ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
ይህንን ማድረግ የሚገባቸውና የሚችሉት በገዳም ያሉ ሰዎች ብቻ አይደሉም፡፡ በዓለም የምንኖር ሰዎችም ብቻችንን የምንሆንበትና በጸሎት፣ በተመስጦ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ፣ ራሳችንን በመመርመር የምናሳልፈው ጊዜ በመመደብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በወጣትነት ዘመኑ እንዳደረገው መኖሪያ ቤቶቻችንን ገዳማት ማድረግ እንችላለን፡፡ ሁኔታዎችን እያመቻቸን ወደተለያዩ ገዳማት እየሄድን ጊዜ ማሳለፍም ጠቃሚ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ምግባችንን፣ መጠጣችንን እና ልብሳችንን በልክ እያደረግን መጥምቁን ባለ ብዙ ፍሬ በሆነበት ጎዳናው ልንከተለው ይገባናል፡፡

በአግልግሎቱ ያስተምረናል፡ -ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ አገልግሎት ልንማራቸው የሚገቡ በርካታ ቁም ነገሮች አሉ በማለት የሚከተሉትን ይዘረዝራሉ፡፡
ቅድስ ዮሐንስ ያገለገለው ለአጭር /ከስድስት ወራት ብዙ ላልበለጠ/ ጊዜ ብቻ ቢሆንም በርካታ ሥራዎችን ሠርቶ አልፏል፡፡ እኛም አገልግሎታችንን ልንመዝነው የሚገባን በርዝመቱ ሳይሆን በጥልቀቱ፣ በውጤታማነቱ፣ በሚያፈራው ፍሬ እና በሚያመጣው ለውጥ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል ዓላማው ሰዎችን ከ #እግዚአብሔር ጋር ማገናኘት እንጂ ሰዎችን በእርሱ ዙሪያ መሰብሰብና መክበር አልነበረም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደሚነግረን «ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳ፣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ነገር ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይጎርፉ ነበር፡፡» /ማቴ.3÷5-6/ እርሱ ግን «እኔ በውኃ ለንስሐ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡» እያለ ሰዎቹ እርሱን እንዲከተሉ ሳይሆን የ #ጌታችንን መምጣት ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርግ ትምህርት ያስተምራቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

የመጀመሪያዎቹ #ጌታችንን የተከተሉት ደቀመዛሙርት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ነበሩ፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን መታጀብ /በሕዝብ መከበብ/ ለሚያስደስተን የ #እግዚአብሔርን ሳይሆን የእኛን ተከታዮች እንደ ፈሪሳውያን ለምንፈልግ አገልጋዮች ትልቅ ተግሳጽ ነው፡፡
«በማግስቱ ዮሐንስ ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር እንደገና በእዚያው ቦታ / #ጌታችን በተጠመቀበት/ ቦታ ነበር፡፡ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም በዚያ ሲያልፍ አይቶ «እነሆ የ #እግዚአብሔር በግ» አለ ሁለቱ ደቀመዛሙርትም ይህን ሲናገር ሰምተው #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ተከተሉት» /ዮሐ.1÷35-37/

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም በርካታ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት የነበሩና የእርሱን ጥምቀት የተጠመቁ ሰዎች በቀላሉ ወደ ክርስቲያኖች ማኅበር እንደተቀላቀሉ ይነግረናል፡፡ /ሐዋ.18÷24-19፣ 6፣ 13÷24/
ራሱም ይህንን አቋሙን እንዲህ በማለት ልብ በሚነኩ ቃላት እንዳጋለጠው ወንጌላዊው ዮሐንስ በወንጌሉ መዝግቦታል፡፡
ሰዎች ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥተው «መምህር፣ በዮርዳኖስ ከአንተ ጋር የነበረው፣ ስለ እርሱም የመሰከርክለት … ሰው ሁሉ ወደ እርሱ እየሄዳ ነው» ባሉት ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰ «ከላይ ካልተሰጠው በቀር ማንም አንዳች ሊቀበል አይችልም፡፡ «እኔ #ክርስቶስ አይደለሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ» እንዳልሁ እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡ ሙሽራይቱ የሙሽራው ነች፡፡ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሟል፡፡ እርሱ ሊልቅ፤ እኔ ግን ላንስ ይገባል፡፡»
እውነት ነው፡፡ ሙሽራይቱ ቤተ ክርስቲያን የሙሽራው የ #ክርስቶስ ነች፡፡ አገልጋዮች ሚዜ ናቸው፡፡ ሥራቸውም ሙሸራይቱን ወደ ሚዜው ማቅረብ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል በድፍረት ነው፡፡ እርሱ በነበረበት ወቅት ሔሮድስ አንቲጳስ የወንድሙን ሚስት አግብቶ የሚገሥጸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በበረሃው ሳለ ደፋር፣ ለሰው ፊት የማያደላ፣ መሆንን ተምሮ ነበርና ገብቶ ገሠፀው፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዲህ ይላሉ «ከአገልግሎቱ ሊያዘገየው ወይም ሊያስተጓጉለው የሚችል ቢሆንም እንኳን ተገቢውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አላለም፡፡ አስተሳሰቡም እንዲህ ነው « #እግዚአብሔር እንዳገለግል ፈቃድ ከሆነ አገለግላለሁ፤ ካልሆነም የእርሱ ፈቃዱ ይሁን፡፡ ዋናው ነገር እውነትን መመስከር ነው» ቅዱስ ዮሐንስ ስለእውነት ራሱን አሳልፎ ቢሰጥም ከሞተ በኋላም ቢሆን የትምህርቱ ድምፅ ሄሮድስን ሲወቅሰው ኑሯል፡፡»
እውነት ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ከሞተ በኋላም ቢሆን ራሱ አስራ አምስት ዓመት ዙራ አስተምራለች፡፡ ሔሮድስም ከሞት ተነሥቶ የሚመጣ እስኪመስለው ድረስ ይፈራው እንደበር ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ጽፏል «በዚያን ጊዜ የአራተኛው ክፍል ገዢ የነበረው ሄሮድስ /አንቲጳስ/ ስለ #ኢየሱስ ዝና ሰማ፤ ባለሟሎቹንም እንዲህ ከሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶ መጥቶአል ማለት ነው፤ ይህ ሁሉ ድንቅ ተዓምራት በእርሱ የሚደረገውም ለዚህ ነው» አላቸው፡፡ /ማቴ.14÷1-2/፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ያማልደናል

ቅዱስ ዮሐንስ ዛሬ እኛን #እግዚአብሔር ለወዳጆቹ በሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት በጸሎቱ ከ #እግዚአብሔር ያማልደናል፡፡
ቤተ ክርስቲያንም ዘወትር «ሰአል ለነ ዮሐንስ» «ዮሐንስ ሆይ ለምንልን»፤ ትለዋለች፤ «በአንተ ዮሐንስ መጥምቅ መሐረነ» «ስለ ዮሐንስ ስትል ማረን» እያለችም ትጸልያለች፡፡ እኛም ገድሉንና፣ መልኩን በመጸለይ፣ መታሰቢያው በሚደረግበት ጊዜም በስሙ ዝክር በመዘከር፣ ቸርነት በማድረግ በረከትን ለማግኘት ልንተጋ ይገባናል፡፡
«ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀመዛሙርቶቼ ስም ቢያጠጣ፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም» /ማቴ.10÷42/
«የቅዱስ ዮሐንስ ጸሎቱና በረከቱ ይደርብን! አማላጅነቱ ይደረግልን»

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

ምንጭ፡­­ ©ማኅበረ ቅዱሳን
#መስከረም_4

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም አራት በዚህች ቀን #ወንጌላዊው_ቅዱስ_ዮሐንስ ልደቱ ነው፣ የድባው #አቡነ_ሙሴ እረፍታቸው ነው፣ #ነቢዩ_ኢያሱ_ወልደ_ነዌ አረፈ፣ #አባ_መቃርስ_ሊቀ_ዻዻሳት አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ

መስከረም አራት በዚህች ዕለት ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ከእናቱ ማርያም ባውፍልያ ከአባቱ ዘበዴዎስ የተወለደበት ዕለት እንደሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን መዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡ የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡

እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ "በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን" እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም "አይዞሽ አትዘኚ" አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ " #እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን" ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም "በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ" አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በ #ጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡

በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ #ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስዶታል።

#ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላስተማረው ምሥጢር የለም፡፡ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በ #እግዚአብሔር ዘንድ ነበረ…" ብሎ የ #ጌታችን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ሲል በመሀል መልአኩን በዮርዳኖስ ባሕር ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ መልአኩም የዮርዳኖስን ባሕር በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ ውጭ ሲያፈስ ተመለከተው፡፡ ዮሐንስም ተገርሞ "ምን ማድረግህ ነው" አለው፡፡ መልአኩም "የዮርዳኖስን ባሕር ቀድቼ እየደፋሁ ልጨርሰው ነው" ሲለው ዮሐንስም መልሶ "ታዲያ በእንቁላል ስባሪ ነውን?" አለው፡፡ መልአኩም "አዎን" አለው፡፡ ዮሐንስም "በከንቱ ደከምክ" አለው፡፡ ይህን ጊዜ መልአኩም መልሶ "አንተስ እንጂ ደግሞ የአምላክን መገኘት፣ አኗኗሩንም ተመራምረህ በጥበብ ለማግኘት ብለህ 'በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በ #እግዚአብሔር ዘንድ ነበረ..' ብለህ ጀምረህ የለምን? አንተ #ጌታን ተመራምረህ ካገኘህና ከደረስክበት እኔም የዮርዳኖስን ወንዝ በዚህ እንቁላል ቅርፊት ቀድቼ እጨርሰዋለሁ" አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ጊዜ ደንግጦ ዝቅ ብሎ "ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ…" ብሎ ሀሳቡን ለወጠና ሌላ ታሪክ ቀጠለ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ #ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወክሎ #እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለእመቤታችን በአደራ የተሰጠ ሲሆን #እመቤታችንን ከወሰዳት በኋላ ለ16 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡ እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች #እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከ #ጌታችን ጋር ይመሳል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡ #ጌታችን በተሰቀለበት ዘመን የነበረው ጢባርዮስ ቄሳር ልጁ በሽተኛ ነበር፡፡ የ #ጌታችንን የማዳን ሥራ እየሰማ እነ ጲላጦስም ስለ #ጌታችን የሚጽፉለትን ይሰማ ስለነበር ልጁን ከ #ጌታችን መቃብር ላይ እንዲያኖሩለት ላከው፡፡ ልጁም ፈጥኖ ተፈወሰለት፡፡ ጢባርዮስ ቄሳርም በልጁ መዳን ምክንያት የ #ጌታችንን ውለታ ማስቀመጥ ፈልጎ የ #ጌታችንን ሥዕሉን የሚሥልለትን ሲያጠያይቅ ዮሐንስን አገናኙት፡፡ ዮሐንስም #ጌታችንን ልክ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ አድርጎ በመሣል ለጢባርዮስ ቄሳር ሰጠው፡፡ ሲሥለውም በመጀመሪያ #ጌታችንን ልክ እንደተሰቀለ አድርጎ ራቁቱን ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የ #ጌታችን ሥዕልም አፍ አውጥቶ "በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ፣ አሁን ደግሞ አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትሰቅለኝን?" ብሎ ተናገረው፡፡ ዮሐንስም እጅግ ደንግጦ "እንዴት አድርጌ ልሳልህ?" ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም "ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ" አለው፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ ከሳለው በኋላ ሥዕሉን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩል ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የ #ጌታችንን ስነ ስቅለት የሚያሳዩ ሥዕሎች መገኛቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፦
በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ #ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር "#ፍቁረ_እግዚእ" ተባለ፣ የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል "#ዮሐንስ_ወልደ_ዘብድዮስ" ተባለ፣ ለ #ጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የ #ጌታችንን አምላክነት በመግለጡ "#ወልደ_ነጎድጓድ" ተብሏል፡፡ ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ "#ነባቤ_መነኮት ወይም #ታኦሎጎስ" ተብሏል። ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ "#አቡቀለምሲስ" ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ #ባለራእይ ማለት ነው፡፡ የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ 70 ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ "#ቁጹረ_ገጽ" ተብሏል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ሙሴ_ዘድባ

በዚህች ቀን የድባው አቡነ ሙሴ እረፍታቸው ነው። የትውልድ አገራቸው እስራኤል ልዩ ቦታው ቃና ዘገሊላ ነው። ጽንሰታቸውን ቅዱስ ሩፋኤል መጋቢት 8 ቀን ሲያበስር ልደታቸውን ደግሞ ቅዱስ ገብርኤል ታኅሣሥ 8 ቀን የመወለዳቸውን ብሥራት ተናግሯል፡፡ ሲወለዱ ሚካኤል ወገብርኤል በሰው አምሳል ተገልጠው "የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴ" ብለው ስም አወጡላቸው፡፡

በተወለዱም በ40ኛ ቀናቸው ከተጠመቁ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል አቅፎ ይዟቸው #ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ አቁርቧቸዋል፡፡ በእሳቸውም ምክንያት በዚያች ዕለት በቤተ ክርስቲያን የነበሩት ሰዎች ሁሉ ክቡራን በሆኑ በ #ጌታችን እጆች ቆርበዋል፡፡ የአቡነ ሙሴ አባታቸው ዮስጦስ ለሐዋርያው ናትናኤል አጎቱ ነው፡፡ እናታቸው ጵርስቅላ ጌታችን በሠርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን የለወጠለት የዶኪማስ ልጅ ናት፡፡

#ጌታችን ወደ ዶኪማስ ቤት ሠርግ ተጠርቶ የሄደው ዶኪማስ ናትናኤልን ‹‹ሠርጌን እንዲባርክልኝ #ጌታ_ኢየሱስን ከእናቱ ጋር ጥራልኝ›› ብሎት ነው፡፡ #ጌታችን በስብከቱ ‹‹ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልሏቸው›› ብሎ ብሎ ካቀፋቸውና
ካስተማረባቸው ሕፃናት አንዱ ይኽ አቡነ ሙሴ ናቸው፡፡ ጻድቁ ዋሻዎችን እየፈለፈሉ የቅዱሳን ሐዋርያትን ዐፅም በክብር ያስቀምጡ ነበር፡፡ የተሠወሩ አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ወንጌልን በማስተማር ብዙ መከራ የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ በግብፅ "ንጉሥ አንስጣስዮስ" ተብለው 40 ዓመት በንግሥና እና በድንግልና ኖረዋል፡፡

ከዚህም በኋላ በ #እግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ በመልአክም ምክር ዮናኒ የተባለውን ሌላ ሰው አንግሠው ወደ አስቄጥስ ገዳም ገብተው መነኮሱ፡፡ በገዳሙም በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኋላ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የእኛ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሲያርፉ በቅዱስ አትናቴዎስ ተሹመው 2ኛው የኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ‹‹አቡነ ሰላማ ካልዕ›› ተብለው ተሾመው ወደ አገራችን መጡ፡፡ ከመሾማቸው በፊት አባቶቻችን አቡነ አትናቴዎስን ‹‹ጳጳስ ይላኩልን›› ብለው መልእክት ሲልኩባቸው አቡነ አትናቴዎስም ወደ አስቄጥስ ገዳም በመሄድ #እግዚአብሔርን በጸሎት ቢጠይቁት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴን ላክላቸው›› አላቸው፡፡ መነኮሳቱም ሁሉ እንዲሁ አሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ሲሾሙ ሚካኤልና ገብርኤል በወርቅ ወንበር ላይ አስቀምጠዋቸው ‹‹ይገባዋል ይገባዋል›› ብለው ቅብአ ክህነት ቀብተዋቸዋል (ጵጵስና ሾመዋቸዋል፡፡) አቡነ ሙሴም ከተሾሙ በኋላ 14000 መነኮሳትን አስከትለው ወደ ቅድስት አገራችን መጡ፡፡ አቡነ ሙሴ ንግሥናቸውን ትተው ወደ ኢትዮጵያ መተው 16 ፍልፍል ቤተመቅደሶችን የሠሩ ሲሆን 8ቱ የተሰወሩ ናቸው፡፡

በገዳማቸው በቅድስቱ ውስጥ ጥልቀቱ የማይታወቅ እጅግ ጥልቅ የሆነ ጉድጓድ አለ፡፡ በውስጡም ስውራኑ አብያተ ክርስቲያናት ይገኙበታል፡፡ ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተቀረጸውና ፍልፍል የሆነው የገዳማቸው የቤተልሔሙ ስፋት ሜትር ከሃያ ሲሆን ጣራው እንደ አቡነ አሮን ክፍት ሆኖ ሳለ ዝናብ ግን አይገባበትም፡፡ ዝናብ የማያስገባው የቀዳዳው ስፋት አንድ ሜትር በአንድ ሜትር ነው፡፡ ጻድቁ በሀገራችንም ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ብዙ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽና ወንጌልን በማስተማር ብዙ ደክመዋል፡፡ በተለይም በዋናነት የሚታወቁት በሰሜን ወሎ አውራጃ ወልድያ ወረዳ መቄት ልዩ ቦታው ገረገራ የሚገኘው ‹‹አዲስ አንባ ዋሻ መድኃኔዓለም›› እና መጀመሪያ እንደመጡ ያረፉባት ‹‹ድባ ማርያም›› ይጠቀሳሉ፡፡

ይህችውም ድባ ማርያም ገዳም ታላቁ አባት አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የመነኮሱባት ናት፡፡ ጻድቁ አቡነ ሙሴ መስከረም 4 ቀን ጌታችን ቃልኪዳን ሲገባላቸው እነዚህን ሁለት ገዳማቸውን ‹‹እንደ አስቄጥስ ገዳም እንደ አቡነ እንጦንስ ማኅበር ይሁኑልህ›› ብሏቸዋል፡፡ በገዳማቸው ከሚኖሩት ቅዱሳን ውስጥ 400 ወንዶች መነኮሳትና 200 ሴቶች መነኮሳያት እንደተሰወሩ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡

ጻድቁ ሌላው ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ገና በእናቷ ማኅፀን ሳትፀነስ የቅድስት አርሴማን ጽላት ያሠሩላት መሆናቸው ነው፡፡ ቁመቱ 2 ሜትር ከ70 የሆነ ግሩም ቤተ መቅደስም ፈልፍለው አንጸውላታል፡፡ #ጌታችንም የሰማዕቷን ጽናትና ረድኤት ከቦታው እንደማይለይባቸው ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ በቃል ኪዳናቸው የታመኑትን ልጆቻቸውን መተትና መርዝ አይጎዳቸውም፡፡ ይህም #ጌታችን የሰጣቸው ልዩ ቃልኪዳናቸው ነው፡፡ ጻድቁ እንደ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ 12 ክንፍ የተሰጣቸው ታላቅ የምሕረት አባት ናቸው፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ ሙሴ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ነቢይ_ኢያሱ_ወልደ_ነዌ

ኢያሱ ማለት የቃሉ ትርጉም መድኃኒት ማለት ነው፡፡ ኢያሱ መባሉ ስለሁለት ነገር ነው አሜሊቃዊያን ድል አድርጎ እስራኤልን ምድረ ርስት እንዲወርሱ አድርጎልና ሁለተኛው ኢያሱ ለ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ምሳሌ እንዲሆን አስቀድሞ #ጌታ ያውቃልና ይህም ኢያሱ አሕዛብን ድል አድርጎ ምድረ ርስት እንዳስገባቸው የሁላችን #ጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ዲያቢሎስን ድል አድርጎ መንግስቱን አውርሶናልና ኢያሱ በ #ጌታችን ይመሰላል፡፡

ኢያሱ ነቢይ የተወለደው በምድረ ግብጽ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ አውሴ ይባላል:: ዘመኑ #‎እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሙሴ ነቢይ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር። ሕዝቡ ልበ ደንዳና አልታዘዝ ባይ ነበርና ለአርባ ቀናት ብቻ የታሠበላቸውን መንገድ አርባ ዓመታት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምህሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም::

ሊቀ ነቢያት ሙሴ ‎ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን ካህናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: በዚህ ወቅትም እድሜው ሠማንያ ዓመት ነበር፡፡ #እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሾመው፡፡ ሕዝቡንም በትጋት ያገለግል ነበር፡፡ በድንቅ ተዓምራት ዮርዳኖስን ከፍሎ አሻገረ የኢያሪኮን ቅጥር አፈረሰ ጠላቶቹን ድል ነስቶ ምድረ ርስት ከነአንን በ #እግዚአብሔር በኢያሱ መሪነት እንድወርሱ አድርጎል፡፡

ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን በተወለደ በ120 ዓመቱ መስከረም 3 ቀን በእዚች ዕለት በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለሠላሳ ቀናት አለቀሱለት::
#በዓለ_ስዕለ_አድኅኖ

፩- የቅዱሳት ሥዕላት ትርጉም፤

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት እና ትውፊት ቅዱሳት ሥዕላት ማለት፤ በአብያተ ክርስቲያናት ግድግዳ፡ በሸራ፡ በብራና፡ በወረቀት እና በመስቀሎች ላይ በቀለም ወይም በጭረት ባለ ሁለት ጎን ሆነው የሚሠሩ የልዑል #እግዚአብሔርን#የእመቤታችንን፡ የቅዱሳን መላዕክትን፡ የጻድቃንን እና የሰማዕታትን ማንነት የሚገልጥ መንፈሳዊ ጥበብ ነው። ሥጋዊውን ዓለም ከሚያንጸባርቁ መንፈሳዊ መልዕክት ከሌላቸው ሌሎች ሥዕላት ፈጽመው ስለሚለዩ ቅዱሳን ሥዕላት ይባላሉ።

፪- የቅዱሳት ሥዕላት አመጣጥ፤

፪-፩ በብሉይ ኪዳን

ሥዕል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለያዘው ቦታ መሠረቱ የሁሉ አስገኝ የሆነው አምላካችን #እግዚአብሔር አስቀድሞ ለነቢዩ ሙሴ ሥዕለ ኪሩብን በሥርየት መክደኛው ታቦት ላይ እንዲያዘጋጅ ማዘዙ ነው። ለዚህም መሠረት በዘጸ. ም. ፳፭፡ቁ ፳፪ “በዚያም ካንተ ጋር እገናኛለሁ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ አነጋግርሃለሁ” ብሎ መናገሩ ነው። #እግዚአብሔርም የተናገረውን የማያስቀር ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴን በሥዕለ ኪሩብ መካከል ሆኖ ድምጹን አሰምቶታል።

፪-፪ በሐዲስ ኪዳን

ከሐዋርያዊ ተልዕኮውና የሕክምና ሞያው በተጨማሪ የሥዕል ጠቢብ የነበረው ቅዱስ ሉቃስም ምስለ ፍቁር ወልዳን (እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ጋር ሆና) በመሳል ለትውልድ አቆይቶልናል። በተጨማሪም ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ለጢባርዮስ ቄሳር የ #ጌታችንን ሥነ-ስቅለት ሥዕል አዘጋጅቶ ሰጥቶታል።

፫- ቅዱሳት ሥዕላት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷ የሆነ ፊደል፡ ሥነ ጽሁፍ፡ ዜማ፡ ኪነ ህንፃ… ወዘተ እንዳሏት ሁሉ የራሷ የሆነ የሥነ ሥዕል ጥበብም ያላት ስንዱ እመቤት ናት። ከጥንተ ክርስትና የአክሱማውያን ዘመን ጀምሮ ሥዕል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቦታ እንደነበረው የአርኪዮሎጂ ግኝቶችና የጥንት አብያተ ክርሰቲያናት ፍርስራሾች ያመለክታሉ። በተለይ በዘመነ አክሱም ተሠርተው በከፊል የፈረሱ እና ከመፍረስ የተረፉ እንደ አብርሃ ወአጽብሐ፡ ውቅሮ ቅዱስ ቂርቆስ፡ ደብረ ዳሞ ገዳም፡ መርጡለ ማርያም፡ ወዘተ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት የያዟቸው
ሥዕሎች የዘመኑን የሥዕል ጥበብ አሻራ ያሳያሉ። በተለይ በመካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሥዕል ጥበብ ያደገበት ዘመን ነበር። በአሁኑ ወቅት በአብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት የምናገኛቸው ሥዕላት በዚህ ዘመን የተሠሩ ናቸው።

፬- የቅዱሳት ሥዕላት ጥቅም፡

፬-፩ ለሥርዓተ አምልኮ

ቅዱሳት ሥዕላት ሰውንና #እግዚአብሔርን የሚያገናኙ መንፈሳዊ ሀብቶች ናቸው። በሥዕል ፊት ቆሞ መጸለይ፡ ወይንም መስገድ ሥዕሉን አምላክ ማድረግ አይደለም። ነገር ግን የሥዕሉን ባለቤት በሥዕሉ ፊት ሆኖ በመማጸን በረከቱን ለማግኘት የሚፈጸም ሥርዓት ነው። ሥዕሉ ለባለቤቱ መታሰቢያ ነው። “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ተብሎ እንደተጻፈ” ምሳ. ፲፡፯ የሥዕሉን ባለቤት አቅርቦ ያሳየናል። ገድሉን፣ ተአምራቱንና ቃል ኪዳኑን ያስታውሰናል። በመንፈስም ድልድይ ሆኖ ከሥዕሉ ባለቤት ያገናኘናል።

ሙሴና አሮን ወደ ደብተራ ኦሪት ገብተው በታቦቱና ሥዕለ ኪሩብ ፊት እየሰገዱ ከ #እግዚአብሔር ትዕዛዝ ይቀበሉ ነበር ዘኁ. ፲፮፡፵፭

፬-፪ ለትምህርት

ቅዱሳት ሥዕላት ሲሣሉ የሥዕሉን ባለቤት ዐቢይ ገድልና ተአምራት በሚያጎላ መልኩ ነው። ስለሆነም ማንኛውም ምእመን የሥዕሉን ባለቤት መንፈሳዊ ተጋድሎ በቀላሉ እንዲረዳ ያደርገዋል። ለምሳሌ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥዕል ሲሣል ለ22 ዓመታት 8 ጦሮችን ከግራ ከቀኝ ከፊት ከኋላ አስተክለው ሲጸልዩ አንድ እግራቸው በቁመት ብዛት መቆረጡን እንዲሁም ስለ ቅድስናቸው ከተሰጣቸው ስድስት የብርሃን ክንፎች ጋር ተደርጎ ይሣላል። ክህነታቸውን ለመግለጽም የእርፍ መስቀልና ጽና ይዘው ይሣላል። የሥዕሉ ባለቤት እንዲታወቅም በሥዕሉ ላይ አጭር የጽሑፍ መግለጫ ይቀመጣል። ”ዘከመ ጸለየ አቡነ ተክለሃይማኖት” እንዲል። በዚህ ሥዕል ምእመናን የጻድቁን ተጋድሎ ይማሩበታል፤ አርአያም ያደርጉታል።

እንግዲህ ቅዱሳት ሥዕላት ይህን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡን ከሆነ በጥንቃቄ በመያዝ መገልገል እንደሚገባና ዘወትር በጸሎት ሰዓት ከፊት ለፊታችን በማስቀመጥ ልንጸልይ እንደሚገባ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
ወደ ቍስጥንጥንያ አገርም በደረሰች ጊዜ ያቺ ሴት ወደ ንጉሡ ሒዳ የቅዱስ እስጢፋኖስን ዜና ከእርሱ የሆኑትን ተአምራት ወደ ቍስጥንጥንያ አገር ወደብም እንደ ደረሰ ነገረችው ሰምቶም እጅግ ደስ አለው ንጉሡም ከሊቀ ጳጳሳቱና ከካህናቱ ከብዙ ሕዝቦችም ጋር ወጣ ከወደቡም በክብር አንሥተው ወደ መንግሥት አዳራሽ እስከ አስገቡት ድረስ በፍጹም ደስታ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተሸክመውት ተጓዙ።

ክብር ይግባውና #ጌታችን_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ከእርሱ ተአምራትን ገለጠ በሠረገላ ሥጋውን ጭነው በሁለት በቅሎዎች በሚስቡት ጊዜ ቍስጣንጢንዮስ ከሚሉት ቦታም ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስንም ሥጋ በዚያ እንዲያኖሩ ስለ ፈቀደ የሚስቡት በቅሎዎች ቆሙ። አልተንቀሳቀሱም በቅሎዎችንም ይመቷቸው ጀመሩ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ ይገባል የሚል ቃል ከአንዱ በቅሎ ሰሙ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉም አደነቁ።

#እግዚአብሔርንም አመሰገኑት የበለዓምንም አህያ ያናገራት እርሱ እነዚህን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከሙትን በቅሎዎች ያናገራቸው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ንጉሡም በዚያ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ይህን የከበረና ንጹሕ የሆነ ዕንቈ ባሕርይ በውስጧ እንዲያኖሩ አዘዘ። ይኸውም ለተመሰገነና ለተባረከ ሐዋርያ የዲያቆናት አለቃና የሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው ነው።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በ ሐዋርያና ሰማዕት በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

#የቀዳሜ_ሰማዕት_ቅዱስ_እስጢፋኖስ
በዓለ ሲመቱ(የተሾመበት) ጥቅምት ፲፯ ቀን
በዓለ ዕረፍቱ ጥር ፩ ቀን
በዓለ ፍልሰቱ መስከረም ፲፭ ቀን ነው ።

ከስንክሳር የተገኘ መረጃ

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ገብረ_ማርያም_ዘደብረ_ሐንታ

ጻድቁ አቡነ ገብረ ማርያም ምግባር ሃይማኖታቸው ከቀና፣ ትሩፋት ተጋድሎአቸው ከሰመረ ደጋግ ወላጆቻቸው ከአባታቸው ኒቆዲሞስ እናታቸው አመተ ማርያም በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት ኅዳር 24 ቀን ተወለዱ፡፡ ዕደሜአቸው ለትምህርት ሲደር እነዚህ ደጋግ ወላጆቻቸው ፈሪሃ #እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ አሳደጓቸው፡፡

አባታችን በልጅነታቸው የወላጆቻቸውን ላሞች እየጠበቁ ሳለ ከእለታት አንድ ቀን #ጌታችን በወጣት አምሳል ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ለምን እንስሳትን ትጠብቃለህ ደቀ መዝሙሬ ጴጥሮስን ዓሣ ማጥመድን ትተህ ተከተለኝ እንዳልኹት በእንስሳት ፈንታ ሰውን ትጠብቅ ዘንድ …››› አላቸው፡፡ አባታችንም ይህንን በልቡናቸው ሲያወጡ ሲያወርዱ ለ2ኛ ጊዜ #ጌታችን በሚያስፈራ ግርማ በእርሻ መካከል ተገለጠላቸው፡፡ ስለዚህም ነገር አባታችን ሲናገሩ ‹‹ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በወጣት አምሳል ሁለት ሰዎች ከእኔ ጋር ሳሉ በእርሻ መካከል ወደ እኔ መጣ፤ እነዚያም ከእኔ ጋር የነበሩት ሁለት ሰዎች ባዩት ጊዜ እጅግ ደንግጠው ከግርማው የተነሣ ወዲያና ወዲህ ወደቁ፡፡ በኋላም ተነሥተው ያዩትን መሰከሩ፡፡

ዳግመኛም በሦስተኛ መምጣት #ጌታችን እንዲህ አለኝ፡- ‹ለምን ዘገየህ አብርሃምን ለአባቱ ርስት ለይቼ ያወጣሁት እኔ እንደሆንኹ አላወቅህምን? አለኝ፡፡" ከዚህም በኋላ አባታችን "እናት አባቱን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም" (ማቴ 10፥37) የሚለውን የ #ጌታችንን አምላካዊ ቃል ሰምተው ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ወጥተው በመሄድ ቀበት በምትባል ቦታ በዓት ሠርተው በጾም በጸሎት እየታደሉ መኖር ጀመሩ፡፡ በዚህም ጊዜ #እግዚአብሔር ያገለግላቸው ዘንድ አንዱን ነብር አዘዘላቸው፡፡ ሰዎችም ከአባታችን በረከትን ለመቀበል ወደ እርሳቸው ይመጡ ነበርና ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አንድ ምእመን ወደ አባታችን በመጣ ጊዜ አባታችንን የሚያገለግላቸው ነብር ሰውየውን ዘሎ ያዘው፡፡ ሰውየውም ‹‹አባታችን አድኑኝ›› እያለ ሲጮኽ አቡነ ገብረ ማርያም ከበዓታቸው ወጥተው ነብሩን በመስቀላቸው ቢባርኩት ኃይሉ ደክሞና ለቃላቸው ታዝዞ ሰውየውን ለቀቀው፡፡ አባታችንም ያንን ወጣት ያየውን ነገር ለማንም እንዳይነግር አዘዙት፡፡ አቡነ ገብረ ማርያም እንደ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ 40 ቀንና 40 ሌሊት እህል ሳይበሉ ውኃ ሳይጠጡ እየጾሙ ወንጌላትን ያነቡ ነበር፡፡ ከመጾማቸውም ብዛት ሰውነታቸው ፍጹም በደከመና አንደበታቸውም መናገር በተሳናቸው ሰዓት የብርሃን እናቱ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም ተገልጻላቸው ‹‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ይህን ያህል ገድል የምትጋደል ሰውነትህንስ የምትታስጨንቃት ለምንድነው?›› በማለት አጸናቻቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ረሀብና ጥሙ ጠፋላቸው፡፡

በአንደኛውም ቀን ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል ወደ አባታችን መጣ፡- ‹‹ገብረ ማርያም ሆይ በተክለ ሃይማኖት ወንበር ከተሾመ ከመርሐ ክርስቶስ እጅ የመላእክትን አስኬማ ትቀበል ዘንድ ወደ እርሱ ሂድ›› አላቸው፡፡ አባታችንም ወደ ደብረ ሊባኖስ ከመሄዳቸው በፊት አቡነ መርሐ ክርስቶስ በደብረ ሊባኖስ ሆኖ ይህን በ #መንፈስ_ቅዱስ መሪነት ዐውቆ ለደቀ መዛሙርቱ ‹‹እነሆ ከፀሐይ ይበልጥ የሚያበሩ ሦስት ከዋክብት ቅዱሳን ይመጣሉ›› አላቸው፡፡ አቡነ መርሐ ክርስቶስም እንደተናገረው እነ አቡነ ገብረ ማርያም ደብረ ሊባኖስ ደረሱ፡፡ አቡነ መርሐ ክርስቶስም የምንኩስናን ልብስ አለበሳቸው፡፡

አቡነ ገብረ ማርያም ከመነኮሱ በኋላ ወደ በዓታቸው ተመልሰው ከበፊቱ ይልቅ በጾም በጸሎት ሲተጉ #ጌታችን አሁንም ተገለጠላቸውና ‹‹በጾም በጸሎት ብቻ ተወስነህ አትቀመጥ ሂድና ወንጌልን አስተምር፣ ድውያንን ፈውስ፣ ሙታንን አንሣ…›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ዳግመኛም በከበረ እስትንፋሱ እፍ አለባቸውና ‹‹መንፈስ ቅዱስን ተቀበል፤ ይቅር ያልካቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል፣ ይቅር ያላልካቸው ኃጢአታቸው አይቀርላቸውም፡፡ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ በምድር ያሰርከው በሰማያት የታሰረ ነው፤ በምድርም የፈታኸው በሰማያት የተፈታ ይሁን›› አላቸው፡፡ #ጌታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ‹‹ካህናት በሊቃነ ጳጳሳት አፍ ይሾማሉ አንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ አፍ ተሾምህ›› እንዳላቸውና እንደሾማቸው ሁሉ አሁንም አባታችን አቡነ ገብረ ማርያምን እንዲሁ ብሎ ራሱ ሾማቸው፡፡ አባታችንም እንደታዘዙት ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረጉ ድውያንን እየፈወሱ ሙታንን እያስነሡ ወንጌልን ዞረው አስተማሩ፡፡ ቂሐ ወደምትባል ምድር ገብተው ጎሽ ወደምትባለው ሀገርም ደርሰው ጣዖታትን የሚያመልኩትን የሀገሪቱን ሰዎች አገኟቸው፡፡ ሰዎቹም የሚያመልኩትን ትልቅ ዘንዶ በመስቀሉ ባርኮ ከገደለው በኋላ በውስጧ ወንጌልን እያስተማረ ድውያንን እየፈወሰ ሲቆይ ሰዎቹም አባታችንን ‹‹ቅዳሴ ቀድስልን›› አሉት፡፡ አባታችንም ስለዚህ ነገር #ጌታችንን በጸሎት በጠየቁት ሰዓት "ሳትናዘዛቸውና ሳታጠምቃቸው አትቀድስላቸው" የሚል ቃል ከሰማይ ወደ አባታችን መጣ፡፡ ያንጊዜም ሰዎቹን ሁሉ ሰብስቦ በ #አብ#ወልደ#መንፈስ_ቅዱስ ስም አጠመቃቸውና ቅዳሴ ቀድሶ አቆረባቸው፡፡
#እመቤታችን ልጇን ይዛ ወደ ግብጽ ከዚያም ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስትሰደድ በእግሯ እየሄደች በሞረት ዋሻ በአቡነ ዜና ማርቆስ ቦታ ግራርያ ከሚባል ቦታ ተቀምጣ እንደነበር የሐምሌው ድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ይናገራል፡፡ በኋላም ተጭነው ከእነ ልጇ በዚህ በአቡነ ገብረ ማርያም ገዳም በሆነ ቦታ ስታልፍ #ጌታችን ለቅድስት እናቱ ‹‹ይህች ቦታ ሐንታ ትባላለች፣ በኋለኛው ዘመን በስምሽ የሚጠራ የእኔ ወዳጅና ታዛዥ የሆነ የታላቅ ጻድቅ ቦታ ትሆናለች›› ብሎ ስለነገራት በኋላም ትንቢቱ ደርሶ ጻድቁ ገዳማቸውን በዚሁ ቦታ ስለገደሙት ገዳሙ ‹‹አማን ደብረ ሐንታ›› ይባላል፡፡ ጻድቁ በመንዝና በመርሐ ቤቴ ከ1245-1268 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ19 በላይ የተላያዩ አብያተ ክርስቲያናትን ተክለዋል፡፡ ጾም ጸሎተኛ ባሕታዊ ከመሆናቸው በተጨማሪ የወንጌል ገበሬ፣ ጻድቅና ደራሲም ናቸው፡፡

አቡነ ገብረ ማርያም በጣም ከሚታወቁበት ድርሰታቸው አንዱ የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት ከታላቁ ሊቅ ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰቱን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር በአንድነት አግልግለዋል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡

በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አቡነ ጽጌ ድንግል ከገዳማቸው ከደብረ ብሥራት ተነሥተው ወደ ደብረ ሐንታ ሄደው እንዲሁ እንደ አቡነ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አግልግሎ ይመለሳል፡፡ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን እንደዚህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ ሌላኛው ገዳም እየሄዱ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና አብረው ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡

ይኸውም በራሳቸው በአቡነ ገብረ ማርያም ገድል ላይ እና በአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ገጽ 72-73 ላይ በሰፊው ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ የሁለቱ ድርሰታቸው የሆነው ‹‹ማኅሌተ ጽጌ›› ድርሰት የ #እመቤታችንንና የልጇን የ #ጌታችንን ሥጋዊ ስደት የሚገልጽ ሲሆን በተጨማሪም ስደት የማይገባው #አምላካችን_ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ አህጉራችን አፍሪካ ተሰዶ የሠራቸውን ድንቅ ድንቅ ተአምራትና የ #እመቤታችንን ንጽሕናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷን የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

አቡነ ገብረ ማርያም አዲስ አፍልሰው በሠሯት ቤተ ክርስያን ውስጥ ልጆቻቸው ተሰበሰቡና ‹‹አባታችን ሆይ የት እናድራለን? ማረፊያን ያዘጋጅልን ዘንድ #እግዚብሔርን ለምነው›› አሉት፡፡ አባታችንም ‹‹ይህ ሥራ ለእኔ አይቻለኝምና እናንተ ለምኑት›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹አባታችን ሆይ አትበትነን›› ብለው ግድ አሉት፡፡ ልጆቹም ግድ ባሉት ጊዜ አባታችን ተነሥቶ ጸለየ፡፡ ስለዚህም ነገር ሲናገር አባታችን እንዲህ አለ፡- ‹‹ከዚህ ነገር አስቀድሞ በቁርባን ጊዜ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ይመጣና ይባርከኝ ነበር፣ እናቱ #ድንግል_ማርያምም ትባርከኝ ነበር፡፡ ስለዚህ ነገር ግን #ጌታችን ተቆጣ፣ እምቢ አለኝ፡፡ ከእኔም ፊቱን መለሰ፡፡ እኔም ብዙ አለቀስኹ የእጁን ቡራኬ አጥቻለሁና፡፡ እናቱ #ድንግል_ማርያምም ፈጽሜ ሳለቅስ ባየችኝ ጊዜ ‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ለምን ታለቅሳለህ?› አለችኝ፡፡ እኔም #እመቤቴ_ሆይ #ጌታዬና_አምላኬ ፊቱን ከእኔ መልሷልና ስለዚህ አለቅሳለሁ አልኳት፡፡ #እመቤታችን_ማርያምም የተወደደ ልጇን ‹ልጄ ሆይ ወዳጅህ ገብረ ማርያምን በምን ሥራ አሳዘነህ?› አለችው፡፡ #ጌታችንም#ድንግል እናቱ ‹እርሱ አሳዝኖኛል፣ የዮሴፍ ልጅ ያዕቆብ ‹ይህን ዓለም የሚወድ የ #እግዚአብሔር ጠላት ይሆናል› (ያዕ 4፡4) እንዳለ ከእኔ ፍቅር ይልቅ የዓለምን ፍቅር ወዷልና› አላት፡፡› እናቱ #እመቤታችንም የተወደደ ልጇን ‹ልጄ ሆይ ወዳጅህ ገብረ ማርያምን አታሳዝነው ይቅር በለው ባጠባሁህ ጡቶቼ አምልሃለሁ› አለችው፡፡ #ጌታችንም ይህን ጊዜ ቅድስት እናቱን ‹የላይኛውን ወይም የታችኛውን ይወድ እንደሆነ ጠይቂው› አላት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ከዚያ ቆሞ ነበርና ወዲያው ለእኔ ‹የላይኛው ያለህ መንግሥተ ሰማያትን ነው፣ የታችኛው ያለህ ይህች ዓለም ናት› አለኝ፡፡ እኔም ያንጊዜ ይህችን ዓለም አልፈልጋትም ነገር ግን ማረፊያ እንዲሰጠን በጸሎቴ የጠየቁት ልጆቼ ከሞቴ በኋላ ተስፋ እንዳይቆርጡ እንዳይበተኑም ብዬ ነው አለኩት፡፡ #ጌታችንም ‹‹ገብረ ማርያም ሆይ ለምን ይህንን ታስባለህ? ለልጆችህ እኔ አስብላቸዋለሁና፡፡ ወዳጄ ዳዊት ‹የጻድቃን ልጆች ይባረካሉ፣ ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፣ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል› (መዝ 111፡33) ብሎ እንደተናገረ እኔ ለፍጥረት ወገን ሁሉ አስባለሁ› አለኝ፡፡ ይህንንም ብሎኝ ሰላሙን ሰጥቶኝ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡››

አቡነ ገብረ ማርያም ያደረጓቸው ተአምራት ተነግረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ በብቸኝነት ሳለ በአንዲት አገር የሚኖር ልጁ የሞተበት ሰው የልጁን አስክሬን ወደ አባታችን አምጥቶ በፊታቸው አስቀመጠውና ‹‹አባታችን ሆይ ልጄ እንደሞተ ተስፋዬ ሁሉ ጠፍቷልና አሁን ብትወድ ከሞት አንሣው ባትወድ ግን እዚሁ ቅበረው›› እያለ አለቀሰባቸው፡፡ አባታችንም የሰውየውን ሁኔታውን አይተው ፈጽመው አለቀሱ፡፡ ልቡናቸውም ታወከባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ይጸልዩ ዘንድ ተነሡና ‹‹…በተቀበረ በ4ኛው ቀን አልዓዘርን ያስነሣኸው አሁንም ይህን ሕፃን አስነሣው…›› ብለው ከጸለዩ በኋላ የልጁን እጅ ይዘው ‹‹በ #ጌታችን_በአምላካችን_በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይል ተነሥ›› ብለው እፍ አሉበት፡፡ ያንጊዜም ሕፃኑ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ አፈፍ ብሎ ተነሣ፡፡ ለአባቱም ‹‹ልጅህን ውሰድ ፈጣሪዬ አስነሣልህ›› ብለው ሰጡት፡፡ ሰውዬውም ከእግራቸው ሥር ሰግዶ የእግራቸውን ትቢያና ሰውነታቸውን ሁሉ ሳመው፡፡ ልጁንም ይዞ ፈጽሞ ደስ እያለው ወደ ቤቱ ሄደ፡፡

በአንዲት ሀገርም አንድ ልጅ ብቻ ያላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ልጁም ወደ አባታችን እየመጣ ‹‹አመንኩሱኝ›› እያለ ሁልጊዜ ይጠቃቸው ነበር፡፡ አንድ ቀንም እንዲሁ መጣና ‹‹አባት ሆይ ካላመነኮሱኝ ወደሌላ ሰው ዘንድ ሄጄ እመነኩሳለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ፈቃደ #እግዚአብሔርን ጠይቀው የፍላጎቱን ፈጸሙለትና አመነኮሱት፡፡ ወላጅ እናቱም መጥታ ልጇ የምንኩስናን ልብስ እንደለበሰ ባየች ጊዜ እያለቀሰች ሄደችና ራሷን ወደ ገደል ውስጥ ጨመረች፣ ሞተችም፡፡ ሰዎችም ተሰብስበው አለቀሱላትና አስክሬኗን ተሸከመው ይቀብሯት ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዷት፡፡ ሰዎችም ወደ አባታችን መጥተው ‹‹ሴትዮዋ ከመቀበሯ በፊት መጥተው ይዩዋት›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ወደ አስክሬኗ አልመለከትም›› አሉ፡፡ እነርሱም በ #እግዚአብሔር ስም ባማሏቸው ጊዜ አባታችን አስክሬኗ ወዳለበት መጡና አዩዋት፡፡ በማግሥቱም ከገነዟት በኋላ አባታችን ከመዝገበ ጸበላቸው
በአፏና በጆሮዎቿ ጸበልን ጨመሩባት፡፡ በፊቷም ‹‹እፍ›› አሉባትና ‹‹በ #ጌታዬ_በፈጣሪዬ_በኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይል ተነሺ›› አሏት፡፡ ያንጊዜም አፈፍ ብላ ከሞት ተነሣች፡፡ አባታችን ከሞት ያስነሷቸው ሰዎች እንዲሁ በጣም ብዙ ናቸው፡፡

27 ዓመት ሙሉ ሆዱን የታመመ አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ አቡነ ገብረ ማርያም በመምጣት ጉዳዩን ሳይነግራቸው አንድ ቀን ቆየ፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን የመጣበትን ጉዳዩን በጠየቁት ጊዜ ‹‹አባት ሆይ ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ ታመምኩ፣ እህል አልበላም ውኃም አልጠጣም›› አላቸው፡፡ አባታችንም ሆዱን ይዘው በእጃቸው አሻሹትና ምራቃቸውን ቀቡት፡፡ በዚህም ጊዜ በሆዱ ውስጥ ልዩ ልዩ ዓይነት ድምፆች ተሰሙ፡፡ በውሻ ድንፅ አምሳል፣ በድመት ድንፅ አምሳል፣ በዝንጀሮ ድንፅ አምሳልና በቁራዎቸ ድንፅ አምሳል ጮኸ፡፡ አባታችንም ልጁን ‹‹ልጄ ሆይ #እግዚብሔር አድኖሃልና ወደ ቤትህ ተመለስ›› አሉት፡፡ ልጁም ‹‹አባቴ ሆይ ተመልሼ ወደቤቴ አልገባም እስከ ዕለቴ ሞቴ ድረስ አልመለስም ከአንተም አልለይም›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹በዚህ መኖር ክፍልህ አይደለምና #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለፈወሰህ ወደ ቤትህ ተመለስ›› አሉት፡፡ በደስታም ወደ ቤቱ ሄደና በሌላ ጊዜ ከብዙ ሰዎች ጋር መጥቶ አባታችን ያደረጉለትን ተአምር ለሕዝቡ ሁሉ መሰከረ፡፡

አቡነ ገብረ ማርያም በእንዲህ ዓይነት አገልግሎት በተአምራታቸው ድውያንን እየፈወሱ ሙታንን እያስነሡ በወንጌል ቃል የነፍስን ቁስል እየፈወሱ የ #ጌታችንንም መከራውን እያሰቡ ራሳቸውን ከመከራው ተሳታፊ በመሆን ብዙ ከደከሙ በኋላ በሥጋ ሞት ከማረፋቸው በፊት ቅዱሳን መላእክት ነጥቀው ገነትንና ሲኦልን አሳይተዋቸዋል፡፡ #ጌታችንም በመጨረሻ ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ከፍጹም ድካምና መታከት ከኃዘንም ታርፍ ዘንድ ወደ ፍጹም ደስታና ወደ ዘላለማዊ ዕረፍት ወደ እኔ ና›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹ #ጌታዬ ሆይ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ?›› ቢሉት #ጌታችም ብዙ አስደናቂ ቃልኪዳኖችን ሰጣቸው፡፡ ‹‹እንደፈጠርኩህ አግኝቼሃለሁና ክብርህ እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ይሁንልህ›› አላቸውና በቅዱሳን እጆቹ ዳስሷቸው ቢስማቸው ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለይታለች።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ በአቡነ ገብረ ማርያም እና አቡነ ጽጌ ድንግል ጸሎት ይማረን በረከታቸውም በእኛ ላይ ይደርብ ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ጴጥሮስ_ዘሃገረ_ጠራው

በዚችም ቀን ደግሞ ጠራው ከሚባል አገር ለከበረ ጻድቅ አባት አባ ጴጥሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ቅዱስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ለ #እግዚአብሔር የተሰጠ የስእለት ልጅ ነው። በአደገም ጊዜ ለታላቅ ተጋድሎ ክልቡ በቆራጥነት ተነሣ በቀንና በሌሊትም በጾም በጸሎት ተወስኖ ሁል ጊዜ #እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሆነ። ሰው የሚመገበውንም ምንም አይመገብም በዱር ያገኘውን ጥቂት ሣርን ይመገባል እንጂ።

ደገኛው ምግቡ ግን ክብር ይግባውና የ #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ስም ማመስገን ነው። በዚህም ምግባቸው የ #እግዚአብሔር ምስጋና የሆነ ቅዱሳን መላእክትን መሰላቸው።

አሎን በሚባል የወንዝ ውኃ ላይም ይመላለስ ዘንድ ተገባው እግሮቹም አይርሱም ሥጋ እንደ ሌለው መንፈስ እስከ ሚሆን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከችግር ብዛትና ከሚለብሰው የብረት ልብስ ክብደት የተነሣ ሥጋው እጅግ ደርቆ የረቀቀም ሁኖ ነበርና በእንዲህ ያለ ተጋድሎም #እግዚአብሔርን ከአገለገለው በኋላ ወደርሱ ሔደ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_15 እና #ከገድላት_አንደበት)
ከዚህም በኋላ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩ ጀመሩ ምሰሶዎችንም በፈለጉ ጊዜ አላገኙም በዚያም አከባቢ ታላቅ የጣዖት ቤት ነበረ በውስጡም ያማሩ ምሰሶዎች አሉ። ድንግሊቱ ታኦግንስጣም ክብር ይግባውና #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ብዙ በማልቀስ ለመነች ያን ጊዜም እሊያ ምሰሶዎች ከጣዖት ቤት ፈልሰው ሐናፂዎች ከሚሹት ቦታ በቤተ ክርስቲያን መካከል ተተከሉ አማንያን ሁሉ ክብር ይግባውና #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን አመሰገኑት ጣዖትን ሲያመልኩ የነበሩም ጣዖቶቻቸውን ሰብረው ክብር ይግባውና ወደ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሃይማኖት ተመልሰው ገቡ በዚያችም አገር ታላቅ ደስታ ሆነ።

ቅድስት ድንግል ታኦግንስጣም ተጋድሎዋን ከፈጸመች በኋላ #እግዚአብሔርንም አገልግላ ደስ አሰኝታ በዚያ ገዳም በደናግሉ መካከል በሰላም በፍቅር አረፈች።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስቷ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባት_ዲዮናስዮስ

በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዲዮናስዮስ አረፈ። ይህንንም ቅዱስ ንጉሥ ዳኬዎስ ሊገድለው ፈልጎት ነበር ግን #እግዚአብሔር ሠወረው ይህም አባት ብልህ አዋቂ ስለነበረ ብዙዎች የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ተረጎመ።

በዘመኑም በሮም ንጉሥ በከሀዲ ዳኬዎስ እጅ ቅዱስ መርቆሬዎስ በሰማዕትነት አረፈ። ሁለተኛም ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት አንቀላፍተው ነቁ እሊህም ለጣዖታት ሊአሰግዳቸው በፈለጋቸው ጊዜ ከዳኬዎስ ፊት የሸሹ ከኤፌሶን አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን የሆኑ ናቸው።

ዳግመኛም በዘመኑ የመነኰሳት አለቃ ገዳማትን የሠራ ግብጻዊው ታላቁ እንጦንዮስ ለመጀመሪያ ጊዜ መነኰስን ሆነ። ይህም ቅዱስ ዲዮናስዮስ በሊቀ ጵጵስናው ሹመት ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ። መንጋዎቹንም በትክክል በፍቅር አንድነት ጠበቃቸው #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

#መስቀሉ ላዳነን ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_17)
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና #እግዚአብሔር አብዲን ወደሚባል ገዳም እንዲሔድ ሊቅ ያዕቆብን አዘዘው ። እርሱም ለልጆቹ መነኰሳት ይህን ነገራቸው ከዚያም ግንብ ውስጥ እንዲኖሩ አማፀናቸው ።

እርሱ ግን ብቻውን ወደ ኢያሪኮ ባሕር ዳርቻ ሔደ መርከብንም በአጣ ጊዜ በባሕሩ ሞገድ ላይ ባረከ ገብቶም ወደ ተርሴስ አገር እስከ ገባ ድረስ በባሕሩ ላይ እንደ ደረቅ ምድር ሔደበት ።

በሀገሩ ጥጋጥግ አልፎ ሲሔድ በትል የተከበበ ቁስለኛ ሰው አገኘና ሊቅ ያዕቆብ ስምህ ማነው ብሎ ጠየቀው እርሱም ስሜ እንጦኒ ነው አባቴም ለባለ መድኃኒቶች ብዙ ገንዘብ ሰጠልኝ ሊፈውሱኝ አልቻሉም ። መምህር ያዕቆብም ስለ ደዌው ተከዘ ጸሎትንም አድርጎ ሁለመናውን በመዳሰስ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ጤነኛ ሁን አለው ወዲያውኑ ዳነ ደቀ መዝሙሩም ሁኖ ተከተለው ።

ከዚህም በኋላ ከረድኡ ጋር ሲጓዝ ሀገረ ዐምድ ደረሱ የንጉሥ አንስጦስን ልጅ እያሳበደ ራሱን በደንጊያ ሲደበድብ አገኙት እርሱን መያዝም የሚችል አልነበረም። ሊቅ ያዕቆብም ይዞ ያመጣለት ዘንድ ረድኡን አዘዘው በአቀረበለትም ጊዜ በከበረ #መስቀል ምልክት አማተበበትና ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ከሰውዬው ወጥቶ እንዲሔድ ሰይጣንን አዘዘው ። ያን ጊዜም በጥቁር ባርያ አምሳል ወጣ የንጉሡም ልጅ በከበረ ሊቅ ያዕቆብ ጸሎት ዳነ አባቱና ወገኖቹ ሁሉ በታላቅ ደስታ ደስ አላቸው ንጉሡም ለከበረ ሊቅ ያዕቆብ ብዙ ገንዘብ ሊሰጠው ወደደ እርሱ ግን አይሆንም አለ ምንም ምን አልተቀበለም ።

ክብር ይግባውና በ #እግዚአብሔርም ትእዛዝ አብዲን በሚባል አገር የገዳም አበ ምኔት ከሆነ ከአባ በርሳቦ ጋር ተገናኝተው በአንድነት ተጓዙ በጒዞ ላይም እያሉ እንጦኒ በሆድ ተቅማጥ በሽታ ታመመና በሦስተኛው ቀን አረፈ ቀበሩትም።

ስሟ አውርሳ ከሚባል አገር በደረሱ ጊዜ የአገረ ገዥውን ልጅ ታሞ አገኙት በሊቅ ያዕቆብም ጸሎት ዳነ መኰንኑም ልጁ እንደ ዳነ አይቶ በታላቅ ደስታ ደስ አለው እስከ ዕለተ ሞቱ ረድዕ ይሆነው ዘንድ ለከበረ ያዕቆብ ልጁን ሰጠው የልጁም ስም ፍቁር ነው ።

ወደ ሊቅ በርሳቦ ገዳምም በቀረቡ ጊዜ መነኰሳቱ ተቀበሏቸው በብዙ ምስጋናም እየዘመሩ አስገቧቸው በዚያችም አገር ጎን የታነፀ የጣዖት ቤት አለ ስሙ ሰሚር የሚባል የፋርስ ንጉሥ በየዓመቱ እየመጣ ለጣዖታት በዓልን ያከብራል የከበረ ሊቅ ያዕቆብም መነኰሳቱን እንዲህ አላቸው እነሆ የፋርስ ንጉሥ እንደመጣ ሰምታችኋል የክብር ባለቤት ስለ ሆነ ክርስቶስ ስለ ስሙ ኑ ደማችንን እናፍስስ ።

መነኰሳቱም በዚህ ምክር እየተስማሙ ሳሉ የንጉሡ ጭፍሮች ወደዚያ ገዳም ደረሱ መነኰሳቱንም ጥቁር ልብስን ለብሰው አዩአቸውና እናንተ ምንድን ናችሁ ከአምልክትስ ማንን ታመልካለችሁ አሏቸው ። ቅዱሳን መነኰሳትም እንዲህ አሏቸው እኛ ከሰማያት የወረደውን በ #መንፈስ_ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል #ማርያም ሰው የሆነ የሕያው #እግዚአብሔርን ልጅ ክብር ይግባውና #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን እናመልከዋለን ጭፍሮችም ወደ ንጉሥ አቀረቧቸው ።

በደረሱም ጊዜ የክብር ባለቤት በሆነ በ #ክርስቶስ ስም በንጉሡ ፊት ታመኑ ንጉሡም ሀገራቸውን መረመረ አባ በርሳቦም የእኔና የወንድሞቼ መነኰሳት አገራችንም ሮም ነው አለ ። አባ ያዕቆብም የእኔ አገር ግብጽ ነው አለ ንጉሡም የአባ ያዕቆብን ቃል ሰምቶ ሊገድለው አልፈለገምና ብቻውን ገለል እንዲያደርጉት አዘዘ ። ከግብጽ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን ስላለው መነኰሳቱን ግን ደማቸው እስቲፈስ ገርፈው ከእሥር ቤት እንዲጥሏቸው አዘዘ የ #እግዚአብሔርም መልአክ ፈወሳቸው ።

በማግሥቱም ጤነኞች ሁነው በአገኛቸው ጊዜ ብዙ ሀብት እንደሚሰጣቸው ተስፋ ሰጣቸው እነርሱ ግን ቃሉን አቃለሉ ። ንጉሡም በወይን መርገጫ ውስጥ በማስረገጥ በግርፋት ጥርሶችን የእጆችንና የእግሮች ጥፍሮችን በማውለቅ ሰባት ቀኖችም ያህል አፍንጫን፣ ከንፈርን፣ ጆሮዎችን በመቆረጥ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ።

በስምንተኛውም ቀን ራሶቻቸውን ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ መምህራቸው ሊቅ በርሳቦም እየአንዳንዱን ለሰያፊ ከሰጣቸው በኋላ ዐሥሩ መነኰሳት ተቆረጡ የንጉሡ የፈረሶች ባልደራስ ያን ጊዜ ለቅዱሳኑ የወረዱትን አክሊሎች አየ ትጥቁንም ፈትቶ ጥሎ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታመነ እርሱንም አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት መምህር በርሳቦም ልጆቹ ከተቆረጡ በኋላ አንገቱን ዘርግቶ ሰያፊውን የታዘዝከውን ፈጽም አለው ያን ጊዜም ሰያፊው ቆረጠው ምስክርነታቸውንም ነሐሴ ሃያ ስምንት ቀን ፈጸሙ።

ንጉሡም ሥጋቸውን በእሳት እንዲአቃጥሉ አዘዘ ምድርም ተከፍታ ሥጋቸውን ሠወረች ንጉሡም አፍሮ ወደ አገሩ ሊሔድ ወደደ ። ያን ጊዜም አባ ያዕቆብ ወደ #እግዚአብሔር ጸለየ ከሰማይም ከጠቆረ ደመና ጋርና ከሚከረፋ በረድ ጋር እሳት በንጉሡ ላይ ዘነመ ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ተቃጥሎ ጠፋ ከእነርሱ አንድ እንኳ አልቀረም ።

የዚያች አገር ሰዎችም በሰሙ ጊዜ ሁሉም ወጥተው ፈረሶቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ገንዘባቸውንም ወሰዱ ወደ ሊቅ ያዕቆብም አምጥተው እሊህን ገንዘቦች ለምትሻው ሥራ ውሰድ አሉት ። እርሱም አልተቀበላቸውም ግን በሰማዕታት መቃብር ላይ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ አዘዛቸው ቤተ ክርስቲያኒቱም እስከ ዛሬ አለች ።

ከዘመናትም በአንዲቱ አገር ቸነፈር ሆነ ወደ ሊቅ ያዕቆብ እንዲጸለይላቸው ላኩ እርሱም ሰምቶ እጅግ አዘነ ማዕጠንትም ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ረጅም ጸሎት ጸለየ ዕጣንንም አሳረገ ። ከዚያም ወጥቶ መልእክተኞችን አትፍሩ አትጨነቁ በሰላም ሒዱ አላቸው ። በደረሱም ጊዜ አገሪቱን ጤነኛ ሁና አገኟት ደስ ብሏቸው የሊቅ ያዕቆብን አምላክ አመሰገኑት ።

ዳግመኛም ለከበረ ሊቅ ያዕቆብ ዳንኤል የሚባል ረድእ ነበረው ደግሞ ለቅዱስ ያዕቆብ ወዳጁ የሆነ አገር ገዥ አለ ለአገረ ገዥውም ወደ ቅዱስ ያዕቆብ ከአባቷ ጋር የምትመጣ ብላቴና አለችው ረዱን ዳንኤልን በኃጢአት ልትጥለው ፈለገችው እምቢ ባላትም ጊዜ ከአባቷ አገልጋይ ፀነሰችና በሊቅ ያዕቆብ ረድእ አመካኘችበት አባቷም ሰምቶ መምህር ያዕቆብንና ደቀ መዝሙሩን ሊገድል ሔደ በጒዞ ላይም ሳለ በላዩ ከሰማይ መብረቅ ወርዶ ዐይኖቹን አሳወረው ።

የመኰንኑም ልጅ ከወለደች በኋላ ወደ ከበረ መምህር ያዕቆብ በጉባኤ መካከል ሕፃኑን አባትህ ማን እንደሆነ ትናገር ዘንድ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም አዝዝሃለሁ አለው ። ሕፃኑም አባቴ የእናቴ የአባቷ አገልጋይ እገሌ ነው አለ የተሰበሰቡትም ሕዝብ ሰምተው አደነቁ የተመሰገነ #እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ።

ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲቀርብ ደቀ መዝሙሩን እንዲህ ብሎ አዘዘው ከዚህ ዓለም የምለይበት ጊዜ ደርሷል በምሞትም ጊዜ ከአባ በርሳቦና ከልጀቹ ጋራ ቅበረኝ ይህንንም ብሎ በሦስተኛው ቀን አረፈ መላእክትም ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ነፍሱን በክብር አሳረጉ ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቶማስ_ሰማዕት

በዚችም ቀን የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ በሕንደኬ አገር ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ ። ቶማስም በሕንድ አገር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ለመሔድ በተነሣ ጊዜ ወደዚያች አገር መግባትን እንዴት እችላለሁ ብሎ አሰበ ። ይህንንም ሲያስብ እነሆ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ተገለጠለትና አትፍራ ቸርነቴ ከአንተ ጋር ትኖራለችና አለው።
#መስከረም_21

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም 21 በዚህች ቀን #ብዙኃን_ማርያም (ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት ነው) እንዲሁም #ቅዱስ_ቆጵርያኖስና #ድንግሊቱ_ዮስቴና በሰማዕትነት ያረፉበትም ቀን ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ብዙኃን_ማርያም

በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ #ጌታችን_መድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ ዕፀ #መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤

#ጉባዔ_ኒቅያ
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አር*ዮስ የሚባል መና*ፍቅ የ #እግዚአብሔር_ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህ*ደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አር*ዮስ ክህ*ደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአር*ዮስ ክህ*ደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአር*ዮስ ክህ*ደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡

በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡

ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ #ወልድ#አብና#መንፈስ_ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡

፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮ*ስን አው*ግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡

#ዕፀ_መስቀል
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የ #ጌታችን_መድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤

ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ #እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከ #እግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የ #ጌታችን_መድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን_መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የ #ጌታችንን_መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት #መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው #መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡

ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው #መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የ #ጌታችንን_መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ #መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ #መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡

#መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ #እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ #መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በ #እግዚአብሔር መሪነት #መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም #ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ #መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የ #ጌታችንን_መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የ #እመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡

የምታድን እርሷን እናቱን ለሰጠን #እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቆጵርያኖስና_ድንግሊቱ_ዮስቴና