ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
#መስከረም_26

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ሃያ ስድስት በዚች ቀን #መጥምቁ_ዮሐንስ የተጸነሰበት፣ የዮስጦስ ልጅ #ቅዱስ_አቦሊ የስጋው ፍልሰት የሆነበት ቀን ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ጽንሰቱ

መስከረም ሃያ ስድስት በዚች ቀን #እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ወደ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ልኮት መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ስለ መወለዱ አበሠረው።

ስሙ የተመሰገነ #እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ #እግዚአብሔር ይማልድ ነበር። ልጅ ያልወለደውን #እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና።

ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ #ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው።

ዘካርያስም የሰውነቱን መድከም የመውለጃውም ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጅ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽማ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል እኔ ያረጀሁ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም እንዲሁ ዘመኗ አልፎ መካን ሁናለች ብሎ የ #እግዚአብሔርን መልአክ ተከራከረው።

መልአኩም እኔ ይህን ልነግርህ ከ #እግዚአብሔር ዘንድ ወዳንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠር ባልተገባህም ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል ብሎ ገሠጸው። ዘካርያስም የወልደ #እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚወለድበት ጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ።

በሚገረዝበትም ቀን የሕፃኑን አባት ዘካርያስን የሕፃኑን ስም ምን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ #እግዚአብሔርን አመሰገነው። ስለ ልጁ ዮሐንስም እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በ #እግዚአብሔር ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አቦሊ

በዚችም ቀን የዮስጦስ ልጅ ቅዱስ አቦሊ የስጋው ፍልሰት ሆነ። ይህም ቅዱስ አቦሊ ከመንግሥት ልጆች ውስጥ ነበር ዐላውያንን ወግቶ በተመለሰ ጊዜ ዲዮቅልጥያኖስን ክብር ይግባውና #ክርስቶስን ክዶ አገኘው።

ያም አቦሊና አባቱ ዮስጦስ ሌሎችም የመንግሥት ልጆች ሁሉ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስን ሊያጠፉትና መንግሥትን ከእርሱ ሊወስዱ ችሎታ ሲኖራቸው የማታልፍ ሰማያዊት መንግሥትን አሰቡ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ አቦሊ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታመነ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አብዝቶ አባበለው። እንዲሁም አባቱ ዮስጦስንና የከበረች እናቱ ታውክልያን አባበላቸው እነርሱ ግን አልሰሙትም ልባቸው በመድኅን #ክርስቶስ ፍቅር ተነድፏልና።

ንጉሡም እነርሱን በዚያ ማሠቃየትን ፈራ ስለዚህም ከመልእክት ደብዳቤ ጋር ወደግብጽ ስሙ ኄርሜኔዎስ ወደሚባል የእስክንድርያ ገዥ ላካቸው በመልእክቱም እንዲህ አለው ዮስጦስና ሚስቱ ታውክልያ ልጃቸው አቦሊም ወደአንተ በሚደርሱ ጊዜ አባብላቸው አለዚያም እየአንዳንዳቸውን ለያያቸው።

በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለዮስጦስና ለሚስቱ ታውክልያ ለልጃቸው አቦሊም ተገልጦላቸው አጽናናቸው ከእነርሱም የሚሆነውን ነገራቸው የጸና ቃል ኪዳንም ሰጣቸው።

ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስም በደረሱ ጊዜ ስለእነርሱ እጅግ አደነቀ እነርሱ መንግሥታቸውን ትተዋልና ክፋ ነገርንም ሊናገራቸው አልደፈረም ከምክራቸው ይመለሱ ዘንድ በለሰለሰ ቃል ሸነገላቸው እንጂ ነገር ግን አልሰሙትም።

ከዚህም በኋላ በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ ለእየብቻቸው ለያያቸው ቅዱስ ዮስጦስን ወደ እንዴናው ከተማ ሚስቱን ታውክሊያን ፃ ወደ ሚባል አገር ልጃቸው አቦሊንም ብስጣ ወደ ሚባል አገር ሰደዳቸው ለእያንዳንዳቸውም የሚአገለግላቸው አንዳንድ አገልጋይ ሰጣቸው።

ቅዱስ አቦሊም ወደ ሀገር ብስጣ በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመነ። መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን በእሳት ቃጠሎና በመንኰራኵር አሰቃየው ሕዋሳቱንም ቆራርጦ ለአንበሶች ጣለው ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስም ከሥቃዩ ሁሉ አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አነሣው።

ብዙዎች ሰዎችም ስቃዩንና ዳግመኛ መዳኑን በአዩ ጊዜ እጅግ አደነቁ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስም አምነው ሰማዕታት ሆኑ።

መኰንኑ ግን እጅግ ተቆጥቶ የቅዱስ አቦሊን ቆዳውን እንዲገፍፉትና ጨውና መጻጻን በማቅ አምጥጠው ቍስሉን እንዲያሹ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት።

ከዚህም በኋላ ቆዳውን አሸክመው በከተማ ውስጥ ሁሉ አዞሩት ወደ #ጌታችንም እንዲህ ብሎ ጸለየ የሕያው #እግዚአብሔር ልጅ #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ሆይ ርዳኝ ከዚህ ሥቃይም አድነኝ። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ መጣ ሁለመናውንም ዳስሶ አዳነው።

መኰንኑም በእርሱ ላይ የሚያደርገውን እስኪያስብ ከእሥር ቤት እንዲጨምሩት አዘዘ። ቅዱስ አቦሊም ቁሞ ጸለየ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና #ጌታችን ተገለጠለትና የመረጥኩህ አቦሊ ሰላም ለአንተ ይሁን እኔም ከአንተ ጋር እኖራለሁ አለው #ጌታችንንም በአየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው ክብር ይግባውና #ለጌታችንም ሰገደለት።

ስሙ አብስኪሮን የሚባል አንድ ባለ ጸጋ ነበር የቤቱንም ግድግዳ አፍርሰው አዲስ ይሠሩለት ዘንድ ሠራተኞችን አመጣ ሥራቸውንም እስኪጨርሱ ከዚያ ይቆሙ ዘንድ ሁለቱን ልጆቹን አዘዛቸው።

ከግርግዳውም ላይ በወጡ ጊዜ ግርግዳው ተደርምሶ ዐሥራ ስድስት ሰዎችና ሁለቱ ልጆቹ ሞቱ። ባለጸጋውም የሆነውን በአየ ጊዜ ልብሱን ቀደደ ጩኾም አለቀሰ ወደ ቅዱስ አቦሊም ሒዶ ከእግሩ በታች ሰገደለት እንዲህም አለው ራራልኝ ሁለቱ ልጆቼ ሙተዋልና ከእነርሱም ጋራ ዐሥራ ስድስት ሰዎች ሞቱ። ከሞትም ብታሥነሣቸው እኔ በአምላክህ አምናለሁ።

ያን ጊዜም ቅዱስ አቦሊ ተነሣ እንዲህ ብሎ ጸለየ ስለ ቅዱስ ስምህ መከራን እቀበል ዘንድ የመረጥከኝ #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ በእኒህ በሞቱ ሰዎች ላይ ኃይልህን ግለጥ። እኒህ ሰዎች ሁሉ እንዲአምኑ ያለ አንተም ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ከሞት አንሣቸው። ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

ከዚህም በኋላ የተገፈፈ ቆዳውን ወስዶ በሞቱት ሰዎች ላይም ዘረጋውና በሕያው #እግዚአብሔር ልጅ በ #ጌታ_በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ከሞት ተነሡ አለ። ወዲያውም ሁሉም ድነው ተነሡ በዚያ ያሉ ሕዝብም ይህን ድንቅ ሥራ በአዩ ጊዜ የክርስቲያን አምላክ የቅዱስ አቦሊም አምላክ #ኢየሱስ_ክርስቶስ አንድ ነው እኛም እናምንበታለን ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለምና እያሉ ጮኹ።

ባለ ጸጋው አብስኪሮንም መጥቶ ለቅዱስ አቦሊ እንዲህ እያለ ሰገደ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ክብር ይግባውና እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ዛሬ አወቅሁ እኔም አምንበታለሁ። ከቤተሰቦቹም ሁሉ ጋር አመኑ መኰንኑም አፈረ።
#መስከረም_29

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ክብር ይግባውና #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም የተወለደበት የልደቱ መታሰቢያ ነው ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። #ከቅድስት_አርሴማና_ከእመምኔቷ_ከአጋታ ጋር ደናግላን በሰማዕትነት አረፉ፤ ዳግመኛም #የቅዱስ_ዮሐንስ_ነባቤ_መለኮት (ወንጌላዊው) እንደ ንስር መጥቆ "ቀዳሚሁ ቃል.." (ዮሐ. ፩፥፩) ብሎ ወንጌሉን የጻፈበት ዕለት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ

በዚችም ቀን ከቅድስት አርሴማና ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ። ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ።

ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ።

እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ #እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች ቅድስት አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የ ቅድስት አርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው።

ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅድስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት።

የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት ቅድስት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የ #እግዚአብሔር ልጅ ሕያው #ክርስቶስ ነው።

ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የ #እግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ።

አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ።

ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ_ነባቤ_መለኮት

ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንደ ንስር መጥቆ "ቀዳሚሁ ቃል.." ( ዮሐ. ፩፥፩) ብሎ ወንጌሉን የጻፈበት ዕለት እንደሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ፡- ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን መዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡ የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡

እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ "በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን" እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም "አይዞሽ አትዘኚ" አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በ #መስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ " #እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን" ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም "በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ" አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በ #ጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ቅዳሴ #ማርያምን እየደገሙ ውኃው በተአምራት ኅብስት ይሆንላቸው ነበር፡፡ ይህን ተአምር ከአደነቀ በኋላ « #ማርያም ሆይ ሁሉን ማድረግ ትችያለሽና ኃጢአቴን አስተስርይልኝ» ይላል፡፡ #ጌታችን «እውነት እላችኋለሁ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም» /ማቴ.17፡20/ በማለት ላመነ የሚሣነው ነገር እንደሌለ ተናግሯል፡፡ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም መልአኩ «ትጸንሻለሽ፣ ትወልጃለሽ ...» ብሎ ባበሠራት ጊዜ ይህ እንደምን ይሆንልኛል? ብላ ስትጠይቅ «ለ #እግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም» ሲላት በፍጹም እምነት ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ እንደቃልህ ይሁልኝ» በማለት የተቀበለች ናት፡፡ ይህንንም ቅድስት ኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስን ተመልታ «ከ #ጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና የታመነች ብፅዕት ናት» /ሉቃ.1፡45/ ብላ መስክራለች፡፡ ላመኑ ሁሉ የሚቻል ከሆነ #እመቤታችን ግን ቅዱሳን ሁሉ የሚማጸኑትን አምላክ በሥጋ ወልዳ ያስገኘች ስለሆነች ለእርሷ የሚሳናት ነገር የለም፡፡ ስለዚህም ነው ላንቺ የሚሳንሽ ነገር የለምና ኃጢአቴን አስተስርዪልኝ፣ የከበደኝን ሁሉ አቅልይልኝ በማለት የለመነው፡፡

1.2. «ተአምርኪ #ማርያም ተሰብከ በኦሪት፣
አመ ተሰነዓውኪ ጳጦስ ምስለ መለኮት፣
ዘርእየኪ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
ጸልልኒ በአዕፁቅኪ ሐመልማላዊት ዕፀት
ሦከ ኃጢአትየ ያውዒ ጽጌኪ እሳት፡፡

«#ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ በደብረ ኮሬብ ባየ ጊዜ ተአምርሽ በኦሪት ተሰበከ ተነገረ፡፡ ምሳሌሽ በሐመልማልና በእሳት አምሳል የታየ #ማርያም ሆይ ጽጌ ልጅሽ ኃጢአቴን ያጠፋልኝ ዘንድ በጥላሽ ሥር አስጠጊኝ፡፡”

ሙሴ በምድያም በስደት ሆኖ የአማቱን የዮቶርን በጎች እየጠበቀ ሳለ በኮሬብ ተራራ ድንቅ ራእይ ታየው፡፡ ቁጥቋጦው በእሳት ሲነድ፡፡ ቁጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ፡፡ ዘጸ.3÷3፡፡ ይህ የምሥጢር ተዋሕዶ ተምሳሌታዊ ራእይ ነበር፡፡ ሐመልማል የ #እመቤታችን ምሳሌ ሲሆን እሳቱ ደግሞ የ #መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ የሐመልማሉ ርጥበት እሳቱን አለማጥፋቱ #አምላክ ሰው ሲሆን ከ #መለኮቱ ክብር ዝቅ ያለማለቱ ምሳሌ ነው፡፡ እሳቱ ደግሞ ሐመልማሉን አለማቃጠሉ #መለኮት#እመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በተዋሐደ ጊዜ እንዳጸናትና እንዳደረገችው የሚያስረዳ ነው፡፡

ደራሲው የ #እመቤታችን_ክርስቶስን የማስገኘት ተአምርና የእርሷ የ #አምላክ እናት መሆን ከጥንት ጀምሮ ሲነገር የኖረ መሆኑን ካስታወሰ በኋላ ጸሎቱን «ጸልልኒ በአዕፁቅኪ ሐመልማላዊት ዕፀትኮ ሦከ ኃጢአትየ ያውኢ ጽጌኪ እሳት» በማለት ያቀርባል፡፡ ይኸም ማለት «ያ ከሐመልማል ጋር ተዋሕዶ የታየው እሳት ጽጌሽ/ ልጅሽ #ክርስቶስ/ ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ በአንቺ ሐመልማልነት አስጠጊኝ” ማለት ነው፡፡

ዳዊት «በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ ይላቸዋል» /መዝ.86፡7/ ብሎ እንደተናገረ በ #እመቤታችን እናትነትና አማላጅነት ጥላ ሥር የሚኖሩ ከልጇ ከ #ክርስቶስ ሥርየተ ኃጢአትን አግኝተው፣ በ #መንፈስ_ቅዱስ ጸጋ ተጐብኝተው ደስተኞች እንደሚሆኑ የተናገረው ትንቢት መፈጸሙን የሚያስረዳ ነው፡፡

ይቀጥላል…
#ጥቅምት_2

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሁለት በዚች ቀን የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ የመጣበት፣ #የቅዱስ_አባ_ሕርያቆስ የልደቱና ዕረፍቱ መታሰቢያ ናት፣ የፈጠጋሩ #ቅዱስ_አቡነ_ማትያስ ዕረፍታቸው ነው፡።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሳዊሮስ

ጥቅምት ሁለት በዚች ቀን የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ መጣ ።

ይህም የሆነው በመናፍቁ ንጉሥ በዮስጥያኖስ ዘመን ነው እርሱም ንጉሡ በኬልቄዶን ሃይማኖት የሚያምን ነው ሚስቱ ንግሥት ግን ሃይማኖቷ የቀና ነው ቅዱስ አባ ሳዊሮስን ትወደዋለች ታከብረዋለችም ንጉሡም በሥውር ሊገድለው ይሻዋል።

ቅዱስ አባ ሳዊሮስንም በሥውር ይገድለው ዘንድ ንጉሥ እንደሚሻው ንግሥት በአወቀች ጊዜ ከአንጾኪያ አገር እንዲወጣና ነፍሱን እንዲአድን ወደ አባ ሳዊሮስ ላከች። እርሱ ግን መሸሽ አልፈለገም ለንግሥትም እንዲህ አላት እኔ ክብር ይግባውና ስለ #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሞት የተዘጋጀሁ ነኝ ንግሥቲቱም ብዙዎች ምእመናንም አብዝተው በለመኑት ጊዜ ከሀገር ወጣ ከእርሱም ጋር ከምእመናን አብረውት ወደ ግብጽ አገር የተሰደዱ አሉ።

ንጉሡም በፈለገው ጊዜ አላገኘውም ፈልገውም ወደርሱ ያመጡት ዘንድ ወታደሮቹን ላከ ክብር ይግባውና #ጌታችን ስለ ሠወረው እነርሱም በቅርባቸው ሁኖ በመካከላቸው ሲጓዝ አላገኙትም። በአንድ ቦታም አብሮአቸው ሲያድር እርሱ እያያቸው እነዚያ የንጉሥ ጭፍሮች አያዩትም እርሱንም አጥተው ተመለሱ።

ወደ ግብጽ አገርም በደረሰ ጊዜ ከቦታ ወደቦታ ከደብር ወደ ደብር በሥውር የሚዘዋወር ሆነ #እግዚአብሔርም በእጆቹ ላይ ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ።

በአንዲት ቀንም ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረሰ በመጻተኛ መነኲሴ አምሳልም ወደ አባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያንም ገባ በዚያንም ጊዜ ቄሱ ዕጣንና ቁርባንን ሊአሳርግ ጀመረ እንደ ሥርዓቱም እየዞረ ዐጠነ። የሐዋርያትንም መጻሕፍት የጻፉአቸውን መልእክቶች የከበረ ወንጌልንም ከአነበቡ በኋላ እጆቹን ታጥቦ ማኅፈዱን በገለጠው ጊዜ በጻሕሉ ውስጥ የቊርባኑን ኅብስት አላገኘውም ደንግጦም አለቀሰ።

ከዚህም በኋላ ወደ ሕዝቡ ተመልሶ እንዲህ አላቸው ወንድሞቼ እነሆ የቊርባኑ ኅብስት ተሠውሮ በጻሕሉ ውስጥ አላገኘሁትምና ይህ የሆነ በእኔ ኃጢአት ወይም በእናንተ ኃጢአት እንደሆነ አላወቅሁም።

በዚያንም ጊዜ የ #እግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት እንዲህ አለው ይህ የሆነ በኃጢአትህ ወይም በሕዝብ ኃጢአት አይደለም ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስ እያለ መሥዋዕትን ለማሳረግ በመድፈርህ ነው እንጂ ቄሱም መልአኩን ጌታዬ ሊቀ ጳጳሳት መኖሩን አላወቅሁም አለው አባ ሳዊሮስም ወደ ቆመበት ቦታ አመለከተው።

ቄሱም ወደ አባ ሳዊሮስ ሒዶ ከእግሩ በታች ሰገደ ቡራኬም ከእርሱ ተቀበለ። ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስም የጀመረውን የቅዳሴውን ሥርዓት እንዲፈጽም ቄሱን አዘዘው። እርሱንም በታላቅ ክብር ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት ከዚህም በኋላ ቄሱ ወደ መሠዊያው በወጣ ጊዜ የቁርባኑን ኅብስት በጻሕሉ ውስጥ አገኘው ካህናቱና ሕዝቡም ሁሉ #እግዚአብሔርን አመሰገኑት።

የቁርባኑንም ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ካህናቱና ሕዝቡም ሁሉ ከሊቀ ጳጰሳት አባ ሳዊሮስ ቡራኬ ተቀበሉ። ከዚያም ወጥቶ ወደ ሀገረ ስሐ(ስካ) ሔደ ስሙ ዶርታዎስ ከሚባል #እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለ ጸጋ ሰው ደርሶ ከእርሱ ዘንድ ተቀመጠ። ምእመናንንም እያስተማራቸውና በቀናች ሃይማኖት እያጸናቸው እስከሚአርፍባት እስከ የካቲት ወር ዐሥራ አራት ቀን ኖረ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት ሳዊሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሊቁ_ቅዱስ_አባ_ሕርያቆስ

ክርስቲያን ሆኖ #እመቤታችንን የሚወድ ሰው ሁሉ ይህንን አባት ያውቀዋል። አባ ሕርያቆስ ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ ሲሆን አካባቢው ብህንሳ (ንሒሳ) ይባላል። ይህቺ ቦታ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳንን ያፈራች ናት።

የስሙ ትርጓሜ ሕርያቆስ/ ኅርያቆስ ማለት (የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ) እንደሚገልጠው ኅሩይ/ምርጥ/ ማለት ነው፤ ለሹመት መርጠውታልና ምርጥ ተባለ፡፡ አንድም ረቂቅ ማለት ነው፤ ምሥጢረ #ሥላሴን ከኹሉ ይልቅ አምልቶ አስፍቶ ይናገራልና፡፡አንድም ፀሐይ ማለት ነው፤ #አብ ፀሐይ #ወልድ ፀሐይ #መንፈስ_ቅዱስ ፀሐይ እያለ ጽፏልና፡፡አንድም ብርሃን ማለት ነው፤ የምእመናንን ልቡና በትምህርቱ ብሩህ ያደርጋልና፡፡ ዘአብርሃ መንበረ ማርቆስ በብርሃን እንዲል፡፡አንድም ንህብ ማለት ነው፤ ንህብ የማይቀስመው አበባ የለም፣ እርሱም የማይጠቅሰው ሊቅ የለምና፡፡

አባ ሕርያቆስን በዚህ ዘመን ነበረ ተብሎ ትክክለኛውን ዓ/ም ለመናገር ይከብዳል። ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት መረዳት እንደሚቻለው ግን የነበረበት ዘመን 4ኛው ወይም 5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደ ሆነ መገመት ይቻላል።

ቅዱሱ በዘመኑ የተለየ ማንነት የነበረው ሰው ነው። ገና ከልጅነቱ #እመ_ብርሃንን የሚወዳት በመሆኑ ቅን የዋህና ገራገር ነበረ። መቼም #እመቤታችን ይወዳል ሲባል እንደ ዘመኑ በአፍ ብቻ እንዳይመስለን። ቀንና ሌሊት ለፍቅሯ የሚተጋ ማዕበለ ፍቅሯ የሚያማታው ሰው ነበር እንጂ።

የእመቤታችን #ድንግል_ማርያምን ስም ሲጠራ ምስጥ ብሎ ልቡናው ይሰወርበት ነበር ዘወትር የእርሷን ፍቅር ከማሰብ በቀር ሌላ ሥራ አልነበረውም። የልጅነት ጊዜው ሲያልፍም ድንግልንና ቸር ልጇን ያገለግል ዘንድ መነነ።

ዘመኑ ዘመነ ሊቃውንት እንደ መሆኑ ሁሉም ለትምሕርት ሲተጉ እርሱ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ነበር የሚተጋው። ከትምሕርት ወገንም የሰሞን ጉዋዞችን አንዳንድ ቅዳሴያትንና የዳዊትን መዝሙር ተምሮ ነበር።

በተለይ ግን የዳዊትን መዝሙር እየጣፈጠው መላልሶ መላልሶ ያመሰግንበት ነበር። ከዳዊት መካከል ደግሞ መዝሙር 44ን ፈጽሞ ይወዳት ነበር። ይህቺ ጥቅስ የምትጀምረው "ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" ብላ ነው። የውስጧ ምሥጢርም ስለ #ድንግል_ማርያምና ስለ #ክርስቶስ ነው።

አባ ሕርያቆስ ይህቺን መዝሙር በቃሉ አጥንቶ? ቁሞም ተቀምጦም ተኝቶም ተነስቶም ያለ ማቁዋረጥ ይላት ነበር። እየጣፈጠችው "ልቡናየ በጐ ነገርን አወጣ" እያለ ይዘምር ነበር። በወቅቱ ታዲያ የብህንሳ ኤዺስ ቆዾስ በማረፉ ምትክ ሲያፈላልጉ #መንፈስ_ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጠ።

ምንም አለመማሩ ቢያሰጋቸውም 'በጸሎቱ በደግነቱ ሃገር ይጠብቃል' ብለው ሾሙት ነገር ግን ምንም በሥልጣን የበላያቸው ቢሆን ተማርን የሚሉ ሰዎች ይጠሉት ይንቁትም ነበር። እርሱ ግን እንደ ጠሉኝ ልጥላቸው እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር ያገለግል ነበር።

አንድ ቀን ታዲያ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ ብቻውን እየተራመደ "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ። እርሱ በምስጋናው ሲደሰት እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር። ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ።

በዚህ ጊዜ ደንግጦ ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው። ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም። ልብሱም አልቆሸሸም። ለራሱ ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር።

"#እመ_ብርሃን" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች #እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው። #እመ_አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ።
#ጥቅምት_3

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሦስት በዚህች ቀን የኢትዮጵያዊው ቄርሎስ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ በዓለ ፅንሰቱ ነው፣ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 51ኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባ_ስምዖን አረፈ፣ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ የምስክርነቱ መታሰቢያ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞#✞✞✞✞✞

#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

ጥቅምት ሦስት በዚህች ዕለት ከመጽሐፈ ሰዓታት ውጭ እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሰ ፈላስፋም ጻዲቅም ደራሲም መናኝ ባሕታዊም የሆነ ድርሰቶቹንም ለቅዱሳን በነፋስ ጭኖ ይልክላቸው የነበረ የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ኩራት ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በዓለ ፅንሰቱ ነው፡፡

አባ ጊዮርጊስ ነገረ ሃይማኖትን ጠንቅቆ የተረዳና የሚያስረዳ ስለነበር በዘመኑ የተነሡ የሃይማኖት ክርክሮች ሁሉ እርሱ ከሌለ አይሳኩም ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ በሸዋ በይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በአባ ኖብና በሰማዕቱ በጊጋር ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር፡፡ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ አሁንም አሉ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር፡፡

ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ፡፡ “ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁ እኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ” ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን፣ ንቡራነ እዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡ አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡ የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ አቀረበ፡- “እናንተ የ#እግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ #ክርስቶስ እውነት የ #እግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ 'አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?” ብሎ እንደ ጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣ እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?” ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡

በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር፡፡ ሊቃውንቱም “እንዲህ ያለው ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ” ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ እንዲመጣ ተደረገ፡፡ በአልጋ ላይ ሆኖም በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ ነገሩት፡፡ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጥልናል “እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተ ክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? #እግዚአብሔር_አብ አይደለምን?” በዚህ ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡ ንጉሡ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ ተደሰቱ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ “በምጽአት ጊዜ የሚመጣው #ወልድ ብቻውን እንጂ #አብና #መንፈስ_ቅዱስ አይመጡም” የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡ ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት የነበረው ሰው እንደ ነበረ ገድሉ ይናገራል፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑበዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡

ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለ ወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚረታ ስላወቀ “ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷልና አትምጣ” የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም አበላ እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡ ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ ተቀስፎ ሞተ፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከታቸው ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ስምዖን

ዳግመኛም በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኃምሣ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ስምዖን አረፈ።

ይህም አባት ከእስክንድርያ ከታላላቆች ተወላጅ የሆነ ወላጆቹም ሃይማኖታቸው የቀና ነው እርሱም ከታናሽነቱ የሃይማኖት ወተትን ጠጥቶ አደገ ስለዚህም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተማረ።

የምንኵስናንም ልብስ ሊለብስ በልቡ አስቦ ወደ አስቄጥስ ገዳም በመሔድ ከእርሱ አስቀድሞ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በአባ ያዕቆብ ገዳም መነኰሰ በየጊዜው በሚጨመር ተጋድሎም ሥጋውን እያደከመ አብዝቶ በመጋደል በእርሱ ዘንድ ኖረ።

ዳግማዊ አባ ማርቆስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ይህን አባ ስምዖንን ስለ በጎተጋድሎውና ስለ አገልግሎቱ ከአባ ያዕቆብ ዘንድ ወሰደው እያገለገለውም ከእርሱ ጋር ኖረ።

አባ ማርቆስም በአረፈ ጊዜ አባ ያዕቆብ ተሾመ ያን ጊዜም እያገለገለው ከአባ ያዕቆብ ጋር ኖረ። ከዚህም በኋላ አባ ያዕቆብ በአረፈ ጊዜ ብዙዎች ካህናትና ኤጲስቆጶሳት የሀገር ታላላቆች ሁሉም ይህን አባት አባ ስምዖንን መረጡት። ትሩፋቱንና የአማረ ሥራውን በእነዚህ በሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ በነበረበት ጊዜ ስለተመለከቱ አምላካዊ ፍቅር አነሣሥቷቸዋልና በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

ከዚህም በኋላ በሹመቱ ጸንቶ መልካምን ጉዞ ተጓዘ #እግዚአብሔርንም አገለገለው የሃይማኖትንም ሕግ በማስጠበቅ የ #ክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ።

በሹመቱ ወራትም ቤተ ክርስቲያን በጸጥታና በሰላም ኖረች። ከዚህም በኋላ እግሮቹን በጽኑዕ ደዌ ታመመ ፈጣሪ #እግዚአብሔርንም ከዚህ ደዌ ያሳርፈው ዘንድ ለመነው። ክብር ይግባውና #ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በሰላም በፍቅር አንድነት አሳረፈው የሹመቱ ወራትም አምስት ወር ከዐሥራ አምስት ቀን ነው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከታቸው ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ (ሰማዕት)
#ማኅሌተ_ጽጌ፤ ምንጩ ትርጉሙና መልእክቱ (ክፍል ሁለት)

በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

የቀጠለ…

2, #ታሪክ

በብሉይና በሐዲስ ኪዳን በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙትን ድርጊቶች እያነሣ የሚሔድና በዚያውም ከታሪኩ ጋር አብሮ ጸሎትና ምሥጢር የያዘ ነው፡፡ ታሪክን ከሚያነሡት መካከል የሚከተሉትን ለአብነት መመልከት ይቻላል፡፡

2.1. «እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦተ ሕግ ከመ ዘፈነ፣
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ስነ፣
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ
ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቁርባነ፣
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ፡፡

ዳዊት ታቦተ ጽዮንን ከአቢዳራ ቤት ወደ ከተማው ባስመጣ ጊዜ በሙሉ ኃይሉ በ #እግዚአብሔር ታቦት ፊት ሲዘምር ሜልኮል ተመልክታ በልብዋ ናቀችው፡፡ በዚህም ምክንያት #እግዚአብሔር ስላዘነባት ልጅ ሳትወልድ ሞታለች፡፡ ሳሙ.6፡12-23፡፡ ደራሲውም ይህንን ታሪክ ካስታወሰ በኋላ «ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ - ዳዊት ለ #እመቤታችን ምሳሌ በሆነች በታቦተ ጽዮን ፊት እንደዘመረ እኔም በሥዕልሽ ፊት ላንቺ እዘምራለሁ»፤ «ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐትኪ ቁርባነ በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ ሜልኮል፡- በዳዊት ይቀርብ የነበረውን የታቦተ ጽዮንን ምስጋና በመናቋ እንደተረገመች ያንቺንም ተአምርሽንና ምስጋናሽን የሚንቅ ሁሉ በሰውና በመላእክት አፍ የተረገመ ይሁን» የሚል ነው፡፡ ሜልኮል የምሳሌዋን የታቦተ ጽዮንን ምሥጋና በመናቋ ከተረገመች ዛሬ የአማናዊቷን ታቦተ ጽዮን የ #እመቤታችንን ምሥጋና የሚንቁና ምሥጋና የሚያቀርቡትን የሚነቅፉ ሰዎች ምን ያኽል የተረገሙ ይሆኑ? እነዚህም «በድፍረትና በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ» /መዝ.3ዐ÷18/ ባለው ርግማን የተረገሙ ናቸው፡፡

2.2. እንበይነ አውሎጊስ ለዳንኤል አመ አርአዮ ስቅለተ፣
ከመ እገሪሁ ሰዓምኪ ወሰአልኪዮ ምሕረተ፣
ለተአምረ ሣህል ወልድኪ በእንተ ፍቅረ ሰብእ ዘሞተ፣
እንዘ ታዘክሪዮ ድንግል ይምሐረኒ ሊተ፣
ከናፍሪሁ ጽጌ አንኂ ስዕመተ፡፡

አውሎጊስ የሚባል የወፍጮ ድንጋይ እየጠረበ በመሸጥ ከዚያ በሚያገኘው ትንሽ ገቢ የሚተዳደር ደኃ ሰው ነበር፡፡ የሚያገኘውንም ገንዘብ ለራሱ ትንሽ ለዕለት ኑሮው ካስቀረበ በኋላ ከርሱ የባሰባቸው ችግረኞችን እየረዳ ይኖር ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በዚህ ግብር ሳለ አባ ዳንኤል የሚባል ባሕታዊ ያየዋል፡፡ ይህም ባሕታዊ አውሎጊስ በዚህ በድህነት ኑሮው እንደዚህ ድሆችን የሚረዳ ከሆነ ብዙ ገንዘብማ ቢያገኝ ምን ያክል ብዙ ሰው በረዳና መልካም ሥራ በሠራ ነበር» ብሎ #እግዚአብሔር ለዚህ ሰው ብዙ ሀብት እንዲሰጠው ሱባኤ ያዘ፡፡ #እግዚአብሔርም ሀብት ለዚህ ሰው /ለአውሎጊስ/ እንደማይጠቅመው ቢነግረውም አባ ዳንኤል በራሱ ሀሳብ ብቻ በመጓዝ ሀብቱን እንዲሰጠው አጥብቆ ስለተማፀነ እንደለመነው ሊያደርግለት ጸሎቱን ተቀበለ፡፡ ከዚህ በኋላ አውሎጊስ እንደልማዱ ድንጋይ ሲቆፍር በማሰሮ የተቀበረ ወርቅ አገኘ፡፡ ወርቁን ወስዶ ለንጉሡ ሰጠ፡፡ ንጉሡ ወርቅ ሲያገኝ ለራሱ ሳያደርግ ለንጉሥ የሚያመጣ ሰው ምን ያክል ታማኝ ቢሆን ነው ብሎ በዚያው በቤተ መንግሥቱ እንደራሴ አድርጎ ሾመው፡፡ አውሎጊስ ከተሾመ በኋላ አጃቢው ክብሩና ሀብቱ ሲበዛ ትሩፋት መጨመሩ ቀርቶ የቀደመ ሥራውንም ተወ፡፡ ለተበደለ የማይፈርድ ባለጉዳይ የሚያጉላላ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ዳንኤል በሕልም #እግዚአብሔር ሲቆጣውና ሲፈርድበት አየ፡፡ የማይገባ ልመና ለምኖ አውሎጊስን የቀደመ ትሩፋቱን እንዲተውና አሁን እንዲበድል ምክንያት ሆኗልና፡፡ አባ ዳንኤል በደሉ ገብቶት ከ #ሥዕለ_ማርያም ሥር ወድቆ ተማፅኖ #እመቤታችን ልጇን ተማጽና ይቅር አስባለችው፡፡
አባ ዳንኤል በሕልም ያየው ነገር ስለከበደው ምናልባት አውሎጊስ ድሀ በድሎ ፍርድ አጓድሎ እንደሆነ ብሎ ሊያየው ቢሄድ እርሱንም የማያናግረው ሆነ፡፡ «ስለ ሰው ፍቅር የሞተ ልጅሽን ስለ አባ ዳንኤል ለምነሽ እንዳስማርሽው እኔንም ይቅር እንዲለኝ የጽጌ ልጅሽን ምሕረት ለምኝልኝ» በማለት እኛንም ባላወቅነው እየገባንና እየፈረድን ለሚመጣብን ቅጣት እንድታስምረን የሚያመለክት ነው፡፡

2.3. ኦ ረዳኢተ ድኩማን ዘይረድአኪ ኢትኃሥሢ፣
እምንበረ ላዕክኪ በምዕር ከመ ገፍታዕኪዮ ለወራሲ፣
ለገፍትዖ ፀርየ ድንግል ኃይለ ጽጌኪ ልበሲ፣
እንዘ ይሣለቅ ተአምረኪ ወሐሰተ ይሬሲ፣
መፍትውኑ ከመ ይህየው ከይሲ፡፡

#እመቤታችንን ተአምር አሰባስቦ የጻፈው ቅዱስ ደቅስዮስ ነው፡፡ #እመቤታችንም ለዚህ ውለታው ሌላ ሰው የማይቀመጥበት ሰማያዊ ወንበር እና ሌላ ሰው የማይለብሰው አጽፍ ሰጥታዋለች፡፡ ከደቅስዮስ ዕረፍት በኋላ በእርሱ ቦታ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ በዚህ መንበር ለመቀመጥና አጽፉን ለመልበስ ሲል «ተው ይህ ለደቅስዮስ ብቻ የተሰጠ ነው» ቢሉት «እኔም እንደርሱ ኤጲስ ቆጶስ ነኝ ከእርሱ በምን አንሳለሁ?» በማለት ከወንበሩ ሲቀመጥ ወዲያው ሞቷል፡፡ ከላይ የተጻፈው ድርሰትም የሚያስረዳው ይህንን ነው፡፡ «ድኩማንን፣ ችግረኞችን የምትረጅ አንቺ ግን ረዳት የማትሽ ሆይ ከወዳጅሽ ከደቅስዮስ ወንበር ላይ በትዕቢትና በድፍረት የተቀመጠውን እንደተቀበልሽው የእኔንም ጠላቶች አጋንንትን እኩያት ኃጣውእን ለማስወገድ የጽጌሽን ማለት የልጅሽን ኃይል ይዘሽ ተነሽ» በማለት ለወዳጆቿ የምትቆም #እመቤታችን ከጠላታችን እንድትታደገን ከታሪኩ አንጻር የቀረበ ጸሎት ነው፡፡

2.4. «በጌጋየ አዳም ወሔዋን ሱራፌል ዘአጸዋ፣
እንበለ ጽጌኪ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኃዋ፣
ተፈሥሒ ድንግል መያጢተ አዳም እምጼዋ፣
በተአምርኪ ውስተ ምድረ ጽጌ አቲዋ
ከመ ጣዕዋ አንፈርዓፀት ጼዋ፡፡

አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት ከገነት ተባረው ወደ ምድረ ፋይድ እንዲወርዱ ተፈርዶባቸው ገነትን ሱራፌል መልአክ በምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍ ይጠብቅ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀት ገነትን «እንበለ ጽጌከ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኃዋ፤ ያለ አንቺ ጽጌ ያለ #ክርስቶስ በሱራፌል ስትጠበቅ የነበረችውን ገነት ሊከፍታት የቻለ ማንም ፍጥረት የለም» ዘፍ.3፡24፡፡ ካንቺ በተገኘ በ #ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሯና ቦታዋ የተመለሰች ሔዋን የእናቱን ጡት ጠብቶ ደስ እንደሚሰኝ እንደሚዘል እንቦሳ ደስ ተሰኘች፡፡ በአጠቃላይ ይህ የሚያስረዳው ያለ #ክርስቶስ ሰው መሆንና በ #መስቀል ተሰቅሎ ቤዛ መሆን ማንም የገነትን በር ሊከፍት እንደማይችል ሲሆን የተዘጋውን የገነት በር የከፈተና የሰው ልጅ ያጣውን የልጅነት ጸጋ የመለሰ #ክርስቶስ ደግሞ ከ #እመቤታችን የተገኘ መሆኑን ነው፡፡ #እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት «መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ» ኢሳ.46÷13፡፡ እንዳለ የተዋረደው የሰው ልጅ የከበረበትና የዳነበት መድኃኒት #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተገኘው ጽዮን ከተባለች ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም ነው፡፡ ይህንን መድኃኒት ለዓለሙ ያበረከተች እርሷ ናት፡፡

3. #ተግሣጽ

አባ ጽጌ ድንግል ይህንን ማኅሌተ ጽጌ ሲደርስ ለ #መስቀልና#እመቤታችን ክብርና ስግደት አይገባም የሚሉ ደቂቀ እስጢፋ የሚባሉ መናፍቃን ተነሥተው ነበር፡፡ በዘመኑ የነበሩት ንጉሥ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጉባኤ አሠርተው አከራክረው መናፍቃኑ ተረትተዋል፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እነዚህን የ #እመቤታችንን ተአምርና ክብር በመግለጽ መናፍቃንን በመገሰጽ በዚህ የተግሣጽ ድርሰታቸው አስተምረዋል፡፡ ለምሳሌ የተወሰኑትን እንመልከት፦
ከመ ይትፌሣሕ ጻድቅ ሶበ ይሬኢ በቀለ፣
በተበቅሎ ፀር ያርኢ ዘተአምርኪ ኃይለ፣
እፎ የሐዩ እመአምላክ እንተ ኪያከ ፀአለ፣
አኮኑ በፍትሐ ጽጌኪ ይሙት ተብህለ፣
ላዕለ አቡሁ ወእሙ ዘአሕስመ ቃለ፡፡

ጻድቅ #እግዚአብሔር ጠላቶቹን ሲበቀልለት ሲያይ ደስ ይለዋል፡፡ ይኸውም የአንቺን ተአምር ኃይል ያሳይ ዘንድ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ያንቺን ተአምር የሚንቁና አንቺን የማያከብሩ ከሐድያን እንዴት በሕይወት ሊኖሩ ይገባቸዋል? ምክንያቱም «በልጅሽ በክርስቶስ ትእዛዝ «እናቱን ወይም አባቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል» /ዘጸ.21፡17/ ተብሎ ተፈርዷልና፡፡ እናት አባቱን የሰደበ ሞት የሚገባው ከሆነ #ክርስቶስ ሰማያዊውን አምላክ ወልዳ፣ ጡቷን አጥብታ፣ አዝላ፣ ተሰዳ ለዓለም ሕይወት ባበረከተችው በ #ድንግል_ማርያም ላይ ቃልን የተናገረማ እንዴት ያለ መከራ ይጠበቀው ይሆን?

ይቀጥላል…
#ጥቅምት_4

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት አራት በዚች ቀን #ቅዱስ_ባኮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱሳን_ነገሥታት_አብርሃ_ወአጽብሓ ያረፉበትም ዕለት ነው፣ ሐዋርያው #ቅዱስ_ሐናንያ በሰማዕትነት ዐረፈ፣ #አቡነ_በርተሎሜዎስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ባኮስ

ጥቅምት አራት በዚህች ቀን የቅዱስ ሰርጊስ ባልንጀራ ቅዱስ ባኮስ በከሀዲ ንጉሥ አንጥያኮስ እጅ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም እንዲህ ነው እሊህን ቅዱሳን ከሀዲው ንጉሥ መክስምያኖስ በያዛቸው ጊዜ እነርሱ ወታደሮች ነበሩና ትጥቃቸውን ቆርጦ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ወደ ሶርያ አገር ወደ ንጉሥ አንጥያኮስ ሰደዳቸው። እርሱም ቅዱስ ሰርጊስን አሠረው ቅዱስ ባኮስን ግን ሰቅለው እንዲደበድቡት በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠልጥለው ከኤፍራጥስ ወንዝ ከባሕር እንዲጥሉት አዘዘ ንጉሡም እንደ አዘዘ እንዲሁ አደረጉ።

#እግዚአብሔር ግን የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ጠብቆ ወደ ወደብ አደረሰው በዚያ ወደብ አቅራቢያም በገድል ተጠምደው የሚኖሩ የአንደኛው ስሙ ማማ የሁለተኛው ባባ የሚባሉ ባሕታውያን አሉ። ለእሊህ ወንድሞችም ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጠላቸውና ሒደው የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ወደ በዓታቸው እንዲወስዱ አዘዛቸው።

በዚያንም ጊዜ መልአክ እንዳዘዛቸው ሔዱ የቅዱስ ባኮስንም ሥጋ አገኙ በአጠገቡም አንድ ቀንና አንድ ሌሊት ሲጠብቁት የነበሩ አንበሳና ተኵላ አሉ እነርሱም ከሰው ሥጋና ከእንስሳ በቀር የማይመገቡ ሲሆኑ ግን ከልዑል አምላክ ዘንድ ስለታዘዙ ነው። እሊያ ቅዱሳንም የቅዱስ ባኮስን ሥጋ ወሰዱ በታላቅ ክብር እያመሰገኑ እስከ በዓታቸውም አድርሰው በዚያ ቀበሩት።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ባኮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን!!

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_ነገሥታት_አብርሃ_ወአጽብሓ

ዳግመኛም በዚህ ቀን ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ያረፉበት ነው። አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ (አህየዋ) ይባላሉ፡፡ መንትዮች የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን የተወለዱት ጌታችን በተወለደባት ዕለት በታኅሣሥ 29 ቀን 312 ዓ.ም ነው፡፡ በታላቁ አባት በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እየተማሩ አድገው በእሳቸው እጅ በ330 ዓ.ም መጋቢት 29 ቀን ተጠመቁ፡፡ በእነርሱም ጊዜ አማናዊው ጥምቀትና ቁርባን መጣልን፡፡ በሀገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ያሠሩ ሲሆን 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡ በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዓርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡

አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በአክሱም ሲኖሩ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ብቻ የዛፍ ቅጠሎችን ከመመገብ በቀር ሌላ ምግብ ባለመመገብ በታላቅ ተጋድሎ ይኖሩ ነበር፤ አህልም አይቀምሱም፤ በየቀኑም አምስት ሺህ ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡ በእርሳቸውም የተጋድሎ ዘመን ደጋግ የሆኑ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃና አጽብሓ ነገሡ፡፡

ነገሥታቱም ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንን እጅግ በጣም ይወዷቸው ነበር፡፡ አባታችንም በእንዲህ ዓይነት ተጋድሎ ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን የብርሃን እናቱ #ድንግል_ወላዲተ_አምላክ ለአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ተገልጣላቸው ‹‹ዲቁናና ቅስናን መቀበል ይገባሃል፣ ለጵጵስና ተዘጋጅ፣ #እግዚአብሔር ይህችን ከፍ ያለችውን ማዕረግ ሰጥተሃልና የልጄ ወዳጅ ሆይ በጸሎትህና በልመናህ በስብከትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁሉ ይድናሉ፣ በእጅህ ጥምቀትንና ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ›› አለችው፡፡ #ጌታችንም እንዲሁ ተገልጦላቸው ‹‹ወደ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አትናቴዎስ ሄደህ ከፍ ያለችውን ማዕረግ ተቀብለህ የኢትዮጵያን ሰዎች አጥምቅልኝ፣ ነቢዩ ዳዊት ስለ እነርሱ ‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ #እግዚአብሔር ትዘረጋለች› ብሎ ተናግሯልና›› አላቸው፡፡ ነገሥታቱ አብርሃንና አጽብሓ ነገረ #ክርስቶስን እያሰቡ ስለ ጥምቀት ልጅነት ይጨነቁ ነበር፡፡ ከሊቀ ካህናቱም ጋር በዚህ ጉዳይ ሲጨዋወቱ ሊቀ ካህናቱ ስለ አቡነ ሰላማ ነገሯቸው፡፡ ነገሥታቱም አቡነ ሰላማን አስጠርተው ስለነገረ #ክርስቶስ ምሥጢር እንዲያስረዷቸው ጠየቋቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ነቢያት በ #መንፈስ_ቅዱስ ተቃኝተው አካላዊ ቃል #እግዚአብሔር_ወልድ ይወለዳል ካሉበት ጀምሮ የልደቱን፣ የትምህርቱን የጥምቀቱን፣ የስቅለቱን፣ የሞቱን፣ የትንሣኤውንና የእርገቱን ነገር ሌላውንም ሁሉ ተንትነው አስተማሯቸው፡፡ ሐዋርያትም በጌታ ተሾመው ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውን እንዲሁ ተረኩላቸው፡፡ ነገሥታቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደስ ብሏቸው ፍሬምናጦስን ‹‹ወንድማችን ሆይ! ይህን ሥርዓት በሀገራችን እንድታስፋፋ›› አሏቸው፡፡ አባታችን ግን ‹‹ለዚህ የሚያበቃ ሥልጣን ያለው እንጂ ለእኔ አይቻለኝም›› አሉ፡፡ ነገሥታቱም ‹‹ይህን የሚችል ማነው?›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹‹በእስክንድርያ ጳጳሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን የሚሾም አባት አለ አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ነገሥቱ ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ አትናቴዎስ ደብዳቤ በመጻፍ ‹‹አባታችንና መምህራችን ሆይ! የምንጠይቅህን እሺ በጀ በለን ይኸውም ወደ ጽድቅ ጉዳና የሚመራንን ጳጳስ ሹምልን›› በማለት ብዙ ወርቅና ብር ገጸ በረከት አስይዘው ከብዙ ሊቃውንት ጋር ፍሬምናጦስን ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡

ከዚህም በኋላ አባታችን ከነገሥታቱ አብርሃና አጽብሓ ጋር ተማክረው ወደ እስክንድሪያ ሄደው በቅዱስ አትናቴዎስ እጅ በአገራችን ላይ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ታኅሳስ 18 ቀን ተሾሙ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ከሾሟቸውና ከመረቋቸው በኋላ ለአቡነ ሰላማና አብረውት ለነበሩ ሊቃውንት መጻሕፍተ ብሉያትን፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትንና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ታቦተ #ማርያምን፣ ታቦተ #ሚካኤልንና ታቦተ #ገብርኤልን አስይዘው ለነገሥታቱም ደብዳቤ ጽፈው ከብዙ ገጸበረከት ጋር በታላቅ ክብር ሸኟቸው፡፡ ቅዱሳን የሚሆኑ ሁለቱ ነገሥታትም አቡነ ሰላማ ከእስክንድርያ ተሾመው መምጣቸውን በሰሙ ጊዜ ‹‹የኢትዮጵያ ሰዎች ሁላችሁ እስከ 40 ቀን ተሰብሰቡ›› ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ አባታችንንም በደብረ ሲናም ሄደው አገኟቸውና ከዚያች ቀን ጀምሮ ሕዝቡም ሁሉ እስከ 40 ቀን ድረስ ተጠመቁ፡፡ በዚያችም ዕለት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በዚያች በደብረ ሲና አገር ላይ ወረደና ሕዝቡን ሁሉ ባረኮ ተመልሶ ሲያርግ ከአባ ሰላማ በቀር ያየው አልነበረም፡፡ ወደ አክሱምም ሄደው ቅዱሳን ነገሥታቱም የአድባራት ሁሉ የበላይ የምትሆን የቅድስት ጽዮንን ቤተ ክርስቲያን በወርቅና በዕንቊ ሠሯትና አባ ሰላማ ባርከው ቀደሷት፡፡ ታቦተ ጽዮንም ከድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በ #መንፈስ_ቅዱስ ገብታ ተገኘች፡፡
አባታችን በእመቤታችንም በዓለ ዕረፍት ጥር 21 ቀን በውስጧ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀድሱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በግራ በቀኝ እየተራዷቸው እርሳቸውም ከምድር ሦስት ክንድ ከፍ ብለው ሥርዓተ ቅዳሴውን ፈጽመው ለነገሥታቱና ለሕዝቡም ሁሉ አቆረቧቸው፡፡ የዚያን ዕለትም እጅግ ታላቅ በዓልን አደረጉ፡፡
#እግዚአብሔር የተለያዩ ምሥጢራትን ይገልጥለታል፡፡ በሄኖክ መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ያለው የሰማይ ምሥጢር ሁሉ ተገለጠለት፡፡ የፀሐይ፣ የጨረቃ፣ የብርሃናት አፈጣጠራቸው፣ የንፋስ መስኮቶቸን ሁሉ በግልጥ ባየ ጊዜ ነቢዩ ሄኖክን ‹‹ሄኖክ ሆይ የራእይህ ምሥጢር እንደዚህ ብሩህ ነውን? የምሥጢርህ መሰወር እንዲህ ግልጥ ነውን?›› ይለዋል፡፡ ዳግመኛም የነቢያት የትንቢታቸው ራእይ ይገለጥለት ዘንድ 40 ቀንና 40 ሌሊት በመጾም ሱባኤ በያዘ ጊዜ የመጻሕፍቶቻቸው ምሥጢር ይገለጥለታል፡፡

ከዚህም በኋላ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል በመማለጃ (በጉቦ) ክህነት በሚሰጥ ጳጳስ ምክንያት በሐዋርያት ግዝት ዓለም ሁሉ በግዝት እንደሚኖር ተመለከተ፡፡ ወደ ጳጳሱ አባ ዮሐንስ ዘንድ ሄደና አገኘው፡፡ ጳጳሱም ‹‹ልጄ በጸሎተ ሚካኤል ደህና ነህን?›› አለው፡፡ አባታችንም ‹‹ደህና ነኝ›› ባለው ጊዜ ጳጳሱ ‹‹ስለምን መጣህ?›› አለው፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ሰው ሁሉ ከአጠገባቸው እንዲርቅ ካደረገ በኋላ ጳጳሱን እንዲህ አለው፡- ‹‹ቅዱሳን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው መጽሐፍ ‹በመማለጃ ክህነትን የተቀበለና የሰጠ የተለየ የተወገዘ ነው› ያሉትን አልሰማህምን?›› አለው፡፡ ዳግመኛም ‹‹እጄን በጫንኩበት #መንፈስ_ቅዱስ ይወርድ ዘንድ ተናገሩ ብሎ በሐዋርያት እግር ሥር ወርቁን አምጥቶ ባፈሰሰው ጊዜ ሲሞን መሠርይን ጴጥሮስ እንዳወገዘው አልሰማህምን? ጴጥሮስም ‹ወርቅህና ብርህ ለጥፋት ይሁንህ፣ የ #እግዚአብሔር ጸጋ በወርቅ የምትገዛ ይመስልሃልን?› አለው፡፡ በመራራ መርዝ ተመርዘህ አይሃለሁና፡፡›› ሐዋ 8፡19፡፡ ‹‹አባቴ ሆይ የውኃ ምንጭ የፈሰሰ የደፈረሰ እንደሆነ የምፈሰውም ውኃ ሁሉ ይደፈርሳል፡፡ ምንጩ ንጹሕ ከሆነ ግን የውኃው ፈሳሽም ሁሉ የጠራ ይሆናል፡፡ አንተ በሐዋርያት ውግዘት ብትገባ ሁሉም የተወገዘ ይሆናል›› አለው፡፡ ጳጳሱም ተቆጥቶ ‹‹አንተ ከእኔ ተማር እንጂ ለእኔ መምህር ልትሆነኝ ትፈልጋለህ?›› በማለት ተናገረው፡፡ በወንጌል ላይ ‹‹እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምዘጉ ወዮላችሁ፣ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም ትከለክሏቸዋላችሁ›› ያለው የ #እግዚአብሔር ቃል በእርሱ ላይ ደረሰ፡፡ ማቴ 23፡14፡፡

ከዚህም በኋላ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ወደ ካህናተ ደብተራ በመሄድ ከንጉሡ ጋር ያገናኙት ዘንድ ጠየቃቸው፡፡ የቤተ መንግሥት ካህናትም ለንጉሡ ነግረውለት አስገቡት፡፡ አባታችንም ንጉሡን ‹‹መንግሥትህ በግዝት ጨለመች፣ ሐዋርያት ጥምቀትም ቢሆን ወይም ክህነት በመማለጃ (በጉቦ) የሚሰጥንና የሚቀበልን አስቀድመው ሐዋርያት አውግዘዋል›› አለው፡፡ ዳግመኛም ‹‹እነሆ ይህ ጳጳስ የሐዋርያትን ትእዛዝ ተላልፎ በጉቦ ክህነት ይሰጣል፣ ጳጳሱም በሐዋርያት ግዝት ከገባ በእጁ የተጠመቁና የተሾሙት ሁሉ የተወገዙ ይሆናሉ፣ እንደዚሁ ዓለሙ ሁሉ በውግዘት ውስጥ ይኖራል›› አሉው፡፡ ንጉሡም ሦስቱ አንድ ላይ ሆነው እንዲነጋገሩ ቀጠሮ ሰጠውና በሌላ ቀን ሦስቱም ተገናኙ፡፡ ጳጳሱም ለንጉሡ ‹‹ይህ በጸሎተ ሚካኤል እኔን ከሹመቴ አንተን ከመንግሥትህ ሊሽረን ይፈልጋል ስለዚህ ልጄ የምነግርህን ስማኝ አስረህ ወደ ትግራይ ይወስዱት ዘንድ እዘዝ›› አለው፡፡ ንጉሡም የጳጳሱት ክፉ የሀሰት ምክር በመስማት ‹‹ይሁን አንተ እንዳልከው ይሁን›› በማለት አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን በጽኑ ማሠሪያ አስረው በግዞት ወደ ሳርድ ይወስዱት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጭፍሮቹም እንደታዘዙት አደረጉና አባታችን በዚያ በግዞት ሁለት ዓመት ታስሮ ቆየ፡፡ ከዚያም ወደ ጽራይ ምድር ወሰዱትና ቆራር በተባለ ቦታ ለተሾመው ሰው ‹‹እንደ ንጉሡ ትእዛዝ ይህንን መነኩሴ እሰረው›› ብለው ሰጡት፡፡ የሀገሩ ሰዎችም አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እጅግ ወደዱትና ወደ ጽራር ሀገር ገዥ ሄደው እንዲፈታው ለምነው ከእስራቱ አስፈቱት፡፡ በሀገራቸውም ወንጌልን አስተምሮ ብዙ ተአምራት እያደረገላቸው ከቆየ በኋላ ወደ ልጁ ሳሙኤል ለመሄድ ተነሣ፡፡ ሲሄድም አቡነ ገብረ ናዝራዊ ጋር ደረሰና አብረው ሳሙኤል ጋር ደረሱ፡፡

አቡነ በጸሎተ ሚካኤል በቅዳሴ ጊዜ #ጌታችን በሕፃን ልጅ አምሳለ በመንበሩ ተቀምጦ ስለሚያየው ሁልጊዜ ሲቀድስ ያለቅሳል፡፡ አንድ ቀን አባታችንን ሲቀድስና ሕፃኑን በመንበሩ ላይ ሲሠዋው ወንድሞቹና ልጆቹ አይተውት በድንጋጤና በፍርሃት ሆነው አልቅሰዋል፡፡ የሕፃኑንም ሥጋ በፈተተው ጊዜ የአባታችን እጁ በለመለመ ሥጋ ይመላል፡፡ ቅዳሴውም ከተፈጸመ በኋላ ሁሉም መጥተው ቅዱስ ሥጋወደሙን በፍርሃት ይቀበላሉ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ አስቀድመው ስለ ሥጋወደሙ መለወጥ ጥርጣሬ የነበራቸው ሰዎች ስለነበሩ የእነርሱን ጥርጣሬ ዐውቆ አባታችን ቅዳሴውን ከፈጸመ በኋላ ‹‹ኅብስቱ የ #ክርስቶስ ሥጋ ወይኑም ደሙ መሆን ይችላልን እያላችሁ በልባችሁ ስታስቡ አይቻለሁና ይኸው ዛሬ በግልጽ እንዳያችሁት አማናዊ ሆኖ ይለወጣልና ተጠራጣሪ አትሁኑ›› ባላቸው ጊዜ እግሩ ሥር ወድቀው ‹‹አንተ ብፁዕ ነህ የተሸከመችህም ማኅፀን ብፅዕት ናት… ›› ብለው ይቅር እንዲላቸው ለመኑት፡፡ አባታችንም ወንጌልን አስተማራቸው፡፡ መነኮሳት ልጆቹ ሩቅ ቦታ እየሄዱ ውኃ በመቅዳት ቢቸገሩ ውኃን አፍልቆላቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ሰዎቹ አንድ ነገር ልንነግርህ እንወዳለን አሉት፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ንገሩኝ ባላቸው ጊዜ የአባቱን ሚስት ስላገባው ንጉሥ ነገሩትና ሄዶ እንዲያስተምረው እንዲገሠጸው ለመኑት፡፡ አባታችንም ‹‹በጽኑ ማሰሪያ ታስሬ በእስር ስለነበርሁ አልሰማሁም›› ካላቸው በኋላ ሄዶ ቢሰማው እንደሚመክረው ባይሰማውና ባይመለስ ግን እንደሚያወግዘው ነገራቸው፡፡ አባታችንም ልጆቹን አስከትሎ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄደ፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ‹‹ንጉሡ የአባቱን ሚስት በማግባቱ ሄደን ስንገሥጸው መከራ ቢያጸናብን ከሰማዕትነት ይቆጠርልናል›› ብሎ ሲነግራቸው ከሰማይ #መንፈስ_ቅዱስ ወርዶ በሁሉም በላያቸው ላይ ሲወርድ አባታችን በግልጽ ተመለከተ፡፡ በረኃብ በጥም ሆነው ከተጓዙ በኋላ ትግራይ ሰወን ከምትባል ሀገር ደረሱ ንጉሡ ከዚያ ነበረና፡፡ ንጉሡም ቅዱሳኑ መክረው ሊመልሱት ካልሆነም ሊያወግዙት መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ ጭፍሮቹን ልኮ ቅዱሳኑን ወደ እርሱ እንዲያመጧቸው አዘዘ፡፡

ለማስፈራራትም ብዙ ጦረኛ ጭፍሮችንና የታሰሩ አስፈሪ አንበሶችን በፊቱ አቆመ፡፡ ቅዱሳኑንም ‹‹ስለምን ወደዚህ ከተማ መጥታችኋል?›› አላቸው፡፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልም ‹‹እውነትን ስለማጽናት ከአንተ ጋር ለመነጋገር መጥተናል›› አሉት፡፡ ንጉሡም እሺ ንገሩን ባላቸው ጊዜ አባታችን የ #እግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለጠበቁ ደጋግ ነገሥታት ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ ንጉሡን አስተማሩት፡፡

ትእዛዙንም ያልጠበቁትን አመፀኞችን እንደቀጣቸው ነገሩት፡፡ በመጨረሻም ‹‹የአባትህን ሚስት ሀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፣ የአባትህ ሀፍረተ ሥጋ ነውና›› የሚለውን ኦሪት ዘሌ 18፡6 በመጥቀስ አስተማሩት፡፡ ዳግመኛም ‹‹ከአባቱ ሚስት ጋር የተኛ የአባቱን ሀፍረት ገልጧልና መሞትን ይሙት ሁለቱም በደለኞች ናቸውና›› የሚለውን የሙሴን ሕግና ሌላም ከሐዲስ ኪዳን እየጠቀሱ አስተማሩት፡፡ አባታችን ካስተማሩት በኋላም ‹‹የክርስቲያን ሚስቱ አንድ ብቻ ናት አንተ ግን ብዙ ሚስት አግብተህ የአባትህንም ሚስት አግብተሃልና ሕግ ተላልፈሃል›› አሉት፡፡ ንጉሡም ተምሮ ከመመለስ ይልቅ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱሳኑን ይደበድቧቸው አዘዘ፡፡ ሲደብድቧቸውም ታላቅ ጩኸት ተነሣ፡፡ ለየብቻ አስረው ካሳደሯቸው በኋላ ንጉሡ ለየብቻ ወደ እርሱ እያስመጣ አናገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውንም በ7 ገራፊዎች በታላቅ ጅራፍ አስገረፋቸው፡፡ ደማቸውም እንደ
#ጥቅምት_7

#አባ_ባውላ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሰባት በዚች ቀን ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ።

ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ #ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና።

#መጀመሪያው ራሱን በዕንጨት ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት እንደ ተሰቀለ ኖረ። ደሙም በአፍንጫው ፈሰሰ ነፍሱንም አሳለፈ #እግዚአብሔርም ከሞት አነሣው።

#ሁለተኛው ዓሣዎችና ዓንበሪዎች እንዲበሉት ራሱን ከባሕር ጨመረ እነርሱ ግን አልነኩትም በባሕርም ሠጥሞ ብዙ ወራት ኑሮ ሞተ። ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ዳግመኛ ከሞት አስነሣው።

#ሦስተኛም ጊዜ ራሱን በአሸዋ ውስጥ ደፍኖ ሞተ #ጌታችንም አስነሣው።

#አራተኛም በውስጡ ስለታሞች ድንጋዮች ካሉት ረጅም ተራራ ላይ ወጥቶ ራሱን ከተራራው ላይ ወደ ታች ወርውሮ ተንከባለለ የተሳሉ ደንጊያዎችም በሥጋው ሁሉ ገብተውበት ሞተ። ረድኡም ያለቅስለት ነበረ #ጌታችንም መጥቶ ከሞት አሥነሣው አጽናናውም ።

#አምስተኛ ከረጅም ዛፍ ላይ ወጥቶ ከስለታም ደንጊያ ላይ ራሱን ወረወረ ከሁለትም ተከፈለና ሞተ ያን ጊዜም #ጌታችን አስነሣው።

#ስድስተኛ ራሱን በእግሮቹ ውስጥ አሥሮ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት እንዲህ ሁኖ ሞተ #እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ከሞት አነሣው አጽናናውም።

#ሰባተኛ ከውኃ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ እጆቹን ዘርግቶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት በመቆም ሞተ ክብር ይግባውና #ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ።

አባ ባውላም ለ #መድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት #ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ። #ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ።

ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ #ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ።

ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

በተጨማሪ በዚች ቀን #የአባ_ባውላ_ረድእ_አባ_ሕዝቅኤል መታሰቢያቸው፣ የቅዱሳን ሰማዕታት #የሚናስና_የሐናሲ_መታሰቢያቸው ነው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_7)