አትሮኖስ
228K subscribers
105 photos
3 videos
41 files
303 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ከሦስት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ እስራት ይሆናል፡፡ በዚህ ሁኔታ እዚያች ከተማ የሚኖረውን ስደተኛ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ የዘዬድኩት መላ ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን ሌሊት ጭምር በመሥራት ብር ማጠራቀም ነበር፡፡ በእርግጥ ተሳክቶልኝ ነበር፤ ግን ሰዎቹ ዓይናቼው ለአፍታ ሰይርገበገብ_እያንዳንዷን ገንዘብ እንዴት እንደሚነጥቁ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ሞላልኝ ስል የለመዱ ፖሊሶች አጋጣሚ አስመስለው ይደርሱብኝና ለወር ያጠራቀምኳትን አስፈራርተው በጉቦ ይወስዳሉ፡፡ የባሕሩ ውሃ ጨዋማ ነውና መላ ሰውነቴ ተላልጦ ሚጥሚጣ የነሰነሱበት ያኽል ያንገበግበኝ ነበር፤ በተለይ የእጄ መዳፍ። ለጥቂት ሳምንታት ያልኩት ሰው ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር በዚያች የተረገመች የባሕር ዳርቻ ከተማ ቆዬሁ፡፡ በእነዚያ ጊዜያት የሰው ልጆችን የድህነት ጥግ ተመለከትኩ። ጭካኔና ጋጠወጥነትን ታዘብኩ፡፡ ድህነት ከፈሪሃ እግዚአብሔር ጋር ካለባት አገር ሄጄ በዚያች የወደብ ከተማ በማዬውና በምሰማው ግራ ተጋባሁ። የሰው ልጅ የት ድረስ እንደሚዘቅጥ አዬሁ፡፡ የድህነት ጥሩ ባይኖርም ብቻውን በስንት ጠዓሙ!? ወንጀልና ጋጠወጥነት ሲጨመርበት ግን የማኅበረሰብ ነቀርሳ ነው፡፡ሰዎች ለሲጋራ ሲገዳደሉ ተመለከትኩ፡፡ የሰው ሞት የመጨረሻ ርካሹ ነገር ነበር። ውሃ ላይ የሚንሳፈፍ የሰው ሬሳ፣ በእግር ገፋ አድርጎ ሥራን መቀጠል ለእኔ ዓይነቱ ክፉ ሕልም ነበር፡፡ እዚህ ግባ የማይባል ብር ዙፋን ላይ ተፈናጦ ፍጡራንን ሲያባላ፤ ሲያዝዝ አዬሁ፡፡ አሜሪካ ከገባሁ በኋላ ለቡና የምከፍለው ሒሳብ እዚያች የተረገመች ወደብ ላይ ተአምር የሚሠራ ገንዘብ ነበር፡፡ የሰው ዋጋ በአገር ዋጋ ልክ እንደሚተመን የገባኝም

ያኔ ነው፡፡ አገር ሲረክስ የሰው ዋጋው አብሮ ይረክሳል፡፡ ለአገር መሞት፣ ለአገር ዋጋ መክፈል ትርጉሙ ስሜታዊ ጀግንነት አይደለም፤ በተዘዋዋሪ የራስን ዋጋ በሚገባ ልክ ለመስፈር የሚደረግ የክብር ትግል እንጂ!!
አሳ አጥማጆቹ ማታ ስራቸውን ሲጨርሱ ጀልባቸውን ጣጥለውልኝ ባህሩ ዳርቻ
ወዳሉ ሕገ-ወጥ መጠጥ ቤቶች እያውካኩ ይጣደፋሉ፡፡ ጀልባዎቹን በወፍራም ገመድ ባሕሩ ዳርቻ ላይ ከተተከሉ ችካሎች ጋር አስሬ፤ እስከ እኩለ ሌሊት እዚያ በውሃ የበሰበሰ ዝርክርክ መረብ ጋር ስታገል አመሻለሁ፡፡ አንዳንዴ መረቡ ስለሚተባተብብኝ ዝም ብዬ እየጠቀለልኩ አስቀምጠዋለሁ፡፡ ጧት ወደ ሥራ ሲሄዱ ታዲያ መረቡን መዘረጋተረ ስለማይችሉ በብስጭት ጥፊም ካልቾም ያቀመሱብኝ ጊዜ ነበር። ብዙዎቹ በመጠጥ የናወዙ ዓሣ አጥማጆች፣ ለቁጣም ሆነ ለደስታ ቅርቦች ነበሩ፡፡ ትዕግስት፣ ትህትና የሚባል ነገር አያውቁም፡፡ በእርግጥ ዓሣ ማጥመድ ጊዜ ጋር እሽቅድድም ይጠይቃል፤ ለደቂቃ መዘግዬት አይፈልጉም። ክብር የሚባል ነገር ያለበት ጊዜና ቦታ ላይ ሆነው ሲያስቡት ነገሩ ክብር ይነካል። ይሁንና የሐበሻ ወኔዬን ዋጥ አድርጌ ሥራውን ለመድኩት፡፡ እንዲያውም ደንበኞቼ በዙ፡፡ ጀልባዎቹን ማዬት ደስ ይለኝ ነበር፤ ማዕበሉ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ደርሶ ሲመለስ ወደውቂያኖሱ ይስባቼዋል፤ የታሠሩበት ገመድ ደግሞ ወደ ዳርቻው ይጎትታቼዋል፤ እንዲሁ ሲወዛወዙ ይነጋል፡፡ አንዳንዴ ሁሉንም ፈትተህ ልቀቃቼው የሚል የእብድ ሐሳብ ውልብ ይልብኝ ነበር፡፡ ጀልባዎቹ እኔን ራሴን ይመስሉኝ ነበር።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የዶ/ርን ስልክ እንደዘጋ ርብቃ ጋር ነው የደወለው<<መቼስ እሁድ ስለሆነ ቤት ትኖሪያለሽ ብዬ ነው?››

‹‹አዎ ቤት ነኝ ..እየመጣህ ነው እንዴ?››

‹‹አዎ ፈልጌሽ ነበር?››

<<ና አለውልህ››አለችው፡፡ ስልኩን ዘጋውና ታክሲ ውስጥ ገባ፡፡

ሲደርስ ቆንጆ ቁርስ ሰርታ ጠበቀችው፤ በጣም የገረመው ያገኛት በህልሙ የመጣችበት ጊዜ የለበሰችውን ቀሚስ ለብሳ ነበር ፡፡

ከቁርስ በኃላ

‹‹አረፍ እንበል እንዴ? >> አለችው በአገጯ ወደ መኝታ ቤቷ እየጠቆመችው….፡፡

‹‹አይ እስቲ መጀመሪያ እዚሁ ሳሎን ሆነን እንነጋገር።

<<እንነጋገር?>>

‹‹አዎ ምነው?››

‹‹እኔ እንጃ እኔና አንተ እንነጋገር ብለን ተነጋግረን አናውቅም ብዬ ነዋ ..እኔ እንነጋገር ሲሉኝ ይጨንቀኛል...፡፡ የሆነ ችግር..የሆነ የተበላሸ ነገር ያለ መስሎ ነው የሚሰማኝ…ይገርምሀል እናትና አባቴ ሁል ጊዜ እንነጋገር እንዳሉና በጠረጴዛ ዙሪያ እንደተቀመጡ ነው... ግን አንድም ቀን በመግባባት አጠናቀውት አያውቁም...እና ቃሉ ያስጠላኛል፡፡››

‹‹እና ካልፈለግሽ ልተወው?››

‹‹አይደለም ..ዝም ብለህ በፊት እንደምታደርገው ቀለል አድርገህ በጨዋታ መልክ አውራኝ ነው ያልኩህ››

‹‹እሺ›› አለ ፈገግ ብሎ‹‹…ባለፈው አንድ ጨዋታ በስልክ ጀምሬልሽ ነበር….ስለ እኔ እና ስለ ፅዮን››

‹‹አስታወስኩት….፡፡››

‹‹እንድንጋባ ትፈልጋለች፡፡››

‹‹በጣም አፍቅራሀለች ማለት ነው ?አደራ ግን እዳትጎዳት... አንተ በጣም ምርጥ ጓደኛ መሆን እንደምትችል እኔ ምስክር ነኝ ..ለእሷ ደግሞ ምርጥ ባል ለመሆን ሞክር፡፡››

‹‹እሞክራለሁ….ከዛ በፊት ግን አንቺ ብታገቢኝ ምን አለበት ብዬ ልጠይቅሽ ነበር የመጣሁት››

<<እኔ....? ጋብቻ>>

‹‹አዎ ጋብቻ...ካፈቀርሺኝ ማለቴ ነው?››

‹‹ስለማፈቅርህማ ነው የማላገባህ..አየህ ታዲ እኔ ስላንተ ምንም አይነት ቆሻሻ ትዝታ እንዲኖረኝ አልፈልግም..7 አመት ሙሉ ህይወቴን በፍቅር አጣፍጠህልኛል...አንተን በማግኘቴ በጣም እጅግ በጣም እድለኛ ሰው ነኝ... ወደ ጋብቻ ¶ይዤህ ገብቼ የሆነ ነገር ታስቀይመኝና ይሄንን ስለአንተ ስገነባ የኖርኩትን የፍቅር ሀውልቴን ታፈርስብኛለህ ብዬ እሰጋለሁ.. ስለዚህ ይቅርብኝ፡፡››

‹‹በቃ የመጨረሻ ውሳኔሽ ይሄ ነው?››

‹‹አዎ ከዚህ በፊት አንተን ለማግባት ሁለት ሶስት ጊዜ አስቤ ነበር፤ቀድሜ ሁሉ ልጅ ልወልድልህ ፈልጌም ነበር፤ከዛ እንድታገባኝ ማለት ነው››

<<ሎጅ?>>

‹‹አዎ ልጅ ልወልድልህ ....ከዛ ላገባህ፡፡››

‹‹እና ሀሳብሽን ለምን ቀየርሽ?››

‹‹ተረጋግቼ ሳስበው የጅል ሴት ዘዴ ሆኖ አገኘሁት..አይህ ወንድ ልጅ እንዲያገባህ የተሳሳትክ መስለህ ማርገዝ ትክክለኛ ዘዴ አይደለም ፡፡ምን አልባት አፍሮ፣ይሉኝታ ይዞት፣አዘኔታ አንጀቱን አላውሶት..ወይም ለልጁ ካለው ፍቅር አንፃር በሁኔታዎች አስገዳጅነት ወደ ጋብቻ ተስማምቶ ሊገባ ይችል ይሆናል..ነገር ግን ቆየት ብሎ ጋብቻው ችግር ላይ መውደቁ አይቀርም፤አይደለም በሆነ ሰበብ አስገዳጅነት ይቅርና በፍፁማዊ ፍቀር እና በሙሉ ፍላጐት የገቡበት ጋብቻ እንኳን አስተማማኝ አይደለም፡፡››

«እና?»

‹‹እናማ ሀሳቤን ሰረዝኩ፡፡››

‹‹ለእኔ ልጅ የመውለዱን?››

‹‹....ኧረ አንተን ማግባቱንም ጭምር፡፡››

‹‹አሁን ግን እኮ ልጅ አርግዘሽልኛል፡፡››

‹‹የምን ልጅ?››

‹‹ልጅ ነዋ... እርጉዝ ነሽ፡፡››

‹‹አንተ እኮ ምላስህ ጥቁር ነው..በእናትህ አታሟርትብኝ፡፡››

‹‹ማሟረት አይደለም.. የእውነቴን ነው…፡፡አሁን የለበስሽውን ቀሚስ ለብሰሽ በህልሜ መጥተሸ ነበር..ለዚህ ነው በጥዋት ወደአንቺ የመጣሁት፡፡››

‹‹ይሄንን ቀሚስ አታውቀውም እኮ ከሶስት ቀን በፊት ነው የገዛሁት..በዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ ደግሞ ካንተ ጋር አልተገናኘሁም፡፡››

‹‹እኔም የገረመኝ እሱ ነው..ጥምዝ የወርቅ ሀብል በፍቅር አጠለቅሺልኝ.. ስሜቴ እንደሚተረጉምልኝ ከሆነ ልጅ ሳታረግዢልኝ አልቀረሺም፡፡ >>

‹‹እንዴ ሀብል አጠለቅኩልህ ማለት እሺ እንዳልከው ልጅ ይሁን ..ከፅዬን እንደሆነስ ..? የግድ እኔ ስላጠለቅኩልህ ከእኔ ነው ማለት ይቻላል?››

‹‹አይ ከፅዮን ጋር መዋሀድ እንደማንችል አይቼያለሁ..በዛ ላይ ሀብሉ ሁለት ተመሳሳይ አንድ ላይ የተጠቀለለ ነበር ...አንዱን እራስሽ አንገት ላይ ስታጠልቂ አንዱን እኔ አንገት ላይ ነው ያደረግሽው፡፡››

‹‹ጥሩ ህልም ነው ፤ግን አንድ የዘነጋሀው ነገር ቢኖር እኔ በየሶስት ወሩ ሳላሰልስ የወሊድ መከላከያ መርፌ እንየተወጋው መሆኔን ነው፡፡››

‹‹አውቃለሁ.... ያ ማለት ግን ላለማርገዝሽ መቶ ፐርሰንት ማስተማመኛ ነው ማለት አይደለም..እዚህ ሰፈር በቅርብ ክሊኒክ አለ?››

‹‹አዎ ምነው ጠየቅከኝ?››

‹‹ተነሽ ሄደን ቼክ እናድርግ?››

‹‹ምኑን?››

‹‹ማርገዝ አለማርገዝሽን >>

‹‹የምርህን ነው እንዴ?›› አለችው በፍራቻም በመጠራጠርም ጭምር.. ምክንያቱም ከዚህ በፊት ታዲዬስ ተመሳሳይ ከህልም የመነጩ ትንቢቶችን ነግሯት እሱ እንዳለው ተግባራዊ ሲሆኑ ደጋግማ ታዝባለች፡፡

‹‹ተነሽ እንጂ፡፡››ትንሽ ካቅማማች በኃላ ተስማምታ ተነሳች.... ተያይዘው ወጡ፡፡

ከአንድ ሰአት በኃላ..ወደቤት ተመልሰው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡

‹‹..ጭራሽ የሶስት ወር እርጉዝ?››በንዴት ተንጨረጨረች፡፡

‹‹ርብቃ አይዞኝ ተረጋጊ እንጂ፡፡››

‹‹እንዴት ልረጋጋ..?እኔ ገና ለገና ስራና ገንዘብ ስላለኝ ብቻ አባት የሌለው ልጅ መውለድ አልፈልገውም፡፡>>

‹‹ምን ማለት ነው? አባቱ እኮ አለሁ... እኔ ነኝ::››

‹‹አንተማ የሌላ ሰው ባል ልትሆን ነው››

‹‹እርሺው ..እኔ እንኳን ልጅ ኖሮኝ ቀድሞውንም ያንቺን ፍላጐት ላክብር ብዬ ነው እንጂ የማፈቅረው ማግባትም የምፈልገው አንቺን ብቻ ነው››...አፍጥጣ በአድናቆት አየችውና‹‹ፅዮንስ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አስረዳታለዋ››

‹‹ምን ብለህ …?ሞራሏ እኮ ሊነካ ይችላል?››

‹‹ጋብቻ የሰው ሞራል ለመገንባት ወይም ለይሉኝታ ሲባል የሚገባበት አይደለም፡፡››

‹‹ቢሆንም እኔ እንጃ ምን ማለት እንዳለብኝ እንኳን ማወቅ አልቻልኩም››

‹‹አባት የመሆን ብቃቴ ተጠራጥረሽ ነው አይደል፡፡››

አይ እሱን እንኮን ፍፁም ልጠራጠር አልችልም..ያንተን አባት የመሆን ብቃት ከተጠራጠርኩማ እኔ የአለም ትልቋ ደደብ ነኝ ማለት ነው..አንተ እኮ የአለም ምርጥ አባትነት ብትወዳደር እንደምታሸንፍ አውቃው››

‹‹እና ምንድነው ችግሩ››

ችግሩማ ምንም እንኳን በአባትነትህ ቅንጣት ጥርጣሬ ባይኖረኝም በባልነትህ ግን እኔ እንጃ..አንተ የትዳር ሰው ይወጣሀል ብዬ ማሰብ ይከብደኛል፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሃምሳ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ የዶ/ርን ስልክ እንደዘጋ ርብቃ ጋር ነው የደወለው<<መቼስ እሁድ ስለሆነ ቤት ትኖሪያለሽ ብዬ ነው?›› ‹‹አዎ ቤት ነኝ ..እየመጣህ ነው እንዴ?›› ‹‹አዎ ፈልጌሽ ነበር?›› <<ና አለውልህ››አለችው፡፡ ስልኩን ዘጋውና ታክሲ ውስጥ ገባ፡፡ ሲደርስ ቆንጆ ቁርስ ሰርታ ጠበቀችው፤ በጣም የገረመው ያገኛት በህልሙ የመጣችበት ጊዜ…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ዛሬ…አሁን

ሳባ ባለ አንድ ፎቅ በሆነ የግቢዋ የአትክልት ስፋራ ከደራሲ ጳውሎስ ጋር ቁጭ ብላ እየተማከረች ነው፡፡ደራሲ ጳውሎስ ከዚህ በፊት ሁለት መፅሀፎችን ፅፎ ለህትመት ያበቃ እጅግ ድንቅ የስነ-ፅሁፍ ችሎታ ያለው ግን ደግሞ  በኑሮ  ያልተሳካለት በድህነት የታችኛው ወለል ላይ የሚገኝ ከዛም አልፎ ጉልት ቸርቻሪ በሆነች እናቱ ተጧሪ ለመሆን የተገደደ የ35 አመት ወጣት ነው፡፡

እርግጥ ሳባም ገና 33 ዓመቷ ላይ ነው የምትገኘው፡፡ግን በዚህ ዕድሜዋ ከጳውሎስ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ሚኒዬነር ሆናለች፡፡የሀብታም ልጅ ሆና ውረስ ስላገኘች አይደለም…ድንገት ሎቶሪ ወጥቶላትም አይደለም፡፡ለአለፉት 10 አመታት ህይወት ያመቻቸችላትን እድል በአግባቡም ከአግባብ ውጭም  በመጠቀም ባገኘችው የገንዘብ ስኬት ነው፡፡
አሁን ከጳውሎስ ጋር የተገናኘችው ለድርድር ነው፡፡እሷ ብር አላት እሱ ደግሞ የስነ-ፅሁፍ ችሎታ አለው፡፡እሷ ላለፉት አንድ አመት መፅሀፍ መፃፍ  ጀምራ ነበር፡፡ልብ ወለድ አይደለም፤የግጥም መድብልም አይደለም..ፍፅም በእንደዛ አይነት ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ፍላጎት የላትም፡፡ለአንድ አመት የደከመችበት መፅሀፍ ጭብጡ ስለሰራዋ ነው…እርግጥ በገዛ ህይወቷ ላይ  የሚያጠነጥን አይደለም፤ባለፉት አስር አመታታ ስትስራ በነበረውና ከመናጢ ድህነት ሚኒዬነር ስላደረጋት ስራ ጠቅላላ ባህሪ፤አስገራሚና አስደማሚ ምስጢራዊ ታሪኮች ነው፡፡ግን በሂደት ረቂቁን መጨረስ ብትችልም ጣዕምና ሰጥቶ፤ የሰውን የንባብ አፕታይት በሚከፍት መልኩ ውበት አላብሶ መጨረስ አልቻለችም፡፡ስንፍና ብቻ ሳይሆን ለዛ  የሚሆነ ቸሎታም ሆነ ልምድ  የላትም፡፡  ለዛም  ነው  አሁን  ከደራሲ ጰውሎስ ጋር በሰው በሰው ተገናኝታ እየተነጋረች ያለችው፡፡

‹‹ረቂቁን አነብከው?››

‹‹አዎ አንብቤዋለው፡፡››

‹‹እና የምትሰራው ይመስልሀል?››

‹‹እሱን አትጠራጠሪ …በደንብ ሰራዋለው፡፡ግን ጥያቄ መጠየቅ እችላለሁ?››

‹‹ጠይቀኝ፡፡››

‹‹ልብ-ወለድ ነው ወይስ የተወሰነ እውነት አለው?››

ይሄ ስራ ህይወትህን የሚቀይር ጥቅም የምታገኝበት ነው፡ግን ያንን ረቂቁን አሳምረህና አስውበህ መፅሀፍ ስላደረከው ብቻ አይደለም የምከፍልህ፡፡መፅሀፉ ታትሞ ከተሰራጨ በኃላ ይዞ ሚመጣው መዘዝ ከባድ ስለሆነ ነው፡፡እያንዳንዱ በረቂቁ ያነበብከው ታሪክ መቶ ፐርሰንት እውነት  ነው፡፡  በታሪኩ  በቀጥታ በትክክለኛ ስማቸው ባይሆንም ታሪካቸው የተጠቀሱ ሰዎች ከፍተኛ  ስልጣን ያላቸው ወይ ደግሞ ሀገሪቱን የሚያሽከረክሩ ሀብታሞች ወይ ደግሞ ሚሊዬን ተከታይ ያላቸው ታዋቂ አርቲስቶች ናቸው…እና  መፅሀፉ ከታተመ እና ካነበቡት በኃላ ስማችን   እየጠፋ ነው ብለው ስለሚያስቡ   አሳደው ወይ ይገድሉሀል ወይ እስር ቤት ያስወረውሩሀል፡፡›

‹‹እንዴ…አልገባኝም፡፡ የፃፍሽው አንቺ ነሽ…. እኔ እኮ በቃ ኤዲተር በይኝ.››

‹‹አይ ደራሲውም አንተ ነህ…..መፅሀፉ በአንተ ስም ነው እንዲታተም የምፈልገው፡፡››

ፍራቻ ውስጥ ገብቶ አይኖቹን እየያቁለጨለጨ‹‹ኸረ ይሄ ነገር ካሰብከኩት በላይ  ከባድና ውስብስብ ነው…..ይቅርብኝ፡፡››አለት
‹‹ወደ ውጭ ሀገር ማለት አሜሪካ ወይም አውሮፓ ለመውጣት ብዙ ጊዜ ሞክረህ      እንዳልተሳካልህ ሰምቼያለው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ፡፡››

‹‹እኔ  ካናዳ ልልክህ እችላለው..መፅሀፉን በስምህ ታትሞ እንዳለቀ ከመሰራጨቱ በፊት አንተ ከሀገር እንድትወጣ አደርጋለሁ፡፡››

ያልጠበቀውን  ነገር  በመስማቱ  በደስታ  ከመቀመጫው  ተነሳና  መልሶ ተቀመጠ‹‹እርግጠኛ ነሽ እንደዛ ማድረግ ትቺያለሽ?››
‹‹አዎ በሶስት ወር ውስጥ ያንን ማድረግ እችላለሁ፡፡በዛ ጥርጣሬ አይግባህ …እኔ እንዳዛ ማድረግ ካቃተኝ..መፅሀፉ ለገበያ አይቀርብም…››

‹‹እንደዛ ከሆነ እንስማማለን፡፡››

‹‹ጥሩ… ማወቅ ያለብህ ይሄ ጉዳይ ለእኔ የህይወትና የሞት  ያህል  ወሳኝ  ነው፡፡ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ የሙሉ ጊዜ ስራህ ይሄ ነው የሚሆነው…ስለመፅሀፉ ከማንም ጋር አትነጋገርም…ማንም ሰው ከመፅሀፍ ግማሽ ገፅም ቢሆን ማንበብ አይችልም፡፡ለዚህም  ምቹ  እንዲሆንልህ  ቢሾፍቱ  ኩሪፍቱ  አልጋ ተይዞልህ…የፈለከው  ነገር  እዛ  ይሟላልሀል..ላፕቶፕ  ጨምሮ   አስፈላጊ   ነገሮች ሁሉ ተዘጋጅተዋል….በጣም ከራቀ ልክ የዛሬ ሁለት ወር ጨርሰህ እንድታስረክበኝ እፈልጋለሁ…ከዛሬ ጀምሮ ከእኔ ጋር በአካል አንገናኝም..ሚስጥራዊ  ቁጥር ሰጠሀለው፡፡ ስትፈልገኝ ትደውልልኛለህ… ስፈልግህ ደውልልሀለው፡፡››

በገጠመው ሎቶሪ መሰል እድል ውስጡ በደስታ እየጨፈረ..‹‹ጥሩ ነው፡፡››አላት፡፡
በዚህ ጊዜ የሳባ ሞባይል ጠራ …አየችውና…‹‹አንዴ ይሄን ስልክ ልመልስ›› በማለት ከመቀመጫዋ ተነስታ ፈንጠር አለችና አነሳችው፡፡

‹‹ሄሎ ፍቅር››

‹‹ሄሎ እንዴት ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ..ፈልጌሽ ነበር..ዛሬ ስራ አለሸ እንዴ?››

‹‹አይ እረፍት ነኝ፡፡››

‹‹እቤት ለምን አትመጪም?››

‹‹እቤት ነው ያልከው…ያንን ጉሮኖህን እቤት ብለህ ስትጠራ አታፍርም?››

‹‹አንቺ ደግሞ ያው እስከምኖርበት ድረስ እቤቴ ነው››

‹‹እ ነው እንዴ? አላወቅኩም ነበር..ለማንኛውም እዛ መምጣት አልችልም፡፡››

‹‹እሺ እኔ ልምጣ፡፡››

‹‹ባክህ ይቅርብህ፡፡››

‹‹ተይ እንጂ..ለሆነ ጉዳይ ፈልጌሽ እኮ ነው?››

‹‹ምነው ገንዘብ ፈለክ?››

‹‹እኔ አንቺን የምፈለግሽ ለገንዘብ ብቻ ነው እንዴ?››

‹‹እ ይቅርታ እሙሙዬ አምሮህ ነው?››

‹‹አረ በናትሽ ለቁም ነገር ነው የፈለኩሽ?››በመልሷ ምርር አለ፡፡

‹‹እሺ አትነጫነጭ. .ና››አለችው፡፡

‹‹እሺ የእኔ ቆንጆ››ብሎ ስልኩን ዘጋና ተንደረደረ፡፡ወደ እሷ ቤት፡፡

የፋሲል እና የሳባ ግንኙነት ግራ አጋቢና ውል የሌለው አይነት  ነው፡፡እሷ የምትፈልግው ለአንድ ጉዳይ ነው…በወሲብ ጎበዝ ስለሆነ በምትፈልገው መንገድና መጠን ስለሚያስደስታት ብቻ ነው፡፡እሷ  ባለፉት  አስር  አመታት  ባሳለፈችው የሥራ ህይወቷ የተነሳ የወሲብ ባህሪዋ ተበላሽቷል፡፡ ሙሉ በሙሉ  የስነ-ልቦና መፋለስ አስከትሎባት ጭምልቅልቅ ያለ ሱስ ውስጥ ገብታለች…እሱ ቋሚ ስራ ስለሌለው ገንዘብ በጣም ያስፈልገዋል...ህይወቱን የሚገፋው ከዚህና ከዛ እየቦጫጨቀ ሞላ ጎደል በመጫወት ነው፡፡ከእሷ ጋር ከተገናኘ በኃላ  ግን በአንፃራዊነት የገንዘብ ችግሩ ተቀርፎለታል፡፡በስራዋ ከምታገኘው ልክ እንደቅጠል ከሚሸመጠጥ ገቢዋ ላይ ጥቂት ቆንጠር አድርጋ በየጊዜው ስለምታስጨብጠው እሷን ለማስከፋትና ቅር ለማሰኘት ፈፅሞ አያስብም…፡፡
እሷም ለአለፉት አንድ አመት ከእሱ ጋ አስፈላጊ በሆኑ ቀናቶች በመገናኘት በምታሳለፈው ጊዜ ደስታኛ ሆነ ቆይታለች..አሁን አሁን ግን ምን ያህል አብራው እንደምትዘልቅ አልገባትም…እሱን በተመለከተ በእስከዛሬ ህይወቷ ያላደረገችውን አንዳንድ ነገሮች በማድረግ ስህተት መስራቷን ታምናለች፤ለምሳሌ እቤቷን ፈፅሞ ማሳየት እንዳልነበረባት ታምናለች..እርግጥ ስለእሷ ሚያውቀው ጥቂት ነገር ነው፡፡ሆስተስ ነኘ ብለዋለች፡፡እሱን ማግኘት በማትፈልጋቸው ቀናቶች ከሀገር ውጭ በረራ አለብኝ ለዚህን ያህል ቀን አንገናኝም ትለዋለች፡፡ስለሚፈራት ያለችውን ሁሉ አመነም አላመነም ይቀበላታል.እሷም ታዘዥነቱ ትወድለታለች፡፡በእሱ ቦታ ሌላ ለራሴ ክብር አለኝ ብሎ የሚመፃደቅ ወንዱ ቢሆን ኖሮ እሷ በምትፈልገው አይነት የተበላሸ የወሲብ ስሜቷን ያስታምምላት እንደሆነ እርግጠኛ
አይደለችም፡፡ከእሱ በፊት ቀርባቸው የነበሩት ሁለት ወንዶች እንዴት አይነት አስቸገሪ ሁኔታ ላይ ጥለዋት እንደነበረ ዛሬም ትዝ ሲላት ዝግንን ይላታል፡፡
አሁን የምትፈራው ይሄ ልጅ ይሄን ሁሉ  ነገር  ለምዶ  በቃህ  ከዛሬ  ወዲያ አንገናኝም ብትለው አሜን ብሎ ተሰናብቷት ይሄዳል? እዚህ ላይ ከባድ ጥርጣሬ አላት፡፡ይህንን ጥርጣሬዋን ለማጥራት የቅርብ የሆነ ጓደኛውን በጎን ቀጥራበት ለአንድ ወር ስታሰልለው ነበር፡፡ስለእሷ ምን እንደሚያስብ?እቅዱና ምኞቱን ምን እንደሆነ ?ለማወቅ፡፡በተቀዳ የድምፅ መረጃ ያገኘችው  መረጃ  ግን  ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የጣላት ነበር ፡፡ፈፅሞ እንዳሰበችው አይነት የዋህና ታዛዥ ብቻ የሆነ ሰው ሆኖ አላገኘችው፡፡እሷ  ላይ  የሞትና  የሽረት  የሆነ  ሰፊና  ጥልቅ  እቅድ እንዳለው ደርሳበታለች፡፡ ይሄን ካወቀች በኃላ ሳትበረግግና ስሜቷን ለእሱ በግልፅ ሳታሳውቀው እንዴት ከላዮ ላይ ጉዳት በማያስከትልባት ዘዴ ገለል እንደምታደርገው  እቅድ ማውጣት እዳለባት ገብቷት እየሰራችበት ነው፡፡
እሱ ግን እሷ ምንም እንደምታቅ ባያውቅም እንደተባለው ከእሷ በጣም የራቀ እና የተለየ እቅድ ነበረው፡፡ከእሷ ለዘላለምም ቢሆን የመለየት እቅድ በአእምሮዋ የለም፡፡በጣም እንደምታፈቅረው ነው የሚያስበው፡፡እሱም እለት ከእለት በጣም እያፈቀራት ሄዷል ፤ከዛም በላይ  ከእሷ  ጋር  ከተገናኘበት  ጊዜ  በኃላ  ኑሮውን ከሲኦል ወደገነት ቀይራለታለች፡፡በምንም አይነት ሁኔታ ይሄንን እድል ማባከን አይፈልግም፡፡ከውበቷም ከሀብቷም ፍቅር ይዞታል፡፡አሁን ወደቤቷ የሚሄደው ከእዚህ ጋር ለተያያዘ ጉዳይ ቀስ ብሎ በእርጋታ ሊያማክራት ነው፡፡ይሄንን ጉዳይ እስከመጨረሻው በፍቅርና በሰላም መስመር ለማስያዝ እስከመጨረሻው ጠብታ ይለፋል፡፡የሰላሙ መንገድ የማይሳካ ከሆነ ግን በየትኛውንም ሌላ አማራጭ በመጠቀም ሀሳቡን ለማሳካት ቆርጧል፡፡በሰላም ከሆነ ፍቅሯንም ሀብቷንም መቆጣጠር ይችላል፤ ያ ተመራጩና በጣም የሚፈልገው ነው፡ካልሆነ ግን

በየትኛውም መስዋዕትነት እሷን ዞር አድርጎ ሀብቷን ጠቅልሎ የመረከብ ፍላጎቱ ጣሪያ የነካ ነው፡፡


💫ይቀጥላል💫


አሁንም ዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ #Share እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅንነት እባካቹ👍

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


..ውበት ማለት ከአይን ሌንስ ሞልቶ የሚተርፍ ውስጥን በደስታ ስሜት የሚያጥለቀልቅ በቀለማት ህብር የደመቀ ምስል ነው፡፡.

ዶ/ር ሶፊያ እና ትንግርት ኮንትኔንታል ሆቴል ምሳ በልተው ከጨረሱ በኃላ መጠጥ እየተጎነጩ ጨዋታ ይዘዋል፡፡

‹‹እሺ ትንግርቴ ህይወት እንዴት ነው?››

ጠየቀቻት፡፡

‹‹እንደምታይው ነው፡፡››

‹‹ላገባ እኮ ነው ..ነግሬሻለሁ አይደል?››

‹‹አላስተዋወቅሽኝም እንጂ ነግረሺኛል፡፡››

‹‹አስቤ ነበር ግን ወደ አሜሪካ በረረ ..ያው ጣጣውን ጨርሶ አንደኛውኑ ከ15 ቀን በኃላ ወደ ሀገር ቤት ይመጣል ...ሊያገባኝ ፡፡የዛኔ አስተዋውቅሻለሁ፡፡››

‹‹ቆንጆ ነው?››ትንግርት ጠየቀቻት፡፡:

‹‹ያንቺን ያህል አያምርም እንጂ ቆንጆስ ቆንጆ ነው፡፡››እንዲህ ስትላት የትንግርት ፊቷ ቀላ፡፡

‹‹የሆንሽ ብሽቅ ነገር እኮ ነሽ...ሰውን መተንኮስ መቼም አታቆሚም፡፡››

እውነተኛ ስሜቴን እኮ ነው እየነገርኩሽ ያለሁት..ውበት ማለት ከአይን ሌንስ ሞልቶ የሚተርፍ ውስጥን በደስታ ስሜት የሚያጥለቀልቅ በቀለማት ህብር የደመቀ ምስል ነው፡፡..እንደዛ የሚሰማኝ ደግሞ አንቺን ሳይ ብቻ
ነው፡፡››

‹‹ታድዬ፡፡››አለቻት በማሾፍ፤ቀጠለች‹‹ግን ሁሌ አንድ ነገር ጠይቅሻለሁ እያልኩ ሳገኝሽ እረሳዋለሁ፡፡›››

‹‹ምንድነው አሁን ጠይቂኛ?››

‹‹ሀዋሳ ከመገናኘታችን በፊት ለስድስት ወራት ያህል በሚሴጅ ታጨናንቂኝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ አይደል?››

‹‹አዎ እኔ ነኝ...ማን መስሎሽ ነበር?››

‹‹እኔ እንጃ.... ብቻ ከድሮ የሽርሙጥና ህይወት ካፈራዋቸው ደንበኞቼ መሀከል የፍቅር ግርሻ ናላውን ያዞረው አንዱ ጀግና መስሎኝ ነበር፡፡››

‹‹ትንግርቴ..በእኔ ተረብሸሽ የማትፈልጊው ህይወት ውስጥ ተሰንቅረሽ ሶስት የባከኑ ዓመታት በማሳለፍሽ ግን በጣም አዝናለሁ፡፡››

‹‹የባከኑ አልሻቸው..እነዛ አመታት ፍፁም የባከኑ የሚባሉ አልነበሩም ...የህይወት ልምዶች ያገኘሁባቸው እና ስብዕናዬን የሞረድኩባቸው ዓመታት ነበሩ፤ያን ስል መከራ አልነበረውም፡፡...ስቃይ
አልተቀበልኩበትም፣አልተሰደብኩበትም፣አልተደ በደብኩበትም ፣አልተዋረድኩበትም ማለቴ አይደለም ግን ከተሰቃየሁት ስቃይ ይልቅ ያተረፍኩት በጎ ነገር ሚዛን ይደፋል እያልኩሽ ነው፡፡››

‹‹ግን በመሀል ህይወት አስጠልታሽ ማለቴ ተስፋ ቆርጠሸ አታውቅም?›› ትንግርት እየፈገገች‹‹ታስቂያለሽ..አንድ በጣም የምወዳት አማረች የምትባል ጓደኛዬ አንድ የሚያምር ንግግር ትናገር ነበር …ምን እንደምትል ታውቂያለሽ

<<ተስፋ የሌለው ሰው ተስፋ አይቆርጥም››ምን ለማለት እንደፈለገች መጀመሪያ አይገባኝም ነበር... በኃላ ግን ከገዛ ህይወቴ ጋር አቆራኝቼ ሳሰላሰለው ተገለፀልኝ…፡፡ እኔ ከዛች ከተለያየንበት ደቂቃ ጀመሮ ተስፋ ሚባል ነገር ከውስጤ ወድሞ ባዶ ንብ የሌለበት ቀፎ ሆኜ ነበር፡፡ሶስቱን አመት ሙሉ ያለምንም ተስፋ ነበር የኖርኩት..ለዛም ነው ያልተቸገርኩት…ምንም አጣለሁ ብዬ የምጨነቅለት፡፡..እዚህ ቦታ መድረስ አለብኝ ብዬ የምጥርበት..ይሄንን ነገር ማግኘት አለብኝ ብዬ የምጓጓለት ነገር አልነበረኝም፡፡››

‹‹ያሳዝናል...ትንግርቴ፡፡››

‹‹አትዘኚ...በህይወት ዝቅታ ወይም ከፍታ ላይ በአጋጣሚ ትንጠለጠያለሽ፡፡ከከፍታው
በምታገኚው ምቾት ተጠምደሽ ወይም ከዝቅታው ውስጥ በሚያጋጥምሽ መከራ ተደቁሰሽ አልባሌ ሰው ሆነሽ እንዳትቀሪ ግን የራስሽ ጥንካሬ ይወስነዋል፡፡ከፍታውም ሆነ ዝቅታው የራሱ የሆነ አውንታዊ አና አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፡፡አሉታዊ ጎኑን ተቋቁመን ጠቃሚውን ነገር መቅሰም የእኛ ፋንታ ነው፡፡››ትንግርት እንዲህ ስትናገር ዶ/ር ሶፊያ እንባዋን እያንጣባጠበች ነበር፡፡

‹‹ቢሆንም ትንግርቴ ይህ ላንቺ ፍፁም የሚገባ ህይወት አልነበረም፡፡››

‹‹ላንቺም እኮ ብር ከፍሎ ሰውን ማስገደል የሚገባሽ ህይወት አልነበረም፤ አሜሪካ ሄዶ ለስድስት ወር በአዕምሮ ህመም ማገገሚያ ሆስፒታል ውስጥ ታግቶ መኖር፤የማትፈልጊያቸውን ኪኒኖች እየጎመዘዘሽ መቃም፤በድንዛዜና በብዥታ ቀናቶችን መግፋት ላንቺም የሚገባ አልነበረም፤አየሽ ሶፊ ‹ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ስር እናደርጋለን› የሚባለው በትክክል የሚሰራው በሶሰሻሎስቶች የመፈክር ባነር ላይ በቲዬሪ ደረጃ ብቻ ነው፡፡…እንደውም
በተቃራኒው ተፈጥሮ ነች እኛን ባብዛኛው የምትቆጣጠረን…የህይወት መስመርሽን አንቺ በፈለግሽው መንገድ ብቻ ማስኬድ አይቻልሽም፡፡ቤተሰብ ወደዚህ ይጎትትሻል፣ጓደኞችሽ ወደዛ ይስቡሻል፣ሀገርሽ ወደ ላይ ታወጣሻለች፣ያላሰብሻቸው አጋጣሚዎች ወደታች ያወርዱሻል፣ስለዚህ የሆነው ሁሉ ሆኗል፤በመሆኑም ደግሞ ለበጎነው ብለን መቀበልና ወደፊት መጓዝ ብቻ ነው የሚበጀን፡፡››

‹‹ለበጎ ነው ስትይ?››

‹‹በምንም ምክንያት ሆነ በምንም አንቺ ጥለሽኝ መሄድሽ በጊዜው ፈተናው ከባድ ቢሆንም በስተመጨረሻ ያመጣው ውጤት ዛሬ ህይወታችን እንዲህ ኖርማል እንዲሆን ስላደረገ ውጤቱ ጥሩ ሆኗል ማለቴ ነው፡፡››

‹‹ግን እኮ ሁለታችንም የምንፈልገው ያንን ኖርማል ያልሆነውን ህይወት ነበር፡፡››

‹‹ቢሆንም ዘላቂ ውጤቱ መልካም አይሆንም ነበር…ማህበረሰብ እንዴት ነበር የሚያሰቃየን...?
መቼ ነው የምታገቡት..?ኧረ ቆማችሁ ቀራችሁ፤ በዛ ላይ የልጅ መውለድ ጉዳይ አለ...


✂️✂️✂️?????????✂️✂️✂️

‹‹...እሱን እኮ ነው የምልሽ ...አደገኛ የሆኑ ውስብስብ የማህበራዊ ህይወት ቀውስ የሚያመጡብን ችግሮች ውስጥ መግባታችን አይቀርም ነበር፡፡››

‹‹ያልሻቸው ነገሮች እንደሚከሰቱ አውቃለሁ ... ቢሆንም ግን ምርጫ ቢቀርብልኝ አንቺን
ከማጣት ያንን ፈተና መጋፈጥን እመርጥ ነበር፡፡››

‹‹ይሆናል…ግን አሁን ሁሉም አልፏል ...መሆን ያለበት ሁሉ አሁን እንደሆነው ሆኗል... በመሆኑም ትክክል ነው፡፡››

‹‹እንዳልሽ ይሁን .…እሺ ግን ሳገባ ሚዜ ትሆኚኛለሽ››ዶክተር ነች ተናጋሪዋ፡፡

‹‹በሰርግ ነው እንዴ የምታገቢው?››

‹‹እስከአሁን አልወሰንኩም…. ግን አንድ ሃያ ሰው ጠርቼ የእራት ግብዣም ቢሆን ማድረጌ ይቀራል?››

‹‹ታዲያ ያገባች ሴት እኮ ሚዜ አትሆንም፡፡››

«ለምን?»

‹‹ባህላችን ነዋ...መነሻ ሀሳቡን ባላውቅም ምክንያቱን ስገምት ግን ያላገባች ሴት ሚዜ ስትሆን እግረ መንገዷን የራሷን አዳም የምታገኝበትን ዕድል እንድታመቻች ታስቦ የተቀየሰ ስውር ዘዴ ይመስለኛል፡፡››

‹‹አንቺ ...ትንታኔሽ አሳማኝ ይመስላል..በቃ እንደዛ ከሆነ ሌሎቹን ሁለት ሚዜዎች ያላገቡ እንዲሆኑ አደርጋለሁ ያንቺ ግን የግድ ነው፡፡››ተሳሳቁ፡፡

‹‹ካልሽ ምንቸገረኝ..የእኔን ልጅም ክርስትና ታነሺያለሽ፡፡››

‹‹እንዴ!!! አረገዝሽ እንዴ?››

‹‹አዎ 1 ወር ከ15 ቀን ሆነኝ፡፡››

‹‹ኦ!!! ፈጣሪ የእኔ ቆንጆ እንኳን ደስ አለሽ፡፡›››ከመቀመጫዋ በመነሳት ተጠምጥማባት እያገላበጠች ሳመቻት እና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች፡፡

‹‹ክርስትና ግን ስትይ ..ሁሴን ኦርቶዶክስ ሆነ እንዴ?››

‹‹ኧረ አልሆነም፡፡››

<<እና>>

‹‹ምን እና አለው ..ያው እሱም ሀይማኖት የለሽ እንደሆነ የእኔ ሀይማኖት ደግሞ አለየለትም፡፡››

‹‹ግን በኑሮችሁ ምንም ችግር አልፈጠረባችሁም?››

‹‹ያው እስከ አሁን በፍቅር ጥላ ስር ስለሆንን ችግር አልፈጠረብንም… በሚያስማማን እየተስማማን በልዩነታችን ደግሞ እንደልዩነታችን እየኖርን ነው፡፡ፍቅር እኮ ሁሉንም ክፍተቶችሽን ይደፍንልሻል...ፍቅር ሲሸረሸር ነው ሜዳ ሁሉ ገደል፣ነጩ ሁሉ ጥቁር፣ንግግሩ ሁሉ ጭቅጭቅ መስሎ ሚታይሽ፡፡››
‹‹እሱስ ትክክል ነሽ፤መቼስ በማርገዝሽ ደስ ብሎታል?»

‹‹ኧረ አልሰማም፡፡››

‹‹እንዴት.?.ማለቴ...>>

‹‹ገና ትናንት እኮ ነው ያረጋገጥኩት...በምን አይነት ሁኔታ እንደምነግረው ግራ ገብቶኝ ነው ያዘገየሁት፡፡››

‹‹በቃ ዛሬውኑ አብረን እንነግረዋለን..ይሄን ደስታ እኔም አብሬያችሁ ሆኜ ማጣጣም አለብኝ፡፡››

ለውሳኔ በተቸገረ የመዋለል ስሜት‹‹ይሻላል ብለሽ ነው?››አለቻት ትንግርት ፡፡

‹‹አዎ ልደውልለት፡፡››

‹‹እንዴ ደውለሽ ምን ልትይው?››

ዶ/ር ሶፊያ ችላ ብላት ሞባይሎን አወጣችና ሁሴን ጋ ደወለችላት፡፡

‹‹ሰላም ነህ ?››

‹‹አለሁልሽ.. እንዴት ነሽ ጠፋሽ?››

‹‹ኧረ አለው...ባክህ እራት ልጋብዛችሁ ፈልጌ ነበር፡፡››

‹‹እነ ማንን?››

‹‹አንተና ባለቤትህን ነዋ ፡፡ >>

<<የት?>>

‹‹ቤቴ ..አንድ ሰዓት እጠብቃችኋለው››

‹‹እሺ ቻው››ስልኩን ዘጋችና ‹‹ቶሎ በይ ስልክሽን ዝጊ…››አለቻት

«ለምን?»

‹‹ይደውልልሻላ እንዳያገኝሽ፤ሰርፕራይዝ ማድረግ አለብን፡፡›› እንደታዘዘችው ስልኳን ዘጋች፡፡

‹‹በቃ አሁን ወደቤት እንሂድና የእራት ዝግጅቱን እናጧጡፈው፡፡››

‹‹አመረርሽ እንዴ?››

‹‹አዎ ተነሽ፡፡››..…ሂሳብ ከፍለው ወጡና ወደ ዶ/ር ሶፊያ ቤት አመሩ...12፡3ዐ ሲሆን ለእራት የሚያስፈልገውን ዝግጅት ሁሉ አጠናቀው ጨርሰው ነበር፡፡የዶ/ር ሶፊ ስልክ ጠራ ሁሴን ነበር ...አነሳችው...

‹‹ደረስክ እንዴ?››

‹‹ኧረ አልደረስኩም..ይቅርታ ልጠይቅሽ ነው፡፡››

<<የምን ይቅርታ ..…?››

<<መምጣት አልቻልኩም፡፡››

<<ትቀልዳለህ እንዴ .. ?ግማሽ ቀን ሙሉ ማድቤት ስንደፋደፍ እኮ የቆየሁት እንዲ ጉድ እንድታደርጉኝ አይደለም...ትመጣላችሁ ኑ፡፡››

=<ይሄውልሽ ዶ/ር ምን መሰለሽ….፡።››

<‹ምንም ምክንያት አልቀበልም ከቀራችሁ የመጨረሻችን ነው፡፡››ስልኩን ጠረቀመችበት... እየሳቀች፡፡

<<አንቺ በባሌ እና በዓይኔ ቀልድ የለም፤ምንድነው ምታመነጫጭቂው፡፡›› አለቻት ትንግርት፡፡

የዶክተሯ ስልክ መልሶ ጠራ..አነሳችው‹‹እሺ ምንድነው?››

<<የትንግርት ስልክ እኮ አልሰራም ብሎኝ ነው... ቤትም የለችም ቢሮም የለችም፡፡››
=‹በቃ አንተ ናና ስልኳን በከፈተች ጊዜ እንደውልላት እና እንድትመጣ እናደርጋለን፡፡››

=‹ለምን ግን ወደ ነገ አናሸጋግረውም..››

<<ኡፍ ነገርኩህ በቃ… ፡፡››ጠረቀመችበት፡፡

=<አሁን እየበረረ ይመጣል…በይ ግቢና ላባብሺ፡፡››

<‹ምንድነው ምለብሰው?›› አለቻት ትንግርት፡፡

‹በጅንስ ሱሪ የእኔ የእራት ግብዣ ላይ ጠረጴዛ ይዘሽ ቁጭ ልትይ ነው?ዳሩ ኢትዬጵያውያን የበዓል ግብዣ...የሰርግ ግብዣ…የተስካር ግብዣ እንጂ የእራት ግብዣ አይገባችሁም፡፡››

=<ኧረ ባክሽ የእኛ ፈረንጅ!!››

<‹በይ መኝታ ቤት ግቢና ልበሺ፡፡››

<‹ምንድነው ምለብሰው?››ድጋሚ ጠየቀች ግራ ተጋብታ
‹‹ከእኔ የራት ልብሶች መሀከል የሚመችሽን መርጠሸ ነዋ፡፡››

‹‹አንቺስ..?››

‹‹እኔማ ማቀራረቡን ልጨርስና እለብሳለሁ...ደግሞ ዛሬ እኮ ሙሽራዋ አንቺ ነሽ>>

‹‹እሺ ››አለቻትና ወደ መኝታ ቤት ሄደች፡፡በራፉን ከፈተች....ወደ ውስጥ ስትዘልቅ ደንግጣ ቆመች፡፡ ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ የተለያየ መጠን ያላቸው አንድ ፎቶና ሁለት ስዕሎች ተለጥፈዋል፤ አዎ እነዚህን ስሎች ታውቃቸዋለች፤በራሷ እጆች የተሳሉ የምናቧ ፈጠራዎች ናቸው.... ተጠጋችና በፅሞና አስተዋለች.. አንዱ የሶፊያን ምስል ነው ለማስታወሻነት የሰጠቻት ነበር፤ድሮ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እያሉ፡፡ቀጣዩ የሁለቱ የጋራ ስዕል ነው፤…. ይህን ደግሞ ስራ ተቀጥረው አዳማ በገቡ
በሁላተኛ ወራቸው አካባቢ ነው የሳለችው ፡፡ የተቀረው ሶስተኛው ግን ፎቶ ነው የራሷ የትንግርት ፎቶ ፤መች እንደተነሳችው አታውቅም፤በጣም ያምራል..… ግዙፍም ነው፡፡

ከውጭ የበራፉን መከፈት ሰምታ ዞር ስትል ዶ/ር ሶፊያ ነች፡፡

‹‹እንዴ እስከአሁን አለበሽም እንዴ? ሁሴን እኮ መጥቷል፡፡››

‹‹ግን እነዚህ እስከዛሬ አብረውሽ ነበሩ?››አለቻት የእሷን ንግግር ችላ በማለት፡፡

‹‹ወደ ፊትም አብረውኝ ይኖራሉ?››

‹‹አሜሪካ ስትሄጂ የት አስቀምጠሸቸው ነበር የሄድሽው?››

‹‹አብረውኝ ሄደው አብረውኝ ነው የመጡት... በይ ነይ ፡፡››አለቻትና ወደ ቁምሳጥኑ ይዛት ሄደች..ከፈተችው፡፡ከተደረደሩት የራሷ ቀሚሶች መካከል ሁለቱም የሚስማማቸውን መርጠው ለበሱ..

ዶክተሯ‹‹እስክጠራሽ እዚሁ ጠብቂኝ፡፡›› ብላት ወጣችና ወደ ሳሎን አመራች፡፡

‹‹እየጠጣህ ሁሴን….››

‹‹እየጠጣው ነው..ግን የእራት ግብዣው ለእኔ ብቻ ነው እንዴ?››

‹‹አይ ለአንተ ለሚስትህ እና ለሌላ ለማታውቀው እንግዳ ነበር፡፡››

‹‹እሷማ የገባችበት ጠፋ ...ሶስተኛው እንግዳስ…?››

‹‹መጥቷል መኝታ ቤት እየለባበሰ ነው፡፡›››

‹‹ሰውዬሽ ነው እንዴ?››

‹‹አዎ፡፡››

‹‹ለዛነዋ እንዲህ ፍልቅልቅ ያልሽው፡፡››

‹‹ኧረ ባክህ..….እሱ ሳይኖርስ ፍልቅልቅ አልነበርኩም እንዴ?››

‹‹ቢሆንም ይለያል...ሴቶች እንዲህ ወዝ ያለው መፍለቅለቅ ሚያጥለቀለቃችሁ ናፍቆታችሁን ከጉያችሁ ስታስገቡ ነው፡፡››

‹‹ወንዶችስ….?ለማንኛውም ተጫወት››ብላው ወደ መኝታ ቤት ሄደች፡፡

‹‹እዚሁ ልጥራልሽ?››

‹‹ኧረ እኔ እመጣለሁ፡፡››

‹‹ቆይ እንደውም.....ሁሴን >>ድምጿን ከፍ አድርጋ ተጣራች፡፡

<<አቤት፡፡ >>

‹‹ባክህ ከረባት ማሰር ትችላለህ? ይሄ ባሌ እንደዚህ አይነት ችሎታ የለውም፡፡ >>

‹‹ከረባቱን ይዘሽው ነይ…፡፡››

‹‹አይ አንገቱ ላይ አንጠልጥሎታል፤ከይቅርታ ጋር አንተ ብትመጣ ፤በዛውም ላስተዋውቃችሁ››
ሁሴን ከመቀመጫው ተነሳና ወደ እሷ አመራ ..አጠገቧ ደረሰ ‹‹ግባ..ሀኒ ተዋወቀው ሁሴን ይባላል .የትንግርት ባለቤት ነው >> ሁሴን ፈራ ተባ እያለ ወደ ውስጥ ሲገባ የገዛ ባለቤቱን አልጋው ላይ ቁጭ ብላ ፊቷን ወደ በራፉ አዙራ ስትቁለጨለጭ አገኛት፡፡

‹‹ምንድነው ጉዱ ? >>

‹‹ግባና ጠይቃታ >>ብላ ትታቸው ወደ ሳሎን ሄደች ፡፡

ከ1ዐ ደቂቃ በኃላ ተሸክሟት በደስታ እየጮኸ‹‹አባት ልሆን ነው...አባት ልሆን ነው፡፡››በማለት እየለፈለፈ ወደ ሳሎን ይዟት ገባ።

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ስልኳን ዘግታ ወደጳውሎስ ተመለሰችና ቁጭ አለች‹‹ወደቢሾፍቱ መቼ መንቀሳቀስ ትችላለህ?››
‹‹በቃ… ነገም ቢሆን መሄድ እችላለሁ…እናቴን መሰናበት ካልሆነ ሌላ የሚያቆየኝ ጉዳይ የለኝም፡፡››

‹‹ጥሩ …ነገ ጠዋት ሁሉ ነገር ዝግጁ አድርጎ የሆነ ሰው ይደውልልሀል ፡፡ መኪና ይይዛል…እሱም አብሮህ ነው እዛ የሚቀመጠው…የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ የሚያመቻቸው እሱ ነው….አንተ መቶ ፐርሰንት ትኩረትህን ስራህ ላይ ብቻ እንድታደርግ ነው የምፈልገው፡፡ ማንኛውም የምትፈልገው ነገር ሲኖር ለእሱ መንገር ብቻ ነው የሚጠበቅብህ..እሱ ያሟላልሀል፡፡ ….እንደቅድሚያ ክፍያ 50 ሺ ብር ጠዋት በእሱ በኩል እልክልሀለው፡፡የተወሰነውን ቀንሰህ ለእናትህ መስጠትና ምርቃት ማግኘት ትችላለህ፡፡እዛ ያለው ሙሉ ወጪህ የሚሸፈነው በእኔ ነው፡፡››

‹‹ከሁለት ወር ቀድሜ ከጨረስኩስ..?››

‹‹ተጫማሪ ቦነስ ይኖርሀል ማለት ነው፡፡››

‹‹ተስማምቼያለሁ.. አሁን መሄድ እችላለሁ…?፡፡››

‹‹አዎ …ምስጢራዊነቱ  ላይ  ግን ተጠንቀቅ…  ህይወትህን  ሊያሳጣህ ከዛም አልፎ…ጦሱም ለእናትህ ሊተርፍ ይችላል›› ብላ ጨብጣ ሸኘችውና..ጋርደኑን ለቃ ወደቤት ገባች፡፡ቀጥታ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የተንጣለለ መኝታ ክፍሏ ነው ያመራችው፡፡ በጣም ደስ  ብሏታል፡፡ይህ  ጉዳይ  ሀሳብ  ሆኗት  ለወራት ሲያስጨንቃት ነበር ፤ እንዲህ መስመር በመያዙ ፈነጠዘች..ይህ መፅሀፍ ለእሷ የኒኩሊየር ቦንብን ያህል  ዋጋ  አለው፡፡እናም  አሁን  የተደሰተችው  መደሰት  ልክ አንድ የአሸባሪ ቡድን መሪ የኒኩሊየር አረር በእጁ ሲገባ የሚሰማውን አይነት ስሜት ነው የተሰማት፡፡
ቀጥታ ወደ ሻወር ቤት ሄደችና ፈጣን  የሆነ  ሻወር  ወሰደች፡፡  ወደቁም  ሳጥኗ ሄደችና ፓንቷንና ጡት ማሳያዣዋን ብቻ  ለበሰችና  ጋዋኗን  ደርባበት  አልጋዋ ጠርዝ ላይ በመቀመጥ ፋሲልን መጠበቅ ጀመረች..አሁን ለዚህ በውስጧ ለሚፈሰው ደስታ ቺርስ ብላ የምትጋብዘው አንድ ነገር አስፈልጓታል፡፡

ፋሲል  ስለእቅዱ  እያሰላሰለ  ተንደርድሮ  ቤቷ  ሲደርስ  ሳሎኑ  ባዶ  ነው፡፡ ተንደርድሮ ወደፎቅ ወጣ፡፡መኝታ ቤት  ገባ፡፡በጋዋን  ግማሽ  እርቃኗን  ሸፍና ግማሹን አጋልጣ  አልጋው  ጠርዝ    ላይ  ቁጭ  ብላለች፡፡ገና  አልፎ  ወደ ውስጥ እንደገባ ነው ከጭኗ የተነሳው ነፀብራቅ አይኖቹ ላይ የተመሰገው፡፡
ሁኔታዋን ሲያይ ፈራት…የመጣበትን እቅድ ማሳካት እንደማይችል ውስጡ ጠረጠረ.. እሷ ለወሬ ሳይሆን ለወሲብ ዝግጁ ሆና ነበር የጠበቀችው ፡፡ከረሜላ እንዲገዛለት እናትዬውን በልምምጥ እንደሚጠይቅ ህጻን ልጅ ለንቦጩን ጥሎ‹‹አንድ ነገር ላስቸግርሽ ነበር››አላት፡፡
‹‹የእኔ ማር ያንተ ወሬ ይደርሳል….እንደምታየው አሁን ተርቤያለሁ..ቅድሚያ መቅደም ያለበትን ነገር ብናስቀድም..››

‹‹ችግር የለውም..ግን ያልኩሽን እሺ እንደምትይኝ ቃል ግቢልኝ›› ለነገሩ ብዙም ትኩረት ባለመስጠት‹‹ቃል ገብቼልሀለሁ››አለችው..፡፡

ግንባሩን በማነቃነቅ እሱም መስማማቱን አረጋገጠላት…
‹‹ግን ቁጥር 5 ነው የምፈልገው››አለችው፡፡

ገባው…ሁለቱ የሚግባቡበት ኮድ ነው ፡፡12 ዓይነት በመሰቃየት የምትረካበት ዘዴዎች አሉ፡፡እያንዳንዱን ዘዴ በቁጥር ስያሜያቸው ለይታ አስጠንታዋለች.. አሳውቃዋለች፡፡
እጇን ይዞ ከተቀመጠችበት የአልጋው ጠርዝ አነሳት፡የለበሰችውን ጋዋን በቀላሉ ካላዯ ላይ አነሳና  እዛው  ወለል  ላይ  ተዋት፡፡፡ከፊት  ለፊቱ  ግድግዳ  የላይኛው ኮርነር ላይ ግድግዳው ውስጥ ከተቀበረ ብረት አንድ  ላይ  በተያያዘ  ጠንካራ ሰንሰለት እጆቿን ለየብቻ አሰራቸው፡፡በተመሳሳይ መልኩ ከወለሉ ጋር አንድ ላይ ተጣብቆ ከተሰራ ሰንሰለት ጋር እግሮቾን አለያይቶ አሰራቸው፡፡በአጠቃላይ ስትታይ ወዲህና ወዲያ ተበለቃቅጣ የ x ምልክት ሰራች፡፡ከወደ ጥግ የሚገኝ ኮመዲኖውን ከፈተና አብረቅራቂ  ሳንጃ  እና የተወለወለ  የፈረስ መግረፊያ አለንጋ አወጣ፡፡ ቀረባትና ሳንጃውን በቅርብ ርቀት ከሚገኘው ደረቅ ወንበር ላይ አስቀመጠው፡፡አለንጋውን አስተካከለና ባለ በሌለ ኃይሉ መቀመጫዋን ለመጠጣት..ደገማት..በጀርባዋ ዞረ..ፍጥነቱም ኃይሉም እየጨመረ ሲመጣ ፊቷ እየተቀያየረ..ድምፅ እያወጣች መጣች፡፡
ይሄንን የወሲብ አይነት ልክ እንደጥሩ ነገር የወረሰችው በምትሰራው የማሳጅ ስራዋ ደንበኛዋ ከሆነ ከአመታት በፊት የሀገሪቱ ትልቅ ባለስልጣን ከነበረ አንድ ሰው ነው፡፡ይሄ ባለስልጣን ለሶስት አመት ያህል የምትሰራበት ማሳጅ ቤት ደንበኛ ሆኖ በወር ሁለት ቀን ይጎበኛት ነበር፡፡

በሚመጣበት ጊዜ በሁለት ጋርዶች ተከቦ አንድ ሻንጣ የማሰቃያ ብረታ ብረቶችንና መግረፊያ  አለንጋዎችን በመያዝ ነበር፡፡ከዛ በሚሰቀጥጥ አይነት ሁኔታ  እንድታሰቃየው፤ እንድትገርፈውና አንዳንዴም በስለት ቆዳውን እንድትሰነጣጥቀው ያስገድዳት ነበር..ማስገደዱ ግን በማሳፈራራት ሳይሆን በገንዘብ ኃይል የሚከወን ነበር፡፡ለአገልግሎቷ በአንድ ቀን ሀያና ሰላሳ ሺ ብር ነበር የሚከፍላት፡፡ከዛም በላይ አሁን የምትኖርበትን ባለአንድ ፎቅ የተንጣለለ ቪላ ቤት የሰራችበትን 250 ካሬ መሬት በነፃ ከማዘጋጃ ያሰጣት

እሱ ነው፡፡በዛ የተነሳ በሚፈልገው መጠን መጨረሻ ጠብታ ድረስ በስቃዩ ደስታ አግኝቶ እንዲረካ የተቻላትን ጥረት ታደርግ ነበር..በሂደት  ግን ለራሷ  ቆይ ልሞክረው ብላ በመጠኑ ስትሞክረው .ከዛ ትንሽ ስትጨምርበት….ሙሉ በሙሉ የባህሪው ተጋሪ ሆነች፡፡ልክ እንደ ሀሺሽ ሱስ ተፀናወታት፡፡እሱ በመሰቃየቱ ብቻ የሚረካ ግለሰብ ነበር.እሷ ደግሞ በማሰቃየትም. በመሰቃየትም የምትረካ ሴት ሆና እርፍ አለች..ከመምህሩ  ደቀመዝሙሩ  ይባል  የለ….እንግዲህ  ይሄ  ሰው  በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ስልጣኑንም ለቆ ከሀገርም  ስለተሰደደ  ሙሉ በሙሉ ግንኙነታቸው ቢቋረጥም ውርሱን ግን አጠንክራ አስቀጥላለች፡፡ከእሱ ጋር ያላት ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ሁለት ወንዶችን በማደን  የስሜቷ አገልጋይ እንዲሆኑ አሰልጥና ልትጠቀምባቸው ሞክራ ነበር ግን ብዙም ሳይዘልቅ ከሽፎባታል… በመጨረሻ በሆነ  አጋጣሚ  ፋሲልን  አገኘችና  ተሳካላት.ይሄው አመት አለፋቸው፡
ፋሲል ስራውን ቀጥሏል፡፡

‹‹ኸረ የእኔ ጌታ ይቅር በለኝ..››

‹‹ይቅርታ አይገባሽም››

‹‹ተው እንጂ አትጨክንብኝ››

‹‹ከጥፋትሽ መማር አለብሽ..ሀጥያትሽ እንዲሰረይልሽ መቀጣት ይገባሻል››

‹‹እሺ የእኔ ፍቅር…እንዳልክ››

የተቆራረጠና በጣር የተሞላው ምልልስ  በግርፊያው  እንደታጀበ ቀጥሏል..ግርፊያው ከመብዛቱ የተነሳ ክንዶቹ እየዛሉ መጡበት፡፡
‹‹እሺ የእኔ ጌታ ሁለተኛ አልመለስበትም…አይለመደኝም››

‹‹ሁል ጊዜ እንዲሁ ነሽ..አትታረሚም››

‹‹በቃኝ አልኩ እኮ..   አይለመደኝም..   ተቃጠልኩልህ…   ሞትኩልህ… ተንገበገብኩልህ›› በዚህ ጊዜ አለንጋውን ወደ ወለል ወረወረና ሳንጃውን አነሳ..በደንብ ተጠጋት.. ሳንጃውን በደረቷ   አሻግሮ   በሁለት   ጡቶቾ   መካከል ሰቅስቆ አስገባው
‹‹ከዚህ ከፍ ያለ ቅጣት ነው ሚያስፈልግሽ››

‹‹ኸረ ይቅር በለኝ የእኔ ጌታ››

ሳንጃውን አጠነከረ …በፍራቻ ተርበተበተች፡፡ወደ ታች ገፋው የለበሰችው የጡት ማስያዣ ማንገቻን ተራ በተራ ሸርክቶ በተነው....የጡት ማስያዣ ከገላዋ ተፋቶ ወደ ወለሉ ወደቀ፡፡መቃተቷን ቀጥላለች..በወጥመድ የተያዘች አይጥ መስላለች፡፡
​​ቀጠለ የለበሰችውን ፓንት ቁልቁል ወደታች ተረተረው..ሙሉ  በሙሉ  ዕርቃኗን ቀርታ መንዘፍዘፍ ጀመረች…ያቺ አስፈሪ..ያቺ አደገኛ ጀግና ሴት..ያቺ ስንቱ ባለስልጣን ስንቱ የከተማው ሀብታም የእሷን አገልግሎትና እገዛ ፈልጎ ያለችበት ድረስ የሚርመሰመስላት ሴት … ራሷ እንዲህ ድንጉጥ..ተርበትባች እና መጠጊያ የሌላት ደካማ ሴት ሆና ስትታይ እውነት ነው ብሎ ማን ያምናል፡፡
ከዛ ፋሲል‹‹ቅጣትሽ ከእኔ መፀነስ ይሆናል..ትወልጂልኛለሽ››አላት ወደ ጆሮዋ ተጠግቶ፡፡
አቃተተች….ተወራጨች‹‹አይሆንም…ፍፁም አይሆንም…ልጅ መውለድ አልፈልግም …በፈጠረህ?››
አልሰማትም..እንዲሰማትም አይጠበቅበትም…የተሰጠውን ትወና በትክክል መተወን ይጠበቅበታል…ልክ ራሷ እንዳሰለጠነችው፡፡የሱሪውን ቀበቶ ፈታና ሱሪውን ወደታች ዝቅ አድርጎ እርቃኗን በሰንሰለት እጅና እግሯ ተሰትሮ እንደታሰረ ተገናኛት፡፡እየለመነችው..እየተማፀነችው፡፡በመጨረሻ ዝልፍልፍ ብላ አንገቷን ወደታች ቀበረች በዛ ቅፅበት እሱም ከውጥረቱ ረግቦ ነበር፡፡

ሱሪውን ወደላይ መለሰና ግራ እጇን ብቻ ከሰንሰለቱ አላቆላት በሩን ከፍቶ ወጥቶ ሄደ…ባለው ልምድ ከዚህ በኃላ ስሯ መቆየት የለበትም፡፡ ከእብደቷ ስትነቃ ስሯ ካገኘችው መልሳ እሱኑ አስራ ትገርፈዋለች..እስክትረጋጋ  ከፊቷ  ዞር  ማለት አለበት፡፡ ለዚህ ነው ሙሉ ለሙሉ እንኳን ከእስሯ ሳይፈታት መፈርጠጡ፡፡
ነፃ በሆነ እጇ በሰንሰለት እስር ውስጥ ያለውን ሌለኛውን  እጇን  ፈታችና እንደምንም እግሯ ብሬክ እንደሚደንስ ዳንኪረኛ እየተንቀጠቀጠባት ወደሻወር ቤት ገባች…ውሀውን ከላዩ ለቀቀችው.. ከላይ ፀጉሯ ላይ እያረፈ  መላ  ሰውነቷን እያራሰ ቁልቁል ወደወለሉ ሲወርድ እሷ ደግሞ በተሰበረ ልብ እና በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆና እንባዋን እያረገፈችና በሀሳብም እየናወዘች ነበር…..ስታስበው የአለምን ሀጥያት ሁሉ ሰብስባ በተከሻዋ የተሸከመች ይመስላታል..ከሸክሙ ክብደት የተነሳ ትከሻዋ ጎብጧ ግንባሯ መሬት ደርሶ በምላሷ እየላሰች ያለች ይመስላታል..ከዚህ የአእምሮም መጨለም.ከዚህ የልብ መጥቆር…ከዚህ የመንፈስ መታወክ…የትኛው መሲዕ እንደሚያድናት ምንም የምታወቀው ነገር የለም፡፡ለሶስት አመት ብላ የጀመረችው ስራ ዛሬ ነገ ስትል አስር አመት ሙሉ  ሰርታዋለች..እያንዳንዱን ቀን በዚህ ስራ ላይ ባሳለፈችበት መጠን ብዙ ብር እና ብዙ ልብን የሚሰባብር ሀዘን ለራሷ እየሸለመች ነው፡፡በቅርብ ጨከን ብላ ስራዋን እርገፍ እድርጋ ካላቆመች እየሄደች ሳለ ድንገት ተዝለፍልፋ ወድቃ እስከመጨረሻው ሊያበቃላት እንደሚችል እየተሰማት ነው…በቃ ደክሟታል፡፡ይሄ መፅሀፍ  አልቆ  ታትሞ  ገበያ  ላይ  ከዋለ የዛን ጊዜ ሀሳቧ  ይሳካላታል..ነፃ  ትወጣለች፡፡ከዛ ጨለማ ስራዋ  ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ትገላገላለች፡፡ ከዛ በኋላ ምንድነው የምትሰራው….?ለአመታት የሚያኖራት በቂ ብር ባንክ ደብተሯ ውስጥ ስላላት ያ ብዙም አያስጨንቃትም፡፡

ከሻወር ወጣችና ሰውነቷን  በፎጣው  አደራርቃ  ወደአልጋዋ  ሄደችና  ……ጥቅልል ብላ ተኛች፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንችስ


#ክፍል_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ፋሲል ጥሏት ከሄደ ከ5 ሰዓት በኋላ ደወለላት..ከእንቅልፏ ነቅታ እዛው አልጋ ላይ እየተገላበጠች ስታስብ በነበረበት ጊዜ ነበር የደወለላት እና ለእራት የቀጠራት፡፡እየደበታትና ከዛም ተነስቶ እራስ ምታት እየጀማመራት ስለነበር የእራቱን ግብዣ በደስታ ነበር የተቀበለችው…፡፡በዛ ላይ መቼ እንደሆነ ባታውቅም በቅርብ የምታጣው ሰው ስለሆነ እንደመሰናበቻ አሪፍ አሪፍ የተባሉ ጊዜያቶችን ከእሱ ጋር ማሳለፍ ትፈልጋለች፡፡ለዚህ ነው ብዙ ሳታስለምነው በመስማማት ለባብሳና ተቆነጃጅታ ወደቀጠራት ቦታ ሄደችው፡፡

ፋሲል ከሳራ ጋር ያለው ለአንድ አመት ከሁለት ወር የዘለቀ የፍቅር ግንኙነት ህይወቱን ምስቅልቅል አድርጎበታል፡፡እርግጥ የእሱ ህይወት መቼም ከመርመስመስ ርቆ አያውቅም፡፡አሁን ግን ችግሩን የተለየ ያደረገው ማፍቀሩ ነው፡፡22 ዓመት ሆኖት በ11 ዓመት ምትበልጠውን በዕድሜ ታላቁ የሆነችዋን ሴት ከልብ አፍቅሯታል፡፡እርግጥ እሷን ብቻ ሳይሆን ብሯንም ከእሷ እኩል  ነው የሚያፈቅረው፡፡ ግን የሚገርመው ምንነቷን በጥልቀት አያውቅም:: ሀገር ቢያንሾካሹክበትም..ጓደኛቹ ቢያላግጡበትም ለእሱ ለውጥ አያመጣም.. በቃ አፍቅሯታል፡፡ እሷ ግን ታፍቅረው ወይስ  ዝም  ብላ  እንደመደበሪያ  እያየችው ይሆን? በእርግጠኝነት መናገር አይችልም፡፡ግን ማመን የሚፈልገው እንደምታፈቅረው ነው፡፡ቢሆንም ስሜቷን አንብቦ ፍላጎቷን መተንበይ ለእሱ ኪሊማንጀሮን ተራራ በሩጫ የመውጣት ያህል ከባድ ነው የሆነበት፡፡ሁለ ነገሯ ግራ ያጋባዋል…ንግግሯ ግራ ያጋባዋል…አኗኗሯ ግራ ያጋባዋል..የወሲብ ልምዷ ግራ ያጋባዋል..የወደፊት ዕቅዷ ሳይቀር ግራ ያጋባዋል፡፡

እርግጥ እሱ በእሷ ፍቅር ተንኮታኩቶ እንዲወድቅ ካደረገው ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ በየቀኑ ያለስስት የምታስጨብጠው  ረብጣ  ብር  ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ይሄ ግራ አጋቢውና  ነፍሱን  ስልብ  የሚያደርገው  የወሲብ አሰራሯ ነው፡፡በቃ እንደኮኬይን ዕፅ ሱስ ሆኖበታል፡፡ሊተውት የማይቻል  ክፉ ሱስ፡፡ግን ቢሆንም ለዘላቂ ጥቅሙ ሲል ማድረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡

ከተቻለ ይህቺን ሴት ፍጹም ማጣት አይፈልግም፡፡ በአስቸኳይ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት ማሰብ ከጀመረ ሰነባብቷል..ዛሬ ዝግጅቱን አጠናቆ ዕቅዱን ወደተግባር የሚቀይርበት ቀን ነው፡፡ ሊያስደንቃት ወስኗል፡፡
የቀጠራት ሆቴል ብዙውን ጊዜ የሚገናኙበት  ነው፡፡ሁለቱም  ከሆቴሉ ባለቤቶች ሆነ ከአስተናጋጆቹ ጋር ጠንከር ያለ ትውውቅ አላቸው….ስትደርስ ሆቴሉ በተስተናጋጆች ተሞልቷል፡፡ከገመተችው በላይ ሰዎች መኖራቸው ብቻ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ ወንድሜ ነው፤ ጓደኛዬ ነው ፤የአጎቴ ልጅ ነው እያለ ያሰታዋወቃት ስድስት ሰባት የሚሆኑ በእሱ በኩል የምታውቃቸው ሰዎች ሁለትና ሶስት ሆነው እዚህና እዛ ተቀምጠው ስታይ ያልተለመደ ነገር ስለሆነባት ግራ ተጋባች…እውነታው በእሱ ሚስጥራዊ ግብዣ  ተጠርተው  የመጡ  የቅርቡ ሰዎች ናቸው፤ሌሎቹ ደግሞ ባጋጣሚ እግር ጥሏቸው የታደሙ የሆቴሉ ቋሚና ድንገተኛ ደንበኞች ናቸው፡፡ሁሉ ነገር ሙሉና ባሰበው መልኩ የተቀናጀ ቢሆንም አንድ ነገር ግን ቅር አሰኝቶታል..

የኤልሳ እዚህ መገኘት  ነው፡፡ኤልሳ  የልጅነት  ፍቅረኛው  ነበረች፡፡ነበረች  ማለት አሁን ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ አቁመዋል ማለት አይደለም፡፡በተለያየ ጊዜ እየተገናኙ ሳባ እንዳታውቅ እየተጠነቀቀ ይገባበዛሉ..አብረው ይቅማሉ.. አብረው ይጨፍራሉ አልፎ አልፎም አብረው  ያድራሉ፡፡ከዛ  በላይ  በጣም  አደገኛው  ነገር ሁሌ ኤልሳ ስለእሱ እና  ስለሳባ  ግንኙነት በምትጠይቀው ጊዜ የሚመልስላት መልስ ፈፅሞ እሷን እንደማያፈቅራት፤ የቀረባት ለገንዘቧ ሲል ብቻ እንደሆነና እንደምንም ጠቀም ያለገንዘብ ከተቀበላት በኃላ አፍንጫሽን ላሺ ብሎ እሷኑ እንደሚያገባ ከመቶ ጊዜ በላይ ነበር እየማለ ያረጋገጠላት፡፡እውነታው  ግን ዛሬ እየሆነ ያለው ነው፡፡ ፋሲል ሳባን የሚያፈቅራትን  ያህል  ኤልሳ  ደግሞ  እሱን  ታፈቅረዋለች፡፡ለዚህ  ነው ስለ ዛሬው ዝግጅት ዕቅድ ሚስጥራዊ ሆኖ ከእሷ ጆሮ እንዲጠበቅ አጥብቆ ተግቶ የነበረው..አልተሳካለትም እንጂ..አሁን ነገር እንዳታበላሽበት ልቡ ፈርቷል፡፡

በቅርቡ ሳባ የገዛችለትን የጣሊያን ሱፍ ለብሶ ዝንጥ ብሏል..ሳባ ልዩ የሆነ ረጅም ብርቱካናማ የራት ልብስ ለብሳለች፡፡ሁለቱም ውብ ሆነዋል፡፡እራት ቀረበ… ወይን ተቀዳ…ምግቡ በመጐራረስ ተበልቶ መአዱ ከፍ ካለ በኃላ ፋሲል ከመቀመጫው ተነሳና ወደመድረኩ ተንቀሳቅሰ፤ ሙዚቃውን አዘግቶ ማይኩን   ተቀበለና ጉሮሮውን አፀዳድቶ መናገር ጀመረ፡፡‹‹የእኔ ፍቅር በአሁኗ ሰዓት እዚህ በታደመው ህዝብ ፊት ላንቺ የምናገረው አንድ ነገር አለኝ››አለ፡፡የሆቴሉ   አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ፀጥ አለ..ለወሬ የቋመጡ ጆሮዎች ከየአቅጣጫው   ተቀሰሩ፡፡እሷ ደስ የማይል ነገር ውስጧ ተፈጠረ‹‹እባክህ አታድርገው…እኔ አንተን መቼም ማግባት አልፈልገም››አለች በልቧ፡፡

‹‹ማይኩን እንደያዘ ወደእሷ ቀረበና ከፊት ለፊቷ  ተንበረከከ፡፡ልክ  በሆሊውድ ፊልም ላይ ሲደረግ እንዳየው እሷ ከምትሰጠው ገንዘብ ቆጥቦ የገዛውን የጋብቻ ቀለበት ከኪሱ ውስጥ አወጣና፡--------

‹‹የእኔ ፍቅር ሚስቴ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ.. ታገቢኛለሽ?››

ሲል በጥርጣሬም በፍራቻም ጠየቃት፡፡በእሷ ላይ ምንም አይነት የስሜት ለውጥ አልታየም፡፡ አልበረገገችም፤ አልተፍለቀለቀችም፡፡ አልተኮሳተረችም፡፡ብቻ በፊት  በነበረችበት ሁኔታ ፀጥ ብላ ተቀመጠች፡፡ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ስለገባት ነው ደንዝዛ የነበረው…ገፍትራው ቤቱን ጥላ ትውጣ…ወይስ ጣቷን ቀስራ እንዲያጠልቅላት ትፍቀድለትና ስለቀጣዩ ጉዳይ ቀስ ብላ ታስብበት.ይሄንን ነገር  የመሞከር ዕቅድ እንዳለው ታውቃለች.ግን እንዲህ በፈጠነ ቀን ለማድረግ ይሞክራል ብላ ፈፅሞ ግምቱ አልነበራትም..ያ ነው በጣም እንድትደነግጥ ያደረጋት፣ይሄንን በማሰላሰል ከእራሷ ጋር ሙግት ገጥማ ባለችበት ጊዜ
ፋሲል አሻግሮ የኤልሳን ፊት መለዋወጥና የአይኗን ማጉረጥረጥ በጎሪጥ ከሩቁ አያትና ,ጀርባውን ሰጣትና አጠገቡ ወዳለችው ሳባ ዞሮ ስሯ በመንበርከክ

‹‹የእኔ ፍቅር ታገቢኛለሽ …?መልስሽን  በጉጉት  እየጠበቅኩ  ነው?››በማለት ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄውን አቀረበላት ፡፡እምቢ ብትለው የጓደኞቹ  እና  የኤልሳ መሳቂያ ሆኖ እንደሚከርም ሲታሰበው ውስጡ ቀዘቀዘበት፡፡
በተቃራኒው ሳባ የጠረጠረችው  ነገር  በመሆኑ  እንደመተከዝ  አለች..አሁን ጥያቄውን መቀበል አለባት.. በምንም አይነት እነዚህ ሁሉ ሰዎች መካከል እምቢ ብላው አጉል ትኩረት መሳብ አልፈለገችም፡፡በምንም አይነት ሁኔታ ግን ግንኙነታቸው ከሳምንት በላይ እድሜ እንደማይኖረው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ሆነች፡፡ሀለቃዋ ስለእዚህ ፍቅረኛዋ ከሰማችበት ቀን አንስቶ ይቅርብሽ እያለች

ስታስጠነቅቃት ነበር፡፡የልጁ ፍላጎት የወሲብ ስሜቷ ላይ ብቻ ተገድቦ እዛ ላይ እንዳማይገታ ደጋግማ ነግራታለች፡፡
፡፡ እሷ ስትፈራው የነበረው ነገር በመድረሱ አዘነች፡፡ እያዘነችም ጣቷን ዘረጋችለት….መተወን ጀመረች‹‹አዎ የእኔ ውድ አንተን ከማግባት በላይ በህይወቴ ተመኝቼ የማውቀው ሌላ ፍላጎት አላስታውስም ››አለችው፡፡ ቤቱ በጭብጨባ ና በፉጨት ተናጋ፡፡ካሜራ ሆነ ሞባይል በመጠቀም ብዙዎች ምስላቸውን በፎቶ ለማስቀረት ተረባረቡ፡፡በዚህ መካከል ኤልሳ በግራና በቀኝ እጇ ሁለት የቢራ ጠርሙሶች ይዛ ተጠጋቻቸው፡፡አመጣጧ በሳባ እይታ ትክክል ስለነበረ ፊት ለፊት እያየቻት ነው፡፡ቀረበቻቸው ባለ በሌለ ኃይሏ ሁለቱንም ጠርምሶች በአንድ ጊዜ ሁለቱም ተጣማሪዎች ግንባር ላይ  ለማሷረፍ  ሰነዘረች፡፡  ሳባ  ዝግጁ  ሆና ስጠብቃት ስለነበረ ቅጽበታዊ በሆነ ፍጥነት ከራሷ ግንባር ላይ ስትመክት ለፋሲል የተሰነዘረው ግን ግንባሩ ላይ ተፈረካከሰ..ሳባ ሁለቱንም ጠርሙሶች መክታ ማስቀረት ትችል ነበር ግን አላደረገችውም፡፡ እንደውም ያላሰበችው መልካም አጋጣሚ ስለተከሰተላት ውስጧ ተፍነክንኳል፡፡ይህ አጋጣሚ እንደሎተሪ እድል ያልታሰበና አቅልን በደስታ የሚያስት ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡እና እድሏን እስከመጨረሻው ልትጠቀምበት ወሰነችና ትኩረቷን ሰበሰበች፡፡
ከደቂቃዎች በፊት ደስታ ውጦት የነበረው ሆቴል በጩኸት እና በድንጋጤ ተተረማመሰ፡፡ወዲያው የአካባቢው ፖሊሶች ተደውሎላቸው ደረሱ፡፡ኤልሳን ወደ እስር ቤት ፋሲልን ወደ ሆስፒታል ወሰዱት፡፡ሳባም ቃሏን ለፖሊስ ሰጥታ የከፋውና የጨለመ በሚመስል ፊት ግን ከውስጥ በሚፍለቀለቅ  የደስታ  ስሜት ወደ ሆስፒታል ሄደች፡፡

ፋሲል በቢራ ጠርሙሱ አምስት ቦታ የተበታተነው ጭንቅላቱ በጥንቃቄ ተሰፍቶ ከተጠጋገነ በኃላ እዛው እንዲተኛ ተደረገ..ሀኪሙ እንኳን ወደቤት ገብቶ እየተመላለሰ ሊታከም ይችላል ብሎ ነበር ፤ሳባ  ግን  እንዲያ  እንዲሆን አልፈለገችም፡፡
የወደፊት ባሏ ሙሉ ጤናው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲመለስ እንደምትፈልግ በመናገር ቢያንስ ለሶስት ቀንም ቢሆን እዛው ሆስፒታል ተኝቶ ሀኪሞች የቅርብ ክትትል እንዲያደርጉለት አጥብቃ በመከራከር አሳመነቻቸው፡፡

አስፈላጊውን ክፍያ ከፍላ ወደ ቤቷ ስትመለስ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡
ሰባት ሰዓት ላይ ስልኳን አነሳችና ወደአንድ የቅርቧ ወደሆነና ቆሻሻ ስራዎችን ወደሚሰራላት ሰው ደወለች፡፡ችግሩ እንደተፈጠረ  ወደሆስፒታል  በምትመጣበት ጊዜ መንገድ ላይ አግኝታው ስለሁኔታው አብራርታለት ነበር፡፡

‹‹ሄሎ››

‹‹የነገርኩህ ሆስፒታል የመኝታ ቁጥር 13 ተኝቷል››

‹‹አዎ… ፋሲል ፀጋዬ ይባላል››

‹‹ሦስት ቀን አለህ..ነገ ብትፈፅመው ግን  ደስ ይለኛል›››

‹‹አዎ… ከተኛበት እንዲነሳና ዳግመኛ ወደቤቴ መጥቶ ፊቴን እንዲያየኝ አልፈልግም፡፡››
‹‹ሁሉ ነገር በሚስጥር እና በጥንቃቄ ይከወን››

‹‹ቻው››ስልኳን ዘጋች  እና  ተረጋጋታ  እንቅልፏን  ተኛች፡፡በሦስተኛው   ቀን ወንድሙ ፋሲል ማረፉን ደውሎ አረዳት፡፡

ኤልሳ ፍቅረኛዋ የነበረውን ፋሲል ፀጋዬን አስባና አቅዳ በመግደሏ በተጨማሪም የሟች እጮኛው ላይም የመግደል ሙከራ በማድረጓ በሁለት ወንጀል ተከሳ

ከወህኒ ቤት ፍርድ ቤት ስትመላለስ ከቆየች በኃላ በስተመጨረሻ በቀረበባት ክስ ሁሉ ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ የ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባት በቋሚነት ወደ ወህኒ ተወረወረች፡፡አይ!! ምስኪኗ ግልፍተኛዋ አፍቃሪ፡፡

ከዛ በኃላ ሳባ ደስታ የሚሰማት አና ስጋቷ ሁሉ ተወግዶ ሰላም የምታገኝ መስሏት ነበር…፡፡ከገባችበት አጉል ግንኙነት በሰላም የተገላገለችና ቀጣይ ህይወቷን ለማስተካከል እረፍት የምታገኝ መስሏት ነበር ግን ተሳስታ  ነበር.ፈፅሞ የፋሲል ምስል ከምናቧ ሊደበዝዝ አልቻለም፡ቀን ስትቆም ስትነሳ በየምክንያቱ ትዝ ከሚላት በተጨማሪ ልትተኛ ብላ አይኗን ስትጨፍን በህልሟ እየመጣ ያሰቃያት ጀመረ..ስራዋን ተረጋግታመስራት አልቻለችም.፡፡መጀመሪያውኑ ስልችት ብሏት የነበረውን ስራዋን ይበልጥ አንገሸገሻት..ያ ጳውሎስ የተባለው ደራሲ በፍጥነት ስራውን ጨርሶ መፅሀፉን አሳትማ ሁሉን ነገር ድብልቅለልቅ አድርጋ ራሷን ነፃ እስክታወጣ ድረስ ቸኮለች፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


..ከአንዱ ለምኖ ለአንዱ በመስጠት ብልጽግናን ማምጣት አይቻለም::

ለታዲዬስ ፣ትንግርት፣ሁሴን፣ዶ/ር ሶፊያ፣ፎዚያ እና ኤልያስ ዛሬ ልዩ ቀን ነች፡፡ለስድስት ወር የለፉበትን ...እንቅልፍ አጥተው ገንዘባቸውንም ዕውቀታቸውንም ያፈሰሱበት የድርጅታቸው የመጀመሪያ ፍሬ እነሱም የሚያዩበት ለማህበረሰቡም የሚያስተዋውቁበት ቀን ነው፡፡

ዝግጅቱ በሸራተን አዲስ የሚካሄድ ሲሆን የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ዲኤታ፣የተለያዩ ሀይማኖት አባቶች፣የኤንባሲ ሰዎች፣ታዋቂ ሙዚቀኞች፣የፊልም አክተሮች፣አትሌቶች፣ነጋዴዎች፣
ለዚህ ድርጅት ከምስረታው እሰከአሁን ከፍተኛ እገዛ ካደረጉት ከየተለያዩ የፌስ ቡክ ግሩፖች የተወከሉ ወጣቶች፣ከተለያዩ ሚዲያዎች የተሰበሰቡ ጋዜጠኞች እና ካሜራ ማኖች..አዳራሹን
ሞልተውታል፡፡

የዛሬው ዝግጅት ዓለማ በዋናነት ሁለት ሲሆን ሌላም አንድ ንዑስ ዝግጅት አለ፡፡መድረኩን የሚመራው ጋዜጠኛ ሁሴን ነው..ማይኩን ይዞ ወደ መድረክ ወጣና ጉሮሮውን ሞርዶ ንግግሩን
ጀመረ::

‹‹ክቡራን እና ክብሯት ጥሪያችንን ተቀብላችሁ እዚህ የተገኛችሁ ሁላችሁም እንዲሁም በየቤታችሁ ሆናችሁ ዝግጅቱን በቀጥታ በቴሌቨዥን ስርጭት እየተከታተላችሁ ያላችሁ በአጠቃላይ በድርጅታችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን እስከፍፃሜውም በፅሞና እንድትከታተሉን እየጠየቅን በቀጥታ ወደ ዝግጅቱ እንገባለን፡፡በቅድሚያ የድርጅታችን መሪ የሆኑት ዶ/ር ሶፍያ ፕሮግራሙን በንግግር እንዲከፍቱልን እንጠይቃለን… ዶ/ርን ወደ መድረክ ሸኙልን፡፡››ዶ/ር ሶፊያ በጭብጨባ ታጅባ ወደ መድረክ ወጣችና ማይኩን ከሁሴን ተቀብላ ንግግሯን ማሰማት ቀጠለች፡፡

‹‹ክቡራን እና ክቡራት የመንግስት ባለስልጣናት፣የሀይማኖት አባቶች፣ከተለያዩ የማህበራት ዘርፎችን በመወከል
የተገኛችሁ፣በየቤታችሁም በመሆን እየተከታተላችሁን ያላችሁ በአጠቃላይ..እንኳን ለዚህች ቀን አደረሰን አላለሁ፡፡

የዛሬው ፕሮግራማችን ሁለት ዓላማዎች አሉት፡፡ አንደኛው የወላጆች እና ልጆች የምረቃ በዓል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለድርጅታችን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ነው..እኔ አሁን አትኩሬ የተወሰነ ማብራሪያ ልሰጣችሁ የምፈልገው በመጀመሪያው ላይ ነው..ሁለተኛውን በተመለከተ አቶ ታዲዬስ ቆየት ብሎ ያብራራላችኋል፡፡

እንግዲህ እንደመነሻ ይሆነን ዘንድ የዛሬ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን አካባቢ በበጎ ፍቃደኝነት አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናትን እናሳድጋለን ብለው ከተመዘገቡ በብዙ ሺዋች ከሚቆጠሩ ባለቀና ልቦች መካከል ለጊዜው አቅማችንን መሰረት አድርገን 15ዐ ግለሰቦችንና በቡድን ከመጡት መካከል ደግሞ 5ዐ ዎቹን ወደ ስልጠና አስገብተን ነበር፡፡እንግዲህ በአንድ ወር ስልጠና ውስጥ በድርጅቱ ህግና የስልጠና ማኑዋል የተሰጣቸውን ስልጠና በመከታተል ከ15ዐ ዎቹ ግለሰቦች መካከል 43 በቡድን ሆነው ከመጡት መካከል ደግሞ 31 መስፈርቱን ማሟላት ስላልቻሉ ከይቅርታ ጋር እንደ ፍላጎታቸው ህፃናትን እንዲያሳድጉ ልንፈቅድላቸው አልቻልንም፡፡የተቀሩት እንግዲህ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው እንሆ ዛሬ በእናንተ ፊት መርቀን ልጆቻቸውን በአደራ እናስረክባቸዋለን፡፡››

የደመቀ ጭብጨባ ከአዳራሹ...ቀጠለች ዶ/ር ‹‹ዛሬ አሁን ለነገርኳችሁ ወላጆች የምናስረክባቸውን ልጆችም ለ3 ወር በካምፕ በማስገባት ስልጠና ሰጥተናቸዋል፡፡ልዩነቱ ህፃናቱን አንዴ ወደ ማሰልጠኛ ካስገባናቸው:: የምንፈልገውን ብቃት እስክናገኝባቸው ድረስ የፈጀውን ያህል ይፍጅ እንለፋባቸዋለን፡፡ ልጆቹን ከበሸቀጠ የድህነት መንደር እንዲሁም በስነ- ምግባር እና በሞራል ከዘቀጠ ጎዳና ላይ ነው የምንሰበስባቸው፤አመላቸውን ማረቅ፣ ስነ- ልቦናቸውን መገንባት፣ጤንነታቸውን ማስተካከል፣ ተስጥኦቸውን ለይቶ ማወቅ፤ወዘተ እንደሀሳባችን እስክናሳካ 3 ወር ፈጀብንም ሶስት
አመት ተስፋ አንቆርጥባቸውም፡፡ የራሱ ጉዳይም ብለንም እርግጠኛ ባልሆንበት ሁኔታ ለአሳዳጊ ወላጅ አሳልፈን አንሰጣቸውም፡፡ይህ ነው ልዩ የሚያደርገን.. እንጂማ መአት በህፃናት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች እንዳሉ እናውቃለን...፡፡.››

ወላጅ ለመሆን ስልጠናውን ወስደው መስፈርቱን አላሟላችሁም ብለን ከመለስናቸው ውስጥ የተወሰኑት በጣም ተበሳጭተውብን ነበር፤ላሳድግ ባልኩ መልካም ልስራ ባልኩ እንዴት እከለከላለሁ?የሚል መከራከሪያ ሀሳብ
ነበራቸው፡፡ግን እኛም ያንን ስናደርግ እያዘንን ነው... እየገነባን ያለነው የወደፊቱን ትውልድ
ነው፡፡አንድ ሰው ገንዘብና ፍላጎት ስላለው ብቻ ዝግጁ የሆነ ስነልቦና እንዲሁም የወላጅ ባህሪ
ሳይኖረው ልጅን ያህል ነገር አሳድግ ብለን አንስተን አንሰጠውም..በፍፁም እንደዛ
አናደርግም፡፡በእኛ መአከል ሰልጥነው ልጅ የተረከቡ ሰዎች በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት
ከዚህ ከእኛ ጋር ለወሰዷቸው ልጆችም ብቻ ሳይሆን ከአብራካቸው ለወጡትም
ህፃናት፣ለዘመዶቻቸው ልጆች ፣ለጎረቤቶቻቸው ልጆችም ያገኙትን ዕውቀት እንዲጠቀሙበት
እንፈልጋለን፡፡አርአያ እንዲሆኑበት እንፈልጋለን፡፡ ለዛ ነው ማኑዋሉንም አዘጋጅትን ለእያንዳንዱ ያደልነው፡፡

‹‹ልጅ ማሳደግ ማብላትና ማጠጣት ብቻ ሳይሆን..የወደፊት የህይወት ዓላማቸውን፤ ተሰጥኦዋቸውን ከስር ከመሰረቱ እያጎለበቱ መንገድ ማስያዝን ይጠይቃል፡፡ ይሄንን ነው ጠቅላላ የሀገራችን ወላጆች ሊከተሉት የሚገባው መንገድ፡፡ ህብረተሰቡም እንደህብረተሰብ...መንግስትም እንደመንግስት የየራሳቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እጠይቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ አሁን ቀጥታ ወደ ምረቃ በዓሉ እንሄዳለን፤ ክብር የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ዲኤታ ለተመራቂ ወላጅ እና ህፃናት የምስክር ወረቀት ይሰጡልን ዘንድ እንጠይቃለን፡፡››

ሚንስቴሩ በሙሉ ሱፍ ሽክ ብለው በከረባት እንደታነቁ በተጀነነ እርምጃ ወደ መድረክ ወጥተው ከዶ/ር ጎን ቆሙ ፡፡ሁሴን የተመራቂዎቹን ስም ተራ በተራ ሲጠራ ወላጆቹ ከተረከቧቸው ህጻናት ጋር በመምጣት የምስክር
ወረቃታቸውን እየወሰዱ ወደ መቀመጫቸው ይመለሳሉ፡፡ ከነዚህ ተመራቂዎች ውስጥ..ሰሎሞንና የውብዳር አንድ ወንድ ልጅ(እነሱ የጠየቁት ሁለት ቢሆንም በታዲዬስ የሚመራው ቴክኒክ ብድን ግን በዚህ በአንዱ ልጅ ላይ የሚያሳዩት አፈፃፀም ታይቶ ከአመት በኃላ ሌላ ልጅ ሊጨመርላቸው ይችላል እንጂ አሁን ባለው ሁኔታ ከአንድ ልጅ በላይ አይፈቀድላችሁም በማለት ከለከሏቸው) ሌላው..ዶር ሶፊያና ከፕ/ዬሴፍ ጋር አንድ ሴት ልጅ፣ፎዚያ እና ኤልያስ አንድ ሴት ልጅ፣ፅዮን እና ዓላዛር ..ትንግርት እና ሁሴን አንድ ልጅ በመረከብ ከራሳቸው በመጀመር አርዓያነታቸውን አሳይተዋል፡፡

የምስክር ወረቀት የመስጠት ፕሮግራም ሲጠናቀቅ የክብር እንግዳውንና ዶ/ር ሶፊያ መድረኩን ለቀው ወደ መቀመጫቸው ሄዱ.... ሁሴን ቀጣዩን ፕሮግራም ማስተዋወቅ ጀመረ…፡፡

‹‹ክብሯን እንግዶች ወደ ቀጣዩ ፕሮግራማችን ከመሸጋገራችን በፊት የሙዚቃ እረፍት

እናደርጋለን..ድምፃዊ ሀሊማ እና ሄለን ወደ መድረክ፡፡››

በአካልም በየቤቱም እየተከታተሉ ያሉ አይኖቻቸውን ወደ መድረኩ ላኩ፡፡

የተባሉት ሙዚቀኞች ወደ መድረክ ሲመጡ ታዩ …ሀሊማ ጊታሯን ይዛ ወንበር ስባ ተቀመጠችና ማይኩን ወደ አፏ አስተካክላ አመቻቸች፡፡ሄለን ወደ ፒያኖው አመራች፡፡አብዛኛው ህዝብ አስታወሳቸው፡፡ ባለፈውም በቴሌቨዥን ቃለ መጠየቅ የተደረገላቸው ጊዜ ብቃታቸውን አሳይተዋል፤በአይድል ውድድርም እንደዛው…፡፡ ጀመሩ ሄለን ፒያኖውን ስታናግረው ሀሊማ ጊታሯን እየተጫወተች በድምጿም ታንቆረቁር ጀመር..
የብዙነሽ በቀለን <<የእናት ውለታዋን›› ነው የዘፈነችው...ሙዚቃው ሲጠናቀቅ በአዳራሹ የሞላው ህዝብ በጭብጨባና በፉጨት ሸኛቸው፡፡

ሁሴን ሁለተኛው ዝግጅት እንዲቀጥል ወደ ታዲዬስ አስተላለፈ፡፡

ታዲዩስ መድረኩን ተረከበ‹‹እኔ ስለ ሁለተኛው ዝግጅት ጥቂት ነገር ለማለት ነው ..ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት…..ይሄን ለማድረግ ፈልገን ሳይሆን ተገደን ነው..ከአንዱ ለምኖ ለአንዱ በመስጠት ብልጽግናን ማምጣት አይቻለም፡፡ እቅዳችን ድርጅታችን እራሱን በራሱ እያስተዳደረ ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ነው፡፡ለዚህም ይረዳን ዘንድ መንግስትን ከከተማ በራቀ ቦታ 10-20 ሺ ካሬ ሜትር መሬት እንዲሰጠን ፕሮፖዛለችንን አስገብተናል.. እስከ አሁን አሉታዊም ሆነ አውንታዊ መልስ አልተሰጠንም፡፡

ከተሳካልን ግን በዛ መሬት መንደራችንን እንመሰርታለን፤እርሻ እናርስበታለን፤የተለያ የእንጨት ስራ ፣የብረት ስራ ፣የቅርፀ ቅርፅ ስራ፣የጥበብ ስራ፣የፈጠራ ስራ እንሰራበታለን፡፡ የተለያ የስልጠና ማዕከሎችን እንገነባበታለን..በዛን ጊዜ እኛ የምንፈልገው እኛን ለመርዳት የፈለገ አንድ ግንበኛ በአንድ አመት ውስጥ ለ4 ቀንም ቢሆን መንደራችን ድረስ መጥቶ የሚገነባ ነገር በመገንባት በዕውቀቱን እንዲያገለግለን ...የህክምና
ዶክተሩም የሚታከም ነገር ካለ መጥቶ በማከም እንዲያግዘን…ሰዓሊውም በዓመት ለ3 ቀንም ቢሆን ወደ መንደራችን መጥቶ ቢያንስ የስዕል ችሎታ ኖሯቸው ለሚፍጨረጨሩ ህፃናት ትንሽ ዕውቀት አስጨብጠጧቸው ከልምዱ አካፍሏቸው ለእራሱም የመንፈስ እርካታ አግኝቶ እንዲመለሰ ነው የምንፈልገው፤ እዚህ አገር ባለን ችሎታና እውቀት በነጻ በጎ ነገር የምናደርግበት ሁኔታዎች ናቸው መመቻቸት ያለባቸው...እሱ ነው ሰጪውንም ተቀባዩንም የሚጠቅመው.. ሽርፍራፊ ገንዘብ ለተቸገረው መስጠቱን ሁለችንም ካንጀትም ሆነ ከአንገት እናደርገዋለን… ለውጥ ግን አላመጣልንም..፡፡ እኛ መንግስትንም ሆነ ህዝቡን የምናስቸግረዉ ይሄንን ህልማችን የሆነውን የሰላምና የብልፅግና መንደራችንን እስክንገነባ ድረስ እንዲያግዘን ብቻ ነው...ከዛ በኃላ እንዳልኳችሁ ነው…፡፡

መንግስትም የጠየቅነውን መሬት በአፋጣኝ ይሰጠን ዘንድ በዚህ አጋጣሚም ደግሜ ጠይቃለሁ፡፡ትላልቅ አለም አቀፍ ስብሰባ በሚካሄድበት ጊዜና አንድ የትልቅ የሀገር መሪ በሚመጣበት ወቅት በድህነት በጎዳና የሚርመሰመሱትን ህፃናት ከከተማው ዞር
ለማድረግ ከመጨነቅና ከመሳቀቅ ይልቅ አሁን እኛን በማገዝ መሰረታዊ በሆነ መንገድ ዘላቂ መፍትሄ ብናበጅበት ለመንግስትም ለማህበረሰቡም ይጠቅመዋል እላለሁ፡፡

ስለዚህ ሁላቹሁም በግለሰብ ደረጃም ቢሆን

በድርጅት ደረጃ ታግዙናላችሁ ብለን ስላሰብን ነው ፊታችሁ በእምነት የቀረብነው፡፡አላማችንን
ቀለል አድርጋችሁ እንዳታዩት፡፡ ወላጅ የሌላቸውን ህፃናት አሳዳጊ ወላጅ እንዲያገኙ ብቻ አይደለም ውጥናችን…የይስሙላ ወላጆች
ሁሉ ከአብራካቸው ለተፈለፈሉ የገዛ ልጇቻቸው እውነተኛ ወላጅ እንዲሆኑ ማብቃት ነው፡፡
በምንመሰርተው መንደር ውስጥ በምናቋቁመው ማሰልጠኛ ማዕከል በመንግስት ስርዓተ ትምህርት መካተት ሲገባቸው ያልተካተቱትን ግን ደግሞ ለህብረተሰቡ አስፈላጊ የሆኑትን ስልጠናዎችም እንዲሰጡ ማድረግ ነው ዓላማችን፡፡

ልጆች እንደተወለዱ ከህፃንነታቸው ጀምሮ ሚበሉትንና ሚጠጡትን ብሎም ሚለብሱትን ነገር ብቻ ሳይሆን ስለሚያስቡት፣ ስለሚፈልጉት እና ስለሚጠሉት ነገር እየተከታተልን ማገዝ
መቻል አለብን፤ወጣቶቻችን እኛ የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን እነሱ የሚፈልጉትን ትምህርትም
እንዲማሩ እገዛ በማድረግ ኃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል...ለአቅመ አዳም እና ሄዋን የደረሱ ጥንዶች ወደ ጋብቻ ከመግባታቸው
በፊት የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው ስልጠና
የሚያገኙበት ዕድል መፍጠር አለብን፤በፍቅር ህይወት እና በጋብቻ ህይወት መካከል ስላለው
ልዩነት ግንዛቤ እንዲጨብጡ፣ ስለልጆች አስተዳደግ፣ስለቤት አስተዳደር እንዲያውቁ ቀድሞ ስልጠና መሰጠት አለበት ፤ የእኛ ተቋም በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ሽንቁሮች
ሁሉ ለመድፈን የሚጥር ይሆናል….ዋና አላማችን ግን ህፃናቶቹ ናቸው፡፡ስለጋብቻ
የምናሰለጥነው፣ስለቤተሰብ
ምንሰብከው፣ስለልጆች አስተዳድግ የምንደሰኩረው፤ወደ ጎዳና ወጥቶም ሆነ የስም
ወላጆቹ ጋር እየኖረ የህይወት ውሉ የጠፋበት ብኩን ትውልድ ሆኖ የሚያድግ ልጅ እንዳይኖር
ነው፡፡
የቁሳቁስ ዕድገቱንና የቴክኖሎጂ ምጥቀቱን መንግስት እንደ መንግስት ለራሱ ህልውና ሲል ይሰራልናል...እኛ ግን ችላ የተባለውን ግን በህይወት ውስጥ ወሳኝ ስለሆነው መንፈሳዊ ግንባታ ላይ እንደዜጋ መስራት አለብን፡፡ ስለእውነት፣ስለፍቅር፣ስለበጎነት፣ስለሰባአዊነት፣የሚያስተምሩ ተቋሞች መገንባት ያስፈልገናል፡፡ የዛን ጊዜ ነው አንዳችን ለአንዳችን
መኖር የምንጀምረው፡፡

ስግብግብነትን፣ጭካኔ፣ሙስናን እና አድራባይነትን ከውስጣችን አውጥተን በቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም የበለፀገ ደስተኛ ህብረተሰብ መገንባት የምንችለው፡፡ ስለዚህ አብረን እንጣር፡፡ አግዙንና ሀሳባችንን ከግብ እናድርስ እላለሁ፡፡ጊዜችሁንና ቀልባችሁን ሰጥታችሁኝ ስላዳመጣችሁን አመሰግናለሁ፡፡››

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለሀለቃዋ ትብለጥ ፍቅረኛዋ መሞቱ ድብርት ውስጥ እንደከታት  ተናግራ  የአንድ  ወር ፍቃድ ወሰደች፡፡እረፍቷን ጨርሳ ተመልሳ ከመግባቷ በፊት መጽሀፉም አልቆ እስከወዲያኛው ይገላግላት ይሆናል፡፡አዎ ተስፋዋ ያ ነው፡፡
ሳባ እረፍት ከወሰደች በኋላ ቤት መዋል ጀመረች፡፡ራሷን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስም ኃይለኛ መደበትና ጭንቀት ውስጥ ገባች፡፡እርግጥ ይሄ
የመደበት ችግር አሁን ፍቅረኛዋ ስለሞተ ወይም እሷ ራሷ ስላስገደለችው ድንገት የተከሰተባት በሽታ አይደለም…ከእሷ ጋር ሶስት አራት አመት በደባልነት ኖሯል…ቢያንስ በስድስት ወር አንዴ የሆነ ምክንያት  ፈልጎ ይቀሰቀስባታል፡፡
ይተወኛል ብላ ለ15 ቀን ከቤቷ ሳትወጣ እረፍት ለማድረግ ብትሞክርም ነገሮች ግን እየባሱባት መጡ..በዚህም ምክንያት የስነ-ልቦና ባለሞያ እንድታናግር አንድ  ወዳጇ  ጨቀጨቃትና  በሀሳቡ  ተሰማምታ  የጠቆማት ሆስፒታል ሄደች፡፡
በተቻላት መጠን ጥሩ አለባበስ ለብሳ ፤ከወትሮዋ በተሻለ ነቃ ለማለት፤ የተቻላትን ጥረት አድርጋ በጠዋት ተነስታ መኪናዋን አስነስታ በተሰጣት አድራሻ ሄደች፡፡ቀድማ ደውላ ቀጠሮ አስይዛ ስለነበረ.እንደሄደች ነበር ነርሷ የተወሰኑ ፎርሞችን እንድትሞላ በማድረግ ወደ ዶክተሩ እንድትገባ ያደረገቻት፡፡

ብዙ ጊዜ ለህክምና ወደተለያዩ የከተማዋ ስመጥር ሆስፒታሎች ሄዳ አገልግሎት አግኝታ ታውቃለች…አሁንም የገባችበት የዶክተሩ ምርመራ ክፍል ከዚህ በፊት ከምታውቃቸውና ከጎበኘቻቸው ብዙም የተለየ አይደለም…ግን በራፉን ከፍታ ወደውስጥ እንደገባች ፈዛለች፡፡ለውስጧ ጥልቅ ድረስ እስኪሰማት   ድረስ ደንዝዛለች፡፡

‹‹ጤና ይስጥልኝ አረፍ በይ›› ሲላት ሁሉ አልሰማችውም.አይኗን አይኖቹ ላይ ተክላ በቆመችበት ቅዝዝ ብላ እየተመለከተችው ነው፡፡

እጁ ላይ ያለውን የእሷን ካርድ እየተመለከተ ‹‹ወይዘሪት ሳባ….አረፍ በይ››ሲላት እንደምንም ከመደንዘዝ ለመንቃት እየሞከረች እግሯን የመጎተት ያህል አንቀሳቀሰችና እንድትቀመጥ በተነገራት ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹እሺ ሳባ ዶ/ር ጀማል እባላለሁ.››ሲል ራሱን አስተዋወቃት፡፡

ዝም አለችው

‹‹እስኪ ስለራስሽ ጥቂት ንገሪኝ›› አላት፡፡

‹‹ግራ ገባት..ሀኪም ቤት ለስነ-ልቦና ህክምና የመጣች ሳይሆን የሆነ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላ የሆነ አማላይ ወንድ  ወንበሯን ተጋርቶ ሊጀነጅናት ሙከራ እያደረገ እሷ ደግሞ እየተግደረደረችና እየተሸኮረመመች ያለች ነው የመሰላት፡፡

‹‹ስለእኔ ምን?››

‹‹ስለ ማንኛውም ነገር….ሳባ ማን ነች?ምንድነው የምትወደው? ምንድነው የምትሰራው? ፡፡››

‹‹ስራዬ የሆነ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ ነው ምሰራው…ተቀጥሬ   እንኳን ማለት ይከብዳል…በኮሚሽን ነው የምሰራው፡፡የምኖረው ብቻዬን   ነው…ማለት አንድ ዘበኛ እና ተመላላሽ የቤት ሰራተኛ አለኝ... ጥሩ ኑሮ እኖራለው፡፡ግን ደግሞ ብቸኛ እና ደስታ የራቀኝ ሰው ነኝ..ሁሉ ነገር እየሰለቸኝ ነው…ለምን እንደምኖር እራሱ ግራ እየጋባኝ ነው፡፡››ሁሉን ነገር ተወችና ቀጥታ ወደ መደምደሚያው በመሻገር አሁን ሰላለችበት ሁኔታ ወደማብራራቱ ተስፈነጠረች፡፡

‹‹ጥሩ…. እንዲህ አይነት ስሜት ይሰማሽ የጀመረው ከመቼ ጀምሮ ነው?››

‹‹ሶስት አራት አመት..ግን የከፋ የሆነው ከሀያ ቀን በፊት ጀምሮ ነው፡፡፡››

‹‹በቅርብ በህይወትሽ የተከሰተ ጠንከር ያለ ነገር ነበር?››

‹‹አዎ ለአንድ አመት ፍቅረኛዬ የነበረ  ሰው  ቀለበት  እያሰረልኝ  ሳለ  እኔ የማላውቃት ልጅ ፍቅረኛው ሆና በጠርሙስ ጭንቅላቱን ከፈለችውና ሞተ…ከዛ ወዲህ ይመስለኛል ነገሮች እየባሱ የሄዱት፡፡››የታሪኩን ግማሽ እውነት ነገረችው፡፡

‹‹ገባኝ….ግን የትኛው ነው በጣም ያመመሽ…?››ሲል ጠየቃት

‹‹ከምንና ከምኑ?››

‹‹ከፍቅረኛሽ ሞትና….ከመከዳትሽ?››
ደነገጠች…እንዲህ ፈፅሞ አስባ አታውቅም..‹‹መከዳት…ስለፍቅረኛው ማለትህ ነው?››

‹‹አዎ››

ዝም አለች..ምን እንደምትመልስ ግራ ገባት፡፡ሳባ ልክ እንደጓደኛሽ ቁጠሪኝ ….ነፃ ሁኚ፡፡

‹‹አይ ፋሲልን .ማለቴ ፍቅረኛዬን በተመለከተ የሚሰማኝ ስሜት ግራ የተጋባ ነው…ሞቱ ይሄን ያህል ይረብሸኛል ብዬ ፈፅሞ አስቤ አላውቅም  ነበር….የእኔና የእሱ ግንኙነት በተወሰኑ የጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ ነበር…ፍቅረኛውን በተመለከተ ምንም የሚሰማኝ ነገር የለም..በእርግጥ እስከመጨረሻው ቀን ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም..ባውቅም በእኔ ላይ ማግጦብኛል ብዬ የምበሳጭበት ምክንያት አይታየኝም...እኔም ታምኜለት አላውቅም እሱም ይታመንልኛል የሚል እምነት አልነበረኝም..እውነቱን ለመናገር እንዲታመንልኝም ፍላጎቱ አልነበረኝም.. በአጠቃላይ ስለፍቅረኛው ማወቄ ምንም ትርጉም የሰጠኝ አይመስለኝም፡፡››

‹‹ምን አልባት ትዳሩን ትፈልጊው ነበር…?በእሱ ሞት ምክንያት በመበላሸቱ ተበሳጭተሻል?››

‹‹በተአምር እንደዛ አይነት ፍላጎት አልነበረኝም...ቀለበቱን ሲያደርግልኝ ድንገት ሳያማክረኝ ነበር ያደረገው...ማማከር ሳይሆን ስለወደፊታችን አውርተን እንኳን አናውቅም...እንዳገባው ሲጠይቀኝ በጣም ብዙ በሚያውቁት ሰዎች ፊት ስለሆነ እሱን ላለማሸማቀቅ እና ግርግር ላለመፍጠር ነበር  ጣቴን  የዘረጋሁለት..እና መቼም ላገባው እቅድ አልነበረኝም፡፡ግን የገረመኝ በመሞቱ በውስጤ ቅሬታ ተፈጥሯል …ፈፅሞ ልረሳው አልቻልኩም…ከእሱ የማጣው  አንድ  ብቸኛ  ነገር ወሲብ ነው….ያንን ደግሞ ካሰብኩበት ከሌላ ሰው በቀላሉ ማግኘት እችላለሁ…ያው የእሱን ያህል ሊሆን ባይችልም ማለቴ ነው..እና ለምን ከአዕምሮዬ ላወጣው እንዳልቻልኩ አልገባኝም፡››

‹‹ግን እሱ ብቻ ነው የሚያስጨንቅሽ? ማለቴ እሱ በህይወት እያለስ ሌላ ምቾት የሚነሳሽ ጉዳይ ነበር?››

‹‹እየተጠነቀቀች እራሷን ከመጠን በላይ ላለማጋለጥ እየጣረች ከሁለት ሰዓት በላይ ከዶ/ሩ ጋር አወራች….በጊዜያዊነት የሚያረጋጓትን ሁለት መድሀኒቶችን መውሰድ ከሚገባት የተወሰነ ምክር ጋር ለግሷት ለሳምንት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷት አሰናበታት….

በመምጣቷ ተደስታለች …በዶ/ሩ መስተንግዶ ተደስታለች..ልቧ ለምን እንደደነገጠባት አልገባትም…ያምራል…ከአይኖቹ የሚረጫቸው ብርሀን የሰውን ልብ በቀላሉ ይሰረስራሉ፡፡ንግግሩ እርጋታ የተለባሰና እንዲያወሩ የሚያበረታታ ነው፡፡ በዛ የተነሳ በቆይታዋ ተደስታለችም…የተወሰነ ቀለል የማለት ስሜትም እየተሰማት ነው..ትንሽ ቅር ያላት ቀጠሮ ከሳምንት በኋላ መሆኑ ነው፡፡ ከሁለት ወይም ከሶስት ቀን በኋላ መልሳ ብታገኘው ደስ ይላት ነበር.ደግነቱ ችግር ካለና የተለየ ስሜት ከተሰማት እንድትደውልለት ነግሯት ቁጥሩን ሰጥቷታል፡፡መኪናዋን ራሷ እያሽረከረች ቀጥታ ወደቤቷ ሄደች..አዲሱ ዘበኛዋ በራፉን ከፈተና ወደ ውስጥ አስገባት..፡፡ይሄንን ዘበኛ ከቀጠረች አስር ቀን ቢሆነው ነው፡፡የመጀመሪያውን ዘበኛ ያሰናበተችው የመጀመሪየውን ዘበኛ ከእሷ ጋር አስተዋውቋት ያስቀጠረው ፋሲል ስለነበረ ነው፡፡ከእሱ ጋር የሚያገናኛት ምንም አይነት ትዝታ አትፈልግም፡፡ደግሞ ምን አይነት ሚስጥራዊ ግንኙነት እንዳላቸው ስለማታውቅና በዛም ጥርጣሬ ስለነበራት ያልሰራበትን የሶስት ወር ደሞዙን ሰጥታ አሰናበተችው፡፡

ከዛም እንደተለመደው መኝታ ቤቷ ገባችና ራሷን ሸሸገች..


💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ለሀለቃዋ ትብለጥ ፍቅረኛዋ መሞቱ ድብርት ውስጥ እንደከታት  ተናግራ  የአንድ  ወር ፍቃድ ወሰደች፡፡እረፍቷን ጨርሳ ተመልሳ ከመግባቷ በፊት መጽሀፉም አልቆ እስከወዲያኛው ይገላግላት ይሆናል፡፡አዎ ተስፋዋ ያ ነው፡፡ ሳባ እረፍት ከወሰደች በኋላ ቤት መዋል ጀመረች፡፡ራሷን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስም ኃይለኛ መደበትና ጭንቀት ውስጥ…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ

እንደምንም ራሷን ተቆጣጥራ ያዘዛትን መድሀኒት በስርዓቱ ተጠቅማ በቀጠራት ቀን ከሳምንት በኋላ በሰዓቱ ሄደች።እንደደረሰች  በሞቀ  ፈገግታና  ጠበቅ  ባለ ሠላምታ  ተቀበላትና።

"ቁርስ በልተሻል?›› ሲል ጠየቃት፤ግራገባት፡፡ አሰበች   ቁርስ   አልበላችም
..ጭርሱኑም ትዝ አላላት።ሳትመልስለት  የለበሰውን  ነጭ  ጋዎን  አውልቆ መስቀያው ላይ እያንጠለጠለ

"ጥሩ እኔም አልበላሁም...ወጣ ብለን እንብላ"አላትና ወደ መውጫው መራመድ ሲጀምር ቀድማው ከክፍሉ ወጣች፡፡ቆለፈውና ጎን ለጎን እየተራመዱ መኪናውን ወዳቆመበት ቦታ እየመራ ወሰዳት ፡፡ጋቢናውን ከፈተና ካስገባት  በኋላ  እሱ  ዞሮ ገባና አንቀሳቀሰው… ሆስፒታሉን ለቀው ወጡና አስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ የመናፈሻ ድባብ ያለው አሪፍ ሆቴል ይዟት ገባ።ቁርስ እዛው በሉ…ማኪያቶ እየጠጡ ወሬ ጀመሩ።

"ሳምንቱ ጥሩ አለፈ አይደል?"

  "ምንም አይል?"

"እንዴት ምንም አይል... አመመሽ እንዴ ...ደውይልኝ ብዬሽ ነበር?››
"አይ ያን ያህል አላመመኝም..ግን ያው ወጣ ገባ ነበር"
"ያው እንዲህ አይነት ህመም በፍጥነት የሚወገድ አይደለም..  የረጅም  ጊዜ ክትትልና ትዕግስት ይጠይቃል።በተለይ ያንቺ ጥረት ወሳኝነት አለው፡፡

  ምክንያቱም ከበሽታው እንድታገግሚ ለማድረግ የሚያግዙሽ ነገሮች ምን ምን እደሆኑ በዝርዝር ብታውቂያቸውም በሽታው ግን በራሱ ከአንቺ በተቃርኖ ስለሚቆም ተግባራዊ ማድረጉ ፈተና ነው››

‹‹አልገባኝም››

‹‹በቀላሉ ላስረዳሽ… ለምሳሌ ጨጓራ በሽታ ያለበት ሰውን መድሀኒት ትሰጪውና ከዚህና ከዚያ አይነት ምግቦች ተጠበቅ ብለሽ ምክር ብትሰጪው  ትዛዙን ለመተግበር የምግብ አምሮቱን መገደብ ብቻ ነው የሚጠበቅበት፤ ስለዚህ በቀላሉ ይከውነዋል፡፡ እንደአንቺ አይነት ችግር ያለበት  ሰው  ግን  ለምሳሌ  ጠዋት እንደተነሳሸ አልጋሽን አንጥፊ ብትባይ እሺ አነጥፋለሁ ልትይኝ ትችያለሽ፡፡ግን በተጫጫነሽ ቀን እንኳን ተነስቶ አልጋ ማንጠፍ ይቅርና ..አንሶላውንም ከፊትሽ ላይ ማንሳት ላትችይ ትችያለሽ. .ምክንያቱም ነገሮችን እንድትከውኚ የሚያዘው አእምሮሽ ነው…ችግር የተፈጠረው ዋና  ማዘዣ  ጣቢያው  ላይ  በመሆኑ  ነገሮች ሁሉ ቀላል አይሆኑም ፡፡እርግጥ በጣም ጥሩ ነገር አሁን ባለው ሁኔታ አንቺ አስቸጋሪው ደረጃ ላይ አልደረስሽም…እንደምንም ተረባርበን ወደኋላ መመለስና ሁሉን ነገር ማስተካከል አለብን፣አሁን ካለሽበት አንድ ስቴፕ ወደፊት ከሄደ ግን ከባድ ነው የሚሆንብን….ለዚህ ነው ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገሽ በከፍተኛ ትእግስት ጤናሽ ላይ ብቻ ማተኮር እንዳለብሽ ከማስጠንቂያ ጋር የምነግርሽ፡፡

"እኔ ደግሞ ትዕግስት ነው የሌለኝ....በቃ ምን ለማግኘት ነው ይሄንን ሁሉ ስቃይ ታግሼ ለመኖር የምጥረው? የሚለው መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ ነው።›

‹‹ግድ የለም፤ መጀመሪያ ካለሽበት የተጨናነቀ ህይወት ራስሽን አላቂና ዘና ባለ መንፈስ ከዛ በኋላ የምትፈልጊውን ሞት ትሞቺያለሽ››

‹‹አይ ዶክተር እየቀለድክብኝ  ነው አይደል?››

‹‹አይ እየቀለድኩ አይደለም..ለመሆኑ ስራ እረፍት ላይ ነሽ አይደል?"

"አዎ  እረፍት ወስጄያለሁ ..››

‹‹...ምን ያህል?"

‹‹አንድ ወር...ግን ከዛም በኋላ የምመለስ አይመስለኝም  ።››

‹‹ሳባ ...ኑሮ አያሳስብሽም አይደል..?.ማለቴ ፋይናንሺያል?"

"ለመጪው መቶ አመት በዚህ ምድር ላይ ብንኖር  ገንዘብ የሚቸግረኝ አይመስለኝም።››

"ጥሩ አሁን ወደሆስፒታል እንመለስና በቀደም ካቆምንበት እንቀጥል፤››  አላትና ተያይዘው ወደሆስፒታል ሄዱ።ለአንድ ሰዓት ያህል ካወሩ በኋላ ተጨማሪ አንድ ኪኒን አዘዘላትና ሳምንት በተመሳሳይ ቀን እንዲገናኙ ቀጠሮ በመስጠት አሰናበታት።ስትመጣ ከነበረችበት የበለጠ ተደብራ ነበር የተመለሠችው።ይሄ ሳምንት እየጠበቁ እሱ ጋር መመላለስ ብዙም ምቾት እየሠጣት አይደለም። መኪናዋን እየነዳች ወደቤቷ እየተጓዘች ሳለ ስልኳ ጠራ ...አሁን የያዘችውን ቁጥር በጣም ጥቂት የራሴ የምትላቸው ሰዎች ናቸው የሚያውቁት።ከነዛ ውስጥ ማን እንደደወለላት ለማወቅ በመጓጓት በአንድ እጇ መሪውን እንደያዘች በሌላ እጇ  ወደኪሷ  ገባችና  ስልኩን  አወጣች  የደዋዩን  ማንነት  ስታይ   ደነገጠች

...መኪናውን ወደዳር አቆመችና አነሳችው ።

"ሄሎ ራጂ"የ12 አመትና የ5ተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ብቸኛና ተወዳጅ ታናሽ ወንድሟ ነው የደወለላት።እሱን እንኳን ደውላ ካናገረችው አንድ ወር ሊሞላት ነው።‹‹ጨርቄን ጥዬ አልሄድኩም እንጂ እኔማ በትክክል አብጄያለሁ››  ስትል በውስጧ አሰበች።ከእዛኛው ጫፍ ወንድሟ እያወራ ነው።

‹‹እህቴ. ምነው ጠፋሽብን...?ብዙ ጊዜ ስንደውል ስልክሽ አይሰራም››ቅሬታውን አሰማ፡፡

‹‹የእኔ ማር ደህና ነኝ..ትንሽ ስራ ስላጨናነቀኝ ነው..ለመሆኑ እናትህ ደህና ነች››

ከራጂ ጋር በአባት እንጂ  በእናት  አይገናኙም።ግን  የራጅ  እናት  ለሳባ  የእንጀራ እናቷ ብቻ ሳትሆን የልጅነት አብሮ አደግ ጓደኛዋ ጭምር ስለሆነች ቀረቤታቸው ዘመናት ያስቆጠረና የተለየ አይነት ነው።

‹‹እማዬማ...ደህና ነች ማለት ይከብዳል?››

ሳባ ደነገጠች"እንዴ ምን ሆነች...?  አመማት እንዴ?››

‹‹እኔ እንጃ እህቴ?.ካንቺ ጋር ተጣልታቹሀል እንዴ?››

‹‹ማንና ማን.. እኔና ስንድ? የት ተገናኝተን...ይሄን ወሬ ከየት አመጣኸው?››

‹‹እህቴ ባትቀየመኝ ኖሮ እንዲህ አትረሳኝም ነበር...አንድ ልጄን አስቀይሜ የአባቷ መንፈስስ እንዴት ይታዘበኛል? እያለች ቀኑን ሙሉ ስታለቅስ ነው የምትውለው.. አይኗ እንዳይጠፋ ፈርቼ ነው የደወልኩልሽ››

ሳባ ጭንቅላቷ ላይ ብው ብሎ የሚነድ እሳት የተነሰነሰባት መሰላት‹‹የእኔ ማር...እናትህ ተሳስታለች...እሷ መቼም  እኔን  ልታስቀይመኝ  አትችልም...  ደግሞም በሆነ ነገር ብቀየምስ በግልፅ እንዲህ አድርገሽኛል እላለሁ እንጂ  እንዴት እቀየማለሁ፤ ከአንተና ከእሷ ውጭ ሌላ ቤተሠብ አለኝ እንዴ?››

‹‹እሱማ የለሽም...ግን?››

‹‹ግን ምን?››

‹‹እኔ እንጃ ባትቀየሚ.ዛሬ እኛ ጋ ትመጪ ነበራ...››

‹‹የት አሰላ?››

‹‹አዎ ››

ብዥ  አለባት  ...መድሀኒት  ስትወስድ  የሚሰማትን  የመደንዘዝ  አይነት ስሜት ይሰማት ጀመረ..፡፡

‹‹ዛሬ ለምን?››

‹‹ነገ  የአባዬ  የሰባት  አመት  መታሰቢያው  አይደለ  እንዴ....?ባትቀየመኝ  በአባቷ መታሰቢያ ቀን ከቤቷ አትቀርም ነበር ብላ እኮ ነው የምታለቅሰው..››

‹‹ራጂ ቆንጆ...አሁን መኪና እየነዳሁ መጥፎ ቦታ ነኝ ያለሁት...ማታ ልደውልልህ››

‹‹እሺ እህቴ እወድሻለሁ፡፡››

‹‹እኔም   እወድሀለሁ    የእኔ    ማር፡፡››ስልኩን    ዘጋችና    ..መኪናዋን    አንቀሳቀሰች ...ወደአስፓልት መሀል ካስገባች በኃላ መጠምዘዣ እስክታገኝ ወደፊት ነዳች፡፡ ከዛ አቅጣጫዋን ለውጣ መንዳት ጀመረች.፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ እንደምንም ራሷን ተቆጣጥራ ያዘዛትን መድሀኒት በስርዓቱ ተጠቅማ በቀጠራት ቀን ከሳምንት በኋላ በሰዓቱ ሄደች።እንደደረሰች  በሞቀ  ፈገግታና  ጠበቅ  ባለ ሠላምታ  ተቀበላትና። "ቁርስ በልተሻል?›› ሲል ጠየቃት፤ግራገባት፡፡ አሰበች   ቁርስ   አልበላችም ..ጭርሱኑም ትዝ አላላት።ሳትመልስለት  የለበሰውን  ነጭ  ጋዎን  አውልቆ…»
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁሴን ተቀበለውና ቀጠለ <<ታዲዬስ ባለው ነገር ላይ ምንም አልጨምርም.. ቀጥታ ወደ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ገብቼያለሁ፡፡እዚህም ያላችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ አላማችንን የምትደግፉ በስልክም በኢሜልም ሆነ በተመቻችሁ ዘዴ ቃል መግባት ትችላላችሁ ... ከዛ በፊት ግን ይሄንን ዝግጅት የምንጀምረው፤በስጦታ ነው፡፡ስጦታውን የምትሰጠን ሰዓሊ ሰላም ነች.. ሰዓሊ ሰላም ወደ መድረክ…፡፡››

ሰላም ሸንከል ሸንከል እያለች ወደ መድረክ ስትወጣ ትንግርት ከኃላዋ 120 ሳ.ሜ በ 60 ሳ.ሜ ስፋት ባለው በሸራ ላይ የተሳለ ስዕል ይዛ ተከትላት ወጣች፡፡ስዕሉ ለህዝብ እይታ ቀረበ፡፡

<<እኛ ለእኛ›› የሚል ርዕስ አለው፡፡

አንድ ህፃን የተቦተራረፈ ልብስ እና የቆሸሸ ፊት ይዞ አስፓልት ዳር ከሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ
ጠርዝ ላይ ቂቢብ ብሎ በመውጣት ሞልቶ በመትረፍ አካባቢውን ሙሉ ከሸፈነው ቆሻሻ ላይ የተጣለ ምግብ ጎንበስ ብሎ የሚፈልግ ይመስላል፤አንደኛው እጁ ግን ወደ አስፓልቱ ተቀስሯል፤በተቀሰረው እጁ አቅጣጫ የቆመች የቤት መኪና ትታያለች፣ከመኪናዋ ውስጥ አንድ በተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የሚገኝ የፀዳ ልብስ የለበሰና የተመቸው ህፃን በመስኮት ተንጠራርቶ መፅሀፍ እና ዳቦ ለጎስቆላው ልጅ ሊያቀብለው ሲንጠራራ ያሳያል፡፡

ሁሴን ቃላ መጠየቅ ሊያደርጋት ወደ ሰላም ተጠጋ

‹‹ስምሽን ብታስተዋውቂን?››

‹‹ሰላም እባላለሁ..ሰላም ታዲዬስ፡፡››

‹‹ሰላም እሺ ..…ለምንድነው ወደዚህ መድረክ የወጣሽው?››

‹‹ይሄንን ስዕል ለድርጅቱ በስጦታ ላማበረክት፡፡››

‹‹በጣም ጥሩ ነው ..ማነው የሳለው?››

<<እኔ ነኛ፡››

‹‹ለምን ርዕሱን ..እኛ ለእኛ አልሽው?››

‹‹ለእኛ ከእኛ ውጭ ማንም ስለሌለ ነዋ...ታዲዬስ አባት ባይሆነኝ እኔ ይሄኔ እዚህ

መድረክ ላይ ሳይሆን ሀዋሳ መንገድ ዳር ቁራሽ ዳቦ መግዣ ሳንቲም እየለመንኩ ነበር
ምታገኙኝ…..እባካችሁ የኢትዮጰያ ህዝቦች በጠቅላላ መጥናችሁ ውለዱ፤ልመና የሞራል
ነቀርሳ ነው ማንም ህፃን እንዲለምን አትፍቀዱ፤ጎዳናዎች ከቦታ ወደ ቦታ መተላለፊያዎች እንጂ ፈጽሞ የህጻናት መኖሪያዎች መሆን የለባቸውም፤ታዲ አባቴ ከዛ
የጎዳና ሰቆቃ አውጥተህ ሰው ስላደረግከኝ አመሰግንሀለው እሺ ... ደግሞ በጣም ነው
የምወድህ....ሁላችንም ልጆችህ
እንወድሀለን..ሁሉም የዓለም አባቶች እንደ አንተ እንዲሆኑ እንፈልጋለን..››ይሄን ስትናገር እንባዋን መግታት ስላልቻለች መድረኩ ጥላ ወረደች..አዳራሹን የሞላው ህዝብ ዓይኞች ሁሉ
በዕንባ ፈሳሽ ተሞሉ፡፡ሁሴን ከደቂቃዎች ዝምታ በኃላ መናገር
ጀመረ‹‹እሺ ሰላምን እንደሰማችኋት ይሄንን በነዛ
ትናንሽ እጆቿ የተሳለውን ድንቅ ስዕሏን በስጦታ አቅርባልናለች.. እናም ለጨረታ እናቀርበዋለን..፡፡
ሰላም ማለት የታዲዬስ ልጅ ነች..ቅድም ልዩ ጥኡመ ዜማ ለጆሮችን ያሰሙን ሀሊማ እና
ሄለንም የታዲዬስ ልጆች ናቸው፤ሚጡና ሙሴ
የሚባሉም ልጆች አሉት...በተለይ ሙሴ የልጅ ሳይንቲስት ነው…ስለሱ ሳስብ ምን እንደሚታሰበኝ ታውቃላችሁ ሰው ከሞተ በኋላ
ነፍሱ በሌላ ሰው አካል ሆና ዳግም ወደዚህ ምድር ትመጣለች የሚል እምነት የሚያራምዱ
ማህበረሰቦች አሉ ፤ያ እምነት እውነት ከሆነ የታዲዬስ ልጅ የሆነው ሙሴ የቶማስ ኤዲሰንን
ነፍስ ይዞ ለኢትዬጵያውያን ተስፋ ሊሆን የተፈጠረ ሳይሆን አይቀርም ብዬ እጠረጥራለሁ…. በአጠቃላይ ቅድም ታዲዬስ
የተናገረው ንግግር ለመናገር ብቻ ሳይሆን እሱ በተግባር ስለፈተነው ህጻናትን ከመሰረቱ ኮተኩተን ካሳደግናቸው ገና ከጥዋቱ ፍሬያቸው እንደምናይ ስላረጋገጠ ነው..፡፡

አሁን ወደ ሰላም ሥዕል ጨረታ እንግባ..በነገራችን ላይ ከዚህ ፕሮግራም በኋላ የሰላምን ሌሎች ድንቅ ስዕሎችን ማየት ከፈለጋች በሚቀጥለው ክፍል ጎራ በሉ..(ይሄንን ሲናገር በየቤታቸው ሆነው ዝግጅቱን በቴሌቨዠን ለሚከታተሉት ካሜራው የሰላም ስዕል ወደ ሚገኙበት ክፍል በማዞር ማስቃኘት ጀመረ ..13 የሚሆኑ የተለያየ ርዕስ እና መጠን ያላቸው ስዕሎች በግድግዳው ላይ ተሰባጥረው ለዕይታ ምቹ ሆነው ተሰቅለው አሳየ፡፡

ሰላም ለድርጅቱ በስጦታ ያበረከተችው ስዕል ከሸራተን ሆቴል አልወጣም..በሼኩ ትዕዛዝ ይመስላል በ1ዐዐ ሺ ብር መነሻ የተጀመረውን ጫረታ ፉክክር ዝግጅቱ ላይ ታድመው የነበሩት የሜድሮኩ ስራ አስኪያጅ በሁለት ሚሊዬን ብር እዛው አስቀሩት..ድርጅቶችም ግለሰቦችም ያቅማቸውን ወረወሩ..አጠቃላይ ቃል የተገባውና እጅ በእጅ የተሰጠው በድምሩ 25 ሚሊዬን ብር ሆነ፡፡

ሁሴን ፕሮግራሙን ወደ ሶስተኛው ዝግጅት ሊያሸጋግር ፈለገ‹‹ቅድሚያ ግን ሄለን እና ሀሊማ ወደ መድረክ ዳግም እንዲወጡ አደረገ...የቴዲ አፍሮን ላምባዲና ነው ያቀረቡት፤ ልክ እንዳጠናቀቁ ሁለተኛውን ሙዚቃ ሊቀጥሉ ሲሉ ትንግርት በምልክት አስቆመቻቸው እና ወደ መድረክ ወጣች ፡

‹‹ይቅርታ ለየት ያለ ዜና በስልክ ስለደረሰኝ ነው ወደ መድረክ የወጣሁት..ቴዲ አፍሮ ከሄለን እና ሀሊማ ጋር አዲስ አበባ ላይ አንድ ኮንሰርት በማዘጋጀት ገቢውን ለድርጅቱ እንዲሚያስገባ ነግሮናል.. ለጊዜው 1ዐዐ ሺ ብርም በአካውንታችን ዛሬውኑ እንደሚያስገባ አብስሮናል፤እንግዲህ እዚህ ዝግጅት ላይ የታደሙ ድምጻዊያኖቻችን እና ኮሜዲያኖችም ቅድም እንደሰማችሁት አንድ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁልን ቃል ገብተው ነበር..ይሄ ሁለተኛ ኮንሰርት መሆኑ ነው፡፡እናመስግናለን ››ብላ ወረደች፡

..በዚህ ዜና በጣም የፈነጠዙት ሀሊማ እና ሄለን ናቸው ፤ከሚወዱትና ከሚያደንቁት ለእነሱ እንደ ህልም ከሆነው ቴዲ አፍሮ ጋር በአንድ መድረክ ሊሰሩ ነው..በደስታ በተጥለቀለቀው ስሜታቸው የሚቀጥለውን ሙዚቃ መጫወት ጀመሩ.. የሰርግ ዘፈን ነው‹‹..ሙሽራዬ ሙሽራዬ ... የወይን አበባዬ››ሙዚቃውን ተከትሎ ከጀርባ ካለው በር ወደ መድረክ ሲወጣ የታየው ታዲዬስ ነው፡፡ ቅድም ከለበሰው ልብስ በተለየ አለባበስ ሙሉ ሱፍ ለብሶ ቀኝ እግሩን አስቀድሞ ታየ.. ከኃላው ነጭ የተንዘረፈፈ ቬሎ የለበሰች ወጣት ተከትላዋላች... ርብቃ ነኝ..፡፡እጅ ለእጅ ተቆላልፈው በዝግታ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ወደ መድረኩ ወጡ…ጥጉን ይዘው እንደተጣበቁ ቆሙ፡፡

ሙዚቃው እንደቀጠለ ነው..ሌሎች ጥንዶች በተመሳሳይ ሁኔታ በተመሳሳይ አለባበስ ወጡ ዶ/ር ሶፊያ እና ፕ/ዬሴፍ ናቸው፡፡ ከነ ታዲዬስ ጎን ቆሙ..አሁንም ሌላ ጥንዶች ተከተሉ ፎዚያና ኤልያስ(የእነ ኤልያስ ጋብቻ ልዩነታቸውን በምን ሁኔታ ፈተው ወይም ለመፍታት ተስማምተው ለዚህ ጥምረት እንደበቁ ለጊዜው ከጥንዶቹ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ሰው የለም) ህዝብ ከፍተኛ መደመም ወስጥ ገብቷል..በመጨረሻ ጥንድ ሆነው የወጡት የነ ሀሊማ የሙዚቃ አስተማሪዋ አይነ ስውሯ ፅዬን እና የሰላም የስዕል አስተማሪው ዓልዓዛር ናቸው፡፡ሙዚቃው አልቆ ተቋረጠ..ከዛ አምስቱም የታዲዬስ ልጆች ከያሉበት ወደመድረክ ወጡና ታዲዬስን እና አዲሷን እናታቸውን ርብቃን ከበው ቆሙ..በተመሳሳይ ሌሎች ጥንዶችም ዛሬ ለማሳዳግ የተረከቧቸው ልጆች ወደ መድረክ ወጥተው በእያንዳንዱ ጥንዶቹ መካከል በፈገግታ ቆሙ..ህዝቡ በደስታ እና በዕልልታ አዳራሹን አደበላለቀው፡፡

ሁሴን ወደ መድረኩ ወጣና መናገር ጀመረ….
መቼስ በፕሮግራሙ ትንሽ ግራ ሳትጋቡ አትቀሩም..ይሄ የመጨረሻ ፕሮግራማችን የቀደሙት ፕሮግራሞች ቅጥያ ነው ፡፡እንግዲህ የያዝነው ትውልድን በአዲስ መልኩ መገንባት አይደል..ለዛ ደግሞ ቤተሰብ መመስረት ዋናው መሰረት ነው፡፡ እነዚህ አራት ጥንዶች የማህበሩ መስራቾች እና አባላት ናቸው፡፡ እንደምታዬቸው ሁሉም ጥንዶች ለየራሳቸው ልጅ ለማሳደግ ተረክበዋል፤ ከዛም በተጨማሪም ለሰርግ የበጀቱትን በጀት ለድርጅታችን ገቢ
አድርገዋል..ዶ/ር ሶፊያና ፕ/ዬሴፍ 400 ሺ ብር፣አቶ ታዲዬስ እና ወ/ሮ ርብቃ 1ዐዐ ሺ ብር
፣አቶ ኤልያስ እና ወ/ሮ ፎዚያ 5ዐ ሺ ብር፣በተመሳሳይ አቶ ዓላዛር እና ወ/ሮ ፅዬን 5ዐ ሺ ብር በጠቅላላው 6ዐዐ ሺ ገቢ በማድረጋቸው እኛስ ለምን ጋብቻቸውን በዚህ ፕሮግራም ላይ እውቅና አንሰጠውም በማለት
ነው እንዲህ ፊታችሁ ያቆምናቸው፡፡ ስለዚህ አንዴ በነ ሄለን ሙዚቃ ሙሽራዬ እያልን ወደ
መውጫቸው እንሸኛቸዋለን ….በዛውም ፕሮግራማችንን እናጠናቅቃለን፡፡

እናመሰግናለን፡፡

😔ተፈፀመ😔


ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ። ድርሰቱ ሲያልቅ 500 #Subscriber እንገባለን ብዬ ነበር አልተሳካም አሁንም ቢሆን ድርሰቱ የተመቸው ሌላ ድርሰት #እንዲቀጥል ፍላጎት ያለው ቻናሉን #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሃምሳ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ሁሴን ተቀበለውና ቀጠለ <<ታዲዬስ ባለው ነገር ላይ ምንም አልጨምርም.. ቀጥታ ወደ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ገብቼያለሁ፡፡እዚህም ያላችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ አላማችንን የምትደግፉ በስልክም በኢሜልም ሆነ በተመቻችሁ ዘዴ ቃል መግባት ትችላላችሁ ... ከዛ በፊት ግን ይሄንን ዝግጅት የምንጀምረው፤በስጦታ ነው፡፡ስጦታውን የምትሰጠን…»