STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ለመደባ አያገለግሉም የተባሉት ውጤቶች አልተሰረዙም ተብሏል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር አቶ መሳይ ደምሴ ለተጠየቋቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ፦

TIKVAH-ETH ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አዳምጦ ቃል በቃል ያሰፈረው!

የውጤት ግሽበት ምን ማለት ነው??

"ያልተጠበቀ ውጤት እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ የፈተና አሰጣጥ በተለይም የ12ኛ ክፍል ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ሲሰጥ የተመዘገቡ ውጤቶች አሉ የ10 ዓመት ሊሆን ይችላል ወይም ከዚያ በላይ ነገር ግን ባልተጠበቀ መልኩ መቶ እና ሁለት መቶ፣ ሶስት መቶ በሁለት ወይም በሶስት የትምህርት አይነት ወይም በአራት የትምህርት አይነት መቶዎች አይመዘገብም። ዘንድሮ ግን በርካታ ውጤት ከ90 በላይ የተመዘገቡት በተለይ በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናትና ይሄ ያልተጠበቀ ነው። 6002 የሚሆኑ ተማሪዎች አጠቃላይ መቶ ሙሉ በሙሉ ያስመዘገቡት ውጤት ከዚህ በፊት ከተለመደው ባለን ሪከርድ የለም።"

ውሳኔው በራሳቸው ሰርተው ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ችግር አይፈጥርም?

" ችግር አይፈጥርም፤ 7 የትምህርት አይነቶች ናቸው የተሰጡት የመጀመሪያዎቹ ሰኔ 6-7 የተፈተኑት ፈተናዎች እንግሊዘኛ ለሁሉም፣ ለተፈጥሮ ሳይንስና ለማህበራዊ ሳይንስ፣ ሂሳብ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ፤ አፕቲትዩድ ለሁሉም ለማህበራዊ ሳይንስ ጆግራፊ፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፊዚክስ ተፈትነዋል። የጋሸበ ውጤት አለ የሚል ግምት ሲፈጠር የሰኞና የማክሰኞ፣ የመጀመሪያዎቹ ፈተናዎችም በኮሚቴ ታይቷል። በአንፃራዊነት የተማሪዎች ውጤት ተቀራራቢ ነው የነዚያኛዎቹ ግን የጋሸበ ነው ያልተጠበቀ ነው።"

የጋሸበ ውጤት የታየባቸው አካባቢዎች?

"የቴክኒክ ኮሚቴው ያጠናው አጠቃላይ በሀገሪቱ ነው። በጣም በተወሰኑ ክልሎች በ4 ክልሎች በደቡብ፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል አንድ ዞን፣ ኦሮሚያ የተወሰኑ ዞኖች የተወሰኑ ቁጥር፣ በርከት የሚለው በአማራ ክልል ሆኖ የጋሸበ ውጤት የተመዘገበበት ሁኔታ አለ። ነገር ግን በአንፃራዊነት ነው ሲታይ ግን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሰጠው ፈተና ሰኞ እና ማክሰኞ ግሽበት ያሳያል።"

ለምደባ የማያገለግሉት የትምህርት አይነቶች ዕጣ ፋንታቸው ምንድነው?

"ህብረተሰቡንም #የሚያወዛግበው እና ግልፅ ያልሆነላቸው ይሄ ነው። እጣ ፈንታቸው... በልጆቹ ውጤት ሰርተፊኬት ላይ ይመዘገባል። ከዚህ በፊትም ቢሆን መንግስት ባለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር በሚያወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ያስገባል። ሲያስገባ የሚወስደው መስፈርት አለ መስፈርቱ እሱ በወሰነው ነው። በዚህ አራቱ ትምህርት ይወሰድ ብለን ወስነናል። መንግስት ነው የወሰነው። የዩኒቨርሲቲ የማቀበል አቅም ...እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት መንግስት ኢንቨስት ለማድረግ አስተምራለሁ፣ በቀጣይ የሃገሪቱን እጣ ፈንታ የሚወስኑ አካላት ናቸው ብሎ የወሰደው compulsory ሶስቱ የትምህርት አይነቶች ናቸው ሂሳብ፣ እንግሊዘኛ እና አፕቲትዩድ ወሳኝ ናቸው እንደገና በፈተና አሰጣጥም የተረጋጋ በውጤትም በተማሪዎች ነካከል የጎላ ልዩነት ስለሌለ ተፅኖ ስለማይፈጥር ነገር ግን ሰኞና ማክሰኞ የተፈተኑት ለመደባ አያገለግሉም የተባሉት ውጤታቸው አልተሰረዙም ህብረተሰቡ ጋር ግን እንደተሰረዘ ተደርጎ ይወራል አልተሰረዙም! በልጆቹ ሰርተፊኬት ላይ ይቀመጣል። ከተቀመጠ በኃላ ለስኮላርሺፕ ይጠቀሙበታል፣ ለግል ዩኒቨርስቲ ተቋማት ይጠቀሙበታል። ሙቁረጫ ነጥብ 4ቱ የተወሰዱት በግልፅ ህብረተሰቡ እንዲያውቀውና እንዲረዳው የምንፈልገው ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች #ብቻ ነው፣ ለሌላ ይጠቀሙበታል።"

መቁረጫ ነጥብና ምደባው እንዴት ይከናወናል?

"የመቁረጫ ነጥቡን የሚወስናው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ነው፤ ከምን ተነስቶ? ከአራቱ ትምህርት ውጤቶች ትምህርት ተነስቶ። ህብረተሰቡ ማወቅ ያለበት ከ400 ታርሟል። ከ400 ከፍተኛ ውጤት ያመጣው በግሌ በማውቀው ወደ 336 ያመጣው ከ400 ከፍተኛው ውጤት ነው 6 መቶ ምናምን የነበረው ሰው። በግምት እኛ ባለን መረጃ አምና እስከ 150,000 ተማሪዎችን ተቀብሏል ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ከዚያ ባነሰ አይቀበልም ከዚያ በተሻለ ሊቀበል ይችላል። ለጊዜው ግን እኔ የማውቀውና የምረዳውም የአምናውን እንኳን ብንወስድ 150,000 ተማሪ የመቀበል አቅም ይኖራቸዋል ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከላይ ተነስቶ ወደታች ይሄዳል።"

ማነው ኃላፊነቱን የሚወስደው?

"ሃላፊነቱን የሚወስድ አካል ይኖራል። ይህንንም አጣርቶ የሚያቀርበው አሁን በሃገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ ካጣራ በኃላ ነው። ተጠያቂ የሚሆነው። ኮሚቴው ተዋቅሮ አልቋል ወደስራም ተገብቷል። ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው። በየደረጃው ያለ አካል ከላይ እስከታች ኤጀንሲውም ጋር ችግር ካለ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ችግር ካለ፣ ችግር አለ ተብሎ ተዳሶ እርምጃ ይወሰዳል። ወደፊት ለህብረተሰቡ ግልፅ ይሆናል።"

TIKVAH_ETHIOPIA ጻፈው

@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
📍Ethio Telecom ለ3 ቀናት የሰጠው #ነፃ የኢንተርኔት፣ ድምፅና መልእክት አገልግሎቶች ዛሬ ለሊት 6 ሰአት ይጀምራሉ።

📍ሁሉም የሚሰሩት ከለሊቱ 6 ሰአት #እስከማታ 12 ሰአት ድረስ #ብቻ ናቸው።
መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#SamaraUniversity

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ መርሃ ግብር ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ አድርጓል።

➤ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ
     ➭ ጥቅምት 21 እና 22/2015 ዓ.ም

➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ
     ➭ ኅዳር 01 እና 02/2015 ዓ.ም

ተማሪዎቹ በተጠቀሱት ቀናት #ብቻ በተቋሙ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት ምዝገባ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አድርጓል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
MoE circular #exitexam dates.pdf
#MoE

አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ መሰረትም ፦

- ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣

- የተማሪዎች ምረቃ በዓል፣

- የሪሜዲያል ፈተና ውጤት አያያዝ በተመለከተ ቅያሪ መደረጉን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።


በዚህም ፦

- በ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ #በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

- በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል ተብሏል።

- የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።

- የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Sent from Dr.Adane (KUE)

ከዚህ ቀደም በጤናና በሕግ የትምህርት መስኮች ለሚመረቁ ተማሪዎች ብቻ የመውጫ ፈተና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ 240ሺ የሚደርሱ ተመራቂዎች በመንግሥትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ይታወቃል!

በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል።

የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።

በቀሪ ጊዚያችሁ....

1. የመውጫ ፈተናው አስፈላጊ መሆኑን አምኖ መቀበል (ልምድ እንዳላችሁ አለመርሳት ወደ ኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ለመግባት ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ናችሁ (10ኛ እና 12ኛ ክፍል)፡፡ የመውጫ ፈተናውን በአይምሮ ደረጃ አምኖ አለመቀበል ጊዚያችሁን ይበላል፡፡

2. ለፈተና ይጠቅማል ብላችሁ ያሰባችሁበትን ክፍል ለይታችሁ መከለስ! ያላጣራችሁት ቦታ ካለ በደንብ ለፈተና በሚሆን መልኩ ማንበብ/መከለስ (በእያንዳንዱ የኮሌጅ ቆይታ ወቅት ለፈተና  አንብባችሁ ሊሆን ስለሚችል ምን አልባት ክለሳ ማድረግ ሊበቃ ይችላል)፡፡

3. ከፈተናው ሁኔታ (ፎርማት) ጋር ፈጥኖ ለመግባባት መሞከር (ኦን ላይን ከሆነ መልመድ፤ ፈተናው ስለሚዳስሰው ነጥብ ማወቅ፤ ልምምድ ማድረግ፤ ሞዴል ፈተናዎችን በትኩረት መስራት፤ የጥያቄዎቹን ይዘት ለማወቅ መሞከር፡፡

4. የሚዘጋጁ የናሙና ፈተናዎችን በትኩረት መፈተን እና በደንብ መለማመድ የቀደመ የህግ እና የጤና መውጫ ፈተና ይዘቶችን ጠይቆ ልምዶችን መውሰድ፤ ምን አልባት ኦን ላይን ያሉ ናሙናዎችን እንደ መለማመጃ መውሰድ፡፡

5. የጊዜ መርሃ ግብር ማውጣት፤ በአንዴ ብዙ ለመሸፈን መሞከር ትኩረት ስለሚያሳጣ ቀሪ ጊዚያችሁን በጥብቅ ፕሮግራም መምራት (ከማህበራዊ ሚዲያ መቀነስ፤ ከጨዋታ መቀነስ፤ ከእንቅልፍ መቀነስ (በቀሪው ጊዜ ተቸግራችሁ ከቁጭት መዳን ትችላላችሁ) እና ለዚህ ፈተና የመጨረሻ አቅማችሁን መጠቀም፡፡

6. በዚህ ወቅቱ በቡድን ማጥናት፤ ሙከራዎችን መስራት፤ ሊያስረዷችሁ የሚችሉ ሰዎችን መፍጠር ያስፈልጋል፤ በከበዳችሁ ክፍል ላይ ጊዜ በማጥፋት ወደ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዳትገቡ የሌሎችን እርዳታ ለመቀበል ክፍት መሆን አስፈላጊ ነው፡፡

7. ከወዲሁ እና በፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን ቀንሱ የኮምፒዊተር አጠቃቀም፤ የማርፈድ፤ ጥሩ ስሜት ያለመፈጠር፤ የድካም፤ የመጨናነቅ፤ ወዘተ፡፡

አስታውሱ በማንኛውም መለኪያ ፈተናውን ማለፍ በእናንተ ጥረት እና ዝግጅት ልክ ነው የሚወሰነው! ሳያጠኑ ለማለፍ መመኘትም ሆነ ሳያጠኑ ወድቆ ቅር መሰኘት አዋጪ Rational አይሆንም!

From: Dr.Adane (KUE)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Result

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን #ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡ 
    
👉 በዌብ ሳይት፡- eaes.et
👉 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
👉 ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በማመሳሰል " ውጤት እንገልጻለን " ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተለልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

እንዴት ውጤት ልመልከት ?

በዌብ ሳይት ለማየት ፦

1. eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ፦

1. 6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በመላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።

በቴሌግራም ቦት ፦

1. @eaesbot ይፈልጉ

2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ፡፡

የ የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#GAT የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

" 62 (50%) እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ / 80 ፐርሰንታይል ያገኙ በሚፈልጉበት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ "

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (National GAT) የመቁረጫ ነጥብ አሳውቋል።

በዚህም መሠረት ፤ አጠቃላይ ከተፈተኑት ጥያቄዎች ውስጥ 62 (50%) እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል (80 Percentile) ያገኙ ተፈታኞች #ብቻ ለመማር በሚፈልጉበት ተቋም አመልክተው መማር የሚችሉ እንደሆነ ተገልጿል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus በመግባት እና የተማሪውን የመግቢያ ስም (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላሉ ተብሏል።

በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት ፤ በሁሉም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test-NGAT) ተፈትነው ያለፉ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡ ይታወሳል።

(ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ/ም በትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot