TIKVAH-ETHIOPIA
1.38M subscribers
54.6K photos
1.35K videos
197 files
3.61K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ProsperityParty ብልጽግና ፓርቲ [Prospertity Party] በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ ገለጹ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ…
#TPLF #ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቢሮ እንደሚከፍት ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ መንግስት ግን የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸዉ ረዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተናገሩት፦

ብልጽግና ፓርቲ ለትግራይ ክልል የተሾሙ ግለሰቦች እንዳሉ ሰምቻለሁ እነማን እንደተሾሙ ግን ወደ ፊት የሚሆነዉን የምናይ ይሆናል፡

ብልጽግና በትግራይ ክልል ብዙ ደጋፊ አለው ብዬ አላምንም፤ ማንኛዉም ፓርቲ ህጋዊ እስከሆነ ድረስ ግን በትግራይ ክልል የመንቀሳቀስ መብት አለዉ።

#EthioFM #አባቱመረቀ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው ዕለት በተከበረው 124ኛው የዓድዋ ድል በዓል ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፦

"ሰሞኑን የህዳሴው ግድብ አስመልክቶ የቀረበው የውል ሰነድ ቆምብለን ከውጫሌው ውል በመማር በውሉ የሰፈሩ ሓሳቦችና ቃላቶች፣ በሉኣላዊነታችን ላይ የመጡ ከዛም አልፎ ለሌላ ጂኦፖለቲካዊ ዓላማ ማስፈፀሚያ ገፀ በረከትና እጅ መንሻ ሆኖ እንዳያገለግል በከፍተኛ ጥንቃቄና ሓላፊነት መፈፀም ይገባል።”

#TPLF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የኤርትራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር መዋጋት አይፈልግም ፤ ኢሳያስ እና ጥቂት የህግደፍ አባላት ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል" - ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳይ

📹#7MB #EthioForum #TPLF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

ከዚህ ቀደም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ፣ የኢፌዴሪ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዲኤታና በሌሎች የስራ ሀላፊነቶች ላይ የሰሩት በተጨማሪ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ውስጥ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።

#TPLF #FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TPLF

ዛሬ በነበረው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ትግራይ ክልል ተወካዮች እንዳልተሳተፉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለBBC አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ ህወሓት በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታ ላይ የነበሩ አባላቱ ፣ የክልሉ ተወካይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ኃላፊነታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን ለBBC ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው፥የፓርላማው የስልጣን ዘመን ማክተሙን በመግለጽ ፣ ከፓርላማው በተጨማሪ ፓርላማው ያቋቋመው መንግሥም ፣ ካቢኔም የተመረጡት ለ5 ዓመት መሆኑን ጠቅሰው የሰልጣን ዘመናቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TPLF #SHANE

በ19 የህወሓት ቡድን አመራር እና አባላት በአዲስ አበባ የሚገኙ ቋሚ ንብረቶቻቸው ላይ እገዳ መጣሉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ፡፡

ንብረታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ እና እንዲታገድ የተደረገባቸው የህወሓት ቡድን አመራርና አባላት ፦

- ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በቅፅል ስማቸው ወዲ ወረደ፣
- ሌተናል ጀነራል ፍስሃ ኪዳኑ በቅፅል ስማቸድ ፍስሃ ማንጁስ ፣
- ሜጀር ጀነራል አበበ ተ/ሀይማኖት በቅፅል ስማቸው ጆቤ፣
- ሜጀር ጀነራል ሀልፎም እጅጉ በቅፅል ስማቸው ወዲ እጅጉ፣
- ሜጀር ጀነራል ተስፋዬ ግደይ፣
- ብርጋዴር ጀነራል ሃ/ስላሴ ግርማይ በቅፅል ስማቸው ወዲ እንቤተይ፣
- ብርጋዴር ጀነራል ምግበ ሀይለ፣
- ብርጋዴር ጀነራል ተክላይ አሸብር በቅፅል ስማቸው ወዲ አሸብር
- አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ
- አቶ ሀሰን ሽፋ ሲሆኑ በአጠቃላይ በድምሩ 19 ናቸው።

በሌላ በኩል መቐለ ሆነው ለህወሓት ቡድን መረጃ ሲሰጡ ፤ የፋይናንስ እና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን በድብቅ ሲያቀርቡ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብሶችን በመልበስ በጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ ተመሳስለው ጥቃት ሲፈጽሙ ከነበሩ ግለሰቦች መካከል 14 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ለሰብአዊ ድጋፍ በመጓጓዝ ላይ የነበሩና እያንዳንዳቸው 20 ሌትር የምግብ ዘይት የያዙ 2,200 ጄሪካኖችን የጫነ አንድ ተሽከርካሪ ከእነ ተሳቢው አስገድደው አቅጣጫውን እንዲቀይር በማድረግ በድብቅ ለህወሓት ለመላክ ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በተጨማሪ ግብረ ሃይሉ የሼኔን ቡድን ሲደግፉ የነበሩ 141 ተጠርጣሪ ግለሰቦች የፋይናስ ስርአት እንዲቋረጥ እና ገንዘባቸው እንዲታገድ ተደርጓል፡፡

ዝርዝር መግለጫው : telegra.ph/ETH-05-31

@tikvahethiopia
#TPLF

ጠቅላይ ሚኒስትሩ TPLFን በተመለከተ ምንድነው ያሉት ?

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... አሁን ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀን የማንገባበት በርካታ ምክንያቶች ያሉን ቢሆንም አንገባም ብለን ከቆምን በኃላ ነገሩን በተለየ መንገድ ለማየት ጥረት እያደረግን ባለንበት በዚህ ወቅት አሁንም TPLF አላረፈም። አሁንም TPLF በግራ በቀኝ ሊነካካን ይፈልጋል። 

ለ7ኛው ስህተት የሚጓዘው TPLF በፍፁም ድል ማግኘት የማይችል እንኳን ቢሆን በወጣቶች የትግራይ ልጆች ላይ በህይወት የመቀጠፍ የመቁሰል አደጋ የሚያስከትል ስለሆነ 7ኛው ስህተቱ መስመር ስቶ ሳይሄድ መማር የሚችልበት እድል መፍጠር የራሱ (TPLF) ቢሆንም እንኳ እንደባላንጣ አትንኩን ፤ እረፉ ለማለት እወዳለሁ።

የነካካችሁን እንደሆነ በተለመደው መንገድ የከፋ ቅጣት ይደርስባችኃልና።

ትላንትና እንኳን ክስ አቋርጠን እስረኞች ይውጡ ስንል የTPLF ጀሌዎች ከፊሉ የአማራ አካውንት ከፊሉ የኦሮሞ አካውንት አስመስሎ በመክፈት እኛን ለማባላት ሳይተኙ አድረዋል። አማራ መስለው ፣ኦሮሞ መስለው ብዙ ጥረት አድርገዋል። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-01-09
TIKVAH-ETHIOPIA
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 'ህወሓት' እና ሸኔ' ን በሽብርተኝነት ፈረጀ። 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛው መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ም/ቤቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ "ህዝባዊ…
#TPLF

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት የሰየመውን ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሽብርተኝነት ስያሜ #ይነሳ #አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

በምክር ቤቱ ውስጥ የብልፅና አባላት ሕወሓትን ከአሸባሪነት ለመሰረዝ ያለመ ዝግ ስብሰባ ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔን ጨምሮ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በተገኙበት ሲያካሂድ እንደዋለና በውይይቱም በርካታ መግባባት ያላስቻሉ ጠንካራ ሐሳቦች መሰንዘራቸውን ጋዜጣው ከምንጮቼ  ሰምቻለሁ ብሏል።

ይሁን እንጂ በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2014 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት ላይ ለመምከር ለመጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ለጠዋት ጠርቶት የነበረውን ስብሰባ ወደ ከሰዓት በማጠፍ፣ በዚሁ ቀን ጠዋት አስቸኳይ ስብሰባ ለፓርላማ አባለቱ መላኩ ተገልጿል፡፡

ፓርላማው ሕወሓትንና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ድርጅት ወይም በመንግሥት ‹" ሸኔ "  ተብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን በአሸባሪነት የፈረጀው በሚያዚያ በ2013 ዓ.ም. ነበር፡፡

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
#TPLF

" ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል " - ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ

ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት በአብላጫ ድምፅ ተሰርዟል።

የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በዛሬው የምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ወቅት ፤ " የሰላም ስምምነቱ ቀሪ ጉዳዮች ቢኖሩም ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል " ሲሉ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ምክር ቤቱ ህወሓትን ከሽብርተኛ ድርጅት ዝርዝር ያነሳው የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ነው።

በስምምነቱ አንቀጽ 7/2 C መሰረት የፌዴራል መንግሥት በህወሓት / TPLF / ላይ የተጣለውን የሽብርተኝነት ስያሜ በምክር ቤቱ እንዲነሳ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል " - ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት በአብላጫ ድምፅ ተሰርዟል። የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በዛሬው የምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ወቅት ፤ " የሰላም ስምምነቱ ቀሪ ጉዳዮች ቢኖሩም ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል " ሲሉ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ…
#TPLF

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት / ከሽብርተኛ ድርጅትነት በተሰረዘበት የዛሬው የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር።

ከተገኙት የፓርላማ አባላት መካከል 61 የፓርላማ አባላት ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት መሰረዙን #ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል።

5 የፓርላማ አባላት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

በዚህም #በአብላጫ_ድምፅ ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት ይነሳ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ፀድቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔውን ተከትሎ ባሰራጨው መረጃ ፤ " በህወሓትና በፌደራል መንግስት በኘሪቶሪያ የተደረገውን ሥምምነት ለማጽናት ህወሐትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ማንሳት #አማራጭ_የሌለው ጉዳይ መሆኑን የውሳኔ ሃሳቡ በቀረበበት ወቅት ተነስቷል " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት / ከሽብርተኛ ድርጅትነት በተሰረዘበት የዛሬው የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር። ከተገኙት የፓርላማ አባላት መካከል 61 የፓርላማ አባላት ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት መሰረዙን #ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል። 5 የፓርላማ አባላት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። በዚህም #በአብላጫ_ድምፅ ህወሓት ከሽብርተኛ…
#TPLF

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ እንዲሁም የፌዴራል መንግስትን ወክለው ከህወሓት ጋር የተደራደሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስለ ህወሓት / TPLF ከሽብርተኛ ድርጅትነት ዝርዝር መሰረዝ በተመለከተ ምን አሉ ?

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦

" #ሠላም ሰጥተን የምንቀበለው በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ያሉ ቅሬታዎችን በይቅርታ በማለፍ የትግራይም ማህበረሰብ የሀገራችን አካል በመሆኑ፣ ዜጎች ማግኘት የሚገባቸውን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የትግራይ ሕዝብ በም/ ቤቱ መቀመጫ አግኝተው በሀገራቸው ጉዳይ ላይ እኩል እንዲወስኑ እና እንዲሳተፉ ዕድል መስጠት የሚያስችል የሠላም ስምምነቱ አካል በመሆኑ የህወሓትን የአሸባሪነት ስያሜ ማንሳት ያስፈልጋል።

ሌሎች ቀሪ ስራዎች አካታች ሀገራዊ የምክክር መድረኮችን በማመቻቸት በሀገራችን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ይሰራል። "

ህወሓት በህ/ተ/ም/ቤ ከአሸባሪ ድርጅትነት በ61 ተቃውሞ ፣ በ5 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ተሰርዟል።

@tikvahethiopia
#TPLF

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አካል የሆነው ፓለቲካዊ ውይይት በአስቸኳይ በተጠናከረ መልኩ እንዲጀመር ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት ጠየቀ።

ድርጅቱ ለአንድ ሳምንት ያህል ዝግ ስብሰባ ሲያካሄድ ቆይቶ ትላንት ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን አጠናቋል።

ህወሓት መስከረም 14 /2016 ዓ.ም አመሻሽ ባወጣው መግለጫ ፥ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከትሎ ህዝቡ ከጥይት ድምፅ ርቆ ተነፃፃሪ ሰላም ማስገኘቱንና ስምምነቱ ተከትሎ  የቴሌ ፣ የባንክ ፣ የመብራት ፣ የአውሮፕላን እና በተወሰነ መልኩ የየብስ የትራንስፓርትና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች መጀመር መቻላቸው በማስታወስ የሰላምን ውድ ዋጋ አወድሷል።

የሰላም ሂደቱ በፅኑ መሰረት እንዲቀመጥ እንዲደለድልና በሙሉነት እንዲተገበር በማድረግ የህዝብ ስቃይ እንዲቀረፍ በማስቻል በኩል አሁንም ብዙ ይቀራል ያለው መግለጫው ፤ የህዝብ ስቃይ ሙሉ በሙሉ ማስቆም የሚያስችል ፦
-  የተቀናጀ ፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል እንዲካሄድ
- ነፃ ያልወጣው ህዝብ በአስቸኳይ ነፃ እንዲወጣ የሚያስችል ስራ እንዲሰራ
- ተፈናቅሎ በየማረፍያ ማእከላት የሚገኝ ህዝብ ወደ ቄየው ተመልሶ መደበኛ ኑሮው እንዲመራ እንዲደረግ
- ተጠያቂነት ተረጋግጦ የተበደለ እንዲካስ የሚያደርግ ትግል እንዲካሄድና ፓለቲካዊ ውይይት ተቋማዊ ሆኖ በአስቸኳይ እንዲጀመር በተደራጀ መልኩ እንዲመራ ወስኛለሁ ብሏል ህወሓት በመግለጫው። 

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውጤት የሆነው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በሁለንተናዊ መንገድ እንደሚደግፍና እንደሚያጠናክር ያረጋገጠው የህወሓት መግለጫ ፤ የፌደራል መንግስት ትግራይ የደረሰባት ውድመት የሚመጥን በጀት እንዲመደብ ፣ የክልሉ ፀጋዎች የሚያጎለብት የህዝቡን ችግር የሚቀርፍ የማገገም እና የመልሶ ግንባታ ስራ ሳይውል ሳያድር እንዲጀመር በፅኑ ለመታገል ወስኛለሁ ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በማንነታቸው ብቻ በእስር የሚገኙ ትግራዎት እንዲፈቱና የተበደሉ ፍትህ እንዲያገኙና እንዲካሱ ለማስቻል ከበፊቱ የጠነከረ ፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ መወሰኑን ገልጿል።

የህወሓት መግለጫ ለትግል አጋሮቹ ባስተላለፈው ባለ 7 ነጥብ ጥሪ ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ' ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ' በአገራቸው እና በአከባቢያቸው ሰላም እንዲሰፍን ያላቸው ከፍተኛ ጉጉትና ፍላጎት በመግለፅ ከሁሉም ህዝቦች በሰላምና በአብሮነት ለመስራት ዝግጁ መሆናችን ደጋግመን እናረጋግጣለን " ሲል መግለፁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

More - @tikvahethiopiatigrigna
                         
@tikvahethiopia
#TPLF

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)  ለሳምንታት በዝግ በማካሄድ ላይ የሚገኘው ስብሰባና ግምገማ እያጋባደደ መሆኑ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ አካላት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ህወሓት ለ40 ቀናት ያህል በማካሄድ ላይ የሚገኘው ዝግ ስብሰባና ግምገማ ወደ መገባደጃው እየደረሰ ነው። 

እያንዳንዱ የደርጅቱ ስራ አስፈፃሚና ማእከላዊ ኮሚቴ የሂስና ግለ ሂስ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን ፤ የግምገማ ውጤቱ በድርጅቱ ካድሬዎች ወደ ሚካሄደው ስብሰባ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበት ተጨማሪና ማስተካከያ ከታከልበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የድርጅቱ የስራ አስፈፃሚና የማእከላይ ኮሚቴ እንዲሁም የካድሬዎች ስብሰባና ግምገማ ከተካሄደ በኃላ ህወሓት ጉባኤ እንደሚጠራ የገለጹት የመረጃ ምንጮቻችን ፤ ጉባኤው ለማሳለጥ ከድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ 3 ፣ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን 3 ፣ እንዲሁም ካድሬዎች 3 በድምር  ዘጠኝ አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ተመርጧል።

ዘጠኝ አባላት ያሉት የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ የህወሓት ጉባኤ ለማካሄድ መቼ እንደሚጠራ ቁርጥ ያለው ቀን ያልታወቀ ሲሆን ድርጅቱ ለ40 ቀናት ያህል በዝግ ስለ አካሄደው ስብሰባ  መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

የትግራይ ህዝብ ከጦርነት ማግስት ድርቅና ረሃብ ጨምሮ በበርካታ ፓለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ተዘፍቆ እያለ ህወሓት ለ40 ቀናት በዝግ ስብሰባ መቀመጡ ከውስጥም ከውጭም የሚነቅፉት ብዙዎች ሲሆኑ ፤ ጥቂቶች ደግሞ ድርጅቱ ጉዞው ለማጥራት የሚያስችለው ጥልቅ ሰብሰባና ግምገማ ማካሄዱ ይደግፉታል።  

ባለፉት ወራት በጊዚያዊ መንግስቱ (ክልሉን በበላይነት በሚመራው) እና በህወሓት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር 6 የዞን የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊዎች ፣ አንድ የስራ አስፈፃሚ የሚገኝባቸው 4 የህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ አባላት ከመንግሰት የስራ ሃላፊነት ማንሳቱና ማገዱ ይታወሳል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክሻህ አትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                                       
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" ላለፉት 39 ቀናት ያካሄድኩትን ሰብሰባ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት አጠናቅቃለሁ " - የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ

" ለ64 ቀናት ስብሰባ ተቀምጠን ህዝብን የሚረባ ጠብ ያለ ቁምነገር የለም " - የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜደንት ጌታቸው ረዳ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ላለፉት 39 ቀናት ከፀጥታ ሃይሎች ፣ ከተተኩ ነባር አመራርሮች በጥምር ያካሄደውን ገምገም፤ ግለሂስና ሂስ በዚህ ሳምንት እንደሚያጠቃልል አስታውቋል።

" የግምገማ ፣ የግለሂስና ሂስ መድረኩ ከሁለት ቀናት በማይበልጥ ጊዜ ይጠናቀቃል " ያለው መግለጫው ፤ " ቀጥሎ የድርጅቱ ካድሬዎችና አባላት የሚሳተፉትበት ጉባኤ ይካሄዳል " ብሏል።

" የቀጠለው መድረክ ከተጠናቀቀ በኃላ በድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴና ቁጥጥር ኮሚሽን መካከል በተደረሰ ስምምነት መሰረት መላ አመራር ፣ አባላትና ህዝብ የሚሳተፉበት ጉባኤ ይካሄዳል " ሲልም አሳውቋል።

አሁን ህወሓት ጉባኤው የሚያካሂድበት የተቆረጠ ቀን አላስቀመጠም።

ህወሓት ለ39 ቀናት ስብሰባ እንደተቀመጠ ቢገልፅም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ባላፉት ሳምንት በሽረ እንዳስላሴና በማይጨው ከተሞች በመገኘት ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ስብሰባው ለ64 ቀናት መካሄደውንና ለህዝብ የሚረባ ጠብ የሚል ቁምነገር እንዳልተገኘ ተናገረዋል።

የትግራይ ህዝብ ከጦርነቱ ማግስት በከባድ ድርቅና ረሃብ እንዲሁም ጦርነት ወለድ ችግሮች ተተብትቦ እያለ ይህን ያህል ቀናት አመራሮች ሰብሰባ መቀመጣቸውን የሚነቅፉት እጅግ በርካቶች ናቸው ሲል የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                      
@tikvahethiopia            
#TPLF

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ በራሳቸው ፍቃድ ከሃላፊነት መልቀቃቸው እየተነገረ ይገኛል።

ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ ጥር 21 /2016 ዓ.ም ለህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፅፍውታል በተባለና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ የመልቀቂያ ደብዳቤ ፤ " ከጥር 21 /2016 ዓ.ም ጀምሮ ከህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንደለቀቅኩ አስታውቃለሁ " ብለዋል።

ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በፌደራል ደረጃ ታጣቂዎች በማቋቋም ወደ ቀድሞ ህይወታቸው እንዲሰማሩ በሚሰራው መንግስታዊ መስሪያ ቤት ተሹመው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል ሲል የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ህወሓት ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር የለም ፤ ከማዕከላይ ኮሚቴ አባልነት ስለመልቃቸውንም ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ በይፋ አልሰጠም።

Via @tikvahethiopiaTigrigna                             
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF #ህወሓት

ክልላዊ ፣ አገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ባካተቱ 6 ነጥቦች ላለፉት ከ41 ቀናት በላይ ስብሰባ መቀመጡን የገለፀው ህወሓት ዛሬ ባለ 6 ገፅ መግለጫ አውጥቷል።

ጥር 22/2016 ዓ.ም ባወጣው መገለጫ እንዳስታወቀው ረጅም ጊዚያት ወስዶ ያካሄደው የድርጅቱ የፓሊትና የማእከላይ ኮሚቴ  የግምገማ ፣ የሂስና የግለሂስ መድረክ ወደ ቀጣዩ ጉባኤ የሚያሸጋግሩ ወሳኔዎች የተወሰኑበት ነው ብሏል።

ህወሓት በመግለጫው  ፦
- ለትግራይ ህዝብ
- ለድርጅቱ አመራርና አባላት
- ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች
- ለኤርትራ ህዝብ
- ለዓለም ማህበረሰብና ለትግሉ ደጋፊዎች እንዲሁም ሌሎችም አካላት መልእክት አስተላልፈዋል። 

ህወሓት በተለይ ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች ባስተላለፈው መልእክት ፤ " ህወሓት ለትግራይ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች የሰላም ስትራቴጂክ አማራጭ ከመሆን በዘለለ በማንም ህዝብ ላይ ጥላቻ አንደሌለው አረጋግጣለሁ " ብሏል።

" ከኤርትራ ህዝብ የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረግ የትግል አጋርነት ነበረን አጋርነቱና የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ መደጋገፉ ይቀጥላል " ያለው ህወሓት " የኤርትራ ህዝብ የኤርትራ ሰራዊት በሃይል ከያዛቸው የትግራይ ግዛቶች ለቆ እንዲወጣ ጫና እንዲያሳድር የሚያስታውስ ጥሪ አስተላልፈዋል። 

ህወሓት " ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብና ከትግላችን ደጋፊዎች " በሚል ባስተላለፈው መልእክት " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ፣ ስምምነቱ መሰረት ያደረገ ውይይት እንዲካሄድ ፣ የትግራይ የግዛት አንድነት እንዲረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ፣ የትግራይ መልሶ ግንባታ እንዲፋጠን ፣ ሰብአዊ ወንጀል የፈፀሙ በዓለም አቀፍ ህግ እንዲዳኙ እንዲደረግ የበኩላችሁ እንድትወጡ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል " ማለቱ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።    
                                       
@tikvahethiopia            
#ProsperityParty #TPLF

ህወሓት እና ብልፅግና የጀመሩት ፓለቲካዊ  ውይይት ቀጥለውበታል።

ፓርቲዎቹ ዛሬ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት አካሂደዋል።

ህወሓት ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ብልፅግና እና ህወሓት መሰረታዊ የአላማና የአይዲዮሎጂ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው " ያለ ሲሆን " ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገባ በርከታ የጋራ አጀንዳዎች አሉዋቸው " ብሏል።

ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ፤ " ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረናል " ሲል ገልጿል።

" ከዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተናል " ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ፦

- " በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

- ማንኛውንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።

- የኮሚኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል።

- የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

#ProsperityParty #TPLF

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የህወሓት (TPLF) ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የተሳተፉበት ውይይት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ከሌሎች ከፍተኛ የፌዴራል ባለስልጣናት ጋር መደረጉ ይታወሳል።

በወቅቱም ከ ' ህወሓት ' ህጋዊ እውቅና  ማግኘት ጋር በተገናኘ ውይይት ተደርጎ ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከውይይቱ በኃላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫቸው ፤ ' ህወሓት / TPLF ' መልሶ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ የመመዝገብ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ የፌደራል መንግስት እንደማይደግፈው ገልጸው ነበር።

በዚህም ያለው #የህግ_ክፍተት በአስቸኳይ ታርሞ ምዝገባው እንዲፈፀም መመራቱን ሲናገሩ ተደምጠው ነበር።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ሲል የ ' ህወሓት ' ን ህጋዊ ሰውነት #መሰረዙ ይታወቃል።

ፓርቲውም " ስረዛው ይነሣልኝ " ሲል ጥያቄ ቢያቀርም ቦርዱ ያን ሊያደርግ የሚችልበት ምንም ህጋዊ መንገድ እንደሌለ አሳውቆ ነበር።

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ " ምናልባትም ህወሓት ዳግም እውቅና ሊያስገኝለት የሚያስችለው እንደሆነ እየተነገረ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray #TPLF

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የዛሬውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን አወደሱ።

አቶ ጌታቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር በትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው ብለውታል።

ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ " ህወሓት / TPLF / ዳግም እውቅና ሊያስገኝለት የሚያስችለውን መንገድ የሚጠርግ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የዛሬውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን አወደሱ። አቶ ጌታቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር በትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው ብለውታል። ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ…
#Update

ፓርላማው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን / በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድለትን የአዋጅ ማሻሻያ አጽድቋል።

" የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን " የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በ2 የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው።

" በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ " የፖለቲካ ፓርቲዎችን " በልዩ ሁኔታ " እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው።

የጸደቀው የአዋጅ ማሻሻያ ፥ " ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል " ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ " የተደረገው ህወሓት #በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል።

" አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል " ሲል አዋጁ ደንግጓል።

#EthiopiaInsider
#TPLF

@tikvahethiopia