الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.2K subscribers
386 photos
18 videos
8 files
919 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም via @Hayatbintkedir_bot
ጥያቄና መልስ ቁጥር ዘጠኝ/⑨ በሃምድ (አልሃምዱ ሊላህ) ብለው የሚጀምሩ ሱራዎች ስንት ናቸው ?? ሀ// 3 ለ// 4 ሐ// 5 መ// 6 ሠ// 7 ረ// መልስ የለም። ቴሌግራማችን ሼር ያድርግ👇 ትዳር በኢስላም/الزواج في الإسلام
መልስ ቁጥር ዘጠኝ/⑨ኝ

9)በሃምድ (አልሃምዱ ሊላህ) ብለው የሚጀምሩ ሱራዎች ስንት ናቸው ??

መልስ ሐ// 5 ናቸዉ እነሱም👇

1 ፋቲሃ
2 አንአም
3 ካህፍ
4 ሰበእ
5 ፋጢር ናቸው።

(ﺍﻟﻔﺎﺗﺤﺔ ـ ﺍﻷﻧﻌﺎﻡ ـ ﺍﻟﻜﻬﻒ ـ ﺳﺒﺄ ـ ﻓﺎﻃﺮ)
ለተሳተፋችሁ በሙሉ አላህ እዉቀትን ይጨምርላችሁ በርቱልኝ የሙስሊም ጀግናዉች ጀዛኩምሏሁ ኸይረን ኢንሻአላህ እንቀጥላለን ቴሌግራማችን
#ሼር_ያድርጉ👇👇
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
ጥያቄና መልስ ቁጥር አስር/⑩ 10) ከሚከተሉት ውስጥ የትኞቹን ማግባት ነው በቁርአን ውስጥ እርም የተደረገው? ? ሀ// እናት ለ// ልጆች ሐ// እህት መ// አክስት ሠ// የወንድም ልጅ ረ// የሚስት እናት ሰ// የሚስት ልጆች ሸ// ሁሉም             ቴሌግራማችን ╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ- ╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam

መልስ ቁጥር አስር/⑩

10) ከሚከተሉት ውስጥ የትኞቹን ማግባት ነው በቁርአን ውስጥ እርም የተደረገው? ?

መልስ ሸ// ሁሉም ነዉ።

حُرِّمَتْ عَلَيْكُمْ أُمَّهَاتُكُمْ وَبَنَاتُكُمْ وَأَخَوَاتُكُمْ وَعَمَّاتُكُمْ وَخَالَاتُكُمْ وَبَنَاتُ الْأَخِ وَبَنَاتُ الْأُخْتِ وَأُمَّهَاتُكُمُ اللَّاتِي أَرْضَعْنَكُمْ وَأَخَوَاتُكُم مِّنَ الرَّضَاعَةِ وَأُمَّهَاتُ نِسَائِكُمْ وَرَبَائِبُكُمُ اللَّاتِي فِي حُجُورِكُم مِّن نِّسَائِكُمُ اللَّاتِي دَخَلْتُم بِهِنَّ فَإِن لَّمْ تَكُونُوا دَخَلْتُم بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ وَحَلَائِلُ أَبْنَائِكُمُ الَّذِينَ مِنْ أَصْلَابِكُمْ وَأَن تَجْمَعُوا بَيْنَ الْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

እናቶቻችሁ፣ ሴት ልጆቻችሁም፣ እኅቶቻችሁም፣ አክስቶቻችሁም፣ የሹሜዎቻችሁም፣ የወንድም ሴቶች ልጆችም፣ የእኅት ሴቶች ልጆችም፣ እነዚያም ያጠቡዋችሁ እናቶቻችሁ፣ ከመጥባት የኾኑትም እኅቶቻችሁ፣ የሚስቶቻችሁም እናቶች፣ እነዚያም በጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ በእነርሱ የገባችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴቶች ልጆች፣ (ልታገቧቸው) በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ፡፡
በእነርሱም (በሚስቶቻችሁ) ያልገባችሁባቸው ብትኾኑ (በፈታችኋቸው ጊዜ ሴቶች ልጆቻቸውን ብታገቡ) በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ የእነዚያ ከጀርባዎቻችሁ የኾኑት ወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችም በሁለት እኅትማማቾችም መካከል መሰብሰብ (እንደዚሁ እርም ነው)፡፡ ግን ከዚህ በፊት ያለፈው ሲቀር (እርሱንስ ተምራችኋል) አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
🍃አል ኒሳእ 23( النساء 23 )🍃

ለተሳተፋችሁ በሙሉ ጀዛኩምሏሁ ኸይረን አላህ እዉቀትን ይጨምርላችሁ🌷🌷🌷🌷

            ቴሌግራማችን#ሼር_ያድርጉ👇👇👇

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
ጥያቄና መልስ ቁጥር አስር/⑩ 10) ከሚከተሉት ውስጥ የትኞቹን ማግባት ነው በቁርአን ውስጥ እርም የተደረገው? ? ሀ// እናት ለ// ልጆች ሐ// እህት መ// አክስት ሠ// የወንድም ልጅ ረ// የሚስት እናት ሰ// የሚስት ልጆች ሸ// ሁሉም             ቴሌግራማችን ╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ- ╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
ጥያቄና መልስ ቁጥር አስራአንድ/⑪

11) ዒሳ (አሌይሂ ሰላም) ጌታ አለመሆኑን ራሱ የተናገረበት ተከታዩ አያ ምን ሱራ ላይ ይገኛል ???

لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ

እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡

ሀ//ሡረቱል በቀራ ቁ፡38
ለ//ሡረቱል መርየም ቁ፡4
ሐ//ሡረቱ አል ዒምራን ቁ፡72
መ// ሡረቱል ኢኽላስ ቁ፡3
ሠ//  መልሱ የለም

            ቴሌግራማችን
#ሼር_ያድርጉ👇👇👇

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር~በኢስላም::::::☜   #ክፍል_አምስት/⑤ት ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ሀይማኖቶች... #ከአንድ በላይ ሚስት በአይሁዳዎች እምነት       ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ሀይማኖቶች የተፈቀደ እና ወሰን ያልተቀመጠለት ድንጋጌ እንደነበር ከላይ አሳልፈናል። አይሁዶች ከአንድ በላይ ሚስትን የሚፈቅዱ ሲሆን#ቱልሙድ በሚባለው ሰው ሰራሽ መፅሀፋቸው የሚስትን ቁጥር አራት መሆን አለበት የሚል…
☞ትዳር_በኢስላ☜

 
#ክፍል_ስድስት/⑥

☞ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ህዝቦች ዘንድ
 
#በቀደምት_ቻይናውያን_ዘንድ
የቻይና ወንዶች በቀድሞ ዘመን የመጀመሪያ ሚስታቸውን ካገቡ በኃላ በርካታ ልጅ አገረዶችን በመግዛት እንደፈለጉ ይጠቀሙባቸው ነበር።
#በኃላየ ተገቡት ወይም የተገዙት ሴቶች ለመጀመሪያዋሚስት ታዛዥ የመሆን ግዴታ አለባቸው ከሌሎች ሚስቶቹ የሚወለዱት ልጆች ለመጀመሪያዋ ሚስት እንደልጅ ታስበው ያድጋሉ።
☞ የቻይና ሴቶች ለባሎቻቸው ባሪያ በመሆን ራሳቸውን እስከማቃጠል የደረሰ መስዋእትነት ይከፍሉ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። የቻይና ባሎች  የሚፈልጓቸውን ሴቶች በቁጥር ሳይገደቡ በህጋዊ ጋብቻ ያገባል። ባል ከመጀመሪያ ሚስቱም ሆነ ከሌላው ማህበረሰብ ለምን አገባህ የሚል ወቀሳ አልነበረም። እንዳውም ወንዶች ከአንድ በላይ እንዲያገቡ ይበረታቱ ነበር።ከዚህም በተጨማሪ
#ገንዘብ_ያለው_ቻይናዊ_ወንድ_በገንዘቡ_የሚፈልጋቸውን_ሴቶች_በመግዛት_እንደሚስት_እንደሚስት_አድርጎ_ይጠቀምባቸው_ነበር
☞ ይህ የጥንት ቻይናውያን ባህል እና ወግ ሆኖ አልፏል።አሁን ቻይናውያን ከሚፈፅሙት አስፀያፊ ተግባር ጋር ሲነፃፀር ያ ትውልድ የተሻለ ያሰየሚመደቡ የአሁኖቹ ቻይኖች እንደበፊቱ በህጋዊ መንገድ
#ከአንድ_በላይ ሴቶችን ባይዙም ሰለጠን ብለው አንድትን ሴት ለአራትና ለአምስት በአንድ ጊዜ ከሚገናኙት ብልሹ ህዝቦች የሚመደቡ ናቸው።አላፍር ብለው የእነሱን ተግባር እንደመልካም በመቁጠር ያለፉት ህዝቦች ተግባር ሲኮንኑ ይደመጣሉ።መኮነን ያለበትን እንኳ በቅጡ የማያውቁ እንስሶች፣
  
#በቀደምት_ህንዶች_ዘንድ
   በጥንታዊያን ህንዶች ዘእንዲሰጡ እንደቻይናዎቹ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተለመደ ተግባር ነው።ለሴቶች የሚሰጠው ግምት ከወንዶች በእጅጉ ያነሰ ነበር፣ሴቶች ሙሉ ማንነታቸውን  ለባሎቻቸው አሳልፈው እንዲሰጡ ይገደዳሉ። የህንድ ወንዶች ከአካባቢያቸው እና ጎሳዎቻቸው እራቅ ብለው በመሄድ የፈለጉት ያክል ሴት ያገቡ ነበር። ከሚስቶቹ መካከል የተሻለችውን በመምረጥ ሌሎቹን ሴቶች እንድትመራ እና እንድታስተዳድር ይደረጋል። በብዛት ይህን ስልጣን የሚሰጣት የመጀመሪያ ሚስት ናት። አንዳንድ የህንድ ወንዶች በሺ የሚቆጠሩ ሚስቶች ያገቡ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል።
#ሪባ_የሚባለው_የህንድ_ንጉስ_3000_ሚስቶች እንደነበሩት ይነገራል። በጣም የሚገርመው ከጥንታዊ ህንዶች ሴቶች መካከል አንድ ጊዜ ከተገቡ እንዳጋጣሚ ባላቸው ከሞተከዚህ በኃላ አለም በቃኝ ብለቅ እራሳቸውን በእሳት የሚያቃጥሉም ጎሳዎች ነበሩ.በቀደምት ፈረንሳዊያን_ዘእቃ
   ከሁለት ንግስት ሴቶች በስተቀር በአጠቃላይ ፈረንሳይ ለሴት ልጆች ቦታ የምትሰጥ አገር አልነበረችም እነርሱ ዘንድ ሴት ልጅን እንደተራ መገልገያ እቃ ይቆጥራሉ።አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ጥፋት የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል። በፈረንሳይዎች ዘንድ አንድ ወንድ የፈለገውን ያህል ሴት ማግባት ይችላል። ብዙ ሴት ማግባት የወንድነት መገለጫ መሆኑን ማህበረሰቡ የሚያምንበት ተግባር ነው። ከዚህ በጣም የከፋ ው ለመስማት የሚዘገንነው አንድ ስሩት እናቱን ፣ ሴት ልጁን፣ እህቱን እንዲሁም 2 እህትማማቾችን ማግባት የሚችልበት ማህበረሰብ ነበር። ለነገሩ አሁንስ ቢኖን በሙስሊሞች ላይ ጣታቸውን የሚቀስሩት ምእራባዊያን ተግባራቸው ከዚህ የተለየ ነው እንዴ? ሴት ልጆቻቸውን የሚደፍሩ ምእራባዊያን ቁጥራቸው ቀላል ነው ?በቀደምት ግብፆች ዘንድ
   በጥንታዊ ግብፆች ዘንድ ነጠላ ሚስትን አብዛኛው ማህበረሰብ የሚያገባ ቢሆንም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትም እንግዳ አልነበረም። በተለይ የግብፅ ንጉሶች እና የንጉስ ቤተሰቦች በስፋት ይተገብሩት ነበር። ይህ ማለት ግን ተራው ማህበረሰብ ማግባት አይፈቀድለትም ማለት አይደለም።
አንድ ወንድ ሁለት ሴቶችን የሚያገባ ከሆነ ሁለቱን ሴቶች በየግላቸው ራሱን በቻለ ቤት በማኖር ባል በየተራ ሚስቶቹን እየዞረ ይጠይቃል ነገር ግን
#መጀመሪያ መጀመሪያ የተገባችው_ሴት የተለየ ክብር እና ቦታ ትይዛለች
   
#በጥታዊ ግሪኮች_ዘንድ
   ጥንታዊ ግሪኮች ከሴት ልጅ ይልቅ ለወንድ ልጅ ልዩ ክብር ስለነበራቸው
#ሚስት የሚያገቡበት ዋናው_አላማ ወንድባልጅ ለማግኘት እንደሆነ ይነገራል።ሚስቱ መውለድ የማትችል ከሆነ የመፍታት ሙሉ መብቱ የወንድ ነው። ሴቶች ባል ካገቡ በኃላ ከቤት መውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር። በእርግጥ ለሴት ልጅ ክብሯ ከቤት አለመውጣቷ ነው።በግሪኮች ዘንድ አንድበእጅጉ የተለመደ ቢሆንም ወንዶቹ እንደሚስታቸው የሚቆጥሯት አንድ ተጨማሪ ሴት በየቦታው ትኖራለች።ከዚህ በተጨማሪ የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ስለነበር በአገሩ ህግ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚፈቀድና የሚበረታታ አዋጅ ወጥቶ ነበር፣ለምሳሌ ሶቅራጥስ በህጋዊ መንገድ ያገባቸው ሁለት ሚስቶች ነበሩት።.

  
#በጥንታዊ_ሮማዊያን_ዘንድ
   እንደሌሎች ሀገሮች ሁሉ ጥንታዊ ሮሞች ከአንድ በላይ ሚስት የሚፈቅድ ህግ ነበራቸው። ይህንንም ቤተክርስቲያን ትቀበለው እና ታፀድቀው ነበር። ጊዜው እየረዘመ ሲመጣ ከ1750  ዓ. ል በኃላ ከአንድ በላይ ሚስት ቤተክርስቲያኗ አትደግፍም በማለት የሌላ ህግ በማውጣት መከልከላቸው ይታወቃል።ይህ ክልከላ የፈጣሪ ትእዛዝ የሌለበት ሰው ሰራሽ ፈጠራ ከመሆን ውጭ እንደቁም ነገር ሃይማኖታዊ ሽፋን ተሰጥቶት በማስረጃነት ሊቀርብም ሆነ ሌሎችንም ለመተቸት ከግምት የሚገባ አይደለም.ከአንድ_በላይ_ሚስት_በጥንታዊ_አረቦችጥንታ   አረቦች ያለገደብ የሚበቃቸውን ያህል ሚስት ያገቡ እንደነበር የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።ብዙ ሴቶች ማግባት የሀይለኝነት ፣ የታዋቂነት፣የጀግንነትና የባለፀጋነት መገለጫ አድርገው ይቆጥሩታል።አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ባገባ ቁጥር ደረጃውም በዛው ልክ እየጨመረ ይሄዳል ተብሎ ይታሰብ ነበር 
#አንዳንዶቹ_ስድስትአ_ንዳንዶቹ_አስር_ሌሎቹ_ደግሞ_እስከመቶ የሚደርሱ ሚስቶች ነበሯቸው።እንደምሳሌ ብንመለከት ፣ የነብዩ ሰአወ አጎት አብዱልሙጠሊብ፣ሱፍያን ቢንሀርብ እና ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ነበራቸው ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባህ ሰባት ሚስቶች ነበሯቸው
    ☞ ነብዩ  ﷺ እስልምናን ይዘው ሲመጡ አብዛኛዎቹ የአረብ ንዳቸው ከአስር ያላነሱ ሚስቶች ነበሯቸው።ለምሳሌ ሱዑድ ኢብኑ መዕቀብ ፣ዑርወት ኢብኑ መስኡድ፣ሱፍያን ኢብኑ አብዲላህ እና መስኡድ ኢብኑ አምር እያንዳንዳቸው አስር አስር ሚስቶች ነበሯቸው።

ቀይስ ኢብኑ ሳቢት ሲያወሩ እንዲህ ይላሉ፣ስምንት ሚስቶች በስሬ እያሉ እስልምናን ተቀበልኩ፣ከዛም ወደአላህ መልእክተኛ ዘንድ መጥቼ ይህን ነገርኳቸው እሳቸውም "ከእነሱ ውስጥ አራት ምረጥና ሌሎቹን ፍታ" አሉኝ ይላል.
   ☞ አብደላህ ኢብኑ ኡመር ሲያወሩ በጃሂልያ ይላሉ በጃሂልያ ዘመን ያገባኋቸው አስር ሚስቶች በስሬ እያሉ እኔም ሚስቶቼም እስልምናን ተቀበልን።ከእነርሱ 4 ብቻ እንድመርጥ ነብዩ ﷺ አዘዙኝ"ይላል።

   ☞ ነውፈል ኢብኑ ሙአዊያህ እንዲህ ይላሉ፣ "5 ሚስቶች በስሬ እያሉ እስልምናን ተቀበልኩ፣ከዛም ወደአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓሌይሂ ወሰለም ዘንድ መጥቼ ጠየኳቸው፣ እርሳቸውም "አንዷን ፍታ ሌሎቹን ያዝ" አሉኝ ይላል።
    በዚያን ጊዜ(በጃሂልያህ ዘመን) በአንድ ወንድ ስር የሚኖሩ ሴቶች መብዛታቸው ብቻ ሳይሆን ከወንዶች በኩል የሚደርስባቸው በደል እጅግ የሚዘገንን ነበር  ወንዶች ያለገደብ
ያገቧቸውን ሴቶች አይደለም በፍትህ ሊያስተዳድሯቸው የሚያስፈልጋቸውን እንኳን መሰረታዊ ነገሮች አያገኙም ነበር የሰው ልጅ መሆናቸው ግምትየሚሰጠው አልነበረም።
ይቀጥላል #ሼር_ያድርጉ
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::☜   .#ክፍል_ስምንት/⑧ት       #ከአንድ በላይ ሚስት በኢስላም #እስከ_አራት_የተፈቀደ_ለመሆኑ_ማስረጃ                 #ቁርአናዊ_ማስረጃ    አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣ وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ…
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜

  ክፍል ዘጠኝ/⑨ኝ

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

    አላህ ለወንድ ልጅ ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ማግባት እንዲችል ሲፈቅድለት የሰው ልጅ ሊደርስበት የማይችል ሚስጥራዊ ሂክማ አለው።

    በኢስላም ውስጥ አብዛሀኞቹ  በቁጥር የተገደቡ ኢባዳዎች የቁጥራቸውን ሚስጥር ጥራትና ልቅና የተገባው ጌታችን አላህ ሱወ ብቻ ነው የሚያውቀው።የዙህር ሶላት ለምን አራት ሆነ፣የመግሪብ  ሶላት ለምን ሶስት ሆነ፣ሱብሂ ለምን ሁለት ሆነ፣ ለምን 5ወይ6 ወይም አንዳንድ አልሆነም? ሁሉም ሶላቶች ለምን ተመሳሳይ ቁጥር አልኖራቸውም?እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ።ነገር ግን የእነዚህን የተለያየ ቁጥር ያላቸውን የኢባዳ አይነቶች ሚስጥር የሚያውቃቸው አላህ ብቻ ነው።የሰውነት የአካል ክፍላችን ብዛት ብናስተነትን እና እያንዳንዱን የቁጥር መጠን ለምን ሆነ ብንል፣አይናችን ለምን 2 ሆነ፣ጆሮስ ለምን 2 ሆነ፣የእጅ ጣቶች ለምን 5 ሆኑ፣ለምን 4 ወይም 6 ዘልሆነም?? የሚለውን የብዛቱን ሚስጥር አዋቂው አላህ ብቻ ነው።

   ☞ ከአንድ በላይ ሚስት ያውም ደግሞ 4 የሚለው ቁጥር ለምን ተመረጠ ቢባል መልሱ ሁሉን አዋቂ የሆነው ጌታችን ብቻ የዚህ ሚስጥር ባለቤት ነቅ የሚል ምላሽ ይሆናል።

   ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የራሱ የሆነ ጥበብ መኖሩ እንዳለ ሆኖ ኡለሞች የሚዘረዝሯቸው አስደናቂ ጥበቦች አሉት እነዚህ ጥበቦች እንደሚከተለው አንድ ሁለት እያልን እንዘረዝራለን፣

1/
#የአላህ_መልእክተኛን_ሰአወ_ሱና_ለመከተል_ሲባል

   እንደሚታወቀው የአላህ መልእክተኛ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩ ድረስ ከአንድ በላይ ሚስቶች ነበራቸው።የአላህ መልእክተኛ ከአንዳንድ እሳቸው ብቻ ከሚለዩባቸው ተግባራቸው በስተቀር የእሳቸውን ፈለግ እንድንከተል ታዘናል።ይህንን አስመልክቶ አላህ በቁርአኑ እንዲህ ብሎናል፣

لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 21)

    ☞የአላህ መልእክተኛ የደነገጉትን መቀበል እና ሃቅ ነው ብሎ ማመን የሙስሊሞች ግዴታ ነው።ከአንድ በላይ ሚስት በሸሪዓ የተፈቀደ እና የተወደደ ነው የሚለውን መቀበል በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አያስፈልግም ብሎ የጠላ ወይም መሆን አልነበረበትም ብሎ የተቃወመ ከኢስላም እንደሚወጣ የኢስላም ሊቃውንት ይስማማሉ።

     ነብዩ ሰአወ ለዱኒያም  ለአኼራም ለኡመታቸው የተሻለውን ነገር ሳያመላክቱ መጥፎን ነገር ሳያሰረጠነቅቁ አላለፉም። መጥፎውን እና ደጉን የማስተማር ሀላፊነት አላህ አስቀምጦላቸዋል።ነብዩ ሰአወ በንግግራቸው፣በተግባራቸው እና አይተው በማፅደቅ ያስተምራሉ።ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚወደድ እና የተሻለ እንደሆነ በተግባራቸው አስተምረውናል።ለሰዎች ሚስጥሩ በግልፅ ያልተገለፀው ከአንድ በላይ ሆኖ መግባትም እንደዚሁ ለሴቶች ትልቅ ጥቅም እንዳለው ያስገነዝባል።ለዚህም በርካታ ምክንያቶች መጥቀስ ይችላሉ።ከእነዚህም ውስጥ ነብዩ ለህዝባቸው ሲያስተምሩ የተሻለውን ወይም የበለጠ ጥቅም የሚያስገኘውን ነው ካልን ለሴቶች ኡመቶቻቸው የሚጎዳ ወይም የበለጠ ጥቅም የማያስገኝ በፍፁም ሊደነግጉ ወይም ሊያመላክቱ አይችሉም።ሌላው እናታችን አኢሻ ረአ ከሁሉም ሴቶች እንደምትበልጥ ነብዩ መስክረዋል።እሷ ከነብዩ ሚስቶች ከዘጠኝ አንዷ ናት ስለዚህ ከአንድ በላይ ሚስት ሆና መግባት ደረጃን የሚቀንስ ከሆነ ከሴቶች ሁሉ የምትበልጠው እናታችን አኢሻ ረአ ለምን በእሷ ላይ ሌላ ተገባባት።በሌላ አነጋገር ከአንድ በላይ ሚስት ሆኖ ሴቶችን ክብር ይቀንሳል ወይም ሴቶችን ከጓደኞቻቸው የበታችነት እንዲሰማቸው ያደርጋል ብሎ ማሰብ አኢሻን ረአ የበታች ነበረች ብሎ እንደማሰብ ይቆጠራል።ይህ አስተሳስብ ደግሞ ከኢስላም ጋር ይጋጫል።

    ☞ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ከአንድ በላይ ካላገባው ጋር ሲነፃፀር በደረጃ የተሻለ እንደሚሆን ነብዩ ሰአወ በሃዲሳቸው እንዲህ ሲሉ  ተናግረዋል፣

     
#ሰኢድ_ኢብኑ_ጁበይር_ረአ ባስተላለፉት ሀዲስ"አብደላህ ኢብኑ አባስ አግብተሃል?ሲል ጠየቀኝ እኔም አላገባሁም አልኩት፣አግባ ከዚች ኡማ የተሻለው ብዙ ሚስቶች ያሉት ነው"" አለኝ ይላሉ። ሀዲሱን ቡኻሪ ዘግበውታል።

2
#ሳያገቡ_እድሜያቸው_የገፉና_የሚፈቱ_ሴቶች_መኖርና_መበራከት

  እነዚህ ሁለት አይነት ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።እድሜያቸውን ከገፉ በኃላ ለመጀመሪያ ሚስት የሚፈልጋቸው ወንድ አናሳ ነው።ወይም ደግሞ እንደሚታወቀው ወንዶች ለማግባት መሰረታዊ የሚባል የቤት ወጪን የሚሸፍኑበት ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። ይህን ገንዘብ በልጅነት እድሜያቸው ካላገኙ እስቲሳካላቸው የተወሰነ ጊዜ መጠበቃቸው አይቀሬ ነው።በዚህም የተነሳማግባት ከነበረባቸው እድሜያቸው ከገፉ በኃላ ይሆናል። የእነሱ አለማግባት በእኩያታቸው ያሉ ሴቶች ቶሎ ላያገቡ ይችላሉ።እነዚህ በእድሜያቸው ብዙ ከሄደ በኃላ ሚስት ሊያገቡ የሚያስቡ ወንዶች በእድሜ ከእነሱ ጋር እኩል የሆኑ ሴቶች ሳይሆን ለጋ የሆነችውን ሴት ይመርጣሉ። በዚህም ምክንያት እነዚህን ሴቶች ለመጀመሪያ ሚስትነት የሚፈልጋቸው ወንድ አናሳ ይሆናል ማለት ነው። ያለባል እንዳይቀሩ መፍትሄ ይሆን ዘንድ ከአንድ በላይ መፈቀዱ ኢስላማዊ ጥበብ ነው። በተመሳሳይ የተፈታችንም ሴት ለመጀመሪያ ሚስትነት የሚፈልጓት ወንዶች እጅግ አናሳ ናቸው።ለዚህም መፍትሄው ያለባል ከመቅረት ሁለተኛ ማግባት ነው
  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ
            3_4_&_5

👇በቀጣይ ርዕሳችን ይቀጥላል ሺንሻአላህ
#ሼር_ያድርጉ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ያጀማዓ እንዴት አመሻችሁ ?? በጥያቄዉ ዙሪያ ሌላ ሀሳብ ይዤላችሁ ቀረባለዉ ።
ሀሳቡም ይህ ነዉ 👇👇

በየሳምንቱ ጥያቄና መልስ ይኖረናል ግን ሽልማቱ በየሳምንቱ ሳይሆን ያገኛቹት ዉጤት በእየሳምንቱ እየተደምረ በአምስተኛዉ ዙር ያምታገኙት ነጥብ ነዉ አሸላሚ የማደርጋችሁ ።
ስለዚህ በያሳምንቱ ጥሩ ነጥብ መስመዝገብ አለባችሁ እናም በዚህ ሀሳብ ይምትስማሙ ላይክ በማድረግ አሳዩኝ👉👍

ልብ በሉ ሽልማት ብቻ ለማግኘት ሳይሆነ ለእዉቀትም መስራት እንዳለብን አትዘንጉ❗️❗️

እንስማማለን 👍
አይ አንስማማም ይቅር👎

ይበልጥ ለይክ በገኝዉ ሀሳብ እንወስናለን ኢንሻአላህ

ቴሌግራማችን ለወዳጅ ዘመዷ
#ሼር_ያድርጉ👇👇

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ዛሬ ጥያቄና መልስ አለን ኢንሻአላህ
ዝግጁ ናችሁ??
ዝግጁ የሆናችሁ ??? ☜ 👍
#ሼር_በማድረግም_ያስተላልፉ👇

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal

እዚህ ቻናል ለይ 👆ነዉ
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
ጥያቄና መልስ ቁጥር አስራስድስት/⑯ት

16) ሰይዱል ኢስቲግፋር (የኢስቲግፋሮች ሁሉ የበላይ) በመባል የሚታወቀው ዚክር (ዱዓ) የቱ ነው?? @Tidar_Be_Islam
መልስ ቁጥር አስራስድስት/⑯ት

16) ሰይዱል ኢስቲግፋር (የኢስቲግፋሮች ሁሉ የበላይ) በመባል የሚታወቀው ዚክር (ዱዓ) የቱ ነው??

#መልሱ_ሸ //  ነዉ መልስ የለዉም

‎حَدَّثَنِي شَدَّادُ بْنُ أَوْسٍ رَضِيَ اللَّهُ
‎عَنْهُ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : "
َيِّدُ_الِاسْتِغْفَارِ أَنْ تَقُولَ : اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ وَأَبُوءُ بِذَنْبِي، فَاغْفِرْ لِي ؛ فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ ". قَالَ : " وَمَنْ قَالَهَا مِنَ النَّهَارِ مُوقِنًا بِهَا، فَمَاتَ مِنْ يَوْمِهِ قَبْلَ أَنْ يُمْسِيَ، فَهُوَ مِنْ أَهْلِ الْجَنَّةِ، وَمَنْ قَالَهَا مِنَ اللَّيْلِ وَهُوَ مُوقِنٌ بِهَا، فَمَاتَ قَبْلَ أَنْ يُصْبِحَ، فَهُوَ مِنْ أَهْلِ الْجَنَّةِ ".

ሸዳድ ኢብኑ አውስ  (رَضِيَ اللَّهُ
‎عَنْهُ، )እንደነገሩን የአላህ መልክተኛ (ﷺ )እንድህ አሉ:👇-

#የኢስቲግፋር (አላህን ምህረት መለመን) ሁሉ አይነታ እንድህ ማለት ነው:-↡↓↓

አላህ ሆይ!  ፈጣሪዬ አንተ ነህ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ፈጥረህኛል፡፡ እኔ ባሪያህ ነኝ፡፡ እኔ የቻልኩትን ያክል ያንተን ቃልዳኪን ለመሙላት እሞክራለሁ፡፡ ከስራሀው ነገር ከክፉው በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ በኔ ላይ ለዋልከው ጸጋህ እውቅና እሰጣለሁ፡፡ ሐጢአቴም እናዘዛለሁ፡፡ ማረኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሐጢአትን የሚምር የለም፡፡
በቀኑ ክፍል ከልቡ አምኖ ና እርግጠኛ ሁኖ ይህን ዚክር ያለ ሰው
ከማምሸቱ በፊት ቢሞት እንኳ እሱ
#የጀነት ሰው ነው::
በምሽቱ ክፍል ከልቡ አምኖ ና እርግጠኛ ሁኖ ይህን ዚክር ያለ ሰው
ከማንጋቱ በፊት ቢሞት እንኳ እሱ
#የጀነት ሰው ነው::
ቡኻሪ

🌷የአላህ ምንኛ መታደል ነው አላህ ለኔም ለናንተም ያግራልን አሚን🤲🤲
#ሼር_ያድርጉ👇👇👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
#ሴት_ልጅን_ሸሪዐዊ_ዕውቀት_ማስተማር_ሕብረተሰብን_ማስተማር_ነው!

ሴቶች ...☜
– እናቶች
– እሕቶች
– ሚስቶች
– ልጆች ናቸው ።

ሴት ስትማር እራሷን ቀይራ ልጇንም በኢስላማዊ ተርቢያ ኮትኩታ ታሳድጋለች።

☞ያኔ መጪው ትውልድም ከመሠረቱ ያብባል ። ሕፃናት አፋቸውን በ “ላኢላሃ ኢለላህ” በ “አላሁ አክበር” ከሊማ ይፈታሉ ።
☞ለማንነታቸው ተምሳሌት ማንንም ሳይሆን ታላቁና ተወዳጁ የአላህ ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን እና ሶሓቦችን ያደርጋሉ።  ገና በልጅነት አዕምሮዋቸው ግባቸውን በጀነቱል ፊርደውስ ይቀርፃሉ ።

በኢስላም ውስጥ ለኢስላም ኖረው ለኢስላም መሞትን ይመኛሉ ።

☞ያኛው ተናፋቂ የነሶሓቢው ኢብኑ ዑመር ፣ ኢብኑ መስዑድ (ሪድዋኑላሂ ዐለይሂም) ፣ የነ ኢማሙ ሻፊዒይ ፣ የነኢማሙ አሕመድ ፣ የነኢማም ቡኻሪ ፣የነኢብኑ ሐጀር ፣ የነኢብኑ ተይሚያህ  የነኢማም ዐብዱልወሃብ፣ የነኢብኑ ባዝ ፣ የነአልባኒ ተተኪ ትውልድ ይፈጠራል ።

በሽርክና ቢድዐ የተጨማለቀው ጨለማ ዘመን በዕውቀት ላይ በተመረኮዘው ተተኪ ትውልድ በተውሒድና በሱና ብርሐን ይታደሳል

በጭፍን ተከታይነት ፣ በዘር ወገንተኝነት ፣ በጅሕልና ፅልመት ፣ በአውሬነት ባሕሪ የተላበሰ ክፉ ዘመን የነገው እናቶች በገበዩት ሸሪዐዊ ዕውቀት እራሳቸውን ልጆቻቸውንም ኮትኩተው በኢስላማዊ አደብ በማሳደግ ትውልድን ሊቀይሩ ከምንም በላይ አስፈላጊና ይበልጥ የተገባ ነው ።
☞ስለዚህ ውዷ እሕቴ ይህን ሃላፊነትሽን ለመወጣት ዛሬውኑ ሸሪዐዊ ዕውቀትን መፈለግ ይኖርብሻል የሚለው ትልቁ ልባዊ ምክሬ ነው ።
#ሼር_በማድረግም_አስተላልፉት

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
★:::::::::እኔ ፆመኛ ነኝ! :::::::::★

የአላህ መልእክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል:-
ከእናንተ አንዳችሁ በፆመ ጊዜ:-

 
#ፀያፍ አይናገር 🚫

#አይጩህም 🚫

አንድ ሰው ከሰደበው ወይም ከተጋደለው ''እኔ ፆመኛ ነኝ'' ይበል::

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግቦታል#
ሼር👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ
አስደሳች ዜና በወንድማችን ሀሰን አህመድ
 
ጋብቻ  በኢስላም  
      ጣፋጩ  የህይወት  መንገድ በሚል ርዕስ አዲስ መፅሐፍ ለእህት ወንድሞቹ ለህዝበ ሙስሊሙ አበረከተ !!

መፅሐፉ ስለ ጋብቻ ምንነት ፣ስለ ጋብቻ አስፈላጊነትና  አንገብጋቢነት ፣ ስለ ትዳር በቂ የሆነ  ግንዛቤ   እንድንይዝ  የሚረዳን መፅሐፍ ነዉ ።


እንዲሁም መፅሀፉ ሰላም የሰፈነበትን፣እዝነትና ፍቅር የበዛበትን ፣ጣፋጭና ደስተኛ የትዳር ህይወት ለመመስረትና ለመምራት እንዲሁም ኢስላማዊ ቤተሰብ ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ።

መፅሃፉን ለማግኝት በዚህ አድራሻችን ያናግሩን👇
📞09_56_57_69_02/ 0956566902 ☜

📞ደዉለዉ ይዘዙን።
#ሼር_በማድረግም_ያስተላልፉ
📌እህቶች ግን ሚድያ ላይ ለምንድነው የምትወጡት???

የተገላለጠችዋን ሲመክሩ ጭራሽ ሙተነቂቦችም መውጣት ጀመሩ።ኒቋቧን ለብሳ ወጥታ ቁርኣን ትቀራለች፣ኪታቦችን ታስቀራለች፣የኒቋብ style ታሳያለች አረ ስንቱን ወል ዒያዙ ቢላህ!   አስለን የመሰተር አላማው ምንድነው??!  ከሙተበሪጃዋ በምን ተለየሽ አንቺም ወጥተሽ ያዙኝ ልቀቁኝ ካልሽ???  ለምን ዲናችንን እናሰድባለን???
ለሙሃዶራህ 👈 ነውኮ ካልሽ አንቺ አታስፈልጊም ሚድያ ላይ ወጥተሽ ለማስተማር   ጀግና የሱናህ ወንድሞች አሉን እነሱ ይበቃሉ።       ማስተማርና ማቅራት ከፈለግሽ እህቶችሽን ብቻ ወንዶች የማያዩሽን ቦታና ጊዜ መርጠሽ አስተምሪ።  ሚድያ ላይ በምንም መልኩ መውጣትሽ አያስፈልግም።  
አሁን አሁን ላይ ሙተነቂቦች በጣም እየበዙ ነው ሚድያ ላይ መውጣት።
    ወንዶች ፊት የተለያዩ የሚስቡ ድርጊቶችን ወጥታ ታሳያለች።
ቆይ ወንዶች የተሸፈነችዋም ሴት ጭምር እንደምትፈትናቸው አታውቂምን???????
ከሙተበሪጃዋ ባላነሰ መልኩ ሙተነቂቧም የምትፈትነው እንዳለ ዘነጋሽው????
የመሸፈንሽ አላማ ምንድነው??????  አይደለም ቪድዮሽን ድምፅሽ ራሱ አያስፈልግም በምንም በቃ አንቺ ተሰተሪ የውጩንም የውስጡንም ኒቋብ/ሂጃብ ተላበሺ።
ሀያዕ ሊኖረን ይገባል    ሀያዕ ከሌለን እመኚኝ አንከበርም። ሀያኣችን ነው ከፍ ዝቅ የሚያደርገን።
         አሁንም የምልሽ፦ለማስቀራትና ለማስተማር በሚል ሰበብ ሚድያ ላይ ወጥተሽ ወንዶች ፊት አታውሪ። አያስፈልግም።   ከቻልሽ በፅሁፍ ካልቻልሽ ሁሉን መተው።        እህቶችሽን ብቻ አቅሪ።    ብዙ የሱና አንበሶች አሉ እነሱ ይሸፍናሉ ቀሪውን።
ንግግር አላብዛ  እናም እህቴ እስካሁን ለፖሰትሽው ተፀፅተሽ ቪድዮሽን አጥፊ ለሚቀጥለው ደግሞ ላለ መስራት ለረቡና ቃል ግቢለት!
ሀያዕ 👈ከኢማን ነው።  ኒቋብ ከሀያዕ ጋር ነው የሚሄደው።
ወሏሁ አዕለም

#ሼር_አድርጉልኝ_ለሁሉም_ይድረስ

👉#ቴሌግራማችን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
Video
ألسلام عليكم ورحمة الله وبركاته إخواني وأخواتي في كل بلاد العالم أهلان وسهلان فيكم وأنا أخوكم إسم محمد ربيع من إثيوبيا من ألفين إحدا عشر وحتى الآن في البيت بمرض الله يحفظكم ومن كل مرض ومن كل إبتلاء يارب العالمين وساكن في بيت العجار وعنده ثلاث أولاد ماعند شيء لأولاد في يدي إلا ربالعالمين أرجو مصعاد ألمؤمن أخوالمؤمن من فرج عن مؤمن كربة من كرب الدنيا نفس الله له كربة من كرب يوم القيامة رقم الحساب البنك تجااري ألإثيوبيا ١٠٠٠١٨٥٢٠٢٧٤٨ رقم جوال ٠٩٣٦٩٧٩٨٣٥ إسم محمد ربيع

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ
ወበረካቱሁ ውድ ወንድሞቼና ውድ እህቶቼ እንዴትነችሁ ደህናነችሁ ሰላምነችሁ የአላህ ሰላምና ረድኤት በረከት እዝነት አይለያቹሁ እኔ ወንድማቹሁ መሀመድ ረቢኢ ነኝ ከኢትዮጵያ አዛኙ አላህ ከኩፉ ቀደር ይጠብቃችሁ በሙሉ አፊያ ያረበል አለሚን በጤና ችግር ምክንያት ቤት እንደለሁኝ አብዘኛ ወንድሞቼ እህቶቼ የውቋሉ ባላቸው ነገሪና በዱዓቸው ከጎኔ ያልተለዩኚ አጅሩን አዛኙ አላህ በእዝነቱ በዲን በዱንያ ይክፈላቸው ያረበል አለሚን

የልጆቼን ህይወት ለመታደግ ተባበሩኝ በአላህ ቀደር ቤት ለመሆንና የወንድሞቼን የእህቶችን እጂ ለማየት ተገደድኩኝ አዛኙ አላህ ከኩፉ ቀደር በእዝነቱ ይጠብቋቹሁ የሰው እጂ የሚያሰይ ነገር አያምጧባቹሁ ያረበል አለሚን

የአካዉንት ቁጡር 1000185202748 ነው ስልክ ቁጥር 0936979835 ስም መሀመድ ረቢኢ ነኝ ከኢትዮጵያ ሀፈዘኩም አሏሁ ወምንኩሊ በላእ ያረበል አለሚን

#ሼር_በማድረግም_ተባበሩን

@Tidar_Be_Islam
@Tidar_Be_Islam
❗️እሷን ፍታት እና ከእኔ ጋር እንጋባ❗️

➻አንዳንድ እህቶች ለሌላዋ እህታቸው ብቻ ሳይሆን ለራሳቸውም አያዝኑም።❗️

እንዴት ብትሉ........❗️
የያዝካትን ሚስት ፍታትና እኔ ጋር እንጋባ ማለታቸው ለራስም ካለማሰብ የመነጨ ነው ለማለት ፈልጌ ነው። ምናልባት ይሄን የምትፈፅም ሴት በእህቷ ላይ የፈፀመችው ግፍ በራሷ ላይ ዞሮ እንደሚመጣባት ባለማስተዋሏ ሊሆን ይችላል። እውነታው ግን እህቷን በድላ ያገባች ሴት ቢዘገይም በሌላዋ እህት ተገፍታ መውጣቷ አይቀሬ ነው። ሌላዋን አስፈትታ በሀራም የመሠረተችውም ትዳር ለእሷ የተባረከና ፍሬያማ ሳይሆን አቃጣይ እሳት እንድሁም  ፍሬውም መራራ ሊሆንባት ይችላል። ምክንያቱም አላህ ፍትሃዊ ጌታ ስለሆነ የተበደለችውን እህት ብሶት ከንቱ አያደርገውም።
እንደአባባልም  "በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም" ሲባል አልሰማችሁም? አዎ "አልጀዛኡ ሚን ጂንሲ አል ዐመል" ነው።

ስለዚህ ሁለተኛ አግብታው መኖር እየቻለች ከእሷ እኔ እሻልሃለሁ ብላ በማታለል ወይም ባል የመጀመሪያዋን በምን ምክንያት እንደጠላት ስላወቀች ብቻ የእሷን ግድፈቶች እንደምትሞላለት በመግለፅ አታልላ ማስፈታቷ
#ሀራም ነው።

ኢብኑ ሂባን በዘገቡት እና አልባኒ ትክክለኛ ባሉት ሀዲስ  "አንድት ሴት (በዲን) እህቷ እቃዎች ልትጠቀም  የእህቷን ፍች መጠየቅ  አይፈቀድላትም ማለታቸው የራሷን
#ትዳር ለመመስረት በማሰብ ሌላዋን ማስፈታት ሀራም መሆኑን በግልፅ ጠቋሚ ነው። ከዚህም በተጨማሪ " የአንድትን እህት ባል ልቦና በማስኮቦለል የእህቷን ትዳር ማናጋት ለአላህ እርግማን ያጋልጣል።
ማንም እንደሚያውቀው ይሄ አይነት በደል ከምንም በላይ  ከምቀኝነት የመነጨ ነው። ምቀኝነት ደግሞ ቦታው ጀሃነም ነው

ስለዚህ እህቶች ትዳርን በዚህ መልኩ ለመመስረት አትሞክሩ። ነፍ ለሆነ ባል በዚህ ፀያፍ ድርጊት አትሳተፊ🚫
#ሼር_ያድርጉ👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
!!!!!!!! ጥቆማ !!!!!!!!!!

#ዛሬ ከመሸ የዙል-ሒጃህ ጨረቃ  ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ሲሆን እሁድ ሰኔ 9 ደሞ የዒደ-ል-አዽሓህ በዓል ይሆናል።

☞ከዚህ ሰ
ዐት ጀምሮ የወርቃማዎቹ የዱንያ ንጉስ እና ቅዱስ ቀናቶች ነፋስ መንፈስ ጀምሯል።

☞በእውነቱ ለዚህ ዐይነታ ፀጋ መወፈቅ በራሱ ትልቅ የሆነ መመረጥ ነውና አላህን እናመስግን።

☞አደራ ትኩረታችን በአጠቃላይ አላህ
ወደሚወዳቸው ዒባዳዎች ላይ ይሁን።

💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን
#ሼር!👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
❗️ትዳር መተማመን እንጂ ሴምካርድ መለዋወጥ አያስፈልገውም።🚫

አሁን አሁን ግን ተጋቢዎች ከመተማመን ይልቅ ሴምካርድ  መለዋወጥ እንድሁም የኢሞና የዋስታፕ የተለያዩ አካውንቶችን ተለዋውጦ ሲጠቀሙ።

የሆነ ነገር  ሲመጣ ዘራፍ አካኪ ዘራፍ ማን አባቱ ነው? ማን አባቷ ነች ተበራክቷል።
ቆይ ቆይ ግን  ባሻዬ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እስኪ ሴት ሆና የማትጠየቅ አለች ብለህ ታምናለህ ?
እንደዛ ካመንክ አንተ የዋህ ብቻ ሳኮን ሞኝም ነህ። ጅልም ነህ።

ሴትልጅ አገባችም አላገባችም ጠያቂዋ እንደ ድሮው የክረምት  ዝናብ አቋርጦ አያውቅም። በቃ ወንዶች እንደ ቦይ ውሃ ባገኙበት እየፈሰሱ ጠራርገው ይዘው ለመሄድ መጠየቅ እና መላከፍ ይወዳሉ፣ አብሶ በዝህ ዘመን ሴቱ ኦላይን በሚያድርበት ወቅት።

እንግድህ ምን ታደርገው ከላይ ነው የተጠያቂነትን ሙሃባ የተቼራቼው። በርግጥ አሁን አሁን ይህ የተጠያቂነት ሙሃባ ወደኛም እየዞረ እንደሆነ ቢሰማኝም (ዘ እራስን እንደመቆለል) የእነሱ ግን ይበልጣል።
ታዳ ይህን እያወቅክ አካውንትና ሴምካርድ መቀያየር ጨጓራ ለመሸመት ማለቴ በጨጓራ በሽታ ለመያዝ አለያም ትዳርክን ለማፍረስ ፣ ምሶሶህን ለመቀል እራስህ ያመቻቼህ አይመስልህም ?
አይመስልህም ወይ ወንድሜ? አረ ተው ጥሩ አይደለም ። እንደዝህ ማድረግ ለትዳርህም ለአንተም አይበጅም።

#ትዳር_መተማመን_እና_ግልፀኝነት እንጂ የሚያስፈልገው ሴምካርድና አካውነት መቀያየር አይደለም።❗️
ወንድ ከሆንክ የሚስትህን የልብ ፓስዋርድ በፍቅር አሸንፈህ ተቀበል። ያንግዜ ማንም ጠየቀ ተቆላመጠ የሚስትህን ልብ ከፋቹ አንተ ብቻ እንጂ ሌላው ቴክስት ከማረግ ያለፈ ሚና አይኖረውም።

እህት ወዳንችም ልንጣ ወይስ በዝህ ይብቃ ?
ቆይ ቆይ ትንሽ ሳላርከፈክፍብሽማ አይበቃኝም

❗️አንች ግን ወንድና እንትን ያዩትን መልከፍ ይወዳሉ የሚለው እውነታዊ አባባል ላንች እንድገባሽ በትልቁ ተፅፎ እናተ ቤት መሰቀል አለበት ወይ ? እንደ ምን ነክቶሽ ነው ግን? ሴምካርድ፣ አካውንት ካልቀየርከኝ ሞቼ እገኛለህ የምትይ ?

ኤጭ ስታስጠሊ እንዳንች አይነት ከሆን ሚስት
#ትዳር ይንሳኝ ታስጠሊያለሽ ጭራሽ እኮ የኢሞን አካውንት የባንክ አካውንት አስመሰልሽው።

ቆይ ግን ምድነው ባልሽጋ ከታገልሽ አይበቃም ? የስልኩን  ትግል ምን አመጣው ? እንደ ለእናተ ስንል ሰዓዳን ሰይድ ብለን ሴቭ እናርግ እንደ ?
የእውነት ያስጠላል። ሰው በተለያዩ ጉዳዮች ከሴትጋ ሊያወራ ይችላል። ሁለተኛም የመደረብ አቅም እንዳለው አይረሳ። ዋነ።ናው አቅሙ ነው።

አንች ግን ሴት ልጅ ባልዋን ማርካ የማያዝ ስንት ተፈጥሮዊ ጥበብ እያላት ሴምካርድ ካልቀየርኩ ስትይ የእውነት ሰገጤነትሽን  ያሳያል እንጅ ብልጠትሽን  አያሳይም።
ይልቅ የፍቅር ብልጣብልጥ ሆነሽ ባልሽን እና ትዳርሽን አክብረሽ ያዥ እንጅ በኢንተርነቴ በመጣች ሴት ትዳርሽን ለመበተን የቤትሽን ሰላም አታናጊ።

ምክናየቱም
#ትዳር የሚፈልገው መተማመን እንጂ ሴምካርድ መለዋወጥ አይደለም እና❗️ #ሼር_ያድርጉ👇


            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
❗️ያስፈልገዎታል!❗️
              
#ጀናባን_የሚመለከቱ_ህግና_ደንቦች!

የቃላት መፍቻ፡-

1.  
#መኒይ (የዘር ፈሳሽ)፡-

- በስሜት ተስፈንጥሮ ከእርካታ ጋር የሚወጣ ፈሳሽ ነው፡፡
- ለወንድ ወፍራምና (ወደ ቢጫነት የሚያደላ) ነጭ ፈሳሽ ሲሆን ለሴት ደግሞ ቀጭንና ቢጫ ነው፡፡ [ሙስሊም፡ 311] ሽታው ወደሊጥ ሽታ የቀረበ ነው፡፡ በሆነ ምክንያት እነዚህ መታወቂያዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡
- ከወጣ በኋላ የሰውነት መቀዝቀዝ ዘና ማለት (ፉቱር) ይከተላል፡፡
- ፈሳሹ ሚዛን በሚደፋው የዑለማእ እይታ ጦሀራ እንጂ ነጃሳ አይደለም፡፡ ይህን የሚደግፉ ሶሒሕ ማስረጃዎች መጥተዋል፡፡ [ሙስሊም፡ 694] [አልኢርዋእ፡ 1/197]
- በውንም ይሁን በህልም ከወጣ ገላን መታጠብ ግዴታ ነው፡፡

2.  
#መዚይ፡-

- ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግ (የሚያጣብቅ)፣ ቀለም አልባ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡
- አወጣጡ ከእርካታ ጋር አይደለም፡፡ ተስፈንጥሮ ስለማይወጣ መውጣቱ ላይስተዋል ይችላል፡፡
- ነጃሳ ስለሆነ የነካውን አካል ማጠብ ይገባል፡፡ ልብስን ግን የነካው ቦታ ላይ ውሃ በመርጨት ማፅዳት በቂ ነው፡፡
- የነካውን ቦታ እንጂ ገላን መታጠብ ግን ግዴታ አይደለም፡፡ ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡

3.  
#ወዲይ፡-

- ከሽንት በኋላ የሚወጣ ነጭ ሽታ አልባ ፈሳሽ ነው፡፡
- የሚያጣብቅ አይደለም፡፡
- ብይኑ ከሽንት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

4.   📌ከሴቶች ብልት የሚወጣ ፈሳሽ፡-

- ከማህፀን የሚወጣ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡ መጠኑ ከሴት ሴት ይለያያል፡፡
- ሴቷ መውጣቱንም ላታስተውለው ትችላለች፡፡
- አካልንም ልብስንም ቢነካ አይነጅስም፣ ጦሃራ ነው፡፡
- ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡ ከሁለቱም መፀዳጃዎች በኩል የሚወጣ ነገር ውዱእ ያፈርሳልና፡፡ አወጣጡ ቋሚ ከሆነ ግን ለያንዳንዱ ሶላት ወቅቱ ከገባ በኋላ ውዱእ እያደረገች መስገድ ይገባል፡፡ ውዱእ ካደረገች በኋላ ቢወጣ ቦታም አይሰጠውም፡፡

#ገላን_መታጠብ_ግዴታ_የሚሆነው_መቼ_ነው?

1. በውኑ ግንኙነት ከተፈፀመ የዘር ፈሳሽ (መኒይ)
#ቢፈስም_ባይፈስም ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
2. ግንኙነት
#ባይፈፀምም የዘር ፈሳሽ (መኒይ) #ከእርካታ ጋር ከወጣ ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
3. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡
4. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ ነገር ግን ሲነቃ ምንም አይነት የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካላገኘ በማያሻማ መልኩ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ኡሙ ሱለይም የተባለችዋ ሶሐቢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዲት ሴት ኢሕቲላም ከሆነች (በህልሟ ግንኙነት ስትፈፅም ካየች) የመታጠብ ግዴታ አለባትን?” ብላ ስትጠይቅ “ፈሳሽ ካየች አዎ” ሲሉ መልሰውላታል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
5. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ የመታጠብ ግዴታ አለበት፡፡
6. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ ፈሳሽ አገኘ፡፡ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) እንዳልሆነ እርግጠኛ ከሆነ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ የነካውን ግን ሊያጥብ ይገባል፡፡ ብይኑ የሽንት ብይን ነውና፡፡
7. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን
#መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘ በ ሽታ ወይም በቻለው መንገድ ለመለየት ይሞክርና ጥርጣሬው መኒይ ወደመሆኑ ካደላ ይታጠብ፡፡ ጥርጣሬው መዚይ ወደመሆኑ ካደላ ግን በተለይም ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት አስቦ ከነበር እንደ መዚይ ይቁጠረውና የነካውን ቦታ ብቻ ይጠብ፡፡ ገላውን የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡
8. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን
#መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘና ግምቱ ወደየትኛውም ካላደላ፣ ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት #ያላሰበ ከሆነ ጉዳዩ አወዛጋቢ ቢሆንም ትክክለኛው ትጥበት የለበትም የሚል ነው፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡ [ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን፡ 11/161]

#የጀናባ_አስተጣጠብ_ሁለት_አይነት_ነው፡፡

1. የሚያብቃቃ ማለትም ግዴታውን ለማውረድ የሚጠበቅ ሲሆን እሱም ሙሉ አካልን በውሃ ማዳረስ ነው፡፡ ባይሆን መጉመጥመጥና በአፍንጫ ውሃ መሳብ (ኢስቲንሻቅ) እንዳይረሳ፡፡ ለትጥበት ኒያ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ አንድ ሰው ጀናባ ማውረድን ሳያስብ እንዲሁ ውሃ ውስጥ ዋኝቶ ቢወጣ መላ አካላቱ ውሃ መንካቱ ብቻ ጀናባው ለመውረዱ በቂ አይሆንም፡፡ ይስተዋል! ይህን ትጥበት ካደረጉ በኋላ ውዱእም ባያደርጉ መስገድ ይቻላል፡፡ ባይሆን ከትጥበቱ መሀል ውዱእ የሚያፈርስ ነገር መፈፀም የለበትም፡፡
2. ሌላኛውና በላጩ ግን በቅድሚያ ሁለት እጆችን መታጠብ፡፡ ከዚያም ኢስቲንጃእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ውዱእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ከእራስ ጀምሮ ቀሪ አካላትን ውሃ ማዳረስ፡፡ እግርን ከውዱእ ጋር ማጠብም ይቻላል፤ መጨረሻ ላይ ማጠብም ይቻላል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

❗️ማሳሰቢያ፡-

ሴቷ ለትጥበት ስትል የፀጉር ጉንጉኗን የመፍታት ግዴታ የለባትም፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም: ኡሙ ሰለማህ ለጀናባህ ወይም ለሐይድ ትጥበት ፀጉሯን “ልፍታው ወይ?” ብላ ስትጠይቃቸው “አይ! የሚበቃሽ ከእራስሽ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ማፍሰስ ብቻ ነው” ብለዋታል፡፡ [ሙስሊም] ስለዚህ ፀጉር ሳይፈታ ውሃ መድረስ ከቻለ መፍታት አይጠበቅም፡፡

ለማጣቀሻነት የተጠቀምኩት
1. ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን
2. ፈትሑልዐላም ፊ ዲራሰቲ አሓዲሢ ቡሉጊልመራም እና ሌሎችም

#ሼር_ማድረጉን_ አይርሱ👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞ሴት ልጅ ባሏን ሳታስፈቅድ
       ከቤቷ መዉጣቷ
              ሁክሙ☜

ጥያቄ፦ አንድ እህት ዘወትር ባሏን ሳታስፈቅድ ቤተሰቦቿ ዘንድ ወይም  የሴቶች ፕሮግራም ለመካፈል ትወጣለች። ባለቤቷ ሲቆጣት እኔ ግዴታን እየተወጣሁ ነበር ትለዋለች። ይህ ተግባሯ ወንጀል ይሆንባታልን?


መልስ፦ ሴት ልጅ በባሏ ፍቃድ ቢሆን እንጅ ያለ ፍቃድ ከቤቷ መዉጣት አይፈባትም።  ያለፍቃድ መዉጣቷ በሷ ላይ ሀራም ይሆንባታል። ሀዘንተኛን ለማፅናናት፣ የታመመን ለማየት ወይም ቤተሰቦቿን ለመጠየቅም ቢሆን የባለቤቷ ፍቃድ ሳይኖር መውጣት አይገባትም።

ባል በወንጀል እስካላዘዛት ድረስ ሚስት ለባሏ ታዛዥ መሆን አለባት። በመልካም ነገር ካዘዘ ባልን መስማት እና መታዘዝ ግዴታ ነው።  ባለቤቷ እስካልፈቀደላት ድረስ ወደ ዘመዶቿም ሆነ ዘመድ ወዳልሆኑ ሰዎች መሄድ ክልክል ነዉ።

ነገር ግን ባል ሀቋን መጠበቅ አለበት። ለሚስቱም ገር ሊሆን ይገባል። ከእሷ ጋር በመልካም ፀባይ ሊኗኗር ይገባል።

ለተለያዩ ጉዳዪች ለመዉጣት ስታስፈቅደዉ፤ የምትሄድበት ቦታ የሚወገዝ ነገር የሌለበት ከሆነ እና ለመጥፎ ነገር ከመተባበር ከፀዳ
ሊፈቅድላት ይገባል።  ይህ በመልካም መኗኗርና ክፍተቶችን ማጥበብም ነው። ባል በሚስቱ ላይ ግትርና ሻካራ ሊሆንባት አይገባም።
የሚስት ታዛዥነት በመልካም ነገር እስካዘዛት ድረስ ብቻ ነው።  በመጥፎ ተግባር እና በወንጀል ካዘዛት ግን መታዘዝ የለባትም። መታዘዝ በመልካም ነገር ላይ ብቻ ነዉ። ለምሳሌ፦ ወላጆቿን እንድትዘልፍ፣ አስካሪ መጠጥ እንድትጠጣ ወይም ሰላት እንዳትሰግድ ቢያዛት ልትታዘዘው አይገባትም። በሷ ላይ ሀራም ይሆናል። ነብዩ አለይሂ ሰላቱ ወሰላም እንዲህ ብለዋል፤
(إنما الطاعة في المعروف)
«መታዘዝ በመልካም ነገር ላይ ብቻ ነው»

በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል፦
(لا طاعة لمخلوق في معصية الخالق)
«የፈጣሪን ትእዛዝ በመተላለፍ ላይ ላይ ፍጡርን መታዘዝ አይቻልም!»

ለምሳሌ፤ ወደ ቤተሰብ ወይም ጎረቤት በመሄድ ጊዜ አለማሳለፍ፣ ወይም የተወሰኑ የምግብ አይነቶችን እንዳትሰራ ወይም ሌላ የተፈቀዱ ነገሮችን ካዘዛት መታዘዝ አለባት።

ወላሁ አእለም

ሸይኽ ኢብን ባዝ  ረሂመሁላህ
ምንጭ:– የሸይኹ ድረገፅ#ሼር_ያድርጉት_ይጠቅማል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞:::::::ውዷ እህቴ::::::☜

☞ማንም በደበረው ጊዜ ሰርች 🔍አድርጎ ዳውሎድ ⬇️አድርጎ  የፈለገውን ያክል ጊዜ ተጠቅሞ  የሚደልትሽ ጊዜአዊ በርናሜጅ  አትሁኝ እህቴ‼️

❗️ባሁን ጊዜ በሚድያ ፍቅርን እና ጋብቻ እየተባለ መንዘላዘል ሆኗል  ትዳር በሚድያ ይቅርና እንደድሮው በቤተሰብ ተጫጭቶ  እና ተጋብቶ  እንኳን  አልሳካ እያለነው   አላህ ካዘነላቸው ውጭ።

❗️በየሚድያው ግድግዳ ጀርባ ተሰግስገው ሴትንልጅ መጫወቻ  መቀለጃ  ጊዜ ማሳለፊያ አድርገው ከያዙ  አላማ የሌላቸው አላማ ቢስ  ወንዶች ተጠንቀቂ‼️ አንችን የእውነት የሚወድሽ ወንድ  በቀጥታ ፊትለፊት ይመጣል እንጅ  በበርናሜጅ ጀርባ ተደብቆ  በቅቤ ምላሱ ሲአነፍርሽ እና ሲአቀልጥሽ  አይውልም

ሌነም ነዉ ፁሁፉ
#ሼር_ያድርጉት❗️

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam