን እንደሆነ ስላልገባት ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔ አሁን በቅርብ የማገባ ይመስልሻል? >>

‹‹ለምንድነው የማታገባው?››

‹‹ማን ነች ፍቃደኛ ሆና እኔን ልታገባኝ የምትችለው?››

‹‹በጣም ዕድለኛዋ ሴት ነቻ፡፡›› ፎዚያ ከምሯ ነው እውነተኛ ስሜቷን የምታወራው፡፡

‹‹አይምሰልሽ .. በዙሪያዬ ያሉ ሴቶች ሁሉ በፍቅር እንጂ ትዳርን ለሚያህል ቁም ነገር ብቁ እንዳልሆንኩ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡››

‹‹ይሄ አንተን በተመለከተ ትክክለኛ ምልከታ ነው ብዬ አላስብም፡፡›› አለች ቅሬታን በዛለ ድምፅ፡፡

‹‹እንዴት ... ? ሌላው ይቅር በአንቺ አመለካከት እኔ ለትዳር የምሆን ግለሠብ እመስልሻለሁ?›› ሲል ጠየቃት ፡፡

‹‹እውነቱን ልንገርህ?›› በታፈነ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዋ!.. ንገሪኝ ... ትክክለኛ ስሜትሽን ንገሪኝ፡፡››
‹‹እንግዲያው እኔ ሙሉ በሙሉ ያንተ አይነት ወንድ እስከማገኝ ትዳር ሚሉት ነገር አልሞክርም፡፡››
ደነገጠ፡፡ እንደምትወደው ያውቃል፡፡ ይሄን ያህል ተፅዕኖ ውስጥ እንደከተታት ግን ልብ ብሎ አስተውሎት አያውቅም፤ ውይይታቸው ከወትሮው በመጠኑም ቢሆን ጠንከር እያለ ስለመጣበት ርዕስ ለመቀየር ተገደደ፡፡

‹‹ኦ! ይሄ ቡናሽ ልዩ ነው፤ ከደባሪው እራስ ምታቴ ገላገለኝ›› አላት፡፡

‹‹ስለተሻለህ ደስ ብሎኛል፤በነገራችን ላይ ቀን ትንግርት መጥታ ነበር፡፡››

‹‹እንዴት ሳትደውልልኝ መጣች ..…?››

‹‹እኔ እንጃ፡፡ ሁኔታዋ ግን ከወትሮው የተለየ ሆነብኝ፡፡ ሁሉ ነገሯ ወደ ኖርማል ተመልሷል... አገባች እንዴ?›› የገረማትን ነገር ጠየቀችው፡፡

‹‹አይመስለኝም.. ስራ ግን ቀይራለች›› መለሠላት፡፡

<<ለማንኛውም የሆነ ዕቃ አምጥታልሃለች፡፡ >>

‹‹ምን አይነት ዕቃ? >> ለማወቅ በተጣደፈ ስሜት ጠየቃት፡፡

‹‹እኔ እንጃ ሥዕል መሠለኝ፤ታሽጓል፡፡ መኝታ ቤት አስቀምጬልሀለሁ፡፡››

ተስፈንጥሮ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ፡፡ በግምት ሠማንያ በስልሳ የሚሆን በፍሬም የተወጠረ፤ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ሸራ አገኘ፡፡ በጥድፊያ ልባሱን አነሳው፡፡የሚያፈዝ ስዕል ነው፡፡ የጥንት ንግስቶች የሚለብሱትን አይነት አብረቅራቂ ወርቀዘቦ ልብስ የለበሠች እንስት ትታያለች፡፡ እግሮቿ መሬት አይረገጡም፡፡ በአየር ላይ የምትራመድ ትመስላለች፡፡ ፀጉሯን ንፋሱ እያንሳፈፈው በአየር ላይ ተበታትኖ ሲታይ ሰማይ ጠቀስ ማማ ላይ የተሰቀለ የታላቅ ሀገር የተከበረ ባንዲራ ይመስላል የእጆቿ ጣቶች ውበታቸው የገነት ደናግሎችን አይነት ነው፡፡ በቀኝ እጇ ዓይነ ሥውሮች የሚጠቀሙበትን አቅጣጫ መጠቆሚያ ነጭ ዘንግ ይዛለች፡፡ ፊቷ የተለየ ነው፡፡ እንደ ሠው ዓይን፣ አፍንጫ፤ ከንፈር ሳይሆን በቦታው የሙሉ ጨረቃ ቅርፅ ይታያል፡፡ በጨረቃዋ ዙሪያም በህብረ ቀለም የደመቀ የብርሃን አምድ ያንፀባርቃል፡፡የሥዕሉ ጥልቀትና ምጥቀት... ውስጡ የተዳፈነውን የፍቅር እቶን ቀሠቀሠበት፡፡ የናፍቆት እሳት መላ ሰውነቱን ሲለበልበው ተሠማው፡፡

ትንግርት መጽናኛ የሚሆነውን ውድ ስጦታ ስላበረከተችለት ከልብ አመሠገናት፡፡ ፊት አልባ ሥዕል የተሳለላት ድብቋ ደራሲ ግን በምን ተአምር በአካል ሊያገኛት እንደሚችል ከመቼውም ጊዜ በላይ ግራ ገባው፡፡ ስዕሉን እንደታቀፈ ወደ አልጋው ሄደና በጥንቃቄ ተኛ፡፡ የቀለሙ ሽታ ከደራሲዋ ሰውነት የሚመነጭ መግደላዊት ማሪያም የክርስቶስን እግር ያጠበችበትን የአልባስጥሮስ ሽቶ አይነት እንደሆነ ሁሉ በረጅሙ ስቦ ወደ ውስጡ ማገው.. የስሜቱ ጥጋ.. ጥግ ድረስ ገብቶ ለውስጡ ሀሴት እንዲሰጠው በመመኘት ፡፡ በስዕሏ ፋንታ ዋናዋንም አንድ ቀን በአካል አግኝቷት እዚሁ አልጋው ላይ እንዲህ አቅፎት በእጆቹ እየዳበሳት..በከንፈሮቹ እየመጠጣት. በትንፋሹ እያጋላት... በሙቀቱ እያቀለጣት... በፍቅሩ እያሰከራት አብሯት እንደሚተኛ ተስፋ በማድረግ…፡፡...

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች  በባለፈው #ፖስት 10 ሰው ብዬ 2 ሰው ብቻ ነው #ሰብስክራይብ ያደረገው 10 ሰው #ሰብስክራይብ አድርጉና ቀን በቀን እንልቀቅ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ እሷን ላለመረበሽ ስትል የተኛች መስላ አደፈጠች..እናም.ቅድም ወዳቋረጠችው ትዝታ ተመልሳ ገባች፡፡

ከ11 አመት በፊት ጥቅምት- 2004

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተምራ ለመመረቅ ቸኩላ ነበር፡የቸኮለችው ግን ለግል ደስታዋና እራሷን ለመቻል ካላት ጉጉትና ፍላጎት ብቻ አልነበረም፡፡ዋናው ለአባቷ ስትል ነበር፡፡ለአባቷ ምቹ  ሁኔታ መፍጠር እንዳለባት ፅኑ እምነት  ስላላት ነበር፡፡ቀና ብሎ እንዲኖር፤ቢያንስ ከጓደኞቹ ጋር ውጭ ውሎ እንዲገባ..ከጓደኞቹ ጋር ቀብር ሲሄድ፤ሰርግ ቤት ወዳጆቹ ሲጠሩት ብድግ ብሎ ሄዶ ከሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ውሎ ስቆና ተደስቶ አንዲመጣ፡፡አዎ ለእሱ ለሁለት እግሮቹ የሚሆኑ ዘመናዊ አርቴፊሻል እግሮች እና እሱ ሊነዳት የሚችል አንድ መኪና ልትገዛለት፡፡ይሄ የህይወቷ ትልቁ ምኞቷ ነበር፡፡ግን ማይታሰብ ነው የሆነባት፤በወቅቱ ጭራሽ እራሷንም ማኖር እየከበዳት ነበር ፡፡ይባስ ብሎ በዛው ወር   አባቷን ልታየው ወደ ትውልድ ከተማዋ አሰላ ሄዳ ነበር፡፡አባቷም ትንሹ  ወንድሟም ስለናፈቋት ተነሳችና ሄደች፡፡ስትደርስ  አባቷ  ሳሎን በእጅ የሚገፋ ማንዋል ዊልቸሩ ላይ ቁጭ ብሎ ነጭ ጋቢ ተከናንቦ ፊት ለፊቱ ያለ ቴሌቪዥን ላይ አይኖቹን ተክሎ እያየ ነበር፡፡ የበራፉ መንገጫገጭ  ድምፅ አነቃውና ፊቱን ወደበራፉ ዞር አደረገ..ፊቱ በአንዴ እንደ ጠዋት ፀሀይ ብርሀን ረጨ…ቦርሳዋን እዛው በራፍ ላይ ጥላ ተንደርድራ በመሄድ ሶፋው ላይ ሙሉ በሙሉ ዘላ ወጣችና አባቷ አንገት ላይ  ተጠመጠመችበት…እጁን  ዘረጋና ግራና ቀኝ ፊቷን እያገላበጠ ጉንጮቿን ሳማት፡፡
‹‹የእኔ እንቁ..በሰላም ነው…?እንዴት መጣሽ?››

‹‹ምን ማለት ነው?አልናፈቅኩህም እንዴ…?እንደዛ ከሆነ ተመልሼ መሄድ እችላለሁ››አለች የውሸት እንደማኩረፍ ብላ..፡፡
‹‹አንቺ እኮ ፀሀዬ ነሽ..ማነው ፀሀይ ጥዋት ስለወጣችለትና ስለነጋለት የሚከፋው…እንዲሁ ሳትደውይ ድንገት ብርት በማለትሽ ምን ገጥሟት ይሆን ብዬ ነው?››

‹‹አይ ደህና ነኝ…ሰርፐራይዝ ላድርጋችሁ ብዬ ነው፡፡››ስትል እንጀራ እናቷ ከኋለኛው ክፍል ውስጥ ተወዳጁን ታናሽ ወንድሟን እጁን እየጎተተች  መጣች፡፡‹‹እንዴ አባትና ልጅ በምስጢር ተጠራርታችሁ ትገናኙ ጀመር?››አለቻት  የእንጀራ እናቷ ስንዱ፡፡
‹‹ምነው ቀናሽ እንዴ?››

‹‹ብቀናስ…መብት የለኝም?›እያለች ወደ እሷ ተጠጋችና ጉንጭ ለጉንጭ  በመሳሳም የሞቀና የደመቀ ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡

አዎ የዛን ጊዜ አባትዬውን ልትጠይቅ አሰላ በሄደች ጊዜ በማግስቱ  አባትዬውን ልታዝናና ወደከተማ ይዛ ለመውጣት ፈልጋ ልብስ እየቀየረችለት ነበር…
‹‹አባዬ ይሄኛው ጃኬት ይሻልሀል?››

‹‹ልጄ አሁን ቤታችን ብናሰልፍስ..?ይሄ እኮ የተወለድሽበትና ያደገሽበት ሀገር ነው፤ብዙ የምታውቂያቸው ሰዎች ብዙ ጓደኞች አሉሽ.››.

‹‹እና? ››

‹‹እናማ እኔን እያንጓተቱ በአስፓልት ላይ መሄድ …››

‹‹አይ አባዬ..ትቀልዳለህ እንዴ.?አንተ እኮ ሁለ ነገሬ ነህ..አይቻልም እንጂ ቢቻል አንገቴ ላይ አንጠልጥዬ በየሄድኩበት ይዤህ ብዞር  በደረስኩበት  ሁሉ  ከጎኔ ብትኖር ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አባዬ አንተ እኮ ጌጤ ነህ…አለሜ፡፡››

‹‹ይሁንልሽ ልጄ …››ሲል ተሸነፈላት፡፡

ቤተክርስቲያን ይዛው ሄደች..ከዛ ሆቴል ይዛው ገባች፡፡ አዝናናችው..፡፡ ወደማታ ሲሆን ወደቤት ይዛው ገባች፡፡ ከቤተሰብ ጋር ስትስቅና ስትደሰት አመሸች፡፡ በበፊት መኝታ ክፍሏ ትንሹ ወንድሟን አቅፋ ተኛች፡፡

ለሊት በመነሳት ባልና ሚስቱን ቀሰቀሰችና አባቷን ወደ ቤተክርስቲያን ይዛው ሄደች፡፡ ሶስት ሰዓት ሲመለሱ ቁርስ ተዘጋጅቶ በልተው እስከ  ስድስት  ሰዓት  ቆየችና በማግስቱ ስራ ለመግባት ወደአዲስ አበባ ለመሄድ ተነሳች፡፡ በዚህ  ጊዜ ስንዱ በኩርቱ ፌስታል ሙሉ እቃ ይዛ ከጓዳ ወጣችና ወለሉ መሀከል ከሻንጣዋ ጎን አስቀመጠችው፡፡

‹‹ምንድነው ይሄ ደግሞ? አንቺ መቼስ ዘላለምሽን ኮተት አታጪም..ተማሪ  ሆኜ እሺ፤አሁንም አታቆሚም?››ነበር ያለቻት፡፡
‹‹አንቺ የእናት እጅ ለዘላለም እምቢ አይባልም››

ተከራክራ እንደማታሸንፋት ስለምታውቅ ወደአባቷ ሄደችና..አገላብጣ ስማ ተሰናበተችው፡፡ በቀጣይ እንጀራ እናቷን ተሰናብታ 500 መቶ ብር እጇ ላይ አስቀመጠችና ወንድሟን ወደላይ አንስታ አገላብጣ ስማው ለመሄድ ተዘጋጀች፡፡
የእንጀራ እናቷ ስንዱ ብሩን ለመመለስ ጣረች ‹‹ኸረ አይሆንም .አንቺ ከየት ታመጪዋለሽ?፡››ብላ ብትከራከራትም አልሰማቻትም፡፡ ብሩን የምትመልሺ ከሆነ እኔም የቋጠርሽልኝን ነገር ጥዬ ነው የምሄደው ብላ ስታስፈራራት ነበር በሃሳቧ የተስማማችው፡፡

አባትዬው መሀል ሳይገባ በትዝብት ሁለቱንም ይመለከት ነበር.እውነት ሳባ ከልቧ ለቤተሰቡ ብዙ ነገር ለማድረግ ፍላጎትም ምኞትም ነበራት…ግን  በወቅቱ ሁሉ ነገር ከአቅሟ በላይ ነበር፡በአራት ሺ ብር የወር ደሞዝ እራሷንም ማኖር በጣም እየከበዳት ነበር፡፡እነሱን ለመጠየቅ ለምትመጣበት እና ያንን ብር እንጀራ እናቷ እጅ ላይ ለማስቀመጥ አንኳን ብዙ ፍላጎቶቿን መግደልና ምቾቶቿን መስዋእት ማድረግ ነበረባት..አንባዋ እንዳቀረረ አባቷን በድጋሚ ስማ ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ ከበራፍ ላይ ባጃጅ አስቆመችና መናኸሪያ ድረስ አደረሳት፡፡

ወደአዲስ አበባዋ ተመለሰች…ማታ ከመተኛቷ በፊት ስንዱ የቋጠረችላትን ፌስታል ከፈተች፡፡ ውስጥ ያሉትን ቋጠሮዎች ዘረገፈችና…ተራ በተራ ማየት ጀመረች ሽሮ፤በርበሬ፤ምስር ክክ፤አተር ክክ የቀረ ነገር የለም፡፡
‹‹ይህቺ እኮ ከእናትም በላይ ነች››አለችና በጉንጮቿ ያለፍቃዷ   የሚንኳለለውን ዕንባ አበሰችና ፒጃማ ፈልጋ ቦርሳዋን ከፈተች፡፡ የተጣጠፈ ካኪ ወረቀት አገኘች፡፡

ግራ ገብቷት አነሳችውና ውስጡን ስትከፍት የተጠቀለለ በዛ ያለ ብር አገኘች. ወረቀቱን ዳግመኛ አነሳች፤ውስጡን ገለጠችው፤የአባቷ የእጅ ፅሁፍ ነበር፡፡

‹‹ለታክሲ ትሆንሻለች ብዬ ነው፡፡እንደሚቸግርሽ  አውቃለሁ  ግን ታውቂያለሽ እንደልቤ መሻት ላግዝሸ አልቻልኩም፡፡ አይዞሽ  ትንሽ  ወር  ነው  ነገሮች ይስተካከላሉ እስከዛው እንደምንም በርቺልኝ...ደግሞ አንቺ የእኔ ልጅ ነሽ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ትችያለሽ››ይላል፡፡

ደብዳቤውን ጨምድዳ ወለሉ ላይ ወረወረች…በእንጀራ እናቷ ገደብ  በሌለው ደግነት ተነክታ የጀመረችውን ለቅሶ በሰፊው ለቀቀችው..ብሩን አነሳችና ቆጠረችው…ሶስት ሺ ብር ነው፡፡
‹‹አሁን እኔ ሰው ነኝ....ተማሪም ሆኜ የቤተሰቦቼ ሸክም….አሁንም  ስራ  ይዤ ለዛውም አባቴ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እያለ ከእነሱ ብር መቀበል…››በዛን ቀን ሁሉ ነገር ነበር ያስጠላት …ህይወት እራሱ አስጠላቻት…የሆነ ነገር መቀየር እንዳለባት ተሰማት…አዎ የህይወቷን መስመር ማስተካከል እንዳለባት ወሰነች፡፡ አዎ እንደዛ ነው የተሰማት…‹‹ወይ እንደምንም ቀልጠፍጠፍ ብዬ የተሻለ ደሞዝ የሚያስገኝ የተሻለ ሰራ ማግኘት አለብኝ፡፡ አልያም ደግሞ ረከስ ያለ ኑሮ የሚገኝበት ክፍለሀገር ሄጄ መኖር.›ስትል ነበር የወሰነችው፡፡
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ናኦል የእህቱን ድምፅ ከሰማ አራት ቀናት አልፎታል፡፡ይሄ ያልተለመደና ሊታሰብ የማይችል ነገር ነው፡፡እህቱ ቢዚ ብትሆን እንኳን አራት ቀን ሙሉ ቢያንስ ሚሴጅ ትልክለታለች ወይም ኢሜል ትልክለታለች እንጂ እንዲሁ ዝም ልትለው አትችልም፡፡እንዲህ አይነት ነገር አላስለመደችውም፡፡በተለይ የመጨረሻ ጊዜ ስትደውልለት በመጥፎ አየር ፀባይ ወደብራዚል መድረስ አቅቷቸው ያልሆነ ከተማ አርፋ አልጋ ክፍል ሆና ነበር የደወለችለት፡፡የአየር ፀባዩ ከተስተካከለ በማግስቱ ወደብራዚል በረራውን እንደምትቀጥልም ነግራው እሱም አምኗት ነበር፡፡በማግስቱ ትደውልልኛለች ብሎ ጠብቆ ነበር፡፡ማህበራዊ ሚዲያ ላይም ደጋግሞ ሊያገኛት ሞክሯል ፡፡፡ግን ምንም አይነት እንቀስቃሴ የለም፡፡ሚሲጅም ላከላት.. ኢሚልም ደጋግሞ ፃፈላት፡፡መልስ የለም፡፡መስራቤቷ ሄዶ አመለከተ..የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተፈጥሮ ጥበቃ መስሪያ ቤት ጋር ተፃፅፈው የሚያገኙትን አዲስ መረጃ ከለ ወዲያውኑ እንደሚያሳውቁት ነገረው ሸኑት፡፡የሄደችበትን ድርጅት ድህረ-ገፅ ፈልጎ መረጃ ማሰስ ጀመረ…በአራተኛው ቀን ማታ እቤቱ ቁጭ ብሎ በትካዜ ላይ ሳለ ሰውነት የሚያርድ ልብ የሚያቆም ዜና ከድህረ ገፅ ላይ አነበበ፡፡
‹‹ለተግባራዊ ስልጠና ከፔሩ ወደብራዚል ስትሄድ በአየር ፀባይ መበላሸት ምክንያት ፔሩ ኢኩዩቶስ ከተማ አርፋ የነበረችው ኢትዬጴያዊቷ የተፈጥሮ ጥበቃ ባለሞያ ኑሀሚ በቀለ የገባችበት ጠፋ፡፡ወጣቷ የተፈጥሮ ጥበቃ ኢኬስፐርት አንድ ሆቴል ውስጥ ከአንድ ግለሰብ ጋር አብራ ያደረችና ጥዋትም በታክሲ ተሳፍራ ወደኤርፖርት ጉዞ እንደጀመረች ከሆቴሉ ሰራተኞች ማጣራት ቢቻልም ከዛ በኃላ ግን ኤርፖርት እንዳልደረሰች ታውቋል፡፡ምን አልባትም ወደሀገሯ መመለስ ስላልፈገች እራሷን ሰውራ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ፖሊሶች ግምታቸውን የተናገሩ ሲሆን ፍለጋው ግን መቀጠሉን ታውቋል›› ይላል፡፡
ጮኸ…ኡ..ኡ ብሎ ጨኸ፡፡ግድግዳው ላይ የተንጠለጠለውን መስታወት በቦክስ ነረተው፡፡መስታወቱ ተፈረካክሶ ወለሉን ሞላው፡፡እጁን ሁለት ቦታ ሸረከተውና በደም ታጠበ…ሰራተኛዋ በርግጋ በውስጥ ልብሷ ብቻ መኝታዋን ለቃ መጥታ ፊቱ እስክትቆም ድርስ እራሱን እንደመሳት አድረጎት ነበር…በሶስት መቶ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቤታቸው የተኙ ጎሮቤቶች ከእንቅልፋቸው ባነው ግራ እስኪጋቡ ድረስ ነው የጮኸው፡፡
‹‹እህቴ የደሀዋ ኢትዬጵያ ዜጋ ልትሆን ትችላለች..ግን ደግሞ የእኔ እህት ነች…..እኔን ትታ ገነትም ቢሆን መቅረት አትፈልግም…እህቴ አንድ ነገር ሆናለች፡፡እህቴ ታፋናለች፡፡››
‹‹ምንድነው …..ምን ሆነህ ነው…..?ኑሀሚ ምን ሆነች?››ሰራተኛዋ ነች የምትጠይቀው፡፡
‹‹በሄደችበት ሀገር ጠፋች ነው የሚሉት..ሰው እንዴት ዝም ብሎ ይጠፋል….?እህቴን ወንጀለኞች አፍነዋት ነው፡፡››
ከእጁ እየተንጠባጠበ ያለውን ደም በጨርቅ እያሰረችለት‹‹ተረጋጋ እስኪ…የሰው ሀገር አይደለች ያለችው ..ምን አልባት መንገድ ጠፍቷት ያልሆነ ስፍራ ገብታ ያልሆኑ ሰዎች እጅ ወድቃ ሊሆን ይችላል ፡፡››ስትል
…ልታፅናናው ሞከረች፡፡
‹‹አንቺ ደግሞ ከፊቴ ጥፊ …መንገድ የሚጠፋት እንደአንቺ ደንባራ ነገር አደረግሻት እንዴ?፡፡›› አበሳጨችው፡፡
‹‹ያው ማንኛውም ሰው በሰው ሀገር ሲሆን መደናበሩ ይቀራል?››
ከተቀመጠበት ተነሳና ጀኬቱን ከሶፋው ላይ አነሳ …ወደመኝታ ቤቱ ሄደና የመሳቢያውን ኪስ ከፍቶ የሆነ ያህል ብር በማውጣት በኪሱ ጨመረ …ከሌለኛው መሳቢያ ሽጉጥ አወጣና በጀርባው ሽጦ ወጣ ፡፡ሰራተኛዋ ሳሎኑ መሀከል ተገትራ ግራ በመጋባት እየጠበቀችው ነበር፡፡ቀጥታ ወደሳሎኑ በራፍ ሄዶ መክፈት ጀመረ፡፡
‹‹እንዴ ብቻህን በውድቅት ለሊት ወዴት ነው…?በዛ ላይ ቆስለሀል…ልብስ ልልበስና አብሬህ ልምጣ›››አለችው፡፡
‹‹ወዴት ነው የምትመጪው?››
‹‹ወዴት ማለት ምን ማለት ነው…?ለእኔም እኮ እህቴ ነች …ልፈልጋት ነዋ፡፡››
‹‹አሀ ልትፈልጌት ..ደቡብ አሜሪካ?››
‹‹የትስ ቢሆን እንኳን ሰው ከብትም ጠፍቶ ዝም ተብሎ መቀመጥ ይቻላል እንዴ?፡፡››
እንግዲያው ደቡብ አሜሪካ ትንሽ እራቅ ስለሚል ወፈር ያለ ልብስ ልበሺ ደግሞም የእግር መንገድ ስላለው ደህና ጫማ አድርጊ››አላት፡፡
‹‹ደግ…መጣሁ ቆየኝ ››አለችና ተንደርድራ ወደመኝታ ቤቷ ሄደች፡፡ይንን ንግግር በሰላሙ ጊዜ ሰምቶት ቢሆን ኖሮ ሆዱን ይዞ እስኪያመው ይስቅ ነበር፡፡ዛሬ ግን አይችልም፡፡
‹‹አለማወቅ ደጉ ››አለና ሳሎኑን ከፍቶ ወጣና ዘግቶ ቀጥታ ወደውጨኛው የአጥር በራፍ ሔደ..ወለል አድርጎ ከፈተውና ፒካፕ መኪናውን አስነስቶ ግቢውንም አካባቢውን ለቆ ወጣ፡፡
አስራአምስት ደቂቃ ከነዳ በኃላ ስልኩን አንስቶ አንድ አእምሮ ውስጥ በስውር የተቀመጠ ቁጥር አስታወሰና‹‹አስቸኳይ›› ብሎ ፃፈበትና ላከው፡፡እዚህ ቁጥር ላይ ሲፅፍ ከሶስት አመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡የሞትና የሽረት ጉዳይ ካልሆነ እንዳይደውል ተነግሮታል፡፡እና ሁል ጊዜ መደወል ወይም መልዕክት መላክ ይፈልግና ግን ደግሞ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ እንደቀልድ ችላ ማለት ስለማይችል ውጦ ስሜቱን ያዳፍነዋል፡፡ያም ቢሆን ግን ስለጤንነቷና ስለለችበት ሁኔታ በተዘዋዋሪም ቢሆን በየጊዜው ያረጋግጣል፡፡ ግን አሁን ጊዜው ደርሷል…ለእሱ ከእህቱ መጥፋት በበለጠ የህይወት እና የሞት ሽረት ጉዳይ የለም...ለዛ ነው ይሄን መልዕክት በድፍረት የላከላት፡፡
መልዕክቱ የተላከው ምስራቅ የምትባል በእሱም ሆነ በእህቱ ህይወት ላይ ከፍተኛ ድርሻ እና ተፅዕኖ ያላት የደህንነት ሰው ስልክ ላይ ነው፡፡አሁን ካጋጠመው ችግር መፍትሄ ልታስገኝለት የምትችል በምድር ላይ አንድ ትክክለኛ ሰው ብትኖር እሷ ነች፡፡እሷ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከአለም አቀፍ የዲፕሎማሲው ማህብረሰብ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ስላላት የሆነ ነገር ልታደርግለት እንደምትችል እርግጠኛ ነው፡፡
ቀጥታ ወደ እስታዲዬም ነው የነዳው፡፡መስቀል አደባባይ ሲደርስ መኪናውን አቆመና ወደ መቀመጫወቹ በመሄድ ኩርምት ብሎ ተቀመጠ፡፡በዛ በውድቅት ለሊት በሰባት ሰዓት አልፎ አልፎ ውር ውር ከሚሉ መኪኖች ውጭ አካባቢው ጭር እንዳለ ነው፡፡ብርዱ ግን ያንሰፈስፋል፡፡የጃኬቱን ዚፕ አንሸራተተና ወደላይ ቆለፈው፡፡ይሄንን ብርድ እና ስቃይ ያውቀዋል ፡፡ሰውነቱ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ ውስጥም ጭምር ነው ያለው፡፡ በርካታ አመታት በዛ በጮርቃ እድሜው ከአንዲቷና ከተወዳጅ እህቱ ጋር በረንዳ ኖሮ ያውቀዋል፡፡አሁን መልዕክት ልኮላት እስክትመልስለት ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ በብርድ እየተጠበሰ የሚጠብቃት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት እንዳገኘቻቸው በትዝታ አመታትን ወደኃላ ተመልሷ ማመንዠግ ጀመረ ፡፡የ12 አመት ጮርቃ ታዳጊ እያሉ እንደተለመደው 22 በሚገኝ በረንዳቸው ላይ በተለመደው መልኩ ተኝተው ነበር፡፡ሰዓቱ ልክ አሁን ባለበት ተመሳሳይ ሰዓት ላይ ነው ፡፡ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ፡፡እሱና እህቱ እርስ በርስ ተቃቅፈው አሮጌ ብርድልብስና ከላይ ጆንያ ደርበውበት ጋደም ብለው ወጪ ወራጁን በማየት ላይ ነበሩ፡፡
‹‹ምነው ወንድሜ እንቅልፍ እምቢ አለህ እንዴ?››ስትል ኑሀሚ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እህቴ…ያቺን ሴትዬ አየሻት?››
‹‹የቷን?››
‹‹ያቺ ከስልክ ፖሉ አጠገብ ያለችው ልጅ፡፡››
ከትከሻዋ ቀና አለችና አየቻት‹‹አዲሷን ልጅ እያልከኝ ነው?››
‹‹አዎ…አዲሷን ልጅ…፡፡››