😓 #ንነጽር_፺፰
ከሰኞ እስከ ዕለተ አርብ ድረስ እየሰቀልኩት ነበር፤ አልሰቀል ብሎ አስጨንቆኝ፤ ግን የተሰቀለው ክርስቶስ ረዳኝ መሰለኝ ልክ ዕለተ አርብ ላይ ሰቅዬ ጨረስኩት። በዚያው ዕለት ደግሞ ከጌታዬ ጋር መቃብር ውስጥ ጨመርኩት። ዛሬ በዕለተ እሑድ ክርስቶስ ሲነሣ እኔ ቀብሬው የነበረው ግን አልተነሣም።
ሳስበው ግን እንዳይነሣ ያደረገው ሞቶ የተነሣው ክርስቶስ ነው። ምክንያቱም ስሰቅለውና ስቀብረው ያየው እርሱ ነበራ! ተነሥቶ እንዳይከተለኝ አጥብቄ የለመንኩት ለክርስቶስ ነበራ!
ስሰቅለው ግን በጣም ነበር ያስቸገረኝ። አንዱን ስሰቅለው ሌላ ይመጣል፤ ጨርሼ ሰቀልኩ ብዬ ላርፍ ስል ሌላላ ይታወሰኛል። እያልኩ እያልኩ ከሰኞ እስከ አርብ ደረስኳ። አርብ ከስንት ስቃይ በኋላ ሰቀልኩትና ዕረፍትን አገኘኹ። መሰቀሉን ያረጋገጥኩት ደግሞ በዕለተ አርብ መጨረሻ ላይ እካህኑ ጋር ሄጄ ጠብጠብ... ጠብጠብ...እያደረጉ ቃሌን የሰጠኋቸው ጊዜ ነው።
ጌታዬ ሆይ በዕለተ አርብ የሰቀልኳትን #ኃጢአቴን ትንሣኤ ስለሌላት በብዙ እባርክሃለው። እኔ እንደሰቀልኳት አንተ ደግሞ ቀብረህ አስቀርተሃታልና አመሰግንሃለው🙏
#ኃጢአቴን_ነው_የቀበርኳት!
መ ል ካ ም የ ት ን ሣ ኤ በ ዓ ል !
@MekuriyaM