ቅንጭብጭብ
7.63K subscribers
408 photos
9 videos
1 file
497 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

የአፍ መሸፈኛ ማስክ አትጠቀሙ!!

የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ በርካታ የጤና ተቋማት እንደገለጹት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የሚያስፈልገው ለሚከተሉት ብቻ ነው 👇
.
👉 ምልክቱ ለታየባቸው፤
👉 ለኮሮና በሽተኛ አስታማሚዎች፤
👉 ለሕክምና ባለሙያዎች፤
.
🔵 ምልክቱ ላልታየበት ሰው የአፍ መሸፈኛ ለብሶ መሄድ ይልቁንም ጉዳት አለው
.
👉 አፍ ላይ ለቫይረስ ምቹ የትንፋሽ እርጥበት ይፈጥራል፤
👉 ማስኩን ለማስተካከል ፊታችንን እንድንነካካ ይገፋፋል፤
👉 ለሚያስፈልጋቸው ባለሙያዎች እጥረት ይፈጥራል፤
👉 የሐሰት የደኅንነት ስሜት በመፍጠር ከጥንቃቄ ያዘናጋል፤
👉 ለስግብግብ ነጋዴ ብዝበዛ ክፉኛ ይዳርጋል፤
.
አንድን ነገር ጥቅም እና ጉዳቱን ሳናውቅ እንደፋሽን ማድረግ አይጠቅምም።
ሐኪሞች «አትልበሱ» እያሉ መልበስ ከጉዳት በስተቀር ጥቅም የለውም።
.
የተሻለው አማራጭ አንድ ወይ ሁለት ማስክ ገዝቶ ምልክቱ ሲታይብን ወደሐኪም ቤት ስንሄድ እንድንለብሰው በቦርሳችን ማስቀመጥ ነው። ለማስክ መግዣ የምንጨፈጭፈውን ብር ሳኒታይዘር ወይም አልኮልገዝቶ አዘውትሮ መጠቀም ይሻላል።

ንክኪዎችን መቀነስ
እጅን በሳሙና በአግባቡ መታጠብ
#ሲያስነጥሱ አፍዎን ይሸፍኑ
ፊትን ከመነካካት መቆጠብ
የጋራ መገልገያዎችን በአልኮል ማፅዳት

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር #8335 ይደውሉ

ሼር በማድረግ ላልሰማ አሰሙ!
#ኮሮናቫይረስ #ኮቪድ19

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይበል የሚያሰኝ ውሳኔ... (ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ)

መጋቢት 7 ቀን ከተወሰኑት ውሳኔዎች በተጨማሪ፦

1. ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ መንገደኞች ሁሉ በራሳቸው ወጪ ለዚሁ ዓላማ በተወሰኑ ሆቴሎች ውስጥ ለ14 ቀናት ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ።

2. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት እንዲያቆም።

3. መንግሥት የሀይማኖት ተቋማት እና የአምልኮ ስፍራዎች ላይ የምዕመናን መሰባሰብ በጊዜያዊነት መቋረጡን የሚደግፍ ሲሆን፣ የኮቪድ19 ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ያስችል ዘንድ ንክኪን በማያስከትሉ ሌሎች አማራጮች አምልኮ ቢካሄድ ይመረጣል።

4. ማረሚያ ቤቶች ጊዜያዊ ማቆያቸውን እና ሌሎች ስፍራዎችን በመጠቀም ጭምር መተፋፈግን እንዲያስቀሩ። በተጨማሪም፣ አዲስ ታራሚዎች ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባታቸው በፊት የኮሮና ቫይረስ ምርመራን እንዲያካሂዱ። ታራሚዎችን መጠየቅ ለተወሰነ ጊዜ የተከለከለ ሲሆን፣ በቀላል ጥፋት ምክንያት ማረሚያ ቤት የገቡ ወይም የእርምት ጊዜያቸው የተቃረበ ታራሚዎች እንዲፈቱ።

5. የውጪ ዜጎችን መተናኮል ተቀባይነት የሌለው እና ኢትዮጵያዊ ያይደለ ጥፋት ነው። ሕዝቡ ቫይረሱ ዘርና ዜግነትን የማይለይ መሆኑን ተገንዝቦ፣ የውጪ ዜጎች ላይ ጣት ከመቀሰር እና ከማግለል ይልቅ፣ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ቫይረሱን የመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ ይኖርበታል።

6. ላለፉት ቀናት የማስተባበር ሥራን ሲሰሩ የነበሩ ወጣቶችም፣ የበጎ ፈቃድ ሥራዎቻቸውን ሲቀጥሉ በተመሳሳይ መልኩ ራሳቸውን እንዲጠብቁ እና ቫይረሱን የመከላከያ እርምጃዎችን ተፈጻሚ እንዲያደርጉ።

7. ኮሚቴው ወሳኝ የነፍስ አድን ሥራዎችን በቂ መገልገያዎች እና መሣሪያዎች ሳይኖሯቸው በማከናወን ላይ የሚገኙትን የሕክምና ባለሙያዎች ያመሰግናል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ፣ ኮሚቴው በትምሕርት ላይ ያሉትን ጨምሮ፣ ሁሉም የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ጥሪውን ያቀርባል።

8. የመጀመሪያው ዙር በአሊባባ አማካኝነት በጃክ ማ የተበረከቱት የምርመራ ቁሶች፣ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎች እንዲሁም ቫይረሱን የተመለከቱ መመሪያዎች ስብስብ እሁድ መጋቢት 13፣ 2012 ይደርሳሉ። ከዚህ አንጻር፣ ኮሚቴው በመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም እንዲደርሳቸው ለታሰበላቸው የአፍሪካ ሀገራት ለማሰራጨት ቅድመ-ዝግጅት እያካሄደ ይገኛል።

9. የጭፈራ ቤቶች እና የመጠጥ ቤቶች ቫይረሱን የመከላከል እና ስርጭቱን የመግታቱ አካል ሆነው፣ በጊዜያዊነት ሥራቸውን ያቆማሉ።

10. ይህንን አሳሳቢ የጤና ሁኔታ በመጠቀም ከገበያ ዋጋ ከፍ ባለ መጠን በመሸጥ ትርፍ ለማጋበስ በሚሞክሩ ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ይቀጥላል።

11. ክልሎች ከፌደራል መንግሥት ድጋፍ እየተደረገላቸው፣ ዝግጁነታቸውን ብቁ ለማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛሉ።

#ኢትዮጵያ
#ኮሮና #ኮቪድ19

@kinchebchabi @kinchebchabi
የኮሮና ቫይረስ #ምርመራ እና 5ተኛ ዙር #የደም_ልገሳ
#share #ሼር

የደም እጥረት ሊያጋጥም ስለሚችል ኑ ደም እንለግስ!!!

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ብዛት ዘጠኝ ደርሷል።

የደም እጥረት ከመከሰቱ በፊት ደም እንለግስ!
በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስ #ምርመራ እናድርግ።

እርሶ የሚለግሱት ደም የሦስት ሰዎችን ሕይወት ከሞት ይታደጋል። ኑ ደም እንለግስ!

ነገ እሁድ - ጠዋት 3:00 ጀምሮ
ቦታ - ቀይ መሥቀል ማኅበር (ስታዲየም አካባቢ)
ለበለጠ መረጃ - 0945956262

እባክዎ ሼር በማድረግ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
#ኮሮናቫይረስ #ኮቪድ19
#ዓኢ #ዓውደ_ኢትዮጵያ

@awdeethiopia @awdeethiopia
ዓውደ ኢትዮጵያዎች ከደም ልገሳ በኋላ የተነሱት ወቅታዊ ሁኔታን ያገናዘበና ማህበራዊ ፈቀቅታን (ርቀት) የጠበቀ የሕብረት ፎቶ 👏👌

#ኮሮና_ቫይረስ #ኮቪድ19
@awdeethiopia ገጽ የተወሰደ

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi