ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ፍኖተ_ቅዱሳን
በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
#መግቢያ
#ፍኖት ማለት መንገድ ማለት ነው ። በቅዱስ መፅሐፍ የሰው ሕይወት በመንገድ ተመስሏል ። ጌታችን "በመንገድ ላይ ሳለህ በጠላትህ እወቅበት " ማለቱ በዚህ ዓለም ሕይወትህ በጠላት ዲያቢሎስ ላይ ጠቢብ ሁንበት ማለቱ ነው ። (ማቴ 5÷25) የሰው ሕይወት በመንገድ የተመሰለው በመንገድ አንዱ ወደ ላይ ሲወጣበት አንዱ ወደ ታች ሲወርድበት ሁሉም ወዳሰበው ሲደርስበት እንደሚኖር ሁሉ በዚህ ዓለም አንዱ ጽድቅ ሰርቶ ከክብር ወደ ክብር ሲሸጋገርበት ሌላው ደግሞ በሚያልፍ ዘመኑ ፍዳው የማያልፍ ኃጢአት ሲሰራ ኖሮ በወደደው ኃጢአት እንደ ጠፍ ጨረቃ ከክብር እያነሰ ስለሚሄድበት ነው ። የሰው ልጅ የፈጣሪውን ሕግ በማፍረሱ ምክንያት ወደዚህ ዓለም ተጥሎ ወደ አምላኩ የሚያደርሰውን እውነተኛ መንገድ አጥቶ 5500 ዘመን ሲባዝን ኖረ ። ይህ ዓመተ ፍዳ ሲያልቅ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ አንድ አካል አንድ ባህርይ ሆኖ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኘውን እውነተኛ መንገድ አስተማረ ። እርሱም "የፅድቅና የህይወት መንገድ እኔ ነኝ " በማለት ከፈጣሪው አንድነት ተለይቶ ከክብር ተራቁቶ የነበረውን የሰው ልጅ ወደራሱ አንድነት ሊያዋህደው እንደ መጣ ተናገረ ። እርሱን በፍፁም ህይወታቸው ለሚመስሉት ወደ ሕይወትና ክብር የምትወስደውን ጠባብ መንገድ በቃል ያስተማረና በተግባር ሰርቶ ስሩ ያለ ፣ ቅዱሳንን የጠራ ፣ የተቀበለና ያከበረ እውነተኛው ፍኖተ ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ምንም እንኳ ይህች ዓለም ፍጡራንን ይቅርና ፈጣሪዋን ኢየሱስ ክርስቶስን እንኳ ሳይቀር በመከራ የተቀበለች ብትሆንም ባለንበት ዘመን በድፍረትና በትዕቢት በእግዚአብሔር ቅዱሳን ላይ የሚነገረውን ነገር ስንመለከተው ግን መጠኑን ያለፈ ሆኖ ይታያል ። እንኳንስ በቅዱሳን ላይ ይቅርና በማንኛውም ሰው ላይ እንኳ ሊነገር የማይገባውን ነገር የሚናገሩ ሰዎች ከአንደበታቸው የሚወጣውን የድፍረት ቃል አውቀውት ይሆን ? ይህ ነገር የሚያስከትለውን ውጤትስ ተረድተውት ይሆን ? ምናልባት የቅዱሳንን ማንነትና እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ያለውን ተቆርቋሪነት ባያውቁ ይሆን ? የሚል ጥያቄ ይፈጥራል። ስለዚህም የማያውቁትን ለማሳወቅ ፡ ለሚያውቁት ደሞ ለማስታወስ ነገረ ቅዱሳንን መማማር አስፈለገን ።

....ይቀጥላል፡፡
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ፍኖተ_ቅዱሳን
በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
#ክፍል_1
#ቅድስና_ምንድነው ?
#ቅዱስ የሚለው ቃል "ቀደሰ" ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አመሰገነ ፣ ለየ፣ መረጠ፣አከበረ ማለት ነው ። ቅዱስ የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ሲነገር #ቅዱሳን ይሆናል። ቅድስና #የባሕሪና #የፀጋ ተብሎ በ2 ይከፈላል።
#የባሕርይ_ቅድስና
ቅድስና የባሕርይ ገንዘብነቱ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ። ይህም ማለት ቅድስናው ከእርሱ የማይለይ ፣ ቅድስናው ከእርሱ ከራሱ የሆነ ፣ ቅድስናውን ከሌላ ከማንም ያልተቀበለው ፣ ማንም ሊወስድበትም የማይችል ፣ በቅድስናው መጨመርና መቀነስ የሌለበት ዘለዓለማዊ ፍፁም ቅዱስ ማለት ነው ።
#የፀጋ_ቅድስና
የጸጋ ቅድስና ማለት ከእግዚአብሔር በፀጋ(በስጦታ) የተሰጠ ወይም የተገኘ ማለት ነው ። ከላይ እንደተገለፀው በባሕርዩ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ የፍጡራን ቅድስና መገኛውና ምንጩ እርሱ ብቻ ነው ። "እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ " በማለት ሰው ሁሉ የቅድስናው ተሳታፊ ይሆን ዘንድ በአባታዊ ቸርነቱ ለሰው ልጆች ሁሉ ጥሪውን አቅርቧል (ዘሌ.19÷2) #ቅዱስ የሚለው ቃል ለእግዚአብሔርም ከሰው ወገን ቅዱሳን ለሆኑ ሰዎችም የሚነገር ከሆነ እንዴት ተለይቶ ይታወቃል ? ለእግዚአብሔር የሚቀፀለው #ቅዱስ የሚለው ቃል ለሰው መነገሩስ ምን ያህል አግባብ ነው ? የሚል ጥያቄ ይነሳ ይሆናል ። ቅዱስ የሚለው ቃል ሲነገር የቅድስናው ደረጃና መጠን የሚታወቀው ቃሉ በሚቀፀልለት ባለቤት ማንነት ነው ። #ቅዱስ የሚለው ቃል ለእግዚአብሔር ሲነገር ተናጋሪውም ሆነ ሰሚው ዕፁብና ድንቅ ረቂቅና ምጡቅ የሆነውን ፣ የሰው አዕምሮ ከማድነቅ በስተቀር ሊደርስበት የማይቻለውን የእግዚአብሔርን ቅድስና ያስባሉ ያስረዳሉ ። ለምሳሌ ጌታችን "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ " ብሏል ። (ዮሐ 8÷12) እንዲሁ ደሞ ደቀመዛሙርቱን "እናንተ የዓለም ብርሀን ናችሁ " ብሏቸዋል ። (ማቴ 5÷14) #ብርሀን የሚለው ቃል ለክርስቶስም ለሐዋርያትም የተነገረ አንድ ቃል ሲሆን በክርስቶስና በሐዋርያት መካከል ያለው ልዩነት ግን የፍጡርና የፈጣሪ ነው ።ይህን በተመለከተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል ፦ "ለእግዚአብሔር እና ለሰዎች ተመሳሳይ አገላለፆችን እንጠቀማለን ፤ ሆኖም ግን ለእግዚአብሔር ስንናገር የሚኖረን አረዳድና ለሰዎች ስንናገር ሊኖረን የሚገባው አረዳድ የተለያየ ነው ። ምንም እንኳ ቃሉና አገላለፁ አንድ ዓይነት ቢሆን ስለ እኛ የሚነገረውን ስለ እግዚአብሔር ከሚነገረው ጋር አንድ ዓይነት አድርገን ልንረዳው አይገባም ፤ ስለ እግዚአብሔር ሲነገር ለእርሱ እንደሚገባ አድርገን መረዳት ይገባናል ፤ አለበለዚያ ታላቅ ስህተት ላይ እንወድቃለን ። "ብሏል #ቅዱስ የሚለው ቃል ከፍጡራን ወገን ለሚከተሉት ሊቀፀል ይችላል። #ቅዱሳን_መላእክት #ቅዱሳን_መካናት #ቅዱሳን_ዕለታት #ቅዱሳን_ንዋያት (ንዋያተ ቅድሳት ) #ቅዱሳን_ሰዎች ። በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር የሆነ የተለየ ነገር ሁሉ ቅዱስ ነው ።

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#ክፍል_2
(በቀሲስ ደጀኔ ሽፍራው)
#10ሩ_ማዕረጋተ_ቅድስና
መንፈሳዊ ህይወት የቅድስና ኑሮ እንደ መሆኑ መጠን በጥምቀት ጀምሮ ደረጃውን የጠበቀ እድገት ያለበት ሕይወት ነው ።ከዚህም በሃላ እግዚአብሔርን በፍፁም ልቡናቸው ሰውነታቸውና ሕዋሳቶቻቸው እያመሰገኑ አሰረ ፍኖቱን የሚከተሉ ሰዎች ከቅድስና ወደ ከበረ ቅድስና ከሚኖሩበት መንፈሳዊ ኃይል ወደ ሌላ ታላቅ መንፈሳዊ ኃይል ይሸጋገራሉ ። እነዚህ የቅዱሳን የመንፈሳዊ ጉዞአቸው የእድገት ደረጃዎች 3 ናቸው ። እነዚህም #ወጣኒነት (ንፅሀ ስጋ) ፣ #ማዕከላዊነት (ንፅሀ ነፍስ) እና #ፍፁምነት (ንፅሀ ልቡና ) በመባል ይታወቃሉ ። በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ስር ደግሞ የተለያዩ ማዕረጋት አሉ ።በንፅሀ ስጋ 3 በንፅሀ ነፍስ 4 በንፅሀ ልቦና 3 ሲሆኑ በጠቅላላው #10ሩ ማዕረጋተ ቅዱሳን በመባል ይታወቃሉ ።
#ንፅሀ_ሥጋ /ወጣኒነት/
ይህ ደረጃ ወጣንያን በባሕርዩ ፍፁም ከኾነው እግዚአብሔር ፍፁም ፀጋን ተቀብለው ለመክበር ቁርጥ ተጋድሎ የሚጀምሩበት ሕይወት ነው ። በዚህም ጊዜ ጠላት የተባለ ሰይጣን የተጋድሎ ሕይወታቸውን የሚያቀጭጭ ፈተና ያመጣባቸዋል ። እነርሱ ግን በፍፁም ተጋድሎ በእግዚአብሔር ፀጋ ከአንዱ ማዕረግ ወደ ሌላው ይሸጋገራሉ ።
#1ኛ #ጽማዌ ፦ ዝምታ ማለት ነው ። ይኸውም አውቆና ፈቅዶ በመናገርና በመቀባጠር ከሚመጣው ኃጢአት መቆጠብ ነው ።ይህን የመጀመሪያውን ደረጃ በዝምታ ማለፍም ታላቁን የሰይጣን ፆር /እሳትን / በተጋድሎ ማጥፋት ነው ።አንደበት እሳት ነውና።
#2ኛ #ልባዌ ፦ ልባዊ ማለት ልብ ማድረግ ፣ ማስተዋል ማለት ነው ። ጌታ በወንጌል "መስማትንስ ትሰማላቹ ነገር ግን አታስተዉሉም " ይላቸው የነበረው ማስተዋል ታላቅ ማዕረግ ስለሆነ ነው ።
#3ኛ #ጣዕመ_ዝማሬ ፦ይህ ደግሞ ሳይሰለቹና ሳይቸኩሉ ምስጢርና ትርጓሜውን እያወጡ እያወረዱ በንቁ ሕሊና ማመስገንና መጸለይ ማለት ነው ። አንድ ሰው የሚፀልየውን ፀሎትና የሚያቀርበውን ምስጋና በትርጓሜና በምስጢር በውሳጣዊ ልቡናው እያዳመጠ የሚያደርሰው ከሆነ ተመስጦን ገንዘብ ማድረግ ይቻለዋል ። ጸጋ መንፈስ ቅዱስንም እየተጎናፀፈ ከዚህ ከስጋዊ አለም ማምለጥ ይቻለዋል።
... ይቀጥላል ...

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#ክፍል_3
#10ሩ_ማዕረጋተ_ቅድስና
ከባለፈው የቀጠለ ንፅሀ ስጋን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች ቀጥለው የሚሸጋገሩት ወደ ንፅሀ ነፍስ ነው ። ትሩፋተ ስጋን አብዝቶ የሰራ ሰው የሚሸጋገረው ትሩፋተ ነፍስን ወደ መስራት ነውና ። በዚህም መሰረት አንድ ሰው ከንፅሀ ስጋ በሃላ አብዝቶ ትሩፋተ ነፍስ ከሰራ የሚከተሉትን መዓርጋት ገንዘብ ማድረግ ይችላል
#4ኛ #አንብዕ ፦ እንባ ማለት ነው ። የሀዘን እንባ ሰው በደረሰበት ሀዘን ልቡ ተወግቶ ፊቱን አስከፍቶ የሚያለቅሰው ሲሆን የደስታው እንባ ደግሞ ልቡናው በሐሴት ተሞልቶ ሰውነቱ ስሜቱን መቆጣጠር ባቃተው ጊዜ የሚያለቅሰው ነው ። "አንብዕ " ግን ከዚህ ፈፅሞ የተለየ ነው ። ይኸውም ቅዱሳን ሰውነታቸው በሐዘን ሳይከፋ በስጋዊ ሐሴትም ሳይሞላ ሳይሰቀቁ ከዓይናቸው የሚያፈልቁት እንባ ነው ።
#5ኛ #ኩነኔቅዱሳን ከራሳቸው ሰውነት ጋር የሚያደርጉት ( የፈቃደ ስጋና የፈቃደ ነፍስ መጋጨት ) ዋናው ነው ። በዚህ ተጋድሎ ፈቃደ ስጋቸውን ሙሉ ለሙሉ ለፈቃደ ነፍሳቸው ለማስገዛት የበቁ ሰዎች "ለመዓርገ ኩነኔ " በቁ ይባላል ። ኩነኔ ማለት በአጭር ቃል ስጋን ለነፍስ ማስገዛት ማለት ነው ። ስጋ ለነፍስ ተገዛ ማለት ደሞ እንስሳዊ ባህሪያቸው ፍፁም ደክሞ መልአካዊ ባህሪያቸው ሰልጥኖ ይታያሉ ። ለስጋዊ ደማዊ ሰው የሚከብደውን ሁሉ መስራት ይችላሉ ። ለምሳሌ በቅጠላ ቅጠል ብቻ ለብዙ ጊዜ መኖርን ፣ ከእንቅልፍ መጥፋት የተነሳ በትጋሃ ሌሊት ማደርን ፣ በየቀኑ እጅግ ብዙ ስግደት መስገድን ፣ ከስግደትና ከፀሎት ውጪ በሚሆኑበት ሰዓትም ከቅዱሳት መፃህፍት አለመለየት
#6ኛ #ፍቅር ፦ ፍቅር ታላቅ ፀጋ ነው ። እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚባለው የባህሪ ገንዘቡ ስለሆነ ነው ። ሰዎች በተጋድሎ እየበረቱ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሁሉ ሳይንቁ አስተካክሎ መውደድ ነው ። ለዚህ ደረጃ የበቃ ሰው ሌላውን ሰው ኃጥዕ ጻድቅ ፣ አማኒ ከሃዲ ፣ ነጭ ጥቁር ፣ ደቂቅ ልሂቅ ፣ አዋቂ አላዋቂ ሳይል አስተካክሎ መውደድ ነው ።
#7ኛ #ሑሰት ፦ ይህ ደግሞ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልሳዕ በኢየሩሳሌም ሆኖ የሶርያው ንጉስ ወልደ አዴር እልፍኙን ዘግቶ ከባለስልጣናቱ ጋር የመከረውን ማንም ሰው ሳይነግረውና ሳይሰማ በሚያውቅበት ፀጋ ካለበት ቦታ ሆኖ ጠፈር ገፈር ሳይከለክለው እንደ ፀሀይ ብርሃን ካሰቡት ደርሶ የፈለጉትን ነገር ማወቅ ማለት ነው ። ይህም በኢየሩሳሌም ሆኖ በቢታንያ የአልዓዛርን ሞት አይቶ የነገራቸውን ጌታን የሚመስሉበት ፀጋ ነው ።
... ይቀጥላል ...

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#የመጨረሻው_ክፍል
... ከባለፈው የቀጠለ ...
ከላይ ሁለቱን ደረጃዎች ተመልክተናል ። ወጣኒነትና ማዕከላዊነትን። አሁን ደግሞ የመጨረሻውን ደረጃ ፍፁምነትን እንመልከት ። ይህ የመጨረሻ ደረጃ እንደ መሆኑ መጠን በ2ቱ ደረጃዎች ሰባቱን መዓርጋት ገንዘብ አድርገው ወደዚህ ለመሸጋገር የሚጋደሉትን ሰይጣን በገሃድ ተገልጦ መዋጋት የሚጀምርበት ጊዜ ነው ።ዘንዶና እባብ ፣ አንበሳና ነብር እየሆነ በመምጣት ለማስፈራራት ቢሞክር ያልደነገጡለትን ሽፍታ እየመሰለ መደብደብ ሁሉ ይጀምራል ። መዝ 90 እና መሰል ፀሎትን በመፀለይ ድል ይነሱታል ።መደ ሚቀጥሉት ማዕረጋትም ይሻገራሉ ።
#8ኛ #ንፃሬ_መላዕክት ፦ እዚ ደረጃ ሲደርሱ እነሱን የሚረዷቸውን መላዕክት በየነገዳቸውና በየአለቆቻቸው በሚኖሩባቸው ዓለማተ መላዕክት (በኢዮር ፣ በኤረር ፣ በራማ ) እንዳሉ በዓይነ ስጋ በዐፀደ ስጋ ለመመልከት መብቃት ፣ ምስጋናቸውንም መስማትና ከዚህ ዓለም ፈፅሞ ተለይቶ ከሰማያውያን ጋር መኖርን መጀመር ነው ።
#9ኛ #ተሰጥሞ_ብርሃን ፦ ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር የባሕሪ ገንዘብ በሆነው በሚያስደንቀው ብርሃን ውስጥ መዋኘት ነው ። ይህ ብርሃን ፍፁም ልዩ ነው ።ይህም እነርሱ በዛ ብርሃን ውስጥ እያሉ ሌላ ለዚህ ማዕረግ ያልበቃ ሊያየው የማይችል ብርሃን ነው ።ጨለማ የማይሰለጥንበት ፣ እንደዚህ ዓለም ብርሃን የማያቃጥል ፣ በጨረሩ አይንን የማይበዘብዝ ፣ ነፍስን ከስጋ መለየት የሚያስችል ደስታ እስኪሰማ ድረስ ልዩ መዓዛ ያለው ነው ። እነዚህን ፀጋዎች የሚያውቁት የኖሩባቸው ቅዱሳን ናቸው ። እኛ ደሞ ከመፃህፍት ብቻ እንረዳቸዋለን ።
#10ኛ #ከዊነ_እሳት (ነፅሮተ ስሉስ ቅዱስ) ፦ ይህ የመጨረሻው ማዕረግ ነው ። ወደዚ ደረጃ የደረሱ ቅዱሳን ሰውነታቸው ለአጋንንት የሚያቃጥልና የማያስቀርብ ይሆናል ።እነዚህን አጠቃለው የያዙ የልብ ንፅህናን ገንዘብ አድርገዋልና ለነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ ይበቃሉ ።ለዚህ መብቃትም ታላቅ ብቃትና ማዕረግ ነው ። በባሕሪው የማይታየውን እግዚአብሔርን ለባሕሪያቸው በሚስማማ መልኩ እስከ ማየት በቅተዋልና።
❖ ተፈፀመ ❖

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret