ቅንጭብጭብ
7.18K subscribers
413 photos
9 videos
5 files
502 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
እኔ #ጎፈሬው በእምነት ተሾመ (#Bcrazykid)በጎፈሬነት ለሐገር አቀፍ ውድድር ቀርቤያለሁና የሚከተለውን ሊንክ በመንካት #Vote እንድታደርጉኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
#እኔ_ጎፈሬ_ነኝ!

https://www.wishpond.com/lp/2390399/entries/177585260

ሊንኩን በመጫን - ድምፅዎን ይሥጡኝ

ድምፅ ለመሥጠት
1, ሊንኩን ተጭነው በ opera/browser ይክፈቱ
2. ከፎቶው በታች Email ያስገቡና #Vote የሚለውን ይጫኑ
3 #send_confirmation የሚለውን ይጫኑ
4 የ Email አድራሻችሁን በመክፈት confirm በሉ

ጓደኞቻችሁ ድምፅ እንዲሰጡኝ #ሼር
አመሰግናለሁ

https://www.wishpond.com/lp/2390399/entries/177585260
እናታችን ሙንተሃ ሸረፋ በጠና ታማብናለች ሁለቱም ኩላሊቶቿ አገልግሎት መስጠት አቁሟል። እናታችን ሙንተሃ ለ1 አመት ስድስት ወር ዲያለሲስ ስታደርግ ቆይታለች ነገር ግን አሁን ከአቅሟ በላይ በመሆኑ የእናንተን እርዳታ ትሻለች።

እናታችንን ለመርዳት የምትፈልጉ
የንግድ ባንክ ቁጥር 1000138716892
ሙንተሀ ሸረፋ

ላይ የቻላችሁትን አድርጉልን ይላሉ ቤተሰቦቿ።
አሁን በሞባይል ባን ኪንግ መላክ ትችላላችሁ።

ስልክ - 0911320174

እባክዎ መርዳት ባይችሉ እንኳ ለሌሎች #ሼር ያድርጉ

https://www.gofundme.com/zgvx82-for-my-mom?member=1128452&utm_source=twilio&utm_medium=sms&utm_campaign=contacts-v2-invite-to-donate
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

በገጣሚ አሸናፊ ጌታነህ ዘልደታ የተዘጋጀ #ላንቺ_ሲሆንማ... የግጥም ሰብስብ መጽሐፍ ቅዳሜ መጋቢት 14 2011 ዓ.ም ጠዋት ከ3 ሰዓት ጀምሮ 22 ማዞሪያ ባታ ኮምፕሌክስ በሚገኘው አቤል ሲኒማ አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት በአኬቡላንስ ባንድ ታጅቦ ይመረቃል።

መጽሐፉ 83 ግጥሞችን በ117 ገጾቹ የያዘ ሲሆን ገጣሚው የሀገር ፍቅርን፣ሰላምን፣ አንድነትን ፣ታማኝነትን፣ ተስፋን፣ ጽናትን፣ ትዕግስትን ፣አብሮ መኖርን ፣ስኬትን ፣የእናት የቤተሰብ የጓደኛን ፍቅር በሚያስደምም ግጥማዊ ጥበብ ከሽኖበታል።የኋላውን በምልሰት የፊቱን በናፍቆት አሻግሮ በብዕሩ ያመላክተናል።ሀገራዊ ክስተቶችን በጊዚያቸው እንደነበሩ ያስቃኘናል። ቅኔያዊ ግጥሞችና ምጸታዊ ስንኞች ተካትተውቡታል።

አንጋፋዎቹ ደራስያንና መምህራን በእርማትና አርትኦት ስራ እገዛ አድርገዋል ብቃቱንም መስክረዋል።
በእለቱ ደራስያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።የዳዊት ድሪምስ ባለቤትና መስራች ኮች ዳዊት ገ/እግዚአብሄር አነቃቂ የሆነውን ድንቅ ንግግሩን እንሰማለን።
... ይምጡ ብቻ ሁሉም አለ።

የሰማ ላልሰማ ያሰማ #ሼር
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ቬሎና ቦሎ
(አሌክስ አብረሃም)
የዮርዳኖስ የሰርግ ቪዲዮ ከሌሎች የሰርግ ቪዲዮወች የሚለየው ሰርጉ ላይ የትራፊክ
ፖሊስ አጭር ትእይንት ስለተካተተበት ነበር እንዴት ማለት ጥሩ ነው
ለዮርዳኖስ ሰርግ ጊዜ አጃቢ ሁነን ለምሳ ወደሙሽሪት ቤት እየሄድን ነበር ድንገት
ከሰማይ ዱብ ያለ የሚመስል የትራፊክ ፖሊስ የሙሽራውን መኪና ከነሙሽሮቹ አስቆመና
‹‹መንጃ ፈቃድ ›› አለ ኮስተር ብሎ ፍጥነቱና መኮሳተሩን ለተመለከተው በሙሽሮቹ መኪና
ጥንዶቹ ሳይሆኑ ጥንድ ፈንጅወች ተጭነዋል የሚል ጥቆማ የደረሰው ነበር የሚመስለው
‹‹ምን አጠፋሁ ሙሽራ እኮ ነው የጫንኩት ›› አለ ሹፌሩ
‹‹ እሱን ማን ጠየቀህ የመኪናው ቦሎ አልታደሰም ›› ብሎ ሹፌሩ ጋር ክርክር ገጠመ ::
ድፍን ሚዜ ወርዶ ትራፊክ ፖሊሱን መለመን ጀመረ
‹‹ኧረ በናትህ ሙድ የለውም ሰርግና ሞት አንድ ነው ሲባል አልሰማህም ምናለ ብታልፈን
ለዛሬ ›› አለች አንዷ ግማሽ ጀርባዋ የተራቆተ መዘነጥ ያለመደባት የምትመስል ዘናጭ
በያዘችው አበባ የትራፊክ ፖሊሱን አይን ልትመነቁለው ደርሳ ነበር
‹‹እኮ ...ይሄ መኪና ‹ቴክኒካል› ችግር ቢኖርበትስ በሰርጋችሁ ቀን ሃዘን ሆነ ማለት
አይደል ...ሰርግና ሞት አንድ ነው ማለት ያነው አደጋ ሙድ የለውም ብሎ አያልፍም ››አለ
ሙሽሪትን በአይኑ እየቃኘ
‹‹እሱማ ልክ ነህ ግን አሁን ሙሽሮቹን ጭነን ወደምርመራ እንሂድ እንዴ ›› አለ አንዱ
ሞቅ ያለው ሹፌር በማሾፍ
‹‹ ሙሽራ ጭነህ እንጦሮጦስ ከመውረድ ይሻላል ›› አለና ኩም አደረገው
የሙሽራው ንስሃ አባት ወርደው ትራፊክ ፖሊሱን ለመኑት ‹‹የኔ ልጅ ቃሉ እንደሚል
እ.....ጋብቻ ቅዱስ ... ምኝታውም ንፁህ ነውና ማበረታታት ነው ያለብን ›› እያሉ ስብከት
ጀመሩ
‹‹አባቴ እኔ መች መኝታቸውን ህገወጥ ነው አልኩ መኪናቸውን እንጅ ›› አለ ትራፊኩ
ቀዝቀዝ ብሎ ነበር
በብዙ ልመና ትራፊክ ፖሊሱ የሙሽሮቹን መኪና ከለቀቀ በኋላ አንዷ ከጎኔ የተቀመጠች
በጣም ቆንጆ እና ነብሷን እስክትስት የዘነጠች ወጣት (ለሰርግ አጃቢነት የተፈጠረች
የምትመስል ) እንዲህ አለች
‹‹....ትራፊክ ፖሊሱ ሙሽሪት ሰፈር ነበር በፊት ጠይቋት እንቢ ብለዋለች ወ.......ይ
ወንዶች ! ››
አሙቁልኙ እንዲህ አለ በዜማ
‹‹የኛ ሙሽራ ባለቬሎ
አስቆማት ባለቦሎ
አስቆማት
ባለ ቦሎ
.... እልልልልልልልልል ቦሎው ያልታደሰ መኪና ተከትለን ወደሰርጉ ቤት .... ይሄ ሁሉ
ሲሆን ካሜራ ማኑ እየቀረፀ ነበር ፡፡ የሰርግ ቪዲዮውን ስናየው ታዲያ የትራፊክ ፖሊሱና
የሰርገኛው ንትርክ አጠቃላይ ሰርጉን ‹ቬሎና ቦሎ› የሚል ‹ከሆሊውድ የመጡ
ባለሙያወች › የተሳተፉበት የፍቅር ኮሜዲ ፊልም አስመስሎት ነበር ፡፡ (የሰርግ ኮሜዲ የሚባል የለም ብየ ነው።)

ፅሁፉን ከወደዳችሁት 👍 #ሼር በማድረግ ደግሞ ለወዳጆ ይጋብዙ

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ቀልብን የሚገዛ ከጥንታዊ ምሳሌዎች አንዱ እንዲህ ይላል...

በአንድ ትልቅ ቤተ መንግሥት ውስጥ የምትኖር አንዲት ውብ ልዕልት ነበረች። ይህቺም ልዕልት ከነገሮች ሁሉ ፥ ከተፈጥሮም ሁሉ የሚያስደስታት ልቧንም በ ሀሴት የሚሞላው አጥብቃ የምትወደው አንድ ነገር ነበራት። እርሷም በ መስኮቷ አሻግራ የምታያት አንዲት ውብ ወፍ ናት። ይቺ ወፍ ሁሌም ደስተኛ ሁና ደስተኛ ታረጋታለች። ሁሌ ነፃ ሁና ነፃ ታረጋታለች። ሁሌም አዲስ ሆና ልዕልቷን አዲስ ታረጋታለች። ሁሉም ነገር ቀላል እንደ ሆነ ከርሷ ትማራለች። የህይወትን ዜማ በጠራው ሰማይ ላይ ሁሌ እያዜመች ልጅቷን ወደ ሌላዓለም በምናብ ትልካታለች።

ታድያ ልዕልቷን የሚከነክናት አንድ ነገር ነበር። እርሱም ይቺ ወፍ ሁሌ ማታ ማታ ስለምትሄድባት ደስታዋ ቀን ላይ ብቻ የተመሰረተ ነበር። ማታ ላይ ከእውነተኛው ህይወቷ ጋር ፊት ለፊት ትጋጠማለች። ሃሳቧ ወደ ምናብ ዓለም ሚያስገባትን ነገር ታጣለች። አሁን ላይ ያለው ህይወቷን ሸሽታ ወደ ፊት ሽምጥ በሀሳብ ምትጋልብበትን ሰበብ ታጣለች። ለዚህ ማታ ቀኑ ሲመሽ እሷም ይመሽባታል። ህይወቷን ለትንሿ ወፍ አሳልፋ የሰጠች ያህል ማንነቷን ቀኑ ሲመሽ ታጣዋለች።

ይህ እንዲ ከሆነ ከዓመታት በኋላ ለዚች ውብ ልዕልት አንድ መላ ይመጣላታል። እሱም ወፏን ይዞ ቅርጫት ውስጥ ማስቀመጥ። ወፏን የራስ የማረግ መላ። እርሷ ጋር ሁሌ እንድትቀመጥ። እንደ ልዕልቷም አኗኗር ወፏም እንድትኖር። ለንጉሱ አባቷ ይሄን ትነግርና ወፏ ትያዛለች። በቅርጫትም ተደርጋ በሚያምር መልኩ ኑሮን ከልዕልቷ ቤት እንድታደረግ ትደረጋለች።

ነገር ግን ወፏ ከበፊቱ የተለየ ፀባይ አመጣች። አትናገር አትጋገር ዝም ብላ ተክፍታ ቀኑንም ማታውንም ታሳልፋለች። ምግብ አትበላ። አትዘምር። አትበር። ኩርችም እንዳለች ትቀመጣለች። ንግስቲቷ ግራ ተጋባች። ወፏ ተከፍታ እርሷንም ታስከፋለች። በኋላ ላይ ነገሩን እቤት ውስጥ ከነበሩ ሽማግሌ ትጥይቃለች። " አየሽ ልጄ ወፏ ማትጫወተው ካንቺ የራስ ወዳድነት ስሜት የተነሳ ከማንነቷ አላቀሽ ሌላ ማንነት ስለሰጠሻት ነው። አንቺን እንዲመችሽ እሷን ከሚመቻት ኑሮ ነቀልሻት። ነፃነቷን ገፈሽ መሆን ማልትችለውን መኖርም ማትችለውን አኗኗር እንድትኖር ፈረድሽባት። ወዳጅሽ በገዛ እራስሽ ጠላት አደረግሻት። ካንቺ ያማረ ቅርጫት የርሷ የፈረሰ ጎጆ ትርጉም አለው። መብረር ማንነቷ ስለሆን ገና ለገና ከኔ ትለያለች ብለሽ ነፃነቷን ነፈግሻት። ሰው ለማንነቱ ሲል ይሞታል። ማፍቀር ሚቻለው እራስን ሲኮን ብቻ ነው። ማንነቱን የተሰረቀ ሰው ሰራቂውን እንደ ጠላት ያየዋል። የሰውን ማንነት ለመቀየር መነሳት በራሱ ሰውን ካለማክበር ስለሚጅምር የጦርነት የመጅመርያው ፊሽካ ነው።ወፏም እንዲው ናት ለዚህ እራሷን ትሁን ልቀቂያት። ያኔ ውበቷም ከርሷም አልፎ ላንቺ ያበራል። ቂም ሳይሆን ፍቅር ላንቺ ይኖራታል። ለትውልድ ምታስተላልፈው ምንም ቂም አይኖራትም። በኋላም ዘምን አልፎ ዘመን ሲተካ የሁለታቹም ዘር አንድ ላይ መኖር ትቀጥላላቹ።

ልዕልቷም ወፏን ለቀቀቻት ወፏም እንደበፊቱ ሆነች። ልዕልቷም ለራሷ ችግር እራሷ መፍትሄ ሌላውን በማነካ መልኩ መፈለግን ለመደች። ማንነትን ማሳጣት ጠላት መሆን እንደሆነ አወቀች። ሁሉም አለኝ የሚለውን ነገር እንዲከበርለት እንደሚፈትፈልግና ይህም ዘመናት የሚዘልቅ ወዳጅነትን እንደ ሚያስፍን ተረዳች። በአንፃሩ ማንነትን መንካትና እንደኔ ሁን ማለት ለትውልድ ሚተርፍ የቂም በቀል ንቅሳት እንደሚያተርፍ ተረዳች። የራስን ይዞ የሌላንም ማክበር!

ለወዳጅዎ #ሼር ያድረጉ...
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ሰም እና ወርቅ 20ኛው የኪነ ጥበብ ምሽት "ኢትዮጵያዊነት"በተሰኘ የፊልም ፌስቲቫል ምክንያት በሐምሌ 25 ይቀርብ የነበረው መርሐግብር ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም በአ.አ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ ዶ/ር ብርሃኑ ግዛው ፤
አቶ ታዬ ቦጋለ፣
ደራሲ ዘነበ ወላ፣
ገጣሚ ነብይ መኮንን፣
መምህር የሻው ተሰማ ፣
ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ፣
ደራሲ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር
መምህርት እጸገነት ከበደ
ገጣሚያኑ ልሳን ሀጎስና
ፍጹም ታደሰ ከመሶብ የባህል ባንድ ጋር ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
መረጃውን ለሌሎች እንዲደርስ እንደሚያደርጉ እምነት አለን፡፡ ከላቀ ልባዊ ምስጋና ጋር፡፡
0911 125788 #ሼር

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ከአፍሪካ አንባገነን መሪዎች ዝርዝር ዉስጥ ስሙ የማይጠፋው በ 1970ዎቹ የኮሞሮስ መሪ የነበረው ወጣት አሊ ሶሊህ አንዱ ነዉ አሊ ሶሊህ በብዛት ምሽቱን የሚያሳልፈው ከሀገሪቱ ምርጥ ምርጥ ቆነጃጂት እና ኮረዶች ጋር ጭፈራ ቤቶች እየተዘዋወረ በመዝናናት ነው ከብዙ አስገራሚ ታሪኮቹ ውስጥ ትኩረትን የሚስብ አንድ እውነተኛ ገጠመኝ እነሆ ...

አሊ ሶሊህ አንድ ለሊት በእንቅልፍ ልቡ ወይም በሕልሙ አንድ ውሻ እያሳደደ ይነክሰዋል በነጋታው ከእንቅልፉ ሲነቃ ለሊት ባየዉ ሕልም ሰበብ በሀገሪቱ ወስጥ ያሉትን ውሾች በሙሉ እንዲገደሉ አዋጅ ያስነግራል። አብዛኛው ሕዝብም ይፈራዉ ስለነበር እንደታዘዘው ውሻውን ጨክኖ ገደለ ታድያ አሊ ሶሊህ ቃሉ ምን ያህል እንደተገበረ ለማረጋገጥ በከተማው አዉራ ጎዳናዋች ሲዘዋወር አንዲት ባልቴት ግቢ ውሰጥ አንድ ውሻ ታስሮ ያያል በዚህን ጊዜ አሊ ሶሊህ ሽጉጡን ያወጣና ውሻውን ከገደለ በኃላ ባልቴቷን ወደ ዘብጥያ በመላክ የለየለት አምባገነን መሆኑን አስመስክሯል


ለወዳጅዎ ያጋሩ... #ሼር
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ሼር_ይደረግ!!!

#አንሸበር_እንጠንቀቅ
_______

ኮሮና ቫይረስ አፍሪካን ማመስ ከጀመረ ሰነባብቷል...
ዛሬ በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ጃፓናዊ ተገኝቷል። (ገና ሊቀጥል ይችላል!)

አሁን ላይ ዓለምን እያዳረሰ ያለው የቫይረሱ ወረረሽኝ ኢትዮጵያም ውስጥ ተገኘ ብሎ ያለቅጥ መሸበር አይጠቅመንም!።

#መረጃ_ስለ #ኮሮና_ቫይረስ

ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!
በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!

ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ! < የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም። ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡
< በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

< አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጉሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::

2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡

ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?

1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላበተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡

< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡

3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

ተጨማሪ...
ምን እናድርግ?
______

1 #እጃችንን_እንታጠብ
አዘውትረን በሳሙና እና በውሃ ለሀያ ሴኮንድ እጆቻችንን አዘውትረን እንታጠብ።

2 #መጨባበጥ_ይቅር

3 #ሰው_ከሚሰበሰብበት_እንራቅ

4 #እንሸፈን
በሚያስለን ወይንም በሚያስነጥሰን ግዜ ፊታችንን በክንዳችን ወይም በመሸፈኛ እንሸፍን።

5 #ፊታችንን_አንነካካ

6 #የጋራ_መገልገያዎችን_አንነካካ
ብዙ ሰው የሚነካካቸውን ነገሮች ማለትም የበር እጀታዎች፣ የደረጃ መደገፍያዎች እና የመሳሰሉትን አንነካካ። ምናልባት ከነካን እጅን በሳሙና መታጠብን አንርሳ።

7 #ነጻ_የስልክ_መስመር
የበሽታው ምልክቶች ከታዩብን #8335 ነጻ የስልክ መስመር መደወል አንርሳ።

አስታውሱ!
ወረርሽኙን ማቆም ባንችል እንኳን ፍጥነቱን መቀነስ እንደምንችል አንዘንጋ።

______ #በተለይም

#ወጣቶች በበጎ ፈቃድ በየቦታው ተደራጅታችሁ ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ህብረተሰቡን እናግዝ።

#የእምነት_ተቆማት የስብከት እና የአምልኮ መርሐ ግብሮቻችሁን ለምእመናኖቻችሁ ጤና ቅድሚያ በመስጠት ላልተወሰኑ ጊዜያት ብታስተላልፏቸው።

#መንግስት ቫይረሱ ብሔራዊ አደጋ መደመሆን እንዳይሸጋገር የላቦራቶሪ እና የለይቶ ማቆያዎች አቅሙን በአፋጣኝ መገንባት ቢችል ....

መረጃውን ሼር በማድረግ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ #SHARE it!
(© ከተለያየ ድረ ገፅ የተሰበሰበ)

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
የኮሮና ቫይረስ #ምርመራ እና 5ተኛ ዙር #የደም_ልገሳ
#share #ሼር

የደም እጥረት ሊያጋጥም ስለሚችል ኑ ደም እንለግስ!!!

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ብዛት ዘጠኝ ደርሷል።

የደም እጥረት ከመከሰቱ በፊት ደም እንለግስ!
በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስ #ምርመራ እናድርግ።

እርሶ የሚለግሱት ደም የሦስት ሰዎችን ሕይወት ከሞት ይታደጋል። ኑ ደም እንለግስ!

ነገ እሁድ - ጠዋት 3:00 ጀምሮ
ቦታ - ቀይ መሥቀል ማኅበር (ስታዲየም አካባቢ)
ለበለጠ መረጃ - 0945956262

እባክዎ ሼር በማድረግ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
#ኮሮናቫይረስ #ኮቪድ19
#ዓኢ #ዓውደ_ኢትዮጵያ

@awdeethiopia @awdeethiopia
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
ይህ የአብዮተኞች ድምፅ ነው፡፡

የባለቅኔው ልጅ ሜዳ ወድቆ እኛ ቤት ደፍተን ቤት መተን አንገጥምም!!!



አዳሜ እና ሄዋኔ ትሰሙ እንደሆነ ስሙ!!! እዚህ ጋር ያንተን ላይክና ኮሜንት ለመሰብሰብ የሚፃፍ ትርክት የለም! ይልቅዬ ኪስህን አስዳብስሃለሁ! መፍትሄ አፈላላጊ አድርጌ እሾምሃለሁ ፡ ከችግር ፈጣሪነት አረንቋ ትላቀቃለህ !!!

ዳይ ዳይ ዳይ ሙስሊም ነሽ ክርስቲያን ነሽ ጦማሩን በሚገባ ተከታትለሽ የሚጠበቅብሽን ታደርጊያለሽ /ውልፍት እንዳትይ!/

እንደው የማያገባህ ጉዳይ ውስጥ ገብቼ እዘላብዳለሁ የምትል ካለህም መሰነባበቻ ቆመጥ ይሳብብሃል ወደ ጥልቁ ፅልመትም ትወረወራለህ፡፡

°°°°°°°°°°°••••••••••°°°°°°°°°°

ይህ የማየው ሰው ማነው ካላችሁ የታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ /አያ ሙሌ/ ልጅ ዳንኤል ነው ሸህ አብዱ ፡፡

ስለ ሙሉጌታ ተስፋዬ በኔ አንደበት ለማውራት ይከብደኛል ፡ ይልቁኑ አዋቂ ዘያሪዎች ያወጉትን ከኮሜንት መስጫው ሳጥን ሊንኩን አኖራለሁ፡፡ ግን ይሄንን ብቻ ልንገርህ አንተ ካህሊል ጂብራን ትላለህ አንተ እነ ሩሚን ምናምን ጠቃቅሰህ ደረትህን ልትነፋብኝ ትችላለህ እኔ ግን እልሃለሁ ቅድሚያ ባለኝ የሃገሬ ምጡቅ ላይ ኩራቴ ያይላል ፡፡ የኛ ባለቅኔ ነው ሙሉጌታ ፡ አፍህን ሞልተህ መኩሪያዬ የምትለው ነፍስያው የምትጥም የከተበው የማይነትብ ባለ ብሩህ አዕምሮ ባለቤት! ( በሱ ስራዎች የዝናን ማማ የተቆናጠጣችሁ አርቲስቶቻችን እስኪ በሉ መስክሩ)


✿ እንግዲያው ወደ ቁም ነገሩ እንምጣ ✿

እርሱ ሳለ እንዳሻው ይቦርቅ የነበረ አባቴ መከታዬ ነህ እያለው ከእርሱ ጋር ቅኔውን ሲደረድር የቆየው ልጁ ዛሬ እንደቆሻሻ ተጥሎ ይገኛል፡፡ የባለቅኔውን ሙሉጌታ ተስፋዬን የአዕምሮ ጭማቂ ለህዝብ ያጠጡ አርቲስቶቻችንም በመከራ የሚጠቀማትን ዳቦ በሻሂ ሲምግ በሶ ብጥብጡን ሲጠቀም እያዩ ያልፋሉ!!!

☞ እሺ ስለማያውቁት ነው ብለን ቨቀናነት እናስብና እወቁልን ብለን እየጮህን ነው፡፡

☞ ይሄ አብዮት ስያሜው #የግጥም_አብዮት ሆኖ ሳለ የግጥም አባቶችን ውለታ አለመክፈል ይከብደዋልና ሊጮህ ተገዷል፡፡

☞ እርግጥ ነው ፡ የወደቀን የሚወድ እምብዛም የለም ( ብር ካልሆነ ለማንሳት ገድም አንል)

✿ ወድ አብዮተኞቻችን ሆይ አሁን ጥያቄው አጭር እና ግልፅ ነው ፡ ይህ ሰው ሶማሌ ተራ ላይ ድንጋይ ትራሴ ብሎ ተጎሳቁሎ ይገኛል ፡፡ የሚበላውን እህል የከፈተውን ጉሮሮ ከሚዘጋ ፈጣሪ ዘንድ እንጂ በራሱ የሚያገኝበት መንገድ የለውም፡፡ አባቱን በማጣቱ ምክንያት በደረሰበት ጫና ምክንያት ከጭንቀት አልፎ ድብርት ከድብርት አልፎ ድብታ ውስጥ ገብቷል፡፡ እውነት ለመናገር ያ በብዙ ሰዎች ይከበብ የነበረው የበርካታ ዝነኞችን ፊት ይቃኝ የነበረ አይን ዛሬ በብቸኝነት ሲከበብ የአዕምሮ ቀውስ ቢገጥመው አይገርምም!

✿ በልዩ ቀና ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ንቁ! እዚህ መንደር በርካታ ፈጣሪ ፀጋውን ያበዛላችሁ ሰዎች እንዳላችሁ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እውነት ለመናገር የጥቂቶቻችሁ እገዛ ብቻ ይህን ምስኪን ይታደገዋል፡፡

✿ ይህ አብዮት የግጥም ልጅ ወድቆ ቤት አይደፋም ቤት አይመታም ! ይሄ የምታዩት ሰው መጠለያ አጥቶ እኛ ከፀጋዬ ቤት ወል ቤት ከወል ቤት ሰንጎ መገን እየዘለልን አንገጥምም!!!!

ወደን ሳይሆን በግዳችን ይሄን ግዳጅ እንወጣለን ፡ ያኔ ነው ከፍታችን! በሉ በሉ የምን መቆም ነው ለጊዜው ጥቂት ብር ወርውሩ ጊዚያዊ ማደሪያ ቤቱ ይሰራለት ዘንድ የሚበላው የሚለብሰው እንዳይቸግረው ጠግቦ ያድር ዘንድ ብቻ!!!


እንግዲህ በኔ ቅዱስ ታደሰ ንጉሴ እንዲሁም ፍቃዱ ስማቸው መኮንን ከእናንተ የሚገኘውን ሳንቲም በማሰባሰብ ከሌሎች አብዮተኛ ገጣሚ ጓዶች ጋር በመሆን ለጊዜው የሚያስፈልገውን ለማድረግ በሚል ብቻ እንቀሳቀሳለን ፡፡ ሳትሰስቱ በሚመቻችሁ በኩል አለሁ በሉ፡፡

➊ ቅዱስ ታደሰ ንጉሴ ☞ 1000160263664 /የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ/

➋ፍቃዱ ስማቸው መኮንን☞19859107 /አቢሲኒያ ባንክ/


አረ ቀስስስስስ አትሻሙ ፡ እዚህ ጋር እኛ አነስተኛ #ቤት ለማሰራት፣ የሚበላው እንዳይቸግረው እና የሚለብሰውን እንዳያጣ ለማድረግ ጥቂት ሰው ነው የምንፈልገው!


ወዳጄ #ዋናው ዋናው ዋናው ስራ በቀጥታ ጉዳዩ #ለሚመለከታቸው ሰዎች አሳውቁና #እንዲሰበስቡት ይሁን ፡፡ የባለቅኔው ውለታ ያለባችሁ ተፍ ተፍ በሉ ሳይካትሪስትም ያሻዋልና አለሁ አለሁ በሉ ፡፡

ወዳጄ አዳምጠኝ ይሄ የከፋ ነገር አይደለም እጅግ በጣም ቀላል ነገር ነው ፡ እጅህን አትሰብስብ ፡ ነገ ላይ ራሱን አቅንቶ ታላቅ ነገር የሚሰራ ሰው ሜዳ ላይ ወድቆ እጅህ ቆርሶ እንዳይበላ፡፡

★የፍቅር ዘማች ወለየዎች ከወዴት ናችሁ?!

★ኢትዮጵያውያን አርቲስቶቻችን ውለታው የለባችሁም ወይ? ትላንት ሙሉጌታ ሳይሞት እንዲህ ባረኩ ኖሮ የምትሉትን ጉዳይ ለምን በልጁ ክሳችሁት አዕምሯችሁ እረፍት አያገኝም?!!!

እዚህ አብዮት ውስጥ ሰው ልትገል ደም ልታፋስስ የገባህ ካለ አሁኑኑ ለቀህ ውጣ፡ እንሆ አብዮቱ ሰው ሰው የሚሸቱ ስራዎችን የሚሰራ ነውና ሰው ለማዳን የምትሻ አብረኀን ዝለቅ ፡ ጣፋጩን ፍሬ ትበላለህ 🙏

#ሼር/SHARE እያደረጋችሁ ለመላው ኢትዮጵያውያን የማድረስ ግዴታችሁን ተወጡ፡፡ እንደ ሜቄዶኒያ ያላችሁ #ግብረ_ሰናይ ተቋሞች እያያችሁ አትለፉ !



"በመዋረድ ቀን፣ የለም ዘመድ፥
ዘመድ እንኳ ቀን ሲጎድል፣ ይኾን የለም ወይ ባዕድ፣
የሥጋ ኑሮህ ሲሟላ፣ ሲትረፈረፍልህ ማዕድ፣
ከነገድህ ያልኾነው፣ ከዘርህ የማይወለድ፣
የሚዛመድህ ብዙ ነው፣ ባዳም ይኾንሃል ዘመድ፣

ቀን ሲጎድል ግን፣ እንዲህ ነው፤

ሐዋርያውን ቢጠይቁት፣ ዐላውቀውም ብሎ ካደ፣
ፈጣሪውን ተወና፣ ከባዕድ ጋር ተዛመደ፤
ዘመድስ ዮሐንስ ነው፣ የነጎድጓድ ልጅ ብርቱ፣
መቃብር እስኪወርድ ድረስ፣ አልተለየምና ከእናቱ፤

ግጥም(በግዕዝ)☞የቅኔ ሊቅ አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ
ትርጉም ☞ በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ዳይ ዳይ ዝም ብለህ አትይ ሼር እያደረክ የበኩልህን ተወጣ ይህን አስከፊ ጊዜ ተጋግዘን እንሻገር ፡፡

ሀሉም ቢተባበር __ የት ይደረስ ነበር 🙏🙏🙏
#የግጥም_አብዮት
@kinchebchabi
@kinchebchabi
@kinchebchabi