الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር~በኢስላም::::::☜   #ክፍል_አምስት/⑤ት ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ሀይማኖቶች... #ከአንድ በላይ ሚስት በአይሁዳዎች እምነት       ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ሀይማኖቶች የተፈቀደ እና ወሰን ያልተቀመጠለት ድንጋጌ እንደነበር ከላይ አሳልፈናል። አይሁዶች ከአንድ በላይ ሚስትን የሚፈቅዱ ሲሆን#ቱልሙድ በሚባለው ሰው ሰራሽ መፅሀፋቸው የሚስትን ቁጥር አራት መሆን አለበት የሚል…
☞ትዳር_በኢስላ☜

 
#ክፍል_ስድስት/⑥

☞ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ህዝቦች ዘንድ
 
#በቀደምት_ቻይናውያን_ዘንድ
የቻይና ወንዶች በቀድሞ ዘመን የመጀመሪያ ሚስታቸውን ካገቡ በኃላ በርካታ ልጅ አገረዶችን በመግዛት እንደፈለጉ ይጠቀሙባቸው ነበር።
#በኃላየ ተገቡት ወይም የተገዙት ሴቶች ለመጀመሪያዋሚስት ታዛዥ የመሆን ግዴታ አለባቸው ከሌሎች ሚስቶቹ የሚወለዱት ልጆች ለመጀመሪያዋ ሚስት እንደልጅ ታስበው ያድጋሉ።
☞ የቻይና ሴቶች ለባሎቻቸው ባሪያ በመሆን ራሳቸውን እስከማቃጠል የደረሰ መስዋእትነት ይከፍሉ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። የቻይና ባሎች  የሚፈልጓቸውን ሴቶች በቁጥር ሳይገደቡ በህጋዊ ጋብቻ ያገባል። ባል ከመጀመሪያ ሚስቱም ሆነ ከሌላው ማህበረሰብ ለምን አገባህ የሚል ወቀሳ አልነበረም። እንዳውም ወንዶች ከአንድ በላይ እንዲያገቡ ይበረታቱ ነበር።ከዚህም በተጨማሪ
#ገንዘብ_ያለው_ቻይናዊ_ወንድ_በገንዘቡ_የሚፈልጋቸውን_ሴቶች_በመግዛት_እንደሚስት_እንደሚስት_አድርጎ_ይጠቀምባቸው_ነበር
☞ ይህ የጥንት ቻይናውያን ባህል እና ወግ ሆኖ አልፏል።አሁን ቻይናውያን ከሚፈፅሙት አስፀያፊ ተግባር ጋር ሲነፃፀር ያ ትውልድ የተሻለ ያሰየሚመደቡ የአሁኖቹ ቻይኖች እንደበፊቱ በህጋዊ መንገድ
#ከአንድ_በላይ ሴቶችን ባይዙም ሰለጠን ብለው አንድትን ሴት ለአራትና ለአምስት በአንድ ጊዜ ከሚገናኙት ብልሹ ህዝቦች የሚመደቡ ናቸው።አላፍር ብለው የእነሱን ተግባር እንደመልካም በመቁጠር ያለፉት ህዝቦች ተግባር ሲኮንኑ ይደመጣሉ።መኮነን ያለበትን እንኳ በቅጡ የማያውቁ እንስሶች፣
  
#በቀደምት_ህንዶች_ዘንድ
   በጥንታዊያን ህንዶች ዘእንዲሰጡ እንደቻይናዎቹ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተለመደ ተግባር ነው።ለሴቶች የሚሰጠው ግምት ከወንዶች በእጅጉ ያነሰ ነበር፣ሴቶች ሙሉ ማንነታቸውን  ለባሎቻቸው አሳልፈው እንዲሰጡ ይገደዳሉ። የህንድ ወንዶች ከአካባቢያቸው እና ጎሳዎቻቸው እራቅ ብለው በመሄድ የፈለጉት ያክል ሴት ያገቡ ነበር። ከሚስቶቹ መካከል የተሻለችውን በመምረጥ ሌሎቹን ሴቶች እንድትመራ እና እንድታስተዳድር ይደረጋል። በብዛት ይህን ስልጣን የሚሰጣት የመጀመሪያ ሚስት ናት። አንዳንድ የህንድ ወንዶች በሺ የሚቆጠሩ ሚስቶች ያገቡ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል።
#ሪባ_የሚባለው_የህንድ_ንጉስ_3000_ሚስቶች እንደነበሩት ይነገራል። በጣም የሚገርመው ከጥንታዊ ህንዶች ሴቶች መካከል አንድ ጊዜ ከተገቡ እንዳጋጣሚ ባላቸው ከሞተከዚህ በኃላ አለም በቃኝ ብለቅ እራሳቸውን በእሳት የሚያቃጥሉም ጎሳዎች ነበሩ.በቀደምት ፈረንሳዊያን_ዘእቃ
   ከሁለት ንግስት ሴቶች በስተቀር በአጠቃላይ ፈረንሳይ ለሴት ልጆች ቦታ የምትሰጥ አገር አልነበረችም እነርሱ ዘንድ ሴት ልጅን እንደተራ መገልገያ እቃ ይቆጥራሉ።አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ጥፋት የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል። በፈረንሳይዎች ዘንድ አንድ ወንድ የፈለገውን ያህል ሴት ማግባት ይችላል። ብዙ ሴት ማግባት የወንድነት መገለጫ መሆኑን ማህበረሰቡ የሚያምንበት ተግባር ነው። ከዚህ በጣም የከፋ ው ለመስማት የሚዘገንነው አንድ ስሩት እናቱን ፣ ሴት ልጁን፣ እህቱን እንዲሁም 2 እህትማማቾችን ማግባት የሚችልበት ማህበረሰብ ነበር። ለነገሩ አሁንስ ቢኖን በሙስሊሞች ላይ ጣታቸውን የሚቀስሩት ምእራባዊያን ተግባራቸው ከዚህ የተለየ ነው እንዴ? ሴት ልጆቻቸውን የሚደፍሩ ምእራባዊያን ቁጥራቸው ቀላል ነው ?በቀደምት ግብፆች ዘንድ
   በጥንታዊ ግብፆች ዘንድ ነጠላ ሚስትን አብዛኛው ማህበረሰብ የሚያገባ ቢሆንም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትም እንግዳ አልነበረም። በተለይ የግብፅ ንጉሶች እና የንጉስ ቤተሰቦች በስፋት ይተገብሩት ነበር። ይህ ማለት ግን ተራው ማህበረሰብ ማግባት አይፈቀድለትም ማለት አይደለም።
አንድ ወንድ ሁለት ሴቶችን የሚያገባ ከሆነ ሁለቱን ሴቶች በየግላቸው ራሱን በቻለ ቤት በማኖር ባል በየተራ ሚስቶቹን እየዞረ ይጠይቃል ነገር ግን
#መጀመሪያ መጀመሪያ የተገባችው_ሴት የተለየ ክብር እና ቦታ ትይዛለች
   
#በጥታዊ ግሪኮች_ዘንድ
   ጥንታዊ ግሪኮች ከሴት ልጅ ይልቅ ለወንድ ልጅ ልዩ ክብር ስለነበራቸው
#ሚስት የሚያገቡበት ዋናው_አላማ ወንድባልጅ ለማግኘት እንደሆነ ይነገራል።ሚስቱ መውለድ የማትችል ከሆነ የመፍታት ሙሉ መብቱ የወንድ ነው። ሴቶች ባል ካገቡ በኃላ ከቤት መውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር። በእርግጥ ለሴት ልጅ ክብሯ ከቤት አለመውጣቷ ነው።በግሪኮች ዘንድ አንድበእጅጉ የተለመደ ቢሆንም ወንዶቹ እንደሚስታቸው የሚቆጥሯት አንድ ተጨማሪ ሴት በየቦታው ትኖራለች።ከዚህ በተጨማሪ የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ስለነበር በአገሩ ህግ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚፈቀድና የሚበረታታ አዋጅ ወጥቶ ነበር፣ለምሳሌ ሶቅራጥስ በህጋዊ መንገድ ያገባቸው ሁለት ሚስቶች ነበሩት።.

  
#በጥንታዊ_ሮማዊያን_ዘንድ
   እንደሌሎች ሀገሮች ሁሉ ጥንታዊ ሮሞች ከአንድ በላይ ሚስት የሚፈቅድ ህግ ነበራቸው። ይህንንም ቤተክርስቲያን ትቀበለው እና ታፀድቀው ነበር። ጊዜው እየረዘመ ሲመጣ ከ1750  ዓ. ል በኃላ ከአንድ በላይ ሚስት ቤተክርስቲያኗ አትደግፍም በማለት የሌላ ህግ በማውጣት መከልከላቸው ይታወቃል።ይህ ክልከላ የፈጣሪ ትእዛዝ የሌለበት ሰው ሰራሽ ፈጠራ ከመሆን ውጭ እንደቁም ነገር ሃይማኖታዊ ሽፋን ተሰጥቶት በማስረጃነት ሊቀርብም ሆነ ሌሎችንም ለመተቸት ከግምት የሚገባ አይደለም.ከአንድ_በላይ_ሚስት_በጥንታዊ_አረቦችጥንታ   አረቦች ያለገደብ የሚበቃቸውን ያህል ሚስት ያገቡ እንደነበር የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።ብዙ ሴቶች ማግባት የሀይለኝነት ፣ የታዋቂነት፣የጀግንነትና የባለፀጋነት መገለጫ አድርገው ይቆጥሩታል።አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ባገባ ቁጥር ደረጃውም በዛው ልክ እየጨመረ ይሄዳል ተብሎ ይታሰብ ነበር 
#አንዳንዶቹ_ስድስትአ_ንዳንዶቹ_አስር_ሌሎቹ_ደግሞ_እስከመቶ የሚደርሱ ሚስቶች ነበሯቸው።እንደምሳሌ ብንመለከት ፣ የነብዩ ሰአወ አጎት አብዱልሙጠሊብ፣ሱፍያን ቢንሀርብ እና ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ነበራቸው ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባህ ሰባት ሚስቶች ነበሯቸው
    ☞ ነብዩ  ﷺ እስልምናን ይዘው ሲመጡ አብዛኛዎቹ የአረብ ንዳቸው ከአስር ያላነሱ ሚስቶች ነበሯቸው።ለምሳሌ ሱዑድ ኢብኑ መዕቀብ ፣ዑርወት ኢብኑ መስኡድ፣ሱፍያን ኢብኑ አብዲላህ እና መስኡድ ኢብኑ አምር እያንዳንዳቸው አስር አስር ሚስቶች ነበሯቸው።

ቀይስ ኢብኑ ሳቢት ሲያወሩ እንዲህ ይላሉ፣ስምንት ሚስቶች በስሬ እያሉ እስልምናን ተቀበልኩ፣ከዛም ወደአላህ መልእክተኛ ዘንድ መጥቼ ይህን ነገርኳቸው እሳቸውም "ከእነሱ ውስጥ አራት ምረጥና ሌሎቹን ፍታ" አሉኝ ይላል.
   ☞ አብደላህ ኢብኑ ኡመር ሲያወሩ በጃሂልያ ይላሉ በጃሂልያ ዘመን ያገባኋቸው አስር ሚስቶች በስሬ እያሉ እኔም ሚስቶቼም እስልምናን ተቀበልን።ከእነርሱ 4 ብቻ እንድመርጥ ነብዩ ﷺ አዘዙኝ"ይላል።

   ☞ ነውፈል ኢብኑ ሙአዊያህ እንዲህ ይላሉ፣ "5 ሚስቶች በስሬ እያሉ እስልምናን ተቀበልኩ፣ከዛም ወደአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓሌይሂ ወሰለም ዘንድ መጥቼ ጠየኳቸው፣ እርሳቸውም "አንዷን ፍታ ሌሎቹን ያዝ" አሉኝ ይላል።
    በዚያን ጊዜ(በጃሂልያህ ዘመን) በአንድ ወንድ ስር የሚኖሩ ሴቶች መብዛታቸው ብቻ ሳይሆን ከወንዶች በኩል የሚደርስባቸው በደል እጅግ የሚዘገንን ነበር  ወንዶች ያለገደብ
ያገቧቸውን ሴቶች አይደለም በፍትህ ሊያስተዳድሯቸው የሚያስፈልጋቸውን እንኳን መሰረታዊ ነገሮች አያገኙም ነበር የሰው ልጅ መሆናቸው ግምትየሚሰጠው አልነበረም።
ይቀጥላል #ሼር_ያድርጉ