መዝገበ ቅዱሳን
20.7K subscribers
1.92K photos
9 videos
6 files
24 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
††† እንኳን ለቅዱስ መርቆሬዎስ እና ለቅዱሳኑ ቴክላ: አበከረዙን: ዱማድዮስ እና ኄኖክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ †††

††† ቅዱሱ ከቀደምት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በ200 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለደ ይታመናል:: ወላጆቹ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና የመጡት በተአምር ነው:: ስማቸውም #ታቦትና_ኖኅ ይባላሉ:: ቅዱሱ መጀመሪያ " #ፒሉፓዴር" ይባል ነበር:: ትርጉሙ "የአብ ወዳጅ" እንደ ማለት ነው::

ቀጥሎም " #መርቆሬዎስ" ተብሏል:: ይኸውም " #የኢየሱስ_ክርስቶስ_አገል ጋይ" እንደ ማለት ነው:: በጦርነት ኃይለኛ: በመልኩ ደመ ግቡና ተወዳጅ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ስለ ክርስትናው መከራን የተቀበለው በ20 ዓመቱ ነው:: ዘመኑም በዳኬዎስ ቀዳማዊ ነው::

ስለ ሃይማኖቱም ለ5 ዓመታት መከራን ታግሦ በ25 ዓመቱ (ማለትም በ225 ዓ/ም) ሕዳር 25 ቀን አንገቱን ተከልሏል:: በዓለማቀፍ ደረጃም ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብሩ ከሊቀ ሰማዕታት ቀጥሎ የሚገኝ ነው::

በተለይ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲሆን ቤቱ በታነጸበት ሁሉ ተአምራትን ያደርጋል:: ስለዚህ ነገር ታሪክ ብቻ ሳይሆን እኛ ኃጥአንም ምስክሮች ነን:: ጋሹ አምባን ጨምሮ ዛሬም ቅዱሱ ድንቆችን ይሠራል::

††† ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ †††

††† ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኄኖክ ከአባታችን አዳም 7ኛው ደግ ሰው ሲሆን አባቱ #ያሬድ ይባላል:: በእርግጥ ቅዱሱ ሚስት አግብቶ #ማቱሳላና ሌሎች ልጆችን ወልዷል:: አካሔዱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነበርና ሞትን አላየም::

#ነቢዩ_ኄኖክ በ1486 ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ( #መጽሐፈ_ኄኖክን) ጽፏል:: የዚሕ መጽሐፍ ባለቤት ደግሞ ሃገራችን ናት:: ቅዱሱ ብዙ ሰማያዊ ምሥጢሮችን ተመልክቷል::

የእርሱ ሞትን አለመቅመስ #በአቤል ሞት የፈሩትን #ውሉደ_አዳም በተስፋ አነቃቅቷቸዋል::
"በአቤል አፍርሆሙ:
ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለው ሊቁ:: (ዘፍ. 5:24, ኄኖክ. 4:1)

††† ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት †††

††† እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር::

እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " #ሐዋርያዊት" ብላ ታከብራታለች::

††† ቅዱስ አበከረዙን ጻድቅ ወሰማዕት †††

††† ስም አጠራሩ የከበረ ታላቁ #አባ_አበከረዙን ወደ ክርስትና የተጠራው ከሽፍታነት (ስርቆት) ሕይወት ነው:: ከአጋሮቹ ጋር ገዳም ለመዝረፍ ሒደው አንድ ባሕታዊ ከማታ 12:00 እስከ ጧት 12:00 ሲጸልይ አይተው ተጸጽተው ንስሃ ገብተዋል::

አበከረዙን ግን ዓለምን ንቆ በምናኔ ለ7 ዓመታት ተጋድሏል:: ነገር ግን ሰማዕት ለመሆን ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከገዳም ወደ ከሃድያን ነገሥታት ሃገር ሔዶ ስመ ክርስቶስን ሰብኩዋል:: በእርሱ ላይ ከደረሱ ስቃዮች ብዛት የተነሳ ከሥጋው: ከአጥንቱና ከደሙ የተረፈለት የለም::

እንዲያውም አንዴ በዓየር ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ደሙ በአፍና በአፍንጫው እየጐረፈ ለ10 ቀናት ቆይቷል:: በወቅቱ የመኮንኑ ሴት ልጅ እየመጣች ያለ ርሕሪሔ ታሰቃየው ነበርና እርሷን መልአክ ወርዶ ቀሥፎ ገደላት::

እርሱ በተሰቀለ በ22ኛው ቀን: እርሷ በተቀበረች በደግሞ በ12ኛው ቀን ከተሰቀለበት አውርደውት ከሞት አስነስቷታል:: ታላቁ አበከረዙንን በዚህች ቀን ብዙ አሰቃይተው: ወገቡን ሰብረው: አንገቱንም ሰይፈው ገድለውታል::

††† ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ †††

††† ለቤተ ክርስቲያን በንጹሕ ሕይወታቸው ካበሩላት ዐበይት ቅዱሳን አንዱ #ቅዱስ_ዱማድዮስ ነው:: እርሱ ወደ ክርስትና የመጣው ከባዕድ አምልኮ ሲሆን መሪው #መንፈስ_ቅዱስ ነው:: ጣዕመ ሕይወቱን ሲሰሙት ዕዝነ ልቡናን ደስ ያሰኛል::

ገና በወጣትነቱ እንደ #ሐዋርያት ሰብኮ አሕዛብን አሳምኗል:: እንደ #ጻድቃን አካሉ አልቆ አጥንቶቹ እስኪታዩ ተጋድሏል:: እርሱ #ድንግል: #ንጹሕ: #መነኮስ: #ባሕታዊና #ካህን ነው:: ግን ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላል:: በዚህ ምክንያት ካደረበት አይውልም: ከዋለበትም አያድርም::

እርሱ በጸሎቱ የተዘጉ ማሕጸኖችን ከፍቷል:: ዕውራንን አብርቷል:: ለምጻሞችን አንጽቷል:: አንካሶችን አርትቷል:: በፈጣሪው ኃይል ፈሳሽ ወንዝን አቁሟል:: እንደ ገናም እንደ ነበረው መልሶታል::

የቅዱስ ዱማድዮስ መጨረሻው ደግሞ #ሰማዕትነት ነው:: በበዓቱ ውስጥ ሳለ ከደቀ መዝሙሩ ጋር ክፉዎች በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: ድንጋዩም የኮረብታ ያህል ነበር:: ልክ በዓመቱ በዚህች ዕለት ምዕመናን ሥጋውን አፍልሠዋል::

††† ቸር አምላክ ከነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃንና ሰማዕታት ክብርን ያሳትፈን::

††† ሐምሌ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ)
3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
4.ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት)
5.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት)
6.ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት
7.ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት
8.ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት
9.አባ ይስሐቅ ሰማዕት
10.አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ
11."25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
3.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

††† "እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::" †††
(ዕብ. 6:10-13)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@petroswepawulos

ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን አለው።

የከበረ ዮሐንስም ንጉሥ ሆይ እንዲህ አትበል እንዲህ አንተ እንደምትለው አይደለም የከበረች ድንግል እመቤታችንስ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆድዋ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእርሱ ኅብረ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋር መልኳ ይለወዋወጥ ነበር። በንጹሕ ብርሌ ውስጥ ውኃ በጨመሩ ጊዜ ውኃ መስሎ እንደሚታይ ወይን ጠጅም ቢጨምሩ ያንኑ መስሎ እንደሚታይ ወይም ከውስጡ በተጨመረው ቀይም ቢሆን ቀልቶ እንደሚታይ ቅጠልያም ቢገባበት ቅጠልያ መስሎ እንደሚታይ። ድንግልም በሆድዋ ውስጥ የልጅዋ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋራ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። እንደ ሮማን አበባ የምትቀላበት ጊዜ አለ እንደ ናርዶስም የምታብለጨልጭበት ጊዜ አለ የለመለመ ቅጠል የምትመስልበትም ጊዜ አለ ከወለደች በኋላ ግን አልተለወጠችምና ዮሴፍ በአንድ በቀድሞው ኅብረ መልኳ ተወስናለት መልኳን ተረዳ ማለት ነው አለው። በዚያን ጊዜ በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ከወርቅ የተሠራ የእመቤታችን አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ሥዕል ነበረችና አፈ ወርቅ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ አፈ በረከት ዮሐንስ መልካም ተናገርክ የሚል ቃል ከእርሷ ወጣ።

ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያሉት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት በዚያን ጊዜ ንጉሥ አዝዞ ወርቅ ሠሪ አስመጥቶ ለከበረ ዮሐንስ የወርቅ ልሳን አሠርቶ ለሚያየው ሁሉ መታሰቢያ ምልክት ሊሆን አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሥዕል ዘንድ ሰቀለው። ቅዱስ ዮሐንስንም ከዚያች ቀን ወዲህ ልሳነ ወርቅ ብሎ ጠራው አፈ ወርቅም ተብሎ እስከዛሬ ተጠራ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#መነኮስ_ቅዱስ_ዘካርያስ

ዳግመኛም በዚችም ቀን ደግሞ የመነኰስ ዘካርያስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። የዚህም መስተጋድል የአባቱ ስም አቃርዮስ ነው። ይህም አቃርዮስ የምንኲስና ልብስ ሊለብስ ሽቶ ለሚስቱ ነገራት እርሷም በነገራት ነገር ተስማማች። ወንድና ሴት ሁለት ልጆች አሉአቸው እነርሱንም ከእናታቸው ዘንድ ትቶ እርሱ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔዶ ከአንድ አረጋዊ አባት መነኰስ ዘንድ በዚያ መነኰሰ።

ከጥቂት ወራትም በኋላ በሀገር ውስጥ ረኃብ ሆነ ሚስቱም ልጆቿን ይዛ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደባሏ አቃርዮስ መጣች በረኃብም ስለ ሆነው ችግር ነገረችው አቃርዮስም እነሆ እግዚአብሔር በመካከላችን ፍርድን አድርጎ ልጆቻችንን አካፈለን እኔም ወንዱን ልጄን እወስዳለሁ አንቺም ሴት ልጅሽን ውሰጂ አላት ይህንንም ብሎ ልጁን ወሰደ ይኸውም ዘካርያስ ነው እርሷም ሴቷን ልጅዋን ይዛ ተመለሰች።

ከዚህም በኋላ ልጁን ዘካርያስን ወደ ቅዱሳን አረጋውያን አቀረበው እነርሱም በላዩ ጸለዩ ባረኩትም እርሱ ፍጹም መነኲሴ እንደሚሆንም ትንቢት ተናገሩለት።

ዘካርያስም ከበጎ ሥራ ጋር በገዳም ውስጥ አደገ መልኩም እጅግ ያማረ ነው ስለርሱም ጉርምርምታ ሆነ መነኰሳቱም እርስበርሳቸው ይህ ወጣት ይህን ያህል እጅግ መልከ መልካም ሲሆን በገዳም ውስጥ በመነኰሳት መካከል እንዴት ይኖራል ተባባሉ።

ዘካርያስም ስለርሱ መነኰሳት እንዳንጐራጐሩ በሰማ ጊዜ ናጥራን ወደሚባል ተራራ ስር ወደአለች ዐዘቅት ሔደ ልብሱንም አውልቆ በረግረግ ውስጥ ተኛ ሥጋውም ተነፋፍቶ ጠቆረ ተመላልጦም ቈሰለ ብዙ ዘመንም በደዌ እንደኖረ ሆነ፤ ከዚህም በኋላ ልብሱን ለብሶ ወደ ገዳም መጣ ያወቀውም የለም። ከብዙ ቀኖችም በኋላ አባቱ አስተውሎ ልጁ ዘካርያስ እንደ ሆነ አወቀውና መልክህን የለወጠው ምንድን ነው ብሎ ጠየቀው አርሱም ያደረገውን ሁሉ ነገረው።

በእሑድ ቀንም ሥጋውንና ደሙን ሊቀበል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ እግዚአብሔርም ያን ጊዜ ሥራውን ለአባ ኤስድሮስ ገለጸለት እርሱም ዘካርያስ የሠራውን ለወንድሞች መነኰሳት አስረዳቸው እነርሱም አስቀድሞ እንደ ሰው ሁነህ መጣህ ዛሬ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ሁነህ መጣህ አሉት።

ይህ አባት ዘካርያስም በብዙ ገድል ሲጋደል ኖረ ትሕትናን ቅንነትን ያማረ የትሩፋትን ሥራ ሁሉ ገንዘብ አደረገ አባቱም ስለርሱ እኔ በገድል ብዙ ደክሜአለሁ ነገር ግን ከልጄ ሥርዓተ ገድል አልደረስኩም ብሎ ተናገረ።

በዚህ ተጋድሎውም አርባ አምስት ዓመት ኑሮ እግዚአብሔርን ከአገለገለው በኋላ በፍቅር አንድነት አረፈ መላ ዘመኑም ሃምሳ ሁለት ነው። ከዚህም ሰባቱን ዓመት በወላጆቹ ቤት አርባ አምስቱን በገዳም ኖረ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)