STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#MoE

ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።

ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተሻለ ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ " የደከሙባቸው ትምህርቶችን” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርስቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።

Credit : ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

106 ሺህ ተማሪዎች
ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ተካተዋል፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡

የ Remedial ፕሮግራሙ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፕሮፌሰሮች ኮሚቴ በማዋቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት የትምህርት አይነት ይዘቶችን ለይቷል።

በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዘኛ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ የትምህርት አይነቶችን የሚወስዱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ እንግሊዘኛ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ትምህርት አይነቶችን እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ይዘቶቹን መሰረት አድርጎ በተቋማት የሚዘጋጅ (ከ30 በመቶ) እና በማዕከል የሚዘጋጅ (ከ70 በመቶ) የሚያዝ ፈተና በመፈተን በድምሩ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚያገኙ ተማሪዎች መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ይችላሉ ብለዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድሚያ የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሀዱ ዘግቧል።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡

ከሀምሳ በመቶ በታች ካመጡት ተማሪዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ አመት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሪሜዲያል እንዲወስዱ የተወሰነ ሲሆን ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚንስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት የሚፈልጉ የግል ከፍትኛ የትምህርት ተቋማትም በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የልህቀት ማእከል ተብለው በተለዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል የተዘጋጀ የአቅም ማሻሻያ ሪሜዲያል ትምህርት ማስተማሪያ ተዘጋጅቶ ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መላኩን ጠቁመዋል፡፡

አያይዘውም የማስተማሪያ ሰነዱ ለተማሪዎቹ ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ማስተማር የሚችሉት ይሄንን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ለአሀዱ በሰጡት ቃል አመላክተዋል፡፡

Credit : #Ahadu

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ትላንት ለአሀዱ በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት " ለአንድ ዓመት " በሚል የተገለፀው ስህተት እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀው እንዲታረም ብለዋል።

የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) የሚሰጠው ከዚህ በፊት እንደተገለፀው ለአራት ወራት እንደሆነ አመልክተዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ እንደሚወስዱ ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።

እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ዋና ዋና ይዘቶች እና መታወቅ ያለባቸውን እስከ #አራት_ወር ተወስዶ ተማሪዎቹ አቅማቸውን የሚሞላ ትምህርቶችን እንዲማሩና እንዲከልሱ ይደረጋል።

የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 % እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70% ተመዝነድ በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ የቆዩት በዚያው ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል /Scholarship/ ስለተሰጣቸው ተማሪዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 3.3 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

ከነዚህም መካከል 263 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት (ከ700) እንዲሁም 10 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት (ከ600) በማምጣት የላቀ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

መንግሥት ለእነዚህ 273 ተማሪዎች የካቲት 21/2015 ዓ.ም የእዉቅና ሽልማት መስጠቱ ይታወሳል፡፡ በዕለቱ ለእነዚህ ተማሪዎች በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የትምህርት ዕድል /Scholarship/ እንደተሰጣቸውም ተገልጿል፡፡

ተማሪዎቹ ከመስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ዕድሉን በመጠቀም እንዲማሩ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውም ተመላክቷል፡፡ ወደ ዉጪ እስከሚሄዱ ድረስ ባሉት ግዜያትም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

የተፈጠረዉ የትምህርት ዕድል አስገዳጅ አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሀገር ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሌለ ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:- https://www.facebook.com/fdremoe

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል #መቅደላአምባ_ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎች የተደረገ ማስተካከያ ስላለ ምደባቸውን እንደገና ገብተው እንዲያሁ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

250 ሺህ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመጪው ሐምሌ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።

ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና እንዲወስድ የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE #ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች #በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። 

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።

ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#ኢብኮ #tikvah

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

"በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 49 ሺ ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ዘመቻ ከአንድ ወር በኋላ ይጀመራል" - የትምህርት ሚኒስቴር፡፡

የትምህርት ምዘና ጥናት ውጤቶችን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ አውደ ጥናት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት ጥራት ውጤት ምዘና እንዲሁም የ4ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት ምዘና ጥናት ይፋ ሆኗል።

በናሙና በተወሰዱ ትምህርት ቤቶች በተደረገው ምዘና ዝቅተኛ ውጤት መገኘቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሥርዓቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም ያሉት ሚኒስትሩ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ባሉት 49 ሺ ትምህርት ቤቶች የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ዘመቻ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር ይፋ አድርገዋል፡፡ በዘመቻው ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የቀድሞ ተማሪዎች እና ማህበረሰቡ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አመልክተዋል፡፡

ርዕሰ መምህራንን ለማብቃት የሚያስችል ማዕከል እየተቋቋመ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ #EPA #MoE



የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

" የትምህርት ሥርአቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤትና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና ውጤት የጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ " በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ የለውጥ ስራዎች እየተሠሩ ነው ፤ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም ይገባል " ብለዋል።

" የትምህርት ሥርአቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም " ያሉት ሚኒስትሩ " በሚታዩት ውጤቶች ሳንደናገጥ ዘርፉን ለመለወጥ ጠንክሮ መሥራት ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

👉 የተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ማነስ ፣
👉 ተስፋ መቁረጥ፣
👉 የመምህራን እጥረትና ተነሳሽነት አለመኖር፣
👉 የትምህርት ቤቶች መሠረተልማት መጓደልና ለመማር ማስተማር ምቹ ያለመሆን
👉 የትምህርት ቤቶች አመራር መጓደል #ለውጤቱ_መውደቅ ምክኒያቶች መሆናቸው በጥናቱ ተመላክቷል።

የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥም የትምህርት ዘርፍ ችግሮችን ፈጥኖ  ማረም እንደሚገባም ተገልጿል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በቀጣይ ወር የሚጀመር ሀገራዊ  ንቅናቄ እንደሚኖር እና ማህበረሰቡን በማስተባበር ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ሥራ እንደሚሰራ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህ ሂደት ወላጆች የትምህርት ቤቶች ባለቤቶች መሆናቸውን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚገባቸውና  ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤት(NLA)  እና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና ውጤት በባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ምንጭ፦ የትምህርት ሚኒስቴር


@NATIONALEXAMSRESULT
#MoE

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎችን አፈፃፀምን በተመለከተ ለህ/ተ/ም/ቤት ባቀረቡት ሪፖርት የ2015 የፈተና ዝግጅትን በተመለከተ አብራርተዋል።

ለ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ፣ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በየትምህርት አይነቱ እራሱን የቻለ የፈተና ዝግጅት ቢጋር እንዲዘጋጅ ተደርጓል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ " የ12ኛ ክፍል ዋናና የሙከራ ፈተና በፈተና በቢጋሩ መሰረት ከተለኪ ባህሪያት አንፃር ተገቢና አስተማማኝ ጥያቄዎችን በጥንቃቄና #ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በተዘጋጀ የስራ መመሪያ ቼክ ሊስት መሰረት በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከቀናት በፊት ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
MoE circular #exitexam dates.pdf
#MoE

አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ መሰረትም ፦

- ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣

- የተማሪዎች ምረቃ በዓል፣

- የሪሜዲያል ፈተና ውጤት አያያዝ በተመለከተ ቅያሪ መደረጉን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።


በዚህም ፦

- በ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ #በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

- በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል ተብሏል።

- የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።

- የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot