ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
179K subscribers
277 photos
1 video
16 files
195 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ወሮበሎቹ የሚፈልጉትን ማግኘታቸው አያስደስተውም የሉተር ዕቅድ ቢጨናገፍ ደስታው ነበር፡፡ ነገር ግን ሉተር ጎርዲኖን ካላስለቀቀ ኤዲ ካሮል አንን ማግኘት አይችልም፡፡

ካሮል አንን በእጄ ካስገባሁ በኋላ ጎርዲኖ መያዙ አይቀርም  ሲል አሰበ፡ ይህ ግን የሚሆን አልመሰለውም፡፡ ጎርዲኖ በዚህ ጊዜ ውስጥ ርቆ
ሊሄድ ይችላል፡ ሌላው አማራጭ ሉተር ካሮል አንን በመጀመሪያ በእጁ
እንዲያስገባለት መደራደር ቢሆንም ሉተርን ለማስገደድ ምንም ማስፈራሪያ የለውም፡ ሉተር በአንፃሩ ካሮል አንን ይዟል፡

ወዲያው አንድ ሃሳብ ብልጭ አለበት፡፡ ጎርዲኖ በእኔ እጅ እኮ ነው ያለው፤ እሱን እንደማስፈራሪያ መጠቀም እችላለሁ› አለ፡፡ እነሱ ካሮል አንን ይዘዋል፧ እሷን ለማግኘት ከእነሱ ጋር መተባበር አለብኝ፤ ነገር ግን ጎርዲኖ በዚህ አይሮፕላን ላይ ነው ያለው፡፡ እሱን ማግኘት ከፈለጉ ከእኔ ጋር
መተባበር ይኖርባቸዋል
ሁሉም ነገር በእነሱ እጅ አይደለም ሲል በአዕምሮው አውጠነጠነ።

ስለዚህ የድርድሩን መዘውር በእጁ ማስገባት የሚችልበት መንገድ
ይኖር እንደሆን ማሰብ ጀመረ፡፡

አንድ መንገድ ይኖራል።

ለምንድን ነው እነሱ በመጀመሪያ ጎርዲኖን የሚወስዱት? ልውውጡ
መሳ ለመሳ ነው መከናወን ያለበት፡፡›

ከዚያም ንዴቱን ውጦ በጥልቅ ማሰብ ጀመረ፡

‹እንዴት ነው ልውውጡ ሊከናወን የሚችለው?

ጎርዲኖን ሊወስዱ በሚመጡበት ጀልባ ካሮል አንን ይዘው መምጣት
አለባቸው።
ለምን አይሆንም?  ሲል ከራሱ ጋር ተሟገተ፡፡ እሷን ያገቷት ከቤታቸው ብዙም ባልራቀ ቦታ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህም  ቦታ አይሮፕላኑ ከሚያርፍበት ቦታ ብዙም እንደማይርቅ ገምቷል፡፡ ምናልባትም ከአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦታ እሷ እስከታሰረችበት ቦታ ድረስ የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ ሊሆን ይችላል፡ ይሄ ደግሞ ሩቅ አይደለም፡፡

ኤዲ ባሰበው እቅድ ሉተር የሚስማማ ከሆነ ጓደኞቹን በስልክ ሊያናግር
የሚችለው አይሮፕላኑ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ቦትውድ (ካናዳ) ላይ ሲደርስ ይሆናል፡፡ ከቦትውድ ቀጥሎ አይሮፕላኑ የሚያርፈው ከሰባት ሰዓት ጉዞ በኋላ ማለትም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ሼዲያክ ላይ ነው: ወሮበሎቹ ደግሞ
በሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ እዚያ ቦታ ላይ ካሮል አንን ይዘው መምጣት
አለባቸው::

ኤዲ ካሮል አንን አስቀድሞ በእጁ ሊያስገባ እንደሚችል ሲያስበው ደስታውን መቆጣጠር አቃተው፡ የሉተርንም ጎርዲኖን የማስለቀቅ ጥረት
ሊያመክን እንደሚችል ትንሽ እድል እንዳለ ሲያስበው ደግሞ ተጨማሪ
ደስታ ፈጠረለት፡፡ ይሄ ደግሞ በስራ ባልደረቦቹ በኩል ጀግና ያስብለዋል፡
እነዚህን ነፍሰ ገዳይ ወሮበሎች መያዝ ከቻለ ጓደኞቹ ቀደም ብሎ ለፈጸመው ክህደት ምህረት ያደርጉለታል፡፡
መለስ ብሎ ሲያስበው ደግሞ ብዙ ተስፋ ማድረግ እንደሌለበት ገባው፡፡
ይሄ ሁሉ ገና ሀሳብ ነው፡፡ ሉተርም ባሰበው እቅድ አልስማማም ሊል ይችላል ኤዲ ያቀረበውን እቅድ ወሮበሎቹ የማይቀበሉ ከሆነ አይሮፕላኑን
የተባለው ቦታ እንደማያሳርፍ ያስጠነቅቃል፡ ነገር ግን ወሮበሎቹ የኤዲን
ማስፈራሪያ ከባዶ ዛቻ እንደማይዘል መገመት አያቅታቸውም፡፡ ኤዲ ሚስቱን ለማዳን ሲል የተባለውን ሁሉ እንደሚፈፅም ያውቃሉ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን
ሰው በእጃቸው ከማስገባት ውጭ ምንም ፍላጎት የላቸውም፡፡ እኔ ከነሱ
በላይ የተቸገርኩ ስለሆንኩ አቅመ ቢስ ነኝ ሲል አሰበ፡፡ ይህም ወደ ቀድሞው መከፋት ወሰደው፡፡

ሆኖም ኤዲ ያሰበውን ለሉተር ለመንገር ሰውዬውን ለመፈተን አሰበ፡፡
ቢያንስ ሰውዬውን ጥርጥርና ጭንቀት ውስጥ መክተት ይችላል፡፡ ምናልባት ሉተር የኤዲን ማስፈራራት አምኖ ላይቀበል ይችላል፡ ግን እንዴት እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ‹ኤዲ ውሸቱን ነው› ለማለት ወኔ ይጠይቃል፡፡ ሉተር ደግሞ ፈሪ እንደሆነ ታይቷል፤ በተለይ አሁን፡፡

ኤዲ ያሰበውን ለመሞከር ቆረጠ፡፡ ከሉተር በኩል ሊመጣ የሚችለውን
ተቃውሞ ለመመከት የሚያስችል ምላሽ አስቀድሞ መቀመር አለበት፡፡

ሉተር እንቅልፍ ካጡት ተሳፋሪዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በእንግዳ መቀበያው አንድ ጥግ ቁጭ ብሎ ብቻውን ዊስኪውን ይጨልጣል፡፡አይሮፕላኑ የፈጠረበት የሆድ መታወክ አሁን ስለቀነሰለት ፊቱ ፈካ ብሏል መጽሔት እያነበበ ነው፡፡ ኤዲ አጠገቡ ሄደና ጀርባውን ነካ አደረገው፡፡ ሉተር ኤዲን ሲያይ ደንገርገር አለው፤ ፍርሃት ብጤም ስለተሰማው ጠብ ጠብ ሸተተው፧ ኤዲም ‹‹ሚስተር ሉተር ካፒቴኑ ሊያናግርህ ይፈልጋል›› አለው፡፡

ሉተር ስጋት ገባው፡፡ ከተቀመጠበት አልነሳ ሲል ኤዲ ተነስቶ የጭንቅላት ምልክት አሳየው፡፡ከዚያም ሉተር መጽሔቱን አስቀመጠና የመቀመጫ ቀበቶውን አላቆ ተነሳ፡፡

ኤዲ ሉተርን ወደ ማብረሪያው ክፍል ሳይሆን ወደ መጸዳጃ ቤት ወሰደው፡፡፤

መጸዳጃ ቤቱ በትውከት ሽታ ታውኳል፡፡ እንደ እድል ሆኖ አንድ ሰው እጁን እየታጠበ ስላገኘ ኤዲ መጸዳጃ ክፍሉ ውስጥ እንዲቆይ ለሉተር የእጅ ምልክት ሰጠውና እሱ ማበጠሪያ አውጥቶ እያበጠረ ጠበቀው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እጁን የሚታጠበው ተሳፋሪ ከመጸዳጃ ክፍሉ ወጥቶ ሄደ፡፡ ኤዲም የሰውየውን መውጣት ተከትሎ ሉተር ያለበትን መጸዳጃ በር ቆረቀረ ሉተርም ‹‹ምን ፈለግህ?›› ሲል አምባረቀ፡፡
‹‹አፍህን ዝጋና አዳምጥ›› አለው፡፡ ኤዲ ከሉተር ጋር ጠብ ለመፍጠር አላሰበም፡፡ ሉተር ግን ጠብ ጠብ ብሎታል፡፡ ‹‹እዚህ አይሮፕላን ላይ ምን
እንደምትፈልጉ ደርሼበታለሁ ዕቅዳችሁን አውቄዋለሁ አሁን  የእቅድ
ለውጥ አድርጌያለሁ፤ እኔ አይሮፕላኑን የማወርድበት ቦታ ላይ ካሮል አንን
በጀልባ ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ›› አለው፡፡ሉተር አፉን በንቀት ሸረመመና ‹‹አንተ ጥያቄ ማቅረብ እኮ አትችልም የተባልከውን ማድረግ እንጂ›› አለው፡፡

ሉተር እንዲህ አይነት መልስ ይሰጣል ብሎ ኤዲ አልገመተም፡
‹‹እንግዲያውስ ስምምነታችን እዚህ ላይ አብቅቷል›› አለው ኤዲ፡
ሉተር መጨነቁን ፊቱ እያሳበቀበት ነው፡፡ ‹‹አንተ እኮ ምርጫ የለህም፧
ስለዚህ አፍንጫህን ተይዘህ አይሮፕላኑን የተባልክበት ቦታ ላይ ማውረድ
ያቺን ከአፍ የወደቀች ጥሬ የምታክል ሚስትህን ማስመለስ ትፈልጋለህ፧
ስለዙህ አፍንጫህን ተይዘክ
አውሮፕላኑን የተባልክበት ቦታ ላይ ማውረድ አለብህ››

‹‹እውነት ነው፡፡ ነገር ግን…›› ኤዲ ራሱን እየነቀነቀ ‹‹አላምናችሁም›› አለው ሉተርን «እንዴት አምናቹሀለው እኔ እናንተን አምኜ ሁሉን ነገር አድርጌ ብትከዱኝ እድሌን ማበላሸት የለብኝም።አዲስ ድርድር
እንድናደርግ እፈልጋለሁ፡፡››

የሉተር የመንፈስ ብርታት አሁንም ፍንክች አላለም፡:
አዲስ ስምምነት የለም›› አለ ፈርጠም ብሎ፡፡

አሁን ኤዲ ሉተርን የሚያንበረክክበትን ነገር መዘዘ ‹‹እሺ እንግዲያው
ወህኒ ትወርዳለህ›› አለው፡፡

ሉተር የንዴት ሳቅ ሳቀና ‹‹ምንድን ነው የምታወራው?›› ሲል ጠየቀ
ኤዲ አሁን ጥንካሬ ገባው፡፡ በአንጻሩ ሉተር ደግሞ ደካማ ሆኗል፡ለካፒቴኑ ሁሉን ነገር እነግረውና በሚቀጥለው የአይሮፕላን ማረፊያ ከተማ ላይ ለፖሊስ እንሰጥሃለን፡፡ ፖሊስ እዚያ ቦታ ላይ እንዲጠብቅህ በመገናኛ ሬዲዮ እንነግራለን፡፡ ካናዳ ውስጥ እስር ቤት ትወረወራለህ ጓደኞችህ ሊያድኑህ አይችሉም፡፡ ሰው በማገት፣ በባህር ላይ ውንብድናና በመሳሰሉት ወንጀሎች ትከሰሳለህ፡፡ እስር ቤት ውስጥ ትበሰብሳለህ›› አለው።

በመጨረሻ ሉተር መርበድበድ ጀመረ ‹‹ሁሉም ነገር በዕቅዱ መሰረት
እየተፈጸመ ነው›› ሲል የኤዲን ሀሳብ ተቃወመ ‹‹አሁን እቅዱን መለወጥ
አይቻልም፤ ጊዜ የለም፡፡››
📕ተአምረተ_ኬድሮነ

#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹እኮ የምታደርጉትን ነገር አቁሙ ነው እያልንሽ ያለነው  ..በግልጽ እንንገርሽ  መሰለኝ….እርሱ መዳን አይችልም ማለት መዳን የለበትም …..እሱ ከዳነ  እኛ እንጠፋለን ማለት-ነው….ስለዚህ  እረዳሽንም አረዳሽንም እሱን ለመግደል የምናደርገው ጥረት አናቆምም….እኛ በራሳችን ማድረግ  ዳግመኛ  መሞከር ያልፈለግነው  የፖሊሶች አይን እየተከታተለን ስለሆነ ነው፡፡››

‹‹ቆይ እስኪ አሁን የተመረዘበትን መድሀኒት የሰጣችሁት እናንተ ናችሁ….?››

‹‹እሱን ማወቅ ምን ይጠቅምሻል….?›.›

‹‹አይ እሱማ ምን ይጠቅመኛል..እንዲሁ ተገርሜ እንጂ››

‹‹ምንም የሚገርም ነገር የለም..አሁን ባቀረብንልሽ ሀሳብ
ትስማሚያለሽ ወይስ አትስማሚ..

….?››ይጠይቃታል ሰሎሞን ተብዬው….

ወዲያው  አዕምሮዋን አሰርታና የነገሮችን አካሄድ በፍጥነት በመተንበይ ‹‹አረ  እኔ ምን አገባኝ… እናንተ ለራሳችሁ ሰው ያላሰበችሁ እኔ ምን አስጨነቀኝ..እስማማለሁ…››ብላ ትመልሳለች ሰሚራ፡፡

እነሱም ካሰቡት በጣም በፍጥነት  ስለተስማማችላቸው ተደሰቱ..

‹‹አሪፋ…በጣም ጥሩ ውሳኔ ነው››ሰላም፡፡ 

ሰሎሞን  ‹‹እንግዲህ ስንት ቀን እንጠብቅሽ….?››

ሰሚራ ‹‹አንድ ሶስት ቀን እፈልጋለሁ››

‹‹ሶስት ቀን አይበዛም››

ኮስተር ብላ ‹‹ሰው ለመግደል እኮ ነው እየተስማማን ያለነው ..ሰው ለመግደል ሶስት ቀን እንዴት ሆኖ ነው የሚበዛው….?››

ሰሎሞንም በአሪፍ መስመር  እየሄደ ያለው ጠቃሚ ስምምነት ላለመበረዝ  ለስለስ ብሎ‹‹ያው ሞት አፍፍ ላይ ያለ ሰው ለመግዳል ብዙም አይከብድም  ብዬ ነዋ…በተለይ ላንቺ››

‹‹ላንቺ ስትል …….?ስታየኝ ገዳይ እመስላለሁ….?›› መለሰች ሰሚራ ኮስተር ብላ ፡፡

‹‹አይ አረ በፍጽም እንደዛ ማለቴ ሳይሆን የህክምና ዕወቀቱ ስላለሽ..የትኛው መድሀኒት ሰውዬውን በቀላሉ ሊገድለው ይችላል የሚለውን በደንብ ስለምታውቂ ብዬ ነው፡፡››

‹‹እንዳልከው መግደሉ ቀላል ነው..ግን ግድያውን ማንም  ሊደርስበት የማይችል እና  ፖሊስም በምርማራም ሊያረጋግጠው የማይችል መሆን አለበት››

‹‹አየሽ እኔ ቀልቤን በጣም ነው የማምነው…ገና እንዳየውሽ ለዚህ ስራ እንደምትረጂን እርግጠኛ ሆኜ ነበር..እሷ ግን አይሆንም ብላ በጣም ስትከራከረኝ  ነበር የሰነበተችው….እንድረታት አደረግሸኝ …ጀግና ሴት ነሽ..ስራውን በጥንቃቄ እና በፍጥነት ስሪልን እንጂ 100 ሺ ብር ቦነስ አለሽ››ሰሎሞን በፈገግታ ተሞልቶ   አሞገሳት፡፡

‹‹ችግር የለም..ባይሆን እድር ከሌላችሁ እድር ግቡ….››
‹‹ለእሱ አታስቢ›› ብለው  በደስታ ተሰናብተዋት በፈገግታ እደታጀቡ ይሄዳሉ፡፡

ሰሚራ እነሱ እደወጡ ነበር ምን ማድረግ እዳለባት ማሰብ የጀመረችው‹‹…ሰው እዚህ ድረስ መጨካከን የጀመረው መቼ ነው…….?›› ለዛውም በቤተሰብ ደረጃ…እራሷን በድንጋጤ የጠየቀችው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር… ‹‹…ምን ቢያደርጋቸው ነው የራሳቸውን ሰው እንዲህ ለማስገደል የሚጥሩት..….?››ሰው ሰውን  ከሞት ለማትረፍ‹‹…..የሰውን ህይወት ለማስተካከል ይለፋል ገንዘብን ይከሰክሳል እንጂ እንደነዚህ  የራስ ሰውን ለመግደል ምን አነሳሳቸው...….?

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 37,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄