አትሮኖስ
228K subscribers
104 photos
3 videos
41 files
303 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ስምንት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የጣርያው ስር ክፍል

የጠዋቱ አራት ሰዓት መጣ፣ ሄደ፡

በየቀኑ ከሚመጣልን ምግብ የሚተርፈንን በቤቱ ውስጥ ቀዝቃዛ ሆኖ ባገኘነው በልብስ ማስቀመጫ መሳቢያው ስር አስቀመጥነው፡ በሌላኛው የህንፃው ክፍል አልጋ በማንጠፍ ላይ ያሉት ሠራተኞች ቀጥሎ ደግሞ ወደ ታችኛው ክፍል
መውረዳቸው ስለማይቀር ይህንን ክፍል ለሚቀጥሉት አራት ሰዓታት
አያዩትም፡

እኛም ክፍሉ ስለሰለቸንና የተመደበችልንን የተወሰነች ቦታ በደንብ ለማየት ስለጓጓን የመንትዮቹን እጆች ይዘን ልብሶቻችንን የያዙት ሻንጣዎች ወዳሉበት የልብስ ሳጥን በፀጥታ አመራን፡ እስካሁን ልብሶቻችንን ከሻንጣ አላወጣንም ነገ ብዙ የሚያማምሩ ክፍሎች ወዳሉበት ትልቁ ቤት ስንገባ፣ ልክ ፊልሞች
ላይ እንደምናየው እኛ ለመጫወት ወደ ውጪ ስንወጣ ሠራተኞቹ ደግሞ ሻንጣዎቻችንን ከፍተው ልብሶቻችንን ያስተካክሉልናል በወሩ መጨረሻ ላይ ባለው አርብ ሠራተኞቹ ለማፅዳት ሲመጡ በእርግጠኝነት እዚህ ክፍል ውስጥ አንኖርም።

በትልቁ ወንድሜ መሪነት ወደ ጨለማው፣ ጠባቡና ዳገታማው ደረጃ አመራን የመተላለፊያው ግድግዳዎች ጠባብ ከመሆናቸው የተነሳ በትከሻዎቻችን
እየታከክናቸው ማለፍ ነበረብን፡፡

“ያውና!”

ጣራ ስር የሚሰሩ ብዙ ክፍሎች አይተን የምናውቅ ቢሆንም ይሄኛው ግን በጣም የተለየ ነው በቆምንበት ተገትረን ዙሪያውን በጥርጣሬ ተመለከትን ክፍሉ ጨለም ያለ ሲሆን ቆሻሻና አቧራማ ነው ከአቧራው የተነሳ ሩቅ ያሉት ግድግዳዎቹን ማየት የማይቻል ነበር የሆነ ሞቶ ሳይቀበር የቀረ ነገር ሳይኖር አይቀርም መሰለኝ ሽታው ንፁህ አይደለም፡ ክፍሉ በአቧራ
በመሸፈኑ ምክንያት በተለይ ጨለም ባሉት ጥጋጥጎች ላይ ያለው ሁሉም ነገር የሚንቀሳቀስ
ይመስላል።

ከመግቢያው ባሻገር አራት መስኮቶች ከጀርባው ደግሞ ሌሎች አራት መስኮቶች ሲኖሩት ጎንና ጎኑ ግን መስኮት የለበትም በደንብ ካልተጠጉ በስተቀር ምን
እንዳለ ማየት አይቻልም ተራ በተራ

ከደረጃው ላይ ወረድን፡

ወለሉ ከእንጨት የተሰራ ሲሆን ለስላሳና የበሰበሰ ነው። በፍርሀት ስሜት እየተጠነቀቅን ቀስ እያልን ስንራመድ ወለሉ ላይ ያሉት ነፍሳት በሁሉም አቅጣጫ ተርመሰመሱ ክፍሉ ብዙ ቤቶችን ሊያሳምር የሚበቃ ቁሳቁስ ተቀምጦበታል ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ነገሮች የተሸፈኑበት ነጭ ጨርቅ
አቧራው ለብሶ ግራጫ ሆኗል፡ የተሸፈኑትን ዕቃዎች ዝም ብዬ ስመለከት የሚያንሾካሹኩ ጣዕረሞቶች ስለመሰሉኝ ጀርባዬን በረደኝ፡፡

ራቅ ያለውን ግድግዳ ተደግፈው በመደዳ የቆሙ ጌጠኛ ቁምሳጥኖች አየን ጠጋ ብለን ስንመለከት እያንዳንዳቸው በጥንታዊ ልብሶች የተሞሉ ሆነው
አገኘናቸው: እኔና ክሪስቶፈር በጥርጣሬ እየተመለከትናቸው ሳለን መንትዮቹ ደግሞ እኛ ላይ ተለጥፈው በትላልቅና በፈሩ አይኖቻቸው ዙሪያውን ያጤናሉ።

“እዚህ ይሞቃል ካቲ” አለች ኬሪ

“አዎ ይሞቃል”

“እዚህ መሆን አስጠልቶኛል!”

ወደ ኮሪ ስመለከት ትንሽ ፊቱ በፍርሀት ተውጧል ዙሪያውን እየተመለከተ ጎኔ ልጥፍ ብሏል በድሮ ሰዎች ልብሶችና አለባበሶች መመሰጤን አቁሜ የእሱንና የኬሪን እጆች ግራና ቀኝ ያዝኩና ሁላችንም ይህን ቦታ እንዴት
እንደምናደርገው ማሰብ ጀመርን፡ መታየት ያለበት ነው፡ በሺዎች የሚቆጠሩ አሮጌ መፃህፍት፣ ጥቋቁር የሂሳብ ሰነዶች፣ የቢሮ ጠረጴዛዎች ሁለት ትልልቅ ፒያኖዎች ሬዲዮኖች፣ በሁሉም መጠንና ቅርፅ ያሉ የቀሚስ
አይነቶች የወፍ ጎጆ ከነመስቀያው መጥረጊያ፣ አካፋዎች፣ በፍሬም ውስጥ የተቀመጡ የሞቱ ዘመዶቻችን ፎቶግራፎች ይታያሉ። ፎቶግራፉ ላይ ያሉት
ሰዎች አንዳንዶቹ ቀላ ያሉ አንዳንዶቹ ጥቁር ፀጉር ያላቸው ሲሆኑ ሁሉም በሚባል አይነት የሚያስፈሩ፣ ጨካኝ፣ መራራ፣ ያዘኑ፣ ተስፋየለሾችና ባዶ
አይኖች ያሏቸው ናቸው እምላለሁ አንዳቸውም ደስተኛ አይኖች የሏቸውም።አንዳንዶቹ ፈገግ ብለዋል ብዙዎቹ ግን አላሉም አንድ በመጠኑ ፈገግ ያለች፣ እድሜዋ ምናልባት አስራስምንት አመት የሚሆናት ልጅ ፎቶ ቀልቤን
ሳበው ፈገግታዋ ሞናሊዛን አስታወሰኝ፡ ይቺ ግን የበለጠ ቆንጆ ናት።ጡቶቿ ተለቅ ያሉ ከመሆናቸው የተነሳ ክሪስቶፈር አንዱን ቀሚስ እያመለከተ
“የእሷ ነው!” አለ

“ቁንጅና ማለት ይሄ ነው” አለ በአድናቆት ተሞልቶ :: የተርብ የመሰለ ወገብ፣ ሞላ ያለ ዳሌ፣ ጎላ ያሉ ጡቶች: ካቲ… እንደዚህ አይነት ቅርፅ ቢኖርሽ ሀብታም ትሆኚ ነበር:"

“እውነት?” አልኩት በመሰላቸት፡ “ምንም አታውቅም ማለት ነው ይህ የሴት ተፈጥሯዊ ቅርፅ አይደለም ከውስጥ ኩርሲ ለብሳ ነው፡ ኩርሲው ወገቧን አጣብቆ ይይዛትና ከላይና ከታች ያለውን ጎላ አድርጎ እንዲታይ ያደርገዋል ''
“የሌለው ስለጨመቅሽው አይወጣም” አለ፡ ሌላ ቅርፅዋ የሚያምር ወጣት ሴት ተመለከተና “ታውቂያለሽ የሆነ ነገሯ እናታችንን ይመስላል፡ ፀጉር አሰራሯ ቢቀየርና ዘመናዊ ልብስ ብትለብስ ቁርጥ እሷን ነው የምትመስለው:"

“ይህቺ ልጅ ደስ ትላለች እናታችን ግን የበለጠ ውብ ናት” ብሎ አጠቃለለ

ይሄ ትልቅ ቦታ ፀጥታና ጭር ያለ ከመሆኑ የተነሳ የራስን የልብ ትርታ
መስማት ይቻላል ሆኖም ግን እያንዳንዱን ነገር መመርመር፣ እያንዳንዱ ሳጥን ውስጥ ያለውን መፈተሽ፣ እነዚያን ያረጁና የሚሸቱ ልብሶች መሞከርና እንደነሱ ማስመሰል ደስ የሚል ነገር ነበር ግን በጣም ይሞቃል። ያፍናል
ሳምባዬ ከሰበሰበው አቧራና ቆሻሻ አየር የተነሳ የተዘጋ መሰለኝ፡
ክሪስቶፈር መንትዮቹ ማማረር እንደጀመሩ ስለተመለከተ። “አሁን ተመልከቱ መስኮቶቹን በትንሹ እንከፍታቸዋለን፡ ከዚያ ንፁህ አየር በትንሹም ቢሆን ይገባል ማንም ሰው ከምድር ሆኖ የመስኮቶቹን መከፈት ማየት አይችልም::”
አለ፡፡ ከዚያ እጄን ለቀቀና ሳጥኖቹንና ዕቃዎቹን እየዘለለ ትቶኝ ወደ ፊት ሮጠ፡ ከዚያ የማይታይበት ቦታ ሆኖ ኑ ያገኘሁትን ተመልከቱ!” ሲል
ተጣራ ድምፁ ውስጥ መደነቅ ይሰማል።

የሆነ ደስ የሚል አስገራሚ ነገር ለማየት ሮጥን፡ ያሳየን ግን አንድ ክፍል ነው ክፍሉ ቀለም አልተቀባም ግን ኮርኒስ ነበረው፡ ፊት ለፊት ያለውን መቀመጫ ስንመለከት ክፍሉ ለአምስት ልጆች የሚሆን የመማሪያ ክፍል
ይመስላል ክፍሉ ውስጥ ከተቀመጠው ባረጁ መፃህፍት ከተሞላው መደርደሪ? በላይ ጥቁር ሰሌዳ ተሰቅሏል፡ የእኔ ሁሉንም እውቀት ፈላጊ! ወዲያውኑ የመፅሀፍቱን ርዕሶች ጮክ ብሎ ማንበብ ጀመረ፡ መፃህፍቱ ስሜቱን ከፍ
ለማድረግ በቂ ነበሩ ወደ ሌላ አለማት የማምለጫ መንገድ እንዳገኘ አወቀ:

ወደ ትንንሾቹ መቀመጫዎች ቀረብ ብዬ ስመለከት ስሞችና ቀኖች ተፅፎባቸዋል:: ለምሳሌ ጆናታን፣ ዕድሜ 11፣ 1864: አዴል፣ ዕድሜ 9፣ 1879። ይህ ቤት እንዴት አሮጌ ነው! ይህን ጊዜ መቃብራቸው ሳይቀር በአፈር ተሸፍኗል እነሱ ግን በአንድ ወቅት እነሱም ወደዚህ ተልከው እንደነበረ ሊነግሩን ስማቸውን
ትተውልናል። ግን ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያጠኑ ብለው እንዴት ወደዚህ ይልኳቸዋል? ግን አያቶቻችን እንደሚጠየፉን እንደኛ አይነት ልጆች ሳይሆኑ የሚፈለጉ ልጆች ይመስሉኛል፡ ምናልባት ለእነሱ ጊዜ መስኮቶቹ በደንብ
ተከፍተው ይሆናል ወይም ሰራተኞቹ ጥጉ ላይ ባሉት ምድጃዎች ላይ ከሰልና
እንጨት ያነዱላቸው ይሆናል።
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ጀርመን በእንግሊዝ ላይ የምታወርደው የቦምብ ናዳ እስኪቆም ድረስ መንግስት ትያትር ቤቶችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ዳንስ ቤቶችን ቢዘጋም ዳንስ ቤቶች ግን ህጉን ተጋፍተው የሌሊት ስራቸውን እየሰሩ ነው፡፡ ሄሪም በአንድ ዳንስ ቤት ውስጥ ተወሽቆ የአሜሪካን ሙዚቃ በጆሮው እየተንቆረቆረ ውስኪውን ይጨልጣል፡ ሬቤካን እንዴት ሸውዶ ጥሏት እንደሄደ እያሰበ እያለ ወንድሟ ድንገት ከች አለበት፡፡

እዳውን ሳይከፍል ከምግብ ቤቱ በመውጣቱ የጅል ስራ ሰርቷል ሬቤካ ደግሞ ክብሯን ሽጣ ገንዘብ የምትከፍል ዓይነት ሴት አይደለችም፡ ትንሽ
ስታስቸግር የምግብ ቤቱ ኃላፊ ፖሊስ ጠራ፡ ቤተሰቦቿም ፖሊስ ጣቢያ
ተጎተቱ፡፡ እንዲህ አይነቱን ችግር ሄሪ ዘወትር ሲሸሽ ነው የኖረው፡፡ ዛሬ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ሰላሳ ያህል እስረኞች ጋር ጣቢያ ተዘግቶበታል፡፡ ክፍሉ
መስኮት የሚባል ነገር የሌለው ከመሆኑም በላይ በሲጋራ ጢስ ታፍኗል፡

ሬቤካ ሄሪ የቀረበበት ክስና ማስረጃ የሚያከራክር አይደለም፡፡ ለመሰረተችበት ክስ የምግብ ቤቱ ኃላፊ ምስክር ሆኖ የሚቀርብ ሲሆን ጌታ ሞንክፎርድም የጠፋውን የሸሚዝ ማያያዣ በተመለከተ ከሰውታል፡ ከዚህም የከፋ ነገር አለ፡ በወንጀል ምርመራ መምሪያ ሲመረመር ነው የዋለው
ከሁለት ወይም ከሶስት ዓመት ወዲህ ጌጣጌጥ ጠፍቶብናል የሚሉት
አመልካቾች በርክተዋል፡ አመልካቾቹ ጌጣጌጦቹ ተሰርቀዋል የሚል ግምት
የላቸውም ምክንያቱም ለመውሰድ ዕድሉ ያላቸው እንግዶቻቸው ብቻ ናቸው ለፖሊስ የሚያመለክቱትም እንዲያው ከተገኙ በማለት ነው፡፡

በምርመራው ወቅት ሄሪ አይናገር አይጋገር መልስ ለመስጠት አሻፈረ ብሏል፡፡ ሆዱ ግን ታምሷል፡፡ እስካሁን የፈጸመው ስርቆት እንዳልታወቀበት እርግጠኛ ቢሆንም በተቃራኒው የሰማው ነገር ፍርሃት ለቆበታል፡

መርማሪው አንድ የጠበደለ ዶሴ አውጥቶ እስካሁን ጠፉ የተባሉትን
ጌጣጌጦች ዘረዘረና ‹‹ይሄ ሰው ከፍተኛ የጌጣጌጥ ፍቅር የተጠናወተው ብቻ
ሳይሆን ጌጣጌጥም ያውቃል አለ። ፋይሉ እሱ በተለያዩ ጊዜያት የመነተፋቸውን ጌጣጌጦች ጉዳይ የያዘ ሳይሆን አይቀርም ሲል ገመተ።
ስርቆቶቹ በተፈጸሙበት ጊዜ ሄሪ በነዚህ ቦታዎች ላይ እንደነበር የሚመሰክ
ምስክሮችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ቤቱም በፖሊስ
መበርበሩ አይቀርም:
አብዛኛዎቹን ጌጣጌጦች ቢሸጣቸውም ጥቂቶቹን አስቀምጧቸዋል፡ የሽሚዝ
ማያያዣውን የሰረቀው አንድ ፓርቲ ላይ ሰክሮ ከሚያንቀላፋ ሰው ላይ ነው: እናቱ ያደረጉትን የአንገት ጌጥ ደግሞ የወሰደው አንድ ሰርግ ላይ ከአንዲት ሀብታም ሴት ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ስራህ ምንድነው ብለው ቢጠይቁት ምን ብሎ ሊመልስ ነው?

ለረጅም ጊዜ እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እስሩን አጠናቆ ሲወጣ ደግሞ ውትድርና ውስጥ ይከቱታል፡፡ ይሄ ደግሞ ከእስር ቤት አይሻልም።
ይህን ሲያስበው ብርድ ብርድ አለው።

መርማሪው የሸሚዙን ኮሌታ ጨምድዶ ከግድግዳ ጋር ቢያላጋውም ትንፍሽ አልል አለ፡፡ ዝምታው ግን የትም አያደርሰውም፡፡ሄሪ ነጻ
ለመውጣት ያለው አንድ እድል ብቻ ነው፤ ደኛው በዋስ እንደለቁት
ማድረግና ከአገር መጥፋት፡፡ ልክ በሰዓታት
ዳኛው በዋስ እንዲለቁት
ለዓመታት እንደታሰረ ሰው ያህል ነጻነቱን ተመኘ፡፡

ሀብታሞችን እየዘረፈ አኗኗራቸውን እየተላመደው መጥቷል፡፡ ጧት ዘግይቶ ከእንቅልፉ ይነሳል፤ የሚያማምሩ ልብሶች ይለብሳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ደግሞ እንደ መሰሎቹ አነስተኛ ቡና ቤት ሄዶ ወይም እናቱን ይዞ
መዝናናቱንም አልተወም፡፡ ነገር ግን የእስር ቤት ኑሮ ለጠላቱ አይስጠው ቆሻሻ ልብስ፣ አሸር ባሽር ምግብ፣ መተፋፈጉ ከሁሉም በላይ ደግሞ ትርጉም የሌለው ኑሮ፡፡

በዋስ እንዴት ሊወጣ እንደሚችል ማሰብ ጀመረ፡፡ ፖሊስ የዋስ መብቱ እንዲከበርለት ባይፈልግም ዳኞቹ መወሰን አለባቸው፡፡ ሄሪ እስር ቤት ገብቶ
ባያውቅም ከየስዉ አፍ እንደሰማው የዋስ መብት የሚከለከለው ለግድያ
ወንጀል ብቻ ነው፡ ይሄን ደግሞ ሁሉም ሰው ያውቀዋል፡፡ ባብዛኛው ዳኞች ፖሊስ የጠየቀውን ነው የሚያደርጉት፡ ሁልጊዜም ባይሆን ተከሳሾች አሳዝነው ከነገሯቸው ሆዳቸው ሊራራ የሚችልበት አጋጣሚ ይኗራል አንዳንዴ ደግሞ ጋጠወጥ ፖሊስ ሲገጥማቸው የበላይነታቸውን ለማሳየት
ሲሉ ዋስ የሚፈቅዱበት ጊዜም አለ፡፡ የዋስ መብቱን ለማስከበር የሚያሲዘው
ገንዘብ አያጣም፡፡ ለዚህ ችግር የለበትም፡፡ ረብጣ ገንዘብ አለው፡፡ ስልክ
እንዲደውል ስለተፈቀደለት እናቱ ጋ ደውሎ ‹‹የዋስ መብቴን ሊያከብሩልኝ
ነው እማማ›› አለ ሄሪ

‹‹አውቃለሁ የኔ ልጅ›› አሉ ‹‹እናቱ አንተ ሁልጊዜ ዕድለኛ ነህ››

ብዙ ጊዜ ከችግር አምልጫለሁ አሁን ግን እንጃልኝ ሲል አሰበ፡፡

የእስር ቤት ዘበኛው ‹‹ማርክስ›› ሲል ተጣራ
ሄሪ ተነስቶ ቆመ ዳኞቹ ሲጠይቁት ምን እንደሚል ያቀደው ነገር የለም፡ እንደመጣለት የመናገር ችሎታ ያለው ቢሆንም ለዚህ ጊዜ ግን ተዘጋጅቶ ቢሆን በወደደ፡፡ ክራቫቱን አጠባብቆ ኮቱን ቆላለፈ፡ አገጩን አሻሽና ጢሙን እንዲላጭ ቢፈቅዱለት ተመኘ፡፡ በመጨረሻ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለትና የሸሚዙን ማያያዣ አምባር ከክንዱ ላይ አንስቶ ኪሱ ከተተው፡፡

ችሎቱ ውስጥ ሲገባ ፊት ለፊት የዳኞቹ መንበር ጉብ ብሏል፡ ህዝብ የተቀመጠበትን ቦታ ሲያማትር እናቱ የክት ልብሳቸውን ለብሰው ራሳቸው ላይ ቆብ ደፍተው ተቀምጠዋል፡ የዋስ ገንዘብ እንዳለ ለማመልከት ይመስላል አስር ጊዜ ደረታቸውን ይደባብሳሉ፡ ከአንዷ ሀብታም ላይ የመነተፈውን የኮት ማያያዣ ጌጥ አድርገውት ሲያይ ፍርሃት ጨመደደው፡፡ እጁ
እንዳይንቀጠቀጥበት የተከሳሽ መቀመጫውን ፍርግርግ ለቀም አድርጎ ያዘ፡፡

አፍንጫው አለቅጥ የረዘመው አቃቤ ህግ ‹‹ክቡር ፍርድ ቤት፣ ተከሳሹ
የሎርድ ሞንክፎርድ የሆነ ሃያ ፓውንድ ጥሬ ገንዘብና ጥንድ ከወርቅ የተሰሩ የሸሚዝ ማያያዣዎች ስርቆትና አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተመግቦ ሳይከፍሉ የመውጣት ጥፋት በመፈጸም ተከሷል፡ ፖሊስ የበርካታ ገንዘብ ስርቆት ጉዳይ እየመረመረ ስለሆነ ይህ ተከሳሽ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ይጠይቃል›› አለ፡፡

ሄሪ ዳኞቹን ሲመለከት ሁለቱም በንቀት ያዩታል፡ እነሱም ፊታቸው የቀረበ ሁሉ ጥፋተኛ ነው የሚሉ ይመስላሉ፡ ፍርሃት ፍርሃት አለው፡፡እንግዲህ የመሃል ዳኛው ናቸው ወሳኙ፡፡ ሰውዬው ሪዛቸው የሸበተ ሲሆን ገፅታቸውን ላነበበ በስራ ዘመናቸው በርካታ የክስ ጉዳይ ሲዳኙ የኖሩ
መሆኑን ያሳያል፡፡ እሳቸውን ነው መጠንቀቅ ሲል አሰበ ሄሪ፡፡

የመሃል ዳኛውም ‹‹የዋስ መብት ትጠይቃለህ?›› አሉት

ሄሪ ግር አለው ‹‹ወይ አምላኬ፤ አዎ ጌታዬ›› አለ፡፡

የትልቅ ሰው ንግግሩን ሶስቱም ዳኞች አስተዋሉ፡
ሄሪም ይህን ተገንዝቧል፡፡ የሰዎችን ግምት ማስለወጥ በመቻሉ ይኮራል፡ የዳኞቹ ሁኔታ ስላበረታታው አሞኛቸዋለሁ ሲል አሰበ፡፡

‹‹ምን ትላለህ?›› ሲሉ ጠየቁት።

‹‹አንድ ችግር ሳይፈጠር አይቀርም ጌታዬ›› ሲል ጀመረ፡ በዚህ ጊዜ ዳኞቹ ለመስማት በማቆብቆብ ወንበሮቻቸው ላይ ሲቁነጠነጡ ታዩ፡፡

‹‹እውነቱን ለመናገር በዚያ ምሽት ካርልተን ቡና ቤት
አንዳንዶቹ ሰዎች በጣም ጠጥተው ነበር›› አለና ዳኞቹን አማተረ፡

‹ካርልተን ክለብ ነው ያልከው?››

ሄሪ ከሚገባው በላይ የሄደ መሰለው፡፡ ምናልባትም የዚህ ክለብ አባል ነኝ ማለቱን ሊያምኑ ይችላሉ፡፡

ከዚያም ፈጠን ብሎ ‹‹በእውነት በጣም ያሳፍራል፡፡ ነገር ግን አሁኑኑ
እቦታው ድረስ ሄጄ ሁሉንም ሰዎች ይቅርታ እጠይቃለሁ›› ልክ የምሽት
ልብስ መልበሱን ድንገት እንዳስታወሰ ለመምሰል ‹‹ይህን የለበስኩትን ልብስ
ለውጬ›› አለ።
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስምንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

..ደልቲ ገልዲ በራሱ የሚተማመን ጀግና በመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ
ከእሱ በላይ ሰው ያለ አይመስለውም" ስለሆነም፥ የሚፈልገውን አጣለሁ የሚል ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለውም" በስሙ ሲዘፈንና ሲዘመር ጥርሱን እየፋቀ በርኳታው (መቀመጫው) ላይ ቁጭ ብሎ ወይንም ጋደም ብሎ መዝናናት ነው;

ጀግንነት ከሀብት ጋር ገና ዕድሜው ሳይገፋ፥ «ቤት ለእንቦሳ» ሲል «እንቦሳ እሠር» ብሎ፥ ተቀብሎታል" በእርግጥ እያንዳንዱ
የሐመር ጓዳ ላጠቃላይ ማኅበረሰቡ ግልጽ ነው። ተካፍሎ መመገብ፥
ተሰባስቦ መጨፈር፥ ተከባብሮ መኖር፥ ጠላትን በጋራ ማጥቃትና
መደናነቅ የማኅበረሰቡ ወግና ልማድ ነው። ደልቲ ገልዲም የዚህ ባህላዊ ኑሮ ተሳታፊና ተገዥ በመሆኑ ኃይሉን ተማምኖ ሌላውን የሐመር አባል ማጥቃትም ሆነ ንብረት መቀማት ክብሩን ለውርደት፥ ሀብቱን
ለጥፋት ስለሚያበቃ ከልጅነቱ ጀምሮ ክብርንና መብትን በጥንቃቄ
መያዙንና ተከባብሮና ተመካክሮ መኖርን ሊዘነጋ አልቻለም።

ደልቲ ገልዲ፥ በዚያን ሰሞን ወደ መንደራቸው የመጣችውን እንግዳ የተመለከታት በኲራት ነበር" የለበሰችውን ጨርቅና
የምትሸተው ቃና ከአካባቢው ልጃገረዶች ጠረን የተለየ በመሆኑ ራቅ
ብሎ ነው ያስተዋላት።

«እንደ ሐመር ሴቶች ቆዳ የማትለብሰውና ጭኖቿን የማታሳየው ምናልባት የሚያሳፍር ነገር ቢኖርባት ይሆናል» ብሎ፥ከመገመቱም
በላይ የሴትነት ጠረኗን የዋጠው ሽታ አስጠልቶት ነበር በተደጋጋሚ
ቀናት እንዳያትም በሚኰርፍ ነገር መተጣጠቧ ብልግናዋን ከማረጋገጡም በላይ መጥፎ ጠረኗን ለማጥፋት መሆኑን አምኖበታል"

የሐመር ልጃገረዶች በውኃ አይታጠቡም። «ብልታቸውን ውኃ ከነካው መካን ይሆናሉ» ስለሚባል፣ በጣም ነውር ነው" ይህችኛዋ እንግዳ ግን አልፎ አልፎ ብቻ ሳይሆን ዘወትር ስትተጣጠብ ያያታል" «መካንነቷ መቼም የማይቀር ነው" ግን ሴት ሆና ስትተጣጠብ
የማታፍር ምኒቱ ባለጌ ናት?» እያለ ኮንኗታል። ሌላውም እንደሱ
በድርጊቷ ጠልቷታል"

ሆኖም እሱ የጀግኖች ጀግና ነው፤ እንዲህ ዓይነቷን ባለጌ ልክ የማግባቱ ኃላፊነት ከሱ ትከሻ ላይ የወደቀ ነው" ስለዚህ፣ እንግዳይቱን በግርፋትም ቢሆን ሥነ ሥርዓትን ሊያስተምራት ይችላል"
ይህን ለማድረግ ደግሞ፣ እሷን ማግባት አለበት" ካለበለዚያ ዝንቧንም እሽ ማለት ላይችል ነው ደግሞኮ የሱ ሚስቶች በመልካቸው ጥቋቁሮች ናቸውI ስለዚህ ነጭ ሚስት ያስፈልገዋል" ሀብቱ
እንደሆነ የትየለሌ ነውI ሦስት በረት ከብት፣ በየጋጡ ብዛት ያለው ፍየል፣ በየጫካው ለቍጥር የሚታክት ቀፎ አለው" በዚያ ላይ የቀጭኔ፣ የጎሽ፣ የአንበሳና የሰው ገዳይ ነው።

ስለዚህ፣ ይህችን ባለጌ ለማረቅ እንዲችል እሷን የራሱ የሚያደርግበት በቂ ሀብት አለው። እና፣ የሚጠየቀውን ጥሎሽ ከፍሎ የሱ ንብረት ካደረጋት በኋላ ቢቀጣት ጠያቂ የለበትም። ለዚህ ሁሉ
ግን፣ ሚስቱ እንድትሆን ማድረግ እንዳለበት አመነ። አብሯት የመጣው ከሎ ሆራ እንደሆነ ምኗም እንዳልሆነ አረጋግጧል"

አንድ ቀን ካርለትና ከሎ ሆራ ሲጨዋወቱ ደልቲ ገልዲ
«ነጋያ» ብሎ አጠገባቸው ለመቀመጥ ይዞት በሚዞረው በርኮታ ላይ
መሣሪያውን ጭኖቹ መሃል አድርጎ ተቀመጠ" ከዚያም፣ «ባል  አለሽ?» ብሎ በቋንቋው ጠየቃት" ይሉኝታና ፍርሃት የሐመርን
ተወላጅ ሲያልፍም አይነካካውም" ደግሞስ ሰው ሰው ነው" ያውም
እሱ ጀግናው። ከሎ ሆራ ያለውን ለካርለት ተረጐመላት።

«የለኝም» አለችው" ካርለት በቀኝ እጇ ግንባሯ  ላይ
የተበታተነውን ጸጕር ወደ ኋላዋ እየመለሰች።

«አባትሽ ስንት ከብት አለው?» አላት፣ ደልቲ።

«ከብት የለውም፣ ፕሮፌሰር ነበር" ስለዚህ ደመወዙ…»
ፕሮፌሰር፣ ደመወዝ ያለችው ሊገባው አይችልም። ከባለጌ የሚጠበቅ
ተራ የተራ ነገር ይሆናልና ስለሱ ማሰብ አያስፈልግም።

«ቀፎና ፍየልስ?» ጠየቀ ደልቲ።

«የለውም» አለች" አባቷ ደሃ ቢሆን ነው ማለት ነው ወደዚህ የላካት ብሎ አዘነላት" በሐመር ማኅበረሰብ ሀብት ማለት ከብት፣ ፍየል፣ ቀፎ ነው። ከዚህ ውጭ ደመወዝ፣ ቪላ፣ መኪና ብሎ ሐተታ፣
የሚገባው የለም። ደልቲ ገልዲ በክልሉ የሀብት ሁሉ ባለቤት አባወራው እንደሆነ
አሳምሮ ያውቃል" ስለዚህ፣ እንግዳዋን ስለ እናቷ
አያስፈልግም" ደግሞ ሴትን፣ «ሀብት አላት ወይ?» ብሎ መጠየቅ ነውር ነው። የእንግዳዋን አባት ሁኔታ እንደሆነ ጠይቆ፣ ድህነቱን
ተረድቷል

ደልቲ ገልዲ በእሱና በእንግዳዋ አባት ሀብት መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል ሰፍቶ ታየው" ለምግብ ማቅረቢያ፣ ለመኝታ የምትጠቀምበት፣ በተለይም ማታ ማታ «ፋ» የምታደርገው መብራትና ብልጭልጭ ቅራቅንቦዋ፣ ከሱ ንብረት አንፃር ሲታይ
ጠጠርና ተራራን ማወዳደር ቢሆንም፣ አባቷ ሀብቱን ለምን ለእሷ እንደተወላት ግራ ገብቶታል። የሱ ወገን የሆኑት የሐመር ሴቶች የግሌ የሚሉት ሀብታቸው የሚለብሱት ቆዳ፣ ጨሌና አንባራቸውን ብቻ
እንደሆነ ጥርት አድርጎ ያውቃል።

ያም ሆነ ይህ ግን፣ እንግዳዋን አግብቶ በግርፋት መግራት እንዲችል ሊያገባት መፈለጉን ለሽማግሎች ማማከር አለበት ሽማግሎች የሚሉት ባይታወቅም ብልግናዋን ገልጾ ሊገራት እንደሚፈልግ
ሲነግራቸው እነሱም ይህን ስለሚረዱ ተቃውሞ እንደማይኖራቸው
ተማምኗል" አንድ ግን ግራ የገባው ጉዳይ አለ" ጋብቻውን ሽማግሎች ቢቀበሉት «ልጅቱን ለማግባት፣ አባቷ የት ተገኝቶ በሽማግሎች
ይጠየቃል? ጥሎሹንስ እንዴት ወስዶ ከችግሩ ይላቀቃል?» ብሎ
አሰበ።

ይህ ከሆነ በኋላ ግን፣ ብዙም ሳይቆይ ደልቲ ገልዲና ካርለት በምሽት ጭፈራ ተገናኙ ካርለት ያ አስደናቂ ጥያቄ ሲጠይቃት
የነበረው ወላንሳ እየዘለለና እያሸበሸበ ሲደንስና ሲሥቅ፣ ደጋግማ
ስታየው ሁሉን ነገር በተለይም ስለሱ የሚባለውን ሁሉ አስታወሰች። ስለዚህ፣ ዛሬ ይህን ስሙ በሐመር ሰማይ ላይ የሚንሳፈፍ ሰው ማንነት ማወቅ አለባት"

ያም ሆኖ ግን ካርለት ስሜቷ ለሁለት ተከፈለባት" በአገሯ ምን ዓይነት ውበትና ጠባይ ያላቸው ወንዶች በሴቶች እንደሚፈቀሩ፣ ከሞላ ጎደል ታውቃለች። እሷም ብትሆን በአፍላው የወጣትነት ጊዜዋ የነበራት የስሜት ቅብጥብጥነትና በምታፈቅረው ወንድ ላይ

ታጠምደው የነበረውን መረብ አስታወሰች" ሆኖም ይህ ሰው እዚ
ከምታውቃቸው ሰዎች በብዙ መልኩ ይለያል ለነገሩ የደልቲ ውበት
ጭጋግ ለብሶ ይታያልI ያውም ይኖራል ብላ ያልገመተችው ውበ
የሐመር ልጃገረዶችን ሕሊና ያማልላል ተብሎ የሚደነቀውን ልበ ሙሉ ወንድ ጭጋጉን በታትና ሥነ ውበቱን በትክhል መቁጠር አለባት" የለንደኑ፣ የቦኑ፣ የማንቸስተሩ..ወጥመዷ ያለውን የመያዝ ችሎታም መፈተን ይኖርባታል"

እንደ ባልጩት ድንጋይ የለሰለሰውን ገላውንና በጨረቃ የሚያንፀባርቁት ጥርሶቹን ባሰበች ቍጥር ጥርት ጎላ እያሉ ታይዋት
ስለዚህ፣ ማራኪውና የመጨረሻ ዓይነት የጭፈራ ምት መጀመሪያው ጊዜ መቃረቡን ስታውቅ፣ ሐሳቧን ተግባራዊ ለማድረግ ለሩጫ
እንደሚዘጋጅ ሯጭ አደፈጠች።

ያን የወቅቱን ወላንሳና ቀብራራ ሐመር ጠብቃ ለዳንስ ስትጋብዘውና እያኮበኮበ፣ አየሩን በመቅዘፍ ቀርቦ ጥቁሩ ጭኑ ከነጩ ጭኗ ሲተሻሽ፣ ሸካራና ጠንካራ እጆቹ ትከሻዋን ሲይዙ፣ ስሜቱ
በስሜቷ ውስጥ ሲሟሟ፣ ያለችበትን ቦታና ሰዎችን በመዘንጋት የሚያቃጥል፣ የሚነዝርና በሰመመን የሚያሰጥም ስሜት እንደ
ተሰማት፣ ከራሷ ቍጥጥር ውጭ ሆነች" ስለዚህ፣ ሁሉን ነገር ዘንግታ
ተንጠራርታ አንገቱን በማቀፍ ከንፈሯን ከከንፈሩ ጋር ለማላተም
ተጣጣረች ደልቲ ግን፣ በጠንካራ እጆቹ እጇን ያዝ አድርጎ፣ የዳንሱን ቦታ ጥሎ፣ ወደ ጫካ ይዟት ገባ፤ ጥቁሩና ነጭ አባይ ጫካ መሃል ተገናኙ።
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ስምንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ጠበብ ብሎ ዘመናዊነትን የተላበሰው ክፍል በእንግዶች ተጣቧል። በእያንዳንዱ ጠረጴዛ መሃል ፈንድሻ በቆሎና የተለኮሰ
ሻማ ተቀምጧል። በአመዛኙ ተስተናጋጁ የሚጠጣው ውስኪ ነው ::

የጃዝ ሙዚቃውን ስልት ተከትለው እየነጎዱ እጃቸው
ከሰው ጉያ ውስጥ ዘው ብሎ ሲገባ ከንፈር ከከንፈር ሲላተም...ነፍሳቸውን የሚያውቁ የማይመስሉ ፍቅረኞች ጥግ ጥግ ይዘው
ይታያሉ።

ታዲያ ተመልካችና የሚታይ ተናጋሪና ታዛቢ... ያለ
አይመስልም፤ ክፍሉ ውስጥ ሁሉም እንደተመቸው ይዝናናል።

የደረታቸውና የእጃቸው ጡንቻ ያበጠ የሰማይ ስባሪ
የሚያካክሉ “ቦዲ ጋርድ" መሳዮች ባንኮኒውን ከበው ከጃዙ ሙዚቃ በላይ አልፎ አልፎ ድምፃቸው እስኪሰማ ድረስ ያውካካሉ።

ዓለም አቀፍ የአየር ሜዳ ጠቆር ብሎ ከጥቁሩ ሰማይ ጋር የተመሳሰለው ተራራ  ሌሎችም የአዲሳባ መንገዶችና ቤቶች
ተሰበጣጥረው በሚበሩት አንፖሎች ብርሃን የጃዝ ሙዚቃው ከሚንቆርቆርበት ኢምፔሪያል ሆቴል ሰባተኛው ፎቅ ላይ ሆኖ
ይታያል።

ቀኑ የሥራ መጨረሻው ሳምንት አርብ በመሆኑ ብዙው ጠጥቶና ደንሶ ጥቂቱም ጠንብዞ ቅዳሜን ተኝቶ ለማሳለፍ
ተዘጋጅቶ መምጣቱ ያስታውቃል።

“ይህ እንግዲህ አዲሱ ሆቴል ነው" አለ ስቲቭ እሱ
ውስኪውን እሷ ማርቲኒን “ችርስ ብለው አጋጭተው ከተጎነጩ በኋላ።

“ዘመናዊ ነው። እንዲህ አይነት ሆቴል አዲሳባ ያለህ
እያስመስልህም አለችውና እየተዟዟረች ውጭውን በርቀት ተመልክታ

“አዲሳባ በዘመናዊነቷ ሳይሆን በተፈጥሮ አቀማመጧ በአመቺው የአየር ፀባይዋ... በተለይም ድሃና ሃብታም ተሰበጣጥሮ
የሚኖርባት ብቸኛ ከተማ መሆኗ ያረካኛል ስትለው ስቲቭ አንገቱን
በመወዝወዝ አባባሏን ተቀበሎ፡-

“ወደ ኢትዮጵያ እንዲህ ቶሉ እንደምትመለሽ አላውቅም
ነበር። እንዴት ቶሎ
ተመለስሽ? አላት
“ይህን ለመግለጽ ይከብደኛልስቲቭ።
ምናልባት ሙያዬን
ስለምወድ። ከዚህ ውጭ ግን ለረጅምጊዜ ፍቅር ምን እንደሆነ ለመረዳት ባለመቻሌ ካለበለዚያ ያገኘሁትን አዲስ የህይወት ልምድ ይበልጥ ቀርቤ ለማወቅ... ብቻ በትክክል መግለጽ ይከብደኛል”
አለችው። ማርቲኒ የያዘ ብርጭቆዋን እያሽከረከረች።

“ፍቅር ምን እንደሆነ አታውቂም?

“የፍቅር ደራሲውም ተዋናዩም እየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እንጂ ፍቅር ምን እንደሆነ አላውቅም” አለችው ፈገግ ብላ

“በእርግጥ ማንም አውቀዋለሁ ለማለት ይከብደዋል" ሲል

“አፈቅርሁሽ ሲሉኝ በጣም እደነግጣለሁ። ምክንያቱም
ትልቅ ሃላፊነት እንደመሸከም እቆጥረዋለሁ: ለምን በምን
እንዴት... እኔን አፈቀረ ለሚለው ጥያቄ መመለስም ያቅተኛል መፈቀሬን ከተቀበልኩ ከራሴ በላይ የምሽከመው ሰው አለ ማለት ነው። ይህ ደሞ ሕይወቴን ያከብድብኛል ነፃነቴን ይነፍገኛል!
ሌላውን ለማግኘት· · ብጎመጅም ያሰብሁትን ካገኘሁ በኋላ ይሰለቸኛል:: አብሮ መዋል መኖሩ ያስጠላኛል። ብቸኝነት ደግሞ አልወድም

“ይሁን እንጂ ብቸኝነቴን የምመርጥበት ጊዜ ይበልጣል በልጅነቴ  ደጋግሜ ያነበብሁት ትንሹ  ልዑል መጽሐፍ ላይ
እንዳለችው ቀበሮ ሌውን ለመልመድ ትዕግስትና ተራርቆ መኖርን እመርጣለሁ:: ፍቅር  እራስን  አሳልፎ መስጠት ነው ሲሉም እሰማለሁ  እውነት ግን አይመስለኝም።  ብዙዎች እራሳችንን
አሳልፈን ሰጠን ይሉና በኋላ ሌላውን እያስለቀሱ  እሪሳቸውን ይወስዳሉ።

የሰጠውን መውሰድ እንደሌለበት ሃላፊነት የሚሰማው ሰው ይኖራል ብዬ አልገምትም። በጊዜያዊ ስሜትና በፍቅር መካከል ያለው ልዩነት አይገባኝም። ከፍተኛ መካከለኛና አነስተኛ ስሜት
ይኖራል። ከፍተኛውን ስሜት እንደ ፍቅር እንቆጥረዋለን። ፍቅር ግን ሊሆን አይችልም። ፍቅር መስዋዕትነት መስጠት  መከራን መቀበል  ነው... በበደል በንዋይ የሚፈታ በጊዜ የሚኮሰምን
አይደለም፡ የምናየውና መሆን የነበረበት ፈፅሞ ይለያያል። ስለዚህ
ለሌላ ፍቅር አለ ብዬ ራሴን በመደለል የጥቅም ቁማር መጫወት አልፈልግም ውስጣዊ እሳት ሲበዛ ስሜት ሊገነፍል ሲቃረብ
መቃበጥ ! በተረፈ የሚያምኑበትን መልካም ሥራ በትጋት መስራት: ፍቅርን ከሥራ ጋር እንጂ!...” አይኖችዋን ሽቅብ በልጥጣ
የግንባሯን ቆዳ ሸበሸበችው።

ስቲቭ በዚህ ርዕስ ላይ ብዙ ሊሞግታት የሚያስችለው
ሀሣብ አጣ ሰዎች ከገሃዱ አለም እንከን የሌለው ፍቅር ቀርቶ ለምሣሌ የሚበቃ ፍቅር በማጣታቸው ስለ ፍቅር በተነሳ ቁጥር
የሚያነሱት ሸክስፒር  በምናቡ ስለፈጠረው  “የሮሚዎና ዡሌት”
ፍቅር መሆኑን ስለሚያውቅ ፍቅር ለጋራ ጥቅም እንጂ አንዱ ለሌላው መስዋዕት ለመሆን አለመሆኑንም ሲያስብ፤ ካርለት የጃዙን
መዚቃ  ተመስጣ እያዳመጠች ቆየችና፡

“ልንደንስ ብንችል ምንኛ ደስ ይለኝ ነበር'' አለችው

“ጥሩ ሃሣብ'' ብሉ በተራው ሂሣቡን ዘጋ

መብራቱ የሙዚቃውን ስልት ተከትሎ ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም ይላል
በዳንሱ መድረክ ላይ ደጋግመው። በዳንሱ
ከሚውረገረጉት መካከል ካርለትና ስቲቭ ይገኙበታል።

የብሬክ የቫልስ የብራዚል ዳንስ ሳምባ ሳይቀር ካርለት
እየደነስች የስቲቭን ወሲባዊ ስሜት አጦዘችው:: ከዳሌዋ ግራና ቀኝ
ነቅነቅ ነቅነቅ ብላ ወደፊት ከወገቧ በታች ስትናጥ፤ ወገቧን ለአመል ያህል ይዞ በሚሽከረከረው ዳሌዋ ሲደነቅ ምራቁን ሲውጥ እንደቆዩ ረጋ ያለው ይህች ዓለም ትቀየር የሚላው የኤሪክ ክላፕተን ሙዚቃ
ጀመረ: ካርለት ከሰውነቱ ተጣብቃ እንደ እባብ እየተጥመለመለች
ዳሌዋን እያንቀሳቀሰች, በትንፋሽዋ ደረቱን ስታተራምስው የመውደቅ
ያህል ላዩዋ ላይ ዘፍ አለባት

እሷም አቅሙ እያነሳት ስሜቷ እየገፈተራት መጣና “ስቲቭ እንሃድ" አለችው፡ ተከትሏት ወጣ። መኪናቸው ውስጥ እንደገቡ
ከንፈሩ ከከንፈሯ ገጠመ: ተንቀሳቀሱ... ፓንቷ ቁልቁል ሲንሽራተት ጭኖችዋም ተከፈቱ…..

“የወሲብ ፈውስ" የሚለው የማርቪን ጌይ ሙዚቃ ዜማ
በርቀት ተሰማት፡ ካርለት ዓለሟን ቀየረች... ለመፈወስ ነጎደች...
ሙዚቃው ይስረቀረቃል... ደስ የሚለው ሙዚቃ  እየራቀችም ተከተላት... ከፈተችለት ጆሮዋን አይኗን ልቧን. ሙዚቃውም
እንደ ምንጭ ውሃ ኩልል እያለ እየሰረሰራት ወደ ውስጧ ፈሰሰ።

💫ይቀጥላል💫
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
#ክፍል_ስምንት
////

"ሠላም ነሽ ታአምር?"

"ሠላም ነኝ"

" አባዬ...ድምፅህን ስለሠማው ደስ ብሎኛል"

"እኔም ደስ ብሎኛል የእኔ ጣፋጭ...ግን ስልኬን እንዴት አገኘሽ?"

"የጓደኛዬ የቢጡ አባት ነው አባቴን ባገኝ ደስ ይለኛል እያልኩ ሳለቅስ አሳዘንኩትና ..ከፌስብክ ላይ ፈልጎ ባንተ ስም የሚመሳሰል ሶስት ቁጥር ሰጠኝና …ሞክሬ …ሞክሬ..  ከዛ አገኘውህ...እናም ደስ አለኝ"

"ውዴ..እስከዛሬ ፈልጌ ስላላገኘውሽ በጣም ይቅርታ...እቴቴን ስላስቀየምኳት ፈርቼ እኮ ነው"

ዕድሜ ልኬን ከብዙ ሰዎች ጋር በክፉም በደጉም ብዙ ንግግር ተነጋግሬያለሁ... እንደዛሬው ግን የምይዘው የምጨብጠው ጠፍቶኝ አያውቅም...ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፊት ብቀርብ እራሱ እንዲህ አልርበተበትም።

"አባዬ"
አልተቀየምኩህም..እቴቴም ደግሞ ሰው ሳያያት ክፍሏ ውስጥ ትደበቅና ያንተን ፎቶ እና የእናትህን ፎቶ እያየች "የእህቴን አደራ በላሁ›› እያለች ታለቅሳለች ..፡፡

"እውነትሽን ነው..?"

"አዎ አባዬ እውነቴን ነው"

""ታአምሬ"

"ወዬ አባዬ"

"ስልኩ..ማለት የደወልሽልኝ በማን ስልክ ነው?"

"ስልኩ የራሴ ነው...እማዬ ከአሜሪካ ስትደውል በራሴ ስልክ እንዳናግራት ልካልኝ ነው"

"እና በዚህ ብደውል አገኝሻለሁ?"

"አዎ ግን..ማለቴ አንተን እንዳገኘሁህ እቴቴ ስለማታውቅ ፈርቼ ነው"

"ችግር የለም"

ሲመችሽ..እንዳወራሽ ስትፈልጊ ሚስኮል አድርጊልኝ"

"እሺ አባዬ"

"ቻው...እወድሀለሁ"

"እኔም በጣም ወድሻለሁ..ቻው"ስልኩ ተዘጋ፡፡

ስልኩን ከዘጋሁ በኃላ እንኳን እንባዬንም ስሜቴንም መቆጣጠር አልቻልኩም.፡፡ አልጋውን ለቅቄ በመውረድ ቤት ውስጥ ከላይ ወደ ታች እየተመላለስኩ   ወለሉ ላይ የተዝረከረከኩትን ዕቃዎች  እየረገጥኩ ዘለልኩ ..፡፡በቃ እብድ ነው የሆንኩት ። የማልረባ ነኝ...፡፡እኔ ሰው አይደለሁም፡፡መኖር ፈፅሞ አይገባኝም…

ከብዙ ቆይታና  መታገስ በኋላ ጋሽ ሙሉአለም ድምፅ አውጥተው ተናገሩ ...፡፡ ውስጤ መተራመሱ  ብሶ ቤቱን በማተራመሴ እሳቸውንም እየረበሸኩ መሆኑን እስከአሁን ልብ አላልኩም ነበር።

"ልጄ ምን ገጠመህ?"

‹‹አያቴ ጉድ ሆኜሎታለሁ? ..እኔ እኮ ሰው አይደለሁም?

‹‹ሠው አይደለሁም ስትል?

"በስህተት እና  ሀጥያት የተጨማለቅኩ እርኩስ ነኝ።

"እንደዛማ ከሆነማ እንደውም ኦርጅናሌ ሰው ነህ...››

‹‹አያቴ ትክክል ኖት ..ግን ይሄን ታሪክ ብነግሮት  ቀጥታ ይጠሉኛል...ዛሬውኑ ነው ቤቱን ለቀህ ውጣልኝ የሚሉኝ "

"ይበልጥ አጓጓኸኝ..‹.ምን ሰራው ቢለኝ ነው ይሄንን ልጅ የምጠላው?›እያልኩ ውስጤን እየጠየቅኩ ነው?...እስቲ ንገረኝና የትዕግስቴንና ይቅር የማለት ችሎታዬን  ልክ ልፈትሽበት።››

"ልጄ ደወለችልኝ"

"ልጄ ..?.›

‹‹አዩ አያቴ ገና ከመጀመሪያው ደነገጡ አይደል?"

"ሂድ ከዚህ…. ቀላማጅ፡፡ እኔ አልደነገጥኩም...ይልቅ ቅድምአያት ስላደረከኝ ተደስቼ ነው"

‹‹ይሁን እሺ….ልጅቷን የወለድኩት ካሳደገችኝ ከአክስቴ ልጅ መሆኑን ስነግሮትስ ምን ይሰማዎታል....? 40 ለሚሆን ደቂቃ ከመጀመሪያው አንስቼ አወራሁላቸው...በፅሞና አዳመጡኝ።

"የማልረባ ሰው ነኝ አይደል?"እንዲጮሁብኝ …እንዲረግሙኝ ፈልጌለሁ፡፡

.እሳቸው ግን ለስለስ ብለው ሀዘኔታ ባጠቃው አነጋገር"የማትረባም ብትሆንም ልጄ ያው ሰው ነህ… ዋናው እሱ ነው።ሰው ደግሞ በማንኛውም ጊዜና አጋጣሚ አውቆም ሆነ ሳያውቅ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ስህተት ይሰራል!ምክንያቱም ሰው እንደዛ ስለሆነ?ልዩነቱ አንዳንድ የሰራውን ስህተት ለመሸፈን ሌላ ስህተት ሲጨምር አጠቃላይ ሁኔታውን ጭምልቅልቅ አድርጎ እስከወዲያኛው ያበላሸዋል..፡፡ሌላው ደግሞ ስህተቱን በማረምና ያስከፋቸውን ሰዎች በመካስ ቀሪ ህይወቱን ያስተካክላል..፡፡.ደግሞ ያንተ የሚገርም ነው..፡፡ልጅ አለችህ..ልጅቷ ደግሞ ስህተት ልትሆን አትችልም..፡፡.እሷ ንፁህ እውነት ነች...፡፡ስህተቱ እሷ የተገኘችበት መንገድ ነው...፡፡እሱም ቢሆን አንዴ የተዘረጋ መንገድ ነው... በመንገድ ዙሪያ ያለውን ገደል ማስተካከል  ነው የምትችለው፡፡ መንገድን ለሁለት በመክፈል የለያዩት ገደሎች ድልድይ መስራት ነው የምትችለው፤ድልድዩ ደግሞ በይቅርታ ብረትና በፍቅር አርማታ ነው የሚገነባው... ፡፡

‹‹እንደሚሉት ቀላል አይደለም››

‹‹አትሞኝ ልጄ ፤የሰው ልጅ ከባባድ ነገሮችን ለመስራት ብዙም አይቸግረውም …ብዙ ጊዜ እንዝላል የሚሆነው ጥቃቅን ነገሮችን ለመስራት ነው፡፡ያው ዞሮ ዞሮ ጥቃቅን ነገሮች ተደምረው ነው ከባድ ችግሮችን የሚፈጥሩት ፡፡አሁን የነገርከኝን ታሪክ ስትሰራ በአንድ ቅፅበትና በአንድ ቀን አይደለም..ቀስ በቀስ፣አንድን በአንዱ ላይ እየደረብክ….በአመታት ውስጥ ነው የሆነው፡፡ለማጥፋት እንደዛ ከሆነ ያንን የጠፋውንም ለማደስ እንደዛው ቀስ በቀስ ምን አልባት የአራት እና በአምስት አመታት ጥረትና ልፋት ይጠይቅ ይሆናል..ግን በየእለቱ የምትችለውን ስራ.››

‹‹እንዴት አድርጌ አያቴ?››

‹‹ይው እኮ አስበህበትም ባይሆን ዛሬ ጀመርክ፡፡››

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹ያው ከልጅህ ጋር አወራህ፣ድምፆን ሰማህ፤ምን ያህል አንተን እየናፈቀች እንደሆነ እና በአንተም ምንም ቅሬታ እንደሌላት ከአንደበቷ አረጋገጥክ፡፡››

‹‹አዎ አያቴ እሱን እንኳን እውነቶትን ነው፡፡››

‹‹አዎ እውነቴን ነው፤ አሁን ማድረግ ያለብህ ከጭንቀትና ትካዜ እራስህን ሙሉ በሙሉ አላቅና ከልጅህ ጋር ያለህን ግንኙነት በጥበብ በጣም ሳታግለበልበው ፤በጣም ሳታደፋነው በሚገባው ልክ  ይዘህ አስቀጥለው››

‹‹ማግለብለብ ማለት?››

‹‹ለምሳሌ የሚቀጥለው እሁድ ብር ብለህ ደብረብርሀን ሄደህ ላግኝሽ ብትላት ቤተሰቦቾ ሳይዛጁበት ይሰሙና ልጃችንን ይዞብን ሊጠፋ ነው ብለው ፈፅሞ እንዳታያትና እንዳታናግራት በሊያደርጉ ይችላሉ.. ወይም እናቷ ጋ አሜሪክ ሊልኳት ይችላሉ….ስለዚህ መጀመሪያ በስልክ ግንኙነትህን በደንብ አጠንክር..ስለቤተሰቦችህ አሁናዊ ሁኔታ ቀስ በቀስ ከልጅህ እየጠየቅክ ተረዳ..፡፡ታዲያ ስትጠይቃት በጥበብ ማለቴ ድንገት በወሬ በወሬ ትዝ ብሎህ እንዳነሳህ እያስመሰልክ መሆን አለበት..፡፡የዛሬ ልጆች ቀላሎች አይደሉም…..እሷን ስለዘመዶችህ መረጃ ለማግኘት እየተጠቀምክባት እንደሆነ ከተሰማት ልትቀየምህ ትችላለች፡፡ከዛ አጠቃላይ ሁኔታውን ከተረዳ በኃላ ምን አይነት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብህ ትወስናለህ…፡፡ችግሮችሀን በደረጃ ከፋፍላቸው…ከዛ እያንዳንዱን በተናጠል ስታየው  መፍትሄ ለማበጀት ያን ያህል ከባድ አይደለም…..፡፡

ለምሳሌ የልጅህን በአካል ማግኘት፤ከልጅህ እናት መታረቅ፤የአክስትህን ልጆች ይቅርታ መጠየቅ፤ የአክስትህን ባል ይቅር እንዲልህ መማፀን፤ የእራስህን ህይወት ለልጅህ በሚመጥን መልኩ ማስተካከል፡ እነዚህን ሁሉ ኮተት ችግሮች በአንድ ኩንታል ውስጥ ጠቅጥቀህ ካየሀቸው  ዘላለም በጫንቃህ ተሸክመህ ስታላዝን ትኖራለህ እንጂ መቼም አትፈታቸውም፤ግን እያንዳንዱን በፔስታል ለየብቻ አድርገህ ያዛቸው ቅደም ተከተል ስትሰጣቸው በአንድ ጊዜ አንዱ ፔስታል ብቻ ተሸክመህ መዞር ቀላል ስለሆነ ሳትጨናነቅ በተወሰነ ጥረትና መስዋዕትነት ትፈታዋለህ፡፡ እሱን መፍታትህ ለሁለተኛው ፔስታል ውስጥ ላለው ችግርህ መፍቻ መንደርደሪያ ይሆናል.እንደዛ ነው ልጄ››
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ስምንት


ጎይቲና ካርለት እንጨታቸውን ለቃቅመው አስረው፤ ዛፍ ስር
ተቀምጠዋል ነፋሻ ነው ቀኑ ፀሐይዋን ግን ባዘቶ ዳመና እየሸፈናት ሽቅብ ወደ ቡስካ ተራራ ያቀናል" እፅዋቱ ይወዛወዛሉ ወፎች ያዜማሉ ጎይቲም ታዜማለች ... ካርለት ደግሞ ህብረ ዝማሬውን ህሊናዋን ከፍታ ትቀዳዋለች

"ይእ ዛሬ ማታ ትልቅ ፌስታ እኮ ነው"

"ለምን?"

"አያ ደልቲ ከብት ይወጋላ! ከዚያ እየተበላ: ሸፈሮ ቡና
እየተጠጣ ይቆይና ማታ ሰማዩ ላይ በምትዋኘው ጨረቃ ልብሽ ስውር
ብሎ ጫካ እስኪገባ መጫወት ነው! ብላ ጎይቲ ከተቀመጠችበት ተነስታ እያቀነቀነች ዳሌዋን በማዞር መደነስ ጀመረች ጎይቲ ልቧ በሃዘን የተሰበረ ቢሆንም እራሷን ለማስደሰት
የምታደርገውን ጥረት ካርለት ስታይ አይ የሰው ልጅ ለምን ይሆን
ከደስታ ጊዜ ይልቅ በመከራው ጊዜ መዝፈን የሚወድ? ብላ ስታስብ


"ይእ ቁጭ ብለሽ
ታያለሽ?" ጎይቲ ካርለትን ሳቅ ብላ "ጠየቀቻት

ካርለቴ!- ልጃገረድ
ዳንስ አይታ አስችሏት ተመልካች ትሆናለች ቢባል ማን ያምናል!"

ጎይቲ እንደ ወንዶች እየሰገረች በማቀንቀን ካርለትን እንደ ልጃገረድ ደንሽ አለቻት ተነሳች ካርለት እየተሳሳቁ እንደ ወንድና
ልጃገረድ እየሆኑ ሲደንሱ ቆዩና ሮጠው ከስኬ አሸዋ ሄዱ  እዚያም
ዘፈኑን አስነኩት ከዚያ ጭሮሽ ውሃው ጎን ጎይቲ የተፈጨውን የካሮ አፈር አውጥታ በጥብጣ ካርለትን

"ይእ! ነይ ልቀባሽ?" አለቻት

"ልቀባ ብለሽ ነው ጎይቲ?"
ታሾፊያለሽ ይሆን? ዛሬማ መቅበጥሽ የት ይቀራል!"

"ከማን ጋር  ጎይቲ?"

"ይእ ተአንበሳሽ ነዋ!"

"እሱማ ተቀይሞኝ ሄዷል ..."

"ይእ! አያ ደልቲ እንዳስቀየምሽው እንደናሱ
(የጎሳው አባል ብትሆኝ ኖሮ ይመታሽ ነበር አንች ግን ፀንጋዛ (ባዕድ) ነሽ
ከብት ዝላይ ላይ ወይም ታገባሽ በኋላ ካልሆነ ዝንብሽንም እሽ ማለት ስለማይችል ራቅ ብሎ ብስጭቱን ሊያቀዘቅዝ ነው የሄደ‥

የሐመር ወንድ ሲቀየም እንደ አንበሳ ነው ጎምለል ብሎ ጫካ ይገባል እንጂ እንደ ሴት ቃል መለዋወጥ አይወድም ወይ ይማታና
ካለበለዚያም ከአጠገብሽ ይሄድና በኋላ ሁሉንም ረስቶ ይመጣል ወንድ ቂም ሲይዝ ነውር ነው!''

"እኔና ደልቲም ዛሬውኑ እንታረቃለን በይኛ?"

ይእ! እየነገርሁሽ የሐመር ወንዶችን ባህሪ ልቅም አድርጌ ነው የማውቀው" በረቱ በከብት የሞላ የአባቱን ጠላት የገደለ
የሐመር ወንድ ልቡ እንደ ክረምት ወንዝ ሞልቶ የተንቸረፈፈ ነው አያ ደልቲ እንዲያ ስለሆነ ነው ሲንጎማለል ሲያገሳ ሲጨብጥ ልቡ እንደ አዙሪት አሽከርክሮ ሳንቃ ደረቱ ላይ የሚጥል" አለቻት

"ዛሬ እድለኛ ነኛ! ካርለት ሳቅ ብላ ጎይቲን አየቻት

"ይእ! ዛሬማ የልብሽ መቦረቂያ ቀን ናት አያ ደልቲ ያን ሁሉ ጎጆ አልፎ አንች ዘንድ ለምን መጣ?ውሃ አምጭልኝስ ብሎ
ለምን ላከሽ  ሞኝት! ተኝቶ አልሞሻል ማለት ነው ተዚያ ህልሙን ሊያይ መጣ አየሽ  ስትንቀሳቀሽ ደግሞ ዳሌሽን ማዬት ፈልጎ ውሃ አምጭልኝ ብሎ ላከሽ  ህልሙ እውን መሆኑን አረጋግጦ
በዐይኖቹ የሚያረግደውን ሰውነትሽን ጎረሰው  ያን ጉርሻውን ማታ ጫካ መካከል ወስዶሽ እስቲውጠው ሲያመነዥከው ያመሻል  ዛሬ ማታ በጨረቃ ድባብ የአያ ደልቲ የጥም መቁረጫ አንች ነሽ!" ጎይቲ
በተናገረች ቁጥር ልቧ ቅልጥ ብላ የፈሰሰች ያክል ሰውነቷ ዛለ ዐይኖችዋ ተስለመለሙ ካርለትም ጎይቲ በተናገረችው ጎመጀች  ጮማ እንደሚያኝክ ሰው አፏ ደስ በሚል ፈሳሽ ተሞላ

"ጎይቲ ዛሬ አንች ለምን ከእሱ ጋር አትቀብጭም?"

"ይእ! እንዲያ በይኝ!" ብላ ጎይቲ እያጨበጨበች ሳቀችና

  "ምነው ካርለቴ ይኸማ ነውር ነው!" ብላ ኮስተር አለች

ካርለት ኮስተር ብላ ስታያት ስሜቷ ተምታታባት ኦ!
አምላኬ አጠፋሁ ይሆን! ጎይቲ ያለችው ከሐመር ማህበራዊ ህይወት
ጫፍ ላይ ነው ካላረገዘች
ተደግፋ ወደማትነሳበት
ገደል ትወድቃለች ስለዚህ
ምን አልባት የመውለድ ችግሩ የከሎ ከሆነ ብላ አስባ

"ጎይቲ ምን ችግር አለው - እስቲ ማህፀንሽንም ፈትሽው”?"

ካርለቴ በሆነማ በማን እድሌ የአባቴ ደንብ ግን አይፈቅድም" ብላ ትክዝ አለችና" ከሎ ስንቱን  የለመድሁትን ህይወት ነስቶኛል የእኔ በደል ግን የከፋ ነው ልጅ ወልዶ እንዳይስም በልጅነቱ የተሰበረው ልቡ እንዳይጠገን አደረኩት ያ
በደሌ አንሶኝ ደሞ ከደሙ ውጭ ልክዳው! የአባቴን ደንብ ከምሽር: የእሱን እምነት ከማጣ አሁኑኑ ጦሽ ብዬ እንደ ወፍ እንቁላል ለምን አልፈርጥም አለች
ካርለት የምትናገረው  ጠፋት ጓደኛዋ: አዛኝዋ መካሪዋ ጎይቲ አንተነህ ፅልመት ሊውጣት እየገሰገሰ ገው እሷ ደግሞ
በጓደኝነቷ ወደ ብርሃኑ ስባ ልታስቀራት ትፈልጋለች ከእሷ ጉተታ ጎን ባህልና ደንብ ፅልመቱ ውስጥ ሆኖ ጠምጥሞ አስሮ ወደ እሱ
እየሳባት ነው" ጎይቲ ህይወቷ በጨለማ አይዋጥም ባለኝ አቅም
ሊጥላት ከሚስባት ጋር እሳሳባለሁ ... እያለች ካርለት ስታስብ

"ካርለቴ ዙሪ ላሸክምሽ?"  ብላ ጎይቲ እንጨቱን አሸክማት የራሷንም ተረዳድተው ተሸክማ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ጎይቲ
እያንጎራጎረች እየተሳሳቁ ከኋላ በጨሌ የተሽቆጠቆጠውን የፍዬል
ቆዳቸውን እያወናወኑ የማታ ጀምበር ሳትጠልቅ ለመድረስ ወደ መንደራቸው ሄዱ።

ካርለትና ጎይቲ መንደር ደርሰው ዕረፍት ከወሰዱ በኋላ ጎይቲ ካርለትን ጉያዋ አስገብታ ፀጉሯን በካሮ አፈር እንደገና እጣንና ቅቤ
አላቁጣ ስታለሳልስላት አንድ ጊዜ የሴት ጩኸት ሰሙና ተሯሩጠው
ሄዱ ጩኸቱን ወደሰሙበት  አቅጣጫ ኮቶ ቀደም ብላ የአየችውን በምልክት እያሳየቻቸው አፏን በመተምተም ዝም በሉና ተደበቁ ብላ በጆሯቸው አንሾካሾከችላቸው"
ሸረንቤ ሚስቱን ጎንበስ አድርጎ እየገረፉት ነው ካርለት ያን ስታይ ስቅጥጥ አላት" ኮቶና ጎይቲ ግን አስቂኝ ትርኢት እንደሚያዩ
ሁሉ በሳቅ ይፍነከነካሉ

ጎይቲ ለምን ይመታታል?" ካርለት አካሏ በፍርሃት
እየተንገጫገጨ ጠየቀቻቸው"

"ይእ! ሚስቱ አይደለች,"

"ብትሆንስ? አለች ካርለት ዐይኗን በየተራ ወደሁለቱም
አቅጣጫ እያንከራተተች ኮቶና ጎይቲ በካርለት ጥያቄ ሳቁባት

ይእ! ሴት ስትገረፍ ጥሩ ነዋ!" አለች ኮቶ ፈገግ በማለት ወደ ካርለት ዞራ

"ለምን?" የካርለት የግንባር ቆዳ ተጨማደደ ፊቷ ጨው
እንደነሰነሱበት ሁሉ ነጣ

"ይእ! ደግማ አታጠፋማ  ደሞ መመታት ፍቅር ነው ሴት ልጅ ባሏ ዘንድ ስትመጣ እንደ ዱባ ድፍንፍን ብላ ነው ድቡልቡሉን የሴትን ልጅ ልብና ጭን የሚበረግደው ግርፊያ ነው" ብላ ሳቀች ኮቶ

"አሁን እናንተ ስትመቱ ደስ ይላችኋል?"

"ይእ! ግርፊያ አይነት አይነት አለው በዓይነቱ ተሆነ:
ናፍቀሽ ከጠበቅሽው ደስ ይላል ለምን ደስ አይለን" አለች ኮቶ ጎይቲ ግን ዝም አለች

"አንችስ ጎይቲ?"


"እኔማ እድሜ ለእንዳንች አይነቱ ብመኝስ የታባቴን አገኘዋለሁ  እንደምትታለብ ላም አንገቴን በዚ
ለስላሳ የህፃን እጁ ይሸኝ እንጂ  እይ ይልቅ! ተመልከቱ የሚያረጋትን ..." አለች ጎይቲ ግርፊያውን በጉጉት እያየች

ሸሮምቤ ሚስቱ የሆነ ነገር ስትቀባጥር ከቆየች
ግርፊያውን አቁሞ ቀና በይ? አላት አርጩሜውን ወርውሮ በሾርቃ ከተቀመጠው ቅቤ በቀኝ እጁ ጣት ጠንቁሎ ጀርባዋን ቀባ ቀባ አደረገላት„ ሚስቱ ግን ቆጣ ቆጣ ትላለች እንባዋን እየጠረገች።

ካርለት ለተገረፈችው ሴት አዘነችላት በመጨረሻ ግን እጅዋን ጎትቶ ወደ ጎጆው ይዟት ገባ ጎይቲና ኮቶ ተያይተው ከልባቸው
ተሳሳቁ

"ምንድነው?" ካርለት የባሰ ግራ ተጋባች

"ይእ! ቆጣ ቆጣ ስትል አላየሻትም አሁን ትንሽ ቆይተሽ ብታያት ቁጣዋ በደስታ ተተክቶ ታገኛታለሽ "
#ባል_አስይዞ_ቁማር

#ክፍል_ስምንት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

‹‹..ለምንድነው በርሬ የመጣሁት…?››እራሷን ጠየቀች… አዎ ላፓቶፑን አስታቅፋው ፊቷን አዙራ ለመሄድ ነበር…እንደዛ ለማድረግ ታዲያ መኪናዋን ለምን ወደጊቢው ውስጥ አስገብታ አቆመች..?‹‹አሮጊቷ ናቸው ሀሳቤን ያዛቡብኝ፡፡››ስትል ለራሷ ሰበብ ሰጠች፡፡

‹‹ልዩ ሰላም አደርሽ…?ግቢ ..አረ ብርድ ላይ …››ተንስፈሰፈ….፡፡

እርግጥ የሆነ ቀን መጥታ በራፉን እንደምታንኳኳ እርግጠኛ ነበር..ማታ ፌስቡኩን ዲአክቲቬት ሲያደርግም ለዛ አላማ እሷን ለማመቻቸት ነበር.. ግን ደግሞ ፈፅሞ በዚህ ፍጥነት በዚህ ለሊት እሷን በደጁ ቆማ አያታለሁ ብሎ አልጠበቀም…በዛም የተነሳ በጣም ነው የደነገጠው..
‹‹ብርዱ ›› ሲላት የእውነት በረዳት….ገባችና ቆመች፡፡ …በራፉን ዘጋና‹‹ ነይ ..››እጇን ይዞ ወደመኝታ ቤቱ ጎተታት…ዝም ብላ ተጎተተችለት…አልጋው ጠርዝ ላይ እንድትቀመጥ አመቻቸላት…፡፡
‹‹ስንት ሰዓት ነው…?እንዲህ ነግቷል እንዴ ?አለና ሞባይሉን ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ተመለከተ …የሰዓቱን ገና ለሊት መሆን ሲያይ ደነገጠ ፡፡
ከእግር እስከፀጉሯ እየመረመራት‹‹ደህና ነሽ ግን ?›› ባለማመን ጠየቃት.፡፡
‹‹ደህና አልመስልም?››
‹‹እሱማ በጣም ደህና ትመስያለሽ..እብጠትሽም ቁስልሽም ከቦታው የለም…..ግን በዚህ ሰዓት ስትመጪ ችግር ከተፈጠረ ብዬ ነው?››
‹‹ለምን ፌስቡክህን ዲአክትቤት አደረከው?››
‹‹ስላበሳጨሁሽ አዝኜ ነው››
‹‹ስለአበሳጨኸኝማ አይደለም..እኔ መርዝ ንግግሮቼን እንዳልክልህና ይበልጥ እንዳላፍር እራሴንም እንዳልጠየፍ ስለፈለክ ነው፡፡››አለችው…ከተናገረችው ውስጥ ምንም ስህተት ስላልነበረበት ዝም አለ፡፡
‹‹እንካ ይሄው ላፕቶፕህ..ከቦርሳዋ አወጣችና ሰጠችው…..ኪሷ ገባችና የተጠቀለለ ብር አውጥታ አንድ በአንድ እየቆጠረች. ይሄ ለህክምና ያዋጠኸው ነው፣ይሄ ደግሞ ለላዳ የከፈልክልኝ ነው፣ይሄ ደግሞ ወደቤት ስሄድ የላዳ ብለህ እዛ ኮመዲኖ ላይ ያስቀመጥክልኝ ነው፣ልክ በአራጣ ተበድሮ ብድሩን አንድ በአንድ እየቆጠረ እንደሚያስረክብ ሰው እጁ ላይ እያስቀመጠች ስትንጣጣበት እሱ ያለምንም ተቃውሞ ተቀበላትና እንደነገሩ ፊት ለፊቱ ጠረጴዛ ላይ ወርወር አደረገው..ላፕቶፕንም አስቀመጠው…
እና በሚያምሩ አይኖቹ ፊት ለፊት እያያት…ብዙ ብዙ ነገር እንዲል ፈልጋለች...እንዲሰድባት..እንዲረግማት ..እንዲያደንቃት.. እንዲያዝንላት… ብቻ አንድ መስመር ይዞ የሚናገራን ነገር ከአንደበቱ መስማት ፈልጋለች..እሱ ግን ንፉግ ነው የሆነባት.. የምትፈልገውን አልሰጣትም…፡፡
‹‹አሁን ለሊት ነው.. አንቺም በርዶሽ እየተንቀጠቀጥሽ ነው… ጫማሽን አውልቂና አልጋ ላይ ውጪ፡፡እኔም ገና እንቅልፌን አልጠገብኩም.. ትንሽ እንተኛና ሲነጋ ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን፡፡››አላት፡፡
ለመጮህ ፈለገች…ገፍትራውና ሰድባው እቤቱን ለቃለት ልትወጣም ዳዳት...ግን እንደዛ እየተመኘች ባለችበት ሰዓት ትዕዛዟን አክብራ ጎንበስ ብላ ጫማዋን እያወለቀች ነው…ልብ እና አዕምሮ ሁለቱም የራሳችው የሆነው መደማመጥ አቁመው በየፊናቸው ያሰኛችውን ሲያደርጉ ማለት እንዲህ ነው፡፡ጫማዋን አወለቅችና ልክ እንደለመደች የፍሬንዷ አልጋ ሙሉ በሙሉ ወጣች…እሱ ለሊቱን ሙሉ ተኝቶበት ከወጣበት ቦታ አልጋ ልብሱንና ብርድ ልብሱን ገልጣ ገባች….፡፡
‹‹እሱስ ተከትሎኝ መጥቶ ከጎኔ ይተኛ ይሆን እንዴ.?››ይሄንን ያሰበችው ከተኛች በኃላ ነው….ግን እንዲተኛ ፈልጋለች ወይስ አልፈለገችም..?›ለዚህ ጥያቄ በውስጧ የተቀመጠ አውንታዊም ሆነ አሉታዊ መልስ የለም…፡፡
ቃል ከተቀመጠበት ወንበር ተነሳ.. በግርጌ በኩል ያለውን አልጋ ልብስ እና ብርድ ልብስ ገለጠና ከጎኗ ያለውን አንዱን ትራስ በማንሳት በተቃራኒው ቦታ በማስቀመጥ ከውስጥ ገብቶ ከሰውነቷ እንዳይነካካና እንዳያሳቅቃት ወይም እንዳይፈታተናት እስከቻለው ድረስ ርቀቱን በመጠበቅ ጠርዙን ይዞ ተኛ፡፡እንግዲህ የተመሰቃቀለ አስተኛኘት ተኙ ማለት ነው….
‹‹እንደ እኔ አይነት የተመሰቃቀለ አስተሳሰብ ያለው ሰው የተመሰቃቀለ አስተኛኘት ተኝቶ እንዴት ነው የሚሆነው…?፡፡››በውስጧ አብሰለሰለች፡፡
ሳታስበው ቃላለቶች ከአንደበቷ አመለጧት‹‹ምነው ፈራህኝ እንዴ..?››አለችው፡፡
‹‹..ይህ ማለት እንግዲህ ምን ማለት ነው ?››እራሷን ነው በትዝብት የጠየቀችው፡፡
እስቲ አስቡት…እንድትተኛ የምፈልገው በትክክሉ እንደእኔው ወደላይ ዞረህ ነው እያለችው አይደል…?ይህ ንግግር ደግሞ ጥሩ መንዛሪና ተርጓሚ ካገኘ ከዛም በላይ ስውር መልእክት ሊኖረው ይችላል ፡፡እንድታቅፈኝና ከመንቀጥቀጤ እንድትታደገኝ እፈልጋለሁ የሚል የተለጠጠ መልእክት ያስተላልፋል…አጋኖ ተርጎሚ ካገኘ ደግሞ ከዛም በላይ..፡፡
ጭራሽ ይባስ ብሎ ‹‹አረ በፍፅም….ይልቅስ የፈለኩት ሳሎን መተኛት ነበር…እንደዚህ ታስቢያለሽ ብዬ ነው እዚህ የተኛሁት፡፡››አላት፡፡ይሄ መልስ ደግሞ እሷ ከምታውቃቸው ወንዶች ሁሉ ልታገኘው የማትችል ግራ የሆነ ግን ደግሞ ትክክለኛ ሀሳብ ያዘለ መልስ ነው፡፡
‹‹መተኛትህ ካልቀረ ታዲያ በትክክል ተኛ..››አለችው፡፡
‹‹እሺ››ብሎ ትራሱን ይዞ ከጀርባዋ ዞሮ ተስተካክሎ ተኛ….አቅጣጫውን አስተካከለ እንጂ በመሀከላቸው ያለውን ክፍተት ለማጥበብ እልደፈረም… ፍላጎቱም አልነበረውም፡፡እሷም ከዛ በላይ አልፈለገችም ..አልጠየቀችም.
በመከፋትና በከፍተኛ ብስጭት የመጣችው ልጅ ከስንት ጊዜ በኃላ ደስ የሚል ስሜት ተሰማት..እንደው ደስ የሚል ስሜት ማለት ምን ማለት ነው ካላችሁ…?የሆነ ፍፅማዊ መረጋጋት፤መረበሽም መቆጨትም የሌለበት…በሸለቆ ውስጥ እንደሚንኳለል የምንጭ ውሀ ጥርትና ኩልል ብሎ የሚፈስ የአእምሮ ሞገድ..አዎ እንደዛ ነው እየተሰማት ያለው…እና እንቅልፏ መጣ፡፡

ይቀጥላል
#ህያብ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በኤርሚ

"የትም አለሁ ልጅሽ የማውቃትን አንዲት ልጅ አስታወሰችኝ። ብቻ ተይው የማይገናኝ ነገር ነው" አለኝና ትክዝ አለ

"ምንድነው እሱ"

"አይ ምንም" ሸኝቸው ከተመለስኩ በኋላ ለደቂቃዎች ሁኔታውን አሰብኩትና ለምን እንቁን ሲያያት እንደዚህ ፈዘዘ ለሚለው ጥያቄ መልስ ያገኘሁ መሰለኝ ስለሷ ምንም ስላልነገርኩትና ቢጠይቀኝም እንደማልነግረው ስለሚያውቅ ነው።

ከዚህ በኋላ ያሉት ጥቂት አመታቶች ተመሳሳይ ነበሩ። ለእረፍት መምጣት፣ ከዮኒ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ጊቢ መሄድ፣ ከቢኒ እና ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር የነበረንን ግንኙነት መቀጠል፣ መማር፣ ማንበብ፣ የተለያዩ ሆስፒታሎች አፓረንት መውጣት.... ባጠቃላይ ብዙም አዲስ ነገር የሌለበት ተመሳሳይ ጡዘት ነበር።

የመጨረሻ አመት ላይ ውጥረቱ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ነበር። ዩንቨርስቲያችን ከፍተኛ ውጤት ያመጡ አስር ልጆችን ስኮላርሽፕ እንደሚሰጥ ያወቅንበት ጊዜ ነበር። ጥቂት ቢ እና ኤ ማይነስ ውጤቶች ቢኖሩኝም እድሉን አገኛለሁ ብዬ እየተፍጨረጨርኩ ነበር። ቢኒ እና ሀብትሽ እንኳን በእርግጠኝነት ከአስሮቹ መሀል ይሆናሉ። ሀብታሙ እስካሁን ያለው ውጤቱ ኤ እና ኤ ፕላስ እንደሆነ ነው የምናውቀው። ቢኒ ደግሞ ሁለት ቢ ሌላው ኤ በአጠቃላይ የግቢያችን ሰቃዮች የእስኮላሩም ባለ እድሎች ይሆናሉ ብዬ ከምጠብቃቸው መሀል ናቸው።

ውጥረቱ እንዳለ ቀጥሎ ፋይናል ፈተና ተፈተንን እና እፎይ አልን። ምርቃታችን አንድ ሳምንት ሲቀረው ሂዊ እና ቤዛ ወጣ ብለን ፈታ እንበል ብለው ሲጨቀጭቁኝ እሺ አልኳቸው። ሌላ ፕሮግራም ያለብን ይመስል ከግራ ቀኝ እየተቀባበሉ አስዋቡኝ።

"ለቢኒ ልደውልለት እንዴ ከተመቸው አብሮን ቢሆን ደስ ይለኛል" ስላቸው እርስ በርሳቸው ተያዩና ቤዛ

"ትችያለሽ" አለችኝ። እሺ ብዬ ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት ሁለቴ እንደጠራ አነሳውና

"ሀሎ ዶክተር ህያብ እንደምን አሉ" አለኝ ድምፁን እንደ ሽማግሌ እያደረገ ሳቅሁና በምላሹ

"አለን እግዚአብሔር ይመስገን እርሶስ እንዴት ኖት ዶክተር ቢኒያም" አልኩት።

"አለን ክብሩ ይስፋ ይገርሞታል አሁን ከባድ ቀዶ ጥገና አለብኝ እና ወደዛ ልገባ" አቋረጥኩትና

"እንደዛ ከሆነማ አብረን ቀደን እንጠግነዋለን ሀ ሀ ሀ ሀ የት ነህ ከነ ቤዚ ጋር ልንወጣ ነው ከቻልክ ተቀላቀለን" አልኩት።

"ደስ ይለኛል እንደውም ብቻዬን ደብሮኝ ነበር"

"ሀብትሽስ" አልኩት

"ሀብትሽማ አክስቱ ከአዲስ አበባ መጥታ ረስቶኛል ያው አትፍረጅበት የመዓረግ ተመራቂ ነገር "በል አሁን ወሬውን ተውና ውጣ እኛ ወተናል" ስልኩን ዘጋሁና ቦርሳዬን አንስቼ ከዶርም ወጣን።

በኮንትራት ራቅ ወዳለ ቦታ ሄድንና አንድ ውስጡም ውጪውም ውብ ወደሆነ ሆቴል ገባን።

"እናንተ ፈታ እንበል ብላችሁ ሆቴል ኧረ ፌር አይደለም" አለ ቢኒ ወደነሂዊ እያየ እኔም ሀሳቡን ተጋርቼው በጥያቄ መልክ አይን አይናቸውን እያየሁ እያለ ሂዊ

"ህያብ ሰርፕራይዝ አለሽ" አለችና ሳታስፈቅደኝ አይኔን በጨርቅ አሰረችው። እጄን ይዛኝ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ወደ ፎቅ ደረጃ ወጣንና በድጋሚ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ቆምን

"አይንሽን መግለጥ አይቻልም" አለችኝ ቤዚ

"እኔንም ግራ እያጋባችሁኝ ነው ምንድነው ነገሩ" ቢኒ ተናገረ። የበር መከፈት ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ተዘጋ።

"ሰፕራይዝ" ብለው ባንዴ ጮሁና አይኔ ላይ ያለውን ጨርቅ ሲያነሱት እኔ ደግሞ በተራዬ ጮህሁ። አንዴ ወደግራ አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ደግሞ ፊት ለፊቴ ወደተንበረከከው ዮኒ እያየሁ ነው። ከመደንገጤ የተነሳ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል። ቤዚን ሳያት ጭንቅላቷን በአዎንታ ነቀነቀችልኝ ሂዊም እንደዛው ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ድንዝዝ ብሎ ቆሟል።

"ታገቢኛለሽ የኔ ቆኝጆ" ብሎ ለሁለተኛ ጊዜ ደገመልኝ

"አዎ የኔ ፍቅር አዎ አገባሀለሁ" የደስታ እንባ ከአይኔ ኮለል ብሎ ወረደ። ግራ እጄን ዘረጋሁለትና የቀለበት ጣቴ ላይ የሚያምር ቀለበት አድርጎልኝ ሳም ካረገው በኋላ ጥምጥም ብሎ አቀፈኝ.... እኔም ልጥፍ አልኩበት...

ወዲያው በሩ ጓ ብሎ ሲዘጋ ሰማሁ ከእቅፉ ወጥቼ ዞር ስል ቢኒ የለም። ምን ሆኖ ነው ግራ ተጋባሁ...
የቢኒን ነገር በይደር ያዝኩትና ወደ ደስታችን ተመለስኩ። እነ ሂዊ ትንሽ አብረውን ከቆዩ በኋላ ቻው ብለውን ሄዱ እነሱን አስወጥቼ በሩን ዘግቼ ስዞር ዮኒ አጠገቤ መጥቶ ቆሟል። ጊዜ እንኳን ሳይሰጠኝ ከንፈሬ ላይ ተጣበቀ።

ሁሉም ነገር በስሜት ጡዘት ውስጥ እየሆነ ነበር ማንም መመሪያ ሳይሰጥ እያንዳንዱን ምዕራፍ ገለጥነው ከምዕራፎቹ መሀል አንደኛው ላይ ግን ነገር ተበላሸ። ከምትወደው ዮናታን ጋር በስሜት አለም የምትቃትተው ህያብ ጠፋችና የአስራ ሶስት አመቷ ህያብ ተከሰተች።

"እባክህን ተወኝ.... ሳግ... እንባ... እባክህን አትንካኝ.... ብዙ ትንቅንቅ..... ለእናቴ መድኋኒት ልገዛ ነው.....እናቴን አሟታል..... እባክህን ተወኝ ልሂድ....." ከላዬ ላይ ምንጭቅ ብሎ ተነሳና እየወዘወዘኝ ህያብ ህያብ ብሎ መጣራት ጀመረ ድምፁ ከሩቅ ቢሰማኝም ካለሁበት የህልም አለም ግን መንቃት አልቻልኩም

"እባክህ ተወኝ" ግራ ሲገባው መሰለኝ በተኛሁበት ውሃ አምጥቶ ፊቴ ላይ አርከፈከፈብኝ የውሃው ቅዝቃዜ ካለሁበት መጥፎ አለም መንጭቆ አወጣኝና ተነስቼ ቁጭ አልኩ። የሆነው ሁሉ ስለገባኝ አይኑን ማየት ፈራሁ እንገቴን ባቀረቀርኩበት ከጀርባዬ መጣና ጥምጥም ብሎ አቀፈኝና

"የኔ ፍቅር" አለኝ ሀዘኔታ በተሞላበት ቅላፄ

"ወዬ ውዴ ይቅርታ እሺ በጣም አዝናለሁ እንደዚ የምሆን አልመሰለኝም ነበር" ምላሴ ተሳሰረ ጫፉን እንኳን ስለማያውቀው እንዲያውቅም ስለማልፈልገው ታሪክ ምን ብዬ አስረዳዋለሁ።

"ተደፍረሽ ነበር አይደል" አለኝ። ረጅም ደቂቃ መልስ ሳልመልስለት ዝምም አልኩት

"ይገባኛል ህያብ ማውራት የማትፈልጊው ርዕስና ቁስልሽ እንደሆነ ግን እኔ ባልሽ ልሆን ነው ህመምሽም መካፈል ሀዘንሽን መጋራት እፈልጋለሁ። ሚስቴ ብቻዋን ስትሰቃይ ማየት የበለጠ ነው የሚያሳምመኝ" ንግግሩ አንጄቴን በላው ግን ምን ብዬ ልንገረው ምክንያቱም እኔም እናቴም የነገርነው አዲስ አበባ ተወልጄ እንዳደኩ ነው። ለእናቴ ደግሞ ቃል ገብቼላታለሁ
ማንም ቢጠይቀኝ የአዲስ አበባ ልጅ እንደሆንኩ እንድናገር ነግራኛለች። ምክንያቷ የትውልድ መንደሬን ስም በተናገርኩ ቀጥር ያንን መጥፎ አጋጣሚ በየጊዜ እንዳላስበው ብላ ነው። ይህም የሆነው ሰለዛ ሀገር ከሷ ጋር እንኳን ባወራንበት አጋጣሚ ከሷ ዞር ብዬ ሳለቅስና ሁኔታዎቼ ሲቀያየሩ ስላየች ነበር። እሷም ስለዛ ላታወራ እኔም ማንም ቢጠይቀኝ የተወለድኩት አዲስ አበባ እንደሆነ ልናገር ቃል ያስገባችኝ።

ከጊዜ በኋላ ሁኔታውን ለመድኩትና እውነትም አዲስ አበባ የተወለድኩ እስከሚመስለኝ የምናገረው ውሸት እውነት ሆነልኝ።

"አዎ ልክ ነህ ተደፍሪያለሁ ግን እንዴት? የት? ምናምን ብለህ አትጠይቀኝ ምክንያቱም ድጋሚ በዝርዝር ካሰብኩት እታመምብሀለሁ። ብቻ እመነኝ ከዚህ ሁኔታ ውስጥ እወጣለሁ እንደዚ የምሆን ስላልመሰለኝ ነው እኮ ችላ ብዬው የነበረው"

"ይገባኛል አትጨነቂ የስነ ልቦና አማካሪ ትፈልጊያለሽ"

"አዎ ግን አንተ አትቸገር በራሴ አደርገዋለሁ የማውቃቸው ጎበዝ ሳይካትሪስቶች አሉ" ደረቱ ላይ ልጥፍ ብዬ እቅፍ አድርጎኝ ተኛን ወዲያው ወደ እንቅልፍ አለም ተሸጋገርኩ
#ትንግርት


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

....‹‹እምትገርሚ ነሽ፡፡ እንደምታውቂው አንድ ዓመት ሙሉ አንድ ቤት አብረን ሠርተናል፡፡ ምርጥ ጓደኛሞችም የነበርን ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን ምን ያህል ደደብ ኖሬያለሁ፡፡ በእውነት በራሴ አፍሬያለሁ፡፡ እኔ እኮ ስለራሴ አንድም ሚስጥር ሳልሸሽግ ነበር ዘርግፌ የምነግርሽ፡፡.....

ለማንኛውም ስታጃጅይን የኖርሽ መስሎ ስለተሰማኝ ትንሽ እንደተቀየምኩሽ ልደብቅሽ አልፈልግም፡፡ ቢሆንም በስራሽና በእውነተኛ ማንነትሽ በጣም ኮርቼብሻለሁ፡፡

እኛን በተመለከተ የሠራሻቸው ስዕሎች ኖረሽ ያየሻቸው የእውነተኛ ገጠመኞችሽ ውጤት በመሆናቸው ሕያው ናቸው፡፡ ውስጤንም ነክተውኛል፡፡ ብቻ ብዙ ማውራት ፈልጌ ነበር ግን ድብልቅልቅ ያለ ስሜት እየተሰማኝ ስለሆነ አልቻልኩም፡፡ በአጠቃላይ ድንቅ ነሽ፡፡ በቅርብ ታላቅ ሠዓሊ እንደምትሆኘ እርግጠኛ ነኝ፡፡››

ሌላዋ ሴት..

‹‹... እማዬ ትሙት ስላስገደድሽኝ እንጂ እኔ መፃፍ አይሆንልኝም፡፡ ስለ ሥዕል ብዙም ባላውቅም ሥዕሎችሽ የሚያምሩ ይመስለኛል፡፡ ግን አይገቡም ወይም እኔ ደደብ ስለሆንኩ ይሆናል፡፡ ውይ በእማዬ ሞት በቃ አንድ ቀን በርጫ ይዤ መጥቼ ከመረቀንኩ በኋላ የተሠማኝን በቀላሉ አወራልሻለሁ፡፡ ግን እማዬ ትሙት የዛን ቀንም በፅሁፍ እንዳትይኝ፡፡ ከፈለግሽ ስናገር መቅዳት ትቺያለሽ፡፡››

ሠለሞን...

‹‹ካየሁሽ ቀን ጀምሮ ተራ ሴት አለመሆንሽን

እንደለፈለፍኩ ነው፡፡ ይሄ ደደብ ጓደኛሽ እንኳን

አያደምጠኝም ነበር፡፡ አንዳንዴ ደራሲ...ሌላ
ጊዜ ደግሞ ወሮበላ...አልፎ አልፎ ደግሞ ከፍልስፍና ት ቤት በመመረቂያ ወቅት
የተባረርሽ ተማሪ ትመስይኝ ነበር፡፡ ይሄንን ለማጣራት ሠላይ ሁሉ ቀጥሬ ላሠልልሽ ያሰብኩበት ጊዜም ነበር፡፡በኋላ ምን
አስጨነቀኝ ብዬ ተውኩት፡፡ ግን እግዚአብሔር ቸር ነው፡፡ በቀኑ ባላሰብኩት ሁኔታ ገለፀልኝ፡፡ ለማንኛውም ወደ ቁም ነገሩ ልግባና ስለ ሥዕሎችሽ ትንሽ ላውራሽ ... እንደውም ምንም አላወራሽም፡፡ ብቻ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ
ኤግዚብሽን እንድታዘጋጂ እፈልጋለሁ፡፡ ወጪው ጠቅላላ እስፖንሰር እምሆንሽ እኔ ነኝ፡፡ ጠቅላላ ሴቶች ትርኪ ምርኪ ነገር
ሲከውኑ ዕድሜያቸውን የሚያበክኑ አድርጌ
እቆጥር ነበር፡፡ ለካ እንዳንቺ አይነቷ ከወንድ የምታስንቅ ጀግና ከጎኔ ኖራለች፡፡ እታች ሸለቆ ውስጥ አዘቅዝቄ ስመለከትሽ እላይ ከጨረቃ ጎን ተንሳፍፈሽ አገኘሁሽ፡፡ የኤግዚብሽኑን ነገር እንዳትረሺ፡፡ በአገሪቱ ላይ ስምሽ እንዲነግስ እፈልጋለሁ፡፡ ጋዜጠኞች አንቺን ለማነጋገር እና ታሪክሽን ለመፃፍ ሲተረማመሱ ማየት እፈልጋለሁ፡፡ ድንቅ ነሽ!፡፡››

ሁሴን...

‹‹ደደብነቴ እንደዛሬ ፍንትው ብሎ ተገልፆልኝ አያውቅም፡፡ በከፍተኛ ጥረት የሠበሠብኳቸው ሁለት ዲግሪዎች ባዶ ሆነው ታዩኝ፡፡ ታውሬ ነበር ማለት ነው፡፡ በእኔ ጅልነት አጠገቤ ያሉ ነገሮች ሚስጥር ሆነው ሲቆዩብኝ እበሽቃለሁ፡፡
ለነገሩ አንዳንድ ጊዜ አጠገብሽ ካለ ነገር ይልቅ
እሩቅ ስላለ ነገር የበለጠ ዕውቀት ይኖርሻል፡፡
ምናልባት እንዲህ የታወርኩት በዛች ድብቅ
ደራሲ የተነሳ ይሆናል፡፡ ውስጤን ተቆጣጥራዋለች፡፡ የማሰብ አቅሜም ተዳክሟል፡፡ ለማንኛውም ፍቃደኛ ከሆንሽ ስለ
ሕይወትሽ ታሪክ፣ስለ ስራዎችሽ እናም ስለ አጠቃላይ ማንነትሽ ተከታታይ ታሪክ በጋዜጣዬ ላይ መፃፍ እፈልጋለሁ፡፡ የፈለግሽውን ያህል ብር ልከፍልሽ ፍቃደኛ ነኝ፡፡ ስዕሎችሽን በተመለከተ አድናቆቴን በቃላት ልገልፅልሽ ያዳግተኛል፡፡ግን አንድ ውለታ እንድትውይልኝ እፈልጋለሁ፡፡ የደራሲዋን ስዕል ሳይልኝ፡፡ በተለያየ ጊዜ ስለሷ የማውቀውን ሁሉ ነግሬሻለሁ፡፡ባንቺ ምናብ ምን እንደምትመስል ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ ቢያንስ መፅናኛ ይሆነኛል፡፡ ለማንኛውም ለሊት ደውልሻለሁ፡፡ ላወራሽም እፈልጋለሁ፡፡ ያንቺው አክባሪና አፍቃሪ ነኝ፡፡››
ማስታወሻ ደብተሯን አሽቀንጥራ ወለሉ ላይ ወረወረችው፡፡ ‹‹ስሜት አልባ እመስለዋለሁ እንዴ?ዛሬም በዚች ልዩ ቀኔ ስለእኔ ምን እንደምታስብ ንገረኝ ስለው እሱ ምንም ሳያውቃት ስላፈቀራት ሴት ይደሰኩርልኛል? ለምንድነው ግን የሠው ልጅ ሲባል ካየነው ነገር ይልቅ ያላየነው ከዳሠስነው ይልቅ ያልነካነው ከአገኘነው ይልቅ ያጣነው ነገር ይበልጥ ዋጋ ያለው መስሎ የሚሠማን? በእጃችን ላይ ያለው እንቁ ለምን ድንጋይ መስሎ ይታየናል?፡፡ >> መዓት ጥያቄዎችን እራሷን ጠየቀች፡፡ መልስ ሳታገኝ እንቅልፍ ይዟት ጥርግ አለ፡፡
        ።።።።።።።።።

ሁሴን ዛሬ ቤቱ የገባው በጊዜ ነው፡፡ እራሱን በመጠኑ ስላመመው በእንቅልፍ እንዲያልፍለት ሳሎን ሶፋ ላይ ጋደም ቢልም እንቅልፍ ግን አልወሰደውም፡፡ሰሞኑን መደበት ውስጥ ተነክሯል፡፡እንዲሁ ምክንያቱ ባልገባው ነገር ይጨናነቃል..በማያበሳጭ ነገር ይበሳጫዋል፡፡ብቻ መላ ፀባዩ ቅይርይር ብሏል፡፡ፎዚያ ከጓዳ በር ብቅ አለች፡፡

‹‹ትምህርት ቤት አልሄድሽም እንዴ?››ጠየቃት፡፡

አትኩራ እያየችው‹‹ ዛሬ የለንም ..ምነው አንተ ጠቋቆርክ?››አለችው፡፡

‹‹ደህና ነኝ፡፡ ትንሽ ብቻ ተጫጭኖኛል፡፡››

‹‹ቡና ላፍላልህ?››

‹‹ስራ ከሌለሽ ደስ ይለኛል፡፡››

‹‹ኧረ የለኝም፡፡›› በማለት እየተንደረደረች ወደ ኩሺና ገባች፡፡

ሁሴን ስለ ፎዚያ ሲያስብ ይገርመዋል፡፡ አንድ ላይ መኖር ከጀመሩ ሦስት ዓመት አልፎአቸዋል፡፡ አንድም ቀን አስከፍታው ወይንም የማያስደስተውን ነገር ለመስራት ሞክራ አታውቅም፡፡ በመጀመሪያ የተገናኙበት አጋጣሚ ትዝ አለው፡፡ ትክክለኛ ቀኑንና ወሩን አያስታውሰውም ብቻ ከሦስት ዓመት በፊት ነው፡፡ ቢሮ አምሽቶ ጨለምለም ሲል በዝግታ እየነዳ ወደ ቤቱ እያመራ ሳለ ሲጋራ አሠኘውና ኪሱን ቢዳብስ ማግኘት አልቻለም፡፡ መኪናውን ጥግ አሲዞ አቆመና ወደ ኪዎስክ ጎራ አለ... ሲጋራ፡፡ ገዝቶ ሲመለስ ግን ዓይኖቹ አንድ ነገር ላይ አረፉ፡፡ የመብራት ምሰሶ ስር አንድ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰች ልጅ እግር ወጣት ሴት ቁጭ ብላ ታለቅሳለች...ያረጀ ሻንጣ አጠገቧ አለ፡፡ ሻንጣው ላይ የተወሰኑ ደብተርና መጽሀፎች ይታያሉ፡፡ አልፏት እንዳይሄድ የሆነ የማያውቀው ስሜት ሰቅዞ ያዘው፤ አቅጣጫውን ቀየረና ወደእሷ በማምራት
ተጠጋት፡፡ ቀናም ብላ አላየችውም፡፡ እንባዋ በቀጥታ ከአይኖቿ ወደ መሬት ይንጠባጠባል.. ጠብታዎቹም ሲደጋገሙ መሬቱን እያጎደጎድት ነው..ጥቃቅን የብሶት ኩሬ እየፈጠሩ..፡፡

‹‹ምን ሆነሽ ነው የእኔ እህት?›› ጠየቃት፡፡

…ዓይኖቿን ወደ ላይ በልጥጣ ተመለከተችው፡፡

ጎንበስ አለና ቀኝ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ‹‹ከቤት ተጣልተሽ ነው?›› ሁለተኛ ጥያቄ ጠየቃት፡፡

በደከመና በተጎተተ ድምፅ‹‹አ...ዎ›› ስትል መለሠችለት፡፡

‹‹ታዲያ ጎዳና ላይ ምን ትሠሪያለሽ? ጎረቤት ወይም ዘመድ ጋር ለምን አትሄጅም? ያስታርቁሻል፡፡››

‹‹ዘመድ የለኝም፡፡››

‹‹እናትና አባት ብቻ ነው ያለሽ?››

‹‹እናትም አባትም የለኝም፡፡ አንድ አክስት ብቻ ነበር ያለችኝ እሷው ነች ያ.ባ..ረ..ረ..›› ሳግ ስለተናነቃት ንግግሯን መቋጨት አልቻለችም፡፡ ከኪሱ ሶፍት አወጣና ፊቷ ላይ የተረጨ እንባዋን አበሠላት፡፡ ትንሽ ካረጋጋት በኋላ እጇን ይዞ አስነሳት፡፡ በጥርጣሬ እያየችው በዝግታ ተነስታ ቆመች፡፡

‹‹ይኸውልሽ አሁን መሽቷል፡፡ ለዛሬ እኔ ቤት ታድሪና ነገ የሚሆነውን ነገር እንነጋገራለን፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ የዱርዬ መጫወቻ እንድትሆኚ ጥዬሽ ልሄድ አልችልም፡፡››
​​#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከምሽቱ 5 ሰዓት ስንዱ ስራዋን ጨርሳ ለመተኛት ወደመኝታዋ መጥታ ከውጭ ቀርቅራ የሄደችውን መኝታ ቤት ስትከፍት ነበር..ሳባ 14 ዓመት ወደ ኋላ የተጓዘችበትን ረጅም የትዝታ ጉዞ አቋርጣ የተመለሰችው፡፡ስንዱ ቀስ ብላ ከፍታ ገባች ስታያት ጭብጥብጥ ብላ በተኛችበት አይኗን ቁልጭ ቁልጭ ታደርጋለች፡

‹‹ውይ ቀሰቀስኩሽ እንዴ?››

‹‹አይ አረ አልተኛሁም ነበር?››

‹‹ምነው እስከአሁን?አመመሽ እንዴ?››

‹‹አይ ምንም አልል..እንዲሁ የባጥ የቆጡን ሳስብ ነው?››

‹‹ካልተኛሽማ እራት ላምጣልሽ?››

‹‹አረ እኔ ነገም አልበላ..ቅድም እኮ ጠቀጠቅሸብኝ.ይልቅ. ስትደክሚ ነው የዋልሽው ነይና ተኚ›› ‹‹ካልሽ እሺ››
አለችና..ወደቁምሳጥኑ.ሄዳ ከፈተችና ለብሳ ስትሰራበት የቆየችውን ቀሚስ አውልቃ ሌላ ፒጃማ ከውስጥ አውጥታ ስትለብስ ከተደረደሩት ልብሶች መካከል የሆነ ቢጫ ልብስ ከቁምሳጥኑ ተንሸራቶ አልጋው ጠርዝ ላይ ወደቀ…ሳባ ጨርቁ ሳታስበው ትኩረቷን ሳበውና እጇን ዘረጋች…ወደራሷ ጎተተችው፡፡

‹‹እንዴ ስንድ ይሄ ምንድነው?››

‹‹የመነኩሴ ልብስ ነዋ››

‹‹የመነኩሴ?…እትዬ ልትመለኩስ ነው.እንዴ?››እትዬ ያለችው የስንዱን እናት ነው፡፡

‹‹አይ እሷ ገና ሌላ ለማግባት ሁሉ ሳታስብ አትቀርም››ስትል ቀለደች

‹‹እና የማን ነው?››

‹‹የእኔ?››

ሳባ ቆሌዋ ነው ተገፈፈው

‹‹ምን?›ከተኛችበት  ብርግግ ብላ ተነሳችና ቁጭ አለች፡፡

‹‹ምነው ?ይሄን ያህል ያስጨንቃል እንዴ?››

‹‹እኔ እኮ ደረቅነትሽን ስለማውቅ ነው እስከዛሬ ዝም ያልኩሽ…ሰባት አመቱ ካለፈ ግን ግድ አናግራታለሁ ብዬ እቅድ ነበረኝ››
ስንዱ ፒጃማውን ለብሳ ጨርሳ ወደአልጋው ወጣችና ከጎኗ ቁጭ ብላ‹ምን የምታናግሪኝ ነገር አለ.?ምንም እኮ የለም›አለቻት
‹ለምን የለም…?ገና እኮ 34 አመትሽ ነው….ሰላሳ አራት አመት ማለት ደግሞ ገና ሙሉ ወጣት ነሽ ማለት ነው.አብዛኛው የአዲስ አበባ ሴት በዚህ እድሜዋ ከእናቷ እቅፍም አትወጣም..ገና በዚህ እድሜያቸው ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ስለማግባት ራሱ የሚያስቡት››

‹‹እና ታዲያ እኔ ስለምን ላስብ..በህይወቴ በጣም የማፈቅረውን ሰው አግብቼ ልዩ የሆነ የትዳር ጊዜ አሳልፌያለሁ፤በህይወቴ በጣም የምወዳቸው አንድ ሴትና አንድ ጎረምሳ ወንድ ልጅ አለኝ…እና ከዚህ በላይ ምን ለማግኘት ብዬ ስለዚህ ጉዳይ አስባለሁ?›

‹‹ተይ እንጂ ስንዱ..አባዬስ በዚህ ውሳኔሽ  ደስ  የሚለው ይመስልሻል?  በዛ  ላይ እኔም እህት ራጂም ወንድም ይፈልጋል፡››

‹‹አይ እንደዛ ከሆነ አንቺ የምትወልጂውን ልጅ ወንድም አድርጎ መቀበል ይችላል አንቺም እንደዛው.እኔ ባሌን ሳገባው በህይወት እስካለህ ድረስ ሳይሆን በህይወት እስካለሁ ድረስ ለአንተ ታምኜ ያንተ ሚስት ሆኜ እኖራለሁ ብዬ  ነው ቃል የገባሁለት… ይሄንን ቃሌን ከማጥፍ ደግሞ ዛሬውኑ ብሞት  ይሻለኛል..በይ አሁን ተኚ›› ብላ ከጭንቅላቷ በላይ ያለውን ማብሪያ  ማጥፊያ  ተጭና  አጠፋችና ትራሷን አስተካክላ ተኛች…ሳባም  እሷ  እንዳደረገችው  አደረገችና  እቅፍ አደረገቻት…፡፡

‹‹ስንድ››

‹‹ወይ ሳባ››

‹‹ከድሮም ጀምሮ ባንቺ የማፍቀር ፀጋ እንደቀናሁ ነው..እኔም በህይወቴ ያንቺ አይነት ፍቅር ማፍቀር ብችል አንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰለሽ?››

‹‹ትቺያለሽ አንድ ቀን እንደዛ የምታፈቅሪውን ሰው አምላክ ይሸልምሽ ይሆናል፡፡››

‹‹ያ ቀን ሳይመጣ አረጀሁ እኮ ››

‹‹ሳቢ እኔ ካንቺ ባላውቅም እስትንፋስሽ በውስጥሽ እስካለ ድረስ ለምንም ነገር አይረፍድም…እንደውም አንዴ የነፍስ አባቴ የነገሩኝን አጭር ታሪክ ልንገርሽ››

‹‹እሺ ንገሪኝ››

‹‹ሰውዬው ነፍስ ካወቀ ጀምሮ በራዕይ አንድ ዛፍ ስር የተቀመጡ አዛውንት መምህር ሲያገኝና የእሳቸው ደቀ መዝሙር በመሆን ጥበብንና እውቀትን ሲያስተምሩት በተደጋጋሚ ያያል።ከዛም እድሜው ሲጎለብትና ሙሉ ወጣት ሲሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ቆርጦ ይነሳል።ሰውዬው እኛን እድሜውን ሙሉ በራዕይ ሲመለከታቸው የኖረውን መምህር ፍለጋ አለምን ለመዞር ቁርጠኛ ነበር።ከዛም ስንቁን ሸክፎ ጉዞ ጀመረ።ከመንደሩ ወጣ እንዳለ ከአንድ ሽማግሌ ጋር ተገናኘ።ሽማግሌው በሚያስደነግጥ ግርማ ሞገስና በፍፁማዊ ፀጥታ ዛፍ ስር ቁጭ ብለዋል።

ወደእሳቸው ጠጋ አለና"ሲታዩ ተጓዠ ይመስላሉ?"ሲል ጠየቃቸው

"አዎ:-እኔ ተጓዥ ነኝ፡፡ በዚህ እድሜዬ ሙሉ ዓለምን በጠቅላላ ዞሬያለሁ ማለት ይቻላል።"ሲሉ መለሱለት።

"እርሷ ትክክለኛው ሰው ኖት...እኔ ፍፁማዊ ለሆነ መምህር ደቀመዝሙር መሆን ታላቁ ምኞቴ ነው።ቤቴንና መንደሬን ለቅቄ የህልሜ ሰው የሆነውን
በዕውቀት የበሰለና በጥበብ የመጠቀ መምህር ፍለጋ እየወጣሁ ነው።እባክዎ በየት ብሄድ የምፈልገውን አይነት መምህር  ላገኝ  እና  የእሱ የዘላለም ደቀመዝሙር መሆን እንደምችል ሊጠቁሙኝ ይችላሉ?"ሲል ጠየቃቸው። ሽማግሌውም የተወሰነ አድራሻዎች ሰጡት...ወጣቱም አመስግኖ ተለያቸውና በጉጉትና በተስፋ ጉዞውን ቀጠለ።
ወጣቱ እንዳሰበው ሳይሆን ከአንድ መምህር ወደሌላው እየዞረ  ለ30  አመት ምድርን ካሰሳት በኃላ የሚፈልገውን አይነት ጥበብና እውቀት  ኖሮት  ልብን ሊያሸንፍ የሚችል መምህር  ሊያገኝ  ስላልቻለ  ተስፋ ቆርጦ አዝኖና  በጣም ተከፍቶ ወደመንደሩ የመልስ ጉዞ ጀመረ፤በሚገርም አጋጣሚ ወደመንደሩ ሲቃረብ ከሰላሳ አመት በፊት አግኝቶና አውርቷቸው የነበሩት አዛውንት ሰውዬ ይበልጥ አርጅተው እዛው ዛፍ ስር እንደተቀመጡ አገኛቸው።ወዲያው  እንዳያቸው ተገለፀለት፤ግማሽ እድሜውን ፈጅቶ ሲፈልጋቸው የነበሩት መምህር እራሳቸው እንደሆኑ አመነ፤ የተቀመጡበትም ዛፍ ልጅ ሆኖ በተደጋጋሚ በህልሙ ሲያየው የነበረው እንደሆነ እርግጠኛ ሆነ። እናም ተንደርድሮ ወደ እሳቸው ቀረበ።እግራቸው ስር ተደፋና"ከሰላሳ አመት በፊት ስጠይቆት ለምን እርሶ እንደሆኑ አልነገሩኝም?"ሲል ጠየቃቸው

"ልጄ በወቅቱ ለአንተ ጊዜው አልነበረም።ለዛ ነው ሊገለፅልህና ልትለየኝ ያልቻልከው።አለምን በመዞር የተወሰነ ልምድ ማግኘት እና  የተወሰነ መብሰል ነበረብህ።አሁን በብስለት ማየት ችለሀል።ከሰላሳ አመት በፊት ግን እንዲህ አልነበርክም።አግኝተኸኝ ነበር ግን ልታየኝ አልቻልክም።አውርተኸኝ ነበር ግን እያዳመጥከኝ አልነበረም።እና በጠየቅከኝ መሠረት የተወሰኑ አድራሻዎችን ሰጠሁህ ፡፡ አድራሻዎቹ የተሳሳቱ ቢሆንም ግን ተምረህባቸዋል...እኔም ይሄው.ሰላሳ አመት ሙሉ ከዚህ ዛፍ ስር አልተንቀሳቀስኩም ፡፡አንተን ተመልሰህ እስክትመጣ እየጠበቅኩህ ነበር አሉት።

‹‹እሺ ምን ለማለት ነው?››አለቻት ሳባ

‹‹ምን አልባት እስከዛሬ ፍለጋሽ የራቀ ቦታ ሆኖ እየኳተንሽ ይሆናል የኖርሽው…ለአንቺ የሚሆነው ነገር በእግዜር ተዘጋጅቶልሽ  በቅርብሽ  በቀላሉ  በምታገኚበት ቦታ ተቀምጦ ሳለ ሳታይው ቀርተሸ እንዳይሆን ብዬ እሰጋለሁ፡፡እና ቀኑ ደርሶ በማስተዋል አይንሽ ተገልጦ ያንቺ  የሆነውን  አንድምታይ  እርግጠኛ ነኝ …በይ አሁን ደህና እደሪ ለሊት መነሳት አለብን፡፡››
ሳባ እሷን ላለመረበሽ ስትል የተኛች መስላ አደፈጠች..እናም.ቅድም ወዳቋረጠችው ትዝታ ተመልሳ ገባች፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ባለ ኮፍያ ጀኬት አወጣና ሰጣት፡፡በፈገግታ አመሰገነችውና እርምጃዋና ሳታቆም ለበሰች፡፡

ፊት ለፊታቸውም ያሉት እራቅ ብለዋል ኋላም ያሉት ቢያንስ በ20 እርምጃ ወደኃላ ቀርተዋል፡፡፡ስለዚህ በምቾት ታወራው ጀመረ፡፡

‹‹ቁራኛዬ..ስለመልካምነትህ አመሰግናለሁ››አለችው፡፡
‹‹ቁራኛዬ ማለት ምን ማለት ነው?››ጠየቃት፡፡
‹‹በሀገራችን የጥንት ጊዜ ቁራኛዬ የሚባል ባህላዊ የፍርድ ስርዓት ነበር፡፡ በዳይና ተበዳይ፤ሰራቂና ተሰራቂ ፤ገዳይና የተገደለበት ፍርድ የሚሰጥበት ቦታ እስኪደርሱ ድረስ እንዲህ እንደእኔና እንደአንተ በአካባቢው ሽማግሌ ሸማቸውን አንድ ላይ ይቋጥርሩትና እርስ በርስ አቆራኝተው ይልኳቸዋል፡፡በጉዞቸው ታዲያ አንድ ሌላውን በመንከባከብ..ከአደጋ በመጠበቅ ፍርድ እስከሚያገኙበት ቦታ ድረስ በሰላም የመድረስ ግዴታ አለባቸው፡፡ከዛ ተከራክረውና ማስረጃቸውና አቅርበው የተወሰነው ከተወሰነ በኃላ ነገሩ ይደመደማል ፡፡
‹‹የሚገርም ባህል ነው፡፡››
‹‹አዎ ነው..ለመሆኑ ትክክለኛ ስምህ ማን ነው?፡፡››
‹‹ካርሎስ››
‹‹የእኔ ኑሀሚ ነው ..ኢትዬጵያዊ ነኝ፡፡››
‹‹ኢትዬጵያ የት ነች..?ኢስያ አህጉር ውስጥ ነች?››
‹‹አይ አፍሪካ ነች….ምስራቅ አፍሪካ፡፡››
‹‹እ አዎ አስታወስኩ…ታዲያ እዚህ እንዴት ተገኘሽ?››
‹‹በናንተ ተጠለፍኩ እንጂ… የተባበሩት ድርጅት የተፈጥሮ ጥበቃ ፅ/ቤት ባዘጋጀው አለምአቀፍ ሴሚናር ላይ ለመካፈል ነበር አመጣጤ፡፡››
‹‹እ የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ ነው የምትሰሪው?››በአድናቆት ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ …ነበር፡፡››
‹‹እድለኛ ነሽ…የተፈጥሮ ጥበቃ ወታደር መሆን ከምንም በላይ የሚያኮራ ስራ ነው፡፡በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ በከፍተኛ ትጋትና ጥረት ምድርን ለማውደም እየሰራ ነው….ያ በጣም አሳሳቢ እና አደገኛ ጉዳይ ነው..ግን ደግሞ ተስፋ እንዳንቆርጥ የሚያደርገን እንደአንቺ አይነት ጀግኖች ያንን ጥፋት ለማክሰም ሲለፉና ሲጥሩ ስለምናይ ነው፡፡ ››
እሷ ለተፈጥሮ ጥበቃና እንክብካቤ እሱ በሚያስበው ልክ ቁርጠኝነቱ ሆነ ፍላጎቱ እንደሌላት ብታውቅም ያንን በግልፅ ልትነግረው አልፈለገችም፡፡ስለእሷ አሁን እየተሰማው ባለው አድናቆትና ክብር እንዲቀጥል ፈልጋለች..ምን አልባት በሆነ አጋጣሚ ሊጠቅማት አንደሚችል አሰበች፡፡
‹‹ተፈጥሮ ላይ ያለህ ፍላጎት ጥልቅ ይመስላል?፡፡››

‹‹አዎ እዚህ በምታይው መልኩ ለመኖሬ ምክንያቴ ለተፈጥሮ ካለኝ ቀናኢነት የተነሳ ነው፡፡ከአማዞን ጫካም ሆነ ከአማዞን ወንዝ ፍቅር ይዞኛል፡፡ይሄው እዚህ ከገባሁ አምስት አመት አለፈኝ…በተቻለኝ አቅምና ዕውቀት የዚህ ደን ውስጠ ሚስጥሩን በርብሬ እያጠናሁ ነው፡፡እስከአሁን ሁለት መፅሀፍ አሳትሜያለሁ….አሁን ደግሞ ሶስተኛውን እየሰራው ነው፡፡››ብሎ አስደመማት፡፡
‹‹የእውነትህን ነው የምታወራኝ?››
‹‹አዎ እውነቴን ነው፡፡››
‹‹እስኪ ስለአማዞን ጥቂት ንገረኝ፡፡››አለችው
‹‹ምን ልንገርሽ…?››
‹‹ስለአጠቃላይና መሰረታዊ ነገሮች፡፡››
 
‹‹እሺ …አማዞን የአለማችን ትልቁ ደን ሲሆን 40 በመቶ በሚሆኑት የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ላይ አርፏል፡፡ የአማዞን ጥቅጥቅ ደን 9 ሀገራት ላይ የረፈ በዓለም ላይ ትልቁ ሞቃታማ ደን ሲሆን የሚያካትታቸው ሀገሮችም ብራዚልን  60% ፣ ፔሩ  13% የደን ሽፋን ፣ ኮሎምቢያ 10% እና ቀሪው 17% ቬንዙዌላ ፣ ኢኳዶር ፣ ቦሊቪያ ፣ ጉያና ፣ ሱሪናሜ እና የፈረንሳይ ጓያና የአማዞን ደን የጋራ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የአማዞን ስፋት የህንድን ሁለት እጥፍ ያክላል፡፡ያ ማለት አማዞን አንድ ላይ ተካሎ እራሱን የቻለ አንድ ሀገር ይሁን ቢባል ከ30ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያሉት የአለማችን 9ኛው ትልቁ ሃገር ይሆን ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹ይገርማል፡፡››ብላ አድናቆቷን ገለፀችለት፡፡
በዛ ተበረታቶ ማብራሪያውን ቀጠለ‹‹ሌላው በአማዞን ደን ከ350 በላይ ነበር ጎሳዎች በውስጡ ተበታትነው ሲኖሩበት ከእነዛ ጎሳዎች መካከል ከ75 በላይ የሚሆኑት ጎሳዎች እርስ በእርስ ተገናኝተው የማያውቁ እራሳቸውን ከሌላው ማህበረሰብ፤ከመንግስትም ሆነ ከማንኛውም ቴክኖሎጂ ያራቁ ናቸው፡፡ ስለእንስሳቱ ንገረኝ ካልሺኝ ደግሞ አማዞን በአለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አጥቢ አንስሳት፤አዕዋፋት እና በደረት የሚሳቡ ፍጡራን የሚገኙበት ደን ነው፡፡በዛ ጥቅጥቅ ደን 400 ቢሊዮን ዛፎች፤40 ሺህ የእጽዋት እና 1300 የአዕዋፍ ዝርያዎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡››
በገለፃው የእውነት ከልቧ ተደምማበት‹‹እውነትም ከዚህ ደን ጥልቅ የሆነ ፍቅር ይዞሀል››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡
‹‹አዎ…በትክክል ገልጸሸዋል፡፡››

ንግግሩን ያቋረጠው ከኃላቸው የፉጨት ድምፅ ሲሰማ ነው፡፡ፈጠን አለና ክንዷን ጨምድዶ እየሄድበት ካለው ጠባብ መንገድ ዞር አድርጎ በመውሰድ አንድ ግዙፍ ዛፍ ጋር አጣብቋት በሰውነቱ ጋርዷትና ቆመ ፡፡እሷን በግንዱና በራስ መካከል አድርጎ ስላቆማት ትንፋሽ አጠራት፡፡ቢሆንም እንደምንም ችላው ‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
በእጅ ላይ ያለውን ሽጉጥ እንዳቀባበለ ወደፊት ደቅኖ የሚሆነውን እየጠበቀ ነው….እጁን አፉ ላይ በመጫን ዝም እንድትልና ድምፅ እንዳታሰማ ጠየቃት ፡፡ወዲያው ሰቅጣጭ የሚያጎራ አይነት የሰው ድምፅ ተሰማ …እሱን ተከትሎ…ሶስት ተከታታይ ፉጨት ተሰማ፡፡
የሆነ አደጋ ተፈጥሮል፡፡እርዳታ እየጠየቁ ነው፡፡ከጀርባዬ ተከልለሽ በጥንቃቄ ተከተይኝ አለና ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ…በአንድ እጇ ትከሻውን ይዛ ከወጋቧ ወደታች አጎንብሳ ልክ እንደእሱ እየተሹለከለከች ወደኃላ መጎዝ ጀመሩ፡፡ ከሶስት ደቂቃ በኃላ ተፈላጊው ቦታ ሲደርሱ የሚዘገንን ነገር ገጠማቸው…የሆነ ኩሬ መሳይ እረግረግ ቦታ ላይ ስድስት ሚሆኑት አጋቾቾ ክብ ሰርተው መሳሪያቸውን አቀባብለውና ደቅነው እንተኩስ አትኩሱ እየተባባሉ ይጨቃጨቃሉ፡፡መሀከል ላይ ያ ሲነሱ ከቤት ክንዷን ጨምድዶ ያወጣት አውሬ መሳየ ሰው ተዘርሯል፡፡ እሱ መሆኑን ያወቀችው በተንጨፈረረ ፀጉሩ እና በለበሰው ጃኬት ነው፡፡በሙሉ ሰውነቱ አንኮንዳ ዘንዶ ልክ እንደጥምዝ ቀለበት ተጠምጥሞበት ወደረግረጉ ጉድጓድ እያሰመጠው ነው፡፡እዲህ አይነት ነገር እንኳን በአካል በፊልም አንኳን አይታ አታውቅም፡፡ዝግንን አላት፡፡አረ በፈጣሪ የሆነ ነገር አድርጉና አድኑት››ጮኸች፡፡
ሁሉም ዞር ዞር እያሉ አዮት››መናገሯን እንጂ ምን እንዳለች የገባው የለም፡፡››ለካ ያወራችው በአማርኛ ነው፡፡ሁል ጊዜ ከልክ በላይ ስትደነግጥና ስትናደድ ከአማርኛ ቋንቋ ውጭ በአንደበቷ ለምን ሌላ ቋንቋ እንደማይገባ ሁሌ እንደገረማት ነው፡፡ትዝ ሲላት ወዲያው ስህተቷን አረመችና በእንግሊዘኛ ደገመችላቸው፡፡እነሱ በእስፓኒሽ ተነጋገሩና መተኮስ ጀመሩ …ደም እየተንኮለለ መፍሰስ ጀመረ ..የሰውዬው ይሁን የአናኮንዳው አላወቀችም፡፡ሁለቱም ኩሬ መሳይ እረግረግ ውሀ ውስጥ ሰመጡና ከእይታቸው ተሰወሩ፡፡ከተወሰነ ደቂቃዎች መደናገጥ እና ቁዘማ በኃላ ሁሉም እንደቀድሟቸው በሰልፍ ገብተው መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡