አትሮኖስ
228K subscribers
104 photos
3 videos
41 files
303 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሁለት

///
    እሁድ ነው በዛ ላይ ክረምት፡፡አየሩ ጨላማና ጭጋጋማ ነበር፤በዛም የተነሳ ከመኝታዬ መውጣት አልቻልኩም..ሞቆኛል ብርድልብሴን ተከናንቤ የሀሳብ ድር እያደራሁ የምኞት ሸማ እየሸመንኩ ነው፡፡እኔ እየብ ነኘ፤ማለት ስሜ እዬብ ነው፤ ህይወቴም ልክ እንደመፅሀፍ ቅዱሱ እዬብ ከምቾትና ከድሎት ህይወት በተአምራዊ ሁኔታ የተፋታ  ወደ ድህነት አዘቅት ተሸቀንጥሮ የተጣለ ነው፡፡

ልዩነቱ የዛኛው እዬብ መከራ የመጣበት በሰይጣንና በእግዚያብሄር መካከል በተፈጠረ ቁማረ መሰለ ክርክር በማያውቀው ጉዳይና የእሱ ባልሆነ ስህትት የአለምን ቅጣት ሁሉ እንዲቀጣ የተደረገ ነው..በእኔ ምልከታ እሱ ላይ የተደረገበት ግፍ ነው፤ አረ እንደውም ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች እንደሚጠቀሙበት ሚስኪን አይጥ ነው ያደረጉት፡፡

   የእኔ ጉዳይ ግን እንደዛ አይደለም...እያንዳንዷን ያሳልፍኳት መከራ እያንዳንዷ የገጠመኝ ጨለማ ችግርና የብቸኝነት ስቃይ ከገዛ ራሴ ጥፋት የተመዘዙ ፤ወድጄና ፈቅጄ በምርጫዬ ወደ ህይወቴ ያመጣኋቸው የድክመቶቼ ውጤቶች ናቸው…እንደውም ሳስበው ከሚገባኝ በታች የተቀጣው ሰው ነኝ፡፡ስለዚህ ታላቄ እዮብ በማይገባው ስቃይ ተሰቃይቶ እንኳን እግዜሐብሄርን ሲያመሰግን ከኖረ እኔ ግን ከሚገባኝ በታች  እየተቀጣሁ እያለሁ እንኳን ሁሉ ግዜ ከምስጋና ይልቅ ንጭንጬ ለምን  አንደበቴን እንደሚቆጣጠረው ግራ ይገባኛል፡፡

ለአለፉት ሁለት አመት   የዘወትር ጸሎቴ፤ ስነሰና ስተኛ  መፅሀፍ ቅዱሴን ገልጬ መፅሀፈ-እዮብ ላይ ሄደና የእዬብን ምሬት ልክ ከራሴ ምናብ እንደመነጨ በመቁጠር  አንበለብል  ነበር ፡፡

..ያ የተወለድኩበት ቀን ይጥፋ...ያም ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ለሊት።ያ  ቀን ጨለማ ይሁን፣ እግዚሐብሄር ከላይ አይመልከተው፣ብርሀንም አይብራበት።ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፣ደመናም ይረፍበት።የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው።ያን ሌሊት ጪለማ ይያዘው።በአመቶች ቀኖች መካከል ደስ አይበለው።በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቆጠር።እንሆ ያ ሌሊት መካን ይሁን።እልልታ አይግባበት።...........ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት። አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፣........በመሀፀን ሳለሁ ለምን አልምትሁም?ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን አልጠፋሁም?ጉልበቾች ስለምን ተቀበሉኝ? ጡትስ ስለምን ጠባሁ።አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፣አንቀላፍቼ ባረፋሁ ነበር።

     አሁን ግን ይህንን የምሬት እንጉርጉሮ ማላዘን ካቆምኩ ሰነባበትኩ፤ ምክንያቱም በጥቂቱም ቢሆን ጭል ጭል የምትል ሻማ በህይወቴ የሆነ ጫፍ ላይ ተለኩሳ ማብራት የጀመረች ይመስለኛል.. ፡፡እንደነገርኳችሁ አቶ ሰሎሞን   ሆቴል ስራ ካገኘሁ ከአንድ ወር በኃላ የምኖርበትንም ቤት አገኘሁ፡፡የምኖርበት ግቢ ከሆቴሉ ተያያዥ ወይም ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን ሰፊና በዛፎች የተሞላ ነው፡፡በግቢው ውስጥ አንድ ኪችን፤ አንድ ሳሎን እና አንድ ሻወር ቤት ያለው መለስተኛ ቢላ አለ፡፡ይሄ ቤት የፊት ለፊቱ ሳሎን ከሌሎቹ ክፍሎች ጋር የሚያገናኘው በራፍ ታሸጎል፡፡ እኔ ሳሎኑ ውስጥ እኖራለሁ፤የተቀረውን ክፍል ነጋሽ’ዩ ሙሉአለም ይኖሩበታል፡፡ለዚህ ለምኖርበት ቤት በቀጥታ ኪራይ አልከፍልም፤ በምትኩ ግን የተወሰኑ አገልግሎቶችን ለቤቱ ባለቤት እሰጣለሁ፡፡
እኚህ እቤት የሚጋሩኝ ሰውዬ ማለቴ አቶ ሙሉአለም የአለቃዬ ማለት የሆቴሉ ባለቤት የአቶ ሰሎሞን አባት ናቸው፡፡

አዛውንቱ አቶ ሙሉዓለም የሚገርም ባህሪ አላቸው ፡፡ከቤት መውጣት ካቆሙ ሶስተኛ አመታቸውን ሊጨርሱ ነው፡፡በኮሮና ሰሞን በጣም የሚወዷት የእድሜ ዘመን ባለቤታቸው በዚህ በሽታ ተይዛ ሞተችባቸው...ከዛ እሳቸውም በፍራቻ እራሳቸውን ኳረንቲን አስገቡ፡፡ ይሄ በዛን ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገር ደረጃ በአዎጅ ሁሉም ዜጋ ባለበት እንቅስቃሴውን ገቶ እንዲቀመጥ ታዞ ስለነበር የእሳቸውም የተለየ አልነበረም…፡፡ግን ከወራት በኃላ አዎጁም ተነሳ ሁሉም ሰው ቀስ በቀስ ማስክ እያደረገ ከቤት መውጣት ፤ከዛም በሂደት ያለማስክስ ልክ እንደበፊቱ መተረማመስ ጀመረ፤ እሳቸው ግን ከቤታቸው ደጃፍ መውጣት አምቢኝ አሉ..፡፡ፀሀዮም ትቅርብኝ ጨረቃም አትናፍቀኝም አሉ፡፡ልክ እድሜ ልክ ተፈርዶበት ከርቸሌ እንደገባ ሰው በክፍላቸው ተከተቱ፡፡
ልጃቸው እራሱ በሳምንት አንድ ቀን መስኮታቸውን ይከፍቱና ከመስታወት ወዲያ ማዶ ሆኖ ያያቸዋል .እዛው በሶስት ሜትር ርቀት ሆነው አይን አይኑን  እያዩት  የሚያወሩትን ያወሩትና ይለያያሉ..ከቤታቸው ደጃፍ ለመሻገር ፍቃደኛ አይደሉም…ከማንም ሰው ጋር ለመነካካት አይፈልጉም፡፡

እና አኔ አንደኛ በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ከሆቴል አሰራና አምጥቼ  በራፍ  ስር  በማስቀመጥ …‹‹አያቴ ምግብ አምጠቻለሁ ያስገቡት፡፡›› እላቸዋለሁ፡

‹እሺ ዞረ በል›› ይሉኛል፡፡

‹‹እሺ ››ብዬ ዞሬ ወደ ክፍሌ ገባለሁ..እሳቸው ቀስ ብለው በራፉን ከፈት አድርገው መጋኛ እንዳያጠናግራቸው የፈሩ ይመስል ግራና ቀኛቸውን ገልመጥ ገልመጥ ያደርጉና የመመንጨቅ ያህል የምግብ ሰሀኑን በማንሳት ወደ ውስጥ ተመልሰው በመግባት በራፉን መልሰው ጠርቅመው ይዘጉታል፡፡
እና ሌላ የሚፈልጉት   ነገር ካለ ይነግሩኛል…ብዙውን ጊዜ በሳምንት አንድ ጠርሙስ ውሰኪና  መፅሀፍ ነው የሚጠይቁት፤ አልፎ አልፎ የራስ ምታት መድሀኒት ያዙኛል፡፡በአጠቃላይ ከውጭ የሚፈልጉት ነገር በጣም ጥቂት ቢሆንም ያንኑ ጥቂቱን  ካለበት ፈልጌ  የማቅረብ ኃላፊነቱ የእኔ ነው፡፡

በተጨማሪ  ከስራ ሰዓት ውጭ  እቤት ስሆን እኔም ሳሎኔ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ፤እሳቸውም ወይ ተቀምጠው ውስኪቸውን እየተጎነጩ ወይ አልጋቸው ላይ ተጋድመው ይደሰኩሩልኛል ፡፡እኔም የጣሙኝንም ያላጣሙኝንም ወሬዎች በማዳነቅ እና በተመስጦ አዳምጣቸዋለሁ፡፡ አልፎ አልፎም ስለውጩ ዓለም ወቅታዊ ሁኔታ የተወሰነ ወሬዎች እነግራቸዋለሁ..ያው ድምፅን ትንሽ ከፍ አድርጎ ማውራት ይጠይቃል እንጂ ከግድግዳ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ በደንብ ለመደማመጥ ተቸግረን አናውቅም፡፡
ከእኔ በፊት ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት መአት ሴትና ወንዶች እዚህ ቤት ገብተው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ግን ከአንድ እና ሁለት ወር በላይ መቆየት አልቻሉም ነበር..አብዛኞቹን አቶ ሙሉ አለም አልፈላጓቸውምና እንዲለቁ ተደረጉ ፤ የተወሰኑት ደግሞ ጠቅላላ ሁኔታውና የእሳቸውን ዲስኩርና ወሬ  በግድ ማድመጥ ሰልችቶቸው በራሳቸው ለቀው ይሄው ዛሬ እኔ ጋር ደረሰ..ለእኔ ግን ይሄው 11 ወር ሆኖኛል.እሳቸውም እስከዛሬ ከምስጋና ውጭ ስሞታ አቅርበውብኝ አያቀውቁም፤ እኔም ከቀን ወደቀን ከእሳቸው ጋር ያለኝ ትስስር እየጠነከረ እና እንደውም አያቴ እየመሰሉኝ መቸገሬን ስገልፅ እየተገረምኩ ነው፡፡አሁን ስገምት እንደውም ባሉካው እራሱ እየወደደኝ እና እያመነኝ የመጣበት ዋናው ምክንያት ከእሳቸው በሚያገኘው ተደራራቢ ሙገሳና ምሳጋና የተነሳ ይመስለኛል፡፡

ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን እስከአሁን ጋሽ ሙሉአለም በአካል አይቻቸው አላውቅም…ልጃቸው እንኳን እንደሚያደርጉት በመስታወት አሻግሬ በሩቅ ለማየት እኔም ሞክሬ አላውቅም እሳቸውም አበረታተውኝ አያውቁም አንድ ቀን ጋሼ ‹‹መልኮት እኮ ናፈቀኝ ››አልኳቸው፡፡

‹‹ምነው ሳታውቀው እንዴት ሊናፍቅህ ቻለ….?

«የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም ሲሉ አልሰማህም?››

‹‹እኔ ግን እኮ በደንብ  አውቆታለሁ….እንደውም የማላውቀውን አያቴን ነው የሚመስሉኝ…..››
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አራት
////

እንዳትሰማኝ ድምፄን ዝቅ አድርጌ‹‹የእውነት አድናቂሽ ነኝ"አልኩ  ..እውነቴን ነው ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ብቻዋን ገልብጣ ገድገድ ሳትል ...እኔ ገና በግማሽ ብርጭቆ ጉልበቴ  እየተብረከረከ ነው።

ተነሳሁና የተከፈቱ መስኮቶችን መዘጋጋት ጀመርኩ..ማብራቶችን አጠፍሁ፡፡ የሴትዬዎን ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ይዤ ወጣሁና የሆቴሉን በራፍ ቆልፌ ቁልፉን በጥንቃቄ ሚስጥር ኪሴ ውስጥ ሽጉጬ  ወደ አልጋ ክፍል አመራሁ...አቀብያት በዛው ወደ ቤቴ ሄዳለሁ ሞባይሌን አውጥቼ ሰዓት ሳይ 7፡40 ይላል።
ደረስኩና አንኳኳሁ...

‹‹ግባ ክፍት ነው››

የሚል ድምፅ ስሰማ ቀስ ብዬ በራፍን ወደ ውስጥ ገፋ አደረኩትና  ውስኪ ጠርሙስ የያዘ እጄን አስቀድሜ አንገቴን አሰገግኩ፡ መሀል ወለል ላይ ቆማ ተበትኖ ጀርባዋ ላይ የተኛውን ፀጉሯን አንድ ላይ ጠቅልላ እያሰረችው ነው..ቅድም ለብሳ የነበረውን ጅንስ ሱሪ አውልቃ ስስ የለሊት ቢጃማ ቀሚስ ለብሳለች...፡፡ ቢጃማው ሮዝ ቀለም ሲኖረው አጭር እና በቀላሉ አይን ውስጥ የሚመሰግ ነው...አስተውሎ ላየው ቀሚስ ሳይሆን ቁምጣ ነው የሚመስለው..እና ያ የሚንቀጠቀጥ እና ሊፈርጥ የደረሰ ዳሌዋ በከፊል እርቃን ነው...፡፡

"በራፍ ላይ ተገትረህ ታድራለህ ወይስ ትገባለህ ?"

"እ እሺ ገባለሁ ››አልኩና ወደውስጥ ገብቼ ጠርሙሱን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጬ ለመውጣት ዞር ስል  እሷ ከቦታዋ ተንቀሳቅሳ ወደበራፍ እያመራች ነው፡፡

‹‹...ብርድ አስመታሀኝ ››"በሚል ሰበብ  ክፍት ጥዬ የመጣሁትን በራፍ ዘጋችና ቆለፈችው፡፡

"ቆይ እኔ ሳልወጣ?"አልኩ ደንግጬ፡፡

"ትንሽ አጣጣኝ እና ትሄዳለህ.. ያውልህ ብርጭቆ…

"ቅዳልኝ" የንግግሯ ቃና ወደ ትዕዛዝ ያዘነበለ ነው.፡፡
ግራ በመጋባትና በመርበትበት  እንዳለቺኝ አደረኩና እዛው ጠረጴዛ ጎን ያለ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ..፡፡እሷም ወደእኔ መጣችና ብርጭቆዋን አንስታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች ...፡፡አቀማመጧ በእኔ ትክክል ነው...፡፡አይኔ ወደታች ወደተጋለጠው ጭኗ እየተንሸራተተ አስቸገረኝ ፡፡...እሷ የእኔን ሁኔታ ከቁብም የቆጠረች አይመስልም፡፡ጭኗ እንደሴቶች ጭን ልል እና ለስላሳ አይደለም…፡፡እንደስፖርተኛ የዳበረ እና ፈርጣማ ነው፡፡ሲነኩት ትንቡክ የሚል አይነት ሳይሆን ሲነካ ጭፍልቅ  የሚያደርግ አይነት፡፡

"አሁን ጋሼ እንዲህ ከእንግዳ ጋር በውድቅት ለሊት ቤርጎ ውስጥ  ገብቼ ዘና ስል  ቢያየኝ ምን ይለኛል? ጓደኞቼስ ቢያዩ ተረባቸውን እችለዋለሁ?››

በዝምታ ውስጥ ሆና የቀዳሁላትን  ጠጥታ  ጨረሰችና ከተቀመጠችበት ተነስታ እራሷ ለራሷ ቀዳች ፡፡..ልትቀዳ ስትል ታከከቺኝ..እናም ደግሞ የተቀባችው ሽቶ ያለፍላጎቴ በአፍንጫዬ ሰርጎ ገባ...እና እየጠጣሁ ካለሁት መጠጥ ጋር ተጋግዞ አነቃቃኝ...፡፡

ወደቦታዋ ተመልሳ ተቀመጠች ፡፡አቀማመጧ ግን እንደቅድሙ እግሮቿን አጣምራ ሳይሆን ፈርክክ አድርጋ ከፍታ ነው፡፡ ...እና በክፍተቱ አይንን ሚያጥበረብር ቀይ ፓንት አየሁ..፡፡ለምን አየህ ?ብላ ተነስታ የምታንቀኝ መስሎኝ  ከመርበትበቴ የተነሳ ብርጭቆ ውስጥ ያለችውን መጠጥ በአንድ ትንፍሽ ገርገጭ አድርጌ አጋባኋት፡፡

"በቃ እግዜር ይስጥልኝ አሁን  መሸብኝ ልሂድ..›› ለማለት አስቤ ገና አፌን ሳልከፋት ከተቀመጠችበት ተነስታ በድጋሚ ቀዳችልኝ፡፡ ..ለመናገር የተከፈተ አፌን ቀስ ብዬ ዘጋሁትና  አንዴ መጠጡን አንዴ እሷን እያፈራረቅኩ ማየት ጀመርኩ።"አሁን ብዥ እያለብኝ ነው..፡፡ሞባይሌን አወጣሁና ሰዓት ተመለከትኩ...8:18 ይላል።

"ምነው መሸብህ እንዴ?"

"አይ አንቺን እንቅልፍ ነሳሁሽ ብዬ ነው"

"ጥሩ አስመሳይ ነህ"አለችኝ.፡፡

‹‹እስቲ በጌታ አሁን እንዲህ ይባላል?››አንገቴን በእፍረት ከማቀርቀር ውጭ ምንም መልስ አልሰጠኋትም፡፡ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደሻንጣዋ በመሄድ መጎርጎር ጀመረች‹‹...ምን ልትሰጠኝ ነው?"ብዬ ሳሰላስል  ክሬም ቅባት አወጣችና አልጋ ላይ ወረወረች..መቀመጫዋን ወደ እኔ ፊቷን በተቃራኒው ወደግድግዳው አዞረችና በቆመችበት አጭሩን የለሊት ቀሚሷን ሞሽልቃ አወለቀች።አይኖቼን ጨፈንኩ..ገለጥኩ...መልሼ ጨፈንኩ...ቅድም በስሱ ካየሁት  ቀይ  ፓንት በስተቀር ምንም የጨርቅ ዘር በሰውነቷ አልቀረም....፡፡ጡቶቾ እንደሩሲያ አስፈሪ ሚሳዬሎች ጫፋቸውን ወደእኔ   ቀስረው ልቤን አራዷት ብላችሁ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን እየታዩኝ አይደለም፡፡ፐ!! ከኃላዋ የሚታየው የሰውነቷ  ቅርፅ  ግን ከአንገቷ በላይ ያለውን መልኳን በሁለት ሶስት እጥፍ ይበልጣል።

ዘለህ ተጠምጠምባት የሚል ስሜት  ከሁሉም የስሜት ህዎሳቶቼ ተሰባስቦ ጉሮሮዬ ላይ ተወተፈብኝ... እጇቼ ገላዋን ለመዳሰስ አይኖቼ ከግራ ወደቀኝ እያገላበጠ  መላ ሰውነቷን በምስጠት ለመመልከት፤ አፍንጫዬ አንገቷ ስር ተደፍቶ ጠረኗን ወደውስጥ መማግ፤ጆሮዎቼ አፍ አካባቢ ተለጥፈው ከአንደበቷ የሚወጣውን ሹክሹክታ በፅሞና ለማዳመጥ እና እንትኔ ደግሞ ጭኖቾን ፈልቅቆ ወደ ውስጠቷ መስመጥ ፈለገ(ውይ እንትኔ ለካ የስሜት ህዋሳቴ አይደለም...ነው እንዴ?)

ዘፍ ብላ በሆዷ አልጋው ላይ ተኛች...አሁን በህይወቴ በአካልም በፊልምም ጭምር ካየኋቸው ባለ እርቃን ሴቶች ሁሉ ተወዳዳሪ የሌላት ፍፅም አማላይ ሆና ታየችኝ፡፡.. ፀጉሯ ብትን ብሎ ከፊል ጀርባዋን እና የተንተራሰችበትን ትራስ ሸፍኖታል..፡፡ከዛ ወረድ ስንል ልምጥ  ብሎ የሚታየው ወገቧ  የሩብ ጨረቃን ቅርፅ ይዞ አይንን ያፈዛል ፡፡..ከዛ ሽቅብ ወደላይ ስንወጣ መቀመጫዋ ቀይ ፅጌረዳ አበባ የሸፈናቸው ግዙፍ መንታ ተራሮች ይመስላሉ፡፡..ከዛ በመነሳት ለሁለት ተከፍለው የተዘረጉት እግሮቾ ለምለም መስክ ላይ የተዘረጋ የአክሱም ሀውልትን ይመስላሉ...እጣቶቾ ደግሞ....

"ትንሽ እሸኝና ትሄዳለህ.."የሚለው ንግግሯ ስለውበቷ ተቀኝቼ ሳልጨርስ ከሀሳቤ አናጠበኝ።

" ሎሺኑን ተጠቀምና እሸኝ.."ደገመችልኝ።

"እሸኝ ማለት ምን ማለት ነው..?እንዴት ነው የማሻት..?የሚታሽና የማይታሽ የሠውነት ክፍል ይኖራት  ይሆን ?ካሸዋትስ በኃላ የሚከተል ነገር ይኖራል..?በሰከንድ ውስጥ በምናቤ  ብልጭ ድርግም ያሉ  ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው..፡፡እጆቼን ሰበሰብኩና ወደአልጋው ተራመድኩ፡፡ ጠርዝ ላይ ተመቻችቼ ተቀመጥኩ..፡፡ጃርባዋን ያለበሰውን ፀጉሯን ሰበሰብኩና ወደትራሱ አሻገርኩት...እና ሎሺኑን አነሳሁና ጨመቅ ጨመቅ አድርጌ እጄ ላይ አፈሰስኩና   ከትከሻዋ ጀመርኩ...፡፡ይህ ሰውነት ከዚህ በፊት እንደማውቃቸው የሴት ገላዎች የሀር ጨርቅ አይነት ልስላሴ የለውም..፡፡በዳበሩ ጡንቻዎች የተገነባና በጠንካራ ቆዳ የተሸፈነ ልዩ አይነት ሰውነት ነው፡፡ቢሆንም ሲያሹት እጅን ሙልጭ ሙልጭ እያደረገ ቢፈታተንም ደስ ይላል፡፡ ‹‹ አዎ ትግስት ካለኝ  ተገልብጣ በጀርባዋ ስትተኛና ከፊት ለፊቷ ያለውን የሰውነት ክፍሏን እንዳሻት ስትመቻችልኝ ቀስ ብዬ ልክ እንደዚህ ሎሺን ጡቶቾን አሸት አሸት እያደረኩ ከውስጣቸው ፍቅር እንዲያመነጩ አስገድዳቸዋለሁ፡፡›› ስል በአይነ ህሊናዬ በመሳል ጎመዣሁ..ምራቄን ገርገጭ እያደረግኩ ዋጥኩ ።
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አምስት

////

አሁን ወደ ቤቴ ልሄድ ወሰንኩና ወደ እሷ ዞርኩ ...እና አሁንም በድጋሜ ከፊል  እርቃኗን ስመለከት እርብድብድ አልኩና"አይ በዚህ ሰአት ዘበኞቹ ሰለሚተኙ ግቢውን አይከፍቱልኝ ይሆን እያልኩ እያሰብኩ ነው።››

"ነውእንዴ? ታዲያ እዚህ እደራ!!"ብላ ዘጭ ያለው ሞራሌን መልሳ ሰማይ ሰቀለችው..፡፡እያንቀጠቀጠኝ የነበረው የውስጥ ቅዝቃዜ ከውስጤ እየተወገደ በምትኩ ሙቀት ሲራወጥ ታወቀኝ፡፡

"ይሻላል?"

"አዎ ..ችግር የለውም...፡፡አለችና አንሶላውን እና ብርድ ልብሱን ገልጣ ከውስጥ ገባች...፡፡እኔም በአፌ ምራቅ እየሞላ ጫማዬን ማውለቅ ጀመርኩ፤ ሸሚዜን አወለቅኩ፤ፓክ አውቴንም አልተውኩ አወለቅኩ፤ በመጨረሻ ሱሪዬን አወለቅኩና ልክ እንደእሷ በፓንት ብቻ ወደ አልጋ ላይ እየተስገበገብኩ ወጣሁ።..እያየኋት ብርድልብሱን  ወደእኔ ገፋችና  በአንሶላና አልጋልብሱ ተጠቅልላ አንደኛውን ጠርዝ ይዛ ተኛች ..

"ብርድልብሱን ልበስ..ደህና እደር"ብላኝ መብራቱን አጠፋችና ለሽ...፡፡

"እንደተባልኩት በብርድ ልብሱ እርቃኔን ጠቅልዬ ለመተኛት ሞከርኩ...፡፡ምን አይነቱ እንከፍ ነኝ እስኪ ደህና እደር እንዳለችኝ ያልሆነ ነገር ከምቀባጥር በክብር ፈጠን ብዬ ይሄን ክፍል ለቅቄ ብወጣስ?...እሷ እያንኮራፍች ነው፤እኔ ግን ..?እኔማ በሁለት እጇቼ እንትኔን አፍኜ ይዤ እየተገለባጥኩ ነው።በግድ ጉብ ልበልባት ይሆን ?አይ ይሄ  አይሆንም ጓደኞቼ በፓለቲካ ምክንያት ታስረው ጀግና ሲባሉ እኔ በአስገድዶ ደፈራ ሀያ አመት ....አይ መታገስ መልካም ነው፡፡እኔ ደግሞ በትግስት አልታማም ..በእፅዋት ሳይንስ ከሀረማያ በዲግሪ ተመርቄ አዲስአበባ ላይ በአስተናጋጅነት ተቀጥሬ በመስራት ኑሮዬን እየገፋሁ ያለው ትሁት ትዕግስተኛ። ከዚህ በላይ ትግስት ምን አለ...?በተወለድኩባት አዲስአበባ ከተማ  በተማርኩበት ሞያ ስራ ለማግኘት ከአመት በላይ በየመስሪያ ቤቱ  ተንከራተትኩ ..ምንም ጠብ ያለልኝ ነገር የለም...አንድ መስሪያ ቤት ጋምቤላ ልላክህ ይላል...ሌላው ጋ ስሄድ የበጋ ስንዴ ፕሮጀክት አርሲ ላይ አለን እዛ እንላክህ ይለኛል።"ምነው ውትድርና የሰለጠንኩ መሠላቸሁ እንዴ? "ብዬ በእነሱ ይሁን በራሴ እያላገጥኩ አላውቅም ሁሉንም እርግፍ አድርጌ  ያለሞያዬ ስባክን ይሄው ይሄን የመሠለ ፈተና…..

የባጥ የቆጡን ሳስብ ምንጊዜ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም፡፡ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስደኝ፡፡ ….....የበር መንኳኳት ነበር ከእንቅልፍ አለም መዞ ያወጣኝ
‹‹...ማነው? ምንድነው ?››በርግጌ ተነሳው፡፡

"ፅዳት ነው ሰዓት ደርሷል"

"ፅዳት "ዙሪያ ገባውን ቀኘሁ፡፡ነግቷል፡፡ክፍሉ ባዶ ነው.፡፡.ልጅቷ የለችም...፡፡ልብሷቾም ሆነ ዕቃዋቾ የሉም...፡፡ጠረኗ ብቻ ነው ያለው...፡፡ሄዳለች ማለት ነው..፡፡.ምኑ እንክርፍፍ ነገር ነኝ በፈጣሪ...?ምን አለ በጥዋት ተነስቼ ቢያንስ ለመጨረሻ ጊዜ እነዛን አይኗቾን ማለቴ መቀመጫዋን አይቼ በተሰናበትኳት...፡፡በንዴት ከላዬ ላይ ብርድ ልብሱን አሽቀንጥሬ  ከላዬ ላይ ወረወርኩ፡፡ ...ከአልጋው ወረድኩ… ጠረጴዛ ላይ ያለውን ልብሴን ሳነሳ የሆኑ ባለመቶ ብር ድፍን ብሮች  እና ብጣሽ ወረቀት ድብ ብሎ ወለል ላይ ወደቀ...ብሩን ተውኩና ወረቀቱን አነሳሁት አነበብኩት።

‹‹ደህና ሁን ቆንጇ...ቁርስ በእኔ ነው"ይላል ...
ብሩን አነሳሁና ቆጠርኩት 500 ብር ነው፡፡
‹‹እኔን ብሎ ቆንጆ›› አልኩና በቅጡ እንኳን ልብሴን አስተካክዬ ሳለብስ  በንዴት ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ፡፡

ከውስጤ እየተንቀለቀለ ያለው ንዴት በቀላሉ ሊበርድልኝ ስላልቻለ እቤቴ ስደርስ እንኳን የበራፍ አከፋፈቴና አዘጋጌ ኃይል የተቀላቀለበት ነበር ፡፡

‹‹አንተ ቀልማዳ….››

‹‹አቤት አያቴ››

‹‹የትአባህ ነው ያደርከው…?ሰው ያስባል አትልም እንዴ…?ከአሁን አሁን መጣ እያልኩ ቁጭ ብዬ እኮ ነው ያደርኩት››

‹‹ውይ በጣም ይቅርታ ..ጋሼ ስራ አዞኝ እስከ 9 ሰዓት ስሰራ ስለነበር ደከመኝና እዛው ተኛሁ፡፡››

‹‹እና ሮጥ ብለህ አንድ አፍታ መጥተህ ላድር ነው ብትል የትኛውን ድንበር ስታቆርጥ ነው››ጠንከር ባለ የንዴት ቃና ሲቆጡኝ እንባዬ በአይኔ ሞላ ..ተበሳጫቼ  አይደለም..፡፡ይሄን ያህል የሚያስብልኝ ሰው ይኖረል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበረ…፡፡
‹ሁለተኛ አይለመደኝም››ቃል ገባሁ፡፡
‹ፍፅምዐእንዳይለመድህ .
ትደግመውናትጣላኛለህ
.በል አሁን እንደደካከመህ ድምፅህ  ያስታውቃል ትንሽ ተኛ፡፡››

‹‹እሺ አያቴ›አልኩና አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ፡፡

‹‹ዜና ወርቅ… ›
›.‹‹የዜናወርቅ አዎ እንደዛ ብላ ነበር ስሟን  የነገረችኝ…ለዛም ይመስለኛል የዜናወርቅ የሚለው ስም ከእምሮዬ ሞልቶ እየፈሰሰ ያለው….
‹‹ወይ ጉድ ፍቅር ስለሚለው ቃል እራሱ ያሰብኩት ከስንት ጊዜ በኃላ መሆኑ ነው…?አዎ ከስድስት ረጂም አመት በኃላ …፡፡ ፍቅርን እርም ብዬ ነበር…፡፡ልክ እየደጋገሙ እየተንበገበገ ባለ እሳት እጣቱን ከተው እስኪቆስልና ቆዳወ እስኪገሸለጥ ድረስ እያቃጠሉ እንዳስፈራሩት ልጅ አይነት ነበርኩ፡፡.አዎ ፍቅርን የምፈራው ልክ ያ ህፃን ልጅ እድሜ ልኩን እሳትን በሚፈራበት መጠን ነው፡፡እና ጊዜያዊ ስሜቴን ማስወገድ አለብኝ.››.አስቤ አስቤ ሲደክመኝ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

‹‹ወይ ዝም ብዬህ ቻው እንኳን  ሳልልህ ሄድኩ አይደል?››

‹‹አዎ…ግራ አጋባሺኝ እኮ››

‹‹አይ አስቸኮይ ነገር ስላጋጠመኝ ነው .ይቅርታ››

‹‹አይ ምንም አይደል…ግን እቤቴን ማን አሳየሽ? ››

‹‹አለቃህ…ማለቴ የሆቴሉ ባለቤት ለመነኩትና ከአንድ ጩጬ ጋ ላከኝ፡፡››

‹‹እሺ የቤቱን በራፍስ ማን ከፈተልሽ...?እኔ ተኝቼ ነበር››

‹እሱን ተወው .በመምጣቴ አልተደሰትክም እንዴ?››

‹‹አረ በጣም ተደስቼያለሁ…ነገሮች ድንገተኛ ስለሆኑብኝ ግራ ተጋብቼ ነው››

‹እንደዛ ከሆነ እቀፈኝ››

‹‹እሺ…ይሄው….ወደራሴ ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት…››

‹‹እዬብዬ.›በተሰባበረ እና በሚያቃትት ድምፅ ጠራችኝ፡፡

‹‹ወዬ ዜናዬ.››

‹በጣም ሞቀኝ…ልብሴን ላውልቅ››

‹አዎ አውልቂ…. እንደውም እኔም ላውልቅ.››አልኩና እኩል እየተረዳዳን  ልብሳችንን አወለቅንና እርቃናችንን ተመልሰን እቅፍቅፍ ብለን ተጋደምን….፡፡እርቃናችን ሲፋተግ እሳት ፈጠረ..ነደድኩ… ከንፈሯ ላይ ተጣበቅኩባት…ጭኗን ፈለቀቅኩና ሰርስሬ ከመሀል ገባሁ….ቃተተች…‹‹ወይ የእኔ ጀግና ጎዳኸኝ….ቀስ በል..አመመኝ›››
በእጆቼ አፏን አፈንኳት..እንደዛ ያደረኩት የዜናወርቅን የመቃተት ጩኸት አያቴ እንዳይሰሙንና እንዳይረበሹ ስለፈራሁ ነው፡፡እንኳን እንዲህ የምትቃትት ሴት ይቅርና ጮክ ብሎ የሚያወራ ወንድ ጓደኛ  እዚህ ቤት ይዤ መጥቼ አላውቅም፡ተጨነቅኩ፡፡ ስላፈንኳት እሷ ተንፈራገጠች…፡፡ግራ ገባኝ፤ ልልቀቃትና መጮኸን ትቀጥል ወይስ እንዳፈንኳት ልቀጥል …?ብትሞትብኝስ..?፡፡ከመጨነቄ  የተነሳ ላቤ መንጠባጠብ ጀመረ …ተስፈንጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁ፤መኝታዬ ባዶ ክፍሉም ኦና  ነበር…ዜናወርቅ ሀሳብ ብቻ ነበረች.፡፡ምኞት የፈጠራት ህልም››
‹‹ተመስገን›አልኩ፡፡
‹‹ተመስገን ያልኩት ዜናወርቅ ቤቴ ስላልመጣችና ስላልተዋሰብን ተደስቼ አይደለም..ይልቁንስ የእውነት ሆኖ ጋሽ ሙሉአለም ስላረበሽኳቸውና ስላላስቀየምኳቸው ተደስቼ ነው ተመስጌን ማለቴ..አንዳንዴ ግን ህልም ባይኖር በምኞታችን እና  በምናገኘው ነገር መካከል ያለውን ክፍተት በምን እንሞላው ነበር?››

ይቀጥላል
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰባት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ብዙ ፍላጎቶች አሏት..ለዛውም ያልተገሩ ፍላጎቶች ።አንደኛውን ለማሟላት በቀኝ ትጓዛለች ..ሌላው ደግሞ ወደግራ ያስፈነጥራታል...እንዲሁ የፍላጎቶቾን ጭራ ተከትላ ከግራ ቀኝ ስትላጋ ትከርምና በስተመጨረሻ እራሷ ከራሷ ትጠፋለች‹‹...የት ነው ያለሁት?ምን እየሠራሁ ነው? ምንድነበር የምፈልገው?››የአንድንም መልስ መመለስ አትችልም.... ፍፅም ድንዛዜ ውስጥ ትገባለች።ነፍሷ በማጥ ተይዛ እዛው ጭቃ ውስጥ መውጣት አቅቷት የምትንቧጫረቅ  ይመስላታል..‹‹.ጭቃ ውስጥ ገብቼ እንደዚህ እየዳከርኩ ያለሁት እኔ ነኝ ሌላ ሰው?›› ግራ ይገባታል...እራሷው ከእራሷ ትጠፋለች።አንድ ሰው እራሱ  ጠፊ እራሱ ደግሞ ፈላጊ ሲሆን የሚፈጠረው ነገር?
ለሊቱ በመከራ ነው የነጋላት..ምን አልባትም በህይወቷ ካጋጠሟት እጅግ አታካችና ደባሪ ለሊቶች ውስጥ አንዱ ነው….አስራአንድ ሰዓት ከሆነ በኃላ ክፍሏ ውስጥ መቆየት አልቻለችም ፡፡ መኝታዋን ለቃ ወረደችና  ቁምሳጥኗን ከፋፍታ ፊት ለፊት ያገኘቻውን ልብስ ያለምንም ማሰብ ለባበሰችና ስልኳንና የቃልን ላፕቶፕ በቦርሳዋ ከተተች፡፡  ከክፍሏ ይዛ ወጣች…በሩን ስትዘጋና ስትከፍት እናቷን እንዳትቀሰቅስና እሄዳለሁ አትሂጂም የሚል አተካራ ውስጥ ላለመግባት ብላ በጥንቃቄና በፀጥታ  ወደታች ወረደች ፡፡ የሳሎኑን በራፍ ከፍታ ወጣች... ግቢው ውስጥ የለሊቱን መንጋት የሚያበስሩ ባለ ብዙ ቀለም ማራኪ  ወፎች ከአንዱ   ዛፍ ወደሌላው ዛፍ እየተሸጋገሩ ሲዘምሩ ከሚሰማው ተፈጥሮዊ  ዝማሬ በስተቀር ሙሉ አካባቢው ፀጥ ያለ ነው፡፡ወደ ዘበኛው ቤት ሄደችና በስሱ አንኳኳች‹‹…..ማነው….?››የሚል ሻካራ ድምጽ ከውስጥ ተሰማ፡፡
‹‹ድምፅህን ቀንስ እኔ ነኝ?››
‹‹እትዬ ልዩ ምነው?››የ50 አመቱ ጎልማሳ እሷን የ23 አመቷን ልጅ እትዬ እያለ ሲጠራት ሁሌ እንዳስፈገጋት ነው…ብዙ ጊዜ ልዩ ብቻ ብሎ እንዲጠራት ነግራውም አስፈራርታውም ነበር..እሺ ይላል እንጂ በተአምር ተሳስቶ ልዩን ከእትዬ ነጠሎ ጠርቷት አያውቅም.. አሁንማ እሷም ለመደችው …
‹‹ድምፅ ቀንስ እኮ አልኩህ…ፈልጌህ ነው?››
‹‹እሺ እሺ..›› እየተደናበረ ወጣ፡፡››
‹‹ምነው…? ፈለግሺኝ….?››
‹‹መኪና ይዤ ልወጣ ነው፡፡››
‹‹ከማ ጋር?››
‹‹ከአንተ ጋር ››
‹‹ምን አልሺኝ እትዬ?››
‹‹ብቻዬን ነዋ…እዚህ አካባቢ በዚህን ሰዓት አብሮኝ ሊሄድ የሚችል ሰው ይታይሀል?..አሁን ክፈትልኝ…እስከዛ ሞተር ላሙቅ ››እለችውና መኪኖች ወደሚቆሙበት ስፍራ ሄደች…
ሶስት ሚኪኖች በተርታ    ተጠጋግተው ቆመዋል፡፡ዝም ብላ የእናቷን ሰማያዊ ኮሮላ መኪና ውስጥ ገባች፡፡ያው በእነሱ ቤት ልምድ መኪኖች ግቢ ውስጥ ከገቡ በኃላ ቁልፋቸው አይነቀልም..ምን አልባት ኢመርጀንሲ ተፈጥሮ ቢፈለጉ ገና ቁልፉን ከቤት ወይም ከሹፌሮች ጋር ከመፈለግ መንዳት የሚችል ሰው ወዲያው ገባ ብሎ ይነዳቸዋል..ይህ ህግ የወጣው በእሷ ምክንያት ነው..፡፡ያው በተለያ ሰበብ ሁሌ አደጋ ስለማያጣት…ሹፌር ፍለጋና ቁልፍ ፍለጋ ህይወቷንም ጭምር ሊያሳጣት የደረሰ አጋጣሚ ተከስቶ ስለነበር ይሄ ውሳኔ ተወሰነ..እና ይሄው ዛሬ ለራሷ ረዳት…፡፡
ላፕቶፑን ያለበትን ቦርሳዋን ከጎኗ አስቀመጠችና ቁልፉን አሽከርክራ ሞተሩን አስነሳችው.‹‹.መቼስ እማዬ የመኪናውን የሞተር ድምፅ ሰምታ በመንቃት መጥታ እንደማትቀውጠው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››አለች
ዘበኛው በራፉን በልቅጦ ከፈተና እየተጎተተ ወደእሷ መጣ….. በአሳዛኝ ሁኔታ እየተቅለሰለሰ‹‹እትዬ ልዩ ግን አትዬ እንዴት እንደሚቆጡኝ እየታየኝ ሆዴ ተሸብሮብኛል…. ሊያባርሩኝ ሁሉ ይችላሉ፡፡›› አላት፡፡
ኪሷ ገባችና ድፍን ሁለት መቶ ብር በማውጣት በእጁ አስጨበጠችው… ‹‹ከሰደበችህ በዚህ ቻለው…ከባረረችህ  ግን ደውልልኝ እኔ አስቆማታለሁ…›› አለችው፡፡
በደስታ ተፍለቅልቆ‹‹እሺ የእኔ ደግ..ይሁን እችለዋለሁ…በይ  ሂጂ›››አለታ
መኪናውን አስነሳችና ግቢውን ለቃ ወጣች….መንገዱ  ነፃና ምንም አደናቃፊ  ስለሌለበት 25 ደቂቃ ነው የፈጀባት፡፡በራፉ ላይ ደርሳ የመኪናዋን አፍንጫ የግቢ በራፋቸው ላይ አስደግፋ አቆመች ..ሰአቷን ስታይ ሰውነቷ ቀዘቀዘ.. ‹‹በዚህ ሰዓት ለምን መጣሁ? ምንድነው የማደርገው..?›› ግራ ገባት…፡፡
‹‹በዚህ ለሊት እንደመርዶ ነጋሪ የሰው በራፍ አላንኳኳም፡፡የራሱ ቤት እንኳን ቢሆን የራሱ ጉዳይ….የኪራይ ቤት ለዛውም አሮጊት…..ምን አለ የዛን ቀን ስልክ ቁጥሩን ተቀብዬው ቢሆን.. አሁን ደውልለትና ቀጥታ መጥቶ ይከፍትልኝ ነበር….ከዛ ይሄንን ላፕቶፕ አፍንጫው ላይ ወርውሬለት የመኪናዬን መሪ ወደኃላ አዙሬ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ይሄን ሰፈር እለቅ ነበር…ከህይወቴ እስከመጨረሻ አሽቀንጥሬ እወረውረውና ከእነመፈጠሩም እረሳው ነበር፡፡››ስትል አብሰለሰለች፡፡
የመኪናዋ መሪ ላይ ተደፍታ እነዚህንና መሰል ሀሳቦች እያሰበች ሳለ ባልገመተችው ሁኔታ የግቢው ትንሿ በራፍ ከውስጥ መንጓጓት ጀመረች…..ነቃ አለችና, ከተደፋችበት    ተነሳች፡፡ በራፉ ተከፍቶ ነጭ በነጭ የለበሰች አንድ ሰትዬ ወጡ …አሮጊቷ የቃል  አከራይ ናቸው፡፡አለባበሳቸውን ብቻ አይቶ ወደቤተክርስቲያን ሊሄዱ  እንደሆነ መናገር ይቻላል…ከወጡ በኃላ ባልተለመደ ሁኔታ መኪና በራፋቸውን ታኮ መቆም እንዳስገረማቸውም እንዳስደነገጣቸውም ከሁኔታቸው መገመት ይቻላል፡፡…ልዩ ያንን ስለተረዳች ፈጠን ብላ ገቢናውን ከፈተችና በመውረድ ወደ እሳቸው ተጠጋች፡፡
‹‹ደህና አደሩ ማዘር …የቃል ጓደኛ ነኝ፡፡››
‹‹እ…የበቀደሞ ልጅ  ነሽ;››
‹‹ቆቅ አሮጊት ናቸው››ስትል አሰበች… እንዲህ በፍጥነት ያውቁኛል ብላ አልገመተችም ነበር፡፡
‹‹አዎ..አውቀውኛል››
‹‹ታዲያ ሰላምም አይደለሽ…?ገና ለሊት ነው እኮ፡፡››
‹‹‹አዎ ከቃል ጋር 12.30 የሆነ ቦታ ለመሄድ ተቀጣጥረን ነበር …ሳላስበው ትንሽ ቀደም ብዬ መጣሁና ማንኳኳት ደበረኝ፡፡››
‹‹እና አትደውይለትም ነበር?››
‹‹ሞክሬ ነበር..ዘግቶታል መስለኝ አይሰራም››ውሸት መቼስ የተካነችበት ነው..ከልጅነቷ ጀምሮ በብቃት የምትሰራቸው ሶስት ነገሮች ሌብነትና ቅጥፈት እና ወሬ(የሰው ሚስጥር)ማነፍነፍ ናቸው…፡፡
‹‹ግቢያ ….በራፍን ልክፈትልሽና ሚኪናዋን ታስገቢያት?››
የበቀደምለታው ግልምጫ ከዛሬው መሽቆጥቀጥ ጋር አመዛዝና ፈገግ አለች፡፡በቀደም የዱርዬ ገፀ ባህሪ ተላብሳ ነው ፊታቸው የተጋረጠችው ዛሬ ደግሞ የሞጃ ልጅ .ስለዚህ አይፈረድባቸውም፡፡
‹‹…ግዴለም ማዘር እርሶ ይሂዱ እኔ ከፍቼ አስገባዋለሁ››አለቻቸው፡፡
‹‹እሺ ልጄ.ደህና ዋይ ..››.ብለው በራፍን ለቀውላት ወደፊት መራመድ ሲጀምሩ የእሳቸውን ቀልብ ምትማርክበት የሆነች ሸር ነገር ብልጭ አለችላት…ኪሷ ገባችና ድፍን ሁለት መቶ ብር አወጣች፡፡
‹‹ማዘር.. ››
‹‹አቤት ልጄ›› ባሉበት ቆሙና ፊታቸው ወደ እሷ አዞሩ..ሮጣ ሄደችና ተጠጋቻቸው.
.‹‹‹ይቅርታ ይቺን ሙዳይ ምፅዋት ውስጥ ያስገቡልኝና..ያሰበችው ይሳካላት ብለው ይፀሉልኝ፡፡››
ፊታቸው ሲፈካ በግልፅ ይታያታል…‹‹ልጄ ይሳካልሽ…. ተባረኪ… ወይ አንቺም እንደቃልዬ  ነሽ መሰለኝ..ለመሆኑ ስምሽ ማነው?››ሲሉ ጠየቋት፡፡
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

በፊት ፍቅር ማለት....?ብለው ሲጠይቋት በመራቀቅ እና በልበ ሙሉነት ትዘረዝር ነበር::አሁን ከዚህ ልጅ ጋር በአጋጣሚ ከተላተመች በኃላ ግን...ፍቅር ማለት ...?ብለው ሲጠይቋት መልሷ  ረጅም ዝምታ  ነው።እንደዛ ማድረጓ ፈልጋ አይደለም  …ከእሱ ጋር ከተጋራችው ስሜት አንፃር ፍቅርን ለመተንተን ብቁ የሆነ ሀሳቧን የሚመጥን ቃል  በከንፈራ ላይ ስለሌለ ነው።

በቀደም ሜቅዶኒያ በሄድ ቀን በጣም አሪፍ ሚባል ጊዜ ነበር ያሳለፉት…ከአባቱ ጋር አስተዋወቃት…አብረው ከሁለት ሰዓት በላይ አዛውንቶቸን በመንከባከብ የሚሰሩ የበጎ ስራ አገልግሎት ሰራዎችን  ሰሩ፡፡
ይሄ ተግባር  ለቃል  የዘወትር የእለተ እሁድ የግማሽ ቀን ተግባሩ ነው…ለልዩ ግን የመጀመሪያ ኤክስፒሪያንሶ ነበር..እና ከጠበቀችው በተቃራኒ እጅግ አስደሳችና ጭፈራ ቤት አምሽቶ ከመዝናናት በላይ በተሻለ ጥልቅ የሆነ ደስታ የሚሰጥ ተግባር ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡
ስራቸውን ጨርሰው በአባቱ ተመርቀው እና ተሰናብተው ከወጡ በኃላ መንገድ ላይ‹‹ምንም ነገረ ሳይከፈል ምንም ነገር ጥቅም ሳይገኝበት እንዲህ አይነት ፈታኝ ስራዎችን  መስራት የሚገርም ስብዕናን የሚጠይቅ  ነው››አለችው፡፡
‹‹ አይ በነፃ ይመስልሸል እንጄ በነፃ አይደለም…በዚህ ምድር ላይ ያደረግሽው ሁሉ ይመለሰልሻል.አሁን እነዚሀ የአረጋዊያንን ልብስ አጥበሽ በምርቃት ብቻ ተቀብለሽ ስትሄጂ በነፃ ያገለገልሽ መስሎሽ ይሆናል..ግን በሌላ መንገድ ታገኚዋለሽ…ለምሳሌ አሁን አይበለውና መኪናሽ ከሆነ መኪና ጋር ተጋጭታ አደጋ ደርሶብን ሆስፒታል ብንገባ   አንድ የማናውቀው ሰው ለሁለታችንም በናፃ ደም ለግሶን ከሞት ሊያተርፈን ይችላል፡፡ …ያደረግሽው በጎ ነገር ሁሉ ይፍጠንም ይዘግይም ይመለስልሻል…መጥፎውም ነገር እንደዛው›› እንደዛ ነበር ያላት፡፡
ያው እሷ በሰዓቱ ምንም እንኳን በንግግሩ ብትደመምም በትክክለኝነቱ ግን ሙሉ በሙሉ አላመነችበትም..ቢሆንም የሰማችው ግን በፅሞናና በመመሰጥ ነበር…ባለው ነገር ሙሉ እምነት ያልተሰማት ምክንያት ዕድሜያቸውን ሁሉ ክፍ ስራ እየሰሩ ግን ደግሞ በሰላም የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በዙሪያዋ ስለምታውቅ ነው፡፡ለቃል ግን እንዳዛ አላለችውም…፡፡ምን አልባት እንደዛ ብላው ቢሆን ‹‹በሰላም እየኖሩ መሆናቸውን በምን አወቅሽ…? ሰላም ማለት እኮ ትርጉሙ ሰፊ ነው..በህይወታቸው ደስተኛ ናቸው…?ጥሩና ሰላማዊ እንቅልፍ እየተኙ ነው…? አይነት ጥያቄዎችን በመጠየቅ በእጅ አዙር ይመልስላት እንደነበር እርግጠኛ ነበረች፡፡
ከዛን ከሰአት እንጦጦ ሄድ.. በየካፌውና ሬስቶራንቶቹ እየቀያየሩ ድንቁና አረንጓዴ  የሆነውን ወጣ ገባ መልካ ምድር እየጎበኙ ንፅህንና ነፋሻማውን አየር እየማጉ በደስታ ሲፈነጥዙ ዋሉና ማታ አንድ ሰዓት እቤቱ በራፍ ድረስ አድርሳው  ቅር እያላት ወደቤቷ ሄደች…፡፡
ከዛን ወዲህ ሁለት ቀን ተገናኝተው ሻይ ቡና ብለዋል…አሁን ግን ካየችው ሌላ ሁለት ቀን አለፋት ፡፡ናፍቆታል፡፡‹‹
‹‹አይገርምም ..አሁን ናፍቆኛል ስል መድህኔ ቢሰማ ምን ያህል ልቡ ይሰበራል?››ሳታስበው እራሱ ዝግንን አላት…፡፡ቢሆንም  ግን መናፈቋ የማይካድ ሀቅ ነው: አሁን በዚህ ምሽት እያደረገች ያለችው አልጋዋ ላይ እየተገላበጠች ስለእሱ ማሰላሰል ነው..ስለመድህኔ አይደለም…ስለቃል እንጂ ፡፡
‹‹አዎ እስኪ አይኑን ልየው›› አለችና ከመኝታዋ ተነስታ ላፕቶፖን ከተቀመጠበት አመጣች፡፡ ወደቦታዋ ተመልሳ ከፈትችው፡፡
እንዲህ አይነት ስራዎችን በተለያዩ ሰዎች ላይ እንደምትሰራ  የምታውቅ አንድ የትምህር ቤት ጓደኛዋ‹‹ ለምን ግን ደህንነት መስሪያ ቤት ሲርቪስን አታስገቢም፤አንቺ እኮ የተፈጠርሽው ሰላይ ለመሆን ነው፡፡ ብልሀቱንም፤ተንኮሉንም ማስመሰሉንም ተክነሽበታል››ትላት ነበር…፡፡በወቅቱ አስተያየቷን ብትቃወማትም አሁን ሳታስበው ግን እውነቷን ነው ብላ ማመን ጀምራለች፡፡
..ከእሱ መኝታ ቤት የቀበረችው ካሜራ ጋር የሚያገናኘውን ቁልፍ ተጭና እሱ ወደ መኝታ ቤቱ እስኪገባ መጠበቅ ጀመረች፡፡የፊት ለፊቱ ክፍል እንዳለ አውቃለች፡፡ ሙዚቃና አንዳንድ የሚንጋጉ ድምፅች  ከሚቀጠልው ክፍል ውስጥ መኖሩን ያሳብቃሉ…፡፡
መኝታ  ቤቱ ተከፈተ…ቃል ገባና በራፉን ዘጋው…፡፡ትኩረቷን ሰብስባ መከታተል ጀመረች፡፡ወደ ቁም ሳጥኑ ቀረበ፡፡ከፈተ.. ፡፡ቢጃማ አወጣ..፡፡
‹‹ውይ ልብሱን  ሊቀይር  ነው…፡፡››አለች..ግራገባት…ምን ታድርግ..?፡፡
‹‹ለጊዜው ቀይሮ እስኪጨርስ ላፕቶፑን ልዝጋው..ወይስ እኔ ከስሩ ዞር ልበል..?፡፡›› ውሳኔ ላይ ሳትደርስ ከላይ የለበሰውን ሸሚዝ አወለቀና በስነስርአት አጣጥፎ ጥግ ላይ ካለች ጠረጴዛ  ላይ አስቀመጠ..ሲሊፐሩን አወለቀና ባዶ እግሩ ምንጣፍ ላይ ቆመ፡፡ ሱሪውን መዥርጦ አወለቀ…ሰማያዊ ፓንት እየታያት ነው፡፡
‹‹..ወይ ምን እየሰራሁ ነው….?.ሱሪውን በተመሳሳይ አጣጥፎ  አስቀመጠ…፡፡
‹‹እንዴ ሌላ ነገር ሊያወልቅነው እንዴ?›› ስትል እግዜር ይስጠው አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀምጦት የነበረውን ፒጀማ አነሳና በየተራ ለበሰ…፡፡መሀል ወለል ምንጣፍ ላይ በጉልበቱ ተንበረከከ… …፡፡
‹‹እንዴ ምን እየሰራ ነው..?ስትል እጁን ወደፊቱ ዘረጋ….ከዛ ድምፅ አውጥቶ ከዚህ በፊት ሰምታው የማታውቀው አይነት አዲስ ፀሎት መፀለይ ጀመረ..‹‹ታድሎ የየትኛው ሀይማኖት ፀሎት ይሆን ..?ምን አልባት አንድ ቀን በደንብ ስንግባባ ጠይቀው ይሆናል..እናም አብሬውም ከጎኑ ተንበርክኬ እጆቹን በእጆቼ ይዤ እፀልይ ይሆናል፡፡››ስትል ተመኘችና ፀሎቱን በጥሞና መከታተል ጀመረች፡፡
///
የውበቶች ሁሉ ድምር ውበት...የሙዚቃዎች ሁሉ ጥቅል ዜማ....የብርሀን ሁሉ  ብርሀን ...የሠው ልጆች ሁሉ ጥምር እስትንፍስ ...እሱ እግዚያብሄር ነው።መላእክቶች ቅርንጫፍ ላይ የበቀሉ ወረቃማ ቅጠሎች ናቸው። ፀሀይ ከልብ አንድ ጥግ መንጭታ  ለአጥናፍ አለሙ ብርሀንና ሙቀት የምትለግስ  የህይወት ምንጭ ነች።  ጨረቃ ከአይኖቹ ብሌን ጫፍ የምትገኝ  የውበት ፈርጥ ነች..ከዋክብቱ ግንባሩ ላይ ልክ እንደፀጉር የተበተኑ  ድንቆች ናቸው ....እኛ የሰው ልጆች  የአእምሮው ህብረሰረሰር ቅንጣት ህዋስ ነን።የእኛ ኢምንት ሀሳቦቻች  ከሱ  እልቆ መሳፍርት ሀሳብ  እየተሸረፍ ሚበተኑ ህልሞቻችን ናቸው። አፅናፍ አለም በእጅ መዳፍ ላይ የተበተኑ የሚነበብና የሚተነተኑ  መስመሮች ናቸው። የምድር ደኖችና ተክሎች  እግሮቹ ላይ የበቀሉ ፀጉሮች ናቸው።  የፍጥረታት ነፍስ ከትንፍሹ የተሸረፈች  የህይወት እርግብግቢት ነች።እግዚያብሄር ሁሉም እና አጠቃላዪ ማለት ነው። ጥልቀቱ ወሰን አልባ ርዝመት የማይደረስበት ...ልኩ ይሄን ያህል ነው የማይባል ...  የነገሮች ሁሉ የመጨረሻው ቅንጣት ኢነርጂ ... በጊዜ የማይገመት በቦታ የማይታጠር   ኤልሻዳይ አምላክ ነው።
/
ከዛ ፀሎቱን እንደጨረሰ ትንፋሽ በጥልቀት ወደውስጥ እየሳበ ከዛ አምቆ ይቆይና ወደውጭ ይለቀዋል…መልሶ ወደውስጥ ይስብና ወደውጭ ይለቀዋል.. ያለመታከትና መሰልቸት ለአስር ያህል ደቂቃ እንደዛ ካደረገ በኃላ...ባለበት ያለምንም እንቅስቃሴ አይኖቹን ጨፍኖ ፀጥ አለ…፡
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና ተያይዘን ወጡ ...

‹‹እሺ ቦታ ትመርጣላችሁ ወይስ እኔ ልምረጥ?››መድህኔ ነው ወደ መኪና ከመግባታቸው በፊት የጠየቀው፡፡

"ቦታውን አንተ ምረጥ ..ግን ጭፈራ ቤት መሆን አለበት"አለችው ልዩ፡

"አሪፍ ነዋ"አለ ፊቱ በርቶ..ከዛ ወደ መኪናው መራመድ ጀመረ...ተከተሉኝ፡፡

እስከ ለሊቱ ሰባት ሰዓት ቀወጡት ..በዋነኝነት ተዋናዬቹ ሶስቱ ነበሩ፡፡ ከመሀከላቸው ቃል መጠጥ አይጠጣም .... ውሀ ይዞ እነሱን መከታተል ነበር ዋና ስራው፡፡ሲጨፍሩ ያየቸዋል... ሲንገዳገዱ ይደግፋቸዋል... ፡፡ እነሱም በእሱ ተማምነን ዘና ብለን እየቀወጡ ነው ምሽቱን በፈንጠዝያ ያሳለፉት።ለነገሩ ልዩም በአብዛኛው ከእሱ ተለጥፋ ነው ያመሸችው፡፡

‹‹ሚስትህ ባሌን እኳ አንሳፋፈችው››አለችው፡፡

‹‹ምነው ቀናሽ እንዴ?››

‹‹ለምን አልቀና እኔ እንደአንተ ደመበራድ አይደለሁም››

እና ምን ይሻላል

‹‹ያው ምን ይሻላል .መጨረሻቸውን ማለት ነው››

እስከወዲያኛው ብትቀማሽስ››

ትሞክረዋ›

<<ምን ታደርጊያለሽ››
እሾክን በሾክ ነዋ…እሷ እኮ ባል አላት›› አለችው…ፉከራዋ አሳቀው፡፡

መድህኔና ጊፍቲ ስለእነሱ ሹክሹክታ ደንታም ሳይሰጣቸው በጭፈራቸው ተመስጠዋል፡፡ ሁለቱም አደገኛ ጨፋሪዎች ናቸው ...ደግሞ በሚገርም ጥምረት ተግባብተው በአየር ላይ የመብረር ያህል አቅላቸውን ስተው ተጣብቀው ሲደንሱ ላያቸወ ከአየን ያውጣችው ያስብላሉ ፡፡ አሁን እዚህ ጭፈራ ቤት ያሉ ሁሉ ልዩና ቃልን ቀዝቃዛ ፍቅረኞች ….ጊፍቲና መድህኔ ደግሞ የበለጡ የሚያምሩና የሚግባብ የጋለ ፍቅር ላይ ያሉ ጥንዶች እንደሆኑ ምሎ ሊናገር ይችላል። ‹‹ግን በትክክልም መሆን ያለበት እንደዚህ ነው።አዎ መድህኔ እኮ በጣም ቆንጆ ፤ዘናጭ፤ ሀብታምና ጥሩ ስነምግባር ያለው ሰው ነው...እና ጊፍቲ መድህኔ ፍቅረኛዋ ቢሆን በጣም ጥሩና የተመቸ ኑሮ ትኖራለች...አዎ እሱን ብታገኝ በጣም እድለኛ ነች።›ስትል አብሰለሰልች፡፡

ግን መድህኔ እንደምትይው ሁሉን የሚያሟላ ተመራጭ ወንድ ከሆነ አንቺስ ለምን እሱን ለቀሽ ቃልን ተመኘሽ?ብሎ የሚጠይቃት ሰው ካለ ምን አይነት መልስ ልትመልስ እንደምትችል አታውቅም..

.ስለቃል የሚሰማት ስሜት ጥልቅና መንፈሳዊ ነው"..ልክ የመድህኔን ኳሊቲ በቀላሉ ዘርዝራ እንደተናገረችው የቃልን እንደዛ ማድረግ አትችልም...እና ደግሞ የቃልን ጉዳይ ባይሆንባት በማንም ሌላ ወንድ መድህኔን መቀየር አትፈልግም ነበር...እና ደግሞ ማንም ሌላ ሴት መድህኔን ልትቀማት ሞክራ ቢሆን ኖሮ አንገቷን ቀንጥሳ ነበር የምትጥላት።ስለ ቃል ሚሰማት ስሜት ይሄን ያህል ውስብስብ ነው

ሰባት ሰዓት ስላለፈ እዛው ሲጨፍሩበት ካመሹበት ሆቴል አንድ ባለ ሁለት አላጋ ክፍል ተያዘና እየተጓተቱ ሄድን ፡፡እውነት ለመናገር ብክት እስኪሉ ሰክረዋል.... መኝታ ቤት እንደገቡ ብርድ ልብስ ገልጦ ከውስጥ የገባ የለም...ልዩና መድህኔ አንድ አልጋ ላይ ቃልና ጊፍቲ አንድ ላይ ተመሳቅለው ተኙ። ልዩ ከጎኖ እጮኛዋን መድህኔ ሰውነቷ ላይ ተለጠፋ የተኛች ቢሆንም ነፍሷ ግን ቃል እቅፍ ውስጥ ነበር ተሸጉጣ ያደረችው።
///
ጥዋት አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ከአንቅልፋቸው ተነስተው ሁሉም ለብሰው ያደሩትን የተጨማዳደ ልበሳቸውን በተቻለ መጠን አስተካከሉና ወደሬስቶራንት ጎራ ብለው ፤አፒታይታቸው በፈቀደላቸው መጠን ቁርስ በልተው በማጠናቅ ሆቴሉን ለቀው ለመውጣት ዝግጁ ሆኑ ከዛ ልዩ ጊፍቲን ቢሮዋ ድረሰ ሸኝታት ወደትምህርት ቤት እንድትሄድ በተመሳሳይ ደግሞ መድህኔ ቃልን መስሪያ ቤቱ ድረስ አድርሶት ወደስራው ሊሄድ ድልድል አወጡ፡፡ልዩ እንዲሆን የፈለገችው ተቃራኒውን ነበር...እሷ ቃልን እንድትሸኘው መድህኔ ደግሞ ይህቺን መዥገር ነገር እንዲያደርሳት… በዛውም ሁለቱ ስለማታው የሰመረ የዳንስ ጥምረታቸው እያወሩና ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ እንዲሄዱ ፈልጋ ነበር ….ግን እንዴት ብላ ተቃውሞ ታቅርብ …?ሳትወድ በግድ በድልድሉ ተስማማችና ደስተኛ እንደሆነች ለማስመሰል እየጣረች ጊፍቲን አሳፍራ ወደቢሮዋ ጉዞ ጀመረች…ለረጂም ደቂቃ ምንም አልተነጋገሩም…..ጊፍቲ ነበረች ከዝምታዋ ያነቃቻኝ፡፡
‹‹ምነው እኔን ጥለሽ ጭልጥ አልሽ .?››
ድንገት አፏ ላይ የመጣላትን መልስ መለሰችላት‹‹ስለማታው አስደሳች ምሽት እያሰብኩ ነበር› …እንደዛ ያለችው. እውነት ስላለችው ነገር እያሰበችበት ስለነበር ሳይሆን ሰለማታው ቆይታቸው ምን እንደተሰማት ለመገምገም እንዲረዳት ነው፡፡
‹‹ውይ ብታይ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል...እንዲህ አይነት ፍንጥዝጥዝ ያለ ምሽት ካሳልፍኩ ረጂም ጊዜ ሆኖኝ ነበር.በጣም አመሰግናለሁ›› አለች ጊፍቲ…
ልዩም‹‹አሀ አንዳሰብኩት በጣም ደስተኛ ነበረች ማለት ነው?››ስትል በውስጧ አሰበቸና ይበልጥ ዝርዝሩን ለመረዳት ንግግሯን ቀጠለች ‹‹ደግሞ በጣም ደናሽ ነሽ›ስትል የአድናቆት ቃል ሰነዘረች፡፡
‹‹አዎ ዳንስና ጭፈራ በጣም ወዳለሁ..ግን ባልሽን ጫፍ ላይ አልደርስም…በስመአብ አጥንት ያለው እኮ አይመስልም››
ጊፍቲ በአንድ ቀን ቆይታ ለመድሀኔ ያደረባት አድናቆቶ ካሰበችው በላይ የተጋነነ ሆኖ ነው ያገኘችው…እርግጥ መድሀኔ ሁሉም የሚያወራለት ጨፋሪ እንደሆነ እራሷም ልዩ ታውቃለች…ጊፍቲ በምታወራለት ልክ ግን ሌላ ሰው ሲያደንቀው ሰምታ አታውቅም..እሷ ያው እንደቃል የቀዘቀዘች ባትሆንም ለጭፈራ ያን ያህል ስለሆነች በእሷ ልክ የመድሀኔን ችሎታ ባይታያት አይፈረድባትም፡ስለዚህ ይሄ መደነቋ ሳይበርድ ልትጠቀምበት ይገባል ብላ አሰበች…በጣም ፈጣን የሆነ እቅድ በእምሮዋ ተሰነቀረ፡፡
‹‹ውይ ይቅርታ…አንድ ነገር እያሰብኩ ነበር…ከመድህኔ ጋር ሳምንት ኩሪፍቱ ለመሄድ ቀጠሮ ነበረን፤ በእኛ እስፖንሰርነት ለምን አንቺና ቃል አትቀላቀሉንም››
ከተማ ወጥቶ የመዝናናት ምንም አይነት ዕቅድ የላቸውም ….ግን እሷ ከተስማማች መድህኔን ከከተማ ወጥቶ መዝናናት እንደምትፈልግ መናገር ብቻ ነው የሚጠበቅባት….ምንም አይነት ወሳኝ የስራ ቃጠሮ ይኑረው ወይም ሌላ ፕሮግራም ሁሉንም ጣጥሎ ፍላጎቷን እንደሚያሞላላት እርግጠኛ ነች…ለዛ ነው በልቧ ሙሉነት የግብዣውን ሀሳብ ያቀረበችላት፡፡
‹‹ወይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…?ግን ቃል የሚመቸው አይመስለኝም….መስሪያ ቤቱ ለአምስት ቀን ፊልድ ክፍለሀገር ሊለከው ነው…ነገ ክፍለሀገር ይሄዳል..››አለቻት፡፡
ልዩ በጊፍቲ መልስ ደስ አለት ፡፡ደስ ያለት ለአምስት ቀን ሙሉ ቃልን ላታየው ባለመቻሏ አይደለም…ግን በጉዞችን የቃል አለመኖር ጥሩ ሆኖ ነው ያገኘችሁት… ጊፍቲን ከመድህኔ ጋር ይበልጥ እንዲቀራረብ ለማድረግ አሪፍ እድል ይሆናል ብላ ስላሰበች ነው፡፡
‹‹ታዲያ ለምን አንቺ አትቀላቀይንም ?..በሌላ ዙር ደግሞ ቃልን ጨምረን ተሟልተን እንሄዳለን››
‹‹ተይ ባክሽ..ብቻችሁን ብታሳልፉ ይሻላል?፡፡››መግደርደር መሆኑን በደንብ በሚያሳብቅ ፈራ ተባ ባለ ንግግር መለሰችላት፡
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሠላሳ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ቃል ቤት የተፈጠረው ድራማ ወር አልፎታል….በዚህ የጊዜ ክፍት ውስጥ መአት ነገሮች ተከስተዋል.ልዩ ትምህርቷን ተመርቃ ዲገግሪዋን ይዛለች…በምረቃት ፕሮግራሟ ላይ ቃል መድሀኔና ጊፍቲም ጭምር ተገኝተው ደስታዋ ተካፋይ ሆነዋል.እርግጥ ነገሩ ቀላል አልነበረም፤ በተለይ የልዩ እናት መድሀኔን ዝግጅቱ ላይ ሲመለከቱት ንዴታቸውን መቆጣጠር አቅቶቸው እንዴት ተደርጎ በማለት ሂድልኝ ሊሉት ፈልገው ነበር ፤በልዩ ግሳፄ ነው እንደምንም እራሳቸውን ተቆጣጥረው ሊያልፉት የቻሉት…፡፡በወቅቱ ልዩ ቃልን ከእናቷ ጋር ማስተዋወቅ ስለቻለች ከፍተኛ ደስታ ተስምቶታል…፡፡ሌላው ልዩና ቃል አንድ ላይ በመተጋገዝ    መድህኔ እና ጊፍቲ አብረው እንዲቀጥሉ ማድረግ ችለዋል፡፡መድሀኔም እንደምንም እቤተሰቦቹን በማሳመን የጊፍቲ ሆድ ከመግፋቱ በፊት በቅርብ ለመጋባት ወስነው ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ለእነልዩ ነግረዋቸዋል፡፡እንደውም የጊፍቲ አንደኛ ሚዜ ልዩ የመድሀኔ ደግሞ ቃል ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ያው ጓደኝነታቸውም ቃል በሚፈልገው መሰረት እንደድሮ ቀጥሏል‹‹..አሁን ይሄ ታሪክ ሙሉ ሊሆን የቀረው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡የእኔና የቃል ጉዳይ..እሱንም ጠብቁኝ በቅርብ ይሆናል….እስከአሁን እኔ አስቤ ያላሳከሁት ነገር የለም፡፡››ስትል ዛተች
ቀኑ ቅዳሜ  ነው...ከቃል  ጋር   ለመገናኘት ተቀጣጥረው ነበር።
እሱ ወደሚገኝበት ቦታ እየነዳች ስለእሱ በማሰብ ትለፈልፋለች…ብቻዋን ስትለፈልፍ ለሚመለካተታ እግረኛ ከኃላ የመኪናው ወንበር ላይ  ተኝቶ የሚያዳምጣት ሰው አለ ብሎ ነው የሚያስበው
‹‹ቆንጆ ነው።ቆንጆ የሚጠላ ሰው የለም። ግን ከስጋው ቁንጅና ይልቅ በነፍስ ቁንጅና ነው ቀድሜ እጅ ሰጠሁት ።እርግጥ የነፍስ ውበትን ልክ እንደስጋ ውበት በቀላሉ  ለመለየት አይቻልም። ድብቅና ስውር ነው።መረጋጋትና በአስተውሎት መገምገምን ይጠይቃል። ውስጣዊ ስለሆነ በውስጣዊ አይን ብቻ ነው ሊታይና  ሊረጋገጥ የሚችለው።እሱን በተመለከተ ግን የውጭ ውበቱን ዘግይቼ ና ተረጋግቼ ነው ያየሁት።ቀድሞ ውስጤ የሠረገው የነፍሱ ውበት ነው። ያሽመደመደኝ ሰባአዊነቱና የተሞረደ አስተሳሰብ ነው።እንደእሱ አይነት ሰው ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም።መኖሩን ካወቅኩም በኃላ የእኔ ሰው መሆን አለበት ብዬ ቀን ከሌት ከመቃዠት ውጭ ሌላ ምንም አይነት የስጋም ሆነ የነፍስ ስራ የለኝም፡፡ ››
የተቃጠሩበት ቦታ ለመድረስ ከአንድ ፌርማታ በታች ሲቀራት መኪናዋ ድንገት  ተበለሸባት፡፡እቤት ደወለችና ነገረቻቸው..ሌላ መኪና አምጥተው እስኪቀይሩላት መኪዋን ቆላለፈችና .በእግር ቃል ወደሚገኝበት ቦታ በእግሯ ወክ በማድረግ ሄዳ አገኘችው‹‹ ምሳ  ልጋብዝህ ብላው እዛው አካባቢ አንድ ሬስቶራንት ይዛው ገባች..።እሷ ቁርስ ስላልበላች በጣም እርቧታል..እሱ ይራበው አይራበው አታውቅም።ግን ከረሀቡም በላይ የእሷ ዋና አላማ ከእሱ ጋር የምታሳልፈው ጊዜ በሰበብ አስባብ ማስረዘም ነው።
ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጠዋል ..የየምርጫችውን አዘዙ ።  ሰዓቱ ስድስት ሰዓት ያልሞላ ቢሆንም በሬስቶራንቱ ውስጥ ያሉት ተስተናጋጆች እነሱ ብቻ አይደለሉም።ቢያንስ 30 ፐርሰንት የሚሆነው ወንበር በጥንድም ነጠላም ሆነው በተቀመጡ ሰዎች ተይዞል።
ከተወሰነ ጥበቃ በኃላ ምግባቸው ቀርበ፡፡
እሷ ለመገብ እጇን ወደምግቧ በመዘርጋ ላይ እያለች ቃል  አንገቱን ለፀሎት ሲያቀረቅር አየችና በእፍረት በአየር ላይ ያንከረፈችውን እጆን ቀስ ብላ ወደሃላ ሳበችውና እሷም በተመሳሳይ አንገቷን ደፋች፡፡
እሱ ፀሎቱን ለእሷ በሚሰማ ነገር ግን ሌሎችን በማይረብሽ የተለሳለሰ ድምፅ ቀጠለ
‹‹እነዚህን የምግብ ግብአቶች ዘርተው ያበቀሉ ተንከባክበው ለፍሬ ያበቁ የገበሬ እጆች የተባረኩ ይሁኑ።የተመረቱትን ግብአቶች ከገበሬው በመግዛት ያለንበት ድረስ በማምጣት የሸጡልን ነጋዴዎች ምስጋናችን ይድረሳቸው።ይሄን እንጀራ ለማስገኘት ጤፍን ወደ ድቄትነት የቀየሩልን የወፍጮ ቤት ባለቤቶችና ሰራተኞች ባሉበት ምስጋናችን ይድረሳቸው ፤ ድቄቱን አብኩታና  ጋግራ ይሄን የመሠለ ማራኪ እንጀራ እንድንቆርስ ላደረገችን እንጀራ ጋጋሪዎ እመቤት እናመሠግናለን።ይሄንን መአዳችን ላይ የቀረበልንን ሚስጥራዊ ውሀ  እንድናገኝ  ኃላፊነታቸውን በበጎነት ለተወጡ የውሀ ልማት ባለሞያዎች እናመሠግናለን።ይሄንን ምግብ በግሩም ሁኔታ እንዲበስል የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲኖር ላደረጋችሁልን የማብራት ሀይል ሰራተኛች እናመሠግናለን።በቀን ውስጥ ስለተደረገልን ሁሉ አናመሰግናለን፡፡››
ብሎ የተለመደ ገራሚ አይነት ፀሎቱን ካንበለበለ በኃላ የቀረበላቸውን መመገብ ጀመሩ

አልፎ አልፎ እያወሩ በመሀልም እየተጓራረሱ በመብላት ላይ ናቸው ።የእሷ አይኖቸ ግን በመሀል ሳትፈልግ ከጎናችው አንድ ወንበር ተሻግሮ ከሴት ጋር ካለው ጎልማሳ ሰው ላይ ይንከራተት ጀመር ‹‹..አሁን ፊት ለፊቴ ያለው ሰው ቃል ባይሆን  ግንባሬን ብሎ በተቀመጥኩበት ጎልቶኝ ይሄድ ነበር?››ስትል አሰበች፡፡
ቢሆንም ግን እራሷን መግታት አልቻለችም፡፡እርግጥ ችግሯ ሰውዬው አይደለም  …፡፡ከጣቱ ወርቅ አውልቆ ኪስ ወስጥ ሲከት አይታ ነው...፡፡ሰውዬው እንደዛ  ያደረገው አብራው ያለችው  ሴት ወደ ጠረጰዛው መጥታ ከፊት ለፊቱ ከመቀመጧ በፊት ነው።ወርቁን ከእጣቱ በችኮላ መንጭቆ በማውለቅ ጃኬት ኪስ ውስጥ  እንደነገሩ    ሻጥ ስላደረገው  በተንቀሳቀሰ ቁጥር  አይኗ ላይ በማብረቅረቅ  እየተፈታተናት ስለሆነ ነው...አስሬ   አይኗ ወደእሱ አየቀባዠረ  የምትቅበጠበጠው።ለጥንዶቹ ምግብ ሲቀርብላቸው ሰውዬው  ሊታጠብ ቀድሞ  ከተቀመጠበት ተነሳና ወደ መታጠቢያ ቤት አመራ..
ልዩም ምንም ሳትናገር ድንገት ከተቀመጠችበት ተነሳችና ምግብ ስትበላበት የነበረ እጇን እንዳንከረፈፈች ከኃላው ተከተለችው... መታጠቢያ ቤት ገብቶ እጅን ሲታጠብ ከአጠገብ ያለው መታጠቢያ ስር ቆመችና ለመታጠብ እጇን ዘረጋች...ታጥቦ ጨርሷ ለመውጣት ሲራመድ እሷም መታጠቧን አቁማ ለመዞር የፈለገች መስላ ተጋጨችው...ቀድሞ ይቅርታ ጠየቃት‹‹...ችግር የለውም› ብላ አሳለፈችው...አንድ አስር እርምጃ ከተራመደ በኃላ ጠበቃችና ከኃላ ተከተለችው።ስትደርስ ወንበሩ ላይ ተደላድሎ ተቀምጦ አብራው ያላቸውን ሴት ለማጉረስ እጅን እየዘረጋ ነበር ...በፊት ለፊታቸው አልፋ ወደ ወንበሯ ሄደችና  ተቀመጠች...ምግብና ሳትጠግብ ያቆመች ቢሆንም መልሳ መብላት መጀመር አልቻለችም ..እጇን ከታጠበቸ በኃላ እንዴት ብላ እጇን ትዘርጋ?

ቃል በዝምታ አቀርቅሮ ምግብን እየተመገበ ነው...ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ሳያያት"ምነው ብይ እንጂ ››አላት፡
"አረ ጠገብኩ እኳ ...ታጥቤ ስመጣ እያየሀኝ"
"ከጠገብሽ ጥሩ ነው...እስከአሁን በልተሽ የጠገብሽው ለራስሽ ነው..ቀጥሎ ደግሞ ለእኔ ብይልኝ"አላት፡፡
አባባሉ ግራ አጋባት"እውነትህን ነው?"
"አዎ እውነቴን ነው"አለ ኮስተር ብሎ።
"እንዲህ ብለኸኝማ  እምቢ አልልህም"አለችና እንደአዲስ መብላት ጀመረች።
ምግባቸውን ጨርሰው፤ እጃቸውን ታጥበው ፤  ብና አዘው እየጠጡ ነው። ምንም እያወራት አይደለም ።ሁለቱም የራሳቸው ሀሳብ እያመነዠጉ ነው።ከጎናቸው ያሉት ጥንዶች የሚበሉትን ጨረሱና ለመታጠብ ሴቲቱ ቀድማ ወደመታጠቢያ ቤት ሄደች ...እሱ ቁጭ ካለበት ሳይነሳ ፊቱ ያለውን የቢራ ጠርሙስ እያነሳ እየተጎነጨ ነው...
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

የድባለ አባት ኬድሮንን እንዳያት.. እጁን እንዳንከረፈፈ ከተቀመጠበት ተነሳና‹‹ኬድሮን ምን ተፈጠረ…?ምን ሆንሽ ?›› እያለ ወንበሩን ለቆ ወደእሷ ቀረበ፡፡

ሴትዬዋ መለፍለፏን አላቆመችም….‹‹ምንድነች ማነች…? ታውቃታለህ እንዴ…?ነው ሚስትህ ነች የላከቻት..?››

‹‹አይ  አይደለም…ተረጋጊ የጎረቤት ልጅ ነች.?››

‹ትሁና ..ነይ ውጪልኝ…ቤቴን ማንም እንዲደፍረው አልፈልግም …ከፈለክ ውጭ አናግራት ›› ብላ ክንዷን ይዛ ልትጎትታት ብትሞክርም ንቅንቅ ልታደርጋት አልቻለችም…ሴትዮዋ ግራ ግብቷት እራሷን  አጠንክራ ደግመኛ ሞከረች….ግዙፍ የዋርካ ግንድ የማነቃነቅ  አይነት ነው የሆነባት፡፡
‹‹ምንድነች ይህቺ ጉድ …ውስጧ  ጋንኤል አለ እንዴ?››ስትል የድብአለ አባት በቆመበት ደንዝዞ ሚገባበት ጠፍቶት ኩምሽሽ አለ...የድብአለ  አባት በእነኬድሮን ሰፈር ኬድሮን ከመወለዷ  በፊት የገባ በመሆኑ ስለእሷ ታሪክና ሀሚቶችንም ጨምሮ በዝርዝር ስለሚያውቅ ነው የተጨነቀው…ሴትዬዋ ደግሞ ገና ወደ ደሎ ከተማ ከገባች 6 ወርም ያላለፋት በመሆኑ ስለ እንደዚህ አይነት ታሪክ ምንም ምታውቀው  ነገር የላትም፡፡

‹‹ጋሼ  ለአዲሷ ሚስትህ ስለእኔ አልነግርካትም እንዴ?፡፡››

ሰውዬው ልክ በጣም ሚፈራውን ባለስልጣን እንደሚያናግር ሰው አንገቱን ደፍቶ ዝም አለ፡፡
በጥርጥሬ ልጅቷን አትኩራ እየተመለከተች‹‹ምንድነው ያልነገርከኝ…?ነው ልጅህ ነች…?›ስትል ጠየቀች ፡፡

‹‹አይ የእሱ ልጅ አይደለሁም…እናቴ በሬዱ ትባላለች፡፡ በሬዱ ዲንቃ….አባቴ ደግሞ ዳቢሎሰ ነው…እና ለአዲሱ ባልሽ መልእክት ለመናገር ነው የመጣሁት….ሚስትህ ልጆቾን ይዛ ወደሀገሯ ልትሄድ ነው..እኔ ደግሞ ድባአለ  ጓደኛዬ ስለሆነ እንዲሄድ አልፈልግም…ማለቴ እውነቱን ለመናገር  እኔ እንኳን ቢሄድ ብዙ ግድ የለኝም.. ግን እሱ እኔን ጥሎ መሄድ እንደማይፈልግ እያለቀሰ ነው የነገረኝ…እውነቱን መሆኑን ደግሞ አይኖቹን አይቼ አምኜዋለሁ፡፡ ስለዚህ እንዲሄዱ አልፈልግም…እንዳይሄዱ ደግሞ አንተ እሷን ይቅርታ ጠይቀህ ወደልጆችህ ትመለሳለህ፡

‹‹አንቺ ምን አይነት ጉድ ነሽ…በዚህ  ዕድሜሽ ስለ እንዲዚህ አይነት ነገሮች  ምኑን አውቀሽ ነው ምትዘባርቂው…ይሄኔ ቤተሰቦችሽ ጠፍተሸባቸው እየፈለጉሽ ነው…በይ አሁን ቤቴን ለቀሽ ወደቤትሽ ሂጂ››ሴትዬዋ ተንዘረዘረች …

የድባአለ  አባት ምንም ለመናገር አልደፈረም፡፡

ኬድሮን መናገር ጀመረች..‹‹አንዳልሺው እሄዳለሁ....አሁን ሁለታችሁም ዘና ብላችሁ የጀመራችሁትን እራት ብሉ… ከዛ ስትተኙ ያልኩትን  ባተፈፅሙ ምን እንደሚያጋጥማችሁ ቀድመ ማስጠንቂያ እንዲያሳያችሁ ለዳቢሎሱ አባቴ አሁን ነግሬዋለሁ…እና ምርጫውን  የእናንተ ነው…እርግጠኛ ነኝ የዱብአለ አባት ነገ ለእራት ቆቅ  ወይም ጅግራ አድኜ አመጣና ወደልጆችህ መመለስህን በማስመልከት አብረን እራት እንበላለን….አንቺም ሌላ ሚስት የሌለው ባል እንደምታገኚ እምነቴ ነው.››ብላ ፊቷን አዙራ ስትወጣ ሰውየው ከደነዘበት እንደመባነን ብሎ ‹‹ኬድሮን ልሸኝሽ ?መሽቷል እኮ›አላት፡፡

‹‹አይ ጋሼ እንደማልፈራ ታውቃለህ አይደል? ›

‹‹አዎ እሱስ አውነትሽን ነው፤ደህና እደሪ››ብሎ በቆመበት ሸኛት፡፡
እቤቱን ለቃ እንደወጣች ሴትዬዋ ተንደርድራ በራፏን ከቀረቀረች በኃላ ወደውሽማዋ  ዞራ

‹‹ምን ጉድ ነው ?ማነች ይህቺ ልጅ….?ደግሞ የዳቢሎስ ልጅ ነኝ ትበለኝ እንዴ …?በእሷ  ቤት ማስፈራራቷ  ነው?ወላጆቾ በዳቢሎስ እያሰፈራሩ ነው ያሳደጓት መሰለኝ?››

‹‹እውነቷን ነው…እናቷ ከዳቢሎስ ነው የፀነሰቻት ተብሎ ይወራል›› ብሎ  በመጀመር ሙሉ ታሪኳን ከመጀመሪያው አንስቶ በሚያውቀውና በሰማው መጠን ብትንትን አድርጎ አስረዳት….ሴትዬዋ ይበልጥ በነገራት ቁጥር ይበልጥ በፍራቻ እየተንዘፈዘፈችና እተንቀጠቀጠች ነበር..

‹‹ምን አይነት ጣጣ ውስጥ ነው የገባሁት..?እና ምን ይሻለናል…?››
‹‹ለማንኛውም አሁን እንተኛና..  ነገ የሚሆነውን አይተን እንወስናለን››
አልተከተራከረችውም…እንደቅዱሙ ጩሀቱም ወኔውም ከውስጧ ተሰልቦ ባዶ ሆኗል፡፡ ሹክክ ብላ ወደ አልጋው ሄደች፡፡ እሱም ተከተላትና እንደወትሯቸው ተቃቅፈው ግን ደግሞ በዝምታ ተኙ፡፡

ኬድሮን ቤታቸውን ለቃ ወደቤቷ በድቅድቅ ጨላማው ውስጥ ሰንጥቃ በምታሄደበት ጊዜ‹‹የት እንደሆንክ ማላውቀው አባቴ እንግዲህ ይሄንን ጉዳይ ቀለል ባለ መንገድ እድጨርሰው እርዳኝ….ማለት አሪፍ የሆነ አሳማኝ ህልም እንዲያዩ  አድርግልኝ›.ካልሆነ ግን ታውቃለህ ሌላ ዘዴ እጠቀማለሁ…በዛ ደግሞ የሆነ ሰው ይጎዳል...እኔ እንኳን ማንም ቢጎዳ ብዙም ደንታ እንደሌለኝ ታውቃለህ ግን እናቴ ትከፋብኛለች...ለእሷ ስል ነው ደግና ጥሩ ሰው ለመሆን የምሞክረው እና አግዘኝ›በማለት መልእክት ይሁን ፀሎት ባለየለት ንግግር ነበር መልኩንም ሆነ ማንነቱን በቅጡ የማታውቀው አባቷን ፌበር እየጠየቀች  ወደቤቷ  የተመለሰችው፡፡ኬድሮን ብዙ ጊዜ ስለአባቷ ከሰው ጋር ስታወራ ዳቢሎስ ነው አባቴ ብላ በድፍረት የምትናገረው የእውነት እንደዛ ብላ ስለምታምን ሳይሆን እንሱ እንደዛ ብለው ስለሚያሟትና ከአንደበቷ አውጥታ ስታረጋግጥላቸው በፊታቸው ላይ የምታየውን ድንጋጤና በአካላቸው ላይ የምትመለከተው መንቀጥቀጥ ስለሚያረካት እና በእነሱ ላይ የበለጠ ኃይልና የበለጠ የበላይነት ስለሚያጎናፅፋት ነው፡፡

ይቀጥላል
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

የድባአለ አባትንና አዲሱ ሚስቱ ግን ከለሌቱ ስምንት ሰዓት  አልጋቸውን ለቀው ወርደው የቤቱ ወለል ላይ ጎን ለጎን በላብ እንደተዘፈቁ ቁጭ ብለው በመነጋገር በጥዋት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚለያዩና ሰውዬውም ወደሚስቱ መመለስ እንዳለበት ወስነው ነበር እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሱት… ኬድሮን ማታ ባስፈራራቻቸው ላይ ተመስርተው ብቻ ሳይሆን እሷ እንዳለችው ሁለቱም ባዩት ህልም የተነሳ ነው..የሚገርመው ደግሞ ሁለቱም ያዩት ህልም በጣም አስፈሪ እና ሰቅጣጭ  መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምንም ልዩነት የሌለው ከመጀመሪያው እሰከመዝጊያው ተመሳሳይና አንድ አይነት በመሆኑ ነው፡፡

ጥዋት ሁለት ሰዓት ሳይሞላ ይዞ የወጣውን ሻንጣ እንዳንጠለጠለ ወደቀድሞ ቤቱ ተመልሶ ሚስቱ እግር ስር ተደፋ፤እሷም ሆነች ልጆቹ በእልልታ ተቀበሉት….ኬድሮምም ወደተለመደ እረኝነቷ  ከመሄዷ  በፊት ከድባለ  እናት  እቃ የገዙት የጎረቤት ሴቶች ጋር በየቤታቸው  በመዞር.. ሰውየው ስለተመለሰ የገዛችሁትን እቃ በስጦታ መልክ መልሳችሁ እንደምታስደስቷት አምናለሁ›› በማለት በአዋጅ መልክ ለሁሉም በመናገር ነበር ወደሰራዋ የተሰማራችው...እንዳላቸውም ማታ ስትመለስ ሁለት ጅግራ እንደተሸከመች እነከድር  ቤት ስትደርስ እቤቱ ትናንት ከነበረው በተቃራኒው በደስታ ደምቆና በሳቅ ፍክቶ ነበር የጠበቃት..
ደጃፉን አልፋ‹‹ ቤቶች›› የሚል ድምፅ እንዳሰማች ነበር.ከድር ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ በመብር የተጠመጠመባት እናትየውም በደስታና በስስት አቅፋ እየወዘወዘቻት ሞጨሞጨቻት ..ከዛ ቤቱ ሰላም መመለሱን አረጋግጣ…ከቤቱ የተሸጡ እቃ አንድም ሳይቀር መመለሱን አይታ ጀግራውን ለደስታቸው ማድመቂያ ይሆን ዘንድ አስረክባ ወደቤቷ ስትመለስ  ድባለ  ከኃላዋ ተከትሎ አስቆማት

‹‹እሺ አሁን ደግሞ ምን ፈለክ?››

‹‹አንድ ነገር ልነግርሽ ነው››

‹‹እኮ ቶሎ ንገረኝና ወደቤቴ ልግባበት››

‹‹ሳድግ  አገባሻለሁ፡፡››

‹‹ማግባት ማለት? አንደዚህ እንደአባትህና እናትህ?››

‹‹አዎ ምነው?››

‹‹ቲሽ ምነው ትላለህ እንዴ…?››

‹‹ልጇች አስታቅፈኸኝ ..ሌላ ሴት ልታገባ››

‹‹አረ እንደዛ አላደርግም አንቺን እኮ በጠም ፈራሻለሁ››

‹‹በል እርሳው .እኔ ባል መቼም አለገባም››

‹‹ቻው በቃ ..እኔም ሚስት አላገባም››ብሎ አንገቱን በመድፋት ፊቱን አዙሮ ወደቤቴ ተመለሰ…

እሷም እያጉረመረመች ወደቤቱ እርምጃዋን ቀጠለች፡፡በዛ ዕድሜዋ እኚንና መስል እንደታአምር ሚነገሩ ድርጊቶችን መከወን የዘወትር ተግባሯ ነው፡፡እርግጥ ያው ተደጋግሞ እንደተነገረው እድሜዋና የሰውነቷ እድገት ተመጣጣኝ አልነበረም..ከእኩዬቾ በጣም የገዘፈችና የጠነከረች…ገና በአስር አመቷ ከሩቅ ታይተው ሚለዩ ጡቶች ያጎጠጎጠች..መቀመጫዋ ወደኃላ መግፋትና መንቀጥቀጥ የጀመረ በትክክል ሰትወለድ በአካባቢወ ኖሮ የሚያውቅ ሰው ካልሆነ በስተቀር ስለ ዕድሜዋ የሰማ ማንኛውም ሰው የማያመምነው አይነት ነው፡፡አሁን አብሯት ሲያወራ የነበረው ጓደኛዋ ዱባለ እንኳን  ድፍን ሁለት አመት ቢበልጣትም በማያጠራጥር  ሁኔታ ታላቁ የምትመስለው እሷ ነች፡
///

11 አመት ሲሞላት ወደ ትምህርት ቤት ተመለሰች፡፡ካርዷን ይዛ ሄደችና 3ተኛ ክፍል ተመዘገበች፤በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ቀን ብቻ ነው ክፍል ውስጥ ተገኝታ መምህራኑ የሚያስተምሩትን ትምህር የምትከታተለው፡፡ግን ደግሞ ያ የሚያመጣው ምንም አይነት ለውጥ የለውም…አንዱን የመማሪያ መፅሀፍ አንዴ ካነበች በኃላ  ፍፅም አትረሳውም… ሳምንቱን ሙሉ ክፍል ውስጥ መቀመጥ ለእሷ ብክነት ነው፡፡

13 ዓመት ላይ ሆና ነው፡፡የምትወዳት እናቷ ትታመምና ለተሻለ ህክምና ወደጎባ ሆስፒታል ሪፈር ተባላችና  እዛ ለአንድ ወር እንድትተኛ ይደረጋል፡በወቅቱ በታመመች ጊዜ ወደእዛ ይዟት የሄደው ታላቅ ወንድሟ ወይም የኬድሮን አጎት ነበር፡፡ከሳምንት ቆይታ በኃላ ግን ኬድሮን እናቴን ሄጄ ካለየሁ ሞቼ እገኛለሁ ትላለች…አረ ተይ እሷ እራሷ ሰሞኑን ስለሚሻላት ትመጣለች ብትባል ካላካችሁኝ ጠፍቼ ሄደለሁ በማለቷ ያው ካላቸው ልምድ ምንም ነገር አምርራ ከተናገረች እንደምታደረገው ስለሚያውቁ መሰፈሪያ ገንዘብ ሰጥተው ወደጎባ ከሚሄድ የጎረቤት ሰው ጋር በአደራ ሆስፒታል ድረስ ወስዶ ከእናቷ እና ከአጎቷ ጋር እንዲያገናኛት ይልኳታል፡፡በሰላም ትደርሳለች፡፡
አደራ የተቀበለውም ሰው እጇን ይዞ ሆስፒታል ድረስ በመውስድ ከእናቷና ከአጎቷ ጋር ያገናኛትና ወደራሱ ጉዳይ ይሄዳል…እዛ ሆስፒታል እናቷን እየተንከባከበችና አጎቷን እየገዘች አራት ቀን ያህል ከቆየች  በኃላ ግን ምንም እንኳን እናትዬው እየተሻላት ቢሆንም የጀመረችውን ህክምና እስክታጠናቅ ለተጨማሪ 10 ቀን መቆት አለባት ስለተባለ ከትምህርቷ ብዙ እንዳትስተጓጎል ይዟት የመጣው ሰውዬ ይዟት እንዲመለስ ይስማሙና በለሊት ከሰውዬው ጋር በአይሱዙ የጭነት መኪና አሰፍረው ይልኳታል፡፡

ደሎ መና ከጎባ ከተማ 110 ኪ.ሜትር ያህል የሚርቅ ቢሆንም መንገዱ ግን እጅግ በጣም አስቸጋሪ መልካአምድር ያለበት በተለየ ከጎባ አንስቶ እስከግማሽ ርቀት . ሪራ እስከተባለችው የገጠር ከተማ ድረስ ያለው መሬት በኢትዬጵያ ሁለተኛው ከፍተኛ ቦታ ባቱ ተራራ ሚገኝበት ከ4420 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ ያለውና እጅግ ሚያንዘፈዝፍ ብርድ ያለበት በዛ ላይ እጅግ ጠመዝመዛ ገደልና ቁልቁለት እናም ደግሞ እንደእባብ ተጠማዞ በማያልቅ መንገድ  የተነጠፈበት ነው፡፡በአስፈሪው ወጣ ገባ መንገድ 50 ኪሎ ሜትር ያህል ከተጓዙ በኃላ ቀሪው ደግሞ ዝቅ እያለና በተነፃፃሪ የተሻለ የሚባል መንገድ  ሆኖ ግን ጥቅጥቅ ባለ ጫካና በአስፈሪ አውሬዎች የታጨቀ መንገድ በማቋረጥ ነው ደሎ ከተማ የሚገባው፡
ኬደሮን ከደሎ ወጥታ ሌላ ከተማ ስታይ ይሄ መጀመሪያ ገጠመኝ ነበር፡፡ትራንስፖርቱ አይሱዙ ጭነት መሆኑ በአካባበው የተመደ ትራንስፖርት ስለሆነ ነው፤ከመንገዱ አስቸጋሪነት የተነሳ ዋናው የትንስፖርት አይነቶች አይሱዙ ጭነት፤ኤፍ.ኤስ. አር ጭነት ፤ፒካፕ መኪና ሲሆን አልፎ አልፎ አይሱዙ ቅጥቅጥ ይገኛል...ከዛ ውጭ የተለመደው አይነት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስና ሎንቺን፤ብሎም ሚኒባስ ያንን መንገድ አያስቡትም፡፡አይደለም እነሱ እራሳቸው የአይሱዙ ሹፌሮቹ ቢሆንም እያንዳንዱን የመንገዷን ወጣ ገባና  ኩርባ፤ ዝቅታና ከፍታ አብጠርጥረው የሚያውቁ ሰለሆነ ነው የሚወጡት.እዛ መንገድ ላይ ለመሾፈር ቅድሚያ በረደትነት አራትና አምስት አመት ቀጥቅጦ ማገልገልገልና የመኪናውን ብቻ ሳይሆን የመንገዱንም ፀባይ አብጠርጥሮ  ማወቅ የሚጠይቅ የጀግና ስራ ነው፡፡

ይቀጥላል
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/
ዙሪያቸውን ሲያዩ ነግቷል …ቢያንስ 12 ሰዓት ሆኗል….ሁለቱም ከተጣበቁበት ተላቀው ልብሳቸውን ከየወዳደቀበት በመለቃቀም መልበስ ጀመሩ ..ኬድሮን መጀመሪያ ቀሚሷን አንስታ አጠለቀች….ቀጥሎ ፓንቷን ስታነሳ ቦታው ላይ የተወሰነ የተበታተነ ድንጋዬች በደም ነጠብጣብ ቀልመዋል…አንዱን ድንጋይ አነሳችና  ሱሪውን ለብሶ ጨርሶ ቲሸርቱን በመልበስ ላይ ወደአለው  አንድሪው ተጠጋችና በእጆቹ አስጨበጣችው..  በአካባቢው የተሰበሰቡትን ሰዎችን ከቁብ ሳትቆጥር ጉንጩን ሳመችና አጀቡን ሰንጥቃ በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ ወደድንኳኑ  ተመለሰች….ስትደርስ ንስሯ ሻንጣው ላይ ቁጭ ብሎ የትዝብት በመሰለ አስተያየት እየተመከለታት ነበር ..ቶሎ ብላ አገልግሏን አነሳችና ትከሻዋ ላይ አንጠለጠለች፡፡  ንስሩን ገፈትራ አስነስታ ሻንጣውንም አነሳች‹‹ጀግናዬ በል ቶሎ እንሂድ ››አለችው ንስሯን፡፡
ጊዜ አላጠፋም….ክንፉን ዘረጋና ወደላይ ከፍ ብሎ አንጠለጠላት..እይታዋን አንድሪውን ጥላ ወደመጣችበት አቅጣጫ ስታማትር እሱ ከፊት እየመራ ሌሎች ከኃላ እየተከተሉት  እሷ ወዳለችበት አቅጣጫ እየሮጠ ነው፡፡በመቶ ሜትር ከፍታ ላይ ሆና እጇን ለስንብት አውለበለበችለት…. ጥላው እንዳትሄድ በእጁም እየተወራጨ በእግሮቹ መሬቱን እየተመተመ፤ በአንደበቱም ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ እየጮኸ ተማፀናት…ልቧ ራርቶ ልትመለስ አልቻለችም….ሶስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ ስትደርስ ተስፋ ቆርጦ መሬት ላይ ዝርፍጥ አለ…..ከዛ ከእይታው ተሰወረች .፡፡

አምስት ሰዓት አካባቢ ከበረሩ በኃላ ነው ኬንያ ድንበር ሞምባሳ ወደብ  ተጠግቶ ከሚገኝ ኢንዲያና ውቅያኖስ ውስጥ የጣላት፡፡እሱ አገልግሏንና ሻንጣውን ይዞ ወደ ዳር  በረረና ዋኝታ ጨርሳ ሰእስክትመጣ ዛፍ ላይ በመቀመጥ እረፍት በመውሰድ ይጠብቃት ጀመር፡፡

የተለየ ምሽተና የተለየ ለሊት ነበር ያሳለፈችው….እና በወሲብ ወቅት የወራዛውን ላቧን  መሬት ላይ ስትንከባለል በአቧራ የቆሸሸና ሰውነቷን ድንግልናዋን ስታስረክብ  በጭኗ መካከል ተንሻሮ የተንጣበጠበ ደሟን በኢንድያና  ውቅያኖስ ጨዋማ ውሀ እያጠበችውና እያፀዳአቸው ነው……አሁን ትናንት የነበረችውን ኬድሮንን አይደለችም….ሴት ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ሌላ የሆነ የተከፈተላት የኃይል በር እንዳለ እየተሰማት ነው…..አንድሪውን ወዳዋለች…..ከእሱ ጋር በፈፀመችው ነገር ምንም አይነት ፀፀት እየተሰማት አይደለም…እንደውም በተቃራኒው የተለየ አይነት እርካታን  የመሞላትና የመባረክ ስሜት ነው እየተሰማት ያለው…..ለምን ተጨማሪ ጊዜ ከእሱ ጋር እዳላሳለፈች አታውቅም…..የማትቆጣጣረው ኃይል በአስቸካይ አካባቢውን ለቃ እንድትወጣ አስገድዷታል…እንጂማ ቢያንስ አንድ ተጨማሪ ቀንና አንድ ተጨማሪ ወሲብ ከአንድሪው ጋር ቢኖራት ፍፅም ደስተኛ ትሆን ነበር፡፡
የሰውነቷንም ሆነ  የሀሳቧንም ቆሻሻ እዛው ኢንዲያና ውቅያኖስ  ላይ ካራገፈች በኃላ ወደወደቡ ዳር ወጥታ  ንስሯ ወዳለበት ቦታ ሄደችና እሱ ባለበት ዛፍ ስር ቁጭ አለች…..ከላይ ካለበት የዛፉ ጫፍ  ሻንጣውን እና አገልግሉን ይዞ በሮ በመውረድ  ከጎኗ አረፈ…..ሻንጣዋን ከፈተችና ሌላ ቀሚሰ በማውጣት የለበሰችውንና የረጠበውን ቀሚስ በማውለቅ ደህናውን ለበሰችና እርጥቡን ጨምቃ የግንዱ ቅርንጫፍ ላይ አሰጣችው፡፡
ከዛ አገልግሉን ወደራሷ አስጠጋችና እናቷ ከቆጠረችላት ገና ግማሹን እንኳን ያልተበላለት ጩኮ ከፈተችና ለመብላት ተዘጋጀች…ንስሯ አፍጥጦ ሲያያት ነበር ‹‹..ወይ ይቅርታ አንተም ለካ እርቦሀል….››ብላ ሄደህ የሚታደን ነገር ፈልገህ  ተመገብ …ታዲያ ከ30 ደቂቃ በላይ እንዳትቆይ….››አለችው

ልክ እንደ ሰው ያለችውን በፅሞና ሰምቶ በአየር ላይ ተንሳፈፈና ሰማዩን ሰንጥቆ ከእይታዋ ተሰወረ…..እሷም ጩኮዋን እየቆረሰች  በኮዳዋ በያዘችው ውሀ እየማገች መመገብ ጀመረች…እስክትጠግብ ከበላች በኃላ .. ግንዱን ተደግፋ  ጋደም ብላ ስለአንድሪው እያሰበች የንስሯን መምጣት እየተጠባበቀች ነው….20 ደቂቃ በኃላ ንስሯ በመንቁሩ የሆነ ቦርሳ ነገር አንጠልጥሎ መጣ ፤ግራ ገባት… ስሯ አረፈ….
‹‹የሚበላ ይዘህ ና አልኩህ እንጂ ቦርሳ አልኩህ?››
እጇ ላይ አስቀመጠላት…..የሚያምር አነስተኛ የእጅ ቦርሳ ነው፡፡ተቀበለችውና ከፈተችው…የሚያብረቀርቁና አይን ላይ ብዙ አይንት ቀላማትን ሚረጩ ሁለት የእጅ መዳፍ ያህል መጠን የሚሆኑ ጌጦች ናቸው››
‹‹ምንድናቸው…?››ንስሯን ጠየቀችው…፡፡
አእምሮውን ከፈተላት…አልማዝ እንደሆነ አወቀች፡፡
‹ከየት አመጣኸው?››
ባህሩ መሀከል …የመርከብ ዘራፊዎች እርስ በርስ እየተገዳደሉ አንድ ሌላውን ሲዘርፍ ከመሀከላቸው ነጥቆ እንዳመጣ ምስሉን በአእምሮዋ ልኮ እንድታውቀው አደረጋት፡፡
‹‹ስንት ያወጣል……?››
‹‹የአንድ ሻንጣ ብር  ምስሉን በእምሮዋ አሳያት……እስከዚህን ዕድሜዋ ድረስ ስለገንዘብ እስባም ሆነ ተጨንቃ አታውቅም…አሁን ግን እልማዙን ስታይ ሆነ ስለሚያወጣው ገንዘብ ንስሯ ሲነግራት የተለየ ስሜት ነው የተሰማት…ምን አልባት ይሄ ሴት ከመሆኟ ገራ በውስጧ በቅሎ ያደገ አዲስ ስሜት ሳይሆን እንደማይቀር ገመተች፡፡ብር  የሚያስገኛቸውን ነገሮች አንድ በአንድ ማጣጣም ቀጣይ ተግባሮ እንደሚሆን አለመች፡፡
‹‹በል አሁን ወደሀገራችን እንሂድ….የእማዬ ቡና ናፍቆኛል››አለችው፡፡
አንጠልጥሎት በአየር ላይ አዋላትና ዞሮ ከጀርባዋ ተጣበቀ..  ከኬንያ ወደ ኢትዬጵያ አቅጣጫውን አስተካክሎ መብረር ጀመረ፡፡

ይቀጥላል
​​#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስር


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
ዛሬ ላይ..
ለሊት 11 ሰዓት ተነስተው ቤተክርስቲያን ሄዱ፤ለአባትየው ሰባት ዓመት ፍትሀተ-ፀሎት ከመደረጉ በተጨማሪ የስንዱም የምንኩስና ስርዓት ፀሎት ተደርጎ እማሆይ አፀደማርያ ተብላ ቆብ ደፋች.ይሄ ድርጊት በአብዛኛው  ሰው  ዘንድ መደነቅን ለጥቂቱ ደግሞ ለሀሜት አሳልፎ ሰጣት…ከቅዳሴ በኋላ ከቤት ተዘጋጅቶ የመጣውን ፀበል ፃዲቅ ሰንበቴ ቤት በመታደም ከተቋደሱ በኋላ ቤት ላለው ዝግጅት ተመለሱ ቀኑን  ሙሉ ባለፉት 6  ዓመታት እንደተደረገው  ችግረኞችና  የኔ ቢጤዎች ሲመላለሱበት ዋሉ…ሳባ በዕለቱ አብዛኛውን ፕሮግራምና ሽር ጉዱን ብትሳተፍም ከአስር ሰዓት በኃላ ግን ደከማት፡፡  ተዝለፍልፋ ሰው መሀል ከመውደቋ በፊት እየተጎተተች ወደመኝታ ቤት ገባችና አልጋ ላይ ወጥታ ተዘረረች..ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰዳት…እንቅልፏ ግን እጅግ  ሰቅጣጭ  የሆነ ቅዠት የሞላበት ነፍስ አስጨናቂ ነበር…ደግሞ የሚገርመው  ሕልሙ  እንደ ሆረር ፊልም ከአንዱ አሰቃቂ ትዕይንት ወደሌላ በተሸጋገረ ቁጥር ጭንቀላቷ ውጥርጥር እያለ ሲለጠጥ በትክክል ይታወቃታል…በተለጠጠ ቁጥር ደግሞ ውጥረቱ የሆኑ ነርቮቿን እንደሚበጣጥስ ይሰማትና ከህመሙ ራሷን ለማዳን ከእንቅልፏ ለመንቃት እየጣረች ነው.. አዎ ይታወቃታል..በደንብ ከልቧ እየጣረች ነው…ግን አልቻለችም፡፡ ስንዱ እቃ ለመውሰድ ወደመኝታ ቤት ስትገባ ሳባ በላብ ተደፍቃ ስትወራጭ በማየቷ ወዝውዛ ነበር ከእንቅልፏ ያነቃቻት..

‹‹ወይ ስንድ..ገላገልሺኝ.. እመሰግናለሁ›አለችና ተጠመጠመችባት፡፡
ስንዱም ጭንቅላቷን እያሻሸቻት‹‹ምንድነው ይሄ ሁሉ ላብ? አሞሻል እንዴ አንቺ ልጅ?›ስትል ጠየቀቻት፡

‹‹አይ ሰሞኑን ትንሽ አሞኝ የታዘዘልኝ መድሀኒት ነበር..ስመጣ ግን  ረስቼው መጣሁ››

‹‹ታዲያ ለምን ከዚህ አይገዛልሽም?››
‹‹አይ እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አይነት አይደለም..ማዘዣው ስለሌለኝ አይሸጡልኝም፡፡ግዴለሽም አሁን ትንሽ ስለተኛሁበት ይሻለኛል..ወደ እንግዶችሽ ተመለሺ››

‹‹እሺ በቃ መለስ መለስ እያልኩ አይሻለሁ..››ብላ ግንባሯን ሳመችና በራፉን ዘግታላት ወጥታ ሔደች፡፡
ሳባም መልሶ እንቅልፍ እንዳይወስዳትና ወደተመሳሳይ ቅዠት ገብታ ስቃይ ውስጥ ላለመግባት ስትል ወደሀሳብ ውስጥ ገባች ወደ ትናንቷ ተመለሰች፡፡ትዝ ይላታል የዛን ሰሞን አሰላ ሄዳ ቤተሰቦቿን ጠይቃ ከተመለሰች በኋላ እና አባቷ ደብቆ ሻንጣዋ ውስጥ ያስቀመጠላትን 3ሺብር ካገኘች በኋላ ምንም ሰላም ማግኘት አልቻለችም ነበር፡፡ ቀንና ለሊት ሕይወቷን እንዴት ማስተካከል እንደምትችልና ከቤተሰቧ ድጎማ እራሷን አላቃ በተራዋ ለቤተሰቦቿ ተገቢውን ድጋፍ እንዴት ልታደርግ እንደምትችል ማሰብ ነበር ቋሚ ስራዋ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን ተዓምር ተከሰተ፡፡፡:

ትዝ ይላታል ማክሰኞ ቀን ነው፡፡ ስራ ገበታዋ ላይ ሆና  በተለመደ  መልኩ ባለጉዳዬችን እያስተናገደች ሳለ ረፋድ ላይ አንድ እጅግ ዘመናዊ ጥራት ያላቸው ብራንድ ልብሶች የለበሰች፤ውድ የሆኑ አብረቅራቂ ጌጣጌጦችን ጆሮዎቿና እጆቿ ላይ የደረደረች ሴት ወደ ቢሮዋ የገባችው፡፡ልክ እንዳየቻት ነው  ልቧ የደነገጠላት..በሁለመናዋ ነው የቀናችባት….አየሩን ሞልቶ ወደ አፍንጫዋ ሰርጎ በገባው ውድ ሽቶዋ ሳይቀር ቀናችባት፡፡እናም ሳታስበው ከወትሮ በተለየ አይነት ፈግታና ቅልጥፍና ሴትዬዋን ማስተናገድ ጀመረች፡፡ እሷ የምትጨርሳቸውን ስራዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ቢሮዎች የሚሰሩ እና የሚፈረሙ ፊርማዎችን  ሳይቀር ሴትዬዋን  የራሷ  ቢሮ አስቀምጣ እሷ (ልክ ጉቦ ይሰጥሀል እንደተባለ ኤክስፐርት) ተዟዙራ አስጨረሰችላትና ሰጠቻት፡፡
ከዛም ሴትዬዋ..ወረቀቷን ተቀብላ ትሄዳለች ብላ  ስትጠብቅ  ተመቻችታ  ፊት ለፊቷ ተቀመጠችና….‹‹ስሜን መቼስ ከሰነዱ አንብበሻል…ትብለጥ እባለለሁ…››

‹‹እኔ ደግሞ ሳባ››ስትል የራሷንም ነገረቻት፡፡

‹‹ሳባ ዋው…ስምሽም እንደመልክሽያምራል››አለቻት፡፡የሴትዬዋ ንግግር ቀጥታ ልቧ ላይ አርፎ ነበር ቅልጥ ያደረጋት፡፡ አንድ ጎረምሳ ወንድ እንኳን እንደዛ አይነት አስተያየት ቢሰጣት የዛን አይነት ስሜት በውስጧ አያጭርባትም፡

‹‹አመሰግናለሁ….›› አለች ሌላ ምትለው ነገር ስለጠፋት፡፡

ሴትዬዋ ቀጠለች‹‹ስራ እንዴት ነው?››

‹‹ያው እንደምታይው ነው…ምንም አይልም››

‹‹ምንም አይልም ነው ወይስ ጥሩ ነው ነው?›

‹‹አይ ምንም አይልም…ጥሩ የሚባል ስራ እንዲህ በቀላሉ ይኖራል ብለሽ ነው?›› አለቻት ሰሞኑን ስላለችበት ብሶት እያሰላሰለች፡

‹‹እንደ አንቺ ቆንጆ፤መለሎ ቁመና የተስተካከለ የሰውነት ቅርፅ ያላትና በዛ ላይ የተማረች ሴትማ በጣም ጥሩ የተባለ ስራ ሊኖራት የግድ ነው…››አለችና እጇን ወደ ቦርሳዋ ሰዳ የቢዝነስ ካርዷን አወጣችና ጠረጴዛዋ ላይ እያስቀመጠችላት
‹‹ይሄውልሽ ሳባ ለምን እንደሆነ አላውቅም ወድጄሻለሁ ምን አልባት ጥሩ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ በምትፈልጊበት ቀን ደውይልኝ….በይ ቻው  ለመስተንግዶሽ አመሰግናለሁ፡፡››ብላ ጉንጯን ሳመችና ቢሮዋን ለቃ ወጣች፡፡ ሳባም በተቀመጠችበት መቀመጫ ደንዝዛ በፈዘዙ አይኖቿ ከኋላዋ ተከተለቻት ሴትዬዋ እየተሞናደለች ቢሮውን ለቃ ስትወጣ በራፍ ላይ ሁለት ወጠምሻና ባለጡንቻ ወጣቶች እየጠበቋት.ነበር….መሀከል አስገብተዋት ይዘዋት ሄዱ…፡፡

‹‹ይህቺ ባለስልጣን ነች ወይስ የባለስልጣን ሚስት?› ስትል ራሷን ጠየቀች….ብንን እንደማለት አለችና ትታላት የሄደችውን ቢዝነስ ካርድ አነሳችና…አየችው..
ትብለጥ ግዛው፡፡

‹‹ቤርሙዳ ማሳጅ ቤት›› ይላል፡፡

‹‹እንዴ ባለማሳጅ ቤት ነች ግን አስመጪና ላኪ  ነው  የምትመስለው›› ስትል የስራዋ አይነት ከግምቷ ውጭ ሰለመሆኑ አብሰለሰለች፡፡ሌላ ባለጉዳይ ገባባት፡፡ሳትወድ.በግዷ.ሀሳቡን ለጊዜው በልቧ ሸሸገችውና ወደስራዋ ተመለሰች፡፡ማታ ቤት ገብታም ስለሴትዬዋ ማሰቧን አላቋረጠችም ነበር፡፡ ወንድ ብትሆን "ፍቅር ያዘኝ እንዴ?ብላ ራሷን መጠራጠር ትጀምር ነበር...ሴትዬዋ የማሳጅ ቤት ባለቤት መሆኗን ከቢዝነስ ካርዷ ብትረዳም ‹‹የፈለገችኝ ለሌላ ስራ ቢሆንስ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት። እንደምንም ራሷን   ተቆጣጠረችና አራት ቀን በመቆየት በአምስተኛው ቀን ደወለችላት፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በማሳጅ ስም እየሰራችው ያለችው ስራ ካሰበችው በጣም ውስብስብ ፤ከግምቷ በጣም የረቀ፤ ካደገችበት ስነ-ምግባር ያፈነገጠ፤ የተለየ አይነት አለም ሚያሳይ ቢሆንም ወደ ቦርሳዋ በሚፈስላት ብር ስለሚካካስ አሜን ብለ ተቀብላው ለአመታት ሰትሰራ ነበር፡፡እንጂማ ስራ ሲያስጀምሯት ማሳጅ ቤት ብለው የሰበኳት ስብከት ፌክ መሆኑን የተረዳችው ስራ በጀመረች ሶስት ወርም ሳይሞላት በፊት ነበር፡፡ምክንያቱም ከሚሰጡት አገልግሎቶች ውስጥ ትክክለኛ ያልበተበረዘና ያልተከለሰ ማሳጅ 25 ፐርሰንትም አይሆንም...አሱ ሽፋን ነው፡፡
ወደስራው ጠልቃ ከገባች በኃላ ብዙ ብዙ ገራሚ ገጠመኞችን አስትናግዳለች… አንዳንዶቹ እስከህይወቷ ፍፃሜ የማትዘነጋቸው አይነት ናቸው፡፡
ከበርካታ ያልተለመዱ አይነት ገጠመኞቾ መካከል  አንድን ለምሳሌ ያህል ለማየት ብንችል ነገሮችን ግልፅ ያደርግልናል፡፡ስራ በጀመረች በአራተኛው አመት ነው፡፡ደምበኛ እንዳላት ተነግሯት በሰዓቷ ስራ ቦታዋ ተገኝታ እየጠበቀች ነው፡፡ እንደተባለውም በሰዓቱ በራፍ ተንኳኳ… ከፈተች፡፡በራፍ ላይ በመግባትና ተመልሶ ሮጦ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ውዝግብ ውስጥ የገባ ስሜት ላይ ያለ ጎልማሳ  ሰው  ቆሟል..ሰውዬውን  ታውቀዋለች… በአካል አይደለም..ታዋቂ ሰው ነው..ግን ምንድነው?  ተዋናይ  ነው?  ፖለቲከኛ ነው…? ግልፅ ብሎ ሊታወሳት አልቻለም፡፡‹‹ጌታዬ እንኳን ደህና መጡ ይግቡ.›› አለችና በራፉን በሰፊው ከፈተችለት..የመዝለል ያህል ፍንጥር አለና ወደ ውስጥ ገባ…እሷም በራፉን ዘጋችና  ተከተለችው…እቤቱ  ውስጥ  ከወዲህ  ወዲያ መንጎራደድ ጀመረ‹‹…ጌታይ ችግር አለ? ››ጠየቀችው፡፡

‹‹እዚህ መምጣቴ ትክክል ነው ወይስ ስህተት አላውቅም››

‹‹ጌታዬ ስህትም  ሆነ  ትክክል  አንዴ  መጥተዋል..አረፍ  ይበሉና  ትንሽ ይረጋጉ..እዚህ መምጣቶት ስህተትም ቢሆን የሆነ ጥቅም አይጠፋውም….ደግሞ ነገሮች እንደአጠቃቀማችን ይወሰናሉ…የህይወት ጨለማ ክፍሉ ውስጥ ዳካሮ መውጣት የብርሀኗን ውበት የበለጠ እንድናጣጥም  ግንዛቤያችንን ይጨምርልናል፡፡››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡››ብሎ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ፡፡ሳባም ወደፍሪጁ ሄደችና የታሸገ ውሀ በማምጣት ከጎኑ ያለ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለት..ከፈተና ገርገጭ.ገርገጭ አድርጎ ግማሽ ያህሉን ከጠጣለት በኃላ ከደነና መልሶ አስቀመጠው፡፡ለእኔ እዚህ ቦታ መምጣት ቀላል አይደለም…እዚህ እንድመጣ የጠቆመኝ አንድ ወዳጄ ነው….

‹‹ጥሩ ነው…ምን አይነት አገልግሎት ነው የሚፈልጉት…ሙሉ ማሳጅ ..የእግር ማሳጅ አለ…ከአንገት በላይ ማሳጅ አለን…ሌሎች አገልግሎቶቹም አሉን.መጠጥና
…››
‹‹አይ እንዳዛ አይደለም…የዘረዘርሻቸውንም ሁሉ አንዳቸውንም አልፈልግም…እኔ የምፈልገው እንድታዳምጪኝ ብቻ ነው…ቆይ አሉና እጃቸውን ወደ ኮት ኪሳቸው በመክተት አንድ መለስተኛ ጥራዝ ያለው መፅሀፍ  አወጡና  ዘረጉላት፡፡ግራ በመጋባት ተቀበለችና አነበበችው›

‹‹የኢየሱስ ተአምራዊ የማዳን ስራ››የሚል ርዕስ አለው፡፡ጀርባውን ገልብጣ አየችው ፀሀፊ-ፓስተር ጴጥሮስ ዳንሳ ይላል፡፡ ከፊት ለፊቷ ያለው ሰው ፎቶ ገጭ ብሎበታል…እንደአዲስ ደነገጠች..ሰውዬው በደንብ ታውቀዋለች..በፕሮቴሰታንቱ መንደር በጣም ታዋቂና ዝነኘ ፓስተር ነው…በዛ ላይ የራሱ ሆነ ቴሌቬዥን ጣቢያ ስላለው.በተደጋጋሚ ስብከቱን በቴሌቪዥን መስኮት አዳምጣለች፤አሷ  ጋር መምጣቱ ለምን እንደዚህ እንደከበደው ወዲያው ነበር ግልፅ  የሆነላት..ኸረ መምጣቱ ለእሷ ለራሷ በጣም ገርሟታል..››

‹‹ፓስተር.በእውነት የአርሷ እዚህ  መምጣት  ለእኔ  ትልቅ  ክብር  ነው….እና እንዳሉኝ የሚፈልጉት እንዳዳምጧት ከሆነ በሙሉ ነፍሴ  የለምንም  ፍርድና ትዝብት እንደማዳምጧት እርግጠኛ ይሁኑ››

‹‹እሺ እንደዛ ከሆነ .ማወራሽ ስለመፅሀፉ ነው፡፡በእጅሽ ስለያዝሺው መፅሀፍ ፡፡ መፅሀፉ እውነተኛ የህይወት ገጠመኜ የሰፈረበት ነው፡ይሄ ገጠመኝ ምንም ማጣፈጫ ያልተጨመረበት ንፅህ እውነት ነው ብዬ  አምን  ነበር።ላለፍት  9 ዓመታት ሰፋ ያለ ህዝብ በታደመበት አውደ ምህረት ላይ  ያለመሰልቸት ተርኬዋለሁ። ምዕመኑም አንዳንድ ሶስቴ ሌላውም 13ቴ ደጋግሞ ሰምተውታል። ግን አይ ሰልችቶኛል የሚል የለም፡፡ ከእልልታው ጥቂት ዝንጣፊ የሚቀንስ የለም።በጌታ ሰው አንደበት የሚነገር የጌታ ተአምር እንዴት ሰለቸኝ ማለት ይቻላል...?መታሰብስ።

የዛሬ 14 አመት ለአገልግሎት ደቡብ ኢትዬጰያና ሱዳን ድንበር  አካባቢ  ወደሉ ጎሳዎች እሄዳለሁ።እርግጥ ብቻዬን ሳይሆን ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ነበር።እና ጉዞችን ጥቅጥቅ ደን የምናቋርጥበት ከአውሬ ጋር ድብብቆሽ የምንጫወትበት አስደናቂና አስፈሪ ነበር..ግን ደግሞ ጌታ ከእኛ ጋር ስለነበር በዝምታ ሳይሆን በዝማሬ ነበር የተጓዝነው። መንገድ ከሚገኝበት የሁለት ቀን የእግር መንገድ ተሂዶ ነው የሚደረሰው። ጌታ ይመስገን በሰላም ደረስን።ጌታን አገለገልን በሶስት ወር ቆይታችን 10 ብቻ የነበሩትን አማኞች ወደ ሶስት መቶ አሳድገን በመንደሩና በአካባቢው  የጌታ  አገልጋዬች  አድርገን  ጉባኤ  አደራጅተን  ቤተክርስቲያን መስርተን አንደኛውን ጓደኛችንን እዛው  እንዲያገለግል  ትተን  የመልስ  ጉዞ ጀመርን።

በመሀል ደረቀ ጉሮሮውን ለማርጠብ ከጎኑ ካለው ጠረጴዛ ውሀውን አነሳና ላይ የተቀመጠለትን ሀይላደንድ ውሀ በመክፈት እየተጎነጨ በተመስጦና በስሜት ትረካውን ቀጥሏል…፡
…በሁለተኛው ቀን ከጓደኞቼ ነጥለው ጠለፍኝ።አንድ መፅሀፍ ቅድስ ብቻ ነበር በእጄ የያዝኩት፡፡ጌታ ሆይ አንተ ጠብቀኝ አልኩ።የጠለፍኝ ሰዎች ቋንቋቸው የማይገባ እጅግ ከሰው ተነጥለው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የሚኖሩ 2መቶ የማይሞላ ቁጥር ያላቸው አባላት ያላቸው ጎሳዎች ናቸው።
ከወሰዱኝ በኃላ አንድ ጠባብ ጎጆ ውስጥ ጠርቅመውብኝ በራፍን ገንጥዬ እንዳላመልጥ ሁለት ጦር የቀሰሩ ጠባቂዎች በራፍ  ላይ  አስቀመጡ።መፅሀፍ ቁዱሴን ደረቴ ላይ ለጥፌ እኔ ፀልያለሁ...ያለማቆረጥ ከጌታ ጋር አወራለሁ።ሶስታ ቀንና ሶስት ለሊት  እዛች  ጠባብ ጎጆ  ውስጥ  አሳደሩኝ፡፡  በአራተኛው ቀን የተለየ ነገር መታየት ጀመረ፡፡ ውጭ ታላቅ  ክብረ  በዓል  ለማዘጋጀት  ትርምስ  ላይ እንደሆኑ ይታየኛል።‹‹ጌታ ሆይ  ተአምራትህን  በዚህ  ዝግጅት  ላይ  አድርግ›› እያልኩ ፀሎቴን ቀጠልኩ.. ሲጨልም ምቀምሰውን ምግብ አንድ ልጃገረድ ይዛልኝ መጣች፡፡ ጠባቂዎቹ ወደውስጥ እንድታልፍ ፈቀድላት...:: ጎምበስ ብላ ምግብን እያቀረበችልኝ
"አይዞህ"አለችኝ፡፡

‹‹ እንዴ ጌታ ስራውን መስራት ጀመረ ››አልኩ...አማርኛ ትችላለች..

"ለምንድነው የያዙኝ...?ከእኔ ምን ፈልገው ነው ?"ከእሷ ባነሰ ደካማ ድምፅ ጠየቅኳት።
"ለመስዎእትነት..ለአማልዕክቱ ሊያቀርብህ ነው" አለችኝ... ያልጠበቅኩትን መልስ ነበር ያገኘሁት…የጌታ ጥበቃ በዙሪያዬ እንዳለ ባምንም..የልጅቷ በዛን ሰዓት

ከአማርኛ  ችሎታ  ጋር  ስሬ  መከሰት  አንድ  ምልክት  እንደሆነ  ባልጠራጠርም
...ሰውነቴ በፍራቻ መራድ፤አፌም በድንጋጤ መድረቁ አልቀረም ነበር።"
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እሷ እየተንደረደረች ወደቤቷ ገባችና ፎቁን ወጣች መኝታ ቤት ገባች፡፡ የሆነ ነገር አደናቅፎት እንዳትወድቅ እንኳን  መብራቱን  ማብራት  አልፈለገችም።በዳበሳ ከልጋዋ ላይ ወጣችና ጠርዙን ያዘች፡፡ ወደ ኮመዲኖ ተንጠራራች ቀን በጅምር ያቆመችውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳችና ክዳኑን ከፍታ አንደቀደቀችው።

"እስኪ ይሄ ምስኪን ልጅ ምን አደረገኝ?"እራሷን እረገመች። ምነው እግሬን በሠበረው በማለቱ ወደእሱ በመሄዶ እራሷን ወቀሰች፡፡
….////…
ሳባ አሁን በዚህን ሰዓት 80ሺ ብር የተገዛ ባለ 2 ሜትር የተንጣለለ ግዙፍ አልጋ ጠርዝ ላይ ተኝታ  ያቺን ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የነበረችዋን  የዋህ  ንፅህ  ጉጉ ተስፈኛ ወጣት አብዝታ እየናፈቀቻት ነው፡፡አሁን ያላትን  ሀብትና  ንብረት  ሁሉ ከፍላ ይቺን ሚስኪን ወጣት ከነሙሉ ክብሯ፤ ንፅህናዋና፤ የዋህነቷ እንዲውም ከሙሉ ተስፋዋ ጋር ቢመልሱላት ዓይኗን ሳታሽ ነበር የምትስማማው፤ ግን ያንን ማድረግ እንደማይቻል ስታውቅት ተስፋ ቆርጣ ይበልጥ አንገት ያስደፋታል፡፡
ደግሞ ይህ ተስፋ መቁረጧ ጫፍ ላይ አድርሶ እርሷን እንድታጠፋ እና ካለችበት ቅዠት እንድትገላገል ቢያግዛት  ደሰተኛ  ትሆን  ነበር፡፡ግን  ህይወትን  በአዲስ መንፈስ አድሳ ከድባቴ እራሷን አላቃ ከሚወቅራት እራስ ምታትና ከሚያኮረማምታት የመንፈስ መሰበር ተላቃ አዲስ ህይወት ለመጀመር የሚያስችላት አቅም ለማግኘት ሆነ እስከዛሬ ባለፈችበት የሀጥያት  መንገድና የተበላሸ የህይወት መስመር የተነሳ እራሷን ተጠይፋ ከህይወት መዝገብ  ላይ በፍቃዷ እራሷን ለማሰናበት የሚያስችል ብቃትና ፅናት ማግኘት አልቻለችም፡፡ያ ደግሞ በአየር ላይ አንገትን በገመድ ታንቆ እንደመንጠንጠል አይነት የሚያቃትት ስሜት ነው እንዲሰማት እያደረጋት ያለው፡፡
አሁን እንደዚህ ምስቅልቅል ባለ ህይወት ላይ ሆና ለሚያያት ሰው ምን ሆነሽ ነው
?ብለው ቢጠይቋት እንዲህ ሆኜ ነው ብላ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ የምትመልሰው ለሰሚው ሚዛን የሚደፋና ለእሷም እንዲያዝኑላት የሚያደርግ ምንም ምክንያት የላትም… ምክንያቱም ትክክለኛ ምክንያቷን(ነፍስ ገዳይነተዋን)መናገር አትችልም…ብትናገር ማረፊያዋ እስር ቤት ነው፡፡
እነዛን ሚስጥሮች የማያውቁ  ሰዎች ደግሞ‹‹ባፈቀረችውና ልቧን አሳልፋ በሰጠችው ሰው የመከዳት ችግር አልገጠማትም ..የገንዘብ እጥረት ወይም ኪሳራ ፍፅም የለባትም..የሆነ ወንጀል ሰርታ የተከሰሰችበት ጉዳይ ፈፅሞ የለም..የህክምና ምርመራ አድርጋ እንዲህ አይነት ቋሚ የጤና ችግረ አለብሽ ተብሎ አልተነገራት…ታዲያ ምንድነው እንዲህ የሚሰባብራት?›› ብሎ ቢያስብና ቅብጠት ነው ብሎ ፍርድ ቢሰጥ አይገርምም፡፡
እውነታው ግን አሁን በዚህ ወቅት የሳባ መንፈሶ ተሰብሯል ፤የመኖር ጉጉቷ ተንቆሻቁሾል፤በውስጧ ምንም አይነት  የደስታ  ቅመም  መመረት  ካቆመ ሰነባብቷል፡፡ የመኖርም  ሆነ  የመሞት  ፍላጎቷን  አጥታለች፡፡ማፍቀርም  ሆነ መፈቀር ሳይቀር ትርጉመ ቢስ ሆኖባታል፡፡በአጠቃላይ ስሜተ ቢስ እየሆነች ነው፡፡እንደሚታወቀው ስሜት ማለት የሠው  ልጅ  መንፈሳዊ  ወዝ  ነው።  የሰው ልጅ ህይወትን ጣፍጭና ወዝ ያለው የሚያደርገው የስሜቱ ውጣ  ውረድ ነው ። ሰው ሲከፍው ከላለቀሰና ሲደሰት ካልሳቀ ከፍተኛ የስሜት መሠበር እንዳለበትና ጠንካራ ህክምና እንደሚያስፈልገው በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።ጠንካራ ስሜት ያላቸው ሰዎች ህይወታቸው ደማቅና ከሩቅ ትኩረት የሚስብ ናቸው።ግን ደግሞ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሲሰበሩም በትልቁና በቀላሉ ነው፧፡ለዚህ  ነው  የሠውን ስሜት መስበር አስጠሊታ ሀጥያት የሚባለው።
እለቱ ማክሰኞ እኩለቀን አካባቢ ነው።ሰራተኛዋ አለም የምትሰራውን ሰርታ ወደቤት ለመሄድ ስትወጣ ቀናውን በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ እንደወትሮው ሲያነብ አገኘችው፡፡ኮቴዋን ሲሰማ ቀና ብሎ ‹‹ልትሂጂ ነው?››አላት፡፡
‹‹አዎ ልሄድ ነው….ግን አንድ ነገር ላማክርህ ነበር፡፡›› ከመቀመጫው ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ‹‹ምንድነበር?››ጠየቃት፡፡
‹‹የዚህች ልጅ ነገር በጣም አሳስቦኛል…ይሄው መኝታ ቤቷ ከተሸሸገች ሁለት ወር ሊደፍናት ነው..ምግብ አትበላ፤ መጠጣትና ..መተኛት ብቻ ነው ስራዋ…፡፡አሁንማ ሰውነቷ አልቆ አልቆ ስንጥር አክላለች..በዚሁ ከቀጠለች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ መሞቷ አይቀርም፡››
‹‹የእሷ ነገር እኔንም አሳስቦኛል…..አንቺ ምን አሰብሽ?››
‹‹እንዴ ግራ ገባኝ ..ከቤት መውጣት እምቢ ካለች፤ ህክምናዋና ካቆረጠች፤ መብላትና መጠጣት ካቆመች..እራሷን ቀስ በቀስ እየገደለች እኮ ነው….አንድ ነገር ከሆነች ደግሞ እኔና አንተ መጠየቃችን አይቀርም.. በተለይ እኔ……በጣም አሳስቦኛል፡፡››
‹‹ቆይ ዘመዶች የሏትም እንዴ?››
‹‹አላት …አሰላ ናቸው እንጂ  ዘመዶች  አሏት  ፡፡እሷ  ግን  ያለችበትን  ሁኔታ ለማንም እንዳንናገር በጥብቅ ነው ያስጠነቀቀችኝ…ግን አሁን አሁን ምርጫ የለኝም..ግፋ ቢል ስራውን መልቀቅ ነው፣ እስር ቤት ከመግባት ስራዬን ባጣ ይሻለኛል…እንደምንም የእንጀራ እናቷን ስልክ አግኝቼያለሁ…ልደወልላት ነው፡፡››
‹‹እኔ የሆነ ነገር አስቤ ነበር››አላት ቀናው፡፡

‹‹ምን?››
‹‹አሁን አልነግርሽም…ግን አንድ ሳምንት ይፈጅብኛል..እንደምንም አንድ ሳምንት ጊዜ ስጪኝና ልሞክር… እስከዛ ምንም ለውጥ ካላሳየች እንዳልሺውም ትደውይላቸዋለሽ፡፡››
ለተወሰነ ደቂቃ እንደማሰብ አለችና‹‹..እሺ  ካልክ…እስከዛሬ  ያልሞተች  መቼስ በአንድ ሳምንት ውስጥ አትሞትም ››ብላ ተሰናበተችውና  ወጥታ  ሄደች፡፡ቀናው ወደ ነበረበት መቀመጫ ተመልሶ ተቀመጠና ማሰላሰል ጀመረ..ምን  አድርጎ ቀጣሪው ከገባችበት የመደበት ስሜት ሊያወጣት እንደሚችል አሰበ …ቢያንስ የተወሰነ ቀና ብላ ወደህክምና ክትትሏ እንድትመለስ ማድረግ እንዳለበት ወሰነና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ግቢውን ቆላለፈና   አነስተኛ ምንጣፋና አንድ መፅሀፍ ይዛ ወደ ትልቁ ቤት ገባ።
የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ውስጡ እየገፋፋው ነበር የከረመው ዛሬ  ደግሞ የአለም ንግግር በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር አስገደደው…እርግጥ ከእሷ የሚያጋጥመውን መልስ ምን እንደሚሆን አያውቅም ግን ምንም ሆነ ምንም ለመጋፈጥ ወስኗል......ሳሎኑን አልፎ ወደፎቅ የሚወስደውን ደረጃ ተያያዘው... መኝታ ቤቷን ቀስ ብሎ ገፍው፡፡ አንገቱን  አሰገገና  ወደ  ውስጥ  ተመለከተ... እንደዚህ ባለ ቅርበት ካያት  ብዙ  ቀናት  አልፈዋል....ፀጉሯ  ተንጨፍርሮና  እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ አስፈሪ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ሆዷ ከጀርባዋ የተጣበቀ ነው የሚመስለው ፤በጣም ከስታለች፤ አይኖቾ ኮርኒሱ ላይ እንደተሰካ ነው ወደ ውስጥ ዘልቆ ገባና መልሶ ዘጋው።በዚህ ጊዜ አይኖቾን አንከባለለችና ወደእሱ ተመለከተች
..የሆነ ነገር እንድትለው ፈልጎ ባለበት ተገትሮ ቆመ...፡፡
ምንም አላለችውም..ወደጥግ ሄደና ግድግዳውን አስጠግቶ ምንጣፉን አነጠፈ... እንደብዲስት መነኩሴ እግሩን አጣምሮ ቁጭ አለ።መፅሀፍን ከፊት ለፊቱ አስቀመጣና እጇቹን አቆላለፈ...ከዛ ልክ እንደእሷ ፀጥ አለ...ልዩነቱ የእሷ ፀጥታ በድንዛዜ ሲሆን የእሱ ፀጥታ በንቃት ነበረ...
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ባለፋ ሶስት ወር ውስጥ ተሰምቷት የማያውቅ ደስ የሚልና የሚያፅናና ስሜት ተሰማት…..እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቷን ለመታጠብ ወደ ሻወር ቤት ገባች፡፡ግዙፉ መስታወት ፊት ቆማ የለበስችውን ቢጃማ በቁሟ አወለቀችና እዛው ከእግሯ በታች ወለሉ  ላይ  ረገጠችው…መላ  እሷነቷን  በፅሞና  ተመለከተች…. ፀጉሯ በዛ ርዝመቱና ብዛቱ ጭብርር ብሎ ከመንግስት ተሰውሮ ዋሻ ውስጥ ለአመታት ተደብቆ የኖረ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ….አማላይ  የነበረው  የሠውነቷ ቅርፅ አሁንም እንዳለ ቢሆንም የሰውነቷ ክብደት ግን በተጋነነ ሁኔታ መቀነሱ ወደፊት ወጥተው በጉልህ የሚታዩት አጥንቶቾና  ወደ  ውስጥ  ጎድጉደው  ጭል ጭል የሚሉ አይኖቾ ምስክር ናቸው፡፡ከሁሉም በላይ ያስደነገጣት  ግን  የብልት ፀጉሯ ነው…ከስራዋ ባህሪ አንጻር ለአመታት በሶስት ቀን አንዴ ስትላጭ የኖረች ሴትዬ  ለወራት  ችላ  የተባለው  የብልቷ  ፀጉር  በአስፈሪ  ሁኔታ   አድጎና ተንጨፍርሮ እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ በመሀከል ስንጥቅ መኖሩን እራሱ በእጅ ዳብሰው ካልበረበሩት ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ አስደነገጣት….
….የቀኝ አጇን  ዘረጋችና  አንገቷን  ጠምዝዛ  ብብቷን  ተመለከተች  ..ተመሳሳይ ነው፡፡ በፀጉር ከመሸፈኑም በተጨማሪ ሽታ ከሩቁ ይገፋተራል፡፡ይሄ ሁኔታ ደግሞ ይበልጥ አስገረማት፡፡
‹‹ለምንድነው ግን በቁማችንም እያለን ጭምር ለጥቂት ቀናት ትኩረታችንን ከራሳችን ላይ ስናነሳ እንዲህ በፍጥነት የምንሸተው..?››ስትል ጠየቀች፡፡መልሱን ለመመለስ ግን ብዙም አላስቸገራትም፡፡  ምክንያቱም ከማሳጅ ስራዋ ጋ ተያይዞ ከወሰደቻቸው ኮርሶች አንደኛው የሰው ልጅ አመጋገብ ስርዓት በተመለከተ ነበር ፡፡ ከሺ አመታት በፊት የሞቱ ሰዎች መቃብር ተቆፍሮ ሲገኝና የጥርሳቸው ጤንነትና ጥንካሬ ሲፈተሸ አሁን ካለው የሰው ልጅ ጋር የማይነፃጸር እጅግ ንጹህና ጠንካራ  እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ምክንያቱም ደግሞ አመጋገባችን ሆኖ ነው የተገኘው፡፡አሁን አብዛኛው ምግቦች ከኬሚካል ጋ ንክኪ ያላቸው… ስኳርነት የበዛባቸውንና  ጤንነትን ሳይሆን ጥፍጥና መሰረት ያደረጉ ናቸው…ስለዚህ እነዚህ ገብተው ተፈጥአዊ ሰውነታችንን በክለዋል….በዛ ላይ ምንቀባቸው ቅባቶች የምንረጫቸው ሽቶዎች፤ የምንታጠብበት ሳሙና በጠቅላላ እንዲህ በቀናት ውስጥ በቁማቸንን እንድንሸት ዋና ምክንያቶች መሆናቸው ለመረዳት ብዙ ምርምርም አያስፈልግም፡፡ ወደመኝታ ቤቷ ተመለሰችና የቁም ሳጥኗን ኪስ ከፈተችና  የፀጉር  መላጫ ማሽኗንና መቀስ አውጥታ በመያዝ ወደ ሻወር ቤት ተመለሰች፡፡ምንም ማሰብ እና መጨነቅ አላስፈለጋትም፡፡ከፀጉሯ ጀመረች…..ከርዝመቱ ወጥራ ወደፊት እየያዘች…..ወገብ ላይ ትጎምደው ጀመር፡፡ ወለሉ በተንጨባረረ እና በተቆጣጠረ
ፀጉር ተሞላ፡፡ ባለከመከም ጎፈሬ ሆነች፡፡በመስታወቱ የተለየች አይነች እስከዛሬ እሷ ራሷ ማታውቃት አይነት ሳባን ተመለከተች፡፡መቀሷን አስቀመጠችና ማሽኗን አመቻቸችና ወደብልቶ ጎንስ ብላ እግሯን ፈርከክ በማድረግ ታጭደው ጀመረ…..ሁሉን ነገር ጨርሳ ሰውነቷን  ታጥባና  ፀድታ ከሻወር ለመውጣት ከ2 ሰዓት በላይ ነው የፈጀባት፡፡
ከዛ ወደመኝታዋ ተመልሳ የተወሰነ እረፍት አደረገች.. ከተኛበት  ብንን  አለችና ስልኳን አነሳች፡፡ እንዲህ አይነት ጥንካሬ እና ፍላጎት በደቂቃ ውስጥ ከየት እንዳመጣች አታወቅም፡፡ደወለች..ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ዶክተር››

‹‹ሳባ ለመሆኑ በህይወት አለሽ…?ምን ነካሽ…?ሌላ ሌላው ይቅር እሺ ህክምናሽን ግን እንዴት ታቋርጪያለሽ…ያልተመቸሽ ነገር ካለም እኮ ተነጋግረን ማስተካከል እንችል ነበር..››
‹‹ምን አልተመቻትም ብለህ አሰብክ…ያደረኩት ነገር አግባብ ነበር እንዴ?›ስትል መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን ከህክምናሽ ጋር ምን አገናኘው..ምን አልባት በእኔ ህክምናውን መከታተል የሚከብድሽ ከሆነ እኮ በሀገሪቱ ያለሁት የስነ-ልቦና ሀኪም እኔ  ብቻ አይደለሁም
… ተነጋግረን ሁኔታዎችን መስመር ማስያዝ እንችል ነበር››

‹‹ኖኖ ዶክተር እንደዛ አስቤ አይደለም…እኔ እንደውም አንተ ካላከምከኝ ማንም ሊያክመኝ አይችልም››አለችው፡፡
የተናገረችው ትክክል ይሁን አይን እራሷም እርግጠኛ አይደለችም…እርግጥ ከእሱ ውጭ በሌላ ሀኪም መታከም አትፈልም….ደግሞም በእሱም ቢሆን መታከሙን የምትችል መስሎ አልተሰማትም፡፡ህመሟ አካላዊ ቢሆን ችግር የለውም፡፡ ጉበቷ ወይም ኩላሊቷ ቢሆን ወይም ማህፀኗን አሟት ልብሶቾን አወላልቃ እግሮቾን አንፈርክካ መላ ሚስጥሯን ለእሱ  ማሳየት  ቢሆን  ምንም  አይመስላት ነበር፡፡…..እሱ ፊት ስትቀርብ ከኤፍሬም  ጋር  በገዛ  ምርመራ  ክፍሉ  የሰራችው ነውር ነው ትዝ የሚለው የገዛ ወንድሙን ስታማግጥበት…ዝግንን አላት፡፡
‹‹እና ታዲያ ለምን እራስሽን  ሰወርሽ….?እንዴት  እዲህ  ይጠፋል…..?ደግሞ ለህክምና ፋይል ላይ ያስመዘገብሽ መረጃ በጠቅላላ የተሳሳተ ነው….አድራሻሽን ጭምር  ..አንድ ትክክል የሆነው ስልክ ቁጥርሽ ቢሆንም እሱንም ጠርቅመሽው ይሄው ስንት ወር፡፡››

ደስ አላት…ስለእሷ እንዲህ ሲጨነቅና ሲብሰለሰል መክረሙ ደብዝዞ እና ሊከስም ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረ ተስፋዋ በጥቂቱም ቢሆን ቢል ቢል እያለ  እንዲነቃቃ ተጨማሪ ነዳጅ ሆኖ ሲያነቃቃት ተሰማት፡፡
‹‹እና አሁን እንዴት ነሽ…?የት ነሽ..?ሀገር ውስጥ ነሽ?››

‹‹አዎ እዚሁ ነኝ፡፡››

‹‹እና እንዴት ነሽ?፡፡››

‹‹እኔ እንጃ ..ምን ላይ እንደሆንኩ አላውቅም…እንዴት እንደሆንኩ አላውቅም….. መኖሬን እራሱ አላውቅም….ለምን አሁን አንተ ጋ እንደደወልኩም አላውቅም….
››አለችው፡፡

ከንግግሯ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከወራት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ካገኛት እጅጉኑ የከፋ እንደሆነ ወዲያው ተረዳ….ስለእሷ ሲያስብና   ሲጨነቅ   የከረመው   ግን ከዚህም የከፋ ነገር ላይ እራሷን ትጥላለች ብሎም ጭምር ስለሰጋ ነበር…እራሱን ያጠፋ ሰው ዜና በሶሻል ሚዲያም ሆነ በሜን እስትሪም ሚዲያ ሲሰማ ደንግጦ በንቃት ዜናውን እስከመጨረሻው ለማየት ሲጥር የነበረው እሷን አስቦ ነው፡፡አሁን  ግን በከፋ ሁኔታ ላይም ሆና ቢሆን በህይወት መኖሯ ብቻ አስደሰተው፡፡
‹‹አይዞሽ ይሄ በማንኛውም ሰው ላይ በሆነ ጊዜ ላይ የሚከሰት ነው..አንቺ ደግሞ ከዕድሜሽ በላይ ብዙ ነገር ያየሽና ብዙ ነገር ምታውቂ ጠንካራ ልጅ ነሽ...እኔም ደግሞ በፈለግሽኝ ጊዜና መንገድ ከጎንሽ ነኝ፡፡››
‹‹አንተ ከጎኔ መሆንህን በመስማቴ ተደስቼያለሁ…አመሰግናለሁ፡፡››

‹‹እና መች ብቅ ትያለሽ?›

‹‹እኔ እንጃ››አለችው የምትለው ግራ ገብቷት…

‹‹እኔ  እንጃ  ማለት  ምን  ማለት  ነው…ህክምናው  ቢቀር  አንኳን  ናፍቀሺኝል… ሆስፒታል መምጣት ካስጠላሽ የፈለግሺው ቦታ መገናኘት እንችላለን፡፡››
‹‹ካልክ ነገ ስንት ሰዓት ይመችሀል?››

‹‹እንቺ የሚመችሽን ሰዓት ነገሪኝ እኔ ፕሮግራሜን አሬንጅ ማድረግ እችላለሁ›› እሷን ከማግኘት የሚቀድምበት ምንም ጉዳይ የለውም፡፡
‹‹በቃ 10 ሰዓት እንገናኝ..››

ደስ አለው….‹‹እሺ የት እንገናኝ?›› ነገረችው
‹‹ችግር  የለም….እንገናኛለን…››

‹‹እሺ ዶ/ር ….አመሰግናለሁ››