መዝገበ ቅዱሳን
22.8K subscribers
1.93K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
እስከዛሬ_ድረስ #በላስታ_ተራራ_ጭላዳ_እህል_እንዳይበላ_ለገዘቱት #በጎንደር_ከተማ_ጅብ_እንስሳቶችን_እንዳይበላ_ለገዘቱት፡፡ ለታላላቆቹ አባቶች ለአቡነ ዓቢየ እግዚእና ለአቡነ ዮሴፍ ዓመታዊ በዓል (ግንቦት 19) በሰላምና በጤና አደሳችሁ፡፡

/#በጻድቃን_ተዓምራት_ማድረግ_ለምትጠራጠሩ፤/
#ጻድቃን_ከበዓለ_ዕረፍታቸው_በኋላ_ዛሬም_ከማማለድም_አልፈው_በቃልኪዳናቸው_ተዓምራት_እንደሚያደርጉ_ኑና_እዩ_ተመልከቱ፡፡ ተዓምራትን ማየት ለምትፈልጉ ኹሉ ሂዳችሁ እዩ!!!!!)፡፡

፠ ክብረ በዓላቸው
✍️ የአቡነ ዓቢየ እግዚእ በተንቤን መረታ ደብረ መድኃኒት፣ በጎንደር ከተማ ጥንታዊ በኾነው በዓቢየ እግዚእ ኪዳነምሕረት፣ በመቀሌ እንዳ ገብርኤል /እንዳ አቡነ ዓቢየ እግዚእ/፣ በአዲስ አበባ ሞጆ አካባቢ ባለው ቤ.ክ በድምት ይከበራል፡፡) እንዲሁም
✍️ (የአቡነ ዮሴፍ በላስታ ላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኘውና ወደ ላለበላ የሚጓዝ ኹሉ ሊያየው በሚችል በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘውና በኢትዮጵያ በከፍታ ከራስ ደጀን ተራራ ቀጥሎ በሚገኘው የዋሻ ገዳማቸው ይከበራል)፡፡

ሁለቱም ቅዱሳን አስካሁን ጊዜ ድረስ የሚታይ ባለ አስደናቂ የቃልኪዳን ተዓምራት አላቸው፤ አቡነ ዮሴፍ ከላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ገዳማቸው #ጭላዳ_እህል_ጠባቂ_ሳያሻው_እህል_እንዳይበላ_ገዝተውታል፤ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ቦታ (ለምሳሌ በጎንደር ከተማ) አሁንም ድረስ #ጅብ_እንስሳቶችን_እንዳይበላ_ገዝተዋል፡፡

#አቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋቱ
* በወሎ ላስታ ሰውንና ዝንጀሮን በቃል ኪዳን ያስተሳሰሩ
#እስከዛሬ_ድረስ_ዝንጀሮ_እህል_እንዳይበላ_የገዘቱ
* እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው፤
* ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑ (እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባና አቡነ ዘርዓ ቡሩክ) ናቸው፤
* ወደ ደብረ ሐዊ በመሄድ ሱባዔ ገብተው ቅዱስ ያሬድን በተሰወረበት የተመለከቱ፤
* ገዳማቸው በላሊበላ በቅርበት አቡነ ዮሴፍ ተራራ ተብሎ በሚጠራ ተራራ ቦታ ላይ የሚገኝ የዋሻ ቤ.ክ አላቸው፡፡

#አባ_ዓቢየ_እግዚእ_
* አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ፡፡
* አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጕመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው::
* በሕፃንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ፡፡
* ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኰስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኵሰዋል፡፡
* በደብረ በንኰል ገዳም በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያንን አግኝተዋል፤ በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር፡፡
ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል፡፡
* ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ፡፡ ከትግራይ እስከ ደንቢያ ሃገረ ስብከታቸው ነው::
* አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ፤ ቀኑ ነሐሴ 10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ፤ ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ፤ ይህን ድንቅ ያዩ ከ1,000 በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል፤ ይህም ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል::
* ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ፤ ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች፤ ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ፥ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር፤ በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ፥ እባብና መሰል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት፤ ይህንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ፤ በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ፡፡
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ ‹‹በስምህ የተማጸኑ፥ በቃል ኪዳንህ ያመኑ፥ በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም፤ በሰማይም እሳትን አያዩም፤ ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም፡፡›› ብሏቸው አርጓል፡፡ ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል፡፡
ዛሬም ድረስ ከብቶችን ጅብና መሰል አውሬ እየበላ የሚያስቸግራቸው ምዕመናን ገድላቸውን ሲያስነብቡ ይርቃሉ፡፡
* አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው፥ 3 ሙታንን አስነስተው፥ ብዙ ድውያንን ፈውሰው፥ ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው፥ የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው፥ በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል፡፡
** አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን፡፡
@petroswepawulos
††† እንኳን ለቅዱስ መርቆሬዎስ እና ለቅዱሳኑ ቴክላ: አበከረዙን: ዱማድዮስ እና ኄኖክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ †††

††† ቅዱሱ ከቀደምት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በ200 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለደ ይታመናል:: ወላጆቹ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና የመጡት በተአምር ነው:: ስማቸውም #ታቦትና_ኖኅ ይባላሉ:: ቅዱሱ መጀመሪያ " #ፒሉፓዴር" ይባል ነበር:: ትርጉሙ "የአብ ወዳጅ" እንደ ማለት ነው::

ቀጥሎም " #መርቆሬዎስ" ተብሏል:: ይኸውም " #የኢየሱስ_ክርስቶስ_አገል ጋይ" እንደ ማለት ነው:: በጦርነት ኃይለኛ: በመልኩ ደመ ግቡና ተወዳጅ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ስለ ክርስትናው መከራን የተቀበለው በ20 ዓመቱ ነው:: ዘመኑም በዳኬዎስ ቀዳማዊ ነው::

ስለ ሃይማኖቱም ለ5 ዓመታት መከራን ታግሦ በ25 ዓመቱ (ማለትም በ225 ዓ/ም) ሕዳር 25 ቀን አንገቱን ተከልሏል:: በዓለማቀፍ ደረጃም ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብሩ ከሊቀ ሰማዕታት ቀጥሎ የሚገኝ ነው::

በተለይ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲሆን ቤቱ በታነጸበት ሁሉ ተአምራትን ያደርጋል:: ስለዚህ ነገር ታሪክ ብቻ ሳይሆን እኛ ኃጥአንም ምስክሮች ነን:: ጋሹ አምባን ጨምሮ ዛሬም ቅዱሱ ድንቆችን ይሠራል::

††† ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ †††

††† ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኄኖክ ከአባታችን አዳም 7ኛው ደግ ሰው ሲሆን አባቱ #ያሬድ ይባላል:: በእርግጥ ቅዱሱ ሚስት አግብቶ #ማቱሳላና ሌሎች ልጆችን ወልዷል:: አካሔዱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነበርና ሞትን አላየም::

#ነቢዩ_ኄኖክ በ1486 ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ( #መጽሐፈ_ኄኖክን) ጽፏል:: የዚሕ መጽሐፍ ባለቤት ደግሞ ሃገራችን ናት:: ቅዱሱ ብዙ ሰማያዊ ምሥጢሮችን ተመልክቷል::

የእርሱ ሞትን አለመቅመስ #በአቤል ሞት የፈሩትን #ውሉደ_አዳም በተስፋ አነቃቅቷቸዋል::
"በአቤል አፍርሆሙ:
ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለው ሊቁ:: (ዘፍ. 5:24, ኄኖክ. 4:1)

††† ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት †††

††† እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር::

እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " #ሐዋርያዊት" ብላ ታከብራታለች::

††† ቅዱስ አበከረዙን ጻድቅ ወሰማዕት †††

††† ስም አጠራሩ የከበረ ታላቁ #አባ_አበከረዙን ወደ ክርስትና የተጠራው ከሽፍታነት (ስርቆት) ሕይወት ነው:: ከአጋሮቹ ጋር ገዳም ለመዝረፍ ሒደው አንድ ባሕታዊ ከማታ 12:00 እስከ ጧት 12:00 ሲጸልይ አይተው ተጸጽተው ንስሃ ገብተዋል::

አበከረዙን ግን ዓለምን ንቆ በምናኔ ለ7 ዓመታት ተጋድሏል:: ነገር ግን ሰማዕት ለመሆን ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከገዳም ወደ ከሃድያን ነገሥታት ሃገር ሔዶ ስመ ክርስቶስን ሰብኩዋል:: በእርሱ ላይ ከደረሱ ስቃዮች ብዛት የተነሳ ከሥጋው: ከአጥንቱና ከደሙ የተረፈለት የለም::

እንዲያውም አንዴ በዓየር ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ደሙ በአፍና በአፍንጫው እየጐረፈ ለ10 ቀናት ቆይቷል:: በወቅቱ የመኮንኑ ሴት ልጅ እየመጣች ያለ ርሕሪሔ ታሰቃየው ነበርና እርሷን መልአክ ወርዶ ቀሥፎ ገደላት::

እርሱ በተሰቀለ በ22ኛው ቀን: እርሷ በተቀበረች በደግሞ በ12ኛው ቀን ከተሰቀለበት አውርደውት ከሞት አስነስቷታል:: ታላቁ አበከረዙንን በዚህች ቀን ብዙ አሰቃይተው: ወገቡን ሰብረው: አንገቱንም ሰይፈው ገድለውታል::

††† ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ †††

††† ለቤተ ክርስቲያን በንጹሕ ሕይወታቸው ካበሩላት ዐበይት ቅዱሳን አንዱ #ቅዱስ_ዱማድዮስ ነው:: እርሱ ወደ ክርስትና የመጣው ከባዕድ አምልኮ ሲሆን መሪው #መንፈስ_ቅዱስ ነው:: ጣዕመ ሕይወቱን ሲሰሙት ዕዝነ ልቡናን ደስ ያሰኛል::

ገና በወጣትነቱ እንደ #ሐዋርያት ሰብኮ አሕዛብን አሳምኗል:: እንደ #ጻድቃን አካሉ አልቆ አጥንቶቹ እስኪታዩ ተጋድሏል:: እርሱ #ድንግል: #ንጹሕ: #መነኮስ: #ባሕታዊና #ካህን ነው:: ግን ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላል:: በዚህ ምክንያት ካደረበት አይውልም: ከዋለበትም አያድርም::

እርሱ በጸሎቱ የተዘጉ ማሕጸኖችን ከፍቷል:: ዕውራንን አብርቷል:: ለምጻሞችን አንጽቷል:: አንካሶችን አርትቷል:: በፈጣሪው ኃይል ፈሳሽ ወንዝን አቁሟል:: እንደ ገናም እንደ ነበረው መልሶታል::

የቅዱስ ዱማድዮስ መጨረሻው ደግሞ #ሰማዕትነት ነው:: በበዓቱ ውስጥ ሳለ ከደቀ መዝሙሩ ጋር ክፉዎች በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: ድንጋዩም የኮረብታ ያህል ነበር:: ልክ በዓመቱ በዚህች ዕለት ምዕመናን ሥጋውን አፍልሠዋል::

††† ቸር አምላክ ከነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃንና ሰማዕታት ክብርን ያሳትፈን::

††† ሐምሌ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ)
3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
4.ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት)
5.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት)
6.ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት
7.ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት
8.ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት
9.አባ ይስሐቅ ሰማዕት
10.አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ
11."25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
3.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

††† "እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::" †††
(ዕብ. 6:10-13)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@petroswepawulos
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ መስከረም ፳፫ (23) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን #ጻድቃን_ወሰማዕት
#አውናብዮስና_እንድርያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል
በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ #ቅዱሳን_አበው_አውናብዮስ_ወእንድርያስ +"+

=>4ኛው መቶ ክ/ዘ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዘመነ
ከዋክብት ይባላል:: ምናልባትም በዓለም ላይ ላለፌት
1,500 ዓመታት ያንን ዘመን መልሶ ማየት አልተቻለም::

*ያ ዘመን ብዙ #ሰማዕታት ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #ሊቃውንት ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #ጻድቃን ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #ደናግል ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #መነኮሳት ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #ባህታውያን (ግኁሳን) ነበሩበት::

+ዘመኑ #ዘመነ_ብርሃን ነው:: እልፍ አእላፍ ቅዱሳን
በዚህ ዘመን አብርተዋልና:: ጠላት ሰይጣንን ከቦታው
አሳድደው አስጨንቀውታል:: በዚህ ዘመነ ብርሃን ከወደ
ምሥራቅ ካበሩ ከዋክብት መካከል ደግሞ በዚህ ዕለት
አባቶቻችን ቅዱሳን አውናብዮስና እንድርያስን
እናዘክራለን::

+ቅዱሳኑ ባለ ብዙ ሃብት ነበሩ:: ከሰማዕታት: ከጻድቃን:
ከደናግል: ከሊቃውንቱም አሉበት:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

¤በተጠቀሰው ዘመን በቅዱስ #ጊዮርጊስ ሃገር በልዳ
ከከበሩ ወገኖች ተወልደዋል::

+የቅዱሳኑ ወላጆች ክርስቲያኖች: በዚያውም ላይ ባለ
ሥልጣኖችና ሃብታሞች ነበር:: ልጆቻቸውን
(አውናብዮስንና እንድርያስን) ሥጋዊውንም:
መንፈሳዊውንም ትምሕርት አስተምረዋቸዋል:: ወጣት
በሆኑ ጊዜ ወላጆቻቸው የዚህን ዓለም ነገር
ሲያስቡላቸው: እነሱ ግን የተሻለውን እድል ያስቡ ነበር::

+ዘወትር ገድላተ ቅዱሳንን ያነቡ: ዜና አበውን ይሰሙ
ነበርና ይመንኑ ዘንድ ልቡናቸው አወካቸው:: በአንዲት
ሌሊት ግን በመንፈስ ቅዱስ አጋዘዥነት ወስነው:
ከሃገራቸው #ልዳ ወጥተው ወደ ገዳም ሔዱ::

+ክብር ለቅዱሳኑ #አባ_ሮማኖስና #አባ_በርሶማ ይሁንና
በወቅቱ በሶርያ ምድር ገዳማዊ ሕይወት ተስፋፍቶ: ብዙ
አድባራት በበርሃ ውስጥ ነበሩ:: 2ቱ ቅዱሳንም በአንዱ
ገዳም ውስጥ ገብተው አገለገሉ::

+ተጋድሏቸውን እያበረቱ እስከ ምንኩስና ደረጃም ደረሱ::
ተጋድሏቸው በጾም: በጸሎትና በትእግስት ብቻ
አይደለም:: በትሕትና በፍቅር በደግነትና በመታዘዝም
ጭምር ነበር እንጂ::

+የምንኩስናና የገዳማዊ ሕይወት ጠላት 'ፍቅረ ዓለምና
ፍትወት እንስሳዊት' ናቸው:: አንድ ሰው ከዚህ ዓለም
ቁሳቁስ ሳይርቅ መናኝ መሆን አይችልም:: ቅዱሳኑ ግን
በመንኖ ጥሪት ይህችን ዓለም ከነኮተቷ ናቁዋት:
አቃለሏት::

+የሥጋ ፈቃዳቸውን ያጠፉ ዘንድ ሰውነታቸውን በጾምና
በጸሎት: ዕረፍትም በማሳጣት ቀጧት:: #እግዚአብሔር
ደግሞ ስለዚህ ፈንታ ጸጋውን አበዛላቸው:: ቅዱሳኑ
በሶርያ ገዳማት ለዘመናት ከተጋደሉ በሁዋላ ወደ ግብጽ
ለመውረድ ወሰኑ:: ምክንያታቸው ደግሞ:-

1ኛ.ከውዳሴ ከንቱ ለመራቅ
2ኛ.ከቅዱሳን አበው ለመባረክ እና
3ኛ.ለተሻለ ተጋድሎ ለመብቃት ነበር:: እየጸለዩ
እያመሰገኑም ግብጽ: ቀጥሎም ገዳመ አስቄጥስ ደረሱ::

+ታላቁ #ርዕሰ_መነኮሳት_አባ_መቃርስን ፊት ለፊት
ቢያገኙት ደስ አላቸው:: ሐሴትንም አደረጉ::
እግዚአብሕርን በማደሪያዎቹ ማግኘት ይቻላልና:: የታላቁ
ቅዱስ ደቀ መዝሙር ሆነው: በድንግልና ተጠብቀው:
በተጋድሎ በርትተው በቦታው ለ3 ዓመታት ቆዩ::

+እግዚአብሔር ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ፈልጐአቸው
ነበርና በዚያ ሰሞን በከተማ የነበሩ ሊቃውንት ወደ ገዳም
መጡ:: ገዳማውያንንም ዻዻስ ስላረፈብን "የምንሾመው
መልካም እረኛን ስጡን" አሏቸው::

+ገዳማውያኑ ሱባኤ ገብተው ቢጠይቁ መንፈስ ቅዱስ
ቅዱስ አውናብዮስን መረጠ:: አበውም ቅዱሱን ዽዽስና
ሲሾሙት ወንድሙን እንድርያስን ረዳት አደረጉት:: 2ቱ ቅዱሳን ከበርሃ ወደ
ከተማ መውጣታቸውን ተከትሎ ተጋድሏቸውን ለማበርታት
ወሰኑ::

+ምክንያቱም ለአንድ ገዳማዊ ከተማ ውስጥ ከመኖር
በላይ ፈተና የለምና:: ቅዱሳኑ ቀን ቀን ድውያንን
ሲጠይቁ: ሙታንን ሲቀብሩ: ሕዝቡን ሲያስተምሩ:
ሥጋውን ደሙን ሲያቀብሉ ውለው ሌሊት ይጋደላሉ::

+ለፈቃደ ሥጋቸው ሳያደሉ እንዲህ ባለ ቅድስና ኖረው
ደግሞ ሌላ ፈተና መጣ:: የከተማው ሃገረ ገዢ አረማዊ
በመሆኑ "ለጣዖት ስገዱ: ክርስቶስን ካዱ" ይል ጀመር::
ቅዱሳኑ ሕዝቡን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም
ሊያስተምሩ ወደዋልና መኮንኑን "ተው! ተሳስተሃል"
አሉት::

+በዚህ ምክንያትም ብዙ ስቃይ ገጠማቸው::
በመጨረሻም በዚህች ዕለት ሰማዕት ሆነዋል:: ጌታም
ስለ ድንግልናዊ ሕይወታቸው: ስለ ወንጌል
አገልግሎታቸውና ስለ ሰማዕትነታቸው 3 አክሊላትን
አቀዳጅቷቸዋል::

=>አምላከ አበው ቸርነቱን ይላክልን:: የቅዱሳኑን
በረከትም ያሳድርብን::

=>መስከረም 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱሳን ጻድቃን አውናብዮስ ወእንድርያስ (ሰማዕታት)
2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ መንክራዊ
3.ቅድስት ቴክላ ድንግል
4.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል

=>+"+ በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ
ማን ነው? ነገር ግን ስለ #ጽድቅ እንኩዋ መከራን
ብትቀበሉ #ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ:
አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን
በልባችሁ ቀድሱት:: +"+ (1ዼጥ.3:13)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@petroswepawulos
††† እንኳን ለቅዱስ መርቆሬዎስ እና ለቅዱሳኑ ቴክላ: አበከረዙን: ዱማድዮስ እና ኄኖክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ †††

††† ቅዱሱ ከቀደምት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በ200 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለደ ይታመናል:: ወላጆቹ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና የመጡት በተአምር ነው:: ስማቸውም #ታቦትና_ኖኅ ይባላሉ:: ቅዱሱ መጀመሪያ " #ፒሉፓዴር" ይባል ነበር:: ትርጉሙ "የአብ ወዳጅ" እንደ ማለት ነው::

ቀጥሎም " #መርቆሬዎስ" ተብሏል:: ይኸውም " #የኢየሱስ_ክርስቶስ_አገል ጋይ" እንደ ማለት ነው:: በጦርነት ኃይለኛ: በመልኩ ደመ ግቡና ተወዳጅ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ስለ ክርስትናው መከራን የተቀበለው በ20 ዓመቱ ነው:: ዘመኑም በዳኬዎስ ቀዳማዊ ነው::

ስለ ሃይማኖቱም ለ5 ዓመታት መከራን ታግሦ በ25 ዓመቱ (ማለትም በ225 ዓ/ም) ሕዳር 25 ቀን አንገቱን ተከልሏል:: በዓለማቀፍ ደረጃም ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብሩ ከሊቀ ሰማዕታት ቀጥሎ የሚገኝ ነው::

በተለይ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲሆን ቤቱ በታነጸበት ሁሉ ተአምራትን ያደርጋል:: ስለዚህ ነገር ታሪክ ብቻ ሳይሆን እኛ ኃጥአንም ምስክሮች ነን:: ጋሹ አምባን ጨምሮ ዛሬም ቅዱሱ ድንቆችን ይሠራል::

††† ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ †††

††† ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኄኖክ ከአባታችን አዳም 7ኛው ደግ ሰው ሲሆን አባቱ #ያሬድ ይባላል:: በእርግጥ ቅዱሱ ሚስት አግብቶ #ማቱሳላና ሌሎች ልጆችን ወልዷል:: አካሔዱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነበርና ሞትን አላየም::

#ነቢዩ_ኄኖክ በ1486 ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ( #መጽሐፈ_ኄኖክን) ጽፏል:: የዚሕ መጽሐፍ ባለቤት ደግሞ ሃገራችን ናት:: ቅዱሱ ብዙ ሰማያዊ ምሥጢሮችን ተመልክቷል::

የእርሱ ሞትን አለመቅመስ #በአቤል ሞት የፈሩትን #ውሉደ_አዳም በተስፋ አነቃቅቷቸዋል::
"በአቤል አፍርሆሙ:
ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለው ሊቁ:: (ዘፍ. 5:24, ኄኖክ. 4:1)

††† ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት †††

††† እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር::

እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " #ሐዋርያዊት" ብላ ታከብራታለች::

††† ቅዱስ አበከረዙን ጻድቅ ወሰማዕት †††

††† ስም አጠራሩ የከበረ ታላቁ #አባ_አበከረዙን ወደ ክርስትና የተጠራው ከሽፍታነት (ስርቆት) ሕይወት ነው:: ከአጋሮቹ ጋር ገዳም ለመዝረፍ ሒደው አንድ ባሕታዊ ከማታ 12:00 እስከ ጧት 12:00 ሲጸልይ አይተው ተጸጽተው ንስሃ ገብተዋል::

አበከረዙን ግን ዓለምን ንቆ በምናኔ ለ7 ዓመታት ተጋድሏል:: ነገር ግን ሰማዕት ለመሆን ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከገዳም ወደ ከሃድያን ነገሥታት ሃገር ሔዶ ስመ ክርስቶስን ሰብኩዋል:: በእርሱ ላይ ከደረሱ ስቃዮች ብዛት የተነሳ ከሥጋው: ከአጥንቱና ከደሙ የተረፈለት የለም::

እንዲያውም አንዴ በዓየር ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ደሙ በአፍና በአፍንጫው እየጐረፈ ለ10 ቀናት ቆይቷል:: በወቅቱ የመኮንኑ ሴት ልጅ እየመጣች ያለ ርሕሪሔ ታሰቃየው ነበርና እርሷን መልአክ ወርዶ ቀሥፎ ገደላት::

እርሱ በተሰቀለ በ22ኛው ቀን: እርሷ በተቀበረች በደግሞ በ12ኛው ቀን ከተሰቀለበት አውርደውት ከሞት አስነስቷታል:: ታላቁ አበከረዙንን በዚህች ቀን ብዙ አሰቃይተው: ወገቡን ሰብረው: አንገቱንም ሰይፈው ገድለውታል::

††† ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ †††

††† ለቤተ ክርስቲያን በንጹሕ ሕይወታቸው ካበሩላት ዐበይት ቅዱሳን አንዱ #ቅዱስ_ዱማድዮስ ነው:: እርሱ ወደ ክርስትና የመጣው ከባዕድ አምልኮ ሲሆን መሪው #መንፈስ_ቅዱስ ነው:: ጣዕመ ሕይወቱን ሲሰሙት ዕዝነ ልቡናን ደስ ያሰኛል::

ገና በወጣትነቱ እንደ #ሐዋርያት ሰብኮ አሕዛብን አሳምኗል:: እንደ #ጻድቃን አካሉ አልቆ አጥንቶቹ እስኪታዩ ተጋድሏል:: እርሱ #ድንግል: #ንጹሕ: #መነኮስ: #ባሕታዊና #ካህን ነው:: ግን ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላል:: በዚህ ምክንያት ካደረበት አይውልም: ከዋለበትም አያድርም::

እርሱ በጸሎቱ የተዘጉ ማሕጸኖችን ከፍቷል:: ዕውራንን አብርቷል:: ለምጻሞችን አንጽቷል:: አንካሶችን አርትቷል:: በፈጣሪው ኃይል ፈሳሽ ወንዝን አቁሟል:: እንደ ገናም እንደ ነበረው መልሶታል::

የቅዱስ ዱማድዮስ መጨረሻው ደግሞ #ሰማዕትነት ነው:: በበዓቱ ውስጥ ሳለ ከደቀ መዝሙሩ ጋር ክፉዎች በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: ድንጋዩም የኮረብታ ያህል ነበር:: ልክ በዓመቱ በዚህች ዕለት ምዕመናን ሥጋውን አፍልሠዋል::

††† ቸር አምላክ ከነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃንና ሰማዕታት ክብርን ያሳትፈን::

††† ሐምሌ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ)
3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
4.ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት)
5.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት)
6.ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት
7.ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት
8.ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት
9.አባ ይስሐቅ ሰማዕት
10.አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ
11."25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
3.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

††† "እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::" †††
(ዕብ. 6:10-13)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ሁሉ በእጅጉ ሲገረምና ‹‹በአምላከ ታዴዎስ ስም አምናለሁ›› ሲል የባለጸጋው ልጅ ሙሳ ግን ‹‹በምትሃት አሳይቶን ነው እንጂ የእውነት አይደለም›› በማለት አባቱንም እንዳያምን ይናገር ጀመር፡፡ ይህንንም ሲናገር በመጀመሪያ ያለፈችው እናቲቱ ግመል እረግጣ ገደለችው፡፡

አቡነ ታዴዎስም ንጉሡን፣ አባቱን አፍጃልንና ሕዝቡን የሞተ እንደሚነሣ ሲያስምሯቸው ‹‹የሞተ ይነሣልን? እስኪ ይህ የሞተው ልጅ ይነሳና ሁሉም አይቶ ይመን›› አሏቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹ዛሬ ተቀብሮ ይዋልና ነገ በሦስተኛው ይነሣል›› ብለዋቸው ተቀብሮ ዋለ፡፡ በማግሥቱም አፍጃልን ጠርተው ‹‹‹አልዓዛርን ከሞት ባስነሣው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልጄ ሆይ ና ውጣ› ብለህ ከልጅህ መቃብር ላይ አኑረው› ብለው ዘንጋቸውን ሰጡት፡፡ ሄዶም እንዳሉት ቢያደርግ ልጁ አፈፍ ብሎ ተነሥቷል፡፡ ይህንን ያዩ የሀገሩ ሰዎች ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል፡፡ እሳቸውም 12 አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸው ሞቶ የተነሳውን ሙሳን ሙሴ ብለው ሰይመው አስተምረው ሊቀ ካህናት አድርገው ሾመውት አቡነ አኖሬዮስን ይዘው ወደ ጽላልሽ ዞረሬ ተመልሰዋል፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በኋላ አባ ያዕቆብ የተባሉ ጳጳስ ከግብፅ መጡ፡፡ የአቡነ ታዴዎስን ዜና ሲሰሙ ተደስተው ከአቡነ ፊሊጶስ ጋር ሆነው አስጠርተዋቸው ‹‹የአባታችሁን ዜና ገድል ንገሩኝ›› አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም ‹‹ጨዋታ በአስተርጓሚ አይሰምርም›› ብለው ወደ ጌታችን ቢጸልዩ የጳጳሱ ቋንቋ ለታዴዎስ፣ የታዴዎስም ቋንቋ ለጳጳሱ ተገልጦላቸው የመሸ የነጋ ሳይመስላቸው 40 ጾምን ሲጨዋወቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ጳጳሱ ከንጉሡ ተማክረው ‹‹ሊቀ ካህናት ዘጽላልሽ›› ብለው ሾመዋቸዋል፡፡

በነግህና በሰርክ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ፣ ቀን ወንጌልን እየሰበኩ፣ ሌሊት ከባሕር ገብተው ሲጸልዩ እያደሩ በታላቅ ተጋድሎ እየኖሩ ሳለ ከ10 ዓመት በኋላ ሰይጣን በንጉሡ በዓምደ ጽዮን ፍቅረ ዝሙት አሳድሮበት በክፉዎችም ምክር አታሎት የአባቱን ቅምጥ አገባ፡፡ አቡነ ታዴዎስም ይህን ሲሰሙ እንደ ነቢዩ ኤልያስና እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ገሥጸው አወገዙት፡፡ ገሥጸውና አውግዘው አቡነ ማትያስን አስከትለው ሲመለሱ ቅምጧ የንጉሡ ሚስት በፈረስ ተከትላ ደርሳ የኋሊት አሳስራ ዛሬ ‹‹ማርያም ገዳም›› ከሚባለው ቦታ ፊት ለፊት ካለው ትልቅ ገደል ውስጥ ሁለቱንም ጣለቻቸውና ጥር 29 ቀን በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡

በሰማዕትነት ዐርፈው ደማቸው ከፈሰሰበት ከገደሉ ስር በፈለቀው ጸበላቸው ‹‹ታዴዎስ ወማትያስ›› እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያለ የተጠመቀ ሰው እንደ 40 ቀን ሕፃን እንደሚሆን ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቷቸዋል፡፡ ይህ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ የተሠራው ቤተ ክርስቲያናቸው በጠላት ወረራ ጊዜ ፈርሶ ቦታው ጠፍ ሆኖ የኖረ ቢሆንም የአካባቢው ሕዝብ ቦታውን ከልሎ በክብር ሲጠብቀው ስለኖረ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ የአቡነ ታዴዎስ ታቦታቸው በ2005 ዓ.ም ከኢቲሣ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ወጥቶ ጻድቁ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ በተሠራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያናቸው በታላቅ ክብር ገብቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑም ከኢቲሣ በእግር የአንድ ሰዓት ተኩል ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቃን_ቅዱሳን_ማሕበረ_ዶጌ (ዴጌ ጻድቃን)

በዚህች እለት የጻድቃን ቅዱሳን ማኅበረ ዶጌ አክሱም አካባቢ በቁጥር ወደ 3000 የሚሆኑ ከመድኃኔዓለም ጋር ማኅበር ይጠጡ የነበሩ በአንድ ላይ የተሰወሩ ቅዱሳን መታሰቢቸው ነው፡፡ እነዚህም ጌታችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ በመካከላቸው ተገኝቶ የጽዋ ማኅበራቸውን አብሯቸው የጠጣ ሦስት ሺህ ቅዱሳን ‹‹ማኅበረ ጻድቃን ወይም ማኅበረ ደጌ›› እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ማኅበሩን ያቋቋመው ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ነው፡፡ በኋላም ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ጋር አብረው ማኅበር የጠጡ እነዚህ ሦስት ሺህ ቅዱሳን አክሱም አካባቢ ባለው በአቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ገዳም ጥር 29 ቀን በዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ይከብራሉ፡፡ ማኅበረ ዴጌ ማለት የደጋጎች ሀገር ማለት ነው፡፡ የደጋጎች ሀገር የተባለበት ምክንያት ብዙ ሺህ ቅዱሳን ተሰብስበው ስለሚኖሩበት ነው፡፡ ገዳሙ የሚገኘው በትግራይ ክልል በአክሱም አውራጃ ከአክሱም ከተማ ወደ ደቡብ ምዕራብ በሚወስደው መንገድ አስራ ሁለት ኪሎሜትር ያህል ርቀት ላይ ነው፡፡

በቦታው ላይ ጥንት መሥዋዕተ ኦሪት ይሠዋበት ነበር፡፡ በኋላም በ40 ዓ.ም ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ወደ አገራችን በመጣ ጊዜ በቦታው ላይ ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን አጥምቋል፡፡ በወቅቱ የነበረችው ንግሥትም በቅዱስ ማቴዎስ እጅ ተጠምቃለች፡፡ ቅዱስ ማቴዎስም ንግስቲቱን ካጠመቀ በኋላ ቀጥሎ መኳንንቱን፣ መሳፍንቱንና የጦር ሠራዊቱን ሁሉ አጥምቋቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ የጻድቃንን ማህበር አቋቁሞ በጌታችን ስም በየወሩ በ29 ቀን እየተሰበሰቡ ጽዋ እንዲጠጡ አድርጓቸው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዷል፡፡

በ365 ዓ.ም በአስፍሕ ወልደ አብርሃም ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ‹‹ሮምያ›› ከምትባል መንደር ቅዱሳን ‹‹ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁአን ናቸው መንግስተ ሰማያት የነርሱ ናትና›› ያለውን ዳግመኛም ‹‹አባቱንና እናቱን ሚስቱንና ልጆቹን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ብሎ ጌታችን የተናገረውን አስበው ቅዱሳን የዚህም ዓለም ጣዕም ጥቅም ንቀው ሀገራቸውን ትተው መንነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን በአክሱም ከተማ በስተሰሜን በሐውልቱ ጀርባ ቤተ ቀጠንት በሚባል ስፍራ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህል እንደ ተቀመጡ በዚያም ምቾትና ድሎት ስለተሰማባቸው ‹‹ለዚሁ ለዚሁማ ሀገራችንን ለምን ትተን መጣን? ስለዚህ ሱባዔ ገብተን በጾም በጸሎት ተወስነን የምንሄድበትን ቦታ በረከተ ነፍስ የምናገኝበትን ስፍራ እግዚአብሔር እንዲያሳየን እናመልክት›› ብለው ሱባዔ ገቡ ጾም ያዙ፡፡

ከሱባዔውም በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻላቸው ግማሾቹን እያንዳንዳቸው የሚኖሩበትን በዓት አመልክታቸው፣ በዚያም በጾምና በጸሎት ጸንተው እንዲኖሩ ነገረቻቸው፡፡ ሦስት ሺህ ያህሉን ደግሞ ከላይ ወደጠቀስነው ሥፍ ሄዱ፡፡ ከእነርሱ የተቀሩት ደግሞ ወደ ቆየፃ ሓባር፣ ተድባ፣ አኮርየን፣ ተንስሓ፣ ደብረ አንሳ ወደ ተባሉ ቦታዎች ሄደዋል፡፡ ተጨማሪ ሥስት ሺህ የሚሆኑት ደግሞ እዚያ ከነበሩት ጋር ተደመሩ፡፡ ከዚህም በኋላ እነዚህ ቅዱሳን ‹‹ከሁሉ ፍቅር ይበልጣል›› የሚለውን ጠብቀው በእምነት በፍቅር በአንድነት ጸንተው በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ተዝካረ ሰንበትን ጠብቀው ማኅበር ይጠጡ ጀመር፡፡ በዚህም ጊዜ የማኅበረ ዴጌ ታሪክ ተቀየረ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአምሳለ ነዳይ ድሀ መስሎ በመካከላቸው ተገኘ፡፡ ግን ማንም አላወቀውም ነበር፡፡ ጌታችንም ከእነርሱ ጋር አንድ ማኅበርተኛ ሁኖ እንዲታወቅ ጠየቃችው፣ እነርሱም ፈቀዱለትና አንዱ የማኅበሩ አባል ሆነ፡፡ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህልም ከእነርሱ ጋር ሳይለይ ቆየ፡፡ በዚሁ ጊዜ ‹‹እስቲ ለእኔም ተራ ስጡኝ እንደአቅሜ ዝክር ላውጣ›› አላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ድህነቱን አይተው ‹‹አይሆንም አንተ ድሀ ነህ፣ ከኛ ጋር ሁነህ በዓሉን አክብር እንጂ ምን አለህና ነው የምትደግሰው? ይቅርብህ›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹አይሆንም ስጡኝ እንጂ›› ብሎ ግድ አላቸው፡፡ እነርሱም ካልክማ ብለው ቀን ወስነው ሰጡት፡፡ ቀኑም ጥር 29 ነበር፡፡