الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
ሰዉ ነኝና በስህተት አስቀይምያችሁ ይሆናል አዉ ሰዉ ነኝ ተሳሳች #ዛሬ_ግን_ከትንሽዬ_መልዕክት_ጋር_ይቅርታን_ልጠይቃችሁ

ሰዉ ነኝና በምሰራዉ ስራ ለይ ለናንተ ግዜ አጥቼ ላስቀይማችሁ እችላለዉ እና ይቅር በሉኝ❗️

❗️ንዴት እና ቁጭት !! ምንም ነገር አይፈታም
ምንም ነገር አያስተካክልም
ግን ሁሉን ነገር ያበላሻል።
( አስተውል)

☞ውድቀትህን የተመኙ ስኬትህን ያያሉ  ሁሌም ኋላህን ሣይሆን ወደ ፊት ተመልከት ።

☞ሁሌም በህይወትህ አጋጣሚ  ክፉውን በመልካም እንጂ በክፉ አትመልስ  ምክንያቱም ከበቀል ይልቅ  የህሌና ቅጣት እጂግ ይከፋልና!

☞ብዙ ጊዜ በጉጉት ከጠበቅነው ይልቅ በድንገት የምናገኛቸው ነገሮች የተሻሉ ናቸው እኛ ከምንጠብቀው ይልቅ ፈጣሪ የሚሰጠን የተሻለ ነውና!!

☞በአስቸጋሪ ፈተና መካከል ደስታህ ተቀምጦ ይሆናልና መቸም በአላህ ተስፋ አትቁረጥ!

☞ትክክለኛ ህይወት ማለት በትላንቱ እየተማሩ ዛሬን በአግባቡ  በመኖር ለነገ መዘጋጀት ነው።

☞የምትፈልገውን የምታገኘው ስለተወደድክ ስለወደድክ ስለቀደምክ ሣይሆን ስለተፈቀደልህ ነው።

☞ዝም ማለት ሁሌ  እሽ ማለት አይደለም።
አንዳንዴ ለማይገባው ሰው ማብራራት ሰልችቶኛል ማለት ነው።

=>አዕምሮህ ማግኔት ነው 
መልካም ነገር ያስባል
መልካም ነገር ይስባል
መጥፎ  ያስባል
መጥፎ ይስባል
ስለዚህ መልካም ነገሮችን ብቻ አለማምደው።

=>ምንጊዜም ችግር  በህይወትህ ላይ እንደማያቋርጥ ዝናብ ከተደራረበብህ ይህን አስብ አላህ ጥላ ይሆንሀል!

=>ትዝታ ካለ ትላንት ይኖራል
ተስፋ ካለ ነገን እንጠብቃለን
ፍቅር ካለ
ዛሬ #በአላህ_ፈቃድ ያምራል።

☞ፍቅር መጀመር በጣም እጂግ በጣም ቀላል ነው በፍቅር መቆየት ግን ዋጋ ያስከፍላል።

❗️ማውራት ከመጀመርህ በፊት ከጭንቅላትህ ጋር መገናኘትህን አረጋግጥ!

☞ወደ ስኬት ስትጓዝ  ወደ ኋላ አትመልከት   ካሰብከው ከደረስክ ግን የነበርክበትን አትርሣ!!

#መሣሣት_የሰወች_ባህሪ_ነው #ይቅርታን_መጠየቅ ግን ሥህተትን የሚያክም መድሀኒት ሲሆን ይቅር ባይነት ደግሞ የታላላቅ ሰወች መገለጫ  ነው።

☞መጥፎ ንግግር ከእንጨት ላይ እንደተመታ ሚስማር ነው  በይቅርታ ብትነቅለውም ጠባሣውን አይተውም!!

=>ሰውን ጭቃ ቀብተህ ለማቆሸሽ  ጭቃ ስትቆነጥር  ቅድሚያ የምታቆሽሸው የራሥህን እጂ ነው።

☞ባለው ነገር ደስተኛ ያልሆነ ሰው የፈለገውን አግኝቶም አይረካም እና ደስታን በትንሽ ነገር ተለማመደው።

እናም በአጭሩ ማለት የፈለኩት ነገር ቢኖር በምንሰራዉ ስራ ለይ ብዙ ፈተና ሊያገጥመን ይችላል።  ንዴታችን ባለመቆጣጠር ሰዎችን ልናስቀይም እንችላለን።

እና ለሁሉም ነገር
#አዉፉ_/ይቅር በሉኝ።

አላህ ረመዳንን ፆመዉ ከሚጠቀሙት ያድርገን አሚን ከእህታችሁ ☞
#ሀያት_ቢንት_ኸዲር

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
!!!!!!!! ጥቆማ !!!!!!!!!!

#ዛሬ ከመሸ የዙል-ሒጃህ ጨረቃ  ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ሲሆን እሁድ ሰኔ 9 ደሞ የዒደ-ል-አዽሓህ በዓል ይሆናል።

☞ከዚህ ሰ
ዐት ጀምሮ የወርቃማዎቹ የዱንያ ንጉስ እና ቅዱስ ቀናቶች ነፋስ መንፈስ ጀምሯል።

☞በእውነቱ ለዚህ ዐይነታ ፀጋ መወፈቅ በራሱ ትልቅ የሆነ መመረጥ ነውና አላህን እናመስግን።

☞አደራ ትኩረታችን በአጠቃላይ አላህ
ወደሚወዳቸው ዒባዳዎች ላይ ይሁን።

💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን
#ሼር!👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
ሱረቱል ካህፍ ላይ ...

#ዛሬ_ጁምዓ_ነው ሱረቱል ካህፍን ለመቅራት አላህ ለወፈቃችሁ አራት ቦታ ላይ ቆም በሉ፦
﴿ولا تطع من أغفلنا قلبه عن ذكرنا﴾
ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውን ፍላጎቱንም የተከተለውን ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ፡፡

☞ነጃሳን ልብ አላህ እሱን ከማውሳት እንዲዘናጋ ያደርገዋል ምክንያቱም የአላህ የተከበረ ነውና የተከበረ ነገር ደሞ ነጃሳ ላይ አይገኝም።

{وَإِذِ ٱعْتَزَلْتُمُوهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ إِلَّا ٱللَّهَ}
«እነርሱንና ያንን ከአላህ ሌላ የሚግገዙትን በተለያችሁ ጊዜ...»
☞አካልህን ከቆሻሻ እና ከሽርክ ቦታ ማራቅህ ለቀልብህ ሰላምን መረጋጋትንና ደስታን ያመጣልሃል። አቂዳህንም ያጠነክርልሃል

{فَأْوُۥٓا۟ إِلَى ٱلْكَهْفِ يَنشُرْ لَكُمْ رَبُّكُم مِّن رَّحْمَتِهِۦ وَيُهَيِّئْ لَكُم مِّنْ أَمْرِكُم مِّرْفَقًۭا}
ወደ ዋሻው ተጠጉ፡፡ ጌታችሁ ለእናንተ ከችሮታው ይዘረጋላችኋልና፤ ከነገራችሁም ለእናንተ መጠቃቀሚያን ያዘጋጅላችኋል» (ተባባሉ)፡፡

☞አላህን ፈልገህ ስሜትህ ወደ ማይፈልገው ቦታ ብትሄድ እንኳን አላህ ላንተ ሁል ነገርህን ያስተካክልልሃል።

{قَالَ لَهُۥ صَاحِبُهُۥ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَكَفَرْتَ بِٱلَّذِى خَلَقَكَ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍۢ ثُمَّ سَوَّىٰكَ رَجُلًۭا}
ጓደኛው (አማኙ) እርሱ ለእርሱ የሚመላለሰው ሲኾን «በዚያ ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከፈጠረህ፣ ከዚያም ሰው ባደረገህ (አምላክ) ካድክን» አለው፡፡

☞ሷሊህ ጓደኛ ሁሌም አላህን ያስታውስሃል አቅልህንም እንድታስተካክል ይረዳሃል ከጥፋትም እንትርቅ ሰበብ ይሆንሃል። አላህን የሚያስታዉስ ጓደኛ አላህ ይስጠን አሚን። 🤲

ሰሉ አላ መሀመድ(ﷺ)👇
#ሼር

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam