አትሮኖስ
228K subscribers
104 photos
3 videos
41 files
303 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹የሚያስቸኩልሽ ነገር የለም›› አለ ኮንስታብሉ ‹‹አባትሽ ሊወስዱሽ
እየመጡ ነው፡፡››

የማርጋሬት ልብ በድንጋጤ ቀጥ አለ፡ እንዴት ሊሆን ይችላል? አሁን
ያለችበት ቦታ አባቷ የማያውቁት ስለሆነ ደህነኛ ቦታ ነው ብላ ተማምና ነበር፡፡

አባቷን ዝቅ አድርጋ ነበር የገመተቻቸው፡ በዚህ ደቂቃ ውስጥ ሊይዟት ይመጣሉ! ሃሳቡ አንቀጠቀጣት ‹‹የት እንዳለሁ እንዴት አወቀ አባባ?›› አለች፡፡

ወጣቱ ፖሊስ በኩራት ‹‹ትናንት ማታ ስለመጥፋትሽ የቴሌግራም መልዕክት ደርሶን ነበር፡፡ ስመጣ አየሁት፡፡ በጨለማ የመጣሽ ጊዜ
አላወቅኩሽም ነበር፡፡ ስምሽን ግን አስታወስኩት፡፡ ከተገኘሽ ለጌታ ኦክሰንፎርድ
እንዲነገራቸው ቴሌግራሙ ያዛል፡፡ እዚህ እንዳመጣሁሽ ለአባትሽ ደወልኩ››

ማርጋሬት ብድግ አለች፧ ልቧ በጣም ይመታል፡፡ ‹‹እሱን አልጠብቅም
አሁን ነግቷል›› አለች፡፡

ፖሊሱ ስጋት ገባው ‹‹ትንሽ ቆይ›› አለ፡፡ ዞር አለና ‹‹ሃምሳ አለቃ እመቤት ማርጋሬት መሄዴ ነው እያለች ነው›› ብሎ ነገረው፡፡
ሄሪ ማርክስ ‹‹እዚህ ይዘው ሊያቆዩሽ አይችሉም ባንቺ እድሜ ከቤት ጠፍቶ መሄድ ወንጀል ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ መሄድ ከፈለግሽ ቀጥ ብለሽ
ሂጂ›› አላት፡፡

ሃምሳ አለቃውም ‹‹ነገር ግን ጫማ የለሽም፤ ስቶኪንግሽ ተቀዳዷል፡፡ አባትሽ ጋ ልደውልልሽ›› አላት፡፡
ማሰብ ጀመረች፡፡ ጣቢያ እንደደረሰች ነው ለአባቷ ስልክ የተደወለው፡፡
አሁን አንድ ሰዓት አልሞላውም ማለት ነው፡፡ አባቷ ደግሞ ከዚህ በኋላ
እዚህ ለመድረስ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በላይ ይፈጅባቸዋል፡ ‹‹ደህና›› አለች ለደጉ ፖሊስ ‹‹አመሰግናለሁ፡፡››

ሄሪ ወደ ፖሊስ ስታዘግም አየና ‹‹ጅል›› አላት፡፡
ፖሊሱ አንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ ወስዶ አስገባት፡፡ ወንበሮቹ ተራ ናቸው፡
አንድ አግዳሚ ወንበር ይታያታል፡፡ ከላይ ማቀፊያ የሌለው አምፑል ተንጠልጥሏል፡ መስኮቱ በብረት ፍርግርግ ተዘግቷል፡ ሃምሳ አለቃው ይህ
ክፍል ከባለጉዳይ መቀበያው ክፍል የተሻለ ነው ብሎ እንዴት እንዳሰበ
አልገባሽ አላት፡፡ ልትነግረው ዞር ስትል በሩን ፊቷ ላይ ጠረቀመው፡፡ አንድ
ክፉ ነገር እንዳለ በልቧ ጠረጠረችና ፍርሃት ገባት፡፡ ተወርውራ በሩ ጋ ሄዳ
ለመክፈት ታገለች ከዚያም ፍርሃቷም እውነት መሆኑን በሩ ሲቆለፍ አረጋገጠች፡፡ የበሩን እጄታ በሃይል ነቀነቀችው፤ ነገር ግን በሩ የሚከፈት አልሆነም በተስፋ መቁረጥ በሩ ላይ ልጥፍ አለች፡፡

ከውጭ በኩል ሳቅ ይሰማታል፤ ከዚያም ሃሪ ‹‹እናንተ እርጉሞች›› ሲል
ተሰማት ‹‹አፍክን ዝጋ›› አለው ፖሊሱ፡፡

‹ምንም መብት የላችሁም ልጅቷን ለማቆየት፤ አንተም ታውቃለህ አለው።

‹‹አባቷ የተከበሩ ሰው ስለሆኑ ነው እንደዚህ ያደረኩት›› አለ፡

ማርጋሬት ያሰበችው ባለመሳካቱ በምሬት ተንገበገበች፡ የማምለጥ
እቅዷ ውሃ በልቶታል። ይረዱኛል ብላ የገመተቻቸው ሰዎች አታለዋታል ለትንሽ ጊዜ ነፃ
ነበረች አሁን ግን ነፃነቷ አብቅቷላተል ምድር ጦር
መምሪያው መሄድ አለመቻሏ አንገበገባት
ከጦርነቱ ለመሸሽ የፓን አሜሪካ ንብረት በሆነችው አይሮፕላን ተሳፍራ ኒውዮርክ ልትሄድ ነበር። ይህን ያህል ደክማም እድሏ አልሰምር አላት፡፡

ከብዙ ቆይታ በኋላ ከበሩ ወደ መስኮቱ ሄደች። በመስኮት አጮልቃ
ስታይ ምንም ነገር የማይታይበት ጓሮና የሸክላ ግድግዳ ብቻ ነው::
በሽንፈትና በአቅመቢስነት መስኮቱ ጋር ተገትራ የአባቷን መምጣት
ከመጠባበቅ በስተቀር ምንም ምርጫ አልነበራትም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኤዲ ዲኪን ለአይሮፕላኑ የመጨረሻ ፍተሻ አደረገ እያንዳንዳቸው የ1500 የፈረስ ጉልበት ያላቸው አራቱ ሞተሮች የተቀቡት ዘይት ያብለጨልጫል፡ እያንዳንዱ ሞተር የሰው ቁመት አለው። ኤዲ እያንዳንዱን የሞተር ክፍል መርምሮ ሲጨርስ ዘጋጋና ከመሰላሉ ላይ ወረደ። አይሮፕላኑ ለበረራ ሲዘጋጅ ቱታውን ያወልቅና ሰውነቱን ታጥቦ የአየር መንገዱን የበረራ ዩኒፎርም ይለብሳል።

ከአይሮፕላን ማረፊያ ወደቡ ወጥቶ ሲሄድ ፀሀይ ገና አልጠለቀችም፡ከዚያም የስራ ባልደረቦቹ ወደሚገኙበት ሆቴል አመራ: በአይሮፕላኑና
በሚሰራው ስራ ይኮራል። አትላንቲክ አቋራጭ በረራ ከሁሉም የበረራ ስራ
የበለጠ ስለሆነ አየር መንገዱ ያሰማራው አሉ የሚላቸውን የበረራ ሰዎች
ነው።

ሆኖም ይህን ስራ በቅርቡ ለመተው አቅዷል፡ አሁን እድሜው ሰላሳ ሲሆን ትዳር ከያዘ ዓመት ሆኖታል። ሚስቱ ካሮል አን ነፍሰ ጡር ናት ይህ ስራ ለወንደላጤ ምንም አይልም እሱ ግን ከቤተሰቡ ርቆ መኖር
አይፈልግም፡ የራሱን ስራ ለመጀመር በቂ ገንዘብ አጠራቅሟል፡ አሜሪካ
ውስጥ ይህን ስራ ለመስራት የሚያስችለው አየር ማረፊያ አለ፡፡" አይሮፕላን ይጠግናል፣ ነዳጅ ይሸጣል፡ በኋላም አይሮፕላን ገዝቶ ያከራያል፡

ሆቴሉ ውስጥ ሲገባ ረዳት ኢንጂነሩን ሚኪን አገኘው፡ ሚኪ ተጫዋች ሲሆን ኤዲን በችሎታው ይወደዋል። ሚኪ ስልክ እየተነጋገረ ሳለ ኤዲንን
ሲያይ ‹‹እድለኛ ነህ አሁን መጥቷል ላገናኝህ›› አለው ለደዋዩ ‹‹አንተን ነው
የሚፈልገው›› ብሎ የስልኩን መነጋገሪያ ለኤዲ ሰጠና ብቻውን መነጋገር
እንዲችል ጥሎት ሄደ።
ኤዲም ስልኩን ተቀበለና ‹‹ሄሎ?›› አለ፡

‹‹ኤድዋርድ ዲኒኪን ነህ?›› ብሎ ጠየቀ ደዋዩ፡፡

ኤዲ ግንባሩን በግርታ ቋጠረ፡ በስልክ የሚሰማው ድምጽ አዲስ ሆነበት ከዚህ በፊትም ማንም ኤድዋርድ ብሎት አያውቅም፡፡ ‹አዎ ነኝ
ማን ልበል?›› አለ፡

‹‹ቆይ ትንሽ ጠብቀኝ ባለቤትህን ላገናኝህ አጠገቤ ነው ያለችው›› የኤዲ ልብ ተንጠለጠለ ካሮል አን ለምንድነው ከአሜሪካ የደወለችልኝ ችግር አለ ማለት ነው?› ሲል ተጨነቀ፡፡

ከአፍታ በኋላ የካሮል አን ድምጿ ተሰማ ‹‹ኤዲ›› አለች እምባ እየተናነቃት፡

‹‹እንዴት ነሽ ማርዬ ምን ሆነሻል?››

ካሮል አን የባልዋን ድምጽ ስትሰማ ለቅሶዋን ለቀቀችው።

ኤዲ በዚያች ደቂቃ ውስጥ ክፉ ነገር አዕምሮው ውስጥ አቃጨለበት፡
‹ካሮሌ ላይ ምን ደርሶባት ይሆን? ውርጃ ገጠማት ይሆን? ቤቱ ተቃጠለ?
ማን ይሆን የሞተው? የሚሉ ሃሳቦች በአንድ ላይ መጡበት፡፡

«ካሮል ተረጋጊ ደህናም አይደለሽ?››

‹‹አይ ምንም አልሆንኩም›› አለች እየተነፋረቀች፡

‹‹ታዲያ ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺው?›› አለ ሆዱ በፍርሃት እየተንቦጫቦጨ፡

‹‹ምን ተፈጠረ ንገሪኝ የኔ ውድ?››

‹‹እነዚህ ሰዎች እቤት መጡ››

ኤዲ ይህን ሲሰማ በድንጋጤ የበረዶ ክምር ሆነ ‹‹የምን ሰዎች? ምን
አደረጉሽ?››

‹‹መኪና ውስጥ ከተው ወሰዱኝ››

‹‹ወይ አምላኬ! ማን ናቸው?›› ንዴቱ ደረቱ ላይ ውጋት ለቀቀበትና
መተንፈስ አቃተው፡

‹‹ጎድተውሻል?››

‹‹አይ ደህና ነኝ፡ ነገር ግን ኤዲ ሰዎቹ ያስፈራሉ››
ምን እንደሚል ጨነቀው፡ ብዙ ነገሮች አዕምሮው ውስጥ መጡበት፡፡"
የሆኑ ሰዎች ሚስቱን አግተዋታል፡፡ ምንድነው ነገሩ? በመጨረሻም
‹‹ለምን?›› ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹ምክንያቱን አልነገሩኝም››

‹‹ምን አሉሽ?››

‹‹ኤዲዬ የሚሉህን በሙሉ አርግላቸው፡፡ የማውቀው ይህን ብቻ ነው››

ንዴትና ፍርሃት እየተፈራረቁበት ‹‹አንቺን ከሚያሰቃዩብኝ ያሉትን
አደርግላቸዋለሁ›› አለ፡፡

‹‹እውነት?››

‹‹አዎ የኔ ማር››

‹‹ተመስገን አምላኬ ላንተ ምን ይሳንሃል›› አለች ካሮል አን።

‹‹መቼ ነው ያገቱሽ?››

‹‹ከሁለት ሰዓት በፊት››

‹‹አሁን የት ነው ያለሽው?››

‹‹ከኛ ቤት ብዙም አይርቅም.›› ብላ ሳትጨርስ የድንጋጤ ጩኸት
አሰማች፡፡
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ዲመካና ቱርሚ ሁለቱም የሐመር አውራጃ የገጠር ከተሞች ናቸው" ለቆላማው የሐመር ክፍል ቱርሚ፣ ለደጋማው ደግሞ ዲመካ
አማካዮች ሲሆኑ፣ ሁለቱም ደረቅና ቁጥቋጦ የበዛበት መሬት ያላቸው ናቸው። ቱርሚ መንገድ ዳር ያለ ከተማ ሲሆን፣ ከዲመካ ይልቅ ሁለት ትናንሽ ምግብ ቤቶች፣ ወደ አምስት የሚደርሱ ሻይና ቂጣ
መሸጫ ቤቶች፣ ሁለት በመጠን ከፍ ያሉና ትናንሽ ሳሙና፣ ባትሪ ድንጋይ፣ ክብሪት...የሚሸጥባቸው መንገድ ላይ የሚዘረጉ ሱቆች አሉ። በተለይም በገበያ ቀን ከተማዋ ደመቅዐመቅ ብላ ትታያለች
ገበያ ውስጥ ለመጠጥ ቦርዴና የአበሻ አረቄ፣ ግልድም የሚሆን ከጥጥ
ተሠርቶ ከኮንሶ በነጋዴዎች የሚመጣ ሳዳጎራ፣ ጨሌና አንባር፣በቆሎና ማሽላ ዓይነተኛ ሸቀጦች ናቸው" ቱርሚ፣ በከብት እርባታና
በቁፋሮ ምርት ለሚተዳደረው የሐመር ሕዝብ ድል ያለች ከተማ፣
ታምሮና ተውቦ የሚታዩባት፣ ጐረምሳና ሴቱ አብሮ መሸታ ገብቶ የሚደባበስባት፣ የተጣላ የሚታረቅባት፣ ሽማግሎች ተሰባስበው
የሚመክሩባት፣ ብርቅዬ ከተማ ናት ለሐመሮች።

ዲመካ ግን፣ ከዋናው መንገድ ወጣ ብላ፣ ሰቀላ ቤቶች በአራት ማዕዘን ተሰትረው የሚታዩባት ከተማ ናት። በየሰቀላ ቤቶች ፊት ለፊትና በስተኋላ የግራር፣ የብርብራ.ዛፍ ያለ ሲሆን ከከተማው ግርጌ፣ ከወንዙ ጥግ በሚስዮናውያኑ የተተከለ በፀሐይ ብርሃን በሚንቀሳቀስ መስኖ የለማ የፍራፍሬ፣ የበቆሎና ሌሎችም ወቅታዊ
አዝርእቶች የሚታይ ሲሆን፣ ከጎን በኩልም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሕንፃና ጋራዡ፣ ዲመካን አንድ ዓይና ከመሆን አድኗታል"የገበያ ቀን፣ በየሰቀላ ቤቱ ጠጅ የሚሸጥ ሲሆን፣ ምግብ ቤት ግን ከናካቴው የለም" ደግነቱ፣ እንግዳ ብርቅ በመሆኑ ጋባዡ ብዙ ስለሆነ
እግር የጣለው ሰው ሕቅ ብሎ ሲያዝን አይሰማም" በተረፈ ገበያ ውስጥ ያለው ሸቀጥ ከቱርሚ ጋር ተመሳሳይ ነው ሁለቱንም ከተሞች ቡስካ ስር ካሉት ላላና ሻንቆ እስከ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዳ
መንደር ድረስ የሚያገናኛቸው የማኅበረሰብ ሕይወት የሆነው የከስኪ ወንዝ ነው ከብቱ፣ ፍየሉ፣ በጉ፣ ሰው፣ አዕዋፍ...ሁሉም ጥሙን
ይቈርጥበታል።

ካርለትና ከሎ ሆራ ከዲመካ ወጣ ብላ ከምትገኘው የሻንዛ መንደር መኖር ከጀመሩ ሁለት ወራት አለፋቸው የክልሉ ኗሪዎ
ከሎ ሆራን እንዳዩ፣ «የሆራ ሻላ ልጅ» እያሉ፣ ሰላምታና ስጦታ አጐረፉለት ቆዳ ለባሽ እናቱና እኅቶቹም ደረታቸውን በመድቃት
የደስታ እንባ እያነቡ አስተናገዱት።

ካርለት፣ በቆይታዋ የተለያዩ ልምዶችን አገኘች። ከዘመናዊ ሕይወቷ እንደ ባንዲራ ወርዳለችI ይህን አጋጣሚዋን ግን በግላዊ
ትርጕሟ እንደ መጥፎ ከመውሰድ ይልቅ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰዷ የሚሰማት ስሜት የደስታ ስሜት ነው። ይህ ደግ
ማኅበረሰቡን ለመቅረብና ለመርዳት እንድትጣጣር አድርጓታል ስለዚህ፣ ካርለት የከሎ ሆራን እናትና እኅቶች፣ የአካባቢው ሴቶችና ወንዶች ለመቅረብ የቋንቋ ትምህርቷን በማጠናከር ልትግባባ ሞክራለች ቢሆንም ግን፣ በወደፊቱ ጥናቷ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት
እየሆነባት የመጣው በሴቶች ላይ ያለው ባህላዊ ተፅዕኖ እንደ ጋለ ብረት ምጣድ አላስጠጋሽ አላት"¸

በማኅበረሰቡ፣ ሴት ሣቂታ ወንድ ኰስታራ ነው" ሴት በልጃገረድነቷ የአባቷ፣ ባል ካአገባች ደግሞ የባሏ ጥገኛ ናት" ስለዚህ
በልባዊ ኵራት የተሞሉት የሐመር ወንዶች ካርለት ሴት ሆና እንዴት ባሏን ወይንም አባቷን ጥላ ወደ እነሱ እንደ መጣች በጣም
አስገርሟቸዋል" ሽማግሎች እንዲያውም፣ «ይእ! እሷ ምን ታድርግ? አባቷ ወይም ባሏ፣ ብቻዋን መልቀቃቸው ከቶ ምን ያሉ ነፈዞች ቢሆኑ ነው» ብለው አውግዘዋል"
ስለሆነም፣ ካርለት የጥናት ኮተቷን ይዛ ለጥያቄ ቀረብ ባለቻቸው ቍጥር የደስታ ገጽ ስለማታይባቸው ለተወሰነ ቀን ግራ ተጋብታ
ነበር" አንድ ቀን ግን ወንዶች ሊያደርጉት ባሰቡት ስብሰባ ለመካፈል ሄደች። ገላጣ ስፍራ ላይ ካለ ትልቅ ግራር ጥላ ሥር፣ የሻንቆ መንደር
ሽማግሌ፣ አባወራ፣ ጐረምሶች ተሰብስበዋል" ከወገብ በላይ ራቁት
ሆነው፣ ቆዳቸው የተሸበሸበ፣ ጸጕራቸው ገለል ብሎ ሽበት ጣል
ጣል ያደረገበት አዛውንት በሁለት ወገን ጦር የተሰካበት ብትር ይዘው፣ መሬቱን ወጋ ነቀል እያደረጉ ወዲያ ወዲህ እየተንቀሳቀሱ
ንግግር ሲያደርጉ ሁሉም ጸጥ ብሎ በተመስጦ ሲያዳምጥI ካርለት
ስብሰባውን ለመካፈል ጓጕታ ቀስ እያለች ተጠግታ ልትቀመጥ ስትል
ሁሉም ዘወር ብለው አይዋትና በስብሰባው መካፈል እንደማትችል
ነገሯት"

ካርለት፣ ወንዶችን ለመቅረብ አለመቻሏ ብቻ ሳይሆን፣ ሴቶችም
ምሥጢራቸውን ሊገልጹላት ባለመቻላቸው ግራ ተጋብታ ቅር ተሰኘች" በተለይ ደግሞ፣ ለመሳተፍ ጓጕታለት በነበረው የወንዶች
ስብሰባ ልትካፈል ባለመቻሏ ጥልቅ ኀዘን ከመስማት አልፎ ለወደፊቱ አደርገዋለሁ ብላ የደከመችለት ጥናት ሊሳካ አይችልም ብላ ሠጋች"
ስለዚህ፣ ዓይኗ ቁንዶ በርበሬ መስሎ እስኪቀላ ድረስ እያለቀሰች፣ «ከሎ! ለምን ወንዶች ጥያቄዎቼን ለመመለስ ፈቃደኛ
አይሆኑም? ለምንስ በስብሰባቸው እንዳልካፈል ይከለክሉኛል? በዚህ
ዓይነት ጥናቴንስ እንዴት ማድረግ እችላለሁ? » ብላ ጠየቀችው።

«በሐመር ማኅበረሰብ ሴት ወንድን ለመርዳትና ለማገልገል የተፈጠረች ጸጋ ናት። ለወንዶች ትንባሆ ታዘጋጃለች ልጃገረድ
ከሆነችም ታርሳለች፤ የከብቶችን በረት ታጸዳለች ሕፃናትን ትንከባከባለች ምግብ ታበስላለች.እንጂ ከወንድ ጎን ተቀምጣ ስለ
ማኅበረሰቡ ችግር በመነጋገርና በመምከር መፍትሔ መፈለግና ጦርነት
መግጠም አትችልም።

«ካርለት፣ አንቺ ወንድ ብትሆኚ ኖሮ ምንም ችግር ላያጋጥምሽ ይችል ነበር" ሆኖም ግን አንቺ ሴት ነሽ። ለሐመር ሴቶች የወጣው
ደንብ ማንኛዋንም ሴት ያጠቃልላል፣ ብለው ስለሚያምኑ በስብሰባቸው እንድትካፈይ አለመፍቀድ ብቻ ሳይሆን፣ የምትጠይ
ቂያቸውንም ሙሉ በሙሉ ለመመለስ ፈቃደኛ አይሆኑም" እኔም
ይህ ችግርሽ እጀ ሰባራ ሊያደርግሽ እንደሚችል እየተሰማኝ መጥቷል" ምናልባትም ችግሩ ግልጽ ከሆነልሽ የግልሽን መፍትሔ
ውሰጂ» አላት"

ካርለት ፈጽሞ ያልጠበቀችውን መልስ በማግኘቷ በባህላዊ
ልዩነቱ በጣም ተሸማቀቀች በአሁኑ የጥናት አያያዟ በእርግጥ ለመቀጠል አለመቻሏ ቁልጭ ብሎ ታያት በአእምሮዋ አውጥታ
አውርዳ የወሰነችው ውሳኔ፣ እስከ አሁን ያደረገችው ጥረትና ጒዞ ጥሩ የድንጋይ ምት እንዳረፈበት መስተዋት ከሽ ብሎ ሊሰበር
የተቃረበ መስሎ ታያት። ያ ችሎታዋንና ጥንካሬዋን የሚያስመሰክረው፣ ማንነቷን የሚያረጋግጠው፣ ብቃቷን ማያዋ መስተዋት
እንዲሰበር ግን ጭራሽ አትፈቅድም። በዚህም ተባለ በዚያ የጀመረችውን ከግቡ ለማድረስ ሕሊናዋ እሷን ወደፊት መግፋት
አለበት" ሰዎች ከጎሪላና ከእፉኝት፣ ከአንበሳና ከተኩላ ጋር በሐሩርና
በረዶ መኖር መቻላቸውን አስመስክረዋል" እሷም ዓላማዋን ከግቡ
ለማድረስ ተጣጣፊና ጠንካራ ለመሆን ከራሷ ጋር ተማማላች" ግን ምን መላ ትምታ? ለተወሰነ ቀን ካለ ዕረፍት በዚህ ጉዳይ ላይ ስታስብ ከቆየች በኋላ ምንም እንኳ የችግር ኮተቱን ዓይኗን ጨፍና አላይም
ብትልም፣ የሚያጋጥማት ሥቃይ ከባድ መሆኑን አውቃ ቀበቶዋን አጠበቀች

ከዚያም፣ ያሰበችውን መላ ለመጀመር ያስችላት ዘንድ ባል አለማግባቷን የሚገልጽ ወሬ ለአገኘችው ሁሉ አወራች" ወሬው ተዛምቶ በየመንደሩ መዳረሱን ስታረጋግጥ ደግሞ ጐረምሶች፣ ወጣት
ባለትዳር ወንዶች፣ ያላገቡና ባለ እጮኛ ልጃገረዶች ምሽትን ተገን አድርገው ወደሚቦርቁበት የምሽት ጭፈራ «ኢቫንጋዲ» ለመካፈል ነኢማ ከምትባለው የከሎ ሆራ እኀት ጋር ስትሄድ ምንም ተቃውሞ ሳይደርስባት ቀረ።
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ

መጀመሪያ የደራረቀ እንጨትና ግንድ ቀጥላ ለጉልቻ የሚሆን ሦስት ድንጋይ አቅርባ እሳት አቀጣጠለችና ውሃ የያዘውን
ቶፋ ወደ አንደ በኩል ዘንበል አድርጋ ጣደችው ከዚያ በለሻ እንዲበላ ስታቀብለው “አንችስ ብይ እንጂ ተወተቱም ጠጭ…"
አላት ጭብጦውን እያላመጠ።

ይእ! ይልቅ አታስቀምጠው ጠጣው። የኔ በኋላ ይደርሳል“ ብላ በጨንዋዛ ቅጠል የተቋጠረውን ሽፈሮ ቡና ፈታ በሚቆለቆሰው
እሳት በመቅጃው የቅል ጭልፋ ዙሪያ ትጉልጉል የሚለውን እንፋሉት እንዳያቃጥላት ተጠንቅቃ የቡና ገለባውን ጨመረች:

ሰማዩ ላይ እንደ ጨሌና ዛጎል ከዋክብት ሆጨጭ ብለዋል። በስተ ሰሜን በኩል ደግሞ ብናኝ ዳመና አቅፎ የያቸው ከዋክብት
ብልጭ ድርግም... ይላሉ: የምሽት በራሪዎች የሌሊት ወፍ ጉጉት የማታ ተረኞች ሆነው ወዲህ ወዲያ ይበራሉ: ጅብ ይጮሃል
አንበሳው ያገሳል... ጦጣና ዝንጀሮ ፀጥ ብለዋል: ጉሬዛዎች ግን እንደ ዶሮ ሰዓት እየጠበቁ “ጉርር ጉርር. ጉርርርር..." እየተቀባበሉ ያውካኩና ጸጥ እረጭ ይላሉ።

ዳራና ደልቲ በሚነደው የሳት ወላፈን እሷ አንድ ጉልበቷን
አጥፋ መሬት ላይ አጋድማ፧ ሌላውን ጉልበቷን አጥፋ አቁማ አልፎ አልፎ እንጨቱን ቆስቆስ እያደረገች አይኖችዋን ጨለማው ውስጥ ተክላለች።

ደልቲ በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ የአባቱን ከዋክብት እንደ እሳት እየተንቦገቦጉ ቁልቁል ተወርውረው የሚጠፉትን “ሚቲዎሮች”
እያየ ያስባል።

በሁለቱ መካከል ንግግር የለም:: ፀጥታ ሆኗል: በሐመር ባህል የቡና ሥነሥርዓት እርጋታና ፀጥታ የሰፈነበት ነው:: ህፃናት
እንኳን ይህን ስለሚያውቁ  ቡረቃቸውን ገተው ያደፍጣሉ። ሴቷ ወንዱ ሽማግሌው ከራሳቸው
ጋር የሚነጋገሩበት ራሳቸውን የሚመዝኑበት አደብ የሚገዙበት በጎና እኩይ ተግባራቸውን የሚፈትሹበት... ነው የቡና ሥነ ሥርዓት ለሐመሮችሽማግሌ
ትናንትን የሚያደንቅበት ዛሬን የሚያመሰግንበት ነገን በተስፋ የሚጠባበቅበት ግለሰቡ ለማህበረሰቡ ደህንነት ሰላምን፡ ጥጋብን የሚመኝበት የአባት የአያት ደንብ ወደ ልጅ የሚሸጋገርበት ጠላትና ወዳጅ ጠንቅቆ የሚታወቅበት ምላስ አጥራ ህሊና ገዝፎ መግባባት የሚመጣበት ነው የቡና ሥነ ሥርዓት። ይህ የቡና ሥነሥርዓት ለህፃን ለወጣት ለአዋቂ ለሽማግሌ ለእንግዳ ክፍት ነው። ያሻው ሁሉ ይሳተፋል እድሜና ደረጃውን ጠብቆ ይዳረሳል። የሐመር በር መዝጊያ የለውም። የሐመር ሕይወት ጓዳ የለውም፡ የሐመር ማህበረሰብ “ከሌላው ኪስ ወስደህ የኔን ኪስ ሙላ በሚል ስግብግብነት ምኞት ላይ አልተመሰረተም።

ደስታ ችግር ጦርነት... የጋራ ነው: የአንዱ ምርኩዝ ሌላው ነው: ግለሰብ ህብረተሰብን አይረሳም። ህብረተሰቡም ግለሰቡን
አይጥልም ያሳድገዋል ሃብት ያካፍለዋል ይድረዋል ለጀግንነቱም
ያሞግሰዋል...

ስሰዚህ ደልቲና ዳራ ምንም እንኳ ጫካ መሃል ብቻቸውን ቢሆኑም ህሊናቸውና አካላቸው ግን በባህላቸው ደንብና ሥርዓት
የተገነባ ነው: ፀጥታው ተጠብቆ ዝምታው ሰፍኖ እሱም ሆነ እሷ ትናንትን ቃኝተው ዛሬን አስታውሰው ነገን ሲያልሙ በሐሳብ
ተውጠው ቆዩ።

ከዚያ ዳራ ሾርቃውን ጠረግ ጠረግ አረገችና የቅል ማንኪያውን አንስታ ቶፋው ውስጥ ጨምራ ከቡናው ሁለቴ ቀድታ ሰጠችው ደልቲ ቡናውን ለማብረድ ግራና ቀኝ ጎለል አደረገና ፉት ብሎ “ፕስስ ፕስስ.." እያለ ወደ ምስራቅ ምዕራብና ወደ መሬት የሸፈሮ ቡናውን አርከፍክፎ- “የአባቴ ሰማይ ዝናብ ይጣል በሽታዎች ከሐመር ምድር ይጥፉ፤ ከብቶች  ፍየሎች በጎች
አያገሱ  በሰላም ይግቡ ይውጡ..." ብሎ መረቀና ወደ  ዳራ ዞሮ ቡናውን ፉት ብሎ “ፕስስ..” አለና ሽፈሮ ቡናውን አርከፈከፈባት፡

ዳራ ደንገጥም አፈርም ሳትል አይኗን ከወረወረችበት
ሳትመልስ በሃሣብ እንደሰመጠች
“..ተባረኪ... ዘርሽን ያብዛው የአባትሽ የሐመር ምድር የልጆችሽ መቦረቂያ ይሁን... የባልሽ ጥገት ይብዛ" ብሎ መረቃትና ቡናውን በፀጥታ መጠጣት ጀመረ።

ሰረቅ አድርጋ አየችው: በውስጧ እንደ ህፃን የሚላወሰው እሱ ነው ከፊት ለፊቷም የተቀመጠው እሱ ነው፡ ፍቅር የሰጣት የመረቃት እሱ ነው። ስለሱ ያላትን ስሜት አሁንም በእርግጠኝነት አጤነች ስለ ጀግናው የሚባለውንም አስታወሰች።

ጥጃና ፍየል ስትጠብቅ ወንዶች የድሜ ጓደኞችዋ እነሱ ጠመንጃ እያሉ እንጨት ቆርጠው እየተሸከሙ እንደ ጥይት ዳውላ እየወረወሩ ይሄ ከብት የኔ ያ እርሻ የኔ... እየተባባሉ ሲጫወቱ። እሷም የእድሜ እኩዮችዋ ከሆኑት ልጃገረዶች ጋር ከከስኬ ወንዝ
የጭሮሽ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየለቀሙ, ልጅ እያቀፉ... ሲጫወቱ
ይቆዩና ጫካው መሃል ሚስትና ባል ሲባባሉ ቆይተው ዘፈን ሲጀምሩ
ስለ ሐመር ተራራ ስለ  ሐመር ሰማይና ምድር... ስለከብቶች ሲያዜሙ ይቆዩና የሐመር ጀግኖችን ህፃናቱ ሲያወድሱ የደልቲ ስም የደልቲ ጀግንነት... ይነሳል። ወንዶች ህፃናት “እኔ ነኝ እሱ እኔ ነኝ
ሲባባሉ እሷም ከሌሎች የእድሜ ጓደኞችዋ ጋር “ደልቲን የሆነውን ወንድ እኔ ነኝ የማገባው ! እኔ ነኝ የማገባው" ሲባባሉ አንዳንዴ ሁለት አንዳንዴ ሦስት እየሆኑ ሲያገቡት የነበረው የልጅነት ዘመኗ
ታወሳት። እንዲህ ዳሌዋ ሰፍቶ ጡቶችዋ አጎጥጉጠው ሰውነቷ
አምሮ ባለበት የቡረቃ ዘመኗ ያ ስም አብሯት አደገ:: የዚያ ጀግና መግነጢሳዊ የፍቅር ሃይል በውስጧ እየተገለባበጠ  ሲያስጨንቃት ኖረ።

ገበያ ስታየው ትንፋሽዋ ቁርጥ ያለባት ሲመስላት  ስሙ ሲነሳ እንደ አውሬ  ስትደነብር  ፍትወት ሲያስቸግራት ከልቧ
አውጥታ ጉያዋ ውስጥ በሰመመን ስታስገባው፤ በፍቅሩ ወዲያ ወዲህ
ስትንገላታ ኖረች: ነገ ነገን ሲተካ የሷ አምሮትም ከቀን ወደ ቀን ሲጨምር ከስኬ ወንዝ አሸዋ ጭራ ጭሮሽ ውሃ ስትቀዳ ያ በውስጧ
አብሯት ያደገው ጀግና ድንገት ሽቅብ ወደ ቡስካ ተራራ ሲወጣ አየችው ደነገጠች! ግራ ገባት: “አያ ደልቲ! እሱ ኮ ነው…..የኔው.." ብላ ቀባጠረች። ጓደኞችዋ ሳቁባት አላየቻቸውም።
አልሰማቻቸውም እሱም የለም: ጫካው ሰወረው። እሷ ግን ታየዋለች።አካሉ ቢሄድ እሱ ልቧ አለ፡ አወጣችው አየችው ወደደችው! አቀፈችው...

ይእ!  እሰይ እሱንም ከውስጤ ያለውንም አየሁት..." ቀና ብላ ፀሐይን ሰማዩን... ቦርጆን አመሰገነች።

“እይ! እሽ ምን ልሁን! እሽ ምን ላርገው.." ጓደኞቿ እንደገና ሳቁባት። ጆሮዋ ግን አይሰማም አይኗ አያይም... ሁሉም ጀግናዋን ሊዳብሱ ሄደዋል። ውስጧ ያለው የፍቅር ሃይል ለፍንዳታ ተዘጋጀ ተቀባበለ። ሃይሉ ናጣት ወዘወዛት, አሻት... አዞራት አሽከረከራት... ዛፍ ጥላ ስር በደመ ነፍስ ሄዳ አረፈች መረጋጋት ስትጀምር ቡስካ ተራራን ቀና ብላ አየችው: ነይ" አላት። ወሰነች
ለመሄድ ጀግናዋን ጫካ መሃል ለመፈለግ  ቆረጠች። ሄደች “አቅጣጫ ያላት ጀልባ ንፋሱም ይረዳታል ይባል የለ አገኘችው::

ደልቲ ዳራ የቀዳችለትን ሸፈሮ ቡና አራት ጊዜ እየተቀበለ ጠጣና  ሾርቃውን ከፊት ለፊቱ አስቀመጠው: በሐመር ደንብ የጠጡበትን እቃ ማቀበል ጨምሩልኝ ሲሆን ማስቀመጥ ግን በቃኝ ማለት ነው:: ዳራ ለራሷ መጠጣት ጀመረች። በሐመር ባሀል ወንድ በሐመር ባሀል ወንድ
አንበሳ ነው ሴቷ አንበሳ መጀመሪያ ግዳይ ትጥላለች: ወንዱ ጎፈር
አንበሳ ግን ቀድሞ ይባርካል ይበላል፤ ይጠግባል፤ ተንጎማሉ ሄዶ
ለመከታነቱ ተዘጋጅቶ ይጋደማል። ሴቷ አንበሳና ደባሎችዋ የጎፈር
አንበሳው ግሣት ደህንነታቸው ህልውናቸው ነው... እሱ ሲጠግብ
እሱ ሲጠነክር ይረካሉ። ዳራም አንበሳዋ ከጠገበ በኋላ ጭብጦዋን በላች ቡናዋን ጠጣች ከዚያ እቃውን ሸካከፈች።
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ስድስት



#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

ከሀያ ቀን በኃላ ፤ስለእሷ ማሰብ ካቆምኩ በኃላ ...ኦልሞስት ከረሳኋት በኃላ  ድንገት ተከሰተች። እለቱ ቅዳሜ ነው ፤ቅዳሜ ለአብዛኛው ሰራተኛ የደመቀች ቀን ነች። ፈገግታ የሚፈስባት ..ሙዚቃ የሚንቆረቆርባት..የዳንስ ጥበብ  የሚጠበብባት ወሲብ የሚወሰብባት በስራ ሳይሆን በመዝናናት ብዛት የሚደከምባት...በወጪ ብዛት ኪስ የሚታጠብባት አዲስ ፍቅረኛ የሚጠባበስባት ክንድ ላይ ያለ ፍቅረኛ ድንገት ሾልኮ የሚሰወርበት… የታሪክ መፃፊያ ቀን ነች።
ከቅዳሜው የተትረፈረፈው ወደ እሁድ ይዘዋወራል።

ያው ከላይ በገለፅኩላችሁ ምክንያት ለእኛ ለአስተናጋጆች ዋና የስራ ቀናችን ነው።እና በዛው ልክ ወከባ አለ፡፡ ከአንዱ ወደሌላው  ጠረጴዛ መስፈንጠር ..ከአንዱ ተስተናጋጅ ትዕዛዝ ወደሌላው...ብቻ ከባድ ግን ደግሞ ወሳኝ ቀን ነች።ከባድ ያልኩት የስራውን ጫና ፤ የተስተናጋጆቹ ወከባ፤ የትዕዛዝ መደበላለቅ፤ የሰከራሙ ትንኮሳ፤የሂሳብ መጉደል የመሳሰሉትን ጫና አስቤ ነው። ወሳኝ ያልኩት ሳምንቱን ሙሉ የማናገኘውን ቲፕ እና መሠል ተጨማሪ ገቢ የምናገኝበት ቀን ስለሆነ ነው።ዛሬም እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት እንደወትሮ የተለመደ ስራዬን እየሠራሁ ሳለ ጋሼ አስጠረኝ።

‹‹አቤት ጋሼ፡፡››

‹‹ወንበርህን ለሌሎቹ አስረክብና    ቪ.አይ.ፒ ቁጥር 4 ያሉትን እንግዶች አስተናግድ"

ፈጠን ብዬ ‹‹እሺ ጋሼ "አልኩና በደቂቃ ውስጥ ወንበሬን ለጓደኞቼ አስረክቤ ወደታዘዝኩት ቦታ ሄድኩ ፡፡  በእኛ ሆቴል ስድስት የቪ.አይ.ፒ ቦታዎች አሉ።ልክ እንደትያትር ቤት በሆቴሉ ሰፊ አዳራሽ አራቱ ኮርነሮች ላይ  ከፍ ብሎ የተገነብ ሲሆን ወደ እዛ የሚወጣው ከሆቴሉ ሳይገባ በውጭ በኩል ባለ እስቴር ነው።የሁሉም መግቢያ ለየብቻ ሲሆን ቀጥታ በጓሮ በር ገብቶ መልሶ በጎሮ መውጣት ያስችላል..የቤቱ ዙሪያ በጠንካራ ኮንክሪት ግድግዳ የተገነባ ሲሆን አንድ ጎን ማለት ወደሆቴሉ ያለው ጥይት በማይበሳው  መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ነው ..፡፡መስታወቱ እታች ሆቴል ያለውን እንቅስቃሴ ጭፈራውንና እያንዳንድን እድምተኛ ቁልጭ አድርጎ ሲያሳይ ከሆቴል ወደላይ ግን ድፍን ጥቁር መስታወት ግድግዳ ብቻ ነው የሚታየው።ክፍሉ በጣም ዘመናዊ፤ ምቹ ሶፋዋች እና እንደ አማራጭ የባለጌ ወንበሮች ከምቹ ባልኮኒ ጋር ተገጥሞላቸዋል
መብራቶቹም በምርጫ የሚቀያየሩ  ተደርገው የተሠሩ ሲሆን ሙዚቃን በተመለከተ ቀጥታ እታች የሚለቀቀው በጥራት የሚመጣበት ወይም ያንን ዘግቶ እዛው የራሳቸውን የተመረጠ ሙዚቃ የሚጠቀሙበት አማራጭ አለው። እዛ ክፍል …ተጠቃሚዎች ወይ በራፍ ላይ  ቆሞ ወይ ውስጥ ተቀምጧ የሚያስተናግዳቸው  የብቻቸው አስተናጋጅ ይመደብላቸዋል። የተለየ ፕራይቬሲ ከፈለጉ ደግሞ  አስተናጋጅ ከክፍሉ ውጭ  ይሆንና ልክ መጥሪያውን ተጭነው ከመድገማቸው በፊት ተስፈንጥሮ በመግባት ትዛዛቸውን ተቀብሎ የሚፈልጉትን ያመጣላቸዋል።

ይህን  ክፍል የሚጠቀሙት ለደህንነታቸው ወይም ለስማቸው አብዝተው የሚጨነቁ ትላልቅ የቢዝነስ ሰዎች፤ዝነኞችና እና ባለስልጣኖች ናቸው። ቢሆንም ለሁሉም አገልግሎቶች ከመደበኛው  ከአራት እጥፍ በላይ ያስከፋላል ።አስተናጋጅም ብዙን ጊዜ ጠቀም ያለ ጉርሻ ያገኛል።እናም ሁሉም እዚህ ቦታ ሲመደብ በደስታና  በፈንጠዝያ ነው የሚቀበለው።

ደረስኩ ..በራፋን እንደመቆርቆር አደረኩና ገፋ አድርጌ ስከፍት ደነገጥኩ...፡፡እንደጠበቅኩት ቀለል ያሉ ሰዎች አይደሉም የገጠሙኝ። እርግጥ ሴቲቷ ጀርባዎን ሰጥታኝ የተቀመጠች በመሆኑ ፊቷ አይታየኝም፡፡ግን ዝንጥ ብላለች።ደማቅ ሰማያዊ ረጅም ቀሚስ፤ መካከለኛ ታኮ ካለው ሰማያዊ ጫማ ጋር አስማምታ ለብሳለች። ፀጉሯ የእውነት የእሷ ከሆነ ውብ መሆኑን  በቀላሉ መናገር ይቻላል ፤ወገቧ ላይ ተበትኖ  ይታያል .፡፡

.ሰውዬው ከእኔ ፊት ለፊት ናቸው ያሉት ፤ትልቅ ሰው ናቸው።ቆፍጣና ፤ኮስታራና አስፈሪ  ..ፀጉራቸው ገብስማ ነው..፡፡ሙሉ ዠንጉርጉር የመከላከያ ልብስ ለብሰዋል።ትከሻቸው ላይ አራት ኮከብ ወደጎን ተደርድሯል።መቼስ በዚህ አለባበስ የሆነ ስብሰባ ላይ ወይም ወሳኝ ሀገራዊ ተልዕኮ ላይ አምሽተው ከጊዜ መጣበብ የተነሳ ወደቤታቸው ጎራ ብለው ለመቀየር ሳይችሉ ቀጥታ መተው ነው እንጂ ይሄ የክብር ልብስ ቦታው አይመስለኝም"በውስጤ አጉረመረምኩ ...

እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ወደፊት የተወሰነ እርምጃ ጠጋ አልኩና ‹‹ጌታዬ የጎደለ ነገር አለ?››ብዬ ጠየቅኳቸው፡

"ሚበላ ምን አላችሁ?"ጎርናና እና ሻካራ ድምፅ...እኚ ጄኔራልማ እቤታቸው ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸውን አስቀምጠው ነው ከዚህች ኮረዳ ጋር የሚማግጡት› በሆዴ አማኋቸው፡፡እስቲ አሁን ምን አውቄ ነው ለሰከንድ ያየኋቸውን ሰዎዬ ወደማማትና መፈረጅ የገባሁት ብዬ እራሴን ወቀስኩ።

"ጌታዬ ሜኑ ላምጣ"

"አይ አንድ ክትፎ አምጣልን...ክትፎቸው አሪፍ ነው" አለች ሴቲቱ...አሁንም  በደበዘዘው ብርሀን ከእኔ በተቃራኒ የዞረ ፊቷ እየታየኝ አይደለም ።ድምፆ ግን የሚነዝር ኃይል ነበረው። የሚያደነዝዝ...በምን ምክንያት ነዘረኝ...?ስለምንስ ውስጤ ተናጠ... ?

"በቃ ጎረምሳው እንዳለችህ አድርግ"አሉኝ ጄኔራሉ ..ንግግራቸው  ብቻውን ምሽግ የሚንድ አይነት ነው፤ተስፈንጥሬ ወጣሁ።በተቻለ ፍጥነት በልዩ ሁኔታ ክትፎውን አሰርቼ ይዤ ተመለስኩ።

"የእጅ ውሀ እዚሁ ልታመጣልን ትችላለህ?"ሴቲቱ ነች ጠያቂዋ፡

"ይቻላል እመቤቴ.. አሁን አመጣለሁ"አልኩና በደቂቃ ውስጥ የእጅ ውሀ ይዤ መጣሁ። ተንደርድሬ ሄጄ በክብር ጎንበስ ብዬ ልክ እማማ ኢትዬጰያን እያስታጠብኩ እንደሆነ ኩራት እየተሠማኝ ጄኔራሉን አስታጠብኩና ወደ ሴቲቱ ዞር ስል ፊት ለፊት አይን ለአይን ግጥም ...ምን ተአምር ነው?...ልደሰት ወይስ ልዘን? ላልቅስ ወይስ ልሳቅ ?

ጎንበስ ብዬ እያስታጠብኳት ቢሆንም ግን በደመነፍስ ነው። ድምፅ አውጥቼ ላወራት አልቻልኩም  ? አውቅሻለሁ... ጋብዘሺኛል.. እርቃን ገላሽን በዓይኖቼ አይቻለሁ...በጣቶቼ ዳብሼሻለሁ ልላት ፈፅሞ አልቻልኩም።

‹‹አይ የጎረምሳ ነገር....ውሀውን ደፍተህ ጨረስከው እኮ"አሉኝ ጀኔራሉ እንደመሳቅ ብለው። ለካ እሷ መታጠብን ጨርሳ እጇን ብትሰበስብም እኔ ግን አይኔን አይኖቾ ላይ እንደተከልኩ ፈዝዤ ውሀውን ማንጮርጮሬን ቀጥያለሁ...በጄኔራሉ ንግግር ባነንኩና ተስፈንጥሬ ከስራቸው ወደበሩ መራመድ ጀመርኩ።

"በራፋ አካባቢ ነኝ፤ ስትፈልጉኝ መጥሪያውን ተጫኑ ››አልኩና  ክፍሉን ዘግቼላቸው  ወጣሁ።የእጅ ማስታጠቢያውን አስቀምጬ በረንዳው ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተሸከረከርኩ መብሰልሰል ጀመርኩ፡፡

"ፍፅም እንደማታውቀኝ እኮ ነው የሆነችው...ምን አይነቷ ባለጌ ነች?" ከንፈሬን በብስጭት ነከስኩ ..‹‹አንድ ለሊትም ቢሆን እኮ እንዲህ በቀላሉ የሚረሳ ነገር  አልነበረንም ያሳለፍነው..? ነው ወይስ ውሽማዋን ፈርታ ነው?››

"ብትፈራ ይፈረድባታል .. ጄኔራሉ እኮ እንኳን በጎናቸው የሸጎጡት ሽጉጥ ተጨምሮበት ይቅርና እንዲሁ ያን ግንባራቸውን ቋጠር ፈታ ሲያደርጉት ያርበደብዳሉ...እኔስ ሀይ ሰላም ነሽ የሚል አጭር ሰላምታ እንኳን ለመስጠት ድፍረት ያጣሁት እሳቸውን ከመፍራት አይደል?።ግን ውሽማዎ ናቸው ነው ያልኳችሁ ..?ያንን በምን አወቅኩ ?አልነገሩኝ...ሲሳሳሙ እንኳን አላየሁም"

የመጥሪያው መንጣረር ከሀሳቤ አናጠበኝ። ፈጥኜ ወደውስጥ ገባሁና መሽቆጥቆጤን ሳልቀንስ "አቤት ጌታዬ"አልኩኝ፡፡
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ካርለት ድንኳናን ዘግታ ስትፅፍ የሰው ኮቴ የሰማች መሰላትና ጆሮዋን አቁማ አዳመጠች

"ካርለት?"

"የስ" ብላ ቶሎ በማስተካከል "ዬ! አለች - እንደ ሐመር ልጃገረዶችı ካርለት የጠራት ሰው ማን እንደሆነ አውቃዋለች
ደልቲ ነው ቀብራራው ጀግና የድንኳኗን ዚፕ ከፍታ ፈገግ ብላ አየችው" ሰውነቱ በአኖ (ከኦሞ ወንዝ ዳር በመጣ የተላቆጠ አፈር)
ተዥጎርጉሯል፥ ጴሮው (መሃል አናቱ ላይ ባለው ጌጥ) ላይ የተሰካው
የቀጭኔ ላባ በንፋስ ይርገበገባል ... እሱ ግን ፊቱን ዞሮ በርኮታው
ላይ ቁጭ ብሎ ጥርሱን በልምጭ ይፍቃል"

አንቺ ንብ አደለሽ
ምነው ቀፎሽን ዘጋግተሽ መቀመጥሽ

"ደልቲ ንፋሱ: ልጆችም
እንዳያስቸግሩኝ አለችው
ፈገግ ብላ እያየችው" እሱ ግን መልሷ አልተዋጠለትም ይህች ሰው! ነፋስና ልጅ የምትጠላ ምን ልትወድ ነው እህ! ብሎ ቆሽቱ
እያረረ ሃሣቡን ሳይናገር ከታጠቀው ዝናር አንድ ቀላህ አውጥቶ
ውታፏን ከፈተና በአውራ ጣቱ ጀርባ የትንባሆ ዱቄት ፈሰስ አድርጎ ጎንበስ ብሎ በአፍንጫው ቀዳዶች ሞዠቅ ሞዠቅ አድርጎ ሽቅብ ማገና በዐይኖቹ እንባ ፍጭጭ ብሎ ደጋግሞ ካስነጠሰው በኋላ
ትንባሆውን ለካርለት አቀበላት በሐመር ሴት ልጅ ትንባሆ መሳቧ ነውር የለውም! በፍቅረኞች መካከል ትንባሆ (ሱረት) መሰጣጣት ደግሞ አንዱ የመግባባታቸው ምልክት ነው።

"ሽማግሎች ለዛሬ ከብት ውጋ ብለውኝ ይኸው በሬዬን ይዠ መጣሁ" አላት ካርለት ትንባሆው ካስነጠሳት በኋላ ምክንያቱን የሰማች ቢሆንም ከእሱ አንደበት ለመስማት ብላ።

"ምነው  ምናጠፋህ?" ስትለው  መፋቂያውን አኘክ አኘክ አድርጎ ተፋና ረጋ ብሎ፣

"አንች ሰው ምነው ሥርዓት ቢኖርሽ ሴት በየት አገር ነው
የወንድን ጥፋት የምትጠይቀው?" አላት ደልቲ ካርለት እንዲህ
ስታጠፋ ጎንበስ ብላ እግሯን
እንድትይዝ አድርጎ ጡቷን
እንዳይመታ እየተጠነቀቀ ሁለት ሶስት ቀን በባራዛ አርጩሜ ደህና አድርጎ እየገረፈ ቢገራት ልክ እንደ ስልጡን አህያ ትሰግር እንደነበር አስታውሶ እህ! ሽማግሎች እንዳሉትስ በመታረሚያዋ ጊዜ
ስታጠፉ እኔ እንጂ ሌላ ማን ይታዘንበታል! ብሎ አዝኖ ጢቅ አድርጎ ምራቁን ተፋና ጥርሱን ይፍቅ ገባ።

"ጎይቲ ስታለቅስ ነው የምትውል አይተሃት ታውቃለህ?"አለችው ካርለት በጥያቄዋ ጎርጉራ አንድ አዲስ ነገር ባገኝ ብላ።

"ሰማሁ! እኔን እህቴን ምን የከፋ ችግር መጣባት! አዘነ
ደልቲ።

"ለዚህ ምን መፍትሔ አለው ታዲያ?" ስትል ካርለት ደልቲ
ሰረቅ አድርጎ አይቷት

"ምን መፍትሄ ይኖረዋል  ሽማግሌ ያለውን መቀበል ነው እንጂ።

"ጎይቲ ከከሎ ጋር ከተጋቡ ወዲህ እኮ ሌላ ወንድ አታውቅም "እንደገና ለዓመል ያህል ሰረቅ አድርጎ እንደዘበት አያት የለበሰችው
ቆዳ የፊተኛው ክፍል ጉያዋ ውስጥ ተሸጉጦ: የቀኝ ጭኗ ውስጥ ክፍል እንደ ጥጥ ንጥት ብሎ ታየው"

"ተታናናሽ ወንድሞቹ ጋርስ  አልቀበጠችም?"

"ከሎ ታናሽ ወንድም እኮ የለውም ሁሉም የእሱ ታላላቆች ናቸው"" ስትለው ታናሽ ወንድም እንደሌለው እያወቀ የረሳበት ምክንያት እየገረመው
"ተዘመዱ ወንዶችስ ጋር?" ካርለት የሰጎን ላባ የሰካበት ጴሮ  የተተለተለውን ሳንቃ ደረቱን እንደ አቦ ሸማኔ ቀጠን ያለ ወገቡን አይታ ምራቋን ከምላሷ ስር መጣ ዋጠችና,

"ከማንም ጋር አልቀበጠችም ካለ ከሎ በቀር" አለችው

"እህ!" ሲል ካርለት ቀጥሎ የሚለውን ለመስማት ጆሮዋን መዘዘች እሱ ግን ጭራሽ ያልጠበቀችውን ጥያቄ

"የምጠጣው ውሃ ትሰጭኝ?" አለ ከኮዳዋ በኩባያ ቀድታ ውሃ
ስትሰጠው ቀና ብሎ አይቷት

"እሱን አንች ጠጭው፤ ለኔ በሾርቃ ስጭኝ" አላት ካርለት ውሃ ለማምጣት ሄደች ደልቲ አረማመዷን÷ ዳሌዋን ወገቧን ከኋላዋ የሚወናወነውን ቆዳዋን ጥርሱን እየፋቀ አየና ምራቁን ጢቅ አድርጎ ተፋና የበረቱ ከብቶች ቀለማቸው የተለያዬ ነው  ቀይ፥
ዳልቻ: ነብርማ: ነጭ የካርለትም ቀለሟ ነጭ መሆኑ ሚስቶቹን
እንደ ከብቶቹ ቀለም ማሳመሩን ሲያስብ የደስታ ስሜት ተሰማው መልሶ ደግሞ የሐመር ልጃገረዶች እንዳለቁ ሁሉ ከዚች አግድም አደግ ጋር ቢቀርብኝስ ብሎ አሰበ አንዴ ግን አገባሻለሁ ብሏል1
ስለዚህ ቃሉን ማጠፍ አልፈለገም ግዴለም አገባታለሁ ድምጿ ግን
ምነው ተዛሬ ነገ ቃናው አይጣፍጥ?  ብልግናዋና ድምጿ እንጂ ሴትነቷስ  እያለ ሲያስብ ካርለት ውሃ በሾርቃ ይዛለት ብቅ አለች

ከርቀት እያያት  ደሞ ደህና ገብሮ የነበረው ሰውነቷ እንደ ምስጥ ንጉስ ተመልሶ ለሰለሰ እያለ ሲያስብ ካርለት ሰው ጠርቷት
ዘወር ስትል የጀርባዋ ሰንበር ታየው  ከሎ ከብት ሲዘል የተገረፈችው"
ደልቲ ትንሽ ፈርጠም ብሎ ሳቅ  አለ ካርለት
አላየችውም ትዝ አለው ስትገረፍ ሰውነቷ የተንቀጠቀጠው ወድቃ
የተዘረረችው

ባለጌ! ብሎ ተቆጨና መልሶ ደግሞ አዘነላት ጀርባዋ ላይ
ያሉት የግርፊያ ሰንበሮች ጥቂት ናቸው ለሐመር ልጃገረድ ደግሞ
የግርፊያ ሰንበር ሌላው ውበቷ ሲሆን ዳንስ ቦታና ጫካ ውስጥ ወንዱ
እንደ አኮርዲዎን መጫወቻ ሰንበሮቹን በጣቱ እየነካካ የፍቅረኛውን የፍቅር ቅላፄ በማስተካከል የጋራ የፍቅር ስሜት የሚፈጥሩበት ነው
ሴቷና ወንዱ

በልጃገረድ ጀርባ ላይ ባለ የግርፊያ ሰንበር ላይ ሻካራ የእጅ ጣት ጫፎችን ማንቀሳቀስ ትናጋው በፍቅረኛው ምላስ የተነካ ያህል በስሜት ንዝረት መላ ሰውነቱ ያረግዳል ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ
የግርፊያ ሰንበሯ ጀርባዋ ላይ የበዛ ዘመደ ብዙ' ካነሰ ደግሞ ዘመደ ትንሽ ናት ይባላል ብዙ ጊዜ ልጃገረዶች እርስ በርስ
ስለዚህ ሲጨዋወቱ

ይእ! ይሄ ሁሉ ማን ሲዘል የተገረፍሽው  ነው? ተብላ
የተጠየቀች እንደሆነ እጅዋን አዙራ ጀርባዋን እየዳሰሰች

ይእ! ይሄ የባልዳምቤ
ይሄ የሸረምቤ ይሄ የላሎምቤ …እያለች ትዘረዝራለች ልጃገረዷ በእነዚህ ሁሉ ዘመዶችዋ ስትፎክርና ሳትፈራ ስትገረፍ ያያት ደግሞ ስንትና ስንቱ ወንድ ተመኝቷታል ከስንቱ ጋርስ ቀብጣለች ሊያገባት የፈለገውስ እንዴት እንደሚበዛ መገመቱ አይቸግርም አንድ
የሐመር ወንድ ደግሞ ሌላው የተመኛትን ያፈቀራትን የራሱ አድርጎ ከማግባት የበለጠ ትልቅ
ክብር የለም  በሐመር የጋብቻ አለም።

ካርለት ግን የተገረፈችው ለአንድ ቀን ብቻ ነው፤ የዛን ቀንም  ግረፉኝ ብላ አልፎከረችም  ስትገረፍም ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ
ስታለቅስ በመጨረሻም ህሊናዋን ስታ ስትወድቅ ምድረ ጎረምሳ ተሳስቆባታል እንጂ ማንም ለፍቅር አልተመኛትም ደልቲ ይህን
አስታውሶ

ወዲህ ወዲያ ስትል እንደ ፍየል ጅራት ስትወናወን እንጂ እሷስ ብትሆን ስንትና ስንት ዘመዶችዋ ከብት ሲዘሉ ብትኖር ኖሮ
የመገረፉ እድል መች ያመልጣት ነበር! እያለ ሲትከነከን ካርለት
አጠገቡ ደርሳ ውሃ የያዘ ሾርቃውን አቀበለችው
እየተጉመጠመጠ ደጋግሞ ተፋና ስምጥጥ አድርጎ ጠጥቶ ባይሮ ኢሜ ብሎ
አመሰገናት እግዜር ይስጥልኝ ለማለት

ካርለት ሾርቃውን
ሾርቃውን ልትመልስ ሄደች ያን ጊዜ ደልቲ ደሙ ፈላ  ነደደው ተቀብላ ፈንጠቅ አድርጋ ደፋችውና
ይህች አሳሳች! ብሎ እራሱን ለማረጋጋት እየሞከረ ከመቀመጫው ተነሳ

"ይእ! እህ የታል አያ ደልቲ?  አለ አሁን ውሃ ብሎኝ
ሰጥቸው መጣሁ አላልሽኝ?" አለች ጎይቲ ከካርለት ጋር ወደ ድንኳኗ
እየተጠጉ
"ጎይቲ  አሁን እኮ እዚህ  ቁጭ ብሎ ስናወራ ቆይተን ውሃ ስጭኝ ብሎኝ ሰጥቸው ሾርቃውን መልሼ: አንችን ጠርቸሽ መጣን በዚህ ቅፅበት የት ሄደ?"

"ይእ! እኔን ትጠይቂያለሽ ደሞ ይልቅ አንች ምንሽ  ውስጥ ከተትሽው? አያ ደልቲ መቼም ካለ ነገር እንዲህ ሹልክ ብሎ እንደ
ሌባ አይጠፋም ተቀያየማችሁ?"

"ኧረ በጭራሽ"
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹እማዬ…አንቺ እማዬ……››
እታች ምድር ቤት ሁሉም ከየክፍሉ እየወጣ እሷ ወደአለችበት የመጀመሪያ ፎቅ የሚያስወጣውን መወጣጫ  ግር ብለው በመምጣት መክበብ ጀመሩ…. እናቷ ከእሷ ፊት ለፊት ካለው መኝታ ቤቷ  ልብሳቸውን እንኳን በቅጡ ሳይለብስ በተለመደ ድንጋጤዋ እያለከለከች
‹‹ምን ተፈጠረ ልጄ.?ደግሞ ምን  ሆነሽ ነው?››
‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ያሳደግሺኝ?››ጮህችባቸው፡፡
‹‹አረ ተረጋጊ ልጄ …እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው.?››

‹‹እኔ ለምንድነው እንደሌላው ሰው ጥሩ መሆን የማልችለው…? እኔ ለምንድነው ስርዓት የሌለኝ? አለሌ የሆንኩበት ምክንያት ምንድነው›?

እናቷ የምትለፈልፈውን  ሌሎች ሰራተኞች እንዳይሰሙ በመጨናነቅ  ይመስላል እቅፍ አረጓትና የሚወራጩ  እጆቾን አንድ ላይ በዛ ግዙፍ ሰውነታቸው በመጭመቅ  አንጠልጥለው ወደመኝታ ቤታቸው አስገቧትና  አልጋዋ  ላይ በማሳረፍ በራፍን ሄደው ዘጉት…እሷም ከንዴቷ እንደመብረድ ብላ ሹክክ ብላ ተነሳችና ሙሉ በሙሉ ወደ አልጋዋ ላይ ወጣች..፡፡ከውስጥ ገባችና ተኛች…፡፡በቃ ደከማት..እናቷም እንደእሷው አደረጉ፡፡ ቀስብላው ወደአልጋው ላይ ወጡና ከጎኗ በመተኛት ክንዳቸውን አንተርሰው ከራሳቸውጋር ልጥፍ አደረጓት፡፡
ሰው ሲከፋው እንዲህ እንደእሷ ሮጦ የሚወሸቅበት ጉያ ወይም ተንተርሶ  የሚተኛበት ክንድ ወይም እቅፋ ውስጥ ገብቶ የውስጥ ቁጣውንና ለቅሷውን የሚያቀዘቅዘዝዝት ምሽግ ካላው እድለኛ ነው። ሲከፍ ወደ  መጠጥ ቤት ሮጦ አልኮል ከመጎንጨት የሚያፈቅሩት ሰው እቅፍ ውስጥ ኩርምትምት ብሎ በማልቀስ የመረጋጋት አማራጭን መጠቀም ውጤታማና ብልሀት የታከለበት ውሳኔ  ነው።በተለይ ያ ክንድ እንዲህ እንደልዩ የእናት ሲሆን የቀጥታም ሆነ የጎንዬሽ ጉዳቱ ለዜሮ የቀረበ ነው።

‹‹የእኔ እርግብ…. አንቺን የሚስተካከል ደግ የለም እኮ…ከአንቺም እኩል  ለሰው አዛኝ እና ሰናይ ምግባር ያለው ልጅ ማግኘት ከባድ ነው….ይሄን  እኔ ብቻ  አይደለሁም ሀገር ምድሩ ነው የሚያወራው…እዚህ ቤት የሚርመሰመሱ ሰራተኞች አንቺ ሲያምሽ አብረው ሚታመሙት፤ ፈገግ ስትይ ሲገለፍጡ የሚውሉ ናቸው እኮ...የሰፈሩ አሮጌት ምረቃትን  ካንቺ እኩል የተመረቀ ማን አለ..?ከአኔ ከእናትሽ ቦርሳ እየመዠረጥሽ ለሰፈር አሮጊትና ሽማጊሌ ብሬን ስታድይ፤ የተመመ ችግረኛ ስታሳክሚ ፤መማር ላቃተቻው ህፃናት ደብተርና ዩኒፎርም እየገዛሽ ስታድይ አይደል እንዴ የኖርሽው?
ልጄ እኔ እንደውም ይሄ ሁሉ ደግነትና ቸርነት ከየት አምጥታው ነው ?እያልኩ ዘወትር እንደተደምኩብሽና እንደኮራሁብሽ ነው..አንቺ ይሄ ክፍ አመል ባይጠናወትሽና ባይለክፍሽ እንከን አልባ መልአክ እኮ ነበርሽ..ልጄ ታዲያ ምን ላድርግሽ እንድትፈወሺልኝ ያልሞከርኩት ህክምና የላጠጣሁሽ ጠበል የለም..የእኔ ቆንጆ ሰው ሲቸገር ምንም ነገር ለመሞከር ይደፍራል፤አጣብቂኝ  የትኛውንም የተነገረውን ነገር ያምናል፤ የትኛውንም መጥፎ የተባለ ስምምነት ይፈርማል፤የትኛውንም የሚወደውን ነገር  አሳልፎ ይሰጣል።አዎ ችግር እንደዛ ያደርጋል።እኔም በዚሁ በአንቺ ችግር ምክንያት የሰራሁትን ዛሬ ልንገርሽ…ሚስጥር አድርጌ ይዤው ነበር.. እግዜር ይቅር ይበለኝና ይሄውልሽ ጠንቆይ ቤት ሁሉ እኮ መፍቴ ይሰጠኝ መስሎኝ ሄጄ ጠይቄያለሁ….ግን መፍትሄ አልተገኘም፡፡
‹‹እጄን አስቆርጪው…በእጄ አይደለ ምሰርቀው…በቃ አልፈልጋቸውም.. ሁለቱ እጆቼ ይቆረጡ፡፡››
‹‹በስመአብ በይ ልጄ ..በስመአብ…የሚነሳው በእጅ ቢሆንም ቀድሞ  የሚሰርቀው  እኮ እዕምሮ ነው..እምሮሽን አላስቆርጥ?››
›‹‹እማዬ  ብቻ እኔ አንዲህ እየተዋረዱ መኖር ሰልችቶኛል…ትንሽ ጊዜ ነው የምሰጥሽ ….ካለበለዚያ..››
‹‹ካበለዚያ ምን?››
‹‹እራሴን አጠፋልሻለሁ..ከዛ ግልግል ነው፡፡››
‹‹አረ ተይ ልጄ…. ተይ እኔ እናትሽ እንኳን አላሳዝንሽም..?ሌላ ትርፍ ልጅ እንዳለው ሰው እንዲህ ትያለሽ..? አንቺ እኮ ከታችም ከላይም የሌለሽ ብቸኛ ልጄ የአይኔ ማረፊያ ነሽ…እኔ ባለኝ ሀብት በአለም በየትኛውም ጥግ ለዚህ ፈውስ ቢኖር የምሰስት ይመስልሻል ?ለምን ብዬ…ከሰባራ ሳንቲም አንስቶ ሙሉ ካማፓኒው ያንቺው ነው..እኔ ከአሁን ወዲህ የምኖረው እራሴን ለማስደሰት ሳይሆን አንቺ በሁሉ ነገር የተሳካልሽ ሆነሽ ስትስቂ ለማየት ነው…፡፡››
‹‹እና ታዲያ ምን አድርጊ እያልሺኝ ነው?››
‹‹ካልሆነ ለሁለተኛ ጊዜ እዛው አሜሪካ ሂጂና ትሞክሪ ይሆን ?››
‹‹እማዬ እኔ የትም ሀገር መሄድ አልፈልግም..ደግሞ የፈረንጆች የቅዠት ሀሳበ መሞከሪያ መሆን ሰልችቶኛል፡፡››
‹‹እሺ.በቃ ከመድህኔ ጋር ተማከሬ የሆነ ነገር አደርጋለሁ፡፡›› 
‹‹ከእሱ ጋር አትማከሪ በራስሽ ከቻልሽ አድርጊ ካለበለዚያ…፡፡››
‹‹በቃ በቃ. እሱን ለእኔ ተይውና ተኚ.›
እጃቸውን ፀጉሯ ውስጥ ከተው ሲዳብሷት የሆነ ፀጥ ያለ ውቅያኖስ ውስጥ እየዋኘች ያለች መሰላት…ወዲያው እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡

  ይቀጥላል
#ህያብ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በኤርሚ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

"እኔ ምንም እየገባኝ አይደለም ቢኒ ምንድነው እያወራህ ያለኸው"

"ተረጋጊ እነግርሻለሁ.... ዮናታን የያዝነው ክፍል ድረስ መጥቶ እንድናወራ ጠየቀኝ.... እሺ ብየው ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ባር አመራን እናም ቁጭ ብለን ያልጠበኩትን ነገር ነገረኝ"

"ቀጥል ምን አለህ"

#ምሽት_8_ሰዓት_ላይ

የሆነውን ሁሉ እኔ ነኝ የምተርክላችሁ.... ቢኒያም

ከዮናታን ጋር ወደ ባሩ ከወረድን በኋላ መጠጥ አዘዘ እና
"የውልህ ቢኒያም ተረጋግተህ እንድትሰማኝና ከቻልክ እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ..."

"ለማንኛውም የምትለኝን ልስማህ" እስከዚህ ድረስ እንኳን አብሬው የመጣሁት ድጋሚ ካስተማረን F እንዳያስታቅፈኝ በሚል ፍራቻ ነው

"ሁሉም ሰው የሚያውቀው እኔ ሴት አተራማሽ እንደሆንኩ ነው። በእርግጥ እውነታም አለው ጥቂት ከማይባሉ ሴቶች ጋር ግንኙነት ነበረኝ ግን ነበር ነው ከ2 አመት በፊት በመጀመሪያ እይታ አንዲት ልጅ ልቤ ውስጥ ገባች። እናም ልክ ለሌሎቹ እንደሚሰማኝ ተራ ስሜት ነው ብዬ የነበረው ህይወቴን ለመቀጠል ሞከርኩ ግን እንደድሮው መሆን አቃተኝ። ለተወሰነ ጊዜ ስወዛገብ ከረምኩና ፍቅሬን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝና እሷን የኔ እንዴት እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ።

ልጅቷ ኮስታራ እና የማያስቀርብ ፊት ነው ያላት ያለኝ አማራጭ አብራ ከምትማራቸው ሴቶች ስለሷ ሊነግረኝ የሚችል ሰው ፈልጌ መቅረብ ነበር እናም የትናዬትን ቀረብኳት...."

"ሰውዬ ስለምን እያወራህ ነው" እዚህ ጋ መምህር መሆኑን ረሳሁ

"ቢኒያም ለኔ ሁሉም ነገር የተገለፀልኝ ዛሬ ነው.... እና ከቻልክ ተረጋግተህ ስማኝ"

"ከየትናዬት ጋር ከተቀራረብን በኋላ በተደጋጋሚ ቢሮዬ እየጠራኋት ስለ ህያብ እንድትነግረኝ አደርጋት ነበር።"

"ምን እያልክ ነው እና ህያብን አንተም ታፈቅራታለህ" ማመን ከበደኝ

"አዎ ያውም በመጀመሪያ እይታ ነው ያንበረከከችኝ ለማንም ሴት እንደዚህ ሆኜ አላውቅም። የኔ ብትሆን ብዬ በምናቤ ስስላት የነበረችን ልጅ ነው በአካል ያገኘኋት"

"እሺ ከዛስ ምን ተፈጠረ"

" የትናዬት እንኳን ጠርቻት ሳልጠራትም እየመጣች ብዙ ነገር እንዳውቅ አደረገችኝ። የምትነግረኝ ነገሮች ግን ህያብን እንድቀርብ ሳይሆን እንድፈራ እና እንድሸሽ የሚያደርግ ነበር።"

"ምን ብላህ ነው"

"በመጀመሪያ ከሷ ጋር ኢለመንተሪ ጀምሮ አብረው እንደተማሩ እና እንደምትታየው ሳይሆን ውስጥ ውስጡን ወንድ አተራማሽ እንደሆነች ነገረችኝ። አላምንም ስላት በማስረጃ አረጋገጠችልኝ።"

"መቼ ነበር ያረጋገጠችልህ ማለቴ የት"

"ከአመት በፊት ካንተ ጓደኛ ጋር ቤርጎ ሲገቡ በአይኔ በብረቱ አየሁ እናም የምትለኝ እውነት እንደሆነ አረጋገጥኩ"

"የውልህ ዮናታን ያየኸው እውነት ነው ግን እንደምታስበው አይደለም። ጓደኛችን በሀይሉን ፍቅረኛው ከድታው ሌላ ሰው ጋር ሆነች እናም እሷን ማስቀናት እንደሚፈልግ ነገረን.... እኔም ለህያብ ነገርኳትና እምቢ ብትልም በግድ አሳመንኳት ከዛ ፍቅረኛው የምታይበትን ሁኔታ አመቻችተን አብረው ወደ ክፍል ሲገቡ እንድታያቸው አደረግን። ግን አንተ እዛ እንደነበርክ ማንም አላወቀም እንዴትስ ልትገኝ ቻልክ"

"የትናዬት ናት አላምንም ስላት 'ከቢኒያም ጋር ፍቅር ፍቅር እየተጫወተች የገዛ ጓደኛው ጋር ትማግጥበታለች' አለችኝ ማረጋገጥ ከፈለክ ብላ ወደዛ ቦታ ወሰደችኝ እና በአይኔ እንዳይ አደረገችን በሰዓቱ ራሴን መቆጣተር አቅቶኝ ነበር እናም እሱን ልደበድብ እሷን ልሰድብ ስራመድ የትናዬት አስቆመችኝ.... ከዛ በኋላ የምትለኝን ሁሉ አምናት ነበር እስከ ትላንትና ድረስ..... አሁን ግን ሁሉንም ከራሷ ከህያብ ነው ማረጋገጥ የምፈልገው"
ነገሩ ካሰብኩት ውጪ ሆነብኝ የትናዬት ተንኮለኛ ብትሆንም ይህን ያክል ርቃ ትሄዳለች ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"እሺ ሌላስ ምን ነገረችህ"

"አንተ ፍቅረኛዋ እንደሆንክ እና አዲስ አበባ ከሌላ የወለደቻት ልጅ እንዳለቻት"

"ምንድነው የምታወራው እኔ ከህያብ ጋር አብሬ ስለምታይ ፍቅረኛዋ ነው ብትል እሺ ግን ልጅ ከየት ፈጥራ ነው የነገረችህ...." ኪሱን በርብሮ የሆነ ፎቶ አወጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ። ህያብ ልጅ አቅፋ.....

"ግን እኮ እህቷም ልትሆን ትችላለች" ካልኩ በኋላ ለእናቴም ለአባቴም አንድ ነኝ ብላ የነገረችኝ ትዝ አለኝ።

"አይደለችም ልጇ ነች ይሄን አረጋግጫለሁ ግን አንተ የምታውቅ ነበር የመሰለኝ"

"ኧረ በፍፁም ግራ እያጋባህኝ ነው" ፎቶውን ተቀብሎኝ ወደ ኪሱ ከተተና

"ቢሆንም ይሄ ጉዳዬ አይደለም.... ለሷ ያለኝን ፍቅር ያለፈ ታሪኳ ሊቀይረው አይችልም የሚያሳስበኝ የአሁኑ ነው..." ግንባሩን አሸት አሸት እያደረገ ትንሽ ከቆየ በኋላ

"ቢኒያም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እናም ሳትዋሽ መልስልኝ" አለኝ

"እሺ ጠይቀኝ"

"ከህያብ ጋር ፍቅረኛሞች ናችሁ?"

"አይደለንም" ፈገግ ሲል አየሁት

"እሺ ታፈቅራታለህ" ከንግግሩ እኩል ደነገጥኩ

"አይ አላፈቅራትም" መሬት ተንበርክኮ መሳም ነው የቀረው ደግሞ ደጋግሞ ፈጣሪን አመሰገነ... ሁኔታውን ሳይ የነገረኝ ሁሉ እውነት እንደሆነ ገባኝ።

"እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ"

"ጠይቀኝ" አለኝ በፈገግታ ተሞልቶ

"የትናዬት ፍቅረኛህ ካልሆነች ወይም የሆነ ግንኙነት ከሌላችሁ እንደዛ ተጠባብቃችሁ አንገትህን ስትስምህ...." ሳያስጨርሰኝ

"እሱ ለኔም የሚገርም አጋጣሚ ነበር። ህያብ እኛ ወደተቀመጥንበት ስትመጣ እኩል አየናት እናም የትናዬት ሳላስበው ጥምጥም ብላብኝ ሳመችኝ። ደንግጬ ስለነበር ላስቆማት አልቻልኩም ምን እያረግሽ ነው ብያት ዞር ስትልልኝ ህያብ ቆማ እያየችን ነው ወዲያው አንተ መተህ ወሰድካት"

"እንጂ ምንም አይነት ግንኙነት የላችሁም"

"ቢኖረን ለምን እዋሽሀለሁ"

ወደ ያዝነው ክፍል ከተመለስኩ በኋላ ረጅም ሰዓት ወስጄ ለማሰብ ሞከርኩ ከሁሉም አንድ ነገር ደጋግሞ አቃጨለብኝ.... "ህያብን ታፈቅራታለህ"

አዎ አፈቅራታለሁ አልኩ ጮክ ብዬ ልክ እንዳንተ መጀመሪያ ያየኋት ቀን ነው ልቤን የሰረቀችው ግን ምን ያደርጋል እሷ የምታፈቅረው አንተን.... ወዲያው በንግግሬ ደንግጬ ዝምም አልኩ ደግነቱ ከራሴ ውጪ የተናገርኩትን ማንም ሊሰማ አይችልም። ፍጥጥ እንዳልኩ ነጋ ግን ከራሴ ጋር ልስማማ አልቻልኩም እውነት ህያብ የሌላ ሰው ስትሆን ማዬት እችል ይሆን???
።።።
እኔ ነኝ ህያብ!
ፍንድቅድቅ ብያለሁ ከዚህ የበለጠ ምን ሊያስደስተኝ ይችላል በማፈቅረው ሰው መፈቅርን የመሰለ ምን ነገር አለ። ከነገረኝ ነገሮች ሁሉ ዮናታን ያፈቅርሻል የሚለው ሙሉ እኔን ተቆጣጥሮኛል።

"ህያብ ደስታሽን ላበላሽ ፈልጌ ሳይሆን እባክሽ ጥያቄዬን መልሽልኝ" ጮክ ብሎ ተናገረ

"ምን አልከኝ ቢኒ" በራሴ አለም ስዋዥቅ ምን እንዳለኝም አልሰማሁትም ነበር።

"ልጅ አለሽ" ከመደንገጤ የተነሳ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ።

"ህያብ እንደጓደኛሽ የምታይኝ ከሆነ እውነቱን ንገሪኝ ልጅ አለሽ" ከተቀመጠበት ተነስቶ እጄን ያዘና አንድቀመጥ አደረገኝ ከዛ በተማፅኖ አይን አይኔን ያይ ጀመር "እባክሽ ህያብ ላስጨንቅሽ ፈልጌ አይደለም... ግን ዮናታን ፎቶ ሲያሳየኝ ተጠራጠርኩ" የባሰ ድንጋጤ

"ምን? ዮናታንም ያውቃል"

"አዎ እሱ ነው የነገረኝ ስነግርሽ እኮ አልሰማሽኝም መሰለኝ"
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

‹‹ጎሽ ጥለኸኝ አልተሰወርክም…አጠገቤ አለህ ማለት ነው? ››ስትል የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰችና…በከፍተኛ ፍራቻ እና ጥርጣሬ ዓይኖቾን ገለጠች…..ወንዝ የሚባል ነገር ስራቸው  የለም…የሲኦል ምልክትም አይታያትም…. በሳር ፤ በትናንሽ አረንጓዴ ቁጥቆጦች እና የሚያማምሩ በቀለማት  በተሸቆጠቆጡ አበቦች የተሞላ ወብ ቦታ ነው…ግን ግራ አጋቢ ቦታ…፡፡
ከስር መሬት ከላይም መሬት ነው የሚታያት ..ግዙፍ ዋሻ መሰል  ነው እንዳትል ምኑም ዋሻ አይመስልም…የተለመደው አይነት ምድርና ሰማይ ነው የሚታየኝ ብላም እንዳትገምት በቆመችበት መሬት እና ወደላይ አንጋጣ  በምታየው መሬት(ሰማይ)  መካከል ያለው ልዩነት  የሚታወቀውን   ሰማይ  ከመሬት የሚርቀውን ያህል እርቆ አይደለም የሚገኘው…በግምት ከመቶ ሜትር አይበልጥም፣
‹‹ተገልብጠን ከምድር ስር ይሆን እንዴ ያለነው….?ማለቴ ምድርን ከታች ወደ ላይ የምናያት..ማለቴ አሁን ላለሁበት ሚስጥራዊ ቦታ ምድር ሰማይ  ትሆን እንዴ…?›ስትል በውስጧ ብትጠይቅም ለመግለጽ የፈለገችውን  ሀሳቡ ለእሷው ለራሷ ተምታታባት…

ትክክለኛ መልስ ለመግኘት ወደ እሱ ዞረችና ‹‹የት ነው ያለነው…..?›› ስትል ጠየቀችው

‹‹እቤቴ››አላት

አበባ.. ትንንሽ ቁጥቋጦች.. እዚህም እዛም የሚፈልቁ  ምንጮች… ለጥ ያለ ማለቂያው የማይታወቅ ሜዳ ነው የሚታያት‹‹ ….ይሄ ነው ቤትህ…..?››

‹‹አይ አይደለም….››አላት ፍርጥም ብሎ

‹‹….ቆይ ቆይ…›› እሰከአሁን በሁኔታው ተመስጣ ልብ ያላለችውን  ነገር አየች…., ልብስ ለብሶም ሆነ እንደዚህ ሙሉ እርቃኑን ፊት ለፊቷ ቆሞ አይታው አታውቅም ነበር….እስከዛሬ ግምሽ አካሉ በውሀ እንደተሸፈን ከእምብርቱ በላይ ነበር የምታየው….በጣም ተገረመች…የምታየው ፍጥረት  ሰው አይደለም….….?ሰው ካልሆነ ታዲያ ምንድነው ከተባለ መልሱ ለመግለፅ በጣም ይከብዳል…?፡፡ ምን ተብሎ እንደምትገለጽው እሷም ምንም አልገባትም  ..እንደዚህ አይነት ፍጡር እሷ አይታ አታውቅም…፡፡እግሮቹ  ጣት አልባ ናቸው… ልሙጥ እና እንደሰፌድ የተዘረጉ…ወይም የዓሳ ክንፍ የመሰሉ …..ብልቱ ደግሞ ምታህለው…ያልተገረዘች የሴት ቂንጥር በሏት… ወደ ፊት እንደባቄላ  ነው አጎንቁላ  የምትታየው…
ወይኔ ጉዴ››አለችና ሳቋ አመለጣት…ያሳቀት …?ስንት ቀን አሁን ቢደፍረኝስ .. ?እያለች የተጨነቀችው አጉል  መጨነቅ በምናቧ መጥቶባት ነው …‹‹አሁን በዚች እንኳን መድፈር ሽንቱንስ መሽናት ይችላል…?›› የሚል ሀሳብ አሰበችና ሳቋን አረዘመችው …
ሌላው በትክክል ሰው አይደለም ብላ ያሰበችው ዋናው ምክንያት  ባለጭራ መሆኑ ነው..ጭራ አለው፡፡ ጭራው ደግሞ ከኃላ ከመቀመጫው የላይኛው ክፍል በቅሎ ወደታች በመሄድ በእግሮቹ መካከል አልፎ ወደፊት ተቆልምሟል.‹‹.እንደውም ከእውነተኛው ብልቱ ይልቅ ጭራውን እንደብልትነት ቢጠቀምበት ያዋጣዋል›› ስትል በውስጧ  አሰበችና ድጋሚ  ፈገግ አለች፡፡

‹‹ስለእኔ ተፈጥሮ አስበሽ እና ተመራምረሽ ጨረሽ?››ብሎ አስበረገጋት
‹‹አይ ምን እመራመራለሁ….?እንዲሁ አዲስ  ነገር ሆኖብኝ ነው እንጂ..››በአፍረት መለሰችለት፡፡
‹‹ግን አልፈራሺኝም…››
‹ለምን እንዳልፈራውህ እኔንም ገርሞኛል…?››የእውነትም ለምን እንዳልተንቀጠቀጠች…?ለምን ፊቷን አዙራ ወደተንጣለለው ሜዳ ፈርጥጣ እንዳልሮጠች …?ለምን ያንን ጆሮ ሰንጣቂ የዘወትር ጩኸቷን እንዳላስነካችው ?ለእሷም አልገባትም…በቃ ከመደነቅና ከመገረም ውጭ በስሜቷ ላይ ያስከተለው የጥላቻውም ሆነ የፍራቻ ስሜት አልነበረም….
‹‹ስለዚህ ወደቤት መሄድ እንችላለን?›› አለና ጎንበስ ብሎ የቆመበትን አካባቢ መሬት በእጁ ሲነካ በአስገራሚ ፍጥነት አብረቅራቂ የወርቅ ሳጥን ከተሰነጠቀው መሬት ተፈልቅቆ  ወጣ…..
‹‹ፓንትሽን  አውልቂ››አላት
‹‹ለምን …? ምን አስበህ ነው…?››ስትል ግራ በተጋባ ስሜት ጠየቀችው፡
‹‹በዚህች ዕቃዬ ምን አስባለሁ?›› አላት እና አሳፈራት….እሷም ልትለው የፈለገችው  በዚህ ዕቃህ ምን ለማድረግ አስበህ  ነው…›ነበር..ያው ልቧን በትክክል ነው ያነበበው፡ 

‹‹እንደዚህ ሆነሽ ወደ እኔ ቤቴ መግባት አትችይም  …..ጨረር ይጎዳሻል››

መከራከሯን ትታ ፓንቷን አወለቅችና እጆቾን እፍረቷ ላይ አደራርባ ቆምች….በእጁ ካንጠለጠለው ሳጥን  የሆነ ሰማያዊ መልከ ያለው የጠፈርተኞችን የሚመስል ልብስ አወጣና  አለበሳት….ሙሉ በሙሉ በልብሱ ተጠቀለለች …ከዛ እጁን ወደ ፊት ሲዘረጋ  እስከአሁን እይታዋ ውስጥ ያልገባ ግን ከቆመችበት በአንድ ሜትር ርቀት የነበረ ወርቅማ የብረት በር ወለል ብሎ ተበረገደ……ከዛ እቤት ሳይሆን አይታ የማታውቀው በምናቧ እንኳን ገምታው የማታውቀው በተረት አለም ብቻ የሚገኝ አይነት ምትሀታዊ የዘመነ ፤ የፀዳ  እና ፀጥ ረጭ ያለ ከተማ ከፊታቸው ተነጠፈ…‹‹..እርግጠኛ ነኝ ይሄ ሁሉ እስከአሁን የሆነውና ያያሁት እውነት አይደለም….ህልም ላይ ነኝ ..ገና ከእንቅልፌም አልተነሳሁም›› በማለት እራሷን ለማፅናናትም ለማረጋጋትም ሞከረች….፡፡ግን አልተሳካላትም፡፡

…ምንም አይነት እሱን መሳይም ሆነ ሌላ ፍጡር ሳታይ ነው በወርቃማ ብርሀን ያሸበረቀውን ከተማ ሰንጥቀው እሱ ቤት የደረሱት፡፡ ይዞት የገባው አንድ  ከግድግዳው ሰማያዊው ብርሀን የሚተፋ  ቤት ውስጥ ነው ፡፡አራት ክፍል ቢኖሩትም ሁሉም  ባዶ ነበሩ..ምንም ዕቃ የላቸውም…

‹‹እንዴ…ይሄ ነው ቤትህ..?››

‹‹አዎ ምነው… ?

አልወደድሺውም…?››

‹‹አይ ቤቱማ አሪፍ ነው..ግን ባዶ እኮ ነው….ቤትን ቤት የሚያሰኘው ደግሞ ጣሪያና ግድግዳ ብቻ ሳይሆን ውስጡም የሚገኝ መጠቀሚያ ቁሳቁስ ነው….››

‹‹ባዶ…››አለና ወደውስጥ ገብቶ ግድግዳውን ተጠጋና ማብሪያ ማጥፊያ የሚመስል ነገር ተጫነ..
ተአምር ተፈጠረ…ድፍን ግድጋዳው እየተከፋፈተ ፍሪጅ …ቴሊቭዝን የመሳሰሉት ዕቃዎች… ወለሉም እየተከፈተ ጠረጵዛ ወንበር በመውጣት እቤቱን ሞሉት…. አደመቁት….. 

ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉን ነገር ችላ ብሎ‹‹አረፍ በይ …››አላት 

‹‹ምን ጉድ ነው….!!እስኪ መኝታ ቤትህን አሳየኝ..?››ሌላ ተአምር ለማየት ከመጓጓት የመነጨ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

መጣና እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ይዟት ሄደ …ወደ ቀጣዩ ክፍል….በተመሳሳይ ባዶ ነበር…
-‹‹የትኛውን ልጫን …››አለችው ግድግዳ ላይ ወደተለጠፉት ማብሪያ ማጥፊያ እጇን እየሰነዘረች
‹‹አልጋ ከፈለግሽ ነጩን ተጫኚ..››

ተጫነችው፡፡

ከእምነበረድ ይሁን ከእንጨት ይሰራ ለጊዜው መለየት ያቃታትን   ነጭ አንሶላ ….ነጭ አልጋልብስ የለበሰ አልጋ ከወለሉ ውስጥ ተአምራዊ በሆነ ክስተት በመውጣት  ተዘረጋ…..

‹‹ወይ እዚህ ላይስ መተኛት እፈልጋለሁ..››

‹‹ታዲያ ተኚያ …ማን ከለከለሽ››

‹‹ግን ይሄንን የለበስኩትን ደባሪ ልብስ ማውለቅ እችላለሁ?››

‹‹ቆይ… ››ብሎ ወደሳሎን ሄደ…. ምን እንዳደረገ ባታውቅም ወዲያው ሰማያዊው የነበረው የቤቱ መብራት  ወደ ብርማ አይነት ተለወጠ…እሱ ተመልሶ እሷ ወዳለችበት መጣ

‹‹አሁን ትችያለሽ አውልቂው››አላት፡፡ 
‹‹ወይ እንዴት ደባሪ መሰለህ ››አለችና ለማውለቅ ብትሞክርም  የተቆላለፉትን ነገሮች እንዴት ልትፈታታቸው እንደምችል አልገባትም... ምታደርገው ግራ ገባት

‹‹አቦ ምን ቆመህ ታየኛለህ ? ናና ከእዚህ  ወጥመድ ውስጥ አውጣኝ እንጂ››ቁጣ የተቀላቀለበት ልመና አሰማች፡፡
#ትንግርት


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በዓይናችን ዓይተን ከወደድነው ነገር ይልቅ በምናባችን ቀርፀን ደጋግመን የተመኘነው ነገር ወደ ጣኦትንት የመቀየር ዕድሉ ሰፊ ነው፡

የውብዳር ለብ ባለ ውሃ ሠውነቷን ተለቃልቃና ፎጣ አገልድማ ፓንቷን በእጇ ይዛ ከባኞ ቤት በመውጣት ወደ መኝታ ቤቷ ልትገባ በእርምጃ ላይ ሳለች ሁሴን የሳሎኑን በር ከፍቶ ገባ፡፡

‹‹እኔ አላምንም፡፡ ቤቱን ማን አሳየህ?›› ወደ እሱ እየተራመደች ነበር የምትናገረው፡፡

ጉንጭ ለጉንጭ ከተሳሳሙ በኋላ ግማሽ እርምጃ ራቅ በማለት አስተዋላት፡፡ ድንቡሽቡሽ ያለች የምትበላ ብስል ቀይ ወይዘሮ ነች፡፡ ያገለደመችው ሮዝ ቀለም ያለው ፎጣ ከወገቧ እስከ ጉልበቷ ሸፍኗታል፡፡ ሌላው አካሏ እንደተጋለጠ ነው፡፡ ጡቶቿ አሁንም እንደልጃገረድነቷ እንዳጎጠጎጡ ናቸው፡፡ የቆዳዋ ጥራትም አስደምሟታል፡፡

‹‹ምን ያፈዝሀል? ቁጭ በል እንጂ›› አለችው፡፡ በእሷ ውበት መደመሙን ስታስብ ውስጧን የንዝረት ስሜት ተሰማት፡፡

‹‹ለምን አልፈዝ፡፡ ጓደኛዬ ለካ ይሄንን ሠውነት እንደ አሞሌ ጨው ሲልስ እያደረ ነው እንዲህ

‹‹ኡ . ኡ . ቴ <ቅጡም የምንኩስና ነው› አለች አክስቴ.... ለማንኛውም ልብሴን ለብሼ ልምጣ.... የሚጠጣ ከፈለክ ፍሪጁን ከፈት አድርግ፡፡›› በማለት እየተውረገረገች ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡

ሁሴን ፍሪጁን ከፍቶ ቢራ አወጣና እየተጎነጨ ማሠብ ጀመረ፡፡ ስለ ሰሎሞን ነበር የሚያስበው፡፡ በመጀመሪያ የውብዳርን ያፈቀራት ጊዜ ጨርቁን መጣል ነበር የቀረው፡፡ እሷን ማግባት ካልቻለ በህይወት መኖር
እንደማይችል ደጋግሞ ሲምል ነበር፡፡ በወቅቱ ደግሞ የእሷ ቤተሠቦች ፍቃደኞች አልነበሩም፡፡ ይሁን እንጂ የእሱ ፍቅር ብርታትና መስዋዕትነት የመክፈል ፅናቱ እሷንም ሙሉ በሙሉ በፍቅሩ እንድትጠመድና ከቤተሠቦቿ ፍቃድ ውጭ አሻፈረኝ ብላ እቤቱ እንድትገባ አስገደዳት፡፡ እናም ትዳራቸው በእንደዛ አይነት ሁኔታ በጽኑ ቁርጠኝነትና በከፍተኛ ደስታ ተጀመረ፡፡ ንብረት መጣ፣ልጆች ተወለዱ፣ሁሉ ነገር የሰመረ መሰለ፡፡ዳሩ ግን ውሎ አድሮ አካል ሲቀራረብ ፍቅር ቀስ በቀስ ከመሀከል ሾልካ ተነነች፤አንዳቸው ለአንዳቸው የወዳጅ ጠላት ሆኑ፡፡

‹‹እሺ አቶ ሁሴን... ደህና ነህ?›› እስከተረከዟ የሚደርስ ረጅም አብረቅራቂ ጥቁር ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ዊግ የተቀላቀለበት ሹሩባዋ ያምራል፡፡ የሁለት ጡቶቿ አካፋይ የስምጥ ሸለቆ ስንጥቅ መስሎ በከፊል ይታያል፡፡ የተቀባችው ሽቶ የሳሎኑን አየር በሠከንድ ነበር የቀየረው፡፡

‹‹አለሁልሽ... ከውዱ ባለቤትሽ ጋር ነበር የመጣነው ግን ከበራፍ ተመለሰ፡፡››

‹‹ምነው ውሽማው ጠራችው እንዴ?›. ግዴለሽ በሆነ አሽሞጣጭ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ! ውሽማው ጋር ነው የሄደው፤ወይዘሪት ገንዘብ ጋር ።

‹‹እነ ዕፀ-ህይወት ትምህርት ቤት ናቸው እንዴ? ... የጫወታውን አቅጣጫ ወደ መጣበት ጉዳይ እንዲያመራላት ነበር ጥያቄውን የሠነዘረው፡፡››

<<አዋ>>

‹‹ልደታቸው ደረሠ አሉ፡፡ ለምን ዝግጅቱ በእናንተ ወጪ እኔ ቤት አይሆንም? በዛውም እኔ አገባበታለሁ፡፡ ‹ብልጥ ዝንጀሮ በሞኝ ክምር ያገባል› አይደል የሚባለው፡፡›› ፈገግ አለች... ስለመጨቃጨቃቸው እንደሰማ እርግጠኛ ሆነች‹‹ሀሳብህ ጥሩ ነው፤ ቢያንስ ከጓደኛህ ይሻላል፡፡››

‹‹የእሱ ሀሳብ እንዴት ነው?››

‹‹እንደነገረህ ነዋ ..! ሆቴል ይዘጋጅ ነው የሚለው፡፡ አሁን አሁን ምን እያሠብኩ እንደመጣሁ ታውቃለህ፤ ለእሱ ስል ይሄንን ሳሎን ወደ ሆቴልነት በመቀየር በመጠጥ ሞልቼ ለእሱ እንዲመች ማድረግ… ፡፡››

‹‹እንግዲያው ከጓሮ ያሉትን ሰርቪስ ክፍሎችም ወደቤርጎ ቀይሪልን፤ እኔም አንዳንዴ ሴቶችን ሸጎጥ አድርጌ መጣና አረፍ እልበታለሁ።

‹‹ምን አንተስ የእሱ ጓደኛ አይደለህ፡፡››

‹‹ከእሱ በፊት እኮ የአንቺ ጓደኛ ነበርኩ…ኧረ እንደውም የዕቃ ዕቃ ባልሽ አልነበርኩ እንዴ?››

ፊቷ ቀላ፡፡ የውብዳር ሁል ጊዜ ስለ እሷ እና ስለ ሁሴን የልጅነት ታሪክ ስታስብ የሠውነቷ ሙቀት ይጨምራል፡፡ በተቀራራቢ ጊዜ አንድ ሠፈር ውስጥ ከማደጋቸው አንፃር ጣፋጭ የሆነ የልጅነት፤ ከዛም ዘሎ እስከ አሁን የዘለቀ የጓደኝነት ቁርኝት በመሀከላቸው አለ፡፡ ከሠሎሞን ጋር እንዲገናኙ መሠላል የሆናቸውም እሱ ነበር፡፡

ካለፈ ትውስታቸው እንደመባነን አለችና ‹‹አዋ እሱማ ለእኔም ጓደኛዬ ነህ፡፡ካንተ ጓደኝነት ያተረፍኳቸው ሦስት ትላልቅ ነገሮች ምን እንደሆኑ ታውቃለህ? ምርጥ ተወዳጅ ልጆች፣ብዙ ብር እና የምሁር ደደብ የሆነ ባል ናቸው፡፡ እና ላማርርህም ሆነ ላመሠግንህ ግራ ይገባኛል፡፡ ባይገርምህ ወደ ኃላ ተመልሼ ሳስብ የዛን ጊዜ ከእሱ ይልቅ አንተን ለምን እንዳልጠበስኩህ ድንቅ ይለኛል፡፡ እንደ ቤተሰብ ሆነን አብረን ማደጋችን እንደወንድምና እህት እንድንተያይ ተፅዕኖ ያሳደረብኝ ይመስለኛል፡፡ ግን እንደ አሁኑ በሳል
ሆኜ ቢሆን ኖሮ መቶ ጊዜ ደጋግሜ አንተን ነበር የምጠብሰው

‹‹ድሮም ሆነ አሁን ዱርዬ እንደሆንኩ እኮ ደጋግመሽ ነገርሽኝ ነበር››፡›› ሁሴን የድንጋጤ ንግግር ነበር የተናገረው፡፡ የውብዳር ስለ እሱ እንደዚህ አይነት ስሜት እንደሚሰማት ገምቶ አያውቅም፡፡

‹‹ዱርዬማ ዱርዬ ነህ፡፡ ግን ንፁህ ዱርዬ ነህ፡፡ አፍቃሪም ነህ፡፡ ከተረጋጋ ማህበራዊ ሕይወት ይልቅ በማዕበል የሚናወጽ ግን በደስታ የተጥለቀለቀ ሕይወት ይበልጥ ዋጋ አለው፡፡ ደስታ በሕይወት ለመኖር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው የምትረዳው ባጣኸው ጊዜ ነው፡፡ ፍቅር አልባ ሕይወት እኮ በቃ..… ንብ አልባ ባዶ ቀፎ ማለት ነው፤ንብ የሌለበት ባዶ ቀፎ ደግሞ ማር ሊመረትበት አይችልም፡፡ ብር ምን እንደሚያደርግልህ ታውቃለህ፡፡ ቁሳዊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያስገኝልሀል፡፡ ውጫዊ ችግሮችህን ሁሉ በቀላሉ ታስወግዳለህ፡፡ ሀብታም ሆነህ ሳለ የፍቅር ካዝናህ ባዶ ከሆነ ግን ..በቃ ቀንና ሌት ስለ እሱ ብቻ ታስባለህ፡፡ ሌሎች ፍላጎቶችህ ሁሉ ስለተሟሉ ሌላ የምትጨነቅበት ጉዳይ አይኖርማ፡፡ ስለዚህ ይበልጥ በፍቅር እጦትህ እንድትሠቃይ ትሆናለህ፡፡››

‹‹ቆይ ይሄንን ያህል እስክትማረሩ ድረስ ምን
ትሠራላችሁ፡፡ ለምን አትነጋገሩም?፡፡ የተከሰቱ
ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት ጥረት ለምን
አታደርጉም ? ፍቅር እኮ ዘላለማዊ ነገር አይደለም፡፡ ይወለዳል .. ያድጋል .. ይሞታል፡፡በልጅነቱ .. በወጣትነቱ አልያም አርጅቶ ሊሞት ይችላል፡፡ የዕድሜውን ርዝመት የሚወስነው ግን ሁለቱ ፍቅረኛሞች ስለፍቅር ባላቸው ግንዛቤና ለፍቅራቸው በሚያደርጉለት
እንክብካቤ መጠን ነው፡፡ እናንተም አያያዙን
ያወቃችሁበት አይመስለኝም፡፡ ሲጋቡ
አይታችሁ ተጣድፋችሁ ተጋባችሁ፤ ይሄው
ጀርባ ለመሠጣጣትም ብዙ አልዘገያችሁም፡፡ለማንኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ ሌላ ጊዜ በእርጋታ ቁጭ ብለን በሠፊው እንነጋገርበታን፡፡

አሁን ወደ መጣሁበት ጉዳይ እንመለስ
መግባባት ስላቃታችሁ የልጆቹ የልደት ዝግጅት ጉዳይ….፡፡››

‹‹እንዳልክ እሺ፡፡መቼስ አንተ ጠይቀኸኝ ምንም ነገር እምቢ ማለት እንደማልችል ስለሚያውቅ ነው የላከህ፡፡ ከዛ በፊት ግን ስለራበኝ የሚበላ ነገር እንድታመጣ ሠራተኛዋን ልዘዛት›› በማለት ወደ ማብሠያ ክፍል አመራች፡፡

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

..በህይወቷ እንዲህ አይነት ድንዛዜ ውስጥ ገብታ አታውቅም...የአባቷን  የሙት አመት መታሰቢያ ቀን መርሳት ማለት ..በቃ እያበቃላት መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ያለፉትን ስድስት አመታት እሷ ነበረች  ቀድማ  ለእንጀራ  እናቷ የምታስታውሳትና ለድግስ የሚያስፈልገውን ነገር ቀድማ የምታሟላው።ሳምንት ሲቀረው ጓዟን ጠቅልላ ወደአሰላ ትሄዳለች።የአባቷን ሀውልት ታሳድሳለች..አካባቢውን ታፀዳለች..በሀውልቱ ላይ ደርቀው የከሰሙ አበቦችን አስወግዳ በምትካቸው አዲስ ትተክላለች..ያሉትንም ውሀ  ታጠጣለች...ቤት ውስጥ በድግሱ የእንጀራ እናቷን ትረዳለች...በዕለቱ ታዲያ አንድም ችግረኛና የኔ ቢጤ በከተማው አይቀርም፤ ቀኑን ሙሉ ወደእነሡ ቤት ሲጓዙና ከድግሱ በልተው ወደቤት ይዘው የሚሄዱትን በፌስታል ተቋጥሮላቸው የሞተውንም ነፍስ ይማር ብለው እነሱንም መርቀው ይሄዳሉ።ይሄ መታሰቢያ ባለፉት ስድስት አመታት በጠቅላላው በአሰላ ከተማ የታወቀ ነው። እሷ ግን ይሄው የዘንድሮውን ረሳችው፡፡ከአይኖቿ የሚንጠባጠበውን እንባ እያበሰች "አባዬ በጣም ይቅርታ፡፡›› አለች፡፡

በዚህ ጊዜ ቱሉ ዲምቱ የክፍያ ጣቢያ ደርሳ የክፍያ ትኬት ለመቀበል መኪናዋን አቁማ ነበር።ታናሽ ወንድሟን ካወራች በኃላ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም።ወደቤቷ ሄዳ እንኳን ቅያሪ ልብስ ለመያዝ አልሞከረችም።ጭራሽ በሀሳቧም አልመጣ፡፡ቀጥታ መኪናዋን አዙራ ወደአሰላ መሄድ ብቻ ነበር የታያት፤እያደረገች ያለውም ያንን ነው።የቤታቸው የውጭ በራፍ ጋር የመኪናዋን አፍንጫ አስጠግታ የመኪናዋን ክላክስ ስታስጓራ አስር ሰዓት  ተኩል  ሆኖ  ነበር። ከሰፈሩ  በግርማ  ሞገሡ  አንደኛ የሆነውን ፊት ለፊቷ የሚታያትን የግንብ አጥር እና ፍረንች ዶር ያሰራችው እሷ ነበረች...አጥሩን ብቻ ሳይሆን ከድሮ ቤታቸው ማለት እትብቷ ከተቀበረበት እና ካደገችበት ቤት ፊት ለፊት ያለውን ቪላ ቤት ያሰራችው እሷ ነች።ግን ይህን ሁሉ ያደረገችው ውድ አባቷ ከሞተ በኋላ ነው።በህይወት እያለ የሚወደውንና መላ ህይወቱን የለፋበትን ግቢ እንዲህ አሳምራውና ቀይራው ቢያይላት ኖሮ እንዴት ይደሰት እንደነበረ ትገምትና የብስጭት እንባዋን  ትዘራለች።ሁሌ ስለእንደዚህ አይነት ጉዳይ አንስተው ከስንዱ ጋር ሲያወሩ"አሁንም  እኮ መንፈሱ ያይሻል...ለእኔና ለወንድምሽ በምታረጊው ነገር ባለበት ሆኖ ይመርቅሻል..ልክ በህይወት እያለ ይኮራብሽ እንደነበረው  አሁንም  ይኮራብሻል..››እያለች ልታፅናናትና ከገባችበት ሀዘን መንጭቃ ልታወጣት  ትሞክራለች።ግን ይህ አይነቱ  የእንጀራ እናቷ የማፅናኛ ንግግር እሷን ይበልጥ ጥልቅ ወደሆነው ሀዘን ውስጥ ነው ጎትቶ የሚሸጉጣት

‹‹አባቴ ባለበት ሆኖ እኔን የሚያየኝ ከሆነማ በጣም ነው የሚያፍርብኝ...በእውነት ይህቺ ልጅ እኔ ያሳደኳት ከአብራኬ የወጣች ልጅ ነች ?››ብሎ መጠየቁ አይቀርም...ምክንያቱም በትክክልም ባለበት ሆኖ ስራዬን የሚያይ ከሆነ ቤቱን ማሳመሬን ብቻ አይደለም የሚያየው..ሚስቱን እና ልጁን መንከባከቤንና መርዳቴን ብቻ አይደለም የሚያየው አመት እየጠበቅኩ በስሙ የአሰላን ድሆች ማብላቴን ብቻ አይደለም የሚያየው...እርግጥ እነዚህን ስራዎቼን ባየ ቁጥር ፈገግ ሊል ይችል ይሆናል፡፡ግን ደግሞ በየዕለቱ በስራ  ህይወቴ  የማሳልፈውን ነገሮች ካየስ..?.በእየዕለት ህይወቴ የሆንኩትንና እየሆንኩ ያለሁትን የሚያይ ከሆነስ..?ልጁ አጨበርባሪ እንደሆነች ሲያይስ.?ልጁ እልል ያለች ፕሮፌሽናል ሸርሙጣ መሆኗን ሲያይስ? ከዛም  አልፎ  ገዳይና  ቂመኛ  መሆኗን ሲያይስ?››እኚህንና መሠል ነገሮችን በውስጧ እያሰበች ሽምቅቅ ትላለች።አባቷ በሄደበት በዛው እንዲመቸውና ፊቱን ወደኃላ ዞሮ እንዳያያት ዘወትር ትፀልያለች።አዎ አባቷም  ሆነ  ሌሎች የሚወዷት ሰዎች ከዛሬ አስር አመት በፊት የነበረችውን ሳባን ብቻ አውቀው በዛ ትዝታ እንዲኖሩ እንጂ ካዛ ወዲህ እንደ አዲስ በውስጧ በቅላ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረቻትን አውሬዋን ሳባን እንዲያውቁ ፈፅሞ አትፈልግም...

የአሁኗን ሳባ ከእነሱ ለመደበቅ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም።
በሀሳብ ጭልጥ ካለችበት የበራፍ መከፈት ነው ያባነናት፡፡ራጂ ነበር ..የከፈተላት።መኪናዋ አዲስ ስለሆነች አይቷት አያውቅም።ማንነቷን ስላለየ  ወጣና ቀረባት፤እህቱ መሆኗን ሲያውቅ እየፈነጠዘ ሰላምም ሳይላት  ወደውስጥ ሮጠ.‹‹..እናቴ ማን እንደመጣ እይ ? እናቴ አላልኩሽም እህቴ  መጣች...እህቴ መጣች" ደስታውንና ፈንጠዝያውን ስታይ ውስጧ ርብሽብሽ አለባት፡፡
‹‹እንደዚህ የሚንሰፈሰፉልኝ ቤተሠቦች እያሉኝ ለምንድነው ብቸኝነት ውስጤን የሚከታትፈው? ›› ስትል እያሠበች ከገቢናው ከፍታ ወረደችና ወንድሟ  ክፍት ጥሎት በሄደው ትንሹ በር ገብታ እራሷ የመኪናውን መግቢያ በራፍ ከፈተችና መኪናዋን ወደ ግቢ ውስጥ አስገብታ ገና በቅጡ ሳታቆም ስንዱ ልጇን አስከትላ እጇን እንደ ክንፍ እያርገፈገፈች ስትመጣ አየቻትና ፈጠን ብላ  መኪናዋን በማቆም ወረደችና… ወደእሷ ተንደረደረች፡

አይን  ለአይን  ሳይተያዩ ገና ሁለት ወርም በቅጡ ያልደፈነ ቢሆንም አሁን በሰላምታ ተቃቅፈው ሲላቀሱ ላያቸው ባለፈው ሁለት አመት ጭራሽ ያልተገናኙ ነው የሚመስለው፡፡

‹‹ለመሆኑ.አለሽ…?ምነው.ከሳሽ?››ፊቷን.እየዳበሰች.በመንሰፍሰፍ.ጠየቀቻት…ስንዱ የሳባ እኩያ ብትሆንም አባቷን በማግባቷና  በዛም  ምክንያት እናቷ መሆን በመቻሏ  ሁሌ  ንግግራቸው የሀያ አመት ልዩነት በመሀከላቸው ያለ ነው የሚመስለው፡፡

ቤት እንደገባች ምግብ ተሰርቶ በልታ ቡና ተፈልቶላት ጠጥታ  ለነገው  ድግስ የሰፈር ሰው ሁሉ ቤታቸው ስራ ላይ  ስለነበረ  እነሱን  ተቀላቅላ  ማገዝ ብትፈልግም ራስ ምታቷ ስለተቀሰቀሰባትና ከሰው ተቀላቅላ ሆይ ሆይታ ውስጥ መሳተፉን ስላልቻለች በስንዱ ገፋፊነት እሷ መኝታ  ቤት  ገብታ እንድትተኛ አድርጋት ወንድሟም እየመጣ እንዳይረብሻት አስጠንቅቃው በራፉን ከውጭ ዘገታባት ወደስራዋ ሄደች፡፡

ሳባም የድሮ የአባቷ መኝታ  ክፍል  አባቷ ይተኛበት የነበረ አልጋ ላይ ወጥታ ኩርምት ብላ ተኛች የተወሰነ  ድካም  ቢኖርባትም እንቅልፍ ሊወስዳት ግን አልቻለም፡፡እስከአሁን ሁለት ጊዜ በዶክተሩ የታዘዘላትን ለሳምንት ያህል በተከታታይ ስትወሰደው የነበረውን መድሀኒት መውሰድ ነበረባት..ጥዋት ለህክምና ብላ ከቤት እንደወጣች ስላልተመለሰች አልያዘችውም ዛሬ የታዘዘላትንም ተጨማሪ መድሀኒት  ወደፋርማሲ  ጎራ  በማለት  ልትገዛ አልቻለችም..ጭራሽ ትዝም አላላት፡፡

‹‹የራሱ ጉዳይ አለችና ››ወደሀሳቧ ተመለሰች፡፡
እዚህ ቤት መምጣት .ከዛም በላይ እዚህ ክፍል መግባት… ከዛም በላይ  እዚህ አልጋ ላይ ተኝቶ ስለአባቷ  ማሰብ  አንኳን  አሁን  እንደዚህ  አእምሮዋ  በጭንቀት እና በድባቴ ምስቅልቅል ባለበት ጊዜ ይቅርና በፊትም ራሷን መግዛትና ስሜቷን ማረቅ በምትችል ጊዜ በጣም ነበር የሚረብሻት…በጣም ነበር ሀዘን ውስጥ የሚጨምራት፡፡ይሄ ቤት የተወለደችበት ነው፡፡እናቷ የሞተችው እሷ ከተወለደች ከአንድ አመት በኃላ ነበር፡፡አዎ  የአንድ  አመት  የልደት  በዓሏ  ሊከበርላት  አንድ ቀን በቀረበት ጊዜ ነው፡እናትዬው ከመሞቷ በፊት ለእሷ የልደት ክብረበዓል የሚሆኑ ሁሉንም ዝግጅት አሰናድታ ጨርሳ ነበር.በድንገተኛ በሽታ ማታ ሁለት ሰዓት አመማት..ወዲያው አፋፍሰው አሰላ ሆስፒታል አስገቧት…አምስት ሰዓት ህይወቷ አለፈ፡፡ ከዛ አባትዬው ለብቻው ሆኖ ነጭ ላቡን ጠብ በማድረግ ምንም እንዳይጎልባት አድርጎ አሳደጋት፡፡ታዲያ ሁል  ጊዜ  የእሷ  ልደት 
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ፔሩ/አማዞን ወንዝ
ዳግላስን ከኑሀሚ ነጥለው በአማዞን ወንዝ ላይ የተወሰነ ይዘውት ከተጓዙ በኋላ ሌላ እጅግ በጣም የተቀናጣ ግን ደግሞ መለስተኛ ዘመናዊ ጀልባ አጠገብ አቆሙና አሸጋገሩት፡፡ምንም እየገባው ነገር ባይኖርም ግን ደግሞ መከራከርና መጨቃጨቅ ባለመፈለጉ እንዳደረጉት እየሆነላቸው ነው፡፡ልክ ከትንሿ ጀልባ ወደቅንጡ ውሀና ዘመናዊው ጀልባ አሸጋግረውት ገና ወለሉ ላይ እንዳረፈ..አንድ ሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ፤ደማቅ ጥቁር ፀጉሯ መቀመጫዋ ላይ የደረሰ ፤መልኳ ጉርድርድ ያለ ግን ደግሞ ሳቢ የሚባል የደም ግባት ያላት ሴት ከውስጥ ወጣችና ተንደርድራ መጥታ ተጠመጠመችበት፡፡ግራ ገባው፡፡ብዥም አለበት፡፡ይህችን ሰውነቱ ላይ ተጠምጥማ በእንባ በመታጀብ እየሳመችው ያለችውን ልጅ የሆነ ቦታ የሆነ ጊዜ ያውቃታል..አዎ በአእምሮ ብልጭ ድርግም እያለችበት ነው ..ግን የት እና እንዴት እንደሚያውቃት ምንም ትዝ ያለው ነገር የለም፡፡
‹‹ቤብ..ሰላም ነህ…?ወይኔ በኢየሱስ……ምንም አልሆንክም…?›› መላ እሱነቱን እየተሸከረከረች አያች  ግንባሩን ጉንጮቹን እጆቹን እያፈራረቀችና እያገለባበጠች ትሰመው ጀመር፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ወጠምሻና አብረቅራቂ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች አንገታቸውን አቀርቅረው ዙሪያቸውን ከበው እየሆነ ያለውን በቆረጣ እየተመለከቱ ናቸው፡፡ልጅቷ እየጎተተች ወደውስጥ ይዛው ገባች ፡፡ደረጃውን እየወረዱ ወደውስጠኛው መኝታ ክፍል ይዛው ገባች፡፡ ሰፊውን ክፍል አልፋ አልጋ ወደ ተነጠፈበት መለሰተኛ ክፍል ይዛው ገባቸው፡፡ባለመሳሪያዎቹ ባሉበት በረንዳ እንደቀሩ ናቸው፡፡

ዳግላስ በገባበት የቅንጡ ጀልባዋ መኝታ ቤት ውስጥ የምታምር ድንብሽብሽ ያለች በግምት ሶስት ወይም አራት አመት የሚሆናት ጥቁር ሉጫ ፀጉሯ ግንባሯ ላይ ድፍት ብሎ ግማሽ ፊቷን የሸፈናት ልጅ ጭልጥ ያለ የሰላም እንቅልፍ ውስጥ ገብታለች፡፡ህፃኗን በትኩረት ሲያያት የሆነ ብዙ ቀለማቶች በአእምሮው ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም እያሉ ይረብሹት ጀመረ፡፡በፀጥታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠና ቀኝ እጁን ወደ ልጅቷ ልኮ በቀስታ ግንባሯ ላይ የተደፋውን ፀጉሯን ከግንባሯ ላይ እያነሳ ትራሱ ላይ አስተኛው..እናትዬዋ ስሩ በፀጥታ ቆማ የሚያደርገውን እየተመለከተች ነው፡፡አሁን ሙሉ በሙሉ የልጅቷ ገፅታ ይታያል፡፡ይህቺ ልጅ ልብ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ ውስጥም እንዳለች እርግጠኛ ነው፡፡ይሄንን የተረዳው ደመነፍሳዊ በሆነ ስሜቱ ነው፡፡በትክክለኛው ግን ምንም ትዝ እያለው ያለ ነገር የለም፡፡
አንገቱን ቀና አደረገና ጎኑ የቆመችውን አማላይ ሴት ተመለከታት‹‹የምታግዢኝ ነገር የለም?››ሲል ጠየቃት፡፡
የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ሙሉ ፍቃደኛ እንደሆነች በሚያረጋግጥ ንግግር ‹‹ምን ላድርግልህ የእኔ ፍቅር? የፈለከውን ጠይቀኝ››አለችው፡፡
‹‹አሞኛል ..በፊት የምወስዳው መድሀኒት ወይም ኪኒን ነገር ይኖራል?፡፡››
ደነገጠች….የእሷን   መደንገጥ  ተከትሎ  እሱም  ደነገጠምም  ግራ ተጋባምም‹‹ዛሬ መድሀኒትህን አልወሰድክም እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እስከማስታውሰው ድረስ ለበርካታ ቀናት ምንም አይነት መድሀኒት የወሰድኩ አይመስለኝም፡፡››
‹‹ይሄ የፓብሎ ተግባር ነበር፡፡ግን እሱ ራሱ የት እንደገባ ምንም የሚታያውቅ ነገር የለም፡፡ቆይ መጣሁ›› ብላ ሔደችና ከሁለት ደቂቃ በኃላ ሁለት ኪኒኒ ከእሽግ ውሀ ጋር ይዛ መጣች፡፡ኪኒኖቹን ከእሽጉ ፈልቅቃ አቀበለችው….‹‹ውሀውን ከፈተችና በል ዋጥና ለአንድ ሰዓት ያህል ጋደም በል… ስትነሳ ሰላም ትሆናለህ….››
‹‹አልገባሽም ..አመመኝ ስልሽ እኮ ህመም አይደለም..ምንም የማስታውሰው ነገር የለም እያልኩሽ ነው..አንቺን ጭምር ማንንም አላስታውስም››የተረዳችው ስላልመሰለው ፍርጥ አድርጎ እውነቱን ነገራት፡፡
‹‹ገባኝ የእኔ ፍቅር ..ሁሉ ነገር ይስተካከላል… ብቻ ያልኩህን አድርግ… መድሀኒቱን ዋጥና ከልጅህ ጎን ተኛ፡፡››እንዳለችው መድሀኒቱን ተቀበላትና ዋጠ፡፡ጫማውን አወለቀና ቀስ ብሎ አልጋው ላይ ወጣና ከልጁ ጎን ተኛ፡፡ፊት ለፊት ካለው የልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ አልጋ ልብስ አወጣችና አለበሰችው፡፡ ቀስ ብላ ክፍሉን ዘግታለት ወጣችና ከጠባቂዎቹ ራቅ ብላ የጀልባዋ በረንዳ ላይ ባላ ወንበር ተቀምጣ ከወንዙ ባሻገር ያለውን ጥቅጥቅ የአማዞን ደን በተመስጦ መመልከቷን ቀጠለች፡፡

ኑሀሚ ያለችበት ጎጆ የተወታተፈ በራፍ ሲከፈት ሰማችና የጨፈነ አይኗን ከፈተች፡፡ከአጋቾቾ መካከል አንዱ ነው፡፡፡አሁን እጆ ላይ ተጣብቆ ከወዲህ ወዲያ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ቅጭልቅል እያለ የሚረብሻትን ሰንሰለት ተቆራኝቷት የነበረው ልጅ ነው፡፡በእጁ የሚበላ ነገር በሰሀን እና የሚጠጣ ውሀ በላስቲክ ኩባያ ይዞል፡፡ወደእሷ ተጠጋና በርከክ ብሎ ምግብን አስጠግቶ አስቀመጠላትና የስፓንሽ ቋንቋ ዘየ በተጫነው ግን ደግሞ ባልተደነቃቀፈ እንግሊዘኛ፡፡‹‹ተነሽ ይሄን ምግብ ብይ…ከጥቂት ጊዜ በኃላ በእግር ረጅም መንገድ መጓዛችንን ስለምንቀጥል ጥንካሬው ያስፈልግሻል፡፡››አላት፡፡
ጎኑ ላይ የያዘውን አብረቅራቂ ኮልት ሽጉጥ በጎሪጥ እየተመለከተች‹‹ወደየት ነው የምትወስዱኝ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹እሱን ለአንቺ ለመናገር ፍቃዱ የለኝም፡፡››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹እባክህ…እህት የለህም..እኔ እኮ በጣም ከሩቅ አህጉር የመጣው ምስኪን ወጣት ነኝ…ምን ላደርግላችሁ ነው እንዲህ ከእኔ ጋር የምትሰቃዩት?››አሳዛኝ መስላ ለመቅረብ ሞከረች፡፡
‹‹እህት አለኝ ….ግን ላደርግልሽ የምችለው ነገር ቢኖር  አንድ ምክር ላንቺ መስጠት ብቻ ነው፡፡››

‹‹ምንድነው? እባክ ንገረኝ፡፡››

‹‹ፈፅሞ የሞኝ ስራ እንዳትሰሪ…››
ያልጠበቀችው የምክር አይነት ስለነበር‹‹ምን ማለት ነው?››በማለት ጠየቀችው፡፡

‹‹ጥዋት በምንጓዝበት ጊዜ በየመሀከሉ ሁኔታሽን ስከታተለው ነበር… ለማምለጥ ወይም ለመፋለም የመፈለግ አዝማሚያ አይቼብሻለው፡፡ በእርግጠኝነት ትንሽ እንቅስቃሴ ወይም ሙከራ ካደረግሽ ከመሀከላችን አንድ ወዲያው ነው የሚደፋሽ… እመኚኝ ሌሎቹ እንደእኔ ልስልስ እና ደካማ ነገር አይደሉም፡፡ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ጭካኔም ያላቸውና ሰውን በመግደልና ድመት በመግደል መካለከል ምንም ልዩነት የማይታያቸው ገዳዬች ናቸው..እንደውም አጋነንከው ከላልሺኝ ለእነሱ ወሲብ ማድረግና ሰውን መግደል ተመሳሳይ አይነት እርካታ ነው የሚያጎናፅፋቸው፡፡››ሲል መስማት ከምትፈለገው ተቃራኒ የሆነ አስቀያሚ ዜና ነገራት፡፡

‹‹እና መጨረሻዬን ምንም ሳላውቅ ልክ እንደፋሲካ በግ ዝም ብዬ ልነዳ ?››

‹‹እኔ እንግዲህ እንደዛ የሚሻል ይመስለኛል፡፡በህይወት ነገ ተነገ ወዲያ ምን እንደሚከሰት አይታወቅም፡፡ነገ ይዛ የምትመጣውን እድል ለመጠበቅ ደግሞ ዛሬ በህይወት ቆይቶ ነገ ላይ መገኘት ያስፈልጋል፡፡በይ እንዳልኩሽ የቀረበልሽን ብይ…  የእግር ኮቴ እየተሰማኝ ነው፡፡
‹‹ልሂድ››ብሎ ቁጢጥ ካለበት ምንጭቅ ብሎ ተነሳና በራፉን ከፍቶ እንደአመጣጡ ተመልሶ ሄደ፡፡