#ነሐሴ_16
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_ድንግል_ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ፣ የሰማዕታት አለቃ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ ሥጋው የፈለሰበት ነው፣ #ቅዱስ_ጊጋር በሰማዕትነት ሞተ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ዕርገተ_ማርያም
ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን #ድንግል_ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር ።
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው ። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በ መንፈስ_ቅዱስ ተነጠቀ ።
የክብር ባለቤት #ጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስን የእመቤታችን #ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው ። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ #እግዚአብሔር አዞሻል አሏት ። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን #ማርያም ሥጋዋ ወጣ ።
የክብር ባለቤት #ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ።
አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት ። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች ።
ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ።
ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ #ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳቸው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ።
ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን ።
በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው ። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን #ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።
የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።
#ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን #ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት።
በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው ። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው።
እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምም ክብር ይግባውና #ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር #ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ ።
የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና ።
#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት #ድንግል_ማርያም አማላጅነት ይማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ፍልሰተ_አጽሙ
በዚህችም ዕለት የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው። የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን #ድንግል_ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሆኗል ስለዚህም እርሷን መውደዱን የሚያወቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ።
#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በኃያሉ ተጋዳይ በቅዱስ ጊዮርጊስም ጸሎት በእኛ ላይ ምህረት ይቅርታ ቸርነት ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጊጋር_ሰማዕት
በዚህችም ቀን የሶሪያ መስፍን ጊጋር በሰማዕትነት ሞተ። ሰማዕት የሆነበትም ምክንያት #ጌታችን ከእመቤታችን ከእናቱ ከ #ድንግል_ማርያም ጋራ በተሰደደ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ሳለ ኄሮድስ ሰምቶ ከበው ይዘው ይገድሏቸው ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ ጊጋርም ጭፍሮች እንዳገኟቸው አሸሻቸው።
ስለዚህም ኄሮድስ ተቆጣ ጊጋርንም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ሕዋሳቱንም ሁሉ ቆራረጠ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ተገልጦለት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት በሦስት አክሊሎችም ተጋረደ ሦስት አክሊላትን ተቀዳጀ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ_16)

#እመቤታችን ልጇን ይዛ ወደ ግብጽ ከዚያም ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስትሰደድ በእግሯ እየሄደች በሞረት ዋሻ በአቡነ ዜና ማርቆስ ቦታ ግራርያ ከሚባል ቦታ ተቀምጣ እንደነበር የሐምሌው ድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ይናገራል፡፡ በኋላም ተጭነው ከእነ ልጇ በዚህ በአቡነ ገብረ ማርያም ገዳም በሆነ ቦታ ስታልፍ #ጌታችን ለቅድስት እናቱ ‹‹ይህች ቦታ ሐንታ ትባላለች፣ በኋለኛው ዘመን በስምሽ የሚጠራ የእኔ ወዳጅና ታዛዥ የሆነ የታላቅ ጻድቅ ቦታ ትሆናለች›› ብሎ ስለነገራት በኋላም ትንቢቱ ደርሶ ጻድቁ ገዳማቸውን በዚሁ ቦታ ስለገደሙት ገዳሙ ‹‹አማን ደብረ ሐንታ›› ይባላል፡፡ ጻድቁ በመንዝና በመርሐ ቤቴ ከ1245-1268 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ19 በላይ የተላያዩ አብያተ ክርስቲያናትን ተክለዋል፡፡ ጾም ጸሎተኛ ባሕታዊ ከመሆናቸው በተጨማሪ የወንጌል ገበሬ፣ ጻድቅና ደራሲም ናቸው፡፡
አቡነ ገብረ ማርያም በጣም ከሚታወቁበት ድርሰታቸው አንዱ የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት ከታላቁ ሊቅ ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰቱን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር በአንድነት አግልግለዋል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡
በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አቡነ ጽጌ ድንግል ከገዳማቸው ከደብረ ብሥራት ተነሥተው ወደ ደብረ ሐንታ ሄደው እንዲሁ እንደ አቡነ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አግልግሎ ይመለሳል፡፡ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን እንደዚህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ ሌላኛው ገዳም እየሄዱ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና አብረው ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡
ይኸውም በራሳቸው በአቡነ ገብረ ማርያም ገድል ላይ እና በአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ገጽ 72-73 ላይ በሰፊው ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ የሁለቱ ድርሰታቸው የሆነው ‹‹ማኅሌተ ጽጌ›› ድርሰት የ #እመቤታችንንና የልጇን የ #ጌታችንን ሥጋዊ ስደት የሚገልጽ ሲሆን በተጨማሪም ስደት የማይገባው #አምላካችን_ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ አህጉራችን አፍሪካ ተሰዶ የሠራቸውን ድንቅ ድንቅ ተአምራትና የ #እመቤታችንን ንጽሕናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷን የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
አቡነ ገብረ ማርያም አዲስ አፍልሰው በሠሯት ቤተ ክርስያን ውስጥ ልጆቻቸው ተሰበሰቡና ‹‹አባታችን ሆይ የት እናድራለን? ማረፊያን ያዘጋጅልን ዘንድ #እግዚብሔርን ለምነው›› አሉት፡፡ አባታችንም ‹‹ይህ ሥራ ለእኔ አይቻለኝምና እናንተ ለምኑት›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹አባታችን ሆይ አትበትነን›› ብለው ግድ አሉት፡፡ ልጆቹም ግድ ባሉት ጊዜ አባታችን ተነሥቶ ጸለየ፡፡ ስለዚህም ነገር ሲናገር አባታችን እንዲህ አለ፡- ‹‹ከዚህ ነገር አስቀድሞ በቁርባን ጊዜ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ይመጣና ይባርከኝ ነበር፣ እናቱ #ድንግል_ማርያምም ትባርከኝ ነበር፡፡ ስለዚህ ነገር ግን #ጌታችን ተቆጣ፣ እምቢ አለኝ፡፡ ከእኔም ፊቱን መለሰ፡፡ እኔም ብዙ አለቀስኹ የእጁን ቡራኬ አጥቻለሁና፡፡ እናቱ #ድንግል_ማርያምም ፈጽሜ ሳለቅስ ባየችኝ ጊዜ ‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ለምን ታለቅሳለህ?› አለችኝ፡፡ እኔም #እመቤቴ_ሆይ #ጌታዬና_አምላኬ ፊቱን ከእኔ መልሷልና ስለዚህ አለቅሳለሁ አልኳት፡፡ #እመቤታችን_ማርያምም የተወደደ ልጇን ‹ልጄ ሆይ ወዳጅህ ገብረ ማርያምን በምን ሥራ አሳዘነህ?› አለችው፡፡ #ጌታችንም ለ #ድንግል እናቱ ‹እርሱ አሳዝኖኛል፣ የዮሴፍ ልጅ ያዕቆብ ‹ይህን ዓለም የሚወድ የ #እግዚአብሔር ጠላት ይሆናል› (ያዕ 4፡4) እንዳለ ከእኔ ፍቅር ይልቅ የዓለምን ፍቅር ወዷልና› አላት፡፡› እናቱ #እመቤታችንም የተወደደ ልጇን ‹ልጄ ሆይ ወዳጅህ ገብረ ማርያምን አታሳዝነው ይቅር በለው ባጠባሁህ ጡቶቼ አምልሃለሁ› አለችው፡፡ #ጌታችንም ይህን ጊዜ ቅድስት እናቱን ‹የላይኛውን ወይም የታችኛውን ይወድ እንደሆነ ጠይቂው› አላት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ከዚያ ቆሞ ነበርና ወዲያው ለእኔ ‹የላይኛው ያለህ መንግሥተ ሰማያትን ነው፣ የታችኛው ያለህ ይህች ዓለም ናት› አለኝ፡፡ እኔም ያንጊዜ ይህችን ዓለም አልፈልጋትም ነገር ግን ማረፊያ እንዲሰጠን በጸሎቴ የጠየቁት ልጆቼ ከሞቴ በኋላ ተስፋ እንዳይቆርጡ እንዳይበተኑም ብዬ ነው አለኩት፡፡ #ጌታችንም ‹‹ገብረ ማርያም ሆይ ለምን ይህንን ታስባለህ? ለልጆችህ እኔ አስብላቸዋለሁና፡፡ ወዳጄ ዳዊት ‹የጻድቃን ልጆች ይባረካሉ፣ ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፣ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል› (መዝ 111፡33) ብሎ እንደተናገረ እኔ ለፍጥረት ወገን ሁሉ አስባለሁ› አለኝ፡፡ ይህንንም ብሎኝ ሰላሙን ሰጥቶኝ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡››
አቡነ ገብረ ማርያም ያደረጓቸው ተአምራት ተነግረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ በብቸኝነት ሳለ በአንዲት አገር የሚኖር ልጁ የሞተበት ሰው የልጁን አስክሬን ወደ አባታችን አምጥቶ በፊታቸው አስቀመጠውና ‹‹አባታችን ሆይ ልጄ እንደሞተ ተስፋዬ ሁሉ ጠፍቷልና አሁን ብትወድ ከሞት አንሣው ባትወድ ግን እዚሁ ቅበረው›› እያለ አለቀሰባቸው፡፡ አባታችንም የሰውየውን ሁኔታውን አይተው ፈጽመው አለቀሱ፡፡ ልቡናቸውም ታወከባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ይጸልዩ ዘንድ ተነሡና ‹‹…በተቀበረ በ4ኛው ቀን አልዓዘርን ያስነሣኸው አሁንም ይህን ሕፃን አስነሣው…›› ብለው ከጸለዩ በኋላ የልጁን እጅ ይዘው ‹‹በ #ጌታችን_በአምላካችን_በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይል ተነሥ›› ብለው እፍ አሉበት፡፡ ያንጊዜም ሕፃኑ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ አፈፍ ብሎ ተነሣ፡፡ ለአባቱም ‹‹ልጅህን ውሰድ ፈጣሪዬ አስነሣልህ›› ብለው ሰጡት፡፡ ሰውዬውም ከእግራቸው ሥር ሰግዶ የእግራቸውን ትቢያና ሰውነታቸውን ሁሉ ሳመው፡፡ ልጁንም ይዞ ፈጽሞ ደስ እያለው ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
በአንዲት ሀገርም አንድ ልጅ ብቻ ያላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ልጁም ወደ አባታችን እየመጣ ‹‹አመንኩሱኝ›› እያለ ሁልጊዜ ይጠቃቸው ነበር፡፡ አንድ ቀንም እንዲሁ መጣና ‹‹አባት ሆይ ካላመነኮሱኝ ወደሌላ ሰው ዘንድ ሄጄ እመነኩሳለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ፈቃደ #እግዚአብሔርን ጠይቀው የፍላጎቱን ፈጸሙለትና አመነኮሱት፡፡ ወላጅ እናቱም መጥታ ልጇ የምንኩስናን ልብስ እንደለበሰ ባየች ጊዜ እያለቀሰች ሄደችና ራሷን ወደ ገደል ውስጥ ጨመረች፣ ሞተችም፡፡ ሰዎችም ተሰብስበው አለቀሱላትና አስክሬኗን ተሸከመው ይቀብሯት ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዷት፡፡ ሰዎችም ወደ አባታችን መጥተው ‹‹ሴትዮዋ ከመቀበሯ በፊት መጥተው ይዩዋት›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ወደ አስክሬኗ አልመለከትም›› አሉ፡፡ እነርሱም በ #እግዚአብሔር ስም ባማሏቸው ጊዜ አባታችን አስክሬኗ ወዳለበት መጡና አዩዋት፡፡ በማግሥቱም ከገነዟት በኋላ አባታችን ከመዝገበ ጸበላቸው