ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_3
#የፍቅር_አይነቶች(Types of Love)
ብዙ ጊዜ ሰዎች ፍቅር ያዘኝ አፈቀርኩ ሲሉ ይሰማሉ ። እንደ ባለሙያዎች አገላለፅ ከሆነ 12 አይነት ፍቅር አለ ። እነሱን አንድ በአንድ እናያለን ከዛም የተያዘ ሰው የትኛው ፍቅር እንደያዘው እራሱን ያይበታል ። #1ኛ_ሮማንቲክ_ላቭ (Romantic Love ) ፦ ይሄኛው የፍቅር ዓይነት የሚይዛቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰውነትን ቅርፅ ብቻ አይተው የሚያፈቅሩ ሰዎች ናቸው ። ሌሎቹን መሰረታዊ ነገሮች ግምት ውስጥ አያስገቡም ። ለምሳሌ ጥሩ ጸባይ እና ባህሪን፣ የአመለካከት ጥራትን ፣ ሃይማኖትን ፣ ስነምግባርን የመሳሰሉትን ነገሮች አያዩም ።የሚያዩት ተክለ ሰውነትን ብቻ ነው ። ነገር ግን ፍቅር እንደያዛቸው ይናገራሉ ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜ ቀናተኛ ናቸው ። ያፈቀሩትን ሰው ከእነሱ ውጭ ከሌላ ሰው ጋር ምንም ዓይነት ጤነኛ (Normal) ግንኙነት እንዲኖረው እንኳን አይፈልጉም ። ይህ ፍቅር ትኩረቱ ብዙ ጊዜ #በሩካቤ ሥጋ መውደቅ እንጂ #ትዳር አይደለም ። ስለዚህ እንደዚህ አይነቱ ፍቅር አይዘልቅም ።
#2ኛ_ፖሽኔት_ላቭ(Possinate Love) ፦ ይህ ፍቅር ስሜታዊ ፍቅር ነው ። ፖሽኔት ላቭ በጣም አስቸጋሪና ከባዱ የፍቅር ዓይነት ነው ። ሕይወትን የመመሰቃቀልና በጣም የማጨናነቅ ባህርይ አለው። ህሊናን እረፍት ከመንሳቱ ጎን ለጎን የወጣቶችን የወደፊትን የሕይወት ምዕራፍ የማጨለም ጉልበት አለው ። ለምሳሌ በስሜታዊ ፍቅር የተያዘ ሰው ትምህርት መማር ሁላ ሊያስጠላው ይችላል ። ከሰው ጋር ተደባልቆ ጊዜውን ከማሳለፍ ይልቅ ያፈቀረውን ሰው እያብሰለሰለ ለብቻው መሆን ይፈልጋል ፤ ምግብ እንኳን ይዘጋዋል አይምሮው ከፍቅር ውጪ ምንም ነገር ማሰብ አይፈልግም ። በመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ በዚህ አይነቱ ስሜታዊ ፍቅር ተይዞ የተሰቃየ ሰው አምኖንን እናውቃለን ። /2ኛ ሳሙ 13/ በዚህ ፍቅር የተያዙ ሰዎች ለጊዜው እውነተኛ ፍቅር እንደያዛቸው ሊያስቡ ይችላሉ ። ማስተዋልን ሳይቀር የሚጋረድበት የፍቅር ዓይነት ነውና። የሚገርመው ደሞ ኀላ ላይ ያስጨነቀውን ያህል ከልብ ውስጥ መጥፋቱ አይቀርም ። እንዲህ አይነቱም ፍቅር ቆይታው ሩካቤ ስጋ እስኪፈፀም ድረስ ብቻ ነው ። ፍቅሩም ከዛች ቅፅበት ጀምሮ ይቆማል ። ይህን በዳዊት ልጅ በአምኖን ላይ ማየቱ ብቻ በቂ ነው ።
#3ኛ_ሎጂካል_ላቭ(Logical Love)፦ በዚህ አይነት ፍቅር የተያዙ ደግሞ የፍቅር መነሻቸው #መመሳሰል ነው ። ብዙ ጊዜ በሎጂክ ሕግ ነው የሚመሩት ። ሲያፈቅሩ በህይወታቸው ውስጥ ከዛ ሰው ጋር የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር ስላዩ ነው ። ለምሳሌ እሷ ዲግሪ ካላት የምትመርጠው ዲግሪ ያለውን ነው ። እሷ ስራ አስኪያጅ ከሆነች የምትመርጠው ማናጀር ነው ። እነዚ ከነሱ ጋር የሚያመሳስላቸውን አቻቸውን ማፍቀር የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው ። እንዲህ ሲባል ደግሞ በስራ ጠባይና በት/ት ማዕረግ የተመሳሰሉ ተጋቢዎች ሁሉ እዚህ ፍቅር ውስጥ ናቸው ማለት ግን አንችልም ። ይህ ፍቅር እንደሌሎቹ ሁሉ ዘላቂ አይደለም ። ምክንያቱም ያፈቀረችው ሰው ከእለታት 1 ቀን ያንን ስራ ሊለቅና ሊቀይር ይችላልና ። በዚህ ጊዜ እርሷ የፈለገችው የተመሳሰሉበት መስመር ተቀየረ ማለት ነው ። በተጨማሪም ያቺ ሴት ሥራውን እንጂ ሌሎች ነገሮቹን ስለማታውቅለትና በሕይወቱም ሳትማረክለት የጀመረችው ብዙ ነገር ስላለ ፍቅሩም ላይዘልቅ ይችላል፡፡
🌼🌼🌼ይቆየን

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_4
#የፍቅር_አይነቶች (Types of Love )
#4ኛ_ፍሬንድ_ሺፕ_ላቭ (Casual Friendship/ non - Lovel )፦ ይሄኛው ፍቅር ብዙም አያስቸግርም ። የሁለቱም ግንኙነት ጤነኛ /Normal/ ግንኙነት ነው ። ሊዋደዱ ይችላሉ ። የሕይወታቸውንም ምስጢር ይለዋወጣሉ ፣ ፍቅራቸው ከሩካቤ ሥጋ ነፃ ነው ። የሰከነ ማንነት አላቸው ። መጨናነቅ የሚባል ነገር የላቸውም ፤ እንዲሁም ጤነኛ ኑሮ ይኖራሉ ።እነሱን የሚያስደስታቸው ዝም ብሎ ጥምረታቸው ብቻ ነው ።
#5ኛ_ፉሊሽ_ላቭ(Foolish Love) ፦ "የጅል ፍቅር " አንዳንዶች በሞኝነት ራሳቸውን የሚያታልሉበት የፍቅር ዓይነት ነው ። ለምሳሌ ምንነቷን ሳያውቅ ፎቶዋን በማየት ብቻ ከመሬት ተነስቶ ፍቅር የሚይዘው ሰው አለ ። ያችን ልጅ ለማፍቀር ቢያንስ በባህርይ ፡ መጣጣም እንዳለበት እንኳን አይገምትም ። ፎቶዋን አይቶ ብቻ ወደዳት ! በቃ ! ቆረጠ ። እንዲህ አይነቱ ፍቅር የጅል ፍቅር ይባላል ። አንድ ሰው በፎቶ ያየውን ሰው በአካል ደግሞ ቢያየው እንደጠበቀው ሆኖ ላያገኘው እንደሚችል መገመት አለበት ። በፎቶ የተዋበ ሰው ውስጣዊ ባህርይውም እንደፎቶው ውበት ላይኖረው ይችላልና ። ገንዘብንም አይተው የሚያፈቅሩ ሰዎች ተርታቸው ከዚህ ዓይነቱ ፍቅር ውስጥ ነው ። ገንዘቡን አይተው የተጠጉት ሰው ገንዘቡ ያለቀ ቀንስ ?
#6ኛ_ፓሰሲቭ_ላቭ (Possessive Love) ፦ ዝነኛን ሰው የራስ ለማድረግና "እገሌኮ የእኔ ነው " የሚለው ስሜት የሚፈጠርበት የፍቅር አይነት ነው። ይሄኛው ፍቅር የሚይዛቸው ብዙ ጊዜ ሴቶች ናቸው ።የእኔ ነው የሚሉትን ሰው በዝናና ለራስ ክብር መጠቀሚያነት ብዙውን ጊዜ ይፈልጉታል ። የእኔ ነው ለማለት ያህል እንጂ ፍቅርን ተቀራርበውና በጥልቀት አጣጥመውት አይደለም የሚጀምሩት ። ለዛሬ ይብቃን ቀጣይ ደሞ ከ7 - 9 ያሉትን እናያለን ።

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_5
#የፍቅር_አይነቶች (types of love)
እንደሚታወቀው ባለፉት ክፍሎቻችን 12 አይነት የፍቅር አይነቶች አሉ ብለን ከ12ቱ አይነት 6ቱን ማየታችን ይታወቃል ። እነሆ ቀጣይ ከፍልን ዛሬ እናያለን ።
#7ኛ_አንሰልፊሽ_ላቭ (unselfish love) ፦ ይህ ፍቅር የሚጀምረው ራስ ወዳድ ካለመሆን የሚመነጭ የፍቅር ዓይነት ነው ። ለምሳሌ በዚህ ፍቅር ውስጥ የሚገባ ሰው ለቀረበለት የፍቅር ጥያቄ የእሺታ መልስ ሊሰጥ ይችላል። የሚሰጠው ግን "እሷ ከምትጎዳ እኔ ልጎዳ " በሚል ዓይነት ስሜት ነው ። ነገር ግን ያንን ፍቅር ውስጡ ላያምንበት ይችላል ። የሰውን ጉዳት ስለማይፈልግ ብቻ ግን ፈቃደኛ ይሆናል ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜ በባህርያቸው ገራም ፣ ለስለስ ያሉ ፣ ቅንና ቁምነገረኝነት ያለባቸው ፣ ለጀመሩት የፍቅር ሕይወት ይህ ይገጥመኛል ብለው ሳይፈሩ ራሳቸውን መስዋዕት የማድረግ ባህርይ እንዳለባቸው ይታመናል ።
#8ኛ_ጌም_ፕሌይንግ_ላቭ (Game Playing Love) ፦ ይሄኛው የፍቅር ዓይነት ደግሞ ነውሩ በጣም ደምቆ የሚታይ የፍቅር ዓይነት ነው ። ይህ አፍቃሪ ራሱን ማርካት ብቻ የሚፈልግ አፍቃሪ ነው ።ለሰው ሕይወት ግድ አይሰጠውም ። ለጊዜው ጠንካራ አፍቃሪ መስለው ሊታዩ ይችላሉ ። #አፈቀርኩ ካሉት ሰው ጋር ሁልጊዜ መጫወት ነው የሚፈልጉት ። ለትዳር መሰረት የሚሆነው ነገር አይታያቸውም ። ዓላማቸው አንድ ነገር ብቻ ነው ። እሱም የሩካቤ ሥጋ ጥማቸውን ማርካት ብቻ ! ከዚያ በሗላ ደግሞ ሌላ ሰው ይቀይራሉ ። አሁንም ደግሞ ይቀይራሉ ። እንዲህ እንዲህ እያሉ ልቅ በሆነ ዝሙት መስከር በጣም ነው የሚያስደስታቸው ። እንዲህ አይነት ሰው ባህሪው እስካልተቀየረ ድረስ ለትዳር ፍፁም ምቹ አይደለም ። ይህ ባህሪ ብዙውን ጊዜ በወንዶች ላይ እንደሚንጸባረቅ ይታመናል። እነዚህ ሰዎች በሕይወታቸው ሰፊውን ቦታ የሚይዘው #ስሜት ነው ።
#9ኛ_ኢምፒቲ_ላቭ (Empty Love ) ፦ "ባዶ ፍቅር" ከምንም ነገር ተነስተው ባዶ ፍቅር የሚይዛቸው ሰዎች አሉ ። ለጊዜው "ፍቅር ያዘኝ " ይበሉ እንጂ ፍቅራቸው ግን ምንም ጣዕምና ትርጉም የሌለው ነው ። ለምን እንዳፈቀሩ ቢጠየቁ እንኳን በቂ መልስ የላቸውም ። ፍቅር ፍቅር የሚሆነው ደግሞ ሰጥቶ መቀበል ሲኖርበት ነው ። በእነዚህ ሰዎች መካከል ግን ፍቅርን መስጠትና መቀበል የሚባለው ነገር እንኳን በቅጡ አይታወቅም ። ፍቅርን ሰጠን ቢሉ እንኳን በቂ መልስ ግን የለውም ። ብቻ ባጋጣሚ ስለተገናኙ ተቀራርበው ሊሆን ይችላል። ግን ቅርበታቸው ትርጉምና ደስታ የማይሰጥ ዓይነት ባዶ ቅርበት ሲሆን ቁርጠኝነትም ስሜትም በውስጡ የሌለው የፍቅር ዓይነት ነው። በቀጣይ ደሞ የቀሩትን እናያለን ። ሃሳብ አስተያየት ኢዮአታም ላይ ልትነግሩኝ ትችላላቹ ።

🌼share it

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret