TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION

የአማራ ክልል ኮሮና የቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ኮማንድ ፖስት ባህርዳር ፣ አዲስ ቅዳም ፣ ቲሊሊ እና እንጅባራ ከተሞች ማንኛውም አይነት የህዝብ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ውሳኔ አሳልፏል።

በከተሞቹ ከነገ 6:00 ስዓት ጀምሮ ለአስራ አራት ቀን (14) የሚቆይ ማንኛውም አይነት የህዝብ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ተወስኗል።

እገዳው በልዩ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ የደረቅና የፈሳሽ ጭነት ተችከርካሪዎችን እንዲሁም የውኃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች አይጨምርም። የድንገተኛ አገልግሎት የሚሰጡና ወረርሽኙ ለመግታት የሚሰሩ በጎ ፍቃደኞች ግን መንቀሳቀስ ይችላሉ።

መመሪዎችን ተላልፈው የሚገኙ ሰዎች በህግ ተጠያቂ የሚደረጉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ለዚህም የፀጥታ አካላት ኃላፊነት ወስደዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- ቤልጂየም ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃች የ12 ዓመት ታዳጊ ህይወቷ ማለፉ ተሰምቷል።

- በስፔን በ 24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ የ849 ሰዎች ሞት ተመዘግቧል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 8,189 ደርሷል። የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥርም ወደ 94,417 ከፍ ብሏል።

- ሩሲያ በ24 ሰዓት ተጨማሪ 500 የኮሮና ቫይረስ ኬዞችን ሪፖርት አድርጋለች።

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ነው። እስካሁን ባለው ሪፖርት 3,177 ደርሷል።

- በዓለም ላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 800,000 አልፏል። ከ39,000 በላይ ሰዎችም ላይመለሱ አሸልበዋል። 172,438 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

- ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዳማ ከተማ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ከተገኘበት ግለሰብ ጋር ንክኪ ነበራቸው ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ 29 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ እንደሆኑ መረጋገጡን የከተማዋ አስተዳደር ጤና መምሪያ አስታውቋል።

ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው የተረጋገጠው ተጠርጥረው ምርመራ ከተደረገላቸው 42 ሰዎች ውስጥ ነው።

ከቫይረሱ ነፃ የሆኑት ሰዎች ሙሉ በሙሉ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ለቀጣዩ 14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ክትትል እንደሚደርገላቸው ተገልጿል።

ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው ቀሪዎቹ ሰዎች በምርመራ ላይ እንደሚገኙና ውጤታቸውንም እየተጠባበቁ ይገኛሉ ተብሏል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ሀገር አቀፍ መረጃዎች፦

- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሥራ እንዲውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለግሰዋል።

- ሼህ ሁሴን አሊ አላሙዲ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን ለመግታት የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በተጨማሪ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ማኔጅመንት፣ አመራር እና ሠራተኞች ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ለተመሳሳይ አላማ አበርክተዋል።

- የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 14, 000 ሰራተኞቹን በጊዚያዊነት ከስራ አሰናብቷል። ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱት በአሜሪካና በአውሮፓ ገበያዎች የምርቶቹ ዋነኛ ተቀባይ የነበሩት ድርጅቶች በኮሮና ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ ነው።

- መከላከያ ሰራዊት ነገ በአዲስ አበባ የቫይረሱን ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ መልዕክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በሄሊኮፕተር ይበትናል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በማርሽ ባንድ የታጀበ የማንቂያ ቅስቀሳ ያደርጋል፡፡

- አልማ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቋል።

#DW #etv #EliasMeseret #fbc #ena
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ሴራሊዮን ገባ!

ሴራሊዮን በሀገሯ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሪፖርት አድርጋለች። ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ እድሜው 37 እንደሆነና ወደፈረንሳይ የጉዞ ታሪክ ያለው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሀገር መከላከያ ሰራዊት!

በነገው ዕለት መጋቢት 23/2012 ዓ/ም መከላከያ ሰራዊት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ፓምፕሌት የመበተን ፕሮግራም እንዳለው መገለፁ ያታወቃል።

ነገር ግን ፖምፕሌቱን መበተን ካንዱ ወዳንዱ ንክኪን የሚፈጥር በመሆኑ ለህዝብ ደህንነት ሲባል ፓምፕሌት በሄሊኮፕተር መበተን #የቀረ መሆኑን አሳውቋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለመላው ህዝብ የሚያስተላልፈው መልዕክት በተቋሙ ሚዲያዎች ማለትም በፌስ ቡክ ገፁ፣ በመከላከያ ቴሌቪዥንና በመከላከያ ሬዲዮ የሚያስተላልፍ መሆኑንም ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች 59 ደረሱ!

በጎረቤታችን ኬንያ ውስጥ በ24 ሠዓት 234 ናሙናዎች ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የ9 ሰዎች ምርመራ ውጤት ፖዘቲቭ ሆኖ ተገኝታል። አጠቃላይ በሀገሪቱ ያላ የቫይረሱ ተጠቂዎችም 59 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከሆነው ግለሰብ ጋር ንክኪ ላላቸው ተጠርጣሪዎች ለይቶ መቆያ በመሆን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።

ለተጠርጣሪዎች ከመኝታ አገልግሎት በተጨማሪ የምግብና ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፤ የዞኑ ጤና መምሪያ በመደባቸው የጤና ባለሙያዎች ክትትል ይደረግላቸዋል ብሏል።

ምንጭ፦ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ ከእንጅባራ...

'የእንጅባራ ገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር' ቢከራይ በዓመት ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣውን ማዕከል ለኮሮና ቫይረስ የተጠረጠሩ ዜጎች ማቆያ እንዲሆን መሰጠቱ ተገልጿል። ባለሶስት ፎቁ ህንፃ ከ400 በላይ ክፍሎች ያሉት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ7,600 በላይ ታራሚዎች እንዲፈቱ ተወስኗል!

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመከላከል በሚል ከ7,600 በላይ ታራሚዎችን በይቅርታ እንዲፈቱ ወስኗል።

ከእስር በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው፦

- የሚያጠቡ እናቶች፣
- የአመክሮ ጊዜያቸው አንድ ዓመት የቀራቸው፣
- ቀላል ወንጀል ፈፅመው ጊዜያቸው አንድ ዐመት የቀራቸው፣
- የሌላ አገር እስረኛ ዜጎች ናቸው።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BOTSWANA

በቦትስዋና 3 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ። ግለሰቦቹ የብሪታንያ እና ታይላድ የጉዞ ታሪክ ያላቸው የቦትስዋና ዜጎች ናቸው። ይህም ተከትሎ በሀገሪቱ የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል፤ የሀገሪቱ ዜጎችም ከመጪው ሀሙስ ጀምሮ ለ28 ቀን እጅግ አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ከቤታቸው እንዳይወጡ ታዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የ2012 ምርጫ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደማይካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ቦርዱ በተፈጠረው ሁኔታ የተነሳ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫውን ማካሄድ የማይቻለው መሆኑን በመረዳት ያወጣውን የጊዜ ሰሌዳ በመሰረዝ በሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ለጊዜው እንዲቆሙ መወሰኑን ገልጿል።

የወረርሽኙ ሥጋት ተወግዶ ሁኔታዎች ሲመቻቹ እንደገና ግምገማ በማድረግ አዲስ የምርጫ ኦፕሬሽን እቅድና ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቀሴውን የሚያስጀምር እንደሚሆንም አሳውቋል።

#NEBE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የምርጫ 2012 ኦፕሬሽን እቅድ እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ የፈጠረውን ችግር ገምግሞ ያሳለፈው ውሳኔ መግለጫ!

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በታንዛኒያ የመጀመሪያው የኮቪድ-19 ሞት ተመዘገበ!

የታንዛኒያ ጤና ሚኒስቴር የመጀመሪያው የኮቪድ-19 ሞት መመዝገቡን ሪፖርት አድርጓል። ሟቹ የ49 ዓመት የታንዛኒያ ዜጋ ነው።

በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ 19 የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ታማሚዎች የሚገኙ ሲሆን 1 ሰው ደግሞ ሙሉ በሙሉ አገግሟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ከነገ 23/07/2012 ዓ.ም ጀምሮ በደሴ ከተማ ተግባራዊ የሚሆኑ ውሳኔዎች፦

1. በከተማው ያሉ ሁሉም ትልልቅ የገበያ ቦታዋች ከነገ ጀምሮ ዝግ ይሆናሉ !

2. በከተማው የሚገኙ የሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) እና የእንስሳት ትራንስፓርት (ጋሪ) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ይቋረጣል።

3. በከተማው መግብያ በሁሉም አቅጣጫዎች ጫት መግባት አይችልም! በየጫት ቤቱ ሆነ ሽሻ ቤት የሚገኙ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል።

(ደሴ ከተማ አስተዳደር)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጣልያን ተጨማሪ 837 ሰዎች ሞቱ!

ጣልያን ውስጥ በ24 ሰዓት ተጨማሪ 837 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሞተዋል። ቁጥሩ ትላንት ከተመዘገበው ከፍ ብሏል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 12,428 ደርሷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 105,792 የደረሰ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የ4,053 ሰዎች ኬዝ የተመዘገበው በ24 ሰዓት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 26 ደረሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia