الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::☜   .#ክፍል_ስምንት/⑧ት       #ከአንድ በላይ ሚስት በኢስላም #እስከ_አራት_የተፈቀደ_ለመሆኑ_ማስረጃ                 #ቁርአናዊ_ማስረጃ    አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣ وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ…
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜

  ክፍል ዘጠኝ/⑨ኝ

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

    አላህ ለወንድ ልጅ ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ማግባት እንዲችል ሲፈቅድለት የሰው ልጅ ሊደርስበት የማይችል ሚስጥራዊ ሂክማ አለው።

    በኢስላም ውስጥ አብዛሀኞቹ  በቁጥር የተገደቡ ኢባዳዎች የቁጥራቸውን ሚስጥር ጥራትና ልቅና የተገባው ጌታችን አላህ ሱወ ብቻ ነው የሚያውቀው።የዙህር ሶላት ለምን አራት ሆነ፣የመግሪብ  ሶላት ለምን ሶስት ሆነ፣ሱብሂ ለምን ሁለት ሆነ፣ ለምን 5ወይ6 ወይም አንዳንድ አልሆነም? ሁሉም ሶላቶች ለምን ተመሳሳይ ቁጥር አልኖራቸውም?እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ።ነገር ግን የእነዚህን የተለያየ ቁጥር ያላቸውን የኢባዳ አይነቶች ሚስጥር የሚያውቃቸው አላህ ብቻ ነው።የሰውነት የአካል ክፍላችን ብዛት ብናስተነትን እና እያንዳንዱን የቁጥር መጠን ለምን ሆነ ብንል፣አይናችን ለምን 2 ሆነ፣ጆሮስ ለምን 2 ሆነ፣የእጅ ጣቶች ለምን 5 ሆኑ፣ለምን 4 ወይም 6 ዘልሆነም?? የሚለውን የብዛቱን ሚስጥር አዋቂው አላህ ብቻ ነው።

   ☞ ከአንድ በላይ ሚስት ያውም ደግሞ 4 የሚለው ቁጥር ለምን ተመረጠ ቢባል መልሱ ሁሉን አዋቂ የሆነው ጌታችን ብቻ የዚህ ሚስጥር ባለቤት ነቅ የሚል ምላሽ ይሆናል።

   ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የራሱ የሆነ ጥበብ መኖሩ እንዳለ ሆኖ ኡለሞች የሚዘረዝሯቸው አስደናቂ ጥበቦች አሉት እነዚህ ጥበቦች እንደሚከተለው አንድ ሁለት እያልን እንዘረዝራለን፣

1/
#የአላህ_መልእክተኛን_ሰአወ_ሱና_ለመከተል_ሲባል

   እንደሚታወቀው
የአላህ መልእክተኛ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩ ድረስ ከአንድ በላይ ሚስቶች ነበራቸው።የአላህ መልእክተኛ ከአንዳንድ እሳቸው ብቻ ከሚለዩባቸው ተግባራቸው በስተቀር የእሳቸውን ፈለግ እንድንከተል ታዘናል።ይህንን አስመልክቶ አላህ በቁርአኑ እንዲህ ብሎናል፣

لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 21)

    ☞
የአላህ መልእክተኛ የደነገጉትን መቀበል እና ሃቅ ነው ብሎ ማመን የሙስሊሞች ግዴታ ነው።ከአንድ በላይ ሚስት በሸሪዓ የተፈቀደ እና የተወደደ ነው የሚለውን መቀበል በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አያስፈልግም ብሎ የጠላ ወይም መሆን አልነበረበትም ብሎ የተቃወመ ከኢስላም እንደሚወጣ የኢስላም ሊቃውንት ይስማማሉ።

     ነብዩ
ሰአወ ለዱኒያም  ለአኼራም ለኡመታቸው የተሻለውን ነገር ሳያመላክቱ መጥፎን ነገር ሳያሰረጠነቅቁ አላለፉም። መጥፎውን እና ደጉን የማስተማር ሀላፊነት አላህ አስቀምጦላቸዋል።ነብዩ ሰአወ በንግግራቸው፣በተግባራቸው እና አይተው በማፅደቅ ያስተምራሉ።ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚወደድ እና የተሻለ እንደሆነ በተግባራቸው አስተምረውናል።ለሰዎች ሚስጥሩ በግልፅ ያልተገለፀው ከአንድ በላይ ሆኖ መግባትም እንደዚሁ ለሴቶች ትልቅ ጥቅም እንዳለው ያስገነዝባል።ለዚህም በርካታ ምክንያቶች መጥቀስ ይችላሉ።ከእነዚህም ውስጥ ነብዩ ለህዝባቸው ሲያስተምሩ የተሻለውን ወይም የበለጠ ጥቅም የሚያስገኘውን ነው ካልን ለሴቶች ኡመቶቻቸው የሚጎዳ ወይም የበለጠ ጥቅም የማያስገኝ በፍፁም ሊደነግጉ ወይም ሊያመላክቱ አይችሉም።ሌላው እናታችን አኢሻ ረአ ከሁሉም ሴቶች እንደምትበልጥ ነብዩ መስክረዋል።እሷ ከነብዩ ሚስቶች ከዘጠኝ አንዷ ናት ስለዚህ ከአንድ በላይ ሚስት ሆና መግባት ደረጃን የሚቀንስ ከሆነ ከሴቶች ሁሉ የምትበልጠው እናታችን አኢሻ ረአ ለምን በእሷ ላይ ሌላ ተገባባት።በሌላ አነጋገር ከአንድ በላይ ሚስት ሆኖ ሴቶችን ክብር ይቀንሳል ወይም ሴቶችን ከጓደኞቻቸው የበታችነት እንዲሰማቸው ያደርጋል ብሎ ማሰብ አኢሻን ረአ የበታች ነበረች ብሎ እንደማሰብ ይቆጠራል።ይህ አስተሳስብ ደግሞ ከኢስላም ጋር ይጋጫል።

    ☞ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ከአንድ በላይ ካላገባው ጋር ሲነፃፀር በደረጃ የተሻለ እንደሚሆን ነብዩ
ሰአወ በሃዲሳቸው እንዲህ ሲሉ  ተናግረዋል፣

     
#ሰኢድ_ኢብኑ_ጁበይር_ረአ ባስተላለፉት ሀዲስ"አብደላህ ኢብኑ አባስ አግብተሃል?ሲል ጠየቀኝ እኔም አላገባሁም አልኩት፣አግባ ከዚች ኡማ የተሻለው ብዙ ሚስቶች ያሉት ነው"" አለኝ ይላሉ። ሀዲሱን ቡኻሪ ዘግበውታል።

2
#ሳያገቡ_እድሜያቸው_የገፉና_የሚፈቱ_ሴቶች_መኖርና_መበራከት

  እነዚህ ሁለት አይነት ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።እድሜያቸውን ከገፉ በኃላ ለመጀመሪያ ሚስት የሚፈልጋቸው ወንድ አናሳ ነው።ወይም ደግሞ እንደሚታወቀው ወንዶች ለማግባት መሰረታዊ የሚባል የቤት ወጪን የሚሸፍኑበት ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። ይህን ገንዘብ በልጅነት እድሜያቸው ካላገኙ እስቲሳካላቸው የተወሰነ ጊዜ መጠበቃቸው አይቀሬ ነው።በዚህም የተነሳማግባት ከነበረባቸው እድሜያቸው ከገፉ በኃላ ይሆናል። የእነሱ አለማግባት በእኩያታቸው ያሉ ሴቶች ቶሎ ላያገቡ ይችላሉ።እነዚህ በእድሜያቸው ብዙ ከሄደ በኃላ ሚስት ሊያገቡ የሚያስቡ ወንዶች በእድሜ ከእነሱ ጋር እኩል የሆኑ ሴቶች ሳይሆን ለጋ የሆነችውን ሴት ይመርጣሉ። በዚህም ምክንያት እነዚህን ሴቶች ለመጀመሪያ ሚስትነት የሚፈልጋቸው ወንድ አናሳ ይሆናል ማለት ነው። ያለባል እንዳይቀሩ መፍትሄ ይሆን ዘንድ ከአንድ በላይ መፈቀዱ ኢስላማዊ ጥበብ ነው። በተመሳሳይ የተፈታችንም ሴት ለመጀመሪያ ሚስትነት የሚፈልጓት ወንዶች እጅግ አናሳ ናቸው።ለዚህም መፍትሄው ያለባል ከመቅረት ሁለተኛ ማግባት ነው
  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ
            3_4_&_5

👇በቀጣይ ርዕሳችን ይቀጥላል ሺንሻአላህ
#ሼር_ያድርጉ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam