TIKVAH-ETHIOPIA
1.4M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሬሜዲያል

" በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " - የፌዴራል መጅሊስ

የሬሜዲያል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ቅሬታ አስነስቷል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና መርግብር፤ ፈተናው ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 6/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 6-10/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ይህ የፈተና ፕሮግራም ግን ከ #ኢድ_አል_አድሃ (አረፋ) በዓል ጋር የሚጋጭ በመሆኑ በእስልምና እምነት የከታዮች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል።

እንዲህ ያለ ቅሬታ ሲፈጥር ይህ የመጀመሪያ አይደለም ። ከዚህ ቀደም መሰል ሁኔታዎች ተፈጥረው እንደነበር አይዘነጋም።

የዘንድሮ የሬሜዲያል ፈተና ቀንን በተመለከተ የፌዴራል መጅሊስ ለሃሩን ሚዲያ በሰጠው ቃል ፤ " በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " ሲል ተቃውሟል።

የመጅሊሱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ከማል ሀሩን ፥ " የተማሪዎች የመፈተኛ የጊዜ ሰሌዳ የሙስሊሙን በዓላት ታሳቢ አድርገው መውጣት አለባቸው " ያሉ ሲሆን "  የበዓል ቀናትን ታሳቢ ያላደረገ የፈተና የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ አግባብነት የሌለውና በተማሪዎች የስነልቦና አልፎም የፈተና ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያ
#ሬሜዲያልፈተና
#ሀሩን

@tikvahethiopia
Anti Money laundering law Amharic from COM to HPR (1).pdf
494.2 KB
#ረቂቅ_አዋጅ ፦ " በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ "

#የሕዝብተወካዮችምክርቤት #ኢትዮጵያ
#AntiMoneyLaunderingLaw

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የ2016 የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

ጥዋት የኢድ ሶላት ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች ተከናውኗል።

ከኢድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን በዓሉን እያከበረ ነው።

#ኢድአልአድሃ #አረፋ

መልካም በዓል

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Asset Recovery draft proc. Amharic from COM to HPR (1).pdf
#ኢትዮጵያ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ፤ " ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ስለማስመለስ " ምን ይላል ?

➡️ #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል

➡️ ህጋዊ ገቢ እንዳለው የሚያስረዳ የተመዘገበበት ስርዓት የሌለው ወይም ገቢው እነስተኛ በመሆኑ #ከግብር_ነጻ የሆነ ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ ይወረሳል፡፡

➡️ " በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ያፈራው ንብረት " ማለት ፦

° በራሱ ስም የሚገኝ ንብረት፣

° በራሱ ስም ባይሆንም ለራሱ ጥቅም ሲያዝበት ወይም ሲቆጣጠረው የነበረው ንብረት ፣

° የተጠቀመው ወይም ደግሞ ያስወገደው ንብረት፣

° በሽያጭ ፣ በስጦታ ወይም በማንኛውም ሁኔታ #ያስተላለፈውን ንብረት ይጨምራል፡፡

➡️ ዐቃቤ ሕግ " #ምንጩ_ያልታወቀ_ነው " ብሎ የጠረጠረውን ማንኛውንም ንብረት ዝርዝር እና የተገኘበትን አግባብ የሚያሳይ መግለጫ እንዲያቀርብ በፅሁፍ ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም ሰው ጥያቄው በደረሰው በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ለዐቃቤ ህግ ዝርዝር ማስረጃዎችን በማያያዝ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል።

➡️ የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ ለማስረዳት የሚያቀርበው ማስረጃ ሀጋዊ መሆን አለበት።

ተጨማሪ ....

☑️ አንድ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ አውጥቶ የሚሰራ ነጋዴ ወይም ድርጅት ሕጋዊ ገቢው ተብሎ የሚገመተው ለተገቢው ባለስልጣን በወሩ ወይም በአመቱ ከንግዱ ያገኘሁት ብሎ ያሳወቀው የገቢ መጠን ሲሆን ወይም ተገቢው ታክስ የተከፈለባቸው ገቢዎች ሆነው ሲገኙና የታክስ ደረሰኝ ሲቀርብ ሲሆን ከዚህ ውጪ ህጋዊ ታክስ ያልተከፈለባቸው ገቢዎች ከህጋዊ ገቢ ውጪ ያፈራው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ተብሎ ሊወሰን ይችላል።

☑️ ምንጩን ሲያስረዳ " ከውጪ የተላከለኝ ገንዘብ ነው " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንዘቡ በሕጋዊ መንገድ #በባንክ_ሥርዓት ውስጥ ያለፉ ግብይቶች ወይም ክፍያዎች ስለመሆናቸው በተገቢው የባንክ ደረሰኝ አስደግፎ ማቅረብ የሚገባው ሲሆን ከዚህ ውጪ ያለው ግን እንደ ምንጩ ያልታወቀ ገቢ ተደርጎ ይቆጠራል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ #ምንጩ_ያልታወቀ_ንብረት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተደንግጓል፡፡

በዚህም አዋጁ ወደኋላ 10 ዓመታት ተመልሶ የሚሠራ ሲሆን ይህንንም ለመክሰስ የ5 ሚሊዮን የገንዘብ ገደብ ተቀምጧል፡፡

ይህ የገንዘብ ገደብ የተቀመጠበት ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ወቅት ላይ በሀገሪቱ ያለውን የሰው ሃይል ፣ የመክሰስ አቅም እና የፋይናንስ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የሃብት መጠን ያላቸውን ግለሰቦች በመተው ከፍተኛ ንብረት ያላቸውን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሆነ ተብራርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ሕጉ ወደኋላ (10 ዓመታት) ተመልሶ እንደመስራቱ በሀገሪቱ #ኢኮኖሚ#ማሕበራዊ እና #የፋይናንስ_ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ያደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱትን ግለሰቦችና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን ተጠያቂ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተብራርቷል።

አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ተጠያቂነት ያለምንም የገንዘብ መጠን ተፈጻሚ ይደረጋል።

ስለ ረቂቅ አዋጁ አጭር ማብራሪያ ⬇️
https://t.me/tikvahethiopia/88313

ረቂቅ አዋጁ⬇️
https://t.me/tikvahethiopia/88314

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ #ኦዲት

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ለምክር ቤት እያቀረበ ይገኛል።

በዚህም ወቅት ተከታዩን ሰምተናል ፦

በ2014 የበጀት ዓመት እና ከዚያ በፊት በፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች በተከናወነው የኦዲት ሪፖርት መሰረት እርምጃ የተወሰደ እንደሆነ ማጣራት ተደርጎ ነበር።

በ92 መስሪያ ቤቶች ተመላሽ እንዲደረግ ተብሎ አስተያየት ከተሰጠበት 443 ሚሊዮን ብር እና በዶላር 23,230 ከ43 ውስጥ ተመላሽ የተደረገው 48.2 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ ታውቋል፤ ይህም ተመላሽ ሊደረግ ከሚገባው ጋር ሲነጻጸር 11 በመቶ ብቻ ነው።

ቀሪው 394.8 ሚሊዮን እና 23,230 ከ43 ተገቢው እርምጃ ያልተወሰደበት እና ተመላሽ አልተደረገም።

በተጨማሪ በ2014 #የተሟላ_የማስረጃ_ሰነድ ካልቀረበበት 5 ቢሊዮን 61 ሚሊዮን ማስረጃ የቀረበበት 508. 1 ሚሊዮን ብቻ ሲሆን በመቶኛ 10% ብቻ ማስረጃው ቀርቦ ትክክለኝነቱ ተረጋግጧል።

የተመለሰው ትንሽ ቢሆንም አሰተያየት ተቀብለው ተመላሽ ካደረጉት ተቋማት ውስጥ ፦
የኢንፎርሜሽን ደህንነት መረብ አስተዳደር 5.9 ሚሊዮን ተመላሽ እንዲያደርግ ተብሎ 5.8 መልሷል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 4.1 ሚሊዮን ተመላሽ እንዲያደርግ ተብሎ 3.5 ሚሊዮን መልሷል።
የስፔስ እና ጂኦስፔሻል ስልጠና ኢንስቲትዩት ተመላሽ እንዲያደርግ ከተባለው 5.6 ሚሊዮን ውስጥ 4.4 ሚሊዮን መልሷል።

የሰነድ ማስረጃ አቅርቡ ከተባሉት ውስጥ ፦
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 124.25 ሚሊዮን ውስጥ ሁሉንም መልሷል።
የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 150.2 ሚሊዮን ውስጥ ሁሉንም መልሷል።
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከ3.9 ሚሊዮን 2.2 ሚሊዮን መልሷል።

ሰነዶቹም ትክክለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ኦዲት የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ለምክር ቤት እያቀረበ ይገኛል። በዚህም ወቅት ተከታዩን ሰምተናል ፦ በ2014 የበጀት ዓመት እና ከዚያ በፊት በፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች በተከናወነው የኦዲት ሪፖርት መሰረት እርምጃ የተወሰደ እንደሆነ ማጣራት ተደርጎ ነበር። በ92 መስሪያ ቤቶች ተመላሽ እንዲደረግ…
#ኢትዮጵያ #ኦዲት

የ2015 በጀት ዓመት የፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ክንውን ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው።

ሂሳብ አቅራቢ የነበሩት 173 የፌዴራል መንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች ሲሆኑ የ162 መ/ቤቶች እና 58 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በፌዴራል ኦዲተር መ/ቤት 11 ደግሞ በሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ኦዲት ሊደረጉ ታቅዶ ነበር።

10 መስሪያ ቤቶች 4 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በጸጥታ ምክንያት ኦዲት ተጀምሮ ተቋርጧል። 1 መ/ቤት ቢሮ አላቀረበም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጥሬ ገንዘብ ሂሳብ ላይ ታገቢው ቁጥጥር ይደረግ እንደሆነ ለማረጋገጥ ክትትል ሲደረግ ፥ በሁለት መስሪያ ቤቶች ብቻ ብር 383 ሺህ 238 ከ48 ሳንቲም ጉድለት ተገኝቷል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ኦዲት የ2015 በጀት ዓመት የፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ክንውን ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው። ሂሳብ አቅራቢ የነበሩት 173 የፌዴራል መንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች ሲሆኑ የ162 መ/ቤቶች እና 58 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በፌዴራል ኦዲተር መ/ቤት 11 ደግሞ በሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ኦዲት ሊደረጉ ታቅዶ ነበር። 10 መስሪያ ቤቶች 4 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በጸጥታ…
#ኦዲት #ኢትዮጵያ

ጤና ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር  ከፍተኛ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት መካከል መሆናቸው ተሰምቷል።

ለውሎ አበል እና ለመጓጓዣ እንዲሁም ለግዥ የተሰጠ ክፍያ ሰራተኛው ስራውን አጠናቆ ከተመልሱ በኃላ በ7 ቀናት መወራረድ እንዳለበት መመሪያ አለ።

ነገር ግን በ124 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው ብር 14.1 ቢሊዮን በወቅቱ ያልተወራረደ ወይም ያልተሰበሰበ ተሰብሳቢ ሂሳብ መኖሩ በኦዲት ታውቋል።

ጊዜው ሲታይም ከ1 ወር በላይ እስከ 1 ዓመት 1 ቢሊዮን 193 ሚሊዮን ብር ፤ ከ1 ዓመት በላይ እስከ 5 ዓመት 10.9 ቢሊዮን ብር ፤ ከ5 ዓመት በላይ እስከ 10 ዓመት 1.7 ቢሊዮን ብር ፤ ከ10 ዓመት በላይ 139 ሚሊዮን ነው።

ቀሪው ሂሳብ በቆይታው ጊዜ ያልተተነተነ ነው።

ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት #ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት እነማን ናቸው ?

#ጤና_ሚኒስቴር 6 ቢሊዮን
የመስኖ ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር 1.1 ቢሊዮን
የትምህርት ሚኒስቴር 1 ቢሊዮን 12 ሚሊዮን
በፌዴራል መንግስት የህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት 970.9 ሚሊዮን
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም የህክምና ኮሌጅ 756.3 ሚሊዮን
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 433.5 ሚሊዮን
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 286.8 ሚሊዮን
የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 272.4 ሚሊዮን
የመንግስት ግዥ አገልግሎት 265.2 ሚሊዮን
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 250.7 ሚሊዮን
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር 218.3 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በተጨማሪ የፕሮጀክት ሂሳብ በታየባቸው 4 መስሪያ ቤቶች 514.5 ሚሊዮን በወቅቱ ያልተወራረዳ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ተገኝቷል።

እንደ የፌዴራል መ/ቤቶች የሂሳብ አያያዝ መመሪያ መሰረት የተሰብሳቢ ሂሳብ በቂ ማስረጃ ሲቀርብበት ብቻ  ነው በተሰብሳቢ ሂሳብነት የሚመዘገበው። የተሰብሳቢ ሂሳብ ክምችት እንዳይኖር ቁጥጥር መደረግ አለበትም ይላል።

ነገር ግን በ15 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው 363.1 ሚሊዮን ማስረጃ ባለመቅረቡ የሂሳቡን ትክክለኝነት ማረጋገጥ አልተቻለም።

የተሰብሰቢ ሂሳቡን ትክክለኝነት ማረጋገጥ ካልተቻለባቸው መስሪያ ቤቶች መካከል ፦

🔴 የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 253.3 ሚሊዮን
🔴 የመንግስት ግዥ አገልግሎት 39.1 ሚሊዮን
🔴 ጤና ሚኒስቴር 28 ሚሊዮን ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦዲት የተሰበሰበው ገቢ #ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ሂሳብ ኦዲት ሲደረግ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት #በዶላር የተሰበሰበ 1.3 ሚሊዮን ገቢ ትክክለኝነቱን ማረጋገጥ #አልተቻለም። የፌዴራል ዋና ኦዲተር ማንኛውም ገቢ ተገቢ ማስረጃ ሳይሟላ በገቢ መመዝገብ ፍጹም ትክክል እንዳልሆነ አስገንብዝቦ የገቢ ማስረጃዎች በትክክል ተደራጅቶ እንዲያዝ ተገቢው ማስተካከያም እንዲደረግና እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።…
#ኢትዮጵያ #ኦዲት

በ11 መስሪያ ቤቶች 43.5 ሚሊዮን ብር #ምንም ማስረጃ ሳይኖር ወጪ ተደርጓል።

በ2015 የበጀት ዓመት መ/ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ ወጪ ማድረጋቸውን / በአግባቡ መጠቀማቸውን ፣ ተገቢ ማስረጃ መቅረቡንና ሂሳቡ በትክክል መመዝገቡን ለማጣራት ኦዲት ተደርጓል።

በዚህም ፥ ምንም አይነት ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ የተመዘገበ ክፍያ / ሂሳብ ተገኝቷል።

በ11 መ/ቤቶች 43.5 ሚሊዮን ማስረጃ ሳይኖረው በወጪ ሂሳብ የተመዘገበ ሲሆን ማስረጃም ባለመቅረቡ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አልተቻለም።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 17.4 ሚሊዮን
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ባለስልጣን 8.7 ሚሊዮን
የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት 8.7 ሚሊዮን
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 4.4 ሚሊዮን
የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት 3.3 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ፤ በወጪ ለተመዘገቡ ክፍያዎች የተሟላ ማስረጃ መቅረቡን ለማረጋገጥ በተደረገው ኦዲት በ 48 መ/ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 44 ሚሊዮን 440 ሺህ በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።

የተሟላ ማስረጃ ሳይዙ ወጪ ከመዘገቡት መካከል ፦
🔴 ማዕድን ሚኒስቴር 5 ሚሊዮን 719 ሺህ
🔴 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 5 ሚሊዮን 716 ሺህ
🔴 የጤና ሚኒስቴር 4 ሚሊዮን 677 ሺህ
🔴 ገንዘብ ሚኒስቴር 3 ሚሊዮን 34 ሺህ
🔴 በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገዋኔ የግብርና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ 2 ሚሊዮን 450 ሺህ
🔴 የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት 2 ሚሊዮን 185 ሺህ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የፌዴራል ኦዲተር መስሪያ ቤት ፤ ማስረጃ ካልቀረበ የሂሳቡን #ትክክለኝነት_ማረጋገጥ_እንደማይቻል ፤ የወጪ ማስረጃ ላልቀረበላቸው ክፍያዎች የወጪ ማስረጃ እንዲቀርብላቸው የማይቀርብላቸው ከሆነ #ገንዘቡ_ተመላሽ እንዲደረግ አሳስቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ኦዲት በ11 መስሪያ ቤቶች 43.5 ሚሊዮን ብር #ምንም ማስረጃ ሳይኖር ወጪ ተደርጓል። በ2015 የበጀት ዓመት መ/ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ ወጪ ማድረጋቸውን / በአግባቡ መጠቀማቸውን ፣ ተገቢ ማስረጃ መቅረቡንና ሂሳቡ በትክክል መመዝገቡን ለማጣራት ኦዲት ተደርጓል። በዚህም ፥ ምንም አይነት ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ የተመዘገበ ክፍያ / ሂሳብ ተገኝቷል። በ11 መ/ቤቶች 43.5…
#ኦዲት #ኢትዮጵያ

(ከ2015 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት)

➡️ የበጀት አጠቃቀም ፦

ኦዲት በተደረጉ መስሪያ ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በስራ ላይ ያዋሉት ሂሳብ ሲነጻጸር ከበጀት በላይ ወጪ የተደረገበት ፣ በርካታ ያልተሰራበት በጀት ተገኝቷል።

በ20 መ/ቤቶች በልዩ ልዩ የሂሳብ መደቦች በደንቡ መሰረት #ሳያስፈቅዱ ለእያንዳንዱ የበጀት ኮድ ከተደለደለው በላይ ወጪ የሆነ ሂሳብ ከመደበኛው በጀት ብር 524. 7 ሚሊዮን ፣ ከውስጥ ገቢ 288.9 ሚሊዮን ፣ ከካፒታል በጀት 489.4 ሚሊዮን በድምሩ 1.3 ቢሊዮን ብር ተገኝቷል።

በኮድ ከተደለደለው በጀት በላይ ውጭ ያደረጉ ዋና ዋና መ/ቤቶች ፦
🟠 ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 322.5 ሚሊዮን
🟠 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ተጠሪ ተቋማቱ 267.9 ሚሊዮን
🟠 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 173.2 ሚሊዮን
🟠 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 125.1 ሚሊዮን
🟠 የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 109.5 ሚሊዮን
🟠 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 91.3 ሚሊዮን
🟠 አምቦ ዩኒቨርሲቲ 83.3 ሚሊዮን
🟠 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 75.1 ሚሊዮን

ሁለት መስሪያ ቤቶች ደግሞ 9.7 ሚሊዮን ብር በጀት ስለመኖሩ ሳይረጋገጥ / ሳይፈቀድ ክፍያ ተፈጽሞ ተገኘቷል።

➡️ ከደንብ እና መመሪያ ውጭ የተከፈለ ፦

በ30 መ/ቤቶች ብር 16 ሚሊዮን 470 ሺህ ከደንብና መመሪያ ውጭ አላግባብ ተከፍሏል።

ዋና ዋናዎቹ መ/ቤቶች ፦
🔴 ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 3 ሚሊዮን
🔴 የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት 2 ሚሊዮን 889 ሺህ
🔴 ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊዮን 42 ሺህ
🔴 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊዮን 156 ሺህ

➡️ በመስሪያ ቤት ለሌሉና ከስራ ገበታ ለተሰናበቱ ሰራተኞች የተከፈለ ደመወዝ ፦

በ16 መስሪያ ቤቶች በመስሪያ ቤት ለሌሉ እና ከስራ ለተሰናበቱ ሰራተኞች ብር 485 ሺህ 183 ከ56 ሳንቲም ደመወዝ ተከፍሎ ተገኝቷል።

➡️ በበልጫ አላግባብ የተከፈለ ወጪ ፦

በ32 መ/ቤቶች እና በ9 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በተለያዩ የግንባታና ግዥዎች 4.9 ሚሊዮንና ለውሎ አበልና ሌሎች ክፍያዎች 57.6 ሚሊዮን በድምር 62.6 በብልጫ ተከፍሎ ተገኝቷል።

➡️ የግዥ አዋጅ ደንብና መመሪያ ያልተከተሉ ግዥዎች ፦

በ73 መ/ቤቶች እና በ15 ቅ/ጽቤቶች ብር 2 ቢሊዮን 199 ሚሊዮን የመንግስት ግዥ አዋጅ ደንብ እና መመሪያን ሳይከተል ግዥ ተፈጽሟል።

° በጨረታ መግዛት ሲገባው ያለጨረታ በቀጥታ የተፈጸመ ግዥ 1.8 ቢሊዮን ብር
° መስፈርት ሳይሟላ በውስን ጨረታ የተገዛ 104.3 ሚሊዮን ብር
° ግልጽ ጨረታ መውጣት ሲገባው በዋጋ ማወዳደሪያ የተፈጸመ 96.1 ሚሊዮን ብር
° የዋጋ ማወዳደሪያ ሳይሰበሰብ በቀጥታ የተፈጸመ ግዥ 13.8 ሚሊዮን ብር
° ሌሎች የግዥ ሂደት ያልተከተሉ 134.6 ሚሊዮን ዋና ዋና ናቸው።

ዋና ዋና መስሪያ ቤቶች (ደንብና መመሪያ ሳይከተሉ ግዥ የፈጸሙ)፦
ገቢዎች ሚኒስቴር በዋናው መ/ቤትና በቅርንጫፍ ፅ/ቤት 1.4 ቢሊዮን
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 91 ሚሊዮን
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 65.5 ሚሊዮን
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 62.9 ሚሊዮን
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 57.1 ሚሊዮን
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 37.4 ሚሊዮን
የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት 34 ሚሊዮን

➡️ በአማካሪ መሃንዲሳ ሳይረጋገጥ የተከፈለ ክፍያ ፦

የግንባታ ክፍያ #በአማካሪ_መሃንዲስ ተረጋግጠው መከፈላቸውን ለማረጋገጥ በተደረገ ኦዲት በ2 መ/ቤቶች 170 ሚሊዮን  394 ሺህ በአማካሪ መሃንዲስ የክፍያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሳይቀርብ ክፍያ ተፈጽሞ ተገኝቷል።

👉 ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 169.7 ሚሊዮን ብር ከፍሎ ተገኝቷል።

➡️ የተከፋይ ሂሳብ ፦

በ14 መ/ቤቶች 1.7 ቢሊዮን ብር በተከፋይ ሂሳብ ተይዞ ተገኝቷል። ለማን እንደሚከፈል እንኳን ተለይቶ አይታወቅም።

የተከፋይ ሂሳብ ለባለመብት መለየት ካልቻሉ መስሪያ ቤቶች ፦
🔵 የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር 1.5 ቢሊዮን
🔵 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 131.8 ሚሊዮን
🔵 ማዕድን ሚኒስቴር 29.9 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ

በቀጣዮቹ 10 ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከቀን ወደ ቀን በተሻለ መልኩ ይጠናከራሉ።

በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ መካከለኛው እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
  
በቀጣይ 10 ቀናት ....

አዲስ አበባ

ከኦሮሚያ ክልል ፦
- ቡኖ በደሌ
- ኢሉባቦር
- ጅማ
- ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም ወለጋ
- ምዕራብ ሀረርጌ
- አርሲ እና ምዕራብ አርሲ
- ሰሜን ሸዋ (ሰላሌ)
- ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች

ከአማራ ክልል ፦
- ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር
- ሰሜን እና ደቡብ ወሎ
- የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን
- አዊ
- ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋህግምራ

ከትግራይ ክልል ፦ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፤ ምስራቅ፤ ደቡብ፤ እና ምዕራብ ዞኖች

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፦ መተከል፣ ፓዌ፤ አሶሳ ፣ ካማሺ ዞኖች

ከጋምቤላ ክልል ፦ ማዣንግ እና አኝዋክ ዞኖች

ከሱማሌ ክልል፦ ሲቲ እና ፋፋን ዞኖች

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፦ ጉራጌ፣ ሀላባ ፣ ስልጤ ፣ ጠምባሮ ፣ ሃዲያ ፣ የየም ልዩ ዞን

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፦ ቤንች ሸኮ ፣  ዳውሮ ፣ ከፋ ፣ ሸካ ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፦ ጎፋ ፣ ጋሞ ፣ ኮንሶ ፣ ወላይታ ፣ ጌድኦ ፣ አማሮ ፣ አሪና ደራሼ ዞኖች

የሲዳማ ክልል ዞኖች

ሀረር እና ድሬዳዋ

... ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

ከዕለት ወደ ዕለት ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ገጽታዎች ላይ በመነሳት ፦
° ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤
° ከሱማሌ ክልል ጀራር፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ሊበን እና ዳዋ ዞኖች፤
° ከአፋር ክልል ቅልበቲ፣ ፈንቲ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች፤
° ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን፤
° ከጋምቤላ ክልል ንዌር እና የኢታንግ ልዩ ዞን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

#EthiopianMeteorologyInstitute

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

 በየዓመቱ ከ8 ቢሊዮን እስከ 5.6 ቢሊዮን ብር በጀት ሊመደብለት ይችላል።

የፌዴራል መንግሥት ፤ በየዓመቱ ከአገር ውስጥ ገቢ ምንጭ ከሚመድበው ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከ0.5 በመቶ እስከ አንድ በመቶ ያህል ለአረንጓዴ አሻራ እና ለተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ እንዲሰጥ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ረቂቅ አዋጁ ፤ " የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ለማቋቋም እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ " የሚል ስያሜ አለው።

ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ?

ለም/ ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ባለበት ሁኔታ ከፀደቀ በልዩ ፈንድ ከ2.8 ቢሊዮን ብር እስከ 5.6 ቢሊዮን ብር የሚደርስ በጀት ከመንግሥት ብቻ ሊቀርብለት ይችላል።

ልዩ ፈንዱ ዘጠኝ ዓላማዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል ፦
- የተጎሳቆለ መሬት በተፈጥሮና በመልሶ ማልማት መርህ በመታገዝ እንዲያገግም ማድረግ፣
- የደን ልማትና የደን መልሶ ማልማትን መደገፍ፣
- የአገሪቱን የካርቦን ልቀት ቅነሳ ግብ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ማድረግ፣
- የከተማ ማስዋብ እና አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን መደገፍ የሚሉ ይገኙበታል።

የልዩ ፈንዱ የፋይናንስ ምንጮች ፦
1ኛ. የፌዴራል መንግሥት የሚመድበው በጀት፣
2ኛ. የልማት አጋሮች፣
3ኛ. የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣
4ኛ. የግል ዘርፍ የሚሰጡት ድጋፍ ነው።

የፌዴራል መንግሥት ለፈንዱ ከሚመድበው በጀት የሚሰበሰበው ገንዘብ ለልዩ ፈንዱ በተከፈተው የባንክ ሒሳብ በየ3 ወራቱ በገንዘብ ሚኒስቴር ተቀማጭ ይሆናል። የሌሎች ምንጮች ድጋፍ የሚተዳደርበት አኳኋን የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያና የአሠራር ሥርዓት ይወሰናል።

መንግሥት የሚመድበው ዓመታዊ በጀት የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መሥፈርት መሠረት ለፌዴራል መንግሥትና ለክልሎች ይደለደላል።

ለክልሎች ከሚደለደለው በጀት ላይ የእያንዳንዱን ክልል ድርሻ ለመወሰን የሚያገለግለውን የገንዘብ ሚኒስቴር አዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይቀርባል። ሆኖም ለመሸጋገሪያነት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያፀደቀው ጠቅላላ የበጀት ድጋፍ ቀመር በጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

ከተደለደለው ዓመታዊ የሀብት ድርሻ ላይ በየ3 ወሩ ወደ ተጠቃሚ አካላት ገንዘብ ሊተላለፍ የሚችለው የሥራ አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ፣ ክልሎች ተጓዳኝ በጀት ሲመድቡና በክልሉ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ፈሰስ ሲያደርጉ ይሆናል።

ክልሎች የሚመድቡት ዝቅተኛ ተጓዳኝ በጀት ተፈጻሚ የሚሆነው በተጓዳኝ በጀቱ መጠን ላይ በረቂቅ አዋጁ የልዩ ፈንዱ አስፈጻሚ አካላት በሚል የተዘረዘሩት ፦
° የገንዘብ ሚኒስቴር፣
° የግብርና ሚኒስቴር፣
° የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣
° የኢትዮጵያ ደን ልማት በክልሎች የገንዘብ ቢሮዎች መካከል በሚደረግ ምክክር የጋራ ስምምነት ላይ ሲደረስና በየክልሉና በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤቶች ሲፀድቅ ነው።

እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ሳይተላለፍ የቀረ ገንዘብ በቀጣዩ ዓመት ለልዩ ፈንዱ ከሚመደበው በጀት ጋር ተደምሮ ይደለደላል።

የልዩ ፈንዱ ዓብይ ኮሚቴ አስፈጻሚ አካላት፦
° ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣
° ከኢትዮጵያ ደን ልማት
° ከክልሎች የገንዘብ ቢሮዎች የበላይ ኃላፊዎች ይዋቀራል። የገንዘብ ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ይሆናሉ።

ገንዘብ ሚኒስቴር ከተጠቃሚ አካላት ሚቀበለውን የሒሳብ ሪፖርት በማጠቃለል የልዩ ፈንዱን ሒሳብ ዘግቶ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ3 ወራት ውስጥ በፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይም የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሚወክለው ኦዲተር እንዲመረመር የማድረግ ኃላፊነት አለበት።

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው በዚህ መመሪያ ዉስጥ የእህልና ጥሬጥሬ ፣ የግብርና ምርቶች እና የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች ይገኙበታል ።

በዚህ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ  እቃዎችን ለመወሰን በወጣው  መመሪያ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ማድረግ የወጪ ጫናውን በማርገብ ረገድ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ከተደረጉት መካከል ፦
➡️ ጤፍ፣
➡️ ስንዴ፣
➡️ ገብስ ፣
➡️ ማዳበሪያ ፣
➡️ የእንስሳት መድሃኒት እንዲሁም በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርብ የካፒታል ዕቃዎች ይገኙበታል።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ…
🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ መንግስት እንደ መንግስት ሥራውን እየሰራ አይደለም ” ሲል ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ተቸ።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፤ ዶክተር አብዱልቃድር አደም ስለወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች የፓርቲያቸውን ምልከታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።

ሊቀመንበሩ በነበራቸው ቆይታ  ፦
- የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ጉዳይ
- የኑሮ ውድነት
- የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ
- ከሰሞኑን እየወጡ ስላሉ አዳዲስ አዋጆች
- ስለ ፖለቲካ ህዳሩ
- የመልካም አስተዳደር እጦት
- የኢኮኖሚ ጉዳይ ... ሌሎችም ተነስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም " መፍትሄው ምንድነው ? " ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፓርቲው ምላሽ ሰጥቷል።

ምጣኔ ሀብትን በተመለከተ ዶክተር አብዱልቃድር አደም ምን አሉ ?

“ የMacro Economy መናጋት አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የከፋ ሁኔታ ላይ ደርሷል።

የኢትዮጵያ የልማት ስትራቴጂ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ ነው።

ይልቁንም ትኩረት የሚሹት ፦
➡️ ኢንፍራስትራክቸር፣
➡️ መብራት፣
➡️ ጤና፣
➡️ ውሃ መሠረታዊ ችግሮች ናቸው፤ ዜጎች በእነዚህ ነገሮች ተቸግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚል የሚሰራቸው ፕሮጀክቶች መቃኘት አለባቸው።

ከፍተኛ የሆነ የንግድ ጉድለት አለ። የምንሸጠው እና የምንገዛው ልዩነቱ የሰፋ ነው። የበጀት Deficit አለ።

መንግስት የሚሰበስበውና የሚያወጣውን ገንዘብ ለዚያውም አስፈላጊነታቸው አጠራጣሪ ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘቡ ወጪ ይሆናል።

ይሄ ኢኮኖሚው እንዲናጋ አድርጓል ብለን እናምናለን።”

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-24

#ነእፓ #ኢትዮጵያ #የፖለቲካፓርቲዎችምንይላሉ?
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል። ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው…
#ያንብቡ #ኢትዮጵያ

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ፤ ' መመሪያ ቁጥር 1006/2016 ' ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

መመሪያው ተግባራዊ የተደረገው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ለማድረግና የወጪ ጫናውን ለማርገብ ጠቀሜታ ስላለው መሆኑ ተገልጿል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆኑ እቃዎች እና አገልግሎቶች ዝርዝር ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ናቸው።

1ኛ. እህልና ጥራጥሬ
ጤፍ
ስንዴ
ገብስ
በቆሎ
ማሽላ
ዘንጋዳ
ዳጉሳ
አጃ
አተር ፣ ባቄላ ፣ ምስር፣ አኩሪ አተር፥ ሽምብራ፣ ግብጦ፥ ጓያ እና የመሳሰሉት ጥራጥሬዎች፤
የእነዚህ ዱቄት

2ኛ. የግብርና ግብአቶች
ማዳበሪያ
ጸረ-ተባይ ኬሚካል
የእንስሣት መድሃኒት
የመድሃኒት መርጫ

3ኛ. የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች
👉 እንጀራ
👉 ዳቦ
👉 ወተት

4ኛ. በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርቡ የካፒታል እቃዎች

5ኛ. የወባ መከላከያ አጎበር ፤ ኮንዶም እና ለውሃ ማከሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎች

#MinistryofFinance
#MinistryofRevenues

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

“ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው። ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት፤ ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው እየመጡ የሚሰሩት። ይህ ችግር ግን የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ፤ ያንን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት። ” - ዶክተር በሀሩ በዛብህ (የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር የቦርድ አባል - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

#EMA
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ስፖርት #ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ።

ቡድኑ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ፍጻሜውን እስካገኘበት የሊጉ የመጨረሻ መርሃግብር ድረስ ከመቻል የእግር ኳስ ቡድን ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ ነው ሻምፒዮን የሆነው።

ዛሬ በተካሄደ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድህንን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

በዓመቱ 64 ነጥብ በመሰብሰብም ከመቻል በ1 ነጥብ በልጦ አጠናቋል።

መቻል በዓመቱ የፍጻሜ መርሃግብር ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ተፋልሞ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም በ1 ነጥብ ተበልጦ ዋንጫውን ተነጥቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በመጣበት አመት በታሪኩ የመጀመሪያው የሆነውን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ማሳካት ችሏል።

ቲክቫህ ስፖርት👇
https://t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport    
TIKVAH-ETHIOPIA
" ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ! " - ቋሚ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ፥ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ። በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል። ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ…
🔈#መልዕክት

" ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ፦
- ሰላምን፣ 
- መረጋጋትን
- ፍቅርን
- አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ


#ኢትዮጵያ🙏

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM