ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
6.91K subscribers
463 photos
10 videos
22 files
453 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
😓 #ንነጽር_፺፰

ከሰኞ እስከ ዕለተ አርብ ድረስ እየሰቀልኩት ነበር፤ አልሰቀል ብሎ አስጨንቆኝ፤ ግን የተሰቀለው ክርስቶስ ረዳኝ መሰለኝ ልክ ዕለተ አርብ ላይ ሰቅዬ ጨረስኩት። በዚያው ዕለት ደግሞ ከጌታዬ ጋር መቃብር ውስጥ ጨመርኩት። ዛሬ በዕለተ እሑድ ክርስቶስ ሲነሣ እኔ ቀብሬው የነበረው ግን አልተነሣም።

ሳስበው ግን እንዳይነሣ ያደረገው ሞቶ የተነሣው ክርስቶስ ነው። ምክንያቱም ስሰቅለውና ስቀብረው ያየው እርሱ ነበራ! ተነሥቶ እንዳይከተለኝ አጥብቄ የለመንኩት ለክርስቶስ ነበራ!

ስሰቅለው ግን በጣም ነበር ያስቸገረኝ። አንዱን ስሰቅለው ሌላ ይመጣል፤ ጨርሼ ሰቀልኩ ብዬ ላርፍ ስል ሌላላ ይታወሰኛል። እያልኩ እያልኩ ከሰኞ እስከ አርብ ደረስኳ። አርብ ከስንት ስቃይ በኋላ ሰቀልኩትና ዕረፍትን አገኘኹ። መሰቀሉን ያረጋገጥኩት ደግሞ በዕለተ አርብ መጨረሻ ላይ እካህኑ ጋር ሄጄ ጠብጠብ... ጠብጠብ...እያደረጉ ቃሌን የሰጠኋቸው ጊዜ ነው።

ጌታዬ ሆይ በዕለተ አርብ የሰቀልኳትን
#ኃጢአቴን ትንሣኤ ስለሌላት በብዙ እባርክሃለው። እኔ እንደሰቀልኳት አንተ ደግሞ ቀብረህ አስቀርተሃታልና አመሰግንሃለው🙏

#ኃጢአቴን_ነው_የቀበርኳት!

መ ል ካ ም የ ት ን ሣ ኤ በ ዓ ል !

@MekuriyaM
👌 #ንነጽር_፺፱

ትሕትና ማለት ለካ ከልብ ዝቅ ማለት እንጂ ከላይ ከላይ ዝቅ ማለት አይደለም።
ጣዕም አለው ለካ ትሕትና! ለዚያ ነዋ አባቶቻችን ራሳቸውን ዝቅ እያደረጉ ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ጸጋ የሚጎናጸፉት!

ይህንን ጽሑፍ ደርሷችኹ ማንበብ ከቻላችኹ በሕይወታችኹ ዛሬ አንድ ቁም ነገር ለመሥራት ብቁ እስኪ!
የእውነት ከልቤ ልምከራችኹ ያለምንም ማጉረምረምና መሳቀቅ ከልብ ዝቅ ማለትን ተለማመዱ።

ከልብ ዝቅ ማለትንና ትሕትናን ልትላበሱ ወስናችኹ እንደሆን አንድ መንገድ ልጠቁማችኹ ነው።

ወዲህ ወድያ እየተረማመሰ የምታዩት ሰው ላይ ምንም ሐሳብ አይኑራችኹ። ከላይ ከፍ የሚያደርግ አንድ እግዚአብሔር መኖሩን ብቻ ልብ በሉ። ክርስቶስን በልባችኹ አንግሡት!

እደግመዋለው!
   የምታውቃቸውም ሆነ የሚያውቁህ ሰዎች ሁሉንም ጠቅለል አድርግና የሆነ ቦታ ስጣቸው። አዕምሮህ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥጦታዎችና ሀብቶች ብዛት እንዲመላለሱ ፍቀድ። እነዚያ ጸጋዎች በሙሉ ከትሕትና ሥር መቀመጣቸውን አገናዝብ። እናማ ሰዎች የፈለገ ነገር ያድርጉልህ/ያድርጉልህ፤ አንተ ግን ኢየሱስን በልብህ ዙፋን አስቀምጠውና መሬት መሬቱን ውደድና ከመሬት ተቀመጥ ትልቅ ክብር አትፈላልግ።

ይኸውልህ
ሰዎች ያልክ እንደሆነ ስለ አንተ አይገዳቸውም። እመነኝ ብትራብም ሆነ ብትጠማ ከልቡ እኔን የሚልህ ልታገኝ አትችልም! ስለዚህ ከልብህ ዝቅ በልና በእግዚአብሔር ታመን እንጂ!

ያኔ ከልብ ዝቅ ማለትን ክብርን እንደሚሰጥ፤ ትሕትና ደግሞ የተለየ ደስታና ሰላም እንዳለው አይቶ መጓዝ ብቻ ነው!
'በጊዜው ከፍ ለማለት ለጊዜው ዝቅ ማለት'ን ይበጃልና ዝቅ በል ዝቅቅቅ!

◎●●Join us on telegram
      
@MekuriyaM
Forwarded from ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media (፩ Mekuriya Murashe)
👌 #ንነጽር_፺፱

ትሕትና ማለት ለካ ከልብ ዝቅ ማለት እንጂ ከላይ ከላይ ዝቅ ማለት አይደለም።
ጣዕም አለው ለካ ትሕትና! ለዚያ ነዋ አባቶቻችን ራሳቸውን ዝቅ እያደረጉ ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ጸጋ የሚጎናጸፉት!

ይህንን ጽሑፍ ደርሷችኹ ማንበብ ከቻላችኹ በሕይወታችኹ ዛሬ አንድ ቁም ነገር ለመሥራት ብቁ እስኪ!
የእውነት ከልቤ ልምከራችኹ ያለምንም ማጉረምረምና መሳቀቅ ከልብ ዝቅ ማለትን ተለማመዱ።

ከልብ ዝቅ ማለትንና ትሕትናን ልትላበሱ ወስናችኹ እንደሆን አንድ መንገድ ልጠቁማችኹ ነው።

ወዲህ ወድያ እየተረማመሰ የምታዩት ሰው ላይ ምንም ሐሳብ አይኑራችኹ። ከላይ ከፍ የሚያደርግ አንድ እግዚአብሔር መኖሩን ብቻ ልብ በሉ። ክርስቶስን በልባችኹ አንግሡት!

እደግመዋለው!
   የምታውቃቸውም ሆነ የሚያውቁህ ሰዎች ሁሉንም ጠቅለል አድርግና የሆነ ቦታ ስጣቸው። አዕምሮህ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥጦታዎችና ሀብቶች ብዛት እንዲመላለሱ ፍቀድ። እነዚያ ጸጋዎች በሙሉ ከትሕትና ሥር መቀመጣቸውን አገናዝብ። እናማ ሰዎች የፈለገ ነገር ያድርጉልህ/ያድርጉልህ፤ አንተ ግን ኢየሱስን በልብህ ዙፋን አስቀምጠውና መሬት መሬቱን ውደድና ከመሬት ተቀመጥ ትልቅ ክብር አትፈላልግ።

ይኸውልህ
ሰዎች ያልክ እንደሆነ ስለ አንተ አይገዳቸውም። እመነኝ ብትራብም ሆነ ብትጠማ ከልቡ እኔን የሚልህ ልታገኝ አትችልም! ስለዚህ ከልብህ ዝቅ በልና በእግዚአብሔር ታመን እንጂ!

ያኔ ከልብ ዝቅ ማለትን ክብርን እንደሚሰጥ፤ ትሕትና ደግሞ የተለየ ደስታና ሰላም እንዳለው አይቶ መጓዝ ብቻ ነው!
'በጊዜው ከፍ ለማለት ለጊዜው ዝቅ ማለት'ን ይበጃልና ዝቅ በል ዝቅቅቅ!

◎●●Join us on telegram
      
@MekuriyaM
🛑 #ንነጽር_፻ |100|

#ሕጻናት_በነበርን_ጊዜ
የእግዚአብሔርን መኖር አናውቅም። ከእናትና ከአባታችን በቀር ማንም ጠባቂ እንደሌለን ነበር የምናውቀው። ከወላጆቻችን በላይ የምንቀርበውም ሆነ የምንወደው ማንም አልነበረም።

#ትንሽ_ከፍ_ስንል
ሰዎች "እግዚአብሔር፣ እግዚአብሔር' ሲሉ ስንሰማቸው 'እግዚአብሔር ማን ነው?' ብለን መጠየቅ ጀመርን። ከዚያም 'እግዚአብሔር አይታይም፥ ድምጹም አይሰማም እሱ ግን ለሁላችንም ያየናል። ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር ስናደርግ ይመለከተናል።' ተብሎ ስለሚመለስልን እግዚአብሔርን እንፈራው ነበር።

#ወደ_ወጣትነት_ስንሸጋገር
እግዚአብሔርን አወቅነው ግን መግለጥ ተሳነን። መኖሩንም አረጋገጥን ግን መፍራት ከበደን። ተቅበዘበዝን የምንይዘው፣ የምናየው ነገር በሙሉ እኛን አናስቆም አለ። ያኔ ልጅ እያለን እናትና አባታችንን እጅግ እንወድ የነበርነው መልካም ሕጻናቶች እዚህ ጋር ስንደርስ እነርሱን መሳደብና መምታት ጀመርን። ትንሽ ካደግን በኋላ እንፈራው የነበረውን እግዚአብሔር ወደ ጎን ገፍተር አደረግነው።

#ከዚያም_አለፍንና
አባት ወይም እናት ወደ መሆን በቃን። ልጅም ኖረን። "ለልጆቻችን ስለ እግዚአብሔር መናገር እያለብን፤ ለእግዚአብሔር ስለ ልጆቻችን መናገር ጀመርን።" እኛ ላይ ደርሶ ያየነው አላዋቂነት ለልጆቻችንም ለማትረፍ በቃን። ከመንግሥቱና ከጽድቁ ይልቅ ስለ ልጆቻችን ማሰብ ጀመርን። ከእግዚአብሔር ራቅን። ከልጅነት እስከ ሽምግልና ድረስ ያለውን ዘመናችን እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከመታዘዝ ይልቅ፥ በዓለም ዲስኩር ታጅበን፣ በብልጭልጭታው ታጭቀን፣ በዘፈን በዳንኪራው ተመስጠን፣ በዲያቢሎስ ሐሳብ ተውጠን ይኸው ዛሬም እዚያው አለን።

❝አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይኹን!❞

◍◍◍Join us on telegram
@MekuriyaM
🌿 #ንነጽር_፲፩

“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
  — ፊልጵስዩስ 4፥6

ሐዋርያው "አትጨነቁ" ሲል ምን ማለቱ ነው? እንዴት ነው አለመጨነቅ የምንችለው ብሎ የሚጠይቅ አይጠፋም።
:
በእርግጥ ምንም እሚያስጨንቅ ነገር የለም ማለት አንችልም። ምክንያቱም
#ጭንቀት ባይኖር ኖሮ #አትጨነቁ ባልተባልን ነበር።

እንዲሁ
#አትጨነቁ ብቻ ብሎ ዝም ቢለን፤ ታድያ ምን እናድርግ ማለታችን አይቀርም ነበር። ነገር ግን ከእነ መፍትሔው ስለተቀመጠልን #ጭንቀትን የማስወገድ አቅማችን እጅግ እንዲጨምር ያደርገዋል።

እኛ ለጌታ ሩቅ ብንሆንም እርሱ ለእኛ ቅርብ እንደሆነ ገና ከጅምሩ ተስፋችንን እንዲለመልም አበሠረን። ቀጠለና በክፉም በደጉም ወደ ፈጣሪያችን መጮህ እንዳለብን ነገረን። ምክንያቱም እርሱ ለእኛ ቅርብ ነውና።

#የሚያስጨንቃችኹን ነገር እስኪ ለአንዳፍታ ቆም ብላችኹ አስቡት..... ይሄኔ'ኮ በአላፊ ጠፊ ነገር ትጨነቁ ይሆናል። ግዴ'ለም በጸሎትና በምልጃ ከምስጋናም ጋር ወደ እግዚአብሔር ጩኹ እንጅ በአ ን ዳ ች #አትጨነቁ
አንድ ሰው ሲጨነቅ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን እየተጠራጠረ ነው ወይም አያምንም ማለት ነው።

አንድ ሰው ሲጨነቅ በእግዚአብሔር ቃል ይጠራጠራል ወይም ማመን ከብዶታል ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ተጨንቀን እናውቃለን። ይህን ቃል ሥናስታውስ ግን ጭንቀታችን እንደሚቀል 100% እርግጠኛ ነኝ።

ይህን በመሰለው ግን
#መጨነቅ ይገባናል እላለኹ👇

“በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበርና፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።”
  — 2ኛ ቆሮ 2፥4


JOIN
@MekuriyaM
👁‍🗨 #ንነጽር_፻፩

   ፍቅር   ይዞኛል

አዎ አልዋሽም ይዞኛል፡
የማፍቀር ወግ ደርሶኛል።
መቼም አትሰለቸኝ፡
ፍቅሯም ተመቸኝ።
ደግሞ ሁሉም ይወዳታል፡
በእንተዝ ናፈቅረኪ ይሏታል።

ከምድር ያይደለ ነው እንጂ ከአርያም፡
ፍቅር ይዞኛል ከድንግል ማርያም

◦◦◦JOIN US ON TELEGRAM
          @MekuriyaM
Forwarded from ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media (Mekuriya ፩)
🌿 #ንነጽር_፳፰
ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች "ሕይወት ውስብስብ ናት፤ ፈተናዋም እጅግ የበዛ ነው።" ሲሉ ይደመጣሉ።
◦◦◦
አዎ ትክክል ነው... በዚህ ምድር ላይ ከኖርክ አይቀር ትወሳሰባለህ፤ ትፈተናለህም!
◦◦◦
ነገር ግን ወዳጄ የአንተ የሕይወት መስመር ልትረዳው የምትችለው በገጠሙህ ፈተናዎች አይደለም፤ በገጠሙህ ፈተናዎች ላይ በሰጠኸው ምላሽ እንጂ።

ሰላም ለምድራችን🙏
@MekuriyaM
ፍቅር ለሕዝባችን🙏
#ንነጽር_107

የቀረ ነገር አለ!

ወተት ውስጥ ጥቁር ነገር ወይም ደስ የማይል ሽታ ያለው ነገር ገብቶበት ካየኸው ወተቱን ትደፋዋለህ። ማር ቢገባበትሳ? ከወተቱ የበለጠ ጣፋጭ ነገር ስለተጨመረበት ብለህ ትጠጣዋለህ እንጂ አትደፋውም አይደል? ነገር ግን ጣዕሙን ይቀይረዋል፤ ከወተትነት ጣዕም ሊወጣ ይችላል።

አየህ! ከዚያ በኋላ ግን ወተት ጠጥቻለሁ ብለህ ከተናገርክ ውሸት ተናግረሃል ማለት ነው። ምክንያቱም የወተቱ የራሱ ጣዕም ብቻ አይደለም ያጣጣምከው፤ የጠጣኸው ወተት ብቻ አይደለም ከማር ጋር ነው የጠጣኸው።

ጣዕሙን ይበልጥ ማራኪ ሊያደርገው ይችላል። ነገር ግን የወተቱ ጣዕም ብቻ እንዳልሆነ ልብ በል!
በዚያው ተቃራኒ ሊያበላሸውም ይችላል። ሊያበላሸው የቻለው ማሩ እንደሆነም ጠንቅቅ!

ላወራ የፈለግኩት ስለ ወተት ጣዕም አይደለም!

ወዳጄ! ሕይወትህ ውስጥ ሊገቡ የምትፈቅድላቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? መልካም እየመሰሉ የኋላ ኋላ ግን ሕይወትህን የሚመርዙ ከሆኑስ አስበህበት ታውቃለህ? አንተ የአንተን ሕይወት መምራት አቅቶህ ስንት ሰው ጠየቅክ? ከዚያስ እነሱ በሰጡህ ውሳኔ ሄድክበት?

ምላሽህ "አዎ!" ከሆነ የእነሱ ውሳኔ በአንተ ሕይወት ላይ እያዩት ነው እንጂ እኮ አንተ የራስህን የሕይወት መንገድ እየገሰገስክ አይደለም። አንተ ጭንቅላት የለህም አታስብም? አስብ አሰላስል ት ች ላ ለ ህ!

ሁለት ተመሳሳይ ስልኮች በአንዳንድ እጅህ ያዛቸው። ከዚያም አንደኛው ላይ Data on አድርግና Internet ተጠቀም። አንደኛው ላይ ግን Data'ውን off አድርውና Internet ለመጠቀም ሞክር። ልዩነት ፈጥረሃል አይደል? ለዚያውም ትልቅ ልዩነት ነገር ግን ሁለቱም ተመሳሳይ ስልኮች ናቸው። የሁለተኛውን ስልክ Data on ብታደርገውስ እሱም እንደ መጀመርያው ይሠራል።

ስለ ስልክ አጠቃቀም ልነገርህ አይደለም!

አንተ ጋር የሆነ የቀረ ነገር አለ። እሱን አግኘውና አብራው! ከዚያስ?የራስህን ሕይወት በራስህ ሐሳብና አቅም ምራው!!


ሐምሌ 13/2016
ወልቂጤ ኢትዮጵያ
🫳 Dn Mekuriya Murashe

🌝 ስለማከብርህ(ሽ) ላክኩልህ(ሽ)፤ ካከበርከኝ(ሽኝ) Join እና Follow አድርገኝ(ጊኝ)እጅግ ካከበርከኝ(ሽኝ) Share አድርግልኝ(ጊልኝ)

🫵Join us on Telegram
t.me/Dilla_Live
t.me/Dilla_Live

t.me/MekuriyaM
t.me/MekuriyaM

🫵 Follow us on Tiktok
http://tiktok.com/@mekuriya19


“እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥6



አሳዳጊው ሆይ በሁሉ አሳድገን🙏
ማንን ነው የሰጠኸኝ?

🫵
#ንነጽር_109

በጨነቀኝ ጊዜ አጽናኝ ይሆነኝ ዘንድ
#ማንን_ነው_የሰጠኸኝ? ልፋቴን ሳዋየው መፍትሔ እንዲሆነኝ #ማንን_ነው_የሰጠኸኝ? ብኩንነቴን ሲገባኝ ያበረታኝ ዘንድ #ማንን_ነው_የሰጠኸኝ? ምድር ስትመሽብኝ ማረፍያ ይሆነኝ ዘንድ #ማንን_ነው_የሰጠኸኝ? ብዬ ስጠይቅህ ምላሽ ይሰጠኝ ዘንድ #ማንን_ነው_የሰጠኸኝ??

"ልጄ ሆይ ምላሽ ይሆንህ ዘንድ
#መጽሐፍ_ቅዱስን፤ አጽናኝ፣ አበርታች... ይሆንህ ዘንድ #ቃሌን አልሰጠሁህምን?" የምትለኝ የምትለኝ መስሎ ታየኝና አጽናናኸኝ።

ከአንተ እና ከባለሟሎችህ ውጪ ለካ ማንም የለኝም!

ክርስቶስ ሆይ! አንተንና ባለሟሎችህን ብቻ እንድቀርብ ቀርቤም ሰው እንድሆን እርዳኝ🙏

“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ" አቤቱ ሆይ ስማኝ🙏

https://t.me/MekuriyaM
https://t.me/MekuriyaM