ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_2
#ፕሮቴስታንት /ጴንጤ /
ፕሮቴስታንት ተቃዋሚ ከሚለው የእንግሊዘኛ ቃል የተወሰደ ነው ። ይህም ሊሆን የቻለው የካቶሊክ ፓፓ የነበረው አቡነ ሊዎ አስረኛ የቅ/ጴጥሮስን ትልቅ ቤተክርስቲያን ለማሰራት በማሰቡ መንግስተ ሰማያት መግቢያ ብሎ ካርድ መሸጥ ጀመረ ። ማርቲን ሉተር ግን መንግስተ ሰማያት በክርስቶስ እንጂ በካርድ አይገባም ብሎ ተነሳ ።ይባስ ብሎም 90 ነጥቦችን ነቅሶ አውጥቶ ለጠፈላቸው ። ተቃዋሚ ሲሉትም ፕሮቴስት አሉት እሱን የተከተሉትን ደግሞ ፕሮቴስታንት አሏቸው ። አሁን ደሞ እስቲ ልዩነታችንን እንያቸው #1ኛ.ፕሮቴስታንት የንስሀ አባት አያስፈልግም ይላሉ ። ኦርቶዶክስ ግን ከ7ቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን አንዱ በመሆኑ ከታላቅ አክብሮት ጋር ትገለገልበታለች ። ጌታችን በወንጌል "ኃጢያቱን የተዋቹለት ቀረችለት ፡ "የያዛችሁበትም ተያዘችበት " በማለት አስተምሯልና ። (ዮሀ 20:23 ማቴ 16:19)። ደሞ በፕሮቴስታንት ሴቶች ስልጣነ ክህነት ሊኖራቸው ይችላል ። በኦርቶዶክስ ግን አይቻልም ። ጌታ የመረጣቸውና ስልጣነ ክህነትን የሰጣቸው ለወንዶች እንጂ ለሴቶች አይደለም ። #2ኛ. ፕሮቴስታንቶች የእምነት መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ይላሉ ። ይህም ማለት በቤተክርስቲያን ሊቃውንት መፃህፍትና ሲወርድ በመጣው ቤተክርስቲያናዊ ትውፊትና አዋልድ መፃህፍት ላይ እምነት የላቸውም #3ኛ.ፕሮቴስታንቶች የቅዱሳን አማላጅነት አያስፈልግም ይላሉ ። ኦርቶዶክስ ግን ቅዱሳንን በተሰጣቸው ቃልኪዳን መሰረት ያማልዳሉ ብላ ታምናለች ። #4ኛ.ፕሮቴስታንቶች ጥምቀት እግዚአብሔርን ለማምለክ ምልክት እንጂ ድኀነት አያስገኝም ይላሉ ። በኦርቶዶክስ ግን በክርስቲያናዊ ህይወት የመጀመሪያ መግቢያ በር በመሆኑ ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባትና ሚስጥራትን ለመካፈል አስፈላጊ መሆኑን ታምናለች #5ኛ.ፕሮቴስታንቶች ቁርባን መታሰቢያ እንጂ የክርስቶስ ሥጋና ደም አይደለም ይላሉ ።ኦርቶዶክስ ግን መለኮት የተዋሀደው ነብስ የተለየው ቁርባን አማናዊ የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው ትላለች #6ኛ.ፕሮቴስታንቶች ለመዳን ማመን ብቻ በቂ ነው ስራ አያስፈልግም ይላሉ ።ኦርቶዶክስ ግን እምነትና ምግባርን ነጣጥላ አትመለከትም ። ስራ የሌለው እምነት ነብስ የተለየው ስጋ ነው የሞተ ነው ትላለች ። #7ኛ.ፕሮቴስታንቶች መፅሀፍ ቅዱስን ሁሉም በሚገባው መልኩ መተርጎም ይችላል ይላሉ ። ኦርቶዶክስ ግን ማንም እንደፈለገውና እንደመሰለው እንዲተረጉም አትፈቅድም ።ወስብሀት ለእግዚአብሔር ። የአባቶቻችን የተባረከች በረከታቸው ፡ ርትዕት ሀይማኖታቸው ፡ ጥርጥር የሌላት ድል የማትነሳ እምነታቸው ከኛ ትሁን ለዘለአለሙ አሜን ።

ምንጭ= ኰኲሕ ሐይማኖት
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_3
#የይሖዋ_ምስክሮች /ጆቫ ዊትነስ/ *
የይሖዋ ምስክሮች የተባለው የሃይማኖት ተቋም በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በቻርልስ ራስል የተመሰረተ ሲሆን ራስል ቀደም ባሉት ጊዜያት ክርስቲያን የነበረ ሲሆን በኀለኛው የወጣትነት ዘመኑ በአርዮሳውያን የኑፉቄ ትምህርትና በሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት እንዲሁም በአንዳንድ የክህደት ትምህርት (Atheists) አራማጆች ተፅዕኖ ስር ወደቀ ። እ.ኤ.አ በ1872 አካባቢ ከነዚህ የተበረዙና የተዛቡ አስተምህሮዎች በመነሳት ራስል የራሱን አስተምህሮ (Doctrine) በመቅረፅ በአሜሪካ ውስጥ ለማሳተም ቻለ ።እስቲ ጥቂት እምነታቸውን እንመልከት #1ኛ .ጆቫዎች ቤተክርስቲያንና የአለም መንግስታት ሁሉ የሰይጣን ስራ ውጤቶች ናቸው ብለው ያምናሉ #2ኛ.ዜጎች በወታደራዊ ተቋማት እንዳይገቡ ያደርጋሉ ። ለሰንደቅ አላማ የክብር ሰላምታ መስጠትን እንደ ባዕድ አምልኮ አድርገው ይቆጥሩታል #3ኛ. የሰው ነብስ ትሞታለች ብለው ያምናሉ #4ኛ.የሰው ልጅ ከትንሳኤ ቡሃላ ገነት በምትሆነው ምድር ለዘላለም ይኖራል /ምድር ገነት ትሆናለች/ ብለው ያምናሉ #5ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ክርስቶስን ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ሳይሆን መለኮታዊ ባህሪ ያለው ንዑስ አምላክ ነው ብለው ያምናሉ #6ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ሰብአ ሰገል በቤተልሔም በጌታችን ፊት ያደረጉት ስግደት የማይገባና የመራቸውም ኮከብ ከሰይጣን የተላከ እንደሆነ ያምናሉ ። #7ኛ.ጆቫዎች ክርስቶስ አስቀድሞ በሰማይ ከተፈጠረ በኀላ በዚያው ኗሯል ፡ ወደ ምድር እንዲመጣ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማም ስለ ይሖዋ መንግስት ለመመስከር ነው ይላሉ ። #8ኛ.የይሖዋ ምስክሮች የዳግም ልደቱ መጀመሪያ በሚሆነው ጥምቀቱ ለእግዚአብሔር ልጅነት የተሾመ ነው በዚህም የአብ መንፈሳዊ ልጅ በመሆን የይሖዋ መንግስት ገዢ /ንጉስ/ ሆኗል ብለው ያምናሉ ። #9ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ መላዕክት ሚካኤል ነው ብለውም ያምናሉ ። #10ኛ.የይሖዋ ምስክሮች የሰው ልጅ በስጋ ሲሞት ነፍሱም አብራ ትሞታለች። ዘላለማዊነት የይሖዋ ብቻ የተለየ ባህሪ ነው ብለው ያምናሉ ። #11ኛ. የይሖዋ ምስክሮች ኃጢያተኞች ከፃድቃን ተለይተው እንደሚጠፉ እንጂ በሲኦል የሚሰቃዩ መሆናቸውን አይቀበሉም ። ሌላው ቀርቶ ሰይጣን ይጠፉል እንጂ አይሰቃይም አባታችን አዳምም አንዴ ስለሞተ ትንሳኤ አያገኝም ይላሉ ። #12ኛ .መንፈስ ቅዱስ የሥላሴ አንዱ አካል ሳይሆን የይሖዋ ሀይል ነው ብለው ያምናሉ ። #13ኛ. በብዙ ትንሳኤ ያምናሉ ።ማለትም የታናሽ መንጋ ትንሳኤ ፣ምድራዊ ትንሳኤ ፣ የይሖዋ ምስክሮች አባል ላልሆኑትና ፃድቅ ለሆኑት የሚደረግ ትንሳኤ ብለው ትንሳኤን ከፉፍለው ያምናሉ። ወስብሀት ለእግዚአብሔር ።የአብ ፀጋ ፡ የወልድ ቸርነት የመንፈስቅዱስ ህብረት አንድነት ከኛ ጋር ይሁን ለዘለአለሙ አሜን
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#በመንፈሳዊ ሕይወትህ ለውጥ እንዲኖሮት ከፈለጉ


1ኛ የፀሎትን ህይወት ተለማመድ ተጠቀምበትም፣
#2ኛ ከመንፈሳዊ አባቶችና ሊቃውንት መ/ራን ምክርና ትምህርት አትራቅ
#3ኛ ከቅዱሳት መፃህፍት ጋር ያለህን ግንኙነት አዘውትር፣
#4ኛ የምትውልባቸውን ቦታዎች ፥የምታነባቸውን
መፃህፍት፥የምትመርጣቸውን ባልጀሮችህን ምረጥ፤ለመንፈሳዊ ህይወትህና ለሌሎች ወንድሞችህና እህቶችህ የሚያሰናክሉ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ፣

#5ኛ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ መሆንህን ዘወትር አትዘንጋ፣
#6ኛ አግባብ ያልሆነ ሃፍረትንና ፍርሃትን አስወግድ፥በራስህ ማስተዋልም
አትደገፍ፣
#7ኛ አላዋቂነትህን ተቀበል 'እኔ ብቻ' አትበል ውዳሴ ከንቱንም
አትፈልግ፣
#8ኛ ለሰራሃው ሃጢአት ሳትዘገይ ንስሃ ግባ፣
#9ኛ ልበ ደንዳናነትንና አመፀኛነትን ከአንተ አርቃቸው፣
#10ኛ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖርና የቃሉ ሙላት
በውስጥህ ኖሮ ከክርስቶስ ጋር መኖርን ተለማመድ በቃሉም
ፀንተህ ተገኝ፣
#11ኛ የቅዱሳንን ተጋድሎና ፍቅር በመመልከት እነርሱን
ለመምሰል ትጋ፣

#12ኛ ከዚህ በፊት የነበርክበትን የሃጢአት ህይወት ኮንነው
#13ኛ ሰዎችን/ባልንጀራህን አፍቅር ከጥላቻም ራቅ፣
#14ኛ ነገርን ሁሉ ለበጎነው ብለህ ተቀበል። ጌታ ሆይ ይህን
እንድናደርግ እርዳን አሜን
ይቆየን::
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_4
#የፍቅር_አይነቶች (Types of Love )
#4ኛ_ፍሬንድ_ሺፕ_ላቭ (Casual Friendship/ non - Lovel )፦ ይሄኛው ፍቅር ብዙም አያስቸግርም ። የሁለቱም ግንኙነት ጤነኛ /Normal/ ግንኙነት ነው ። ሊዋደዱ ይችላሉ ። የሕይወታቸውንም ምስጢር ይለዋወጣሉ ፣ ፍቅራቸው ከሩካቤ ሥጋ ነፃ ነው ። የሰከነ ማንነት አላቸው ። መጨናነቅ የሚባል ነገር የላቸውም ፤ እንዲሁም ጤነኛ ኑሮ ይኖራሉ ።እነሱን የሚያስደስታቸው ዝም ብሎ ጥምረታቸው ብቻ ነው ።
#5ኛ_ፉሊሽ_ላቭ(Foolish Love) ፦ "የጅል ፍቅር " አንዳንዶች በሞኝነት ራሳቸውን የሚያታልሉበት የፍቅር ዓይነት ነው ። ለምሳሌ ምንነቷን ሳያውቅ ፎቶዋን በማየት ብቻ ከመሬት ተነስቶ ፍቅር የሚይዘው ሰው አለ ። ያችን ልጅ ለማፍቀር ቢያንስ በባህርይ ፡ መጣጣም እንዳለበት እንኳን አይገምትም ። ፎቶዋን አይቶ ብቻ ወደዳት ! በቃ ! ቆረጠ ። እንዲህ አይነቱ ፍቅር የጅል ፍቅር ይባላል ። አንድ ሰው በፎቶ ያየውን ሰው በአካል ደግሞ ቢያየው እንደጠበቀው ሆኖ ላያገኘው እንደሚችል መገመት አለበት ። በፎቶ የተዋበ ሰው ውስጣዊ ባህርይውም እንደፎቶው ውበት ላይኖረው ይችላልና ። ገንዘብንም አይተው የሚያፈቅሩ ሰዎች ተርታቸው ከዚህ ዓይነቱ ፍቅር ውስጥ ነው ። ገንዘቡን አይተው የተጠጉት ሰው ገንዘቡ ያለቀ ቀንስ ?
#6ኛ_ፓሰሲቭ_ላቭ (Possessive Love) ፦ ዝነኛን ሰው የራስ ለማድረግና "እገሌኮ የእኔ ነው " የሚለው ስሜት የሚፈጠርበት የፍቅር አይነት ነው። ይሄኛው ፍቅር የሚይዛቸው ብዙ ጊዜ ሴቶች ናቸው ።የእኔ ነው የሚሉትን ሰው በዝናና ለራስ ክብር መጠቀሚያነት ብዙውን ጊዜ ይፈልጉታል ። የእኔ ነው ለማለት ያህል እንጂ ፍቅርን ተቀራርበውና በጥልቀት አጣጥመውት አይደለም የሚጀምሩት ። ለዛሬ ይብቃን ቀጣይ ደሞ ከ7 - 9 ያሉትን እናያለን ።

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#ክፍል_3
#10ሩ_ማዕረጋተ_ቅድስና
ከባለፈው የቀጠለ ንፅሀ ስጋን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች ቀጥለው የሚሸጋገሩት ወደ ንፅሀ ነፍስ ነው ። ትሩፋተ ስጋን አብዝቶ የሰራ ሰው የሚሸጋገረው ትሩፋተ ነፍስን ወደ መስራት ነውና ። በዚህም መሰረት አንድ ሰው ከንፅሀ ስጋ በሃላ አብዝቶ ትሩፋተ ነፍስ ከሰራ የሚከተሉትን መዓርጋት ገንዘብ ማድረግ ይችላል
#4ኛ #አንብዕ ፦ እንባ ማለት ነው ። የሀዘን እንባ ሰው በደረሰበት ሀዘን ልቡ ተወግቶ ፊቱን አስከፍቶ የሚያለቅሰው ሲሆን የደስታው እንባ ደግሞ ልቡናው በሐሴት ተሞልቶ ሰውነቱ ስሜቱን መቆጣጠር ባቃተው ጊዜ የሚያለቅሰው ነው ። "አንብዕ " ግን ከዚህ ፈፅሞ የተለየ ነው ። ይኸውም ቅዱሳን ሰውነታቸው በሐዘን ሳይከፋ በስጋዊ ሐሴትም ሳይሞላ ሳይሰቀቁ ከዓይናቸው የሚያፈልቁት እንባ ነው ።
#5ኛ #ኩነኔ ፦ ቅዱሳን ከራሳቸው ሰውነት ጋር የሚያደርጉት ( የፈቃደ ስጋና የፈቃደ ነፍስ መጋጨት ) ዋናው ነው ። በዚህ ተጋድሎ ፈቃደ ስጋቸውን ሙሉ ለሙሉ ለፈቃደ ነፍሳቸው ለማስገዛት የበቁ ሰዎች "ለመዓርገ ኩነኔ " በቁ ይባላል ። ኩነኔ ማለት በአጭር ቃል ስጋን ለነፍስ ማስገዛት ማለት ነው ። ስጋ ለነፍስ ተገዛ ማለት ደሞ እንስሳዊ ባህሪያቸው ፍፁም ደክሞ መልአካዊ ባህሪያቸው ሰልጥኖ ይታያሉ ። ለስጋዊ ደማዊ ሰው የሚከብደውን ሁሉ መስራት ይችላሉ ። ለምሳሌ በቅጠላ ቅጠል ብቻ ለብዙ ጊዜ መኖርን ፣ ከእንቅልፍ መጥፋት የተነሳ በትጋሃ ሌሊት ማደርን ፣ በየቀኑ እጅግ ብዙ ስግደት መስገድን ፣ ከስግደትና ከፀሎት ውጪ በሚሆኑበት ሰዓትም ከቅዱሳት መፃህፍት አለመለየት
#6ኛ #ፍቅር ፦ ፍቅር ታላቅ ፀጋ ነው ። እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚባለው የባህሪ ገንዘቡ ስለሆነ ነው ። ሰዎች በተጋድሎ እየበረቱ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሁሉ ሳይንቁ አስተካክሎ መውደድ ነው ። ለዚህ ደረጃ የበቃ ሰው ሌላውን ሰው ኃጥዕ ጻድቅ ፣ አማኒ ከሃዲ ፣ ነጭ ጥቁር ፣ ደቂቅ ልሂቅ ፣ አዋቂ አላዋቂ ሳይል አስተካክሎ መውደድ ነው ።
#7ኛ #ሑሰት ፦ ይህ ደግሞ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልሳዕ በኢየሩሳሌም ሆኖ የሶርያው ንጉስ ወልደ አዴር እልፍኙን ዘግቶ ከባለስልጣናቱ ጋር የመከረውን ማንም ሰው ሳይነግረውና ሳይሰማ በሚያውቅበት ፀጋ ካለበት ቦታ ሆኖ ጠፈር ገፈር ሳይከለክለው እንደ ፀሀይ ብርሃን ካሰቡት ደርሶ የፈለጉትን ነገር ማወቅ ማለት ነው ። ይህም በኢየሩሳሌም ሆኖ በቢታንያ የአልዓዛርን ሞት አይቶ የነገራቸውን ጌታን የሚመስሉበት ፀጋ ነው ።
... ይቀጥላል ...

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
5ቱ የዝሙት ብልቶች
--------------------------------
#1ኛ ዝሙተኛ ጆሮ ፡- የሰው ገመና ያዳምጣል ፣ ዘፈን ያዳምጣል …
#2ኛ ዝሙተኛ ዓይን ፡- የታቃራኒ ጾታን ኣካል ይመለከታል ፣ ጸያፍ ትዕይንቶችን ይመለከታል …
#3ኛ ዝሙተኛ እግር ፡- ወደ መጠጥ ቤት ይገሰግሳል ፣ ወደ ሲኒማ ቤት ይገሰግሳል ፣ ወደ ጭፈራ ቤት ይገሰግሳል ፣ ወደ ጠንቋይ ቤት ይገሰግሳል ….
#4ኛ ዝሙተኛ እጅ ፡- የተቃራኒ ጾታን አካል ይዳብሳል ፣ ጉቦን ትቀበላለች ፣ የሰውን ነፍስ ታጠፋለች …
#5ኛ ዝሙተኛ ምላስ ፡- ዘፈንን ታወጣለች ፣ ስድብን ታወጣለች ፣ የተወገዙ እጾችን ታጣጥማለች ፣ ኣመጻን ታነሳሳለች ፣ የሰውን ስም ታጠፋለች …….
የእነዚህ የዝሙት ብልቶች ስብስብ በስጋና በመንፈስ የተበላሸ ኣካልን ይፈጥራሉ ፡፡ ዘመናችን ወደየት እየሄደ እንደሆነ በምንሰማውና በምናየው ነገር ማረጋገጥ ይቻላል ፡፡ ትልቁም ፣ ትንሹም ፣ ጤነኛውም ፣ በሽተኛውም ወሬው ዝሙትና ዝሙት ነው ፡፡ የወሬ ማሳመሪያው ዝሙት ነው ፡፡ የነገር መጀመሪያው ዝሙት ነው ፡፡ መዝናኛው የዝሙት ወሬ ነው ፡፡ ሁሉም ነገር ዝሙትን እና ሴሰኝነትን ይሸታል ፡፡
አሁን ላይ እያየነው ላለነው መቅሰፍት አንዱና ዋነኛው ምክንያቱም ይሄው ነው።
የወጣቱ ኣለባበስ የተቃራኒ ጾታን ቀልብና ልብ ካልማረከ የለበሰ ኣይመስለውም ፡፡ አንዳንዱ ወንድ ጅንስ ሱሪውን በማጥበብ የውስጥ ልብሱን በማሳየት እና በማሳጠር ባቱን ወጥሮ እና ቁርጭምጭምቱን ገልጦ በመሄድ እህቱን አልያም ግብረ ሰዶማዊ ወንድሙን መስሏል ፡፡ አንዳንዶቹ ሴቶች ደግሞ ከላይ እስከ ታች ድረስ ሰውነታቸውን ወጣጥረው ሊፈነዳ ያለ ልብስና በመልበስ አጭር ቀሚስ በመልበሰ የኣካላቶቻቸውን ብልቶች በማሳየት የለበሱ- ራቁተኛ ሆነዋል ፡፡
ይህ እንደ ሰሃራ በረሃ የተራቆተ አለባበስ የትውልዱን ግብረ ገብነት ላጭቶ ወደ እንስሳነትና ኣውሬነት እያሸጋገረ ነው ፡፡ ምግብ ሲሰነብት እንደሚበላሸው ሁሉ ትውልድም ዘመናትን ሲቆይ እየተበላሸ መጥቶ ከመጥፋት ላይ ደርሷል - 8ኛው ሺህ ፡፡ በኣለባበስ ስርዓትና እና በግብረ ገብነት የተራበ ትውልድ መጨረሻው የምድጃ እንጨት ነው ፡፡
ዓይንን ፣ ጆሮን ፣ ምላስን ፣ እግርን ፣ እጅን በመንፈሳዊው ምርመራ ማስመርመርን እናስቀድም !
ከቤት ተነስተን ወደቤተክርስትያንም ሆነ ወደ ማንኛውም ቦታ ስንሄድ ኣሳፋሪ እና አሸማቃቂ አለባበሳችንን እንፈትሽ !

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret