ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
6.9K subscribers
463 photos
10 videos
22 files
453 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
#ንነጽር_107

የቀረ ነገር አለ!

ወተት ውስጥ ጥቁር ነገር ወይም ደስ የማይል ሽታ ያለው ነገር ገብቶበት ካየኸው ወተቱን ትደፋዋለህ። ማር ቢገባበትሳ? ከወተቱ የበለጠ ጣፋጭ ነገር ስለተጨመረበት ብለህ ትጠጣዋለህ እንጂ አትደፋውም አይደል? ነገር ግን ጣዕሙን ይቀይረዋል፤ ከወተትነት ጣዕም ሊወጣ ይችላል።

አየህ! ከዚያ በኋላ ግን ወተት ጠጥቻለሁ ብለህ ከተናገርክ ውሸት ተናግረሃል ማለት ነው። ምክንያቱም የወተቱ የራሱ ጣዕም ብቻ አይደለም ያጣጣምከው፤ የጠጣኸው ወተት ብቻ አይደለም ከማር ጋር ነው የጠጣኸው።

ጣዕሙን ይበልጥ ማራኪ ሊያደርገው ይችላል። ነገር ግን የወተቱ ጣዕም ብቻ እንዳልሆነ ልብ በል!
በዚያው ተቃራኒ ሊያበላሸውም ይችላል። ሊያበላሸው የቻለው ማሩ እንደሆነም ጠንቅቅ!

ላወራ የፈለግኩት ስለ ወተት ጣዕም አይደለም!

ወዳጄ! ሕይወትህ ውስጥ ሊገቡ የምትፈቅድላቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? መልካም እየመሰሉ የኋላ ኋላ ግን ሕይወትህን የሚመርዙ ከሆኑስ አስበህበት ታውቃለህ? አንተ የአንተን ሕይወት መምራት አቅቶህ ስንት ሰው ጠየቅክ? ከዚያስ እነሱ በሰጡህ ውሳኔ ሄድክበት?

ምላሽህ "አዎ!" ከሆነ የእነሱ ውሳኔ በአንተ ሕይወት ላይ እያዩት ነው እንጂ እኮ አንተ የራስህን የሕይወት መንገድ እየገሰገስክ አይደለም። አንተ ጭንቅላት የለህም አታስብም? አስብ አሰላስል ት ች ላ ለ ህ!

ሁለት ተመሳሳይ ስልኮች በአንዳንድ እጅህ ያዛቸው። ከዚያም አንደኛው ላይ Data on አድርግና Internet ተጠቀም። አንደኛው ላይ ግን Data'ውን off አድርውና Internet ለመጠቀም ሞክር። ልዩነት ፈጥረሃል አይደል? ለዚያውም ትልቅ ልዩነት ነገር ግን ሁለቱም ተመሳሳይ ስልኮች ናቸው። የሁለተኛውን ስልክ Data on ብታደርገውስ እሱም እንደ መጀመርያው ይሠራል።

ስለ ስልክ አጠቃቀም ልነገርህ አይደለም!

አንተ ጋር የሆነ የቀረ ነገር አለ። እሱን አግኘውና አብራው! ከዚያስ?የራስህን ሕይወት በራስህ ሐሳብና አቅም ምራው!!


ሐምሌ 13/2016
ወልቂጤ ኢትዮጵያ
🫳 Dn Mekuriya Murashe

🌝 ስለማከብርህ(ሽ) ላክኩልህ(ሽ)፤ ካከበርከኝ(ሽኝ) Join እና Follow አድርገኝ(ጊኝ)እጅግ ካከበርከኝ(ሽኝ) Share አድርግልኝ(ጊልኝ)

🫵Join us on Telegram
t.me/Dilla_Live
t.me/Dilla_Live

t.me/MekuriyaM
t.me/MekuriyaM

🫵 Follow us on Tiktok
http://tiktok.com/@mekuriya19


“እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥6



አሳዳጊው ሆይ በሁሉ አሳድገን🙏