TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ረመዷን

በመላው ዓለም ላይ የሚታወቁት የዝምባብዌ ዜግነት ያላቸው የእስልምና መሁር ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ስለ ቅዱሱ የረመዷን ወር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ፦

ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦

" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።

ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤  ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "

መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን እንመኛለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ትንሳኤ

እንኳን አደረሳችሁ !

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !

መልካም በዓል !
#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት መለዋወጫ !

ከዚህ ቀደም ተከፍተው አገልግሎት ላይ የነበሩት የመልዕክት መቀበያዎች በተደጋጋሚ በቴሌግራም ቴክኒንክ ችግር አገልግሎታቸው እየተደነቃቀፈ ነው።

በዚህም ምክንያት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚመጡትን መልዕክቶች ለማግኘት ችግር ሆኗል ፤ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ችግሩን ለመቅረፍ እና በየትኛውም መልኩ ነፃነቱ የተጠበቀ ለቲክቫህ አባላት ብቻ የሚያገለግል የሀሳብ መለዋወጫ በቅርቡ ይፋ የምናደርግ ሲሆን እስከዛው ድረስ ግን በዚህ አዲስ መልዕክት መቀበያ ላይ ብቻ መልዕክት ማጋራት ይቻላል  👉@tikvah_eth_BOT

በተጨማሪ @tikvah_Ethiopia_Fam ወይም ደግሞ 0703313630 መደወል ይቻላል።

በቲክቫህ ቤተሰብ ውስጥ ማስተላለፍ የሚቻሉ መልዕክቶች ምን አይነት ናቸው ?

- የፀጥታ ችግሮች፣ የደህንነት ስጋቶች፣ የወንጀል ድርጊቶች በመንግስት አካላት / ተቋማት የሚፈፀሙ ማንኛውም አይነት አስተዳዳራዊ በደሎች፤
- የየመንገድ ፣ የውሃ፣ እንዲሁም የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚና የሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎች፤
- በግልም ሆነ በጋር የማያጋጥሙ ችግሮች፣ ሊበረታቱ የሚግባቸው ተግባራት፣
- ለሀገር እና ለትውልድ ጠቃሚ ናቸው የሚባሉ ሃሳቦችን፣
- የእርስ በእርስ እገዛዎች ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች፣
- ጥቆማዎችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ይሄ ነገር ለቤተሰቡ ቢጋራ መልካም ነው የምትሉትን (ዜና ፣ መረጃ) ሁሉ ማቅረብ ትችላላችሁ።

ምን መላክ አይቻልም ?

ስድብ፣ የጥላቻ ንግግር ፣ የማንኛውም የግለሰብ ማንነትን በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካ ፣ ህዝብን በጅምላ የሚፈርጅ፣ ፣ ህዝብ ላይ ጥላቻን የሚያሰርፅ፣ ሀገር ሊያስጣ የእርስ በእርስ ግጭት የሚያባብስ፣ ሀሰተኛ መረጃ ፅሁፍ / መልዕክት መላክ በፍፁም አይቻልም። በየትኛውም አካል ላይ ትችትም ይሁን ቅሬታ ለመግለፅ የሚፈልግ የቤተሰቡ አባል የሚጠቀማቸውን ቃላት የመምረጥ ግዴታ አለበት።

ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም መልዕክት ስትልኩ የራሳችሁ የግላችሁ መልዕክት መሆኑን በማስረጃ አስደግፋችሁ ላኩልን። እናተ ያላረጋገጣችሁትንና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስላያችሁት የራሳችሁ በማስመሰል ማንኛውም መልዕልት መላክ ፍፁም አይቻልም።

ማስታወሻ ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት #በፌስቡክ#ዩትዩብ#ቲክቶክ ላይ ምንም አይነት የመሰባሰቢያ መድረክ (ገፅ) የላቸውም።

ትዊተር ፦ https://twitter.com/tikvahethiopia?t=jZrpieALuIGzw6OM-HWgEw&s=09

ሀሳባችን ስንገልፅ ቃላትን እንምረጥ !!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ!!
#TikvahFamily

@tikvah_eth_BOT
#ዒድ_አልፈጥር

ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በችግር ላይ የወደቁትን ፤ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በጦርነት እና በግጭት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣ ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩ ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
መልካም በዓል !

ፎቶ፦ አቤል ጋሻው (ፋይል)

#TikvahFamily ❤️

@tikvahethiopia
#ትዊተር

ለጥንቃቄ ...

የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች እና ተቋማት #የማረጋገጫ_ምልክት ከትላንት ጀምሮ ተነስቷል።

ታዋቂው ቱጃር ኤሎን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ከገዛው በኋላ በመተግሪያው ላይ የመጡ ለውጦች በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ እየሆኑ ይገኛል።

ከዚህም ውስጥ አንዱ ትዊተር ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠውን የማረጋገጫ መልክት (Twitter verification) በክፍያ መጀመሩ ዋነኛው ነው።

ለግለሰብ በወር 8 ዶላር ለድርጅት ደግሞ 1000 ዶላር ማስከፈል የጀመረው መተግበሪያው ከትላንት ጀምሮ ክፍያ ያልፈጸሙ ያላቸውን አካውንቶች የማረጋገጫ ምልክታቸውን አንስቷል።

የማረጋገጫ ምልክታቸው የተነሳው በሀገራችን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ታዋቂ ሰዎች ፣ የሚዲያ ተቋማት ፣ ትልልቅ የመንግስት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ መስሪያ ቤቶች ነው።

በርካቶች ይሄንን ውሳኔ  በተመሳሳይ ስም የሚከፈቱ " የማረጋገጫ ምልክት " የሚኖራቸው አካውንቶች እንዲኖሩ እድሉን ይከፍታል በሚል የተቃወሙት ቢሆንም ውሳኔው ግን ተግባራዊ ተደርጓል።

ይህም ሀሰተኛ መረጃን ያባብሳል ተብሎ ተሰግቷል።

በተለይ አሁን ላይ የማረጋገጫ ምልክቱን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ ለአጭበርባሪዎች (Scammers) በር በመክፈት በርካቶችን ሊጎዳ ይችላል።

የገጾችን ትክክለኛነት ለማሳየት የምንጠቀምበት ይህ የማረጋገጫ ምልክት ከዚህ በኋላ ለማረጋገጫነት ብዙም ጥቅም የሚኖረው አይመስልም።

የገጹ ተከታይ ብዛት እንደ ማረጋገጫ መውሰድ ብንችልም እንደ ሀገራችን የሀሰተኛው ገጽ ተከታይ ቁጥር ከትክክለኛው በሚበልጥበት ሁኔታ የገጹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥም አዳጋች ያደርገዋል።

ከዚሁ ከትዊተር ማረጋገጫ ምልክት መነሳት ጋር በተያያዘ ጦርነት ውስጥ ባለችው ሱዳን የሆነ አንድ ጉዳይን እናጋራችሁ።

በጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ (RSF) የትዊተር አካውንት ያለው ሲሆን አካውንቱም 82.7K ተከታይ እና የሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት ነበረው።

ትዊተር ትላንት ይህንን የማረጋገጫ ምልክት ባነሳበት ሰዓታት ውስጥ የሰማያዊ ምልክት #የገዛ በተመሳሳይ በRSF ስም የተከፈተ 26 ሺ ተከታዮች ያሉት ገፅ ጄነራል መሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) በጦርነቱ ላይ #እንደተሞቱ አድርጎ አንድ ፅሁፍ አስራጭቷል።

የዚህን የማረጋገጫ ምልክት ከትዊተር የገዛ ገፅ ያወጣውን ሀሰተኛ ፅሁፍ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች አይተውታል ፤ ይህን ሀሰተኛ ፅሁፍ ያመኑም አልጠፉም።

ውድ ቤተሰቦቻችን በትዊተር አዲስ አሰራር ሁሉም ሰው ሰማያዊ የማረጋገጫ ምልክት እየገዛ በመሆኑ የሰማያዊ ምልክት ያላቸው አካላት ናቸው የሚያሰራጩት በማለት ሁሉንም የምታዩትን መረጃዎች አትመኑ፤ መረጃዎችን መርምሩ፣ አጣሩ። እናመሰግናለን !!

#TikvahFamily

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
ሃሳብን መግለፅ ... በጥሩ ቃላት !

ሁሉም ሰዎች ከእኔ / እኛ ጋር አንድአይነት ወጥ የሆነ አመለካከት፣ አስተሳሰብ ይኖራቸዋል ብሎ መጠበቅ ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነው።

ነገር ግን ከእኛ ጋር የሚቃረን ሃሳብ በተመለከትን ወቅት ለዛ ግብረመልስ የምንሰጥበት መንገድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።

ይህን ለማለት መነሻ የሆነን የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፍፁም ከመስመር የለቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ነው።

እኛ ያልደገፍነው ወይም ከእኛ ጋር የማይስማማ / ያላሳመነን ሀሳብ ስንመለከተ ከሰዎች ጋር እልህ እና ንትርክ፣ ጥላቻ ውስጥ በማያስገባ ቃላት በመጠቀም ሀሳባችንን ብንገልፅ የተሻለ ነው።

ለምሳሌ ፦

አንድ የግለሠብ ሃሳብ / ማንኛውም አይነት ዜና / መረጃ / ንግግር በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ብንመለከት እና ያን ነገር ፍፁም በእኛ ዘንድ ተቀባይነት ባይኖረው እንዲህ በሚል ሃሳባችንን ብንገልፅስ ...

• ንግግሩ / መረጃው ሀሰት ከሆነ ፤ " ይህ ፍፁም ሀሰት ነው ፤ እኔ ይህ ሀሰት ስለመሆኑ በቂ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ " በሚል የኛን ማስረጃና ሃሳብ ማቅረብ።

• ሃሳቡን ካልደገፍነው / ካልወደድነው ፤ " እኔ ይህንን ሀሳብ በፍፁም አልደግፈውም / አልወደድኩትም ምክንያቱም ... ይህ ይህ ስለሆነ " ብንል።

• ጥላቻን የሚሰብክ መልዕክት ከሆነ ፤ " ይህ በእኔ አመለካከት ጥላቻን የሚሰብክ ስለሆነ አመለካከትህን ብታርም እና ቀና አመለካከት ብትይዝ " በሚል ወንድማዊ ምክር ብንለግስ።

በእርግጥ ያለንበት ሁኔታ በብዙ የሚያበሳጭ ፣ የሚያቆስል ፣ የሚያናድድ ጉዳዮች የተሞላ ቢሆንም በሌሎችም ጉዳዮች ሃሳብ ስንገልፅ እርስ በእርስ ለመግባባት ፣ ለመተራረም እና አብሮነትን ለማጠናከር በሚያግዙ ቃላት ብንመላለስ በትንሹም ቢሆን ሰላማዊ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን መፍጠር ይቻላል።

ማንም ሰው እራሱንም ሆነ ሰውን እንዲሁም የገዛ ሀገሩን እስካልጎዳ፣ ሌላውን እስካልበደለ ድረስ የፈለገውን ሀሳብ የማራመድ መብት ቢኖረውም ያንን የሚገልፅበት መንገድ ነገ የተሻለ ለውጥን ሊያመጣ በሚችል መልኩ መሆን አለበት።

ተቃራኒ ሃሳብ ስንመለከተ ዘለን የገለሰቡን ብሄርን ፣ ማንነትን በመተንኮስ፣ በጥላቻ እንዲሁም በእልህ በፍረጃ የምንሰጠው ሃሳብ ችግር ከመፍጠር እና ከማባባስ ውጭ የሚፈይደው ነገር አይኖርም።

ሃሳብ እና አስተያየት የምንሰጥባቸው ቦታዎችን መምረጥ ተገቢ ነው ፤ የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ፣ በፖለቲካውም ላይ ፣በትምህርቱም ላይ ... እየገቡ ከሰዎች ተቃራኒ ሃሳብ ጋር መጋጨት እና መነታረክ ከምንም በላይ ለራስ ጤና ጎጂ ነው።

በጅምላ / ሌሎች ሰዎች ስለፃፉ ብቻ ሳይሆን ስለምናውቀው ጉዳይ በተሻለ ቃላት ሃሳባችንን የሚገባው ቦታ ላይ ብናስቀምጥ በተሳሳተ መንገድ እየሄዱ ያሉ በርካቶችን መለወጥ ይቻላል።

እዚህ ጋር ልብ ማለት የሚገባው ፦ በማህበራዊ ሚዲያው ሆን ተብለው ለጥላቻ ፣ ለግጭት ፣ ሰዎችን ለማበሳጨት እና ስሜታዊ ለማደርግ የሚከፈቱና ሁሉም ገፆች ላይ እየገቡ የሚፅፉ በርካታ ሀሰተኛ አካውንቶች መኖራቸውን ነው።

#tikvahfamily

@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል። በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መቋረጡን በዚህም ምክንያት " ምን ተፈጥሮ ነው ? " በሚል ጭንቀት እንደገባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቡን አባላት መልዕክት ይዞ ኢትዮ ቴሌኮምን አነጋግሯል። ኢትዮ ቴሌኮም ፤ እውነት ነው ኔትዎርክ ተቋርጧል ሲል አረጋግጦልናል። " ኔትዎርክ የተቋረጠው ፋይበር ተቆርጦ…
#Update

ኢትዮ ቴሌኮም በ " ፋይበር መቆረጥ " ምክንያት በትግራይ ተቋርጦ የነበረውን የኔትዎርክ አገልግሎት ለማስቀጠል ሲያከናውን የነበረውን የጥገና ስራ ማጠናቀቁንና አገልግሎት መመለሱን አሳውቆናል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ፤ ሰራተኞቹ ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ በሁለት ቦታዎች ላይ የነበረውን የፋይበር መቆረጥ በመጠገን ወደነበረበት መመለስ ችለዋል።

የፋይበር መቆረጥ ያጋጠመው በ " አላማጣ " እና በ " ሰመራ " በኩል ሲሆን በምን ምክንያት ሊቆረጥ እንደቻለ የማጣራት ስራ ለመስራት እየተሞከረ ነው ተብለናል።

" የፋይበር መቆረጥ በተለያዩ ቦታዎች አልፎ አልፎ ያጋጥማል " ያለን ኢትዮ ቴሌኮም በሁለቱ ቦታዎች ያጋጠመውን የፋይበር መቆረጥ ምክንያት ለማወቅና " በዚህ ነው ሊቆረጥ የቻለው " የሚለውን ለመለየት እየተሰራ ነው ሲል አስረድቶናል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሪሜዲያል

ትምህርት ሚኒስቴር ከአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና ጋር በተያያዘ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ?

ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና አሰጣጥን በተመለከ ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኃላ ከፈተናው ጋር በተያያዘ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል ለማወቅ ችሏል።

በዚሁ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥ በሚከተለው መልኩ እንዲከናወን ተወስኗል።

- በ26/10/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕርግራም ፈተናዎች #ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ እንዲደረግ ተወስኗል።

- ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ #ካምፓስ ያላቸውን #የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት ፈተና  ወደ ፊት ቀርቦ በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ እንዲደረግ ተወስኗል።

- በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች ፈተና መስጠቱን ወደ መስከረም ወር ማስተላለፉ በተማሪዎችና በተቋማት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት በማስገባት የተዘጋጁትን ፈተናዎች በመለወጥ ፈተናዎች ኢንክሪፕትድ ሆነው ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ደርሰው እንዲባዙና ሁሉም ፈተናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እንዲሰጡ እንዲደረግ።

- የፈተና ጥያቄዎች ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ከመድሳቸው በፊት ተማሪዎች #ከቀኑ_6 ሰዓት ላይ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ አዳራሽ ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ በማድረግ እንዲፈፀም ውሳኔ ተላልፏል።

ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከላቸው ውሳኔ መሰረት ተማሪዎቻቸው #ከቀኑ_6 ሰዓት ተፈትሸው ወደመፈተኛ ክፍል ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ መልዕክት እያስተላለፉ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከየተቋማቱ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።

#TikvahFamily

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጨረሻዋ ውድድር የሆነውን የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ውድድር ማድረግ ጀምራለች። በውድድሩ ሀገራችን ፦ - በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ - በአትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ - በአትሌት ሎሜ ሙለታ ተወክላለች። መልካም ዕድል ! @tikvahethiopia
#ተጠናቋል

በዚህም ድል አልቀናንም !

በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ ድል አልቀናትም።

ዘርፌ ወንድማገኝ 4ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ሎሜ ሙለታ 12ኛ ፣ ሲምቦ አለማየሁ 13ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

ሀገራችን በሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት ስታካሂድ የነበረውን ውድድሮች ሁሉ #አጠናቃለች

ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ብዛት ከዓለም 6ኛ ደረጃ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ኬንያን በመከተል 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። ኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 4 የብር እና 3 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ነው ያገኘችው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዋና ገፅ / @tikvahethiopia ስፖርት በተለይ አትሌቲክስ #ሀገራዊ ስሜትን ፣ አብሮነትን ፣ አንድነትን ያጠነክራል የሚል እምነት ስላለው የሀገራችን ልጆች የተካፈሉባቸውን ውድድሮች ሁሉ #ከስፍራው ከፎቶ ጋር ሲያደርስ ቆይቷል።

ስፖርታዊ መረጃዎችን በ @tikvahethsport መከታተል ትችላላችሁ።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
እንኳን #ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
እንኳን ለመስቀል #ደመራ በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የ2016 ዓ/ም የመስቀል በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን ለምታከብሩ ቤተሰቦቻችን በሙሉ በዓሉ የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር በሀዘን ውስጥ ያሉትን ፣ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንን እያሰብን ፣ ለሀገራችን እና ለሀገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ፍፁም ሰላምን እንዲሰጠን ፈጣሪን እየተማፀንን እንዲሆን አደራ እንላለን።

መልካም በዓል!
#TikvahFamily

@tikvahethiopia
እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" መስመሩ መበጠሱን ነው እንጂ ያረጋገጥነው በምን ምክንያት እንደተበጠሰ ማወቅ አልቻልንም " - አቶ ሞገስ መኮንን

ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እንዲሁም ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በመበጠሱ በሰመና መቐለን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እነዚህ ሁለት መስመሮች የተበጠሱበትን ምክንያት የጠየቅናቸው ሲሆን ፤ " መስመሩ መበጠሱን ነው እንጂ ያረጋገጥነው በምን በምን ምክንያት እንደተበጠሰ ማወቅ አልቻልንም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁለቱ መስመሮች መቼ ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ? ሲል ጥይቄ አቅርቧል።

አቶ ሞገስ መኮንን ፦

- በቀላል የሚገናኙ መስመሮች ይኖራሉ ፤ በቀላል ሊገናኙ የማይችሉ እና የተበጠሰበትን ቦታ ብቻ ሳይሆን መስመር መቀየር የሚያስፈልጉም ሊኖሩ ስለሚችሉ እነዚህን እርግጠኛ ባልሆንንበት በዚህ ቀን ሊባል አይችልም ብለዋል።

- ከትናንት በስቲያ ከሰዓት በኋላ ከደብረ ብርሃን- ሸዋሮቢት ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ የተበጠሰውን መስመር አገልግሎቱን ለማስቀጠል ግብዓቶችን የማሰባሰብ ስራ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

- ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋውን መስመር በተመለከተ የተበጠሰው ዛሬ ረፋድ ላይ መሆኑን በመግለፅ ከባህር ዳር ያለው ርቀት ከ100 ኪሎ ሜትሮች በላይ በመሆኑ ለጥገና ጊዜ የሚፈልግ መሆኑንና አገልግሎት ለማስጀመር ይሄ ነው የሚባል ቀን ማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመዋል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ዒድ_አልፈጥር

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ #የሰላም#የአንድነት#የፍቅርና #የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

መልካም በዓል !

#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች አንድ አባት  በጎረምሶች ተከበው ሲመቱ ፣ ሲሰደቡ ፣ ሲዘለፉ ፣ ሲዋከቡ በቪድዮ ታይቷል።

ይህን እጅግ አሳፋሪና በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን ሚያሳይ ቪዲዮ ያጋሩት ደግሞ እራሳቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ናቸው።

ድርጊቱ ብዙዎችን ክፉኛ አስቆጥቷል። በርካቶች ስለ ነገ በማሳብ ፍርሃት ውስጥ ከቷቸዋል።

በእርግጥ በሀገራችን ያላየነው ግፍ ፣ ያልሰማነው ክፉ ተግባርና ጭካኔ ምን አለ ? እንዘርዝር ብንልስ ቦታው፣ ጊዜው  ይበቃናል ? በፍጹም !

ከዚህ በፊትም እንደምንለው በቪዲዮዎች ተቀርጾ የምናየው ምናልባትእድለኞች ሆነን ከብዙ አንዱ እንጂ ስንት ያላየነው ይኖራል።

ወደ ቪድዮው ስንመለስ ተከበው ሲመቱ፣ ሲዋከቡ ፣ ሲዘለፉ የነበሩት አባት ' እንጀራ ፍለጋ እግር ጥሏቸው እንደመጡ ' ይገልጻሉ የሚጠይቀን የለም ባዮች ጎረምሶች ' እዚህ አካባቢ ምን ትሰራለህ ? ለምን እዚህ መጣህ ? ከመጣህበት ቦታስ እንጀራ የለም ? ' ሲሉ እጅግ በንቀት ያዋክቧቸዋል።

ይህን ተግባራቸውን እንደ በጎ ስራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርተውታል።

የትኛውም ዜጋ በገዛ ሀገሩ የመንቀሳቀስ መብት አለው ? ካልሆነ ስለምን #ኢትዮጵያዊ ይባላል ? ጥፋት ካለበት ፣ ከተጠረጠረ የሚጠይቀው ህግ እንጂ የሰፈር ጎረምሳ አይደለም። ግለሰቦቹ ጥርጣሬ አለን ካሉ ህግን ማሳወቅ እንጂ ማነው ፤ የትኛው ህግ ነው ይህንን መብት የሰጣቸው ? 

ይህ ተግባር በተለይ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተነዛ ያለው የጥላቻ ስብከት ምን ያህል ስር እንደሰደደ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን ነገን እጅግ አስፈሪ ያደርገዋል።

ግልጽ የሆነ የብሄርና የግለሰቦች ጥላቻ ፣ ልብም አእምሮም በጥላቻ መሞላት፣ አይንም በጥላቻ መታወር ፦
- ሌላው ይቅር ታላላቆቻችን እንዳናከብር
- ለእምነታችን ፣ ለሃይማኖታችን ቦታ እንዳይኖረን
- ለሰው ልጅ ትንሽ እንኳን ቦታ እንዳንሰጥ
- ለህግ እና ስርዓት ቅንጣት ታክል ደንታ እንዳይኖረን
- ባህል፣ ወግ ፣ አብሮነት ለሚባለው ጉዳይ ቦታ እንደሌለን
- ነገ እኔስ ምን ይገጥመኛል ? ምን እሆን ይሆን ? በህይወት አጋጣሚ የት እሄዳለሁ ፣ ምን አካባቢ እገኛለሁ የሚለውን ለማገናዘብ እንኳን እንዳንችል ያደርገናል።

ሰዎች ወደው ሳይሆን በስርዓት፣ በግለሰቦች፣ በአንቂዎች ፣ በሚዲያዎች... አማካኝነት ነው ጥላቻ እንዲውጣቸው እና ማገናዘብ ፣ ቆም ብሎ ማሰብ የሚባለውን መሰረታዊ ነገር እንዲያጡት የሚሆነው።

ሰዎች ከመሰል ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አብሮነት ፣ ፍቅር ፣ መግባባት፣ መከባበር ፣ ህግ ፣ ስርዓት፣ ወንድማማችንነትን ከማስተማር ባለፈ በህግ ማረም ፣ ነገ መዘዙ የከፋ እየሆነ ስለሚሄድ ከወዲሁ እንዲገታ በአንድ ላይ ማውገዝ ፣ ተበዳይን መካስ ፣ እውነት ህግ የበላይ ነው የምንል ከሆነም ለራሳችን ስንል ህግን ሁሌም ማስከበር ነው።

ዛሬ ላይ እንዲህ ያሉና ከዚህ ቀደምም በየሀገሪቱ ክፍሎች የሰማናቸው ፍጹም አደገኛ የሚባሉ ጉዳዮች የሳምንት አጀንዳ እየሆኑ እያለፉ ይመስለን ይሆናል ግን በእርግጠኝነት መዘዛቸው የከፋ ሊሆን ይችላል።

ውጤታቸው ዛሬ ሳይሆን ውሎ አድሮ ምናልባትም አመታትን አልፎ ይታይ ይሆናል ስለሆነም እናስብበት ! ትውልዱን ከስህተቱ እናርመው ፤ ወገኑን እንዲጠላ ሳይሆን እንዲወድ ፣ እንዲያከብር እናስተምረው።

በሁሉም ዘንድ አውቀናል ታውቀናል ፣ ዛሬ ስልጣን አለን፣ ሚዲያውም የኛው ነው የምንል ሰዎችም ' አይ የኔ ወገን ስለሆነ ፍጹም ጻዲቅ ነው ፣ አይሳሳትም ፣ ጀግና ነው ፣ ቢሳሳትም ምንም ችግር የለውም እኔ እከላከልለታለሁ ' ከሚል አደገኛ እና ብዙ መዘዘ ካለው አመለካከት መራቅ ይገባናል።

#TikvahFamily
#Ethiopia

@tikvahethiopia
#Humanity❤️

ይህ የሆነው በአሜሪካ ሀገር ሚኒሶታ ነው።

በሚኒሶታ በሚገኝ #ፈጣን_መንገድ ላይ አንድ አሽከርካሪ መንገድ ስቶ ወጥቶ ከመብራት ፖል ጋር ተጋጭቶ እዛው መኪና ውስጥ እያለ መኪናው በከፍተኛ እሳት መያያዝና መንደድ ይጀምራል።

በመንገዱ ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች ይህን አይተው አላለፉም።

መኪናቸውን አቁመው ከሚነደው መኪና ውስጥ አሽከርካሪውን ለማውጣትና ለማዳን ርብርብ ጀመሩ።

ከእሳት ነበልባል ጋር #እየታገሉ ፤ በሹፌሩ በር በኩል ያለውን መስታወት ሰብረው ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል በኃላ አሽከርካሪውን በእሳት ተያይዞ ከሚነደው መኪና ውስጥ በህይወት አወጡት።

በኃላም ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ።

አሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት የከፋ ጉዳት አልደረሰበትም ተብሏል።

ከከፍተኛ እሳት ጋር ተጋፍጠው የሰው ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ሲያደርጉ ከነበሩት አንዱ ከድር ቶላ ይባላል። (ጥቁር ጁንስ ሱሪ በነጭ ጫማ ያደረገው)

ወደ ስራ እየሄደ በነበረበት ሰዓት ነው ይህ ክስተት ያጋጠመው።

ከድር የነፍስ አድን ስራውን ፥ " በህይወቴ እጅግ በጣም አስፈሪው ቅጽበት ነበር። ይህንን መቼም ቢሆን አልረሳውም ሁሌም ቢሆን አስታውሰዋለሁ " ሲል አስረድቷል።

አሽከርካሪው በህይወት እንዲተርፍ ቦታው ላይ የነበሩ ሁሉም ሰዎች ላደረጉት ፍጹም #ሰብዓዊ ተግባርና ርብርብ ፈጣሪን አመስግኗል።

የነበረውን የህይወት አድን ርብርብ የሚያሳይ ቪድዮ ከድር ቶላ መኪና ላይ በነበረ የዳሽቦርድ ካሜራ የተቀረጸ ነው።

Video Credit : Kadir Tolla / ከድር ቶላ

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

" ማህበረሰቡ ያለበትን #የቤት_እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ - ቴሌኮም ጋር በመተባበር 100 ሚሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው " እየተባለ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም #ሀሰተኛ ነው።

በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወረው መልዕክት አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡን #ለማጭበርበር የፈጠሩት ነው።

" ሼር ብቻ እያደረጋችሁ የቤት ባለዕድለኛ ሆኑ ፣ ተሸለሙ " የሚሉት መልዕክቶች በሁለቱም ተቋማት እውቅና የሌላቸው የአጭበርባሪዎች ስራ ናቸው።

" ቤት ታገኛላችሁ ሼር አድርጉ " እንዲህ የሚባል ነገር የለም።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ፤ መሰል #በውሸት የተሞሉ የማጭበርበሪያ ስልቶችን እንድትጠነቀቁ ከዚህ ቀደም በዛ ያሉ መልዕክቶች ተለዋውጠናል ፤ በቂ እውቀትም አላችሁ።

ምናልባት እንዲህ ያለን ሀሰተኛ መልዕክት አምኖ የሚጭበረበር ወዳጅ ዘመንድ እንዳይኖራችሁ አስገንዝቧቸው።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#አረፋ

መልካም በዓል !

" ይህን የተባረከ #የአረፋ_ቀን እምነታችንን በልባችንና በተግባራችን የምናድስበት ፤ ስላጠፋነው ጥፋት / ስህተት ከልብ አዝነን ዳግመኛ ወደዛ ላለመመለስ ቃል የምንገባበት እና ወደ ሁሉን ቻይ አምላካችን #አሏህ 🤲 የምንቀርብበት ቀን ነው። " - ሙፍቲ ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር)

#መልካም_በዓል !!
#TikvahFamily ❤️

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM