መዝገበ ቅዱሳን
20.7K subscribers
1.92K photos
9 videos
6 files
24 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
#ትንቢተ_ኢትዮጵያ

#በ1212 ጀርመን የሚገኝ ብራና መጽሀፍ
ነፍሳቸውን ይማርና አለቃ ታምሩ በኢትዮጵያ ከሰሩት ታላላቅ ሥራዎች አንዱና ዋነኛው ነው።

ትንቢተ-ኢትዮጵያን በ 1212 በግዕዝ የተጻፈውን ወደ አማረኛ በ1949 ዓ/ም ተርጉመው ማተማቸው ነው።
#1ኛ,……#ጊዮርጊስ በፈረስ ሆኖ አድዋ ላይ ይዋጋል።
እውን ሆኖል።

2ኛ,በቋራ አንበሳ ተነፈሰ >> ይልና የአጼ ቴዎድሮስን መምጣት ቀድሞ ትንቢቱ ተናግሮል።

3ኛ, ዘመነ ጎንደር እያለቀ ንግሥናው ወደ ሽዋ ሊመጣ ሲል < ፋሲል ግንብ የቁራ ማደሪያ ይሆንል ይለዋል።

4ኛ, ስለ ንጉሥ አጼ ኃይለስላሴ ደግሞ <<... ፈረሳቸው ሳይቀር ይከዳቸዋል >> ይላል።

5ኛ, ልጅ ኢያሱን ያወሳል ።

#ኢያሱን ላለመካድ መኳንንቶች ተማምለው ነበር።
በኃላ ግን እሱን ክደው የጣይቱ ብጡልን ወንድም ራስ ጉግሳ ገድለው። በዚህ የተነሳ መኮንንቱና ተፈሪ መኮነን << ጥቁር ውሻ ይውልዳሉ.. >> ይላል ፣ ይህ ደግሞ የመንግሥቱ ኃይለማርያምን መምጣት ቀደም ብሎ ተናግሮል ። ታዲያ በዚህ ዘመን << ወላድ እናት ደረቶን ትመታለች ይላል።

6ኛ<<ከስሜን መረብን ከተሻገሩ ዝም በሎቸው >> አባይንና ተከዜን ከተሻገሩ በኃላ ግን እርስ በርሳቸው ይተላለቃሉ >> ይላል ።

ትንቢት ስለ እንቶኔ እሱም እንዲህ ይላል
“ይሄ መንግስትም እንደ አመድ ቡን ብሎe ይጠፋል:: ብዙዎቹም ሀብታቸውን እንኳን የትም ይዘው ለመሄድ እድሉን አያገኙም:: “ምነው” የሚሉበት ግዜም ይመጣል:: ኤርትራውያንም ኢትዮጵያ ውስጥ እህል ውሃ አላቸው ።

ግፍ የሰሩ ሰዎችም “ምነው” ብለው እስኪጸጸቱ ድረስ ፍርዳቸውን ይቀበላሉ ይላል ።
ትንቢት ከውድቀት በኋላ
“በዚያን ግዜ የአህዛብ ንጉስ ይነግሳል:: ለቤተ ክርስትያንና ለክርስትያኖችም መልካም ያልሆነ ግዜ ይሆናል።
ደም ይፈሳል፣ ብዙ በዳር ሀገር ያሉ ክርስትያኖች መክራ ያገኛቸዋል፣ ሰማዕትነት ይቀበላሉ፣ ትልቅ ክብርም ያገኛሉ፣ ከሰማዕትነት ይቆጠርላቸዋል ።r ብዙ ወጣቶችም ይሄን ክብር ይቋደሳሉ:: እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ቅዱስ መርቆርዮስ ሰማዕትነት ይቆጠርላቸዋል። የኑሮ ውድነቱም የከፋ ይሆናል:: የኤድስ በሽታም የሚመሰገንበት ግዜ ይመጣል:: ኤድስ ምናልባትም ለንስሓ ግዜ የማይሰጥ አጣድፎ የሚገድል በሽታ ሳይሆን አይቀርም የሚቆመው መንግስት ለዓለም መንግስታትም ያስቸገረ ይሆናል:: ነገር ግን ስለ ቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ እድሜው አጭር ይሆናል”

#ትንቢት_ስለ_ንጉሥ_ቶዎድሮስ
” ኢትዮጵያን በዘንግ አርባ አመት የሚገዛ ንጉሥ( ቶዎድሮስ ይሉታል) ይነግሳል። የሚነሳውም ከምስራቅ ነው:: በሱ ዘመን ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል። አንድ እንጀራ ለአስር ሰው ያጠግባል። በሱ ዘመን እንኳን የሰው የንጨት ጠማማ አይኖርም፣ ኤርትራም ወደ እናት ሀገሯ ትመለሳለች:: ፍቅርና አንድነት ይሆናል:; ኢትዮጵያ እጅግ ታላቅ ሀገር ትሆናለች::በሱ ዘመን የሚነሱትም ፓትርያርክ እጅግ የበቁና ገቢረ ተአምር የሚያደርጉ ይሆናሉ:: “በዚህ ሰው ንግሥና ዘመን በኢትዮጵያ ፍጹም ሰላም ይሆናል:: በሀገሪቱም በረከት ይዘንባል:: ከሌላው ሀገር ተለይታም የጥጋብና የበረከት ሀገር ትሆናለች:: የበርካታ ሀገር ስደትኞችንም የምታስተናግድ የስደተኞች መጠለያና ማረፍያ ትሆናለች:: ለዘመናት ደም ሲቃቡ የነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያም አንድ ይሆናሉ:: ሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ወንድማማችነታቸውን አድሰው በሰላም በፍቅር ይኖራሉ::

በዛ ዘመን የሚሾሙትም ፓትርያርክ ሕዝብን ከአምላኩ የሚያስታርቁ : ሀገርን በጸሎት የሚጠብቁ ተአምር የማድረግ ጸጋ የተሰጣቸው ትልቅ አባት ናቸው።
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሚያዝያ ጊዮርጊስ "ሚያዝያ ፳፫"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ። ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ። ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ። ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ። ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዓጽሙ።

ዚቅ
በደመ ሰማዕት መዋዕያን : ወበገድለ ጻድቃን ቡሩካን : ተሣሃለነ እግዚኦ።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ። ለወልድኪ አምሳለ ደሙ። መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ። ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ። እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ጻድቃን ይበውኡ ውስቴታ : የዋሃን የዓውዱ መሠረታ : ሰማዕት ይቀውሙ ዓውዳ : በዕለተ #ጊዮርጊስ ስብሐት የዓውዳ ለቅድስት ቤተክርስቲያን።

ነግሥ
ሰላም ለቆምከ ዘአዳም ቆሙ። ወለመልክዕከ በይነ ሰላሙ። ቅዱስ ጊዮርጊስ መክብበ ሰማዕታት ኲሎሙ። ሶበ መተሩ ክሣደከ ምድረ አጥለለት ደሙ። ወጊዜ ሞትከ ብርሃናት ፀልሙ።

ዚቅ
ሶበ መተርዎ ሶበ መተርዎ : ሶበ መተርዎ #ለጊዮርጊስ : ፀሃይ ጸልመ : ወወርኅ ደመ ኮነ : ዬ ዬ ዬ : አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘሰሌዳ ሞገስ መጽሐፉ። ዘያሜኒ ኲሎ ወዘያስተሴፉ። ጥዑመ ዜና #ጊዮርጊስ ለሀሊበ ዕጎልት ሱታፉ። ሰላምከ ወረድኤትከ በላዕሌየ ያዕርፉ። አኮ ለምዕር ዳዕሙ ለዝሉፉ።

ዚቅ
ከመ ሀሊብ ዘዕጎልት : ወከመ ወይን ዘገነት : ይጥዕም ስምከ #ጊዮርጊስ ሰማዕት።

ወረብ
ከመ ሀሊብ ዘዕጎልት ወከመ ወይን ዘገነት/፪/
ስመከ ይጥዕም "#ጊዮርጊስ"/፪/ ሰማዕት/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለክሣድከ ዘተመሰለ ምንሐረ። በአንቅዖ ሀሊብ ወማይ አመ በመጥባሕት ተመትረ። #ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ኲነኔ መጽእረ። በለኒ በቃለ ብሥራት ከመ ነሃሉ ኅቡረ። ጥቃ ቤተ ነፍስየ ለከ ሐነጽኩ ማኅደረ።

ዚቅ
ቅዱስ #ጊዮርጊስ ሶበ ተከለለ : ደም ወሀሊብ እምነ ክሣዱ ፈልፈለ።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለሕሊናከ ዘመከረ በልባዌ። በሞቱ ወበተንሥኦቱ ለተሳትፎ መርዓዌ። ዓቃቤ ሥራይ #ጊዮርጊስ መፈውሰ ደዌ። ለወለት ከመ ቤዘውካ እምአፈ ደራጎን አርዌ። ተረፈ ሕይወትየ ቤዙ እምኲሉ ምንሳዌ።

ዚቅ
ጸርሐ #ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል : ወይቤ እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል።
ዓዲ (ወይም)
ሰኪቦ ለወልድ ትንሣኤ ሞቶ : #ጊዮርጊስ ወረሰ ሰማያዊተ መንግሥቶ።
ዓዲ (ወይም)
ቀዊሞ ገሃደ ውስተ ዓውደ ስምዕ : #ጊዮርጊስ ሰበከ ትንሣኤ ሞቱ ለበግዕ።

ወረብ
ወይቤ #ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ጸርሐ በዓቢይ ቃል ወይቤ/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/
ዓዲ (ወይም)
ጸርሐ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ወይቤ በዓቢይ ቃል/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለፀዓተ ነፍስከ ጽዋዓ ደመ ስምዕ ሰሪቦ። እማኅፈደ ሥጋ በገድል መከራ ስቃይ ድኅረ ረከቦ። #ጊዮርጊስ ስመከ ሶበ እጼውእ በአስተርክቦ። ረድኤትከ ኀበ ሀሎኩ በአርአያ ብእሲ ቀሪቦ። ለትካዘ ልብየ ዘልፈ ያሰስል ዕፅቦ።

ዚቅ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : አጽነነ ርዕሶ #ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።

ወረብ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት "ጊዜ"/፪/ ፮ቱ ሰዓት/፪/
አጽነነ ርዕሶ #ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ እምርጢነ ገለአድ ዘተኃርየ። በላዕለ ድውያን ፈወሰ እስመ ፈድፋደ አርአየ። #ጊዮርጊስ ለከ ትብለከ ነፍስየ። በበድነ ሥጋከ ተማኅጸንኩ ኢታስተኀፍር ተስፋየ። ስዕለተ ከናፍርየ ስማዕ ወፈጽም ጻህቅየ።

ዚቅ
ፈወሰ ዱያነ ወከሠተ አዕይንት ዕውራን : ወኲሎ ፈጺሞ አዕረፈ #ጊዮርጊስ ሰማዕት።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዕደ አግብርቲከ ፪ኤ። ድኅረ ሰለጥከ መዊተ እንዘ ብከ ተስፋ ትንሣኤ። #ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ዓመታት ሱባኤ። ስመከ በተአምኖ ሶበ አወትር ጽዋዔ። አስራበ ረድኤትከ ያጥልል ዘዚአየ ጒርኤ።

ዚቅ
፯ ዓመተ ዘኮነንዎ : ለቅዱስ #ጊዮርጊስ ኢመሰሎ ከመ አሐቲ ዕለት : ብእሲ ጻድቅ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለመቃብሪከ ምክሐ አድያሚሃ ወዓጸዳ። ለምድረ ሙላድከ ልዳ። #ጊዮርጊስ ዘልፈ ሀብተ በረከት ዘእፈቅዳ። ከመ ትጸጊ ሕንባበ ረዳ ለኢያሪኮ በዓውዳ። በዲበ ድማኅየ ትጽጊ እምሰማይ ወሪዳ።

ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር : ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ : ጸሎቱ #ለጊዮርጊስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ።

ምልጣን
ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ከላሌሁ በመጥባሕት #ለጊዮርጊስ ሰማዕት : ጸለየ ጊዮርጊስ ወአውዓዮሙ በነበልባል : አማን ኃያል ገባሬ ኃይል።

አመላለስ
አማን በአማን/፬/
ኃያል ገባሬ ኃይል/፬/

እስመ ለዓለም
ወሰበረ ኆኃተ ብርት ሞዖ ለሞት : ተንሥእ ወልድ በሣልስት ዕለት : ወአግዓዘ ነፍሰ ጻድቃን እምጽልመት ወጽላሎተ ሞት : ካዕበ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ : ገሊላ እቀድመክሙ።

ዓዲ(ወይም)
እስመ ለዓለም
ንግበር በዓለ በትፍሥሕት : በአስተሐምሞ ቅድስተ ፋሲካ : ተዝካረ ትንሣኤሁ #ለጊዮርጊስ : ነገሮ ኅቡዓተ ኲሎ ሥርዓተ ምሥጢር በደኃሪ ይትገበር ዘሀሎ በንዝኃተ ደሙ ለክርስቶስ : ለመፃጉዕ ዘአሕየዎ በቃሉ : ወለዕውርኒ ዘከሠተ ዓይኖ : ተንሥአ እሙታን : ለአልዓዛር ተንሥእ ዘይቤሎ ወለያዕቆብ ዘአዕተዎ ብሔሮ : ተንሥአ እሙታን : ምዕረ ሦዓ ርእሶ ወተዓውቀ በመንፈሱ : በፈቃዱ ወልድ አቅተለ ርእሶ : ተንሥአ እሙታን : ሲኦለ ወሪዶ ሰበከ ግዕዛነ : በመስቀሉ ወልድ ገብረ መድኃኒተ : ተንሥአ እሙታን: ጸርሐት ሲኦለ ወትቤ ሰማያዊ ዝስኩ ዘለኪፎቶ ኢይክል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @petroswepawulos
እንኩዋን ለሐዲስ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ

=>ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ (ተንባላት) በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በሁዋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ (ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም) የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::

+እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ (አሕዛብ) ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ 7 ዓመት ሞላው::

+እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ (የሰንበት በረከት) አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::

+ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው::
ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::

+አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በሁዋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ:: አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::

+ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው #መንፈስ_ቅዱስ አናግሯቸው "#ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::

+በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: (እንዲሕ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው!!!)

+ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን #ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::

+በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::

=>ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

=>ሰኔ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ ሰማዕት
2.አባ ብሶይ አኖብ ሰማዕት (በአንበሳ ጀርባ ላይ የተቀመጠ አባት)
3.ቅዱሳን "5ቱ" ጭፍሮች (በብዙ ስቃይ ሰማዕት የሆኑ ባልንጀሮች)
4.አባቶቻችን የደብረ ቁዋዐት ጻድቃን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

=>+"+ ስለዚሕ #ወንድሞቼ_ሆይ! ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: +"+ (1ቆሮ. 10:14-18)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@petroswepawulos
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ መስከረም ፳፫ (23) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን #ጻድቃን_ወሰማዕት
#አውናብዮስና_እንድርያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል
በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ #ቅዱሳን_አበው_አውናብዮስ_ወእንድርያስ +"+

=>4ኛው መቶ ክ/ዘ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዘመነ
ከዋክብት ይባላል:: ምናልባትም በዓለም ላይ ላለፌት
1,500 ዓመታት ያንን ዘመን መልሶ ማየት አልተቻለም::

*ያ ዘመን ብዙ #ሰማዕታት ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #ሊቃውንት ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #ጻድቃን ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #ደናግል ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #መነኮሳት ነበሩበት::
*ያ ዘመን ብዙ #ባህታውያን (ግኁሳን) ነበሩበት::

+ዘመኑ #ዘመነ_ብርሃን ነው:: እልፍ አእላፍ ቅዱሳን
በዚህ ዘመን አብርተዋልና:: ጠላት ሰይጣንን ከቦታው
አሳድደው አስጨንቀውታል:: በዚህ ዘመነ ብርሃን ከወደ
ምሥራቅ ካበሩ ከዋክብት መካከል ደግሞ በዚህ ዕለት
አባቶቻችን ቅዱሳን አውናብዮስና እንድርያስን
እናዘክራለን::

+ቅዱሳኑ ባለ ብዙ ሃብት ነበሩ:: ከሰማዕታት: ከጻድቃን:
ከደናግል: ከሊቃውንቱም አሉበት:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

¤በተጠቀሰው ዘመን በቅዱስ #ጊዮርጊስ ሃገር በልዳ
ከከበሩ ወገኖች ተወልደዋል::

+የቅዱሳኑ ወላጆች ክርስቲያኖች: በዚያውም ላይ ባለ
ሥልጣኖችና ሃብታሞች ነበር:: ልጆቻቸውን
(አውናብዮስንና እንድርያስን) ሥጋዊውንም:
መንፈሳዊውንም ትምሕርት አስተምረዋቸዋል:: ወጣት
በሆኑ ጊዜ ወላጆቻቸው የዚህን ዓለም ነገር
ሲያስቡላቸው: እነሱ ግን የተሻለውን እድል ያስቡ ነበር::

+ዘወትር ገድላተ ቅዱሳንን ያነቡ: ዜና አበውን ይሰሙ
ነበርና ይመንኑ ዘንድ ልቡናቸው አወካቸው:: በአንዲት
ሌሊት ግን በመንፈስ ቅዱስ አጋዘዥነት ወስነው:
ከሃገራቸው #ልዳ ወጥተው ወደ ገዳም ሔዱ::

+ክብር ለቅዱሳኑ #አባ_ሮማኖስና #አባ_በርሶማ ይሁንና
በወቅቱ በሶርያ ምድር ገዳማዊ ሕይወት ተስፋፍቶ: ብዙ
አድባራት በበርሃ ውስጥ ነበሩ:: 2ቱ ቅዱሳንም በአንዱ
ገዳም ውስጥ ገብተው አገለገሉ::

+ተጋድሏቸውን እያበረቱ እስከ ምንኩስና ደረጃም ደረሱ::
ተጋድሏቸው በጾም: በጸሎትና በትእግስት ብቻ
አይደለም:: በትሕትና በፍቅር በደግነትና በመታዘዝም
ጭምር ነበር እንጂ::

+የምንኩስናና የገዳማዊ ሕይወት ጠላት 'ፍቅረ ዓለምና
ፍትወት እንስሳዊት' ናቸው:: አንድ ሰው ከዚህ ዓለም
ቁሳቁስ ሳይርቅ መናኝ መሆን አይችልም:: ቅዱሳኑ ግን
በመንኖ ጥሪት ይህችን ዓለም ከነኮተቷ ናቁዋት:
አቃለሏት::

+የሥጋ ፈቃዳቸውን ያጠፉ ዘንድ ሰውነታቸውን በጾምና
በጸሎት: ዕረፍትም በማሳጣት ቀጧት:: #እግዚአብሔር
ደግሞ ስለዚህ ፈንታ ጸጋውን አበዛላቸው:: ቅዱሳኑ
በሶርያ ገዳማት ለዘመናት ከተጋደሉ በሁዋላ ወደ ግብጽ
ለመውረድ ወሰኑ:: ምክንያታቸው ደግሞ:-

1ኛ.ከውዳሴ ከንቱ ለመራቅ
2ኛ.ከቅዱሳን አበው ለመባረክ እና
3ኛ.ለተሻለ ተጋድሎ ለመብቃት ነበር:: እየጸለዩ
እያመሰገኑም ግብጽ: ቀጥሎም ገዳመ አስቄጥስ ደረሱ::

+ታላቁ #ርዕሰ_መነኮሳት_አባ_መቃርስን ፊት ለፊት
ቢያገኙት ደስ አላቸው:: ሐሴትንም አደረጉ::
እግዚአብሕርን በማደሪያዎቹ ማግኘት ይቻላልና:: የታላቁ
ቅዱስ ደቀ መዝሙር ሆነው: በድንግልና ተጠብቀው:
በተጋድሎ በርትተው በቦታው ለ3 ዓመታት ቆዩ::

+እግዚአብሔር ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ፈልጐአቸው
ነበርና በዚያ ሰሞን በከተማ የነበሩ ሊቃውንት ወደ ገዳም
መጡ:: ገዳማውያንንም ዻዻስ ስላረፈብን "የምንሾመው
መልካም እረኛን ስጡን" አሏቸው::

+ገዳማውያኑ ሱባኤ ገብተው ቢጠይቁ መንፈስ ቅዱስ
ቅዱስ አውናብዮስን መረጠ:: አበውም ቅዱሱን ዽዽስና
ሲሾሙት ወንድሙን እንድርያስን ረዳት አደረጉት:: 2ቱ ቅዱሳን ከበርሃ ወደ
ከተማ መውጣታቸውን ተከትሎ ተጋድሏቸውን ለማበርታት
ወሰኑ::

+ምክንያቱም ለአንድ ገዳማዊ ከተማ ውስጥ ከመኖር
በላይ ፈተና የለምና:: ቅዱሳኑ ቀን ቀን ድውያንን
ሲጠይቁ: ሙታንን ሲቀብሩ: ሕዝቡን ሲያስተምሩ:
ሥጋውን ደሙን ሲያቀብሉ ውለው ሌሊት ይጋደላሉ::

+ለፈቃደ ሥጋቸው ሳያደሉ እንዲህ ባለ ቅድስና ኖረው
ደግሞ ሌላ ፈተና መጣ:: የከተማው ሃገረ ገዢ አረማዊ
በመሆኑ "ለጣዖት ስገዱ: ክርስቶስን ካዱ" ይል ጀመር::
ቅዱሳኑ ሕዝቡን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም
ሊያስተምሩ ወደዋልና መኮንኑን "ተው! ተሳስተሃል"
አሉት::

+በዚህ ምክንያትም ብዙ ስቃይ ገጠማቸው::
በመጨረሻም በዚህች ዕለት ሰማዕት ሆነዋል:: ጌታም
ስለ ድንግልናዊ ሕይወታቸው: ስለ ወንጌል
አገልግሎታቸውና ስለ ሰማዕትነታቸው 3 አክሊላትን
አቀዳጅቷቸዋል::

=>አምላከ አበው ቸርነቱን ይላክልን:: የቅዱሳኑን
በረከትም ያሳድርብን::

=>መስከረም 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱሳን ጻድቃን አውናብዮስ ወእንድርያስ (ሰማዕታት)
2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ መንክራዊ
3.ቅድስት ቴክላ ድንግል
4.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል

=>+"+ በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ
ማን ነው? ነገር ግን ስለ #ጽድቅ እንኩዋ መከራን
ብትቀበሉ #ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ:
አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን
በልባችሁ ቀድሱት:: +"+ (1ዼጥ.3:13)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@petroswepawulos