TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
60.8K photos
1.54K videos
215 files
4.23K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትሊዴፓ " ከብልጽግና ጋር ልክ እንደሌሎቹ በአገር ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተባብሮ ለመሥራት ይችላል እንጂ የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ገለልተኛ እና ነጻ ፓርቲ ነው " - የቀድሞ የህወሓት አመራር በጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ከህወሓት የተከፈለው ቡድን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም በሂደት ላይ መሆኑን ከአመራሮቹ መካከል አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ…
#Tigray

" የትግራይ የፖለቲካ ቀውስ ወደ ባሰ ሁኔታ በማምራት አሸናፊና ተሸናፊ ሳይኖረው ትግራይንና ህዝብዋ ወደ ከፋ ሁኔታ እየመራ ነው " ሲል የትግራይ ስቪል ማህበራት ጥምረት ስጋቱ ገለፀ፡፡

ጥምረቱ ባወጣው መግለጫ " የትግራይ የፖለቲካ ምህዳር በመበላሸቱ ምክንያት በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚኖር ትግራዋይ አንደነት ላይ ሳንካ ፈጥሯል " ብሏል።

" በጣም የከፋ ፖለቲካዊና ጠባብ አስተሳሰብ አንሰራፍቷል " በማለት ስጋቱ የገለፀው ጥምረቱ ፣ " አሁንም ሁነኛው መፍትሄ ሁሉን አቀፍ አሳታፊ ውይይት በማካሄድ ልዩነት በሰለጠነ መንገድ መፍታት ነው መፍትሄው " ሲል ገልጿል።

የጋራ መግባባት ላይ እንዲደረስ የሚያግዝና የሚያስችል ብሄራዊ ውይይት በአሰቸኳይ እንዲጀመር  " በድጋሜ ጥሪ አቀርባለሁ " ብሏል።

" በአዲሱ ጊዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመው ካቢኔ አቃፊና አሳታፊ አይደለም " ሲል የተቸው ጥምረቱ ፣ " አወቃቀሩ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ የሚያባብስ በመሆኑ ተዋፅኦው ከአሁኑ መታረም አለበት " ሲል አሳስቧል።

" በነባሩ ጊዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመው ጊዚያዊ ምክር ቤት አዲሱ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲያስቀጥለውና ፣ የህዝብንና የአገር በጀት በታለመለት ስራ ላይ እንዲውል የመቆጣጠር ስልጣኑ እንዲወጣ ይፈቅድለት " ብሏል።

የትግራይ ሲቪል ማሕበራት ጥምረት ከ120 በላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ማህበራት ያቀፈ ፣ የቆይታ ጊዜው ባጠናቀቀው በፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተመራው ጊዚያዊ አስተዳደር በተቋቋመው ጊዚያዊ ምክር ቤት ውክልና ያለው መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
" የፊታችን እሁድ ነበር ሰርጉ፣ ተኩሰው ገደሉት። ጅብ በልቶት የተገኘው በጣም ጥቂት አካሉ ነው " - የሟች የቅርብ ሰው

ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ስሬ ወረዳ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ ታጣቂዎችግድያና እገታ ፈጽመዋል።

እገታውን ተፈጸመ የተባለው ከአዳማ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኝ በተለምዶ " ቀለጣ ወንዝ " ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በርካታ ተሳፋሪዎች ታግተው እንደተወሰዱ፣ ሰሞኑን ሊዳር የነበረ ሙሸራ እንደተገደለ፣ ታጋቾች ራቅ ያለ ቦታ ተወስደው ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መሆኑን፣ ከታጋቾች መካከል የተለቀቁም እንዳሉ ነዋሪዎች ነግረውናል።

ሟችን፣ ታጋቾችን በቅርበት የሚያውቁ አንድ አካል በበኩላቸው፣ " ሁሌም ሰኞ፣ ሰኞ ከስሬ ወደ አዳማ ምልልስ የሚበዛበት የገበያ ቀን ነው። ከስሬ ወደ አዳማ በሚሄድ ቅጥቅጥ አይሱዙ ተሳፍረው ከነበሩ ሰዎች የተወሰኑ ሰዎችን መርጠው ወስደዋቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሟቹንም ልጅ አውቀዋለሁ " ያሉት እኚሁ አካል ታጣቂዎቹ ተኩሰው እንደገደሉት ከእገታ የተለቀቁ ልጆች መናገራቸውን አስረድተዋል።

" ሟቹ ጅብ በልቶት የተወሰነ እጅና የተወሰነ ቁርጥራጭ አካሉ ነው የተገኘው። በማግስቱም ተኩስ ስለነበረ ሌላም ሰው ሞቶ እንደሚሆን ተሰግቶ ነበር " ሲሉም ተናግረዋል።

ከእገታ የተለቀቁት የተወሰኑ ታጋቾች ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ በመሆናቸው ለሚዲያ ማብራሪያ ለመስጠት እንደሰጉ፣ ከ50 ከተሳፋሪዎቹ መካከል 25 ወንድና ሴቶች ተመርጠው እንደታገቱም እኚሁ አካል ነግረውናል።

" ሟቹ የፊታችን እሁድ ነበር ሰርጉ፣ ተኩሰው ገደሉት። ጅብ ልቶት የተገኘው በጣም ጥቂት አካሉ ነው። ለወላጅ ስነ ልቦና ሲባል ህዝቡ ተሰብስቦ የተገኘውን ቀብሯል። ስሬ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ረቡዕ ቀብሩ ተፈጽሟል " ነው ያሉት።


በእገታው ተወሰዱ ስለተባሉ ተሳፋሪዎች ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሙከራ ብናደርግም ቢሮው የስልክም ሆነ የመልዕክት ምላሽ አልሰጠም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መምህሯ ላይ እምርጃ ወስደናል " - ትምህርት ቢሮ " የቤት ስራ አልሰራሽም " በማለት ተማሪዋን ተገቢ ያልሆነና አጸያፊ የሆነ ቅጣት የቀጣችው መምህርት ከስራ ታግዳ በህግ ቁጥጥር ስር ተደረገች። የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከተማ በሰላም በር ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት ቤት የ2ኛ ክፍል ተማሪን " የቤት ስራ አልሰራሽም " በማለት ተገቢ ያልሆነ ቅጣት በፈጸመችው…
" አስተማሪ ተማሪውን የመምታት መብት የለውም በተማሪዋ ላይ ያደረሰችው ቅጣት ቀላልም ቢሆን እንኳ የአካል ጉዳት በማድረስ በህግ ያስጠይቃታል " - የህግ ባለሙያ

" የቤት ስራ አልሰራሽም " በማለት የሁለተኛ ክፍል ተማሪዋን ተገቢ ያልሆነና አጸያፊ የሆነ ቅጣት የቀጣችው መምህርት ከስራ ታግዳ በህግ ቁጥጥር ስር መደረጓ መገለፁ ይታወሳል።

በመሆኑም መምህርቷ በተማሪዋ ላይ የወሰደችው እርምጃ በህገመንግስቱ አንደት ይታያል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ጠይቋል።

የህግ አማካሪና ጠበቃ ሳሙኤል ግርማ መምህርቷ የወሰደችው እርምጃ " ቀላል የአካል ጉዳት በማድረስ በወንጀል ህጉ 5/ 35 እስከ 3 አመት ፅኑ እስራት ቅጣት " ሊጠብቃት አንደሚችል ተናግረዋል።


የህግ ባለሙያው ምን አሉ ?

" አስተማሪ ተማሪውን የመምታት መብት የለውም በተማሪዋ ላይ ያደረሰችው ቅጣት ቀላልም ቢሆን እንኳ የአካል ጉዳት በማድረስ በህግ ያስጠይቃታል፣ በወንጀል ህጉ ደግሞ 5/ 35 እስከ 3 አመት ያሳስራል፣ ይህ ድርጊት ግን ከዚህም ባለፈ ነው የሚታየው " ብለዋል።

አክለውም " በአስተማሪ የዲስፕሊን መመሪያ በአስተዳደራዊ እርምጃ ከስራዋ ልትሰናበት የሚያስችል ወንጀል ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

የህግ ባለሙያው " መምህሯ ቅጣት ያደረሰችባት ተማሪ ከ13 አመት በታች ታዳጊ ከሆነች ይሄ ተገቢ ያልሆነ እና በወንጀል የሚያስጠይቅ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" መምህሯ ተማሪዋን የመታችበት መሳሪያ ወይም ቁስ የቅጣቱን መጠን ይወስነዋል " ያሉ ሲሆን  በእንጨት፣ በድንጋይ እና በመሳሰሉት ሆኖ በልጅቷ አካል ላይ መፋፋቅ፣ መድማት የአጥንት መሰበር አይነት ጉዳት ከሆነ ያደረሰችባት ከዚህም ከፍ ያለ ቅጣት ሊጠብቃት እንደሚችል ጠቁመዋል።

በተለይም መምህር፣ ሹፌር እና ሀኪሞች በስራ ያገኟቸውን ሰዎች የበለጠ የመጠበቅ ሃላፊነት አለባቸው። ይሄም እንደ ወንጀል ማክበጃ ይታያል ብለዋል።

የህግ ባለሙያው ሳሙኤል ይሄ ጉዳይ ይፋ መደረጉ እና በመምህርቷ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ለሌሎች አስተማሪዎች መማሪያ የሚሆን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

" በመጨረሻም አሁን ላይ ተማሪዎችን አንደድሮው አይነት ቅጣቶች መቅጣት አይቻልም፣ ምክንያቱም  ከህፃናት መብት ጋር የሚጣረስ ነው " ሲሉ አመላክተዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ብስክሌት #ስኩተር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብ ቁጥር 183/2017 ምን ይላል ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስፋፋት እየሰራ እንደሆነ አመልክቷል።

ይህንንም ለማድረግ በኮሪደር ስራዎች ለሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መንገዶች መሰራታቸውን ጠቁሟል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብ ይፋ አድርጓል።

ደንቡ ምን ይላል ?

በብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የሚሰራ ሰው " የኦፕሬተርነት የሥራ ፈቃድ " ማውጣት ይጠበቅበታል።

በኦፕሬተርነት ሥራ ለመሰማራት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የሥራ ፈቃድ ለማግኘት የተለያዩ መስፈርቶች ማሟላት አለበት።

ከነዚህም ውስጥ አንዱ የብስክሌት ወይም ስኩተር ብዛትን ይመለከታል።

ፈቃድ ለማግኘት ብዛቱ 300 (ሦስት መቶ) እና ከዚያ በላይ የብስክሌት እና/ወይም ከ100 (አንድ መቶ) የማያንስ ስኩተር ለአገልግሎት ማቅረብ መቻል ይኖርበታል።

እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ ጂፒኤስ ያለው ወይም የተገጠመለት ብስክሌት ማቅረብ መቻል ይኖርበታል።

የኦፕሬተርነት ፈቃድ ለማግኘት፣ ለማሳደስ ወይም ለመቀየር  የአገልግሎት ክፍያ አለው። በዚህም ፦
- የኦፕሬተርነት የሥራ ፈቃድ ለማግኘት ብር 8,000.00 (ስምንት ሺህ ብር)፤
- የኦፕሬተርነት የሥራ ፈቃድ ለማደስ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፤ ወይም
- የጠፋን የኦፕሬተርነት የሥራ ፈቃድ ለመተካት ብር 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) መክፈል አለበት።

ለብስክሌት መጋራት አገልግሎት የክፍያ ታሪፍም ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ደንቡ ስለ ተጠቃሚዎች ምን ይላል ?

እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት በብስክሌት መስመሩ የሚገለገሉት ከወላጆቻቸው ወይም ከአሰዳጊዎቸቸው ጋር ሲሆኑ ብቻ ይሆናል።

ከኦፕሬተሩ አገልግሎት የሚያገኝ ተጠቃሚስ ?
➡️ የሚመቸውን የብስክሌት አይነት የመምረጥ መብት አለው።
➡️ የቴክኒክ ችግር ሲገጥም በመተላለፊያ ጣቢያ ላይ ከሚገኘው ብስክሌት በመቀየር ጉዞውን የማጠናቀቅ መብት አለው።

ደንቡ ተጠቃሚዎች ተጨማሪ ሰው መጫን እንደማይችሉ ይገልጻል።

ኦፕሬተር ለአገልግሎት የሚያቀርበው ብስክሌት ምን አይነት ነው ?

ብስክሌቱት የተመረተበት ዘመን ከሁለት ዓመት ያልበለጠ መሆን አለበት።

የብስክሌቱ ዓይነት ሃይብሪድ፣ በኤሌክትሪክ ባትሪ ወይም በማንዋል የሚሰራ መሆን እንዳለበትም ተገልጿል።

የብስክሌት የቀለም ዓይነት አንድ ወጥ ሆኖ ከሌላው ኦፕሬተር ጋር የማይመሳሰል፤ መሆን አለበትም ይላል ደንቡ።

ከዚህ ባለፈ አንድ ኦፕሬተር የኦፕሬተርነት ፈቃድ ከተሰጠበት አገልግሎት እና የጉዞ መስመር ውጪ መስራት አይችልም።

ደንቡ ተጠቃሚዎችን ምን ይከለክላል ?

- ተፈቀደው የመጫን አቅም በላይ መጫን፤
- ብስክሌት እየነዱ መመገብ፣ መጠጣት፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀም፣ ማጨስ፤
- ከኦፕረተሩ የተከራየ ተጠቃሚ ከስምምነት መስመር ውጪ መጋለብ፤
- የሌሎች ብስክሌት መንገድ ተጠቃሚዎችን እንቀስቃሴ ማወክና ለአደጋ በሚጋብዝ መልኩ ብስክሌት መጋለብ፤
- የብስክሌቱን መሪ ለቆ ወይም የብስክሌቱን መሪ በእግር ይዞ መንዳት፤
- በእንቅስቃሴ ወቅት የብስክሌት መስመሩን ለሚያቋርጡ ተሽከርካሪዎች፣ እና ለእግረኛ ቅድሚያ ያለመስጠት፤
- አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ በብስክሌቱ ወይም በብስክሌት መስመሩ ላይ መጋለብ ይከለክላል።

ደንቡ ስለ ቅጣት ምን ይላል ?

ማንኛውም ኦፕሬተር፡-

➡️ ጂፒኤስ ሳይገጠም ወይም በማይሰራ ጂፒኤስ አገልግሎት የሰጠ እንደሆነ 3,000 ብር ይቀጣል።
➡️ ከፀደቀው ታሪፍ በላይ ካስከፈለ 3,400 ብር ቅጣት ይጠብቀዋል።
➡️ በብስክሌቱ ላይ ተጨማሪ ሌላ አካል መግጠም 5,000 ብር ያስቀጣል።
➡️ የኦፕሬተርነት ሥራ ፈቃድ ሳይኖር ወይም ሳያሳድስ አገልግሎት መስጠት 10,000 ብር ያስቀጣል።
➡️ ያልተፈቀደ የብስክሌት ቀለም ቀብቶ አገልግሎት መስጠት 10,000 ብር ያስቀጣል።
➡️ ሌላ ኦፕሬተር የሚጠቀምበትን መለያዎች መጠቀም 10,000 ብር ያስቀጣል።
➡️ የኦፕሬተርነት አገልግሎትና ከተሰጠበት አገልግሎት እና የጉዞ መስመር ውጭ መስማራት 10,000 ብር ያስቀጣል።

ማንኛውም ተጠቃሚ ፡-

🔴 ከተፈቀደው የመጫን አቅም በላይ ጭኖ ቢገኝ 600 ብር ይቀጣል።
🔴 ብስክሌት እየነዱ መመገብ፣ መጠጣት፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀም፣ ማጨስ 500 ብር ያስቀጣል።
🔴 ከኦፕሬተሩ የተከራየ ተጠቃሚ ከስምምነት መስመር ውጪ ከጋለበ 1,500 ብር ይቀጣል።
🔴 የሌሎች ብስክሌት መንገድ ተጠቃሚዎችን እንቀስቃሴ ማወክና ለአደጋ በሚጋብዝ መልኩ ብስክሌት መጋለብ 500 ብር ያስቀጣል።

(ሙሉ ደንቡ ከላይ ተያይዟል ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)፣ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር) እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለመገኘት እንዲችሉ መንግሥት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ አሳወቀ።

መንግሥት ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፥ " ከዚህ በፊት አንዳንድ ወገኖች በፈጠሩት ችግር የተነሣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጉባኤ ለመሳተፍ ላልቻሉ ሦስት አባቶች ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን አሳውቃለሁ " ብሏል።

በመግለጫው ፤ ሀገራዊ ተቋማት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸውን የላቀ ሚና በመረዳት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት እንዲፈታ የመሪነቱን ሚና መጫወቱን አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ግንባታ የነበራትንና የሚኖራትን ሚና በመገንዘብ አስፈላጊውን ድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱን በዚህ አቋሙም እንደሚቀጥል ገልጿል።

" ይሄንን ያልተረዱ አንዳንድ አካላት ችግሮችን ፈጥረው የነበረ ቢሆንም እንኳን፣ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያንዋ እና ለምእመንዋ ሲል በሆደ ሰፊነት ለማለፍ ወስኗል " ብሏል።

መግለጫው " አንዳንድ አካላት " ያላቸውን እና የፈጠሩትን ችግሮች በግልጽ ያላብራራ ቢሆንም ችግሩ እንዲፈታ ሲኖዶሱ ጥያቄ ማቅረቡንና ይህንንም ጥያቄ መቀበሉን ይፋ አድርጓል።

" በሂደቱም ተቀራርቦ መነጋገር ከሁሉም የተሻለ የመፍትሔ መንገድ መሆኑ ታይቷል " ብሏል።

ሲኖዶሱ መንግሥት ነገሩን በሆደ ሰፊነት እንዲመለከተው እንደጠየቀና በዚህም ሶስቱ ብፁአን አባቶች ወደ ሀገራቸው ገብተው በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለመገኘት እንዲችሉ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ሰሌዳ

በኢትዮጵያ የተሽከርካሪ ሰሌዳ (ታርጋ) ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ጸድቋል።

መመሪያው የተሸከርካሪ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ ዓይነቶችና ምልክቶች መወሰኛ እና የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 1050/2017 ነው።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አማካሪ ከድልማግስት ኢብራሂም፤ " የሰሌዳ ለውጡ ዋና ምክንያት ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ታሳቢ ያደረገ ሰሌዳ እንዲኖር ለማስቻል ነው " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ፦
- የአመራረት እና አሰረጫጨት ችግር፣
- የአወጋገድ ችግር፣
- የአሰራር ክፍተት፣
- የሀብት ብክነት፣
- በሲስተም የተደገፈ ስራ አለመኖር ችግር እንደነበር ጠቁመዋል።

ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ጋር ተያይዞ የዕለት የተላላፊ እና የቋሚ መለያ ቁጥር ሰሌዳ አገልግሎት አሰጣጥ ለፎርጅሪ ለብልሹ አሰራር ለበርከታ ወንጀሎች የተጋለጠ በመሆኑ ይህ መመሪያ ችግሩን ይቀርፋል ሲሉ አስረድተዋል።

" መመሪያው በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በተመዘገቡና ለምዝገባ በሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች፣ በተሽከርካሪ አምራች /አስመጪ/ገጣጣሚ ድርጅቶች፣ በተሽከርካሪ መዝጋቢ አካላት እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት እና በግለሰቦች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል " ብለዋል።

የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ዓይነቶች እና ምልክቶች ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ አገልግሎት ይዘት በዓይነት እና በመጠን ወጥ እንዲሆን ለማድረግ፣ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ ምርት ስርጭት አወጋገድ የተሸከርካሪ መረጃ አያያዝ ቁጥጥሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድርግ የመመሪያው ዓላማ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

@tikvahethiopia