TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዘመኑ የይቅርታ ነውና በመሪነት ዘመንህ ለሰራኸው በጎ ስራ #እናመሰግናለን ለተፈፀሙ ጥፋቶችም በታላቅ ፍቅር #ይቅርታ አርገንልሀል!

ትንሽ የይቅርታ ልብ ያለን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወጣት ናዝራዊት...🔝

የናዝራዊት አበራ ታላቅ ወንድም #ያይራድ_አበራ እናታቸው በፍፁም ሰላም እና ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ናዝራዊት ቻይና #ጉዋንዡ ከተማ እንደምትገኝ፣ የኢትዮጲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠበቃ ቀጥሮ እየተከራከራከሩ እንደሆነ ገልጾ ጉዳዩም መልካም ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። የፍርድቤት ውጤት ክትትል ላይ ነን #በፀሎት እርዱን ሲልም ጠይቋል።

በፌስቡክ ላይ የሚሰራጨው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው፤ ህዝቡም በጭንቀት እነደሆነ ይህን የሚያደርገው ተረድተናል! #በቤተሰቦቿ ስም #እናመሰግናለን ብሏል!

በተጨማሪ Yayehyirad Aberra በፌስቡክ ገፁ ይህን መልዕክት አስተላልፏል👇

"Dear all I would like to #appreciate your effort to help my sister and our family by putting a pressure on social media. Unfortunately it is not helping both the case and the families. As much as possible please #stop sharing or signing petitions that is not initiated by the family or her lawyer. And please remove all posts on your page regarding the case. On behalf of our family, I appreciate you share this message as much as possible. Thank you"

Via Dagim Worku
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WKU እጅግ በጣም እናመሰግናለን፤ ያደረጋቹልን ታሪካዊው የአቀባበል ሁሌም በአባላቶቻችን ዘንድ ሲታወስ ይኖራል። የመጣንበትን አላማ እንዲሰካ ለማድረግ የደከማችሁ ቅን ሰዎች እናመሰግናለን!! መላው የተቋሙን አመራሮች፤ ሰራተኞች እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጠቅላላ #እናመሰግናለን!! የተማሪዎች ህብረቱ በ3 ቀን የእንመጣለን መልዕክት ዝግጅት አድርጎ በትልቅ ክብር ስለተቀበለን እናመሰግናለን!!

#ፍቅር_አሸንፏል!!
የጥላቻ ንግግር ይቁም!!
የጥላቻ ንግግር ሀገር ያፈርሳል!!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ሳምንት🔁 #StopHateSpeech!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አሜን_መሀመድ ተገኝቷል! ሁላችሁም ላደረጋችሁት #ትብብር ቤተሰቦቹ ከልብ #አመስግነዋችኃል!! #እናመሰግናለን!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
√ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
√ወሎ ዩኒቨርሲቲ
√ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ #እናመሰግናለን!!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ እየመጣን ነው!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር ክንደያ👆

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላትን የመቐለ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ስራዎች በትዊተር ገፃቸው በየሰዓቱ ለህዝብ ሲገልፁ ስለነበር እንዲሁም በግቢው ቆይታችን መስተንግዶው የተመቻቸ እንዲሆን ስላደረጉ #እናመሰግናለን!!

@tsegbwolde @tikvahethiopi
እናመግናለን!! #ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ላደረጋችሁት አቀባበል፤ ከልብ #እናመሰግናለን!!

ፍቅርን፤ ሰው ማክበርን አስተምራቹናልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ❤️የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላም ተቋም!! ላደረጋችሁልን ፍቅር የተሞላበት አቀባበል #እናመሰግናለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለደሴ ሳፋ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት የአካባቢ የወል ንግድ ምልክትና እውቅና ተሰጥቷል። የወሎ ጋቢ ደግሞ ከሀምሌ 27/2011 በኃላ እውቅና ሊያገኝ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

#እናመሰግናለን~አቶ እንዳልካቸው አበበ

ቀደም ብሎ የቀረበው መረጃ #የስም_መቀያየር የነበረበት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን!! /መረጃው ላይ #ማስተካከያ የሰጡት እንዳልካቸው አበበ የወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የብራንዲንግ አስተባባሪ ናቸው። በTIKVAH-ETH ስም እናመሰግናለን!!/ እንደምንጭነት የተጠቀምነው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሲሆን ይህን ማስተካከያ እነሱም እንደሚወስዱ እና መረጃው ላይ ያለውን የስም መቀያየር እንድሚያርሙ እምነት አለን።/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአጠቃላይ እያቀረባችሁ ያለውን ቅሬታ በገፃችን ላይ ለማቅረብ ተሞክሯል፤ የሁላችሁንም ቅሬታ እዚህ ለማስነበብ ጊዜም አይበቃንም እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች እንዳይቀርቡ ያደርጋል። በመሆኑንም በፈተናው ውጤት ላይ ቅሬታ አለን የምትሉና እስካሁንም ቅሬታችሁን ያሰማችሁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ይህንምልክት በመጫን የሚመለከተው አካል እንዲያየው ድምፅ ስጡበት።

🏷እኛም የሚመለከታቸው አካላት ስለጉዳዩ የሚሰጡት አስተያየት ካለ የምናቀርብ ይሆናል። #እናመሰግናለን

#TIKVAH_ETHIOPIA_FAMILY
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሃዊ_ጉዲና

ይህ የምትመለከቱት ጅማ ከተማ የሚገኝ "ሀዊ ጉዲና" የተባለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤቱ የተሰራው በህብረተሰቡ ርብርብ ሲሆን ተማሪዎች ሲማሩበት የነበረው እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው። የመማሪያ ክፍሎቹ ደረጃቸውን የጠበቁ ባለመሆናቸው ሀገር ተረካቢዎቹ ትምህርታቸው ላይ ተፅእኖ ሲያሳድር ቆይቷል። ነገር ግን አሁን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የጅማ ከተማ ተወላጆች በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን አስገንብተው የፊታችን እሁድ ነሃሴ 26 ያስመርቃሉ።

🏷እነሱ በውጭ ሀገር ሆነው ይህን ለሃገራቸው ካደረጉ እኛ እዚሁ ኢትዮጵያ ያለን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ደግሞ በጅማ ከተማ የሚሰባሰበውን የመማሪያ መፅሃፍ ለዚህ ትምህርት ቤት በማስገባት ለቀጣይ ትውልድ መልካም ስራን ሰርተን እናሳያለን!

•በሰሜን አሜሪካ የምትገኙ የጅማ ከተማ ተወላጆች ላደረጋችሁት ነገር በTIKVAH-ETH ስም #እናመሰግናለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ባነር የተለጠፈው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ ነው

"የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ እንኳን ደህና መጡ! ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እያበረከቱት ላለው ጉልህ አስተዋፆ #እናመሰግናለን!" ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

Via AB/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እናመሰግናለን!

ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እና የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ለዚህ መርኃግብር መሳካት የድርሻችሁን ለተወጣችሁ ለመልካሙ ሀሳብ መልካምነታችሁን ለገለጻችሁ በሙሉ የዚህ ዝግጅት መሳካት ክብሩ የእናንተ ነውና ክብር ይገባችኀል፡፡

በተለይ ባስፈላጊው ነገር ሁሉ ላልተለየው ድጋፋቸው የጋሞ ዞን አስተዳደርን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ለዚህ ስራ ብዙ ድጋፍ ያደረጉ አካላትንም ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ በተለይም ኃይሌ ሪዞርት፣ ኦሞቲክ ጀነራል ትሬዲንግና ዊዝደም አካዳሚ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ዲዛይነሮቻችን፦
•ፌቨን ደረጀ
•በረከት መንግስቱ
•ሂሩት ታዬ
•ሄርሜላ ተሾመ
•ቅዱስ ዮሐንስ

ሳውንድ ሲስተምና ዲኮር፦
•ሙሉቀን መሉ የሳውንድ ሲስተምና ዲኮር ስራ

#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል

በቀጣይ በሌሎች የሀገራችን ከተሞች ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች (ከወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ከአባ ገዳዎች ጋር ተመሳሳይ መድረኮችን እያዘጋጀን የምንመክር ይሆናል። እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ጋር ተመሳሳይ ዝግጅቶችን ይኖሩናል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠናቋል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው 5ኛ ዓመት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱ ታሽጎ ተልኳል። ካለው የተማሪ ቁጥር አንፃር  ማድረግ የቻልነው እጅግ ጥቂት ቢሆንም በቀጣይ ወራት ተጨማሪ ዘመቻ በማድረግ ከቤተሰባችን አባላት ቤት መፅሀፍ በመውሰድ ተጨማሪ ለመላክ ጥረት እናድረጋለን። በዚህ ስራ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያለማንም…
#እናመሰግናለን

በኮቪድ ወረርሽኝ እንዲሁም በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍትን ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱን ለት/ቤቶች አድርሰናል።

በአጠቃላይ የተሰበሰበው መፅሀፍ እንዲከፋፈል ያደረግነው ፦

- መርሳ 2ኛ ደረጃና ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ፣ ውርጌሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሲሪንቃ ሁለተኛ ደረጃ እና ሙሉ ሳይክል ት/ቤት እነዚህ በአማራ ክልል በጦርነት ቀጠና የነበሩ ት/ቤቶች ሲሆን የመማሪያ መፅሀፍት እጥረት እንዳለባቸው ከአካባቢው ቤተሰቦቻችን በደረሰን መረጃ ለሶስቱም ከተሰበሰበው መፅሀፍ አከፋፍለናል። ለእነዚህ ት/ቤቶች በቀጣይም ተጨማሪ ለመላክ ታቅዷል።

- ዶሮ ግብርና ወደዪ ሜዳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አጋዥ እና በቀድሞው ካሪኩለም የታተሙ መፅሀፍትን የላክን ሲሆን በአዲሱ ካሪኩለም የታተሙትን ኮፒ ለመላክ እየተዘጋጀን ነው። በተላኩት መፅሀፍት ውስጥ የልጆች መማሪያ የሚሆኑ የተረት መፅሀፍት አሉበት።

- ማላካ ፣ ኢርባኖ ፣ ህዳሴ የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ት/ቤቶቹ የሚገኙት በደቡብ ክልል ከጅንካ ከተማ በ50 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ሲሆን በስፍራው ያሉ ቤተሰቦቻችን በመማሪያ መፅሀፍ ግብዓት እጥረት ሳቢያ በት/ቤቶቹ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና የሚፈለገውን ያህል ውጤት አይመዘገብም ብለውናል። በዚህም ለሶስቱም ከተሰበሰበው መፅሀፍ በማካፈል ልከናል። ካለው ተማሪ ብዛት በቀጣይ ዙርም ተጨማሪ ለመላክ አቅደናል።

- ቤተሰብ የህዝብ ቤተመፅሀፍ አ/አ ከተማ መካኒሳ አካባቢ የተከፈተ አዲስ ቤተመፅሀፍ ሲሆን መፅሀፍ እንደሚያስፈልጋቸው በገለፁልን መሰረት ተመልክተን ከተሰበሰበው መፅሀፍ አካፍለናል ፤ በተጨማሪ 10 ሺህ ብር ሰጥተናል። በቀጣይ ተጨማሪ መፀሀፍ ለመስጠት ታቅዷል።

- ፈንታው ድንቁ መታሰቢያ አፀደ ህፃናት እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #ቆቦ የሚገኝ ሲሆን በጦርነት ወቅት ለህትመት የሚገለገሉበት ኮምፒዩተር በመሰረቁ 2 ኮምፒዪተርና መፅሀፍትን ልከናል።

(መፅሀፍቱ የተበረከተው ከአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ነው፤ መፅሀፍ ያበረከቱ ቤተሰቦቻችን ስም ዝርዝራቸው በ @tikvahuniversity ላይ ይገኛል ፤ በዚህ ዙር በየቤቱ እየተኬደ ከተሰበሰበው መፅሀፍ በተጨማሪ ከመቶ ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መፅሀፍት በቤተሰቡ ስም ተገዝተው ተጨምረዋል)

ያጋጠሙ ችግሮች ፦ በዚህ ዙር #በየቤቱ መፅሀፍ ለማሰባሰብ እንዲሁም መፅሀፉን ለመላክ ከገጠመ የትራንስፖርት ችግር ውጭ ሁሉንም በቤተሰቡ አቅም ለማድረግ ተሞክሯል።

በቀጣይ ፦ አሁን የጎደሉትን መሙላት እና ተጨማሪ መላክ እንዱሁም በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለመድረስ ታስቧል።

ከአንድ ወር በኃላ በድጋሚ ሌላ ዙር በየቤቱ መፅሀፍ ለማሰባሰብ የሚሰራ ሲሆን በዚህ ዙር በቲክቫህ ላይ ማስታወቂያ የሚያሰሩ / መልዕክት የሚያስናግሩ ሁሉም ድርጅቶች የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያደርጋቸው የማስታወቂያ / መልዕክት ለቤተሰቡ መላኪያ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል።

ከመማሪያ መፅሀፍ በተጨማሪ ፦

👉 #ንፁህ_ወረቀቶችን (ኮፒ ለማድረግ) ፣ 
👉 ያገለገሉ በየቤቱ ያሉ ኮምፒዩተሮችን ፣ ታብሌቶችን
👉 ከከተማ ለወጡት ትምህርት ቤቶች ከመማሪያ መፅሀፍ በተጨማሪ አስተማሪ እና ጥላቻ የማይዘሩ የልብ ወለድና ሌሎች መፅሀፍትን የምናሰባስብ ይሆናል።

(ከዚህ ቀደም በነበሩ 4 ዓመታት በየዓመቱ የነበረውን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባለው ችግር በየአንድ እና ሁለት ወር ለማድረግ ይሰራል)

እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የምናድረገው እጅግ በጣም ጥቂት ቢሆንም ይህን ለማስፋት እንሰራለን ፤ ሁሉም በያለበት #የራሱን ጥቂት አስተዋፆ ማድረግ ከቻለ ብዙሃንን መድረስ ይቻላል። ለማድረግ አቅም ቢያንሰን እንኳን ለወገናችን በጎ በማሰብ ችግሩን እንካፈለው።

#TikvahFamily❤️
0919743630
0703313630

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT