ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
183K subscribers
278 photos
1 video
16 files
200 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

...አይሮፕላኑ ወደ ኋላ የማይመለስበት ቦታ ላይ ሊደርስ የቀረው ትንሽ ነው፡፡ ኤዲ አዕምሮው በጭንቀት እንደተወጠረ ከምሽቱ አራት ሰዓት ወደ ስራው ተመልሶ ገብቷል፡ በዚህ ሰዓት ፀሃይ ጠልቃ ጨለማ ነግሷል፡፡
የአየር ጠባዩም ተለውጧል፡፡ዝናቡ
የአይሮፕላኑን መስታወቶች
ይጠልዛቸዋል ኃይለኛው ነፋስ አይሮፕላኑን እንደወረቀት ስለሚወዘውዘው
ተሳፋሪዎቹን ጭንቀት ውስጥ ጥሏቸዋል፡

የአየር ጠባዩ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ መጥፎ ቢሆንም ካፒቴኑ
የሚያበረው ባህሩ ጋ አስጠግቶ ነው፡፡ ከምዕራብ አቅጣጫ የሚመጣው ነፋስ
ዝቅተኛ የሆነበትን ከፍታ ለማግኘት ሲል ነፋሱን እያሳደደ ነው፡፡

የአየር ጠባዩ በትንበያው ከተገመተው በላይ እየተበላሸ በመምጣቱ
ሞተሮቹ ከተጠበቀው በላይ ነዳጅ አቃጥለዋል፡ ኤዲ ነዳጁ አነስተኛ መሆኑን በማወቁ ተጨንቋል፡፡ በነዳጅ ማጠራቀሚያው ውስጥ በቀረው ነዳጅ ምን ያህል ኪሎ ሜትር ሊሄድ እንደሚችል ለማስላት የስራ ቦታው ላይ ቁጭ አለ፡፡ የቀረው ነዳጅ ኒውፋውንድ ላንድ ካናዳ የማያደርስ ከሆነ አይሮፕላኑ ወደ ኋላ መመለስ የማይችልበት ቦታ ከመድረሱ በፊት ወደኋላ መመለስ አለበት።

ታዲያ ካሮል አን ምን ሊውጣት ነው?

ቶም ሉተር ጠንቃቃ በመሆኑ አይሮፕላኑ ሊዘገይ የሚችል መሆኑን ግምት ውስጥ አስገብቶ ከጓደኞቹ ጋር ያለውን ቀጠሮ ለማስረገጥ ወይም
ለማስለወጥ መንገድ ይፈልጋል፡፡

አይሮፕላኑ ወደ ኋላ የሚመለስ ከሆነ ካሮል አን በአፋኞቿ መዳፍ ስር ለሃያ አራት ሰዓት መቆየቷ ነው፡፡ ኤዲ ከስራ ውጭ በሆነበት ጊዜ ሁሉ አስሬ በአይሮፕላኑ መስኮት ሲመለከት አመሸ፡፡ እንቅልፍ እንደማይወስደው ስላወቀ ለመተኛት እንኳ አልሞከረም፡፡ ካሮል አን በዓይነ ህሊናው እየታየችው ጭንቅ ጥብብ ብሎታል ወይ ስታለቅስ ወይ እጅ እግሯ ታስሮ ወይ በድብደባ ቆስላ ወይ ፍርሃት ፍርሃት ብሏት ወይ ተስፋ ቆርጣ ትታየዋለች፡፡ ምንም ሊያደርግላት አለመቻሉን ሲያስበው በንዴት የአይሮፕላኑን ግድግዳ በጡጫ ይጠልዘዋል፡
አንድ ሁለት ጊዜ ደግሞ ለእሱ ተተኪ ለሆነው ሚኪ ፊን ስለአይሮፕላኑ የነዳጅ ፍጆታ ለመንገር በደመነፍስ በደረጃው እየወረደ ከራሱ ጋር እየታገለ ሳይነግረው ተመልሷል፡

ኤዲ ቶም ሉተርን በመብል ክፍሉ ውስጥ በነገር የነካካው አዕምሮው
በመረበሹ ነው፡፡ ቶም ሉተር ደግሞ ብዙም አይናገርም፡፡ እድሉ ሲጠም.ደግሞ ሁለቱ አንድ ጠረጴዛ ላይ ለመብል ተገናኙና አረፉት፡፡ ከራት በኋላ ኤዲ ምን ያህል ስርዓት የጎደለው ተግባር በተሳፋሪ ላይ ሲፈጽም እንደነበረ ጃክ ሲነግረው አመሸ፡፡ ኤዲና ቶም ሉተር የተጣሉበት ነገር እንዳለ ጃክ አውቋል፡፡ ጃክ ኤዲ ብዙም ሊነግረው እንዳልፈለገ ስለገባው ለአሁኑ ያለውን ተቀብሎታል፡፡ ኤዲ ከዚህ በኋላ መጠንቀቅ እንዳለበት አምኗል፡፡ ካፒቴን ቤከር የበረራ መሀንዲሱ የተሳፋሪዎችን ደህንነት የሚጎዳ ተግባር በግዴታ
እንዲፈጽም መታዘዙን ከጠረጠረ እንኳን አይሮፕላኑን ወደ ኋላ ከመመለስ አይቆጠብም፡፡ ይህም ኤዲ ሚስቱን ከእገታው ለማውጣት የሚያደርገውን መፍጨርጨር ያደናቅፍበታል፡፡ ስለዚህ  ካፒቴኑ  አንድም ነገር ማወቅ የለበትም።

በመርቪን ላቭሴይና በሎርድ ኦክሰንፎርድ መካከል የተነሳው
ጠብ  ትዕይንት ኤዲ በቶም ሉተር ላይ ያሳይ የነበረውን ሁኔታ
እንዲረሳ አድርጎታል፡፡ ኤዲ ሌላ የአይሮፕላኑ ክፍል ውስጥ ሆኖ በሃሳብ ተውጦ ስለነበር  አላየም፡፡  በኋላ ግን አስተናጋጆቹ የነበረውን ሁኔታ አጫወቱት።ሎርድ ጨካኝ ሰው መሆኑን በመረዳቱ ካፒቴኑ አደብ እንዲገዙ ማድረጉ ኤዲን አስደስቶታል፡ ኤዲ ታዳጊው ፔርሲ በዚህ እርጉም ሰው እጅ
ማደጉ አሳዝኖታል፡

ራት ከተበላ በኋላ ተመልሶ ጸጥታ መንገሱ አይቀርም፡፡ በእድሜ የገፉት ተሳፋሪዎች በየመኝታቸው ላይ ይሰፍራሉ፡፡ ብዙዎቹ በአይሮፕላኑ ውዝዋዜ
እንቅልፍን አጥተውት
ሲያንጎላጁ ያመሻሉ፡፡ ከዚያም አንድ በአንድ እያሉ ይተኛሉ፡፡ እንቅልፍ የማይጥላቸው ተሳፋሪዎች ደግሞ ወይ ካርታ ሲጫወቱ ወይም መጠጣቸውን ሲጨልጡ ያመሻሉ፡፡

ኤዲ የአይሮፕላኑን የነዳጅ ፍጆታ በቻርቱ ላይ ይከትባል፡ በግራፉ
የተመለከተው የአይሮፕላኑ
በቀኝ በኩል የነዳጅ ፍጆታ በእርሳስ
ከተመለከተው የእሱ ትንበያ በላይ ነው፡፡ ኤዲ የሃሰት የነዳጅ ፍጆታ ትንበያ ስላሰፈረ ይህ መሆኑ አይቀርም የአየር ጠባዩ መክፋት ደግሞ በትክክለኛው ፍጆታና በትንበያው ፍጆታ መካከል ያለውን ልዩነት እንዲጎላ አድርጎታል።

በቀሪው ነዳጅ አይሮፕላኑ ሊሄድ የሚችለውን ርቀት አስልቶ ሲጨርስ
ጭንቀቱ በረታ፡፡ የአይሮፕላኑም የነዳጅ መጠን አስተማማኝነት ደንብ እንደሚያዘው የቀረውን የነዳጅ መጠን በሶስት ሞተሮች ፍጆታ ሲያሰላው እስከ ኒውፋውንድ ላንድ እንደሚያደርሰው አወቀ።

ሌላ ጊዜ ቢሆን ይህን ሲያውቅ ለካፒቴኑ ወዲያውኑ መንገር አለበት፡ አሁን ግን አልነገረውም፡፡

የነዳጅ መጠኑ በአራት ሞተር ሲሰላ የነዳጅ እጥረቱ በጣም ስለሚያንስ
ምንም አያስጨንቅም፡፡ ከዚህም በላይ የአየር ጠባዩ ከተወሰኑ ሰዓቶች በኋላ ጸጥ ያለ ይሆን ይሆናል፡ የንፋሱ ግፊት ቀለል ያለ ከሆነ አይሮፕላኑ ከተተነበየው ያነሰ ነዳጅ ስለሚጠቀም ለቀረው ጉዞ ነዳጅ ሊተርፍ ይችላል የከፋ ነገር ከመጣ ደግሞ ርቀቱን ለማሳጠር ሲሉ የጊዜ አቅጣጫቸውን
ይለውጡና በሞገደኛው ንፋስ ውስጥ ይጓዛሉ፡፡ በዚህ አይነት ጉዞ ግን የሚሰቃዩት ተሳፋሪዎች ናቸው፡፡

ከኤዲ በስተግራ የተቀመጠው ራሰ በራው ቤን ቶምሰን በሞርስ ኮድ
የተቀበለውን የሬዲዮ መልእክት ወደ ጽሑፍ እየቀየረ ነው፡፡ ኤዲ ከፊታቸው ያለው የአየር ጠባይ የተሻለ እንዲሆን በመመኘት ከቤን ኋላ ሆኖ መልእክቱን ያነባል፡

የመጣው መልእክት ግን ማስደነቅ ብቻ ሳይሆን እንቆቅልሽ ሆኖበታል፡
መልእክቱ የተላከው ኤፍ.ቢ..አይ ኦሊስ ፊልድ ለሚባል ተሳፋሪ ሲሆን

‹ብቁጥጥር ስር ያለው እስረኛ ተባባሪ ሊሆኑ የሚችሉ ከተሳፋሪዎቹ መካhል ያሉ ስለሆነ በጥብቅ ክትትል አድርግ›› ይላል፡

ምን ማለት ነው? ከካሮል አን አፈና ጋር ግንኙነት አለው ይሆን ይህ
መልእክት?› ሲል አሰበ ኤዲ፡ ይህ ሊሆን እንደሚችል ሲያስበው ራሱን
አዞረው።

ቤን የኮድ ትርጉሙን ቀዶ
«ካፒቴን ይህን መልእክት ብታየው›› ብሎ ለአለቃው አቀበለው፡፡

ጃክ አሽፎርድ የሬዲዮ መገናኛ ባለሙያው አስቸኳይ መልእክት መኖሩን ሲናገር ሰምቶ ከሚያፈጥበት ቻርቱ ላይ ቀና አለ፡፡ ኤዲ ከቤን መልእክቱን ተቀብሎ ለጃክ አሳየውና ራቱን እየበላ ላለው ካፒቴን አሳየው።

ካፒቴኑ መልእክቱን አነበበና ‹‹እንዲህ አይነት ነገር ነው የማልወደው›› አለ፡፡ ‹‹ኦሊስ ፊልድ የኤፍ.ቢ..አይ አባል ሳይሆን አይቀርም::››

‹‹ተሳፋሪ ነው?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡

‹‹አዎ፡፡ ሰውየው እንግዳ ባህሪ ነው ያለው፡ ድብርታም ነው፡፡ የተሳፋሪ
ሁኔታ የለውም: ፎየንስ ላይ ቆይታ ሲደረግ ከአይሮፕላኑ ላይ አልወረደም›› አለ፡፡

ኤዲ ሰውየውን ባያስተውለውም ናቪጌተሩ ጃክ ግን አይቶታል፡
‹‹ያልከውን ሰው አውቄዋለሁ›› አለ ጃክ አገጬን እያከከ፡፡ ‹‹ራሰ በራ
ነው፡፡ አብሮት ልጅ እግር ሰው ተቀምጧል፡ ሰዎቹ ሲታዩ ምናቸውም አይጥምም::››
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_አንድ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ከመሐል አትላንቲክ ወደ ቦትውድ (ካናዳ)


ዳያና ላቭሴይ ባሏ ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑን መሳፈሩ በእጅጉ አስቆጥቷታል፡ በመጀመሪያ ዱካዋን እግር በእግር ተከታትሎ በመምጣት መሳቂያ መሳለቂያ ስላደረጋት አፍረት ውስጥ ከቷታል፡ ባሏ እቤታችን እንሂድ ቢላትም ሀሳቧን መለወጥ አትፈልግም ከማርክ ጋር ወደ አሜሪካ ለመሄድ የወሰነች ብትሆንም መርቪን ግን የመጨረሻ ውሳኔዋ ነው ብሎ መቀበል አልቻለም፡፡ ይሄ ደግሞ በቁርጠኝነቷ ላይ ጥላ አጥልቶበታል፡፡እሱም ውሳኔዋን እንደገና እንድታጤነው ደጋግሞ ስላሳሰባት ውሳኔዋን
በተደጋጋሚ ገልጻለታለች፡፡ በመጨረሻ ግን የአየር ጉዞዋ የሰጣትን ደስታ
ነጥቋታል፡፡

በህይወት አንዴ ብቻ የሚገጥም ከፍቅረኛ ጋር የሚደረግ ጉዞ፡፡

ከሳውዝ ሃምፕተን ሲነሱ የነበረው የነጻነትና የደስታ ስሜት አሁን የለም: መርቪን ከመጣ ወዲህ ምቹው አይሮፕላን፣ ከተለያዩ ተሳፋሪዎች ጋር መቀላቀሉና እጅ የሚያስቆረጥመው ምግብ ደስታ እየሰጣት አይደለም፡መርቪን ባጋጣሚ ሲያልፍ ያየኛል ብላ ስለፈራች ከማርክ ጋር መላፋት፣መተሻሸትና መሳሳም አልቻለችም፡፡ መርቪን የት እንደተቀመጠ አታውቅም፡፡ካሁን አሁን ይመጣ ይሆን እያለች ትበረግጋለች። ማርክ ካሊፎርኒያ ስለሚጠብቃቸው ኑሮ በተስፋ ሲያወራና ሲቀልድ ቆይቶ ጣውንቱ ከሰማይ
እንደወደቀ ሁሉ ድንገት አይሮፕላኑ ውስጥ ጥልቅ ካለ ወዲህ ግን ቀልቡ
ግፍፍ ብሏል፡ አሁን የተነፈሰ ፊኛ መስሏል፡፡ ዳያና አጠገብ ቁጭ ብሎ
አንድም ቃል ሳያነብ የመጽሔቱን ገጾች ያገላብጣል፡፡ ስሜቱ መጎዳቱን ዳያና አይታለች፡፡ አንድ ወቅት ላይ ይዟት እንዲጠፋ ከቆረጠች በኋላ ሃሳቧን ለውጣ ነበር፡፡ አሁን ባሏ ስለመጣ ከእሱ ጋር እሄዳለሁ ብላ ሃሳቧን
የማትለውጥ መሆኗን እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡
የአየሩ ሁኔታ እየከፋ መምጣቱ ደግሞ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል

አይሮፕላኑ ልክ ኮረኮንች ላይ እንደሚሄድ መኪና ይንገጫገጫል፡፡ በየሰዉ
ፊት ላይ ፍርሃት ይነበባል፡፡ ተሳፋሪው ሁሉ የሚያወራው ይህንኑ ነው፡

ዳያና ባሏ የት እንደተቀመጠ ማወቅ ፈለገች፡፡ እግረ መንገዴን ባየው እየተዘዋወረች ብትቃኝም መርቪንን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡ በመጨረሻ የቀራት ክፍል የሙሽሮቹ ክፍል ብቻ ነው፡፡

የሴቶች መዋቢያ ክፍል ገባች። ክፍሉ ውስጥ ሁለት ወምበሮች ያሉ ሲሆን አንዱ ወንበር ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ ትኳኳላለች፡፡ ዳያና በሩን ልትዘጋ ስትል አይሮፕላኑ ዘጭ ሲል ሚዛኗን ስታ ልትወድቅ ምንም አልቀራትም፡፡ እንደምንም ተንገዳግዳ ሄዳ ባዶው ወምበር ላይ ዘፍ አለች።

‹‹ተረፍሽ?›› ስትል ጠየቀች ሴትየዋ፡፡

‹‹አዎ፣ አመሰግናለሁ›› አለች ዳያና ‹‹አይሮፕላን እንዲህ ሲሆን አልወድም››

‹‹እኔም አልወድም፡ ከዚህ በኋላ ጉዟችን የከፋ እንደሚሆን አንድ ሰው
ነግሮኛል፡ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል›› አለች፡፡

የአይሮፕላኑ ውዝዋዜ ጋብ ሲል ዳያና ጸጉሯን ማበጠር ጀመረች።

‹‹ሚስስ ላቭሴይ ነሽ አይደለም?›› ስትል ጠየቀች

‹‹አዎ ዳያና በይኝ››
‹‹እኔ ናንሲ ሌኔሃን እባላለሁ:: ፎየንስ ላይ ነው የተሳፈርኩት”
ከሊቨርፑል ካንቺ. . . ከሚስተር ላቭሴይ ጋር ነው የመጣሁት››
‹‹ኦ!›› ዳያና ይህን ስትሰማ ፊቷ በእፍረት ቲማቲም መሰለ፡፡ ‹‹ጓደኛ እንዳገኘ አላወቅሁም ነበር›› አለች በምጸት፡፡

‹‹ይህን አይሮፕላን ለመሳፈር ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ለመሄድ ፈልጌ
ሊቨርፑል ላይ መውጫ አጥቼ ስጨነቅ ባለቤትሽን አየር ማረፊያ ላይ
አገኘሁትና እንዲወስደኝ ለመንኩት››

‹‹እንኳን ቀናሽ›› አለች ዳያና፡፡ ‹‹የእሱ መምጣት እኔን እፍረት ውስጥ
ከቶኛል፡፡››

‹‹ማፈር የለብሽም፡፡ ሁለት ወንዶችን በፍቅር ማጥመድሽ ደስ የሚል
ነገር ነው፡፡ እኔ አንድ እንኳን ፍቅረኛ የለኝም፡፡››

ዳያና ናንሲን በመስታወት አየቻት፡፡ ሴትየዋ ቆንጆ ባትባልም የደስ ደስ አላት፡ ጸጉረ ጥቁር ስትሆን ከሰውነቷ ጋር የሚሄድ ልብስ ለብሳለች።
ስትታይ በራሷ የምትተማመን ትመስላለች፡ መርቪን ሊፍት ቢሰጥሽ
አያስገርምም፡ እሱ እንዳንቺ ያለች ሴት ነው የሚፈልገው አለች ዳያና በሆዷ፡፡
‹‹እንዴት ነው ያሳየሽ ባህሪ ጥሩ ነበር?›› ስትል ጠየቀቻት ናንሲን፡፡
‹‹ብዙም ጥሩ አልነበረም›› አለች በቅሬታ ፈገግታ፡
‹‹አዝናለሁ፡ ይህ ባህሪው ነው የሚያስጠቃው›› አለችና ሊፒስቲኳን ጨረገች

‹‹ሆኖም በችግሬ ጊዜ ስለደረሰልኝ ባለውለታዬ ነው›› አለችና ናንሲ
ተናፈጠች፡ ናንሲ ቀለበት ማሰሯን ዳያና አጤነች፡፡ ‹‹ትህትና ባይኖረውም
ጥሩ ሰው ይመስላል፡፡ ራትም ጋብዞኛል፡ ጨዋታ ያውቃል፡፡ የሴት ልጅን
ልብ የሚሰርቅ ቁመናና መልክ አለው›› አለች፡፡

ጥሩ ሰው ቢሆንም….... አለች ዳያና ‹‹ሰው ይንቃል፡፡ ትዕግስትም የሚባል ነገር ፈጽሞ አልፈጠረበትም፡፡››
ናንሲ ጥቁር ጥቅጥቅ ያለውን ጸጉሯን ታበጥራለች ሽበቷን ለመደበቅ ቀለም ትቀባ ይሆን?› አለች ዳያና በሆዷ።

አንቺን መልሶ በእጁ ለማስገባት ሲል የሚደርስበትን መከራ ለመቀበል ቆርጧል››

‹‹አይደለም ክብሩ ስለተነካ ነው›› አለች ዳያና ‹‹ሌላ ወንድ ስለወሰደኝ ነው ያንጨረጨረው፡፡ ተጋፊ ስለመጣበት ነው ተከትሎኝ የመጣው፡ ጥዬው
እህቴ ቤት ሄጄ ቢሆን ኖሮ እኔን ለመፈለግ እግሩን አያነሳም ነበር››

ናንሲ ሳቀችና ‹‹እንዳነጋገርሽ አንቺን ለማስመለስ ተስፋ ያለው
አይመስልም›› አለች፡፡

‹‹ምንም ተስፋ የለውም›› አለች ዳያና፡፡ ዳያና ድንገት ስሜቷ ስለተረበሸ ከናንሲ ጋር ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገችም፡፡ ሜክአፕና ማበጠሪያዋን ቦርሳዋ ውስጥ ከታታ ለናንሲ ያላት ጥላቻ እንዳይታወቅባት የውሽት ፈገግታ አሳየቻትና ‹‹ወደ ቦታዬ ልሂድ›› ብላ ተነሳች፡፡

‹‹መልካም ዕድል!››

ከሴቶች መዋቢያ ክፍል ስትወጣ ሉሉ ቤልንና ልዕልት ላቪኒያ የመዋቢያ ዕቃዎቻቸውን ያጨቁበትን ቦርሳዎቻቸውን አንጠልጥለው ገቡ፡፡
ወደ ቦታዋ ስትመለስ አስተናጋጁ ዴቭ መቀመጫቸውን ወደ ታጣፊ አልጋ ሲቀይር አየች፡፡ ዳያና አንድ ተራ ሶፋ እንዴት ወደ ተደራራቢ አልጋ ሊቀየር
እንደሚችል ገርሟታል። ዴቭ ከወምበሩ ስር አንሶላና ብርድ ልብስ አወጣና
አነጠፈ፡፡

ተደራራቢ አልጋዎቹ ምቹ ቢሆኑም ከሰው እይታ ውጭ ባለመሆናቸው
ዴቭ መጋረጃ አመጣና ጋረዳቸው፡ ከዚያም በአልጋዎቹ ጎን ትንሽ ታጣፊ
መሰላል አያያዘባቸው፡፡ ዴቭ ይህን የሰራው በሚያስደንቅ ቅልጥፍና ነው፡፡

ዴቭ ወደ ዳያናና ማርክ ዞሮ ፈገግታ ሳይለየው መኝታችሁ እንዲዘጋጅላችሁ ከፈለጋችሁ ንገሩኝና አዘጋጅላችኋለሁ›› አላቸው፡፡

‹‹ተደራራቢ አልጋዎቹ ውስጥ ሲተኙ ሰዎች አይታፈኑም?››
‹‹እያንዳንዱ አልጋ የራሱ አየር ማስገቢያ አለው›› ሲል መለሰ ‹ቀና ብለሽ ብታዪ ያንቺ አልጋ አየር ማስገቢያ አለው፡›› ዳያና ቀና ስትል መስቀያና መዝጊያና መክፈቻ ያለው በብረት ፍርግርግ የተሰራ አየር ማስገቢያ አየች:: "ከዚህ በተጨማሪ›› ሲል ቀጠለ ዴቭ ‹‹የራስሽ መስኮት፣ መብራት፣ የልብስ መስቀያና የመፀሐፍ ማስቀመጫ አለሽ።ከዚህ በተረፈ የምትፈልጊው ነገር
እንዲመጣልሽ ስትፈልጊረመ ይህን ቁልፍ ብትጫኚው ከተፍ እልልሻለሁ›› አላት።
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ዳያና መልስ የመስጠት ያህል ከንፈሩን መጠጠችው፡
ከዚያማ ምን ይወራል! ቀለል እያላት ሲመጣ መላ ሰውነቷ ዘና አለ፡፡
እየሳመችው ወንበሩን ተደገፈች፡፡ እየሳመችው ጡቷ ደረቱን ሲታከክ
ተሰማት፡ እንደገና ገላ ለገላ መተሻሸት መቻሏ ደስታ ፈጥሮላታል፡ በከንፈሩ
ጫፍ ከንፈሯን ሲዳስስ ስሜት ውስጥ ገብታ አፏን ከፍታ ተቀበለችው፡፡ ጫን
ጫን መተንፈስ ጀመረች፡ በእርግጥ የሚያደርጉት ነገር መረን የለቀቀ
መሆኑ ታውቋታል፡ ዓይኗን ስትከፍት መርቪንን አየችው:
በመጀመሪያ እያለፈ ስለነበር አላስተዋላትም ነበር፡ ድንገት ወዳለችበት
ፊቱን ዞር ሲያደርግ ያየው ነገር ከእርምጃው ገታው፡ እሷም ስታየው ፊቷ
በድንጋጤ አመድ ለበሰ፡፡
ዳያና ባሏን በሚገባ ስለምታውቀው ምን ሊሰማው እንደሚችል
አልጠፋትም ምንም እንኳ ከማርክ ጋር በፍቅር  መክነፏን ሰዎች ቢነግሩትም እውነትነቱን ለመቀበል ከብዶታል፡፡ ከወንድ ጋር ስትሳሳም በዓይኑ በብረቱ ሲያይ በድንጋጤ ክው አለ፡፡

መርቪን በንዴት ግምባሩን ከሰከሰ፡፡ ዳያና ባሏ በቀጥታ ጠብ ይጀምራል
ብላ ፈርታ ነበር፡፡ ሆኖም ቃል ሳይተነፍስ ዞረና መንገዱን ቀጠለ፡፡

ማርክ ‹‹ምንድነው ነገሩ?›› ሲል ጠየቃት፡፡ ዳያናን ይዞ እየጨመጨመ
ስለነበር መርቪንን አላየውም ነበር፡፡

መንገር ስለፈራች ‹‹ሰው ሊያየን ይችላል ይበቃናል›› አለችው:

ማርክም ከዳያና መላቀቁን ቢጠላም መሳሙን አቆመ::
ዳያና የመርቪን አድራጎት አናደዳት፡፡ መርቪን የዓለምን ግማሽ ርቀት እግር በእግር ተከትሏት መምጣቱ ሳያንስ ከማርክ ጋር በተላፋች ቁጥር ሊያፈጥባት መብት የለውም፡፡ ትዳር ባርነት አይደለም፡፡ ጥላው መሄዷን
መቀበል አለበት፡ ማርክም በንዴት ሲጋራ ለኮሰ፡፡ ዳያና ባሏን ፊት ለፊ ልትገጥመው ፈልጋለች፡ በቃ አልፈልግህም ልትለው ተዘጋጅታለች

ተነሳችና ‹‹መዝናኛው ክፍል ምን እንዳለ ለማየት ልሄድ ነው›› አለች
‹‹አንተ እዚህ ቁጭ ብለህ ሲጋራህን ማግ›› አለችውና ከማርክ መልስ ሳትጠብቅ እብስ አለች፡

መርቪን የት እንደተቀመጠ ባታውቅም ፍለጋዋን ቀጠለች፡፡ አሁን የአይሮፕላኑ መናወጥ የቀነሰ በመሆኑ ምንም ነገር ሳትይዝ መራመድ ችላለች፡፡ በመዝናኛ ክፍሉ ውስጥ ሰዎች ካርታ ለመጫወት ጉድ ጉድ እያሉ ሲሆን ክፍሉ
በሲጋራ ታፍኗል፡፡ ፊታቸው የመጠጥ ጠርሙሶች
ተኮልኩለዋል፡፡ ሌላ ክፍል ዘው ስትል የኦክሰንፎርድን ቤተሰብ አገኘች፡:ሎርድ ኦክሰንፎርድ ሳይንቲስቱን ካርል ሃርትማንን ከፍ ዝቅ አድርገው ሲሳደቡ መርቪን ላቭሴይ ሰምቶ እሱ እንደተነካ ተቆርቁሮ ሎርዱን
ለመደብደብ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ተሳፋሪው አይቶታል፡ መርቪን አንዳንዴ እውነት አለው፡፡ እሷም ይህን አትክድም፡፡

ከዚያም ወደ ኩሽና ሄደች፡፡ እዚያም ድብልብሉ ኒኪ ሰሃን ሲያጥብ አገኘችው::
ፎቁን ወጣችና ፓይለቶቹ ክፍል ሄደች፡፡ ሁሉም በስራ የተጠመዱ ስለሆነ ወዲያው አላይዋትም፡፡ በኋላ አንዱ አያትና ‹‹ሌላ ጊዜ እያዞርን ሁሉንም ቦታ እናሳይሻለን፡፡ ነገር ግን አሁን እውጭ ያለው የአየር ሁኔታ
መጥፎ ስለሆነ ቦታሽ ሄደሽ እንድትቀመጪ ቀበቶሽን እንድታስሪ እንጠይቃለን›› አላት፡፡

ደረጃውን ወርዳ ስትጨርስ ከማርክ ጋር ፊት ለፊት ግጥም አለች፡ሁኔታው ቢያስደነግጣትም ‹‹እዚህ ምን ልታደርግ መጣህ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹ራስሽ እዚህ ምን ልታደርጊ መጣሽ?›› አላት፡፡ ካነጋገሩ የተናደደ መሆኑ ያስታውቃል

ዞር ዞር እያልኩ እያየሁ ነው፡፡››
መርቪንን ነው የምትፈልጊው?›› አላት፡
‹‹ማርክ ለምንድነው እንደዚህ የምትሆነው?›› አለች ዳያና፡፡
‹‹ምክንያቱም ባልሽን ለማየት ሹክክ ብለሽ በመሄድሽ››

ኒክ ድንገት መጣና ጭቅጭቃቸውን አቋረጣቸው ወደ
መቀመጫችሁ ተመለሱ፡፡ አሁን በረራው ጥሩ ቢመስልም ትንሽ ቆይቶ
አይሮፕላኑ መወዛወዙ አይቀርም›› አላቸው፡፡

ማርክና ዳያና ወደ ቦታቸው ተመለሱ፡፡ ዳያና ያደረገችው የጅል ስራ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ መርቪንን ስትከታተል መርቪን ደግሞ እሷን ተከታትሎ የምትሰራውን አየባት፡፡

ቦታቸው ቁጭ ብለው ጭቅጭቃቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ ኦሊስ ፊልድና
ፍራንክ ጎርደን መጡ፡፡ ጎርደን ነጠላ ጫማውን አወለቀና ላይኛው አልጋ ላይ በመሰላል ወጣ፡፡

ከዚያም ፊልድ ከፒጃማው ውስጥ እጀ ሙቅ ሲያወጣ ዳያና አይታ ደነገጠች፡ ፊልድ ፍራንክ ጎርደንን በጆሮው አንድ ነገር ሲለው ፍራንክ ተቃውሞውን ቢገልጽም ፊልድ  ፈርጠም ብሎ የታዘዘውን እንዲፈጽም ሲነግረው አንድ እጁን ሰጠ፡፡ ፊልድ የፍራንክን እጅ በእጀ ሙቁ ከአልጋው ብረት ጋር አሰረና መጋረጃውን ፊቱ ላይ ጋረደበት፡

‹‹ፍራንክ እስረኛ መሆኑ እውነት ሆነ›› አለ ማርክ፡፡
‹‹እኔ ግን ነፍሰ ገዳይ ነው የተባለውን ማመን አቅቶኛል›› አለች ዳያና፡፡
‹‹እኔ ደግሞ ሳይሆን አይቀርም ብዬ ነው የምገምተው›› አለ ማርክ፡
‹‹ሃምሳ ዶላር ከፍለን በመርከብ ከምድረ ምስኪን ጋር ብንሄድ ይሻለን ነበር››

‹‹ፊልድ እጀ ሙቁን ቢፈታለት ጥሩ ነበር፡፡ ልጁ ካልጋው ጋር ተጠፍሮ
እንዴት ሊተኛ እንደሚችል አይገባኝም፡፡ መገላበጥ እንኳን አይችልም፡፡››
‹‹አንቺ ሩህሩህ ነሽ›› አለ ማርክ እቅፉ ውስጥ እየጣላት፡ ‹‹ሰውየው
እኮ ሴቶችን አስገድዶ የሚደፍር ሰው ነው፡፡ አንቺ ደግሞ እንዴት ሆኖ
ሊተኛ ነው ብለሽ ታዝኛለሽ፡፡››

ዳያና ራሷን ማርክ ትከሻ ላይ አስደገፈች፡ ማርክ ጸጉሯን ይደባብሳል፡፡
ከጥቂት ጊዜ በፊት አናዳው ኤሌክትሪክ ሊጨብጥ ምንም አልቀረውም ነበር፡፡
አሁን ግን ንዴቱ በርዷል፡
ማርክዬ አለች ዳያና ይሄ አልጋ ለሁለት ሰው ይበቃል?›› ስትል
ጠየቀች፡፡

‹‹ፈራሽ የኔ ማር?››
‹‹አይ አልፈራሁም፡፡››

በመጀመሪያ ያለችው ግር ብሎት ነበር፡፡ በኋላ ሃሳቧ ገባውና ፈገግ  አለ፡፡ ‹‹ሁለት ሰው ሊያስተኛ ይችላል፡፡ ነገር ግን ጎን ለጎን አይደለም፡፡አንዳችን አንዳችን ላይ መውጣት ይኖርብናል፡፡ አንቺ እላዬ ላይ መውጣት ትፈልጊያለሽ?››

‹‹አዎ እወጣለሁ›› አለች ዳያና እየሳቀች።

‹‹እስቲ ላስብበት›› አላት ኮስተር ብሎ በቀልድ ‹‹ስንት ነው ኪሎሽ?››

‹‹ብዙም አልከብድህም››

‹‹የቀን ልብሳችንን እንለውጥ›› አላት፡፡

ዳያና ባርኔጣዋን አውልቃ ወምበሩ  ላይ አስቀመጠች፡፡ ማርክ
የሁለቱንም ቦርሳ ከወምበሩ ስር አወጣ፡፡

ዳያና ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ እንደምትፈልግ ስትነግረው ‹‹ቶሎ በይ›› አለና ደረቱ ላይ ለጥፎ ሳማት፡፡ እቅፍቅፍ ሲሉ የብልቱ መቆም
ተሰማትና አህ!› አለች የእሷም ስሜት ተነሳስቶ፡፡ ስትመለስ እሱም ሊሄድ
ተነሳ፡፡ ‹‹ከመታጠቢያ ቤት ስትመለስ እንደቆመ መምጣት አለብህ››
አለችው፡፡

‹‹አይዞሽ አትስጊ፤ እንደገና እንዴት እንደምታቆሚው አሳይሻለሁ›› አላት፡፡

‹‹እስክትመለስ በቅንዝር መሞቴ ነው›› ስትል በጆሮው አንሾካሾከች፡
ማርክ ቦርሳውን አንጠልጥሎ ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ሄደ፡ መርቪን ከተቃራኒ አቅጣጫ እየመጣ ነው፡፡ ሲተላለፉ ልክ አጥር ላጥር እንደሚተያዩ ድመቶች ቢፋጠጡም ቃል አልተለዋወጡም።

ዳያና መርቫን የለበሰውን ቢጃማ አይታ ‹‹ምንድነው እናትህ የለበስከው?›› ስትል ሳቀችበት፡፡

‹‹ሳቂ እስኪበቃሽ›› አለ፡፡ ‹‹ፎየንስ ላይ ላገኝ የቻልኩት ፒጃማ ይሄ ብቻ ነው›› አላት ‹‹የዚህ አገር ሰዎች ከሃር የተሰራ ፒጃማ መኖሩን እንኳን ሰምተው አያውቁም፡፡ ስጠይቃቸው እብድ ነው ሳይሉ አይቀርም››
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ሦስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በአባቷ አድራጎት ስላፈረች መሬት ተከፍታ ብትውጣት በወደደች፡ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ ሁላ በተፈጠረው አስከፊ ሁኔታ የአባቷን ጋጠወጥ ባህሪ እሷም ትጋራ ይሆን?› እያለ እያሰበ የሚያፈጥባት መሰላት፡ የሰዉን አይን ማየት ፈራች:

ሄሪ ማርክስ የቀራት እንጥፍጣፊ ክብሯ ሳይገፈፍ ደረሰላት፡ ቀልጠፍ
ብሎ ተነስቶ በማክበር ወምበሯን ያዝ አድርጎላት፣ ሶቶ እንድትይዘው
ክንዱን ሰጥቷት ከመብል ክፍሉ እንድትወጣ አገዛት፧ ያደረገው ነገር ትንሽ
ቢሆንም እሷን ግን ልቧን ነክቷታል።

አባቷ ለዚህ እፍረት ስለዳረጓት በእጅጉ አንገብግቧታል፡፡ ራት ከተበላ በኋላ በመብል ክፍሉ ውስጥ ለሁለት ሰዓት ያክል የሚከብድ ጸጥታ ነግሶ ቆየ፡ የአየሩ ሁኔታ እየተበላሸ ሲመጣ አባባ እና እማማ የቀን ልብሳቸውን
አውልቀው የመኝታ ልብሳቸውን ለበሱ፡
ፔርሲ ‹‹ይቅርታ እንጠይቅ›› አላት ማርጋሬትን ድንገት፡
ፔርሲ ይህን ሲላት ይቅርታ መጠየቁ የበለጠ እፍረት ውስጥ እንደሚጥላቸው ገመተች፡ ‹‹እኔስ ይቅርታ ለመጠየቅ ድፍረቱ የለኝም››
አለችው ወንድሟን፡፡

‹‹ባሮን ጋቦንና ፕሮፌሰር ሃርትማን ጋ ሄደን አባታችን ስላሳየው ያልተገባ ባህሪ ይቅርታ ብንጠይቅ ነው የሚሻለው›› አለ ፔርሲ፡
የአባቷን ጥፋት ለማለዘብ ይቅርታ መጠየቁ ጥሩ ሳይሆን አይቀርም ስትል አሰበች፡፡ እሷም ቀለል ይላታል፡፡ ‹‹አባባ ግን ይናደድብናል›› አለች
አበዛው! አብዷል መስለኝ ከዚህ በኀላ አልፈራውም›› አለ ፔርሲ፡

‹‹እሱ ማወቅ የለበትም ቢናደድ ደግሞ ግድ የለኝም፧ አሁንስ
ፔርሲ ከዚህ በኋላ አልፈራውም› ያለው እውነት መሆኑን ማርጋሬት
አላወቀችም: ህጻን ሆኖ አባታቸውን ፈርቷቸው እያለ ‹አልፈራውም› ይል
ነበር፤ አሁን ግን ህጻን አይደለም፡፡

ፔርሲ ከአባታቸው ቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱ ማርጋሬትን አሳስቧታል፡ አባቷ ብቻ ናቸው የፔርሲን
ያልተገባ ባህሪ ሊያርቁ
የሚችሉት፤ ፔርሲ ሸረኝነቱን እንዲተው ካልተደረገ አይቻልም፡፡

‹‹በይ እንጂ! አሁን እንሂድና ይቅርታ እንጠይቃቸው፤ ያሉበትን ቦታ እኔ አውቀዋለሁ›› አለ ፔርሲ፡
ማርጋሬት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈራ ተባ አለች እያለች ነው አባቷ
ያስቀየሟቸው ሰዎችጋ መሄድና ይቅርታ መጠየቅ ከብዷታል፤ የሆነውን
ሁሉ መተውና አርፎ መቀመጥ ነው የሚሻላቸው ቁስላቸውን መነካካቱ
ምንም ፋይዳ የለውም፡ ሆኖም የዘር መድሎን ለመቃወም እጅ ለእጅ
መያያዝ ያስፈልጋል።

በመጨረሻ ማርጋሬት ሰዎቹን ይቅርታ ለመጠየቅ ወሰነች፡ መቼም ጥሎባት ቦቅቧቃ ናት፡ ከዚህ ቀደም ላጠፋችው ጥፋት ፈርታ ይቅርታ ሳትጠይቅ መቅረቷ ሁልጊዜ ይጸጽታታል፡
አይሮፕላኑ በወጀቡ እየተወዛወዘ ቢሆንም የወንበሯን መደገፊያ ጠበቅ
አድርጋ ይዛ ተነሳችና ‹‹እሺ እንሂድ›› አለችው ወንድሟን፡
የአይሮፕላኑ መወዛወዝ በፍርሃት መንቀጥቀጧን ደብቆላታል፡ ሁለቱ
ሰዎች ወዳሉበት ክፍል አመራች፡፡

ጋቦንና ሃርትማን ግምባር ለግምባር ተቀምጠዋል፡ ሃርትማን የሂሳብ መጽሐፍ ላይ በተመስጦ አፍጠዋል፡፡ ጋቦን የሚሰሩትን አጥተው በጉዞው ተሰላችተው ተቀምጠዋል፡ በመጀመሪያ ማርጋሬትንና ፔርሲን ያይዋቸው እሳቸው ናቸው፡ ማርጋሬት አጠገባቸው መጥታ ወምበራቸውን ተንገዳግዳ ስትይዝ አዩና ፊታቸውን አኮሳተሩ።

ማርጋሬት ቶሎ ብላ ‹‹ይቅርታ ለመጠየቅ ነው የመጣነው›› አለች፡
‹‹ደፋር ነሽ!›› አሉ ጋቦን የፈረንሳይኛ ቋንቋ ቅላጼ ባለው እንግሊዝኛ፡
ማርጋሬት እንዲህ ያለ ምላሽ ይገጥመኛል ብላ ባታስብም ጥረቷን
ቀጠለች፡ ‹‹በአባታችን አድራጎት በጣም አዝኛለሁ፤ ወንድሜም እንዲሁ
ለፕሮፌሰር ሃርትማን ያለኝ አድናቆት ከፍተኛ ነው፡ ይህንንም ከዚህ ቀደም
ነግሬያቸዋለሁ›› አለች፡:

ሃርትማን ንባባቸውን አቋርጠው ይቅርታውን መቀበላቸውን ራሳቸውን
በመነቅነቅ አመለከቱ፡ ጋቦን ግን አሁንም በቁጣ አበያ በሬ እንደመሰሉ ነው
‹‹እንደ እናንተ ላሉ ሰዎች ይቅርታ መጠየቅ ቀላል ነው›› ሲሉ ማርጋሬት
የምታደርገው ጠፍቷት በድንጋጤ መሬት መሬቱን ታያለች፡፡ ‹ምነው
ባልመጣሁ አለች በሆዷ፡ ‹‹ጀርመን ውስጥ እየተደረገ ያለው ነገር በጣም
እንደሚያሳዝናቸው የሚነግሩን ጨዋ ሰዎች ብቻ ናቸው›› ሲሉ ቀጠሉ ‹‹ግን ምን አደረጉልን፤ እናንተስ ምንድነው የምታደርጉልን?›› አሉ ጋቦን፡፡
ማርጋሬት ፊቷ በድንጋጤ በርበሬ መሰለ፡፡ ምን እንደምታደርግ ግራ ግብት አላት።

‹‹ፊሊፕ ዝም በል እንጂ›› አሉ ሃርትማን ለስለስ ባለ አነጋገር ልጆች እኮ ናቸው›› ወደ ማርጋሬትም ዞር አሉና ‹‹ይቅር ብለናል እናመሰግናለን››

‹‹ጌታዬ ተሳሳትን ይሆን?›› ስትል ጠየቀች::

‹‹በፍጹም›› አሉ ሃርትማን ‹‹እንደውም ጥሩ ነው ያደረጋችሁት ይባርክሽ፧ ጓደኛዬ በጣም ስሜቱ ስለተነካ ነው እንዲህ የሆነው፤ በኋላ እንደእኔ ሲገባው ከንዴቱ መለስ ይላል፡››

‹‹እንግዲህ እንሂድ›› አለች ማርጋሬት እንደከፋት፡
ሃርትማን በመስማማት ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
ፔርሲም በተራው ‹‹ይቅርታ አድርጉልን›› አለና ከእህቱ ጋር ተያይዘው
ሄዱ፡፡

ወንድምና እህቱ በአይሮፕላኑ ውዝዋዜ እየተንገዳገዱ ወደ ቦታቸው
ተመለሱ፡፡ ዴቭ መኝታቸውን እያነጣጠፈላቸው ነው፡፡ ሄሪ በቦታው የለም፡ ምናልባትም ወደ መታጠቢያ ቤት ሄዶ ይሆናል፡፡ ማርጋሬት ልብስ
ለመለወጥ ቦርሳዋን አንጠልጥላ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄደች፡ እናቷ የመኝታ ልብሳቸውን ለብሰው እምር ድምቅ ብለው ከመጸዳጃ ቤት እየወጡ ስለነበር
‹‹ደህና እደሪ የኔ ማር›› ቢሏትም እሷግን ዝግት አድርጋቸው ገባች:
በሴቶች በሞላው መታጠቢያ ቤት ውስጥ የመኝታ ልብሷን ቶሎ ለውጣ ወጣች፡፡ የመኝታ ልብሷ ሌሎቹ ሴቶች ከለበሱት ደመቅመቅ ካሉትና ከሃር ከተሰሩት ልብሶች ጋር ሲነጻጸር ኋላ ቀር መሆኑ ግድ አልሰጣትም፡፡ ባሮን
ጋቦን በኋላ ያሉት እውነት በመሆኑ ይቅርታ መጠየቁ የፈየደው ነገር የለም ለችግሩ ምንም መፍትሄ ሳያመጡ ይቅርታ› ማለት ቀላል ነው።

ወደ ቦታቸው ሲመለሱ እናትና አባቷ መጋረጃቸውን ጋርደው ተኝተዋል፡፡ አባቷ አገር አማን ነው ብለው ያንኮራፋሉ፡፡ ማርጋሬት የእሷ መኝታ እስኪዘጋጅ ቁጭ ብላ ጠበቀች፡፡

ከቤተሰቦቿ ቁጥጥር ነፃ ለመሆን አንድ መንገድ ብቻ ነው ያላት  እነሱን ትታ እየሰራች መኖር አሁን ይህን ለማድረግ ቆርጣለች፡፡ የገንዘብ፣ የስራና የመኖሪያ ቦታ ችግሯን ለመቅረፍ ግን ገና ነች፡፡

ፎየንስ ላይ የተሳፈረችው ዘናጯ ናንሲ አጠገቧ መጥታ ተቀመጠች።
ሴትየዋ የመኝታ ልብስ ነው የለበሰችው፡፡ ‹‹አስተናጋጁ ብራንዲ እንዲያመጣልኝ ፈልጌ ነበር፤ እሱ ግን እረፍት የለውም፧ እዚህ እዚያ ይንከወከዋል
አለች፡ ሲያይዋት ዘና ብላለች፡ ተሳፋሪው እንዲያያት እጇን አውለበለበች
‹‹ለምን ፓርቲ አንጨፍርም፤ ምን ትያለሽ?›› አለቻት ማርጋሬትን፡፡
‹‹ያልሽው ነገር እንግዳ ነው የሆነብኝ›› አለቻት ማርጋሬት፡፡
ናንሲ የመቀመጫ ቀበቷን አጠባበቀች፡ ደስ ደስ ብሏታል። ‹በፒጃማ
ስትሆኚ መከባበር ብሎ ነገር የለም፤ የወዳጅነት ስሜት መስፈን ነው
ያለበት፡፡ ፍራንክ ጎርደን እንኳን ፒጃማው አምሮበታል፡››

ማርጋሬት በመጀመሪያ ስለማን እንደምታወራ  አልገባትም ነበር፡፡
ወዲያው ግን ካፒቴኑና የኤፍ.ቢ.አይ መርማሪው ሲጨቃጨቁ ፔርሲ ሰምቶ
የነገራት ነገር ትዝ አላት
‹‹እስረኛውን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀቻት።
‹‹አዎ››
‹‹አንቺ አትፈሪውም?››
‹‹አይ አልፈራውም፧ ምን ያደርገኛል!››
‹‹ሰዎች ግን ነፍሰ ገዳይ ነው ይሉታል››
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_አራት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት በሰማችው ተንገሸገሸች ‹‹በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው
የነገርከኝ፡፡ ለዚህ ነው እንደ ፍራንኪ ጎርዲኖ ያሉ ወሮበሎች የእጃቸውን
ማግኘት አለባቸው የሚባለው

ትንሽ ዝም ብለው ቆዩና ‹‹ኧረ ለመሆኑ በፍራንኪ ጎርዲኖ እና በክላይቭ መምበሪ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?,,

‹‹እንጃ እኔ አላውቅም›› አላት፡፡

‹‹ፔርሲ መምበሪ ሽጉጥ ይዟል ብሎ ነግሮኛል፡ ፖሊስ ሳይሆን አይቀርም››

‹‹እውነት! እንዴት?››

‹‹እንደዚህ አይነት ልብስ የለበሰው እንዳይታወቅበት ነው››

‹‹ፍራንክ ጎርዲኖን የሚጠብቅ ፖሊስ ይሆናል››

‹‹ለምን? ጎርዲኖ እንግሊዝ አገር ውስጥ ታድኖ የተያዘ አሜሪካን አገር እስር ቤት የሚወስድ ወንጀለኛ ነው፤ ከአይሮፕላኑ ዋጋ ውድነት አንጻር የእንግሊዝ ፖሊስ ኮሚሽን ገንዘቡን ገፍግፎ እስረኛ እንዲያጅብ ፖሊስ
የሚልከው ለምንድነው?››

‹‹አንተን ይሆን የሚከታተለው?›› አለች በጆሮው

‹‹አሜሪካን አገር ድረስ›› አለ ሄሪ ጥርጣሬ ገብቶት ‹‹ለሁለት የወርቅ
አምባሮች ሲል?››

‹‹ታዲያ እዚህ ለምን መጣ?››

‹‹አላውቅም››

‹‹የሆነ ሆነና የጎርዲኖ ጉዳይ ራት ላይ አባቴ ያሳየውን መጥፎ ባህሪ
የሚያረሳሳ ይመስለኛል፡››

‹‹ለምንድን ነው እንደዚያ የሆኑት አባትሽ?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ፡

‹‹እኔ እንጃ ከዚህ በፊት እንደዚህ ሆኖ አያውቅም››
‹‹ከዚህ ቀደም የፋሺስት አስተሳሰብ አራማጆች አጋጥመውኛል አለ
ሄሪ ‹‹እነዚህ ሰዎች ፍርሃት አለባቸው››

‹‹እንደዚያ ነው?›› ማርጋሬት አባባሉ ያስደነቃት ከመሆኑም በላይ ሊሆን የማይችል ሆነባት፡፡ ‹‹ፋሺስቶች ሲያይዋቸው ሞገደኛ ይመስላሉ
ውስጣቸው የተረጋጋ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው ዩኒፎርም ለብሰው ላይ ታች
የሚሉት፡፡ በቡድን ሲሆኑ ነው ደህንነት የሚሰማቸው ዲሞክራሲ የሚጠሉት ለዚህ ነው፡፡ አየሽ ዲሞክራሲ የተለያየ አስተሳሰብ እንዲንፀባረቅ
ይፈቅዳል ገደብ አይጥልም
አምባገነንነትን ለምን እንደሚወዱ ታውቂያለሽ? ወደፊት የሚሆነው የታወቀ ስለሆነና የፋሺስት መንግስት በቀላሉ ለውጥ ስለማይደረግበት ነው››

‹‹አባቴ ኮሚኒስቶችን ወይም ጽዮናዊያንን ወይም የሰራተኛ ማህበራትን
ያለ ምክንያት አይደለም የሚጠላው እነዚህ ሐይሎች
ያንበረክኳታል ብሎ ይሰጋል፡››

‹‹ፋሺስቶች ሁልጊዜ ብስጩ ናቸው›› አለ ሄሪ፡፡

‹‹አባቴም እንዲሁ ነው  አያቴ ሲሞቱ ዕዳ ያለበት ርስት ነው ያወረሱት፧ እናቴን እስኪያገባ ድረስ ተቸግሮ ነበር የኖረው፤ከዚያም
ለፓርላማ አባልነት ተወዳድሮ ቢያሸንፍም በሩን አልረገጠም፤ አሁን ደግሞ
ካገሩ ተነቅሎ ተባረረ›› አለች፡፡

ማርጋሬት ‹ሄሪ ማርክስ ከቤተሰብ ጠፍቼ እንድሄድ ይረዳኝ ይሆን?› ስትል አሰበች አሜሪካ ከገቡ በኋላም እንዳሁኑ ይቀርባት እንደሆነ እርግጠኛ
አይደለችም፡፡ ‹‹አሜሪካ የት ነው ልትኖር ያሰብከው?›› ስትል ጠየቀችው።

‹‹ኒውዮርክ ቤት ተከራይቼ እኖራለሁ፤ አሁን እጄ ላይ ጥቂት ገንዘብ አለኝ፤ ሌላም ገንዘብ የሚገኝ ይመስለኛል፡››

ሄሪ ሁሉን ነገር አቅልሎ ነው የሚናገረው ‹‹ምናልባትም ለወንዶች ቀላል ይሆናል፡፡ ሴት ልጅ ግን ረዳት ያስፈልጋታል››

‹‹ናንሲ ሌኔሃን ስራ ልትቀጥረኝ እንደምትችል ነግራኛለች›› አለች፡
‹‹ሆኖም ወንድሟ ኩባንያውን ከወሰደባት የገባችልኝን ቃል ላትጠብቅ
ትችላለች››

‹‹ከፈለግሽ እኔ አግዝሻለሁ›› አላት፡፡

እሷ እንዲህ አይነት ድጋፍ ነው የፈለገችው

‹‹ትረዳኛለህ?›› ስትል
ጠየቀችው፡፡

ሄሪ ምን ሊያደርግላት እንደሚችል ግልፅ ባይሆንለትም ‹‹ቤርጎ ፈልጌ
አሳይሻለሁ›› አላት፡፡

ይህን ቃል ስትሰማ የተሰማት እረፍት ቀላል አይደለም፡፡

‹‹እግዜር ይስጥህ፡፡ እኔ በህይወቴ ቤርጎ ፈልጌ ይዤ አላውቅም፡፡››
‹የቤት ኪራይ ማስታወቂያ እናያለን››

በታይምስ ጋዜጣ ላይ እንዲህ አይነት ማስታወቂያ አይቼ አላውቅም››አለች አባቷ የሚያነቡት ይህን ጋዜጣ ብቻ መሆኑን አስታውሳ፡፡

‹‹ማታ ማታ የሚወጡ ጋዜጦች ላይ ነው ማስታወቂያዎች የሚወጡት››

እንዲህ አይነት ቀላል ነገር እንኳን ባለማወቋ አፈረች፡፡
‹‹እኔ የሚረዳኝ ሰው ያስፈልገኛል››
‹‹አይዞሽ አትፍሪ እኔ የምችለውን ያህል እረዳሻለሁ››
‹‹በእውነት የሚያስደስት ነው›› አለች ማርጋሬት ‹‹ሚስስ ሌኔሃንና አሁን ደግሞ አንተን ካገኘሁ ኑሮውን እቋቋመዋለሁ፡ ውለታ ከፋይ ያድርገኝ፡፡ ምን እንደምል እንጃ፡:››

ዴቪ ወዳሉበት መጣና ‹‹በመስኮት ተመልከቱ አንድ ነገር ታያላችሁ›› አለ።

ማርጋሬት አይሮፕላኑ ለአስራ አምስት  ደቂቃ ያህል ሳይወዛወዝ
እንደተጓዘ ተገነዘበች፡

ማርጋሬት በመስኮት አሻግራ ተመለከተች፡፡ ሄሪ የመቀመጫ ቀበቶውን
ፈታና በማርጋሬት ጀርባ በኩል አሻግሮ አየ፡፡

‹‹ለእኛ ብለው ይሆናል መብራቱን ሁሉ ያበሩት›› አለ አንዱ፡፡

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የአየር ጥቃቱን በመፍራት በጨለማ ነው የሚጓዙት፡ ማርጋሬት ሄሪ በጣም ወደሷ መጠጋቱን አልጠላችውም:
የአይሮፕላኑ የመገናኛ ሰራተኛ ከመርከቡ የመገናኛ ሰራተኛ ጋር በሬዲዮ
ሳይነጋገር አልቀረም፡፡ የመርከቡ ተሳፋሪዎች ወደ መርከቡ በረንዳ ላይ
ወጡና እጃቸውን አውለበለቡ፡፡ አይሮፕላኑ ከመርከቡ በቅርብ ርቀት የሚበር በመሆኑ ወንዶቹ ነጫጭ የራት ልብስ፤ ሴቶቹ ደግሞ ቅልጥም የሚታከክ
ልብስ መልበሳቸውን በግልጽ ይታያል፡፡

መርከቡ ማዕበሉን በሹል አፍንጫው እየሰነጠቀ ሲጓዝ አይሮፕላኑ አልፎት በረረ፡፡ ማርጋሬት ሁኔታው አስደስቷታል፡ ሄሪን ስታየው እሱም አያትና ተሳሳቁ፡፡ ሰዎች እንዳያዩት በሰውነቱ ከልሏት እጁን ወገቧ ላይ ጣል አድርጓል፡፡ በእጁ ገላዋን ነካ ያደረጋት ቢሆንም በመላ ሰውነቷ ላይ
የኤሌክትሪክ ሞገድ ያህል ሙቀት ለቆባታል፡ ይህ ሁኔታ በመጠኑ ድንግርግር እንዲላት ቢያደርግም እጁን እንዲያነሳ ግን አልፈለገችም ከትንሽ ጊዜ በኋላ ቁልቁል የሚያዩትን መርከብ አልፈው ሲሄዱ ከመርከቡ የሚፈነጥቀው መብራትም እየራቃቸው ሄደ፡፡ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ወደ
ቦታቸው ሲመለሱ ሄሪም ወደ ቦታው ሄደ፡፡

ዋናው ሳሎን ውስጥ ካርታ ከሚጫወቱት ጋር ማርጋሬትና ሄሪ ብቻ
ሲቀሩ ሌሎቹ ተሳፋሪዎች ወደ መኝታቸው ሄዱ፡ ማርጋሬት ከሄሪ ብቻዋን ተቀምጣ እፍረት ተሰማትና ‹‹መሽቷል ብንተኛ ይሻላል›› አለች ወዲያው ለምን እንዲህ አልኩ? አለች ለራሷ መተኛት አልፈለገችም: ሄሪ
ከእሷ መለየቱ ደስ ስላላለው ‹‹እኔም ትንሽ ቆይቼ እሄዳለሁ›› አለ
ማርጋሬት ከመቀመጫዋ ተነሳች ‹‹ወደፊት አሜሪካ ውስጥ እረዳሻለሁ
ስላልከኝ አመሰግናለሁ›› አለች፡፡
" ምንም አይደል"
"መልካም ምሽት"
"ለአንቺም እንዲሁ" አለ ሄሪ
ከመሄዷ በፊት ዞር አለችና እረዳሻለሁ ያልከኝ ከአንጀትክ ነው አይደል?

"አይዞሽ አታስቢ›› አላት፡፡

ማርጋሬት ለሄሪ ያላት ፍቅር እየጨመረ መጥቷል፡፡  ከዚያም  በደመነፍስ እዚያው ቁጭ ባለበት ከንፈሩን ሳም አደረገችው፡፡ ይህም ደስ የሚል ስሜት አጭሮባታል፡፡ ግን ደግሞ ወዲያውኑ ባደረገችው ነገር ክው አለች ያጫረባት ደስታ ጉልበቷን አብረክርኳታል፡፡ ዙሪያ ገባውን
ስትመለከት ሚስተር መምበሪ የላይኛውን አልጋ ሲይዝ የታችኛውን ሄሪ
ይዟል፧ ፔርሲም የላይኛው አልጋ ላይ ተኝቷል፡፡ መጋረጃውን ጋረደች፡፡

መብራቱን አጠፋችና ብርድ ልብስ ውስጥ ገብታ ተኛች። መኝታው ይሞቃል፡፡ በመስኮት ስታይ ከጨለማና ከዝናብ በስተቀር ምንም የሚታይ ነገር የለም፡፡ እሷና ኤልሳቤት ትንንሽ ልጆች ሆነው በበጋ ውስጥ እውጭ ድንኳን ተክለው የሚተኙት ትዝ አላት፡፡

ኤልሳቤት የት ትሆን ያለችው?
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_አምስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ኤዲ ዲኪን ራሱን ለመቆጣጠር ቢሞክርም  ክዳኑ ተዘግቶ እንደሚንተከተክ ጀበና ሆኗል፡ በጭንቀት ሊፈነዳ ምንም አልቀረውም፡፡ ላቡ
አሁንም አሁንም ችፍ ይላል፡ ጨጓራው እየተቃጠለ በመሆኑ ሰውነቱ
እረፍት አጣ፡፡ ቀልቡን ሰብስቦ መስራት አልቻለም፡፡

ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ የእሱ ፈረቃ ያበቃል ወደ መውጫው ሰዓት ላይ የሀሰት የነዳጅ ፍላጎት መጠን አስልቶ በሰንጠረዡ ላይ አሰፈረ።

ካፒቴኑ ጉዞውን
ለማጠናቀቅ የሚያስችል በቂ ነዳጅ ያለው
ለማስመሰልና ወደ ኋላ እመለሳለሁ እንዳይል የአይሮፕላኑን የነዳጅ ፍጆታ
ፍላጎት መጠን አሳንሶ አስልቶ ነበር፡፡ የእሱ ተተኪ የሆነው ሚኪ ፊን ሲመጣ ልዩነቱን እንዳያውቅ የፍጆታ መጠኑን ከፍ አድርጎ በማስላት አካካሰው፡፡ የነዳጅ ፍጆታ መጠን በወጣ ገባነት መለዋወጡን ሚኪ ሲያይ ምን ተፈጠረ ብሎ መጠየቁ አይቀርም፡፡ ኤዲም ይህ የሆነው በወጀቡ ምክንያት ነው ሊለው ተዘጋጅቷል፡፡ የሆነ ሆኖ አሁን ሚኪ ምን እንደሚል ሳይሆን ያስጨነቀው፣ አዕምሮውን የውጥር የያዘው አይሮፕላኑ ኒውፋውንድ ላንድ (ካናዳ) ሳይደርስ ነዳጅ ይጨርስ ይሆን የሚለው ሃሳብ ነው፡፡

የበረራ ህጉ መያዝ ያለበትን መጠባበቂያ የነዳጅ መጠን ቢያስቀምጥም
አይሮፕላኑ የራሱ የሆነ ዝቅተኛ የነዳጅ ፍጆታ መጠን ደንብ የለውም:
አይሮፕላኑም ከአቅም በላይ ለሆነ ችግር የመጠባበቂያ ነዳጅ የለውም::በነዳጅ ችግር ምክንያት አንድ ችግር ቢከሰት አይሮፕላኑ ያለ ጥርጥር ማዕበል በበዛበት አትላንቲክ ውቂያኖስ ውስጥ መውደቁ አይቀርም፡፡ ከወደቀ
ደግሞ በትንሽ ደቂቃ ውስጥ ስለሚሰምጥ ለወሬ ነጋሪ እንኳን የሚተርፍ
የለም፡፡

ሚኪ እንደወትሮው ነቃ ብሎና ለስራ ተነሳስቶ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት
ሲል ደረሰ፡፡ ‹‹ያለን ነዳጅ አነስተኛ መሆኑን ለካፒቴኑ ነግሬያለሁ›› አለው
ኤዲ፡፡

ሚኪም ያለው ነገር ብዙም ስሜት እንዳልሰጠው ሁሉ ራሱን በማነቃነቅ ብቻ መረዳቱን ገለፀለትና ባትሪውን አነሳ፡፡ የመጀመሪያ ስራው የአይሮፕላኑ አራት ሞተሮች በዓይን መቃኘት ነው፡፡

ኤዲ ሚኪን ባለበት ቦታ ትቶ ወደ ተሳፋሪዎች ክፍል አመራ፡ ረዳት.ካፒቴኑ ጆኒ ዶት ናቪጌተሩ ጃክ አሽፎርድና ሬዲዮ ኦፕሬተሩ ቤን ቶምስን ተከትለውታል፡፡ ጃክ ለራሱ ሳንድዊች ሊያዘጋጅ ወደ ኩሽና ሄደ፡፡ ኤዲ ምግብ መብላት አይደለም ምግብ ሲያይ ሊያስታውከው ስለሚደርስ አንድ ሲኒ ቡና ብቻ ጠጣ

ስራ በሌለው ሰዓት ባለቤቱ ካሮል አን በነዚያ አፋኞች መዳፍ ስር መሆኗ ብቻ ነው አዕምሮው ውስጥ የሚመጣው፡፡

አሁን በአሜሪካ ሜይን ስቴት ውስጥ ሰዓቱ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በመሆኑ ጨለማ ነው፡፡ ይሄን ጊዜ ካሮል አን ከመንገላታት ብዛት ዝላና ልቧ
ተሰብሮ ቁጭ ብላ ይሆናል፡፡ ነፍሰ ጡር ከሆነች ወዲህ በጊዜ ነው
የምትተኛው፡ ታዲያ እንድትተኛ ይፈቅዱላት ይሆን? መተኛት ቀርቶ
ጎኗን የምታሳርፍበት ቦታ ቢሰጧት ጥሩ ነበር፡፡

ምሽቱ እየገፋ ሲሄድ ሚስቱን ያገቷት ወሮበሎች ሌላ ክፉ ነገር ያውጠነጥኑ ይሆን? ሲል መጨነቅ ጀመረ፡፡

ወጀቡ እንደገና ተነሳ፡፡

አይሮፕላኑ መናጡ ባሰበት፡ በማዕበል ላይ የሚጓዝ መርከብ መስሏል፡ ግዙፍ አይሮፕላን አንዴ ከፍ እያለ አንዴ ዝቅ እያለ በንፋስ ወዲህ ወዲያ የተንገላታ ይጓዛል። ተሳፋሪዎቹ ስጋት ገብቷቸው ከእንቅልፋቸው ተነሱ አስተናጋጁንም ይጣሩ ጀመር፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሆዳቸው ታውኮ ወደ
መጸዳጃ ክፍል ይሮጣሉ አስተናጋጆቹም ወደ ተሳፋሪዎቹ ተራወጡ፡
ኤዲ ቡና ለመጠጣት ሲሄድ ቶም ሉተር ፊቱ መጥቶ ድቅን አለ፡፡ሉተር በአይሮፕላኑ መናወጥ ደንግጦ ፊቱ አመድ መስሏል፡ ሰውነቱ በላብ
ርሷል፡ ኤዲም ጅንን ብሎ ያየዋል፡፡ ቶምን ጉሮሮውን ፈጥርቆ ሊይዘው ትንሽ ነበር የቀረው፤ ነገር ግን ንዴቱን ውጦ ዝም አለ፡፥

‹‹ይሄ ግን የተለመደ ነው?›› ሲል ጠየቀ ቶም በፍርሃት፡

ኤዲ ያለ ምንም ሀዘኔታ ‹‹ያለ ዛሬ እንደዚህ ሆኖ አያውቅም›› ሲል መለሰለት ‹‹ከዚህ በኋላ በወጀቡ ውስጥ ነው የምንጓዘው፤ ነገር ግን በቂ ነዳጅ ስለሌለን አደገኛ ነው››

‹‹እንዴት?›› ሲል ጠየቀ ቶም፡፡

‹‹ነዳጅ እያለቀ ነው››
ሉተር በድንጋጤ እንደተረበሸ ‹‹ታዲያ ነዳጅ እንደማይበቃ ከታወቀ
በጊዜ ወደ ኋላ እንመለሳለን ብለህ አልነበረም?››

ኤዲ ውስጡ ከሉተር በላይ ተሸብሯል፡፡ ነገር ግን ጠላቱ ቶም በመንቦቅቦቁ ረክቷል፡ ‹‹ወደ ኋላ መመለስ እንችል ነበር ነገር ግን የነዳጅ
ፍጆታ ስሌቱን አሳስቼ ስላሰላሁት የአይሮፕላኑ ሰራተኞች በቂ ነዳጅ ያለ
መስሏቸዋል፡፡ ከእናንተ ጋር ያለኝን ውጊያ ለማጠናቀቅ በቂ ምክንያት እንዳለኝ አስታወስክ?››

‹‹አንተ እብድ!›› አለ ሉተር ተስፋ ቆርጦ ‹ሁላችንንም ልትጨርሰን አስበሃል?››
‹‹እኔማ ሚስቴ በእናንተ እጅ መሆኗ ነው እንጂ እያንዳንድሽን ወሮበላ
ሁሉ አጠፋሽ ነበር››

‹‹ሁላችን ከሞትን ሚስትህን አታገኛትማ››

‹‹አውቃለሁ›› አለ ኤዲ ነገር ግን ሚስቱን በነዚያ አረመኔዎች እጅ ለአንድ ቀን እንኳን ሊተዋት አይፈልግም፡፡ ‹‹ምናልባተም አብጄ ሊሆን ይችላል›› አለ ኤዲ፡

ሉተር በጭንቀት እንደተወጠረ ‹‹ይሄ አይሮፕላን ባህር ላይ ያርፋል አይደል?››

‹‹የተገኘው ባህር ላይ ያርፋል ማለት አይደለም፡፡ አይሮፕላኑ ለማረፍ ፀጥ ያለ ባህር ይፈልጋል፤ ማዕበልና ወጀብ የበዛበት ባህር ላይ ልረፍ ካለ ብትንትኑ ነው የሚወጣው።

‹‹ወይ አምላኬ! እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የተሳፈርኩት ምን አቅብጦኝ
አለ ቶም።

‹‹ሚስቴን ለማፈን የተነሳኸው ምን አቅብጦህ ነው?›› አለ ኤዲ ጥርሱን ነክሶ።

አይሮፕላኑ ድንገት ዘጭ ሲል ሉተር ወደ መጸዳጃ ክፍል ሮጠ፡፡

ኤዲ ተሳፋሪዎቹ ወዳሉበት ክፍል አመራ፡፡ ካርታ የሚጫወቱት ሰዎች
የመቀመጫ ቀበቶዎቻቸውን አስረዋል፡፡ አይሮፕላኑ ሲንዘፈዘፍና ሲወዛወዝ
ብርጭቆዎች ካርታዎችና ጠርሙሶች ምንጣፍ ላይ ይንከባለላሉ፡ኤዲ
ኮሪደሩ ላይ አማተረ፡፡ አሁን አይሮፕላኑ ፀጥ ብሎ መጓዝ ስለጀመረ
መኝታቸው ተመልሰው
ተሳፋሪዎች ተረጋግተዋል፡፡ አንዳንዶቹ ወደ መኝታቸው ተመልሰው በመቀመጫ ቀበቶዎች ተጠፍረዋል። በአይሮፕላኑ መወዛወዝ ከመውደቅ ለመዳን ከመታሰር ውጪ ሌላ ምርጫ እንደሌላቸው አውቀዋል፡፡ አንዳንዶቹ
ደግሞ መጋረጃቸውን ከፍተው ጋደም ብለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ተሳፋሪዎች
ጉዞው ሰላማዊ ባይሆንም ፍርሃታቸውን ዋጥ አድርገው ይጫወታሉ።
አንዳንዶቹ ደግሞ ፍርሃቱ ሰቅዞ ይዟቸው መጫወቱንም ትተውታል
መጽሐፍት፣መነጽሮች፣ፒጃማዎች፣ አርቲፊሻል ጥርስ፣ሳንቲሞችና
አምባሮች ወለሉ ላይ ተበታትነው ይታያሉ፡፡ ኤዲ እሱ በፈጠረው ችግር
አይሮፕላኑ በወጀቡ ውስጥ ለመጓዝ በመገደዱ ምክንያት ያለ ቅጥ
በመወዛወዙ ተሳፋሪዎች መሰቃየታቸውን ሲያስበው በፀፀት ልቡ ተነካ፡፡ ይሄ
ሁሉ ሰውስ በእሱ ምክንያት ያልቅ ይሆን?›

ኤዲ ወደ መቀመጫው ሄደና ተቀመጠ፡፡ ከዚህ በኋላ ስለነዳጁ ፍጆታ
ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ካሮል አንን ከነዚያ አረመኔዎች እጅ መንጭቆ
ለመውሰድ ያለው አማራጭ በዕቅዱ መሰረት የተባለው ቦታ ላይ አይሮፕላኑን በድንገት ማሳረፍ ብቻ ነው፡፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ወሮበሎቹ የሚፈልጉትን ማግኘታቸው አያስደስተውም የሉተር ዕቅድ ቢጨናገፍ ደስታው ነበር፡፡ ነገር ግን ሉተር ጎርዲኖን ካላስለቀቀ ኤዲ ካሮል አንን ማግኘት አይችልም፡፡

ካሮል አንን በእጄ ካስገባሁ በኋላ ጎርዲኖ መያዙ አይቀርም  ሲል አሰበ፡ ይህ ግን የሚሆን አልመሰለውም፡፡ ጎርዲኖ በዚህ ጊዜ ውስጥ ርቆ
ሊሄድ ይችላል፡ ሌላው አማራጭ ሉተር ካሮል አንን በመጀመሪያ በእጁ
እንዲያስገባለት መደራደር ቢሆንም ሉተርን ለማስገደድ ምንም ማስፈራሪያ የለውም፡ ሉተር በአንፃሩ ካሮል አንን ይዟል፡

ወዲያው አንድ ሃሳብ ብልጭ አለበት፡፡ ጎርዲኖ በእኔ እጅ እኮ ነው ያለው፤ እሱን እንደማስፈራሪያ መጠቀም እችላለሁ› አለ፡፡ እነሱ ካሮል አንን ይዘዋል፧ እሷን ለማግኘት ከእነሱ ጋር መተባበር አለብኝ፤ ነገር ግን ጎርዲኖ በዚህ አይሮፕላን ላይ ነው ያለው፡፡ እሱን ማግኘት ከፈለጉ ከእኔ ጋር
መተባበር ይኖርባቸዋል
ሁሉም ነገር በእነሱ እጅ አይደለም ሲል በአዕምሮው አውጠነጠነ።

ስለዚህ የድርድሩን መዘውር በእጁ ማስገባት የሚችልበት መንገድ
ይኖር እንደሆን ማሰብ ጀመረ፡፡

አንድ መንገድ ይኖራል።

ለምንድን ነው እነሱ በመጀመሪያ ጎርዲኖን የሚወስዱት? ልውውጡ
መሳ ለመሳ ነው መከናወን ያለበት፡፡›

ከዚያም ንዴቱን ውጦ በጥልቅ ማሰብ ጀመረ፡

‹እንዴት ነው ልውውጡ ሊከናወን የሚችለው?

ጎርዲኖን ሊወስዱ በሚመጡበት ጀልባ ካሮል አንን ይዘው መምጣት
አለባቸው።
ለምን አይሆንም?  ሲል ከራሱ ጋር ተሟገተ፡፡ እሷን ያገቷት ከቤታቸው ብዙም ባልራቀ ቦታ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህም  ቦታ አይሮፕላኑ ከሚያርፍበት ቦታ ብዙም እንደማይርቅ ገምቷል፡፡ ምናልባትም ከአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦታ እሷ እስከታሰረችበት ቦታ ድረስ የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ ሊሆን ይችላል፡ ይሄ ደግሞ ሩቅ አይደለም፡፡

ኤዲ ባሰበው እቅድ ሉተር የሚስማማ ከሆነ ጓደኞቹን በስልክ ሊያናግር
የሚችለው አይሮፕላኑ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ቦትውድ (ካናዳ) ላይ ሲደርስ ይሆናል፡፡ ከቦትውድ ቀጥሎ አይሮፕላኑ የሚያርፈው ከሰባት ሰዓት ጉዞ በኋላ ማለትም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ሼዲያክ ላይ ነው: ወሮበሎቹ ደግሞ
በሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ እዚያ ቦታ ላይ ካሮል አንን ይዘው መምጣት
አለባቸው::

ኤዲ ካሮል አንን አስቀድሞ በእጁ ሊያስገባ እንደሚችል ሲያስበው ደስታውን መቆጣጠር አቃተው፡ የሉተርንም ጎርዲኖን የማስለቀቅ ጥረት
ሊያመክን እንደሚችል ትንሽ እድል እንዳለ ሲያስበው ደግሞ ተጨማሪ
ደስታ ፈጠረለት፡፡ ይሄ ደግሞ በስራ ባልደረቦቹ በኩል ጀግና ያስብለዋል፡
እነዚህን ነፍሰ ገዳይ ወሮበሎች መያዝ ከቻለ ጓደኞቹ ቀደም ብሎ ለፈጸመው ክህደት ምህረት ያደርጉለታል፡፡
መለስ ብሎ ሲያስበው ደግሞ ብዙ ተስፋ ማድረግ እንደሌለበት ገባው፡፡
ይሄ ሁሉ ገና ሀሳብ ነው፡፡ ሉተርም ባሰበው እቅድ አልስማማም ሊል ይችላል ኤዲ ያቀረበውን እቅድ ወሮበሎቹ የማይቀበሉ ከሆነ አይሮፕላኑን
የተባለው ቦታ እንደማያሳርፍ ያስጠነቅቃል፡ ነገር ግን ወሮበሎቹ የኤዲን
ማስፈራሪያ ከባዶ ዛቻ እንደማይዘል መገመት አያቅታቸውም፡፡ ኤዲ ሚስቱን ለማዳን ሲል የተባለውን ሁሉ እንደሚፈፅም ያውቃሉ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን
ሰው በእጃቸው ከማስገባት ውጭ ምንም ፍላጎት የላቸውም፡፡ እኔ ከነሱ
በላይ የተቸገርኩ ስለሆንኩ አቅመ ቢስ ነኝ ሲል አሰበ፡፡ ይህም ወደ ቀድሞው መከፋት ወሰደው፡፡

ሆኖም ኤዲ ያሰበውን ለሉተር ለመንገር ሰውዬውን ለመፈተን አሰበ፡፡
ቢያንስ ሰውዬውን ጥርጥርና ጭንቀት ውስጥ መክተት ይችላል፡፡ ምናልባት ሉተር የኤዲን ማስፈራራት አምኖ ላይቀበል ይችላል፡ ግን እንዴት እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ‹ኤዲ ውሸቱን ነው› ለማለት ወኔ ይጠይቃል፡፡ ሉተር ደግሞ ፈሪ እንደሆነ ታይቷል፤ በተለይ አሁን፡፡

ኤዲ ያሰበውን ለመሞከር ቆረጠ፡፡ ከሉተር በኩል ሊመጣ የሚችለውን
ተቃውሞ ለመመከት የሚያስችል ምላሽ አስቀድሞ መቀመር አለበት፡፡

ሉተር እንቅልፍ ካጡት ተሳፋሪዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በእንግዳ መቀበያው አንድ ጥግ ቁጭ ብሎ ብቻውን ዊስኪውን ይጨልጣል፡፡አይሮፕላኑ የፈጠረበት የሆድ መታወክ አሁን ስለቀነሰለት ፊቱ ፈካ ብሏል መጽሔት እያነበበ ነው፡፡ ኤዲ አጠገቡ ሄደና ጀርባውን ነካ አደረገው፡፡ ሉተር ኤዲን ሲያይ ደንገርገር አለው፤ ፍርሃት ብጤም ስለተሰማው ጠብ ጠብ ሸተተው፧ ኤዲም ‹‹ሚስተር ሉተር ካፒቴኑ ሊያናግርህ ይፈልጋል›› አለው፡፡

ሉተር ስጋት ገባው፡፡ ከተቀመጠበት አልነሳ ሲል ኤዲ ተነስቶ የጭንቅላት ምልክት አሳየው፡፡ከዚያም ሉተር መጽሔቱን አስቀመጠና የመቀመጫ ቀበቶውን አላቆ ተነሳ፡፡

ኤዲ ሉተርን ወደ ማብረሪያው ክፍል ሳይሆን ወደ መጸዳጃ ቤት ወሰደው፡፡፤

መጸዳጃ ቤቱ በትውከት ሽታ ታውኳል፡፡ እንደ እድል ሆኖ አንድ ሰው እጁን እየታጠበ ስላገኘ ኤዲ መጸዳጃ ክፍሉ ውስጥ እንዲቆይ ለሉተር የእጅ ምልክት ሰጠውና እሱ ማበጠሪያ አውጥቶ እያበጠረ ጠበቀው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እጁን የሚታጠበው ተሳፋሪ ከመጸዳጃ ክፍሉ ወጥቶ ሄደ፡፡ ኤዲም የሰውየውን መውጣት ተከትሎ ሉተር ያለበትን መጸዳጃ በር ቆረቀረ ሉተርም ‹‹ምን ፈለግህ?›› ሲል አምባረቀ፡፡
‹‹አፍህን ዝጋና አዳምጥ›› አለው፡፡ ኤዲ ከሉተር ጋር ጠብ ለመፍጠር አላሰበም፡፡ ሉተር ግን ጠብ ጠብ ብሎታል፡፡ ‹‹እዚህ አይሮፕላን ላይ ምን
እንደምትፈልጉ ደርሼበታለሁ ዕቅዳችሁን አውቄዋለሁ አሁን  የእቅድ
ለውጥ አድርጌያለሁ፤ እኔ አይሮፕላኑን የማወርድበት ቦታ ላይ ካሮል አንን
በጀልባ ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ›› አለው፡፡ሉተር አፉን በንቀት ሸረመመና ‹‹አንተ ጥያቄ ማቅረብ እኮ አትችልም የተባልከውን ማድረግ እንጂ›› አለው፡፡

ሉተር እንዲህ አይነት መልስ ይሰጣል ብሎ ኤዲ አልገመተም፡
‹‹እንግዲያውስ ስምምነታችን እዚህ ላይ አብቅቷል›› አለው ኤዲ፡
ሉተር መጨነቁን ፊቱ እያሳበቀበት ነው፡፡ ‹‹አንተ እኮ ምርጫ የለህም፧
ስለዚህ አፍንጫህን ተይዘህ አይሮፕላኑን የተባልክበት ቦታ ላይ ማውረድ
ያቺን ከአፍ የወደቀች ጥሬ የምታክል ሚስትህን ማስመለስ ትፈልጋለህ፧
ስለዙህ አፍንጫህን ተይዘክ
አውሮፕላኑን የተባልክበት ቦታ ላይ ማውረድ አለብህ››

‹‹እውነት ነው፡፡ ነገር ግን…›› ኤዲ ራሱን እየነቀነቀ ‹‹አላምናችሁም›› አለው ሉተርን «እንዴት አምናቹሀለው እኔ እናንተን አምኜ ሁሉን ነገር አድርጌ ብትከዱኝ እድሌን ማበላሸት የለብኝም።አዲስ ድርድር
እንድናደርግ እፈልጋለሁ፡፡››

የሉተር የመንፈስ ብርታት አሁንም ፍንክች አላለም፡:
አዲስ ስምምነት የለም›› አለ ፈርጠም ብሎ፡፡

አሁን ኤዲ ሉተርን የሚያንበረክክበትን ነገር መዘዘ ‹‹እሺ እንግዲያው
ወህኒ ትወርዳለህ›› አለው፡፡

ሉተር የንዴት ሳቅ ሳቀና ‹‹ምንድን ነው የምታወራው?›› ሲል ጠየቀ
ኤዲ አሁን ጥንካሬ ገባው፡፡ በአንጻሩ ሉተር ደግሞ ደካማ ሆኗል፡ለካፒቴኑ ሁሉን ነገር እነግረውና በሚቀጥለው የአይሮፕላን ማረፊያ ከተማ ላይ ለፖሊስ እንሰጥሃለን፡፡ ፖሊስ እዚያ ቦታ ላይ እንዲጠብቅህ በመገናኛ ሬዲዮ እንነግራለን፡፡ ካናዳ ውስጥ እስር ቤት ትወረወራለህ ጓደኞችህ ሊያድኑህ አይችሉም፡፡ ሰው በማገት፣ በባህር ላይ ውንብድናና በመሳሰሉት ወንጀሎች ትከሰሳለህ፡፡ እስር ቤት ውስጥ ትበሰብሳለህ›› አለው።

በመጨረሻ ሉተር መርበድበድ ጀመረ ‹‹ሁሉም ነገር በዕቅዱ መሰረት
እየተፈጸመ ነው›› ሲል የኤዲን ሀሳብ ተቃወመ ‹‹አሁን እቅዱን መለወጥ
አይቻልም፤ ጊዜ የለም፡፡››
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ናንሲ ሌኔሃን ከማታውቀው ሰው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ መተኛቷ
ሰላም ሳይነሳት አልቀረም:

ምንም እንኳን ክፍሉ የሙሽሮች ክፍል ቢሆንም አልጋዎቹ ተደራራቢ ናቸው፡፡ በሩ ክፍት እንዲሆን ቢፈልጉም በወጀቡ ምክንያት በሩ እየተወረወረ
ይዘጋል፡፡ ስለዚህ አስሬ ሲዘጋ እየተነሱ ከመክፈት ይልቅ አንድ ጊዜ ዘግቶ
መተዉ የሰውን ትኩረት አይስብም:፡

ናንሲ በጊዜ ላለመተኛት ብዙ ጥራለች። በዋናው ሳሎን ሄዳ ለመቀመጥ
ብትፈልግም ወንዶች ብቻ ናቸው የተሰባሰቡት፡፡ ቦታው በሲጋራ ጭስ ታፍኗል፧ በዊስኪ ሽታ ታውዷል፡ በተጨማሪም የካርታ ተጫዋቾች ስድብና
ጫጫታ ጆሮ ይሰነጥቃል፤ ቦታው ለሴት ልጅ የሚሆን አይደለም፤ ስለዚህ
‹መተኛት ሳይሻል አይቀርም› ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች።

ስለዚህ መርቪንና ናንሲ መብራቱን አጠፉና በየአልጋቸው ላይ ሰፈሩ።
ናንሲ ዓይኖቿን ብትጨፍንም እንቅልፍ በአይኗ hልዞር አለ፡፡ ወጣቱ ሄሪ ማርክስ ያመጣላት አንድ መለኪያ ዊስኪ እንኳን ለመተኛት የረዳት ነገር
የለም፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ቢሆንም በዓይኗ እንቅልፍ አልኳል ብሏል፡

መርቪንም እንቅልፍ እንዳልያዘው አውቃለች፡ የላይኛው ቆጥ ላይ
ሰፍሮ ይገላበጣል፡፡ እንደ ሌሎች መኝታዎች የሙሽሮቹ አልጋዎች በመጋረጃ የተሸፈኑ ባለመሆናቸው ላለመታየት ያላት ምርጫ መብራቱን ማጥፋት ነው፡፡

እንቅልፍ አልመጣላት ሲል ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በሀሳቧ መጣች ማርጋሬት በጣም ወጣት፣ የኑሮ ውጣ ውረድ የማይገባትና ወደፊት
ስለሚገጥማት ነገር ቅንጣት ታህል የማታውቅ ልጅ ናት። ከማርጋሬት
በጥርጣሬ የተሞላ ፊት ላይ ያነበበችው ግን ከፍተኛ ነፃ የመሆን ስሜት ነው፡፡ ይህ ደግሞ እሷ ወጣት በነበረችበት ጊዜ የገጠማት አይነት ችግር ነው፡፡ ናንሲም በዚያ ወቅት ከወላጆቿ ጋር አተካራ ውስጥ ገብታ ነበር፧
በተለይ ከእናቷ ጋር፡ እናቷ የተከበረ የቦስተን ቤተሰብ ልጅ እንድታገባ
ብትፈልግም እሷ ግን ገና አስራ ስድስት አመት ሲሞላት ሾን ሌኔሃን
ከሚባል የህክምና ትምህርት ከተማረ ከአባቷ ፋብሪካ ውስጥ ከሚሰራ ካቦ ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረች፡፡ እናትዬው ናንሲ ይህን ልጅ እንዳታገባው ልጁ ከሌሎች ሴቶች ጋር እንደሚማግጥ፣ እናት አባቱን ከፍ ዝቅ እያደረገ
እንደሚሳደብና በየጊዜው እንደሚያመው ሀሜት ብታስወራም ናንሲ ግን
የሚነዛውን ሀሜት እንዳልሰማች በማሳለፍ ሾንን አግብታ እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ አብራው ኖራለች፡፡

ማርጋሬት የእሷን ያህል ጥንካሬ ያላት ልጅ አትመስልም፡፡ ከአባቷ ጋር
ካልተስማማች ከቤታቸው መውጣት ትችላለች፡፡ ይቺ ልጅ በየጊዜው ችግር
እያነሳች እንዳታላዝንና ራሷን ለመቻል እንድትጥር የሚመክራት ሰው ያስፈልጋታል፡ እኔ በእሷ እድሜ የሁለት ህጻናት እናት ነበርኩ› አለች በሃሳቧ፡

ስለዚህ ማርጋሬት ራሷን እንድትችል ጠበቅ ያለ ምክር ለግሳታለች እሷም ቃሏን በመጠበቅ ስራ ልትሰጣት ተስፋ አድርጋለች፡፡

ይሄ ሁሉ ደግሞ የሚወሰነው ከወንድሟ ጋር ባላት ጠብ የሀይል
ሚዛኑን በጨበጠው በአጭበርባሪው ሽማግሌ በዳኒ ሪሌይ ነው፡፡ ናንሲ
እንደገና ወደ ጭንቀቷ ተመለሰች፡፡ ጠበቃዋ ማክ ዳኒ ሪሌይን ይኸኔ
አግኝቶት ይሆን? ከአገኘውስ ስለቀድሞው ወንጀሉ ሲነግረው ምን አለ? ይህ ሁሉ ሴራ እሱ ላይ ግፊት ለማድረግ የተጠነሰሰ መሆኑን ጠርጥሮ ይሆን?›
እነዚህን ገና ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ስታወጣ ስታወርድ እንቅልፍ አጥታ
አልጋዋ ላይ ትገላበጣለች፡፡

የሚቀጥለው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦትውድ ከተማ ነው፡፡ ኒውፋውንድ ስትደርስ ማክጋ ስልክ ደውላ ታረጋግጣለች፡፡በዚያ ጊዜ ሁሉ ነገር ይለይለታል፡

አይሮፕላኑ ሲንዘፈዘፍና ሲንገጫገጭ ናንሲ መላ አካልዋ ተረበሸ፡፡አሁን ደግሞ ብሶበታል፡ በአይሮፕላን በተደጋጋሚ ብትሄድም ከዚህ ቀደም
እንዲህ አይነት ሁኔታ ገጥሟት አያውቅም፡፡ ግዙፉ አይሮፕላን በንፋሱና
በወጀቡ ሲወዛወዝ ስጋት ገብቷት ተወርውራ እንዳትወድቅ የአልጋውን ብረት አጥብቃ ያዘች፡፡ ባሏ ከሞተ ወዲህ ብዙ ችግር ገጥሟታል፤ ‹አሁን ጉልበቴ
በርታ በርታ› ማለት አለበት፤ ነገር ግን የአይሮፕላኑ መንዘፍዘፍ ክንፎቹን
ይገነጥል፣ ሞተሩን ሰብሮ ይጥለው ይሆን?› እያለች መፍራቷ አልቀረም፡፡
ፍርሃቷን ይቋቋምላት ይመስል ትራሷን በጥርሷ ነክሳ ያዘች፡፡ ድንገት
አይሮፕላኑ ቁልቁል ወረደ፡፡ ቁልቁል መውረዱ እንዲቆም በእጅጉ ብትመኝም
መውረዱን ቀጥሏል፡ ይህ ሁኔታ ክፉኛ አስደነገጣት፡፡ ከዚያም ዘጭ አለና
ቀጥ ብሎ መብረር ጀመረ፡
መርቪን እጁን ሰዶ ትከሻዋን ያዝ አደረገና ‹‹ንፋሱ የፈጠረው ወጀብ ነው አይሮፕላኑን እንዲህ የሚያደርገው›› አለ ‹‹ከዚህ የባሰ ሁኔታ እኔ ብዙ
ገጥሞኛል፤ አይዞሽ አትፍሪ›› ሲል አጽናናት፡፡

እጁን በእጇ ፈልጋ አጥብቃ ያዝ አደረገችው፡፡ ከአልጋው ወረደና እሷ አልጋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ ፀጉሯን ይደባብስ ገባ፡፡ አሁንም ፍርሃቷ ሙሉ በሙሉ ባይለቃትም አይሮፕላኑ ሲወዛወዝ መርቪን ያዝ ስላደረጋት በመጠኑ
ቀለል አላት፡፡

ምን ያህል ጊዜ እንደተያያዙ አላወቀችም:: ትንሽ ቆይቶ ወጀቡ ተነሳ፡፡በደምብ ስትረጋጋ የመርቪንን እጅ
ለቀቅ አደረገችው፡፡ ምን ማለት እንዳለባት አላወቀችም።

ናንሲ መብራቱን አበራችና ከአልጋዋ ውስጥ ወጣች፡፡ ከላይ የሆነ ልብስ ደረብ አደረገችና መስታወቱ ፊት ቁጭ አለች፡፡ ሁልጊዜም
ጭንቀት ሲይዛት እንደምታደርገው ፀጉሯን አበጠረች፡፡ በጭንቀቷ ጊዜ የመርቪንን እጅ መያዟ አሳፈራት፡ በዚያ ጊዜ ክብሯን ሸጣ እጁን ለጥቂት ጊዜ በመያዟ በሆዷ
ብታመሰግነውም አሁን ፍርሃቷ ሲለቃት ግን ነገሩ አስፈራት፡፡ እሱም ስሜቷን በመረዳት እፍረቷ እንዲለቃት ብሎ ለጊዜው ክፍሉን ለቆላት ወጣ፡፡

መርቪን ትንሽ ቆይቶ ጠርሙስ ብራንዲ ከሁለት መለኪያ ጋር አመጣና
መጠጡን ቀድቶ አንዱን ሰጣት፡፡ አይሮፕላኑ ትንሽ ይወዛወዝ ስለነበር
በአንድ እጇ መለኪያውን በሌላ እጇ ደግሞ የአልጋውን ብረት ይዛለች:
የለበሰው አስቂኝ ልብስ ባያስቃት ኖሮ ድንጋጤው ቶሎ አይለቃትም አስቂኝ ቢሆንም ልክ ሱፍ ለብሶ
እንደሚንጎራደድ ሁሉ ምንም አልመሰለውም፡፡ ሰው ሞኝ ነው ቢለው ግድ
የለውም፡፡ ልበ ሙሉነቱ አስደስቷታል፡፡

ብራንዲዋን ስትጨልጥ በሰራ አካላቷ ሙቀት ስለፈጠረላት ደጋግማ
ተጎነጨች፡፡

መርቪን ወሬ ለመጀመር ብሎ ‹‹እዚያ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ የሆነ
እንግዳ ነገር አየሁ›› አለ ‹‹እኔ ወደ መታጠቢያ ክፍል ስገባ አንድ በድንጋጤ
ቀልቡ የተገፈፈ ተሳፋሪ ሲወጣ አየሁ፡፡ የመታጠቢያ ክፍሉ መስኮት ተሰብሯል የበረራ መሀንዲሱ ደግሞ ጥፋት ሲፈጸም የተያዘ ሰው መስሎ እዚያ ቆሟል፡፡ መስኮቱ የተሰበረው ከአይሮፕላኑ ውጭ ተወርውሮ በገባ
የበረዶ ቋጥኝ መሆኑን ሊታመን የማይችል ታሪክ ነገረኝ፡፡ እኔ ግን ሁለ±
ሲደባደቡ እንደነበር መገመት አላቃተኝም፡፡››

ናንሲ እዚያ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከሚቀመጡ ታሪክ ስለነገራት በሆዷ
መርቪንን አመሰገነችው፡፡ ‹‹የትኛው የበረራ መሀንዲስ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹እንደ እኔ ቁመቱ ሎጋ የሆነና ፀጉሩ ቃጫ የመሰለ መልከ መልካም ወጣት››
‹‹መሀንዲሱን አወቅሁት፤ ተሳፋሪውስ ማን ነው?››
‹‹ስሙን አላውቀውም፤ ነጋዴ ይመስላል፤ አመድማ ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰውዬ ነው›› አለና መርቪን ተነስቶ ብራንዲ ብርጭቆዋ ውስጥ
ጨመረላት፡፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ወጀቡ እስኪጠፋ ወለሉ ላይ ተቃቅፈው ቆዩና ‹‹መርቪን አልጋው ላይ
እንውጣ ከወለሉ ይልቅ እዚያ ይመቸናል›› አለ፡
ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡ ከዚያም በጉልበቷ እየዳኸች
አልጋው ላይ ወጣች፡፡ መርቪንም ተከተላትና አልጋው ላይ አብሯት ወጣ፡፡
እሱም እቅፍ አድርጎ ያዛት፡፡
በወጀቡ ምክንያት አይሮፕላኑ በተናወጠ ቁጥር ልክ መርከበኛ የጀልባ
ውን ምሰሶ እንደሚይዝ ሁሉ ናንሲ መርቪንን ጭምቅ አድርጋ ትይዛለች፡፡
ወጀቡ ሲቀንስና ዘና ስትል እሱም ሰውነቷን በፍቅር ይነካካቸዋል ከዚያ ትንሽ ቆየችና እንቅልፍ ይዟት ሄደ፡፡.
በሩ ተቆርቁሮ «አስተናጋጅ መቷል» የሚል ድምፅ ስትሰማ ከእንቅልፏ ነቃች።
ዓይኖቿን ስትከፍታቸው መርቪን ደረት ላይ መተኛቷን አወቀች
‹ወይ አምላኬ! አለች እየተርበተበተች፡

መርቪን ከተኛችበት እንድትነሳ በእጁ ገፋ አደረጋትና ‹‹ትንሽ ጠብቀን
አስተናጋጅ›› አለ፡፡

ከበሩ ውጭ የቆመው አስተናጋጅ በተደናገጠ ድምፅ እሺ ጌታዬ
እጠብቃለሁ›› አለ፡፡

መርቪን ከአልጋው ወረደና በአልጋ ልብስ ናንሲን ሸፈናት::

በዚህ አድራጎቱ በሆዷ አመሰገነችው፡፡ አስተናጋጁ እንዳያያት ፊቷን ወደ ግድግዳው አዞረች፡፡

መርቪን በሩን ሲከፍት አስተናጋጁ ገባና ‹‹እንዴት አደራችሁ›› አለ በፈገግታ፡፡

የትኩስ ቡና መዓዛ ናንሲን አወዳት፡፡ ‹‹በእንግሊዝ የሰዓት አቆጣጠር
የሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ነው ማለት ነው?›› አለ አስተናጋጁን

‹‹ልክ ነው ጌታዬ የኒውፋውንድ ላንድ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች
የሰዓት አቆጣጠር  ሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ይዘገያል፡››

‹‹መቼም የአየር መንገዶችን የጉዞ መርሃ ግብር ለሚያዘጋጁ ሰዎች ይህ  የሰዓት አቆጣጠር  ችግር
ሳይፈጥርባቸው አይቀርም፡፡ ባህር ላይ ለማረፍ ምን
ያህል ሰዓት ይቀረናል?›› ሲል ጠየቀ መርቪን

‹‹ከግማሽ ሰዓት በኋላ እናርፋለን፡ ከመርሃ ግብሩ አንድ ሰዓት ጉዟችን
የዘገየው በወጀቡ ምክንያት ነው›› አለና አስተናጋጁ በሩን ዘግቶ ወጣ፡

ናንሲ በሩ ከተዘጋ በኋላ ‹የመስኮቱን መጋረጃ ክፈተው፡ ነግቷል››
አለችው:፡ መርቪን ቡና ሲቀዳ የትናንት ምሽት አዳራቸው ፊቱ ላይ መጥቶ
ድቅን አለ፡፡ ወጀቡ በተነሳ ቁጥር መርቪን እጇን የሚይዛት፣ ወለሉ ላይ
የሚወድቁት፣ የመርቪን እጆች ጡቶቿን ሲጨብጥ፣ አይሮፕላኑ ሲናወጥ፣
እሱ ደረት ላይ ልጥፍ የምትለውና እየደባበሰ የሚያስተኛት ትዝ አላት:
ይህን ሰው በጣም ወድጄዋለሁ› አለች በሆዷ።

‹‹ቡና እንደወረደ ወይስ ከወተት ጋር ነው የምትፈልጊው?›› ሲል
ጠየቃት፡፡

‹‹ጥቁር ቡና ይሁንልኝ፡ ስኳር አልፈልግም››
‹‹እንደ እኔ›› አለና ቡናዋን አቀበላት ናንሲ አመስግና ቡናዋን ጠጣች፡፡

ናንሲ ስለ መርቪን በደንብ ማወቅ ፈለገች፡፡ ቡናውን እየጠጣ ስለእሱ ልማዶች ግምቷን አስቀመጠች፡፡ ቴኒስ ይጫወታል፣ ልብ ወለድ ብዙ ማንበብ አይወድም፣ ገበያ መሄድም እንደዚሁ፣ ቁማር ጨዋታ የሚሳካለት ይመስላል፣ ዳንስ ግን የሚችል አይመስልም፡፡›
‹‹ምንድን ነው የምታውጠነጥኚው?›› ሲል
ጠየቀ ለሕይወት  ኢንሹራንስ አደገኛ እንደሆንኩ አድርገሽ የምታይኝ መሰለኝ፡፡››

ናንሲ ቀልዱ አሳቃት፡፡ ‹‹ምን አይነት ሙዚቃ ነው የምትወደው?›› ለሙዚቃ ጆሮ አልሰጥም›› አለ ‹‹መደነስ ባልጠላም ጥሩ ደናሽ ግን አይደለሁም፡፡ አንቺስ?››

እኔ ድሮ ደንሼያለሁ፡መደነስም ነበረብኝ፡፡ እሁድ እሁድ ሱፍ ከሚለብሱ ወንዶች ልጆች ጋር በዳንስ ትምህርት ቤት ዳንስ እማር ነበር፡፡ከላይኛው መደብ የቦስተን ማህበረሰቦች ጋር ለመግባባት ብቸኛው መንገድ ይህ ብቻ እንደሆነ እናቴ ትነግረኝ ነበር፡ እኔ ግን ከዛ ማህበረሰብ ውስጥ
ብገባ ባልገባ ግድ አልነበረኝም፡: የኔ ቀልብ ያለው ከአባቴ ፋብሪካ ጋር ነው፡፡ እናቴ ደግሞ ይሄን ባህሪዬን አትወደውም ነበር፡››

ሁለቱ አዲስ ፍቅረኛሞች ተያዩ፡፡ መርቪንም ትናንት ማታ እንዴት ሲላፉና ሲላላሱ እንዳመሹ እንደሚያስብ ነቃችበት፡፡ ይህም ሀሳብ እፍረት
ውስጥ ከተታትና ፊቷን ወደ መስኮቱ ስታዞር መሬት ታያት፡፡ አይሮፕላኑ
ቦትውድ ሲያርፍ ህይወቷን የሚለውጠውን የስልክ ጥሪ ማድረግ እንዳለባት ትዝ አላት፡ ‹‹ደርሰናል›› አለችና ከመኝታዋ ዘላ ተነሳች ‹‹ልብሴን ልልበስ›› አለች፡፡
‹‹እኔ ቀድሜ ልውጣ›› አለ መርቪን ‹‹ለአንቺ ጥሩ ነው››
እሺ፧ አሁንስ ምን ቀልብ አለኝ አለች በሀሳቧ። ይህን ለእሱ አልነገረችውም፡፡ መርቪን ልብሱን ስበሰበ፡፡ በሩን ከፍቶ ሊወጣ ሲል
ተጠራጠረና ቆመ፡፡ እሷም እንደገና ሊስማት እንደፈለገ አውቃ ወደ እሱ ሄደችና ከንፈሯን ሰጠችው፡፡ ‹‹ሌሊቱን በሙሉ እቅፍ አድርገህ ስላስተኛኸኝ
አመሰግንሃለሁ›› አለችው:

መርቪን ከአንገቱ ዝቅ አለና ሳማት፡፡ አሳሳሙ ልስልስ ያለ ነበር፡ አፏን በአፉ ግጥም አድርጎ ነው የሳማት፡፡ እየተሳሳሙ ትንሽ ቆዩና ተላቀቁ፡፡

ናንሲ በሩን ከፍታ ያዘችለትና ወጥቶ ሄደ፡፡

በሩን እንደዘጋች የደስታ ሲቃ ተናነቃት፡ ከዚህ ሰው ፍቅር ሊይዘኝ ነው አለች፡ በመስኮቱ ስታማትር አይሮፕላኑ ቀስ በቀስ እየወረደ ነው፡፡

መፍጠን አለባት፡፡

መስታወቱ ፊት ቆማ ፀጉሯን ቶሎ አሰረችና የመዋቢያ ዕቃዎቿን ይዛ የሙሽሮቹ ክፍል አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ሴቶች መታጠቢያ ቤት ሄደች፡፡እዚያ ሉሉ ቤልንና አንድ ሌላ ሴት አገኘች፡፡ የመርቪን ሚስት ግን የለችም:

ናንሲ ፊቷን እየታጠበች ጧት ከመርቪን ጋር ያደረገችውን ውይይት
አስታወሰች፡፡ እሱን ስታስብ ደስታ ቢሰማትም ደስታው የተሟላ ባለመሆኑ
ከጭንቀት ሊገላግላት አልቻለም፡፡ ስለሚስቱ ምንም አላለም፡፡ ትናንት ማታ ስለእሷ ስትጠይቀው ድንግርግር እንዳለው ነው የነገራት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን
ይወዳት ይሆን? ትናንት ማታ ሌሊቱን ሙሉ ደረቱ ላይ ለጥፎ ነው ያሳደራት ይህ ብቻውን ጋብቻን ይፍቃል ማለት ግን አይደለም፡
እኔ የምፈልገው ምንድን ነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ‹መርቪንን እንደገና ማግኘት እፈልጋለሁ ከእሱ ጋር ድብቅ ወዳጅነት  ልመስርት?ታዲያ ለኔ ብሎ ጋብቻውን እንዲያፈርስ እፈልጋለሁ? ከአንድ  ሌሊት
ወሲባዊ ልፊያና መሳሳም በኋላ ይህን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
ሊፕስቲክ ለመቀባት መስታወቱ ላይ አፈጠጠች ናንሲ መጠራጠርሽን አቁሚ
ስትል ለራሷ አሳሰበች እውነታውን ታውቂዋለሽ፤ ይሄን ሰው በጣም ፈልገሽዋል፧ ከአስር ዓመት ወዲህ እጅሽን የሰጠሸው ለዚህ ሰው ነው፡:
አሁን አርባ አመትሽን ደፍነሻል፡ አሁን ተገቢውን ሰው አግኝተሻል፡ እዚህ
እዚያ መርገጥሽን ትተሽ ይህን ሰው በእጅሽ አድርጊ፡፡›

ሰውነቷ ላይ ሽቶ አርከፈከፈችና ወጣች፡

ስትወጣ ከመታጠቢያ ቤቱ አጠገብ የተቀመጡትን ናት ሪጅዌይና ወንድሟን ፒተርን አገኘቻቸው ናት ‹‹ደህና አደርሽ ናንሲ›› አላት::

ይህን ስትሰማ ከአምስት ዓመት በፊት በዚህ ሰው የነበራትን ስሜት
አስታወሳት፡፡ እኔ ከእሱ ፍቅር ይዞኝ ነበር፡፡ እሱ ግን ከእኔ ይልቅ የፈለገው
ብላክ ቡትስ ኩባንያን ነበር፡፡ አሁንም ኩባንያውን በእጁ ለማስገባት
የሚፈልገውን ያህል እኔን አይፈልገኝም፡፡ ለሰላምታው በራስ ንቅናቄ ብቻ
አፀፋዊ ሰላምታ ሰጥታው ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡

አስተናጋጆቹ መኝታዎቹን ወደ ሶፋነት ለውጠዋቸዋል። መርቪን ጢሙን ተላጭቶና በነጭ ሽሚዝ ላይ ሱፍ ልብሱን ለብሶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ‹‹በመስኮት ተመልከች ደርሰናል›› አላት፡፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

..ለአስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ አንድ ከእንጨት የተሰራ ቤት አገኙና ጥልቅ አሉ፡፡ ናንሲ ስልኩ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀምጣ እጇ እየተንቀጠቀጠ የስልኩን እጀታ አነሳችና ‹‹ናንሲ ሌኔሃን ነኝ›› አለች፡፡
ኦፕሬተሩም ‹‹የቦስተን ስልክ ፈላጊ መጥታለች ስልኩን አትዝጉት›› አለ።

ትንሽ ቆይቶ ‹‹ናንሲ ነሽ?›› አለ ከወዲያኛው አገር የመጣ ድምጽ ስልኩን የደወለው ማክ መስሏት ስለነበር የሰማችው ድምጽ የዳኒ ሪሌይ መሆኑን ለማወቅ ትንሽ ጊዜ ወስዶባታል ‹‹ዳኒ ሪሌይ ነህ?,,

‹‹ናንሲ ችግር ውስጥ ውድቄልሻለሁ እባክሽ እርጂኝ›› አለ፡

የስልኩን እጀታ አጥብቃ ያዘች፡፡ የሸረበችው ሴራ ግቡን ሊመታ ይመስላል፡፡ የዳኒ ስልክ የረበሻት ለመምሰል በተሰላቸና ረጋ ባለ ድምፅ
‹‹የምን ችግር ዳኒ?›› አለችው፡፡

‹‹ሰዎች በቀድሞ ጊዜ ላጠፋሁት ጥፋት ከዚህም ከዚያም ስልክ እየደወሉ አስቸገሩኝ››

ይሄማ ጥሩ ብስራት ነው፡፡ ማክ ዳኒ ላይ ሽብር ነዝቷል ማለት ነው› አለች ሆዷ በደስታ እየሞቀ፡፡ ዳኒ ድምፁ ይንቀጠቀጣል፡ እሷም ይህን ነው
የፈለገችው፡፡ ነገር ግን እንዳያውቅባት ስለምን እንደሚያወራ እንደማታውቅ
አስመስላለች፡ ‹‹የምን ችግር ነው? ምንድን ነው እሱ?››

‹‹በስልክ ልነግርሽ አልችልም››

‹‹ታዲያ ጉዳዩ በስልክ የማይነገር ከሆነ ለምን ደወልክልኝ?››

‹‹ናንሲ እንደ ቆሻሻ አትቁጠሪኝ ከጉድ እንድታወጪኝ ነው
የደወልኩልሽ››

‹‹እሺ ተረጋጋ›› በሚገባ ተሸብሯል፡፡ ይህን ፍርሃቱን ደግሞ ልትጠቀምበት ወስናለች፡ ‹‹የሰው ስምና አድራሻ ሳትገልፅ የሆነውን ብቻ ንገረኝ የምትፈልገውን ነገር መገመት አያቅተኝም››

‹‹የአባትሽ ሰነዶች በሙሉ አንቺ ጋ ናቸው?››

‹‹አዎ እኔ ቤት ካዝና ውስጥ ናቸው››

‹‹ሰዎቹ ሰነዶቹን ማየት ሳይፈልጉ አይቀሩም››
ዳኒ ራሷ የቀመረችውን ታሪክ እየነገራት ነው፡ ሴራው እስካሁን በዕቅዱ መሰረት እየተከናወነ ነው፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት የሰጠች በማይመስል ሁኔታ ‹‹እነዚያ ሰነዶች ውስጥ አንተን የሚያስጨንቁህ ነገሮች ያሉ
አይመስለኝም››

‹‹እንዴት እርግጠኛ ሆንሽ?›› ሲል አቋረጣት በንዴት።

‹‹እኔ እንጃ››
‹‹ሰነዶቹን በሙሉ አይተሻቸዋል?››
‹‹አይ ብዙ ሰነዶች ነው ያሉት››
‹‹ምን እንዳለ ማንም አያውቅም፡፡ ሰነዶቹን ገና ድሮ አቃጥለሻቸው
ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፡››
‹‹ልክ ነህ የሆነስ ሆነና ሰነዶቹን መመርመር የፈለገው ማነው?››
‹የጠበቆች ማህበር ነው፡፡ እነሱ ሰነዶቹን ለማየት መብት አላቸው››
‹‹የላቸውም፡፡ ነገር ግን እኔ አልሰጥም ካልኩ ጥሩ አይመጣም››
‹‹አንቺ ጠበቃ አይደለሽ ሊያስገድዱሽ አይችሉም››
ናንሲ ንግግሯን ትንሽ ቆም አደረገች ልቡን ልትሰቅለው፡ ‹‹ስለዚህ ችግር አይኖርም›› አለችው
‹‹አልሰጥም ትያቸዋለሽ?››
‹‹ከዚያም በላይ ማድረግ እችላለሁ። ነገ አሜሪካ ስመጣ አቃጥላቸዋለሁ››
ዳኒ ሳግ እየተናነቀው ‹‹ናንሲ አንቺ እውነተኛ ጓደኛ ነሽ›› አለ፡፡
ከልቧ ልትረዳው እንዳልሆነ ህሊናዋ እየነገራት ‹‹ሌላስ ምን ላድርግልህ?››
‹‹ይሄ ይበቃኛል እንዴት አድርጌ እንደማመሰግንሽ አላውቅም››
‹‹አንተ ካነሳኸው ደግሞ ውለታ ልጠይቅህ ነው›› አለችና ከንፈሯን
በጥርሷ ነከሰችው::
‹‹መቼም ለምን እንዲህ
እንደፈለግኩ ሳታውቅ አትቀርም››
እንዲህ በአስቸኳይ ወደ አሜሪካ ለመመለስ
‹‹አላውቅም ምንድን ነው?›› አላት፡
ፒተር ኩባንያውን እኔ ሳላውቅ ሊሸጥ ተዘጋጅቷል››
ዳኒ ፀጥ አለ፡፡
‹‹ዳኒ አለህ?››
‹‹አለሁ አንቺ እንዲሸጥ አትፈልጊም?››
‹‹እኔ እንዲሸጥ አልፈልግም፡፡ ለግዥ የቀረበው ዋጋ በጣም ዝቅ ያለ ነው፡፡ ከተሽጠ እኔም ቦታ የለኝም: ስለዚህ እንዲሸጥ የማልፈልገው ለዚህ ነው ፒተር ኩባንያው የሚሸጥበት ዋጋ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ያውቃል፡
ነገር ግን እኔን ለመጉዳት ስለሆነ ቢሸጥ ግድ የለውም:፡››
‹‹የሚሸጥበት ዋጋ ጥሩ አይደለም? ኩባንያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
አክሳሪ እየሆነ እኮ ነው››
‹‹ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አታውቅም››
‹‹አንድ የምገምተው ነገር አለ››
‹‹ታውቃለህ፡፡ ምክንያቱን ተናገረው እና ይውጣልህ፡ ፒተር የማይረባ ማኔጀር ስለሆነ ነው››
‹‹እሺ››
‹‹ኩባንያውን በርካሽ ዋጋ ከምንሸጠው ለምን ከኃላፊነት አናነሳውም፡፡
እኔ የኃላፊነቱን ቦታ ልውሰድና ወደ ቀድሞው ስሙ ልመልሰው፡፡ እንደ
ምመልሰውም ታውቃለህ፡፡ ኩባንያው ደህና ደረጃ ላይ ሲደርስ በከፍተኛ ዋጋ
እንሸጠዋለን ከፈለግን››
‹‹እኔ አላውቅም››
‹‹ዳኒ አሁን በድፍን አውሮፓ ጦርነት እየተቀጣጠለ ነው፡ ይህ ማለት አቅርቦት ጥያቄ ይጎርፍልናል፡፡ ሁለት  ሶስት ዓመት ብንቆይ ደግሞ
ቢዝነስ ይጧጧፋል ማለት ነው፡፡ ከምናመርተው ጫማ በላይ የጫማ ኩባንያውን አሁን ከተሰጠው በሁለት ሶስት እጥፍ ዋጋ መሸጥ እንችላለን፡›››

‹‹ነገር ግን ከናት ሪጅዌይ ጋር የፈፀምኩት የጥብቅና ውል ለኔ ጠቃሚዬ ነው›› አለ ዳኒ፡፡

‹‹ጥቅም የምትለውን ተወው፡፡ እኔ እንድትረዳኝ ነው የጠየኩv››
‹ይህን ሁሉ የምትጠይቂኝ ለራስሽ ጥቅም አይደለም?›

አንተ እልም ያልክ ውሸታም ነክ አንተስ ስለራስክ ጥቅም አደለም የምታወራው? ልትለው ፈልጋ ላለመናገር ከራሷ ጋር ታገለችና ‹አባባ ጋ  ያሉትን ሰነዶች እንዳትረሳ›› አለችና ትንፋሿን ያዝ አደረገች

‹‹ምንድን ነው ያልሽው?››
‹‹ባጭሩ እንረዳዳ ነው የምልህ፡፡ እንዲህ ያለ ነገር መቼም የሚገባህ
ይመስለኛል››
‹‹አዎ ገብቶኛል ይሄ ዛቻ ይባላል››
እያደረገችው ያለችው ነገር በሙሉ የሚያሳፍር ነው፡፡ ነገር ግን ከማን ጋር እንደምትወያይ አስታወሰችና ‹‹አንተ አስመሳይ ሽማግሌ! እንደዚህ ያለ ነገር ህይወትህን ሙሉ
ስትፈፅም ኖረሃል››

ዳኒ ሳቀና ‹‹ዛሬ እጅሽ ላይ ወድቂያለሁ፡›› ይህን ተናግሮ ሲያበቃ አንድ
ነገር አዕምሮው ውስጥ አቃጨለና ‹‹እኔ ላይ ግፊት ለማድረግ ብለሽ ራስሽ
ሳትሆኚ አትቀሪም ይህን የጠነሰስሽው›› አላት፡፡

አሁን ወደ እውነቱ ተጠግቷል፡፡
‹‹አንተ ብትሆን እንዲህ
እንደምታደርግ አውቃለሁ፡፡ ከዚህ በላይ አትመርምረኝ፡፡ አንድ ማወቅ የሚገባህ ነገር በነገው የቦርድ ስብሰባ እኔን ከደገፍክ ከችግር ነጻ ነህ ካልደገፍከኝ ግን አለቀልህ›› ስትል ቁርጡን ነገረችው:፡ አሁን በግልጽ
ማስፈራራቱን ተያያዘችው፡፡ እሱ ደግሞ የሚገባው ቋንቋ እንዲህ ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እግሯ ስር ይወድቃል ወይስ ዞር በይ› ይላል?

‹‹እኔን እኮ እንዲህ ልትናገሪኝ አትችይም! እኔ ቂጥሽን ያልጠረግሽ ልጅ
ሳለሽ ጀምሮ ነው የማውቅሽ››

ናንሲ ድምጿን ለስለስ አድርጋ ‹‹ታዲያ እኔን ለመርዳት ይሄ ምክንያት
ሊሆን አይችልም›› አለች፡፡

ትንሽ ቆየና ዳኒ ‹‹ሌላ ምን ምርጫ አለኝ!›› አለ፡፡

‹‹ያለህ አይመስለኝም እኔ ያልኩህን ከማድረግ ውጭ።››

‹‹እሺ›› አለ በገነገነ ሁኔታ፡ ‹‹ነገ ለአንቺ ድምፅ እሰጣለሁ አንቺ
እነዚያን ሰነዶች የምታጠፊ ከሆነ፡፡››

ናንሲ ያሰበችው በመሳካቱ ልታለቅስ ምንም  አልቀራትም፡፡ ዳኒን
ከእግሯ በታች አዋለችው፡ አሁን ድሉ የእሷ ሊሆን ነው፡፡ የብላክ የጫማ
ኩባንያ በእሷ ቁጥጥር ስር ሊገባ ነው፡፡
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሰላሳ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ምን መሰለሽ ፍቅር በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ከብረሀናማ ቀለማቶች የተሸመነ ጥልቁ ስሜት  ነው፡፡ፍቅር ወደ ወደድነው ሰው ልብ ውስጥ ሰተት ብለን የምንገባበትን በር  የምንከፍትበት ማስተር ኪይ ነው፡፡ፍቅር ስለእራሳችን በተለየ መልኩ እንድናስብ የሚያስገድደን የተቀደሰ የዕይታ ብሌናችን ነው፡፡በፍቅር የተነደፈ ደሀ  በውስጡ የሚሰማው አለም ሁሉ የእሱ ንብረት እንደሆነችና አውቆና ንቆ እንደተዋት ነው …የተናቀ እና መጠጊያ አልባው ሰው በፍቅር እቅፍ ውስጥ ሲወድቅ የንግስና ዙፋኑ የእሱ እንደሆነ እና አለም ጠቅላላ ወደእሱ አጎንብሳ እየሰገደችለት እንደሆነ ነው የሚሰማው፡፡

የስልጣን ማማ ላይ ተቆናጦ ልቡ በትዕቢት ያበጠ በፍቅር አዳልጦት ሲዘረጥጥ ..እንዴ ለካ እኔም ሰው ነኝ…?ለካ ማንበርከክ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ለመንበርከክም እገደዳለሁ? ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል፡፡ ….ሰውን ሞት እና መቃብር ብቻ ሳይሆን ፍቅርም ወደ አንድ ተመሳሳይ ስሜት በመጎተት ያቀራርበዋል፡፡…..ግን አሳዛኙ ነገር ይሄ ቅዱሱ ፍቅር ብዙ ጊዜ ድምጥማጡ የሚጠፋው በማይረባ ትርኪ ሚርኪ  እውነትነታቸው ባልተረጋገጡ ጉዳዬች ነው…..ባለመደማመጥ እና ባልተጣራ ወሬ የተነሳ  ነው፡፡

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹ፍቅረኛሽ እንዳገባ ማን ነው የነገረሽ……..? ››

‹‹ከእስር ቤት ወጥቼ ተጠርዥ ልመጣ ስል አንድ እዛ  የምትኖር ጓደኛዬ ከአሰሪዎቼ ቤት የነበረኝን ሻንጣዬን አውጥታ እሷ ጋር አድርጋልኝ ስለነበር…ስትሸኝ አቀብላኝ ነበር ፡፡ይቺ ጓደኛዬ ..በጣም ጥሩ ሰው ነች ለኪስ የሚሆነኝን ትንሽ ብር የሰጠችኝም እሷ ነበረች.. ወደ ኢትዬጵያ   የገባሁትም በለሊት ስለነበረ ሆቴል ነበር የያዝኩት እና በሰላም መግባቴን ለመናገር ለጓደኛዬ ስልክ ደወልኩላት፡፡ ፖስታ ከኢትዬጵያ መቶልኝ እንደነበረ እና ሻንጣ ኪስ ውስጥ ከታልኝ ሳትነገርኝ እንደረሳችው ነገረችኝ፤ስፈልገው አገኘሁት፡፡

‹‹ስልክ ባልደውልላት እና እሷም አስታውሳ ባትነግረኝ ኖሮ አላየውም ነበር…ቀጥታ ፍቅረኛዬ ቤት ሄጄ  ስርፕራይዝ ላደርገው ነበር እቅዴ..እሱ ጋር አንድ ሶስት ቀን አሳልፌ እና አገግሜ  ወደጊንጪ  ቤተሰቦቼ ጋር ልሄድ ነበር  ያሰብኩት..››
ፖስታውን ስከፍተው ግን በቃ የሲኦልን በር እንደመክፍት ቁጠሪው፣…ውስጡ ሲኦላዊ የክህደት እሳት ነበር ያለው..አገባዋለሁ ብዬ ሳልመው የነበረው ሰውዬ የአንድ አመት  ህጻን አቅፎ ሲያባብል የተነሳው ፎቶ ነው፡፡ከመከራዬ አገግምበታላሁ  ከስባራቴ እጠገንበታላሁ ያልኩት ሰው ጭራሽ መከራዬን የሚጨምር.ስብራቴን የሚያባብስ ሆኖ ጠበቀኝ…..ከፎቶ ጀርባ ላይ…..  ናሆም ፍቃዱ እንኳንም ለአንደኛ አመት ልደት አደረሰህ ይላል፡፡ምድር ተሰንጥቃ ብትውጠኝ እወድ ነበር….ምን አይነት ክህደት ነው…?አላስቻለኝም እወነቱን ለማወቅ ጭለማን ተገን አድርጌ ሰፈሩ ሄድኩ….አድፍጬ በአጥር ቀዳዳ አጨንቁሬ ግቢውን ለሰዓታት ቃኘሁ…እውነት ነበረ ፤ልጅ አቅፎ ግቢ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲያባብል እና ሲያጫውት አየሁት…በወለብታ ነው እንጂ ሚስቱንም በመጠኑ አይቼያታለሁ››

‹‹ማንነቷን ግን አላየሽም? ››

‹‹ማንነቷ  ምን ይሰራልኛል…ሮማንንም አገባ ቦንቱን ለእኔ ምንስ ሲጨምርልኝ ምንስ ሲቀንስልኝ?››

‹‹አይ ማንነቷን እስክታውቂ  በደንብ ብታጣሪ..ወይንም እሱን በአካል አግኝተሸ ለምን እንደዛ አደረግክ? ብለሽ ብትጠይቂው ጥሩ ነበረ ….ሁለት ሳምንት ሙሉ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነሽ አትሰቃይም ነበር..በማትፈልጊውን የህይወት መስመር አትጀምሪም ነበር.ብዙ ጊዜ አውነትን ለማደን ብለን እንደ ጀግና መንግድ እንጀምርና ገና የጫካው መግቢያ ጋር ስንደርስ ብርክ ይዞን  እንመለሳለን፤ ቀስታችንን እዛው ጨርሰን ወደኃላ እንመለሳለን.ኩልል እና ጥርት ያለውን እውነት ለማግኘት ግን የጫካው እንብርት ድረስ በእሾኩ እየተወጉ እና በፍርሀት እየራዱ መጓዝን ይጠይቃል  ››

‹‹አልገባኝም››አለቻት ኮስተር ብላ
‹‹ንብረትሽ..ማለት አንቺ ለፍቅረኛሽ የላክሽው ብር  በእጥፍ ጨምሮ አንቺኑ እየጠበቀሽ ነው››

‹‹እንዴት?››

‹‹በላክሽው 300 ሺ ብር ላይ የራሱን ብር ጨምሮ ሚኒባስ ገዝቶበታል››

‹‹እኮ እሱንማ ግቢው ውስጥ ቆማ አይቼያለሁ፡ግን አሁን ንብረትሽ ነው ብሎ የሚመልስልኝ ይመስልሻል…?ልመልስልሽስ ቢል ሚስቱ እሺ ትለዋለች..?እኔስ አሱ ፊት ቆሜ ብሬን ስጠኝ አትስጠየኝ ብዬ የመከራከሩ ጉልበት ይኖረኛል?፡፡›

‹‹ሚኒባሶ በቀን የምትሰራው ብር ያንቺ ድርሻ በስምሽ በተከፈተ የባንክ ደብተር እያስቀመጠልሽ ነው…በጥሬ ብር ደረጃ መቶ ሳላሳ ሺብር ባንክ ተቀምጦልሻል…..ሚኒባሶም ባንቺ ስም ነች፡፡››

‹‹እንዴት ተደርጎ?››

‹‹በቃ በጣም የሚያፈቅርሽ እና ላንቺም ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቦችሽም የሚኖር  እና የሚጨነቅ መልካም ልጅ ነው››

‹‹አይ ያደረገው ነገር እወነት እንዳልሺው ከሆነ ዘራፊ አያሰኘው ይሆናል.. ነገር ግን  ፍቅሬን ትቶ ሌላ አግብቶ ሌላ ልጅ መውለዱ ግን  ከከዳተኛነት ውጭ ሌላ ስያሜ ሊሰጠው አይችልም ፡፡

‹‹አሁን ቀጥ ብለሽ ዛሬውኑ እቤቱ ሂጂ››

‹‹ምን ልፈጥር?››

‹‹ሂጂ አልኩሽ ሂጂ.››

‹‹ሄጄስ?››

‹‹በቃ ግቢውን አንኳኩተሸ ግቢ..ከዛ የሚሆነው ነገር ይሆናል…ይሄንን ካላደረግሽ ግን ህይወትሽን ሙሉ ምትፀፀችበትን ስህተት ነው የምትሰሪው››በብዙ ምክር እና ከማስፈራሪያ  በኃላ አሳምናት  ሸኘቻት….

….ከዚህ በላይ ልትነግራት አልፈለገችም..እራሷ በሂደቱ ውስጥ እንድታጣጥመው ነው የፈለገችው..ፍቅረኛዋ አሁንም አልወለደም ፤አላገባምም…እሱ በምንም አይነት እሷን አልከዳትም…ለአንድ ቀን እንኳን ወስልቶባት አያውቅም..እንደውም ከዳተኛ መባል ካለበት እራሷ ነች….፡፡
እርግጥ እንዳለችው እቤቱ ውስጥ ሴት አለች…አዎ እቤት ውስጥ ልጅም አለ..የሚወደድ ናሆም የሚባል የአንድ አመት ልጅ…ሴትዬዋ  ግን የገዛ እህቷ ነች….ታናሽ እህቷ ..ልጅም የእህቷ ልጅ፡፡ጊንጪ እቤተሰቦቾ ቤት ተቀምጣ የአስራሁለተኛ ክፍል ትምህርቷን በመማር ላይ እያለች አረገዘች….እሱ ሚስጥሩን ሰማ ፤ልጅቷም ህይወቷን እንዳታበላሽ ቤተሰቦቾም በኖሩበት ሀገር እንዳይሸማቀቁ ሁሉንም አሳመናቸውና ዞር አድርጎ አዲስአበባ ወደራሱ ቤት ወሰዳት….ለፍቅሩ ሲል…የእሷ ቤተሰቦች እንዳይሳቀቁ በማሰብ….. ..እሱ ጋር ተሸሽጋ ወለደች..አሁን ትምህርቷንም እየተማረች ነው፡፡››

ታዲያ ፎቶውን ማነው  የላከላት..?ማን ነው እንደዛ እንድታስብ የፈለገው›…?መልሱ የገዛ እህቷ ነች፡፡በእዛች ጭንቅ ጊዜዋ ያፈቀረችውና  ያረገዘችለት ሰው አፍንጫሽን ላሺ  ባላት ወቅት የእህቷ ፍቅረኛ ግን እንደዛ አይዞሽ ማለቱ፤ ሽሽጎ ተንከባክቦ ጭለማውን ጊዜ እንድታልፍ ማድረጉን ..እሷን መንከባከቡ ልጇን መውደዱ ሌላ ነገር እንድታስብ አደረጋት.. የሰው ሀገር በስደት ላይ ባለችው ታላቅ እህቷ እንድትቀና ..እንድታፈቅረው…የራሴ በሆነ ብላ እንድትመኝ …
​​📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሰላሳ_አንድ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋ

ኬድሮን ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ደባበራት እና ከቤቷ ወጣች… ቦሌ አካባቢ  ወደሚገኝ ሰሞኑን ወደተከፈተ  አንድ ሆቴል ነው እየሄደች ያለችው ..መኪናዋን ሆቴሉ ግቢ ውስጥ በማስገባት ምቹ ቦታ ፈልጋ አቆመችና የለበስችውን ልብስ እዛው ከመኪናዋ ሳትወርድ አወላልቃ የዋና ልብሷን በመልበስ  ወደ ዋና ጋንዳው አመራች ..ሰውነቷን  ጭፍግግ ስላለት  ዘና ማለት  ነው የፈለገችው….በዋና ሰውነቷን ማፍታታት……
የዋና ገንዳው አካባቢ እንደደረሰች ዘላ ውሀ ውስጥ ገብታ መንቦጫረቅ አልፈለገችም…የመዋኛ ገንዳውን ዙሪያ ከበው ወደ ተዘረጉ ዘመናዊ ወንበሮች ሄደችና ..ባዳውን ከሆነ አንድ ወንበር ላይ ዘና ብላ በመቀመጥ የሚዋኙትን ታዳሚዎች እያየችና  እየታዘበች መዝናናቷን ቀጠለች…..
…..አበሻም ፈረንጆችም…. ሴቶችም ወንዶችም… ህፃናትም፤ ወጣትና አሮጊቶችም በስብጥር  ሲዋኙ እና ሲንቦጫረቁ ይታያሉ….
ስሜቷ አንቀልቅሎ ወደ እዚህ ስፍራ ያመጣት ለምን እንደሆነ እስከአሁን አልተገለፀላትም .. …?…..  ድንገት ግን ሳታስብ አንድ ወጣት ዕድሜው በግምት በ25 30 ዓመት መካከል የሚገኝ  ወንድ ላይ አይኗ አረፈ…ያምራል… በጣም ነው የሚያምረው..፡፡ ከደረቱ በላይ ያለው የሰውነት ቅርጽ ውጥርጥር ያለ እና ሚማርክ ነው…ፀጉሩ በውሀው አቅም ተሸንፎ በሚመስል ሁኔታ ዝልፍልፍ ብሎ ግንባሩ ላይ ተዘናፍሏል፡፡አይኖቹ ከጨረቃ የተዋሳቸው ይመስላሉ…ኪሊማንጀሮ ተራራ ጫፍ ላይ ያገኘችውን አንድሪውን አስታወሳት፡፡.
እሷ ደግሞ ካለ ችግሯ ወይም ድክመት ሊባልም ይችላል   ስድስት ወር ወይም አመት ምንም ወንድ ሳያምራት ወይም ከምንም አይነት ወንድ ጋር ሳትነካካ ትቆይና ድንገት በሰከንድ ውስጥ በእይታዋ ውስጥ የሆነ ወንድ ገብቶ ቀልቧን ከሰረቀት በቃ..ስግብግብ ነው የምትለው..፡፡በዛኑ ቀን ወይም ከተቻለም በዛኑ ደቂቃ ማግኘትና አምሮቷን መወጣት አለባት….(ያው የእሷ ፍቅር ከአንድ ጊዜ የወሲብ ፍላጎት አያልፍም ..ከዛ በላይ ፈልጋ አታውቅም ..ለእሷ በፍቅር መነሁለል እና . ወንድን እየተከተሉ መዞር ወይም ወንድ አፈቀርኩሽ እያለ ለሀጩን እያዝረበረበ በዙሪያዋ እንዲሽከረከርባት በፍፅም አትፈቅድም….)
.የእሷ ችግር ጊዜያዊ ነው ..ጊዜያዊም ብቻ ሳይሆን ቅፅበታዊም ጭምር ነው….በፈለገች ጊዜ ማግኘት አለባት… .ካለበለዛ እራሷን ሁሉ መቆጣጠር ስለሚያቅታት ጥፋት ታጠፋለች....የማይሰራ ስራ ትሰራለች…የወሲብ ጠኔም በቀላሉ አዙሮ እና አጥወልውሎ ሊደፋት ሁሉ ይችላል….እና አሁንም ይሄ ሻንቂላ ወንዳ ወንድ ወጣት እፊቷ ያለው ሰማያዊ መዋኛ  ገንዳ ውስጥ ጥበባዊ በሆነ ስልት እንደ ዓሳ ነባሪ ብቅ ጥልቅ በማለት እየዋኘ ቀልቧን ስልብልብ አድርጎታል..
‹‹ተይ ይቅርብሽ››እራሷን ለመገሰፅ ሞከረች…እራሷን መገደብ እንደማይሳካላት ግን ከልምድ ታውቃለች… …..ከለበሰችው የዋና ልብስ ስር እግሯ እና እግሯ መካከል ያሳክከት ጀመረ.. እጣቷን ወደ ጭኗ መካከል በመስደድ የሚበላትን አካባቢ አከክ…አከ…ክ አድርጋ ተንፈስ ለማለት አሰበችና   ዙሪያዋን በሰዎች መከበቧን  ሳታስተውል መልሳ ተወችው....ከተቀመጠችበት መቀመጫ ተነሳችና ወደዋናው ገንዳ ቀረበች…ምን ማድረግ እንዳለባት እያሰበች ነው…ድንገት በትይዩ አቅጣጫ በሰማዩ ላይ በሶስት መቶ ሜትር  ርቀት ….   ንስራ ሲያንጃብብ ተመለከተችና
‹‹…ወይ ከመቼው ተከትሎኝ መጣ….ግን እንኳን መጣህ.››ስትል በውስጧ አጉረመረመች…. እሱን በአቅራቢያዋ በማየቷ ደስ አላት..አዎ ይሄ ቀልቧ ያረፈበትን ወጣት ከተቻለ አሁን ለመክሰስ..ካልሆነም ለእራት ለማድረስ የእሱ እርዳታ ያስፈልጋታል….ስለደካማ ጎኑ በእነዛ ሰርሳሪ አይኖቹ  በማየት  ካልነገረራትና በምን ሁኔታ ብትቀርበው የሀሳቧ ሊሳካ እንደሚችል መረጃውን ካላቀበላት ባሰበችው ፍጥነት ሊሰካላት አይችልም ፡፡

ደስታዋ ግን ሀሳቡን አስባ ሳትጨርስ ነው ከውስጧ በኖ የጠፋው….የንስሯን እርዳታ መጠቀም አትችልም…ምክንያቱም ይሄ ሰው ምን አልባት የማይሆን ታሪክ ካለው..ወይም አደጋኛ ሰው ከሆነ ንስሯ  የሆነ ተአምር ፈጥሮ ከእሱ ጋር በምንም አይነት ተአምር እንዳትገናኝ ያደርጋታል..በምኞቷ መካከል ጣልቃ ይገባና ያጨናግፍባታል…ያ እንዲሆን ደግሞ አትፈልግም...ስለዚህ እዚህ ታሪክ ውስጥ ንስሯን አታሳትፈውም፡፡እንደዛ ወሰነች፡፡

..እንዳዛ ከሆነ ደግሞ እየበላት ያለውን በገዛ ጣቶቾ  ስታክ ማደራ ነው…ፈርዶባት ደግሞ በአንዱ የተቀሰቀውን ስሜቷ  በሌላ ወንድ አካክሳ ልታበርደው  አትችልም…ይሄ የእሷ የሆነ ልዩ ባህሪ ነው……
ስለዚህ ይሄን ጉዳይ በራሷ መወጣት አለባት….."ንስሯን ምንም እርዳታ አልጠይቀውም….እሱ በሚዋኝበት አካባቢ እስትራቴጂካል ቦታ መርጣ   ገንዳው ዳር ተቀመጠችና እግራን ብቻ ውሀ ውስጥ በማስገባት ልክ መዋኘት እንደሚፈልግ … ግን ዋና ስለማይችል መግባቱን እንደፈራ ሰው በመምሰል ማንቦጫረቅ እና በእጇ እየጨለፈች በውሀው መጫወት  ጀመረች….
አዎ  ልጁ እየዋኘ ወደስሯ ተጠጋ…ተመልሶ ሄደ ..ሶስት አራቴ በሰሯ ተመላለሰ…በአምስተኛው በአጠገቧ ሲያልፍና በጣም ሲጠጋት…

‹‹ታድለህ ››አለችው

‹‹ምን አልሺኝ…?››

‹‹ እንደ ዓሳ ነው የምትዋኘው…ታስቀናለህ…!!!  ››  

‹‹አመሰግናለሁ…››ብሏት ዋናውን ሊቀጥል ካለ በኃላ መልሶ ወደ እሷ  በመዞር..‹‹ለምን አትገቢም…? ››ሲል ጠየቀት

‹‹መግባት እፈልጋለሁ ..ግን ዋና አልችልም፤ ብሰምጥስ…?››

‹‹አይዞሽ እኔ እጠብቅሻለው ግቢ››

‹‹ኸረ ተው ይቅርብኝ››ተግደረደረች

‹‹ግቢ. በእኔ ተማመኚ››

የምትፈልገው  ሀሳብ ስለሆነ ቀሰ ብላ ገባችና ልክ እንደጀማሪ ዋናተኛ ተንደፋደፈች..በቅርቧ ስለነበረ ቶሎ ብሎ ከስር ገባና  ሰቅስቆ በክንዶቹ
መሀል አድርጎ ወደ ላይ አወጣት …
  
    ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 32,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
​​📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹አይዞሽ..አይዞሽ››

‹‹ያስፈራል..››

‹‹እኔ ደግፍሻለሁ… ቀስ ብለሽ ዋኚ..››እጆቹ ከስር ሲደግፈኝ በማወቅና ባለማወቅ መካከል ሆኖ  አንዴ ጡቶቼን ሲጨፈልቃት..አንዴ ወደጭኑ አካባቢ ሲንሸራተት..እሷም ደግሞ ልክ እንደፕሮፌሽናል ተዋናይ ፍጽም በማስመሰል … አንዴ የፈራች መስላ አንገቱ ላይ በመጠምጠም ከሰውነቱ ስትጣበቅ..አንዴ ከእጁ ሾልካ ውሀ ውስጥ እራሷን በመድፈቅ ስትንደፋደፍ…..በመጋል እና በመቃተት መካከል ሆና ግማሽ ሰዓት ያህል ካለማመዳት በኃላ

‹‹ለዛሬ ይብቃሽ ልወጣ ነው ››አለት…

ቅፅበታዊ ውሳኔው አበሳጫት

‹‹እንዴ ምነው …?በደንብ ሳልችል…?››ኮስተር ብላ..ኮስተር አባባሎን ለተመለከተ ገንዘብ ከፍላው የሚያስተምራትን ሰው የምታወራ ነው የሚመስለው፡፡

መቼም የመልመድ ተስፋ የላትም የሚል  በሚመስል ስሜት ‹‹አረ ባክሽ..!!እኛ በስንት አመትና ልፋት የቻልነውን ዋና አንቺ በአንድ ቀን ..ለዛውም በግማሽ ሰዓት መልመድ ትልጊያለሽ……?.››አላት..
የሚያወሩት በጣም ጥልቅ ያልሆነ የገንዳው ጠርዝ አካባቢ ቆመው ነው..ውሀው እሷን ጡቷ አካባቢ እሱን ደግሞ እንብርቱን አካባቢ ድረስ ሸፍኖቸዋል…ከፊል እርቃናቸውን እየታያዩ ፊት ለፊት ተፋጠው ነው የምያወሩት..እሷ ለወሲብ እየጎመዣች..እሱ በትምክት እየጎረረባት 

‹‹አረ በናትህ ዋናን እኮ የተለየ ጥበብ አደረከው..›› አለችው..እወነቷን ነበር ያለችውት፡፡

እሷ የደሎ መና ልጅ ነኝ..ዋና እየተስገመገመ በሚጋልበው  የያዶት ወንዝ በ3 አመቷ በቀልድ ነው የለመደችው…በዕቃ ዕቃ ጫወታ…ያዶት መዋኘት ለለመደ ሰው  ደግሞ እዚህ የረጋ ወሃ  ላይ መዋኘት ቀልድ ነው፡፡
‹‹እንግዲህ  ጥበብ ካልሆነ ያው ሜዳው…አሳይና››ብሎ አበሳጫት…የጀመረችውን የማጥመጃ ዘዴ በደቂቃ ውስጥ እረስታ ያልሸነፍ ባይነት እና የበላይነት መንፈሷ ከውስጧ ተንቀልቅሎ ገነፈለባት…በቆመችበት ቦታ ድንገት  ሰመጠችና  ውስጥ ለውስጥ መሹለክለክ ጀመረች … ካለችበት ጫፍ ወደሌላ ጫፍ ተወነጨፈችና በሰካንድ በዛኛው ጫፍ ስትወጣ እሱም እሷን ፍለጋ ሰምጦ ኖሮ በድንጋጤ ከመሀከል አካባቢ ከውሀ ውስጥ ሲወጣ ተመለከተችው..አይኑን ከወዲህ ወዲያ አማተረና እሱ ካለበት በብዙ እርቀት ተስፈንጥራ ከውሀ ውስጥ በሰላም እና በፈገግታ ታጅባ ብቅ ጥልቅ እያለች ሲያያት በመገረም  እና በንዴት አፈጠጠባት… በቄንጥና ቲያትራዊ በሆነ ትዕይንት  ከላይ እየተንሳፈፈች ፤ እየዋኛችና  እየተገለባበጠች ስሩ ደረሰች፡፡
‹‹እያሾፍሽብኝ ነበር..…?እኔ ደግሞ የሰመጥሽ መስሎኝ መደንገጤ››
‹‹ብሰምጥስ ምን ያስደነግጥሀል…?››

‹‹እንዴ ሰው አይደለሽ …? ለምን አልደነግጥ…?››

‹‹ስለተጨነክልኝ አመሰግናለሁ››

‹‹አረ ምስጋናሽን ቀቅለሽ ብይው..በአንቺ ቤት አራዳ ሆነሽ በዘዴ መጥበስሽ ነው?››

‹‹ምን ለማለት ፈልገህ ነው…?››ንግግራቸውን በቅርባቸው የነበሩ ሁለት ሰዎች የሚዋኙ መስለው ግን ጆሮቸውን ወደ እነሱ ቀስረው  እያዳመጡ  ነው..ደንታም አልሰጣት፡፡

‹‹ሰምተሻል ባክሽ….እኔ ለእንደአንቺ አየነት ጩሉሌ ከምሸነፍ አራሴን ባጠፋ ይሻለኛል…..

"እኔ ደግሞ በጥቂት ቀን አንተን መጥበስ ካልቻልኩ እራሴን አጠፋለሁ"

"አፍጥጦ አያትና ምንም ሳይናገር ጥሏት ሄደ
እሷም ከገንዳው ወጥታ ወደመኪናዋ ተንደረደረች...

ከፍታ ገባችና በውሀ የራሰውን የዋና ልብሷን አውልቃ ሌላ ልብሷን በመልበስ ከመኪናው ወጣች..ኮፈኑን ተደግፋ ንስሯ ፊት ለፊት ቆማ  ማሰብ ጀመረች …. በአካባቢው የሚያልፍ ሰዎች ከንስር ጋር ባልተለመደ ሁኔታ ፊት ለፊት ተፋጣ  ሲያዩት  በመገረም እየተገላመጡ ሲያልፍ አስተውላለች፡፡

‹‹የሆነውን አይተሀል አይደል…?በቃ ፈልገዋለሁ››የምታወራው ለንስሯ ነው

(ይቅርብሽ የሚል  ቃል ወደ አዕምሮዋ ላከላት)

‹‹ አታበሳጨኝ..በቃ ፈለኩት ማለት ፈለኩት ነው …አሁን የሆነ ነገር አድርግልኝ …ሆቴሉ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ቢራ እየተጎነጨው እጠብቅሀለሁ…››

ተነስቶ በረረ……..

እሷም እንዳለችው ወደሆቴሉ በረንዳ በመሄድ ወንበር ይዛ ተቀመጠችና ቢራ አዘዘች….እንግዲህ ያሰበችው እስኪሳካ ሌላነገር ማሰብም  አልቻለችም…ቀልቧን ሁሉ ጥቁሩ ልጅ ላይ እንደተጣበቀ ነው…….ጭኗ መካከል ይበላት የነበረው አሁንም እየበላት ነው…. ከመብላቱም አልፎ እያቁነጠነጣት ነው… አሁን እንደዚህ የሚያደርጋት የወሲብ ጥማት ነው…እንጂማ በቅጽበታዊ የፍቅር ፍላፃ ተመታ አይመስልም… ‹‹እንደዛ አይነት ደካማነትማ አይነካካኝም…መጀመሪያውኑስ ፍቅር  ምንድነው …...?የፍቅር መነሻውም መድረሻውም አይስማማኝም፡፡ማለቴ በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል ያለው የፍቅር ስሜት መነሻው የተለያየ ቢሆንም መዳረሻው ለምን ተቀራራቢ ወይም ተመሳሳይ ሆነ….ሁል ጊዜ ለምን ፍቅር በወሲብ ልጥ ይታሰራል፡፡ልጡስ ለምን በጋብቻ ሰንሰለት እንዲቀየር ይጠበቃል?ለምን ፍቅር….ወሲብ..መለያት ወይም ፍቅር….ወሲብ ..ጋብቻ ..ልጅ መውለድ….፡፡ሌላስ አማራጭ ለምን  አይኖርም…ለምሳሌ ፍቅር …ጓደኝነት….በቃ፡፡እንደዛ ቢሆን ምንም ገደብ አያጨናግፈውም…አንድ ወንድ መቶ ሴት ቢያፈቅር ሚኮንነው ሰው የለም…ምክንያቱም ፍቅር  ከዛ ጓደኝነት ነው…ባል ይኑራቸው አይኑራቸው….ወደፊት ያግብ አያግቡ አያስጨንቀውም…፡፡ፍቅር ብቻ…ከልብ ማፍቀር ግን ደግሞ እንዳሻቸው ሲበሩና ሲከንፉ እያዩ መደሰት…ሲያገቡ መጨፈር..ሲወልዱ መሳም….ሲያለቅሱ ጉያ ውስጥ ሸጉጦ ማባበል፡፡ግን ይህ ህልም ብቻ ነው …አጉል ምኞት ፡፡ተፈጥሮም ማህበረሰብም አይፈቅድም፡፡ወንድ አንድን  ሴት አፍቅሮ እጆቾን ሲነካ  በሰውነቱ እሳተ ጎመራ ይንቀለቀላል…ከንፈሯን መገሽለጥ ጭኖቾን መፈልቀቅ ቀዳሚ ምኞቱ ይሆናል…በቃ ማህበረሰብም ተፋቀሩ ሲል ተኙ መከተል እንዳለበት ያምናል..ፍቅር እና አልጋ…ነገሩ ጥሩ ነው ጤነኝነትም ነው…ፍቅርም ወሲብም ለሰው ልጅ የተሰጡ ደስታቸውን የሚያመርቱባቸው ተፈጥሮአዊ የስሜት እርካታ ፍብሪካዎቻቸው ናቸው፡፡ግን ቢሆንስ ሁሉም ፍቅር ወደወሲብ  ሁሉም ወሲብ ደግሞ ወደ ጋብቻ መቀየር አለበት ወይ… ?….አይ  ምን እየቀባጠርኩ ነው …አትፍረዱብኝ ምን አልባት ይሄንን አይነት  ከሰው ልጅ  አስተሳሰብ ውጭ የሆነ ነገር ከአባቴ ዝርያ በደም የወረስኩት ይሆናል፡፡››በማለት ስትብሰለሰል ቆየች

ከ15 ደቂቃ በኋላ ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ንስሯ ተመልሷ መጣና በቅርብ ርቀት ጨለማውን እየሰነጠቃ በአየር ላይ ሲንሳፈፍ ተመለከተችው…ሀሳቧን  ሰበሰበችና  ከእሱ አእምሮው ጋር አገናኘችት… ያየችውን ወይም አሁን እያየች ያለውን ነገር ለማየት ….

ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 33,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
​​📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሰውዬው አሁን ያለበት ቦታ ከዚህ እሷ ካለችበት ብዙም በማይርቅ ሌላ ሆቴል ውስጥ ነው..ግን   እየጠጣ አይደለም..ቤርጎ ውስጥ ሆኖ ነው የሚታያት፡፡ደግሞ ብቻውን አይደለም..አንድ ቅንጥስጥስ ያለች ለጋ ወጣት ክንዱ ላይ ተዘርራ በፀጉር የተሸፈነ ጥቁር ደረቱን እየዳበሰችለት  ነው…..እሱ ከወገቡ በታች ቢጃማ ሱሪ አድርጓል… ልጅቱ ግን በፓንት ብቻ ነች…ደግሞ የሰውነታቸው ቀለም ልዩነት ..እሷ ብጭጭ  ያለች ክልስ  የምትመስል ሴት ነች….ደግሞ ስዕል የመሰለ ውበት ያለት..

‹‹ይህቺን ይዘህ ነው ለካ በእኔ ላይ የጎረርክብኝ?››ስትል አሰበች....እና ይበልጥ የፉክክር መንፈሷ ተነቃቃ…

‹‹የእኔ ፍቅር አሁንም እንደተበሳጨህ ነው?››ልጅቷ ነች የጠየቀችው

‹‹በጣም  እኮ የምታናድድ ሴት ነች..አንተን በዛሬው ቀን  ካላወጣሁ እራሴን አጣፋለሁ ትለኛለች?››

(አሁንም ስለእሷ እያወራ መሆኑን ስታውቅ ውስጧ ሞቀ..የሚበላት አካባቢም ጨመረ)

‹‹ታዲያ ጤነኛ ነች ትላለህ?››

‹‹ጤነኛማ አይደለችም››

‹‹ታዲያ ንቀህ ተዋታ..ለምን  አትረሳትም .... ?መቼስ አሁን እኔ እቅፍ ውስጥ ነህ…መጠጡም እዚሁ ክፍላችን አለ.. እራቱም እዚሁ ነው የሚመጣልን..እኔን የመሰለች ዘበኛ አለህ እንዴት ብላ ከየት ታገኝሀለች..ነው ወይስ  እንደፎከረችው እራሷን ታጠፋለች ብለህ ሰጋህ?››

‹‹ፍግም ትበላ››

‹‹ተው ተው እደዛማ አይባልም…አሁን ለሚሰማህ ሰው አሪፍ ጨካኝ አትመስልም…ሁል ጊዜ እኮ አንደበትህ እና ሆድህ አይገናኝም……….››

‹‹እና እንዴት ነው የሚባለው?››

‹‹አይ ያን ያህል ከወደደችህማ እራሷን ከምታጠፋ አንዴ ብትቸገርላት?››

ገፍትሮ ከደረቱ ላይ አስፈነጠራት  ..
እየሳቀች ‹‹አትበሳጭ.. ቀልዴን እኮ  ነው›› አለችው ወደአስለቀቃት ቦታ እየተመለሰች

‹‹እንዲህ አይት ቀልድ አይመቸኝም ..ካንቺ ውጭ የሌላ ሴት ገላ ከማቀፍ እኔም እራሴን ባጠፋ ይሻለኛል…››

‹‹በቃ የእኔ ጀግና›› ብላ ወደ ደረቱ ተመለሰችና ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት… ገለበጣትና እላዬ ላይ ተከመረባት…መሳሙን ሳያቆም በአንድ  እጁ የለበሰውን ቢጃማ ከሰውናቱ መዥርጦ አወለቀ..
በንስራ  ታግዛ እያየችው ያለው   ገበናቸው የወሲብ   ረሀቧን  ከምትቆጣጠረው በላይ  እንዲሆንባት አደረገው ፡፡

   እሷ ልትተኛው የፈለገችው ወንድ ከዕጮኛው ጋር በወሲብ ዳንኪራ እየጨፈረ ነው…እናም ደግሞ በራሱ ታማኝነት እንዴት ተመፃዳቂ እንደሆነ ከንግግሩ ለሁለተኛ ጊዜ መስማቷ የቅድሞውን ብስጭቷን  በእጥፍ እንዲጨምር አደረገው…
ሂሳቧን ከፈለችና መቀመጫዋን ለቃ ወደመኪናዋ አመራች ..መኪናዋን  አስነሳችና  ሰውዬዋ ወዳረፈበት ሆቴል ነዳችው… ንስሯም በሰማዩ ላይ ጭለማውን ሰማይ እየሰነጠቀ ከላይ እየተከተላት  ነው፡፡
ንስሯ‹‹ፍቅራቸውን እና መተማመናቸውን አየሽ አይደል…?ተይው በቃ….››የሚል መልዕክት አስተላለፈላት

‹‹አልተውም.. የማታግዘኝ ከሆነ በራሴ እወጣዋለሁ….››መለሰችለት ለንስሯ

‹‹በራስሽማ የበለጠ ጥፋት ታጠፊያለሽ››

‹‹እንግዲያው ዝም ብለህ በቀላሉ ያሰብኩትን እንደሳካ አግዘኛ››
ንስሩ የመስማማት ምልክት አሳያት ..

አሁን ሆቴል ደረሰችና መኪናዋን ቦታ አስይዛ አቆመችና ሞተሩን አጠፋች ….በቀጣይ ምታደርገውን  ነገር ግን ገና አላወቀችውም .. መኪናዋ ውስጥ ሆና ትኩረቷን ስብስባ  እና ከንስሯ እይታ ጋር እይታዋን በማጣመር  ልክ ለስለላ በድብቅ እንደተቀበረ ካሜራ    ክፍላቸውን ወደመቃኘቱ ተመሰች
አሁን ፍቅረኛሞቹ  ስራቸውን ጨርሰው ሻወር ቤት ግብተዋል…እየታጠቡ ነው ፡፡በመታጠባቸው ውስጥ መተሸሻት ..በመተሻሸታቸው ውስጥ ከወሲባዊ  እርካታ በኃላ ያለ ድሪያ አይነት ማሽካካት ይታይባቸዋል…..  ታጥበው ከጨረሱ በኃላ  ሁለቱም ፎጣ አገልድመው ሻወሩን ለቀው በመውጣት አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አሉ….እሱ ተንጠራራና ፊት ለፊታቸው ካለው ጠራጴዛ የወይን ጠርሙሱን በማንሳት የጎደለውን የወይን ብረጭቆ በመሙላት  አንስቶ ሰጣት ..ለራሱም አነሳና ተጎነጨ ….እሷ ግን ጠቀም አድርጋ ተጎነጨችና አፏን ወደእሱ አሞጠሞጠች …ከፈተላት.. በጉንጮቾ ያቆረችውን  ወይን በከፈተላት ጉንጩ ውስጥ ገለበጠችለት››ይሄንን ስታይ የሆነ ምቾቷ እየቀነሰ መጣ….ያልተለመደ አይነት ሆነባት፡፡

‹‹አሁን ሰርጋችን ቀን  መቼ እናድርገው?››እሱ ነው አይን አይኗን በስስት እያያት የጠየቀው፡፡

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹በእኔ በኩል  በጣም በቅርብ መሆን አለበት ባይ ነኝ››

‹‹ቅርብ ስትል? ››

‹‹በሚቀጥለው ወር ውስጥ››

‹‹እርግጠኛ ነህ….?እኔ ግን  ያለችንን ጊዜ እንደዚሁ  በፍቅር ብናሳልፋት ይሻል ይመስለኛል፡፡

‹‹አንቺ ደግሞ ስንት ወር ያወራንበትን ነገር ከእንደገና ወደኃላ ትመልሺዋለሽ ..አድሮ ቃሪያማ አትሁኚ››ኮስተር ብሎ መለሰላት

‹‹የእኔ ፍቀር ላንተው እኮ አስቤ ነው…ከዚህ ጋብቻ  መሳቀቅ ብቻ ነው የሚተርፍህ  ››
ያንን ጥቁር ፊቱን ይበልጥ አጨልሞ ‹‹ግድ የለም ለእኔ አታስቢ..አንቺ ባለችሽ ጊዜ ቶሎ ቶሎ መኖር መቻል አለብሽ ፡፡.ድል ባለ ሰርግ ማግባት …ልጅ ወልዶ ማቀፍና ማጥባት ላንቺ የሚገቡሽ ነገሮች ናቸው››አላት 

‹‹ትቀልዳለህ…..ከዚህ በፊትም ነግሬሀለው …ዛሬም እንደግምልሀለው የማላሳድገውን ልጅ በፍጽም አልወልድም››

‹‹እንግዲህ ነግሬሻለሁ…

ካልወለድሽልኝ አንቺ ጥለሺኝ ስትሄጂ የምጽናናበት ነገር ስለሌለ  ያው ከሸኘሁሽ በኃላ እራሴን በማጥፋት እንደምከተልሽ እና  በምትቀበሪበት ጉድጓድ አብሬሽ እንደምቀበር አትጠራጠሪ››

‹‹ለምን ታስጨንቀኛለህ?››

‹‹እያስጨነቅኩሽ አይደለም…በትክክል የማደርገውን እየነገርኩሽ ነው…አንቺ ስለመሞትሽ ማሰብን  እርሺውና በየቀኑ ማድረግ የምንችለውን እናድርግ.. እንጋባ… ውለጂልኝ..ከዛ በኃላ ያለውን ነገር ለእግዜር እንተወው ..ምን ይታወቃል የሆነ ተአምር ተፈጥሮ በሀኪም ከተቆረጠው የመሞቻ ቀንሽ በፊት ፈውስ የሚሆን መድሀኒት ይገኝ ይሆናል››
ኬድሮን በምሰማው ነገር እየደነዘዘች ነው።

    ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 34,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሰላሳ_አራት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ብርጭቆውን አንስታ ተጎነጨችለትና መልሳ በማስቀመጥ መልስ ለመሰጠት  ተዘጋጀች….
ኬድሮን በምታየው ነገር  በጣም ደንዝዛለች …አላማዋንም ዘንግታ ….የሚበላትንም ነገር ችላ ብላ በምስጠት እየተከታተለችው ነው..በሌላ እይታ…. በሌላ መነጽር
ቀጠለች ልጅቷ‹‹የእኔ ፍቅር በጣም እኮ ነው የምትገርመኝ…. ዛሬም ተስፋ አትቆርጥም፡፡ በቃ እኔን እኮ ከዚህ በሽታዬ ለማዳን ለአመታት ለፋህ..ያለህን ንብረት ጨረስክ ..እስራኤል፤ህንድ፤አሜሪካም ጭምር ወስደህ በአለምአቀፍ ደራጃ አሉ በተባሉ የህክምና ተቋምና ምርጥ ጠቢቦች እድታከም አድርገሀል…በቃ አልተሳካም …እንደውም በአንተ ጥረት ነው የአንድ እና የሁለት አመት ቀሪ እድሜ ማግኘት የቻልኩት..ስለዚህ ይህቺን ባንተ ጥረት ያገኘኋትን ቀሪ ዕድሜዬን እንዳልከው በፍቅር እናጣጥምና ከዛ በሰላም ሸኘኝ …ባይሆን እዛ ጎጆ ቀይሼ መኖሪያ ቦታ  አመቻችታ እጠብቅሀላሁ..››አለችና ጉንጩን በመሳም ስሩ ውሽቅ አለችበት..እሱም አጥብቆ አቀፋትና በአንድ እጁን  ከአይኖቹ ሚንጠባጠበውን  እንባ ማበስ ጀመረ ..

ከዚህ በላይ መቆየትም ሆነ  በአላማዋ መግፋት አልቻለችም ….መኪናዋን አስነሳችና ወደቤቷ ነዳችው..ተቀጣጥሎ የነበረው የወሲብ ስሜቷ አሁን ከስሟል.‹‹.በዚህ አይነት ፍቅር ውስጥ እንዴት መግባት እችላለሁ?››..ይህቺንስ ሞት ፊት ለፊቷ የቆመባትን ሴት እንዴት መፎካከር ይቻላል… ?ከእሷ መንጠቅ ወይም መስረቅ በየትኛው ሞራል….?
እንደውም ከዚህ በላይ ታሪካቸውን ማወቅ ፈለገች..ልታግዛቸው ፡፡ከቻለች ለመሞከር….ግን ዛሬ አይደለም… ሌላ ቀን …በዚህን ሰዓት በዚህ የጨፈገገ ስሜቷ ውስጥ ሆና ምንም ማድረግ አልቻለችም..አሁን እቤቷ ገብታ ጥቅልል ብላ መተኛት ብቻ ነው የምትፈልገው…መኪናዋን እያከነፈች ነው… ንስሯ ክንፉን እያርገፈገፈ ጨለማውን በመሰንጠቅ ከፊቷ ይከንፋል..ሁኔታው የደስታ ነው….መጀመሪያም አካሄዷ ደስ አላሰኘውም ነበር….ሀሳቧን ቀይራ በቁዘማም ቢሆን ወደቤቷ መመለሷ እሱን እያስፈነጠዘው ነው…፡፡
""""

ምቾት የሌላው ምሽት ነበር ያሳለፈችው….ደግሞ ርዝመቱ እንደተለመደው 11 ሰዓት ከእንቅልፏ ተነሳችና እቤቷ ውሰጥ የተወሰነ የሰውነት እንቅስቃሴ ከሰራች  በኃላ ወደበረንዳዋ ወጣች…ንሰሯ አብሯት ነበር የወጣው…..ለተወሰነ ደቂቃ ሀሳቧን ከራሷ ጋር ነበር ያደረገችው.. ኤርፎኗን ጆሮዋ ላይ ሰክታ ከሞባይሏ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፍተችና  እያዳመጠች ንጽህ የጥዋት  አየር ወደ ሳንባዋ  እየማገች ነው፡፡

ግን በመረጋጋት ውስጥ ሆና በጽሞና ሙዚቃውን ብቻ ማዳመጡን  ቡዙም ልትዘልቀበት አልቻለችም..ሀሳቧ አሁንም ትናንት ላይ እንደተጣበቀ  ነው…የብልቷ መብላት ቢተዋትም አዕምሮዋ ግን አሁንም ድረስ እያሳከከት ነው….እሷ እኮ ወንድ ልጅን ለዚህን ያህል ጊዜ ርዝመት በልቧ አዝላ አታውቅም… ፎክራ ስላላሳካችው ዝታ  ስላልፈፀመች የመሸነፍ ቁጭት የፈጠረባት መብሰልሰል  ይሆናል……….?
አዎ ከንስር ጋር እየኖሩ ሽንፈትን አሜን ብሎ በመቀበል አንገትን መድፋት የማይታሰብ ነው…በምክንያቱም ለንስር መታገል.. ታግሎም ማሸነፍ ተፈጥሮ ያደለው የብቻ  ፀጋቸው ነው…ንስር የሞተ እንስሳ ንክች አያደርግም…የሚገድለውን ለማጥመድ ወይም ኢላማውን ለማግኘት መቶ ኪሎ ሜትር ሊያስስ ይችላል ..አስሶ አንዴ ራዳር ውስጥ ካስገባ ግን ንቅንቅ አይልም..ምንም ተአምር አያዘናጋውም…ግዳዩን ሳይጥል ውልፍች የለም…አዎ አድኖ አሳዶና ታግሎ በመጣል የገደለውን ብቻ ነው የሚበላው….፡፡እይታው ጠሊቅና እሩቅ ነው፡ካአለበት ቆሞ በአምስት ኪሎ ሜተር እርቀት ያለ ነገር ላይ ማነጣጠር ይችላል፡፡ልፋቱ የሌለበትን… አሸናፊነቱ የማይዘመርበትን ንክች አያደርግም… …ይህ የሰው ልጅም የህይወት መስመሩን ለማግኘት የተፈጠረበትን አለማ ለመገንዘብ የእድሜውን እሩብ ሊያባክን ይችላል…. ማባከኑም አግባብ ነው..መስመሩን ከያዘ በኃላ ግን አይኑም ቀልቡም መቶ ፐርሰንት መስመሩ ላይ መሆን አለበት፡፡ ትኩረቱም ጥረቱም ወደዛ ወደህይወት ግብ መዳረሻው የሚያደርሰው ሊሆን ይገባል…. የንስር ህይወት ይሄንን ነው የሚያስተምረው…
እሷም የሰለጠንችው  በንስራ ስለሆነ ኢላማ ያደረገችበትን  ነገር ከግብ ካላደረሰች ያማታል….አሁን እየተሰማት ያለው ስሜት ግን የተለየ ይመስላታል … ምክንያቱም  ከባሪያው ልጅ  ባልተናነሰ ቀዮ እጮኛውንም ከምናቧ ልታስወግዳት አልተቻለትም፡፡
‹‹አዎ መሞት የለባትም….በዚህ ዕድሜዋ መሞት አይገባትም››…ብላ በውስጧ ደመደመች…መልሳ ደግሞ እራሷን ሞገተች፡፡

‹‹ …በዚህ ዕድሜዋ መሞት የለባትም ስል ምን ማለቴ ነው..
…….?ሰው በስንት አመቱ ነው መሞት ያለበት……….?››ስትል አሰበች፡፡

ወጣት ሆኖ የሞተ ሰው ለምን በዛ ዕድሜዬ ሞትኩ ብሎ ይቆጫል ወይም ፈጣሪውን ይወቅሳል….? አይመስለኝም፡፡.ምን አልባት ይሄኛው አለም እና ከሞት ወዲያ ያለው ያኛው አለም ተብሎ ሚከፈል ዓለም ያለ ቢሆን እንኳን   ያኛው አለም  በእግዜር ሙሉ ቁጥጥር እና ፍቃድ የሚተዳደር ነው ሚሆነው..እንደዛ ከሆነ ደግሞ  ከዚህኛው  ዓለም ፍጽም የተሻለ ነው የሚሆነው..ያ ማለት ደግሞ ሞቶ ወደዛኛው አለም የተሸጋገረ ሰው በህፃንነቱም ሆነ በወጣትነቱ ቢሄድ ተገላገልኩ በምድር ከመሰቃየት፤ከመራብ፤ከመጠማት፤ከመጋዝና ከመታሰር እንኳንም በጊዜ ወደዚህ መጣሁ የሚል ይመስለኛል፡፡ሞት ማለት ሙሉ በሙሉ በስጋ መበስበስ እና በነፍስ መክሰም ወይም  ወደ ምንምነትም መቀየር ከሆነ  ደግሞ ለመፀፀት እና  ለምን ቶሎ ሞትኩ …….?ብሎ ለማሰብም የሚያስችል ዕድልም አይኖርም  ….ሞች በቋሚው አዕምሮ  ሲመዘን ነው በልጅነቱ ተቀጨ..በወጣትነቱ ተቀጠፈ የሚባለው….እና አሁንም እሷ የልጅቷ እሞታለሁ ማለት ለምን ይሄን ያህል እንዳሳሰባት አልገባትም .. …….?ነው ወይስ ለተመኘችው ልጅ ስትል ይሆናል..…….?
‹‹እሱ እንዲያዝንብኝ  ስላልፈለኩ ይሆን….?››ስትል እራሷን ትጠይቃለች ..ለጠየቀችው መልስ ከመፈለግ ይልቅ ግን  ሌላ ጥያቄ እየጨመረችበት ነው….
እሷ እንደሆነ በመግደልም ሆነ በማዳን አታምንም…እንደእሷ እምነት  ሰው የኖረበትን ጊዜ አጭርም ሆነ ረጅም ዋናው የኖረውን ያህል ተደስቶ መኖሩ ነው…..እርግጥ መግደል   የእግዜያብሄር  የአታድርግ ክልከላ ውስጥ ከሚካተቱ ትዕዛዞች መካከል አንዱ እንደሆነ ታውቃለች፡፡ቢሆንም ህይወት ከመግደልና ከመገደል ውጭ ህልውናዋ ፀንቶ እንደማይቆምም በተግባር አይታለች….ብዙ መግደል የቻለ ብዙ ይኖራል….ለመግደል የሰነፈ በጠንካራው ተገድሎ በሞቱ ለሌላው መኖር ምክንያት  ሆኖ ያልፋል፡፡ይሄንን ከህይወት ተምራለች፡፡

ግን እግዚያብሄር  አትግደል ሲል ለሰው ብቻ ነው እንዴ  የሚሰራው..…….?ሰውን መግደል ብቻ ነው በኃጥያት የሚያስጠይቀው….? ለምን ….?ሰው በእግዜያብሄር ሀምሳል  ስለተፈጠረ ልዩ መብት ስላለው….?፡፡ነው ወይስ ሰው የእግዜያብሄር ቤተ መቅደስ ነው የእግዜያብሄርን ቤተ መቅደስ ማፍረስ ደግሞ ያው ቀጥታ እሱን መዳፈር ነው…..ከእሱ ጋር መላተም ነው……ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ  ተብሎ ስለሚታሰብ…..?  …አትግደል የተባለው ነፍስ ያለውን ሁሉ ከሆነስ ……….?ያማ የማይቻል ከባድ ትዕዛዝ ይሆናል…፡፡ምክንያቱም እንስሳት ነፍስ አላቸው… ተክሎች ነፍስ አላቸው…ለመኖር ደግሞ ህይወት ያለው ነገር ሁሉ መመገብ  አለበት..ለመመገብ ደግሞ አንዱ ዝርያ ሌላውን እየበላ ነው ነፍሱን የሚያቆየው…ለመብላት ደግሞ የግድ መግደል
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሰላሳ_አምስት

#ተከታታይ ልቦለድ

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹የትናንቶቹን ልጆች ሙሉ ታሪክ ማወቅ እፈለጋለሁ››ለንስሯ ነው እየነገረችው 

‹‹ይቻላል››መለሰለት ዛፉ ላይ ሆኖ
‹‹በቃ አሁን ዝናቡ ሊዘንብ ነው …ዝናቡ ሲያባራ ታጣራልኛለህ››
በእሷ በማሾፍ በሚመስል ሁኔታ  ክንፉን አርገፈገፈ…እሷ እንዲህ ያለችው ግቢዋ ውሰጥ ያሉ አዕዋፋት ዝናቡን ሽሽት በየዛፎቹ ቅርንጫፎች ሲሸሸጉ እና ወደጎጆቸው ሲገቡ ..ዝንጀሮዋችና ጉሬዛዎቾ ወደመጣለያቸው ሲሸጎጡ አይታ… እሷም ውሽንፍሩን  በመፍራት ወደቤት ልትገባ መነሳቷን ከግምት በማስገባት ንስሯም እየዘነበ ካለው ዝናብ ለመጠለል አብሮኝ ተከትሎ ወደቤት  ይገባል በሚል ግምት ነው…..በሀሳብ ውስጥ ሆና በዝንጉነት ያሰበችው ሀሳብ 
ለካ ንስር ነው…
ንሰሯ አይኖ እያየ ወደላይ ተምዘገዘገ .እያነሰ እያነሰ ደመናውን ሰንጥቆ ከአይኗ ተሰወረ ….አዎ ከደመናው በላይ ብቻ ሳይሆን ከሚዘንበውም ዝናብም በላይ ነው የሆነው..እሷ ዝናብን ስትጠለል ንስሯ ንፍስ የቀላቀለውን ውሽንፍር እየሰነጠቀ በኩራትና በአሸናፊነት ከተዘረጋው ደመና እና ከሚረግፈው ዝናብ በላይ  በመምጠቅ  ቁልቁል እያየ ሊዝናናበት..
በንስሯ ሁኔታ ፈገግ አለችና ወደ ውስጥ ገባች…..ቁርስ ልታበስል አስባ ነበር …ግን ምንም አይነት የምግብ ፈልጎት ስለሌላት ወደመኝታ ክፍሏ ገባችና መልሳ አልጋዋ ላይ ወጣች..አዎ በዝናብ መኝታ ውስጥ ሆኖ ማሰብ ወይም ሙዚቃ ማዳመጥ የሚያስደስታት ነገር ነው…

‹‹እስቲ ንስሬ ስለትናንቱ ባሪያ ልጅ እና በቅርቡ  ሟች ስለምትሆነው  ፍቅረኛው ምን አይነት ታሪክ ይዞልኝ ይመጣ ይሆን ……….?የልጅቷስ የማይድነው  በሽታዋስ ምን  ይሆን….?እንድትሞት ልተዋት ..ወይስ ከንስሬ ጋር ሆኜ ላድናት……….?ቆይ እሱ እንደታሪካቸው ሁኔታ ነው የሚወሰነው….አሁን ንስሬ ከቅኝት ሲመለስ ልክ እንደተካታታይ የሆሊውድ ፊልም ታሪካቸውን ይዘረግፍልኛል….››
ምክንያቱን ባታውቅም ንስሯ ካሰበችው በላይ ቆየባት፡፡
ቆይ ቆይ እስኪ ድምጽ ይሰማኛል………….
ገርበብ ያለው መኝታ ቤት ተበረግዶ ተከፈተ…ሌላ ሰው አይደለም ንስሯ ነው….በራፉን  በመንቁሩ ስቦ በመበርገድ በሮ አልጋዋ ላይ ከጎኗ ጉብ ያለው… ክንፎቹን ወደ ውስጥ ሰብስቦ አንገቱን  ቀብሮ ሽብልል ብሎ ተኛ…ጥሩ ነገር ይዞላት እንዳልመጣ ገባት…ሁልጊዜ የሆነ ነገር እንዲያጣራላት ልካው ያገኘው መረጃ አና ከምፈልገው በተቃራኒ ከሆነ እንዲህ ነው ዝልፍልፍ የሚለው…ዝልፍልፍ ማለት ደግሞ በእሱ አያምርም፡፡ 
የንስሯን ሁኔታ ሰለልጁ ታሪክ  ለማወቅ ያለቻትን ጉጉት በእጥፍ ጨመረበት..እራሷን አስተካክላ ሀሳቧን ሰብስባ ወደንስሯ አዕምሮ ዘልቃ ገባች..ያየውን ለማየት…ያወቀውን ለማወቅ
//
የትናንትናው ቀልቧን ሰልቧት የነበረው ባሪያው  ልጅ መላኩ ይባላል ..እሷ ማለት ከሞት ጋር ቀጠሮ ይዛ በስጋት ኑሮ ላይ ያለችው ፍቅረኛው ስም   ደግሞ ሰሚራ ትባላለች…ሁለቱ የተገናኙት ከአራት አመት በፊት ነው….
ንስሯም ስለሁለቱ ፍቅረኛሞች ይዞላት የመጣው ታሪክ መነሻው ከተገናኙበት የዛሬ አራት አመት ወዲህ ያለውን ነው……
አዎ ሰሚራ ነርስ ነች …በአንድ የግል ሆስፒታል ውስጥ በነርስነት በምትሰራበት እና ተረኛ ሆና የስራ  ገበታው ላይ በነበረችበት በአንድ ቀን ከ4 ዓመት በፊት ማለት ነው፡፡አንድ ወጣት በሞት እና በህይወት መካከል ተንጠልጥሎ  አረፋ ደፍቆ  እያቃተተ በአንብላንስ ተጭኖ  ይመጣል..
አጋጣሚ ሆኖ በዕለቱ  ሰሚራ ተረኛ እንደመሆኗ  መጠን   ከሌሎች  ዶክተሮች ጋር ሆና የመጣውን በሽታኛ ህይወት ለማትረፍ  ባለአቅማቸው እና  ቴክኖሎጂውን በመጠቀም  ይሯሯጣሉ…. ወጣቱ ኃይለኛ ገዳይ መርዝ በመላ ሰውነቱን ተሰራጭቶ  አንጀቱን እየበጣጠሰው ነበር ....ከዛ በእነሱ ጥረት  የእግዜርም  በጎ  ፍቃድ  ተጨምሮበት   ከመሞት ይተራፋል… ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ስለነበር  ከገባበት ኮማ ለመንቃት አልቻለም ነበር….ስለሆነም  የጤናው ሁኔታ በአስተማማኝ ሁኔታ እስኪስተካከል  እዛው ሆስፒታል ተኝቶ ክትትል እንዲያደርግ ይወሰናል…
ያ ወጣት ሆስፒታል  ከገባበት ቀን አንስቶ አብረውት የነበሩ አንድ ሴት እና አንድ ወንድ ጎልማሶች ነበሩ….ሰሚራ በወቅቱ ከእነሱ ከራሳቸው  ጠይቃ እንደተረዳችው ሴቷ የበሽተኛው  ፍቅረኛ ወንዱ ደግሞ በአባት የሚገናኘው ግማሽ ወንድሙ  …..….በተጨማሪም ፖሊሶችም ገባ ወጣ ይሉ ነበር…የበሽተኛውን መንቃት ተከትሎ  የሚሰጠውን ቃል ለመቀበል…
እሷም ምንም እንኳን የስራዋ አንዱ ግዳጅ እና ኃላፊቷ  ቢሆንም  ግን በማታውቀው ሌላ ተጨማሪ የተለየ ስሜት እየተገፋፋች በከፍተኛ ሁኔታ ስትንከባከበው ትቆያለች…አብረውት የሚያሰትምሙት ቤተሰቦቹ  እስኪገረሙባት ድረስ፡፡በሽተኛው እስከ ሶስተኛው ቀን ድረስ ከገባበት ኮማ መንቃት አልቻለም ነበር ፤በአራተኛው ቀን ግን ለ5 ደቂቃ ያህል አይኖቹን መግለጥ እና አንደበቱን ማላቀቅ ቻለ..የመዳን ተስፋው በእጥፍ ጨመረ፤ይሄ ሁኔታ  ሰሚራን እና ጓደኞቾን በጣም ቢያስደስታቸውም የመላኩን አሰታማሚ  ቤተሰቦች ግን  በሚገርም ሁኔታ አለመረጋጋት እና ድንጋጤ ውስጥ ከተታቸው፤ይህንንም ጉዳይ ሰሚራ መታዘብ ስለቻለች ግራ ተጋብታ ትዝብቷን በውስጧ ቀብራ ስትብሰለሰል  ትሰነብታለች፤በአምስተኛው  ቀን ግን  ሰሚራ የእለት ስራዋን አጠናቃ ወደቤቷ ስትመለስ  የመላኩ  አስታማሚዎች እቤቷ  በራፍ ላይ ቆመው ሲጠብቋት አገኘች
ሰሚራም  ደንግጣ‹‹ምን  ተፈጠረ..….?ምን እግር ጣላችሁ….?››
ሰላም ምትባለው…የመላኩ  እጮኛ‹‹ተረጋጊ አንድ ነገር ልናማክርሽ ነው….?››አለቻት፡፡
‹‹ምንድነው ምታማክሩኝ …….?ደግሞስ ሆስፒታል ተገናኝተን አልነበር..እዛው እኮ ልትጠይቁኝ  ትችሉ ነበር…?››
የበሽተኛው ግማሽ ወንድም የሆነው ሰሎሞን‹‹አይ እዛማ በስራ ወከባ ላይ ስለሆንሽ የግል ጉዳይ ለማውራት  አይመችም ብለን ነው››
ግራ ትጋባና ‹‹የግል ጉዳይ …….?ማለት ስለ መላኩ ጤንነት ማለታችሁ ነው….?›› ብላ ጠየቀች…ሌላ ከእሷ ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ አልታይሽ ብሏት፡፡
ሰላም እያቅማማች ‹‹አዎ ግን ካላስቸገርንሽ  ወይ እቤትሽ ገብተን ወይ ደግሞ ሌላ ቦታ ሄደን ብናናግርሽ››
ሰሚራ ምታደርገውም ምትናገረውም ግራ ገብቷት  ወደ ቤቷ  ይዛቸው ትገባለች…ወደቤት ከገቡ በኃላ ለውይይት ያቀረቡላት ርዕስ  ከጠበቀችው በጣም የራቀና  አስደንጋጭ ነበር…››
የግማሽ ሚሊዬን ብር ቼክ በእጇ ላይ ካስቀመጡላት በኃላ ….‹‹መላኩን  እንዳይድን አድርጊልን››ነበር ያሏት፡፡
‹‹እንዴ ለምን…….?ለአንቺ ፍቅረኛሽ ለአንተ ደግሞ ወንድምህ አይደል…….?ነው ወይስ ዋሽታችሁኛል….?፡፡››
‹‹አይ እሱን አልዋሸንሽም…ግን አንቺ ማይገባሽ ብዙ ጉዳዬች አሉ..አሁን ብታድኝው እራሱ ሙሉ ጤነኛ አይሆንም ..አካሉ እንደልብ ላይታዘዝለት ይችላል..ወይም አዕምሮው የማሰብ አቅሙ ተዛብቶ  ዘገምተኛ ሆኖ ሊቀር ይችላል….እንደዛ የመሆን እድል እንደሚገጥመው  ደግሞ  የነገራችሁን እናንተው ናችሁ፡፡››
📕ተአምረተ_ኬድሮነ

#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹እኮ የምታደርጉትን ነገር አቁሙ ነው እያልንሽ ያለነው  ..በግልጽ እንንገርሽ  መሰለኝ….እርሱ መዳን አይችልም ማለት መዳን የለበትም …..እሱ ከዳነ  እኛ እንጠፋለን ማለት-ነው….ስለዚህ  እረዳሽንም አረዳሽንም እሱን ለመግደል የምናደርገው ጥረት አናቆምም….እኛ በራሳችን ማድረግ  ዳግመኛ  መሞከር ያልፈለግነው  የፖሊሶች አይን እየተከታተለን ስለሆነ ነው፡፡››

‹‹ቆይ እስኪ አሁን የተመረዘበትን መድሀኒት የሰጣችሁት እናንተ ናችሁ….?››

‹‹እሱን ማወቅ ምን ይጠቅምሻል….?›.›

‹‹አይ እሱማ ምን ይጠቅመኛል..እንዲሁ ተገርሜ እንጂ››

‹‹ምንም የሚገርም ነገር የለም..አሁን ባቀረብንልሽ ሀሳብ
ትስማሚያለሽ ወይስ አትስማሚ..

….?››ይጠይቃታል ሰሎሞን ተብዬው….

ወዲያው  አዕምሮዋን አሰርታና የነገሮችን አካሄድ በፍጥነት በመተንበይ ‹‹አረ  እኔ ምን አገባኝ… እናንተ ለራሳችሁ ሰው ያላሰበችሁ እኔ ምን አስጨነቀኝ..እስማማለሁ…››ብላ ትመልሳለች ሰሚራ፡፡

እነሱም ካሰቡት በጣም በፍጥነት  ስለተስማማችላቸው ተደሰቱ..

‹‹አሪፋ…በጣም ጥሩ ውሳኔ ነው››ሰላም፡፡ 

ሰሎሞን  ‹‹እንግዲህ ስንት ቀን እንጠብቅሽ….?››

ሰሚራ ‹‹አንድ ሶስት ቀን እፈልጋለሁ››

‹‹ሶስት ቀን አይበዛም››

ኮስተር ብላ ‹‹ሰው ለመግደል እኮ ነው እየተስማማን ያለነው ..ሰው ለመግደል ሶስት ቀን እንዴት ሆኖ ነው የሚበዛው….?››

ሰሎሞንም በአሪፍ መስመር  እየሄደ ያለው ጠቃሚ ስምምነት ላለመበረዝ  ለስለስ ብሎ‹‹ያው ሞት አፍፍ ላይ ያለ ሰው ለመግዳል ብዙም አይከብድም  ብዬ ነዋ…በተለይ ላንቺ››

‹‹ላንቺ ስትል …….?ስታየኝ ገዳይ እመስላለሁ….?›› መለሰች ሰሚራ ኮስተር ብላ ፡፡

‹‹አይ አረ በፍጽም እንደዛ ማለቴ ሳይሆን የህክምና ዕወቀቱ ስላለሽ..የትኛው መድሀኒት ሰውዬውን በቀላሉ ሊገድለው ይችላል የሚለውን በደንብ ስለምታውቂ ብዬ ነው፡፡››

‹‹እንዳልከው መግደሉ ቀላል ነው..ግን ግድያውን ማንም  ሊደርስበት የማይችል እና  ፖሊስም በምርማራም ሊያረጋግጠው የማይችል መሆን አለበት››

‹‹አየሽ እኔ ቀልቤን በጣም ነው የማምነው…ገና እንዳየውሽ ለዚህ ስራ እንደምትረጂን እርግጠኛ ሆኜ ነበር..እሷ ግን አይሆንም ብላ በጣም ስትከራከረኝ  ነበር የሰነበተችው….እንድረታት አደረግሸኝ …ጀግና ሴት ነሽ..ስራውን በጥንቃቄ እና በፍጥነት ስሪልን እንጂ 100 ሺ ብር ቦነስ አለሽ››ሰሎሞን በፈገግታ ተሞልቶ   አሞገሳት፡፡

‹‹ችግር የለም..ባይሆን እድር ከሌላችሁ እድር ግቡ….››
‹‹ለእሱ አታስቢ›› ብለው  በደስታ ተሰናብተዋት በፈገግታ እደታጀቡ ይሄዳሉ፡፡

ሰሚራ እነሱ እደወጡ ነበር ምን ማድረግ እዳለባት ማሰብ የጀመረችው‹‹…ሰው እዚህ ድረስ መጨካከን የጀመረው መቼ ነው…….?›› ለዛውም በቤተሰብ ደረጃ…እራሷን በድንጋጤ የጠየቀችው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር… ‹‹…ምን ቢያደርጋቸው ነው የራሳቸውን ሰው እንዲህ ለማስገደል የሚጥሩት..….?››ሰው ሰውን  ከሞት ለማትረፍ‹‹…..የሰውን ህይወት ለማስተካከል ይለፋል ገንዘብን ይከሰክሳል እንጂ እንደነዚህ  የራስ ሰውን ለመግደል ምን አነሳሳቸው...….?

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 37,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
​​📕ተአምረተ_ኬድሮነ

#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ቀጥታ  ለፖሊስ ሄዳ ነገሩን  ማመልከት ፈለገች…ግን በዚህ ሀሳብ  ብዙም አልገፋችበትም.. ሰዎቹን  እንዳየቻቸው ገንዘብን እንደወረቀት የሚበትኑ ናቸው..ስለዚህ ለፖሊስ እንዳመለከተች በሆነ መንገድ ቢደርሱበት በሽተኛውን  በሌላ መንገድ አስወግደው ለእሷም እንደማይመለሱላት እርግጠኛ ነች፡፡አንድ ዜጋ እንዲህ አይነት ፈታኝ  የደህንነት ስጋት አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ወቅት  በሀገሩ ህግ  መተማመን ካቃተውና ፍትህ በጥቂት ገንዘብ እና በትውውቅ በቀላሉ እንደሚጠመዘዝ እያሰበ እና  እያመነ ሲሄድ  አደጋ አለው… ምክንያቱም እንዲህ አይነተ ተመሳሳይ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ  የሚሸሽበት መደበቂያ ይጠፋዋል፡፡

ሰሚራም የዚህ ጥርጣሬ ተጠቂ ስለሆነች ፖሊስን አምና የዚህን አይነት ከባድ ጉዳይ ይዛ ወደፖሊስ መሄድ አልደፈረችም….ከዛ ይልቅ  በራሷ ነገሩን በሚስጥር ለመወጣት ወሰነች..እራሷንም ከአደጋ ከልላ ይሙት በቃ የተወሰነበትን ሰው ለማዳን…፡፡

እንደዛ በመወሰኗ በወቅቱ እራሷንም አስገርሟት ነበር…የገዛ ዘመዶቹ እና  የራሴ የሚላቸው ሰዎች መኖሩን ሳይፈልጉ እሷ ለምን ተጨነቀችለት..ሰው ስለሆነ ብቻ ወይስ ሰባዊነቷ አሸንፎት…..….?
መቼስ ነርስ እንደመሆኗ መጠን በየቀኑ የሞት መንደር ውላ የሞት መንድር  ውስጥ የምታድር ሰው ነች…ሞት ያንን  ያህል የሰው ልጅ የመጨረሻው ክስረት እንዳልሆነ ትገነዘባለች ታምናለችም....፡፡ከሞት ወዲህ ማዶ የሰው ልጅ በመኖሩ ውስጥ የሚያስተናግዳቸው ብዙ ክስረቶች አሉ… ሰውን ከመኖር በታች ከመሞትም በታች የሚያደርጉ የስብዕና ዝቅጠቶች ……
ምን አልባት ይሙት በቃ የተፈረደበት ወጣት ከሞት ተርፎ በገዛ ሰዎቹ የደረሰበትን ክህደት አውቆ   ስብርብር ከማለት ስለእነሱ ምንም ሳያውቅ እንዳፈቀራቸው እና እንዳመናቸው ቢሞት ይሻለው ይሆናል…
መሰል ነገሮችን  በአዕምሮዋ ውስጥ በማጉላላት ለሳዕታት ብትብሰለስልም ይሙት በቃ የተወሰነበትን እና በኮማ ውስጥ የሚገኘውን መላኩን በቃ የራሱ ጉዳይ ብላ ችላ ልትለው አልቻለችም…ስሜቷ ጠቅላላ ይሄንን ልጅ አድኝው የሚል ነበር…
እርግጥ በሰዎች ሀሰብ  ተስማምታ  የታማሚውን  ህይወት እንዲያልፍ ማድረግ ለእሷ ከሱቅ መስቲካ ገዝቶ እንደማኘክ ቀላል ነገር ነው….ያንን ቀላል ነገር በማድረጓም የተሰጣትና  ቼክ እና የሚጨምርላት ቦነስም ህይወቷን ተአምራዊ በሆነ ቅጽበት እንደሚቀይርላት ታውቃለች….የምትወዳቸውን ሽቶዎች ለማርከፍከፍ፤ከደሞዞ የመግዛት አቅም እጅግ የራቁ ብራንድ ቀሚስ እና ጫማዎችን እየቀያየሩ ለመድመቅ…. ቢኖረኝ ብላ እንደህልም የምትመኘውን  መኪና ገዝታ  ለማሽከርከረር…ጠቅላላ የኑሮ ዘይቤዋን  ፍጥነት ይቀይርላት ነበር…
ግን ‹‹ይሄ ሁሉ ቁሳቁስ እና  ድምቀት  በቀሪው ህይወቴ ውስጥ ደስተኛ ሆኜ  እንድኖር ያደርገኛል ወይ ... ….?››ብላ ስትጠይቅ ዝግንን ነበር ያላት ..በየቀኑ ከጣረ ሞት ጋር ግብ ግብ ስትገጥም ታያት…እንኳን በዚህ አይነት ሁኔታ  አቅዳና   ተከፍሏት ግድያ  ፈፅማ ይቅርና  እሷ ቀጥታ የምትከታተለው በሽኛተኛ ህይወት እንደአጋጣሚ ሆኖ እጆ ላይ ሲያልፍ ..‹‹ማድረግ ሲገባኝ ያላደረኩለት ነገር ይኖር  ይሆን እንዴ….….?›› 
‹‹እንደዚህ አይነት መድሀኒት ቢሰጠው ይድን ይሆን… ….?››እያለች መሰል ጥያቄዎችን  እራሷን በመጠቅ መብሰልሰል እና መፀፀት የሁል ጊዜ  ስቃዮ  ነው…እና ይሙት በቃ የተወሰነበትን ወጣት  በሽተኛ  ልታተርፈወ ወሰነች….እራሷን አደጋ ላይ ሳትጥል እሱን ከገዳዮቹ ማዳን…ግን እንዴት አድርጋ….….?

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 39,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
​​📕ተአምረተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በማግስቱ….
ከምሽቱ 1 በሰዓት አካባቢ ነው ሰሚራም ሆነች ዶ/ር እስክንድር የእለቱ የማታ ተረኛ ሆነው ስራቸው ላይ ተስማርተዋል፡፡
ሰሚራ ለመላኩ ዘመዶች ደወለችላቸው…ሰሎሞን ነበር  ስልኩን ያነሳው

‹‹ሄሎ››

‹‹ሄሎ..ሰላም ነሽ?››

‹‹አዎ ሰላም  ነኝ …እንድትመጡ ፈልጌ ነው››

‹‹ማን…..? ››

‹‹እናንተ ናችሁ…. ሁለታችሁም››

‹‹ለምን…..? ምን ተፈጠረ…..?››

‹‹ላደርገው ነው…ማድረግ የምፈልገው ደግሞ እያያችሁ ነው..እናንተ ባላችሁበት››

‹‹አረ ችግር የለውም ..ሁሉን ነገር ካጠናቀቅሽ በኃላ ብትደውይልን ይሻላል››

‹‹እንደዛ አላደርግም…በቃ አሁን በነፍስ ነው ብዬ እንደደወልኩላችሁ አስቡትና  እቤትም ሆነ መንገድ ላይ ለገኛችሁት ሰው እንዲሁም ለሌሎች ዘመዶቻችሁ እየደወላችሁ በነፍስ ነው ተብሎ ተደውሎልናል እያላችሁ ንገሩ ፣እናንተም በ20 ደቂቃ ውስጥ ድረሱ›

‹‹አዎ… በቃ ገባኝ እንመጣለን..ትክክል ነሽ››ስልኩ ተዘጋ 

ሁለቱ ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች ከስድስት በማያንሱ ሰዎች ታጅበው ለመምጣት ከ15 ደቂቃ በላይ አልፈጀባቸውም…..ሰላም ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሆስፒታሉን አተረማመሰችው….ሰሎሞንም እንባውን እየዘራ ወንድሜን እያለ በማጎራት ግቢውን መዞር ጀመረ…
ለስድስት ቀን በኮማ ውስጥ የሰነበተው መላኩ ምን እንደነካው ከዶክተሩና ከሰሚራ ውጭ ማንም በማያውቀው ምክንያት በጣር ነፍስ ጊቢ ነፍስ ውጭ እያቃተተ ነው…ዶ/ር እስክንድር ሲስተር ሰሚራ እና ሌሎች ሁለት ነርሶች ዙሪያውን ከበው  ሊረዱት እየሞከረ ነው..

‹‹ሲስተር ሰሚራ ቶሎ ብለሽ ይሄንን መድሀኒት ውጊው ››ብሎ በወረቀት ላይ የመድሀኒቱን ስም ጽፎ ሰጣት… እሷም ተቀብላ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደችና በሶስት ደቂቃ ውስጥ ይዛ መጣች… መዳሀኒቱን በተንጠለጠው ግሉኮስ ከረጢት ውስጥ በስሪንጅ መጣ ለቀቀችበት ..ቀስ እያለ በቱቦ ውስጥ በመንጠባጠብ ከደም ስሩ ተቀላቀለ…. ከደቂቃዎች በኃላ የበሽተኛው ጣር  እየቀነሰ …መንፈራገጡም እያቆመ መጣ….ከዛ ፀጥ አለ …ሰው ሲሸነፍ ወይም ሲያፈገፍግ ፀጥ ይል የለ….ዶ/ር እስክንድር በማዳመጫ ትንፋሹ አዳመጠው…እጆቹና እያወናጨፈ አንገቱና ቀብሮ በብስጭት ክፍሉን ለቆ ወጣ …ኮሪደር ላይ እነ ሰሎሞን እና አጃቢዎቻቸው ከበቡት.

‹‹ዶክተር..እንዴት ነው በሽተኛው…..?››

‹‹ዶክተር ይሻለዋል ..ፍቅሬ ይድናል…..?››

ለበራካታ ሰከንዶች ተገትሮ ሰላምን አፍጦ ከማየት ውጭ ምንም መናገር አልቻለም፣‹‹….….ይቺን ላየ ሰው እነ ሰላም እና መሀደር ምኑን አክተር ተባሉት ?››ሲል በውስጡ አሰበ…መለስ ብሎም ስለራሱ አሰበ …ወየው ጉድ እኔም ለካ ሌላ ተዋናይ ሆኜያለሁ…አለም ሰፊ መድረክ እኛም ኑሪዎቾ  ተዋናዬች ነን ያለው ማን ነበር …..? ለካ እውነት ነው…›አለና ወደቀልብ በመመለስ ለእነሱ ጥያቄ  መልስ መስጠት ጀመረ 

‹‹አዝናለሁ የተቻለንን አድርገናል…ግን አልተሳካልንም..አርፏል ››ብሎ በተገተሩበት ጥሎቸው እግሮቹን አንቀሳቀሰ  … ግቢውን በጩኸት እና በለቅሶ ሲያደበላልቁት  በውስጡ እየተጠየፋቸው እና እየረገማቸው ጥሎቸው ወደ ቢሮው ሄደ

ሰላም…
..ፍቅሬ ፍቅሬ…
እንጋባለን ብለሀኝ አልነበረ ወይ…
ሙሽራዬ ነሽ አላልከኝም ነበር ወይ..
ለማን ተውከኝ..ለማን ተውከኝ 

ሰሎሞን……
ወንድም ጋሻዬ ….ወንድም ጋሻዬ
የእኔ ብቸኛ..የእኔ ብቸኛ
የአባቴ ምትክ ..የአባቴ ምትክ 
የዓይን ማረፊያዬ….
/////
ከደቂቃዎች በኃላ ሬሳው እየተገፋ ተመላካቹን በእንባ በሚያራጭ እንግሩጉሮአዊ ዜማ እና አንጀት በሚበላ  ሁኔታ በሚያለቅሱት እና ኩርምት ጭብጥ በሚሉት  በወንድሙ  ሰሎሞን እና በፍቅረኛው ሰላም መካከል አልፎ ወደሬሳው ክፍል ተወሰደ…..ሰሚራም እየተንቀጠቀጠች እና እየዘገነናት እራሷን ለማረጋጋት  በትርምሱ መሀል ተሹለክልካ ከሁሉም ነገር በመሸሽ  ቢሮዋ ገብታ ተሸጎጠች
እስከአሁን የሰራችው ስራ እና የፈጠረችው ተግባር ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከቷት እየተንቀጠቀች  ነው..የሚገርመውና ይበልጥ የሚጨንቀው ግን ከአሁን በኃላ የምትሰራው ስራ ነው…
በበቀልም ሆነ በጥላቻ ተነሳስቶ ሰውን ድፍት አድርጎ መግደል በጣም ቀላል ነው…ሳያስበው በሆነ ብረት ማጅራቱን መጠቅለል እና ዝርግፍ ብሎ ሲወድቅ ጭንቅላቱን በድልዱም ብረት መድገም ነው…አዎ እንደዛ ማድረግ ቀላል ነው… የሚከብደው ከገደሉት በኃላ ያለው ነገር ነው፡፡ሬሳውን ምን ላድርገው…?ግቢው ውስጥ ቆፍሬ ልቅበረው..….?ረሀብ ያንገላታው ውሻ ቆፍሮ አውጥቶ ቢያጋልጠኝስ…?በጆንያ አድርጌ ከከተማ አውጥቼ ራቅ ያለቦታ በመውሰድ ጫካ ውስጥ ልጣለው…?.መንገድ ላይ ፖሊስ ለፍተሻ ቢያስቆመኝስ……..?እንደዛ ሳደርግ ሰው ቢያየኝስ……..?ስቃይ ነው….በዛን ቅጽበት ከሟቹ በላይ ገዳዩ ያሳዝናል…በተለይ  ገዳዩ እንደእሷ አማትር ገዳይ ሲሆን ......ሁኔታው  እንደቅዣት ሆኖባት፤ በውስጧ ስትብሰለሰል  ስልኳ ተንጫረረ….
ከፈጣሪ የተደወለባት ነው የመሰላት….በርግጋ ከተቀመጠችበት በመነሳት ተፈናጥራ ቆመችና የደዋዩን ማንነት ለደቂቆች አትኩራ ተመለከተች…. በፈራ ተባ ስሜት አነሳችው

‹‹አቤት››

‹‹የት ገባሽ…..?››

‹‹አለው ፈርቼ ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ነው››

‹‹ምን ያስፈራሻል.…..?.››

‹‹እንዴ ድመት እኮ አይደለም ሰው ነው ያስገደላችሁኝ…..››

‹‹ማለቴ መግደልሽን  ማን ያውቃል..…..?እንደውም ስትፈሪና ስትንቀጠቀጪ የስራ ባለደረቦችሽ እንዳይጠረጥሩሽ…በተለይ ዶክተሩ እንዴት ሞተ ……..?ይሞታል ብለን አልገመትንም ነበር ሲል ሰምቼዋለሁ››

‹‹እ!! እንደዛ  አለ እንዴ…..? ››

‹‹አዎ ብሏል…ለማንኛውም አሁን ምን እናድርግ.››

‹‹ምን ለማድረግ አሰባችሁ?››

‹‹ሬሳውን አሁኑኑ ብትሰጡንና በጥዋቱ ቶሎ ብለን ብንቀብረው ጥሩ ነው፡፡››

‹‹ሬሳውንማ ላሰጣችሁ አልችልም …ጥዋት ነው መውሰድ የምትችሉት››

‹‹አይ አሁኑኑ መውሰድ አለብን… አሁን ሬሳ ሳጥን ገዝተው እንዲመጡ ሰዎች ልኬያለሁ…አንቺ ብቻ ደክተሩን አሳምነሽ እንዲፈርምልኝ አድርጊ…››

‹‹ዶክተሩ እኮ መሞቱን ብቻ ነው የሚያረጋግጥልህ….ሬሳውን በዚህ ምሽት እንድታወጣ የመፍቀድ ስልጣን ያላቸው  ግን ሌሎች ናቸው››

‹‹ሌሎቹን ተያቸው ..ዶክተሩ ብቻ ካስፈረምሽልኝ ካንቺ ምንም አልፈልገም…..ወደቤትሸ ሄደሽ ተረጋግተሸ በድል መተኛት ትችያለሽ…የስራ ኮንትራታችንን እዛ ላይ ይጠናቀቃል….››

‹‹እዛ ላይማ አይጠናቀቅም … መቶ ሺ ብር ጨምርልሻለው ብለኸኝ ነበር››

‹‹ሀይለኛ ብር ወዳድ  ልጅ ነሽ… አይዞሽ አረሳሁትም ግን እንደምታይኝ አሁን ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡ ከሶስት ቀን በኃላ ያው እንደምንም መጽናናቴ  ስለማይቀር  አቀብልሻለሁ…››

‹‹ዋ እንዳትረሳ››

‹‹አረሳም አሁን ያልኩሽን ጨርሺና ደውይልኝ››
ስልኩ ተዘጋ……

ይቀጥላል

#ክፍል 40,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18