TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የታማሚ ሁኔታ፦

ቫይረሱ የተገኘበት 26ኛው ግለሰብ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት 9/2012 ዓ/ም ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም መጋቢት 10/2012 ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል።

ግለሰቡ የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። በአሁን ሰዓት ግለሰቡ በድሬዳዋ የለይቶ ህክምና መስጫ ማእከል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።

#DrLiaTadesse #EPHI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሩዋንዳ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች 75 ደረሱ!

የሩዋንዳ ጤና ሚኒስቴር 5 ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ኬዞችን ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ የቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥርም 75 ደርሷል።

የታማሚዎች ሁኔታ፦

- 4 ተጓዦች ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆን በተደረገላቸው ምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል።

- 1 ግለሰብ ደግሞ ከዚህ ቀደም ከቫይረሱ ተጠቂ ጋር ንክኪ የነበረው ሲሆን በተደረገለት ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

ኮቪድ-19 መድሃኒት ተገኝቶለታል፣መድሃኒት አለው በሚል እጅግ የተሳሳተ አረዳድ፣ አንዳንዴም በተሳሳተ መረጃ የራስን፣ የቤተሰብን እንዲሁም የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ እንዳንጥል እንጠንቀቅ። በአሁኑ ወቅት ይህ ቫይረስ ምንም አይነት ፈዋሽ መድሃኒት፣ ክትባትም የለውም።

በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ ከቀን ወደቀን እየተስፋፋ ነው። ከመዲናይቱም መጥቶ የክልል ከተሞችንም እያዳረሰ ነው። ቁጥሩ ከፍ እንዳይል ሁሉም የጤና ባለሞያዎችን ምክር ሊያዳምጥ ይገባል።

እባካችሁ፦

- የቫይረሱ ምልክቶች ከታየባችሁ ስለወገናችሁ ብላችሁ አትደብቁ ፤ በነፃ የስልክ መስመሮች ጠቁሙ።

- ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራችሁ ወዳጆች ፣ ቤተሰቦች ሌሎችም ለወገኖቻችሁ ስትሉ እራሳችሁን እና ሌሎችን አደጋ ላይ ሳትጥሉ ይፋ በተደረጉት ስልኮች አሳውቁ፤ እራሳችሁን ለዩ።

- ወጣቶች በተለይ ከዩኒቨርሲቲ ተመላሾች ምንም ጉዳይ ከሌላችሁ ከቤታችሁ አትውጡ።

- የአካላዊ መራራቅ ተግባራዊ እንዳልሆነ በየዕለቱ የሚደርሱት ፎቶች እያሳዩን ነው። ምናለ ሰው ባለበት ቦታ ከመሄድ ብንቆጠብ?

በየጊዜው እንደምንለው ሀገራት የመመርመር እና ከቫይረሱ ተጠቂዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለግ አቅማቸው ሲጠናከር በርካታ አዳዲስ ኬዞችን ሪፖርት እያደረጉ ነውና የከፋ ሁኔታ ውስጥ ሳንገባ በእጃችን ያላ ያለውን የመከላከያ መንገድ እንጠቀም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የመመርመር አቅምን በሚመለከት፦

- እስካሁን በአንድ ቦታ ነው ምርመራ እየተደረገ የሚገኘው። በEPHI ውስጥ ብቻ ነው።

- በሁለት (2) ሳምንት ውስጥ እስከ 25 በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የምርመራ ስራው ይስፋፋል። በተለይም የክልል ላብራቶሪዎች ላይ እንዲስፋፋ ይደረጋል። አዲስ አበባ ውስጥም የግል የህክምና ተቋማት ላይም ይስፋፋል።

- በአጭር ጊዜ ውስጥ በመላው ሀገሪቱ ሰፊ ምርመራ የማድረግ አቅም ይፈጠራል፤ ይጠናከራል።

- ከተለያዩ ሀገራት የተገኙ የመርመሪያ መሳሪዎች አሉ፤ እነሱም ለዚህ አገልግሎት ይውላሉ።

- ቴስት ሲደረግ የቫይረሱ ተጠቂ ሊገኝም፣ ላይገኝም ይችላል በዚህ ወቅት ሳይታወቅ አልፎ ህብረተሰቡ ውስጥ ወርዷል? ወይስ አልወረደም የሚለው መለየት ይችላል።

- እስካሁን እየተሰራ ያለው በምልክት እና ከሰዎቹ ጋር ያላቸው ንክኪ ነው የሚታየው። ይሄ ይሻሻላል።

#DrDerejeDuguma #MoH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“Our key message is test, test, test” - Dr Tedros Adhanom

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ወደ በጎንደር ከተማ የሚገቡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉን የከተማ አስተዳደሩ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

በየትኛውም አቅጣጫ ወደ ከተማ የሚገባ ማንኛውም አይነት የህዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ከመጋቢት 24 /2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ተወስኗል።

የተደረገዉ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እገዳ እንዳለ ሁኖ ሸቀጥ የያዙ ተሽከርካሪዎች ተፈትሸው እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡ እገዳው በልዩ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ የደረቅና የፈሳሽ ጭነት ተችከርካሪዎችን አይጨምርም።

ምንጭ፦ ጎንደር ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማስታወሻ!

- ከነገ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በባህር ዳር ፣ ቲሊሊ ፣ አዲስ ቅዳም ፣ እንጅባራ ለ14 የሚቆይ ማንኛውም አይነት የህዝብ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ መወሰኑን እንዳትረሱ።

- በነገው ዕለት የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአ/አ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ፓምፕሌት ለመበተን የያዘው ፕሮግራም ተሰርዟል።

- ከነገ ጀምሮ በደሴ ከተማ ትልልቅ የገበያ ቦታዋች ይዘጋሉ፤ ወደከተማው ጫት መግባት አይችልም፤ በየጫት ቤቱ ሆነ ሽሻ ቤት የሚገኙ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል።

- ዓለም በጭንቅ ውስጥ ባለችበት በዚህ ሰዓት ከባህላችን ያፈነገጠ ቀልድ የሚቀልዱ አይጠፉምና ነገ APRIL 1 (አፕሪል ዘ ፉል) መሆኑን እንዳትዘነጉ።

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንዴት አረፈዳችሁ?

ጤና ሚኒስቴር ሀገራዊ ጥሪ አቅርቦላችኃል!

በዓለም ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሀገራችን ውስጥ መከሰቱም ይታወቃል፡፡ በመንግሥትና በበጎ ፍቃደኛ ሰዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠጠር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ወደፊት የወረርሽኙ ሁኔታ እየከፋ ከመጣ በርካታ የበጎ ፍቃድ ባለሙያዎችን ማሰማራት ስለሚጠይቅ፤

1. በጤና ሙያ ተመርቃችሁ ወደ ሥራ ያልተሰማራችሁ
2. መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት የምትሰሩ የጤና ባለሙያዎች
3. በጡረታና በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ የተገለላችሁ የጤና ባለሙዎች (ለመደበኛ አገልግሎት)
4. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን
5. የጤና ተማሪዎች (በመንግስትና በግል)

ከመጋቢት 24 ቀን 2012 ጀምሮ ከዚህ በታች በተገለፀው የጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ(http://www.moh.gov.et/ejcc/am/node/201) እንድትመዘገቡ ሀገራዊ ጥሪ
እናቀርባለን፡፡

(ጤና ሚኒስቴር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2 ላብሪቶሪዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀመሩ!

በአርማዎር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዮት እና በብሄራዊ የእንስሳት ጤና ምርመራና ጥናት ማዕከል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀምሯል።

ሁለቱ ተቋማት 4 አርቲ ፒሲአር ማሽኖች በመጠቀም በቀን ውስጥ እስከ 400 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንደሚያደርጉ ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በጋምቤላ ክልል መንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች፦

- ወደ ጋምቤላ ከተማ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ከፍተኛና መለስተኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት እንዲቆም ተወስኗል፡፡

- ከጋምቤላ ወደ ሁሉም የክልሉ ዞንና ወረዳዎች የሚደረጉ የህዝብ ማመላለሻ ከመጫን አቅማቸው 50 በመቶ ቀንሰው ህዝብ እንዲያመላልሱ።

- በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የከተማ የህዝብ ማጓጓዣ ባጃጅ፣ ሚኒባስና ሌሎች የህዝብ ማጓጓዣዎች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀናት ታግዷል።

- የመንግስትም ይሁን የግል ሞተር ሳይክሎች ከአሽከርካሪው በስተቀር ሰው መጫን ተከልክሏል።

- ጭፈራ ቤቶች፣ ጫት ቤቶችና ሺሻ ቤቶች የቫይረሱን ተጋላጭነት ስለሚጨምሩ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ተወስኗል።

- ወደ ጋምቤላ ክልል ምንም ዓይነት ጫት እንዳይገባ ተወስኗል፡፡

- በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ያለባቸው መስሪያ ቤቶች ሰራተኛን በመቀነስ እንዲሁም በእድሜ የገፉ፣ ህፃናት የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶች ቤታቸው ሆነው ስራ እንዲሰሩም ውሳኔ ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታማሚዎች ሁኔታ፦

- በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሶስቱ (3) ግለሰቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡

- የመጀመሪያዋ ታማሚ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ጅቡቲ፣ ብራዚል፣ ህንድ እና የመጨረሻ በረራዋ ኮንጎ ብራዛቪል ነው፡፡ የበሽታውን ምልክት በማሳየቷ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆና በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዘች መሆኗ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

- ሁለተኛው ታማሚ የ26 ዓመት ወንድ ሲሆን የስራ ባህሪው ከተለያዩ ተጓዥ መንገደኞች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡

- ሶስተኛው ታማሚ የ32 ዓመት ወንድ ሲሆን ቀደም ብሎ በበሽታው መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ ክትትል ሲደረግለት የነበረ ሲሆን በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

- ሶስቱም (3) ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሌሎች ሰዎች የመለይት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

#DrLiaTadesse

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚል ለተጨማሪ 23 ቀናት እንዲዘጉ መወሰኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቲቪ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GONDAR

በመጋቢት ወር ከውስጥና ከውጭ ሃገር ወደ ጎንደር ከተማ የገቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሌሎችም ዜጎች በሃላፊነት ስሜት ጤና ማዕከል በመሄድ ምርመራ እንዲያደርጉ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ማስተዋል ስዬም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ከንቲባው ከዚህ ጋር አያይዘውም በመጋቢት ወር በአየር መንገድ ከውጭ የመጡ ሃገር ቤት ገብተው ቆይተው ወደ ከተማዋ የሚመጡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው ማረፊያ ቦታ ለ14 ቀን ክትትል እየተደረገላቸው የሚቆዩ መሆኑን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ጎንደር ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ቤት መቀመጥ በብዙ መልኩ ይሄን በሽታ [ኮቪድ-19] ሊከላከል ይችላል" - ዶክተር ፅዮን ፍሬው

በኒውዮርክ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ሃኪም ፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ፣ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ጽዮን ፍሬው ከአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ በአሁን ሰዓት በኒውዮርክ ስላለው የቫይረሱ ስርጭት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ምን መማር እንዳለበት አንስተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

"የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ታይቶበት ህይወቱ ያለፈ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮና ቫይረስ እንደነበረበት እየተጣራ ነው" - ዶ/ር ሊያ ታደሰ [የጤና ሚኒስትር]

የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ህክምና ሲደረግለት የነበረ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ ዛሬ ህይወቱ ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ከሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ትናንት ወደ ጤና ጣቢያ ለህክምና ያመራው ግለሰቡ ዛሬ ህይወቱ ማለፉንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለማረጋጋጥ ናሙና ተወስዶ የምርመራ ውጤቱ እየተጠበቀ መሆኑንም አብራርተዋል። የአስከሬን ምርመራም እየተከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የታማሚ ሁኔታ፦ ቫይረሱ የተገኘበት 26ኛው ግለሰብ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት 9/2012 ዓ/ም ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም መጋቢት 10/2012 ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል። ግለሰቡ የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። በአሁን ሰዓት ግለሰቡ በድሬዳዋ የለይቶ ህክምና…
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፦

- ግለሰቡ በመጋቢት 10 ነው ድሬዳዋ የገባው ከብዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል። ነገር ግን ግለሰቡ 'እራሱን አግልሎ' ስለነበር የተወሰኑ የቤተሰቦቹን አባል ለማግኘት ተሞክሯል።

- ወደድሬዳዋ ለይቶ የህክምና መስጫ ማዕከል ከመምጣቱ በፊት የግል የህክምና ተቋሞች ጋር ሄዷል፤ በህክምና ተቋሞቹ ላይ የሚሰሩ ባለሞያዎችንም የመለየቱ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

- በአጠቃላይ ቫይረሱ ካለበት ግለሰቡ ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎችን በፍጥነት አግኝቶ ወደኳራንታይን ለማስገባት እየተሰራ ነው። ምልክቶችን የሚያሳዩ ካሉ እነሱንም የመለየት ስራ ይሰራል። ንክኪ ያላቸውን ሰዎች በጠቅላላ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ይደረጋል።

#DrFuadKedir

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በድሬዳዋ ከተማ በነገው እለት የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት ርጭት ይከናወናል። የፀረ-ተህዋስ መድሀኒት ርጭት የሚከናወንባቸው መንገዶች፦

- ከኮኔል ድልድይ - ክርስቶስ ት/ቤት - ኮተን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ

- ከኮኔል ድልድይ - ታይዋን - አላይበዴ - ክርስቲያን መቃብር

- ከኮኔል ድልድይ - ደቻቱ - ቀፊራ - አምስተኛ

- ከድ/ዳ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት - ምድር ባቡር ክለብ - ሰዒዶ

ከላይ በተጠቀሱት የከተማው መንገዶች ላይ ከነገ መጋቢት 24/2012 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ ለ1 ቀን ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- UK ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ የ13 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

- በስፔን በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ የ864 ሰዎች ሞት ተመዘግቧል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ9,000 በልጧል። የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥርም ወደ ከ100,000 በላይ ከፍ ብሏል።

- በፊሊፒንስ ተጨማሪ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸውን ሪፖርት ተደርጓል።

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ4,000 በላይ ሆኗል። የቫይረሱ ተጠቂዎችም 188,639 ደርሷል።

- ኦማን የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት ሪፖርት አድርጋለች።

- ፎርድ በመቶ ቀናት ውስጥ 50,000 ቬንትሌተር ሊያመርት መሆኑን አሳውቋል።

- ጀርመን በሀገሯ 149 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሞቱ ሪፖርት አድርጋለች።

- በኢራን የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር 3,036 ደርሷል። በ24 ሰዓት ውስጥም የ138 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

- በዓለም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 872,972 ደርሷል። 43,275 ሰዎች ሞተዋል፥ 184,594 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዩኒቨርስቲዎችን ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መቐለ ዩኒቨርስቲ አዲሱን የኲሓ መለስ ዜናዊ ቴክኖሎጂ ካምፓስ ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሰቲው የዶርሚተሪ አቀማመጥ የመቀየር ፤ ሰፋፊ ወርክሾፖችን የማዘጋጅት፣ መፀዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶችን በበቂ ሁኔታ የማዘጋጀት፣ የምግብ አቅርቦት እና አሰፈላጊ የሆኑ ግብሃቶችን የማሟላት ስራ በማከናዎን ላይ ይገኛል። ዩኒቨርስቲ ተጨማሪ ካምፓሶችን ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ የማዘገጃጀት ሂደት ላይ ይገኛል።

ምንጭ:- መቐለ ዩኒቨርስቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia