TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ሰብሳቢነት የሚመራው እና የፌደራል ፖሊስ ፣ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖችን ያካተተው የፀጥታ ግብረሀይል ሳምንታዊ ውይይት አድርጎል። በተለይ በመዲናዋ የአዲስ አመት በዓል ያለምንም #የፀጥታ ችግር እንዲከበር በሚደረጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ተወያይተዋል።

ህብረተሰቡ የሚመለከታቸውን #አጠራጣሪ ነገሮች #ለፖሊስ በማሳወቅ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ግብረሀይሉ #አሳስቧል

ግብረሀይሉ በህገወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ የገቡ 300 የሚሆኑ ሞተር ሳይክሎችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጎል። በተመሳሳይ ከቀናት በፊት በርካታ ቁጥር ያለው ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና📌

ከአዲስ አበባ ግጭቱ ጀርባ፦

በከተማዋ የሚታየዉ #የፀጥታ ችግር በቀን ጅቦች #ስፖንሰርነት ቅጥረኞች ያነሱት መሆኑ ታዉቋል። አለማዉ ህዝቡን በማባላት ወደ #ሥልጣን መመለስ ነዉ። ቅጥረኞች ሰልጥነዉ የተሰማሩ ከመሆናቸዉም በላይ በሞተር ሳይክል፣ በቤት መኪና እና በፕካፕ ገንዘብ እየተበተነላቸዉ መሆኑን የአይን እማኞች ገልፇል። ረብሻኞቹ ከሌላ ቦታ ተመልምሎ የመጡ ሲሆን የአዲስ አበባ ወጣት የለበትም። በብዙ ቦታዎች ደግሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ግጭት እንዳይፈጠር ሲከላከል እንደነበር ታዉቋል። የግጭት ፕሮጄክቱ ሙሉ በሙሉ የፀረ-ለዉጥ ኃይሉ መሆኑ በተጨባጭ ማስረጃ ተረጋግጧል! ባንዲራ #ሽፋን እንጂ መነሻ አይደለም። ሁለቱንም ባንዲራ የማይወዱ ሰዎች አንዱን ደግፎ ሌላዉን የተቃወሙ ያስመስላል።

ማስታወሻ፦

1. የረብሻኞቹ ፎቶ እና ቪዲዮ ይቀረፅ
2. የመኪኖቹ ታርጋ ይመዝገብ
3. ማስረጃ ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ አድርሱ።

Oduu Ammee📌

Jeequmsi #Finfinnee waraabeyyii guyyaatiin kan qindeeffame ta'uu barameera. Jeeqxoti bakka biraatii filatamanii leenjifamuun bobbaafaman. Makiinaan maallaqa hiraa akka jiranis barameera.

Bakka jeequmsi jirutti suuraa fi viidiyoo jeeqxotaa waraabuu fi taargaa konkolaataa qabuu hin dagatinaa!

ምንጭ፦ አቶ ታዬ ደንደአ(የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update "በሀገሪቱ ካለው #የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ቀን ተራዘመ" እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀና የሀገራችን ሰላም መሆን እንቅልፍ የሚነሳቸው ሰዎች የሚያስወሩት ነው።

🕊እኛ ሁላችንም የኢትዮጵያ ሀገራችን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ነን። በሰላማችን ጉዳይ ከማንም ጋር አንደራደርም🕊
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ ከተማ⬆️

በከተማዋ #ብሔር ተኮር መጠራጠር እንዲሰፍን በበሮች ላይ ቀለም በመቀባት የተሰራው ስራ በህብረተሰቡ እና በመንግስት ንቃት መክሸፉን የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ #ስኳሬ_ሹዳ ገለፁ፡፡

ምክትል ከንቲባው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከፊታችን ባለው መስከረም 17 ለሚከበረው የመስቀል ባዓል ለመላው የእምነቱ ተከታዮች #የእንኳን_አደረሳችሁ መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡

ከመስከረም 18 እስከ 21 በሀዋሳ ከተማ ለሚካሄደው የደኢህዴን 9ኛ ጉባኤ እንዲሁም ከመስከረም 23 እስከ 25 ‹‹በልማታዊ ዴሞክራሲ ማዕቀፍ የለውጥ እንቅስቃሴያችንን በማስቀጠል የኢትዮጵያን ህዳሴ እናረጋግጥ›› በሚል መሪ ቃል በከተማዋ ለሚካሄደው የኢህአዴግ 11ኛ ጉባኤ ለመላው የድርጅቶቹ አባላትና ደጋፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡

በከተማችን ባለፉት 3 ቀናት በተለያየ አካባቢ በተለይም በታቦር፣ በምስራቅና በመናህሪያ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ቀለሞችን በመኖሪያ ቤት በሮች ላይ #በመቀባትና ቀለሙን ተከትሎ የብሔር ግጭት ሊኖር እንደሚችል በማስመሰል በተነዛ ወሬ የከተማዋ ህዝብ መጠነኛ ጭንቀት ውስጥ እንደገባ ይታወቃል፡፡

ይህን አአስመልክቶ የከተማ አስተዳደሩ ከክልሉና ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ #የፀጥታ ጥበቃና የጥናት ስራ ሲሰራ መቆየቱን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሹዳ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት በከተማው በግለሰቦች መኖሪያ ግቢ በሮች ላይ የተቀባ ቀለም መኖሩን ማረጋገጥ እንደተቻለም አቶ ስኳሬ ገልጸዋል፡፡

እነዚህ ቀለሞች አንደኛው የከተማ አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤት የቤቶች ደረጃ ምዝገባ ስራ ክፍል የቀባው ሲሆን ሁለተኛው በከተማዋ በቆሻሻ ማንሳት ስራ የተሰማሩ ማህበራት ገንዘብ የከፈሏቸውን ነዋሪዎች ካልከፈሉት ለመለየት የቀቡት መሆኑን ለመለየት እንደተቻለ ምክትል
ከንቲባው ገልፀዋል፡፡

ከዛ ውጪ የተለየ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ህዝቡን ለማሸበርና የከተማዋን ገፅታ ለማጉደፍ እንዲሁም በህዝቦች መካከል መተማመንና አብሮነት እንዳይኖር በማድረግ ብሔር ተኮር ጥርጣሬ ለማሳደር የቀቡት ቀለም መኖሩንም ለማረጋገጥ ተችሏልም ብለዋል፡፡

በሀገር ደረጃ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እንዳይቀጥል ለማድረግና እንዲቀለበስ ፍላጎት ያላቸው ሀይሎች በተለያየ ጊዜና ቦታ ሲያደርጉት ከነበረው እንቅስቃሴ አንዱ እንደሆነም #ለመረዳት እንደተቻለ አቶ ስኳሬ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም በተደረገው ክትትል ወቅት እኩይ ተግባር ማስፈፀሚያ የሆኑና ገንዘብ የሚከፈላቸው በልመና መስክ የተሰማሩ ጥቂት ግለሰቦች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት መክትል ከንቲባው ከእነርሱ ውጭ ከሌላ አካባቢ በመምጣት አልጋ
በመከራየት ስለት ነገሮችን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ፀጉረ ልውጦች መኖራቸውንም በመጠቆም ነው፡፡

ቀለም በበራቸው የተቀባባቸው ነዋሪዎችም ያለምንም ልዩነት አልፎ አልፎ የተቀባባቸው መሆኑም ተረጋግጧል፡፡ በዚህም በከተማው
የሚኖሩ የደቡብ ብሔረሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን በከተማዋ በሚገኙ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በር ላይም መቀባቱ ተረጋግጧልም ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡

እነዚህ አካላት ላይ በመደረግ ላይ ያለው ምርመራ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ነው ያሉት አቶ ስኳሬ በአሁኑ ወቅት የፀጥታ ሀይሉና ህብረተሰቡ በአንድ ላይ በመሆን አከባቢውን በንቃት እየጠበቀ መሆኑን ተከትሎ በከተማዋ ከተራ ሽብር እና ወሬ በስተቀር የተከሰተ አንዳችም ችግር አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ከፊታችን ያለው የመስቀል በዓልም ይሁን በጉጉት የሚጠበቀው የደኢህዴንና የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤን በከተማዋ ለማክበር ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንደማይገጥም ገልጸው የከተማው ነዋሪዎችና ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች ስጋት እነዳይገባቸው
አሳስበዋል፡፡

ውበት ለከተማችን፤ ስኬት ለህዝባችን…!

©የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቤንሻንጉል⬇️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ዞን #አመራሮች ላይ በተፈፀመ ጥቃት፣ አራቱ ህይወታቸው አለፈ።

መስከረም 16፣2011 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች ላይ የተፈፀመዉን ጥቃት ተከትሎ በከማሽ ዞን የተፈጠረዉን #ዉጥረት ለማርገብ የፀጥታ ኃይል በስፍራዉ ደርሶ #የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ #ሰይፈዲን_ሐሩን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት መስከረም 15፣ 2011 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ ላይ ተካሂዶ በነበረዉ የቤኒሻንጉል እና የኦሮሚያ ክልሎች የጋራ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ የዉይይት መድረክ ላይ ተሳትፈዉ መስከረም 16፣ 2011 ዓ.ም ወደ ከማሽ ዞን በመመለስ ላይ የነበሩ የዞኑ አመራሮች ላይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል፡፡

በጥቃቱም 4 የካማሽ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ህይወታቸዉ አልፏል፡፡ ጥቃቱን የፈፀሙ አካላትን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል መንግስት #የፀጥታ ኃይሎችን በስፍራዉ ማሰማራቱን ኮሚሽነሩ አስታዉቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በከማሽ ዞን አመራሮች ላይ የተፈፀመዉን #ጥቃት ተከትሎ በካማሽ ከተማ ላይ ዉጥረት ነግሷል። የመንግስትና የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል፡፡

ዉጥረቱን ለማብረድ የፀጥታ ሃይሎች በስፍራዉ ገብተዉ የማረጋጋት ስራ እየሰሩ መሆናቸዉን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች መካከል #ግጭት ለመፍጠር የተለያዩ የጥፋት አጀንዳዎችን ይዘዉ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች እንዳሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

እነዚህን ኃይሎች ለመመከት የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስታት የጋራ ዕቅድ አዉጥተዉ እየሰሩ መሆናቸዉን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ገልጸዋል፡፡

በፀረ ሰላም ሃይሎች ዕኩይ ሴራ በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ያለዉ የአንድነትና የትብብር መንፈስ ይበልጥ ያጠነክረዋል እንጂ፣ ሊሸረሽረዉ እንደማይችል ኮሚሽነሩ በመግለጫቸዉ አስታዉቀዋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን በመወከል በ12ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት አቶ አሸብር ረጋሳ ተፈፀመውን ጥቃት በማውገዝ ድርጊቱን የፈፀሙ ኃይሎችን በማጋለጥ ለህግ እንዲቀርቡ የአካባቢው ህዝብ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጥቃቱ ህይወታቸዉን ላጡ የከማሽ ዞን አመራሮች የክልሉ መንግስት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማዉ በመግለጫዉ አስታዉቋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢህአዴግ‼️ በየአካባቢው አየተስተዋለ ያለው #መፈናቀልና ሰብዓዊ መብት #ጥሰት በምንም መልኩ ኢህአዴግ እንደማይታገስ ተመለከተ። ለዚህም #የፀጥታ_አካላት ተገቢውን #እርምጃ እንዲወስዱ አቅጣጫ ተቀምጧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትምህርት ሚንስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ እንደተናገሩት፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን #የፀጥታ_ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥቅምት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ህዝባዊ #ውይይት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ይካሄዳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ‼️በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ #የፀጥታ_ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥቅምት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ህዝባዊ #ውይይት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ይካሄዳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሳሰቢያ‼️

ወህዴግ በማህበራዊ ሚዲያ በቀን 19/03/2011 ዓ.ም #በወላይታ_ሶዶ ከተማ #ሠላማዊ_ሰልፍ እንደሚያደርግ እየገለፀ ያለ ቢሆንም የዞኑ አስተዳደር አሁን ያለውን #የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍቃድ ያልተሰጠ ስለሆነና ነባራዊ ሁኔታን በመገምገም ወደፊት የሚፈቅድ መሆኑ ታውቆ በተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችም ሆነ አባላት የሚደረገው ቅስቀሳ ተገቢ ያለመሆኑን በመገንዘብ #ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን፡፡

©Wolaita ZONE Culture, tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በጎንደር ከተማ አስተዳደር በአጎራባች ወረዳዎች የሚስተዋሉ #የፀጥታ_ችግሮች ወደ ከተማው #እንዳይዛመቱ የሰላም ኮንፈረንስ ሊያካሂድ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ዘለቀ አለባቸው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቁት ዛሬ ከሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ጋር #የሰላም ውይይት ይካሄዳል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሎቄ🔝በዶክተር #ወላሳ_ላዊሶ የሚመራው የሲዳማ ምሁራን ቡድን ከዛሬ 17 ዐመታት በፊት ልዩ ስሙ #ሎቄ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ በመንግስት #የፀጥታ_ሀይሎች ህወይታቸውን ያጡ ዜጎች ቤተሰቦቻቸውን በአካል በመሄድ ጎብኝተዋቸዋል።

ፎቶ፦ ታሪኩ ለማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

ትናንትና እና ዛሬ በአማራ ክልል በሁሉም ቦታዎች የከተራ እና የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከብሯል፡፡ በዓሉ ያለምንም #የፀጥታ_ችግር መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በክልላችን በሁሉም ቦታዎች በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተጠናቋል ብለዋል፡፡

ፖሊስ እና የፀጥታ ኃይሉ ከሳምንት በፊት ዝግጅት እንዳደረጉ የተናገሩት ረዳት ኮሚሽነሩ በአንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ስጋቶች ቢኖሩም ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡

የፀጥታ ኃይሉ ወጣቶች የሃገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ከፖሊስ ጋር እጅ እና ጓንት ሆነው በመስራታቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ማመስገን ይፈልጋል ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡

ነገ የሚከናወነውን ቀሪ በዓልም በተመሳሳይ ዝግጅትና ጥበቃ ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የፀጥታ_ችግር

ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ 96 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ማና ሲቡ ፤ መንዲ ከተማ (ምዕራብ ወለጋ) እና አካባቢው ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

አንድ በአካባቢው ላይ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል፤ ከትላንት ወዲያ ሰኞ  ታጣቂዎች ከማለዳ ጀምሮ ቶክስ በመክፈት ወደመንዲ ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በመንግስት መ/ቤቶችና ተቋማት ላይ ጥፋት ሲያደርሱ እንደነበር አመልክቷል።

ባንኮችም ተዘርፈዋል።

በከተማው የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ እንደሆኑና ከአሶሳ-መንዲ የህዝብ ትራንስፖርት ሙሉ ለሙሉ እንደተቋረጠ በክስተቱ ንፁሃን ሰዎች እየተገደሉ ገልጿል።

መንዲ እና አካባቢው ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ያለው የኸው የቤተሰባችን አባል "ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዛት ያላቸው የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ወደ ከተማ ዘልቀው ገብተው ጥፋት ያደረሱት" ሲል አስረድቷል።

ከአሶሳ ጋር የሚያገናኘውን ዋናውን አስፓልት በመቆረጡ ነዋሪው ትልቅ ስጋት ላይ እንደሆነ ገልጾ " የንፁሃን ደም ከመፍሰሱ በፊት መንግስት ፈጣን መፍትሄ እንዲሰጥ  እንፈልጋለን " ብሏል።

"  ብዙ ዘመዶቼ እዛ ስላሉ እኔም ጨንቀት ላይ ነኝ " ሲል ሀሳቡን አጋርቷል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን የአስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደበላ ኦላና ደግሞ " ከሰኞ ጀምሮ እስከ ትላንት ማክሰኞ ድረስ የፀጥታ ኃይሉ እና ታጣቂዎች እየተዋጉ ነው " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

አቶ ደበላ በአካባቢው ከሰኞ ጀምሮ ተኩስ እንደነበርና #ከተማው ውስጥም ተኩስ እንደነበር አመልክተዋል።

ታጣቂዎቹ ወደ ከተማ ዘልቀው ሳይገቡ እንዳልቀረ ጥርጣሬ እንዳላቸውም ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#የፀጥታ_ጉዳይ

" የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባልን አመልክተናል " - አቶ ውብሸት አበራ

ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ እንደከፈቱ ተሰምቷል።

ለአል ዓይን ኒውስ የደራ ወረዳ፤ ጉንዶ መስቀል ከተማ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ፤ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው የኦነግ ሸኔ ቡድን ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ዘልቀው በመግባት ከባድ ጥቃት እያደረሱ ነው።

ነዋሪዎቹ በቅድሚያ ጥቃቱ በገጠር ቀበሌዎች ላይ መጀመሩን አመልክተው ማለዳ ሶስት ሰዓት ላይ ወደ ጉንዶመስቀል ከተማ በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና የመንግስት እና የግለሰብ ንብረቶችም እየተዘረፈ ነው ብለዋል።

በጉንዶ መስቀል ከተማ ዙሪያ ላይ ባሉት ቀበሌዎች የሚኖሩ ዜጎችም መኖሪያ ቤቶች በታጣቂዎቹ እየተቃጠለ እና ከብቶቻቸው እየተወሰዱባቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ አመልክተዋል። በስፍራው ላይ የመንግስት የጸጥታ መዋቅር እንደሌለም አክለዋል።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት አበራ በሰጡት ቃል ፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ደራ ወረዳ ዋና ከተማ ጉንዶመስቀል መግባታቸውን ገልጸዋል።

" ታጣቂዎቹ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በከተማዋ ባሉ ባንኮች፣ የመንግስት ተቋማት እና የግለሰቦችን ንብረት እየዘረፉ ነው " ያሉት አስተዳዳሪው የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባላቸው ማመልከታቸውን ለአል አይን ኒውስ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ይዘጋሉ።

የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል መንገዶች የሚዘጉት ለ " ፀጥታ ስራ ሲባል " መሆኑን ገልጾ ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኞች ዝግ እንደሚደረጉ ነው ያመለከተው።

የጋራ ግብረ ሃይሉ ከቀናት በኋላ በአ/አ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚከናወነው #የአጀብ እና #የፀጥታ ስራዎች ምክንያት በማድረግ #ሁሉም_የፀጥታ_አካላት_የሚሳተፉበት ወታደራዊ የተግባር ልምምድ እንደሚከናወን አሳውቋል።

ለዚሁ ሲባል የሚከተሉት መንገዶች ለተሽከርካሪ እና ለእግረኞች ዝግ ይደረጋሉ ፦

🚘 ከጎተራ መሳለጫ ወይም ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ጎተራ መሳለጫ ጋር፤

🚖 ከቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሀር የሚወስደው ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መስቀለኛ  ላይ ፤

🚘 ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ ቡልጋሪያ ማዞሪያ፤

🚖 ከሳር ቤት በአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ሳር ቤት አደባባይ፤

🚘 ከካርል አደባባይ በልደታ ፀበል ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት  ለሚመጡ ካርል አደባባይ፤

🚖 ከጦር ሃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ፤

🚘 ከአብነት ወደ ጌጃ ሰፈር አብነት አደባባይ፤

🚖 ከሞላ ማሩ ወደ አብነት ፖሊስ ጣቢያ ለሚመጡ ሞላማሩ መስቀለኛ ፤

🚘 ከበርበሬ በረንዳ ወደ ቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ  ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ፤

🚖 ከተ/ሃይማኖት ወደ ጎማ ቁጠባ ተ/ሃይማኖት አደባባይ፤

🚘 ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ዝግ የተደረገ ሲሆን ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡ 

🚖 ከሽሮ ሜዳ ወደ 6 ኪሎ እና ወደ 4ኪሎ የሚያስኬደው መንገድ  ሽሮ ሜዳ ጋር የሚዘጋ ሲሆን ከ4 ኪሎ ወደ ቤተ መንግስት የሚወስደው መንገድ ዝግ ተደርጓል፡፡ 

🚘 ከቀበና ወደ 4ኪሎ ቀበና አደባባይ ፤

🚖 ከጀርመን አደባባይ እና ከሲግናል አካባቢ ወደ 4 ኪሎ ጥይት ቤት ለሚመጡ ጀርመን አደባባይ ፤

🚘 ከካዛንቺስ መናህሪያ ወደ 4ኪሎ እና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሴቶች አደባባይ፤

🚖 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ፤

🚘 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደበባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል መስቀለኛ ፤

🚖 ከቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ ወደ መስቀል ፍላወር ቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ፤

🚘 ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ አፍንጮ በር፤

🚖 ከፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው 6 ኪሎ ዝግ ይሆናል፤

🚘 ከሚኒሊክ ሆስፒታል ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው መንገድ 6 ኪሎ ቶታል ጋር ዝግ የሚደረግ ሲሆን በተጨማሪም ወደ 4 ኪሎ እና በቅርበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመጡ አቋራጭ መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ተብሏል።

በተጨማሪም #ለእግረኛ ተጠቃሚዎች፦

🚶መስቀል አደባባይ 4ተኛ ክፍለ ጦር ወይም ጥላሁን አደባባይ ዙርያ፣
🚶‍♂ኦሎምፒያ ዙርያ፣
🚶‍♂ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ ከቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከሀራምቤ ወደ መሰቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከትምህርት ሚኒስቴር በአራት ኪሎ ብሔራዊ ቤተ መንግስትና ወደ ቦሌ እንዲሁም ከቀበና ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ዝግ መሆኑ ተነግሯል።

ዝግ ሆኖ የሚቆየው ከለሊቱ 11፡ 00 እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ህብረተሰቡ #አማራጭ_መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ተላልፏል።

(የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል)

@tikvahethiopia
#የፀጥታ_ችግር

ዘላቂ ሰላም ያልተገኘለት እና ዛሬም ድረስ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው ቀጠና መፍትሄው ምንድነው ?

• ከ2010 ዓ/ም አንስቶ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ንብረት ወድሟል። እርቅ ለመፈፀም ተሞክሮ ዘላቂ ሰላም አልመጣም።

• ከሰሞኑ በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ንብረት ወድሟል ፤ እርቅ ለመፈፀም ጥረት እየተደረገ ነው።

• ዛሬ ወደ ገበያ በሚያቀኑ ሰዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ ተጎድተዋል።

በደቡብ ክልል መን፤ በጉራጌ ዞን በመስቃን እና ማረቆ መካከል በተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግሮች እየተከሰቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣ ንብረት ሲወድም ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ሲስተጓጎሉ ፣ የመንግሥት ስራም ሲበደል በአጠቃላይ በቀጠናው ከፍተኛ ተፅእኖ ሲደርስ ቆይቷል።

በአካባቢው ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም የዕርቅ ጥረቶች ተደርገውም ያውቃሉ።

ከሰሞኑን ደግሞ በዚሁ አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ጉዳትም ደርሷል።

አንድ ስለ ጉዳዩ አውቃለሁ ያሉ የቤተሰባችን አባል ፤ " መስቃን እና ማረቆ ባንተ ወረዳ ይሄን ያክል ቀበሌ አለኝ አንተ የለህም የኔነዉ ያለኝ ባንተ ወረዳ እየተባባሉ ግጭት ከተጀመረ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ እስከ ዛሬዉ ቀን ሰዉ ከመሞትና ቤት ንብረት ከመቃጠልና ከመዘረፍ አልቆመም " ብለዋል።

እኚሁ የቤተሰባችን አባል ፤ በዞኑ እንዲሁም በክልሉ ያሉ አመራሮች ለችግሩ ምንም አይነት ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ እንዳልቻሉ ፤ ካቅማችን በላይ ነዉ ብለዉም ለከፍተኛ አካል ለፌደራል መንግስት የሰጡት / ያስረከቡት ነገር እንደሌለ አስረድተዋል።

ከሰሞኑንም በዚሁ ቀጠና ላይ የሰዎች ህይወት መቀጠፉን ንብረት መውደሙን አመልክተዋል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-29

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በአዲስ አበባ ሞተር ብስክሌት እስከ ረቡዕ ድረስ ታገደ።

የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ፤ በከተማው ለሚገኙ የሞተር ብስክሌተኞች በሙሉ ባስተላለፈው መልዕክት ከነገ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ እሮብ ነሀሴ 3/2015 ዓ.ም እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

ቢሮው ፤ ክልከላው በምን ምክንያት እንደተጣለ በግልፅ ያለው ነገር የለም።

ክልከላው #የፀጥታ እና #የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት መሆኑን የገለፀው ቢሮው ፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ቢሮው አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዜዳንቱና ልኡካቸው ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት ሲደርሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሁለቱም በኩል ያሉ ባለስልጣናት የንግድ ትብብርን በተመለከተና በድንበር #የፀጥታ እና #ደህንነት ጉዳዮች (በሶማሌ ክልል እና በሶማሌላንድ) ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እውን ያደርጋል የተባለለንትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤስአርቲቪ ሶማሊኛ ክፍል ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia