ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
4.72K subscribers
454 photos
10 videos
20 files
413 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
🛑 #ንነጽር_፻ |100|

#ሕጻናት_በነበርን_ጊዜ
የእግዚአብሔርን መኖር አናውቅም። ከእናትና ከአባታችን በቀር ማንም ጠባቂ እንደሌለን ነበር የምናውቀው። ከወላጆቻችን በላይ የምንቀርበውም ሆነ የምንወደው ማንም አልነበረም።

#ትንሽ_ከፍ_ስንል
ሰዎች "እግዚአብሔር፣ እግዚአብሔር' ሲሉ ስንሰማቸው 'እግዚአብሔር ማን ነው?' ብለን መጠየቅ ጀመርን። ከዚያም 'እግዚአብሔር አይታይም፥ ድምጹም አይሰማም እሱ ግን ለሁላችንም ያየናል። ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር ስናደርግ ይመለከተናል።' ተብሎ ስለሚመለስልን እግዚአብሔርን እንፈራው ነበር።

#ወደ_ወጣትነት_ስንሸጋገር
እግዚአብሔርን አወቅነው ግን መግለጥ ተሳነን። መኖሩንም አረጋገጥን ግን መፍራት ከበደን። ተቅበዘበዝን የምንይዘው፣ የምናየው ነገር በሙሉ እኛን አናስቆም አለ። ያኔ ልጅ እያለን እናትና አባታችንን እጅግ እንወድ የነበርነው መልካም ሕጻናቶች እዚህ ጋር ስንደርስ እነርሱን መሳደብና መምታት ጀመርን።
ትንሽ ካደግን በኋላ እንፈራው የነበረውን እግዚአብሔር ወደ ጎን ገፍተር አደረግነው።

#ከዚያም_አለፍንና
አባት ወይም እናት ወደ መሆን በቃን። ልጅም ኖረን። "ለልጆቻችን ስለ እግዚአብሔር መናገር እያለብን፤ ለእግዚአብሔር ስለ ልጆቻችን መናገር ጀመርን።" እኛ ላይ ደርሶ ያየነው አላዋቂነት ለልጆቻችንም ለማትረፍ በቃን። ከመንግሥቱና ከጽድቁ ይልቅ ስለ ልጆቻችን ማሰብ ጀመርን። ከእግዚአብሔር ራቅን። ከልጅነት እስከ ሽምግልና ድረስ ያለውን ዘመናችን እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከመታዘዝ ይልቅ፥ በዓለም ዲስኩር ታጅበን፣ በብልጭልጭታው ታጭቀን፣ በዘፈን በዳንኪራው ተመስጠን፣ በዲያቢሎስ ሐሳብ ተውጠን ይኸው ዛሬም እዚያው አለን።

❝አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይኹን!❞

◍◍◍Join us on telegram
@MekuriyaM